ማምሻውን ፖሊሶችና ፌድራል ፖሊሶች ጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን ጉዳት የደረሰባቸው ለቢቢኤን ገለጹ::
ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን በማርከስ ከዚህ ቀደም በገዳማት በመስጅዶች ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ ሲፈጸም መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለት በጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ድረስ በመዝለቅ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸማቸውን በቦታው ላይ ድብደባ የተፈጸመባቸው ለቢቢኤን ገልጸዋል፡፡
በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከሚስቱ ጋር እንደነበር የገለጸው ወጣቱ ፖሊሶቹ ሴት ወንድ ሳይሉ ከሁለት መቶ በላይ በሚሆኑት ምእምናን ላይ ድብደባ እንደፈጸሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቤተክርስቲያኑ የነበሩትን አማኞች በከደበደቡ በሁላ በየክፍለ ከተማቸው በመለየት በመኪና ጭነው እንደወሰዷቸው በድጋሚ እንደደቧቸው ተናግረዋል;፡
በመጨረሻም ፎቶ አንስተው አሻራ ተቀብለው ከምሽቱ 5፤45 እንደለቀቋቸው ለቢቢኤን ገልጸዋል፡፡ መንግስት የሃይማኖት ነጻነት አክብሪያለሁ እያለ የእምነት ተቋማትን ክብር ጭምር በመዳፈር የዚህ አይነት አስነዋሪ ድርጊት በመፈጸማቸው ማዘናቸውን ምእምናኑ ገልጸዋል፡፡
The post ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን ማራካሱን ቀጥሎበታል appeared first on Zehabesha Amharic.