May 1/2014
በዛሬው ቀን በኖርዌይ በተከበረው አለም አቀፍ የሰራተኞች ቀን ላይ በመገኛት የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ በሀገር ቤት የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል እንደሚደግፍ አጋርነቱን አሳያ::
ሜይ 1, አለም አቀፍ የላብ አደሮችና የሰራተኞች ቀን በየአመቱ በመላው አለም በተለያዩ አህጉራት በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ይታወቃል:: ይህ መከበር ከጀመረ ከመቶ ሃያ አመት በላይ የሆነው የላብ አደሮችና የሰራተኞች ቀን ዘንድሮም ሜይ 1 ቀን 2014 (ሚያዚያ 23 ቀን 2006 ዓ.ም ) በተለያዩ አህጉራት ተከብሮል:: በዛሬውም ቀን ሜይ 1 ቀን 2014 በኦስሎና በኖርዌይ በተለያዩ ከተሞች በደማቃ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ በሰብአዊ መብትድርጅቶች፣ ሌሎችም ድርጅቶች እንዲሁም በኖርዊይ የሚኖሩ የተለያዩ ሀገራት ማህበረሰብ ክፍሎች (community) የየሀገራቸውን ባንዲራ እና የየድርጅታቸውን አርማ በመያዝ የሰራተኛውን መብት መከበር የሚጠይቁና ሌሎችንም የተለያዩ መፈክሮችን፣ አርማዎችን በመያዝ በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል:: በኦስሎ እና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባሎች የድጋፍ ድርጅቱ ለአባሎቹ ባደረገላቸው የሰልፍ ጥሪ መሰረት ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በዚሁ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን የሰብዊ መብት እረገጣ የተቃወሙ ሲሆን ለአንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ ያላቸውንም ድጋፍ አሳይተዋል:: በአሁኑ ሰአት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን የሰበሃዊ መብት እረገጣ ፣አፈና፣ እስራትና ግድያ በመቃወም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እና ሰማያዊ ፓርቲ ሰለማዊ ትግል እያደረጉ እንዳለና በሰላማዊ ትግል የወያኔን መንግስት እየተፋለሙት እንደሆነ ይታወቃል:: የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባሎችና አመራሮች የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ እና በማሰማት ለአንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ ያላቸውን የድጋፍ አጋርነታቸውን በማሳየት በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል:: ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!! ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ