Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ እና ዶ/ር በያን ሱባ -በገበየሁ ባልቻ

$
0
0

በገበየሁ ባልቻ

Fikire-tolosa-OLF-and-Ethiopiaባለፈዉ ጊዜ ሁለቱ ልሁቃን ዶፍቶሮች በፈረንጂ እዉቀታቸዉ የተመሰከረላቸዉ ምሁራን (በኢትዮሚዲያ) የተመላለሱትን በመመልከት የበኩሌን በጉዳዩ ዙሪያ ሀሳብ ልሰጥ አስቤ የአባይ ጉዳይ በረድ ይበል በማለት በጋዉን ስጠብቅ ባጀሁ።

ዶ/ር ፍቅሬ ዶ/ር በያን የሚመሩት ድርጅት ኢትዮጵያዊ ይዘት ያለዉ መስሎ ስለታያቸዉ መሰለኝ ዘመን ተሻግረዉ ማህደር ፈልፍለዉ ልዩ ጥናት አካሂደዉ በዘመኑ ያለነዉን ሁሉ የሚያስደምም የምርምር ድርሳን አቀረቡ። በጥናቱ መሰረት ኦሮሞ እና አማራ የአንድ ቤተሰብ ልጆች ከመሆናቸዉም በላይ በየጊዜዉ የኦሮሞ ተወላጆችንን አንገት የሚያስደፋዉን አሉባልታ ወደጎን በመተዉ በማንኛዉም የኢትዮጵያ አስተዳደር ኦሮሞ ያልተሳተፈበት ወይም ደግሞ ኦሮሞ ያልገዛበት ዘመን እንደሌለ በርቀት ተጉዘዉ መረጃ አስደግፈዉ ገለጹልን ። በዚሁ መልእክታቸዉ  ለዶ/ር በያን እንዲህ ያለ የምርምር ሰነድ ካሻችሁ ከጎናችሁ ነኝ ሌሎች ኢትዮጵያዉያንም በኢትዮጵያ ምድር ለሚደርሰዉ ማንኛዉም በደል ዘር፤ ወገን፤ ጎሳ፤ሀይማኖት ሳንለይ አብረን እንታገላለን በማለት ቃላቸዉን ሰጡ። ነገር ግን ማንኛዉም እንቅስቃሴ፤ሀሳብ፤መመሪያ አሉባልታ ላይ ያተኮረ ወይም ደግሞ ፈረንጂን እና የኢትዮጵያ ጠላቶችን የሚያስደስት ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ይዘት ያለዉ የእኛዉ መሆን አለበት በሚል አገላለጽ አድናቆታቸዉን፤ ምስጋናቸዉን፤ ምክራቸዉንና ትብብራቸዉን ለ/ዶር በያን እና ይመሩታል ለተባለዉ ድርጅታቸዉ አበሰሩ እኛም በእጅጉ ደስ አለን።

ዶ/ር በያን ለዚህ ሀገራዊ ጥያቄ መልሳቸዉ ሲጠበቅ ብዙም ሳይቆይ ከመቅጽበት ብቅ አለ። በእዉነቱ የዶ/ር በያን መልስ በእጅጉ ይጠበቅ ነበርና ስማቸዉንና ምስላቸዉን ስንመለከት ልባችን ቀለጠ በስንት መከራ ከፈረንጅኛ ወደ አማርኛ ገልብጠን ስንረዳዉ በተቻለ መጠን ልዉዉጡን እኩል በማድረግ  የዶ/ር በያን መልስ ስምን ሆነ ብሎ በመለወጥ እና ስምን አሳስቶ በመጻፍ ላይ የተነጣጠረ ዉንጀላ እና ክስ ሁኖ ቀረበ (ሼክስፒር ፈይሳ እንዴት ያዩት ይሆን ይህን ነገር?)። በዉነቱ ዶ/ር ፍቅሬ ያን ያህል የተጉዋዙ እና ታሪክን ያብላሉ በፈረንጂ እርሶ የተባሉ ምሁር ይህ ጠፍቷቸዉ አልመሰለኝም። ስምን በተመለከተ ራሺያኖች ኢትዮጵያን ኢፊዮፒያ፣ ጃፓንን  ያፖኒያ…….ሲሉ የኛ የጥንቶቹም ለንደንን  ሎንዶን፤ግብጽ ምስር፤አዉስትሪያ ነምሳ…….ጣሊያኖች ኢትዮጵያን  አቢሲኒያ እንግሊዝን ኢንግልቴሪያ…….እያለ ይቀጥላል። ሌሎቻችሁም በስደት በያላችሁበት እንዲሁ እናንተ ከምታዉቁት አጠራር ዉጭ የአገሬዉ ሰዉ የሚጠራበትን  አጠራር ሳትስሙ የቀራችሁ አልመሰለኝም። እዚህ ላይ አሁን የምንሰማዉ ቋንቋ ዶ/ር በያን እንደሚፈልጉት ወደፊት አሁን ባለበት ሁኔታ ሊቀጥል አይችልም። ቁዋንቁዋ በንግድ፤በትምህርት፤በሀይል፤ከዉስጥና ከዉጭ ባለዉ ግፊት፤በስልጣኔ፤በወረራ አጠራሩ እና አጠቃቀሙ ይለዋወጣል፤ይዳቀላል፤ ካልጠቀመም ይጠፋል ለምሳሌ መኪናን የሚተካ ቴክኖሎጅ ተፈልስፎ መኪና ከጠፋ ያንን ጽንሰ ሀሳብ የሚተካዉ መኪና ከጊዜ ብዛት መጥፋቱ ግድ ይላል።

በዚህ መልኩ የምስራቅ ፍልስፍና አራማጆች፤ ብሄረተኞች፤ ነገድን ለመቀስቀሻነት ለመጠቀም ሲሉ ቋንቋን  ከዳቦ በላይ አቅርበዉታል። እዚህ ላይ በእርግጠኛነት ለመናገር የ/ዶር በያን ልጆችም (ካላቸዉ)  ኦሮምኛዉን ከእንግሊዝኛ በላይ ያዉቁታል ማለት ይከብደኛል ለዛዉም ኦሮምኛዉን ካወቁት። በዚህ በዘመናችን እንኳን ፔሪስትሮይካ የሩሲያኖች ቁዋንቁዋ ወደ እንግሊዝኛዉ ተጠቃልሏል። በጀት፤ካልሲ፤እስክሪፕቶ፤አስቢዳሌ እንደዉ ሌላም ሌላም።ይህ ሁሉ ቅይጠት እና አጠቃቀም የመጣዉ የቁዋንቁዉን ባለቤት ለማስቀየም ሳይሆን ቋንቋ የተናጋሪዉ እንጂ የማንም ባለመሆኑ ነዉ። ወደ ምእራብ ኢትዮጵያ ብዙ የአማራዉ ብሄረሰብ አባሎች ዛሬ ጆሯቸዉን ቢቆርጧቸዉ አማርኛን አይሰሙም በሌላ አካባቢ የተወለዱ ኦሮሞዎችም በአንጻሩ እነዲሁ ከትዉልድ ቋንቋቸዉ በላይ የመጠቀሚያ ቋንቋቸዉን አጥብቀዉ ይዘዋል።

ቁዋንቋ ሀሳብን የመግለጫ ልሳን እንጂ ምንም ማለትም አይደለም። ለምሳሌ የአዉሮፓ ማህበረሰብ አባሎች ቁዋንቋቸዉ እንግሊዝኛ እንዲሆን ወስነዋል። ማንኛችንም እንደምናዉቀዉ እንግሊዝ የአዉሮፓ ማህበረሰብ አገር ወዷትም አይደለም ኢኮኖሚዋም ቢሆን ከሌሎች የበለጠ ስለሆነም አይደለም እንግሊዝ የአዉሮፓ ሀገሮችንም ወርራ ቋንቋቸዉንም እንግሊዝኛ እንዲሆን አስገድዳም አይደለም ነገር ግን በተለያዩ መስፍረቶች እንግሊዝኛ ለማህበረሰቡ ከሌሎች ቁዋንቁዎች በላይ አገልግሎት ይሰጣል በሚል ግምት እንጂ። የህዋት አስተዳደር አማርኛ እና አማራ ላይ ካለዉ ጭፍን ጥላቻ የተነሳ አማርኛን ከስሩ መንግሎ ለመጣል ያላደረገዉ ጥረት አልነበረም ሆኖም ተጠቃሚዉ የሚጠቅመዉን በማወቁ እነሱኑ ጨምሮ አማርኛ አማርኛ እንደሆነ ቆይቷል። አቶ መለስ ወደ ሁዋላ ላይ የአማርኛቸዉ አጠቃቀም ከዋሸራ የተመረቁ አስመስሏቸዉ ነበር ብቻ ለመልካም ስራ ስላልተጠቀሙበት የቋንቋዉ ባለቤት ጠራቸዉ።እዚህ ላይ ከመሰረቴ ሳልወጣ ታላቁ ሎሞኖሶቭ የሩሲያን የቁዋንቁዋ ህግጋት ሲያወጣ የኢትዮጵያን የቋንቋ ህጎች (አማርኛን) ተጠቅሟል ይላሉ ሩሲያኖች በመጻፋቸዉ እንግዲህ ምን ልንሆን? ሩሲያኖች ተዋረዱ ማለት ነዉ? አይ የኛ ፍልስፍና።

ብቻ በማይረባዉ ስትነጫጩ ኑሩ ስላለን በማይረባዉ ስንክሳር ሁሉ ስንባላ እንኖራለን። ህዋትም መርዙን እኛ ዉስጥ እየረጨ መኸሩን ይሰበስባል ፈረንጅም፤አረብም እንዲሁ።  በአጠቃላይ ዶ/ር በያን ዶ/ር ፍቅሬ በዝርዝር የጠቀሱትን መልካም ነገር በመዝለል  ለምን በሱባ እና ጅክሳ ላይ አይናቸዉ እንዳረፈ ከሳቸዉ በስተቀር ማንም ሊያዉቅ አይችልም። አኝህ አንድ ድርጅት እንዲመሩ ስልጣን እና ሃለፊነት የተሰጣቸዉ ሰዉ በዚህ መልሳቸዉ ማንነታቸዉን አመላክተዉናል።

በአዉሮፓም ሆነ አሜሪካ ተፎካካሪ መሪዎች ወደ ስልጣን ሊመጡ ሲሉ ጠያቂዎች እልህ አስጨራሺ፤ የሚያበሳጭ፤ እዉቀትን፤ ድፍረትን፤ አርበኝነትን፤ ማስተዋልን እና መሪነትን የሚለካ ጥያቄ ይጠይቋቸዋል። የዚህ አይነት የከረረ ጥያቄ መሪዉ በዉጥረት ጊዜ የአመራር ችሎታዉን፤ ትእግስቱን፤እዉቀቱን፤ማመዛዘኑን ለመለካት እድል የሚሰጥ አጋጣሚ ነበር። እስቲ እንግዲህ እግዜር የሳያችሁ ዶ/ር በያን እና ዶ/ር ፍቅሬ በአንድ መድረክ ላይ ተገኛኝተዉ ቢሆን ኑሮ ሊደርስ የሚችለዉን በአይነ ህሊና እንገምት ወይም ደግሞ ዶ/ር በያን ትልቅ ጦርና አገር እንዲመሩ እድል ቢሰጣቸዉ  ሊደርስ የሚችለዉን መገመት አስቸጋሪ አይሆንም።

እድል ሆነና እኛ አካባቢ ግን በድርጅትም ሆነ በሀገር አቀፍ ምርጫ መሪዎቻችን በእኛ ተመርጠዉ አያዉቁም እንዲሁ በተንኮል፤ በጭካኔ እና በቡድን ስልጣን ላይ ቁጭ ብለዉ በዉርደት ወይም ይድፋዉ እየተባለ በእርግማን ይወርዳሉ። አቶ መለስ እና ዶ/ር ጳዉሎስን ማለቴ አይደለም የነሱ ከእዚህ በላይ ነዉ።

እንግዲህ ዶ/ር በያንን ልብ እና ትእግስት ይስጥልን እያልን ዶ/ር ፍቅሬን ደግሞ በጎደለን የእዉቀት ክፍተት እንዲሞሉልን እንጠይቃለን የጀመሩትንም የፍቅር ተልእኮ በጀመሩት መንገድ እንዲቀጥሉም አደራ እንላለን ከቂም፤ ከጥላቻ፤ ከመከፋፈል፤ ከተንኮል ምን ይተርፋል?። በዘመናችን ከሻቢያ ብዙ መማር አንችልም ነበር?  ሲንጋፖር ሊሆን የታሰበዉ አገር ዛሬ ፓስታ እና በርበሬ በፖስታ ከአዉሮፓ እና አሜሪካ እየተላከለት አሁን ኑሮ ነዉ ይሄ?። በዉነቱ የህዋት መንግስት አቅፎ ደግፎ ባይዛቸዉ ዛሬ ኤርትራ ዘጠኝ ቦታ አይከፋፈልም ነበር? ለማንኛዉም መቻቻል እና አርቆ ማሰብን ይስጠን። ማነዉ አማራን እና ኦሮሞን ወይም ደግሞ ደቡብን እና ትግሬን ወይም ሱማሌን እና ወላይታን አፋርን የሚለየዉ? ኢትዮጵያዊ ሁሉ በስነልቦናዉም ሆነ መልኩ ጠባዩ ተመሳሳይነት ያለዉ ነዉ ይህም ተፈልጎ ሳይሆን አብሮ በመኖር የፈጠርነዉ ትስስር ነዉ።

ለማንኛዉም በቸር ይግጠመን gebeyhubalcha@yahoo.com ካጠፋሁ በዚህ አናግሩኝ

ገበየሁ ባልቻ

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>