Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የአፋር ህዝብ እንደ ባህል የሚያየውን እጥቅ ለመንግስት እንዲያስረክብ ታዘዘ (የማሣሪያ ማስመዝገቢያውን ሰርተፊኬት ይዘናል)

$
0
0

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦

ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ በአፋር ክልል እንደ አዲስ ህግ ህዝቡ የጦር መሳሪያውን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመንግስት እንዲያስረክብ የሚል ህግ ወጥቷል። ይህን ትእዛዝ ብዙዎችን ያስቆጣ ሲሆን ህጉ የወጣው በሰሜን አፋር የአፋር ነዋሪዎችና የትግራይ ምልሻዎች ተጋጭው አንድ የአፋር ወጣት ከሞተበት ግጭት በኋላ ነበር።
afar gun
በ1998 ዓ.ም አቶ መለስ ዜናዊ በፓርላማ ላይ ስለ አፋር ህዝብ እጥቅ ተጠይቀው ሲመልሱ «የአፋር ህዝብ እጥቅ ባህልና ለእንስሳ ጥበቃ እንጂ ለሽብር አይደለም።» ብለው ነበር አሁንስ? ወደ ሽብር ተቀይሮ ይሁን? ብቻ አላውቅም ግን እንኳን ጠመንጃ ባለ ብዕርም አሸባሪ እየተባለ አይደለም እንዴ? በአሁን ወቅት እኮ የኢህአዴግ ቲፎዞ ካልሆንን አሸባሪ ወይም አሸባሪዎች የምንባልበት ጊዜ ላይ ነን።

እና ወደ መረጃው ስመልሳችሁ ይህን ትዕዛዝ ተከትለው አንዳንድ የአፋር ወጣቶች ከነመሳሪያቸው ጫካ ገብተዋል። ይህን ግን ለአፋር ህዝብ ቀላል ፍርድ አይምሰላችሁ የአፋር ህዝብ እስከ ዛሬ መብቱን የሚያስከበረው በእጁ ነው። ይህ ደግሞ ህወሃት ካለው እቅድ አንፃር ሲታይ ህወሃት ካቀደው ከጀቡቲ መቀሌ ለሚዘረጋው የባቡር ሐዲድ ዝርጋታና ካላቸው ብዙ የአፋር መሬቶች የማጠቃለል እቅድን በቀላሉ ለማሳካት ከሚደረጉት እንቅስቃሴዎች አንድ አካል ነው ብለን እናምናለን። ወያኔ ዳሉልን ጨምሮ በአፋር ክልል በማዕድን እና ጨው የሚታወቁ ቦታዎች ወደ ትግራይ ማጠቃለል ይፈልጋል። ስለዚህ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ካለቸው ስትራቴጂ አንዱ የአፋር ህዝብ የታጠቀውን መሳሪያ ለመንግስት እንዲያስረክብ ማድረግ ነው።

ሁለተኛው ደግሞ በአፋር ወሳኝ ቦታዎች ላይ የትግራይ ተወላጆች በሰፈራ ፐሮግራም መኖር ሲሆን ለሰፈራ ሲመጡ ለልማት ነው ተብለው የሚመጡ ሲሆን በመንግስት የመኖሪያ ቤቶች ይሰራላቸዋል። ካሁን በፊት 60 ሺ የትግራይ ተወላጆች በትንዳሆ ሱኳር ፈብሪካ ስም በአፋር ክልል በአይሳኢታ፣ በዱበብቲና በሚሌ መኖሪያ ቤታቸው ተቀብለው መኖር ጀምረዋል። እዛ አካባቢ ሲኖሩ የነበሩ የአፋር ነዋሪዎች በማይረባ ካሳና በግዴታ ተፈናቀሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአብዴፓ መደበኛ ጉባኤ በሰመራ በሉሲ አደራሽ ተካሄደ፤

ባለፈው ቅዳሜ 15/2/ 2007 የተጀመረው ይህ ሰብሰባ ላይ የተለያዩ አጀንዳዎች የቀረቡ ሲሆን ይበልጥ ያተኮሩበት ለመጪው ምርጫ ስለሚወዳደሩ እጩዎች ነበር። ስብሰባውን ማዘጋጀት የነበረበት የክልሉ አቢይ ኮሚቴ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሰባን እንዲመሩ ተደርጓል። በስብሰባው ላይ በሴኔጋል የሚገኘው የአፍሪካ አምሳደሮች ማህበር ሊቀመንበርና የአብዴፓ ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አምባሳደር ሃሳን አብዱልቃድር የተገኙ ሲሆን በአቶ እስማኤል አሊሲሮና በአምባሳደር ሀሳን መካከል አለማግባባት እንደተፈጠረ ምንጮችን ዘግበዋል። በመጨረሻም አብዴፓን ወክለው ለምርጫ የሚወዳደሩ እጩዎች የፓርቲውና የድርጅቱ ኃላፊዎች እንዲያቀርቡ ተወስኗል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፋር ክልል የክልሉ መሪዎች እርስ በእርሳቸው ትልቅ አለመግባባት ውስጥ እንዳሉ ይነገራል። ለምሳሌ ፦ የፀጥታ ቢሮው አቶ ስዩም አወል እና የአቶ እስማዕል ሚስት ወ/ሮ ፋጡማ አብደላ አይነጋገሩም። የሸሪዓ ቢሮው ሃጂ እስማኤልና አቶ እስማኤል አሊሲሮ አይስማሙም። አቶ ስዩም አወል በክልሉ በክፍተኛ ማዕረግ ያላቸው የፖሊስ የልዩ ኃይልና የድህንነት ኃላፊዎች በእጃቸው ውስጥ ሲሆን ክልሉን እንደፈለጉ የሚያሸከርከሩ ባለስልጣን ናቸው። አሁን አሁን እነዚህ ባለስልጣናት ከመጪው ምርጫ በኋላ በነበሩበት ስልጣናቸው የመቆየት ዕዳላቸው የመነመነ ሆኖባቸዋል።

ምክንያቱም ኢህአዴግ በዚህ አራት አመታት ውስጥ ከአፋር ህዝብ ባጋጠመው ዘርፈ ብዙ ተቃውሞ ምክንያት የሆኑት በእነዚህ ባለስልጣናት ችግር በመሆኑ የህወሓት መሪዎች ተስፋ ቆርጠዋል። አቶ እስማኤል አሊሲሮን ጨምሮ እነዚህ ባለስልጣናት በየጊዜው «ከጫካ ተቃዋሚዎችን እናስገባለን» እያሉ የተወሰኑ ቤተሰቦቻቸውን ከጫካ የገቡ በማስመሰል ብዙ ሚሊዮን ብሮች ከኢህአዴግ የሚቀበሉ ቢሆንም የአፋር በረሃን ከኢህአዴግ ተቃዋሚዎች ነፃ ማድረግ አልቻሉም። ኢህአዴግ እንደሚያምነው ሁሉም በገንዘብ ሃይል አስተዳድራለሁ የሚለውን መርህ አብዴፓዎች ተግባራዊ ማድረግ አልቻሉም።

እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያን ሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የአፋርም ተወካዮች ከመሆናቸው አንፃር አሁንም በአፋር ህዝብ ውስጥ የኢህአዴግ አባል በጣም አነስተኛ ነው።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>