አስደናቂ ለሆነ የረጅም ዘመን አኩሪ ታሪክ ባለቤት የሆነችው፡ እናት ሃገራችን ኢትዮጵያ፡ ከ1762 እስከ 1845 ዓ.ም ድረስ በነበረው 70 አመት ጊዜ ውስጥ፡ በዘር ባይሆንም ልክ እንደዛሬው፡ ልጆቿ ተከፋፍለው፣ ልማትና ብልጽግናዋ ተገትቶ፣ ለሁለንተናዊ ውድቀት የተዳረገችበት ወቅት ነበር።
እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ፡ ለዚያ ውድቀት የዳረጋት፡ የትግራዩ ተወላጅ እራስ ስዑለ ሚካኤል፡ አማቱንና በወቅቱ የነበሩትን ንጉስ አጼ ኢዩአሰን በቤት አሽከሮቻቸው አሳንቆ በማስገደሉ ነበር።
እንግሊዝ አጼ ቲዮድሮስ፡ ያሰሩባትን ዜጎቿን እነ ቆንሲል ካሜሮንን፡ በሃይል ለማስፈታት፡ ወደ ኢትዮጵያ ጦሯን በላከች ጊዜ፡ በሮቤርት ናፒር የሚመራው ወራሪው ጦር ከምጽዋ ዙላ፣ ከዙላ ሰናፈ፣ ከሰናፈ አሸንጌ፣ ከአሸንጌ ሙጃ፣ ከሙጃ መረዋ፡፡ በማረፍ እየተዝናና እና መንገድ እየሰራ ሚያዚያ 2 ቀን 1860 ዓ.ም. በሸሎ እሰኪደርስ ድረስ፡ መንገድ በመምራትና በመንከባከብ አምጥተው፡ የእኒያን ብሄራዊ ጀግና፡ የአጼ ቲዮድሮስን እልፈተ ህይወት ያፋጠኑት፡ አሁንም የትግራዩ ተወላጅ፡ ካሳ ምርጫ፡ ወይንም በንግስና ስማቸው አጼ ዩሃንስ እንደ ነበሩም ይነገራል። ምንም እንኳን በሗላ ከወራሬ ጋር ሲፋለሙ በክብር ቢወድቁም።
ዛሬ በምናሰበው በ1888 ዓ.ም አድዋ ላይ በተካሄደው፡ የኢትዮጵያና የኢጣልያን ጦርነት ጊዜ በእራስ መኮንን የሚመራው ቀዳሚ ጦር። አምባላጌ እንደደረሰ ገና መሬት ሳይዝ በወጊያ የጠመዱትም የትግራይ ተወላጅ ባንዳዎች ናቸው።
በ1928 ዓ.ም በሁለተኛው የኢጣልያ ወረራ ወቅት፡ አርበኛው ፊትለፊ ከጠላት ጋር ሲፋለም፡ በትግራይ በቀሉ ባንዳ በደጃዝማች ሃይለስላሴ ጉግሳ፡ የሚመራው የትግራይ ተወላጆች ስብስብ፡ ተመሳስሎ በጀርባ እየገባ ያልተጠበቀ አድጋ በማድረስ፡ ለሽንፈታችን ትልቅ አስተዋጽኦ ከማድረጉም በላይ፡ ሲሸሽ እየተከታተለ የደከመውንና ቁስለኛ ወንድሙን በመግደል፡ ከኢጣልያን የከፋ በርካታ የኢትዮጵያን አርበኛ ፈጅቷል።
ሀምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም. አቡነ ጴጥሮስ አዲስ አበባ ላይ ሲረሸኑ፡፡
ህዳር24ቀን 1929 ዓ.ም. አቡነ ሚካኤል ጎሬ ላይ ሲረሸኑ፡፡
የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. በግራዞያኒ ትእዛዝ አዲስ አበባ ላይ ከ30 ሺህ የማያንስ ህዝብ ሲጨፈጨፍ፡፡ ትዕዛዝ ፈጻሚዎቹ አሁንም ትውልደ ሰሜን ወንድሞቻችን ነበሩ።
1969ዓ.ም ሶማሌ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅትም፡ ወያኔ መቃድሾ ከተማ ቢሮ ከፈቶ፡ በተለይ በሰራዊታችን ውስጥ የእሱን ሰው አሰርጎ በማስገባት፡ ለጠላት መረጃ ከማቀበል ጀምሮ፡ የሶማሌ የስለላ ማዕከል፡ የኢትዮጵያ ጦር ግንኙነት የሚያደርግበትን፡ ሬዲዮ እየጠለፈ ሲያቀርብለት በመተርጎም፡ ለሶማሌ ሰራዊት እየሰጠ በኢትዮጵያዊያን ላይ ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ ትልቅ ክዕደት ሲፈጽም ነበር።
በአብዛኛው ማለት በሚያስደፍር ሁኔታ፡ በሃገራችን ላይ ወረራ በተሰነዘረ ቁጥር በርካታ የትግራይ ተወላጆች፡ ከጠላት ጎን በመሰለፍ የእናታቸውን ጡት ሲነክሱ ለመኖራቸው ድርሳናቶቹ ሁሉ ቁልጭ አድርገው ያመላክቱናል።
ዛሪም ታሪክ እራሱን ደገመና፡ ትግራይ የፈለቁ ጉዶች ናቸው፡ እኛን በዘርና በሃይማኖት ከፋፍለው፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንደምስራቅ ጀረመንና እንደ ዩጎዘላቢያ ከዓለም ካርታ እንድትፋቅና እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለት አፍ ሞልቶ ደረት ነፍቶ የሚናገር ዜጋ እንዳይኖር 24 አመት ሙሉ ሽንጣቸውን ገትረው በመስራት ላይ ያሉት።
ይህንን ስል ግን ትውልደ ትግራይ ሆነው፡ ለአገር አንድነትና ለወገን ነጻነት፡ የተጋደሉ አልነበሩም። አሁንም፡ የሉም እያልሁ አይደለም። ትናንት እነ አሉላ አባነጋን፣ እነ እራስ ስዩም መንገሻን፣ እነ ደጃዝማች አርያን እነ እራስ መነገሻ ስዩምን፣ ወ.ዘ.ተ. ዛሪም የትግራይ ዲሞክራሴያዊ ንቅናቄ ሰዎችን በተለይም የድርጅቱ መሬ የነበረውንና አሁን በህይወት የሌለውን ፍስሃ ሃይለማርያምን የመሰለ የሃገር
2.. ፍቅር ያንገበግበው የነበረውን። እነ ገብረመደህን አርያን፣ እነ አብርሃ በላይን፣ እነ አብረሃ ደስታን፣ እነ አስራት አብርሃምን ያፈራች ስለሆነ።
መነሻዬ የኢትዮጵያን ታሪክ፡ ወይንም የትግራይ በቀል የጥፋት መልክተኞችን ጉድና ሁላችንም ተደራሲዎች የሆንበትን፡ የወያኔን መግለጫ ቃላት መለኪያ መስፈርት የማይገኝለትን፡ የግፍ ክምር እየናድሁ የምታውቁትን በመድገም ጊዜያችሁን ለማባከን አስቤ አይደለም።
ይልቁንም በትግራዩ ተወላጅ፡ በእራስ ስዑለ ሚካኤል፡ መሰሬ ተንኮል ተበታትና የነበረችዋን ኢትዮጵያን፡ እምዬ ምኒልክ። እንዴት መልሰው እንደገነቧት በአይነ ህሌናችሁ ወደሗላ እንደትመለከቱ ለማነሳሳትና ለውይይት ሃሳብ ለማጫር የተጠቀምሁበት ነው እንጅ።
ወደዛሬው ምልከታየ ስገባ።
አጼ ምኒልክ ነሃሴ 12 ቀን 1836 ዓ.ም በሽዋ ክፍለ ሃገር በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ አንጎለላ ኪዳንምህረት ተወለዱ። ከ12 አመት እድሜያቸው ጀምሮ በግዞትም፣ በማደጎም፣ በአማችነትም ከአጼ ቲዮድሮስ ቤት አደጉ።
ከእድገታቸው እስከ ንግስናቸው ያለውን ታሪክ ለጊዜው ላቆየውና። ከነገሱ በሗላ በተለይም ከዛሬው መሰባሰቢያችን ጋር በቀጥታ የተያያዘውን ከፋሽትት ኢጣልያን ወራሬ ጦር ጋር ያደረጉትን ተጋደሎ ባጭሩ ልጥቀስ።
እምዬ ምኒልክ መላዋን ኢትዮጵያን ከማስረዳደራቸው በፊት። የሽዋ ንጉስ በነበሩበት ወቅት ከኢጣልያን መንግስ ጋር ወዳጅ በመሆናቸው እስከ መሳሬያ እርዳታ ድረስ ያገኙ ነበር። በሗላ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ግን። ኢጣልያን ኢትዮጵያን ለመውረር በነበራት ፍላጎት መሰረት በአጼ ዩሃንስ ጊዜ የጀመረችውን ወረራ እያሰፋችና እየገፋች ስትመጣ። በምኒልክና በኢጣልያን መንግስት መካከል የቆየው መልካም ግንጉነት እየሻከረ ሄደ።
አጼ ምኒልክ ከኢጣልያን ጋር የነበረው ወዳጅነታቸው እንዲቀጥል አጥብቀው ቢጥሩም። በኢጣልያን በኩል ግን ተቀባይነት አላገኙም ነበር። በተለይም የውጫሌ ውል እየተባለ በሚጠቀሰው አንቀጽ 17 ላይ በኢጣልያነኛ የተጻፈው ሃገራቸውን እንደሚጎዳ ሲገነዘቡ ክተት ሰራዊት ምታነጋሬ በማለት የሚከተለውን ጥሬ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ አስተላለፉ።
የአጼምኒልክ ጥሪ ሙሉ ቃል
እግዚያብሄር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ። እኔም እስካሁን በእግዚያብሄር ቸርነት ገዛሁ። እንግዴህ ሞት ለሁሉ ነውና ብሞትም በእኔ ሞት አላዝንም። ደግሞ እግዚያብሄር አሳፍሮኝ አያውቅም። ከእንግዴህም ያሳፈረኛል በዬ አልጠራጠርም።
አገር የሚያጠፋ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ፣ ጠላት እግዚያብሄር የወሰነልንን የባህር በር አልፎ መጧል። እኔም የሃገሬን ከብት ማለቅ የሰውንም መድከም አይቸ ዝም ብለው እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፈር ጀመር። አሁን ግን በእግዚያብሄር እረዳትነት ሃገሬን አሳልፊ አልሰጥም።
የሃገሬ ሰው ከአሁን በፊት የበደልሁህ አይመስለኝም። አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም። ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፣ ለሚስተህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሃዘን እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን በሗላ ትጣላኛለህ። ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም። ዘመቻየ በጥቅምት ነውና የሽዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ወረኢሉ ከትተህ ላግኝህ።
የጥሬው መጨረሻ።
በማለት ካዘዙ በሗላ በእራስ መኮነን የሚመራውን ቃፊር ጦር አስቀድመው እሳቸው ህዳር 2 ቀን 1888 ዓ. ም ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ሰሜን አመሩ።
ንጉሱ በመንገድ ላይ እንዳሉ በራስ መኮነን የሚመራው ቀዳሚ ጦር አምባላጌ ደረሰ። በዚህ ወቅት የኢጣልያን ጦር። የኢትዮጵያን ጦር ከመንግድ እንደመጣና እንደደከመ እንደገናም ቦታ ሳይዝ። ለመምታት ተዘጋጅቶ ቅድም እንዳልኩት በርካታ ትግራይ በቀል ባንዳዎችን በማሰለፍ ውጊያ ከፈተበት። ግን ከ6 ስአት በላይ በፈጀው ጦርነት። ኢጣልያን የመጀመሬያውን የሸንፈት ጽዋ። በእራስ መኮነን ጦር ተጎነጨና ከአምባላጌ ምሽጉ ተባበረ።
አጼምኒልክም ታህሳስ 29 ቀን 1888 ዓ.ም መቀሌ እንደደረሱ። አዚያ ሰፍሮ የነበረውን የጠላት ጦር ዙሬያውን በማስከበብ የሚጠጣው ወሃ ከማሳጣታቸውም በላይ። በውጊያም መድረሻ ስላሳጡት
3.
ያለቀው አልቆ የተረፈው የሃገር ሽማግሌዎችን አማላጅ በመላኩ መንገድ ተከፍቶለት ወደ አዲግራት ሸሸና ለሁለተኛ ጊዜ ሽንፈቱን አጣጣመ።
በዚህ ዘመቻ በኢትዮጵያ በኩል የተሰለፈው ሰራዊት። መቶሽህ እንደሚደርስ የሚገመት ሲሆን። ከዚህ መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆነው አርበኛ ጦርና ጎራዴ ብቻ የታጠቀ እንደነበርና ጠብመንጃ ያለውም ቢሆን ጠላት ከታጠቀው ዘመናዊ መሳሬያ ጋር ሲነጻጸር የሰማይና የመሬት ያህል የተራራቀ እንደነበር የታሪክ ጸሃፍት ያሰምሩበታል።
በዚህ ጦርነት በኢትዮጵያ በኩል የተሰለፉ ዋና ዋና የጦር አዝማቾች።
- እትጌ ጣይቱ ብጡል፡
2.ንጉስ ተክለ ሃይማኖት፡
3.ፍታውራሪ ገበየሁ፡
4.ደጃዝማች ጫጫ፡
5.እራስ መኮንን፡
6.እራስ መንገሻ ስዩም፡
7.እራስ መንገሻ አቲከም፡
8.እራስ ሚካሌል፡
9.እራስ ወሌ ብጡል፡
10.ደጃዝማች በሻህ አቡዬ፡
11.እራስ ጉግሳ፡
12.እራስ አሉላ አባነጋ፡
13.ዋግሹም ጓንጉል፡
14.እራስ ወርቄ የተባሉት ነበሩ።
በኢጣልያን በኩል የጦር አዛዦች ደግሞ፡
- ጠቅላይ አዛዡ ሌትና ጀሪናል ባራቲይሪ፡
- ጀኔል ዦሴፔ ኦሪሞንዱ፡
- ጀኔራል አማኑኤል ደቦርሜዳ፡
- ጀኔራል ማቲዮስ አልቤርቶኒ፡
- ጀኔራል ዦሴፔ ኤሌና፡
- ኮሎኔል ቫሊንዞኖ፡ ነበሩ።
በዚህ የሃይል አሰላልፍ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ልክ የዛሬ 119 አመት ከሌሊቱ በ11 ስአት በኢጣልያን ተንኳሽነት አድዋ ላይ ወሳኙ ጦርነት ተከፈተ።
ሊነጋጋ ሲል ከሌሊቱ በ11 ስአት የተጀመረው ጦርነት። ቀኑን ሙሉ ውሎ ከሌሊቱ 5 ስአት በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቀቀና ሃገራችን ኢትዮጵያ በጥቁር አንበሶች ልጆቿ አጥንት ክስካሽና ደም ፍሳሽ ሃያልነቷ በአም ሁሉ ተናኘ።
ውጤቱም የአለም ህዝብን አስደነቀ። የጀግኖች አባቶቻችን አይበገሬነትም በማያጠራጥር ሁኔታ ታወቀ። በኢጣልያን በኩል ከተሰለፉት የጦር አዛዦች መካከል ከጠቅላይ አዛዡ ከሌትና ጀኔራል ባራቲይሪ በቀር ሌላው የጦር አዛዥ ጀኔራልና ከፍተኛ መኮንን በሙሉ ተደመሰሱ።
በኢጣልያን በኩል ከተማረከውና ቆስሎ ከሸሸው ሌላ 9215 ተዋጊ ሲሞት። ከኢትዮጵያ 7000 ሰው ሞቷል። ከዚህ ውስጥ ከወገን የሞቱ አዋጊዎች።
- ደጃዝማች በሻህ አቡዬ፡
- ደጃዝማች ጫጫ፡
- ፍታውራሪ ገበየሁ፡
- ፍታውራሪ ተክሌ፡
- ቀኛዝማች ታፈሰ አባይነህ፡
- ፍታውራሪ ዳምጠው፡
- ደጃዝማች ማናዬ፡
4.
- ፍታውራሪ ወልደ ሚካሌል።
- ቀኛዝማች ተገኘወርቅ፡
- ፍታውራሪ አምባዬ።
- ቀኛዝማች ተሰማ ወልዴ፡
- ፍታውራሪ ሸንኮሩ፡
- ባላንበራስ በለው፡
14.ባላንበራስ አደራ ወ.ዘ.ተ. ይጠቀሳሉ።
ማጠቃለያ
በጣም የሚገርመው የአውሮፓ ሃያላን መንግስታት። አፍሪካን በቅኝ ለመግዛት። እንደ ቅርጫ ስጋ የተከፋፈሉበትና። እርስ በርስ ላለመነካካት የተፈራረሙት የካቲት 26 ቀን 1877 ዓ.ም ከአድዋ ጦርነት ከ3 አመት በፊት ሲሆን። በክፍፍሉም።
1ኛ. እንግሊዚ፡ ግብፅን፣ ሱዳንን፣ ናይጀርያንና ኬንያን።
2ኛ. ፈረንሳይ፡ ምህራብና ሰሜን አፍሪካን።
3ኛ. ፖርቱጋል፡ አንጎላንና ሞዛቢክን።
4ኛ. ጀርመን፡ ታንዛንያንና ቶጎን።
5ኛ. ቤልጅም፡ ኮንጎን።
6ኛ. ኢጣልያን፡ሶማልያንና ሊብያን ወ.ዘ.ተ በማድረግ ሲከፋፈሉ።
ኢትዮጵያን አልነኳትም ነበር። ምክናያታቸውም የረጅም ዘመን የተጠናከረ መንግስትና። አይበገሬ ህዝብ እንዳላት ስለሚያውቁ። እንደሆነ ይነገራል የተጨበጠ ማስረጃ ባይኖርም።
ዛሪስ በእኔና እናንተ ድርሻ። ሃገራችን ኢትዮጵያ በዓለም ህዝብ ዘንድ የነበራትን ክብር እንዳስጠበቀች ነች ወይ? የሚል ጥያቄ ቢነሳ ሁላችንንም የሚያስማማን መልስ። አይደለም የሚለው እንደሚሆን አልጠራጠርም። ለምን? ከተባለ ልንሰጠው የምንችለው ምላሽ ግን የተለያየ እንደሚሆን እገምታለሁ።
በበኩሌ የእኔና የእናንተ ትውልድ ፈጹም እራስ ወዳድ ስለሆነ። ሌላው ሞቶለት እሱ ተጠቃሚ መሆንን ስለሚያሰላ ነው የሚል ነው ።
እናንተስ በእኔ ሃሳብ ትስማማላችሁ? አይደለም ሌላ ምክናያት ስላለ ነው ወኔ የከዳን የሚል ካለ ለመስማት ዝግጁ ነኝ። መልካም ውይይት እያልሁ እንደ እናንተው ቁጭ ብዬ የግል አስተያይቴን መሰንዘር እችል ዘንድ ዝግጅቴን በምትከተለዋ አጭር የግጥም ስንኝ ልቋጭ።
እርዕሷንም አድዋ ብያታለሁ!!
አድዋ
ከሰሜን ከደቡብ ከመግቢያና መውጫ፣
ከምስራቅ ከምእራብ ከሉም አቅጣጫ።
ቋንቋ ሳይለያቸው ዘር ማንዘር ሳይቆጥሩ፣
አማራ ኦሮሞ በማለት ሳይጠሩ፡
በዚያች የቁርጥ ቀን ቀድመው የደረሱ፣
ጥንት አባቶቻችን እነዝናር ልብሱ፡
ምሳሌ በመሆን በኩራት ሲጠሩ፣
ከመቃብር ጀርባ ዝንታለም ሊኖሩ፣
በአድዋ መልካ ላይ ታሪክን የሰሩ።
አባቶች ነበሩን የሃገር መከታ፣
ህይወት የሚሰጡ በመሆን አለኝታ።
እጅ ለእጅ ተሞሻልቀው በታጠቁት ካራ፣
ፈንጥቀው ያአለፉ እንደ ንጋት ጮራ።
ምኒልክ ለአድዋ ባቀረቡት ጥሪ፣
ያች ጣይቱ ብቱል ሆነች የጦር መሬ።
አዎ!! አድዋ!! አድዋ!! አድዋ!!
5.
የዛሬ ማፈሪያ የትናንት መኩሪያዋ፡
የዛሬ ማፈሪያ የትናንት መኩሪያዋ።
አመሰግናለሁ፡
ማተቤ መለሰ ተሰማ
በ2007 የ119ኛው የአድዋ የድል ባል በኖርዌይ የኢትዮጰያ ማህበር ሲያከብር የቀረበ የውይት መነሻ።
The post አድዋን ስንዘክር፡ – ማተቤ መለሰ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.