እኛን ከአይሲሲ ያዳኑን ኢትዪጲያዊያን ሙስሊሞች ናቸው፡፡ በሀገራችን በፍቅር ነው የኖርነው ክርስቲያኖቹን ለይታችሁ አትወስዱም በማለት ሲል ከአይሲስ ያመለጠው ተናግረዋል::
ቪኦኤ በዛሬው እለት ባስተላለፈው ስርጭት ከሊቢያ ያነጋገረው ኢትዪጲያዊ ቁጥራቸው ያልታወቀ ኢትዪጲያዊያን በአይሲስ መያዛቸውን ገለጸ፡፡
እሱም በአይሲሶች ተይዞ እንደነበር የገለጸው ነዋሪ ክርስቲያንና ሙስሊሙን ለያይተው ሊወስዱ ሲሉ ኢትዪጲያዊያን ሙስሊሞቹ ለይታችሁ እነሱን አትወሱም እኛንም አብራችሁ እረዱን፡፡ በሀገራችን ሙስሊምና ክርስቲያን ተፈቃቅረን ነው የኖርነው ሊቢያ ላይ ታሪካችንን አናበላሽም ክርስቲያኖቹን ብቻ ነጥላችሁ አትወስዱም በማለት እንዳስጣሏቸው ለቪኦኤ ገልጸዋል፡፡
የቪኦኤው ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ ተጠያቂውን አንተ እምነትህ ምንድን ነው ሲል ጠየቀው እሱም ክርስቲያን መሆኑን የገለጸለት ሲሆን ቤንጋዚ ላይ ከአይሲሲ ጩሄው ያስጠሏችሁ ኢትዪጲያዊያን ሙስሊሞች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢትዪጲያ ሙስሊሞች እኛን ለማዳን በሊቢያ ህይወታቸውን አሳልፈው እየሰጡ ለኢትዪጲያን ክርስቲያንኖች ብዙ ብዙ ነው የሚያደርጉልን፡፡ እስላም ክርስቲያን ሳንባባል በፍቅር ነው የምንኖረው በማለት አይሲስ ያለየውን የኢትዪጲያዊያን የሊቢያን አስገራሚ ትንቅንቅ ለቪኦኤ ተርክዋል፡፡
በሌ በኩል አይሲስ በዛሬው እለት ቁጥራቸው ያልታወቁ ኢትዪጲያዊያንን አፍኖ መውሰዱና እነሱም በአሁኑ ጊዜ ተደብቀው እንዳሉ ገልጸዋል፡፡ ቪኦኤ ከአይሲስ ካመለጠው ስደተኛ ጋር ያደረገውን ቆይታ ያድምጡ::
The post አይሲስ በሊቢያ ተጨማሪ ኢትዪጲያንን መያዙን ከአይሲስ ያመለጠው ኢትዪጲያዊ ለቪኦኤ ገለጸ appeared first on Zehabesha Amharic.