አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ሊያደርገው ለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ የመስተዳድሩ የሰላማዊ ሰልፍና ማሳወቂያ ክፍል ዘግይቶ በጻፈው ደብዳቤ የሰልፉ ቀን በሌላ ፕሮግራም መያዙን በመጥቀስ የቀን ለውጥ እንዲደረግ መጠየቁ አይዘነጋም፡፡
ፓርቲው የቀረበውን አስተያየት በመቀበል ሰልፉ ለሚያዚያ 5 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲደረግ መወሰኑን በመግለጽ ለመስተዳድሩ አሳውቋል፡፡ሆኖም መስተዳድሩ ዕለቱ በታላቁ ሩጫ መያዙን በመጥቀስ ለፖሊስ ጥበቃ ለመስጠት የሚያስቸግረው በመሆኑ ሰልፉ ለሚያዚያ 4 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲደረግ የእውቅና ደብዳቤ ጽፏል፡፡ፓርቲው በመስተዳድሩ የተሰጠውን እውቅና አለመቀበሉን ለማሳወቅ ከፍተኛ አመራሮቹን ወደ ከንቲባው ጽ/ቤት ልኳል፡፡
በአሁኑ ሰዓትም አመራሮቹና የመስተዳድሩ ሰዎች በጉዳዩ ዙሪያ እየተነጋገሩ ነው፡