ድርጅታችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በአንድ በኩል በሕዝባችን ላይ ለበርካታ አስርተ ዓመታት የቀጠለውን ሕግና መዋቅር ሰራሽ የፖለቲካ ሸፍጥ በዘላቂነት ለመቅረፍ፣ በሌላ በኩል ሕዝባችንና አገራችን ከተጋረጠባቸው የኅልውና አደጋዎች ለመታደግ በሚደረገው አገራዊ የበጎ ኃይሎች ጥምረት አካል በመሆንና በትጋት በመስራት ላይ የሚገኝ መሆኑን በኃቅ የሚፈርድ ሁሉ የሚረዳው እውነታ ነው። ምንም እንኳን ትጋታችን ለማንም አካል በመታያነት የቀረበ ባይሆንም፣ እጅግ ፈታኝ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳ ሆነን «የተሻለ ነገ» ሊመጣ ይችላል የሚል እሳቤን አንግበን እዚህ ደርሰናል። ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ለመንግስት እንዳሳሰብነው መሰረታዊ የሆኑ የለውጥ ኃሳቦችን መሬት ለማስረገጥና የተሳሳተውን የማደራጃ ትርክት፣ የተዛነፈውን መዋቅራዊና ሥርዓታዊ ማእቀፍ በማስተካከል ሕዝብን ለዘላቂ ሰላምና ሥልጣን ለማብቃት የበኩላችንን ያልተቋረጠ ጥረት ከማድረግ ጎን ለጎን በተለይ
↧