Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

119ኛዉ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በዳላስ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

$
0
0

Kifle Mulat dallas

Obang dalas

Sey Adwa 8
(በስዩምና አሰፍ)
በዳላስና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እሁድ ዕለት (የካቲት 22, 2007) ታላቁን የአድዋ ድል በዓል በደማቅ ሁኔታ ሲያከበሩ ውለዋል። ይሄው በዳላስ ወጣቶች የተሰናዳው እጅግ የተዋጣለት፣ ያማረና የደመቀ በዓል ልዩ ልዩ ዝግጅቶች የቀረቡበት ሲሆን ሶስት ኢትዮጵያውያን በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። በክብር እንግድነት የተገኙት ኢትዮጵያውያን፦

አቶ ኦባንግ ሜቶ (ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር – አኢጋን)
አቶ ክፍሌ ሙላት (አንጋፋ ጋዜጠኛና የቀድሞ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዚዳንት የነበሩ)
ፕሮፌሰር ሰለሞን አዲስ ጌታሁን (በሴንትራል ሚችገን ዩኒቨርስቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ)

በዓሉ በወጣት ስዩም ወርቅነህ ፕሮግራም መሪነት የተካሄደ ሲሆን ከህጻነት ጀምሮ በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ወንዶችም ሴቶችም ታድመውበታል። በዳላስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የጋራ መረዳጃ ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ብርሃን መኮነን በበዓሉ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

የክብር እንግዶቹ በየተራ ባደረጉት ንግግር አድዋ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካ ብሎም የመላው ጥቁር ህዝብ ድል መሆኑን አውስተዋል። በተለይ አቶ ኦባንግ ሜቶ ባደረጉት ንግግር አገራችን ቅኝ ሊገዛ የመጣውን ወራሪ የባዕድ ሃይል አያቶቻችን አሳፍረው መመለሳቸው ሁላችንንም የሚያኮራ ታሪክ ነው ካሉ በኋላ ከ100 ዓመት በፊት አያቶቻችን ያስመዘገቡትን የነጻነት ድል ስናስብ ዛሬ በሃገራችን ውስጥ በራሳችን መሪዎች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የነጻነት እጦትና የመብት ረገጣ ችላ ልንለው አይገባም ብለዋል። በሃገራችን ኢትዮጵያ ፍትህ፣ ነጻነትና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋፅዖ እናድርግ በማለት ታዳሚውን አሳስበዋል።

በመጨረሻም በወጣቶቹ የተዘጋጀው ኬክ በሶስቱም እንግዶች በአንድ ላይ ተቆርሶ ታዳሚዎች አስተያየታቸው እንዲሰጡ መድረኩ ክፍት ከተደረገ በኋላ አስተያየታቸው የሰጡ ሁሉም ወጣቶቹ ይህን የመሰለ በዓል በማዘጋጀታቸው አመስግነው ለወደፊቱ እንዲቀጥል አሳስበዋል። ወጣቶቹም በየአመቱ በአሉን ከዚህ በበለጠ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር እንደሚያዘጋጁ ቃል ገብተው የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል።

The post 119ኛዉ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በዳላስ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>