የደብረ ብርሃን ቅዱስ ኡራኤል ዓመታዊ ንግሠ በዓል ሐምሌ 7/28/2013 ለአስረኛ ጊዜ በደማቅ ይከበራል። በእግዚአብሔር መልካ ም ፈቃድ በቅዱስ ጳዉሎስ እና ሚናፖሊስ ከተማዎች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ታዳሚወች ሁነዉ የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለህዝበ ክርስቲያን ጥሪያችንን ስናስተላልፍ በታላቅ ደስታ ነዉ። የቅዱስ ኡራኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከተቋቋመ ጀምሮ በእግዚአብሔር ቸርነት ከእለት ወደእለት አገልግሎቱን በማስፋት ላይ ይገኛል ፤ የአባቶችን ቡራኬና በረከት እያገኘን የሰላም እና የፈዉስ ቦታ ሁኗል። የቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ባለፉት ዓመታት ታላላቅ ጉባኤወችን አስተናግዷል፤ ይኸዉም በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፓትርያርክ ዘኢትዮጲያ የሚመራዉን ቅዱስ ሰኖዶስ ጉባኤ እና የሰንበት ትምህርት ቤት የአንድነት ጉባኤን በማስተናገድ ህዝበ ክርስቲያኑ የመንፈሳዊ መድረክ ተሳታፊ ሁኗል። አሁንም ከሐምሌዉ ንግሠ በዓል ጋር አብሮ የተያዘዉ ታላቅ ፕሮግራም 1ኛ የካህናት ጉባባኤ ከሐምሌ 22-26/2013፦እንዲሁም የሰንበት ት/ቤት የአንድነት ማህበር የመሃከለኛዉ ምዕራብ ጉባኤ ሐምሌ 7/27/2013 በቅድሱ ኡራኤል በተክርስቲያን ይከናወናል።
የመርሃ ግብሩ ቀናት፦
- ማክሰኞ (7/22/2013) እስከ ሐሙስ (7/25/2005) የካህናት ጉባኤ ይጠናቀቃል።
- አርብ እና ቅዳሜ (26-27/2013) ለህዝበ ክርስቲያኑ የትምህርት ፕሮግራም ከ5pm-7pm
በ7/27/2013 ሙሉ ቀን የሰንበት ት/ቤት ጉባኤ
እሁድ ሌሊት ስርዓተ ማህሌት፤ ጸሎተ ኪዳን ፤ጸሎተ ቅዳሴዉ በብጹዓን ሊቃነጳጳሳት ተመርቶ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
ሁላችንም በአንድነት በቅዱስ ኡራኤል ንግሠ በዓል ተገኝተን የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ጥሪያችንን እያቀረብን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ከጊዜዉ ከሰዓቱ በሰላም ያድርሰን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ደብረ ብርሃን ቅዱስ ኡራኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን።
1144 Earl Street Saint Paul Minnesota 55106