‹ውሳኔው ፖለቲካዊ ነው›› አቶ አዲሱ ጌታነህ
የአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የሰማያዊ ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን ተወካይ እንዲሁም የምዕራብ ጎጃም፣ ምስራቅ ጎጃምና አዊ ዞን የምርጫ ግብረ ኃይል አባል የሆነውን አቶ አዲሱ ጌታነህን ‹‹ማኔጅመንቱን ያውካል፣ የስራ ተነሳሽነት የለውም›› በሚል ከኃላፊነቱ ማንሳቱን በደብዳቤ አሳውቋል፡፡
ይሁንና መስሪያ ቤት ጥቅምት 23/2007 ዓ.ም በብቃቱ መሰረት በኃላፊነት እንደመደበው በደብዳቤ የገለጸ ሲሆን አሁን የተወሰደው እርምጃ ከወቅቱ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ መሆኑን አቶ አዲሱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
‹‹ባህርዳር ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ኃይል እየተፈጠረ ነው፡፡ በተለይ የአንድነት መዋቅር ሰማያዊን ከተቀላቀለ በኋላ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ይህንም ተከትሎ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች ጋር ያደረግናቸው ውይይቶች ብአዴንን አስደንግጦታል›› ያለው አቶ አዲሱ መስሪያ ቤቱ የወሰደበት እርምጃ ፖለቲካዊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የምዕራብ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር በአካባቢው ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል፣ እንዲሁም ምርጫ ቦርድ ከዕጩ ምዝገባ ጋር በተያያዘ የሚፈጥራቸውን ችግሮች ለሚዲያ በማጋለጥ ላይ መሆኑ ከኃላፊነት ለመነሳቴ አንድ ምክንያት ነው ሲል ገልጾአል፡፡
የአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የቦርድ አባላት የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል የባህርዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ላቀ አያሌው፣ የክልሉ ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ያለው አባተ፣ የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ኃላፊ አቶ አየነው ይገኙበታል፡፡
The post የአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ከኃላፊነቱ አነሳ appeared first on Zehabesha Amharic.