ህወሃቶች የፈጠራና የሐሰት ክስ እየፈበረኩ በርካታ ለወገንና ለአገር የሚቆረቆሩ ኢትዮጵያውያንን በአገር መክዳት፣ ዘር ማጥፋት እና ሽብር ፈጠራ ወንጀሎች በመክሰስ እና በማሰር ለከፍተኛ ፍዳና መከራ ዳርገዋቸዋል።
የእነ ሽመልስ ከማልን አርአያ እንዲከተሉ ተመልመለው እንደነ እስክንድር ነጋ፣ ርዮት አለሙ፣ ውብሸት ታየ አንዱዓለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣በቀለ ገርባ፣ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያውያንን ለእስርና ለሰቆቃ ከዳረጉት አቀብያነ ሕግ መሃል ቴዎድሮስ በሃሩ፣ ዘርሰናይ ምስጋናው፣ብርሃኑ ወንድምአገኝ በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው።
ቴዎድሮስ በሃሩ በአሁኑ ግዜ በአሜሪካን አገር በሰላም የተረጋጋ ኑሮ ለመመስረት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። ይሁናና በሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ፣ የሚኖረው ግለሰብ ፍርድ ቤት ስላቀረበው መረጃ የሐሰት ክስ ለመናገር ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ይህ ቪዲዮ ቴዎድሮስና ተባባሪዎቹ የህወሃቶችን ግፍ በፍርድ ቤት ሽፋን ለማስፈጸም የሰሩትን ወንጀል፣ በንጹሃን ዜጎች ያደረሱትን መከራና ፍዳ ለማሳየት ይሞክራል። ህወሃቶች እና ሎሌዎቻቸው በጸረ ሽብር ሕግ ሽፋን በሐሰት ክስ በበርካታ ንጹሃን ዜጎች ላይ ሽብርና ግፍ መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ብዙ መረጃዎች መኖራቸውን ግን በቀላሉ መካድ አይቻልም።