Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የትናንቱን የጭላሎ ተራራ የእሳት አደጋ በመቀስቀስ የተከሰሰው ግለሰብ በ10 ዓመት እስራት ተቀጣ

$
0
0

b921dbb2d1617779408d5dd6f6a9f717_Lአዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአርሲ ዞን በጢዮ ወረዳ በጭላሎ ተራራ ላይ ትናንት የተከሰተውን ቃጠሎ የቀሰቀሰው ግለሰብ በአስር ዓመት አስራት ተቀጣ። የወረዳው ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው  ችሎት የግለሰቡን ጉዳይ የተመለከተ ሲሆን፥ ተከሳሹ ቃጠሎውን መቀስቀሱን በማመኑ በ10 ዓመት እስራት ቀጥቶታል።

ቃጠሎውን የቀሰቀሰው ግለሰብ በዲገሉና ጢጆ ወረዳ ከቡቾ – ስላሴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ወደ ቦሬ – ጭላሎ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ወደሚገኘው ወንድሙ ጋር በእንግድነት የመጣ መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል። የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኡርጋ ግዛው እንደገለጹት፥ ትናንት ጠዋት ረፋድ ላይ በተራራው ላይ በሚገኝ ደን ላይ የለኮሰው እሳት እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ከቆየ በኋላ ነው በቁጥጥር ስር ውሏል።

ቦሬ – ጭላሎ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የተነሳው ቃጠሎ ወደ ሻላ – ጨብቲ፣ ቡርቃ – ጭላሎ እና ሀሮ – ቢላሎ የገጠር ቀበሌ በመዛመት በተፈጥሮ ሀብት ላይ ጉዳት ማድረሱንም ጠቁመዋል። በቀበሌዎቹ የተቀሰቀሰውን እሳት ለመከላከል የአካባቢው አርሶ አደሮች፣ ነዋሪዎች፣ የወረዳና ዞን ፀጥታ ኋይሎች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ከዘጠኝ ሰዓታት በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቀዋል።

አደጋው በሰውና እንስሳት ላይ ጉዳት አለማድረሱ ተመልክቷል። በቃጠሎው የወደመውን የደን ይዞታ መጠን ለማጣራት ፖሊስ ከወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ጽህፈት ቤት ጋር እየሰራ ነው ብለዋል።

በጥበቡ ከበደ /ተጨማሪ መረጃ ከኢዜአ/

The post የትናንቱን የጭላሎ ተራራ የእሳት አደጋ በመቀስቀስ የተከሰሰው ግለሰብ በ10 ዓመት እስራት ተቀጣ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>