ከናቲ ማን
በስደት ወደ ኖርዌይ ያቀናው ገና ጨቅላ እያለ ነበር። ይህ ወጣት ተጫዋች ከልጅነቱ ጀምሮ ልቡ ውስጥ የገባው የእግር ኳስ ጨዋታ ከጎዳና ተነስቶ እስከትላልቅ ስታዲየሞች አድርሶታል። ወጣቱ አሚን አስካር ይባላል። በኖርዌይ ሊግ አስደናቂ የሚባል ብቃቱን እያሳየ ይገኛል። የደረሰን መረጃ እንደሚያመለከተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ለትውልድ ሃገሩ እንዲጫወጥ ጥሪ አቅርበውለታል። አሚን ይህን ጥሪ ይቀበል አይቀበል የታወቀ ነገር ባይኖርም የዘ-ሐበሻ ተከታታዮች ይህን ወጣት በኖርዌይ ሊግ በ2012/2013 የውድድር ዘመን ያስቆጠራቸውን ጎሎች የሚያሳየውን ይህንን ቪድዮ እንጋብዛችሁ።