Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአንዳርጋቸው ጉዳይ በውጭ ሚዲያዎች ለምን ሳይዘገብ ቀረ? – (በመታሰራቸው ዙሪያ የኔ 3 ጥያቄዎች)

$
0
0

andargachew
ስታየሁ ከዋሽንግተን ዲሲ

በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ ትናንት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መንግስት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ታሰሩ የሚል ዜና ካነበብኩ በኋላ የተለያዩ ጥያቄዎች በጭንቅላቴ ላይ ተመላለሱ።

የመን በመንግስት አሰራር ደረጃ ከአፍሪካ ሃገራት የማትሻልና በሙስና የተጨማለቀ አሰራር ስላላት አቶ አንዳርጋቸው እንዴት ለትራንዚትም ቢሆንም መመረጣቸው ድፍረታቸውን ባደንቅም ውሳኔያቸው ገርሞኛል። ጫት በሚቅሙ የመንግስት ሃይሎች የምትመራው የመን በተለይም አቶ አንዳርጋቸውን በጫት ንግድ ልትለውጣቸው ትችላለች የሚለው የብዙዎች አስተሳሰብ ባይስበኝም እኔን የገረመኝ አቶ አንዳርጋቸውን የሚያህል ትልቅ የተቃዋሚ ድርጅት መሪ የመታሰር ዜና አንድ ሳምንት ሙሉ በሌሎች የውጭ ሚዲያዎች አለመዘገቡ ገርሞኛል።

ዜናውን ከዘ-ሐበሻ ካነበብኩ በኋላ በግንቦት 7 ድረገጽ፣ በኢሳት ዝርዝሩን ሰማሁ። ከዛም ወደ የመን ሚድያዎች ጋር በኢንተርኔት አሰሳ ጀመርኩ። ከዚህ በፊት የግድያ ሙከራ በአስመራ ሊደረግባቸው ታቅዶ ከሸፈባቸው ስለተባሉት አቶ አንዳርጋቸው አንዳችም ጉዳይ የሚያወራ ነገር አላየሁም። በአንዳችም ሚድያ ስለመታሰራቸው የተዘገበ ነገር አለመኖሩ ገርሞኛል።

በተለይም የእንግሊዝ ሃገር ፓስፖርት አላቸው የሚባሉት አቶ አንዳርጋቸው እውነት የእንግሊዝ ፓስፖርት ካላቸው እንዴት እንግሊዞች ዝም አሉ? አንድ ዜጋቸው እንዲህ ያለ መታፈን ውስጥ ሲወድቅ ሚዲያዎቻቸውም መንግስታቸውም እንዴት ዝም አለ?

የኤርትራ ባለስልጣናትም ዝም ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ያሉት ነገር የለም። ምንድን ነው ጉዱ? እንደሚባለው ግንቦት 7ና አለኝ የሚለው ኃይል ቀስ በቀስ ከአስመራ ለቆ ለመውጣት ካለው እቅድ ጋር በተያያዘ አቶ አንዳርጋቸው አንድ ነገር ደርሶባቸው ይሆን?

አልጀዚራን የመሳሰሉ ለኢትዮጵያ ጉዳይ ዜናዎች ቅርብ የሆኑ የሌላ ሀገር ሚዲያዎችስ ይህን ዜና አለመዘገባቸው የሚያሳዩን ነገሮች ምንድን ናቸው?

እስኪ ተወያዩበት።


የግንቦት ሰባት የአመራር አባል የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ደህንነት ሽንጎን ያሳሰበዋል

$
0
0

shengoሰኔ 24፣ 2006 (ጁላይ 1፣ 2014)

የግንቦት ሰባት ያመራር አባል የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን በኩል ወደሌላ ሀገር ጉዞ በሚያደርጉበት ወቅት በሀገሪቱ ባለስልጣናት ከሰኔ 16 ጀምሮ መታሰራቸውን እና እስካሁንም ለማሰፈታት የተደረገው ሙከራ ሁሉ እንዳልተሳካ ግንቦት ሰባት ሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም ካወጣው መግለጫና በኢሳት የመገናኛ ምንጭ ከተዘገበው ተረድተናል።  -—[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]——-  

Health: 10 አስደንጋጭ የህክምና ስህተቶች

$
0
0

 

የህክምና ስህተቶች በየጊዜው ይከሰታሉ፡፡ እንደውም በአገረ አሜሪካ በየዓመቱ 200 ሺህ ሰዎች ይሞታሉ፡፡ አንዳንዶች በአጋጣሚ የአካል ጉዳት ያገኛቸዋል፤ ወይም ደግሞ ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል፡፡ በእርግጥ ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት እንደማይጠፋ ሁሉ ሐኪሞችና ነርሶችም ሰዎች ናቸውና ሊሳሳቱ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በጣም የማይሆኑ ስህተቶች ወይም ደግሞ በቀላል ጥንቃቄ ሊወገዱ የሚችሉ አስገራሚ ክስተቶች ሲፈፅሙ ይስተዋላል፡፡ ታዲያ ይህ የጤና ነው ማለት ይቻል ይሆን? እስኪ በታሪክ ውስጥ የማይረሱ የሚባሉትን እናንሳ እና የየራሳችንን አስተያየት እንሰንዝር፡፡

 

medical mistakes1. በተሳሳተ ጭንቅላት በኩል የተደረገ ቀዶ ጥገና፡-
በ2007 እንኳን በሮድ አይላንድ ሆስፒታል በሶስት ሰዎች ላይ ትክክለኛ ባልሆነ የጭንቅላት አቅጣጫ ላይ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸዋል፡፡ እንግዲህ ይታያችሁ በአንጎል ላይ መሳሳት ማለት ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል፡፡ ሁለቱ ስህተቶች ወዲያውኑ በመታወቃቸው ፈጣን ማስተካከያ ተደርጎላቸዋል፡፡ የሶስተኛው ታማሚ ግን ወዲያው ባለመታወቁ ከሶስት ሳምንት በኋላ በ86 ዓመታቸው ለህልፈት በቅተዋል፡፡ በዚህ የተነሳም የሐኪሞቹ ፈቃድ ለሁለት ወራት ያህል እንዲታገድ ሆኗል፡፡

 

2. የተሳሳተ የልብ ዝውውር፡-
በ2003 በዲውክ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ የተደረገው ስህተት ደግሞ ጄሲካ ሳንቲለን እየተባለ ለሚጠራው የ17 ዓመት ልጅ የተደረገና ከደም አይነቱ ጋር የማይሄድና የተሳሳተ የልብ ዝውውር ነበር፡፡ በዚህ የተነሳም የልጁ ሰውነት ወዲያውኑ መስራት አቆመ፤ ከፍተኛ የአንጎል ጉዳትም ደረሰበት፡፡ ይሁን እንጂ ወዲያውኑ በትክክለኛ ልብና ሳንባ ለመተካትና ችግሩን ለማስተካከል ጥረት ቢደረግም ልጁን ከሞት ማትረፍ አልተቻለም፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሆስፒታሉ የትኛውንም አይነት ዝውውር ከማድረጉ በፊት ሁለት ጊዜ የማረጋገጥ ደንብን ተግባራዊ አድርጓል፡፡

 

3. የሁለት ልጆችን ደም ያፈሰሰ መድኃኒት 
በፊልም አክተሩ ዴኒስ ኩይድና ሚስቱ ኪምበርሌዊ ባፊንግተን መንትያ ልጆችን መታቀፋቸው አስደሳች ቢሆንም ከፍተኛ የሚዲያ ትኩረትን የሳበው ግን ልጆቹ ከፍተኛ መጠን ያለውና ሔፓሪን የተባለውን አደገኛ መድኃኒት በስህተት መውሰዳቸውን ተከትሎ ባጋጠማቸው አደጋ የተነሳ ነበር፡፡ እነዚህ መንትያ ህፃናት እንደተወለዱ ላደረባቸው ኢንፌክሽን በደም ስር የሚወሰድ አንቲባዮቲክ ተሰጥቷቸው የነበረ ሲሆን የደም ስራቸው አካባቢ የደም መጓጎል እንዳይፈጠር 10 ዩኒት ሔፓሪን መውሰድ ሲገባቸው ለትልልቅ ሰዎች የሚሰጥ 10,000 ዩኒት ሔፓሪን በስህተት እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡ በዚህ የተነሳም ደማቸው በከፍተኛ ደረጃ በመቅጠኑ ከሰውነታቸው ውጭም ሆነ ውስጥ የደም ፍሰት አጋጥሟቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በሚገርም ገጠመኝ ከ41 ሰዓታት በኋላ ደማቸው መወፈር በመቻሉ ከሞት ተርፈዋል፡፡ ስህተቱ የተፈጠረው በሐኪም የታዘዘውን የልጆች ሔፓሪን አሳስታ የሰጠችው በፋርማሲዋ ምክንያት ነው፡፡ የልጆችም ሆነ የአዋቂዎች ሔፓሪን ብልቃጥ ደግሞ ተመሳሳይ በመሆኑ ነርሷ ልብ እንዳትል አድርጓል ይላል ዘገባው፡፡

 

4. ቆለጥ ያሳጣ ስህተት
ቤንጃሚን ሁትን በመባል የሚጠራ የአየር ኃይል ባልደረባ ወደ ህክምና ያመራው ከሁለቱ የቆለጥ ፍሬዎቹ ውስጥ የግራው በመሟሸሹና በውስጡም የካንሰር ሕዋስ ሳይዝ እንዳልቀረ በሐኪም ስለተጠረጠረ ነበር፡፡ ይህ የቆለጥ ፍሬ ቢወገድም በአንዱ መውለድ ይችላል፤ የወንድ የዘር ፍሬም (sperm) ማምረት ያስችለዋል፡፡ በመሆኑም በቀዶ ጥገና እንዲወገድለት ቆዶ ህክምና ተደርጎለት ሲወጣ ግን የተወገደው የቆለጥ ፍሬ የግራው ሳይሆን ጤናማውን የቀኙ ሆኖ ነበር የተገኘው፡፡ በዚህም ስህተት ይህ ግለሰብና ሚስቱ የሎስ አንጀለስን ሆስፒታል በመክሰሳቸው 200 ሺህ ዶላር ካሳ አስከፍለዋል፡፡

 

5. እግር እግር የሚል ስህተት

 

እጅግ አስገራሚ የተባለውና የ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ግራ አጋቢ ስህተት የተፈጠረው በ52 ዓመቱ ደሊኪንግ ላይ ነበር፡፡ በ1995 በጣም ለተጎዳው እግሩ መቆረጥ እንዳለበት የተነገረው ኪንግ በቀዳጁ ሐኪሙ ስህተት የተነሳ ግን የተቆረጠው ሌላኛው እግሩ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ኪንግ በመጨረሻ ሁለቱንም እግሩን እንዲያጠያ ሆኗል፡፡ ስህተቱ የተፈጠረው ግለሰቡን ለቀዶ ህክምና ዝግጁ እንዲሆን ባደረጉት ነርሶች ነበር፡፡ ለቀዶ ህክምና ዝግጁ እንዲሆንና አስፈላጊው አጠባና ምልክት የተደረገው በጤናማው ላይ በመሆኑ ሐኪሙ በስህተት ሊቆርጡት በቅተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ፈቃዳቸው ለ6 ወር የታገደ ሲሆን ለኪንግም የ250 ሺህ ዶላር ካሳ ከፍለዋል፡፡ በነገራችን ላይ በእኛም አገር ይህ መሰል ስህተት አጋጥሟል፤ በአዲስ አበባ ውስጥ፡፡

 

6. በተሳሳተ ወንድ ያረገዘችው ሴት

 

ሁለት ባልና ሚስት በተለመደው የግበረ ስጋ ግንኙነት መውለድ ያልቻሉ በመሆናቸው በልዩ የሰው ሰራሽ አረባብ ቴክኖሎጂ፣ እንዲፀንሱ ወደስነ ተዋልዶ ክሊኒክ ይሄዳሉ፡፡ እነዚህ ባልና ሚስት ቶማስና ናንሲ በመባል የሚጠሩ ሲሆን የሀኪሙ ኃላፊነት ቶማስን የዘር ሕዋስ (sperm) ከናንሲ የዘር ህዋስ (ova) ጋር በብልቃጥ ውስጥ በማደባለቅና ፅንስን እንዲፈጠር በማገዝ በመጨረሻ ወደናንሲ ማህፀን እንዲረገዝ ማዛወር ነበር፡፡ በዚህም ጥበብ ያረገዘችው ናንሲ የወለደቻት ልጅ የቆዳ ቀለሟ ጠይም መሆኑ ግራ አጋባት፡፡ ናንሲም ሆነች ባሏ በዘራቸው ፈረንጅ እንጂ ጥቁር አልነበሩም፡፡ በዚህ የተነሳ የአባትነት የደም ምርመራ (DNA) ለሶስት ጊዜ ሲደረግ በሁሉም ላይ ያሳየው ጄሲካ የተባለችው ህፃን አባቷ የእናቷ ባል አልነበረም፡፡ ማለትም ጄሲካ አንድሪው ልጅ አይደለችም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያትም ሐኪሙ የናንሲን እንቁላል ሲያዋህድ የተጠቀመው የባሏን ሳይሆን በተመሳሳይ ችግር የመጣን የአንድ ጥቁር ስፐርምን በስህተት በመጠቀም ነበር፡፡ ይህም የሚያሳየው የአንድሪው ስፐርም የጥቁሩን ሚስት አስረግዟል ማለት ነው፡፡ በስህተት የተቀያየሩ ባሎች እንበላቸው ይሆን?

 

7. አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ

 

ይህ ደግሞ በ84 ዓመቷ አዛውንት ላይ የተደረገ ስህተት ሲሆን በቀዶ ጥገና እንዲወገድ የተወሰነው የሐሞት ከረጢቷ ሆኖ ሳለ ተቆርጦ የተጣለው ግን የቀኝ ኩላሊቷ ነበር፡፡ ይህ የሆነው የላብራቶሪ ውጤቱን አሳስቶ በማንበቡ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ሳይቆረጥ የተተወው የሐሞት ከረጢት በራሱ ጊዜ ድኖ ጤነኛ መሆኑም ሌላኛው አስገራሚ ክስተት ነበር፡፡ መጀመሪያውኑም ቀዶ ጥገና አያስፈልገውም ነበርና፡፡ በዚህ ተነሳም ሐኪሙ ከፍተኛ ካሳ የከፈለ ሲሆን ከዚህ ክስተት በኋላ ያለ ሌላ ሐኪም የበላይ ተመልካችነት ቀዶ ጥገና እንዳያከናውን ታግዷል፡፡

 

8. በሆድ ውስጥ የተረሳ መጎተቻ

 

በሲያትል በሚገኘው የዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር የተደረገው ስህተት ደግሞ በሆድ ውስጥ ዕጢ ለማውጣት በተደረገ ቀዶ ጥገና 30 ሳንቲ ሜትር የሚረዝም አጋዥ መጎተቻ (retractor) መሳሪያ ሊረሳ መቻሉ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ወዲያው ስህተት መፈጠሩ በመታወቁ መሳሪያው እንዲወጣ ቢደረግም ለታካሚው ግን 97 ሺህ ዶላር ካሳ ከመክፈል አልዳኑም፡፡

 

9. በስህተት ራሱን ያጠፋው ግለሰብ

 

ሼርማን ሲሞር የተባለ ግለሰብ በከፍተኛ የሆድ ህመም ሲሰቃይ የነበረ ሲሆን ለዚህም ሲባል ሆዱን በግልፅ ለማየትና መነሻውን ለማወቅ ቀዶ ህክምና ይደረግለታል፡፡ ይሁን እንጂ ቀዶ ጥገናው ከተካሄደ እስከ መጀመሪያዎቹ 16 ደቂቃዎች የሰመመን ማደንዘዣ አልተሰጠውም፡፡ ማደንዘዣው ከተሰጠው በኋላ ወዲያው ሊያደነዝዘው ባለመቻሉ ለከፍተኛ ህመም ይጋለጣል፡፡ ይሁን እንጂ በተወሰነ መልኩ ስለደነዘዘ ከሐኪሞቹ ጋር መነጋገርና ስቃዩን ማስረዳት አልቻለም ነበር፡፡ ከሆስፒታል ከወጣ በኋላ ቀዶ ጥገናውን እያስታወሰ በመረበሹ የተነሳ ክፉኛ በመሰቃየቱ ራሱን ሊያጠፋ ችሏል፡፡

 

10. ጡት አልባ ያደረገ ውሳኔ
ዳሪ ኤሰን በመባል የምትጠራ የ35 ዓመት ሴት ጡቶቿ ካንሰር አለባቸው በሚል ምርመራ የተነሳ ሁለቱም እንዲቆረጡ ይታዘዛል፡፡ ይሁን እንጂ ኤሰን አይቆረጡብኝም ብትልም ከሐኪም በላይ አይደለሽም በሚል በመጨረሻ እንዲቆረጡ ይደረጋል፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱም ጡቶቿ ምንም አይነት ካንሰር አልነበረባቸውም፡፡ በዚህ ስህተት የተነሳ ክስ የመሰረተችው ኤሰን ከፍተኛ ካሳ ተቀብላለች፡፡ ጡቶቿንም በገንዘቡ ማስመለስ ችላለች፤ ሰው ሰራሽ ጡቶች በማስገጠም፡፡

medical mistakes

አቶ አንዳርጋቸው በየመን መንግስት ከታገቱ በሁዋላ የኢትዮጵያ ትምባሆ ድርጅት ለየመን ኩባንያ ተሰጠ

$
0
0

የግንቦት 7 አመራር አባል በየመን መንግስት ታግተው ከተያዙ ከአንድ ሳምንት ወዲህ የፕራይቬታይዜይሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ውሳኔ መስጠት በተቸገረበት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት ሽያጭ ጉዳይ ላይ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውሳኔ በመስጠት ለየመን ኩባንያዎች ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ እንዲወስዱ ተደረገ::
andargachew
በአሁኑ ወቅት የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግታ ባለችበት ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የየመኑ ኩባንያ ሼባ ኢንቨስትመንት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 60 በመቶ ባለቤት እንዲሆን መወሰኑ በርካታ ፖለቲከኞችን እያነጋገረ ይገኛል;:

ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው የ70 ዓመት ዕድሜ ባለቤት የሆነው ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 22 በመቶ የሚሆነው አክሲዮን ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ በየመኑ ሼባ ኢንቨስትመንት ሲያዝ፣ ቀሪው 78 በመቶ አክሲዮን ደግሞ በመንግሥት የተያዘ ነበር፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በወሰነው አዲስ ውሳኔ ሼባ ኢንቨስትመንት ተጨማሪ 38 በመቶ አክሲዮን ከመንግሥት ላይ እንዲገዛ የሚፈቅድ በመሆኑ፣ ሼባ ኢንቨስትመንት በብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ላይ አንበሳውን ድርሻ 60 በመቶ ሲይዝ፣ መንግሥት ደግሞ 40 በመቶ ድርሻ ይዞ ይቀጥላል፡፡

ሼባ ኢንቨስትመንት እንዲገዛ ለተፈቀደለት 38 በመቶ አክሲዮን 1.3 ቢሊዮን ብር መክፈል እንደሚጠበቅበት የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ለሪፖርተር ገልጸው፣ ኩባንያው ይህንኑ ገንዘብ እንደከፈለ የስም ዝውውር እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

ብዙም ባልተመለመደ ሁኔታ የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ሽያጭ ላይ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የሥራ አመራር ቦርድ ውሳኔ ለመስጠት የተቸገረው በሁለት ምክንያቶች መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ የመጀመርያው ድርጅቱ በሲጋራ ላይ ብቸኛ መብት (ሞኖፖሊ ራይት) ያለው በመሆኑ፣ ይህ የብቸኝነት መብት የየመኑ ኩባንያ ከፍተኛ ድርሻ በሚይዝበት ወቅት ምን መሆን አለበት? የሚለው ጉዳይ ላይ አቋም መያዝ ባለመቻሉ ነው፡፡ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ትምባሆ ድርጅት በተለያዩ የታክስ ዓይነቶች በየዓመቱ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት የሚያስገባ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ትርፋማ ከሆኑ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ በመሆኑ፣ ለመንግሥት ግምጃ ቤት ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ የሚያደርግ ነው የሚለው ጉዳይ ቦርዱ በአክሲዮኑ ሽያጭ ላይ ለመወሰን እንዲቸገር ማድረጉ ነው፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በሆኑት ወ/ሮ አስቴር ማሞ የሚመራው የፕራይቬታይዜሽን ቦርድ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የመንግሥትን አቅጣጫ በግልጽ ባለመረዳቱ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቅጣጫ እንዲሰጠው መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሁለቱም ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው የአክሲዮን ሽያጩ እንዲከናወን በማዘዙ፣ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተሰበሰበው የፕራይቬይታዜሽን ቦርድ የየመኑ ኩባንያ ከፍተኛ ባለድርሻ መሆን የሚያስችለውን ውሳኔ እንዲወስን ማድረጉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ትምባሆ ድርጅት በተለያዩ አካባቢዎች የትምባሆ ልማት የሚያካሂድባቸው የእርሻ መሬቶች ባለቤት ነው፡፡ የድርጅቱ መሥርያ ቤት ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳር ቤት በሚወስደው መንገድ ከአፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት የሚገኝ ሲሆን፣ ለፀጥታ አመቺ አይደለም በሚል መሥርያ ቤቱ ከዚህ ቦታ ተነስቶ ወደ አቃቂ አካባቢ እንዲዛወር ተወስኗል፡፡ ምንጮቹ እንደገለጹት ድርጅቱ ቃሊቲ አካባቢ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተረከበው ቦታ ላይ የሚያካሂደውን ግንባታ ሲያጠናቅቅ፣ ለበርካታ ዓመታት ከነበረበት ቦታ ይነሳል ሲል ሪፖርተር ዘገባውን አጠናቁአል::

ውድ አንባቢያን በኢትዮጵያ አትራፊና ከፍተኛ ታክስ ከፋይ ከሆኑ ትላልቅ የመንግስ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አቶ አንዳርጋቸው ከታሰሩ ወዲህ ለየመኑ ኩባንያ በጠቅላይ ሚኒስተር መስሪያ ቤት ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ እንዲተላለፍ መደረጉ ዙሪያ ምን ትላላችሁ?

በረመዳን ጾም ወቅት በስፋት የሚበላው ቴምር ለጤና ያለው 10 በረከቶች

$
0
0

34በዚህ የረመዳን ወር፣ ቴምር ይታወሳል። እስቲ ቴምር የሚከተሉት ጥቅሞች አሉትና ተገባበዙ። እኛም ምክሩን ጋበዝናችሁ።

ቴምር በቫይታሚን፣ ማዕድናትና በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ መሆኑ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዲኖሩት አስችሎታል፡፡

1) ስብና ኮልስትሮል፦ ከየትኛውም የኮልስትሮል ዓይነቶች የጸዳና በጣም አነስተኛ የስብ መጠን ያለው መሆኑ ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ተመራጭ ነው፡፡
2) ፕሮቲን፦ ቴምር በፕሮቲንና አስፈላጊ ማዕድናት የበለጸገ መሆኑ ለሰውነት እጅጉን ጠቃሚ ያደርገዋል፡፡
3) ቫይታሚን፡ በቫይታሚን የበለጸገ ሲሆን ፥ ከቫይታሚን ዓይነቶች ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ3፣ ቢ5፣ ኤ1 ን አካትቶ ይዟል፡፡
4) ሀይል እና ጉልበት፦ ቴምር ቀላል የማይባል የሀይል ክምችት ስላለውም ንቁና በሀይል የተሞላን እንድንሆን ያስችለናል፡፡
5) ፖታሲየምና ካልሲየም፦ ቴምር የፖታሲየም ክምችቱ ከፍተኛ በመሆኑ በልብ በሽታ እንዳንጠቃና አካላችን ውስጥ ያለው የኮልስትሮል መጠን እንዲቀንስ ከመርዳቱም በላይ ፥ በአንጻሩ አነስተኛ የሶዲየም መጠንና ከፍተኛ ፖታሲየም መጠን በመያዙ ለጤናማ የነርቭ ስርዐት ወሳኝ ያደርገዋል ፡፡
6) ብረት፥ ቴምር በብረትና በፍሎሪን የበለጸገ መሆኑ ደግሞ ብረቱ የብረት ማዕድን እጥረት ላለባቸው ፍሎሪኑ ደግሞ ጥርስን ከመበስበስ ለመታደግ ይረዳል።
7) ድርቀት፦ ለድርቀትም ቢሆን ውሀ ውስጥ የተነከረ ቴምር መመገብ ፍቱን እንደሆነ ይታወቃል፡፡
8) ሰውነትን ማጽዳት፦ በአልኮል መጠጣት ሳቢያ ሰውነት ውስጥ የሚከማቸውን መርዛማ ኬሚካል ከሰውነታችን ውስጥ በማስወገድም ይረዳል – ቴምር !
9) ካንሰርና የዓይን ችግር፦ የዓይን ህመም ችግርንና የሆድ ካንሰርን ለማከምም ተመራጭ ነው – ቴምር!
10) ቆዳ ችግር፦ ቴምር የቆዳ ችግሮችን በማስወገድም መልካም ዝና ያለው ሲሆን ፥ ጸጉርን በማፋፋት የጸጉር መሳሳትንም ይከላከላል፡፡

Source: Admass Radio Atlanta

በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር የነዋሪዎች ግጭት መፈጠሩን ዘገባዎች አመለከቱ

$
0
0

wpid-eritrea-to-buy-power-from-sudanበኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር አካባቢ በተፈጠረ ግጭት በአካባቢው ውጥረት መፈጠሩንና በግጭቱም አሥር ያህል የሱዳን ወታደሮች መገደላቸውን ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት መረጃውን እያጣራ መሆኑን ገልጿል፡፡

አፍሪካ ፕሬስ ኤጀንሲ የተባለ ድረ ገጽ እንደዘገበው ከሆነ፣ ግጭቱ ባለፈው እሑድ የተቀሰቀሰው ገዳሪፍ በተባለው የሱዳን የድንበር አካባቢ ላይ ነው፡፡

በተቀሰቀሰው ግጭትም አሥር የሱዳን ወታደሮች ሲገደሉ፣ 13 የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸውን ዘገባው ያስረዳል፡፡ ግጭቱ በምን ምክንያት እንደተቀሰቀሰ ዘገባው ያለው ነገር የለም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ በኩል በግጭቱ የተሳተፉትን በትክክል ማወቅ አለመቻሉን፣ ነገር ግን በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ላይ ያሉ ታጣቂ ሚሊሻዎች ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ዘግቧል፡፡

የሱዳን መከላከያ ጦር ግጭቱ እንደተፈጠረ ለድረ ገጹ ቢያረጋግጥም፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ግጭቱ ላይ እንዳልተሳተፈ ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡

‹‹የሱዳን ወታደሮች ከኢትዮጵያ በኩል በመጡ ያልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል፡፡ ነገር ግን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር ግንኙነት የለውም፤›› በማለት የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ኢልስ ዋርሚ ካሊድካድ መናገራቸውም በዘገባው ተካቷል፡፡

ከኢትዮጵያ ድንበር በኩል የገቡት ታጣቂዎች በሱዳን ድንበር ውስጥ የሚገኘውንና በሱዳን ጦር ሥር የሚተዳዳረውን የእርሻ መሬት ለመያዝ ሳይመጡ እንዳልቀረ ተናግረዋል፡፡

የሱዳን መንግሥት ጉዳዩን ለኢትዮጵያ መንግሥት ማሳወቁን ቃል አቀባዩ አስረድተዋል፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ‹‹መረጃውን እያጣራን ነው፤›› ብለዋል፡፡

Source: Ethiopian Reporter

የጋዜጠኞችና ጦማሪያን ጊዜ ቀጠሮ በመደበኛ ችሎት እንዲታይ ታዘዘ

$
0
0


-
ጉዳዩ በግልጽ ችሎት እየታየ ነው ቢባልም ታዳሚዎች ግን መግባት አልቻሉም

zone 9999በተጠረጠሩበት የሽብርተኝነት ወንጀል በቁጥጥር ሥር ውለው ከታሠሩ ሁለት ወራት የሆናቸው የጋዜጠኞችና ጦማሪያን ጊዜ ቀጠሮ ቅዳሜና እሑድ መታየቱ ቀርቶ፣ በመደበኛ የችሎት ጊዜ እንዲታይ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

የተጠርጣሪዎቹ የጊዜ ቀጠሮ በመደበኛ ችሎት እንዲታይ የታዘዘው፣ የሦስቱ ጦማሪያን ማኅሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ኃይሉና አቤል ዋበላ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ሲቀርቡ ነው፡፡

ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. የነበረውን የተጠርጣሪ ጦማሪያን ጉዳይ ለመከታተል በአራዳ ምድብ ችሎት የተገኙ ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ የተለያዩ አገሮች ዲፕሎማቶች፣ የአገር ውስጥና የውጭ ጋዜጠኞች እንደወትሮው ሁሉ በርከት ያሉ ነበሩ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከመምጣታቸው በፊት ዳኛዋ በችሎት የተገኙ ቢሆንም፣ የምርመራ መዝገብ የሚያቀርቡት ሬጅስትራር በሰዓቱ ባለመገኘታቸው ዳኛዋ ያለመዝገብ መሥራት እንደማይችሉ ገልጸው፣ ለሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀጠሮ በመስጠት የተጠርጣሪዎቹን ጠበቃ ማሰናበታቸውን ጠበቃ አመሐ መኮንን ለታዳሚዎች ተናገረዋል፡፡ ተስፋ ያልቆረጡ የችሎቱ ታዳሚዎች ባሉበት ሆነው በመነጋገር ላይ እያሉ ሬጅስትራሯ ከጠዋቱ 4፡05 ሰዓት ላይ ሲደርሱ፣ ‹‹መጡ መጡ›› ተብሎ ጠበቃውም ወደ ችሎት ተመልሰው ገቡ፡፡

በዕለቱ የተሰየሙት ዳኛ የተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ በመደበኛ ችሎት እንዲታይ ያዘዙት በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ አንደኛው ለሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ተቀጥረው የነበሩት ሦስቱ ተጠርጣሪዎች በሰዓቱ ቀርበው ዳኛዋም በሰዓቱ የተሰየሙ ቢሆንም፣ የምርመራ መዝገቡን የሚያቀርቡት የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር በሰዓቱ ባለመድረሳቸው ነው፡፡ ሌላው ምክንያት ደግሞ ተጠርጣሪዎቹ የሚያቀርቡትን አቤቱታ በመደበኛው ችሎት ማስመዝገብ እንዲችሉ መሆኑን ጠበቃ አመሐ መኮንን ተናግረዋል፡፡

ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በቀረቡት ጦማሪያን ማኅሌት፣ በፍቃዱና አቤል ላይ የፌደራል ፖሊስ ለ28 ቀናት የሠራውን የምርመራ ሒደት እንዲያስረዳ ተጠይቋል፡፡ መርማሪ ፖሊስም ያልተያዙ የተጠርጣሪዎቹ ግብረ አበሮች መኖራቸውን፣ ምስክሮችን ሰምቶ አለመጨረሱን፣ ሰነዶችን አስተርጉሞ እንዳልጨረሰና የቴክኒክ ምርመራ እንደሚቀረው አስረድቶ፣ ለተጨማሪ ምርመራ የ28 ቀናት ጊዜ እንዲሰጠው መጠየቁን ጠበቃ አመሐ ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ የተሰየሙት ዳኛ ግን የተጠርጣሪዎቹን ጠበቃ አስተያየትም መስማት ሳያስፈልጋቸው መዝገቡ ረጅም ጊዜ የቆየ መሆኑን በመግለጽ፣ 28 ቀናት እንደማይፈቅዱ አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም ፖሊስ ቀርቶኛል ለሚለው ተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት ብቻ በመፍቀድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ ዳኛዋ የፈቀዱት የ14 ቀናት ማብቂያ እሑድ ሐምሌ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ቢሆንም፣ እሳቸው ግን አንድ ቀን በመጨመር ለሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. እንዲሆን ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ ዳኛዋ አንድ ቀን የጨመሩበትን ምክንያት ሲገልጹ፣ የቅዳሜና የእሑድ ችሎት ለአሠራር አመች ስላልሆነና በጉዳዩም ላይ ዳኞች በመቀያየራቸው ወጥነት የሌለው ነገር እየተከሰተ በመሆኑ፣ አሠራሩን ለማስተካከል መሆኑን ጠበቃ አመሐ መኮንን አስረድተዋል፡፡

ከተጠርጣሪዎቹ ጦማሪያን መካከል በፍቃዱ ኃይሉ ለችሎቱ ባቀረበው አቤቱታ፣ በምርመራ ወቅት እሱ የሰጠውን ቃል ሳይሆን ፖሊስ በራሱ መንገድ እየጻፈው መሆኑን ገልጾ፣ በመዝገቡ ላይ ያለው ቃል የሱ ቃል አለመሆኑ በማስረዳት ድርጊቱን መቃወሙን ጠበቃ አመሐ ተናግረዋል፡፡ ለተጠርጣሪ በፍቃዱ ምላሽ የሰጡት ዳኛዋ፣ አቤቱታውን ማቅረብ ያለበት ክስ የሚመሠረት ከሆነ በመደበኛው ችሎት ላይ መሆኑ አስታውቀው የዕለቱ ችሎት ማብቃቱን ጠበቃው ለታዳሚዎች አስረድተዋል፡፡

በዕለቱ በታዳሚዎችና በፖሊስ መካከል አለመግባባትም ተከስቶ ነበር፡፡ በፖሊስ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩት ሦስቱ ተጠርጣሪ ጦማሪያን ወደ ፍርድ ቤቱ ግቢ ሲደርሱ፣ በግቢው ውስጥ የነበሩ የችሎቱ ታዳሚዎች መጠነኛ ጭብጨባ አሰሙ፡፡ ከችሎቱ ግቢ ያስወጡናል የሚል ፍርኃት ያደረባቸው የተወሰነ ታዳሚዎች ‹‹ተው ተው አታጨብጭቡ›› ሲሉ፣ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ተንደርድረው በመሄድ አንዲትን ልጅ ጎትተው በማውጣት እያመነጫጨቁ ሲገፏት፣ ሌላኛው ወጣት ደግሞ ‹‹እህቴ ናት ልቀቋት ምን አደረገች?›› በማለት ሲቃወም፣ ‹‹ዝም በል›› በማለት ከፖሊስ ግሰጻ ቢደርስበትም መታገስ ያልቻለው ወጣት ‹‹እኔንም ውሰዱኝ›› ሲል አንድ መገናኛ ሬዲዮ የያዘ የፌደራል ፖሊስ ‹‹አምጣው›› በማለት ወጣቱን በመገፍተር ሁለቱንም ወደ ችሎት ወስዷቸዋል፡፡ በፖሊስ የተወሰዱት ሁለቱ ወጣቶች ዮናታን ተስፋዬና ምኞት መኮንን የሰማያዊ ፓርቲ አባል መሆናቸውም ተነግሯል፡፡ ሌሎች የፖሊስ አባላት ወደ ታዳሚዎች በመመለስ ‹‹በሕግ አምላክ ውጡ›› ሲሉ፣ የተወሰኑ ታዳሚዎች ‹‹ምን አደረግን? ዝም ብለን ቆመናል፤›› በማለት መልሰዋል፡፡ ፖሊሱ ‹‹እንዴት ፎቶ ታነሳላችሁ?፣ ማንም ሳያስፈቅድ ማንንም ማንሳት አይችልም፣ እንኳን ሰው ይችን (በጣቱ እያሳየ) መሬት ሳያስፈቅድ ፎቶ ማንሳት አይችልም›› ሲል ታዳሚዎች ከንዴታቸው በረድ ብለው ፈገግ አሉ፡፡ በመጨረሻም ታዳሚዎች እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ እያጉረመረሙ ግቢውን የለቀቁት የችሎት ታዳሚዎች አስፓልት ላይ በመቆም ተጠርጣሪዎቹን ሲወጡ ለመሰናበት መጠበቅ ጀመሩ፡፡ ሁኔታ ያላስደሰተው ፌደራል ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ በኩል አስወጥቶ ወደ ማዕከላዊ መውሰዱ ሲረጋገጥ ታዳሚዎችም ወደየመጡበት ሄዱ፡፡

Source: Ethiopian Reporter

በልደታ ለአንድ ንግድ ቤት በካሬ ሜትር 71,770 ብር የመጫረቻ ዋጋ ቀረበ

$
0
0

d90b93ac02750928f7cce1f439c89e76_Lየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ 489 የንግድ ቤቶችን ለመሸጥ አውጥቶት በነበረውና ቅዳሜ ሰኔ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. በይፋ በተከፈተው ጨረታ፣ በልደታ መልሶ ማልማት ለአንድ ንግድ ቤት

71,770 ብር በካሬ ሜትር ቀረበ፡፡ የንግድ ቤቱ በብሎክ 44 የሚገኝ ሲሆን፣ 44.51 ካሬ ሜትር ስፋት አለው፡፡ አጠቃላይ ዋጋውም 3,194,482 ብር በማውጣት ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በልደታ መልሶ ማልማት ከዚህ በፊት በነበረው ጨረታ በአንድ ካሬ ሜትር 56,000 ብር ቀርቦ ነበር፡፡ በዚህኛው ዙር የተሰጠው 71,770 ብር እስካሁን ከቀረቡት የመጫረቻ ዋጋዎች ከፍተኛው መሆኑን ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

ለኤጀንሲው ለ10ኛ ጊዜና ለዚህ ዓመት የመጀመሪያው የሆነው የንግድ ቤቶች ሽያጭ ጨረታ በአራት ኪሎ ስፖርት ማዕከል ቅዳሜ ማለዳ ተከፍቷል፡፡ በተከፈተው ጨረታ 489 የንግድ ቤቶችን ለመግዛት በርካታ ግለሰቦችና ድርጅቶች ተሳትፈዋል፡፡

ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የጨረታ ሰነዱን ከ7,650 በላይ ግለሰቦችና ድርጅቶች የገዙ ሲሆን፣ የተሳተፉትን ተጫራቾች ቁጥር ለማወቅ የቆጠራ ሥራ ሰኔ 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ዕለት እያካሄደ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የተጫራቾችን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ ጊዜ የወሰደበትን ምክንያት አንድ የኤጀንሲው ኃላፊ ለሪፖርተር፣ ‹‹አንድ ተጫራች አንድ ሰነድ ገዝቶ ሰነዱን በማባዛትና ሲፒኦ በማስያዝ 20 ለሚሆኑ ቤቶች ያስገቡ በመሆናቸው ከተሸጡ ሰነዶች ቁጥር ጋር ሰፊ ልዩነት በመኖሩ ነው፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡ ለሽያጭ የቀረቡት ቤቶቹ በስድስት ክፍላተ ከተሞችና በ12 ሳይቶች የሚገኙ ሲሆን፣ የተለያዩ ስፋትና ብዛት ያላቸው ናቸው፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ በሁለት ሳይቶች የካ አያት 2 በሚባለው 269፣ በየካ አያት 3 ደግሞ 24 በድምሩ 293 ቤቶች ይገኛሉ፡፡ መንግሥታዊ የሆነው የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በየካ አያት 2 ሳይት የሚገኘውንና 57.76 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውን በብሎክ 367 ምድር ቤት የሚገኘውን የንግድ ቤት 25,000 ብር በካሬ ሜትር ለመግዛት ዋጋ የመጫረቻ አስገብቷል፡፡ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ይህንን ሱቅ ለመግዛት ኤጀንሲው ካወጣው የጨረታ መነሻ ዋጋ 6,742 ብር 270 በመቶ ብልጫ ያለው ዋጋ አቅርቧል፡፡

በየካ አያት 2 ከቀረቡት 269 ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የተሰጠው ይህ ቤት በአጠቃላይ 1,444,000 ብር አውጥቷል፡፡ በዕለቱ በርካታ ተሳታፊዎችን ያስተናገዱት ሳይት የካ አያት 2 እና የካ አያት 3 ሲሆኑ፣ በርካታ ተጫራቾችን አሳትፈዋል፡፡ የሁለቱ ሳይቶች ጨረታ በተናጠል ሙሉ ቀን የፈጀ ከመሆኑም በላይ ዝቅተኛ የቀረበው ዋጋ 6,750 ብር ነበር፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ በሁለት ሳይቶች ሰሚትና ሰሚት 2 ከእያንዳንዳቸው 51 እና 70 ቤቶች በቅደም ተከተል በጨረታ ሲቀርቡ፣ የተጫራቾችን ብዛት ከግምት ውስጥ በማስገባትና ጊዜ ለመቆጠብ ተብሎ ጨረታው ለብቻው እንዲከፈት ተደርጐ ነበር፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ በድምሩ ከቀረቡ 127 ቤቶች ውስጥ በሰሚት ሥር ከተካተቱት 51 ቤቶች በብሎክ 188 የሚገኘው የቤት ቁጥር 06 ባለ 57.38 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው የንግድ ቤት የብዙዎችን ቀልብ ስቦ ነበር፡፡ ይህ የንግድ ቤት ከዚህ በፊት ለጨረታ ቀርቦ አሸናፊዎች ግዥ መፈጸም ባለመቻላቸው ድጋሚ ለሽያጭ የቀረበ ነው፡፡ በካሬ ሜትር 8,000 ብር ተሰጥቶበት የነበረ መሆኑን ሪፖርተር ያነጋገራቸው ተጫራቾች ተናግረዋል፡፡ በዕለቱ በርካታ ተጫራቾች የተለያዩ ዋጋዎችን ቢያስገቡም፣ 33,200 ብር በካሬ ሜትር ከፍተኛው ዋጋ ሆኖ ቀርቧል፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 38 ንግድ ቤቶች በአቃቂ ቃሊቲ አምስት፣ በኮልፌ ቀራኒዮ አራትና በልደታ ክፍለ ከተማ 22 ንግድ ቤቶች ለጨረታ ቀርበው በርካታ ግለሰቦችና ድርጅቶች ተሳትፈዋል፡፡ በአጠቃላይ የቤቶቹ ስፋት ድምር ከ26,000 ካሬ ሜትር በላይ ሲሆን፣ ትንሹ 23.4 ካሬ ሜትር ከፍተኛው ደግሞ 98.76 ካሬ ሜትር ነው፡፡ እነዚህ ንግድ ቤቶች በልደታ መልሶ ማልማት ሳይት የሚገኙ ናቸው፡፡

የ10ኛው ዙር የንግድ ቤቶች ሽያጭ ጨረታ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተጫራቾች የተሳተፉበት ሲሆን፣ የአሸናፊዎች ዝርዝር በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን የኤጀንሲው ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡ አሸናፊዎች ውጤታቸው በይፋ ከተገለጸበት ቀን አሥር የሥራ ቀናት በኋላ ባሉ 15 የሥራ ቀናት ያሸነፉበትን ዋጋ 50 በመቶ ወይም በሙሉ በመክፈል የሽያጭ ውል እንደሚፈጽሙ ኤጀንሲው አስረድቷል፡፡

ሃምሳ በመቶ የሚከፍሉ አሸናፊዎች ቀሪውን ክፍያ ንግድ ቤቱን በማስያዣነት በመጠቀም፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአምስት ዓመት የሚከፈል የብድር አቅርቦት ተመቻችቶላቸዋል፡፡ እንደ ኤጀንሲው ገለጻ አሸናፊዎች የቤቶቹን የመጨረሻ የፊኒሺንግ ሥራ፣ የበር፣ የመስኮት፣ የመታጠቢያ ቤት፣ የወለልና የኮርኒስ ሥራ በራሳቸው ወጪ ያሠራሉ፡፡

Source: Ethiopian Reporter


በእነ አቶ መላኩ ፈንታ ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ሆነ

$
0
0

Melaku-Fenta-and-Gebrewahid-Woldegiorgis የፌዴራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን በእነ አቶ መላኩ ፈንታ ላይ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ፡፡ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር በሚገኙት በእነ አቶ መላኩ ላይ የኮሚሽኑ

ዓቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ሦስት የክስ መዝገቦች መካከል በመዝገብ ቁጥር 141356 ላይ ከቀረቡ 28 ክሶች መካከል 23 ክሶችን አሻሽሎ እንዲያቀርብ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15 ወንጀል ችሎት ብይን መስጠቱ ይታወሳል፡፡

የፍርድ ቤቱን ብይን የተቃወመው የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የክስ መዝገቡን ማሻሻል እንደሌለበት በመጥቀስ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ አቤቱታውንና ብይኑን መርምሮ የዓቃቤ ሕግን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሥር ፍርድ ቤቱን ብይን አፅንቶታል፡፡

የሥር ፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ እንዲያሻሽል ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረው ዓቃቤ ሕግ በቡድን በቡድን ያቀረባቸው 23 ክሶችን ነጥሎ እንዲያቀርብ፣ ጊዜና ቀን ያልተጠቀሰባቸውን ክሶች ጠቅሶ እንዲያቀርብና ለክሶቹ ማስረጃነት ያቀረባቸው ሰነዶች ጥቅል በመሆናቸው የትኛው ማስረጃ ለየትኛው ክስ እንደሚያስረዳ ግልጽ ባለመሆኑ አስተካክሎ እንዲያቀርብ ብይን ሰጥቶ ነበር፡፡

ይህንን የከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት ያፀናው በመሆኑ፣ ዓቃቤ ሕግ ሰኔ 27 ቀን 2006 ዓ.ም. በችሎት ቀርቦ ክሶቹን አሻሽሎ የሚያቀርብበትን የጊዜ ትዕዛዝ ይቀበላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Source: Ethiopian Reporter

የአማራ ጉዳይ፤ አለ? ወይስ የለም?

$
0
0

መስፍን ወልደ ማርያም

ግንቦት 2006

mesfinተናግሬ ነበር ማለት ዋጋ የሌለው የወሬ ማጌጫ ነው፤ እስቲ ፍቀዱልኝና ልጠቀምበት፤ ከወያኔ ዋና ምሁር፣ ከመለስ ጋር ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ፊት-ለፊት በቴሌቪዥን በተገኛኘን ጊዜ ‹‹አማራ የሚባል ጎሣ የለም፡›› በማለቴ መለስ ዜናዊና ጭፍሮቹ ብቻ ሳይሆኑ ‹‹አማራ-ነን ባዮች›› በቃልም፣ በጽሑፍም፣ በቴሌፎንም ልክ-ልኬን እየነገሩኝ አንጀታቸውን ቅቤ አጠጥተው ነበር፤ ‹አንዲት ሴት ደውለው እብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል፤› ብለውኛል፤ አንድ ሰው የተናገረው ስሕተት ከሆነ ስሕተቱን በማስረጃ ማጋለጥና የራስን ሀሳብ በማስረጃ መትከል ነው፤ እውቀት የሚዳብረው፣ ሰዎች የሚማሩትና በእድገት ጎዳና የሚጓዙት በተጨባጭ ማስረጃ መነጋገር ሲችሉ ብቻ ነው፤ እኔ አማራ የለም፣ ዜሮ (0) ነው፤ አልሁ፤ አማራ አለ፣ አንድ አለ፤ (1) ነው ያለ ሰው የአንድን ዋጋ ማሳየት አለበት፤ አማራ የለም የሚል ዜሮ ነው ማለቱ ስለሆነ ከሌለ ነገር ምንም አይጠብቅም፤ ከአለ ነገር (ከ1) ብዙ ነገሮችን መጠበቅ ይቻላል።

ዱሮ በልጅነታችን ጭራቅ የሚሉት ማስፈራሪያ ነበረ፤ በአለፉት ሃያ ሦስት ዓመታት አማራ የሚባል ጭራቅ ማስፈራሪያ፣ የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ቋት እንደሆነ ሲነገር ቆየ፤ መለስ ዜናዊም እየደጋገመ ‹አከርካሪቱን ሰብረን ሁለተኛ እንዳያንሰራራ› እናደርገዋለን እያለ እንደዛተ የተሰበረውን አከርካሪት ሳያይ ሞተ፤ በሕይወትም እያለ ቢሆን መለስ ዜናዊ አከርካሪቱን እሰብረዋለሁ የሚለውን አማራ የተባለ ስያሜ እንደሹመት ለነበረከት ስምዖንና ለነተፈራ ዋልዋ ይሰጥ ነበር፤ የክብር ጎሣ እንበለው! ራሱም ቢሆን ከዚህ የክብር ጎሣ ቤተሰብነት አልራቀም፤ አከርካሪቱ እንኳን ሊሰበር አልተገኘም!

ስንት ሺህ ሰዎች አማራ ናችሁ እየተባሉ ከስንት ስፍራ ተፈናቀሉ? አማራ ማለት እነዚሁ የተፈናቀሉት፣ በየጫካው የተገደሉትና የተሰደዱት ብቻ ናቸው? ሌሎችም ካሉ የጎሣ ዝምድና ሳይስባቸውና ከተፈናቀሉት ጋር አብሮ ለመቆም ለምን አልቻሉም? በጋምቤላ በደረገው ጭፍጨፋ የተጨፈጨፉት ጎሣዎች በጣም ትንሽም ቢሆኑ ከካናዳ እስከ አውስትራልያ ዓለምን ያዳራሱት የጎሣ ዝምድና ስሜት ለምን ለእነዚህ አማራ ለተባሉት ተፈናቃዮች አልሠራም? እንግዲህ አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉት፣ የሚገደሉትና የሚሰቃዩት ዘመድና ደጋፊ የሌላቸው ሰዎች ናቸው ማለት ነው፤ ሰውነታቸውም ቢሆን በሕግ ያልተረጋገጠላቸው፣ ሕግ የማይመክትላቸው ናቸው ማለት ነው፤ ይህንን ክርክር ከገፋንበት ዜግነታቸውንም የምንጠራጠርበት ደረጃ ላይ እንደርሳለን፤ ደርግ በጎሣ ላይ የተመሠረተ የውትድርና ሥልጠና ያደረገ ይመስለኛልና በዚህ ጉዳይ ላይ የደርግ ባለሥልጣኖች፣ በተለይም ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አንድ ቀን የሚነግሩን ይኖራል የሚል ግምት አለኝ።

አጥቂና ጨቋኝ ነፍጠኛ የሚባለው ሕዝብ ሲጠቃና ሲበደል ከኡኡታ በቀር ድምጹ የማይሰማው ትርጉሙ የህልውና ነው? ወይስ የወኔ? በሌላ አነጋገር አማራ የሚባል ጎሣ በእርግጥ አለ? ወይስ የለም? ከአለ የሚወራለትን ነፍጠኛነትና ወኔ ምን ዓይነት ብል በላው? ይህ ክርክር ከሃያ ሦስት ዓመታት በፊት አማራ የሚባል ጎሣ አለ ብለው የሞገቱኝን ሰዎች (የሞተውን መለስንና ያሉትን ጓደኞቹን ጭምር)፣ የመላው አማራ ይባል የነበረውን ድርጅት፣ ብአዴን የሚባለውን የወያኔ ድርጅት መሠረተ-አልባነት ለማሳየት እንጂ የሌለውንና ከዚህ በፊት ተቆስቁሶ ያልተነሣውን ጎሣ ለማነሣሣት አይደለም፤ የሌለ ነገር ቢቆሰቁሱት አይነሣም,

በአለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ እነዚህን አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉትን፣ የሚገደሉትን፣ የሚሰቃዩትን ሁሉ ‹‹ሰዎች›› ብናደርጋቸውና ሰዎች ብንላቸውስ? ሰው መሆን የተፈጥሮ ነው፤ ልለውጥህ ቢሉት አይለወጥም፤ ሰው ሆኖ ተወልዶ ሰው ሆኖ ይሞታል፤ ሰው መሆናቸውን ወንጀል የማድረግ ዝንባሌ የሚኖረው ሰይጣን ብቻ ይመስለኛል።

ወይም አማራ የክርስቲያን ሃይማኖትን ተከታይነት የሚገልጽ ስያሜ አድርገን ብንወስደው የእነዚህ ሰዎች መፈናቀል፣ መገደል፣ መሰቃየትና መሰደድ ክርስቲያኖች እንዲጠፉ ለማድረግ ነው? ይህ ከሆነ አንድ ጸረ-ክርስቲያን ኃይል አለ ማለት ይመስለኛል፤ ይህ መደምደሚያ ችግር አለበት፤ ፓትርያርክና ሊቃነ ጳጳሳት ሰይሞ ጸረ-ክርስቲያን ተግባር ነጋ-ጠባ ማከሄድ አታላዩንና ተታላዩን ለመለየት ያስቸግራል።

እነዚህን አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉትን ‹‹ኢትዮጵያውያን›› ብንላቸውስ? ኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ ዜግነት ነው፤ ዜግነት አንድ ሕዝብ በደሙና በአጥንቱ የሚገነባው ነው፤ ዜግነት የሕግ ከለላ አለው፤ ይህንን የሕግ ከላላ ተነፍገው በኢትዮጵያ ምድር ከያለበት የሚፈናቀሉት፣ የሚገደሉት፣ የሚሰቃዩትና የሚሰደዱት ኢትዮጵያዊ ዜግነትን ለማጥፋት የተደራጀ ኃይል አለ ማለት ነው።

አንግዲህ አማራ የሚባሉት ነፍጥ የሌላቸው ነፍጠኞች በምድረ ኢትዮጵያ ሰዎችም ሆነው፣ ክርስቲያኖችም ሆነው፣ ኢትዮጵያውያንም ሆነው መኖር አይፈቀድላቸውም ማለት ነው ወደሚል መደምደሚያ በግድ መድረሳችን ነው፤ ያዋጣል ወይ?

ግራም ነፈሰ ቀኝ አማራ የሚባል ጎሣ እንደሌላ በስያሜው ላይ የሚደርስበትን ጥቃት ለመመከት እንኳን ባለመቻሉ አስመስክሯል፤ በሕይወት ላለ በህልውና ላይ የሚደርስበትን ጥቃት መመከትና መከላከል የተፈጥሮ ነው፤ ይህ ሳይሆን ሲቀር ህልውና የለም።

‘ክርስትና የዋህንን በአድርባይነት መርዝ እየወጉ እና እየተሽሞነሞኑ የሚኖሩበት ሕይወት አይደለም” በክርስትና ስም ”አትናገሩ” ለማለት ለሚዳዳቸው የበግ ለምድ ለባሾች ምላሽ ትሁንልኝ

$
0
0
ዛሬ (ስሙን አልጠቅሰውም) ማንነቱን የማላውቀው ግን ፋይሉ አናት ላይ ነጠላ ለብሶ የተነሳ ፎቶ በትልቁ የለጠፈ የፌስ ቡክ ገፄ አባል እንዲህ የሚል መልዕክት በውስጥ መስመር ላይ ለጠፈለኝ። ” አይ ክርስትና—–ቤተክርስቲያንን ማገልገል አይሻልህም? ” ወዘተ የሚሉ ቃላት ይዟል።ግለሰቡን ከእዚህ በፊት ስለማላውቀው ፋይሉን ከፍቼ ማየት ጀመርኩ።ፕሮፋይሉ ላይ በትልቁ ነጠላ ለብሶ የተነሳውን ፎቶ ለጥፏል።ከወደ አናቱ የሀገራችን ክፍል መሆኑን ፋይሉ ይናገራል።ወደውስጥ ገባሁ።አንዱ ክፍል ላይ አቶ መለስን ፎቶ በትልቁ ለጥፎ የአምላክ ያህል ”ውዳሴ መለስ” ድርሰት ብጤ ለጥፏል።ቀጠልኩ መጎርጎሬን በሌላ ቀን አቶ ኢሳያስን ለጥፎ ከውክሊክ ያገኘውን ታሪካቸውን ተርጉሞ ምንጭ ውክሊክ ብሎ አያይዞታል።በተለይ በእዚህኛው ክፍል ላይ አቶ ኢሳያስ ”በነፃ ምርጫ የተመረጡ በዲሞክራሲ የሚያምኑ” የሚል ጨምሮበታል። እናም ቀደም ብዬ ከቅንነት ሃሳብ የሰጠ የመሰለኝ ሰው አሳዘነኝ እና ለእርሱ እና በቤተክርስቲያን ስም ለሚያጭበረብሩ ሁሉ እንዲህ ማለት ፈለኩ።
ለወዳጄ እና ለመሰሎችህ (የማስታወሻዬ አርዕስት ነች)
138ክርስትና የማጭበርበርያ ጉረኖ አይደለም።ክርስትና እንደ እባብ እየተቅለሰለሱ የዋሃንን የሚነድፉበት የሸለምጥማጦች ጅራፍ አይደለም።ሰው በክርስትና ውስጥ ሲኖር ፍርሃት፣አድርባይነት፣ጥቅምን ማስቀደም እና እኔ ብቻ ‘ደረቴ ይቅላ ሆዴ ይሙላ’ የሚል ከሆነ ክርስቲያን ባይሆን ይመረጣል።ክርስቲያን በመንግስት ዘረኝነት ሲታወጅ ከንፈር እየመጠጠ ዘረኝነትን የሚጠየፈውን መፅሐፍ ቅዱስ ይዞ ሕዝብ ከሚያታልል እራሱን ወደ ትልቅ ባህር ቢወረውር ይሻለዋል።ክርስቲያን የሰው ዘር በሙስና እና በአድልዎ ሲሰቃይ መቃወም ካልቻለ ባይፈጠር ይበጀዋል። ክርስቲያን ሰዎች ሲሰደዱ ያሰደዳቸውን ቡድን ከመውቀስ ይልቅ በቤተ ክርስቲያን ስም በስዱዳን ቁስል ላይ የመርዝ እንጨቱን ከላከ ፍርዱ አይቀርለትም።ክርስቲያን ሰዎች ሲታሰሩ ለታሰሩት መጮህ ካልቻለ እራሱን በራሱ በሰይጣን የጥቅም አሽክላ እንደተበተበ እና ቤተክርስቲያን እየሄደ የዋሃንን የሚሸነግል ይሁዳ ቢባል ሲያንሰው ነው።
በሀገራችን ዘረኝነት ነገሰ በክርስትና ስም እንዳላዩ ያለፉ ቃል ላልተነፈስን ወዮልን፣
በሀገራችን የዋሃን ንፁሃን ምንም የተደበቀ አጀንዳ የሌላቸው መውጫ መግቢያቸው የሚታወቅ (ዞን 9 መጥቀስ ይቻላል) በግፍ ታሰሩ።በክርስትና ስም እኛ የቤተክርስቲያን ነን እያልን ቃል ያልተነፈስን ወዮልን!
በሀገራችን ሰዎች በዘራቸው እና በቋንቋቸው ብቻ እየተለዩ ከኖሩበት ስፍራ በግፍ ተባረሩ (ሐረር፣ወለጋ፣ጉርዳፈርዳ፣ጅጅጋ፣ወዘተ) አይናችን እያየ በክርስትና ስም እኛ የቤተክርስቲያን ነን እያልን ቃል ያልተነፈስን ወዮልን!
የሀገራችን ድንበር እየተቆረሰ ለባዕዳን በሙስና እና በሀገር ክህደት ተቸበቸበ።በክርስትና ስም እኛ የቤተክርስቲያን ነን እያልን ቃል ያልተነፈስን ወዮልን!
ኢትዮጵያውያን በባዕዳን እየታሰሩ በእየቦታው ሲንገላቱ ”ታስሬ አልተየቃችሁኝም” የምትለዋን ቃል ወደጎን ትተን በክርስትና ስም እኛ የቤተክርስቲያን ነን እያልን ቃል ያልተነፈስን ወዮልን! ለታሰሩት፣በዘር እና በቋንቋ አድልዎ እየተደረገባቸው ለተንገላቱት፣በኢትዮጵያዊነታቸው እየተለዩ ለሚታሰሩት መጮህ ክርስትና ነው። ክርስትና በሙስና ፊታቸው ለሚያብለጨልጩ እና በዘረኝነት ለሰከሩ እና ሃገራቸውን ለጥቅም ለሸጡ ወንጀለኞች በመቆም ወይም በአድርባይነት ዝም በማለት አይገለጥም።ክርስትና የዋህንን በአድርባይነት መርዝ እየወጉ እና እየተሽሞነሞኑ የሚኖሩበት ሕይወት አይደለም።
ጉዳያችን
ሰኔ 25/2006 ዓም (ጁላይ 2/2014)

Source: gudayachn

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለአንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታሰር ዙሪያ ተናገሩ

$
0
0

andargachew
አቶ አንዳርጋቸውን ለማስለቀቅ ባለፈው ሣምንት ውስጥ የእንግሊዝን ኤምባሲ ጨምሮ በርካታ ጥረቶች ቢደረጉም የየመን መንግሥት ግን ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሳይሆን መቅረቱንና ድርጅቱ የመሪውን ጉዳይ ወደ ሕዝብ መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ ያገኘው መሆኑን የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለቪኦኤ ገለጹ። ያዳምጡት፦

የመኢአድ/አንድነት የውህደት አመቻች ኮሚቴ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

$
0
0

የኢትዮጵያን ህዝብ የለውጥ ፍላጎት እውን ለማድረግ የመኢአድ እና የአንድነት መዋሀድ ወሳኝ የፖለቲካ ምዕራፍ ነው!!!

የኢትዮጵያን ህዝብ የለውጥ ፋላጎት ዕውን ለማድረግ የተቃዋሚው ጎራ በመሰባሰብ አንድ ግዙፍ አማራጭ ኃይል ወደ መገንባት ሊሸጋገር እንደሚገባ መላው የአገራችን ህዝብ ለረጅም ግዜ ሲያሳስብ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡

በዚሁ መሰረትም ትግሉ የሚጠይቀውን የፖለቲካ ተክለ ቁመና ለመያዝ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የደረሱበትን ወሳኝ የፖለቲካ ምዕራፍ እውን ለማድረግ ከሁለቱም ፓርቲዎች በእኩል ቁጥር የተቀወከሉ አሥር አባላት ያሉት የውህደት አመቻች ኮሚቴ ተቋቁሞ የውህዱን ጉባኤ በስኬት ለማጠናቀቅ በርካታ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

የውህደት አመቻች ኮሚቴው ሁለቱ ታርቲዎች በተናጠል የሚያካሂዱት እና በጋራ ውህዱ ፓርቲ የሚያደርገው ጉባኤ በተያዘለት ግዜ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ተግባር በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ የሁለቱ ፓርቲዎች መዋሃድ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረበት ገዥው ፓርቲም ሆነ ሌሎች አካላት በውህደቱ ሂደት ላይ ተግዳሮት ለመደቀን በርካታ ጥረት እያደረጉ እንደሆነም አስተውለናል፡፡

ስለሆነም መላው የሀገራችን ህዝብ ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተልና ገዥው ፓርቲ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ከግሉ ሚድያ ጋር ተመሳስለው አፍራሽ ተልእኮ እንዲፈጽሙ ባደራጃቸው አካላት እና ሚዲያዎች ሁለቱ ፓርቲዎች የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ የሚያደርጉትን ጥረት በማጠልሸቱ ተግባር ላይ እንዲሰማሩ እየተደረገ ያለውን ስውር ሴራ በጥንቃቄ ማየት እንደሚገባ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡

የሁለቱ ፓርቲዎች መዋቅርም ሆነ ዋነኛ ባለቤት የሆነው የውህደት አመቻች ኮሚቴው መረጃዎችን በጥንቃቄ እንደሚከታተል እና ይፋ እንደሚደረግ እየገለፅን በአጭር ጊዜ ውስጥ ውህደቱን በማጠናቀቅ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ እንደምንሸጋገር ለመላው ህዝባችን እንገልጻለን፡፡ ስለሆነም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ለውህደቱ መሳካት አስፈላጊውን የፋይናንስ፣ የማቴሪያል፣ የሞራልና የሀሳብ ድጋፍ በማድረግ ሀገራዊ ሃላፊነታችንን በጋራ እንድንወጣ ጥሪ እንቀርባለን፡፡

በ1997 ዓ.ም የታየውን የህዝብ የለውጥ ፋላጎት እና የፖለቲካ ተሳትፎ ዳግም ለመመለስ ሳንታክት እንሰራለን!!!

ከውህደት አመቻች ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ

udJ&AEUP

ሰላማዊ ታጋይዋ አንቀላፉ *

$
0
0

ፍኖተ ነፃነት 

10525627_747890138603071_4393882039106665330_nወ/ሮ ስንቅነሽ ገብረየስ አንድዬ ልጃቸውን የ1997 ምርጫን ተከትሎ በታጣቂዎች በተተኮሰበት ጥይት በግፍ ተነጥቀዋል፡፡ልጃቸውን አፈር ካለበሱ በኋላ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲን በመቀላቀል ልጃቸውን በግፍ የነጠቃቸውን ስርዓት ሲታገሉ ህይወታቸው እስካለፈበት ቅጽበት ድረስ ቆይተዋል፡፡
‹‹በዚህች አገር የስርዓት ለውጥ ሳልመለከት ሞት እንዳይቀድመኝ›› ይሉ የነበሩት ሰላማዊ ታጋይዋ ባደረባቸው ህመም ለህልፈተ ህይወት ተዳርገው በአዲስ አበባ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡
የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና መላው አባላት በወይዘሮ ስንቅነሽ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ ወይዘሮ ስንቅነሽ ሊመከተቱት ይናፍቁት የነበረው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን አስተዋእጾ እንዲወጣ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

“በእኔ ስም አይሆነም!”“NON IN MIO NOME”–ሕዝብን የጨፈጨፈ ገዳይ ጀግና አይደለም!

$
0
0

በልጅግ ዓሊ

ክፍል አንድ


ሕዝብን የጨፈጨፈ ገዳይ ጀግና አይደለም!

ልቤ ተሸበረ ከሩቅ ስትጣሪ ሰማሁሽ ሃገሬ፣
ስንቱን ብሶት ላውራሽ እናቴ ዘርዝሬ፣ . . . .

ሀገሬ ድምጽሽን ቀርቤ እንዳልሰማ ፤
አላጥፍ አልጠቀልል መሬት አይደለም ሻማ
ክል እያለ መጥቶ የዝማሬሽ ቃና
ያማልለኝ ገባ ያዘናጋኝ ገባ ከሩቄ ሆነና።

ከሩቅ ቢሆንም ድምጽሽ እንኳን አልጠፋ
ሕያው ያደረገኝ ነፍሴን ያወጀልኝ ነው የልቤ ተስፋ።

Non in Mio Nomeዮሐንስ አድማሱ
ልቤ ተሸበረ /1957

ጣሊያን ቲቮሊ ከተማ የሚገኘው ፍርድ ቤት ሜይ 6/2014 በሰዎች ተሞልቷል። ፍርድ ቤቱ ፍርዱን በሚከታተሉ በመሙላቱ ምክንያት ከፍርድቤቱ ውጭ የፋሽሽቶች ደጋፊዎችም ይሁኑ ተቃዋሚዎች ተሰባስበዋል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በስዊዘርላንድ (ፍላየር)

$
0
0

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በስዊዘርላንድ፦
andargachew tisge

ኢትዮጵያዊነትን ከቴዲ አፍሮ ጋር በኒውዮርክ እናክብር – መግቢያ ነፃ (ከዲሲ አውቶቡስ ተዘጋጅቷል)

$
0
0

ቴዲ አፍሮ በአሜሪካ የነፃነት በዓል ላይ ከሚዘፍኑ አፍሪካውያን ድምጻዊያን መካከል አንዱ መሆኑ ይታወሳል። ይህ ለሃገራችን ትልቅ ክብር ሲሆን ኮንሰርቱ ቅዳሜ ከሁለት ሰዓት ጀምሮ ይደረጋል። መግቢያው በነፃ ሲሆን ከዲሲ አውቶቡስ ይዘው መሄድ ለሚፈልጉ ተዘጋጅቷል። በበርካታ ሕዝብ ጥያቄ መሠረት ሙሉ መረጃው ይኸው፡-

Summer Stage: Central Park NY, NY
Saturday July 5th

Door Open at 2:00 PM

Free cover charge

ኢትዮጵያዊነትን ከቴዲ አፍሮ ጋ በኒው ዮርክ እናክብር – መግቢያ ነፃ ነው

Transportation from DC area: Call 201-203-3442

Teddy NY

“አንዳርጋቸው የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጂ አንድ ግለሰብ አይደለም!!!”–ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል

$
0
0

አንዳርጋቸው የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጂ አንድ ግለሰብ አይደለም!!! ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል

July 3, 2014

በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከታዩ አርቆ አሳቢ፣ አስተዋይና ብልህ ፖለቲከኞች አንዱ የሆነው ታላቁ የነፃነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለሥራ ጉዳይ ሲንቀሳቀስ የመንን እንደመሸጋገሪያ በሚጠቀምበት ወቅት በሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. በየመን ሰንዓ ከተማ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በሀገሪቱ መንግሥት ትዕዛዝ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል:: ምንም አይነት ምድራዊም ይሁን ሰማያዊ መነሻ ምክንያት ለአቶ አንዳርጋቸው በየመን መንግሥት መታገት እና መታሰር ምክንያት ሊሆን እንደማይችል እንደማይገባም በመግለጽ የየመን መንግሥት የነፃነት ታጋያችንን ባስቸኳይ እንዲለቅ ላለፉት ተከታታይ ቀናት የተደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ውጤት አላስገኘም:: ከዚህም በመነሳት አቶ አንዳርጋቸው ለዘረኛው እና ከፋፋዩ የወያኔ ቡድን ሊሰጥ ይችላል የሚለው ስጋታችን ቀን በገፋ እና ምላሽ በራቀ ቁጥር እየጨመረ መጥቷል::
andaregachew-tsege-300x498
በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል በኩል የነፃነት ታጋዩ ለወያኔ ተላልፎ መሰጠቱን መቶ በመቶ እስከምናረጋግጥበት ቅጽበት ታጋዩን የማስለቀቅ ጥረቱ መቀጠል እንዳለበት በጽኑ እናምናለን:: አንዳርጋቸውን ማሰር ይቻላል፤ ምናልባትም በዚህ ቅጽበት ተችሏል፤አንዳርጋቸውን ማሰቃየት ይቻላል፤ ምናልባትም በዚህ ቅጽበት ተችሏል፤ አንዳርጋቸውን መግደል ይቻላል። ሞትን ፈርቶ ወደ ትግል አልገባምና አንዳርጋቸውን በማሰር የአንዳርጋቸውን እንደ እቶን የሚያቃጥል የፍትህ፣ የነፃነት፣ የዴሞክራሲና የእኩልነት መንፈስ ግን ለሴኮንዶች እንኳን ማሰር አይቻልም። አንዳርጋቸውን በማሰቃየት ያን ዘመን ተሻጋሪ የሆነ የትውልዱን መንፈስ የሚገዛ የሁላችንም የምትሆን የጋራ ኢትዮጵያን የመፍጠር ንጹህ ራዕዩን ግን ፈጽሞ ማቁሰል አይቻልም!!! አንዳርጋቸውን በመግደል ዕንቁ ዓላማውን መግደል ከቶ አይቻልም፤ የታሪክ መዛግብት ገጾች ለዚህ ሃቅ በሚመሰክሩ እውነታዎች የተሞላ ነውና። አንዳርጋቸውን በመግደል “ከአባቶቹ የማይበልጥ ትውልድ እንዳልተፈጠረ ይቆጠራል፣ ልጅ አባቱን ሩጦ መቅደም አለበት፣ ስለዚህ እናንተ ወጣቶች እኛን ሩጡ እና ብለጡ ቅደሙን፣ ቀናዎች ሁኑ፣ ርስ በርስ ተዋደዱ፣ ያለፉት ትውልዶች የሰሩትን ስህተት ላለመድገም ታሪክን ከስሩ ተረዱ፣ ያለማወቅ ጠንቅ ከሚያመጣው ጥፋት ለመዳን ሁሌም ለእውቀት ጉጉዎች ሁኑ። ለማወቅ ጣሩ፣ የማይቀረው ሞታችሁ ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲ እና ለነፃ ኢትዮጵያ ይሁን” እያለ ላለፉት በርካታ አመታት ያስተማራቸው እና የኮተኮታቸው የነፃነት ታጋይ አርበኛ ወጣቶችን እና እሳት መንፈሳቸውን መግደል አይቻልም::

ታሪካዊ ስህተት በመሥራት በአዲሱ ትውልድ ልብ ውስጥ የበቀል እና የቂም ጓዝ ለማስቀመጥ እየተንደረደረ ያለው የየመን መንግሥትም ሆነ ወያኔ ሊያውቁት የሚገባው ተፈጥሯዊ ሃቅ ይህ ነው:: አንዳርጋቸውን በአንድ ካቴና በማሰር፤ በአንድ ክፍል ውስጥ በመዝጋት ወይም በአንድ ጥይት በመግደል “መገላገል” የሚቻል አንድ ግለሰብ አይደለም:: አንዳርጋቸው ለሽህ ካቴናዎች የማይታጠፉ እጆች፤ ለሽህ ማጎሪያዎች የገዘፈ ገላ፤ ለሽህ ጥይቶች የሰፋ እና ሽህ ጥይቶችን የሚተፋ ግንባር እና ደረት ያለው ብርቱ ታጋይ ነው። አንዳርጋቸው አንድ ግለሰብ አይደለም፤ የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጅ!!!

አንዳርጋቸው ለአርባ አመታት በሚጠጋ የፖለቲካ ሕይወቱ ሁሉ በረሃ የሚወረወረው አፈር ላይ የሚንከባለለው፤ በእሱ እድሜ በማይታሰብ ሁኔታ እንኳን የበረሃ ሃሩር፣ ጥም እና ረሃብ የሚያንገላታው ነገ ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት ወይ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት ለመምራት ካለው ሰዋዊ ፍላጎት አይደለም:: የሱ ምኞት የሁላችንም የሆነች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ማየት ነው!!! ይህን በተለይ የግንቦት ሕዝባዊ ኃይል አመራሮች እና መላው አባላት ጠንቅቀን እናውቃለን:: አንዳርጋቸው ሁሌ ለሚያልማት ንጽህት ኢትዮጵያ መሥራት የነበረበትን ፈታኝ እና ታሪካዊ ሥራዎች ቀድሞ አከናውኗቸዋል:: ላለፉት 6 እና 7 ዓመታት ከጥልቅ የፖለቲካ ተሞክሮው እየቀዳ ለወጣት ኢትዮጵያውያን በየበረሃው እየዞረ አስተምሯል:: እያማጠ አደራ ብሏል:: እያለቀሰ ምኞቱን፣ ፍላጎቱን እና ራዕዩን ከውስጡ አውጥቶ መዳፉ ላይ በማስቀመጥ ልቡን ለታዳጊዎች አሳይቷል:: ንጹህ ዓላማው ሽህ ባለ ራዕዮችን ፈጥሯል የተግባር ሰዎችን አምርቷል:: የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አንዳርጋቸው እንደመጥምቁ ዮሃነስ በበረሃ እየዞረ ሲያስተምር እና ሲሰብክ ከፈጠረው ንጹህ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ላይ የበቀለ ኃይል ነው::

ትናንት አብሮ ውሎ ዛሬ በድንገት መተጣጣት የትግል አንዱ ባህሪው ነውና ዛሬ አንዳርጋቸው በአካል አብሮን ላይኖር ይችላል:: ነፍሳችን ውስጥ ያሰረፀው ዘላለማዊ መንፈስ ግን እስከመጨረሻ ህቅታችን ድረስ አብሮን ይዘልቃል:: አንዳርጋቸውን በማስቆም ትግሉን አቆማለሁ ብሎ የሚያስብ ካለ ዓለምን እና ሁኔታዎችን መገንዘብ የማይችል ከራሱ የተጣላ የወያኔ አይነት ቂል ብቻ ነው:: አንዳርጋቸውን በማስቆም ትግሉን ማስቆም አይቻልም:: መንፈስን ማስቆም ከቶ ማን ይቻለዋል?? አንዳርጋቸው እኮ መንፈስ ነው:: ሁሉም ቦታ፣ ሁሉም ጫፍ ፣ሁሉም ልብ ውስጥ የሚገኝ እና የሚንሳፈፍ መንፈስ::

የየመን መንግሥት የፈጸመው ድርጊት እጅግ ስህተት መሆኑን ዘግይቶም ቢሆን ተረድቶ የነፃነት ታጋያችንን ባስቸኳይ ይለቀው ዘንድ አሁንም ደጋግመን እንጠይቃለን:: ይህ ሳይሆ ን ቀርቶ ታጋያችን ወያኔ እጅ ውስጥ ከገባ ግን የትውልዱ የበቀል ሰይፍ ከዛሬ ጀምሮ ከሰገባው መውጣቱን እንዲያውቁት እንፈልጋለን:: ወያኔም ይህ የቂል ድርጊት የነፃነት ታጋዮችን የበለጠ ቁጭት እና የበቀል እርምጃዎች ውስጥ የሚከት መሆኑን አብሮ ሊገነዘበው ይገባል:: ለዚህ ቃላችን ታሪክ ምስክር ይሁንብን::

ድል ለ ኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

(ሰበር ዜና) የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፎ ሰጠ

$
0
0

andargachew( የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው፣ የግንቦት ሰባቱ ዋና ጸሃፊና የድርጅቱ ሞተር የሚባሉት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ  ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፈው ተሰጥተዋል። አቶ አንዳርጋቸው ለትራንዚት ሰንዓ የመን በቆዩበት ጊዜ በየመን ደህንነት ሃላፊዎች  ከአሥር ቀናት በፊት የታገቱ ሲሆን፣ ድርጅታቸው ግንቦት ሰባት እርሳቸዉን ለማስፈታት ዉስጥ ዉስጡን በርካታ ጥረቶች ሲያደርግ እንደቆየም ከድርጅቱ የወጣዉ መግለጫ ይጠቁማል።

አቶ አንዳርጋቸውን ለመጎብኘት ጥረት ያደረገው የእንግሊዝ ኤምባሲ፣ በየመን አቶ አንዳርጋቸውን ለማግኘት እንዳልቻለ የገለጸዉ የደረሰን ዘገባ፣ አቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፈው የተሰጡት፣ በየመን መንግስት መያዛቸው በድርጅታቸው ለሕዝብ ይፋ ከመሆኑ በፊት እንደሆነም ለማረጋገጥ ችለናል።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከግንቦት ሰባት አባላት ዉጭ በበርካታ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ በቆራጥነታቸውና ሐሳብ አመንጪነታቸው የሚታወቁ ናቸው። በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት ፣ በቅንጅት ዉስጥ ትልቅ ተሳትፎ ያደርጉ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው፣ ለሰላማዊ ትግሉም መጽሃፍ ጽፈው ያበረከቱ አገር ወዳድ ሰው ናቸው። በወቅቱ የኢሕአዴግ መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን በዝዋይ አስሮ የነበረ ሲሆን፣ በዚያም በደረስባቸው ድብደባ አይናቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰም በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል። አቶ አንዳርጋቸው አገዛዙ በሰላም አይወርድም በሚል ሁለገብ ትግል አደርጋለውሁ የሚለው የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር አባል ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ታጋይ ናቸው።

“ትግሉ የተጀመረው አሁን ነው”–ሻምበል በላይነህ (ከአቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ መሰጠት በኋላ)

$
0
0

የኢሳት 4ኛ ዓመት በሳንሆዜ በአሁኑ ወቅት እየተከበረ ይገኛል። የአቶ አንዳርጋቸውን ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠት ተከትሎ በአዳራሹ ያለው ሕዝብ እንዳዘነ ይነበባል። ሁሉም ተቆጥቷል። አርቲስት ሻምበል በላይነህ ለታዳሚው አንድ ሽለላ ያቀረበ ሲሆን ትግሉ የተጀመረው አሁን ነው ብሏል።

ሽለላውን እና ቪድዮውን ተመልከቱ።

አሁን ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እየተናገሩ ነው፤ ቪድዮው እንደደረሰን እናቀርባለን ይመለሱ።


shambel belayeneh

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>
<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596344.js" async> </script>