በሰደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያጋጠመውን ዙሪያ ገብ ችግር ፣ በመምህራን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል ከዚህ አንፃር መምህራን የትምህርቱን ጥራት ለማስጠበቅና መብቶቻቸውን ለማስከበር ማድረግ ያለባቸውን እንቅስቃሴና መወሰድ የሚገባቸውን እርምጃ በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ መግለጫዎችን በማውጣት በ መላው ዓለም ላሉ ኢትዮጵያውያን ባጠቃላይና በተለይ ለጉዳዩ ባለቤቶች ለኢትዮያጵያ መምህራን ፣ ለተማሪዎችና ለወላጆች እንዲደርስ አድርጓል።