ተክለሃይማኖት አካባቢ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ብቻ ተለይተው ሊፈርሱ መሆኑን በአካባው ሚገኙ ነጋዴዎች ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡
ነጋዴዎቹ እንደሚሉት ከተክለ ሃይማኖት ጀምሮ እስከ ጥቁር አንበሳ የሚገኙ የመኪና ዕቃ መለዋወጫ፣ የጎማ መሸጫ እና ሌሎች የንግድ ሱቆች በአምስት ቀናት ውስጥ እንዲፈርሱ በመንግስት ተወስኗል፡፡ ከንግድ ቤቶቹ በስተጀርባ የሚገኙ የቀበሌ ቤቶች አብረው የማይፈርሱ መሆኑን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ “እኛ ግብር ከፋዮች ሆነን ከሌላው ህብረተሰብ ተለይተን በ5 ቀናት ውስጥ እንድንነሳ መደረጉ ህገወጥ ነው” ብለዋል፡፡
ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ከሚደረግባቸው የአዲስ አበባ አካባቢዎች መካከል በሚጠቀሰው በዚህ ስፍራ በርካታ የንግድ ሱቆች ይገኛሉ፤ በአካባቢው የሚገኙት የንግድ ቤቶች በአማካይ እስከ 4 ሰራተኛ የሚያስተዳድሩ ከመሆኑም በላይ በኮሚሽን ስራ ላይ ለተሰማሩ በርካታ ዜጎች የእለት ጉርስ ምንጭ እንደሆኑ ይታመናል፡፡
ምንጭ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ