(ሰበር ዜና ከፍኖተ ነፃነት) ዛሬ ሐምሌ 9, 2005 ዓ.ም የታሰሩት አባላት 4 ደርሰዋል፡፡ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የታሰሩ 3 የአንድነት አባላትን ለማስፈታት ወደ ስፍራው የሄደውን የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ የሆነው አዲሱ ካሳሁንን ከታሳሪዎቹ ጋር ቀላቅለውታል፡፡
ከአንድነት አዲስ አበባ ዞን ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ የተሰማሩት አባላት በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች በተሳካ ሁኔታ ወረቀት የመበተን ተልዕኳቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል፡፡ በትላንትናው እለት 42 የአንድነት አባላትና ለአንዱ ታሳሪ ዋስ ለመሆን የሄደ ግለሰብ መታሰራቸው አይዘነጋም፡:
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፀረሽብር ህጉ እንዲሻርና በሌላ እንዲቀየር እያሰባሰበ ስለሚገኘው ፊርማ የሚያብራራ በራሪ ወረቀት በመበተን ላይ የነበሩት ባይሳ ደርሳ፣ አለማየሁ በቀለ፣ ግርማ ሹቤ የተባሉትን የአንድነት አባላት ዛሬ ሐምሌ 9 ቀን 2005 ዓ.ም በፖሊስ ታስረዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቀው በዛሬው ዕለት ሁለት መቶ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት በተለያዩ የአዲስ አበባ የክፍሎች በራሪወረቀቶችን በመበተን ላይ ናቸው፡፡
↧
ፖሊስ ማሰሩን የአንድነት አባላትም ወረቀት መበተኑን ገፍተውበታል (ዛሬ የታሰሩት 4 ደረሱ)
↧