Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

አንድነት ፓርቲ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ “የእሪታ ቀን” በሚል ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ይቀላቀሉ! (ግዛቸው ሽፈራው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር)

$
0
0

ጤና ይስጥልኝ !

 

ግዛቸው ሽፈራው እባላለሁ። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር ነኝ።  አንድነት በኢትዮጵያ ሕጋዊ ፍቃድ አግኘቶ፣ በአገሪቷ ባሉ ክልሎች ሁሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀሰ ድርጅት ነው። አንድነት ከማንም ግለሰብና ድርጅት ጋር ፀብ የለዉም። የአንድነት ፖለቲካ የኢትዮጵያዊነት፣ የፍቅርና የመቻቻል ፖለቲካ ነው።  አላማችን ፣ የበለፀገች፣ ልጆቿ፣ በዘር ፣ በሃይማኖት፣ በጾታ ልዩነት ሳይደርገባቸው እኩል የሆኑባት፣ አንድነቷና ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን መመስረት ነው።

GizachewShiferaw

ግዛቸው ሽፈራው , የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር

 

አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኢሕአዴግ መራሹ መንግስት፣  ግልጽነት የጎድለው፣ ተጠያቂነት የሌለው፣ በሙስና የተዘፈቀና የመልካም አስተዳደር ችግር ያለበት እንደመሆኑ፣  በሕዝብ ላይ ትልቅ በደል እያደረሰ ይገኛል። የሚከተለው የተሳሳተና ጎጂ የመሬት ፖሊሲ፣  ዜጎች፣ በልማት ስም፣ በቂ ካሳ ሳይከፈላቸው፣ ከቤታቸው እና ከእርሻ ቦታቸው በኃይል እንዲፈናቀሉ እያደረገ ነው። የሰብአዊ መብት ረገጣው፣ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ….. በግፍ መታሰራቸው፣ የኑሮ ዉድነቱ ሕዝቡ ከሚሸከመው በላይ እየሆነበት ነው።

 

ሕዝባችን ከዚህ የተሻለ ይገባዋል።  ኢትዮጵያዉያን አሁን ያለውን አሳዛኝ ሁኔታ አንቀበለም በማለት፣ ለዉጥ መጠየቅ፣  ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረግ ይኖርብናል።

 

ሕዝቡ ድምጹን ማሰማት የሚችልበት መድረክ ያገኝ ዘንድ፣ አንድነት፣ በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እውቅና ያገኘበት፣ ሁለት ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎችን ፣ እሑድ ሚያዚያ 26 ቀን፣ በአዲስ አበባ እና በደቡክ ክልል በምትገኝ የድራሼ/ጊዶሌ አዘጋጅቷል። የአዲስ አበባ እና የጊዶሌ ነዋሪዎች፣ በነቂስ ወጥተው ድምጻቸውን እንዲያሰሙ በአክብሮት ጥሪ አቀርባለሁ።

 

ነጻነት ነጻ አይደለም። ነጻነትን ከሌሎች አናገኝም። ነጻነትን እኛዉ እራሳችን ነን ለራሳችን ማወጅ የምንችለው። እራሳችንን በግል ካያነው፣ ምንም ማድረግ የማንችል፣  አንድ ተራ ሰው አድርገን ልንቆጠር እንችላለን። ነገር ግን ተራ ሰዎች፣  በሚሊዮን ሲቆጠሩ፣ እነርሱን ማነቃነቅ የሚችል ምንም ኃይል አይኖርም። እንነሳ። ሰልፍ እንዉጣ። ድምጻችንን እናሰማ። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን ! እራሳችንን ነጻ በማወጣት አገራችንን ነጻ እናውጣ !

 

እንግዚአብሄር አገራችን ኢትዮጵያን ይባርካት

 

ግዛቸው ሽፈራዉ

 

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>