ሐሙስ ጅዳ ላይ ያልቀናው ቦንድ ሽያጭ ትናንት ሪያድ ከተማም ከሽፏል።
የሁለቱም ከተሞች እቅድ መክሸፍ ምክንያት የሕወሐት ሰዎች ጉልበት የመጠቀም ስሕተት መሆኑ ያመሳስለዋል።ጅዳ ኮሚዩኒቲ አዳራሽ አቶ ከድር የሚባል የሕወሐት ሰው አንዲትን ስብሰባ የምትሳተፍ እህት በጥፊ መትቶ ሞባይሏን ለመንጠቅ ባደረገው ትንቅንቅ ስብሰባው ወደሁከት ተቀይሮ መበተኑ ይታወሳል።ሪያድ ስለሆነው ደግሞ እንከታተል ።
የትናንቱ የሪያድ ስብሰባ ለኤምባሲው ሩቅ ያልሆኑ ከየብሄሩ ሐያ ሰዎች በድምሩ አንድ መቶ ሃምሳ ሰዎች ብቻ በሚስጥር የተጠሩበት ነበር።መረጃው ለህዝብ ይፋ ከተደረገ በኋላ በርካታ ሰው ወደኮሚዩኒቲው አዳራሽ በማምራት ለመግባት ይጠይቃል።ከመግቢያ በር “የጥሪ ካርድ አምጡ” ይባላል ።”የለንም” ይላል ህዝብ።”ከየትኛው ብሔር ናችሁ?”ብለው በረኞች ሲጠይቁ “ኢትዮጵያውያን ነን።ጉዳዩ እንደዜጋ ይመለከተናል።”ይላሉ።
በዚህ ምልልስ መሐል አንድ ሰው ሞባይል ሲቀርፅ የሕወሐት አባል የሆነ ግለሰብ ይመታውና ሞባይሉን ሊነጥቀው ይሞክራል ።በር ላይ የተሰበሰበው ኢትዮጵያዊ የዚህ ሕወሐት እብሪት አበሳጭቶት ግብግብ ሲጀመር ከአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ህወሀቶች መቀመጫ ወንበር በማንሳት የአዳራሹ መስተዋት በመሰባበር ህዝቡን ለመደብደብ ወደውጭ ይወጣሉ።
የኮሚዩኒቲው ፀጥታ አስከባሪ የሳዑዲ ፖሊሶች በመሐል ገብተው ነገሮች በቁጥጥር ስር ዋለ።የችግሩን መከሰት የሰሙት አምባሳደር መሐመድ ሐሰን መጀመርያ ላይ ፀብ ያጫረውን ሰው አምጡልኝ።የኤምባሲው ሰራተኛ ቢሆን እንኳ በህግ ይከሰሳል።”አሉ።ሰውየውን ህወሀቶች አስቀድመው ቢያሸሹትም በሕዝብ ጥቆማ ያሸሸው ሰው ይያዛል።አምባሳደሩ ሰውየው ህወሐት መሆኑን ሲያውቁ አፈገፈጉ።”በቃ ጉዳዩን ጸውስጥ እንጨርሰዋለን።አሁን ወደጉዳያችን እንግባ።”ብለው በግርግሩ ያለጥሪ ከገቡት ሰዎች ጭምር ስብሰባው ተጀመረ።
ገና እንደተጀመረ አንድ ሰው ብድግ ብሎ “ሀገራችን ውስጥ በሃይማኖታችን ምክንያት ቁምስቅል የምታሳዩን አንሶ በሰው ሐገር እንዴት ትደበድቡናላችሁ?”ብሎ እምባ እየተናነቀው ተናገረ!
ከበር ላይ የህወሓት እብሪተኞች የፈፀሙት የንቀት ድርጊት ከዚህ ሰው ንግግር ታክሎ የመንግሥት ደጋፊ የሚባሉ ሰዎችን ሳይቀር አስከፍቶ እያንዳንዱ ሰው ከወንበሩ ብድግ አዳራሹን ለቆ ወጣ!
ኢትዮጵያ የግል መኝታ ቤታቸው የምትመስላቸውና በሌላው ዜጋ የሐገር ባለቤትነት የማያምኑ ጭፍን የህወሓት ግልፍተኞች የሪያድና ጅዳን የህዳሴ ግድብ የልማት ውይይት(የቦንድ ሽያጭ) በዚህ መልኩ አኮላሽተውታል!!
Ethiopians in Jeddah, Saudi Arabia protest at government Officials