የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ አይሮፕላን በኮቶካ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ሜከስከሱ ከጋና አክራ የወጡ ዜናዎች አመለከቱ::
የመከስከስ አደጋው የተከሰተው ካርጎ አይሮፕላኑ በኤርፕርቱ ለማረፍ ሲንደረደር በነበረው መጥፎ አየር ምክንያት መሆኑን የአየር መንገዱ ባለስልጣናት ተናግረዋል::አደጋው የተከሰተው ጠዋት ሶን የጋና አየር መንገድ ባለስልጣናት ዘግይተው መረጃ መስጠታቸው ታውቋል::
የበረራ ቁጥሩ ET -AQV የሆነው አይሮፕላን ከቶጎ ሎሜ ተነስቶ አክራ ለማረፍ ሲሞክር አደጋው መድረሱን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል::በአይሮፕላኑ ጋር የነበሩ 3 ሰዎች የተረፉ ሲሆን በአሁን ሰአት በወታደራዊ ሆስፒታል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል::