ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ የካቲት 24/2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ መጀመሩን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ ጀመረ:የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ፡፡
በዛሬው ዕለት ፓርቲው የመኪና ላይ የድምጽ ቅስቀሳ እያደረገ ሲሆን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በራሪ ወረቀቶችንም እያደለ ይገኛል፡፡
ይህ በ እንዲህ እንዳለ በሽሮሜዳ አካባቢ በቅስቀሳ ላይ የሚገኘው የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን በፖሊስ ታግቶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየተወሰደ ነው፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በዛሬው ዕለት ፓርቲው የመኪና ላይ የድምጽ ቅስቀሳ እያደረገ ሲሆን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በራሪ ወረቀቶችንም እያደለ ይገኛል፡፡ በሽሮሜዳ አካባቢ በቅስቀሳ ላይ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ ታግቶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየተወሰደ ነው፡፡ ፖሊስ ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው ከማለት ያለፈ ለአፈናው ምንም ምክንያት አልሰጠም::
በሌላ ዜና የምርጫ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ታሰሩ::
ዛሬ የካቲት 24/2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡ ፓርቲው ዛሬ በሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ላይ በጀመረው ቅስቀሳ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቅስቀሳ ላይ የነበሩት ዘላለም ደሳለኝ፣ ምዕራፍ ይመር፣ ይድነቃቸው ፍሬው ተክለና ሳምሶን ግዛቸው ሽሮ ሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከቆዩ በኋላ ወደ ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ ተዛውረዋል፡፡ ከታሰሩት አራት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል ዘላለም ደሳለኝና ይድነቃቸው ፍሬው ዕጩ ተመራጮች ናቸው፡፡
ፖሊሶች በቅስቀሳ ላይ የነበሩትን አባላት በያዙበት ወቅት ‹‹ተልከን ነው›› ማለታቸው የታወቀ ሲሆን ‹‹ቅስቀሳ በቴሊቪዥን እንጅ በመኪና አልተፈቀደም፣ ቅስቀሳ መፈቀዱን አናውቅም፣ ይቀስቅሱ የሚል መመሪያ አልተላለፈልንም›› የሚሉ ምክንያቶችን መስጠታቸው ታውቋል፡፡
The post ሰማያዊ ፓርቲ ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ ቢጀምርም ለቅስቀሳ የወጡት እየታፈኑ መሆኑ ተገለጸ appeared first on Zehabesha Amharic.