Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

(ሰበር ዜና) ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የመን አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፋ ስለመስጠቷ ተናገሩ (ቪድዮውን ይዘናል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሳንሆዜ ካሊፎርኒያ በአሁኑ ሰዓት እየተከበረ በሚገኘው የኢሳት 4ኛ ዓመት በዓል ላይ የተገኙት የግንቦት 7ቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለአንዳርጋቸው ጽጌ ተላልፎ መሰጠት ጉዳይ ተናገሩ። ዘ-ሐበሻ ቪድዮውን ቀርጻዋለች ይመልከቱት።
“አንዳርጋቸውን የምትወዱ ከሆነ አታልቅሱ፤ ለትግል ተነሱ”


Andargache&Birhanu


ነርሷ የአቶ አንዳርጋቸውን ፍቶ ግራፍ ለመጫረት የ$4000 ዳይመንዷን ሰጠች

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሳንሆዜ ካሊፎርኒያ እየተደረገ ባለው የኢሳት 4ኛ ዓመት በዓል ላይ ነርስ መቅደስ ሰይፉ የመን ለኢትዮጵያ አሳልፋ የሰጠችውን የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸውን ፎቶ ግራፍ ለመጫረት $4000 ዶላር የሚገመተውን ዳይመንድ ሰጠች።

ሃግሬ ሆኜ የሃገሬን ሕዝብ ባክም እመርጣለሁ የምትለው ነርስ መቅደስ ሰይፉ የመን አቶ አንዳርጋቸውን ለኢትዮጵያ መንግስት መስጥቷ አንዳስቆጣት ገልጻለች። ዳይመንድ ቀለበቶቿን አውልቃ በጨረታ ለመግዛት ያነሳሳትም ይኸው ጉዳይ እንደሆነ አስታውቃለች።

ቀለበቱና የነርሷ ፎቶ ከነባለቤቷ ይኸው።
andargachew tisge kelebet

kelebet adnargachew

አሳዛኝ ዜና! (አብርሃ ደስታ)

$
0
0

አብርሃ ደስታ

Abrha Destaየሐውዜን ህዝብ እንደገና በህወሓት እየተጨፈጨፈ ነው። “ዓረና ነህ፤ ስምህ በዓረና መዝገብ ተገኝቷል” እያሉ ሰለማዊ ሰዎችን እያስፈራሩ ለህወሓት ይቅርታ ጠይቆ እንዲመለስ እያስጠነቀቁ ካልተሳካ ደግሞ በዱላ እየደበደቡ፣ በድንጋይ እየወገሩ፣ ጥያቄ ለሚያነሳ ሰው በፖሊስ እያሳሰሩ፣ ቤቱ እየፈተሹ ይገኛሉ። አንዳንድ በሐውዜን የሚገኙ ሙሁራን “ዳግማይ ጭፍጨፋ” ብለውታል። ዓረና ይህን ተግባር ይቃወማል።

የዓረና አባላት ያልሆኑ ሰዎች ስማቹ ተገኝቷል እየተባሉ የሚሰቃዩበት፣ ስም ዝርዝር ያልላከ ዓረና ስሙ የሚጠፋበት ስርዓት ተፈጥሯል። ደግሞ ዓረና ህጋዊ ፓርቲ አይደለም እንዴ? ሰው ዓረና የመሆን መብት የለውም እንዴ? የሐውዜን ህዝብ የዓረና አባልና ደጋፊ የመሆን መብት የለውም? የዓረና አባል ተብሎ እንዴት ይንገላታል? እንዴት ይታሰራል? የዓረና አባል መሆን ወንጀል መስራት ነውንዴ? ዓረና’ኮ ህጋዊ ፓርቲ ነው።

የህወሓት ስጋት ምን ያህል እንደሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላል። የሐውዜን ህዝብ ግን ዳግም እየተጨፈጨፈ ነው። ለህዝብ ካልቆምን ለማን ልንቆም ነው። ወይስ የሐውዜን ህዝብ ሊጨርሱት ፈልገዋል?! እንደ የሰኔው 15, 1980 ዓም ሙከራ!?

ህወሓት ግን ሰፈሩ የበላሹሎ!

https://www.facebook.com/abraha.desta2?fref=nf

ግንቦት 7 የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለወያኔ ፋሽስቶች አሳልፋ መስጠቷን በማስመልከት መግለጫ አወጣ

$
0
0

የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለወያኔ ፋሽስቶች አሳልፋ መስጠቷን በማስመልከት የወጣ መግለጫ

Ginbot_7_Logo_Lሰኔ 27 ቀን 2006 ዓ.ም

የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ለሥራ ጉዳይ  በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ  ታግቶ መቆየቱ ማስታወቃችን ይታወሳል።  [ሙሉውን መግለጫ  ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

‹‹ፍትህ ይስፈን ንፁሀን ይፈቱ›› የሚሉ ዜጎችን ማሰር የኢፍትሃዊነት ትልቁ ማሳያ ነው! አንዋር አካባቢ ሰግደው የሚመለሱትን ፖሊሶች ለመያዝ እያዋከቡ ነው

$
0
0

muslim 1

muslim 3 addis ababa
አርብ ሰኔ 27/2006

ከሳዲቅ አህመድ

‹‹ፍትህ ይስፈን ንፁሀን ይፈቱ›› የሚሉ ዜጎችን ማሰር የኢፍትሃዊነት ትልቁ ማሳያ ነው! አንዋር አካባቢ ሰግደው የሚመለሱትን ፖሊሶች ለመያዝ እያዋከቡ ነው!

ሀ/ጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ ፖሊሶች ከደህንነቶች ጋር ሆነው በሰላማዊ ሁኔታ ተቃውሞ አሰምቶ ሲመለስ የነበረውን ህዝብ በመተንኮስ ወደ አላስፈላጊ ሁኔታ ለማስገባት ያደረጉት ጥረት በህዝቡ ሰላማዊነት ምክንያት ሊከሽፍ ችሏል።አንድ ሰው ይዘው የነበረ ሲሆን ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ተደራድሮ አስለቅቆታል።

‹‹አፈና፣ ግፍና ማስገደድ ይቁም!›› በሃይማኖታችን እና በዜግነት መብታችን ላይ የሚደርሱ የመብት ጥሰቶችን የሚገልፅ ብርቱ መፈክር

አርቲስት ዳምጠው አየለ አረፈ

$
0
0

Damtew-Ayele
(ዘ-ሐበሻ) በስደት ለረጅም ዓመታት በኖርዌይ የቆየው ዝነኛው የባህል ሙዚቃ ተጫዋች አርቲስት ዳምጠው አየለ አረፈ።

በስደት በሚኖርባት ኖርዌይ ላለፉት ጥቂት ወራት በሕመም ሲሰቃይ የከረመው አርቲስት ዳምጠው ህመሙ ሲጠናበት ወደ ሃገር ቤት በኢትዮጵያውያን ድጋፍ የተላከ ሲሆን ከቤተሰቦቹ ጋርም ጁን 16 ቀን 2014 ከስምን የስደት ዓመት በኋላ ተገናኝኝቶ ነበር።

የሃገር ፍቅር ስሜት በውስጡ ያለው ይኸው ድምጻዊ በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ህክምና ሲከታተል እንደነበር የገለጹት የዘሐበሻ ምንጮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመኖሪያ ቤቱ ሲታከም የነበረ ቢሆንም ወደማይቀረው ዓለም ይህችን ምድር ተሰናብቷል።

ዘ-ሐበሻ በአርቲስት ዳምጠው አየለ ሕልፈት የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ትገልጻለች።

‹‹ፍትህ ይስፈን ንፁሀን ይፈቱ›› የሚሉ ዜጎችን ማሰር የኢፍትሃዊነት ትልቁ ማሳያ ነው! አንዋር አካባቢ ሰግደው የሚመለሱትን ፖሊሶች ለመያዝ እያዋከቡ ነው

$
0
0

አርብ ሰኔ 27/2006

ከሳዲቅ አህመድ

‹‹ፍትህ ይስፈን ንፁሀን ይፈቱ›› የሚሉ ዜጎችን ማሰር የኢፍትሃዊነት ትልቁ ማሳያ ነው! አንዋር አካባቢ ሰግደው የሚመለሱትን ፖሊሶች ለመያዝ እያዋከቡ ነው!

ሀ/ጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ ፖሊሶች ከደህንነቶች ጋር ሆነው በሰላማዊ ሁኔታ ተቃውሞ አሰምቶ ሲመለስ የነበረውን ህዝብ በመተንኮስ ወደ አላስፈላጊ ሁኔታ ለማስገባት ያደረጉት ጥረት በህዝቡ ሰላማዊነት ምክንያት ሊከሽፍ ችሏል።አንድ ሰው ይዘው የነበረ ሲሆን ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ተደራድሮ አስለቅቆታል።

‹‹አፈና፣ ግፍና ማስገደድ ይቁም!›› በሃይማኖታችን እና በዜግነት መብታችን ላይ የሚደርሱ የመብት ጥሰቶችን የሚገልፅ ብርቱ መፈክር

በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታገትና ለወያኔዎች ተላልፎ መሰጠት ለተቀዋሚዎች የማንቂያ ደውል ነው

$
0
0

(ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌ)

የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው በየመን መታፈንን ከሰማን ጊዜ ጀምሮ አብዛኛው ሀገር ወዳድና የኢትዮጵያን የነጻነት ቀን ናፋቂ ወገኖችን ያሳሰበና እረፍት የነሳ ጉዳይ እንደሆነ በየቀኑ በየማህበራዊ ድህረ ገጽ ከሚወጡት ነገሮች መረዳት እንችላለን :: በርግጥ ወያኔ በስልጣን በቆየባቸው በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች ብዙ የተማሩ ኢትዮጵያን ሙህሮች፣ ብዙ የፖለቲካ ሰዎች በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ ለብዙ ነገር ሰላባ ሲሆኑና ህይወታቸውን እስከሚያጡ ድረስ ሆነዋል :: ሰሞኑን ግን በነጻነት ታጋያችን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ በየመን የደረሰው እገታና ለነብሰ በላው የወያኔ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱ እውን እንደሆነ ስሰማ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በእኔም ላይ በጣም ከባድ የሆነ የሀዘን መንፈስ የፈጠረብኝ ሲሆን በወያኔ መንግስት ላይ ያለኝን ጥላቻ ይበልጥኑ ከፍ እንዲል ያደረገ ክስተት ሆኖል እንዳርጋቸው ወደ ትግል ሲገባ እራሱን ለሞት በማዘጋጀት ሊደርስበት ያለውን ማንኛውንም መሰዋትነት ለመክፈልና ሁሉንም መከራ ለመቀበል ዝግጅነቱን በማሳየት እንደሆነ ከሚሰራቸው ስራዎች መረዳት ይቻላል ::በርግጥ እውነተኛ ትግል መስዋህትነትን እንደሚያስከፍል ባውቅም የእኝህ እድሜያቸውን በሙሉ ለነጻነት ሲታገሉ የኖሩ የነጻነት ታጋይ ላይ የደረሰው ነገር ግን በውስጤ ሁለት ነገሮችን ጭሮብኛል ያለፈ ሲሆን አንድን ነገር ግን እንዳውቅ ረድቶኛል:: አንዱ እንዳርጋቸው ቢታሰርና የፈለገው ነገር በእሱ ላይ ቢደርስ እንኮን ለወያኔዎች የእግር እሳት የሆኑ እንዳርጋቸው የወለዳቸው ብዙ ሚሊዩኖች የነጻነት ታጋዮች ኢትዮጵያኖች በየስፍራው ተወልደዋልና ደስ ይለኛል::

Photo: የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው በየመን መታፈን ሁላችንንም ኢትዮጵያኖችን የወያኔን መሰሪነት አውቀን በቁጣ በወያኔ መንግስት ላይ መነሳት ይገባናል ::የወያኔ መንግስት እሱን በሚቃወሙ ባሉ ሰዎች ላይ ሁሉ እየወሰዳቸው ያለው በግፍ የተሞሉ እርምጃዎች ምን ያህል አንባገነን መንግስት እንደሆነ አመላካች ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን መታፈንም አመላካች ሲሆን በወያኔ ሴራ የተቀነባበረ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም :: የወያኔ መንግስት ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር በነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ላይ የሆነው ነገር የኢትዮጵያን ሕዝብና ተቃወሚዎችን ይበልጥ የሚያጠነክርና ለትግል ይበልጥኑ እንዲነሳሱ የሚያደርግ መሆኑ ነው:: የእንዳርጋቸው በየመን መታሰር ለተቃዋሚ መሪዎች ሊያነቃቸው ያለ ትልቅ ደውል የተደወለ ነው የሚመስለኝ :: በሀገርም ውስጥ በውጭም ያሉ የተቀዋሚ ድርጅቶች አንድ በመሆንና በመተባበር ልዮነታችንን ወደ ጎን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብንም  በማስተባበር በጋራ ጠላታችን ላይ በመዝመት ይሄን አረመኔ መንግስት ለማስወገድ በጋራ እንናሳ::  ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ውድቀት ለወያኔ!!

Photo: የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው በየመን መታፈን ሁላችንንም ኢትዮጵያኖችን የወያኔን መሰሪነት አውቀን በቁጣ በወያኔ መንግስት ላይ መነሳት ይገባናል ::የወያኔ መንግስት እሱን በሚቃወሙ ባሉ ሰዎች ላይ ሁሉ እየወሰዳቸው ያለው በግፍ የተሞሉ እርምጃዎች ምን ያህል አንባገነን መንግስት እንደሆነ አመላካች ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን መታፈንም አመላካች ሲሆን በወያኔ ሴራ የተቀነባበረ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም :: የወያኔ መንግስት ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር በነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ላይ የሆነው ነገር የኢትዮጵያን ሕዝብና ተቃወሚዎችን ይበልጥ የሚያጠነክርና ለትግል ይበልጥኑ እንዲነሳሱ የሚያደርግ መሆኑ ነው:: የእንዳርጋቸው በየመን መታሰር ለተቃዋሚ መሪዎች ሊያነቃቸው ያለ ትልቅ ደውል የተደወለ ነው የሚመስለኝ :: በሀገርም ውስጥ በውጭም ያሉ የተቀዋሚ ድርጅቶች አንድ በመሆንና በመተባበር ልዮነታችንን ወደ ጎን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብንም
በማስተባበር በጋራ ጠላታችን ላይ በመዝመት ይሄን አረመኔ መንግስት ለማስወገድ በጋራ እንናሳ::
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ውድቀት ለወያኔ!!

አሁን ላይ ነገሮች ሁሉ የተቀየሩ ነው የሚመስለው የአቶ እንዳርጋቸው ጉዳይ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ከመሆን አልፏል :: በአሁኑ ሰአት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ እና የአመለካከት ልዩነቱን ወደ ኋላ በመተው እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል ቃል ጉዳዮን በንቃት እየተከታተለው ሲሆን የታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መያዝና በወያኔ እጅ ላይ መውደቅ ለአንዳንድ ሆድ አደር ወያኔዎች ብቻ ፈንጠዝያ የፈጠረና ያስደሰተ ቢመስልም ብዙ ኢትዮጵያ ወገኖችን ግን ከሌላዉ ጊዜ በተለየ መልኩ በእልህና በቁጭት ለትግል እንዲነሳሱ ያደረገ ክስተት እንደሆነ በፊስ ቡክ በውስጥ መልክት ከሚደርሰኝ ደስ የሚልና የሚያበረታታ ጽሁፍ ለመረዳት ችያለው::

ድርጊቱ ለተቃዋሚዎች የማንቂያ ደውል መሆን ይገበዋል ለነጸነት እንታገላለን የሚሉ ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ለነጻነት እየታገልን ያለን ኢትዮጵያኖች የወያኔን መሰሪነት አውቀን ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ በቁጣ በወያኔ መንግስት ላይ መነሳትና በወያኔ ላይ ያለንን የከረረ ጥላቻ በእንቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ ልንገልጽ ይገባናል ::የወያኔ መንግስት ስልጣኑን በሀይልና በጉልበት ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ እሱን በሚቃወሙ ባሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ ሁሉ ይኼው አረመኔው የወንበዴ ስብስብ እየወሰዳቸው ያለው በግፍ የተሞሉ እርምጃዎች ምን ያህል አንባገነን መንግስት እንደሆነ አመላካች ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን መታፈንም የዚሁ አመላካች ነው::ዛሬ ላይ የአንዳርጋቸው መታፈን በርግጥ የወንበዴዎችን ቡድን ጮቤ እያስረገጣቸው እንደሆነ አስባለው የወያኔ መንግስት ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር በነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ላይ የሆነው ነገር የኢትዮጵያን ሕዝብና ተቃወሚዎችን ይበልጥ የሚያጠነክርና ለትግል በጥንካሬ እንዲነሳሱ የሚያደርግ መሆኑ ነው:: የእንዳርጋቸው በየመን መታገትና በወያኔዎች የተቀነባበረ ሴራ ለወያኔዎች ተላልፎ መሰጠት የየመንን መንግስት ባደረገው ከህግ ውጭ የሆነ አሳፋሪ ድርጊት ለወደፊት የታሪክ ተወቃሽ የሚያደርገው ቢሆንም የመኖች በሰሩት ስራ ወደ ፊት ተጠያቂ እንደሚሆኑበት ምንም ጥርጥር የለኝም::ዋናው መታወቅ ያለበት ግን ድርጊቱ ለተቃዋሚ መሪዎች ትልቅ የቤት ስራ የሰጠና ሊያነቃቸው ያለ ደውል የተደወለ ነው የሚመስለኝ ::

በሀገርም ውስጥ በውጭም ያሉ የተቀዋሚ ድርጅቶች በስሜትና፣ በደመነብስ የምንጓዝበት ዘመን ያብቃ፣ እየሰራን ያለውንም ስራ እንመርምር ፣እንንቃ የወያኔን መሰሪ ሴራ ለማክሸፍ አንድ በመሆንና በመተባበር ልዮነታችንን ወደ ጎን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብንም በማስተባበር ነጻነታችንን ህውን ለማድረግ በጋራ ጠላታችን ላይ በመዝመት ይሄን አረመኔ መንግስት ለማስወገድ በጋራ እንናሳ::

በመጨረሻም ለወያኔዎች የማስተላልፈው መልእክት ቢኖር እውነተኛ ታጋይ ሊታሰር ሊሞትም ይችላል የተጀመረውን ትግል ግን ልታስሩትም ሆነ ልትገሉት ከቱ አትችሉም ::ኢትዮጵያ አንድ እንዳርጋቸው ብቻ ሳይሆን ሚሊዮን እንዳርጋቸው ፈጥራለችና በከንቱ አትደከሙ:: ወደዳችሁም ጠላችሁም የእንዳርጋቸውን ፈለግ በመከተል ሁላችንም የነጻነት ታጋዮች ነን!!!

አቶ አንዳርጋቸው አምላክ ከአንተ ጋር ይሁን

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
gezapower@gmail.com


አቶ አንዳርጋቸው “ለኢትዮጵያ መንግሥት ተሰጡ” ሲል ግንቦት ሰባት አስታወቀ (VOA Amharic)

$
0
0

የየመን መንግሥት የግንቦት ሰባትን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ ሰጥቷል ሲል ግንቦት ሰባት አስታውቋል፡፡

ግንቦት ሰባት በዌብ ሳይቱ ላይ ባሠፈረው መግለጫ “የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቶ መቆየቱ ማስታወቃችን ይታወሳል።” ብሏል፡፡

ግንቦት ሰባት ይቀጥልና “የየመን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ያገተብንን የንቅናቄዓችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም – ይልና – የአገሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም ማየት የተሳነው የየመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ አምባገኑን ወያኔ መርጦ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል።” ብሏል፡፡ “በዚህም ሳቢያ – ይላል የግንቦት ሰባት መግለጫ – የየመን መንግሥት ይቅርታ የማያሰጥ፤ ዘመን የማይሽረው ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወዳጅ ጎረቤት ትሁትና ቀና ቢሆንም ጥቃት በሚያደርስበት የቅርብም ሆነ የሩቅ ጎረቤት ላይ ግን ቁጣውን የሚመጥን የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ያውቅበታል።”

ግንቦት ሰባት ያወጣውን ሙሉውን መግለጫ ለማየት ከሥር የተያያዘውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ፡፡
DEA54BEE-2996-4145-A17A-2842A121CD0E_w640_r1_s

የሕዝባዊ ስብሰባ ጥሪ ለሚኒሶታ ኢትዮጵያውያን ሁሉ!

$
0
0

ኢትዮጵያውያንን በመግደል፣ በማሰር ፣ ሰብአዊ መብታቸውን በመርገጥ፣ በማስረብ እንዲሁም በዘር፣ በጎሳ ፣ በእምነት ፣ በመከፋፈል በሥልጣን የሚገኘው የወያኔ መንግሥት የለመደበትን የክፍፍል ድርጊት ለመፈጸም በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ መዕካሎች ላይ ማለትም የእምነት ፣ የማሕበረሰብና የእስፖርት ቦታዎች ላይ ትኩረት በመሰጠት ሥራውን እያካሄደ ይገኛል። በዚህም ውጥኑ መሰረት በሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያውን ለ31 ዓመታት በመሰብሰብ የእግርና ፣ የቅርጫት ኳሶች ጨዋታና የባሕል ፌስቲባል የሚያካሔዱትን በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽንን ለመክፈል ለሶስት ዓመታት በተከታታይ (ከ2004-2006ዓ.ም)ጥረት ቢያደርግም በኢትዮጵያውያን ተቃውሞ የክፍፍል ሴራው ከሽፎ በሔዱበት ቦታ ሁሉ ተመልካች በሌለበት በገንዘብ የገዙ ተጫዋቾችና ዳኞች ብቻ ውርውር የሚሉበት ባዶ እስታድየም ይዘው ቀርተዋል። ለዛንድሮ ሙክራቸው ሚንሶታን ምርጫቸው አድርገው በሚኒሶታ ሕዝብ ተቃውሞ ባዶ ስታድየም ይዘው ለመቀመጥ ተገደዋል። ገንዘብ በመስጠትና በመደለል እስታደየሙ ውስጥ ሱቆች የሚከፍቱ ( Venders) ፣ ምግብ የሚሸጡ ሰዎችን ለመግኘት ቢሞክሩም አልተሰካላቸውም። ከፍ ያለ ምስጋና ለሚኒሶታ ሕዝብ እናቀርባለን።

በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚታገዘው የወያኔ መንንግሥት የፖለቲካ ተቃዋሚዎችንና ሌሎች ኢትዮጵያዉያንን ከውጭ መንግሥታት በተለይም ከሱዳን፣ ከሳውዲ-አረቢያና ከየመን ጋር በማበር ሲያስገድል ፣ ሲያስዝና ሲያሳፍን ቆይቷል። ከሰሞኑም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የግንቦት 7 ዋና ጻሐፍን የየመን መንግሥት ከስናዓ አይሮፕላን ጣቢያ ወደ ሌላ ሶስተኛ አገር ትራንዚት ከሚያደርጉበት ጓዟቸውን አሳናክሎ በጸጥታ ኃይሎቹ በመያዝና በማሳር ካጉላሏቸው በኋላ ለወያኔ መንግሥት አሰልፎ ሰጥቷቿዋል። ይህን የዓለም አቀፍ ሕግን የተላለፈ የየመን መንግሥት ሕገወጥ ድርጊት ለማውገዝና ለወደፊትም በጋራ ሆነን በዚህ ጉዳይና በአካባቢያችን የወያኔ ሰላዮችና ከፋፈዮች የሚፈጽሙትን ደባ ለመከለከልና ለመመከት ሕዝባዊ ስብሰባ የተዘገጃ ስለሆነ በስብሰባው እንዲሳተፉ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።

 

ቦታ (Place) : 1821 University Ave   2nd floor ( Fairview & University)

Saint Paul, MN 55104 

ቀን ( Date) : እሑድ ሰኔ 29, 2006 ዓ.ም   ( Sunday, July 6, 2015 )

ሰዓት (Time) ፡ ከሰዓት በኋላ 9፡00 ሰዓት( 3፡00pm )

በሚኒሶታ የተቋቋመው ግብረኃይል

 

IMG_0371

አዜብ መስፍን በጠና ታመዋል፤ የአባዱላ ገመዳ ልጅ አረፈ – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ ከፖለቲካው መድረክ እየተገለሉ የመጡት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በጠና መታመማቸውን ቅርበት ያላቸው ታማኝ ምንጮች አስታወቁ። በስኳር ህመምና በደም ግፊት እየተሰቃዩ የሚገኙት አዜብ መስፍን የሰውነት ክብደታቸው እንደቀነሰና የመጎሳቆል ሁኔታ በገጽታቸው እንደሚታይ የጠቆሙት ምንጮቹ ለስኳር በሽታ በየእለቱ ከሚወስዱት መድሃኒት በተጨማሪ ለደም ግፊትም እንክብሎችን እንደሚወስዱ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። አዜብ በመኖሪያቸው አብዛኛውን ቀናት እንደሚያሳልፉ የጠቆሙት ምንጮቹ በፖለቲካው የደረሰባቸው ኪሳራ ብስጭት ውስጥ እንደከተታቸውና ለበሽታ እንደዳረጋቸው አያይዘው ገለጸዋል።

ቦሌ ከሳይ ኬክ ቤት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኘውና አቶ ስዩም መስፍን ለ19ዓመት የኖሩበት እንዲሁም አቶ ሙክታር ከድር ለሁለት አመት የኖሩበት መኖሪያ ቪላ ውስጥ የሚኖሩት አዜብ መስፍን ከዚህ በተጨማሪ ቦሌ ሩዋንዳ መታጠፊያ ላይ የሚገኘውን የቀድሞ የደህንነት ቢሮ ለአዜብ በቢሮ መልክ እንደተሰጣቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል።
azeb
ቀን ቀን በዚህ ቢሮ ለብቻቸው ያሳልፉ የነበሩት አዜብ መስፍን በጠና ከታመሙ ወዲህ ላለፉት አምስት ሳምንታት ወደዚህ ቢሮ ገብተው እንደማያውቁና በቤታቸው እንደሚያሳልፉ ያስታወቁት ምንጮቹ አክለውም ፓርቲው በሚያካሂዳቸው ስብሰባዎች መገኘት እንዳቆሙና ለመጨረሻ ጊዜ የተገኙት ከሁለት ወር በፊት ኢህአዴግ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ላይ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚሁ ጉባኤ ከተሰብሳቢው ኋላ ለብቻቸው ተቀምጠው የታዩት አዜብ ምንም ሳይናገሩና አስተያየት ሳይሰጡ ስብሰባውን ከመጨረሳቸው ባሻገር ከስተውና ተጐሳቁለው እንደነበር ምንጮቹ አስታውሰው ከዚያ ወዲህ ህመሙ እየጠናባቸው እንደሄደ አያይዘው ገለፀዋል። አዜብ የባለቤታቸውን ቦታ በመተካት የጠ/ሚ/ርነቱንና ፓርቲውን የመምራት እቅድና ምኞት በተቀናቃኛቸው ስብሃት ነጋ ከከሸፈባቸውና የሚተማመኑባቸው የደህንነት ባለስልጣናትና የፓርቲው ቁልፍ ሰዎች እስር ቤት መወርወርና መባበረር ለከፍተኛ የሞራል ድቀትና ለበሽታ እንደዳረጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። አዜብ የኤፈርት ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ተብለው ቢሰየሙም ምንም አይነት የአመራር ሚና እንደሌላቸው የጠቆሙት ምንጮቹ በነስብሃት ተመድበው ተቋሙን ሲመሩ የቆዩት አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ወደ ራዲዮና ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ እንደሆኑና ከርሳቸው በኋላ ደግሞ የአርከበ እቁባይ ታናሽ ወንድም ጌታቸው እቁባይ እየመሩት መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል።

ከአዜብ ጋር በተፈጠረ ያለመግባባት ከኤፈርት ለቀው የቆዩት ጌታቸው እቁባይ የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ እንዲመለሱ መደረጉን አመልክተዋል። አዜብ ወደ ትግራይ -መቀሌ ከተጓዙ 6 ወር እንዳለፋቸው አክለዋል። በኤፈርት ውስጥ የአዜብ ደጋፊዎች በነስብሃት ተለቅመው መውጣታቸውን ያስታወሱት ምንጮቹ በቅርቡ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር የሚለውን የአዜብ ስልጣን በመግፈፍ ሊያባርሯቸው መሆኑን አረጋግጠዋል። …ይህ በእንዲህ እንዳለ የአባዱላ ገመዳ ልጅ ወጣት ኮሚያስ አባዱላ ከዚህ አለም በሞት እንደተለየ ታውቋል። የ26 አመቱ ወጣት ኮሚያስ አባዱላ በጉበት በሽታ ምክንያት ወደ ታይላንድ- ባንኮክ ተልኮ ለአንድ አመት ሲታከም ከቆየ በኋላ ሊድን ባለመቻሉ ከአራት ሳምንት በፊት ህይወቱ አልፏል። በባንኮክ ለአንድ አመት የሆስፒታል ቆይታው ለህክምና ብቻ ከ880ሺህ ዶላር ወጪ እንደተረገለት ታውቋል። በተመሰሳሳይ ሶስተኛ ታናሽ እህቱ (የአባዱላና ራሄል ልጅ) ከአምስት አመት በፊት በገጠማት የሳንባ፣ የአንጀትና የአእምሮ በሽታ በባንኮክ ሆ/ል ለሁለት አመት ህክምና የተከታተለች ሲሆን፣ ለህክምናው ጠቅላላ የወጣው 2.5ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ከዚህ ቀደም ይፋ በተረገው መረጃ መገለፁ ይታወሳል። ይህ ሁሉ ገንዘብ ከህዝብ የተዘረፈ ለመሆኑ አያጠያይቅም። ይህቺ ናት አገሬ! ..ለማንኛውም የአባዱላ ወንጀል ልጁን አይመለከተውም። ወጣት ኮሚያስ በአባቱ ድርጊት ነፃናነት ስለማይሰማው – በየእለቱ አልኮል ይጠጣና ይበሳጭ እንደነበረ ቅርብ የሆኑ ጓደኞቹ ተናግረዋል። የጉበት በሽታውም መንስኤ ይኸው ነው። ነፍስ ይማር!

በሳንሆዜ የኢትዮጵያውያን ቀን ሲከበር ጃኪ ጎሲ እንቅስቃሴው እንዲህ ነበር (Video)

$
0
0

ባላገሩ ዘፈን በቅድሚያ – ከዛም ደግሞ ባንዲራው ይቀጥላል።

ባንዲራው ይቀጥላል – ይመለሱ ቪድዮን እየጫንነው ነው።
jacki gossee

የኢትዮጵያውያን ቀን በሳንሆዜ በደማቅ ስነ-ሥርዓት ተከበረ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) እየተካሄደ ባለው 31ኛው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል አንዱ አካል የሆነው የኢትዮጵያውያን ቀን ዛሬ ጁላይ 4 ቀን 2014 ዓ.ም በደማቅ ስነስርዓት ተከበረ። በበዓሉ ላይ የኔልሰን ማንዴላ ጠባቂ የነበሩት ሻምበል ጉታ ዲንቃ በሕይወት ዘመናቸው ላደረጉት አስተዋጾ ተሸልመዋል።

በጣም ደማቅ በነበረው በዚህ በዓል ላይ ቅኝት የባህል ቡድን ሕዝቡን ቁጭ ብድግ ያደረገ የባህል ትር ኢቶችን ያሳየ ሲሆን በተጨማሪም ቴዎድሮስ ታደሰ፣ ፋሲል ደመወዝ፣ ጃኪ ጎሲ፣ ፋንትሽ በቀለና ሌሎችም ይህንን በዓል በከፍተኛ ሁኔታ ሲያደምቁት አምሽተዋል።

በሳንሆዜ እየተደረገ ባለው በ31ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የተለያዩ ንግድ ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ተቋማት፣ ምግብ የሚያቀርቡ፣ ጌጣጌጥና አልባሳት የሚሸጡ፣ የእስልምና፣ የኦርቶዶክስና የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችና ሌሎችም የራሳቸውን ድንኳን በመከራየት አላማቸውን እና ሥራዎቻቸውን ካለፈው እሁድ ጀምሮ ሲያስተዋውቁ የከረሙ ቢሆንም ከትላንት ሐሙስ ምሽት ጀምሮ ጥሩ ደንበኞችን ሲያስተናግዱ ቆይተዋል።

የዛሬውን የሳንሆዜ ደማቅ የኢቶጵያውያን ቀን በፎቶ ይከታተሉት።
guta
esfana san jose cali 1

esfana san jose cali 2

esfana san jose cali 4
art
esfana san jose cali 9

esfana san jose

esfna san jose cal 9

esfna san jose cali 1

esfna san jose cali 3

esfna san jose cali 5

esfna san jose cali 6

esfna san jose cali 8

esfna san jose cali 10

esfna san jose cali 12

ተጨማሪ ፎቶዎችን ከፈለጉ እዚህ ይጫኑ

የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ሥራ አስፈፃሚ መንግስት በአዲስ አበባ የፓርቲው አባላት ላይ የሚፈጽመውን ውንብድና በመቃወም መግለጫ አወጣ

$
0
0

መንግሥታዊ የውንብድና ጥቃት በአስቸኳይ ይቁም !!

ከአዲስ አበባ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሥራ አስፈፃሚ የተሰጠ መግለጫ

 

 Millions of voices for freedom - UDJ

photo- Millions of voices for freedom – UDJ

የሕወሓት /ኢህአዴግ ቡድን ለአለፉት 23 ዓመታት ወደር የሌለው የሰብአዊ መብት ረገጣ በዜጎች ላይ ሲፈጽም መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው እውነታ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት ይህ የሰብአዊ መብት ረገጣ በእጅጉ ተባብሶ ወደ መንግሥታዊ የውንብድና ጥቃት ተቀይሯል፡፡ ዜጎች መንግሥት ባሰማራቸው የደህንነት ኃይሎች ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በጅምላ ይታሰራሉ፣ ይደበደባሉ፣ በስውር እስርቤቶች ተወርውረው ደብዛቸው እንዲጠፋ ይደረጋል፡፡ 


መንግሥት በየጊዜው የሚያወጣው የሀሰት፣ አድገናል፣ ተመንድገናል፣ ዜጎች ዕልል በሉ በማለት የሚያናፍሰው ባዶ ፕሮፓጋንዳ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሲያጣ ወደ ተቃዋሚ ኃይሎች ጣቱን በመቀሰር የተደራጀ የማፍያ ቡድን በግልጽ በማሰማራት በጠራራ ፀሐይ የውንብድና ተግባር በማስፈፀም ላይ ይገኛል፡፡ 


‹‹መንግሥት ሀገር ማስተዳደር እንዳልቻለ አዲስ አበባ ማሳያ ነች!›› በማለት የአዲስ አበባ አንድነት ም/ቤት ባዘጋጀው ሰላማዊ ሠልፍ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው የተሳተፉበት የእሪታ ቀን በተሳካ ሁኔታ ከተጠናቀቀ ጊዜ ጀምሮ በአንድነት ፓርቲ አመራርና አባላት ላይ የሚፈጽመው አሳፋሪ መንግሥታዊ ጥቃት ኢህአዴግን ወደ ተራ ውንብድና መውረዱን የሚያሳየን ሃቅ ነው፡፡
ባለፉት 2 ወራቶች በአዲስ አበባ የአንድነት አባላቶች ላይ ከትንኮሳ ጀምሮ እስከ አካል ማጉደል ወንጀል ኢህአዴግ ባደራጃቸው የደህንነት መታወቂያ በያዙ ኃይሎች ጥቃት ተፈጽሞብናል፡፡
እነዚህ የጥፋት ኃይሎች በጠራራ ፀሐይ የሰው ጥርስ አውልቀው፣ ጭንቅላት ፈንክተው በተዘጋጀላቸው መኪና ተኩራርተው በአደባባይ ሲሄዱ አንድም የፀጥታ ኃይል ሊያስቆማቸው ያለመቻሉ ኢህአዴግ መንግሥታዊ የውንብድና ጥቃት በአንድነት ፓርቲ ላይ እየፈፀመ ለመሆኑ በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡

የእዚህ መንግሥታዊ የውብድና ጥቃት ሠለባ የሆኑት አባሎቻችን ፡-
1ኛ አቶ ስንታየሁ ቸኮል የአዲስ አበባ አንድነት ሥራ አስፈፃሚና የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ግንቦት 12 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በቀን በውንብድና ተግባር ተደብድቦ ጭንቅላቱ ተፈንክቷል፡፡
2ኛ አቶ አስራት አብርሃ የብሔራዊ ም/ቤት አባል በስውር እስር ቤት ለቀናት ታስረው በፍርድ ቤት በዋስ ተለቋል፡፡
3ኛ አቶ ፀጋዬ አላምረው የብሔራዊ ም/ቤ አባልና የፓርቲው የሂሳብ ክፍል ኃላፊ በቅድመ ውህደት የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ሰኔ 1ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በኢህአዴግ አባላት ተደብድቧል፡፡
4ኛ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ የአዲስ አበባ አንድነት የም/ቤት አባልና የወረዳ 17 የአንድነት ሥራ አስፈፃሚ በደህንነት ኃይሎች ሰኔ 12 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በቀን ተደብድቧል፡፡
5ኛ አቶ ምሥራቅ ቦጋለ የአንድነት ፓርቲ አባል በወሮበሎች ተደብድቦ ሁለት የፊት ጥርሶቹ ወልቋል፡፡
6ኛ አቶ ደረጀ ጣሰው የአዲስ አበባ ህዝባዊ ንቅናቄ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፓርቲው ለቅስቀሳ አዋሳ በላካቸው ወቅት ከሰኔ 13 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም እስከ ሰኔ 19 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ድረስ በግፍ በአዋሳ ታስረው በዋስ ተለቀዋል፡፡

7ኛ አቶ ኃይሉ ግዛው የአዲስ አበባ ህዝባዊ ንቅናቄ አብይ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ም/ቤት አባል ፓርቲው ለቅስቀሳ አዋሳ በላካቸው ወቅት ከሰኔ 13 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም እስከ ሰኔ 19 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ድረስ በግፍ በአዋሳ ታስረው በዋስ ተለቀዋል፡፡

8ኛ አቶ አብርሃም አራጌ የአዲስ አበባ ህዝባዊ ንቅናቄ አብይ ኮሚቴ አባል ፓርቲው ለቅስቀሳ አዋሳ በላካቸው ወቅት ከነመኪናቸው ከሰኔ 13 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም እስከ ሰኔ 19 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ድረስ በግፍ በአዋሳ ታስረው በዋስ ተለቀዋል፡፡

9ኛ ወጣት መልካሙ አምባቸው በዩኒቨርሲቲ የፓርቲው አደረጃጀት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ከግንቦት 18 እስከ ሰኔ 6 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በግፍ ማዕከላዊ ታስሮ በዋስ ተለቋል፡፡

1ዐኛ አቶ እንግዳወርቅ ማሞ የአዲስ አበባ የአንድነት ሥራ አስፈፃሚና ፀሐፊ ሰኔ 19 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም መንገድ ላይ ጠብቀው በመኪና ለመግጨት ሞክረው ባለመቻላቸው አራት የታጠቁ የደህንነት መታወቂያ የያዙ ኃይሎች በጠራራ ፀሐይ አፍነው ወደ መኪናቸው ለማስገባት ያደረጉት ጥረት በግለሰቡ አልሞት ባይ ተጋዳይነት ቢከሽፍም የጥፋት ኃይሎቹ በያዙት የሽጉጥ ሰደፍ ተደብድበው ሁለት የፊት ጥርሳቸውን አውልቀው አስፓልት ላይ ዘርረዋቸው መኪናቸውን አስነስተው ሲሄዱ አንድም የፖሊስ ኃይል ሊያስቆማቸው አልቻለም፡፡

11ኛ አቶ ሰይፉ ገላጋይ የወረዳ 17 የአንድነት አባል ግንቦት 26 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በወንጀለኞቹ ተደብድቧል፡፡
12ኛ መ/ር አጥናፉ ሙላቱ ወረዳ 12/13 የአንድነት አባል በፈጠራ ክስ ተመስርቶበት በመንገላታት ላይ ይገኛል፡፡
13ኛ አቶ ሠለሞን ስዩም ወረዳ 12/13 የአንድነት ብ/ሥ/ኮሚቴ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ስውር ጥቃት ተፈጽሞበታል፡፡
ይህ ሁሉ የውንብድና ተግባር በአለፉት ሁለት ወራቶች መንግሥት ባደራጃቸው ወንበዴዎች የተፈፀመ እኩይ ተግባር ነው፡፡ ጥቃቱ ከ2ዐዐ7 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ በፊት የአንድነት ፓርቲን መዋቅር ለማፈራረስ ሆን ተብሎ በህወሓት/ኢህአዴግ የደህንነት ኃይሎች ታቅዶ የሚከናወን ስለመሆኑ ቅንጣት ያህል አንጠራጠርም፡፡ ጥቃቱ ቀጣይነት ያለው እንደሆነ አንዳንድ ፍንጮች ከወዲሁ እያመላከቱን ናቸው፡፡


የሕወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የአንድነትን አባላትን በማሰቃየትና በማሸማቀቅ፣ በመደብደብ የአካል ማጉደል ጉዳት በማድረስ አባላትን በማዋከብ የሚያደርገውን አስነዋሪ ተግባር እያወገዝን ከእኩይ ተግባራቸውም እንዲታቀቡ እንጠይቃለን፡፡
ኢህአዴግ እየፈፀመ ያለውን መንግሥታዊ የውንብድና ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም እንዲሁም እስካሁን በተደራጀ መልኩ ወንጀሉን የፈፀሙትን በጉያው ያቀፋቸውን የጥፋት ኃይሎች ቡድን ለህግ እንዲያቀርብ የአዲስ አበባ አንድነት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አጥብቆ ይጠይቃል፡፡
ትግሉ ለህገ-መንግሥትና ለሕግ ከማይገዛ አምባገነናዊ አገዛዝ ጋር መሆኑን ጠንቅቀን የምናውቅ በመሆኑ አሁንም ሳንገል እየሞትን ለዴሞክራሲና ለሕግ የበላይነት እውን መሆን ዛሬም ነገም አጥብቀን በሠላማዊ መንገድ ብቻ በመታገል ከሕዝባችን ጋር ለድል እንበቃለን፡፡

ቃል ኪዳናችንን ጠብቀን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት እስኪሆን በጽናት እንቆማለን!!
የአዲስ አበባ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
ሰኔ 26 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም
አዲስ አበባ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
*************************************************

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ኢሕአግ/ በአንዳርጋቸው ዙሪያ መግለጫ አወጣ

$
0
0

(የአርበኞች ግንባር ሠራዊት በምረቃ ላይ - ፎቶ ከፋይል)

(የአርበኞች ግንባር ሠራዊት በምረቃ ላይ – ፎቶ ከፋይል)


ጋዜጣዊ መግለጫ

የማፈኛ መዋቅሩን መሰረት በማድረግ በርካቶች ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን እጅግ በከፋና በሚዘገንን ሁኔታ በማጥፋት እኩይ ተግባሩ የሚታወቀው አረመኔው የወያኔ ስርዓት በአገራችን የተንሰራፋውን መጠነ-ሰፊ ተግዳሮት ከመሰረቱ ለመንቀል በሚደረገው ትግል ብርቱ ጥረትና እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን መንግስት ጋር በማበር የአንድን ሰው ከአገር አገር የመንቀሳቀስ መብት በመጣስ የየመን መንግስት ለወያኔው ማስረከቡ አጥብቀን የምናወግዘውና የምንቃወመው ሲሆን ድርጅታችን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በደረሰው አፈና መሰረት በማድረግ ማንኛውንም አይነት እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን አበክረን እናስታውቅለን።

ለአገርና ለወገን ዕድገት ብልጽግና ሲሉ በመታገላቸው ሳቢያ የየመን መንግስት እሳቸውን አፍኖ በማስረከቡ ምክንያት አገር ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ትግል ለአንድም ደቂቃ ቢሆን የሚገታው አለመሆኑን እብሪተኛው ቡድን ሊረዳው ይገባል።

በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በደረሰው የተቀነባበረ አፈና ዛሬ ላይ መግለጫ የማውጣታችን ምክንያት ጉዳዩ እስኪረጋገጥ በሚል እንጂ ቀደም ባሉት ቀናቶች መግለጫ ማውጣት ይጠበቅብን እንደነበረ እናምናለን ስለሆነም መላው የአገራችን ለውጥ ናፋቂ ወገናችን ሁሉ ይሄንኑ ሃሳባችንን በቅጡ እንዲረዳልን እናስገነዝባለን።

እንደ አንድ ታጋይና አታጋይ እሳቸውን በተቃውሞ ትግል ማጣታችን ቃላት ሊገልጸው ከሚችለው በላይ በውስጣችን ቁጣን ፈጥሯል ።

አገዛዙ አቶ አንዳርጋቸውን ከየመን መንግስት መረከቡ ለውጥ ናፋቂው ሕዝብ በፍርሃት ተሸብቦ ለትግል እንዳይነሳሳና ማንኛውም ተቃዋሚ የትም ሄደ የትም ከገባበት ገብተን በእጃችን ለማስገባት የሚያስችለን የዲፕሎማሲ ግንኙነት አለን በሚል ስጋት ለመፍጠር የተሰራ ቀመር ስለመሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም ።

ትምተኛውና ዘራፊው ቡድን ያልተረዳው ነገር ቢኖር ሕዝቡ ለሚያነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ትኩረት ሰጥቶ በማዳመጥ አግባባዊ በሆነ መልኩና ሕዝቡን ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚችል መልኩ ምላሽ እስካልሰጠ ድረስ በማፈን፣ በማሳደድ፣ በማዋከብና በመግደል የሚመጣ መፍትሄ አለመኖሩን ብቻም ሳይሆን በሕዝብ ላይ የሚወሰዱ ጭፍን ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች በጨመሩ ቁጥር ስርዓቱ ራሱን ወደ መቃብር ጉድጓድ እያስጠጋ እንዳለ ሊረዳው ይገባል።

አንድነት ሃይል ነው!
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/
ሰኔ 28 -2006 ዓ/ም


ያንዳርጋቸው መንገድና የኔ ጡመራ!

$
0
0

በደረጀ በጋሻው ከምስራቅ አፍሪቃ

አንባገነኖች ባህሪያቸው ተመሳሳይ በመሆኑ በማምን ላይ ሲሞዳሞዱ ህሊናቸውን አይቆረቁራቸውም።

የመን የምትባል ከቀይ ባህር ማዶ ያለች የአረቦች ምድር ሰሞኑን የፈጸመችው የልወደድ ባይነት ፖለቲካዊ “ግልሙትና”ታሪክና ትውልድ በመሪር ትዝታው ሲያስታውሱት የሚኖር ወራዳ ተግባር ነው። ሀገሪቱን ድሮም አትጥመኝም። አሁን ጨርሶ ጠላኋት።

ወገኔ አንዳርጋቸው በምርጫ 97 ማግስት ከወዳጄ ያሬድ ጋር ዝዋይ ማጎርያ ካምፕ መከራ የቀመሰና ወያኔን አብጠርጥሮ የሚያውቅ ፥”ነጻነትን የማያውቅ ነጻ አውጪ”በተሰኘው ምርጥ መጸሐፉ ገዢውን ሃይል በጥልቀት እንድናውቅ የበኩሉን ድርሻ የተወጣና የአውሮፓ ዮሮም ሆነ የንግስት ኤልሳቤጥ ባውንድን በጡረታ እየተቀበለ እንደማንኛውም ዲያስፖራ ፖለቲካን የቢራ ላይ ጨዋታ ማድመቅያ ያላደረገ የነጻነት ፋኖ ነው።

ዛሬ በግፍ አንበሶች ጉድጓድ እንደተጣለው ዳንኤል ከአንድዬ በቀር ምንም ሊታደገው የማይችል ምስኪን መሆኑን ስሰማ ውስጤ ይደማል። ያቺ ሐገር ሊታደጓት የሚባዝኑ ልጆቿን ለነጣቂ አውሬ የምትገብር ምድር በመሆኗ መጨረሻዋ የናፍቀኛል። የኔን ዕድሜ ሙሉ መከራ ስትዝቅና እኔንም ለ18 ዘመናት ስታዝቀኝ መኗሯ ዕድሏና ዕድሌ መጣመሩ በውስጤ እንድብሰከሰክ አድርጎኛል።

ዩጋንዳ ሸራቶን ሆቴል ሚሊኒየሙን ድል ባለ ድግስ የወያኔን ቆንስላ ሳንጨምር ያከበርንበትን ምክንያት አንድ ከካናዳ መጥቶ የነበረ ዲያስፖራ ጠይቆኝ በወቅቱ የጣልነው ዕገዳ ወያኔን “ኢትዮጲያዊ አይደልህም ማለታችን ሳይሆን አላግባብ ያሰራቸውን ጋዜጠኞች፥የሰባዊ መብት ተሟጋቾችና የቅንጅት አመራሮችን ሳይፈታና በሩን ለብሔራዊ ዕርቅ አስካልከፈተ ድረስ” ቢፈልግ የሚቀጥለውን ሚሊኒየም ያክበር ብለን አልነበረም። ዲያስፖራው ወዳጄ ቀደም ሲል እንደኔ ዲያስቁራ በነበረ ጊዜ የንበረው ሐገራዊ ወኔ ኮንዶሚኒየም ቤት ለማግኘት ከተመዘገበበት ጊዜ ወዲህ ሸርተት ያለና ተለጣፊ የሚመስል ማንነት ካነገበ ወዲህ በምናደርጋቸው የሃሳብ ልውውጦች ውስጡ መቦርቦሩን ቆሌዬ ነግሮኛል።ምንም ሆነ ምንግን እውነቱን መንገር የኔ ዐቢይ ተግባሬ ነበርና ጋትኩት።ካስመለሰውም ጉዳዩ የርሱ ይሆናል።

ዛሬም ካለንበት ብሔራዊ ቀውስ ለመው

አርቲስት ኪሮስ ዓለማየሁ የክብር ዶክትሬት ሳይሰጠው ቀረ

$
0
0

አብርሃ ደስታ እንደዘገበው የመቐለ የዩኒቨርስቲ የ2006 ዓም የትምህርት ዓመት ዛሬ ቅዳሜ አስመርቋል። በምረቃው ለተወሰኑ ጥሩ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ታዋቂ ግለሰቦች የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥ ተጠቅሶ ነበር። ለክብር ዶክትሬት ማዓርግ ከተጠቆሙ (1) አርቲስት ኪሮስ አለማዮሁ፣ (2) ነጋድራስ ገብረሂወት ባይከዳኝ፣ (3) አባ መልአኩ፣ (4) ዶ/ር ታረቀኝ በርሀ ይገኙባቸዋል። ከነዚህ የተጠቆሙ ግለሰቦች በመቐለ ዩኒቨርስቲ ሰኔት የተመረጡና የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የተሰጣቸው ነጋድራስ ገብረሂወት ባይከዳኝ፣ አባ መልአኩ እና ዶር ታረቀኝ በርሀ ናቸው። አርቲስት ኪሮስ አለማዮሁ ግን የክብር ዶክትሬቱ ሳይሰጠው ቀርተዋል። ኪሮስ አለማዮሁ በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር መቐለ ቅርንጫፍ ነበር የተጠቆመው። ስለ ኪሮስ ስራዎች ከሦስት ሰዓታት በላይ የፈጀ የሙሁራን ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ነበር። ብዙ የመቐለ ወጣቶችም ኪሮስ የክብር ዶክትሬት ይሰጠዋል ብለው ሲጠባበቁ ነበር፤ ይገባው ነበርና።
Kiros alemayehu zehabesha
ኪሮስ አለማዮሁ ለምን ሳይሰጠው እንደቅረ ማወቅ ቀላል ነው። ኪሮስ በህወሓቶች የሚሰጠው ክብርና ስለ አሟሟቱ ማወቅ ዛሬ ለምን የክብር ዶክትሬቱ እንዳልተሰጠው መገመት ይቻላል። ደግሞ የህወሓቶች ባህሪ እናውቀዋለን። አሁን ህወሓቶች ኪሮስን ያስቀሩበት ምክንያት ብዘረዝር የነሱን ያህል ጠባብ እሆናለሁ። ስለዚህ ህወሓቶችን ለመተቸት ብዬ የሰጡትን ምክንያት ብነግራችሁ እነሱ ያሉበት የአውራጃዊነት ጭቃ መርገጤ ነው። ከነሱ ጋር ለመከራከር የነሱን ሐሳብ ማንሳት አለብኝ። የነሱን ሐሳብ ለማንሳት ደግሞ እነሱ ወደሚገኙበት የጠባብነት ደረጃ ራሴን ዝቅ ማድረግ አለብኝ (ከነሱ የተሻልኩ ነኝ እያልኩ ነው፤ ከነሱ የተሻልኩ መሆኔ ለማረጋገጥ ወደነሱ የ አውራጃዊነት ደረጃ መወረድ ያለብኝ አይመስለኝም። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ መዘባረቅ ይቅርብኝ)። መቐለ ዩኒቨርስቲ ለኪሮስ የክብር ዶክትሬት ባይሰጥም እኛ ህዝብ ባለፈው ኪሮስን በዘከርንበት ግዜ ህዝባዊ ክብር ሰጥተነዋል። ከዩኒቨርስቲ ክብር የህዝብ ክብር ይበልጣል ባይ ነኝ። ዩኒቨርስቲም ኮ ከህዝብ አያልፍም።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ለኪሮስ የክብር ዶክትሬት ሳይሰጥ ሲቀር የጎንደር ዩኒቨርስቲ ግን ለ አስቴር አወቀ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል። የመቐለ ዩኒቨርስቲ ኪሮስን አስቀርቶ ለሦስት ሰዎች ብቻ የክብር ዶክትሬት ሲሰጥ የጎንደር ዩንቨርስቲ ግን አስቴር አወቀን ጨምሮ ለ አራት ታዋቂ ሰዎች የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል። የጎንደር ዩኒቨርስቲ ለ አስቴር አወቀ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ዶር ሙሉ ዉበቱና አትሌት መሰረት ደፋር የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

ዩኒቨርስቲው ክብር ቢሰጠውም ባይሰጠውም ኪሮስ አለማዮሁ የትግርኛ ዘፈን ንጉስ ነው።

የድምጻችን ይሰማ ወቅታዊ ጽሑፍ፡ ሺህ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺህ –የፅኑዎች ትግል

$
0
0

ከድምጻችን ይሰማ የተላለፈ ወቅታዊ ጽሁፍ
ቅዳሜ ሰኔ 28/2006

የኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ የከፈተው ሁለንተናዊ ጥቃት እና ጭቆና በብዙ ሚሊዮናት ዜጎች ላይ የተከፈተ ጥቃት ቢሆንም እኛ … ብዙ ሚሊዮናት… ዜጎች ግን ብዝሃነታችን፣ የቋንቋችን መለያየት እና የብሔራችን አንድ አለመሆን እክል ሳይፈጥርብን በእምነት ገመድ ተሳስረን የተከፈተብንን ጥቃት ስንመክት እነሆ ሦስተኛ ረመዳናችንን ያዝን።
muslim1
በእነዚህ አመታት ውስጥ ‹‹ወርቅ በእሳት ይፈተናል!›› እንዲሉ እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም ከባድ የእንግልት እና የመከራ ጊዜያትን አሳልፈናል። መንግስት አንድ መንግስት በዜጎቹ ላይ ሊያደርሰው የሚችለውን ሰቆቃ አንድም ሳያስቀር አሟጦ በእኛ ላይ አድርሶብናል። የሐምሌ 6/2004 የሌሊት ጭፍጨፋ፣ የአርሲ አሳሳው ግድያ፣ የገርባ፣ የደጋንና የሀረሩ ሕይወት ቀጠፋ፣ የዒድ ሶላቱ ህፃንን ከአዛውንት፣ ወንድን ከሴት ያልለየ ድብደባና ግድያ፣ በማእከላዊ በወኪሎቻችን እና በበርካታ ወንድም እና እህቶቻችን ላይ የተፈፀሙ ዘግናኝ እና ኢሰብአዊ አካላዊ ጥቃቶች፣ እንዲሁም ተቆጥረው የማይዘለቁ የእስር፣ የድብደባ እና አካል የማጉደል ጥቃቶች ወሰን ያለፉና መንግስታዊ ጭካኔ የታየባቸው የሰቆቃ ዳራዎች ነበሩ።

የእነዚህ ሁሉ እርምጃዎች የመጨረሻ ግብ ደግሞ አንድነታችንን መበተን፣ ተስፋችንን ማጨለም እና ወደ አፄው ዘመን የተሸማቀቀ ማንነታችን መመለስ ነበር። ዳሩ ግን በፍየል ዘመን በግ ሊያደርጉን ለሚሹ አካላት እጅ ባለመስጠት እና አንድነታችንን በማጠናከር፣ ‹‹ብልጦች አይደለንም! ብልጣ ብልጦች ግን አያታልሉንም!›› እያልን የተቃጡብንን ጥቃቶች ስንመክት ከርመናል። ወደ ፊትም በአላህ (ሱ.ወ) እርዳታ በዚሁ የአንድነት መንፈስ የሚደርሱብንን ጥቃቶች በሙሉ መመከታችንን እንቀጥላለን!
ሺህ ሆነን እንደ አንድ አካል እንድንታገል መሠረቱን የጣሉልን ደግሞ ‹‹አንድ ሆነው እንደ ሺህ›› መታገል የቻሉት ብርቅዬ ወኪሎቻችን ናቸው። አዎን! ወኪሎቻችን አንድ ሆነው እንደ ሺህ ታግለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ የተሰነዘረውን ዱላ ብቻቸውን በማእከላዊ ተጋፍጠውታል፡፡ አቋማቸውን ለማስለወጥ፣ ቅስማቸውን ለመስበር እና ተስፋቸውን ለማጨለም ታቅዶ የደረሰባቸው ኢሰብአዊ ጥቃት ሳይበግራቸው ከብረት ጀርባ ሆነው አቋማቸውን ለህዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡ ስቃዩን እየተሰቃዩለት ላለው የኢትዮጵያ ሙስሊምም የእንኳን አደረሰህ መልእክት አድርሰዋል፡፡ ፅኑ ሆነው ፅናትን አስተምረውናል።

ፅናት ሰላማዊ ትግል ግቡን ይመታ ዘንድ ትልቁ መስፈርት ነው። በዓለም ዙሪያ ግባቸውን መምታት የቻሉ ሰላማዊ ትግሎች አመታትን የወሰዱ፣ የታጋዮችን ፅናት የፈተኑ እና አሜኬላቸው የበዛ ነበሩ። የእኛ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ትግልም ከዚህ የተለየ ሊሆን እንደማይችል መገመት ይቻላል። የትግሉን የመጨረሻ ፍሬ ለማየት ምናልባትም የትውልድ ቅብብሎሽን የሚፈልግ ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ ግን እንደ አላህ (ሱ.ወ) ፍቃድ በቅርቡ ድላችንን እንደምናየው ተስፋ እናደርጋለን።

ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ… ‹‹እንደ ታጋይ በዚህ ትግል ውስጥ ማበርከት ከምንችለው አስተዋፅኦ ምን ያህሉን አበርክተናል? ትግሉን እስከ ድል ደጃፎች ድረስ በፅናት ለመቀጠል ዝግጁነታችን ምን ይመስላል? በትግሉ ዙርያ ምን ያህል የመረጃ ልውውጦችን እናደርጋለን?››

እኒህን እና መሰል ጥያቄዎችን ራሳችንን እየጠየቅን እኛም እንደወኪሎቻችን ሁሉ ሺህ ሆነን እንደ አንድ ከመታገል በዘለለ አንድ ሆነን እንደ ሺህ የምንታገልበትን እና የድሉን ጊዜ የምናቃርብበትን መንገድ ማየት ያስፈልገናል።
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከ ድል ደጃፎች ድረስ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

የኢትዮጵያ ወጣቶች ንቅናቄ “የአቶ አንዳርጋቸው መስዕዋትነት ለትግላችን መፋፋም ወሳኝ ምዕራፍ ነው”አለ

$
0
0

የአቶ አንዳርጋቸው መስዕዋትነት ለትግላችን መፋፋም፣ ለትብብራችን ተግባራዊነትና፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት እውን መሆን ወሳኝ ምዕራፍ ነው!

ጋዜጣዊ መግለጫ

EYNM New Logoየኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ በተፈጠረው ልብ የሚሰብር ክስተት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፀ፤ ይህ ፋሽስት የወያኔ/ኢህአዴግ ሥርዓት የፈፀመውን አሳፋሪና ህገወጥ አፈና በከፍተኛ ምሬት፣ ቁጭትና፣ እልህ አጥብቆ እንደሚቃወም ያሳውቃል። የጎረቤት ሃገራት አቶ አንዳርጋቸውን ጨምሮ በስደት ላይ በሚገኙ አያሌ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ የአፈና ወንጀልን በመፈፀም ንፁሃን ዜጎችን ለሰው በላው የወያኔ/ኢህአዴግ ሥርዓት አሳልፈው ሲሰጡ በተደጋጋሚ ሰምተናል አይተናልም። ድርጅታችን ይህ የወንበዴ መንግስታት አይን ያወጣ ወንጀል ነፃነቱንና ህልውናውን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ጀግንነትንና ጀብድን በመፈፀሙ፤ ለአለም ጥቁር ህዝቦች ብቸኛው የነፃነት ምሳሌ ሆኖ በአለም አቀፍ ደረጃ ለዘመናት በክብር የኖረው መላው የኢትዮጵያ ህዝብን የናቀና ያዋረደ፤ የሃገሪቱን ሉአላዊነትና ክብር በጅጉ የደፈረ፤ ይቅር የማይባል ብሄራዊ ወንጀል መሆኑን በፅኑ ያምናል። በመሆኑም ሥርዓቱ እየፈፀመ በሚገኘው አስከፊና አሳፋሪ ወንጀል ወደፊት ከመጠየቅ በፍፁም እንደማይድንና ምናልባትም እጅግ የከፋ ዋጋ እንደሚያስከፍለው ተገንዝቦ፤ ከዚህ የወንጀል ድርጊቱ በመታቀብ አቶ አንዳርጋቸውንም ሆነ ሌሎች በተመሳሳይ መልኩ ከጎረቤት ሃገራት ታፍነው በየእስርቤቱ የሚማቅቁ አያሌ ንፁሃን ዜጎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ ከወዲሁ በጥብቅ ያስጠነቅቃል።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ከግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ኃይል የተላለፈ አዋጅ

$
0
0

አዋጅ አዋጅ !!! ቀን 28/10/2006
Ginbot 7 Popular Force Song – Ethiopia
ልብ ያለው ልብ በል፤ ጆሮ ያለው ይስማ

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በየመን መታገት አስመልክቶ አጭር መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል። በመግለጫችን የመን ታግዩን ልታግት የምትችልነት የጸጉር ስንጣቂ የምታክል ምክንያት እንደሌላት ሊኖራትም እንደማይችል ስለሆነም ታጋዩ ባስቸኳይ እንዲለቀቅ በተደጋጋሚ ጠይቀን፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ የነፃነት ታጋዩ በፋሽስቱ የወያኔ ቡድን ተላልፎ ቢሰጥ የመን የማይሰረዝ ታሪካዊ ስህተት የምትሰራ መሆኑን ሕዝባዊ ኃይላችንም የበቀል እርምጃዎችን እንደሚወስድ አሳውቀን ወያኔም ምናልባት ትግሉን አስቆማለው በሚል የሞኝ ስሌት ያደረገው ከሆነ ድርጊቱ ትግሉን በዕልህ እና በበቀል አጅቦ ከመውሰድ እና ከማፋጠን የዘለለ ትልቅ የሃሳብ አባት አንዳርጋቸው በሃገሪቱ ሰማይ ላይ የለቀቀውን የኢትዮጵያዊነት ጸረ ወያኔ መንፈስ አስሮ አሰቃይቶ ገሎ ማስቆም እንደማይችል አሳስበን አስገንዝበን ነበር:: መግለጫችን የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ ግን የየመን መንግስት እንደሰጋነው ትልቁን የቁርጥ ቀን ልጅ ለወያኔ አሳልፎ መስጠቱን አውቀናል።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live