Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ በአምቦ ብጥብጥ የሁለት ሚሊዮን ብር ንብረት ወደመብኝ አለ

$
0
0
ከአዲስ አበባ ከተማ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አምቦ ከተማ፣ በቅርቡ በተከሰተው ብጥብጥ ሰለባ ሆኛለሁ ያለው የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ሁለት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት እንደወደመበት አስታወቀ፡፡
744e

ከአዲስ አበባ ከተማ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አምቦ ከተማ፣ በቅርቡ በተከሰተው ብጥብጥ ሰለባ ሆኛለሁ ያለው የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ሁለት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት እንደወደመበት አስታወቀ፡፡

የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ ባለፈው ዓርብ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ በአምቦ ቅርንጫፍ ውስጥ የሚገለገሉባቸው ቁሳቁሶች በሙሉ በእሳት ጋይተዋል፡፡ አቶ ኃይለየሱስ እንዳሉት፣ ብጥብጡ ከመነሳቱ ሦስት ሰዓት ቀደም ብሎ የብጥብጥ አዝማሚያዎች መስተዋላቸው ሪፖርት በመደረጉ ሠራተኞች፣ የጥበቃና የደኅንነት ሠራተኞች ባደረጉት ጥንቃቄ 1.3 ሚሊዮን ብርና በዕለቱ ሲሠራባቸው የነበሩ ሰነዶች በገንዘብ ካዝና ውስጥ እንዲገቡ በመደረጉ ከጉዳት ተርፈዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አንድ ጥበቃ እሳቱ በተነሳበት ወቅት ከመስኮት ሲዘል እግሩ ላይ ጉዳት ከመድረሱ በስተቀር ሠራተኞች ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡

ሚያዝያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ለተቃውሞ ሲወጡ፣ ወደ ከተማው በዘለቀው ብጥብጥ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ በርካታ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

መንግሥት ባወጣው መግለጫ በአምቦና በኬኩታዮ ከተሞች የሰባት ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክን ጨምሮ፣ በተለያዩ መንግሥታዊና የግል ተቋማት ንብረቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ የሚገለገልበት ንብረትነቱ የአቶ ተስፋዬ ተስፋ ሕንፃ ላይ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ፣ ከሕንፃው ፊት ለፊት በተቃጠለ ከባድ ተሽከርካሪ መነሻ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት መኖሩን አቶ ኃይለየሱስ ተናግረዋል፡፡

የተነሳውን ብጥብጥ መንግሥት ሙሉ በሙሉ እንደተቆጣጠረው በማስታወቁ፣ ባንኩ ያቋረጠውን ኦፕሬሽን በድጋሚ ለመጀመር እየተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል፡፡

ነገር ግን ባንኩ የነበረበት ሕንፃ የተቃጠለ በመሆኑና ለዕድሳት ተጨማሪ ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ፣ ሌሎች አመቺ ሕንፃዎችን ለመጠቀም የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ  መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

የባንኩ አምቦ ቅርንጫፍ በ2003 ዓ.ም. ሥራ የጀመረ ሲሆን፣ 468 ደንበኞች አሉት፡፡ ቅርንጫፉ አዲስ እንደመሆኑ ከዋናው መሥሪያ ቤት ጋር በኔትወርክ እንዳልተገናኘ የሚናገሩት አቶ ኃይለየሱስ፣ በሠራተኞቻቸው ጥረት ግብይት ይካሄድባቸው የነበሩ ጠቃሚ መረጃዎች መትረፋቸውን ተናግረዋል፡፡ ሚያዝያ 29 ቀን 2006 ዓ.ም. አቶ ኃይለየሱስ የመሩት የልዑካን ቡድን በአምቦ ከተማ በመገኘት ጉዳት የደረሰበትን ቅንጫፍ ጎብኝቷል፡፡

ጉዳዩን ተራ ብጥብጥ አድርጐ መመልከት ያልወደደው መንግሥት፣ ከብጥብጡ ጀርባ አሉ ባላቸው ኃይሎች ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድ እያስታወቀ ነው፡፡ የኢትዮ-ጂቡቲ

የባቡር መስመር ዝርጋታ ጅማሮ፣ ለማብሰር ባለፈው ሳምንት ድሬዳዋ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከአገር ሽማግሌዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በተነጋገሩበት ወቅት እንዳሉት ከጉዳዩ ጀርባ ባሉ አካላት ላይ መንግሥት ዕርምጃ ይወሰዳል፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles