Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በኢትዮጵያውያን ተቃውሞ የተነሳ የሥርዓቱ አሽከር የሆነው የሸዋፈራው የኮሜዲ ሾው ተሰረዘ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት ኢሕአዴግን አስተዳደር ደግፎ በስደት የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ በሕዝብ ፊት ተሳድቦ ከመንግስት ባለስልጣናት ፍርፋሪ ለማግኘት ሲሰራ የቆየው ሸዋፈራው ደሳለኝ በዋሽንግተን ዲሲ ሰድቦ ለሰዳቢ ለሰጠው ሕዝብ ትያትር ለማሳየት የመጣ ቢሆንም ዝግጅቱ ሳይደረግ መሰረዙ ተሰማ።
shewaferaw
ከዋሽንግተን ዲሲ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች እንዳስታወቁት የወያኔ/ኢሕአዴግ አሽከር የሆነው አርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያውያኑን አይን ፈርቶ ተደብቆ የሚገኝ ሲሆን በየሄደበት ቦታ ሁሉ በሚደርስበት ተቃውሞ በከፍተኛ የስነልቦና ቀውስ ውስጥ መውደቁ ተሰምቷል።

መንግስትን ለማገልገል ሲል በስደት የሚገኘውን ሕዝብ ተሳድቦ፤ በዚሁ ሕዝብ ላይ ገንዘብ ለመሥራት የመጣው ሸዋፈራው ወደ አሜሪካ ከመምጣቱ በፊት በሃገር ቤት የሚገኙ የተለያዩ ሴት አርቲስቶችን “አሜሪካ እወስዳችኋለሁ፤ እዛ ሄደን በየ ስቴቱ ትያትር እናሳያለን” በሚል ቃል በመግባት ሴትነታቸውን ለመጠቀም ባደረገው ግፍ አርቲስቶቹ ከፍተኛ ሃዘን ውስጥ መውደቃቸው የተሰማ ሲሆን እዚህ ከመጣ በኋላ ትያትሩን ሊያቀርብ ሲል በተቃውሞ መመታቱ በሃገር ቤት የተበደሉትን ሁሉ እንዳስደሰተ ምንጮች ጠቁመዋል።

ዛሬ እሁድ በዋሽንግተን ዲሲ ይደረጋል በተባለው የሸዋፈራው ኮሜዲ ሾው ላይ በዲሲ የሚገኙ ታዋቂ አክቲቪስቶች “ካሁን በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል፤ የወያኔ ተላላኪዎች እንደፈለጉት አይጨፍሩብንም” በሚል በጠሩት ቦይኮት የተነሳ ዝግጅቱ ተሰርዟል። ለዚህ ዝግጅት ከቪዛና ከትራንስፖርት ጀምሮ በብዙ ሺህ የሚቆጠሮ ዶላሮች የፈሰሱ ሲሆን በኪሳራ ሊሰረዝ በቅቷል።

ከወያኔ ጋር በመተባበር ለሆዳቸው ያደሩ አርቲስቶች በዲያስፖራው ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰባቸው ሲሆን ሃመልማል አባተ ለሲዲ ምርቃት በጠራችው ኮንሰርት በደረሰባት ቦይኮት 55 ሰው ብቻ ተገኝቶ አፍራ ወደ ሃገር ቤት መመለሷ መዘገቡ አይዘነጋም።

ሸዋፈራው ከዲያስፖራው አፍሰዋለው ያለው $$$ በዲሲ እንዲህ ያለው እክል ያጋጠመው ሲሆን በሌሎች ስቴቶች እንኳን የኮሜዲ ሾው አደርጋለሁ ቢል በየቦታው ባሉ የድጋፍ ሰጪዎች ከፍተኛ የሆነ ችግር እንደሚገጥመው ከወዲሁ እየተነገረ ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዲያፖራው ሕዝብን እየጨፈጨፈ ከሚገኘው መንግስት ጎን ለቆሙ ሆዳም አርቲስቶች ያለው ትዕግስት ተሟጦ ማለቁ ከሚደረጉት እንስቃሴዎች እየታየ ነው።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>