Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Health: በቂ እንቅልፍ አለማግኘት የሚያስከትላቸው 6 የጤና እክሎች

$
0
0

ከአድማስ ራድዮ አትላንታ የተገኘ (በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
እንደሚታወቀው በቂ እንቅልፍ ያላገኘን ከሆነ የመነጫነጭ፣ ለስራ ተነሳሽነት ማጣት እና ድካም የመሳሰሉት ይከሰታሉ። ነገር ግን ከነዚህ ቀላል ከሚባሉ የዕለት ተዕለት ባህሪ ለውጦች በተጨማሪ የዕንቅልፍ እጦት ከፍተኛ የጤና ችግሮች እንደሚያስከትል ለማሳወቅ እወዳለው።

1. የእንቅልፍ እጦት ለከፋ የጤና ችግር ሊዳርግ ይችላል።
✔ የልብ ህመም
✔ የደም ግፊት
✔ ስትሮክ
✔ የስኳር ህመም

2. የመደበት ስሜትን ያስከትላል
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ለረጅም ጊዜ ለእንቅልፍ እጦት የሚዳረጉ ሰዎች የመደበት ስሜት ያጠቃቸዋል።

sleep disorder
3. የሰውነት ክብደት መጨመር
የእንቅልፍ ዕጦት የረሀብ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ ሆርሞኖችን በሰውነታችን እንዲመነጩ ስለሚያደርግ እና ከፍተኛ የምግብ ፍላጎት እንዲኖረን ስለሚያደርግ የሰውነት ክብደታችን እንዲጨምር ያደርጋል።

4. ቆዳችን ያለ ዕድሜ እንዲያረጅ ያደርጋል
የአይን ማበጥና መቅላት ከዚህ በተጨማሪ በዓይን አካባቢ ጥቁር የሆኑ ቀጭን መስመሮችና የቆዳ መሸብሸብ የእንቅልፍ ዕጦት ከሚያስከትላቸው በቆዳ ላይ ከሚታዩ ችግሮች ጥቂቶቹ ናቸው።

5. ውጤታማነትን ይቀንሳል
በቂ እንቅልፍ የማያገኝ ሰው ማንኛውንም ስራ ለመተግበር አቅም ስለማይኖረውና የስራ ፍላጎቱ ስለሚቀንስ በስራ ወቅት የሚፈጠሩ ስህተቶች የጎሉ ይሆናሉ። በዚህም ምክንያት ውጤታማነት በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።

6. ለአደጋዎች ያጋልጣል
እንደ አንዳንድ የጥናት ውጤቶች መረጃ የእንቅልፍ እጦት ለመንገድ ትራፊክ አደጋዎች፣ በስራ አካባቢ የሚደርሱ የማሽን አደጋዎች እና በቸልተኝነት ለሚከሰቱ የእሳት አደጋዎች ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል።

እንቅልፍ ማጣት ከሚያስከትላቸው ጉዳቶች ጥቂቶቹ የገለፅኩላችሁን ይመስላሉ፣ ስለዚህም ለአንድ ሰው በቀን ውስጥ የሚያስፈልገውን የስምንት ሰዓት እንቅልፍ መውሰድ ለጤናማ ህይወት ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ በቂ እረፍት እንድትወስዱ እመክራለው።
ለረጅም ጊዜ በእንቅልፍ እጦት የምትሰቃዩ ከሆነ ወደ ህክምና ቦታ በመሄድ ሀኪምዎን በማማከር ተገቢውን እርዳታ ማግኘት ይኖርብዎታል።


ከስትሮክ አደጋ ራስዎን የሚጠብቁባቸው 5 ምርጥ መላዎች

$
0
0

ሳይንቲስቶች  በተለያዩ  ጊዜያት ምርምሮችን ሲደርጉ ቢቆዩም በርካታ ሰዎች በተሩቅ ለሚፈሩትና በጭንቅላት ውስጥ የደም መፍሰስ ወይም ኦክስጂን አቅርቦት መቋረጥን በማጣት የህመምና ሞት እንዲሁም አካል ጉዳተኝነት ለሚዳርገው ስትሮክ ህመም ግን መቶ በመቶ ውጤታማ ህክምና ማግኘት ቀላል ሆኖ አልተገኘም፡፡ አሁን ላይ ታድያ ባለሙያዎቹ መከላከሉ ላይ እንዲሁም ስትሮክ ቢከሰት ውጤታማ ሆነው የሚቋቋሙበትን መንገድ እየተመለከቱ ይገኛሉ፡፡ በቅርቡ በወጡት አሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ካርዲዮሎጂ ጆርናል፣ በኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦፍ ሜድስን እና ስትሮክ ጆርናል እትሞች ላይ ከህይወት ዘዬ ልምዶች ላይ የሚደረጉ ለውጦች አዳዲሶቹ ከስትሮክ ጥቃት መጠበቂያ ስትራቴጂዎች ሆነው ቀርበዋል፡፡

stroke ተፈጥሯዊውን ደም ማቅጠኛ ውሃ ይውሰዱ!

        ውሃ ደምን በከፍተኛ ሁኔታ የማቅጠን ብቃት አለው፡፡ ደም በቀጠነ መጠን ደግሞ የመወፈርና የመርጋት ጠባዩ በእጅጉ ይወርዳል፡፡ ጭንቅላት ውስጥ በመርጋት የህዋሳትን ስራ የማደናቀፍ አቅሙ ይቀንሳል፡፡ የአሜሪካው ሎማሊንዳ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች በቅርቡ ባወጡት ጥናት በየእለቱ ስምንት ብርጭቆ ውሃን የጠጡ የጥናቱ ተሳታፊዎች ከሶስት ብርጭቆ ውሃ ከጠጡት በ53 በመቶ የስትሮክ ተጋላጭነታቸው ቀንሶ ተገኝቷል፡፡

የጨውን ነገር ያስቡበት!    

ጨው የደም ግፊት በመጨመሩ ይታወቃል፡፡ ከፍተኛ የደም ግፊት አለ ማለት ደግሞ በሆነ ጊዜ ስትሮክ የሚከሰትበት እድል ይጨምራል ማለት ነው፡፡ ጨውን ከምግብ ውስጥ መቀነስ በደም ግፊትና በስትሮክ የመጠቃት አጋጣሚን ይቀንሳል፡፡ ጥናቶቹ እንደሚያመለክቱት ቸውን መቆጣጠር የስትሮክ ጥቃትን የመቋቋም እድልመን እስከ 14በመቶ ይጨምራል፡፡

ከዓሣ ጋር ወዳጅነትን ይመስርቱ!

በኢትዮጵያ በአብዛኛው ዓሣ የሚበላው በፆም ወቅት በመሆኑ ከዓሳ የሩቅ ምስራቅ ሰዎች ያገኟቸውን ጥቅሞች እንዳንጋራ ምክንያት ሳይሆን አልቀረም፡፡ የስትሮክን ነገር ያጠኑ ባለሙያዎች የዓሣን ጉዳይም አብረው አጥንተዋል፡፡ በጥናታቸው መሰረት ለስትረሮክ መከላከል ዋነኛ ስልት የሆነውን የደምን መወፈርና መርጋት ለመቀነስ ተግባር ዓሣ አስተዋጽዎው ላቅ ያለ ነው፡፡ በዓሣ ውስጥ የሚገኙት ኦሜጋ3 ፋቲ አሲድ ንጥረ ነገሮች የኮሌስትሮልን መጠን ለመቀነስና ደም ጭንቅላትን ጨምሮ ወደተፈለጉት አካላት ያለእገዳ እንዲደርስ ያመቻቻሉ፡፡

እንቅስቃሴ መድኃኒት ሲሆን!

ኤሮቢክስ እንቅስቃሴ ፀረ-ስትሮክ መድኃኒት ነው፡፡ መሮጥና የሶምሶማ እርምጃ ካልሆነሎትም የክብደት እንቅስቃሴ ውስጥ ይግቡ፡፡ የትኛውም አይነት እንቅስቃሴ ቢሆን የደም ግፊትን ለመቀነስና የኮሌስትሮልን ምጣኔ በመቀነስ በስትሮክ የመጠቃትን አጋጣሚ በእጅጉ ስለሚቀንስ የሚችሉትን ያህል እንዲንቀሳቀሱ ከጥናቶቹ የተገኙት ውጤቶች ይመክራሉ፡፡

አጫሽ ዋዳጅዎ በስትሮክ ይገድልዎታል!

ሲጋራ ማጨስ ከስትሮክ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ቀድሞም ይታወቃልና ሲጋራ አያጭሱ፡፡ በአዲሱ ጥናት ግን የራስዎ ብቻ ሳይሆን በአካባቢዎ ሚጨስ ሲጋራ ጭስም ለስትረሮክ የማጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ በኦክላንድ ንቨርስቲ ተመራማሪዎች ተሰራው ጥናት እንደሚለው የሲጋራ ጭስ በቀጥታ የሚጋለጡ ሰዎች ካልተጋለጡት አንፃር ለስትሮክ ያላቸው ተጋላጭነት በ82በመቶ ከፍ ብሎ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም አለማጨስ ብቻ ሳይሆን ሲጋራ በብዛት ከሚጨስበት ቦታም ራስዎን ያርቁ ነው የባለሙዎቹ መልእክት፡፡

ከህክምና ይልቅ ቅድመ-ጥንቃቄ እና መከላከሉ አዲሱ ስትሮክ ህክምና ስትራቴጂ እንደሆነ ጥናቶቹ ዕያመለከቱ ነው፡፡ ከውቴቶቹ በመነሳት ተሰጡት ምክሮችም በልምምድ ውጤት የሚያመጡና ቀላል ስትራቴጂዎች መሆናቸውም እየተወሳ ነው፡፡ በጥቂቱ የጨለፍናቸው ስትራቴጂዎች በብዙ ቢተገበሩ ውጤታማነታቸው የበዛ ይሆናል!!

Source- http://www.mahederetena.com/amharic/archives/1860

ኢትዮጵያ ከዓለም ለምን ሁለተኛዋ ደሀ አገር ሆነች?

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

መቀመጫውን በኢትዮጵያ ያደረገ አንድ ታዋቂ የአሜሪካ የዜና አውታር በቅርቡ ኮካኮላ በኢትዮጵያ እንዳይጠጣ በሚል ያሰራጨሁትን ጽሁፍ በማስመልከት የተሰማውን ቅሬታ አስመልክቶ አንድ የኢሜይል መልዕክት ላከልኝ፡፡ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ጻፈ፣ “በድፍረት ልናገርና ሆኖም ግን ኮካኮላ እንዳይጠጣ ለማሳሰብ ስለተጻፈው ጽሁፍ ገቢራዊነት እምነት የለኝም፣ ይህንንም ጽሁፍ በማዘጋጀት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ባለው ‘ሰይጣናዊ’ ገዥ አካል እና በ’ቅዱሳኑ በተባበሩት የተቃዋሚ ኃይሎች’ መካከል ባለው የፖለቲካ ውዝግብ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ በጥቂቱ አንባቢዎችህን ሊያሳስት እንዲችል የታለመ ዓላማን ያዘለ ነው“ በማለት አስተያየቱን አጠቃሏል፡፡
ethiopian kids
ለዚህ አደናጋሪ የውጭ የዜና አውታር ቃል አቀባይ የሰጠሁት ምላሽ አጭር፣ ግልጽ፣ ፈጣን እና የማያወላዉል ነበር ፡፡ እንዲህ የሚል መልስ ሰጠሁት፣ “አዎ እውነት ነው፣ የራሰህ ጉዳይ ነው! በግልጽ ለመናገር እኔ በዚህ ጉዳይ አላዝንም፣ የገዥውን አካል ህሊና ቢስ አካሄድ በመከተል እንደ ገደል ማሚቶ ብትጮህ መብትህ ነው!!!“ በኢትዮጵያ የአንድ የጋዜጠኝነት የእውቅና እና የሙሉ ክብር ህልውና በመረጠው የቃላት አጠቃቀም እና እምነተቢስ የአዘጋገብ ዘይቤ ላይ የሚወሰን ከሆነ ድፍረት ማጣት እና አስመሳይነት እንደ እውነተኛ እና ገለልተኛ የጋዜጠኝነት ባህሪ የክብር መገለጫ ጸጋ ይሆናሉ፡፡

ይህ በድህነት ጥያቄ የቀረበው የትችት ጽሁፍ በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አካል፣ ተባባሪዎቹን፣ ደጋፊዎቹን እና የውስጥ እና የውጭ የፍልስፍናው ጠባቂ ተከራካሪዎቹን ሊያደናግር ሊያስከፋ ይችላል፡፡ እንዲህ ይሉም ይሆናል፣ “ይሄው ደግሞ የእዚህን ጭራቅ ገዥ አካል ስም ጥላሸት ለመቀባት ተነሳ፡፡ ለገዥው አካል ምክንያታዊነት ፍትህን አይሰጥም፣ እናም እስከ አሁን ድረስ ላከናወኑት ለማንኛውም ስራ በፍጹም እውቅና አይሰጥም፡፡“ “አገሪቱ ባለፉት አስርት ዓመታት አስመዘገበችው እየተባለ በየጊዜው ስለሚደሰኮርለት ተስፈንጣሪ የኢኮኖሚክ እድገት በማቀርበው የማስተባበያ አካሄድ የሆድ ቁርጠት ይይዛቸዋል፡፡“ ሁልጊዜ ሰኞ የማቀርባቸውን ትችቶቸ ለምን እንደማልረሳ እና አንድ ቀንም እንደማላሳልፍ ያላቸውን ቅሬታ ያሰማሉ፡፡

እውነታው ግን ምንም ይሁን ምን የፈለገው ነገር ይምጣ፡፡ እራሴን በሞራል ዝቅጠት ስር አለመደበቄ እና ለእራስ ጥቅም፣ ምቾት እና የሞራል ልዕልናን ባልተላበሰ መልኩ እያገለገለ ላለ ጋዜጠኛ የማላዝን በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል፡፡ ሰይጣንን አንደ መላዕክት ወደ ላይ ከፍ አድርጎ በማውጣት እና በማውረድ አላምንም፡፡ ያየሁትን እንደ አየሁት አድርጌ እናገራለሁ፡፡ ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ ለሚጠቀሙበት ለሌሎች ትክክለኛውን ንግግር ለማያቀርቡት እውነተኛ እና ቀጥተኛ የሆነውን ነገር እነገራለሁ፡፡

እንደዚሁም ሁሉ ትክክለኛ ያልሆኑ ነገሮችን ገለልተኛ በሆነ መልኩ አጋልጣለሁ፡፡ ለሰብአዊ መብቶች መጠበቅ፣ ለህግ የበላይነት መርሆዎች እና ተግባራዊነት መቶ በመቶ ገለልተኛ ነኝ፡፡ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ገለልተኛ የሆነ አስተያየቴን እሰጣለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ላይ የሚካሄዱ ነገሮችን ሁሉ በመጀመሪያ ጊዜ እንደ ህገመንግሰት የህግ ባለሙያ እና እንደ ፖለቲካ ሳይንቲስት የህገመንግስቱን መነጽር በማድረግ እመረምራቸዋለሁ፣ አገናዝባቸዋለሁም፡፡ በየጊዜው ወንዶቸም ሆኑ ሴቶች በሚያደርጓቸው አስደንጋጭ እና ሰይጣናዊ ስራዎች ሞራልን የሚመለከቱ ጉዳዮችን እመለከታለሁ፡፡ ድህነት የሁሉም ጭራቆች ሁሉ መሰረት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ለትውልድ የሚሸጋገር ጨለምተኝነትን፣ የሞራል የአካል ዝቅጠትን ትቶልን አልፏል፡፡ ሸክስፒር ጭራቃዊነትን በሚገባ በመገንዘብ በአንቶኒ በጁሊየስ ቄሳር በኩል እንዲህ በማለት ተናግሯል፣ “ሰይጣናዊ ስራ ሰሪዎቹ ሰዎች ካለፉ በኋላም ይኖራል፡፡ በጎው ነገር ከአጥንታቸው ጋር አብሮ ይቀበራል፡፡ ስለዚህ ከቄሳር ጋር ይሆናል፡፡ እንዲህ በማለትም በዚህ ላይ እጨምራለሁ፣ “ጭራቃዊነት በድል አድራጊነት ተንሰራፍቶ እንዲኖር የሚፈቅድለት ብቸኛው መንገድ ደጋግ ወንዶች እና ሴቶች ምንም ነገር አለማድረጋቸው እና አለመናገራቸው ነው፡፡ ስለሆነም ስለድህነት-ከድህነት ስለሚያተረርፉት እና ስለሚሰብኩት ሁሉ ድህነት በኢትዮጵያ ስላለው የሁሉም ጭራቃዊነቶች መሆኑን መናገር አለብኝ፡፡“

ኢትዮጵያ ከዓለም ከመጨረሻዎቹ ደሀ አገሮች ሁለተኛ እንድትሆን ያደረገ ሽንጡን ገትሮ የሚሰራ ጭራቃዊ ኃይል

ባለፈው ሳምንት የኦክስፎርድ የድህነት እና የሰብአዊ ልማት ተነሳሽነት ኦክስፎርድ/Human Development Initiative (OPHD) ዘርፈብዙ የድህነት መለኪያ (በቀድሞ ስሙ U.N.D.P Human Poverty Index) ለአራት ተከታታይ ዓመታት ባቀረበው ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ ከዓለም በድህነት ሁለተኛዋ አገር ሆናለች፡፡ ለዓመታት ሌሎች በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ደግሞ ከታች በድህነት አራንቋ ከተዘፈቁት አምስት የመጨረሻ አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ በድህነት ተተብትባ መያዟ ብቻ ሳይሆን በሰብአዊ መብት አያያዝ እና በሌሎች መለኪያዎችም ዝቅተኛውን ደረጃ ይዛ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 OPHD ባቀረበው ዘገባ መሰረት “በአስከፊ ድህነት“ ውስጥ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት (በቀን ከአንድ ዶላር በታች ገቢ የሚያገኘው) 72.3 በመቶ ይሸፍን ነበር፡፡ ሆኖም ግን የ2014 የOPHD አሀዛዊ መረጃ ከዚህ የበለጠ አስደንጋጭ ነው፡፡ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖረው 82 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በከተማ ከሚኖረው ከ18 በመቶው ህዝብ ጋር ሲነጻጻር የገጠሩ ህዝብ የበለጠ “በአስከፊ የድህነት“ ቀለበት ውስጥ ተተብትቦ ይገኛል፡፡ በ2014 በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ በአስከፊ ድህነት ውስጥ ከሚገኘው ህዝብ ውስጥ አብዛኛው በሚከተሉት ክልሎች ይገኛል፡ ሶማሊ (93%)፣ ኦሮሚያ (91.2%)፣ አፋር (90.9%)፣ አማራ (90.1%)፣ እና ትግራይ (85.4%):: በOPHD የመለኪያ መስፈርት ውስጥ ድህነት ማለት በቀላል አገላለጽ የገንዘብ እጥረት ብቻ ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ከዚህ በተለየ መልኩ አስከፊ የጤና፣ ትምህርት፣ ስነምግብ፣ የህጻናት ሞት እና ብልሹ የውኃ፣ የኤሌክትሪክ፣ የቤት እና የመጸዳጃ ቤት አቅርቦትም በጣም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በመጥፎ የድህነት ገጽታ ውስጥ ነው ያለችው፡፡ ለዚህም ነው ከዓለም አገሮች በድህነት ከመጨረሻዎቹ በሁለተኛነት ደረጃ ላይ ተሰልፋ የምትገኘው!

በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ኢትዮጵያን በስልጣኔ ከፍ ወዳለ ደረጃ በማድረስ የተሀድሶ መሪ በመሆን ኢትዮጵያን ወደ ተምኔታዊ ኢትዮጵያ ለማሸጋገር ሌት ከቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል እየሰራ እንደሚገኝ ሁልጊዜ በብቸኝነት በያዛቸው የመገነኛ ዘዴዎች ይደሰኩራል፡፡ የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በመለስ የቀብር ስነስርዓት ላይ በመገኘት እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው ነበር፣ “ታላቁ መሪያችን አቶ መለስ ዜናዊ ላለፉት ስምንት ዓመታት ከሁለት አሃዝ በላይ እያስመዘገበ ላለው ኢኮኖሚያችን የሀገራችን ህዳሴ ቀያሽ መሀንዲስ ነበሩ“ በማለት ኩራትን በተላበሰ መልኩ ተናግረው ነበር፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አቶ ኃይለማርያም የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዘገባ ባቀረቡበት ወቅት እንዲህ የሚል በኩራት የታጀበ ንግግር አሰምተው ነበር፣ “እያንዳንዱ ሰው ስለኢትዮጵያ ተሀድሶ ነው የሚያወራው“ (ይቀልዳል!?)

የወባ ትንኝ ተመራማሪው እና በብርሀን ፍጥነት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተሸጋገረው እና በ2015 የይስሙላ ምርጫ ከአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በመረከብ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን የሚረከበው ቴዎድሮስ አድኃኖም ባለፈው መስከረም ወደ ኒዮርክ በመሄድ ስለኢትዮጵያ እና አፍሪካ ስኬት ገለጻ አድርጓል፡፡ እንዲህም ብሎ ነበር፣ “ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ እና በፖለቲካው መስክ… ከበቂ በላይ ገስግሳለች:: በኢኮኖሚ እድገት ኢትዮጵያ ባለፉት አስር ዓመታት ከ10 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች…ኢትዮጵያ በእድገት ግስጋሴ ላይ ነች…”

ኢትዮጵያ “በህዳሴ እና በእድገት ግስጋሴ” ላይ ከሆነች በምን ዓይነት መለኪያ ነው ኢትዮጵያ ከዓለም/ፕላኔት በድህነት ከመጨረሻዎቹ አገሮች በሁለተኛነት ደረጃ ላይ የምትገኘው? ለምንድንስ ነው ኢትዮጵያ በህዳሴ እና በእድገት ግስጋሴ በመዝለቅ እራሷን ከድህነት ለማላቀቅ ያልቻለችው? ለምንድን ነው እ.ኤ.አ በ2014 82 በመቶ የሚሆነው በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖረው ህዝብ “በአስከፊ የድህነት” ባህር ውስጥ በመዋኘት ላይ የሚገኘው? በኢትዮጵያ ከ90 ወይም ከዚያ በላይ ከሚሆነው ህዝብ ውስጥ ወደ 60 በመቶ የሚሆነው ዜጋ ለምንድን ነው በቀን ከ1.25 ዶላር በታች የቀን ገቢ የሚያገኘው? ለምንድን ነው ወደ 60 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በአስከፊ የምግብ ወይም በየጊዜው በሚከሰት ለምግብ ዋስትና እጦት የሚዳረገው?

እውነታው ግን ድህነት፣ በሽታ፣ ድንቁርና፣ ሙስና እና የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ብቻ ናቸው በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀቡ በመሄድ ላይ ያሉት፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለ ህዳሴ የሚኖር ካለ የሙስና ተሀድሶ ነው፣ አለ የሚባል ተሀድሶ ካለ የሰብአዊ መብቶች እጦቶች እና ጥሰቶች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ “በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች እድገት እና እመርታ” ማሳየት ሳይሆን እንዲያውም በአስደንጋጭ ሁኔታ ወደ ኋላ ተስፈንጥራ እየሄደች ነው፡፡ ሆኖም ግን በገዥው አካል “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” እና “ልማታዊ መንግስት” (በተሻለ መልኩ ክህደታዊነት እየተባለ በሚጠራው) የገደል ማሚቶ ሰበካ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ እና አጥጋቢ ነው፡፡ ከዚህ በተለየ መልኩ የሚያስብ እና የሚንቀሳቀስ እንዲሁም ስህተት ነው ብሎ የሚሞግት ከተገኘ ያ ግለሰብ የተሳሳተ ወይም ስንኩል እና ጤንነት የጎደለው አስተሳሰብ ነው ተብሎ ይፈረጃል፡፡

ሊሆን በማይችለው ከነባራዊ እውነታው ውጭ በሆነ ነገር ላይ እምነታቸውን የሚጥሉት የገዥው አካል አባላት ማስተባበል በማይቻል መልኩ በተዘጋጀ ማስረጃ የቀረበውን ሰው ሰራሽ የሆነውን ዓለም አቀፋዊ የአየር ንብረት የሙቀት መጠን እንደሚክዱት ዓይነት ቡድኖች እና ግለሰቦች ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በሀገሪቱ ያለውን አስከፊ ድህነት ሙጥጥ አድርጎ በመካድ በዚህች አገር ለሚከሰተው ረሀብ በብቸኝነት ተጠያቂው እራሱ መሆኑን በመዘንጋት ተቃውሞውን ያሰማል፡፡ ይልቁንም ምናባዊ በሆነ መልኩ እራሳቸው ስለፈጠሩት ምናባዊ ህዳሴ ደጋግመው ይደሰኩራሉ!

እዉነታዎች በእራሳቸው ይናገራሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ/Global Financial Integrity የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “የኢትዮጵያ ህዝቦች ደማቸው ተመጧል፣ ፍጹም ከሆነ እጦት እና ድህነት ለመውጣት የቱንም ያህል ጥረት ቢያደርጉም እንኳ በአሁኑ ጊዜ እየተደረገ ባለው የህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ባህር ውስጥ አገሪቱ ወደ ላይ በመስመጥ ላይ ትገኛለች“፡፡

እንደ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ ዘገባ “ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢዋ 365 የኤሜሪካ ዶላር የሆነችው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ2000 እስከ 2009 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 11.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በህግወጥ የገንዘብ ዝውውር ከሀገር ውስጥ ወጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩ 3.26 የአሜሪካ ዶላር በመሆን ካለፉት ሁለት ዓመታት በእጥፍ ጨምሮ ታይቷል… እ.ኤ.አ በ2008 ኢትዮጵያ ከውጭ የተገኘ 829 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን ይህም በህገወጥ የገንዘብ ዝውወር ምክንያት ባክኖ ቀርቷል፡፡“ የኢትዮጵያ የካፒታል ፍሰት ሁኔታ ሲታይ በግምት 3.26 የአሜሪካን ዶላር በአመዛኙ እ.ኤ.አ በ2009 ከተገኘው 2 ቢሊዮን የኤክሰፖርት ምርት ዋጋ በእጅጉ የበለጠ ነው፡፡

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2014 ከዓለም 2ኛዋ ደኃ አገር ለምን ሆነች?

በኢትዮጵያ ሰይጣናዊው ረሀብ ድልን ሊቀዳጅ የቻለበት ዋናው ምክንያት በገዥው አካል የእውቀት ማጣት፣ የችሎታ ማነስ፣ ድንቁርና፣ እብሪ እና ሙሰኝነት እንዲሁም አሁን በህይወት በሌለው በመለስ ዜናዊ ዋና መሀንዲስነት የአምባገነንነት ባህሪ ምክንያት ነው፡፡ መለስ ከሁሉም በላይ እራሱን እንደ የኢኮኖሚ ባለሙያ አድርጎ ይቆጥር ነበር፡፡ መለስ ግማሽ ብስል በነበረው የማርኪሲዝም የፖለቲካል ኢኮኖሚ በማመን ገና በወጣትነት እድሜው ወደ ጫካ በመግባት እራሱን በኢትዮጵያ “የአብዮታዊ ዴሞክራሲ” እና “የልማታዊ መንግስት” “ዋና መሀንዲስ” አድርጎ ሰየመ፡፡ ሆኖም ግን መለስም ሆነ የእርሱ አሻንጉሊት ተከታዮች የአብዮታዊ ዴሞክራሲ እና የልማታዊ መንግስት ህልዮትን እና ገቢራዊ አልሆኑም፡፡ ይልቁንም የልመና እጃቸዉን ለዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ለዓለም ባንክ እየዘረጉ በሌላ በኩል ደግሞ “ኒዮሊበራልን” ለማውገዝ እና ለመርገም ድምጻቸዉን ከፍ አድርገው ይጮሃሉ፡፡ በአንድ ምሁራዊ የትችት መጽሄት ላይ የጸረ ኒዮሊቨራል አቀንቃኝ በሆነው በጆሴፍ ሰትልጊዝ እርማት መሰረት አቶ መለስ እንዲህ ብሎ ነበር፣ ”የኒዮሊቨራል አካሄድ የአፍሪካን ህዳሴ ያላመጣ የሞተ ነገር ነው፣ እናም የአፍሪካን ዓላማ ለማሳካት እና አፍሪካን ወደ ዘላቂ የሆነ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡“

የመለስ መሰረታዊ ለውጥ የይስሙላ ዓላማ በአሁኑ ጊዜ እንደተረሳችው ራሽያ ማዕከላዊ የሆነ የአምስት ዓመት የኢኮኖሚ ዕቅድ ሳይሆን እንደ የእድገት እና ትራንስፎረሜሽን ዕቅድ ያለ ምዕናበዊ ዕቅድ ነው፡፡ ቀደም ሲል በተለያዩ አጋጣሚዎች እንዳየሁት ሁሉ መለስ የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የለውም፣ ይልቁንም ያለው ምዕናባዊ ሀሳባዊ የኢኮኖሚ እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ነው፡፡

የመለስ ዜናዊ የዉሸት ምጣኔ ሀብት ዘየቤ (The Fakeonomics of Meles Zenawi) በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት እንዲህ በማለት ለማሳየት ሞክሬ ነበር፣ “የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ባዶ ሊስት ከመመዝገብ የበለጠ አይደለም፡፡“ ይህ ዕቅድ በረዥሙ ጉዞ ኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ህግ፣ መልካም አስተዳደር እና ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍኑ ለማድረግ ነበር፡፡ ዘመናዊ እና ምርታማ የሆነ የግብርና ዘርፍ ከተሟላ ቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲሁም የዜጎች ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ ለማሳደግ እና የመካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ጋር እኩል ለማድረግ የታለመ ነበር፡፡ ገዥው አካል የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማሳካት ፈጣን እና ዘላቂ እንዲሁም ፍትሀዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት ምሰሶ ስልቶችን በመጠቀም ግብርናን እንደ ዋና የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሞተር በማድረግ ለኢንዱስትሪው መዳበር ጥሩ ከባቢ አየርን ይፈጥራል በማለት ጉራ ያደርጋል፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን የመሰረተ ልማት እና የማህበራዊ ልማትን ማስፋፋት፣ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማካሄድ እና መልካም አስተዳደርን ማስፈን እንዲሁም ሴቶችን እና ወጣቶችን ማጠናከር እና የጋራ ተጠቃሚነትን ማጎልበት በሚል ሀሳብ ይመራል፡፡

በባዶ የኢኮኖሚ እድገት መፈክር ታጅቦ፣ በተደጋጋሚ እየተነገረ ባለ አሰልቺ አገላለጽ ታጅሎ፣ ፋሽንነትን በተላበሱ ቃላት እየተሽሞነሞነ እና በአንድ ታዋቂ ሰው ዲስኩር እየተምነሸነሸ የመለስ የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አደናጋሪና እና ከነባራዊ እውነታው ውጭ ሆኖ ቀርቷል፡፡

ከዚህ ቀደም “የመለስ ምዕናባዊ ኢኮኖሚከስ“ (The Voddo Economics of Meles Zenawi) በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት መለስ ግልጽ በሆነ መልኩ በፍብረካ ላይ በተመሰረተ ስታቲስቲካዊ አሀዝ በመጠቀም በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚክ እድገት ተመዝግቧል ይለው የነበረውን ተራ ማደናገሪያ የሆነ ውሸት በማጋለጥ አቅርቤ ነበር፡፡ ለበርካታ ዓመታት መለስ እና የእርሱ ገዥ አካል የማተለያ የህዝብ ግንኙነትን በመፍጠር እና በማታለል የዓለም የገንዘብ ድርጅትን ከፊት በማድረግ የእርሱን የሸፍጥ የኢኮኖሚ እድገት ዓለም አቀፉን ድርጅት ባስረጅነት ድጋፍ እንዲያደርግ አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ እድገት እንዳስመዘገበች እና ውጤታማ እንደሆነች አድርገው የዓለምን ህዝብ በማደናገር ላይ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አካል የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እውቀት አናሳነት፣ የብቃት የለሽ እና በሙስና ስርዓት በመዘርጋት የሀገሪቱን ሀብት እጠቀራመተ ያለ መሆኑን በማጋለጡ እረገድ እኔ የመጀመሪያው አይደለሁም፡፡ እ.ኤ.አ በሴፕቴምበር 7/2006 እትሙ የኢኮኖሚክ መጽሄቱ/Economic Magazine “የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ስልጣኔ በተስፋፋበት ዘመን አንዱ የኢኮኖሚክስ ማይም“ በማለት የሁኔታውን አሳሳቢነት ገልጾት ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ኖቬምበር 3/2007 የኢኮኖሚስት መጽሄት/the Economist Magazine እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “እውነታው ተግልጦ ሲታይ በእርዳታ የሚገኝ ገንዘብ እና ከቻይና የሚመጣ ብድር ቢኖርም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፍጥነት ማደግም ሆነ በቂ የስራ እድል መፍጠር አልቻለም፡፡ የአበባ ምርት እየተባለ ብዙ በሚወራለት አዲስ የኢኮኖሚ ዘርፍ የተፈጠሩት አዲስ የስራ መስኮች በየዓመቱ በ2 ሚሊዮን እጨመረ ከመጣው የህዝብ እድገት በአፍሪካ ፈጣኑ የህዝብ እድገት ከመሆኑ አንጻር ሲታይ ብዙም አይደሉም… ገዥው አካል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከ2003-2004 በሚያስደምም ሁኔታ 10 በመቶ እድገት አሳይቶ ነበር፡፡ ሆኖም ግን እውነተኛው እና ትክክለኛው የእድገት አሀዝ ከ5-6 በመቶ ማለትም ከሰሀራ በታች ካሉ አገሮች አማካይ የእድገት ምጣኔ በላይ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ እናም ያ መጠነኛ የተሻሻለ የእድገት ምጣኔ ለምሳሌም በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ባሉ ጥቂት ህንጻዎች ሰበብ ኢኮኖሚው ከመጠን በላይ እየጋለ ሄዶ መንግስት በዚያው ዓመት እርምጃ ከመውሰዱ በፊት የዋጋ ንረቱ 19 በመቶ ደርሶ ነበር፡፡ ኢኮኖሚው ለምን በእንደዚህ ያለ ሁኔታ እየዳኸ እንደሚሄድ ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ነው፡፡ በአብዛኛው በውጭ እርዳታ የተንጠለጠለ ሆኖ ከመንግስት ትእዛዘዝ ውጭ – ለአፍሪካ ብቻ ልዩ የሆነ በእርግጠኝነት በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ የንግድ ማህበረሰብ የለም፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 ከፍተኛ የሆኑ የምእራቡ ዓለም ለጋሽ ድርጅቶች እና ፖሊሲ አውጭዎች በበርሊን ከተማ ባካሄዱት ጉባኤ አንድ የጀርመን ዲፕሎማት በመለስ ደካማ የኢኮኖሚክስ አረዳድ መሰረት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር በውል ሊታወቅ እና ሊደረስበት አይችልም“ ብለው ነበር፡፡

ጥቂቶችን ብቻ የማበልጸግ አባዜ የተጠናወተው የኢትዮጵያ ድህነት ገፊ ምክንያት፣

በኢትዮጵያ ለድህነት መሰረታዊ ምክንያቱ “ኒዮሊበራሊዝም” አይደለም፡፡ ይልቁንም ዋናው የድህነት መሰረቱ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ቀያሽ መሀንዲሶች እና በኢትዮጵያ ልማታዊ መንግስት እየተባለ ኢኮኖሚውን በብቸኝነት ይዘው ጥቂቶችን በማበልጸግ ሰፊውን ህዝብ የበይ ተመልካች የማድረግ አባዜ ነው፡፡ ጥቂቶችን የማበልጸግ ስስታዊ አካሄድ የኢኮኖሚ ተግባራትን እና የውጤታማነት መስፈርትን በማየት ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ በፖለቲካ ትስስር የሚከናወን የጥቂቶች የመዝረፊያ አካሄድ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ በሀገሪቱ የአንበሳውን ድርሻ ለማግኘት ማንም ሰው ቢሆን በፖለቲካ እና በጎሳ ትስስር እና መስተጋብር አንድ በመሆን የኢኮኖሚ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ በኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ሙያዊ የቃላት ድርደራ መሰረት እንደዚህ ያለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ “ኪራይ ሰብሳቢነት“ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የግል ወይም የቡድን ግምገማዎች ለግብር ጉዳይ መንግስትን መለማመጥ፣ የወጭ እና የቁጥጥር ፖሊሲዎችን በመንደፍ የገንዘብ ጥቅሞችን ወይም ደግሞ በሌሎች ግብር ከፋዮች ጉዳት ሌሎች ልዩ ጥቅሞችን የማግኘት ወይም ደግሞ የተጠቃሚዎች ወይም ሌሎች ቡድኖች ወይም ግለሰቦች ጋር ውድድር እንዲያደርጉ ይገዳዳሉ፡፡

የመለስ ጥቂቶችን ብቻ የማበልጸግ አባዜ የመለስ ደጋፊ እና የእርሱ ህወሀት ፓርቲ ሎሌዎች (የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር/ኢህአዴግ የጋራ መደጋገፍ ስርዓት በመዘርጋት የተለያዩ ጥቅሞችን የማሳደድ እንዲሁም ለእነርሱ የሚመች ከባቢያዊ ሁኔታ የመፍጠር እና የህዝብ ግዥ ሲፈጸም እና በመሳሰሉት ሁሉ ለጥቅመኛው ቡድን ተጠቃሚ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ የውስጦቹ በውጮቹ ጉዳት መሰረት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ እናም እየንዳንዱ ለገንዘቡ ሲል ሎሌ ይሆናል፡፡ የኢንተርፕሪነር/ስራ ፈጣሪ ግለሰቦች እንኳ ለመኖር ሲሉ ለአዳኙ ግለሰብ/ቡድን ሎሌ መሆን ይፈልጋሉ፡፡

በመለስ ጥቂቶችን የማበልጸግ መርህ መሰረት መንግስት ኢኮኖሚውን በብቸኝነት ተቆጣጥሮ ለእርሱ ደጋፊዎች እና ሎሌዎች ትርፋማ የሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ይይዛል፡፡ የመለስ ገዥ አካል በቁጥጥር፣ በግብር፣ በጠቅላላ ለወጭ እና ለኢኮኖሚያዊ ተግባራት እንቅስቃሴ በበላይነት ይዞ ይመራል፡፡ ታማኞቻቸውን እና ሎሌዎቻቸውን ለመጥቀም ሲሉ በልጓም የማይታዘዝ ስልጣን አላቸው፡፡ በውጤቱም ኢኮኖሚያዊው እንቅስቃሴ፣ የኢንተርፕሪነር ህልውና እና ሌሎችም የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠረው ኃይል የሚወሰን ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው የሀብት ፈጠራ እና ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግበን እያሉ ህዝቡን ጧት ማታ የሚያሰለቹት፡፡

በመለስ ጥቂቶችን የማበልጸግ ስራ በጣም ጥቂት የሚባሉ ነጻ የስራ ፈጣሪዎች ተሳክቶላቸዋል፡፡ ጥቂቶቹ የተሳካላቸውም ቢሆኑ በእርግጠኝነት በመለስ ሎሌዎች ተውጠው ይቀራሉ፡፡ የኢኮኖሚ ስኬታማነት በአመዛኙ የሚወሰነው በፖለቲካ እንቅስቃሴው እና ገዥውን አካል ከመደገፍ አንጻር ባለው አቋም ነው፡፡ ነጻ የሆኑ የስራ ፈጣሪዎች ህልውናቸው ተጠብቆ እንዲቆይ ከተፈለገ ድርጊቱን ቢጠሉትም እንኳ ጥቂቶችን በማበልጸግ ስራ ላይ መሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡ የመለስ ገዥ አካል የቁጥጥር ኃሉን፣ የግብር ስብሳቢ ባለስልጣኑን፣ እና ወጭዎችን እና ድጎማዎችን ለሚደግፉት ሲሰጥ በተቃራኒው ላሉት ግን አይሰጥም፡፡ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ሁሉም ስራ ፈጣሪዎች የመንግስትን ልዩ አያያዝ ለማግኘት ሲባል እና እራሳቸውን ከህጎች፣ ወጭዎች እና እነርሱን ከውድድር ጉዳት ለሚከላከሉ ነገሮች አበርትተው ይሰራሉ፡፡

በመለስ ገዥ አካል ጥቂቶችን የማበልጸግ ስርዓት ውድድር የሌለበት እና በግልጽ ለተወሰነ ቡድን ተብሎ የተቀመጠ ነው፡፡ የሰብአዊ መብተ ቡድኖች፣ ተንታኞች እና ትችት እቅራቢዎች የመለስ ገዥው አካል በእርዳታ ስም ለህዝብ እንዲደርስ የሚላከውን እርዳታ ማለትም ምግብን፣ ማዳበሪያን፣ ስልጠናን፣ ወዘተ ጨምሮ ለፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ ለሚታወቁ ተቃዋሚ ቡድኖች አብዛኛውን ጊዜ እንደሚከለክል ዘገባ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ በማወጣቸው ሳምንታዊ ትችቶቸ ላይ ሳቀርብ ቆይቻለሁ፡፡ እንደ ዓለም ባንክ ዘገባ የኢትዮጵያ ግማሽ አካባቢ የሚሆነው ብሄራዊ ኢኮኖሚ የተያዘው ለስርዓቱ ደጋፊ በሆኑ የንግድ ቡድኖች ማለትም በትግራይ ህዝብ መልሶ ማቋቋሚያፈንድ/Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT) በሚባሉ መንግስታዊ በሆኑ የንግድ ድርጅቶች ነው፡፡ የኢፈርት የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት፣ ኮንስትራክሽን፣ የመድሀኒት፣ እና የስሚንቶ የንግድ ተቋሞች ትርፋማ የሆኑ የውጭ የእርዳታ ስምምነቶችን እና ከመንግስት ባንኮች የብድር አገልግሎት ያለምንም ውጣውረድ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 በተሟላ መልኩ በሳራህ ቫውግሀን እና መስፍን ገብረሚካኤል አማካይነት “Rethiniking business and politics in Ethiopia: The role of EFFORT, the Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ዘገባ ገዥው አካል ከንግድ ድርጅቶች ጋር ቅርብ እና የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው ከበቂ በላይ ማስረጃ እና ትንታኔ ይሰጣል፡፡ የዓለም ባንክ በ2012 “Diagnosing Corruption in Ethiopia“ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ሰፊ ዘገባ እና በዚያ ዘገባ ውጤት ላይ እኔ እራሴ በመለየት በሰጠሁት ትችት ጥቂቶችን የማበልጸግ ወያኒያዊ ተውኔት ምን ያህል በፍትሀዊነት ላይ ድልን እንደተቀዳጀ የሚያሳይ እኩይ ኢመንግሰታዊ ምግባር መሆኑን መግለጼ የሚታወስ ነው፡፡(እነዚህ ትችቶች Al Mariam Commentaries በሚል የእራሴ ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ፡፡) በኢትዮጵያ ጥቂቶችን ማበልጸግ የሚለው ወያኒያዊ መርህ ምናልባትም በማዕድኑ ዘርፍ በይበልጥ ጎልቶ ይታያል፡፡ የዓለም ባንክ ጥናት የመለስን ጥቂቶችን የማበልጸግ መርህ በግልጽ አሳይቷል፡፡

የማዕድን ኩባንያ የማዕድን ፈቃድ ለማግኘት ብዙ ፕሪሚየም/ከተገቢው በላይ እንዲከፍል ይጠየቃል፡፡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች እና የማዕድን ኩባንያው ይህንን ክፍያ በሚስጥር እንዲያዝ ሊያደርጉ ይችላሉ፣ በቀጣይነትም ከአገር ውጭ ባሉ የባንክ ሂሳቦቻቸው ገንዘብ ገቢ እንዲያደርጉላቸው ያደርጋሉ፡፡

አንድ የማዕድን ኩባንያ የማዕድን ፈቃዱን በአስቸኳይ ለማግኘት የሚፈልግ ከሆነ ለበጎ ነገር እርዳታ በሚል ብዙ ገንዘብ እንዲሰጥ በመንግስት ባለስልጣኑ ሊጠየቅ ይችላል፡፡ የበጎ ነገር እርዳታው ለመልካም ነገር የታሰበ ቢሆንም ይህ ገንዘብ በትክክል ለፖለቲካ ፓርቲው ወይም ለባለስልጣኑ የግል ወይም ደግሞ ለቤተሰቡ መጠቀሚያ እንዲውል ሊደረግ ይችላል፡፡

ባለስልጣኖች ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ከማዕድን ኩባንያው ጋር በመስማማት የተወሰነ ኮንትራት ለዘመዶቻቸው እንዲሰጥ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ የማዕድን ፈቃዱን የሚሰጠው ባለስልጣን ለማህበራዊ ልማት ዕቅድ በሚል ከሚጠየቀው ትክክለኛው የገንዘብ መጠን በተጨማሪ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ኩባንያው በእራሱ ወጭ እንዲሰራ ሊጠየቅ ይችላል፡፡

የማዕድን ኩባንያው የማዕድን ፈቃድ ለመውሰድ ሲፈልግ የአካባቢ ስነምህዳር አያያዝ ዕቅድ እንዲያቀርብ ሊጠየቅ ይችላል፡፡ ይህም ጎጂ የሆኑ መርዛማ ኬሚካሎች ወደ ውኃ አካላት በመግባት ብክለትን እንዳያስከትሉ በሚል ምክንያት ነው፡፡ ትክክለኛ ቁጥጥር ከፍተኛ የሆነ ወጭን የሚጠይቅ ተግባር ነው፡፡ የማዕድን ኩባንያው የማዕድን ፈቃዱን ለማግኘት ሲል የሚፈጠሩ ድክመቶችን ለመሸፈን በሚል ተጨማሪ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍል እንዳይጠየቅ ፈቃዱን ለሚያጸድቀው ባለስልጣን ጉቦ ሊሰጥ ይችላል፡፡

ባለስጣኖች ከማዕድን ኩባንያው ትርፍ ድርሻ/share ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ የማዕድን ኩባንያ ከጥቅም ጋር በተያያዘ መልኩ ከማዕድን ትርፍ ለባለስልጣን ዘመድ ነጻ ድርሻ/share ሊሰጥ ይችላል፡፡

ባለስልጣኖች በድብቅ በእራሳቸው በተያዙት ኩባንያዎች የማዕድን ፈቃድ ይሰጣሉ፡፡

ባለስልጣኖች የፈቃድ ማመልከቻ የቀረበበትን መሬት በድብቅ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

ባለስልጣን የማዕድን ስራው ይካሄድበታል ብሎ የሚያስበውን መሬት አስቀድሞ የማዕድን ፈቃዱ ከመሰጠቱ በፊት ሊያከራየው ይችላል፡፡ አንዴ ፈቃዱ ከተሰጠ የመሬቱ ጥሬ ዋጋ ሊጨምር ይችላል፡፡ ባለስልጣኑ ከውስጥ ባለው እውቀት መሰረት በመሸጥ ወይም ደግሞ ፈቃዱን በማከራየት ከኩባንያው ትርፍ ሊያገኝ ይችላል፡፡

ባለስልጣኖች የፈቃድ ምዝገባን ሊያዛቡ ይችላሉ፡፡

የማዕድን ፈቃድ መስጠት የሚችል በመምሪያ ደረጃ ያለ ባለስልጣን የማዕድን ኩባንያ የማዕድን ፈቃድ ለመጠየቅ የሚፈልግ መሆኑን ሊያውቅ ይችላል፡፡ ከዚህ አንጻር ባለስልጣኑ መረጃውን በመገንዘብ ሌላ ከዚህ ስራ ጋር ግንኙነት ያለውን ሰው አስቀድሞ እንዲያውቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በዚህም መሰረት የንግድ ሰው በዚያው በአንድ ዓይነቱ መሬት ላይ ሊያመለክት ይችላል፡፡ ባለስልጣኑ ይህንን መሬት ለዚህ የንግድ ሰው ሊሰጠው ይችላል፡፡ ከዚያም የማዕድን ኩባንያው ይህንን ቀደም ሲል እራሱ እንዲሰጠው አመልክቶ የነበረበትን መሬት ከንግዱ ሰው እንዲገዛው ይደረግ እና የንግዱ ሰው ትርፉን ከባለስልጣኑ ጋር ይካፈላል፡፡

አንድ ማዕድን ፈላጊ ማዕድን ሊያገኝ ይችላል፣ ያገኘበትን አካባቢም ምልክት ሊያደርግበት ይችላል፡፡ በዚህም መሰረት የግኝት ሰርቲፊኬት እንዲሰጠው ጉዳዩን ለሚመለከተው የፈቃድ ሰጭ ባለስልጣን ሊያመለክት ይችላል፡፡ ሙስና የሚያካሂድ ባለስልጣን ግኝቱን ባገኘው ሰው ስም ላይመዘግበው ይችላል፣ ከዚህ ይልቅ የቢዝነስ ጓደኛውን እንዲያውቅ በማድረግ በጓደኛው ስም እንዲመዘገብ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ሙሰኛው ባለስልጣን ከዚህ በኋላ ማዕድኑ በመጀመሪያ የተገኘው በሌላው ሰው እንደሆነ ይነግረዋል፡፡

ኮንትራክተሮች እና አምራቾች በጨረታ፣ የባለቤትነት ጥያቄን በማቅረብ እና እንከን ያለባቸውን ስራዎች በመደበቅ ወይም በማጽደቅ ተግባር ላይ ሊሰማሩ ይችላሉ፡፡

የማዕድን ኩባንያዎች ስለ ማዕድናት ምንነት እና ጥራት የሀሰት መግለጫዎችን በመስጠት ወይም ደግሞ ፈቃድን ለሚያጸድቁት ኃላፊዎች ጉቦ በመስጠት የሙስና ወንጀል ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡

ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛዋ ደኃ አገር ከሆነችበት የውርደት ቦታ የምትላቀቀው መቸ ነው?

ከፖለቲካ ትስስር ጋር የተያያዙ ስራዎች ከስራ ፈጠራ ችሎታ እና ከተነሳሽነት የበለጠ ትኩረት እስከተሰጣቸው ድረስ ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛዋ ደኃ አገር ሆና ትቀጥላለች፡፡

በቁጥር ጥቂት የሆኑ ከላይ የተቀመጡ የተማሩ ዜጎች በህግ ስርዓቱ የተለየ ድጋፍ የሚደረግላቸው እስከሆነ ድረስ እና በጎሳ ዝርያቸው ምክንያት እና በጣም ምርታማ በሆነው የምጣኔ ሀብት ዘርፍ እየተሰማሩ እንዲበለጽጉ በማድረግ የመጀመሪያ ደረጃ ዜግነት እስከተሰጣቸው ድረስ ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛዋ ደኃ አገር ሆና ትቀጥላለች፡፡

ግለሰቦች እና ቡድኖች በስራ፣ በላብ እና በድካማቸው ከሚያገኙት አንጡራ ሀብታቸው ውጭ በፖለቲካ ትስስር ብቻ ያለፉበትን እና የላባቸው ዋጋ ያልሆነውን የሌሎችን ዜጎች አንጡራ ሀብት መዝረፍ እስካላቆሙ ድረስ ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛዋ ደኃ አገር ሆና ትቀጥላለች፡፡

ይህ ሰው አዳኝ መንግስት ደካማ እና ንጹሀን ዜጎችን እያሳደደ አቅማቸውን እያዳከመ ማደኑን እና የስራ ፈጠራ ክህሎታቸውን በማጥፋት እረፍትየለሾቹን ወጣቶች እንዳይሰሩ እና ለሀገሪቱ ዘለቄታዊ ለውጥ እንዲያመጡ እስካላደረገ ድረስ ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛዋ ደኃ አገር ሆና ትቀጥላለች፡፡

ድህነት በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍተው ለሚገኙ ጭራቆች ሁሉ ዋና መሰረት ነው፡፡ ሆኖም ግን ማን (ምንድን) ነው በኢትዮጵያ ውስጥ የድህነት መሰረቱ?

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሰኔ 27ቀን 2006 ዓ.ም

ከልባቸው ደፋር የሆኑ የሀገሬን ልጆች ማየት በመጀመሬ ደስ አለኝ –ኤሊያስ ገብሩ

$
0
0
elias Gebru

ኤሊያስ ገብሩ

ፍኖተ ነፃነት
ኤሊያስ ገብሩ

የሰሞኑ የኢትዮጵያችን ሁኔታ ሀዘን፣ ቁጣ፣ ንዴት፣ እልህ፣ ብሎም የደስታ ስሜትን የቀላቀለ ነበር፡፡ የእሰሩ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ ዛሬ እንኳን ከአንድነት ፓርቲ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ የሺዋስ አሰፋ መታሰራቸውን ሰምተናል፣ አውቀናል፡፡ የዚህ መሰል አካሄድ ግን መዘዘን የሚስከትል ይመስለኛል፡፡

አሁን አሁን ሰዎች እንደጥጃ ከቤታቸው፣ ከየመንገዱ፣ ከሚሰሩባቸው ቦታዎች …እየተወሰዱ መታሰራቸው በሀገራችን እየተለመደ የመጣ አዲስ ክስተት ሆኗል፡፡ ሥልጣን በጨበጡ ኃይሎች ለነገሮች የሚሰጡት ምላሾች የእስር እርምጃ መሆናቸው ከቀጠለ ከትርፉ ይልቅ ኪሳራቸው ማመዘኑ አይቀሬ ነው፡፡ አይንም ጆሮም ያለው መንግሥት ይስማ!

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሰዎች ለምን ይፈራሉ?›› በማለት ራሴን ደጋግሜ የምጠይቅበት ጊዜ ነበር፡፡ አሁንም እጠይቅና የራሴን ምላሽ ለራሴ እሰጣለሁ፡፡ የምቀርባቸውን ሰዎች ጠይቄም ምክንያቱን ለመረዳት ጥረት አደርጋለሁ፡፡ ‹‹ፈሪ ለእናቱ›› የሚል መልስ አስተናግጄም አውቃለሁ፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ ግን ‹‹እመኑ እንጂ አትፍሩ›› ነው የሚለን፡፡

ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከልባቸው ደፋር የሆኑ ወንድ እና ሴት ኢትዮጵያዊ ወገኖቼን በድፍረት ብቅ ብቅ እያሉ ማየት በመቻሌ ደስ ብሎኛል፡፡

አሁን፣ ሕግን አክብሮ በድፍረት መንቀሳቀስ እንጂ ያለተፈጥሯችን መፍራት በብዙ ችግሮች ለተተበተበችው ሀገራችን አይጠቅማትም፡፡ ‹‹ፍትሕ አጥተናል››፣ ‹‹ተርበናል››፣ ‹‹ነጻነት አጥተናል››፣ ‹‹በኑሮ ተማርረናል››፣ … እያሉ የዳር ተመልካች መሆን መፍትሄ አይደለም፡፡ ‹‹ኢትዮጵኖች የጀግና ሕዝቦች ነን›› እንል የለ? ታዲያ ሕግን ተከትለን በተግባር እናሳየዋ!

እጅግ የመረረ ፀረ-ወያኔ ተቃውሞ። የህዝብ ስሜት ኢህአዲግ/ወያኔ ከጠበቀው በላይ ግሏል

$
0
0

እጅግ የመረረ ፀረ-ወያኔ ተቃውሞ። የህዝብ ስሜት ኢህአዲግ/ወያኔ ከጠበቀው በላይ ግሏል

ፍጥነት! የጀግናን ህይወት ለማትረፍ አፋጣኝ የፊርማ መሳባሰብ አምንሲቲ ኢንተርናሽናል

አንዳርጋቸው ኢትዮጵያዊ ነው !!! (በልጅግ ዓሊ)

$
0
0

በልጅግ ዓሊ

ወንድሙን ሲገሉት ፣ ወንድሙን ካልከፋው፣

ሱሬውን አምጡለት፣ ደሙ እንዲገለማው።

 

በጉን በጉ በላው በድዱ ጎትቶ ፣

ለማን አቤት ይሏል፣ ሰሚስ የት ተገኝቶ።

 

የሕዝብ ግጥም

አንዳርጋቸው በሁለት ወንጀለኛ መንግሥታት ትብብር ታፈነ፣ ተወሰደ ፣ ታሰረ ፣ ተሰቃየ።
ይህ አሳዛኝና የሚያበሳጭ ዜና ነው። በዚህ ቅጥፈት በሞላበት ዓለም ውስጥ ሕዝባቸውን በየቀኑ የሚያስሩ፣ የሚገድሉ፣ የሚያፍኑ መንግሥታት ቢተባበሩ ምንም የሚገርም ጉዳይ አይሆንም። አንዱ የሌላውን  እከክ ማከኩ የተለመደ ነው። ይህ የመጀመሪያ ሳይሆን የተደጋገመ የወያኔ ዘረኛ አገዛዝና የአካባቢው ወንጀለኛ መንግሥታት የተለመደ ወንጀል ነው። ወያኔ ገና ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ እንዲሁም ከዚያ በፊት ጀምሮ ያስራል ፣ ይገድላል ፣ ያሰቃያል።

በዚህ ሰሞን በተፈጸመው ግፍ ውስጥ አንዳንድ የሕዝብ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የማነበው ሆነ የምሰማው አንድ በጣም መስተካከል ያለበት አስገራሚ ሃሳብ አለ። “አንዳርጋቸው እንግሊዛዊ ስለሆነ የመኖች አስረው ለወያኔ ማስተላለፍ አይችሉም“ የሚል ንግግርም ይሁን ጽሁፍ አንዳንዴ ብቅ ይላል።  እግሊዛዊነቱስ እሺ ኢትዮጵያዊስ ቢሆን? ይችላሉ ማለት ነው? ለማስፈታት በምናደርገው ጥረት ማናቸውንም መንገድ መጠቀም ይገባ ይሆናል። ግን ደግሞ ዓላማችንን አዘናጊ፣ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ጎጂ ሊሆን አይገባም።

ለመሆኑ ዜግነታችን ምንድነው?

በአንድ ወቅት ከአንድ ጓደኛ ጋር ከሲዊዘርላንድ ወደ ጀርመን በባቡር ስንጓዝ ነበር ። በባቡሩ ባዝል የሚባል የጀርመን ግዛት ሲደርስ የጀርመን ፖሊሶች ገቡና ባቡሩ ውስጥ የተሳፈሩትን ነጮች ማንንም ሳይጠይቁ እኛ ጋ መጥተው መታወቂያ ጠየቁ። እኔ የስደተኛ ፓስፖርቴን ሰጠሁ ። ጓደኛዬ ጀርመናዊ ሆኖ ነበርና የጀርመንን ፓስፖርት ሰጠ። የእኔን ትንሽ ተመልክቶ መለሰልኝ። ጓደኛዬን ግን አብጠርጥሮ ጠየቀው። የጓደኛዬን ብስጭት ሳይ  ሳቄ መጣ ። ሳቄ ደግሞ ምክንያት ነበረው ።

 

ጓደኛዬ ዜግነቱን የቀየረበት ምክንያት ቪዛ ሳይጠየቅ በአውሮፓና በአሜሪካ እንደፈለገ መንደላቀቅ ስለሚችል መሆኑን ብዙ ጊዜ ሲያወራ ሰምቼው ነበር። ያ የተንደላቀቀበት የጀርመን ዜግነት ፓስፖርት መታወቂያ ሳይሆን መጠየቂያ ሆነበት። ።ከዜግነት የሚያገኘው የቪዛ ጥቅም እንኳን በጥቁርነቱ ተሸፈነ። እሱ በጥያቄ ተንገፍግፎ እኔ ግን በስደተኛ መታወቂዬ በሰላም ታለፍኩ። ይህ ቁጥጥር በባቡሩ ላይ ጥሩ ውይይት አጫረ። ጀርመኖች በተከፋፈለ ሁኔታ ሰለ ጀርመንነት. ስለ ስደተኝነት ፤ እሱንም ተከትሎ ስለሚደረገው ወንጀል እንደ ተዐምር ተወራ። እኛም ዘረኞች ብለን ተሳደብን፣ እነሱም በጥቁር ጀርመንነታችን አሹፈው ተሳለቁብን።

 

ታዲያ ይህ መከረኛ ጓደኛዬ የባድሜ ጦርነት ጊዜ ኤርትራ ውስጥ ነበር። ጦርነቱ ሲነሳ እንደ ማንኛውም ጀርመን ወደ ጀርመን ኤምባሲ ሄዶ አመለከተ። ለጀርመን ዜጎች አውሮፕላን እንደሚመጣ ተነገረው። ጠበቀ ። በኩራትም ለዘመዶቹ ሁሉ ጉራውን ነዛ። አውሮፕላኑም መጣ። ነጭ ጀርመኖችን ጫነ፤ ከዛም ነጭ አውሮፓውያንን ቀጠለ፣ አውሮፕላኑ ሞላ . . .  ሁለት  ሴትጥቁር ጀርመኖችን ብቻ ጭኖ ሌሎቹን ጥሎ ሄደ ። ጓደኛዬ ጭንቅላቱን ቀብሮ ፣  በእፍረት ወደ ዘመዶቹ ተመለሰ። በሌላ አውሮፕላን ተሳፍሮ ግብጽ ደረሰ። ካይሮ ጀርመን ኤምባሲ ሄዶ እርዳታ ጠየቀ። ማንም ግን የረዳው የለም።

 

ሌላው 1997 ምርጫ መጭበርበር ምክንያት በተነሳው አመጽ ምክንያት አንድ የማይረባ አሜሪካዊ የሆነ ዜጋችን ፣ ቅንጅትን በጣም ሲወቅስ ነበር ይባላል። “እኛ አሜሪካውያንን ወደ ሃገራችን ሳንመለስ ቅንጅቶች አመጹን ስላስነሱ ይጠየቃሉ። እኛ አሜሪካኖችን አደጋ ላይ መጣል ነው።“ ብሎ ሲመጻደቅ እንደነበር ድፍን የልደታ ሰው የሚያውቀው ነው። የእኛ “አሜሪካዊ“ ስለ አንዲት በቁም ለሞተች ነፍሱ መዳኛ መፈለጉ መሆኑ ነው።

 

የጀርመን ዜግነት ወይም የሌሎች ዜግነትን መውስድ ልዩነቱ ቪዛ ሳይጠየቁ ብዙ ሃገሮች ከመግባት በላይ አይጠቅምም። እሱም መቼም ከእከክልኝ ልከክልህ ፖለቲካ አካባቢ እስካልደረስን ነው። ሰሞኑን የሚታየው ይህ ነው። የእንግሊዝ መንግሥት የአንዳርጋቸውን መታሰር ምክንያት በማድረግ ጦርም አልመዘዘም፣ ማዕቀብም አልጣለ፣ የረባም መግለጫ አላወጣም። ለይስሙላ ከንፈር ከመምጠጥ በላይ ምንም አላደረገም። እኛ ግን እራሳችን በፈጠርነው ዜና “እንግሊዛዊ ስለሆነ ወያኔ ይፈታዋል“ እያልን ተዘናግተን ማዘናጋት አያስፈልገንም። ይህ ከብዙ የተፈጸሙ ሁኔታዎች አለመማር ነው። ምዕራብያውያን ከጥቅማቸው እንጂ እንደ ፕሮፖጋንዳቸው ለዴሞክራሲ የሚታገሉ አለመሆናቸውን ብዙ መረጃዎች ማቅረብ ይቻላል።

 

አንዳርጋቸው . . .  የዘረኛ ገዳይ  መንግሥት ተቃዋሚ እንጂ የእከኩልኝ ልከክላችሁ ፓለቲካ ደጋፊ አይደለም። አንዳርጋቸው ጦር አሰልፎ ለምዕራብያውያን ጥቅም እንደ ወያኔ የሚቆም አይደለም። አንዳርጋቸው የምዕራብያውያን ጥቅም ለማስጠበቅ ቀን ከሌሊት የሚሰራም አይደለም። አንዳርጋቸው ለሱዳን ለም መሬት፣ ለጅቡቲ ውሃ፣ ለየመን ትንባሆ ፋብሪካ የሚሰጥ አይደለም።  ስለሆነም እንግሊዝም ሆነ ምዕራብያውያን ቦታ ባይሰጡት የሚጠበቅ እንጂ ያልተለመደ ተግባባራቸው አይደለም።

 

1997 ምርጫ የንፁሃን ደም እንደ ጎርፍ ሲወርድ አላየንም ፣ አልሰማንም ያሉ  ምዕራብያውያን አሁን ይሰማሉ ብለን ማመን አይኖርብንም። እንዳልሰሙ፣ እንዳላወቁ አውቀው የተኙን ምዕራብያውያን አንድ ጊዜ ይሰሙ ይሆናል ብለን መጠበቅ መቆም አለበት። የእከክልኝ ልከክልህ አለምአቀፋዊ እንቅስቃሴ አባል ሃገሮች ኤምባሲ በራፍ ላይ ቆመን ጮኸን ተመልሰን እቤታችን ቁጭ ብለን ውጤት መጠበቁ መቆም አለበት።

 

ምዕራብያውያን ሁላችንም አንዳርጋቸው ስንሆን ብቻ ነው የሚሰሙን ማንነታችንን የሚረዱት። ተግባራዊ የሆነ ወያኔን አስፈሪ የሆነ እንቅስቃሴ ስናደርግ ብቻ ነው ካለሰልፍ የኛን ማንነት የሚያውቁት፣ ኤምባሲያቸው ሳንሄድ የሚሰሙን።  ጎበዝ መጃጃሉን እናቁም። ከእባብ እንቁላል እርግብ አይገኝምና ጉልበት አድካሚ የኤምባሲ ሰልፍ እናቁምና በተለየ መንገድ እንደራጅ። ያኔ ነው ድምጽም ኃይልም ልንሆን የምንችለው።

 

ራዕይ ያለው ትግል፣ ክፍፍል ላይ ያላተኮረ ትግል ዉጤቱ አመርቂ ነው። ይህ የአንዳርጋቸው መታሠር የፈጠረውን የአንድነት መንፈስ መጠቀም ብልህነት ነው። ትግሉ ከድርጅት ጥቅም ባሻገር ሊሄድ ይገባል። ከድርጅት ጋር ብቻ ካስተሳሰርነው ግን ወያኔ ወደሚፈለገው ክፍፍል፣ ወይም ከኤምባሲ ሰልፍ የማያልፍ ትግል ብቻ ሆኖ ይቀራል። ዛሬ ነው መዘየድ።

 

በዚህ አጋጣሚ የት ሄዱ የሃገር ሽማግሌዎች? የት ሄዱ ምሁራን? የት ሄዱ የፖለቲካ መሪዎች? ዛሬ በዚህ አዋራጅ ወቅት  ፈር ቀዳጅ የሆነ መንገድ ማሳየት ካልቻሉ ምኑ ላይ ነው ሽማግሌነቱ? ፣ ምኑ ላይ ምሁራንነቱ?  ምኑ ላይ የፖለቲካ መሪነቱ ? ውስጥ ለውስጥ ንግግሩ ሊጀመር ይገባል።

 

የሃያ ሦስት ዓመቱን ትግል ዞር ብለን ተመልክተን የወደፊት መንገዳችንን ካላስተካከልን የመን አይደለም አውሮፓና አሜሪካ መጥተው ቢያንጠለጥሉን ማንም ምንም አይላቸውም። የምንሰለፍላቸውም ምዕራብያውያን ምንም አያደርጉም ። እኛ ብቻ ነን ለእኛ መታገል የምንችለው።

 

ዜግነታችን አሁንም ቢሆን ወደፊት ኢትዮጵያውነት ነው። ሊያኮራን የሚችለውና በእኩልነት ልንታይበት የምንችለው በኢትዮጵያውነታችን ነው። ጀርመናዊነት ሆን እንግሊዛዊነት ወይም አሜርካዊነት ነጻ አያወጣንም።  ራሳችን ነጻ የምናወጣው ራሳችንን ነን።

 

ስለዚህም ነው ዜግነታችን ምንድነው? ብለን መጠየቅ ያለብን ዛሬ ነው ። ምዕራብያውያን ባወጡልን መሥፈር ዜግነታችን ለመመደብ ስንሞክር ውርደት ቀለባችን ይሆናል። ቅኝ ገዥዎች እኛን ለመከፋፈል የተጠቀሙበትን መንገድ ለመጠቀም ስንሞክር እነሱም ይንቁናል ። እኛም እንዋረዳለን።  ወያኔ ደግሞ ዜግነታችንን እያዋረደ፣ የሃገርን ጥቅም እየቸበቸበ፣ በጸረ ሽብርተኝነት ስም የጎረቤት ሃገሮች ቡድን እያቋቋመ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። በየመን የደረሰብንን በደል ታሪክ ጽፎት ይቀመጣል።

 

አንዳርጋቸው ኢትዮጵያዊ ነው ። ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚታገል ሰው ነው። ምንም ወንጀል የለበትምና ሊፈታ ይገባል። እንግሊዛዊ ስለሆነ አይደለም መፈታት ያለበት። ምንም ወንጀል ስለሌለበት ነው መፈታት ያለበት። ካለምነም ቅድመ ሁኔታ ነው መፈታት ያለበት። እሱ ብቻ አይደለም ሁሉም በወያኔ ስም እየወጣላቸው የታሰሩ የነጻነት ታጋዮች  መፈታት አለባቸው። ይህ ትግል መሪዎችን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጰያን ሕዝብ ከወያኔ ዘረኛ አፓርታይድ እስር ቤት ማስፈታት አለበት። “መሪዎቻችን ይፈቱ“ የሚለውን መፈክር ትተን “ወያኔ ይወገድ“ የሚለውን ትግል ማጠናከር ነው መፍትሄው።

 

ጎበዝ ጠላቶቻችንን ብዙዎች ናቸው። ምሥጢራችን በየአደባባዩ መገኘት የለበትም። የብዙ ንጹሃን ደም በእኛ ጥፋት ሊፈስ ይችላልና  ትልቅ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ዛሬ ከአንዳርጋቸው ብዙ እንማራለለን። ከትላንትናዎቹ ባለመማራችን ደግሞ የመጣውን ችግርም ማጥናት ያስፈልጋል።

 

ለማጠቃለል ያህል የኩርዶች መሪን  አብደላ ኦጀላንን ማስታወስ ያስፈልጋል። አብደላ ኦጀላን በሶሪያ ውስጥ ይኖር ነበር ። የቱርክ መንግሥት አብደላ ኦጀላን ከሶርያ ካልወጣ ሶርያን  እወራለሁ ብሎ መስፈራራት ይጀምራል። የሶሪያ መንግሥት ሁኔታውን አይቶ አብደላን ከሃገሩ ያስወጣል። አብደላ ኦጀላንን የሚቀበለው ሦስተኛ ሃገር ያጣል። በመጨረሻም ኬንያ ውስጥ በቱርክ የስለላ ድርጅት ይያዝና ወደ ቱርክ ተወስዶ አንድ ደሴት ላይ ብቻውን ታስሮ ይገኛል። በዛ ወቅት አንድ የኩርድ ተወላጅ የነበረ ጓደኛዬ የነገረኝ ትዝ ይለኛል። ኦጀላን በኩርዶች መሃል ፣ በራሱ ሕዝብ መሃል ቢሆን ኖሮ ይህ አይደርስበትም ነው ያለኝ።

 

ከዚህ ትልቅ አባባል መማር ያስፈልጋል። መደበቂያችን ፣ የምንታገልለት ሕዝብ ነውና ትግላችንን ሕዝባችን ውስጥ ማድረግ ይኖርብናል። ከሕዝባችን ውጭ ማንንም ማመን አይኖርብንም። ሕዝብ መሃል አዲስ አበባም ጫካ ነች። ሕዝባችን ላይ እምነት ካለን፣ ሕዝባችንም ለዚህ ለዘረኛ ከፋፋይ መንግሥት  አሳልፎ አይሰጠንም።

 

 

ለሕዝብ ሲታገሉ በወያኔ እስር ቤት ስለሚሰቃዩ የሚያስቡ ሁሉ በሰላም ይክረሙ።

 

 

ፍራንክፈርት ሐምሌ 2014

 

Comment

“ ድንጋይ ቢቆሉት አይሆንም ቆሎ ”

$
0
0

ይድነቃቸው ከበደ

(ይድነቃቸው)

(ይድነቃቸው)

ሉቃ ም.14ከቁ.15-24 “በእግዚአብሔርመንግስት እንጀራ የሚበላ ብፁዕ ነው አለው፡፡እርሱም ግን አንድ ሰው ታለቅ እራት አዘጋጅቶ ብዙዎችን ጠራ፡፡በእራትም ሰዓት አሁን ተዘጋጅቷልና ኑ እንዲላቸው ባሪያውን ላከ ሁላቸውም በአንድነት ያማካኙ ጀመር ይላል፡፡” የሚገርመው የነዚህ ሰዎች ምክንያት ተራና የውሸት ምክንያት መሆኑ ነው “ ፊተኛው መሬት ገዝቻለው ወጥቼ ላየው በግድ ያስፈልገኛል” አለ፡፡ሰው መሬትን መርምሮ የሚያየው ከመግዛቱ በፊት እንጂ ከገዛ በኋላ ነው ? ሁለተኛውም “አምስት ጥማድ በሬዎችን ገዝቼአለው ልፈትናቸው እሄዳለሁ”አለ፡፡በሬን የሚገዛ ሰው በሬውን የሚፈትነው ቀንበር መሸከም መቻሉን አለመቻሉን አይቶ ማረጋገጥ ያለበት ከመግዛቱ በፊት ነው ወይስ በኋላ? በተጠቀሰው መጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ ላይ ታሪኩ በሰፊ ይገኛል፡፡ ምክንያተኛ ሰው ሌላው ቀርቶ እግዚአብሔር ሲጠራው ይቸገራል፡፡

ምክንያት ለሰው ልጅ ለየትኛውም እንቅስቃሴ አስፈላጊ ከመሆኑም ባሻገር ተፈላጊም ጭምር ነው፡፡ምክንያት አያስፈልግም ከሚል መደምደሚያ የሚያደርስ የማናቸውም ሰው ክርክር ዉሃ የማይቋጥር ጉንጭ አልፋ ሙግትነው፡፡ለማድረግ ወይም ላለማድረግ የቀረበው አመክንዮ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? ለማለት ምክንያታዊ አስተሳሰብን መሠረት በማድረግ መሞገት፣ ተመራጭ አሳብን ለማቅርበ እድል ይሰጣል፡፡

በመሆኑም የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውህደት፣ቅንጅት እና ትብብር በተጠና መልኩ ከተከናወነ ውጤት አለው ተብሎ እንደሚነገረው ሁሉ እራስን ከማታለል እና ድክመትን በሌላው ከመሸፈን ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም የሚልአቋም እንዳለም የሚታወቅ ሃቅ ነው፡፡የየትኛውም ወገን ክርክር “ለሃገር የቱ ይጠቅማል?” ከሆነ ፣ምክንያቱ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው ብሎ ለመቀበል አዳጋች አይሆንም፡፡ ነገር ግን ክርክሩ ከነምክንያቱ “ለፓርቲዬ የቱ ይጠቅማል ከሆነ?” ችግሩ የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ ክርክር ምክንያት አልባ ከመሆኑ ባለፈ የስብህና ዝቅጠትም ይሆናል ፡፡የዚህ ጹሑፍ ዋና ዓላማ እነዚህን ሁለት ምክንያቶችን መነሻ በማድረግ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውህደት፣ቅንጅት እና ትብብር በመጠኑ ለመዳሰስ ነው፡፡

ምርጫ 97 በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ስርአት ውስጥ የሩሱን አዎንታዊ እና አሉታዊ አሻራዎች ጥሎ ያለፈ የ10 ዓመት የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡በወቅቱ የአራት ፓርቲዎች ስብጥር የፈጠረው ቅንጅ ለጠላትም ለወዳጅም የሁሉ ጊዜ የቤት ስራሰጥቶ ያለፈ ነው፡፡ይህን ለማለት የሚያስደፍረው ከምርጫ 97 በኋላ እስከ ምርጫ 2002 አዲስ የተቋቋሙት እንዲሁም ነባሮቹ አካሄዳቸው አንዱ ሌላውን በሴራ ፖለቲካ ውጦ ከማስቀረት የዘለለ አደባባይ ተይዞ የተወጣ አንዳችም ቁሙ ነገር አልታየም፡፡ህረተሰብም በምርጫ ሰበብ ከደረሰበት የልብ ስብራት አገግሞ ስለ አገር እና ፖለቲካ ለማሰብ እና ለመተግበር የነበረው ዝጉጁነት እጅግ በጣም አናሳ የነበረበት ወቅት ነው፡፡በአንጻሩ ገዥው ኢሕአዴግ (የወያኔ) መንግስት በሁሉ መልኩ ራሱን በይበልጥ በአምባገነናዊ ስርአት በማደራጀት በእኩይ ተግባሩ የተጠመደበት የሞት ሽርተ ትግል ለማድረግ ተጠቅሞበታል፡፡

ምርጫ2002 እንደ ምርጫ 97 በፖለቲካ ይዘቱም ሆነ ዓይነቱ ፍፁም የተለየ ለይምሰል የተደረገ አገር አቀፍ የምርጫ ሠሌዳ መረሀ-ግብር ለመሸፈን የተካሄደ ምርጫ ነው፡፡ይህ ምርጫ ውጤት እንደማይኖረው ከበቂ ምክንያት ጋር በማስደገፍ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ይሞግቱ የነበሩ ሰዎች ስለመኖራቸው ስንቶቻችን እናስታውስ ይሆን ? ፡፡ በተለይ አንድነት ፓርቲ የመርህ እና የህግ ጥሰት በመፈፀሙ ከፓርቲው አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆነው በፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም ይመራ የነበረው “የመርህ ይከበር” ስብስብ ምርጫ 2002 ፓርቲዎች በተለይ አንድነት ወደ ምርጫው ከመግባቱ በፊት ሊያጤናቸው የሚገባ ነጥቦች እንዳሉ በማስገንዘብ በውይይት ለመርታት ሙከራ አድርጓል፡፡በወቅቱ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሂደቱን ክሽፈት ለማፋጠን የያኔው አንድነት ፓርቲየአንበሳውን ድርሻ በፍቃደኝነት ወስዷአል፡፡

በወቅቱ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ውጤቱ የተተነበየለት ምርጫ 2002 ኢሕአዴግ (ወያኔ) ይህ ቀረ የማይባል የአፈና ሃይሉን ተጠቅሞ የፓርላማ መቀመጫ ጠቅልሎ በማግኘት ሲንፏለልበት ለማየት ግድ ሆኗአል፡፡ በምርጫ 2002 እድሜቻው ለመምረጥ ከደረሱ ኢትዮጵያዊያን መካከል 33%ኢሕአዴግ(ወያኔን) የመርጡ ሲሆን ፡፡የእያንዳንዱ ተቃዋሚ ፓርቲ ማለትም አንድነት፣መኢአድ፣ኢዴፓ እና ሌሎችም በምርጫው የተሳተፉ በድምሩ ያገኙት ድምፅ 15% ነው፡፡ በአጠቃላይ 48 % የሚሆኑት በምርጫው በመሳተፍ ለሚፈልጉት ፓርቲ ድምፅ የሰጠ ናቸው፡፡ነጉሩን ይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው የተቀሩት 52% የሚሆኑት ድምፃቸውን ለማንም አልሰጡም፡፡ በሌላ አገላለፅ በምርጫው ከተሳተፈው ይልቅ ያልተሳተፈው ይበልጣል ማለት ነው፡፡ይህ ደግሞ በገዥው መንግስት እንዲሁም በተቃዋሚዎች 52% የሚሆኑ መራጮች ተስፋም እምነትም አልነበራቸውም ማለት ነው፡፡ ይህ ሒሳባዊ ቀመር ከመርጫ ቦርድ የተገኘ መረጃ ሲሆንመረጃውየቁጥር ልዩነት አለው ቢባል እንኳን መሰረታዊ ሃቁን የሚያስቀይር አይደለም፡፡ በመሆኑም መረጃውን መሠረት በማድረግ እንዲሁም የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታከግምት በማስገባት ምርጫ 2002 ቅድመ ምርጫ ፣የምርጫ ወቅት እና ከምርጫ በኋለ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ፣የገዥው መንግስ እንዲሁም የህብረተሰብ ተሳትፎ በተለይ የነጻ ሚዲያ አስታዎጾ በጥቅል እና በተናጥል በመመልከት ምርጫው “ቅርጫ” ስለመሆኑ ማመላከቻ ነው፡፡

2007 electionከላይ በስሱ ለማየት የተመከረው ሁለት አገር-አቀፍ ምርጫ ከፊት ለፊት እየጠበቅን ላለው ምርጫ 2007 ለተቃዋሚ ፓርቲዎች በገዥው መንግሰት የፖለቲካ ንድፈ-ሃሳብ ሠነድ እንዳለ የሚነግረን ነገር ይኖረዋል፡፡ይህን መነሻ በማድረግ በመጪው ምርጫ 2007 የገዥው መንግስት ባሪያ የሆኑትን በስመ ተቃዋሚ ተመዝግበው ከአሳዳሪያቸው ቀለብ የሚሰፈርላቸውን ወደ ጎን በመተው ፡፡ እውነተኛ ተቃዋሚ ነን የሚሉየኢሕአዴግ (ወያኔ) ንቅዘትና በዘር ከፋፍለህ ግዛው ፖሊስ የሚቃወሙ እንዲሁም ዴሞክራሳዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት ቁርጠኝነቱ አለን የሚሉ ፓርቲዎች ወሣኝ ትግል ሊደረግበት የሚገባውወቅት ነው፡፡

ይህን ትግል በተልካሻ ምክንያት ውጤት አልባ እንዳይሆን የፖለቲካ ሊቃን ብቻ ሳይሆን ስለ አገሪ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ሁሉ ሊመክሩበት፣ውሳኔ ሊሰጡበት እና ተግባራዊ ሊያደርጉት የሚገባ ታላቅ ስራ ነው፡፡በተለይ የዓላማ አንድነት ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች በመጪው 2007 አገር-አቀፍ ምርጫ የሞት ሽረት ሠላማዊ ትግል የሚያደርጎበት ነው፡፡ በእርግጠኝነት ከወዲኹ መገመት እንደሚቻለው ምርጫ 2007 በአገራች እየታየ ያለው ሰላማዊ ትግል ተስፋ ሰጪ የሚሆንበት ወይም ተስፋ የሚጨልምበት ታሪካዊ ወቀት ነው፡፡ታሪክ መስራት ደግሞበተቃዋሚ ፓርቲዎች እጅ የሚወድቅ ሃላፊነት ነው! ይህ አገራዊ ሃላፊነት ከቂም እና ከጥላቻ ፣ከተሳሳተ ሂሣባዊ ቀመር፣ከአገር በላይ ለፓርቲ ማድላትእንዲሁም ከእራስ ወዳድነትና ከስልጣን ጥማትእራስን በመግታት ትውልድ ተሻጋሪ የሆነ ታሪክ በመስራት የአገራችን ዕጣ ፈንታ የሚወሰንበት የምርጫ መጨረሻ መጀመሪያ ነው፡፡ በአርግጥ ይህ ሃላፊነት የፓርቲዎች ብቻ ሣይሆን ለውጥ ፈላጊ የሆነ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሃላፊነት ጭምር ነው፡፡

የዚህ ጽሑፍ ዋና ማጠንጠኛ እውነተኛ ተቃዋሚዎች እና የዓላማ አንድነት ባላቸው ፓርቲዎች መካከል ሊተባበሩ ወይም ሊቀናጁ ከተቻለ ውህደት ሊፈጥሩ እንደሚገባ ለማመላከት ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ አንድነት እና መኢአድ ቅድመ ውህደት መፈፀማቸው እጅግ በጣም አስደሳች ከመሆኑ ባለፍ ለሌሎችም ተስፋ ሰጪ ነው፡፡ከፈፀሙትም ቅድመ ውህደት ወደዋናው ውህደት የሚያደርጉት ጉዞ የተሳካ እንዲሆን ከመመኘት ባለፈ ለውህደቱ አስታዎፆኦ ሊያበረክት የሚችል ማናቸውም ነገሮች መተግበር ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም፡፡ሰማያዊ ፓርቲ በባለፈው ሳምንታት የብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ጥልቀት ያለው ውይይት በማካሄድ ፓርቲው ከመቼው ጊዚ በላይ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመሥራት መዘጋጀቱ መግለጹ ይበል የሚያስብል መልካም ጅማሮ ነው፡፡

በመሆኑም እውነተኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ነን የሚሉና በህብረተሰብ ተቀባይነት ያላቸው ፓርቲዎች በሙሉ፤ ደግመው ደጋግመው እልህ አስጨራሽ ሂደቱን ተከትለው ሊተባበሩ ወይም ሊቀናጁ ከተቻለ ውህደት ሊፈጥሩ ይገባቸዋል፡፡ይህን የሚያደርጉት ተባባሩ ወይም ተሰባበሩ የሚባለውን ለመሸሽ ወይም ለመጋፈጥ ሳይሆን እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ በጥልቀት እራሱን በመፈተሸ ጠንካራና ደካማ ጎኑን በመለየት ከሚዲያ ፍጆታ ባለፈ መሬት የያዝ ስራ ምን ሰራው ?ምንስ ይቀረኛል ?በማለት ጉድለተ የሚሞላበት ስኬት ለሌላው የሚያስተላልፉበት የትብብር፣የቅንጅት እና የውህደት ጊዜው አሁን ነው!!! የማይካድ ሃቅ ቢኖር የፓርቲዎች ትብብር፣ ቅንጅት እና ውህደት መካከል አጋፋሪዎች መኖራቸው ነው፡፡እነዚህን በጥንቃቄ በመለየት እና በማስረዳት ካልተቻለም በመነጠል አሸናፊ ለመሆን ትጋትን የሚጠይቅ የጎን ለጎን ስራ ያስፈልጋል፡፡በይበልጥ ደግሞ ትብብር፣ቅንጅት እና ውህደት ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ለዚህ ጽሑፍ በመግቢያነት የተጠቀሰው ዓይነት ወንዝ የማያሻግርተልካሻ ምክንያቶችን በመደርደር ለሰላማዊ ትግሉ እንቅፋት ላለመሆን እራስን መጠበቅ የተሻለ ነው፡፡

በመጨረሻም የዚህ ጽሑፍ ማጠቃለያ የሚሆነውበባለፈው ምርጫ 2002 ክስተትን በማስታወስ ነው፡፡ እሱም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በተወዳደሩበት አካባቢ 2ኛ ሆነው ነው የተሸነፉት 1ኛ የወጣው የወያኔ ተላላኪ የበለጣቸው 130 ድምፅ ነው፡፡በዚያው አካባቢ መኢአድ ወክለው የተወዳደረው ከ400 በላይ ድምፅ አግኘተው ነበር፡፡ከዚህ የበለጥ ስለትብብር፣ቅንጅት እና ውህደት ምን ጥሩ ማሳያ ይኖራል በማለት መደምደም ባይቻልም እንደግባት ለመጠቀም ግን የተሻለ ነው፡፡በመሆኑም እነዚህን እና መስል ሃቆችን ግምት ውስጥ በማስገባት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጉዞ  “ ድንጋይ ቢቆሉት አይሆንም ቆሎ ” ከመባል እና ተተፍቶ ከመጣል እራስን ማዳን ምንኛ መታደል ነው፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!


እየነጋ ነው!

$
0
0

አንዱ ዓለም ተፈራ
ሐምሌ ፪ ቀን፤ ፳፻፯ ዓመተ ምህረት 7/9/2014
habtamu ayalew
yeshiwas
DEA54BEE-2996-4145-A17A-2842A121CD0E_w640_r1_s

አብርሃ ደስታ

አብርሃ ደስታ


አሁን ደግሞ ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንዔል ሺበሽ፣ አብረሃ ደስታን አሰሩ። አንዳርጋቸው ፅጌን የማሠራቸው ዜና ገና አቦሉ ሳይጠጣ እኒህን ደገሙ። ለምን? አጭሩ መልስ እየነጋ ስለሆነ ነው። ኢትዮጵያዊ ሆኖ የእኒህን ታጋዮች ማንነትና ተግባር የማያውቅ የለም፤ ቢያንስ በትግሉ ዙሪያ ያለነው ኢትዮጵያዊያን። ታዲያ መንጋቱ እኮ፤ የአውራ ደሮውን ጩኸት፣ የጎኅን መፈንጠቅ፣ የጨለማውን መገፈፍ ይጠይቃል። ይህ ደግሞ በገዛ ፈቃዱና ቁጭ ብለው ስለጠበቁት የሚሆን አይደለም። የመሬትን በፀሐይ ዙሪያ መሽከርከር ተፈጥሯዊ ግዴታ ተከታይ ነው። በጭቆና የሚማቅቅ ሕዝብ፤ ለነፃነቱ መነሳቱና ከመካከሉ ቆራጦቹ ጧፍ ሆነው ከፊት መቅለጣቸው ግዴታ ነው። ይህ ነው የኒህ ቆራጥ ታጋዮች ሕይወት ትርጉሙ። እንደኛው ቤተሰብ፣ ንብረትና ምቾት አልጠሉም። ለወገንና ለሀገር ሠጡት። የሕይወታቸውን ትርጉም፤ በጣሊያን ጊዜ ከፋሽስቶች ለመጋፈጥ ከየመንደሩ በባዶ እግራቸው፤ ከመላ ኢትዮጵያ ጫፍ እስከጫፍ ወጥተው እንደቀሩት አርበኞቻችን፤ የኔ ሕይወት ለነገዋ ኢትዮጵያ ሕልውና ይሁን ብለው ያለማመንታት፤ ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነውን ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራውን መንግሥት በመቃወማቸው እስር ቤት ገቡ። ከኛ የተለዩ ልዩ ፍጡር ሆነው አይደለም። እንደኛ አባትና እናት፣ እህትና ወንድም፣ አክስትና አጎት፣ ባለቤትና ልጆች ያሏቸው ናቸው። ሰው ናቸው። አርበኛ ያደረጋቸው ተፈጥሯዊ ልዩነታቸው ሳይሆን፤ ለሕይወታቸው የሠጡት ትርጉም ነው። የብዙኀኑን የኢትዮጵያዊያን ሕይወት የኔ ብለው፣ ስቃያቸውን እነሱ ተሸክመው፣ ለሕዝቡ ጭዳ ሆነው ተሰለፉ። እንደነ አንዱዓለም አራጌ፣ እስክንደር ነጋ፣ ርዕዩት ዓለሙ፤ ሰግዶ ማደርን አልፈልግም ብለው፤ አረዓያችን ሆኑ። እንዲነጋ ምን ማድረግ አለብን።

አይቀሬው ንጋት እየመጣ ነው። የኛ ኃላፊነት ብዙና የተቆላለፈ አይደለም። እኒህ ቆራጦች የነገሩን ምንድን ነው? ፍርሃትን፤ ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራው መንግሥት ቀምቶናል። ከኛ በኩል ፍርሃት ቦታ የለውም። የኢትዮጵያዊያን ጠላት የሆነው ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራው መንግሥት በፍርሃት ተውጧል። ምስክርነቱ፤ ማንንም የሚፈራውንና በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት አለው የሚለውን ግለሰብ ሁሉ እያሠረ ነው። እኒህ ጀግኖች የታሠሩት የዚህ ወይንም የዚያ ድርጅት አባል ስለሆኑ አይደለም። ከሕዝቡ ጋር ስለወገኑ ብቻ ነው። ለዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት፤ ማንኛውም ከሱ ቁጥጥር ውጪ የተደራጀ ክፍል ጠላቱ ነው። እናም የዚህ ወይንም የዚያ ድርጅት አባል መሆን አይደለም የመታሰሪያ ወንጀሉ፤ ከሕዝቡ ጋር የቆመ መሆኑ ብቻ ነው። የሚያስበረግገውና የሚያንቀጠቅጠው የሕዝብ ወገን የሆነ ማንኛውም ድርጅት ነው። ታዲያ ድርጅቶች በሙሉ አንድ ዓላማ እስከያዙ ድረስ፤ ሕዝቡ አሁን ነው ትግሉ ወደፊት መሄድ ያለበት እስካለ ድረስ፣ ንጋቱ በር አያንኳኳ እስከሆነ ድረስ፤ ተልዕኳችንን አንድ አድርገን ሌቱን እናንጋው።

ምንድን ነው የአሁን ጥያቄ? ይፈቱልን ብሎ ልመና አይደለም። ይህ በታሠሩት ቆራጦች ዓይን ጥቃት ነው። ይህን ብናደርግ ለገዥው ቡድን ኩራት ነው። እንኳን ያሠራቸውን ሊፈታ፤ የሚቀጥሉትን ታሳሪዎች እያዘጋጀ ነው። እነሱም ሆኑ መታሠራቸው፤ ጧፍ ሆኖ መንገዱን መሪያችን እንጂ፤ የመንገዱ ማብቂያ አይደለም። ገና የራሱን ጥላ ለማሠር የሚሯሯጥ ጠላት ነው ያለን። አጥንት ቆጠራውን ለገዥው ክፍል እንተውለት። እሱም እንኳ ለአጥንት ቆጠራው ቦታ እንደማይሠጠው አብርሃ ደስታን በማሠር አሳይቶናል። አብርሃ ደስታ በትግራይነቱ፣ ትግሬዎች እየተጠቁ ነው ብሎ የተደራጀ ነበር። አልሆነም። ኢትዮጵያዊነታችንን እንጎናጸፈው። በኢትዮጵያዊነታችን ይኼን ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት እንታገለው። ሁላችንን ሊያስተባብሩን የሚችሉ አራት የትግል ዕሴቶች አሉን።

፩ኛ፤ የኢትዮጵያዊያን ሉዓላዊነት
፪ኛ፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት

፫ኛ፤ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች
፬ኛ፤ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት
እኒህ ናቸው የታጋዮችን አንድነት የሚጠይቁ የትግል ዕሴቶቻችን። በነዚህ ዙሪያ ሁላችን መጠማጠም አለብን። የየድርጅቶች ታሣሪዎች መሆናችንን ለነፃነቱ ጊዜ እንተወውና፤ ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ፣ ለሀገራችን አንድነት፣ በየእስር ቤቱ ለሚማቅቁ ጀግኖቻችንና አሁን በየዕለቱ ለሚታገቱት ቆራጥ ኢትዮጵያዊያን አርበኞቻችን አንድነታችንን እናጠንክር። ይህ ወደ ድል ይወስደናል። እነዚህን ሁሉን አቀፍ የሆኑ አራት ነጥቦች በሚያኩ ዙሪያ ሀገራዊ አጣዳፊ ጥሪዎች ሰሞኑን ድረገፆቻችንን አሙቀውታል። ጥሪዎቻችሁ ወደ መሰባሰቡ እንዲያመራ ፈልጋችኋል በማለት፤ ጥሪዎችን በተደጋጋሚ ያደረጋችሁ ግለሰቦች፤ እኛው ጀማሪዎች እንሁን የሚል ጥሪ በማስቀደም እንድንገናኝ ይኼው በ ( eske.meche@yahoo.com ) እገኛለሁ።

አቶ አንዳርጋቸውን እና ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን እስር በመቃወም በሚኒሶታ የፊታችን አርብ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በጭንቀት ውስጥ እንዳለ የሚነገርለት የሕወሓት/ኢሕአዴግ አስተዳደር የሚገባበት ሲጠፋ በተለይ ወጣት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ጠራርጎ ወደ እስር መክተቱን እና የግንቦት 7 አመራሩን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አፍኖ መውሰዱን በመቃወምና ሕዝቡም ቁጣውን እንዲገልጽ በማሰብ በሚኒሶታ የፊታችን አርብ ጁላይ 11 ቀን 2014 ዓ.ም የተቃውሞ ሰልፍ ተጠራ።
andargachew Tsege
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን አውሮፕላን ማረፊያ ወስዶ በሃገሪቱ ቴሌቭዥን ጣቢያ አጎሳቁሎ ያሳየው ስርዓቱ በተመሳሳይ ቀን የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲ ወጣት አመራሮችን ለቃቅሞ የዲሞክራሲ በርን ጥርቅምቅም አድርጎ መዝጋቱን በመቃወም በሚኒሶታ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲገኝ ጥሪ የቀረበ ሲሆን ሕዝቡም በነቂስ ወጥቶ በሚኒሶታ ዋና ከተማ ስቴት ካፒቶል ደጃፍ ተቃውሞውን እንዲያሰማ ተጠርቷል።

የፊታችን አርብ ጁላይ 11 ቀን 2014 ከጠዋቱ ከ10 ሰዓት ጀምሮ በስቴት ካፒቶሎ አቅራቢያ በሚገኘው ሲርስ ደጃፍ በመገናኘት ወደ ካፒቶሉ በሚያመራው በዚህ ሰልፍ ላይ የታሰሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ ጋዜጠኞችች እና ነፃ አሳቢ ዜጎችና የሃይማኖት መሪዎች እንዲፈቱ ይጠየቃል፤ የአሜሪካ መንግስትም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንዲቆም ጥሪ ይቀርባል።

ሰልፉ የሚደረግበት አድራሻ: 75 Rev Dr Martin Luther King Jr Boulevard., St Paul, MN 55155,
ጠዋት ከ10 ሰዓት ጀምሮ፤ የኢትዮጵያ ባንዲራና ጥቁር በጥቁር ለብሰው እንዲገኙ ይመከራሉ ይላሉ አስተባባሪዎቹ።

ኢሕአዴግ ለቃቅሞ ያሰራቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተባለ

$
0
0

10494588_750671571658261_8784450188684809422_n

habtamu ayalew

yeshiwas
ፍኖተ ነፃነት የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ከትላንት በስቲያ የተያዙት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በዛሬው እለት አራዳ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች ጠቆሙ፡፡
የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች እንደጠቆሙት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ሀብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ም/ኃላፊ የሆነው አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ም/ሰባሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አራዳ ፍርድ ቤት ለጊዜ ቀጠሮ እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮቹ ጠበቆቻቸውን ጨምሮ ማንም ሰው እንዳይጎበኛቸው ክልከላ መደረጉ የሚታወቅ ሲሆን መንግስት ፖለቲከኞቹን ያሰረበትን ምክንያት እስካሁን ይፋ አላደረገም፡፡

ማስታወቂያ –ለሚኒሶታ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ !

$
0
0

የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ

የየመን መንግሥት ከወያኔ መንግሥት ጋር በመተባበር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የግንቦት 7 ጻሐፍን ከሰናዓ አይሮፕላን ጣቢያ  ጠልፎ ከማስተላለፉም በላይ በአገራችን የውስጥ ጉዳይ እየገባ በዜጎቻችንን በመበደል ላይ ይገኛል። ይህንን የየመንን ህገውጥ  ድርጊት ለመቃወምና የወያኔ መንግሥት በአንዳርጋቸው ጽጌና በሌሎች ወገኖቻችን ላይ የሚያደርሰውን ግድያ፣ እስር፣  እንግልትና ሌሎች በደሎችን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ስለተዘጋጀ በሰልፉ ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ጥሪ እናደርጋለን። All Ethiopians in Minnesota are kindly requested to join the demonstration organized to oppose the  illegal action of Yemeni government handing over of Andargachew Tsige, the secretary of Ginbot 7 , to the brutal regime in Ethiopia.

ቦታ ( Place) : Meeting Place, Sears, 425 Rice Street, Saint Paul, MN 55103 then to, Minnesota State Capitol  75 Rev. Dr. Martin Luther King Jr. Boulevard, Saint Paul, MN 55155 

ቀን (Date) : Friday, July 11, 2014

ሰዓት( Time) : 10:00Am

የሚኒሶታ ግብረኃይል ( Task Force In Minnesota)

Free andargachew tsige LG

ከመኢአድ/አንድነት ውህደት አመቻች ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

$
0
0

የውህደት አመቻች ኮሚቴውን በማሰር ውህደቱን ማደናቀፍ አይቻልም!!!

ኢህአዴግ ሰሞኑን የጀመረው እስር የአንድነት/መኢአድን ውህደት የማደናቀፍ አቅም እንደሌለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ማረጋገጥ እንወዳለን

በኢትዮጵያችን በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት እየታገሉ የሚገኙት አንድነትና መኢአድ ከጥልቅ ውይይት በኋላ ወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ የሚፈልገውን በመገንዘብ፤ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ የሚችል የበተባበረ የፖለቲካ ሃይል ለመፍጠር እንዲቻል ስለ ዴሞክራሲ ሲሉ መስዋዕት የሆኑ ውድ ኢትዮጵያውያን በሚዘከሩበት ሰኔ 1 ቀን ለበርካታ ወራት በጋራ ሲሰሩበት የነበረውን የውህደት ስምምነት ከጫፍ በማድረስ የቅድመ ውህደት ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው፡፡

ሁለቱ ፓርቲዎች ውህደቱን በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የውህደት አመቻች ኮሚቴ በማቋቋም ስራቸውን በእቅዳቸው መሰረት በትጋት እየሰሩ ሲሆን የኮሚቴው ሰብሳቢ ወጣቱ ፖለቲከኛ አቶ ሀብታሙ አያሌው ነበር፡፡ ኮሚቴው እንደሚያምነው ህወሃት/ኢህአዴግ የሁለቱን ፓርቲዎች ውህደት ካለመፈለጉም በላይ የተለያዩ ሁኔታዎችን በመጠቀም ለማደናቀፍ እንደሚሰራ እንገምታለን፡፡ ስለዚህ ሀብታሙ አያሌው በኮሚቴ ሰብሳቢነቱ ስራውን በትጋት እየተወጣ ስለነበር ሆን ተብሎ ውህደቱ ላይ እክል ለመፍጠር በአምባገነኑ ስርዓት ለእስር ተዳርጓል ብለን እናምናለን፡፡

የመኢአድ/አንድነት ውህደት አመቻች ኮሚቴ በጥብቅ እንደሚያምነውና ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማረጋገጥ የምንፈልገው የኮሚቴውን ሰብሳቢ ብቻ ሳይሆን እንዳለ ኮሚቴውን ቢያስር የተጀመረው ውህደት ሊደናቀፍ አይችልም፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ ሰሞንን የጀመረው አመራሮች ላይ ያነጣጠረ እስር ወሳኙን ምዕራፍ የተሻገረውን ውህደታችንን የማደናቀፍ አቅም እንደሌለው በድጋሚ እናረጋግጣለን፡፡ እስሩ የሚጠቁመው ነገር ቢኖር ህዝባዊ መሰረቱን እያጣ የሚገኘው ገዢ ፓርቲ ህዝባዊ መሰረት እንዳጣና በጭንቀት ውስጥ ወድቆ ወደ ሃይል ርምጃ እንዳመራ ነው፡፡

የውህደት አመቻች ኮሚቴው እንደሚያምነው እንደገና የተጀመረው ሰላማዊ ታጋዮች ላይ ያነጣጠረው የማሰር ርምጃ የፀረ-ውህደት ዘመቻ ከመሆኑም በተጨማሪ በቀጣዩ አመት የሚካሄደውን ሀገራቀፍ ምርጃ በተለመደው ጉልበትና አፈና ለመንጠቅ ያለመ ነው፡፡ ስለዚህ ኮሚቴው ሀብታሙን ጨምሮ ዜጎች በፖለቲካ እምነታቸውና አቋማቸው እየተፈረጁ መታሰራቸውን አሁኑኑ እንዲቆም እየጠየቀ የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላማዊ ትግሉ ላይ የተጀመረውን የመድፈቅ ርምጃ በማውገዝ ሁለቱ ፓርቲዎች የጀመሩት ውህደት ከፍፃሜ እንዲደርስ የተለመደው ህዝባዊ ድጋፉን እንዲሰጥ ጥሪ ያቀርባል፡፡ ሊሎች ፓርቲዎችም ወደ ትብብር በመምጣት ሀገራችንን ከክፉዎች መታደግ እንድንችል ጥሪ እናቀርባለን፡፡

      ድል የሕዝብ ነው!!!

                           የመኢአድ/አንድነት ውህደት አመቻች ኮሚቴ

                                                ሐምሌ 3 ቀን 2006 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ

udJ&AEUP

የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ባለቤት የምሥራች ኃይለማርያምና ወንድማቸው ብዙነህ ፅጌ…(VOA)

$
0
0

ባለቤታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ያገኛሉ ብለው እንደማያምኑ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ባለቤት ወ/ሮ የምሥራች ኃይለማርያም ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡ ወንድማቸው አቶ በዛብህ ፅጌም የወ/ሮ የምሥራችን ሃሣብ አጠናክረው “አንዳርጋቸው በቴሌቪዥን ሲናገር የተሰማው ከተፈጥሮው ጋር የማይጋጭ እንዲያውም የሚያጠናክረው ነው” ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ዜጋው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ኢትዮጵያ ውስጥ በእሥር ላይ የሚገኙበት የእንግሊዝ መንግሥት የየመንን አድራጎት አውግዞ ኢትዮጵያ ውስጥ በሌሉበት

VOA 1

ሰላማዊ ዜጎችን ማሰር የሽንፈትና የደካማነት ምልክት ነው –ግርማ ካሳ

$
0
0

አገር ቤት ያሉ መሪዎች ቁርጠኝነት ያስደንቀኛል። ግርማ ሰይፉ «ለመታሰር እንዘጋጅ» አለ። ዳንኤል ተፈራ «ገዥዎች፣ እመኑኝ ባሮጌው መንገዳችሁ በርካቶችን ነፃነት ናፋቂዎች በሰፋፊ እስር ቤታችሁ ታጉሩ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የዚህን ትውልድ የነፃነት መንፈስ ግን ልታስሩት አትችሉም» አለ። የፍኖት ዋና አዘጋጅ ነብዩ «ጨቋኞችን መታገል ፅድቅ እንጂ ኩነኔ እንደሌለው አምናለሁ፤ ጭቆናን እምቢ በማለቴ የምጠጣት እያንዳንዷ ፅዋ በፈጣሪ ዘንድ ወሮታ እንደምታከማችልኝም አምናለሁ፡፡ ፍርሀትን ብቻ እፈራለሁ» ሲለን፣ የአዲስ አበባ አንድነት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ያሬድ አማረ ደግሞ «ወደኋላ አንመለስም። ዘመን ተሻጋሪ ወጣቶች በቅለናልና በምንም መልኩ ለሚደረግ ማዋከብ፤ እስራት እና ግድያ ከጀመርነው የሰላማዊ ትግል መስመር ስንዝር አያዘንፈንም፡፡ ደግሞም አምባገነኖች ባሉበት ሀገር የጀግና ቤቱ እስር ቤት አልያም መካነ መቃብር ውስጥ ሊሆንም እንደሚችል ስንጀምር ያለአስረጂ እናውቃለንና» በማለት የትግሉ ደረጃ ምን መስመር ላይ እንዳለ እቅጩን ይነግረናል።

አንድነት እና መኢአድ ሊዋሃዱ ዝግጅት ላይ ናቸው። በየክልሉ ሕዝቡ በሰላማዊ ሰልፎች ተቃዉሞዉን እያሰማ ነው። ሂዱ አዳማ፣ ሂዱ ወላይታ፣ ሂዱ ጎንደር፣ ሂዱ ደሴ ፣ ሂዱ ጂንካ፣ ሂዱ ጊዶሌ ….ሕዝቡ «በቃን፣ መረረን« እያለ ነው። ለ23 አመት የተዘራዉን የዘር መከፋፈል አረም እየነቀለ አንድ ነን እያለ ነው። «ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትምህክተኛ፣ ጠባብ….እያላችሁ አትከፋፍሉንም» እያለ ነው። የሚሊዮኖች ንቅናቄ ተጧጡፎ እንደሚጧጧፍ፣ የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት በስኬት እንደሚጠናቀቅ፣ የምርጫ ዘመቻና ዝግጅት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል፣ የአንድነት አመራሮች እየነገሩን ነው። አገዛዙ ዜጎችን በማሰር ትኩረት ለማስቀየር የሚያደርገውም ደባ አይሳካለትም።

ትላንት ብርቱካንን ሲያስሩ ያበቃ መሰሏቸው ነበር። ትላንት እስክንድርን ሲያስሩ ያበቃ መሰላቸው ነበር። ትላንት ርዮት አለሙን ሲያስሩ ያበቃ መሰላቸው ነበር…..ግን ተሳሳቱ። እነ ሃብታሙ አያሌው ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ዞን ዘጠኖች ….ብቅ አሉ። እነርሱን ደግሞ በጭካኔ እየደበደቡ ወደ ማእከላዊ ወሰዱ። ሚሊዮኖች ግን ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። «የነፃነት ታጋዮችን በማሰር የወጣችው የኢትዮጵያዊነት ፀሀይ ትደምቃለች እንጂ አትጠፋም» እንዳለ ዳዊት ሰለሞን ፣ ገዥው ፓርቲ ሰላማዊ ዜጎችን ማሰሩ ደካማነቱን፣መክሰሩን፣ መሸነፉን ፣ መደንገጡን በአንድ በኩል እያመላከተ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ትንሳኤ መቅረቡን የሚያሳይ ነው።

አንድ በሳል መሪ፣ ችግሮች ሲፈጠሩ፣ ችግሮቹን በዉይይት፣ ሌሎችን በማሳመን፣ ኮምፕሮማይዝ በማድረግ ለመፍታት ይሞክራል። ያኮረፈዉን፣ የሚቃወመዉን፣ ሸፍቶ ነፍጥ ያነሳዉን ለማግባባትና ወደ እርሱ ለማምጣት ይሞክራል። ተቃዉሞ የሚያቀርቡትን፣ የተለያየ ስም እየሰጠ ለማጥፋት አይሞክርም። የኢሕአዴግ መሪዎች፣ እያደረጉ ያሉት ነገር ቢኖር ግን፣ አንድ በሳል መሪ ማድረግ ያለበትን ሳይሆን፣ የአንድነት ፓርቲ መግለጫ እንዳስቀመጠው፣ መንግስታዊ ዉንብድናን ነው። መንግስት እንደ አባት ነበር የሚታየው። ዜጎችን ማክበር፣ ማገልገል ይጠበቅበታል። የዜጎችን ጥቅም በአገር ዉስጥ ሆነ ከአገር ዉጭ ለማስከበር ይተጋል። የኛዎቹ የኢሕአዴግ መሪዎች ግን፣ ዜጎችን እያሸበሩ ነው። ኢትዮጵያዉያንን እያስፈራሩና እያዋረዱ ነው። ጨካኞች፣ ግትሮች፣ ለሰብእና ከበሬታ የሌላቸው፣ ሕግን እየጠመዘዙ፣ ፍርድ ቤቶችን በካድሬ ዳኞች እየሞሉ፣ የዉሸት ምስክር እያቀረቡ ዜጎችን የሚያንገላቱ፣ ያለነርሱ አዋቂ፣ ያለነርሱ ኢኮኖሚስት፣ ያለ እነርሱ ኢንጂነር፣ ያለ እነርሱ የሕግ አዋቂ ያለ አይመስላቸውም። እነርሱን የሚቃወም ሁሉ «አሸባሪ» ነው።

ኤሚ ሰለሞን የምትባል ብሎገር «ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ለምን ጻፋቹህ ? ለምን ያገባናል አላችሁ ? ተብለው በየእስር ቤቱ የታጎሩትና በየጊዜው እያንጠለጠሉ የሚወስዷቸው ስንት ናቸው ? ስንቱን ከሃገር አሰደዱ ? ማነው አሸባሪው ታዲያ ?» ብላ እንደጠየቀቸው፣ በአገራችን የሽብር ተግባር እየፈጸመ ያለው ኢሕአዴግ እራሱ ነው።

«እፎይ! ካሁን በኋላስ መቼም ቢሆን ከደርግ የከፋ መንግስት ሊመጣ አይችልም’ ብለን ነበር። ከ23 ዓመት በፊት . .» እንዳለው ኩሪ ሀገሬ የተባለ ብሎገር፣ ከ23 አመት በፊት፣ ብሶት የወለደው የኢሕአዴግ ሰራዊት ፣ አዲስ አበባ ሲገባ እና ለሰፊዉ ሕዝብ ጥቅም የኢትዮጵያን ራዲዮን እና ኢቲቪ ሲቆጣጠር ፣ ቢያስን የተሻለ ነገር ይመጣል ብለን ነበር። ዳሩ ግን ቅሉ፣ ከፈረንጆች በልመና በተገኘ ገንዘብ ግንብና ፎቅ እየሰሩ፣ ክብራችንን፣ ስብእናችንን፣ ነጻነታችን ገፈው በአገራችን ባሪያ ሊያደርጉን የሞት ሽረት እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው።

ነገር ግን አሁን ከ10 አመት፣ ከ15 አመት በፊት እንደነበረው አይደለም። ሕዝቡ መሮታል። የግፍ ቀንበርን ለመታገስ አይችልም። ኢትዮጵያ እሳት የለበሱ፣ ወኔ የሞላባቸው፣ ነፍጥ ሳይጨብጡ ጀግንነት ለመስራት የተዘጋጁ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዳግማዊ ጣይቱዎች አሏት። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዳግማዊ ባልቻ አባ ነፍሶዎች አሏት። የሚሊዮኖችን ኃይል ደግሞ ሊቋቋም የሚችል ምንም ኃይል አይኖርም።

 
Comment


ሰማያዊ ፓርቲ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰብአዊ አያያዝ ያሳስበኛል አለ

$
0
0

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

semayawi-statment2-300x200የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎችን በማፈንና በማሰቃየት ብሎም በመግደል የአፈና አገዛዙን ለረጅም ጊዜ ሲያራምድ መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እስራትና ግድያውን ህጋዊ ለማስመሰል የተለያዩ አፋኝ አዋጆችን አውጥቷል፡፡ እነዚህን አዋጆችንም ተገን አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባለትን፣ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን፣ እንዲሁም የእምነት ተቋማት መሪዎችን እና በአገዛዙ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ማሰሩን፣ ማሰቃየቱንና ግድያውን ተያይዞታል፡፡ በህገ መንግስቱ የተካተቱ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በሙሉ የሚጥሰውና የአምባገነንነት ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ያፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ ከፀደቀበት እለት አንስቶ ኢህአዴግ ለስልጣኔ ያሰጉኛል የሚላቸውን ፍፁም ሰላማዊ ታጋዮችንና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው በድፍረት የፃፉ ጋዜጠኞችን ብሎም የእምነት ነፃነታችን ይከበር ብለው የጠየቁ የሀይማኖት መሪዎችን በጠራራ ፀሃይ ያለምንም ወንጀል በዚሁ ህገ ወጥ አዋጅ ‹‹የፀረ ሽብር ግብረ ሀይል›› በሚባል ማንነቱ በማይታወቅ የጨለማ ቡድን ወደ እስር ቤት እያጋዘ ይገኛል፡፡

ይህን የሚያጋልጡ ሚዲያዎችንም ለማፈን እስር ቤቶችን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያፈሰሰ የአየር ሞገድ ያውካል፤ በዚህ ሳያበቃ በሀገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ ፖለቲከኞችን ለማሸማቀቅ እንደ ኢሳት ያሉ ሚዲያዎችን የአሸባሪ ልሳን ብሎ በመፈረጅ ሚዲያውን የሚጠቀሙትን ደግሞ ከአሸባሪዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው አድርጎ መወንጀሉን ቀጥሎበታል፡፡ እንደሰማያዊ እምነት ማንም አካል መልእክት የሚያስተላለፍበትን የሚዲያ ተቋም ሊመርጥለት እንደማይችል መንግስት እንዲገነዘበው ከዚህ በፊት በግልፅ ያሳወቀ ሲሆን አሁንም ፓርቲው በዚሁ የፀና አቋሙ እንደሚቀጥል በድጋሚ ይገልፃል፡፡

ባጠቃለይ የዚህን ገዢ አካል የእውር ድንብር ሀገር የማስተዳደር ጉዞ ለመታገል በርካቶች በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም በህወሓት/ኢህአዲግ ግፍና መከራ ተገፍተው ስርዓቱን በሃይል እናስወግዳለን ብለው ሀገር ጥለው የተሰደዱ ዜጎችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የህወሓት/ኢህአዲግ ማናለብኝነትና የስልጣን ጥመኝነትም በግለሰቦች ላይ ከሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ በላይ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትን አስከትሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ይህ ገዢ ፓርቲ የፈጠረው ስርዓት የሀገሪቷን ሰላማዊ የፖለቲካ ምህዳር በማጥበብ ሀገራችንን ወደ አልተፈለገ አለመረጋጋትና ቀውስ እየመራት ይገኛል፡፡ፓርቲያችንም እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም በቅርቡ እየተፈፀሙ የሚገኙ ህገ ወጥ ድርጊቶች ስላሳሰበው ይህን መግለጫ ለማውጣት ተገዷል:-

1. ሰኔ 16 2006 ዓ.ም የየመን መንግስት የዓለም አቀፍ ስምምነቶችንና ድንጋጌዎችን በመጣስና በሰው ሀገር የውስጥ ጉዳይ በመግባት የአማፂ ቡድን ግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዟ ይታወሳል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ለህወሓት/ ኢህአዴግ ተላልፈው መሰጠታቸውን ከ16 ቀናት በኋላ መታወቁና ይህንንም ሁለቱ ሀይሎች ማመናቸው ተሰምቷል፡፡ ነፃነት በሌለበት ሀገር ዜጎች ሰብዓዊ ክብራቸውን ለማስጠበቅ የሚያደርጉት ጥረት የሌሎች ሀገር መንግስታት የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በዓለም አቀፍ ስምምነቶችም ሆነ በተለይ በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ጥላ የሚያጠላ መሆኑን ግንዛቤ አለመወሰዱ እጅግ የሚያሳዝን ድርጊት ነው፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከተያዙ በኋላ ላለፉት 16 ቀናት በምን አይነት ሁናቴ እንደቆዩ ህዝብና ቤተሰቦቻቸው እንዲያውቁት አለመደረጉ፤ ስለ አያያዛቸው ሁኔታም በማህበረሰቡና በፓርቲያችን ውስጥ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዲኖር አድርጓል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሰብዓዊ አያያዝ እያሳሰበው ህወሓት መራሹ የኢህአዴግ አገዛዝ አያያዛቸውን ግልፅ እንዲያደርግ ሰብዓዊ ክብራቸውም እንዲጠበቅ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

2. በዚሁ ሳምንት ገዢው ፓርቲ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የአምባገነኑን መንግስት ህወሓት/ኢህአዲግን ሲታገሉ የነበሩ ፖለቲከኞችን በስመ አሸባሪ ከያሉበት እየለቀመ ህገ-ወጥ እስራት መፈፀሙ ይታወቃል፡፡ ህወሓት/ኢህአዲግ ይህ ግብታዊ ተግባሩ ምንም እንኳን አዲስ ባይሆንም በአሁኑ ወቅት ለውጥን ለማምጣት በቆራጥነት እየታገሉ ያሉ ሰላማዊ ታጋዮችን ማሰሩ በሀገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ፓርቲዎችን ከአማፂ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው በማስመሰል ሰላማዊ ትግሉን ለማዳከምና መጪውን 2007 ዓ/ም ምርጫ ያለ ተቀናቃኝ ለማለፍ የሚደረግ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ የፓርቲያችን ብ/ም/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሺዋስ አሰፋ በሰላማዊ ትግሉ በቁርጠኝነት እየተሳተፈ ባለበት ሁኔታ ለእስር መዳረጉ፤ የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄን በመፍጠር ላይ ያለው የአረና /ትግራይ/ ፓርቲ አመራር አባል የሆኑትን አቶ አብረሃ ደስታ ለእስር መዳረጋቸው ህወኃት/ኢህአዴግ የመጨረሻው መጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ያረጋግጣል፡፡ በመሆኑም አገዛዙ እያካሄደ ያለውን መንግስታዊ ሽብር አቁሞ ለሀገርም ሆነ ለራሱ የሚበጀውን መንገድ እንዲከተል እያሳሰብን የታሰሩት የፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡

በመጨረሻም ፓርቲያችንን መንግስት እያደረገ ያለው ሽብርን የመንዛትና ህግን የመጣስ ተግባሩ መቼም ቢሆን ከሰላማዊ ትግሉ እንደማያቆመውና ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በአፅንኦት እየገለፀ እነዚህንና ከላይ የተጠቀሱትን የገዢውን ፓርቲ መርህ አልባነት፣ ህገ-ወጥነት እና የለየለት አምባገነንነትን አሁን ካለው ነባራዊ እውነታ ጋር አጣምሮ የትግል ስልቱን ደረጃ ከፍ ወዳለ ምዕራፍ ማሸጋገር እንዳለበት አምኗል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ለምናደርጋቸው ሀገር አቀፍ ንቅናቄዎች መላው የሀገሪቱ ህብረተሰብ በንቃት ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ ጥሪውን እያስተላለፈ ለዚህም ቁርጠኛ አመራር ለመስጠት ዝግጁነቱን ለመግለፅ ይወዳል፡፡በዚህ አምባገነንነትን ለመታገል በሚደረገው ንቅናቄም በሀገር ውስጥ የሚገኙ ህጋዊና ሰላማዊ ፓርቲዎች፤አለም አቀፍ ተቋማት፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ሲቪክ ማህበራት፤ መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሰላማዊ ትግሉ ጎን በጋራ እንድንቆም እንጠይቃለን፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር

ሰማያዊ ፓርቲ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም

የአረና ትግራይ መሪ “ተይዘው ጠፍተዋል” የተቃዋሚዎቹ መሪዎች ዛሬም ፍርድ ቤት አልቀረቡም

$
0
0

ባለፈው ማክሰኞ ሐምሌ 1/2006 ዓ.ም ፖሊስ ይዣቸዋለሁ ያላቸውን የሰማያዊና የአንድነት ፓርቲዎች አመራር አባላትን ዛሬም ፍርድ ቤት አላቀረባቸውም።

የአረና ትግራይ የአመራር አባል አቶ አብረሃ ደስታ በተመሳሳይ ቀን መቀሌ ላይ በፖሊስ የተያዙ ቢሆኑም የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ፓርቲአቸው ገልጿል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ds

ፋሽስታዊ ፕሮፖጋንዳው እና ምላሻችን!

$
0
0

ፋሽስታዊ ፕሮፖጋንዳው እና ምላሻችን!( pdf )

ሐምሌ 3 ቀን 2006 ዓ.ም.

Ginbot_7_Logo_Lዘረኛውና ፋሽስታዊ ወያኔ፣ የኢትዮጵያዊያንን የትግል መንፈስ ለመስበር እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነትና ለፍትህ የሚያደርገውን ትግል ወኔ ለመስለብ ያቀደበትን የመጀመሪያውን ፕሮፖጋንዳ ለቀቀ። የህግ ልጓም የማያውቀው ፋሽስት በግፍ የያዛቸውን ሰዎችን እይስሙላው ፍርድ ቤት እንኳን ከመቅረባቸው በፊት “ወንጀለኛ” እያለ እንዲህ ዓይነቱ ፕሮፖጋንዳ እንደሚነዛባቸው ተደጋግሞ የታየ በመሆኑ ይህ ፕሮፖጋንዳ የሚጠበቅ ነበር። ሆኖም ግን ፕሮፖጋንዳው ያዘጋጁ ሰዎች ተስፋ ያደረጉትን ውጤት ያመጣ አልሆነም። ወደፊት ደግሞ ሌሎች ሙከራዎች ይደረጉ ይሆናል፤ ውጤታቸው ግን ከዚህኛው የተለየ እንደማይሆን ይገመታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኢቲቪ የእውነት ጥፍጣፊ እንኳን እንደማይገኝ ያውቃል።

በአሁኑ ተቆራርጦ በተለጣጠፈ ፊልም በታጀበው ፕሮፖጋንዳ ውስጥ፣ መሪያችን አንዳርጋቸው ጽጌ በምግብና ውሀ እጦት ብቻ ሳይሆን በተፈጸመበት የተለያዩ የማሰቃያ ወንጀሎች ብዛት አካሉ መዳከሙ ይታያል። ያም ሆኖ ግን ከእሱ ወጥተው እንድንሰማቸው የተደረጉት ቃላት የመንፈሱን ጥንካሬ ገላጮች ናቸው። እሱ ሥራውን መጨረሱንና በዚህም ምክንያት ህሊናው የተረጋጋ መሆኑን ነው የሰማናቸው ቃላት የነገሩን። በዚህ አጭር አጋጣሚ እሱ ግዴታውን ማጠናቀቁ፤ ሀገራችን ከወያኔ ፋስሽቶች ነፃ የማውጣት ኃላፊነቱ በእኛ ትከሻ ላይ መውደቁን ነገረን። ለዜናው ማጀቢያነት የገቡት ፎቶግራፎችም መሪያችን ፈታኝ በሆነ የተፈጥሮ አካባቢ የከፈለውን መስዋዕትነት የሚመሰክሩ ሆነው ተገኙ።

ጀግናው አንዳርጋቸው ጽጌን በተጎሳቆለ ሁኔታ ማየት ስሜትን የሚጎዳ ቢሆንም የመጀመሪያው ስሜት ካለፈ በኋላ ከፊልሙ በአዕምሮዓችን የሚቀረው ከላይ በአጭሩ የተገለፁት ጥንካሬውና ኃላፊነትን ወደ እኛ በይፋ ያስተላለፈበት አጋጣሚ መሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተሠራው የመጀመሪያ በምስል የተደገፈ የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ከታለበት ዓላማ በተፃራሪ የወያኔን ሹማምንት አውሬነትና የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ትልቅነት አሳይቷል።

ይሁን እንጂ ከላይ እንደተገለፀው ይህ የመጀመሪያ የፕሮፖጋንዳ ሥራ እንጂ የመጨረሻው አይደለም። የማስተዋል ችሎታ ያነሳቸው የወያኔ ፕሮፖጋንዲስቶችም ፊልማቸው ቁጣን ማባባሱ ሲያዩ ፈጥነውም ይሁን ዘግይተው ከዚህ በተለየ አቀራረብ መመለሳቸው አይቀርም። ስለሆነም የኢትዮጵያን ሕዝብ ከወያኔ የጅል ፕሮፖጋንዳ መንፈሱን እንዲጠብቅ ማሳሰብ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። የወያኔ ፕሮፖጋንዲስቶች አሁን የደረሰባቸውን ኪሳራ ለማካካስ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያላለውን አለ ይሉን ይሆናል፤ ቃላትን ፈጥረው እሱ የተናገራቸው ያስመስሉም ይሆናል። የቻይና ቴክኖሎጂ ከወያኔ ድድብና ጋር ሲደባለቅ ምን እንደሚያመጣ አስቀድሞ መገመት ያዳግታል። ኢቲቪ ለዘመናት የተካነበትን ውሸት የመፈብረክ ክህሎትን ወደ ላቀ ደረጃ የማሳደግያ አጋጣሚ አድርጎ ሊጠቀምበት ስለሚችል መንፈሳዊ ዝግጅት ማድረግ ተገቢ ነው።

ከዚህ በተረፈ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጥብቅ ሊያስብበት የሚገባ ጉዳይ አለ።

ጀግናው፣ ብልሁና አስታራቂው አንዳርጋቸው ጽጌ ኢትዮጵያን በማጥፋት ዓላማ ባበሩ፤ ዘርፈውና በልተው በማይጠግቡ፤ የንፁሃንን ደም መጠጣት በለመዱ ዘረኞችና ፋሽስቶች መዳፍ ውስጥ ነው። ለዚህ ምላሻችን ምንድነው? ገና ከአሁኑ እንደታየው በሰላማዊ መንገድ ሥርዓቱን ለመገዳደር የደፈሩ ወጣቶችን ለማሰር አንዳርጋቸው ጽጌን ሰበብ ሲያደርግ የኛ ምላሽ ምንድነው? አገራችን ያፈራቻቸው ምርጥ ዜጎች በሙሉ ወይ ታስረው አልያም ተሰደው ሲያልቁ እያየን ምን እየሠራን ነው? ነፃነታችንና አገራችን ለህወሓት ዘረኞች አስረክበን እንቀመጣለን? በጭራሽ!

አንዳርጋቸው ጽጌ የተመቻቸ ኑሮዉንና ልጆቹን ጥሎ ለነፃነቱና ለሀገሩ የዘመተ ጀግና ነው። ከእኛም የሚፈለገው ይህንኑ ነው። ጀግናችንን ብቻ ሳይሆን አገራችንም ጭምር ከታሰረችበት ማስፈታት የምንችለው አንዳርጋቸው ጽጌ በተጓዘበት መንገድ ስንጓዝ ነው። ለዚህ የተዘጋጀ ሁሉ “አለሁ!” ይበል።

ማንም ዝርዝር መመሪያ በሬድዮ ወይም በቴሌቪዥን እንዲነገረው አይጠብቅ። የቆረጠና የመረረው ጀግኖች የሚገኙበት ድረስ ሄዶ ይቀላቀል። ከልቡ የቆረጠና ጥቂት ፍለጋ ያደረገ ሁሉ መንገዱን አያጣም።

  1. ቀደም ሲል ንቅናቄዓችን – ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ – ያወጣውን የመጀመሪያ እርከን የትግል ጥሪ ተግባሪዊ ለማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በቁርጠኝነት በተግባራዊ ትግልቶች ይመንዘሩት፤
  2. የተቆጣ፣ ጥቃት፤ ውርደት፤ ግፍ የመረረው ሁሉ፤ ለነፃነቱ ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የስነ ልቦና ዝግጅት ያድርግ፤ ከወያኔ ሰላዮች ራሱን ተከላክሎ በያለበት በጥብቅ ከሚያምናቸው ጋር በመሆን በየአካባቢው በቡድን በቡድን ይደራጅ፤ በወያኔ ቀንደኛ ሹሞችና ወንጀለኞች ላይ ይሰልል፤ መረጃዎችን ለንቅናቄዓችን ይላክ።
  3. በየአካባቢያችን የወያኔን ፋሽስቶችን የሚያሸማቅቁ፣ በሁለተናዊ መልኩ (በስነልቦና፤ ማኅበራዊ ተጽዕኖ በመፍጠር፣ በኢኮኖሚ) ጉልበታቸውን የሚቦረቡሩ፣ የሚያድክማቸው፣ ውስጣቸውን የሚሸረሽራቸው ሥራዎችን በቁጭትና በእልህ ሳናሰልስ ተግባራዊ እናድርግ።
  4. በሕዝብ ጎራ ሳይሆን በጥቂቶቹ በወያኔ ፋሽስቶች ጎራ ፍርሃትና ብርክ የሚፈጥሩ የጀግንነት ሥራዎችን በቡድን በመደራጀት በመላው ዓለምና በኢትዮጵያ ውስጥ በብልሃት፣ በጥናትና በስልት በመተግበር ሕዝባዊ እምቢተኝነት እሁን እናድርግ፡፡
  5. ሁሉም ኢትዮጵያዊን የሚቻለውን ሁሉ ትንሿንም ጠጠር ብትሆን ወያኔና ጭፍሮቹ ላይ እንወርውር።
  6. በደጀን የተሰለፈው ኃይል ደግሞ የዘማቹን ስንቅ በማዘጋጀት በገንዘቡ፤ በጉልበቱ፤ በመረጃ ይተባበር።

የአገር ማዳን የክተት ዘመቻ ላይ ነንና በእያንዳንዱ ጉዳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሳንጠብቅ ቀበቶዓችንን አጠባብቀን እንነሳ። ድል እናደርጋለን!! አገራችን ከዘረኞችና ፋሽስቶች መንጋጋ መንጭቀን እናወጣታለን!!

ድል ለኢትጵያ ሕዝብ !!

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ

አቶ ብዙነህ ፅጌ (የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ወንድም) ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ

$
0
0

በኢትዮጵያ መንግሥት የተያዙት ወንድማቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ያገኛሉ ብለው እንደማያምኑ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ወንድም አቶ ብዙነህ ፅጌ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡

አቶ ብዙነህ ፅጌ (የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ወንድም) ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ – ዘገባ

በኢትዮጵያ መንግሥት የተያዙት ወንድማቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ያገኛሉ ብለው እንደማያምኑ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ወንድም አቶ ብዙነህ ፅጌ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አቶ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት የሚገባቸውን ይቀበላሉ ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን ለፈረንሣይ ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

አቶ ብዙነህ ፅጌ የአቶ አንዳርጋቸው ታናሽ ወንድም ብቻ ሳይሆኑ ከለጋነት ዕድሜአቸው ጀምሮ በፖለቲካው ሕይወት አብረው የዘለቁ፤ የቅርብ የሃሣብ ተካፋይና አጋርም ናቸው፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ባለፈው ሰኔ 16/2006 ዓ.ም ሰንዐ – የመን ላይ በፀጥታ ኃይሎች ተያዙ ከተባለ በኋላ ሲጠፉ ዜናውን ቀድመው ለንደን ላይ የሰሙት አቶ ብዙነህ ነበሩ፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውንና አቶ ብዙነህ ፅጌ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ የያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

Andargachew

ዓረና-መድረክ በራያ አዘቦ “ዘመቻ አብረሃ ደስታ”በሚል ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ

$
0
0
(አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)

(አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)

ዓረና-መድረክ እሁድ  ሐምሌ 06 2006 ዓ/ም በራያ ዓዘቦ ወረዳ ሞኾኒ ከተማ “ዘመቻ ኣብረሃ ደስታ” የሚል መፎክር ያለበት ህዝባዊ ስብሰባ ያካሂዳል።

ዓረና-መድረክ ፖሊሲው፣ ስትራተጂውና ኣማራጭ ሃሳቡ ከራያ ዓዘቦና ኣከባቢው ህዝብ ለመወያየትና ለማስተዋወቅ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርተዋል።

ዓረና-መድረክ የሃገራችን የፍትህ፣ ዲሞክራሲ፣ መልካም ኣስተዳደር፣ ሁላቀፍ ልማት፣ የሚድያ ነፃነት፣ ወዘተ ተግዳረቶች በማቅረብ ለነዚህ ችግሮች መፍትሄ ኣማራጭ ሃሳቦች በማቅረብ ወደፊት ሃገራችን የምትመራበት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ምን መምሰል እንዳለበት፣ ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር እውን የሚሆንበት ኣግባብ፣ ባለፈው 17 የትጥቅ ትግል የተከፈለ መስዋእትነትና በኣሁኑ ሰዓት የተገኘው ለውጥ ምን እንደሚመስል ከራያ ህዝብ እንወያያለን።

ጀግናው የራያ ህዝብ የጀንነትና የጀግና ኣድናቂ ነው። የዚህ ህዝባዊ ስብሰባ መጠርያም የኣዲሱ ትውልድ ጀግና የሆነው “ኣብራሃ ደስታ” እንዲሰየም ተደርጓል። ስለዚህ “ዘመቻ ኣብራሃ ደስታ” ከራያ ህዝብ ጋር ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ የምንወያይበትና ኣብረን የምንታገልበት መድረክ ይሆናል።

የዓረና ስራ ኣስፈፃሚ ኣባል የሆነው ኣብራሃ ደስታ በኣሁኑ ሰዓት በኣዲስ ኣበባ ማእከላዊ በመባል የሚታወቀው ማረሚያ ቤት እንደሚገኝ ምንጮች ገልፀዋል።

ዓረና የኢትዮዽያ መንግስት ስለ ኣብራሃ ደስታ ሁኔታ እንዲያስታውቀን እናሳስባለን።

የራያ ዓዘቦና ኣከባቢው ህዝብ በሞኾኒ ህዝባዊ ኣዳራሽ ተገኝቶ ኣማራጫችን እንዲሰማና ሃሳቡን ቢያካፍለን እንላለን።

ነፃነታችን በእጃችን ነው…!!!
“IT IS SO”

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live