Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: የብሔራዊ ቡድናችን አማካይ አዲስ ሕንጻ ለሱዳኑ ክለብ ለመጫወት በ$100 ሺህ ዶላር ፈረመ

$
0
0

addis hinsta
(ዘ-ሐበሻ) ከ31 ዓመታት በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን ለመካፈል የበቃው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የደደቢት እግር ኳስ ክለብ አማካይ ተጫዋች አዲስ ህንፃ ለሱዳኑ አልአህሊ ሸንዲ ክለብ ለመጫወት መስማማቱን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። በደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ብሄራዊ ቡድናችንን ወክለው ከሄዱት ተጫዋቾች መካከል አስደናቂ ብቃታቸውን ካሳዩት መካከል አንዱ የሆነው አዲስ ሕንፃ ለሱዳኑ ክለብ ለመጫወት የተስማማው ለ3 ዓመታት እንደሆነ የሱዳን ጋዜጦች ጽፈዋል።
ትናንት ግንቦት 27 ቀን 2005 ለሱዳኑ አልሃሊ ሸንዲ ክለብ የፈረመው አዲስ ሕንፃ ለዝውውሩም ወደ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዳገኘ ተጠቅሷል።
የ25 ዓመቱ ወጣት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች 73 ኪሎ ይመዝናል። ቁመቱም 1.83 ሲሆን ደደቢት ከመጫወቱ በፊት በባንኮች ስፖርት ክለብ ሲቻወት የሀገር ውስጥና ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ጉልህ ሚና ማበርከቱ የህይወት ታሪኩ ያሳያል። አዲስ ህንፃ የተወለደው ከአዲሰ አበባ በ 30 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው የቢሾፍቱ /ደ/ዘይት/ ከተማ ነው፡፡ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተጫዋች በሰፈር ውስጥ የጨርቅ ኳስ በመጫወት የጀመረው አዲስ በ 1990 ዓ.ም በእግርኳስ ፕሮጀክት ማሰልጠን ጀመረ ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተልም በአዲስ አበባ ባንኮች እይታ ውስጥ ገባ፡፡
አዲስ ህንፃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀላቀለው ክለብ ኢትዮጵያ መድንን ነው፡፡ በ 1997 ዓ.ም በአራት አመትም በመድን ቆይታ አድርጓል፡፡ በ2001 ዓ.ም የኢትዮጰያ ባንኮችን ትኩረት በማግኘቱ ወደ ባንኮች አቅንቶም ክለቡ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ሻምፒዮና ለፍፃሜ ሲበቃም አዲስ ጉልህ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ በቅ/ጊዮርጊስ ተሸንፈው ዋንጫውን ቢያጡም በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ መሳተፍ የሚያስችላቸውን እድል አግኝተዋል፡፡
አዲስ ሕንፃ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወት የጀመረው በ 1997 ዓ.ም በወንድማገኝ ከበደ ይሰለጥን በነበረው የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ እንደነበር የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል። (ከሊሊ ሞገስ – ዘ-ሐበሻ)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>