የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 11 ቀን 2006 ፕሮግራም
<< ...አንድነት የወሰነው የበለጠ ከመኢአድ ጋር ውህደቱን የሚያጠናክር ውሳኔ ነው። የውህዱን ኮሚቴ ስራውን እንዲያቁዋርጥ ተደርጓል። ሌላ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳዩን የሚከታተል ኮሚቴ ነው የተዋቀረው...>>
ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የአንድነት ፕሪዝዳንት ስለ ውቅታዊው የአንድነት አቋም ተጠይቀው ከሰጡት ምላሽ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<<...የአንድነት እና መኢአድ ውህደት በፍጹም ሊቆም አይችልም። ከታች ያሉ አባሎቻችን አብረው እየሰሩ ነው። በቅድመውህደት በተፈራረምነው ሰነድ ለውህደቱ መቀጠል አለበት።መኢአድም ትልቅ መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። በአንድነት በኩል የተፈጠሩ ችግሮች ፓርቲውን የሚያዳክሙ አይደለም ከካቢኔ አባልነት ብንለቅም ከአዲሱ ካቢኔ ጋር መስራታችን ይቀጥላል።ችግሩን አንድነት በመዋቅሩ ይፈታዋል...>>
አቶ ዳንኤል ተፈራ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ አንድነት ፓርቲ የውህዱን ኮሚቴ ስራውን እንዲቋረጥ ማድረጉን በመቃወም ከካቢኔ አባልነታቸው ቢለቁም ትግሉን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል(ሙሉውን ያዳምጡት)
በአሜሪካ ሚዙሪ ግዛት ፈርጉሰነን ላይ በፖሊስ የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ወጣትና ለሕዝቡ ተቃውሞ በፖሊስ የተሰጠው ምላሽ ያመጣው ጣጣ (ልዩ ጥንቅር)
<...ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብር ሰው ተከሰሰ ሲባል ሕዝቡ አሁን አይፈራም። እንደውም ያሾፋል ምክንያቱም ያውቀዋል አግባብ ያልሆነ ስም እየተለጠፈ የሚወሰደው እርምጃ አገሪቱን ወደ ችግር እየገፋት ነው...በፕሪሱ ላይ የሚወሰደው እርምጃ የከፋ ሆኗል። ይህቺ አገር የጥቂቶች ብቻ አይደለችም።ጥቂቶች መሳሪያ ስለተያዘ ደህንነቱን መከላከያውን ስለተቆጣጠሩ ብቻ የፈለግነውን እንወስዳለን ማለት ሁዋላ ያስጠይቃል..ለአፍሪካም ለመካከለኛው ምስራቅና ለዓለም ስጋት የሆኑ አምባገነኖችን መጨረሻ አይተናል....> ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ስለ ወቅታዊው ጉዳይ ለህብር ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
ዜናዎቻችን
የዓለም የጠየና ድርጅት ኢቦላ ኢትዮጵያን ያሰጋታል ሲል አስጠነቀቀ
የመኢአድና የአንድነት ውህደት ሊቀለበስ አይችልም ተባለ
አንድነት ፓርቲ ጠንካራ በመሆኑ በውስጡ የተፈጠሩ ችግሮችን በራሱ ተቋም እንደሚፈታ ተገለጸ
ኢ/ር ግዛቸው የውህዱን ኮሚቴ ያፈረስነው ውህደቱን ለማጠናከር ነው አሉ
ግብጽ በሳተላይት የአባይ ግድብን ሰልላ የውሃ ማቆሪያው ግንባታ አለመጀመሩን ደርሼበታለሁ አለች
ጅቡቲ በቅርቡ በኤርትራ የታገቱባት ወታደራዊ መኮንን በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠየቀች
የኢህአፓ አባላትና መሪዎች በአንድነት ተጠናክረው ክፍፍልን በማስወገድ ለትግል እንዲነሱ ትንሳዔ ኢህአፓ ጥሪ አቀረበ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ፦