Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የ”ምርጫው”ውሎ ምን ይመስላል? –ከተለያዩ ከተሞች የተጠናቀረ

$
0
0

election
-‹‹እየተከተሉ እስከ ድምጽ መስጫው በመግባት ጫና ያደርጋሉ፡፡ ታዛቢ የሚባል ነገርም አላየሁም፡፡›› ሰሜን ወሎ ራያቆቦ

-‹‹በጣም ያሳዝናል፡፡ ራሳቸው ናቸው የሚመርጡት፡፡ ምልክት የሚያደርጉት እነሱው ናቸው፡፡ እንደ አጠቃላይ ፍትሃዊ አይደለም፡፡›› ደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ
-ደብረማርቆስ ከተማ ላይ መንበረ ዘውዴ የሚባል የብአዴን ፀኃፊ ተዘዋዋሪ ታዛቢዎችን የሚጓጓበትን መኪና በማስቆም እንዳይታዘቡ አድርጓል፡፡ ታዛቢዎች ምዕርባ ጎጃም ፈረስ ቤት የሰማያዊ ፓርቲ ምልክት እንዳይኖር ተደርጓል፡፡

-‹‹ከንብ ውጭ ምልክት የለም፡፡ ከዛም ካርድ ይቀዳሉ፡፡ ሶስት ቀበሌዎች ተዘዋውሬ አይቻለሁ፡፡ መምህራን ስለሚጠይቁ ችግር እየደረሰባቸው ነው፡፡ ይህ ምርጫ ይበላል?›› ኦሮሚያ ክልል አደሬ ጮሌ ቀበሌ

-በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ምልክት የለም እየተባሉ እንደተመለሱ መራጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

-‹‹ምክትል ሊቀመንበሩ ከምርጫ አስፈፃሚዎች ጋር በመሆን እያጠቆረ ለመራጩ ይሰጣል፡፡ የመራጩ ስራ ኮሮጆው ውስጥ ማስገባት ብቻ ነው፡፡ የሚሰማ ሰው ካለ አድርሱልን፡፡›› ምስራቅ ጎጃም ዞን ፈለገ ብርሃን ከተማ
-ደቡብ ጎንደር ዞን ወረታ ከተማ ላይ ከፍተኛ አፈና እና ወከባ እየተፈፀመ ነው
-በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ የሆኑት አቶ መለሰ ተሸመ ትናንት ማታ በደህንነቶች ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ አልታወቀም፡፡ በተመሳሳይ በደቡብ ጎንደር ስቴ ወረዳ ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸው ታውቋል፡፡ ሁለቱም ታዛቢዎች እግርና እጃቸው ላይ ከፍተኛ ስብራት አጋጥሟቸው ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል፡፡
-ባህርዳር ላይ የድምፅ አሰጣጡ ሚስጥራዊ አይደለም ተባለ:..በአንድ ምርጫ ሳጥን ላይ አንድ ጊዜ የሚመርጡትም በካድሬዎች 1ለ5 የተጠረነፉት ነዋሪዎች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል፡፡
-አዲስ አበባ ውስጥ የወረዳ 12ና 13 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነው አቶ ይድነቃቸው አዲስ መራጮች ጣት ላይ የሚቀባው ቀለም በሶፍትም እንደሚለቅ ማረጋገጡን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

-መታወቂያ የሌላቸው ነዋሪዎች እየመረጡ ነው

ወረዳ 20 ምርጫ ጣቢያ መታወቂያና የምርጫ ካርድ የሌላቸው ነዋሪዎች እየመረጡ ነው ተብሏል፡፡ ነዋሪዎች በዚህ አካባቢ ነዋሪ ከሆኑ ስድስት ወር ሆኗቸዋል በሚል ያለ ቀበሌ መታወቂያ እየመረጡ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ 5ና 8 ምርጫ ጣቢያ ላይ መታወቂያና የምርጫ ካርድ ያልያዙ ነዋሪዎች እየመረጡ እንደሆነ የአካባቢው የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነት አቶ እስክንድር ጥላሁን ገልጾአል፡፡

-‹‹የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ፡፡ ካለ ንብ ሌላ የሚመረጥ ምልክት አያሳዩንም፡፡ ሌላ ምልክት አሳዩን ስንል ከፈለክ ይህን ምረጥ ከዚህ ውጭ የሚመረጥ የለም ነው የሚሉን፡፡ ይህ ምኑ ምርጫ ይባላል?›› ከደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ (ነገረ- ኢትዮጵያ)

The post የ”ምርጫው” ውሎ ምን ይመስላል? – ከተለያዩ ከተሞች የተጠናቀረ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>