Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ ዛሬ ፍድር ቀርቦ የዋስትና መብቱ ሳይጠበቅ ለዓርብ ቢቀጠርም የትግርኛ ሙዚቃ ለምን ተከፈተ ብሎ በሰው ላይ ጉዳት አድርሷል በሚል 2ኛ የክስ መዝገብ ተከፍቶበታል፡፡

$
0
0

ፍኖተ ነፃነት

10606390_684528351632102_6265250781347686507_nበ4/12/06 እሁድ ማታ በደህንነት ኃይሎች በቁጥጥር ስር የዋለውና በእስር ላይ የሚገኘው ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቢቀርብም ፖሊስ ከሳሹን ስላላገኘሁትና የህክምና ማስረጃውን ስላልደረሰልኝ የጊዜ ቀጠሮ ይፈቀድልኝ ያለ ቢሆንም ወጣት ጥላዬ መርማሪው የምርመራ ስራን እየሰራ አይደለም ይልቁንም ራሱ ቢሮ የያዙኝ ደህንነቶች እየመጡ መርማሪው ባለበት ከእኛ ጋር ለመስራት ፈቃደኛ እስካልሆንክና የምንሰጥህን ተልዕኮ እስካልፈፀምክ እዚህ ትበሰብሳለህ እንጂ አትወጣም እያሉ እንደሚዝቱበት ለፍርድ ቤቱ ቢያስረዳም ፍ/ቤቱ ፖሊስ ለ16/12/2006 ፖሊስ መረጃዎቹን አጠናቆ እንዲያቀርብ እስከዛ የዋስና መብቱ ተቀባይነት አለማግኘቱን ብይን ሰጥቷል፡፡

ወደ እስር ቤት ሊሄድ በሚዘጋጅበት በድጋሚ ተጠርቶ 2ኛ የክስ መዝገብ እንደተከፈበት እና ክሱም በ12/10/2006 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ላይ የትግርኛ ሙዚቃ እንዴት ይከፈታል በማለት በሰላም የሚዝናኑ ግለሰቦች ላይ ጉዳት አድርሶ ተሰውሯል የሚል ሲሆን ስለቀቀረበበት ክስ የተጠየቀው ጥላዬ እኔ ከአካባቢዬ አልተሰወርኩም ሲይዙኝም ከቤቴ በር ላይ ነው እስከዚህ ሰዓትም አላመሽም ፖሊስ እያቀረበ ያለው ክስ ከሳሽ በሌለበት ራሱ እየፈጠረ መሆኑን ፍርድ ቤቱ እንዲረዳልኝ እና የአንድነት ፓርቲ አባል በመሆኔ ባለኝ የፖለቲካ አመለካከት ጫና ለማሳደር የተወጠነ ውጥን መሆኑን መርማሪው ራሳቸው ያውቃሉ በማለት አስረድቷል ፡፡ፖሊስ ለምን ጉዳት የደረሰበትን ግለሰብ እንዳላቀረበና 2ወር ሙሉ ፖሊስ የት ነበራችሁ ብሎ ፍ/ቤቱ ቢጠየቅም ከሳሽ ለጊዜው እዚህ ስለሌለና ልናገኘው ባለመቻላችን የህክምና ማስረጃውን እንድናቀርብ ይፈቀድልን በማለቱ ፍርድ ቤቱ የፖሊስን ማስረጃ ለመመልከት በ2ኛው ክስ ለ14/12/2006 ዓ.ም ለ3፡00 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፖለስ እስካሁን በጥላዬ ላይ ክስ የመሰረተውን ከሳሽን ሊያቀርብ ካለመቻሉም ባሻገር ፍ/ቤቱን የህክምና ማስረጃ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ ማለቱ አግራሞትን ጭሯል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>