ሰለሞን ከተማ ቦሩ፣ ታዛቢ
“ፍጹም ነው እምነቴ” ይናገራል ይህን የአቶ ነሲቡ ስብሐት መጽሐፍ ሳነብ፣ ወደሁዋላ ሄጄ ብዙ ነገር እንዳሰላስልና እንዳይ ብቻ ሳይሆን ገፈቱንና ህመሙን፣ ጭንቀቱንና ብሶቱን፣ የተሸናፊነት መሪር ቁጭቱን እንድነከርበት አድርጎኛል። ያለፉትን፣ የወደቁትን፣ የቆሰሉትን፣ የጨለመባቸውን፣ ተስፋቸው የተቆረጠውን፣ በተሰናከለ ህይወት ውስጥ የሚጉዋዙትን የዛን ዘመን ጀግና ወጣቶች ሁሉ በሚንከራተት አይነ ህሊናዬ እንድዳሥሳቸው፣ እንድባባላቸው አድርጎኛል። ካቻምና አንድ ልጆቻቸው በቀይ ሽብር የተገደሉባቸው አዛውንት “ኢህአፓ ይመጣል፣ ከምላሴ ፀጉር ይነቀል ይህ ባይሆን” እያሉ በምሬት ሲነግሩኝ፤ በህብረተሰባችን ውስጥ የተተከለውን ቁስል እና የነፃነት ተስፋ ከዚህ መጽሀፍ ጋር እንዳቆራኘው አድርጎኛል። –[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—–