Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በቤይሩት ኢትዮያዊቷ ራሷን አጠፋች በሚል ሰበብ….. ኤምባሲው ያለምንም ምርመራ ሬሳዋን አሳፍሩ ማለቱ ብዙዎችን አሳዘነ

$
0
0

በግሩም ተ/ሀይማኖት
ኢትዮጵያዊኖች በአረብ ሀገራት ስደታቸው ጥሩም መጥፎም ይገጥማቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ራሳቸውን አጠፉ በሚል ሰበብም አሰሪዎቻቸው ይገሏቸዋል፡፡ እንዴት ሞቱ የሚል ማጣሪያ ወይም ምርመራ አይደረግም፡፡ ከተቻለ ሬሳቸው ይላካል ካልሆነም ፍሪጅ ውስጥ ተቀምጦ ለተማሪዎች መለማመጃ ይደረጋል፡፡ የሚፈለግ አካልም ይወሰዳል፡፡ ሁሌም ይሄው ነው፡፡
ethiopian woman Arabባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት ቤይሩት ውስጥ ሳይዳ ሀበፊ የተባለ አካባቢ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሞተች፡፡ በአሰሪዎቿ በኩል ራሷን አጠፋች ነው የተባለው፡፡ በፎቶው ላይ እንደምታዩት ከልጅቷ ቁመት ያነሰ መስኮት ላይ ገመድ አስራ ነው ታንቃ የሞተችው ያሉት አሰሪዎቿ፡፡ ራሷን ለማጥፋት የሚያበቃ ምንም አይነት ችግር አልነበረባትም፡፡ ለሞት የዳረጋትን ነገር ቢያስቡ ቢያሰሉ የሚያገኙት ፍንጭ በማጣታቸው በርካታ ጓደኞቿ በሁኔታው ከፍተኛ የሆነ ጥርጣሬ አደረባቸው፡፡
እንዴት ከእሷ ቁመት ባጠረ ቦታ ላይ ታንቃ ሞተች? ሁኔታው አጠራጣሪ ነው ብለው ቤይሩት ላለው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጋግመው ጥርጣሬያቸውን አመለከቱ፡፡ ኤምባሲው ከወትሮ አሰራሩ የተለየ ሁኔታ የለውም፡፡ በእነአለም ደቻሳ ጊዜ የታየው አለመቆርቆር መልኩንም ቅርፁንም አለወጠም፡፡ እንዲያውም ችላ ባይነቱን አሳድገውት የወሰዱት ርምጃ ብዙዎችን ያሳዘነ፣ እንባ ያራጨም ሆነ፡፡
መቼ ይሆን ለሞታችን መብታችን ለመረገጡ ሰሚ እና ተከራካሪ የምናገኘው የሚለው የዘውትር ጥያቄ ደጋግሞ ብልጭ እንዲል አደረገ፡፡ ኤምባሲው ለሉብናናዊቷ አሰሪ ስልክ በመደወል ያላትን እቃ ሰባስባችሁ አምጡ፡፡ በቃ!….
ለልጅቷ ቤተሰቦች ደውለን እንዲከሱ ለማድረግ ቢሞከርም ስልካቸው ሊነሳ አልቻለም፡፡ ያለው አማራጭ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሳወቅ ነውና ይህን ተግባር አከናወንን፡፡ መፍትሄ ይገኝ ይሆን? ሬሳዋ ፍሪጅ ውስጥ ተቀመጦ ቀረ፡፡ መቼ አስታውሰው ይልኩት ወይም ይቀብሩት ይሆን? ኢንሹራንሷንስ ኤምባሲው ዝም ይል ይሆን? ያነጋግራል፡፡

The post በቤይሩት ኢትዮያዊቷ ራሷን አጠፋች በሚል ሰበብ….. ኤምባሲው ያለምንም ምርመራ ሬሳዋን አሳፍሩ ማለቱ ብዙዎችን አሳዘነ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>