Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የማንቸስተር ዩናይትድ አስገራሚ አቋም (ሻምፒዮን ሆነ)

$
0
0

man 1

man 2

man 3

man 4

man 5

man 6ማን.ዩናይትድ ዛሬ ኦልትራፎርድ ላይ አስቶንቪላን በሮበን ቫንፐርሲ 3 ጎሎች በዜሮ አሸንፎ ፕሪምየር ሊጉን ለ20ኛ ጊዜ አሸንፏል። የማን.ዩናይትድን ሲዝን በትንሹ የሚዳስስ አጭር ዝግጅት ከዘ-ሐበሻ ተዘጋጅቷል ይከታተሉት።
ማንቸስተር ዩናይትድ ከሰንደርላንድ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ ሮቢን ቫን ፔርሲ ጎሉን ለማስቆጠሩ እርግጠኛ ነበር፡፡ በስታዲየም ኦፍ ላይት የውጤት መመዝገቢያ ላይ ግን ጎሉ የተቆጠረው በተጋጣሚው ተጫዋች ታየተስ ብራምብል መሆኑ ተፃፈ፡፡ በራስ ላይ የተቆጠረ ጎል ተደርጎ መውሰዱ ቫን ፔርሲ ያለ ጎል አልባ ደቂቃዎች መጨመራቸውን ቀጠለ፡፡ ሆላንዳዊው በክለቡ ማሊያ በመጨረሻ በተጫወተባቸው 10 ሰዓታት አንድ ጎል ማስቆጠር ተስኖታል፡፡ ለ594 ደቂቃዎች ማለት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ላይ ማንቸስተር ዩናይትድ ከኤፍ.ኤ.ካፕ እና ከቻምፒየንስ ሊግ ውጭ ቢሆንም በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ሰንደርላንድን ድል በመንሳት ለሰባተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸንፎ ወጥቷል፡፡ የቡድኑ የውድድር ዘመን የሊጉ ምርጥ ብቃት በታየበት ሰሞን ኮከቡ ጎል አግቢያቸው በጎል ድርቅ መመታት አስገራሚ ቢሆንም የሚነግረን ነገር አለ፡፡ ቡድኑ በሌሎች ቦታዎች ብቃቱን ማሳደጉን ያረጋግጥልናል፡፡
ቻምፒየንስ ሊግ እጅግ አጓጊ በሆነ ደረጃ ላይ ባለበት በዚህ የሩብ ፍፃሜ ወቅት አንድም የእንግሊዝ ክለብ አይገኝበትም፡፡ ይህ ሲሆን ከ1996 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ቡድናቸው የማይዋዥቅ ብቃቱን የሚያበረክት ጎል አስቆጣሪ አለመያዛቸው ያስቆጫቸዋል፡፡ ከሪያል ማድሪድ ጋር በተደረጉት የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ላይ ጎል ማስቆጠር የቻለው የዩናይትድ ተጨዋች ዳኒ ዌልቤክ ብቻ ነው፡፡ ቫን ፔርሲ ከስፔኑ ኃያላን ጋር አልቀናውም፡፡ ከዚህም በኤፍ.ኤ.ካፑ በደርሶ መልሱ የቼልሲ ግጥሚያ ቫንፔርሲ በተጠባባቂነት ተቀይሮ ገብቶም የፈየደው ነገር የለም፡፡ በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ላይ አላቋርጥ ብሎ የነበረው የጎል ፍሰት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ ሊመለስለት አልቻለም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቀድሞው የአርሰናል አጥቂ ለ622 ደቂቃዎች በሜዳ ላይ ቆይቶ አንድ ጎል ብቻ አግብቷል፡፡ ከዚያ ፊት ግን በአማካይ በየ99 ደቂቃው አንድ ጊዜ ኳስና መረብን ያገናኘ ነበር፡፡ ምናልባት ለሁለት ተከታታይ የውድድር ዘመናት ለየክለቦቹ ከሞላ ጎደል በሁሉም ጨዋታዎች ላይ የመሰለፉ ነገር አድክሞት ሊሆን ይችላል፡፡ አምናም ሆነ ዘንድሮ አርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ በቫን ፔርሲ ላይ ተመርኩዘው መቅረባቸው ግልጽ ነው፡፡
በተለይ አርሰናል ለውጤታማነት በተለይ ቫን ፔርሲ ላይ የተንጠላጠለ መሆኑ ጉልህ ነበር፡፡ ዘንድሮ ያለ እርሱም ምን ያህል ጥንካሬው እንደላሸቀ ታይቷል፡፡ በማንቸስተር ዩናይትድ ዌይን ሩኒ ጎል የማስቆጠር ሸክሙን አግዞት 12 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ ስምንት ጎሎችን ያገባው ሃቪዬር ሄርናንዴዝም የሸክሙ ሌላው ተካፋይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሺንጂ ካጋዋ በቅርቡ በኖርዊች ሲቲ ላይ ሃት ትሪክ ከመስራቱ በፊት ከቫን ፔርሲ ቀጥሎ የዩናይትድ ከፍተኛው ጎል አግቢ ፓትሪክ ኤቭራ (4)፣ ጆኒ ኢካንስ (3) እና ራፋኤል ዳ ሲልቫ (3) ነበሩ፡፡ አማካይ ክፍሉ ጎል የማስቆጠር እጥረት ገጥሞት ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ቫን ፔርሲ በድርጊቱ ተመቷል፡፡ በተለይ አንቶኒዮ ቫሌንሲያ፣ ሉዊስ ናኒ እና አሽሊ ያንግ ለችግሩ ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባል፡፡ ሶስቱ አማካዮች ባለፈው የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ ላይ በድምሩ 18 ጎሎችን አስቆጥረው ጎል የሆኑ 30 ኳሶችን አቀብለው ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን ሶስቱ በድምሩ አንድ ጎል ብቻ ያስቆጠሩ ሲሆን ያቀበሏቸው ጎል የሆኑ ኳሶቻቸው ብዛት ዘጠኝ ብቻ ናቸው፡፡ ሪያል ማድሪድ እና ቼልሲ ማንቸስተር ዩናይትድን ከቻምፒየንስ ሊግና ከኤፍ.ኤ.ካፑ ሲያስወጡት የፕሪሚየር ሊግ ተጋጣሚዎች ግን የኦልድትራፎርድ ክለብ ለ20ኛው ዋንጫ እንዲተም ፈቅደውለታል፡፡ ቡድኑ በዚህ ወቅት በፕሪሚየር ሊጉ ላይ እጅግ ደካማ ብቃት ካላቸው ቡድኖች መካከል ሁለቱን (ሬዲንግ እና ሰንደርላንድ) ገጥሞ ከብዙ ልፋት በኋላ ሁለቱንም ማሸነፍ የቻለው 1-0 ብቻ ነው፡፡ ሬዲንግ ከዩናይትድ ጋር ከመጫወቱ በፊት ባደረጋቸው ስድስት ግጥሚያዎች ሁሉ የተሸነፈ ቡድን ሲሆን ሰንደርላንድ ደግሞ ከስምንት ተከታታይ ጨዋታዎች አንድም ድል ያልተቀዳጀ ነበር፡፡
በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሚቆጠሩበት ጎሎች ይልቅ በእጥፍ ለሚበልጡ ጊዜያት ጎል ያስቆጥር ነበር፡፡ ከቫን ፔርሲ ብቃት መቀዝቀዝ በኋላ ግን ይህ ሊሆን አልቻለም፡፡ የሚያስቆጥራቸው ጎሎች ቢያሽቆለቁልም (በሊጉ ላይ) ሽንፈት አልገጠመውም፡፡ የዚህ አብይ ምክንያት የቡድኑ የተከላካይ መስመር ጥንካሬ መጨመር ነው፡፡ ሰር አሌክስ አጥቂያቸው ጎል ማምረት ሲያቆም ተከላካያቸው ብቃቱን አሳድጎ ከሽንፈቶች ታድጓቸዋል፡፡ ለ627 ደቂቃዎች አንድም ጎል ሊቆጠርበት አልቻለም፡፡
በግብ ጠባቂነቱ ቦታ በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ዴቪድ ደ ሂያ ቋሚ ተሰላፊነቱን ለአንደርስ ሊንዴጋርድ አሳልፎ ሊሰጥ እንደሚችል የሚያስጠረጥር ብቃት ነበረው፡፡ ሆኖም በራስ መተማመኑ ከውጤታማነት ጋር በማሳደግ አሁን ቋሚነቱን በአስተማማኝነት ይዟል፡፡ በጨዋታዎቹ ላይ የሚፈጽማቸው ስህተቶች ቁጥር ቀንሰዋል፡፡ አሁንም በራስ መተማመኑ ረገድ ከዚህም በላይ መጎልበት ያለበት ሲሆን በተለይ በክሮሶች ወቅት ያለው በቃላት የሚታማ መሆኑ ቀጥሏል፡፡ የጎል ሙከራዎችን በማዳር ረገድ ያስመዘገበው አሃዛዊ ብቃት በሊጉ በአንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጦታል፡፡ ወጣቱ ስፔናዊ ላይ ከሚሞክሩት የጎል ሙከራዎች 78% በመቶ ያህሉን ያድናል፡፡ በሊጉ ክለቦች በቋሚ ተሰላፊነት ከሚጫወቱት በረኞች ሁሉ ምርጡ ንፀሬ መሆኑነው፡፡ ብዙ የእግርኳስ አፍቃሪዎች በዴ ሂያ ላይ ተስፋ ሲቆርጡ ሰር አሌክስ ግን በእርሱ ፀንተው ቀመራቸው በመጨረሻ ፍሬውን ማፍራት ጀምሯል፡፡
በተከላካዩ መስመር ሪዮ ፈርዲናንድ ተደናቂ ብቃቱን መልሶ አግኝቶታል፡፡ የኔማኒያ ቪዲች ከጉዳት መመለስ በመሀል ተከላካይነት ቦታ ላይ ከአቫንስ ጋር ለተሰላፊነት ከባድ ፉክክር ውስጥ አስገብቷቸዋል፡፡ የዚህ ጤናማ ፉክክር ውጤት ደግሞ የማንቸስተር ዩናይትድን የኋላ መስመር በቀላሉ የማይጣስ አድርጎታል፡፡ በርካታ ጨዋታዎችን ምንም ጎል ሳይቆጠርባቸው መውጣት ችለዋል፡፡ ይህም ሰር አሌክስ ፈርጉሰን የሊጉን ንግስና መልሶ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ያመጡ ዘንድ ምክንያት ሆኗቸዋል።

የዩናይትድ አጥቂዎች የዘንድሮ የጎል ስታቲስቲክስ
ቫን ፔርሲ ሩኒ ሄርናንዴዝ ዌልቤክ ማን ዩናይትድ
- ጎሎች 22 12 8 1 66
- አንድ ጎል ለማግባት ስንት ጊዜ ኳስ ጋር ይገናኛል? 68.26 104.66 38.87 656 329.93
- በየስንት ደቂቃዎች አንድ ጊዜ ጎል ያስቆጥራል? 126.47 132.66 85.5 1113 450
- የመጨረሻ የሊግ ጎሉን ካስቆጠረ በኋላ የተቆጠሩት ደቂቃዎች 332 69 113 702 69
የጎል ዕድልን ወደ ጎልነት የመቀየር ንፃሬ 17.27% 15.78% 24.24% 2.77% 14.53%


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>