Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የኢትዮጵያና የግብፅ የጋራ ሚኒስትሮች ጉባዔ የተለያዩ ስምምነቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

$
0
0
An Egyptian government minister who visited Addis Ababa earlier this week has urged Ethiopia to halt construction of a multi-billion dollar hydroelectric dam project on the Nile's upper reaches – but the request was denied.

An Egyptian government minister who visited Addis Ababa earlier this week has urged Ethiopia to halt construction of a multi-billion dollar hydroelectric dam project on the Nile’s upper reaches – but the request was denied.

ከባለፈው ቅዳሜ አንስቶ እስከ ሰኞ ድረስ የተካሄደው የኢትዮጵያና የግብፅ የጋራ ሚኒስትሮች ጉባዔ የተለያዩ ስምምነቶችን በማፅደቅና በመፈራረም ተጠናቀቀ፡፡

በግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራው የልዑክ ቡድን በስብስቡ ውስጥ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ የትምህርት ሚኒስትርና የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የተካተቱበት ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር የመግባቢያ ሰነድና ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡

በዚህም መሠረት በጤና፣ በሴቶች፣ በትምህርት፣ በንግድና በዲፕሎማሲያዊ ልምምዶች ላይ ስምምነት የተፈረመ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ ተፈርመው ተፈጻሚ ያልሆኑ ስምምነቶችንም ለማስፈጸም በጋራ እንደሚሠሩ የሁለቱም አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ የተካሄደው የሁለቱ አገሮች የጋራ የሚኒስትሮች ስምምነት ላይ አገሮቹ በጋራ የሚሠሩባቸው በርካታ የንግድና የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸው አጽንኦት ተሰጥቶበት ውይይት የተካሄደበት ሲሆን፣ ቀጣዩ ስብሰባ ከሁለት ዓመት በኋላ በካይሮ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡

ከቅርብ ወራት በፊት በኢኳቶሪያል ጊኒ ርዕሰ መዲና ማላቦና በኒውዮርክ በተደረጉ ስብሰባዎች አማካይነት ሁለቱ አገሮች ውይይቶችና ስብሰባዎች ማድረጋቸው አስፈላጊ እንደሆነ መስማማታቸው ይታወሳል፡፡ በቀጣይም በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስብሰባ እንደሆነ ከስብሰባው በኋላ በወጣው መግለጫ ላይ ተገልጿል፡፡

ለዚሁ ስብሰባ ወደ አዲስ አበባ የመጡት የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር የተወያዩ ሲሆን፣ ‹‹ለዘመናት የቆየው የሁለቱ አገሮች የንግድ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሁለቱም አገሮች ነጋዴዎችን ማበረታታት ይገባናል፤›› ብለዋል፡፡

ምንም እንኳን የሁለቱ አገሮች የንግድ ግንኙነት መልካም ነው ቢባልም፣ ሁለቱ አገሮች ካላቸው የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ቅርፅ የተነሳ ከዚህም በላይ መሥራት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

ሁለቱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባው በቀና መንፈስና በወዳጃዊ መልኩ መካሄዱን የገለጹ ሲሆን፣ አገሮቹ በቀጣይ የሚያደርጓቸውን ዘርፈ ብዙ ውይይቶችና ስብሰባዎች በቀና መንፈስ እንዲካሄዱ መንገድ የጠረገ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ከዚህ ስብሰባ ጎን ለጎን በሁለቱ አገሮች ባለሥልጣናት መካከል ውይይቶች የተካዱ ሲሆን፣ በጋራ የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው ስብሰባው ከሁለቱ አገሮች የንግድ ግንኙነት በተጨማሪ በደቡብ ሱዳንና በቡርኪና ፋሶ ስላለው ሁኔታ እንዲሁም ስለፍልስጤም ጉዳይና ኢቦላን በተመለከቱ መወያየታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ይህ አሁን በአዲስ አበባ የተካሄደው የጋራ የሚኒስትሮች ጉባዔ አምስተኛው ሲሆን፣ ስድስተኛ ስብሰባ ደግሞ እ.ኤ.አ. በ2016 በካይሮ እንዲሆን በመወሰን ተጠናቋል፡፡

Ethiopian Reporter


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>