ከአንዶም ገብረሥላሴ
በፌደራል መንግስት የተፈቀደ የማይጨው ተክኒክ ኮሌጅ ቀስበቀስ ወደ ዩኒቨርስቲነት የሚያደርገው እድገት በትግራይ ክልል አስተዳር ወደ ሌላ ቦታ በመዛወሩ የኣከባቢው ህዝብ ማስቆጣቱ መዘገቡ ይታወሳል። የማይጨውና አካባቢዋ ህዝብ በክልል ትግራይ አስተዳደር የኮሌጁ ወደ ዩኒቨርስቲ እድገት በመከልከላቸው ትናንት ከፍተኛ አድማ እንዲያካሂድ ምክንያት ሆነዋል። ባጃጆች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የኮሌጁ ማህበረሰብና የከተማው ኑዋሪ የስራ ማስቆም አድማ ኣድርገው ውለዋል። ለእሁድ 18 / 12 / 2006 ዓ/ ም የሰላማዊ ሰልፍም ለከተማው አስተዳዳሪዎች ጥያቄ አቅርበዋል።
የፌደራል መንግስት ደብዳቤ ተመልከቱ።
ነፃነታችን በእጃችን ነው…!