Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) –ክፍል 3 ከ 3

$
0
0

azeb ግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)
የአቶ መለስን መሞት መንግስት ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም. ይፋ አደረገ። መንግስት ጥር 17 ቀን 2005 ዓ.ም. የመለስ ራዕይ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ህዝብ በሃዘን መግለጹን የሚያብራራ እና መታሰቢያ ተቋም የሚመሰረት ህግ አወጀ። የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ተቋም የገቢ ምንጭ የግል ለጋሾች፣ ገቢ ማስገኛ ፕሮግራሞች፣ የኢትዮጵያ መንግስት እና ሌሎች ምንጮች እንደሚሆኑ አዋጁ ጨምሮ አብራራ። መጋቢት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ደግሞ ህውሃት ‘የመታሰቢያ ተቋም መስራች ጉባኤ’ ተብሎ የሚጠራ ሌላ ድራማ በማዘጋጀት የኢትዮጵያ ህዝብ በአቶ መለስ ራዕይ ፍቅር መጠመዱን እና ይኽን ፍቅሩን በሃዘን መግለጹን የተለያዩ ተናጋሪዎች በጉባኤው እንዲያብራሩ አደረገ። የመታሰቢያ ተቋሙ ግቦች እና ተዛማጅ ጉዳዮችም ተነገሩ። በድርጅታዊ የሚስጢር አሰራር ቀደም ብሎ የተመረጡ የቦርድ አባላት በጉባኤው ላይ አንደ አዲስ ተመረጡ። ወ/ሮ አዜብም ፕሬዘዳንት ተደርጋ ተመረጠች። ‘መለስ እንደተሰዋ ሁሉ እኛም እስከምንሰዋ ድረስ ለመስራት ቃል እንገባለን‘ የሚል የደርግ አይነት መፈክር በማሰማት ምርጫውን መቀበሏን ገለጸች። ይኽ ድራማ የታየው በአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነበር። ይሁንና አዜብ መስፍን በጉባኤው ላይ ‘እንደ መለስ እስከምንሰዋ ድረስ እንሰራለን’ ስትል ‘እስክንሞት ድረስ አምባገነናዊ አገዛዛችን ይቀጥላል’ ማለቷ ይመስላል። አምስት ነጥቦች አነሳለሁ።

Download (PDF, 107KB)

ክፍል 1ን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ክፍል 2ን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


// ]]>

↧

↧

Sport: የቤካም እና የካራገር “ጫማ ሰቀላ”የእንግሊዛውያኑ ብቻ ሳይሆን የኛም ወሬ ሆኗል

$
0
0

david bechekam

david bechekam 2 caragherከአሰግድ ተስፋዬ
የተወዳጁ እግር ኳስ ስፖርት « ፈጣሪ » እንደሆነች የሚነገርላት ነገር ግን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ብዙም ውጤታማ መሆን ያልቻለው እንግሊዝ በተለያዩ ወቅቶች ምርጥ እግር ኳሰኞችን አፍርታለች።
ከነዚህ ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች ኮከቦች መካከል ላለፉት ሃያ ዓመታት በስፖርቱ በስኬታማነት ያሳለፈው ዴቪድ ቤካምና ከልጅነት እስከ እውቀቱ የመርሲሳይዱን ክለብ መለያ ብቻ የለበሰው ጂሚ ካራገርን ፣ ዋይኔ ሩኒን ፣ ማይክል ኦዌንና ሌሎች ተጫዋቾችን መጥቀስ ይቻላል።
ከእነዚህ ተጫዋቾች መካከል በስፖርቱ ባስመዘገበው ስኬት ግንባር ቀደም የሆነው ዴቪድ ቤካምና የሊቨርፑሉ ጂሚ ካራገር « ጫማ መስቀላቸውን» ገልጸዋል። የማንችስተር ዩናይትዱ የተከላካይ መስመር ተሰላፊው ሪዮ ፈርዲናንድ ደግሞ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን ይፋ አድርጓል።
እነዚህ ጉዳዮች የመገናኛ ብዙኃን ሰሞነኛ መሪ ዜና ቢሆኑም ልዩ ትኩረት ያገኘው የዴቪድ ቤካም ጫማ መስቀል ጉዳይ ነው።
አንጋፋውና ውጤታማው የማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ የነበሩት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ካሳደጓቸውና « ፈርጊ ቤቢስ » እየተባሉ ይታወቁ ከነበሩት መካከል አንዱ የሆነው ዴቪድ ቤካም ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በ115 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል። ለአሳዳጊው ማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ ደግሞ 394 ጨዋታዎችን አድርጓል።
የ38 ዓመቱ ቤካም « ቀያይ ሰይጣኖች » በመባል ከሚታወቀው ማንችስተር ዩናይትድ ክለብ ጋር ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችንና የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። በምስራቃዊ ለንደን የተወለደው የመሐል ሜዳ ተጫዋቹ ቤካም ከአሳዳጊው ክለብ ከተለያየ በኋላ ለስፔኑ ኃያል ሪያል ማድሪድ ፣ በአሜሪካ ሜጀር ሶከር ሊግ ተሳታፊ ለሆነው ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ፣ለጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ፣ በመጨረሻ ደግሞ ለፈረንሳዩ ሻምፒዮና ፓሪስ ሴንት ጄርሜን እግር ኳስ ክለቦች ተጫውቷል። ተጫዋቹ በጨዋታ ዘመኑ ከዩናይትድ ጋር ያነሳቸውን ዋንጫዎች ጨምሮ በጠቅላላው 19 ዋንጫዎችን አንስቷል።
ዴቪድ ቤካም በአራት የተለያዩ ሊጎች ከተለያዩ ክለቦች ጋር ዋንጫ በማንሳት ብቸኛው እንግሊዛዊ ተጫዋችም ነው።
ዴቪድ ቤካም ቀያይ ሰይጣኖቹን በተለ ማማጅነት የተቀላቀለው በአውሮፓውያኑ 1991 ሲሆን በቀጣዩ ዓመት ለዋናው ቡድን ተሰልፎ የመጫወት እድል አግኝቷል። ከአንድ ዓመት በኋላ የመጀመሪያውን የፕሮፌሽናል ተጫዋችነት ኮንትራት ፈርሟል። በኦልድ ትራፎርድ በነበረው ቆይታ ያሳየው ምርጥ ብቃቱ ዓለም አቀፍ እውቅና አስገኝቶለታል። ይህንን እውቅናውን ተከትሎም ታላላቅ ተጫዋቾችን በመሰብሰብ የሚታወቀውን የስፔኑን ሪያል ማድሪድን ተቀላቅሎ በአውሮፓውያኑ 2003 የላ ሊጋውን ዋንጫ አንስቷል።
ከስፔኑ ኃያል ወደ አሜሪካው ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ ተዛውሮ ተጫውቷል። በዚህ ክለብ በነበረው ቆይታ በውሰት ለጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ተሰልፎ የመጫወት እድል አግኝቷል። ወደክለቡ ኤልኤ ጋላክሲ ተመልሶ ዋንጫ ካነሳ በኋላ ለፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጄርሜን ፈርሞ ተጫውቷል። እንዲሁም ዋንጫ ካነሳ በኋላ ጫማ መስቀሉን ይፋ አድርጓል።
ቤካም በሦስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር ብቸኛው እንግሊዛዊ ተጫዋች ከመሆኑም በላይ በአውሮፓ ዋንጫ ለግብ የሚሆኑ በርካታ ኳሶችን በማቀበል በታሪክ ሁለተኛው ተጫዋች ነው።
«ለልጅነት ክለቤ ማንችስተር ዩናይትድ ተጫውቼ ዋንጫዎችን አንስቻለሁ። ለአገሬም ከአንድ መቶ በላይ ጨዋታዎችን ከማድረጌም በላይ በአምበልነት መርቻለሁ ። ለታላላቅ ክለቦች ተጫውቻለሁ። ይህ ለእኔ ከስኬትም በላይ ነው» ብሏል ስንብቱን ይፋ ባደረገበት መግለጫው።
«በእግር ኳስ ተጫዋችነት ሕይወቴ ካከና ወንኳቸው ተግባራት ከምኮራባቸው ነገሮች አንዱ አገሬን በአምበልነት መምራት መቻሌ ነው። የሦስቱን አናብስት መለያ በመልበሴ ከታላላቆቹ ተጫዋቾች ተርታ ከመመደቤም በተጨማሪ አገራቸውን ለሚወዱ ደጋፊዎችም የኩራት ምንጭ ሆኛለሁ። በዚህም እድለኛ ነኝ » ብሏል።
ሰዎች ሜዳ ሲገባ ያለውን ሁሉ እንደሚሰጥ ጠንካራ እግር ኳሰኛ እንዲያየኝ እፈልጋለሁ ያለው ቤካም በተጫዋችንት ሕይወቱ የረዱትን ሁሉ አመስግኗል።
የእንግሊዝ ዋና ከተማ የ2012 ኦሊምፒክ የአዘጋጅነት እድል እንድታገኝና እድሉን ካገኘች በኋላም በዝግጅቱ ወቅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገውን የቤካምን ከእግር ኳስ ዓለም መገለል አስመልክቶ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች አድናቆታቸውን ለተጫዋቹ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።
ሰሞኑን ራሳቸውን ከእግር ኳስ ተጫዋችነት ማግለላቸውን ካስታወቁት መካከል የሊቨርፑሉ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ጂሚ ካራገር ይገኝበታል። የ35 ዓመቱ ካራገር ክለቡ ሊቨርፑል እሁድ ከኩዊንስ ፓርክ ሬንጀርስ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ ላይ ከተሳተፈ በኋላ ነው ሙሉ ለሙሉ ከጨዋታ ዓለም የሚገለለው።
ካራገር በእግር ኳስ ተጫዋችነት በሊቨርፑል ባሳለፋቸው 16 ዓመታት ሁለት የኤፍኤ ፣ ሦስት የሊግ ፣ሁለት የኮሙኒቲ ሽልድና አንድ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ቢያነሳም አንድም ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ሳያነሳ ከኳስ ተጫዋችነት መገለሉ እንደሚቆጨው ተናግሯል።
« የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ
አላገኘሁም።ይህ ከፍተኛ ቁጭት ውስጥ እንድገባ አድርጎኛል » ብሏል።
ሊቨርፑል 732 ጨዋታዎችን ያደረገው ካራገር ለክለቡ በርካታ ጨዋታዎችን በማድረግ ሁለተኛው ተጫዋች መሆን ችሏል።ለሊቨርፑል በርካታ ጨዋታዎችን በማድረግ ቀዳሚ የሆነው ያን ካላጋን ሲሆን ተጫዋቹ 857 ጊዜ የመርሲሳይዱን ክለብ መለያ አድርጎ ተጫውቷል።
በቴሌቪዥን የእግር ኳስ ተንታኝ ሆኖ ለመስራት ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኘው ካራገር « ጫማውን የመስቀል » ውሳኔ ላይ የደረሰው ከ12 ወራት በፊት እንደነበረም ገልጿል።
እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ የተከላካይ መስመር ተሰላፊ ሪዮ ፈርዲናንድ ራሱን ከብሔራዊ ቡድን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።
ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን 81 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተው የ38 ዓመቱ ፈርዲናንድ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ለማግለሉ በምክንያትነት የጠቀሰው ትኩረቱን ለክለቡ ለማድረግ በመፈለጉ መሆኑን ተናግሯል። እነዚህ ተጫዋቾች ጉዳይ የሰሞኑ የዓለም የመገናኛ ብዙኃን የፊት ገጽ ዜናና መነጋገሪያ ሆነውሰንብተዋል።

↧

የ’ልማታዊው አርቲስት’ሠራዊት ፍቅሬ የኢቲቪ ፕሮግራም ታገደ

$
0
0

serawit fikre(ዘ-ሐበሻ) በሕዝብ ዘንድ “ልማታዊ አርቲስት” በሚል የመሽሟጠጫ ስያሜ ከሚጠሩት አርቲስቶች መካከል የቀድሞው የደርግ ወታደርና የአሁኑ የወያኔ ስርዓት ዋነኛ አቀንቃኝ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ፤ ለመንግስት በሚያደርጋቸው የአጎብዳጅነት ተግባራት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ የቶክ ሾው ፕሮግራም እንዲያዘጋጅ የዓየር ሰዓት ተፈቅዶላት ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል። ከአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደጠቆሙት አርቲስቱ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ ያቀርበው የነበረው ቶክ ሾው ውለታው ተዘንግቶ እንዲታገድ ተደርጓል።
“ግራና ቀኝ” የሚል ቶክ ሾው ከሌላኛው ‘ልማታዊ’አርቲስት ሽመልስ በቀለ ጋር ላለፉት 6 ወራት ሲያቀርብ የቆየው የደርጉ ወታደር ሰራዊት ፍቅሬ ይህን የዓየር ሰዓት ያገኘው ለመንግስት ባለው ታማኝነት እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም ድንገት ያቀርበው የነበረው ፕሮግራም በወያኔ ካድሬዎች በሚመራው ኢቲቪ እንዲታገድ መዳረጉ አስተተያየት ሰጪዎችን “ፍቅር አለቀ ወይ?” የሚሉ ግምቶችን እንዲሰጡ በር ከፍቶላቸዋል።
የአቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈት ከተሰማ በኋላ አርቲስቶች ጥቁር በጥቁር ለብሰው “ባለ ራዕዩን መሪ” እንዲቀብሩ በማስተባበር እንዲሁም ጥቁር በጥቁር አንለብስም ያሉና ለቅሶ አንደርስም ያሉ አርቲስቶችን “ሲያስጠቁር” (ለመንግስት በማቃጠር) ነበር እየተባለ የሚተቸው አርቲስቱ 6 ወር በቴሌቭዥን ያቀረበው “ግራና ቀኝ” ቶክ ሾው እንዲታገድ የተደረገው “አዝናኝ ፕሮግራም” አይደለም በሚል ምክንያት ነው ተብሏል። ይህ እገዳ እስከመቼ ሊቀጥል እንደሚችል እንደማያውቁ የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከባለፈው እሁድ ጀምሮ መታየት አቁሟል ብለዋል።
ኢቲቪ ወትሮም አዝናኝ ፕሮግራም አቅርቦ የት ያውቅና ሲሉ የሚተቹ አስተያየት ሰጪዎች አዝናኝ ፕሮግራም አይደለም በሚል ቶክ ሾው እንዲታገድ መደረጉ በቂ ምክንያት አይደለም በሚል ከእገዳው በስተጀርባ አንድ ነገር እንዳለ ይገምታሉ። በተለይም እንደሪፖርተርን ያሉ አፍቃሬ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ያሉ ጋዜጦች “በአቶ መለስ ስም መነገድ ይቁም” በሚል በረዥሙ ሲተቹ የከረሙት እንደሠራዊት ያሉትን ሆዳም አርቲስቶች ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች የኢቲቪ ካድሬ መሬዎች የሰራዊትን ማንነት በግልጽ ተረድተው ይሆናል ያገዱት ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
በዚህ ዜና ዙሪያ ዘ-ሐበሻ አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬን ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።
አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ በቅርቡም በአስገድዶ መድፈር አቤቱታ እንደቀረበበት መዘገቡ ይታወሳል።
የአስገድዶ መድፈር አቤቱታውን ዜና ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ለግንዛቤ ደግሞ የታገደውን የሰራዊት ፍቅሬ ሾው አቅርበናል።

↧

የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ከወዲሁ ያስመዘገባቸው ድሎች –ግርማ ካሳ

$
0
0

ግርማ ካሳ
(muziky68@yahoo.com)

ሜይ 20 ቀን 2013

semayawi party አገር ዉስጥ በሰላም የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ፣ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም፣ በአፍሪካ ሕብረት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አውጇል። ከግንቦት 15 እስከ 17 ባሉት ቀናት ደግሞ፣ ኢትዮጵያዉያን ጥቁር አልባሳት በመልበስ፣ አገዛዙ በሚያራምዳቸውን ጎጂ ተግባራት ላይ፣ ያላቸውን ተቃዉሞ እንዲገልጹ ጥሪ አስተላልፏል።

ፓርቲዉ በቅርቡ የተመሰረተ፣ ብዙ አገር አቀፍ መዋቅር ገና ያልዘረጋ፣ ተስፋ የሚሰጥና በወጣቶች የተሞላ ለጋ ፓርቲ ነዉ። ጥሪዉ ከቀረበ ገና ሶስት ሳምንት ብቻ እንደመሆኑም፣ ምን ያህል አስቀድሞ ሕዝቡን በማደራጀት አንጻር በቂ ዝግጅት እንደተደረገ ፣ ጥሪው በይፋ ለሕዝብ ከመተላለፉ በፊትም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር (እነርሱም ዝግጅት እንዲያደርጉ) ምን ያህል ዉይይት እንደተካሄደ አላውቅም። በመሆኑም በግንቦት 17 ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለመተንበይ አስቸጋሪ ነዉ።

እንደዚያም ሆኖ ግን፣ ከወዲሁ በርካታ ድሎችን ተመዝግበዋል ባይ ነኝ። የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት፣ ይሄን ጥሪ ሲያቀርቡ፣ ምን ያህል ድፍረትና ጀግንነት እንዳላቸው ለማረጋገጥ ችለዋል። ሊታሰሩ፣ ሊደበደቡ፣ ሊገደሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ። እነርሱ መካከል ያሉ፣ ብዙዎቹ ኢንጂነሮች፣ ጠበቃዎች ..ናቸው። የገዢው ፓርቲን ተቀላቅለው፣ የስርዓቱ ተጠቃሚዎች መሆን የሚችሉ ናቸው። ነገር ግን ኢትዮጵያንና ሕዝባቸውን አስቀድመዉ፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለዲሞክራሲና ለሕግ የበላይነት በመቆም፣ ከፊት በመቅደም፣ ትግል ምን ማለት እንደሆነ እያሳዩን ነዉ።

በዚህም ምክንያት፣ በፈታኝና ትእግስት አስጨራሽ ሁኔታ ዉስጥ ተኩኖም፣ አገር ቤት የሚደረገዉን የሰላማዊ እንቅስቃሴ፣ መግለጫ ከማዉጣትና ገዢው ፓርቲን ከማውገዝ ያለፈ፣ አንድ ምእራፍ ወደፊት እንዲሄድ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አድርጓል። አንድ በሉ።

ለበርካታ አመታት የዳያስፖራዉ ትኩረት አዲስ አበባ ሳይሆን አስመራ ነበር። አገር ቤት ያሉ ወገኖቻችን ምንም እንደማይሰሩ፣ መስራት ቢፈልጉም መስራት እንደማይችሉ፣ አገር ቤት የሚደረገዉ ሰላማዊ ትግል «ቅዠት» እንደሆነ ነበር የሚነገረን። ነገር ግን በቅርቡ በተለያዩ ሜዲያዎች እንዳነበብነው፣ እንደ ኢሕአፓ-ዴሞክራሲያዊና የኢትዮጵያ ሽግግር ምክር ቤት ያሉ አንጋፋ በዉጭ አገር ያሉ ድርጅቶች፣ የሰማያዊ ፓርቲ ላቀረበው ጥሪ ያላቸውን ኢትዮጵያዊና ወቅታዊ አጋርነት ገልጸዋል። በተለያዩ የፓልቶክ ክፍሎች፣ በኢሳት፣ በራዲዮኖች፣ በድህር ገጾች የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ትልቅ ትኩረት ስቦ ውይይትን ጭሯል። ይሄ ሁሉ እንግዲህ የሚያሳየዉ ዳያስፖራው ትኩረቱን አገር ቤት ወደሚደረገው የሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንዲያዞር ማድረጉን ነዉ።

በዉጭ የሚገኘው ወገን ብዙ ሊረዳ፣ ብዙ ሊደግፍ፣ ትልቅም ሚና ሊጫወት የሚችል ነዉ። ይህ ኃይል አገር ቤት ካለው ኃይል ተነጥሎ፣ አገር ቤት ከሚደረገዉ ትግል እራሱን ለይቶ መቆየቱ ብዙ ጉዳት በትግሉ ላይ አምጥቷል። አገዛዙን በእጅጉ ጠቅሟል። በሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ምክንያት፣ አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል ለመደገፍ ፣ በዳያስፖራ የሚደረገዉን እንቅሳሴ ማየታችን በራሱ ትልቅ ድል ነው። ብዙዎቻችንን አስደስቶናል። በመካከላችን የነበረዉን መከፋፈል አስወግዶ ከዚህ በፊት በቅንጅት ጊዜ እንደነበረው፣ በአንድነት እንድንሰማራ የማድረግ ትልቅ ኃይል አለዉ። ሁለት በሉ።

በድርጅታዊ መዋቅርና በአባላት ብዛት ከሰማያዊ ፓርቲ እጅግ የላቁ እንደ አንድነት ፓርቲ ያሉ በአገር ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አሉ። እነዚህ ድርጅቶች ተመሳሳይ አላማ እንዳላቸው፣ በዚያም ረገድ ሁሉንም አስተባብረው፣ የተጠናና የተደራጀ የሰላማዊ የእምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች ለማድረግ እቅድ እንዳወጡ እንሰማለን። የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ፣ በነዚህ ድርጅቶች ዉስጥ በእቅድና በጥናት ደረጃ የተቀመጡ እቅዶች ወደ ተግባራዊነት እንዲሄዱ የሚያበረታታና አሉታዊ አስተዋጾ የሚኖረው ሆኖ ነዉ ያገኘሁት። ሶስት በሉ።

የሰማያዊ ፓርቲን ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪን አስከትሎ ገዢዉ ፓርቲ እጅግ በጣም በርካታ ወታደሮች አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ እንዳስገባ እየተዘገበ ነዉ። «ከሕዝብ ሊነሳብኝ የሚችለዉን ዉጥረት እንዴት አድርጌ ነዉ የማከሽፈው?» በሚል አገዛዙ ውጥረት ላይ ሊሆን እንደሚችል አስባለሁ። እንግዲህ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ፣ ከወዲሁ ለአገዛዙ ትልቅ መልእክት እንዲደርሰው እያደረገ ነዉ። መልእክቱም «ዝም ብለን አንቀመጥም። ለመብታችን፣ ለነጻነታችን እንሞታለን። ከአሁን በኋላ አንፈራችሁም» የሚል ነዉ። ይሄም በራሱ ትልቅ ዉጤት ነዉ። አራት በሉ።

ሁለት ነገር ብዬ ላቁም። የመጀመሪያዉ ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረበዉ ጥሪ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ቢያቀርበዉም፣ ጉዳዩ ሁላችንምም የሚመለከት እንደሆነ ነው። ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት አለብን። በኢሜል፣ በስልክ፣ በኢንተርኔት፣ በቫይበር …ለምናውቃቸው በሙሉ ጥሪ እናስተላልፍ። ሰማያዊዎች ለመታሰር ተዘጋጅተዋል። እኛ ቢያንስ 5፣ 10፣ 20 አገር ቤት ያሉ ኢትዮጵያዉያንን ጥቁር አልባሳት እንዲለብሱ ማበረታት ሊያቅተን አይገባም። እንረባረብ። «አይ እኔ የማደርገዉ ምን ለዉጥ አያመጣም» በጭራሽ አንበል። ግድ የለም ማድረግ የምንችላትን ትንሿን እናድርግ።

ሁለተኛው ነጥብ፣ ይሄ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ የመጀመሪያዉ እንጂ የመጨረሻዉ እንደማይሆን ነዉ። ከአሁኑ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ትምህርት ተወስዶ፣ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት ፓርቲ፣ መኢአድ፣ አረና ትግራይ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ..የመሳሰሉ አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች በአንድ በኩል፣ እንደ ኢህአፓ-ዴ፣ የሽግግር ምክር ምክር ቤት፣ ሸንጎ ፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የመሳሰሉ በሌላ በኩል ሆነው፣ ትግሉን በማቀናጀት፣ አገረ ሰፊ፣ ተከታታይ፣ የተቀናጀ፣ በዲፕሎማሲና በሕዝብ ግንኙነት የተደገፈ፣ የተጠና፣ ሰላማዊ የእምቢተኘት ዘመቻዎች መደረግ አለባቸው፤ ይደረጋሉምም። አብረን ተያይዘን እስከሰራን ድረስ፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማሸነፋችን አይቀርም።

ሰላማዊ እንቅስቃሴ ማድረጉ የዜጎች ሙሉ አለም አቀፋዊ መብት ነዉ። አሁን ያለው ገዢው ፓርቲ የሚመጻደቅበት ግን እራሱ የማያካብረው ሕገ መንግስት ሁሉ ሳይቀር፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሙሉ መብትን ይደነግጋል። በመሆኑም አንዳንድ የገዢዉ ፓርቲ ካድሬዎች የሰማያዊ ፓርቲን እንቅስቅሴ ሊያጣጥሉት ይችላሉ። ጸረ-ልማት፣ ሽብርተኘንት፣ ጽረ-ሕገ መንግስታዊ፣ አመጽ ቀስቃሽ ወዘተ የሚሉ ክሶችን ሊሰነዝሩ ይችላሉ። ነገር ግን ይሄን በማድረጋቸው የሚነገሩን ነገር ቢኖር ዘመናዊ ፖለቲካ ያልገባቸው፣ የኋላ ቀር የጫካ ፖለቲካ የሚያራምዱና በራሳቸው የማይተማመኑ መሆናቸውን ነዉ።

ተቃውሟችን በልማት ላይ አይደለም። ተቃዉሟችን በአባይ ግድብ ላይ አይደለም። ኢሕአዴግን እንደ ድርጅት አንቃወምም። የኢሕአዴግ ደጋፊዎች ኢሕአዴግን የመደገፍ፣ በኢሕአዴግ ፖሊሲ ዙሪያ የመንቀሳቀስና የመደራጀት ሙሉ መብታቸው እንደሆነ እናምናለን። እንደዉም ኢሕአዴግን ከሚደግፉ ፣ ኢሕአዴግ በመልካም አስተዳደርና በደሞክራሲ ረገድ እንዲያሻሻል ከሚፈልጉ ጋር መነጋገር ያስፈልጋል እንላለን። (እንደዉም እንደታዘብነዉ በርካታ የኢሕ፤አዴግ ደጋፊዎች በይፋ የሚደግፉትን ድርጅት እየጠየቁ ያሉበት ወቅት ነዉ)

ነገር ግን የአገዛዙ ባለስልጣናት ሌላዉን የመርገጥ፣ የማሰር፣ የማንገላታት ፣ የማፈናቀልና የመግደል ስልጣን የላቸውም። በዚህ ረግድ የሚፈጽሙትንም እኩይ ተግባራት «ያቁሙ» ብለን ነዉ ተቃዉሞ የምናሰማዉ።

የምንቃወመው፣ ለሕንዶችን ለአረቦች መሬት እየተሰጠ፣ ዜጎችንን ከዚህ ዘር ናቸው በሚል፣ ከቅያቸው በማፈናቀል የሚደረግን አሳዛኝና ጨካኝ የዘር ማጥራት ወንጀልን ነዉ።

የምንቃወመው፣ ድሃዉ ሕዝባችን፣ ታንቆ ከአመት ወደ አመት፣ ለአባይ ገንዘብ እንዲከፍል እየተደረገ፣ ቢሊዮን ዶላሮች ከአገር ቤት መዘረፋቸውን፣ በቱባ የአገዛዙ ጀነራሎችና ባለስልጣናት፣ በአደባባይ ኬት እንዳመጡት በማይታወቅ ገንዘብ የሚሰሩት ፎቆችንና የሚያንቀሳቀሱ ቢዝነሶችን ነዉ።

የምንቃወመው ዜጎች በአገራችን ብእር ስላነሱ ብቻ፣ ወይም «በሃይማኖት ጉዳይ መንግስት ጣልቃ አይገባ» በማለታቸው፣ ሽብርተኞች እየተባሉ በግፍ መታሰራቸውን ነዉ።

እንግዲህ መብቴ ተረገጠ የሚል ኢትዮጵያዊ ካለ ፣ ይነሳ። መብቱንም ያስከብር።

↧

ሕልምና የኢትዮጵያ ፖለቲካ በተቃራኒው ይተረጎማል

$
0
0

ከኤፍሬም እሸቴ

Melaku-Fenta-and-Gebrewahid-Woldegiorgisየሰሞኑ ትልቁ አገርኛ ዜና (ቢያንስ በዳያስጶራው ዓይን) የመንግሥት ባለሥልጣናት በሙስና ምክንያት መያዝና መታሰር እንዲሁም የባሕር ዳሩ ሰላማዊ ሰዎች ግድያ ጉዳይ ነው። አገር ቤት የማይነበቡት ድረ ገጾችና የጡመራ መድረኮች (ብሎጎች)፣ የአካባቢ ሬዲዮኖችና ማኅበራዊ ድረ ገጾች (ለምሳሌ ፌስቡክና ትዊተር) የሚያወሩት ስለዚሁ ነው።

አጀንዳ አንድ
የባሕር ዳሩ ግድያ ከወንጀልነቱ በላይ ትልቅ መወያያ ሆኖ የሰነበተው የገዳዩ ማንነት ጉዳይ ነው። ገዳዩ የፌዴራል ፖሊስ አባል መሆኑ የተለያዩ መላምቶችን፣ ግምቶችን፣ ትርጉሞችን እያሰጠ ሁሉም በፈለገው መልክ እንዲተችበት ዕድል ሰጥቶ ሰንብቷል። የፖለቲካ ልዩነቶች ብቻ ሳይሆኑ የብሔረሰብ ማንነቶችም እየተነሡ “ገዳዩ ከዚህ ብሔረሰብ ነው፤ ከዚያ ብሔረሰብ ነው” በሚል ጥሩም መጥፎም አስተያየቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። መንግሥትን እና መሠረቱን የሚደግፉት በአንድ በኩል፣ ተቃዋሚዎቹ እና በተለይም የዘር-ፖለቲካን አምርረን እንቃወማለን የሚሉት በሌላ በኩል የሐሳብ ጥይቶች ሲያስወነጭፉ ነበር።

ዝግ እና መተንፈሻ የሌለው ማኅበረሰብ እና ነጻ ማኅበረሰብ ተመሳሳይ አደጋዎችን የሚያስተናግድበት መንገድ እንዴት እንደሚራራቅ ጥሩ ማሳያ ሆኖልኛል። ዝግ እና መተንፈሻ የሌለው ማኅበረሰብ የሌለው ያልኩት ነጻ ሚዲያ የሌለበትን የኛን አገር መሆኑ ግልጽ ነው። ነጻ ማኅበረሰብ ያልኩት ነጻ ሚዲያዎች ያሉበትን እንደሆነው ሁሉ።

Christopher Jordan Dorner የተባለ የሎስ አንጀለስ ከተማ ፖሊስ እና የቀድሞ የጦር ሠራዊት ባልደረባ በሥራ ቦታው በገጠመው አለመግባባት ሰበብ አራት ሰዎችን ገድሎ ለሳምንት ያህል አካባቢውን ሲያሸብር ቆይቶ በመጨረሻ ራሱን እንዳጠፋ መቸም ሳትሰሙ አልቀራችሁም። ከጥር 26 – የካቲት 5/2005 ዓ.ም ድረስ አካባቢውን አሸብሮት ነበር። የታጠቀ ነው። ፖሊስ ብቻ ሳይሆን ወታደርም ነው። የሰለጠነ። በጠላት ላይ ማዞር ያለበትን ጠመንጃ ወደራሱ ዜጎች ሲያዞር እንዴት እንደሚዘገንን መገመት ይቻላል።

ግለሰቡ የሥራ ባልደረቦቹን ከገደለ በኋላ ተሰወረ። ሐሰሳ ተጀመረ። ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን ይሰጡ ነበር። ቀንም ሌሊትም ሲፈለግ ቆየና በሰዎች ጥቆማ ያለበት ተደረሰ። ከዚያም ራሱን አጠፋ። በቃ። ጉዳዩ በዚሁ አበቃ። ስለ ሰውየው ማንኛውንም ዓይነት ማብራሪያ ለሚፈልግ ሰው መረጃዎቹ በስፋት አሉ። ማነው? የት ተወለደ? አደገ? መቼ ወደ ጦሩ ተቀላቀለ? እንዴት ከዚያ ወጥቶ ፖሊስ ለመሆን በቃ? ከባልደረቦቹ ጋር ለምን ተጣላ? ለምን ወደዚህ ዓይነት ወንጀል ሊገባ ቻለ? ወዘተ።

ባሕር ዳርስ? ባሕር ዳር ላይ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ብዙ ሰዎችን ገደለ። ከዚያ … ውዥንብር። ግማሹ 12 ሰው ተገደለ ይላል፣ ሌላው ደግሞ 18 ያደርሰዋል። ሰውየው ማን ነው? መቼ ፖሊስ ሆነ? ለምን ወደ መግደሉ ሊገባ ቻለ? ግድያውን በአጭሩ ማስቆም አይቻልም ነበር ወይ?

ችግሩ ምንድር ነው? ሚዲያ የለም፤ የግል ጋዜጣና ቴሌቪዥን የለም፣ የመንግሥቱም ቢሆን ለዚህ ዓይነቱ ነገር ዝግ ነው። … ነጻ ሚዲያ ሲጠፋና ትክክለኛ መረጃ ሲታጣ በመካከል ምን ይነግሣል? ግምት፣ ውሸት፣ ሽብር፣ ጥርጣሬ። ቢያንስ በዳያስጶራው ሚዲያዎች እና በማኅበራዊ ድረ ገጾች የነበረው እንደዚያ ነው። (‘ዳያስጶራ ልማዱ ነው’ ካልተባለ በስተቀር)።

እንዲህ ዓይነቱ አደጋ ሲከሰት የመጀመሪያው እንዳልሆነ የሚናገሩ ሰዎች አጋጥመውኛል። ሌላም ቦታ የተከሰተ ከነበረ ሊቀጥል እንደማይችል መተማመኛ ማግኘት ይከብዳል። አዕምሯቸው የተቃወሰ መሣሪያ የያዙ ሰዎች መኖር የየትኛውም አገር ችግር ይመስለኛል። ችግሩ ተመሳሳይ ከሆነ መፍትሔውም ከሌላ ትምህርት ሊወሰድበት የሚችል ነው ማለት ነው። በባሕር ዳሩ ጉዳይ እንዳየኹት ግን ዜጎችም ይሁኑ የመንግሥት ሰዎች ነገሮቹን የተመለከቱበት አቅጣጫ ከተለመደው ከዚያው አሰልቺ የአገራችን የዘር-ፖለቲካ አንጻር ብቻ መሆኑ ያሳፍራል።

ለምሳሌ የብዙ ሰው ጥያቄ የ“ፌዴራል ፖሊስ” አባል ከሆነ፣ እነዚህ ፖሊሶች ደግሞ የሰውን ሰብዓዊ መብት በመግፈፋቸው እንጂ ሰላም በማስከበራቸው የሚታወቁ ካልሆነ፣ ግድያው ከተለመደው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አንጻር እንጂ ከወንጀልነቱ አንጻር የተሰጠው ግምት አናሳ ነበር። እንዲያውም ሆን ተብሎ የተፈጠረ የመንግሥት የማሳሳቻ ዘዴ ሆኖም ተተችቶበታል።

አጀንዳ ሁለት
በተመሳሳይ መልኩ የሰሞኑ ትልቅ አጀንዳ የሙስናው እና በሙስናው ምክንያት የተባረሩት ጎምቱ ባለሥልጣኖች ጉዳይ ነው። የባሕር ዳሩን ማስቀደሜ ከምንም ነገር በላይ ክቡሩን የሰው ሕይወትን መጥፋት የተመለከተው ዋነኛ በመሆኑ ነው። በተጨማሪም እንዲህ ዞር ያለበት “ቱቀማ” ሰው ተነሥቶ በየመንገዱ ሲገድል ቢያንስ በእኛ አገር የተለመደ ስላልሆነ ነው። (ቱቀማ (ኦሮምኛ)= ንክ (አማርኛ))።

Berhan Hailuግንባራቸው የማይፈታው ብርሃን ኃይሉ በአቅም ማነሥ (የጉልበት ሥራ መሰለ አይደል?) ከሥልጣናቸው ሲባረሩ መልከ መልካሙ አቶ መላኩ ፈንታ (በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር)፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ገብረ ዋሕድ ወልደ ጊዮርጊስና የባለሥልጣኑ ዋና ዓቃቤ ሕግ አቶ እሸቱ ወልደሰማያት በፀረ ሙስና ኮሚሽንና በብሔራዊ መረጃ ማዕከል ሰዎች መታሠራቸው ተነግሯል። በሙስና ምክንያት፤ ስኳሯ ላይ ተገኝተው ነው ተብሏል። በዝርዝር ምን እንደሆነና ምን እንደተደረገ የአደባባይ ምሥጢር ስለሆነ ደግሞ ማተቱ አንባቢን ማድከም፣ ቦታ ማበላሸት ነው። ጥያቄው እኛ ዜጎች ዜናውን እንዴት ነው የተቀበልነው የሚለው ላይ ነው።

በሙስና ምክንያት ተይዘው ከታሠሩት ከአቶ ታምራት ላይኔ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ መንግሥት በሙስና አሰርኳቸው የሚላቸውን ሰዎች የታሰሩበት ምክንያት በርግጥም ሙስና ነው ብሎ የሚቀበል ብዙ ሰው አይደለም። ታምራት ላይኔም ሆኑ ስዬ አብርሃና ቤተሰቦቻቸው ብሎም እነ መላኩ ፈንታ ሙስና ውስጥ አልገቡም ብሎ የሚከራከር እንደሌለው ሁሉ ዋነኛ የመታሰራቸው ሰበቡ ግን ሙስናው ነው የሚል አይገኝም። በሙስና መታሰር ቢኖር እነ እንትና መቅደም አልነበረባቸውም ተብሎ ስም መጥራት ሲጀመር በአሳሪዎችና በታሳሪዎቹ መካከል ልዩነት ይጠፋል።

በሙስና ሰበብ ከማሰር የደርጉ “የፍየል ወጠጤ” ዘፈን ይሻላል?
ለመናገር ከመፍራት ካልሆነ በስተቀር የኢሕአዴግ መንግሥት ተቃዋሚዎቹን የማስወገጃ ዘዴ ሕጋዊ የሚመስሉ ሕገወጥ ተግባሮች ናቸው። ለምሳሌ በሙስናና በአሸባሪነት ስም ወህኒ ማውረድ። ደርግ ምን ያደርግ ነበር ብንል የማይፈልጋቸውን ሰዎች “የፍየል ወጠጤ” የሚለውን ልብ ነቅናቂ ዘፈን አስቀድሞ ከዚያ በግልጽ ይገድል፤ ያስር ነበር። ሙስና የዘመናችን የፍየል ወጠጤ ናት ማለት ነው? ከሆነ አይቀር አንድኛውኑ የፍየል ወጠጤው ይሻላል። ከጀርባ ከመመታት እያወቁት ከፊት ለፊት መመታት።

“ኮንስፒረሲ ቲዮሪ” የሚወድ ባህል መፍጠር፣
እውነተኛው ምክንያት ሆኖ ለሰበቡ ግን ሌላ ነገር መፍጠር ቀስ በቀስ አዲስ ልማድ እየሆነ ነው። በሙስና ስም የፖለቲካ ልዩነትን ማስተንፈስ ሲለመድ ነገ በትክክሉ ሙስና የፈጸሙ ሰዎች ለወንጀላቸው ሐዘኔታ የሚሰማው ሰው እንዲያገኙ መንገዱ ይመቻችላቸዋል። በርግጥም ሙሰኞቹን ከፖለቲካ መብት ተከራካሪዎች ለይቶ መመልከት ይከብዳል።

አሸባሪ የሚባለውን ቃልና ሐሳብ በዚሁ አገባብ ልንመለከተው እንችላለን። የፖለቲካ ልዩነት ያላቸው፣ መብታቸውን የጠየቁ ሰዎች ‘አሸባሪዎች” ሲባሉ ትክክለኞቹን ከአሸባሪው መለየት ከባድ ይሆናል። በዚህ መምታታት ውስጥ የሚያድጉ ልጆች ምን ዓይነት መረዳት ይዘው እንደሚያድጉ ፈጣሪ ይወቀው።

ተኩላ ሳይመጣበት ለቀልድ “ኡኡኡ ድረሱልኝ፣ ተኩላ በጎቼን ፈጀ” ያለው እረኛ ታሪክ አይመጣባችሁም? ለቀልድ ያለው እውነት ሲሆን ረዳት ያጣው ልጅ ታሪክ። ዛሬ ሙሰኛ እና አሸባሪ የተባሉት ነጻ ሆነው እውነተኞቹ ሙሰኞችና አሸባሪዎች መያዝና ለፍርድ መቅረብ ሲጀምሩ ይኼ መንግሥት እንዴት ተአማኒነት ይኖረዋል? አልቅሶ ቢነግረንም አናምነውም ያኔ። በየራሳችን የኢሕአዴግ “ኮንስፒረሲ” እንደሆነ ስለምንገምት።

ለጥቂት ጥቅም ትልቁን አጥር መናድ
የፍየል ወጠጤው ይሻላል ስል የመግደል ጥሩ ኖሮት አይደለም። የደርጉ እንስሳዊ የጭካኔ በሽታ ከዚያው ዘመን ወደ ሌሎች ዘመኖች የማይተላለፍ ስለሆነ እንጂ። ሕግን የተንኮል ማከናወኛ ስናደርጋት ግን በሽታው በዚያ የማይቀር ተላላፊ እናደርገዋለን። በአገራችን ሕጋዊ ተቋማት ስም የሚፈጸሙ ተንኮሎች ተላላፊ በሽታ ይሆናሉ።

በግብጽ ሆስኒ ሙባረክ ወርደው መሐመድ ሙርሲ ቢመጡም የፖሊሱ ችካኔ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ጭካኔ ያልተሻሻለው ለምንድነው? ሕጋዊ ተቋማቱ ሕገወጥነትን ስለተለማመዱና የተላላፊው በሽታ ተጠቂዎች ስለሆኑ ነው። ኢሕአዴግ ጊዜያዊ ድል ለማግኘት ትልልቅ አጥሮችን መናድን ሕጋዊ አድርጎታል። ዛሬ የተናዱትን የሕግ፣ የባህልና የሥነ ምግባር አጥሮች ዳግም መገንባት ቀላል አይሆንም። በጥቂት ዓመታት እንደተናዱት ማደሱም እንዲሁ በጥቂት ዓመታት የሚሳካ ላይሆን ይችላል። … ነገ ያስፈራል።

የመንግሥት ርምጃዎች ትክክል መሆን አለመሆናቸውን ማን ባጣራልን?
ከዚህ ችግር ልንተርፍ የምንችለው እና መንግሥትም ቢሆን የሚናገረው ነገር በርግጥም እውነት እንዳለው ሊያጣራለት የሚችለው እውነታ-አንጣሪ (Fact-checker ለሚለው የሚለውን ነው የተረጎምኩት) ሚዲያው እና መያዶች (መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ነበሩ። ከእነርሱ ጋር ደግሞ ዓይንና ናጫ፣ እሳትና ጭድ ሆነ። በደርግ ዘመን እንኳን ከመጥፋት የተረፉ መያዶች ከኢሕአዴግ ግን አልተረፉም። እነርሱን ባጠፋ መጠን ራሱን እየጎዳ መሆኑ ከቀን ቀን ግልጽ እየሆነ ነው። ስለ ሀገር እና ስለ መጪው ትውልድ ሲባል ኢሕአዴግ ያፈረሰውን መገንባት መጀመር አለበት። መንገዱንና ሕንጻውን መገንባት ብቻ አገር መገንባት አይሆንም። መንገዱና ሕንጻው ለኢትዮጵያዊው ይገነባለታል እንጂ እኛ ዜጎቹ ለመንገዱና ለሕንጻው አንኖርም። አለበለዚያ አዲስ ነገር በተከሰተ ቁጥር የራሳችንን መላ ምት እየሰጠን “ሕልምና የኛ አገር ፖለቲካ እንደፈቺው” ሆኖ ይቀራል።

ይቆየን፣ ያቆየን

↧
↧

Health: ራስ ምታት! ዓይነቶቹ፤ ምልክቶቹና ህክምናው

$
0
0

head heckራስምታትን የማያውቀው ሰው የለም ለማለት ያስደፍራል፡፡ በህክምና ከጭንቅላት የሚነሳ ማንኛውም ህመም (የአይንና ጆሮ ህመምን ሳይጨምር) እንዲሁም ከኋላ በኩል ካለው የአንገት ክፍል መነሻ የሚነሳ ህመም፣ የራስምታት ይባላል፡፡ የራስምታት በራሱ በሽታ ሊሆን ይችላል፡፡ የበርካታ በሽታዎች ምልክት ሆኖም ይከሰታል፡፡ አንዳንዴ የራስ ምታት የገዳይ በሽታዎች ምልክት የሚሆንበት አጋጣሚዎች አሉ፡፡ የራስምታት በራሱ በሽታ ሲሆን፣ ሶስት አይነት መልክ ይኖረዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በህብረተሰባችን በብዛት የሚታወቀው ሚግሬይን የሚባለው የራስምታት ነው፡፡ ሌሎቹ (tension headache) እና (Cluster headache) ይባላሉ፡፡
ከሶስቱ የራስምታት ዓይነቶች (tension headache) ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ በብዛት ይታያል፡፡
ሚግሬይን የራስምታት (migraine headache) ከ (tension headache) በመቀጠል ከፍተኛ ስርጭት አለው፡፡ ይህኛው የራስምታት አይነት ህፃናትንና አዋቂዎችን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ከጉርምስና ወቅት በፊት ሁለቱም ፆታዎች እኩል በዚህ ህመም እንደሚጠቁ የሚታወቅ ሲሆን፣ ከዚህ ዕድሜ በኋላ ግን በአብዛኛው ሲጠቁ የሚታዩት ሴቶች ናቸው፡፡ ከጠቅላላው ህብረተሰብ፣ ከወንዶች 16 በመቶ፣ ከሴቶች ደግሞ 18 በመቶ የሚሆኑት ይህ አይነት የራስምታት ይታያባቸዋል፡፡
ክላስተር የራስምታት (cluster headache) የሚባለው ስርጭቱ በጣም አነስተኛ (0.1 በመቶ) ሲሆን፣ 85 በመቶ የችግሩ ተጠቂዎች ወንዶች ናቸው፡፡
ሚግሬይን፣ ስር ሰደድ የሆነ የራስምታት አይነት ሲሆን በዘር የሚተላለፍበት እድልም አለ፡፡ የራስምታቱ የሚያናጋ እና የመውቀጥ አይነት ከፍተኛ የህመም ስሜት ይፈጥራል፡፡ ይህ አይነቱ የራስምታት በአብዛኛው በአንድ የጭንቅላት ክፍል ላይ ይበረታል፡፡ አንዳንዴ በግንባር አካባቢ፣ ሌላ ጊዜ በአይን ዙሪያ እንዲሁም በአንገት ጀርባ አካባቢ የህመም ስሜቱ ይፈጠራል፡፡ በአብዛኛው ሕመሙ የጭንቅላትን ቀኝ ወይም ግራ ክፍል የሚያጠቃ ሲሆን፣ ሁለቱንም የጭንቅላት ክፍል የሚያጠቃበት እድል አነስተኛ (ከጠቅላላው 1/3ኛው) ነው፡፡ ህመሙ አንዴ በቀኝ ቆይቶ በግራ የጭንቅላት ክፍል መፈራረቁ በተለይ የሚለይበት ፀባይ ሲሆን፣ በአንድ በኩል ብቻ ከቆየ (ከተደጋገመ) ከሚግሬይን የራስምታት ውጪ የሆኑ በሽታዎች (ለምሳሌ የጭንቅላት ዕጢ) መጠርጠር ይበጃል፡፡ የሚግሬይን የራስምታት የአካል እንቅስቃሴ ሲኖር (ለምሳሌ ደረጃ መውጣት) የሚቀሰቀስ አይነት ነው፡፡ ከየራስምታቱ ጋር ማቅለሽለሽና ማስመለስ፣ ተቅማጥ፣ የፊት አመድ መምሰል (መንጣት)፣ የእጅ እግር መቀዝቀዝ እንዲሁም በብርሃንና በድምፅ በቀላሉ የመረበሽ ምልክቶች ይታያሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ሚግሬይን የራስምታት ያለባቸው ሰዎች ብርሃንና ድምፅ ሽሽት በጨለማና ረጭ ባለ ቦታ መሆንን ተጠቂዎችና ቤተሰቦቻቸው ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክቶቹ ሲታዩ፣ የራስምታቱ ሊጀምር እንደሆነ በሚገባ ያውቃሉ፡፡
ሃያ በመቶ በሚሆኑ የበሽታው ተጠቂዎች ደግሞ ከራስምታቱ ትንሽ አስቀድሞ የሚከሰት እንዲሁም አንዳንዴ ከራስምታቱ ጋር አብሮ የሚቀጥል (aura) የሚባል ምልክት ያሳያሉ፡፡ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ደግሞ ምልክቶቹ (aura) ከራስምታቱ ውጪ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ እነኚህ ምልክቶች ከዕይታ ማዕከል ጀምሮ ወደ ውጪ የሚሄድ የተለያየ ቀለማት ያለው ብልጭታ፣ በእይታ ክልል ውስጥ ማየት የማይቻልበት ክብ ስፍራ መፈጠር ናቸው፡፡ ቀላል የሚባለው (aura) ምልክቶች፣ በአንዱ እጅ ላይ፣ በአፍና አፍንጫ አካባቢ፣ የራስምታቱ በተፈጠረበት የጭንቅላት ጎን የመጠቅጠቅ ስሜት መኖር ናቸው፡፡ የሚግሬይን የራስምታት ተጠቂ፣ ህመሙ ከተወው በኋላ ለሃያ አራት ሰዓታት ያክል የአቅም ማጣት፣ በድምፅና ብርሃን የመረበሽ ምልክቶች ያሳያል፡፡ በዚህ ጊዜ አንዳንድ የህመሙ ተጠቂዎች፣ ህመማቸው ሊያገረሽም ይችላል፡፡
ክላስተር የራስምታት (cluster headache)፣ በአንድ ሳምንት ወይም ወር ላይ ተጠቂውን በተደጋጋሚ አጥቅቶ፣ ከዚያ የወራት ወይም ዓመታት እረፍት ሰጥቶ እንደገና በመምጣት ይታወቃል፡፡ (cluster headache) ሲከሰት በቀን ሁለት ጊዜ ተጠቂውን የሚያሰቃይ ሲሆን፣ አንዴ የተከሰተው ህመም ከሰላሳ ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ተኩል ቆይቶ ይጠፋል፡፡ ህመሙ በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት በመምጣት ይለያል፡፡ ተጠቂውን ከእንቅልፍ የሚቀሰቀስበት ሁኔታም የተለመደ ነው፡፡ እጅግ ሰቅጣጭ አይነት ሲሆን፣ አንዱ አይን አካባቢ ወይም ከአይን ጀርባ የተፈጠረ ይመስላል፡፡ አንዳንድ የበሽታው ተጠቂዎች፣ ህመሙን ‹‹አይኔ ውስጥ እሳት ተቀምጧል›› በማለት ይገልፁታል፡፡ የተጠቃው አይን ይቀላል፣ ያነባል፡፡ ህመም በተፈጠረበት የጭንቅላት ጎን (ወይም አይን) ያለው የአፍንጫ ክፍል (ቀዳዳ) ይታፈናል፣ እንዲሁም ንፍጥ ይወጣዋል፡፡ የዚህኛው አይነት የራስምታት ተጠቂዎች፣ ከሚግሬይን የራስምታት ተጠቂዎች በተቃራኒው ይቅበዘበዛሉ፣ ከወዲህ ወዲያ ይራወጣሉ፤ ጭንቅላታቸውን ከግድግዳ ጋር ያጋጩታል፡፡
የራስምታት በራሱ ጊዜ ሲከሰት (የበሽታ ምልክት ካልሆነ) ምክንያቱ የአንጎል የደም ስሮች መስፋትና በዚሁ የተነሳ በአንጎል ውስጥ በደም ስሮች አካባቢ ያሉ የነርቭ ስሮች፣ ከሰፉት የደም ስሮች በብዛት በሚወጡ ኬሚካሎች መለብለባቸው ነው፡፡ ይህ የነርቮች መቆጣት ነው እንግዲህ የራስምታት የሚባለው፡፡ እንደ ሜግሬይን ያሉ የራስምታት አይነቶች ከራስምታት ውጪ በሆኑ በተለያዩ ምልክቶች፣ ለምሳሌ ማስመለስ እና ማቅለቀሽለሽ የመታጀባቸው ምስጢር ደግሞ የራስምታቱ ጠቅላላውን የነርቭ ስርዓት ማወክ መቻሉ ነው፡፡ ለምሳሌ ሚግሬይን የራስምታት የሰውነትን (sympathetic nervous system) ያውካል፡፡ ይህ የነርቭ ስርዓት ሲነቃቃ (ሲታወክ) ደግሞ በስሩ ያሉ የሰውነት ስርዓቶች (ለምሳሌ የምግብ መፍጨት ስርዓት) ይታወካል፡፡ ለዚህም ነው ከሚግሬይን የራስ ምታት ጋር ብዙ አይነት የጤና መቃወስ ምልክቶች የሚታዩት፡፡
የበሽታ ምልክት ተደርጎ የሚቆጠረውን የራስምታት የሚያመጡ የተለያዩ ምክንቶች አሉ፡፡ በጭንቅላት ላይ ደረሰ አደጋ፣ በአንጎል ውስጥ የሚፈጠር ብግነት፣ የአንጎል ደም ስሮች ውስጥ የሚከሰት ጓጓላ፣ የአንጎል የደም ስሮች መለጠጥ፣ መሳሳትና መፈንዳት፣ በድንገት ከፍተኛ ደረጃ የሚደርስ የደም ግፊት፣ የጭንቅላት ላይ የደም ስሮች መብገን፣ በአይን ውስጥ ድንገት የፈሳሽ ግፊት መጨመር (ግላውኮማ)፣ በተደጋጋሚ ለካርቦን ሞኖክሳይድ ጋዝ መጋለጥ፣ የፓርኪንስንስ በሽታ፣ ጭንቀትንና ደም ግፊትን ለማከም የሚውሉ አንዳንድ መድሃኒቶች፣ ያለ ሐኪም የሚታዘዙ የራስ ምታት መድሃኒቶችን ያለ አግባብ መጠቀም፣ አንዳንድ የልብ ህመሞች (cardiac ischemia)፣ የአንጎል ውስጥ እጢ፣ ማጅራት ገትር፣ የመሳሰሉት ሁኔታዎች የራስ ምታት ያመጣሉ፡፡ የበሽታ ምልክት ተደርጎ የሚታየው የራስምታት፣ ለህይወት አስጊ የሆኑ እንደ የአንጎል እጢ፣ ማጅራት ገትር፣ በአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ ችግሮች ጠቋሚ ሊሆን ሲችል፣ ቀላል የሚባሉ ችግሮች እንደ ቡና ሱስ የማሳሉትንም ሊያሳይ ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን የበሽታ ምልክት የሆነው የራስምታትና ራሱ እንደ በሽታ የሚቆጠረው የራስምታት (migraine, clusture, tension) ተቀላቅለው በአንድ ሰው ላይ የሚታዩበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ለምሳሌ (tension headache) ወይም በበሽታ ምክንያት የሚመጡ የራስምታት የሚግሬይን የራስምታትን ሊቀሰቅሱ ብሎም አብረው ሊታዩ ይችላሉ፡፡
የራስምታት አይነቶችን ለመለየት እንዲሁም የበሽታ ምልክት ይሁን ወይስ በራሱ በሽታ፣ ለመለየት የሚደረጉ የተለያዩ ምርመራዎች አሉ፡፡ በተለይ በበሽታ ምክንያት የሚታየውን የራስምታት መንስኤ ለማወቅ እንደ (MRI, CT scan) የማሳሰሉት መሳሪያዎች ወሳኝ ሲሆኑ፣ የደም ምርመራ ማድረግም ለራስምታቱ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ ችግሮችን (የማጅራት ገትርን ጨምሮ) ለመለየት ያስችላል፡፡ የራስምታትን መንስኤ በተለያዩ መሳሪያዎችና የላብራቶሪ ምርመራዎች መለየት ቢቻልም ሐኪም የሚያደርገው የአካል ምርመራና ከበሽታው የሚወሰደው መረጃ ግን በሽታውን ለመለየት ምትክ የለሽ ነው፡፡
የራስ ምታት እንዴት ይታከማል?
በሌሎች በሽታዎች የተነሳ የሚመጣውን የራስምታት ለማከም፣ በመጀመሪያ የራስምታቱ መንስኤ የግድ መለየት ይኖርበታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ የራስምታቱን ነጥሎ ማከም መሞከር ግን ስኬታማ ካለመሆኑም በላይ፣ መንስኤዎቹ ስር እንዲሰዱ ጊዜ ይሰጣል፡፡ የራስምታት በራሱ እንደ በሽታ ከሆነ ግን የተለያዩ ህክምናዎች የራስምታቱን ብቻ ለማጥፋት ይሰጣሉ፡፡
የሚግሬይን የራስምታትን ለማከም፣ እንደ የራስምታቱ ክብደት የተለያዩ መድሃኒቶች ይሰጣሉ፡፡ ቀለል ላለ የሚግሬይን የራስምታት፣ ያለ ሐኪም ትእዛዝ የሚወሰዱ እንደ ፓራሲታሞል፣ አስፕሪን፣ ዳይክሎፊናክ፣ ኢንደሜታሲን፣ አይቡፕሮፊን የመሳሰሉ መድሃኒቶችን መውሰድ ይቻላል፡፡ ቢሆንም ህፃናት እና በአስራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆች አስፕሪን ባይወስዱ ይመረጣል፡፡ የጨጓራ በሽተኞችም ከፓራሲታሞል ውጪ ያሉትን የህመም ማስታገሻዎች ከመውሰዳቸው በፊት ሐኪማቸውን ማማከር ይገባቸዋል፡፡ የጉበትና የኩላሊት ህመምተኞችም የራስምታት መድሃኒቶችን ያለ ሐኪም ትዕዛዝ መጠቀም የለባቸውም፡፡
ከበድ ላለ ሚግሬይን እንደ ergotamine ያሉ መድሃኒቶች ተመራጭ ናቸው፡፡ የሚግሬይንን የራስምታት የሚቀሰቅሱ የተለያዩ ሁኔታዎች ለምሳሌ፣ ጭንቀት፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ፆም፣ አብረቅራቂ ነገሮችን መመልከት፣ አንዳንድ ሽታዎች፣ የሲጋራ ጭስ፣ አልኮል መውሰድ፣ ቸኮሌት፣ ቡና ወዘተ… ማስወገድ ህመሙ አስቀድሞ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡ የዚህ ህመም ተጠቂ ህመሙን የሚቀስቅስበት ምን ሁኔታ ወይም ነገር እንደሆነ ለይቶ በማወቅ ቀስቃሹን ነገር ወይም ሁኔታ ማስወገድ ይኖርበታል፡፡
ክላስተር የራስምታት ለማከም የተለያዩ ህክምናዎች አሉ፡፡
አንዴ የጀመረውን ህመም ለማስቆም መቶ በመቶ የሆነ የኦክስጅን ጋዝ ከ8-10 ሊትር በደቂቃ ለዚሁ በተዘጋጀ ማስክ አማካይነት ከ10-15 በመተንፈስ፣ ጎን ለጎንም የ(triptan) ወይም (ergot) ዝርያ መድሃኒቶች መውሰድ ፍቱን ነው፡፡ ይህን አይነቱን የራስምታት አስቀድሞ ለመከላከል የ(calcium blocker) ዝርያ መድሃኒቶችን መውሰድ ይቻላል፡፡
(tension headache)ን ለማከም፣ ለቀላል ሚግሬይን የተጠቀሱትን ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የሚወሰዱ መድሃኒቶች መጠቀም ይቻላል፡፡
ከቀላሉ ጉንፋን እስከ ወባ እንዲሁም እስከ ጭንቅላት እጢ ያሉ በሽታዎች ምልክት ሊሆን፣ እንዲሁም በራሱ እንደ በሽታ ሊከሰት የሚችለው የራስምታት አፈጣጠርና ህክምና ይህንን ይመስላል፡፡ S

↧

Sport: ከመንደር ሱቅ ጠባቂነት እስከ የአለም ምርጥ አሰልጣኝነት

$
0
0

Sir-Alex
ከሊሊ ሞገስ
ፈርጉሰን የነገሱበት ሀሙስ
ያ ታሪካዊ ሀሙስ ነበር፡፡ በጠዋቱ ከሰፋፊዎቹ እስከ ታብሎይዶቹ፣ ከቢዝነስ ጋዜጦች የከረረ ፖለቲካ እስከሚያስተናግዱት ድረስ የሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ፎቶግራፍ ማተም ግዴታ የሆነባቸው ይመስላል፡፡ ትልልቆቹ ከፊት ገፆቻቸው አልፈው ልክ 25 ዓመታትን ኖሮ በሞት እንደተለየ ሁሉ እንጎቻ የሚያካክለውን የአሰልጣኙን ምስል ‹‹ከ1986-2013›› የሚል ጉልህ ርዕስ አስከትለውበት አትመዋል፡፡
በወሲብ ቅሌቶች፣ በወንጀልና በዝነኞች የግል ህይወት ብርበራ የሚታወቀው ዘ ሰን እንኳን በሽፋን ገፁ ላይ በሜንጦ የተንጠለጠለ የፀጉር ማድረቂያ ማሽን በማተም የአንጋፋውን ስኮትላንዳዊ የሚያንቧርቅ ቁጡ ባህሪይ ዘመን ማብቃቱን ለመግለፅ ሞክሯል፡፡ ዘ ሰን በየዕለቱ በገፅ 3 ላይ በከፊል ራቁት የሚታዩ ቆነጃጅትን ምስል ማተሙ የአስርት ዓመታት ልማዱ ነበር፡፡ ሐሙስ ጠዋት ግን አማላዮ ሞዴሎች ለሰር አሌክስ ቦታውን ለቀው ወደ ገፅ 9 ሄደዋል፡፡
ዘ ታይምስ የተሰኘው የተከበረ ጋዜጣ ባለ 12 ገፅ ተጨማሪ መፅሔት ለአንባቢዎቹ ያቀረበ ሲሆን ‹‹እግርኳስን የቀየረው ሰው›› በሚል ሙሉ ለሙሉ ለፈርጉሰን አውሎታል፡፡ ቴሌግራፍ እንዲሁ በ16 ገፁ የአሰልጣኙን የዩናይትድ ቆይታ ስኬት፣ ውዝግብና የኃላፊነት ፍፃሜ ተርኳል፡፡ 20 ገፆቹን ሙሉ ለእርሳቸው ያበረከተው ጋርዲያን ‹‹ሰር አሌክስ›› የሚለውን የዩናይትድን ታላቅ ሰው የክብር መጠሪያ ብቻ በትልቁ በርዕስነት መፃፉን መርጧል፡፡ ጋርዲያን የፈርጉሰን ምስል የሰፈረበትን ቲሸርት በ20 ፓውንድ ለገበያ አቅርቧል፡፡ ሁሉም ጋዜጦች የሰር አሌክስን የኋላ ህይወት ለመተረክ ፊታቸውን ወደ ግላስጎው አዙረዋል፡፡ የስኬታቸውን መነሻ ስረ መሰረት ለማግኘት ገና በ16 ዓመታቸው ከትምህርት ቤት የተለዩት፣ በወደብ ሰራተኛነት ያሳለፉትና በወጣትነታቸው ፕሮፌሽናል እግርኳስ ተጨዋች እስኪሆኑ ድረስ የመንደር ሱቅ ጠባቂ ስለነበሩት ፈርጉሰን ፅፈዋል፡፡ የሚያስፈራና ቁጡ ባህሪይ እንዳላቸው ሁሉም ተስማምተውበታል፡፡ ፈርጉሰን ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ሲመጡ ክለቡ በ31 ሚሊዮን ፓውንድ ገና መሸጡ ነበር፡፡ ከአሰልጣኝነታቸው የመልቀቃቸውን ዜና ይፋ ሲያደርጉ ግን የ2.2 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ይዟል፡፡ ይህን አስደናቂ ስኬት የስነ ፅሑፍ ጥበብ በወለዳቸው ገለፃዎች ያልዳሰሰ የለም፡፡ የሊጉ ጨዋታዎች ሊጠናቀቁ ሲቃረቡ ጠቋሚ ጣታቸውን ሰዓታቸው ላይ አሳርፈው የመስመር ዳኞችን የሚሞግቱት፣ አገጫቸው የሚሰነጠቅ እስኪመስል ማስቲካ የሚያኝኩትና ሲሳካም ሁለት እጆቻቸውን ወደ ላይ አንስተው በመፈንጠዝ ረዳቶቻቸውን የሚያቅፉት ባለሙሉ ልብስ አዛውንት ከፕሪሚየር ሊጉ ምስል መታጣታቸው በሀዘን ተገልጿል፡፡
ሰር አሌክስ ለሚዲያውም ‹‹አምባገነን›› የሆኑባቸው ጊዜያት አሉት፡፡ ምቾት የማይሰጧቸውን ጥያቄዎች ያቀረቡ ጋዜጠኞችን ከእርሳቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች አግደዋል፡፡ ልጃቸው ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የሚያስጠረጥር የቢዝነስ ስራ ሰርቷል ሲል ከዘገበው ቢቢሲ ጋር ለረጅም ጊዜ ተቃቅረው ቃለ ምልልስ ከልክለው ኖረዋል፡፡ ለረጅም ዓመታት ‹‹ጡረታ የሚወጡት መቼ ይሆን?›› ሲሉ የጠየቁት ጋዜጠኞች ጥያቄያቸው በድንገት መልስ ሲያገኝ የፈርጉሰንን ደካማ ጎን ከመግለፅ ይልቅ በሰውዬው ዋጋ የማይተመን ስኬት ላይ አነጣጥረዋል፡፡
ከእንግሊዝ ውጭ እግርኳስን ከዕለታት አንድ ቀን የሚያስታውሱት የአሜሪካ ጋዜጦች እንኳን የታላቁን የስፖርት ሰው ጡረታ ዜና በፊት ገፆቻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ የእግርኳስ ፍቅር እምብዛም በሆነባት ሀገር ቁጥር 1 የሆነው ጋዜጣ ኒውዮርክ ታይምስ እንኳን አልዘነጋቸውም፡፡ በተለያዩ አህጉራት የሚታተመው ፋይናንሺያል ታይምስ የፈርጉሰንን የ27 ዓመታት አገዛዝ ውጤታማነት አብራርቷል፡፡ ከኒውዮርክ ማንሃተን እስከ ሆንግ ኮንግ የመልቀቃቸው ዜና ጉልበት ነበረው፡፡ በእውቁ የአሜሪካ መጽሔት ኒውዮርከር ላይ የሀገሬው ሰው ‹‹ሶከር›› ስለሚለው እግርኳስ የተፃፈ ሀገር ማግኘት ብርቅ ነገር ቢሆንም የፈርጉሰን ዜና ግን አብይ ርዕስ ሆኖበታል፡፡ የፍሎሪዳዎቹ ቢሊየነሮች የግሌዘር ቤተሰቦች ማንቸስተር ዩናይትድን በገቡበት ወቅት ከፈርጉሰን ጋር ቃለ ምልልስ ለመስራት ወደ ኦልድትራፎርድ የተጓዘው የመጸሔቱ ዘጋቢ ከአሰልጣኙ ጋር ያሳለፉትን የጥያቄና መልስ ጊዜ ማስታወሻውን ጽፏል፡፡ ‹‹በእንግድነት መቀበያው ክፍል ከተጨዋቾቻቸው ጋር ሲያወሩ አየኋቸው፡፡ ቱታ ለብሰው የፕላስቲክ ውሃ ይዘዋል፡፡ ወደ እኔ መጥተው በቃለ ምልልሱ ክፍል ቁጭ ስንል ግን ሰውየው ብልህ መሆናቸውን ተረዳሁ፡፡ በዘርፉ ብዙ እውቀት ተሞልተዋል፡፡ ሰማያዊው አይናቸው ግን ቆዳን በስቶ የሚገባ ሰቅጣጭ እይታ አለው፡፡ ጥያቄዬን ከመመለሳቸው በፊት ጥቂት ትንፋሽ ወሰዱ፡፡ ዝምታቸው ፍርሃት ይለቃል፡፡ ‹ከሰፈሬ መጥተህ ለምን ነገር ትፈልገኛለህ? ይህ የእኔ ግዛት ነው› የሚል መልዕክት የሚያስተላልፍ ይመስላል፡፡ ዙሪያዬን ተመለከትኩ የወለቀ ጫማ አልነበረም፡፡››
የኒውዮርክ ዘጋቢ ለቃለ ምልልስ ከፈርጉሰን ጋር የተፋጠጠበት ወቅት የአሰልጣኙና የዴቪድ ቤካም ውዝግብ ወሬ ያልተሳበት ጊዜ ነበር፡፡ በንዴት የጦፉት ፈርጊ የመጫወቻ ጫማ ወርውረው የዴቪድ ቤካምን ቅንድብ ሰንጥቀው የተጫዋቹ ቁስል ስፌት አስፈልጎት እንደነበር ይታወሳል፡፡
የጋዜጠኛው ቃለ ምልልስ ርዕሰ ጉዳይ ግሌዘር የገጠማቸውን የደጋፊዎች ተቃውሞ የተመለከተ ነበር፡፡ ፈርጉሰን የአሜሪካውያኑን ባለሀብቶች በመደገፋቸው የማይናቅ ቁጥር ባላቸው የዩናይትድ ደጋፊዎች ዘንድ ቅሬታን ፈጥረዋል፡፡ ሰውዬው የተገኙበትን የሰራተኛ መደብ አስተሳሰብ አዋርደዋል በሚል ተተችተዋል፡፡ ሶሻሊስት አመለካከታቸውን ሳይቀር ተቃርነዋል ቢባልም እስከ መጨረሻው ድረስ ከአሜሪካውያኑ ጎን ቆመዋል፡፡ ፈርጉሰን አይሳሳቱም ብለው የሚያምኑቱ ተቃውሟቸውን ጋብ አድርገዋል፡፡
ሰር አሌክስ በዚህ ፈተና ብቻ አላለፉም፡፡ በማንቸስተር ዩናይትድ አለቃነት የቆዩባቸው ዓመታት አሮጌውንና ዘመናዊውን ጊዜ ያገናኙ ናቸው፡፡ ከሳተላይት አብዮት እስከ ክፍያ ቴሌቪዥን ድረስ ከሀገር ውስጥ ተፅዕኖ እስከ ዓለም አቀፍ ዝና ድረስ ተመልክተዋል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድን በጠጪዎች ከተሞላ ክለብነት አንስተው በኒውዮርክ ስቶክ ኦክስቴንጅ ድረስ እስከደረሰ ግዙፍ ተቋምነት ድረስ አሳድገውታል፡፡ በዚህ ሂደት የአካዳሚ ሰልጣኝ ህፃናትን ወደ ኮከብነት ከፍ አድርገዋል፡፡ የዲሲፕሊን መመሪያቸውን የጣሱ ተጨዋቾችን ለመቆጣጠር በውድቅት ሌሊት እሰከ ንጋት ሊቆይ የታሰበ የተጨዋቾች ፓርቲን በርግደው ገብተዋል፡፡ በቡድናቸው ውስጥ ጥብቅ የአመጋገብ ስርዓት አስርፀዋል፡፡ የአካል ብቃት ባለሙያዎችን ቀጥረዋል፡፡ ዘመናዊነቱ ተነግሮ የማያልቅ የልምምድ ማዕከል አቋቁመዋል፡፡ የፖሊሲያቸውን ቀይ መስመር ለተላለፉት የመውጫ በሩን አሳይተዋል፡፡
በዝና ልባቸው ያበጠ ቱጃር ተጨዋቾችን ፀጥ ለጥ አድርጎ በመግዛት ለውጤት ማሰለፍ እንደሚቻል የፈርጉሰን ዘመን ተሞክሮ ያረጋግጣል፡፡ ከራቪያ ቢሊየነሮች እስከ ባህረ ሰላጤው ከበርቴዎች ድረስ የፈርጉሰንን የውጤታማነት ጉዞ ሊገቱ ሞክረዋል፡፡ ሃብታሞቹ የፈርጊን የፕሪሚየር ሊግ ዘውድ ነቀነቁት እንጂ እሰከወዲያኛው አላወረዱትም፡፡ ሰር አሌክስ ግን የሌሎችን ዘውድ መገርሰስ ይችሉበታል፡፡ የ45 ዓመቱ ፈርጉሰን በአዲስ ሹመኛነት ወደ ኦልድትራፎርድ ሲመጡ የሊቨርፑል ኃያልነት ጣሪያ የነካ ነበር፡፡ ዛሬ ግን የሊቨርፑል ኃያልነት የኋላ ታሪክ ነው፡፡ ‹‹የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ ካልሆንክ በስተቀር ፈርጉሰን የሚወደዱ ሰው አይደሉም›› ይላል በሊድስ ከተማ ተወልዶ ያደገ አንድ ጋዜጠኛ፡፡ ስለምን አይነት ጥላቻ እያወራ መሆኑ ይግባችሁ፡፡ ‹‹አንዳንድ ጊዜ በብስጭት ያሳብዱኛል፡፡ በተለይ በጨዋታዎች ማገባደጃ ላይ ከወንበራቸው ተነስተው ከዳኞች ጋር ሲጨቃጨቁ ጨርቄን ሊያስጥሉኝ ምንም አይቀራቸውም፡፡ ነገር ግን በምስጢር የፈርጉሰን አድናቂ ነኝ፡፡ ለእርሳቸው በቂም የታጀበ ክብር አለኝ››
ሰር ማት በዝቢም እንዲሁ ነበሩ፡፡ በተጋጣሚ ደጋፊዎች የማይወደዱና በ1960ዎቹ ማንቸስተር ዩናይትድን ለተደራራቢ ክብር ያበቁ ታላቅ አሰልጣኝ ናቸው፡፡ በአውሮፕላን አደጋ በርካታ ተጨዋቾቻቸውን በሞት መነጠቃቸው ከአውሮፓ ሻምፒዮንነት አላገዳቸውም፡፡ ሰር ማት እና ሰር አሌክስ ስኮትላንዳዊ ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት እውቁ ጂኪው መጽሔት ለፈርጉሰን ይህን ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር፡፡
‹‹የስኮትላንድ ምዕራባዊ ግዛት በርካታ ታላላቅ አሰልጣኞችን የሚያፈራው ለምንድን ነው?››
ፈርጉሰን መለሱ፡፡
‹‹ግላስኮአዊያንና የምዕራብ ስኮትላንድ ሰዎች በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ያደጉ ናቸው፡፡ እርጥብ፣ ቀዝቃዛ እና ምህረት የለሽ ብርድ አለው፡፡ አንድ የፌብርዋሪ ጠዋት በፍራንሴብራ ወደብ ተገኝተህ ታውቃለህ?›› ፈርጉሰን ጥያቄያቸውን በጥያቄ መለሱ፡፡ ልጅነታቸውን ያሳለፉበት የመርከብ ፋብሪካ የሚገኝበትን የባህር ዳርቻ መጠቆማቸው ነበር፡፡ በቦታው የብረት ቅዝቃዜ ጣቶችን እንደ እሳት የሚያቃጥል መሆኑን ለጋዜጠኛው ነገሩት፡፡ ‹‹ስትኖርበት ትወደው ይሆናል፡፡ ነገር ግን አስቸጋሪው አየር ያንተን የግል ባህሪይ የመለወጥ አቅም አለው›› ሲሉ መልሳቸውን ቀጠሉ፡፡ ጠያቂውም ዝም አላለም፡፡
‹‹ታዲያ አየሩ ለሰዎቹ ምን የሚሰጣቸው የተለየ ነገር አለ?››
የፈርጉሰን አጭርና ግልፅ መልስ ለቃለ ምልልሱ ማሳረጊያ አበጀለት ‹‹ትጋት!››
በዚህ አስገራሚው ሐሙስ ማንቸስተር ዩናይትድ ፈርጉሰንን በሌላ ስኮትላንዳዊ መተካቱን አስታውቋል፡፡ ዴቪድ ሞዬስን፡፡ የዩናዩትድ ደጋፊዎች ሞዬስ በደም ስራቸው ውስጥ ‹‹ብረት›› እንዲኖር ይፈልጋሉ፡፡ ሽግግሩ አጭርና ያልታሰበ ነበር፡፡ የቀድሞው ፈርጉሰን በወጡበት በር፣ የመጪው ጊዜ ሞዬስ ገብተውበታል፡፡

↧

የህወሃት ማበስበሱ ቁማርና የደኅንነቱ ሚና-የቀዩ መስመር ሰላባዎች?

$
0
0

የቀዩ መስመር ሰላባዎች?

By Goolgule.com
May 20, 2013

Woyyane

መለስ ህይወታቸው እንዳለፈ ከተሰጡት አስተያየቶችና ትንቢቶች መካከል ቀዳሚው የመለስ ሞት ለህወሃት ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ መሆኑ ነበር። በዚሁ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግ ዲፕሎማት “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ይህ እንደሚከሰት ቁልጭ አድርገው ተናግረው ነበር።

መለስ አፍነው የያዟቸው የፖለቲካ ችግሮች ጊዜያቸውን እየጠበቁ የሚፈነዱና በመጨረሻም ፓርቲውን እንደሚፈረካክሰው የተገለጸው በየደረጃ የሚፈነዱት ችግሮች እየበረከቱ በመሄዳቸው ነበር። መለስ አፍነው የያዟቸው ችግሮች የእርስ በርስ መበላላት ደረጃ እንደሚያደርሱ በርካታ ወገኖችና መገናኛዎች ጎልጉልን ጨምሮ አመላክተዋል። አሁን አሁን ትንቢቱ የፍጻሜው ጅማሬ ላይ እንደሚገኝ የሚናገሩም አሉ።

የፖለቲካ አቋም ልዩነት ሳይኖር የአስተሳሰብ ልዩነት ማራመድ በህወሃት ዘንድ አይቻልም። ከተሞከረም ክህደት ነው፤ መፈንቅለ መንግስት የማካሄድ ያህል ነው። የርዕዮተ ዓለም ለውጥ የማቀጣጠል ያህል ያስፈርጃል። ሽብርተኛ ያስብላል። ከቶውንም ተቀባይነት ስለሌለው ድንበር ተበጅቶለታል። ድንበሩም “ቀይ መስመር” በመባል ይታወቃል። የ”ቀይ መስመር” ሃሳብ አመንጪና ደራሲ አቶ መለስ ናቸው። “በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ” በሚል የምጸት ስም የሚጠሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም ይህንን የቀይ መስመር ጽንሰ ሃሳብ ለንግግር ያህል ይጠቀሙበታል።haile-and-girma

ቀይ መስመር የሚሰመርበት በውል ተለይቶ የተቀመጠ ውስን ጊዜ የለውም። መስመሩ ሁሌም አለ። ሁሉም ቆመውበታል። ከልምድ እንደሚታየው በህወሃት ህመም ኢህአዴግ ሲያተኩሰው በድንገት መስመሩ በደማቁ እንዲቀባ ይደረጋል። መስመሩ የሚቀባበት ደማቅ ቀለም የሚቀዳው አቶ መለስ አፈር ሳይልሱ “በስብሰናል” ሲሉ ከሰየሙት የኢህአዴግ የ”ማበስበሻ” ባህር ውስጥ ነው።

በኢህአዴግ የ”ማበስበሻ” ባህር ውስጥ ያልተነከረ የለም። በዚህ ባህር ውስጥ ሆነው የሚንቦጫረቁት ተቆጥረው አይሰፈሩም። አዲስ አበባ በአራቱም ማዕዘን፣ በክልልና በክልል ዋና ዋና ከተሞች፣ እንዲሁም በተለያዩ አገራት የሚሰነፍጠው የባህሩ “ግልማት” የዜጎችን የመኖር ህልውና ከተፈታተነ ቆይቷል።

በባህሩ ውስጥ በመርከብ ሆነው በጀልባ የሚቀዝፉትን የሚመለከቱ አሉ። ጀልባ የሚቀዝፉት ጌቶቻቸውንና “ልዕልቷን” እያዩ ሽታውን በለመዱት ባህር ውስጥ ይምነሸነሻሉ። በዛው ባህር ውስጥ በደረታቸው እየዋኙና እየተንቦጫረቁ ግብር የሚያስገቡ አሉ። “ዲጂታል” የሚባሉትና “ምስለኔዎቹ” ደሞ የማበስበሻውን “መረቅ የማቅለሚያ ማዕድን” ይዘው አራት ኪሎ የባህሩ አናትና ማማ ላይ ሆነው ሁሉንም ይመራሉ። የባህሩን የመጫወቻ ህግ የሚበላቸውና ከበሰበሰው ባህር ወደ እቶን የሚወረወሩት “የቀይ መስመር ሰለባዎች ” ይለያሉ። ለይተው ሲጨርሱ ለባህሩ ካፒቴን የፌዴራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ያቀብሉታል። በዚሁ ሂደት ይቀጥላል። አዲስ ነገር የለም። ሊኖርም አይችልም። ይህ መነሻ ነው። ወደ ጉዳዩ እናምራ።

የሰሞኑ ወግ – ኢህአዴግ አመረረ ወይስ ቀለደ?

ሰሞኑን ኢህአዴግ “ሙስና ላይ ዘመትኩ። በህዝብ ጥቆማና ትብበር ሙስና የተንሰራፋበትን ተቋም አበራየሁት። የህዝብ ትብብር አይለየኝ …” በማለት የፍርድ ቤት አሰራርና ህጋዊ የፍርድ አካሄድ እያስኮመኮመ የሚያውጀው አዋጅ ያስገረማቸው ክፍሎች “እንዴት እንመን? እንዴት እንቀበል? ማን ያልተነካካ አለ?” እያሉ ነው። ከተለያዩ አቅጣጫ “ኢህአዴግ አመረረ ወይስ ቀለደ” በሚል ክርክርም እያስነሳ ነው።

የፌዴራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ፓርላማ ቀርበው “ጥናቱ የተጀመረው በአቶ መለስ ትዕዛዝ ከዓመት ከአስር ወር በፊት ነበር” በማለት ምስክርነታቸውን የሰጡበት ዘመቻ አቶ መለስ በህይወት እያሉ ያልተጠናቀቀው በድንገት በመታመማቸው፣ ከዛም በመሞታቸው፣ ከዛም በላይ የሽግግር ወቅት በመሆኑ እንደሆነ አስረድተዋል። መለስ ሲሞቱ ሃይለማርያም ሙስና ላይ ዘመቱ በሚል ስባሪ ታሪክ እንዳያተርፉ፣ ከዚያም አልፎ ዘመቻው የፖለቲካ ልዩነቱ የፈጠረው “የአራግፍ፣ የመንጥር ዘመቻ” እንዳይመስል አቶ አሊ መለስን የዘመቻው “አባትና ባለታሪክ” አድርገው እንዲያቀርቡ መታዘዛቸው ዘመቻው የተለመደው የኢህአዴግ ቀልድ እንደሆነ አመላካች ስለመሆኑ በስፋት አስተያየት የሚሰነዘርበት ጉዳይ ነው።

ምንም ሆነ ምንም ኢህአዴግ ለጀመረው የሙስና ዘመቻ ሊመሰገን ይገባዋል የሚሉ ወገኖች ዘመቻው እንደ ሰደድ እሳት ተያይዞ የሚነድ ስለመሆኑ ሲናገሩ ይሰማል። የኢህአዴግ ደቀ መዝሙር በመሆን የሚታወቁ ድርጅታቸው “የመለስ ቦናፓርቲ” የተሃድሶ ዘመን ተመልሶ እንደመጣ፣ የዚህ ተሃድሶ ፊት አውራሪ ደግሞ እጩ ጠ/ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል እንደሆኑ በኩራት እየተናገሩ ነው።

ከደህንነቱ ራዳር የተሰወረ አለ?

በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የማናቸውም ባለሃብቶችና ባለስልጣናት እለታዊና አጠቃላይ የክትትል መረጃ ተመዝግቦ የተቀመጠ ነው። ዋናው ደህንነት የማበስበሻው ባህር ቁልፍ እጁ ላይ ነው። ሲፈለግ ከዋናው ባህር መዝገብ የሚፈልጋቸው ነቅሶ በስሩ ላላው የኢኮኖሚ ደህንነት ዘርፍ ያቀብላል። ለስራው ቅርብ የነበሩና በቅርቡ አገር ለቀው ናይሮቢ የሚገኙ እንዳሉት በዚሁ አሰራር መሰረት አሁን የታሰሩት ሰዎች ሪፖርት ተጠናቆ የቀረበው የዛሬ አምስት ወር ግድም ነው።

ደህንነቱ ማን ከማን ጋር እንደሚሰራ፣ የትኞቹ ባለስልጣናት ከየትኛው “ባለሃብት” ጋር አብረው እንደሚሰሩ፣ በየትኛው ወገኖቻቸውና ዘመዶቻቸው ስም እንደሚነግዱ፣ የኤክስፖርትና ኢምፖርት ስራ እንደሚሰሩ፣ ያለ ማስያዣ ብድር እንደሚፈቅዱና እንዲፈቀድ መመሪያ የሚሰጡ፣ ወዘተ ሙሉ መረጃ እንዳለው የሚጠቁሙት እኚሁ ሰው “ሙስና ከግል፣ ከድርጅትና ከተቋማት አልፎ በመንግስት ደረጃ የተዘረጋ ነውና ማን ማንን ይወነጅላል?” የሚል ጥያቄ ያነሳሉ። አያይዘውም “አገራችን ውስጥ ሙስና በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በመንግስት ደረጃ የተቋቋመ ነው” ብለዋል።

ሌሎችም እንደሚሉት ሙስናው ሊደበቅ በማይችል ደረጃ አገሪቱን እንደ ወባ ወረርሽኝ ሲያጥለቀልቃት፣ በየአቅጣጫው ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር ህዝብን ሲያንገሸግሸው ለምን ዝምታ ተመረጠ? የሚለው አንኳር ጉዳይ ብዙ ከመላምትነት የዘለሉ ምክንያቶች እየቀረቡበት ነው። በተለያዩ ደረጃ የኢህአዴግን የመበስበስና የእድገት ደረጃ የማሟጠጥ ጉዳይ አንተርሰው አስተያየት የሚሰጡ ቅድሚያ አጀንዳ የሚያደርጓቸው አቶ መለስን ነው።

መለስ ዝምታን ለምን መረጡ?

እርሳቸው ምን ያህል ተዋናይ እንደሆኑ አሃዝ ጠቅሶ መናገር ባይቻልም አቶ መለስ አገሪቱ በሙስና መንቀዟን እያወቁ ዝም ማለታቸው ከተባባሪነት እንደማያሸሻቸው ስምምነት አለ። በፓርላማ፤ ከነጋዴዎችና ከኢንቨስትመንት ማህበረሰብ ጋርና ከተለያዩ አካላት ጋር ሲነጋገሩ ሙስናን አስመልክቶ አስገራሚ ዲስኩር ሲያሰሙ ኖረው ያለፉት አቶ መለስ፣ ሙስናን ተሸክመው የኖሩት በፍርሃቻ እንደሆነ የአብዛኞች ማጠቃለያ ነው። አቶ መለስ ሙስናን እንደ ስልት በመጠቀም በዙሪያቸው ያሉትን “በማበስበስ” እንዳሻቸው ይነዱዋቸዋል።

በሙስና የተጨማለቁና በሙስናው ባህር ውስጥ የሚዋኙትን ባለስልጣናት፣ ካድሬዎች፣ ባለሃብቶች፣ የጊዜው ሰዎችና ዘመዶቻቸው ቢታወቁም አቶ መለስ በመፈክር አብረዋቸው ለመኖር የወሰኑትና በዚያው ይህችን ዓለም ባላሰቡበት መንገድ የተለዩት በጡረታና “ያለህን ብላ” በሚል አካባቢያቸውን ለማጽዳት የሞከሩት ሙስናው ውስን አድራሻና መንደር ስለሌለው ነው። ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተገኘና መለስ የፈሩት ሙስና እንዴት ተደፈረ?

መለስ በህይወት እያሉ ሙስናውን ዝም አሉ የሚሉትን ክፍሎች አጥብቀው የሚቃወሙ ቡድኖች ደግሞ “አቶ መለስ የሙስናው አውራ ናቸው። በመንግስት ደረጃ ለተገነባው የሙስና መንደር ፊታውራሪና ይለፍ ሰጪ ናቸው” ሲሉ ይከራከራሉ። የሙስናውን አዝመራ የዘሩ፣ ኮትኩተው ያለመለሙት፣ መጨረሻ ላይም ባህር አዘጋጅተው የማበስበሻ አረንቋ የተከሉት አቶ መለስ በመሆናቸው ርምጃ ለመውሰድ እንደማይቻላቸው፣ ርምጃ ልውሰድ ቢሉም ሁሉም ስለተበከሉ “በአገሪቱ የጦር አዛዥ፣ የፖሊስ አለቃ፣ የደህንነት ሹም፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ፓርላማ፣ ቀበሌ፣ ክፍለ ከተማ፣ ከንቲባ፣ መሃንዲስ፣ ሆስፒታል … የሚቀር ስለማይኖር በቅድሚያ በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊታወጅ ይገባል” ሲሉ የሙስናውን አደገኛነትና መንግስታዊ መዋቅር ያለው ስለመሆኑ ይከራከራሉ።

ለማስረጃ ከሚያነሱት መከራከሪያ መካከል “ዋናው የሙስና ሻርክ” በሚል ስያሜ የሚጠሩት ባለሃብትና በሳቸው መዋቅር ውስጥ ሆነው ከተራ ወንጀል እስከ አገር አቀፍና ድንበር ዘለል ዝርፊያ የሚፈጽሙ “ማፍያዎች”፣ በፌስታል ብር የሚያቀባብሉ ምስለኔዎች፣ የባለስልጣናትን ሚስቶችና ዘመዶች በንግድ ተቋሞቻቸው በመሰግሰግ የአገሪቱን ህግና ህገመንግስት እንዳሻቸው የሚጋልቡ  ማጅራት መቺዎች፣ የአገሪቱን ባንኮችና የንግድ ስርዓት በማዛባት ሰርተው የሚበሉ ዜጎችን አሟምተው የጨረሱ፣ የራሳቸው ፖሊስና የደኅንነት ሃይል በመገንባት እንደ መንግስት ያቆጠቆጡ ወዘተ በህዝብ ይታወቃሉ። እኒህ ክፍሎች የአቶ መለስን ኮሪዶርና ማረፊያ ቤት ሲመላለሱበት መለስ ዝም ማለታቸው ከምን የመነጨ ሊሆን ይችላል? የሚል ጥያቄ ለሚያነሱ መልሱ አንድ ነው። እሳቸውም፣ ባለቤታቸውም፣ ዘመዶቻቸውም፣ ወገኖቻቸውም፣ የትልቁ “የማበስበሻው ባህር” አባል በመሆናቸው ነው። ከዚያም በላይ ደግሞ ልንካው ካሉ የመገንደስ አደጋ ስለሚከተል ነው። በሌላ አነጋገር ከስር እስከ አናት በተለያየ ደረጃ በህገወጥ የበለጸጉና የትንንሽ መንግስታት መሪዎች የሆኑ ስለበዙ አቶ መለስም ሆኑ እሳቸው የሚመሩት ህወሃት መራሹ አስተዳደር የመከልበስ አደጋ እንዳያጋጥመው በመፍራት እንደሆነ ከውስጥም ከውጪም በስፋት የሚታመንበት እውነታ ነው።

ደብረጽዮን “የጎበዝ አለቃ”!!

መለስ ሲያልፉ ሃላፊነቱን ጠቅልለው የተረከቡት መለስ በመተካካት ሰበብ ያዘጋጇቸው ሰዎች ናቸው። ከነዚህ አዲስ አመራሮች መካከል ዶ/ር ደብረጽዮን ዋናው መሃንዲስ ናቸው። መለስ የፈሩትን ጉድ እሳቸው እንዴት ደፈሩት ለሚለው የሰሞኑ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ክፍሎች ዶ/ር ደብረጽዮንን ከፊት ለፊት ያስቀምጣሉ።

debretsion-e1369002475211-279x300ከደህንነት መዋቅር ቁንጮ ላይ እንዳሉና መለስ ከሞቱ በኋላ ህወሃት ፊትለፊት ያወጣቸው ደብረጽዮን ከዋናው ስራቸው በተጨማሪ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ክላስተር የሚመሩ ናቸው። ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት እንደ እሳቸው ፍላጎት ቢሆን አሁን የተወሰደው ርምጃ ከአምስት ወር በፊት መከናወን የነበረበት ጉዳይ ነበር።

አሁን በቁጥጥር ስር የነበሩት ሰዎች ከአምስት ወር በፊት በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ይታወቅ እንደነበር የሚናገሩት የደህንነት ሰዎች “ከመለስ ህልፈት በኋላ በተፈጠረው የሃይል ክፍፍል  አሸናፊ ሆነው የወጡት ክፍሎች ቅርንጫፍ መቆራረጥ ጀመሩ እንጂ ርምጃው የጸረ ሙስና ዘመቻ አይደለም” ባይ ናቸው። የእነ በረከት ስምዓንና የወ/ሮ አዜብን ቡድን በመጻረር በመለስ ሞት ማግስት ዘመቻ የጀመሩት ቡድኖች ከሙስናው ባህር ውስጥ ተጨልፈው ወደ እቶን ውስጥ እንዲጣሉ ሲወሰን ደረጃ ተዘጋጅቶ እንደሆነ አንዳንድ መረጃዎች ያመለክታሉ።

መለስ አፍነው የያዙት የህወሃት “የመበስበስ” ችግር ገሃድ ከሆነ በኋላ አቶ ስብሃት ነጋ ግንባር ሆነው የወጡ ቢሆንም ለምን ታለፉ? የሚል ጥያቄ ስለመነሳቱ አስተያየታቸውን የሚሰጡት እኒሁ የደህንነት ሰዎች እንደሚሉት “አሁን የተጀመረው ኦፕሬሽን አሸናፊዎቹ ሃይሎች ጉልበታቸውን የሚያሳዩበትና የተጻራሪውን ቅርንጫፍ በመቆራረጥ ዋናውን ግንዶች ማድረቅና ለማገዶ የማዘጋጀት የታሰበ ነው” ዘመቻው በቀጣይነት በጡረታ ስም የሚያስወግዳቸው አውራ ሃይሎች እንዳሉት የሚናገሩት ክፍሎች አቶ አርከበ እቁባይና አምባሳደር ብርሃነ ገ/ ክርስቶስ  በዚህ የማጥራት ቀመር ውስጥ እንዳሉበት ይጠቁማሉ።

ወ/ሮ አዜብ መስፍንና አቶ በረከት ስምዖን ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ጀምረው የነበሩት አቶ ስብሃት  ነጋ ምንም ዓይነት ርምጃ እንደማይወሰድባቸው ያመለከቱት ውስጥ አዋቂዎች “ስብሃት ግን ቅርንጫፎቻቸው በሙሉ ተመልምለው ብቻቸውን ይቀራሉ። በመጨረሻም እንዲደርቁ ይደረጋል” ሲሉ ስለ ስሌቱ የሚያውቁትን ይናገራሉ።

“አቶ ስብሃት ላይ ርምጃ ከተወሰደ የባህሩ ዋና ተዋናዮች በሙሉ ርቃናቸውን ይቀራሉ። ሁሉም መረጃዎች ከወጡ ህወሃት ራሱ ባሰመረው የሞት መስመር ላይ ግንባር ቀደም ተሰላፊ እንዲሆን ያደርገዋል” የሚሉት የመረጃው ሰዎች፣ ለጊዜው አሸናፊ የሆኑት ክፍሎች የተነፈሱ ቢመስላቸውም ውስጥ ውስጡን የጋመ ጉዳይ ስለመኖሩም አመልክተዋል።

የሙስና ፋይል!! የህወሃት ፓናዶል!!

የፌዴራል የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ከበቂ በላይ ጥቆማ እንደሚደርሰው፣ በሚደርሰው ጥቆማ መሰረት የማጣራት ስራ ባከናወነባቸው ተቋማት ላይ ርምጃ ለመውሰድ ሲጠይቅ ማዕቀብ እንደሚደረግበት ሰራተኞቹ ውስጥ ውስጡን የሚነጋገሩበት ጉዳይ ነው። ከደህንነት ጋር በቁርኝት የሚሰራው ይህ ተቋም ሳንጃ የሚሰጠው ህወሃት ሲታመም ነው። ኢህአዴግ ውስጥ ግለት ሲጨምር ሳንጃው ድንበር ተበጅቶ ይታዘዛል። ሰሞኑን የሆነውና ከዚህ ቀደም የተደረጉት ሁሉ የዚሁ አሰራር ነጻብራቆች ናቸው።

“ቴሌ በሙስና ገልምቷል” ከተባለና ዋናው ተፈላጊዎች እንዲሸሹ ከተደረገ ከአራት ዓመት በኋላ  ኮሚሽኑ “ሳንጃህን ካፎቱ አውጣው ተባለ” መባሉን የሚያስታውሱ ክፍሎች፣ በህወሃት ክፍፍል ወቅት በአንድ ጀንበር የተሰራውን የማራገፍ ድራማ ያጣቅሳሉ። አሁን በቅርቡ ኦህዴድ ውስጥ የህወሃትን የበላይነት ለመሸርሸር በተነሱ ወጣት አመራሮች ላይ ሙስናን ተንተርሶ የተወሰደውን የማጥራት ዘመቻ ያክላሉ። አሁንም በተመሳሳይ ሰሞኑን የተወሰደውን ርምጃ ከዚሁ ከኖረው የህወሃት “የመበላላት” ታሪክ ጋር የሚያገናኙት ክፍሎች፣ በግልጽ አሁን አሸናፊ ሆኖ ከወጣው ቡድን ቁንጮና “ልዕልት” ጋር አብረው የሚሰሩ ግለሰብና፣ ባለስልጣን መታሰራቸው ቢድበሰበስም የክስ ሂደቱ እየጠና ሲሄድ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አሁን ለመገመት የሚችግር እንደሚሆን ይናገራሉ።

ህወሃት በተለይም ተሹለክልከው መሪ የሆኑት አቶ መለስ ከበረሃ ጀምሮ ተቀናቃኞችን እንዴት ይበሉዋቸው እንደነበር ያጋለጡት የቀድሞው የህወሃት የገንዘብ ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መድህን አርአያ የሃሳብ ልዩነት አስመልክቶ ውይይት ተደርጎ መስማማት ባለመቻሉ በጣም ሲመሽ  “አሁን እንረፍ፣ እንተኛ” ከተባለ በኋላ በተኙበት በዛው እንዲቀሩ የተደረጉ ስለመኖራቸው ተናገረው እንደነበር በማስታወስ “የአሁኑ ህወሃት ውሳኔውን ተቋማዊ ለማስመሰል። ተቋሙም በህግ፣ በፍርድ ቤት ችሎት፣ በዳኞችና ራሱ መርማሪ፣ ራሱ ከሳሽ በሆነው የፌዴራል የጸረ ሙስና ኮሚሽን የሚመራ በማስመሰል መበላላቱን “ዲጂታል” አድርጎ እየሰራበት ይገኛል።

ለማጠቃለል

የድሃ ልጆች ቦዘኔ ተብለው ሲታሰሩ አገሪቱ ውስጥ የተዛባ ነገር አልነበረም። በፖለቲካ አመለካከታቸው ዜጎች እስር ቤት ሲጣሉ ህግ የተከበረ ነበር። ንጹሃኖች በፈጠራ ወንጀል ሲገረፉና በስቃይ ሲዘለዘሉ ፍትህ አልጎደለም ነበር። እናት በችግር ልጇን ለገበያ ዝሙት ስትልክ ሃፍረት አልነበረም። በዝርፊያ ገንዘብ አዲስ አበባ በህንጻ ስታብድ አግባብነት አይታይም ነበር። ህዝብ በኑሮ ግለት ሌማቱ ሲደርቅና ገንዳ ላይ ምግብ ፍለጋ ህጻናት ሲባትቱ ችግር ሆኖ አይቆጠርም ነበር። አለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰዎች እንደ ከብት በየአቅጣጫው ሲታጎሩ የፍትህ ስርዓቱ አልተዛባም ነበር … ሰሞኑን እስር ቤት የተወረወሩት አቶ ገብረዋህድ ፍርድ ቤት ቀርበው ስለ ባለቤታቸውና ልጃቸው ሲናገሩ “አገሪቱ ምን እየሆነች ነው” አሉ። ከኮብራ ወርደው ወህኒ ቤት ሲገቡ የአገሪቱ የፍትህ ስርዓትና የህግ የበላይነት እንደ ደቀቀ ታያቸው። የባለቤታቸው ከስርዓት ውጪ መታሰር አንገበገባቸው። የልጃቸው መታሰር አቃጠላቸው። ሌሎች ምን ይበሉ? የፕሮፌሰር አስራት ቤተሰቦችና ወዳጆች ምን ይበሉ? የእስክንድር ነጋ ልጅና ባለቤት ምን ይናገሩ? የነበቀለ ገርባ፣ የነ ኦልባና ለሊሳ፣ የነ ሌሊሴ ወዳጆ በኦሮሞነታቸው ብቻ ለስቃይ የተዳረጉና የመከራው ተካፋይ የሆኑት ቤተሰቦቻቸው ይህን ያህል ዓመት ችግሩን እንዴት ተሸከሙት?

የአቶ መለስ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የቅርብ ባልደረባና የስራ አጋር የሆኑት የአቶ ገ/ዋህድ ባለቤትና ልጃቸው መታሰር ጥፋት ከሌለባቸው የሚደገፍ ባይሆንም ለሌሎች ባለስልጣናትና የህወሃት አለቅላቂዎች ታላቅ ትምህርት የሚሰጥ እንደሆነ በተለያዩ የማህበራዊ ድረአውዶች መነጋገሪያ ሆኗል።

 

↧

Tower in the Sky (የሰማይ ላይ ግንብ) –የመጽሐፍ ግምገማ

$
0
0

tower-in-the-sky-300x310 የመፅሐፉ ርዕስ፡- Tower in the Sky (የሰማይ ላይ ግንብ)
ደራሲ፡- ህይወት ተፈራ
አሳታሚ፡- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ
የገፅ ብዛት፡- 437
የታተመበት ዘመን፡- እ.አ.አ. 2012
የመሸጫ ዋጋ፡- 74ብር
በሰለሞን ኃይለማርያም
ይህንን መፅሐፍ ሳነብ በልጅነቴ በአንድ ዕለት ሰንበት እናቴ እጄን ይዛ ወደ ቤ/ክርስቲያን ስትወስደኝ የተመለከትኩትን ልክ እንደፊልም ወደኋላ ወስዶ እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡

Download (PDF, 134KB)

↧
↧

የሙስናው አስር ምስጢር! (ማረ በላዎቹ ርስ-በርስ ተበላሉ!)

$
0
0
በሰሎሞን ተሰማ ጂ. semnaworeq.blogspot.com
Addis Gudayለብዙዎች “ሙስና” የሚለው ቃል በ1989 ዓ.ም ወዲህ የተፈጠረ ሃይለ-ቃል ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን አይደለም፡፡ ቃሉ ግዕዝ ነው፡፡ ትርጉሙም፣“ጥፋት” ማለት ነው፡፡ በአማረኛም የኖረ ሕዝባዊ ግጥም/አባባል አለ፤ እንዲህ የሚል ነው፡፡     “የከንሯ ለዛ፣ የጉንጯ ሙስና፤
         “ዐርብ ሮብ ያስክዳል፣ እንኳን ዐሙስንና፡፡” ይላል -
አዝማሪም፡፡ በዚህ አገባብም መሠረት “ሙስና” የሚለው ቃል ትርጉም “ፈራሹ፣ ረጋፊው-መልኳ፣ ውበቷ እንዳጠፋ ገፋፋኝ” ለማለትና ለማሳበብ ነው የፈለገው (ደስታ ተክለ ወልድ፣ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት፣ 1962 ዓ.ም፣ ገጽ-822)፡፡
በቅርቡ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊዎችን ሰብስበው በ2006 ዓ.ም የበጀት ዓመት፣ አንድ መቶ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ እንሰበስባለን” እያሉ ይዝቱ የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታና አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ፣ በዚህ የብር ጮማና የንዋይ ብርንዶ ውስጥ ተቀምጠው የተጣለባቸውን ኃላፊነትና ታማኝነት ቢዘነጉት ምን ያስደንቃል? ኧረ! ጨርሶ በኢትዮጵያ ብር አንገበያይም ብለው፣ በአሜሪካን ዶላርና በእንግሊዝ ፓውንድ ወይም በስዊዝ ፍራንክ ብቻ እንጠቀም ቢሉ ምን ያስገርማል? (ጥፋቱን ሙሉ ለሙሉ እነርሱ ላይ ማላከኩ ተገቢም፤ ትክክልም አይደለም፡፡ እና የማነው? በወቅቱ የእርምት ርምጃ ያልወሰደባቸው አካል ነዋ!፡፡)
በርእሴ ላይ ንዑስ-ርእስ አድርጌ የተጠቀምኩበት ሌላው ነጥብ “ማረ በላዎች” የሚለው ሃረግ ነው፡፡ ሆን ብዬ ነው፡፡ “ሙሰኞች” የሚለውን ቃል ለመጠቀምም ሆነ ለማለት ቀፈፌሽን ስለያዘኝ ነው፡፡ የዘመኑ አላዋቂ ባለስልጣኖችና የእነርሱን ቃል እንደገደል ማሚቶ የሚደግሙት ሎሌዎቻቸው እንደፈለጋቸው ይበሉት እንጂ፣ “ሙሰኞች” የሚል የግዕዝም ሆነ የዐማረኛ አገባብ የለም፡፡ “ሙሰኞች” ማለት ራሱ “ሙሰኝነት” ነው፡፡ ስለሆነም፣ በአማረኛዬ እንዳልሞስን በማሰብ “ማረ በላዎች” የሚለውን የራሴን ሃረግ መርጫለሁ፡፡ ቃሉ፣ የደስታ ተክለ ወልድ መዝገበ ቃላት (በገጽ-804 ላይ) እንደሚፈታው ከሆነ የሚከተለውን ትርጉም አለው፤ “ማረ በላ” ማለት ይላሉ፣ “ጠጉራም፣ ጥፍራም፣ ነጭና ጥቁር፣ ዐጪር ቁመት ያለው አውሬ ነው፣ ማር የሚበላ አውሬ” ማለት ነው ሲሉም ይገልፁታል፡፡ “ቀይ ማር የሚበላ የቆላ ጉንዳንም” ማለት ነው ሲሉ ይገልጹታል፡፡ “ጉንዳን”ም ተባለ “ዐጪር ቁመት ያለው አውሬ” ለምንነጋገርበት ረእሰ-ጉዳይ ገላጭና ተስማሚ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ስለሆነም፣ ተጠቅሜበታለሁ፡፡ ያልደከሙበትን የሚወስዱና የሚዘርፉ ሁሉ፣ “ገፊ-ማረ በላዎች” ናቸው፡፡
ሙስናና ማረ በላነት በኢትዮጵያ የኖረ ተግባር ነው፡፡ ስሙን እየቀያየረ “ሙስና” የሚለው የዐማረኛ ቃል ከመሆኑ በፊት የተለያየ ስያሜ ነበረው፡፡ በነገሥታቱ ዘመን “እጅ-መንሻ” ወይም “መተያያ” እየተባለ ይታወቅ ነበር፡፡ በዘመነ ደርግ ደግሞ “ብዝበዛና ምዝበራ” የሚል ትርጉም ተሰጥቶት ሲንከባለል ከቆየ በኋላ፣ በ1975 ዓ.ም ገደማ “ጉቦ” የሚል ታርጋ ተለጥፎበት በ1976 ዓ.ም “የሠርቶ አደሩ ቁጥጥር ኮሚቴ” የሚባል የአሁኑ “የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን” የመንፈስ አባት በዐዋጅ ተቋቋመ፡፡ ወያኔ/ኢህአዲግ አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ ሰሞንም የዛሬው “ሙስና” ደርግ ያወጣለትን “ጉቦ” የሚል ስሙን እንደያዘ ነበር፡፡ በነሐሴ 2/1983 ዓ.ም አቶ አሰፋ ደስታ የተባሉት የከፍተኛ 13፣ ቀበሌ 10 “የሰላምና መረጋጋት ኮሚቴ ሊቀመንበር” አንዲት አደጋ ካደረሰች ተሸከርካሪ ሹፌር ላይ ሃምሳ (50.00) የኢትዮጵያ ብር “ጉቦ” የተቀበሉትን የቀበሌው ሰላምና መረጋጋት አባላት አሳፍሰው፣ አሳስረዋቸው እንደነበር አዲስ ዘመን ዘገባ ያወሳል (ገጽ-1)፡፡
የወያኔ/ኢህአዲግ ታጋዮችና ተጋዳላዮች በ1984 እና በ1985 ዓ.ም በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱም እየሄዱ “የደርግ/ኢሠፓ አባላት” ናቸው ብለው የጠረጠሯቸውን ሰዎች ከሥራ ለማባረር ይጠቀሙበት የነበረው የስም ማጥፊያና ከሥራ ማስወገጃ አጀንዳቸው፣ “ያላግባብ የሕዝብ ሃብት የዘረፉ” የሚለው ነበር፡፡ (ያኔ፣ የሕዝብ ሀብት ዘረፉ ይባሉ የነበሩትና በወያኔ/ኢሕአዲግ አባላት ይባረሩ የነበሩት “ደርግ/ኢሠፓዎች ቢበዛ ሠላሳ ሺህ ብር ቪላ ቤት የሠሩ፣ ወይም ደግሞ ባለሦስት ክፍል ዛኒጋባ የቀለሱት “ሚስኪኖች” ነበሩ፡፡) ዛሬ ታሪኩ ተቀይሯል፡፡ ከባለአምስት ፎቅ ሕንፃ በታች ያለው ሹም ካለ “ፋራና ፈዛዛ” ብቻ ነው፡፡
በጥቅምት 14 ቀን 1989 ዓ.ም “አቶ ታምራት ላይኔ ከመከላከያ ሚኒስትርነቱና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱም ሲወገድ፣” የጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ጽ/ቤት የሰጠው መግለጫ እንደሚለው ከሆነ፣ “አቶ ታምራት በምግባረ-ብልሹነት ተወወግዷል” ነው፡፡ “ጥይት ያላንበረከከውን ታጋይ፣ ስኳር አንበረከከውም!” ተብሎ ነበር (አዲስ ዘመን፣ ጥቅምት 15/1989 ዓ.ም፣ ገጽ-1)፡፡ ከወራት በኋላ፣ አቶ ታምራትና ወይዘሮ ሻዲያ ሀሰን ከነግብረ-አበሮቻቸው ተከሰው ፍርድ ቤት ሲቀርቡም፣ የተከሰሱበት ወንጀል “ያላግባብ ሃብት በማጋበስ” የሚል ነበር፡፡ በዚሁ ወንጀልም መሠረት፣ አቶ ታምራት ላይኔ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ወሰነበት ተባለ፡፡ (“ተባለ” የምለው ሆን ብዬ ነው፡፡) አቶ ታምራት እስሩን ሳይጨርስ በ2000 ዓ.ም (በቅንጅት ታሳሪዎች ግርግርና በነፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ ተለማማጭነት ተፈታ፡፡ በቅርቡ ደግሞ ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ፣ በስዊዝ ባንክ አስቀምጦት የነበረው ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተመልሷል፡፡
ከላይ እንደገለጽኩት፣ በታኅሣሥ ወር 1989 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ አቶ መለሰ ዜናዊና የገመናኛ ብዙኃኖቻቸው “ሙስና” የሚለውን ቃል ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም ጀመሩ፡፡ “ሙስና” እና “የፀረ-ሙስና ኮሚሽን” የሚባሉት ቃላት ሕግ ተረቆላቸው፣ ጽሕፈት ቤት ከፍተው፣ “ኮሚሽነርም” የሚባል ሹም ታውቆላቸው መቀፍደድና ማስቀፍደድ ተከተለ፡፡ “ሙስና ሰበብ በቁጥጥር ስር” መዋል የተጀመረው በግንቦት 16/1993 ዓ.ም ነው፡፡ ለማቋቋም የሚያስችለው ውይይት በግንቦት 10/1993 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተካሂዶ፣ ሳምንት ሳይሞላው በግንቦት 16/1993 ዓ.ም ሕግ ሆኖ ፀደቀ፡፡ ወቅቱ በጥድፊያ የተሞላና “የሕወሀት/ወያኔ ስንጠቃ በመቐሌና በሂልት አዲስ አበባ በይፋ የታወቀበት ጊዜ ነበር፡፡ ወያኔ ለሁለት መከፈሉም አርግጥ ነበር፡፡ ይሄንን ሕግ ከሚያረቁትም ሰዎች መካከል የዛሬው የገቢዎችና ጉምሩክ አቃቤ ሕግ አቶ እሸቱ ወልደ ሰንበት ነበረበት፡፡ መቀሌና ባህር ዳር ላይ ምቹ ሆቴሎችን ይዘው “የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና” ሕጉን ማርቀቅ ጀመሩ፡፡(አቶ እሸቱ በ1999 ዓ.ም እንደነገረኝ ከሆነ፣ ሕጉ ባስቸኳይ የተረቀቀው በአቶ ወረደወልድ ወልዴ ትዕዛዝ ሲሆን፣ በአቶ መለሰ ዜናዊ ቀጭን መመሪያም እንደተከወነ ነግሮኛል፡፡ በዚህም መሠረት፣ ሕጉ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ተረቀቀና ወዲያው ጸደቀ፡፡ በግንቦት 19/1993 ዓ.ም የፍትሕ ሚኒስትሩና የፀረ-ሙስና ኮሚሽነሯ ወይዘሮ እንወይ ገብረ መድህን፣ “ሕዝቡ የሙስና ወንጀልን ያለፍርሃት እንዲያጋልጥ” ጥሪ ካቀረቡ በኋላ፣ “የፀረ-ሙስና ሕጉ በቂ ጥበቃ” የሚያደርግለትም መሆኑን መግለጽ ጀመሩ፡፡ ከሁለት ቀናትም በኋላ የሙስናው ቲያትር (ገቢር አንድ) መጋረጃው ተገልጦ መታየት ጀመረ፡፡
በዕለተ ዐርብ ግንቦት 21/1993 ዓ.ም፣ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ “ከፍተኛ የሙስና ሴራ ውስጥ እንደሚገኙ በተጠረጠሩት ባለሥልጣነትና ነጋዴዎች ላይ ርምጃ ወሰድኩ” ሲል ለፈፈ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መምሪያም በበኩሉ፣ በሙስና ወንጀል ተጠርጣሪ የሆኑትን የመንግሥታዊ ተቋማት ኃላፊዎችና ነጋዴዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለጸ፡፡ በዚህም መሠረት፣ አቶ ስየ አብርሃ (ባለስልጣን)፣ አቶ አሰፋ አብርሃ (ባለሥልጣን)፣ አቶ ምህረትአብ አብርሃ (ነጋዴ)፣ አቶ ፍስሃ አብርሃ-ነጋዴ(አራቱን ወንድማማቾች) እና አቶ ቢተው በለይን፣ አቶ ኃይሉ ለገሠን፣ አቶ ሙሉጌታ ገብረ መድህንን፣ አቶ በለጠ አለማየሁን፣ አቶ ብርሃነ ጂጆን፣ አቶ ሶፊያ ኢብራሂምን (እነዚህ ሁሉ በአንድ ወቅት ስንቱን የሚያንጰረጵሩ የወያኔ ሹማምንት ነበሩ) በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡
ከነጋዴዎቹም መካከል አቶ ምንውዬለት አጥናፉና አቶ አበባው ደስታ (የስታር ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤቶች)፣ አቶ ወርቁ መግራ፣ አቶ አበባው ገላዬ፣ አቶ አስናቀ ጀምበሬ፣ ወ/ሮ አጀብነሽ ሳምሶን፣ ወ/ሮ የሺሃረግ ዘውዴ፣ ሚ/ር ገራርድ ማይክል ሞላይን እና ሌሎችም ነበሩ፡፡ አርብ ማታ በዜና ማሰራጫዎች ተነግሮ፣ ቅዳሜና እሑድን ተራው ሕዝብ እንዲሰልቀው አደረጉት፡፡ ሰኞ፣ ግንቦት 24/1993 ዓ.ም ደግሞ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ማክሰኞ ግንቦት 25/1993 ዓ.ም ደግሞ ኮሚሽነሯ ወ/ሮ እነወይ ገብረ መድህን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድረስ ሄደው “የፀረ-ሙስና ምንጠራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል” ተናገሩ (አዲስ ዘመን፣ ግንቦት 17፣ 18፣ 22፣ 25፣ አና 27 ቀን 1993 ዓ.ም፣ ገጽ-1 ላይ ማግኘት ይቻላል)፡፡ የአሁኑም ክስተት፣ ትዕይነተ-ቲያትር ወሙስና (ገቢር ሁለት) እንደማለት ይመስላል፡፡
በሰኔ 1/1993 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው አቶ ስየ አብርሃ፣ በመሃል ዳኛዋ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ውሳኔ መሠረት በዋስ እንዲለቀቁ ተደረገ፡፡ በዚያው ዕለትም፣ የፌዴራል ፖሊስ የምርመራ ማስተባበሪያ ዋና ክፍል የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ ተከሳሹን አቶ ስየ አብርሃን በድጋሚ አሠራቸው (አዲስ ዘመን፣ ሰኔ 2/1993 ዓ.ም፣ ገጽ-1 እና 5)፡፡ ይህንኑ የአቶ ስየ አብርሃንና የፌዴራል ፖሊስን ግብግብ ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ የተነሳ፣ በወቅቱ የፍትሕ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ወረደወልድ ወልዴ ተከሰው በሁለት ዓመታት “የፈተና ጊዜ ገደብ” ፍርድ ተጣለባቸው፡፡ ጉዳዩ ከከፍተኛው ፍርድ ቤት አልፎም ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ተወስዶ ነበር፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ከብቶ ነበር፡፡ በሰኔ 16/1993 ዓ.ም ኮሚሽነሯ ወ/ሮ እንይ በመገናኛ ብዙኃን ቀርበው (አይናቸውን በጨው አጥበው) እንዲህ አሉ፤ “መንግሥት ባለፉት ሰባት ዓመታት ውሰጥ ሙስናን መዋጋት ሁኔታዎችን ሲያመቻች መቆየቱን” ገልጸው ሲያበቁ፣ “በሙስና ወንጀል የተጠረጠረና የተያዘ ሰው፣ የዋስትና መብት የለውም፤” አሉ፡፡ “ምክንያቱም፣” አሉ ኮሚሽነሯ፣ “ምክንያቱም፣ ተጠርጣሪው የዋስትና መብቱ ከተከበረለት፣ ተጠርጣሪው ሊያመልጥ ስለሚችል ነው፤” ሲሉ አከሉበት፡፡
 አስከትለውም፣ “በሙስና የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብት እዳይኖረው የሚከለክል ሕግ መረቀቁንና በቅርብም ሥራ ላይ ይውላል፤” ሲሉ ነበር ያለባበሱት (አዲስ ዘመን፣ ሰኔ 17/1993 ዓ.ም፣ ገጽ-1)፡፡
የአሁኖቹም ተጠርጣሪዎችና የታሰሩበት ዕለት፣ የፍርድ ቤት አቀራረባቸው፣ እንዲሁም ተከሳሾቹ እያሰሙት ያለው አቤቱታ በ1993 ዓ.ም አቶ ስየ አብርሃና ባለቤታቸው እንዲሁም ሦስት ወንሞቻቸው ያሰሙት ከነበረው እምብዛም ልዩነት የለውም፡፡ (ቀንቀሎ ስልቻ፤ ስልቻም ቀንቀሎ ነው፡፡) ይሄንን አባባል ይበልጥ የሚያጠናክረው የናዝሬት ጉምሩክ ኃላፊ የተባሉት የአቶ ተመስጌን ጉልላትን “በጋንቤላ በኩል ወደ ደቡብ/ሱዳን ሊሸሹ ሲሉ ተያዙ!” የሚለውን ዜና በሐምሌ 12/1993 ዓ.ም ከወጣው የአቶ ሳሚ ዩሱፍ አኳኋን ጋር ካስተያዩት ነው፡፡ በወቅቱ አቶ ሳሚ በርካታ ብርና ዶላር ይዘው በሶማሊያ በኩል አድርገው ጂቡቲ ከገቡ በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ ገልጾ ነበር፡፡ የአቶ ሳሚ ዩሱፍ ወንጀል እጅግ አስደንጋጭ ነበር፡፡ (ልክ የሌ/ኮሎኔል ሃይማኖት 61 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ሰነድ ይዛ ልታሸሽ ስትል ያዝናት እንደሚለው ዜና፣ የአቶ ሳሚም ወንጀል ለሰሚውም የሚቀፍ ነበር፡፡) አቶ ሳሚ ቤሳ-ቢስቲን ሳይኖረው/ሳያሲዝ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 22 ሚሊዮን ብር በሕገወጥ መንገድ ከተበደረ በኋላ፣ (ያን ጊዜ፣ “የስኳር ድጋፍ ሰጪ” ከሚባለው ተቋም) “156,000 ኩንታል ስኳር ያለጨረታ ገዝቶ አየር-ባየር ከሸጠ በኋላ ዕዳውንም ሳይመልስ በሶማሊያ በኩል ሊኮበልል ሲል ተያዘ፤” የሚል ነበር (አዲስ ዘመን፣ ሐምሌ 12/1993 ዓ.ም፣ ገጽ-1)፡፡ ዛሬም፣ አቶ ተመስገን የሚኮበልሉበት አቅጣጫ ተቀየረ እንጂ ኩብለላን ነው የመረጡት፡፡ ከሕግ ፊት ሸሽተው እንዳልሆነ ይታወቅልኝ፡፡
እና፣ አቶ ሳሚ ዩሱፍም ሆኑ አቶ ተመስጌን ጉልላት ከምንድነው የሸሹት? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም፡፡ በቀጥታ ወደ መልሱ ከመግባቴ በፊት፣ በግንቦት 4/2005 የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣን ሳነብ ያገኘሁትን መረጃ ላካፍላችሁ፡፡ እንዲህ ይላል፤ “እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት ላለፉት ሦስት ዓመታት ክትትልና ምርመራ ሲደረግባቸው እንደነበረ የታወቀ ሲሆን፣ ከመያዛቸው ሁለት ቀናት በፊት በመቀሌ ከተማ ከሙስና ጋር በተያያዘ ጠንከር ያለ ውይይት መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ ስብሰባም በኋላ ጥንቃቄ በተሞላበት እንቅስቃሴ” ማረ በላዎቹን በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል” -ይላል (ገጽ-37)፡፡ ትልቁ ቁምነገር ያለው የተሰመረበት ንዑስ ዐረፍተ ነገር ላይ ነው፡፡ በፌዴራል መንግሥቱ ዋና ከተማ የሚደረጉ ስብሰባዎችም ሆኑ ውይይቶች “ፍሬ-ከርስኪ” እንደሆኑና የመቀሌቹ ስብሰባዎችና ውይይቶች ግን “መሬት ጠብ የማይሉ” እንደሆኑ ያሳብቃል፡፡ በርግጥም ይህ ለምን ተደረገ ብሎ መመርመር ያስፈልጋል፡፡
የመቀሌዎቹ፣ በ1993 ዓ.ም በእነአቶ ስየ አብርሃም ላይ የእስር ትዕዛዙን የወሰኑት ከዚያው ከመቀሌ ነበር፡፡ አዲስ አበባ በወቅቱ ምቹ አልነበረችም፡፡ ከሚያዝያ 3-7/1993 ዓ.ም ድረስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አመጽና፣ አመጹንም ተከትሎ የነበረው ዝርፊያና ግድያ፤ እንዲሁም የደሕንነትና ኢምግሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ክንፈ ገብረ መድኅን በግንቦት 4/1993 ዓ.ም በመኮንኖች ክበብ መገደል (ወዘተርፈ) አዲስ አበባን የማትታመን ሥፍራ አድርጓት ነበር፡፡ ምርጦቹ ሕወሀቶች መቀሌ ላይ ተሰብስበው፣ “የአቦይ አብረሃ ልጆችና ግብረ-አበሮቻቸው ይታሰሩ!” ቢሉ አያስደንቅም ነበር፡፡ ምክንያቱም፣ ከአዲስ አበባ ይልቅ “መቐለይ” ለሕወሀት ምቹ የቁጥጥር ዞን ስለሆነች ነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ስንቱ የእህት ድርጅት አባል ስለላና ብሰሳ እንደሚያደርግባቸው ስለሚያውቁም ነው መቐለይን የመረጡት (በተለይ ብአዴን)፡፡ ታዲያ “አሁን፣ በ2005 ዓ.ም ሚያዝያ ማለቂያና በግንቦት ልደታ ዋዜማስ መቀሌ ላይ ተሰብስቦ መወሰንን ምን ይሉታል?” የምትሉ እንደማትጠፉ እርግጠኛ ነኝ፡፡ አሁንም ቢሆን፣ አዲስ አበባ ውስጥ ሕዝቡ ባለፈው የቀበሌና የወረዳ/ክፍለ ከተማ ምርጫ እንደታየው ከሆነ ለወያኔ/ኢሕአዲግ ያለውን ስሜት በግልጽ አሳይቷል፡፡” ስለዚህም፣ ከፍተኛው ያገር ገዳይ መቐለይ ላይ ሸብ-ረብ ተደረገ፡፡
ሌላም ምክንያት አለው፡፡ የፌዴራል ዋና ኦዲተርን ሪፖርት ተከትሎ “ውስጣዊ ሴራዎች/Ineternal Conspirencies) መካሄደ ላይ ነበሩ፡፡ በ116 የፌደራል መንግሥቱ ተቋማት ውስጥ በተደረገው የኦዲት ምርመራ መሠረት፣ በ84 መ/ቤቶች ከ5.2 ሚሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደ የጥሬ ገንዘብ ውዝፍ ተገኝቷል፡፡ ይህንን ገንዘብ ደግሞ በየመሥሪያ ቤቱ የአስተዳደርና ፋይናንስ ዋና መምሪያ ኃላፊዎች ሆነው እንዳሻቸው የሚያደርጉት የሕወሀት/ወያኔ አባላት ናቸው፡፡ ሰንደቅ ጋዜጣ በሚያዝያ 23/2005 ዓ.ም እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ችግሩ በይብጥ የሚጎላው በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ነው፡፡ 3.2 ቢሊዮን ብሩ ደብዛው የጠፋው በዚሁ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ምናልባትም ደግሞ ከፍተኛዎቹን የጦር መኮንኖች የሚያነካካ ነው፡፡ ብዙዎቹ፣ በማረ በላነት ይታማሉ፡፡ በአንደ በጀት አመት ግን ይኼንን ያህል ገንዘብ ተመዝብሮ አያውቅም፡፡ ምናልባትም፣ አቶ መለሰ ዜናዊ ታመሙ (ሞቱ) የሚል የተምታታ ዘገባ በነበረበት የሰኔ/2004 ማለቂያ ላይ በስልጣናቸን አንቀጥልም በሚል ተስፋ-መቁረጥ ውስጥ የነበሩ አመራሮች ካቅማቸው በላይ አሽሽተዋል፡፡ ይሄንን ደግሞ የብአዴን መሪዎች በሚገባ አውቀውታል፡፡ ማወቃችንንም ያወቅነው በ11ኛው የኢሕአዲግ ጉባኤ ወቅት የአቶ በረከት ስምኦንንና የአቶ አዲሱ ለገሠን ቀና-ቀና ማለት አብጠርጥረን ስላየነው ነው፡፡
በዋናው ኦዲተር ሪፖርት አማካኝነት የብአዴን ሰዎች ራት ለመሆን የተዘጋጁት ሕወሀቶች ከጊ ጋር ሩጫ ጀመሩ፡፡ መቀሌ ላይ መሽገው ሁለት አባላቶቻቸውን “መናጆ” አድርገው በርካታ የብአዴን አባላትን ባላቸው የደሕንነትና የፀጥታ ዕዝ ሰንሰለት ተጠቅመው በቁጥጥር ሥር አዋሉት፡፡ እራት ሊያደርጋቸው ያሰበውን ብአዴንን፣ ሀሪፍ ምሳ አደረጉት፡፡ ብዘዎቹ የብዐዴን ሰዎች ሲታሰሩ “ችግር ይፈጥሩ ይሆናል የተባሉትም የፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሀነ ኃይሉ፣ ሐሙስ ተወካዮች ምክር ቤቱ የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርታቸውን ከቀረቡ በኋላ ከኃላፊነታቸው መታገዳቸውን አወቁት፡፡  ይህንንም ለማድረግ መቐለይ ላይ መሽጎ የነበረው “የትግራይ ሪፐብሊካን ፓርቲ” አመራር፣ የደሕነትና የፀጥታ ኃላፊዎችን ማዘዙ ብቻ በቂው እንደነበረ አልተጠራጠረም፡፡ በዕለተ አርብ፣ ግንቦት 2/2005 ዓ.ም መጋረጃው ተገልጦ “የሙስናው ወንጀልም ጉዳይ” ለሕዝቡ በሰበር-ዜናነት ተነገረው፡፡ (ሕዝቡ ግን የሚገርም ምላሽ ነበር የሰጠው፡፡ የፕሪሜር ሊጉና የሰውለሰው ድራማ ሲያልቅባቸው ጊዜ፣ “የሙስና ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ” የሚል ድራማ ሊያሳዩን ይፈልጋሉን? ሲል ተዘባበተባቸው፡፡ (ጎበዝ፣ ቸር እንሰንብት!)
በሳምናታዊው የአዲስጉዳይ መጽሔት ቅጽ 7፣ ቁ. 164 ላይ፤ በግንቦት 10 ቀን 2005 ዓ.ም (ገጽ 22-3) የወጣ ነው::
↧

ሰውየው (የመጨረሻ ክፍል) ከይገርማል ታሪኩ

$
0
0

ከይገርማል ታሪኩ

 (የመጨረሻ ክፍል) 

Pen-4የአባጃሌው ልጅ ሀይሌ ከፊታቸው ጥንቃቄ የሚጠይቅ ስራ ይጠብቃቸዋል:: መዐሕድ ድርጅቴ ነው: ቤቴ ነው ብሎ የተቀበለውን አባል አሳምኖ ወደመኢአድ ማሰባሰብ ቀላል ነገር አይሆንም:: ወያኔ መራሹ መንግስት የትጥቅ ትግል ለማካሄድ ሲንቀሳቀሱ ይዣቸዋለሁ ያላቸው በርካታ ሰዎች ከፕሮፌሰር አስራት ወ/የስ ጋር በእስር ላይ ናቸው:: የእስረኞች ቤተሰቦች: ዘመድ አዝማዶች እንዲሁም መላው አባላት መስዋእትነት የተከፈለበት ድርጅት ሲፈርስ ምላሻቸው ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅም:: ጊዜ ወርቅ ነው:: ማንኛውም ነገር በትክክለኛው ወቅት ያለእንከን መፈጸም ይኖርበታል:: የወያኔና አንጋቾቹ የፈጠራ ወሬ የየዋሆችን ልብ ሊፈትን ይችላል:: የፖለቲካ ፓርቲወችም ቢሆኑ እንዳሸን ነው የሚፈሉት:: ጊዜ ከተሰጠ አይደለም የተራው አባል የየወረዳ አስተባባሪወችንም በነበሩበት ማግኘት ይከብዳል:: ጥቃትን ለመመከት ሁሉም የየመሰለውን አማራጭ ሊከተል ይችላል:: መፍጠን ይኖርባቸዋል::

ጠ/ ሚኒስትሩ “ለስልጣን የበቃነው ጀርባችንን በእሳት አስገርፈን ነው” ብለው ያሉት ሀሰትነት የለውም:: ደርግ ከስልጣን የወደቀው እንዲህ በቀላሉ አልነበረም:: የትግራይ ወጣቶችን ጨምሮ መላው ኢትዮጵያዊ ደርግን ለመጣል እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ አድርጓል:: በትግሉ ወቅት ይህ ነው የማይባል ንብረት ወድሟል:: ከሁሉም በላይ የበርካታ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል:: ነገር ግን ደርግን ለመጣል በተደረገው ትንቅንቅ መስዋእት የሆኑት ኢትዮጵያውያን ለትግል የተነሱት ወያኔ የሚያዝ የሚናዝዝበትን አምባገነን ስርአት ለመመስረት አልነበረም- የአምባገነኑን ስርአት አፍርሰው ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በሚያስከብር ስርአት ለመተካት እንጅ:: ወያኔ ግን የህዝብ ልጆች በመስዋእትነታቸው ያስገኙትን ድል ለራሱ በሚመች መልኩ አዘጋጀው:: ለተሰውት የህዝብ ልጆች ካሳ የሚገባኝ እኔ ነኝ ብሎ ድርቅ አለ:: በርግጥ ወያኔ ደረቅ ብቻም አይደለም- ብልጥም ነው::

የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሞቱም ሆነ እንዲጠነክሩ አይፈለግም:: ተቀናቃኝ ፓርቲወች አሉ መባሉ የገዥውን ፓርቲ መልካም ገጽታ በአንድ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል:: የዴሞክራሲ ስርአት አንዱ መገለጫ ከገዥው ፓርቲ ሌላ የተደራጁ ተፎካካሪ ፓርቲወች መኖር ነው:: ታማኝ የሆኑ ፓርቲዎች ከመንግስት ልዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይችላል:: ታማኝ ፓርቲዎች ታማኝ ተቃዋሚ ያላቸው ናቸው:: ታማኝ ተቃዋሚ በሆነ ባልሆነው መንግስትን አይጐንጥም: የሰጡትን በጸጋ ይቀበላል:: ሕዝብንና መንግስትን ለመነጠል አይሞክርም:: በዚህ ስሌት መሰረት መኢአድም ሆነ ሌላ ፓርቲ ቢመሰረት ችግር የለውም:: ችግር የሚሆነው ፓርቲዎች ገንነው መውጣት ከጀመሩ ነው:: ሕዝብ የሚደግፋቸው ፓርቲዎች ቀይ መስመርን የተሻገሩ ናቸው:: ቀይ መስመር ማለት ኢሕአዴግ ለተቃዋሚዎች ያስቀመጠው የመንቀሳቀሻ ዳራ ነው:: ቀይ መስመሩን አይደለም ማለፍ መንካት ቀይ ካርድ ያሰጣል:: ቀይ ካርድ ያየ ግለሰብ ወይም ድርጅት ከጨዋታ ውጭ ይሆናል:: በጥፋትም ይቀጣበታል:: ኢህአዴግ በወረቀት ላይ ያሰፈራቸው የፖለቲካ: የኢኰኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ፖሊሲዎች በትክክል በስራ ላይ ቢውሉ ህልውናው ሊያከትም እንደሚችል ያውቀዋል::  የነጻና የገለልተኛ ማህበራዊና ዴሞክራሲያዊ ተቋሞች መኖር ለህልውናው ጸር ናቸው:: ትክክለኛ ምርጫ ቢካሄድ እንደማይመረጥ ይረዳል:: መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማይደግፈው እንዲያውም እንደሚጠላው ያውቃል:: ስልጣኑን ከለቀቀ ደግሞ በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ለሰራቸው ወንጀሎች ሁሉ መጠየቅ ይመጣል:: ባለስልጣናቱ ያላግባብ ያከማቹት ንብረት ሊወረስ ይችላል:: ስልጣን ከሌለ አይደለም ሀብት ንብረትን ህልውናንስ እንዴት ማስጠበቅ ይቻላል? ተተኪው መንግስት ያለፈውን ሁሉ ይቅር ብሎ የያዙትን ይዘው ከስልጣን ብቻ ገለል እንዲሉ ስለመፍቀዱ ምን ማረጋገጫ ይኖራል? ስለዚህ ወረቀት ላይ ያለው ለተመልካች ፍጆታ የሚውል ነው:: በስራ ላይ የሚውለው በስውር የሚተላለፈው የውስጥ መመሪያ ነው:: ወረቀት ላይ የሰፈረውንና በተግባር እየታየ ያለውን አለመጣጣም የተመለከተ “እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል?” ብሎ ቢጠይቅ መልሱ ቀላል ነው:: “ፖሊሲወቻችን እንከን የላቸውም:: ዴሞክራት ናቸው የሚባሉ ሀገሮችን በጎ ተሞክሮወች ሁሉ ያካተቱ ናቸው:: ችግሩ የአፈጻጸም ነው:: አፈጻጸምን ለማሻሻል አቅምን ማሳደግ የግድ ይላል:: እና ለአቅም ግንባታ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ እጃችሁን ዘርጉ” የሚል መልስ ይሰጥና ሌላ የገቢ ማሰባሰብ ስራ ይሰራል:: የመናገር: የመሰብሰብ: ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ: የመምረጥ: ወዘተ መብቶች በወረቀት ላይ ያሉ እንጅ በተግባር የሚተረጎሙ አይደሉም:: እኒህን በወረቀት ላይ የተጻፉ መብቶች ለመጠቀም የሞከረ ማንኛውም አካል ቀይ መስመሩን የተሻገረ ነው::

መኢአድ ዳዴ ማለት እስኪጀምር ድረስ ከመንግስት ምንም አይነት ጥቃት ሊሰነዘርበት እንደማይችል የተረዱት ሀይሌ ካለምንም ስጋት እንደበፊቱ ሁሉ ጎንደርንና ጎጃምን ከዳር ዳር አዳረሷቸው:: በመኪና የሚኬደውን በመኪና: ለፈረስ የተመቸውን በፈረስ ካልሆነም በእግር:: “ግዴላችሁም እኔ ያጠፋኋችሁ ልሁን” ይላሉ ሻለቃ ያገነገኑ ሰዎች ሲያጋጥሟቸው:: ባርኔጣቸውን ከጭንቅላታቸው ላይ አንስተው ፍጹም ትህትና በተመላበት አኳኋን “ጤና ይስጥልኝ ጌታየ” ብለው ሲቀርቡ አይሆንም ብሎ ገፍቷቸው ሊሄድ የሚችል ሰው አይገኝም:: ቀልቡን ሰብሰብ አድርጎ ያዳምጣቸዋል:: በዚህ መልክ ቀደም ሲል የመዐሕድ አባል የነበሩትን ሁሉ ወደመኢአድ አስገቧቸው:: የየወረዳ ኮሚቴዎችንም አጠናከሩ::

’የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲወች ግንባር’ ለመፍጠር የተደረጉት ብዙ ሙከራወች ገንዘብ: ጉልበትና ጊዜ በልተው ሳይሳኩ ቀርተዋል:: በሀገር ውስጥ ከኦብኮና ከደቡብ ሕዝቦች ጋር ተመስርቶ የነበረው ህብረት ብዙ መሄድ ሳይችል ቀርቶ ፈርሷል:: በውጭ ሀገር የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያካተተው የተቃዋሚ ሀይሎች ህብረትም ቢሆን አባል ፓርቲዎችን ሰብስቦ ይዞ መቀጠል አልቻለም:: ኢዴፓና መኢአድ ተከታትለው ከህብረት ጋር ተፋተናል ሲሉ አውጀው የየራሳቸውን መንገድ ተከተሉ:: በመሰባሰባቸው ተስፋ አሳድሮ የነበረው ሕዝብ ተስፋው ጫጨ:: ሻለቃ ከህዝብ ጋር ተመሳስለው ኗሪ በመሆናቸው የህዝቡን ስሜት ይከታተላሉ:: ይህ የፓርቲወች ህብረት መፍረስ መሰራት እርሳቸውንም አበሳጭቷቸዋል:: “እንዲያው ምን ይሻላል? የልጅ ጨዋታ አደረጉትኮ” ይላሉ ከመሰሎቻቸው ጋር ሲያወጉ:: እንዲህ እንዲህ ሲል ቆይቶ በአራት ፓርቲዎች (መኢአድ: ኢዴፓ: ቀስተደመና: ኢዴሊ) ጥምረት ቅንጅት ተመሰረተ::

የቅንጅት መመስረት በየአካባቢው ይደረጉ የነበሩትን የፓርቲዎች የጎንዮሽ ሽኩቻ አስታገሰ:: ባህርዳር ጽ/ቤት የከፈቱት መኢአድና ኢዴፓ መድህን መጠላለፋቸውን ትተው በአንድነት ቆመዋል:: ቀደም ባሉት ጊዚያት አንዱ የሌላውን ጽ/ቤት ረግጦ አያውቅም ነበር:: አሁን ሁኔታው ተለውጧል:: ሁለቱም ጽ/ቤቶች የጋራ አገልግሎት እየሰጡ ነው:: ኢዴፓዎች ድንቅ ድንቅ ሰዎች አሏቸው:: ጥሩ ሀሳብ ማመንጨት: በሳል አመራር መስጠት የሚችሉ ሰዎችን ያካተተ ስብስብ ነው ኢዴፓ:: መኢአድ በአደረጃጀት ከኢዴፓ በእጅጉ ይበልጣል:: በሻለቃ ሀይለየሱስ ሀላፊነት ስር የሆነው ባህርዳር ልዩ ዞንና ምእራብ ጐጃም ዞን እስከቀበሌ ድረስ ተደራጅቷል:: በየአንዳንዱ የገጠር ቀበሌ አምስት አምስት አባላት ያሏቸው አመራር ሰጪ ኰሚቴዎች ተቋቁመዋል:: የባህር ዳር የመኢአድ ወኒያምና ቆራጥ አባላት ኢዴፓዎችን ወደዋቸዋል:: በመሀል የነበረው የመፈራራትና የመጠራጠር ስሜት አሁን የለም:: አንድ ላይ ተሰብስበው ይመክራሉ: መክረውም በጋራ ይወስናሉ::

የቅንጅት አመራር ከገዥው ፓርቲ ጋር የሚያደርጋቸው ክርክሮች የሁሉንም ቀልብ ስቧል:: አርሶ አደሩ ሳይቀር ክርክሩን ለመከታተል ሬዲዮ ገዝቶ ጆሮው ላይ ለጥፎ ይውላል:: የሰላ አንደበትና የበሰለ ትችት የኢሐዴግን ተከራካሪዎች ያንተፋትፍ ይዟል:: ፖለቲካው ነፍስ እየዘራ ነው:: ባሕር ዳሮች የበለጠ ተነቃቅተዋል:: አሁንም ባሕርዳሮች እንደማእከል እያገለገሉ ነው:: ከየዞኖች በሚመጡ ችግሮች ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል:: የቅንጅት ኮሚቴው ለችግሮች መፍትሄ ፍለጋ ከፖሊስና ከአስተዳደር ጋር ውይይት ያደርጋል:: መፍትሄ ግን የለም:: ያም ሆነ ይህ ቅንጅት በያንዳንዱ ልብ ውስጥ ቦታ ይዟል:: ትልቅ ስኬት! የቅንጅት የምርጫ ምልክት የሆነው ሁለት ጣት የሰላምታ መለዋወጫ ሆኗል:: መቸም ፌስታ ነው:: እስካሁን ስር የሰደደ ችግር አይታይም::

የኢትዮጵያ አርሶ አደር የመላው ኢትዮጵያን ሕዝብ ከ80%-85% ያህል ይሆናል:: ኢሕአዴግ የትግል አጋሬ ነው የሚለው አርሶ አደሩን ነው:: አርሶ አደሩ የሚኖረው በገጠር ነው::  ስለዚህ ቢያንስ 80% የፓርላማ ወንበር እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ ሆኗል:: ቢሆንም እኒህ መአተኛ ቅንጅቶች ወደገበሬው መጠጋት የለባቸውም:: መርዛቸው እንዲህ በቀላሉ የሚነቀል አይሆንም:: ስለዚህ ባህርዳሮች ወደገጠር ተጉዘው አርሶ አደሩን እንዳያሰባስቡ ሆደ ሰፊው ብአዴን መንገዶችን ሁሉ ጥርቅም አድርጐ ዘጋ::

አርሶ አደሩ ተሰባስቦ የሚገኝበት የእረፍት ጊዜ የደብሩ ታቦት የሚከበርበት ቀን ነው:: ለምሳሌ አዴት ታቦቱ መድሀኔአለም ከሆነ አዴቶች የወሩን 27ኛ ቀን ስራ ፈትተው ያከብሩታል:: በእለቱ ቤተክርስቲያን ሄዶ ማስቀደስ: የታመመን መጠየቅ: የተጣላን ማስታረቅ: ዘመድ ወዳጅን መጐብኘት ነው ዋናው ስራ:: ሌላውም ቢሆን እንዲሁ የየራሱን የበአል ቀን በተመሳሳይ ሁኔታ ነው የሚያሳልፈው:: ይህች ቀን አርሶደሩ ቤተክርስቲያን ተሰባስቦ የሚገኝባት ናት:: ቅንጅቶች ይህችን ቀን እንደሚጠብቁ ግልጽ ነው:: የየደብሩ ታቦት ከሚውልበት ቀን የተሻለ አይገኝምና ወደዚያው ይገሰግሳሉ:: ታዲያ ይህን የሚያውቁት ብአዴኖች እለቷን በተለያየ ፕሮግራም (ጤና: ጸጥታ: ልማት ወዘተ) ወጥረው ይይዛሉ:: ባሕር ዳሮች አርሶ አደሩን አሰባስበው የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን ለማስተዋወቅ አልተቻላቸውም:: ከወር አንዲት የበአል ቀን ጠብቀው ተጉዘው ሲደርሱ ፖሊሶች ቀድመው ቦታው ላይ ተገኝተው ’ቤተክርስቲያን ውስጥ የፖለቲካ ስራ መስራት አይቻልም’ በማለት ይከለክሏቸዋል:: ከቤተ ክርስቲያን መልስ ገበሬው ምሳውን እንኳ መብላት አልፈቀድለት ብሎ እስከ ምሽት ድረስ በስብሰባ ይጠረነፋል:: ይህ ቀደም ሲል ያልነበረ ልምድ የተፈጠረው ቅንጅቶች ገበሬውን እንዳያገኙትና እንዳይበክሉት በሚል ነው:: “ቀደም ብለን የያዝነው ፕሮግራም ስለሆነ በእኛ ፕሮግራም ማንም የፖለቲካ ስራ እንዲሰራ አንፈቅድም:: ከፈለጋችሁ በሌላ ቀን ልትጠሩ ትችላላችሁ” እየተባሉ ቅንጅቶች ድካም ብቻ አትርፈው መመለስ ጀመሩ:: ይህንን የተገነዘቡት ሻለቃ አንድ ብልሀት ዘየዱ:: ሀይሌ የማንንም ሀሳብ አይንቁም:: “ከአንድ ራስ ሁለት ይበልጣል: ለእኔ ያልታየኝ ለአንተ ሊታይህ ይችላል” የሚሉት ሀይሌ የሁሉንም ሀሳብ ካዳመጡ በኋላ “ሁሉም የነርሱ ነው:: በየቦታው  ሄደን አቤት ብንልም መፍትሄ ልናገኝ አልቻልንም:: በየገጠሩ ለፍተን ሰውን እንዳናገኝ ስለተከለከልን ካለምንም ውጤት ደክመን እየተመለስን ነው:: አርሶ አደሩ እንዳይከዳቸው በጣም ሰግተዋል:: ፈርተውናል:: እንግዲህ አንድ የሚታየኝ አማራጭ አለ: የቤት ለቤት ቅስቀሳ” ሲሉ ተናገሩ:: ይህ ሀሳብ መተኪያ የሌለው ነው ተብሎ በመታመኑ የቤት ለቤት ቅስቀሳ እንዲካሄድ ተወሰነ:: የየቀበሌው ኮሚቴ አባላት የዚህን ስራ ሀላፊነት ወሰዱ:: በዚህ መሰረት የቤት ለቤት ቅስቀሳው ተጀመረ:: የየቀበሌው ኮሚቴ አባላት ከቤት ቤት እየዞሩ ግንዛቤ ማስጨበጥ ቀጠሉ:: “እናንተ ቅንጅትን እንድትመርጡ የምንፈልገው በምርጫው ቀን በምርጫ ወረቀቱ ላይ ብቻ ነው:: ከዚያ ውጭ እነርሱ የሚሏችሁን ሁሉ እሽ በሏቸው:: ተሰብሰቡ ሲሏችሁ እሽ: ማንን ነው የምትመርጡ ሲሏችሁ እናንተን በሏቸው:: ማን ማንን እንደመረጠ የሚያሳይ መሳሪያ ተክለናል የሚሉት ውሸታቸውን ነው:: እንዲህ አይነት መሳሪያ የለም” እያሉ አስጠኗቸው::

 

በከተሞች አካባቢ የሚደረገው ህዝባዊ ስብሰባ በአንጻራዊነት በእጅጉ የተሻለ ነው:: ቅንጅቶች የምርጫ ምልክታቸውን የያዘ ቲሸርት አሰርተው ለብሰዋል:: ትግሉ ኢሕአዴግን በሰላማዊ መንገድ ከስልጣን ለማስወገድ ነው:: አለበለዚያ መብቶች የሚከበሩባት: ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመስረት አይቻልም:: ኢሕአዴግን ከመንበረ ስልጣኑ ለማንሳት አብዛኛውን የፓርላማ መቀመጫ ማሸነፍ የግድ ይላል:: ስለዚህ የእኔ የእኔ ብሎ ነገር የለም:: ቅስቀሳው መካሄድ ያለበት በጋራ ነው:: በጋራ ወጪ መኪና መከራየት: የቅስቀሳ ወረቀቶችን ማባዛት: ሁሉንም- በጋራ መከወን:: ሕዝቡ ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ከቅንጅቶች ጐን መቆሙን በግብር እያሳየ ነው::  ጽ/ቤቶች  በሰው ተጣበቡ:: ማን ማን እንደሆነ አይታወቅም:: ሁሉም ይወጣል ይገባል: ይሰራል:: አንዳንዶች ስጋት ገብቷቸዋል:: ይህንን እድል ተጠቅሞ ብአዴን ብዙ ነገር ሊያበላሽ ይችላል:: ሻለቃ እንዳባት ይገስጻሉ: ይመክራሉ:: “ቢመጡ እኛ ምን ቸገረን:: በድብቅ የምንሰራው ስራ የለን! ሚስጥር ባይኖርባቸውም ጥንቃቄ የሚጠይቁ አንዳንድ ሰነዶቻችንን ከእይታ አርቀናቸዋል:: እዚህ ያለው ጽ/ቤቱና መገልገያ እቃወች ብቻ ናቸው:: የሚያስፈራን ምንም ነገር የለም:: እንዲያውም እንግዶችን መቀበል ያለብን በትህትና ነው:: አያችሁ በአንድ ሰው ብልጫ አንድ ወንበር ይገኛል: በአንድ ወንበር ብልጫ ደግሞ ገዢ ፓርቲነት:: ያላወቅነው ሰው ሁሉ ጠላታችን ነው ብለን ፊት የምንነሳው ከሆነ ምናልባት ያ ሰው በእውነት ሊያግዘን የመጣ ሰው ቢሆን ሊሸሸን ማለትም አንድ ድምጽ ሊያሳጣን ይችላል” በማለት የአባላትን የጎፈነነ ስሜት ገፈፉ:: ጥድፊያ ነው:: ሁሉም ይሰራል:: ቅንጅቶች ሰርግ የሚደግሱ መሰሉ:: ከሁሉ ከሁሉ ባህር ዳር የተጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ አስገራሚ ነበር:: የባሕርዳር ኗሪ ለስብሰባው ንቅል ብሎ ወጥቷል:: የፖሊና የፔዳ ተማሪወች ቀድመው ስቴዲዮም ደርሰዋል:: የባሕርዳር ስታዲዮም የቅንጅትን እድምተኛ ሰብስቦ መያዝ ባለመቻሉ አካባቢው ሳይቀር በሕዝብ ተጨናንቋል:: እለቱ የጥምቀት በአል የሚከበርበት እንጅ ስብሰባ የሚደረግበት አይመስልም:: ከአዲስ አበባ የቅንጅት አመራር ተወካዮች ተገኝተዋል:: የመድረክ መሪው ሰላማዊ መፈክሮችን ያሰማል:: በዚህ ወቅት አንድ ለየት ያለ ነገር ተከሰተ:: “አንድ በኢትዮጵያ ባንዲራ ያጌጠች መኪና ክላክስ እያሰማችና ከሰው ጋር እየተጋፋች በቀስታ ወደስታዲዮሙ ዘለቀች:: በመኪናዋ ላይ ያሉት ሰዎች የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው መፈክር ያሰማሉ:: የመድረክ መሪው ጩኸት በተቀላቀለበት መንፈስ ደስታውን ገለጸ:: “በጭብጨባ ተቀበሏቸው” አለ:: ስታዲዮሙ በጩኸትና በፉጨት ድብልቅልቁ ወጣ:: በዚያች መኪና የመጡት ሰዎች የሙገር አግሮ ኢንዱስትሪ ሰራተኞች ነበሩ:: ስብሰባው ከታሰበው በላይ በደመቀ ሁኔታ በስኬት ተጠናቀቀ:: በበነጋታው ጠዋት የሙገር አግሮ ኢንዱስትሪ ባለቤት የሬዲዮ ቃለመጠይቅ እየተደረገላቸው ነበር:: “ቅንጅት መኪናችንን አስገድዶ በመውሰድ ለቅስቀሳ ተጠቀመባት” ብለው እርፍ አሉ:: ምን ያድርጉ? ተይዘዋል ማለት ነው:: የእውነት ዴሞክራሲ አለ መስሏቸው መብታቸውን ተጠቅመው ድጋፋቸውን የሰጡት አግሮ ኢንዱስትሪዎች በወያኔ ተስፈኞች ጥርስ ውስጥ ገቡ::

 

የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች በየጽ/ቤቶች እየተገኙ እየተደረገ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ይከታተላሉ: አስተባባሪወችን ይጠይቃሉ:: በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ኦሪያል ብራዚል በጣና ሆቴል የቅንጅትና የህብረት ተወካዮችን አግኝተው አነጋግረዋል:: ሁለቱ ድርጅቶች እያከናወኗቸው ያሉትን ተግባራት: በገዥው ፓርቲ እየደረሱብን ነው ያሏቸውን ችግሮች ገልጸው እኛን ለማፈን ከበላይ አካል ተዘጋጅቶ በተዋረድ እስከቀበሌ ድረስ እንዲሰራበት የተላለፈ የውስጥ መመሪያ ነው በማለት ሰነድ አስረክበዋል:: አሜሪካም ሆነች ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች ግንባራቸውን ኮስተር አድርገው ወያኔን “ዋ!” ብለው ከእኩይ ተግባሩ እንዲታቀብላቸው ሊያስፈራሩላቸው አሻፈረኝ ካለም አርጩሜ ቆርጠው ሾጥ ሾጥ አድርገው ሊያስተካክሉላቸው እንደማይችሉ ያውቃሉ:: ግን ተግባሩ መገለጽ ስላለበትና ለፎርማሊቲም ያህል መሆን ስለሚገባው ተደረገ:: በወያኔ እኩይ ተግባር አንጀቱ ያረረ ሁሉም ነው: የራሱ አባላት ጭምር:: ስለዚህ የወያኔን ብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ ሰነዶችን ማግኘት ከባድ አልነበረም::

 

አይደርስ የለምና የምርጫው እለት ግንቦት 7 1997 ደረሰ:: ሁሉም በጠዋት ተነስቶ ስፍራ ስፍራውን ይዟል:: የቅንጅት ጽ/ቤት በጣም በጠዋት እንዲከፈት በተወሰነው መሰረት ጽ/ቤቱ ውስጥ እንዲሰሩ የተመደቡት ሰዎች በጠዋት ተገኝተው ስራቸውን ማከናወን ጀምረዋል:: ሪፖርት ይቀበላሉ: ሪፖርት ያደርጋሉ:: በምርጫ ጣቢያወች በታዛቢነት የተመደቡት የቅንጅት ሰዎች ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷቸው ተሸኝተዋል:: “ድምጽ መስጠት ከመጀመሩ በፊት የምርጫ ኮሮጆው ባዶ መሆኑን አረጋግጡ: ብአዴኖች ሊያበራግጓችሁ ስለሚሞክሩ በምንም መልኩ ሳትደናገጡ በትእግስት ማጠናቀቅ አለባችሁ:: መራጩ ህዝብ ላይ የሚደረገውን ወከባ ተጋፈጡ:: የሚስጥር ድምጽ መስጫው አካባቢ የኢሕአዴግ ሰዎችን እንቅስቃሴ ተከታተሉ: የድምጽ ቆጠራው እንደተጠናቀቀ የምርጫ ጣቢያው ማህተም ያረፈበት ውጤት ተቀብላችሁ በፍጥነት ወደጽ/ቤት እንድትመለሱ —” ተብለው ተመክረው ነው ቀድመው በየምድብ ቦታቸው እንዲገኙ የተደረጉት:: በሌላ በኩል ከኗሪው ጋር ተመሳስለው በምርጫ ጣቢያወች አካባቢ የሚደረጉ ሁኔታወችን እየተከታተሉ በስልክ ጽ/ቤት ላሉት ሰዎች እንዲያስተላልፉ የተመደቡት ሰዎች በንቃትና በጥንቃቄ ግዳጃቸውን እየተወጡ ነው:: ሁሉም ነገር አሪፍ ነው::  ኢሕአዴግ በምእራብ ጐጃሞች ላይ ተደጋጋሚ የፍተሻ ተኩስ አካሂዶ ችግር የለም ብሎ ደምድሟል:: በወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት የፍተሻ ተኩስ ማለት አንድ ጠላት ሊኖርበት ይችላል ተብሎ የተጠረጠረ አካባቢ ላይ የሚደረግ የሩምታ ተኩስና አሰሳ ነው:: ተኩስ በተደረገበት አካባቢ ጠላት ካለ የአጸፋ ተኩስ ይከፍታል:: ምእራብ ጐጃሞች ይህን የፍተሻ ተኩስ አልፈውታል:: በየስብሰባው ላይ እየተገኙ የገዥው ፓርቲ አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል:: ደረሱብን ብለው ያሏቸውን ችግሮች አሰምተው በሚቀጥሉት አምስት የስልጣን ዘመናቸው ችግሮቻቸው እንደሚቀረፉላቸው በብአዴኖች ቃል ተገብቶላቸዋል:: የየተሰበሰቡበት የውሎ አበል ተከፍሏቸው ተቀብለዋል:: በየስብሰባው ማብቂያ ላይ የቀረበውን ድግስ በደስታ ተጋብዘው ተመራርቀዋል:: ቅንጅት ጸረ ልማት ድርጅት እንደሆነ ተነግሯቸው ልክ ነው ብለው ቅንጅትን አውግዘው ፈክረዋል:: ስለዚህ ብአዴኖች በምእራብ ጐጃም ላይ ስጋት የለባቸውም:: ሙሉ ሀይላቸውን እነርሱን በሚነቅፉና አስተማማኝነታቸው በሚያጠራጥር ዞኖች ላይ ብቻ ማሳረፍ እንዳለባቸው አምነዋል:: እና ለምእራብ ጎጃም የየምርጫ ጣቢያ አስመራጮች የተለየ መመሪያ አልተላለፈም::

 

የምርጫው እለት ማታ መላው የባሕርዳር ህዝብ እንቅልፍ በአይኑ አልዞረም:: በንቃት ይጠብቃል:: መብራት አሁንም አሁንም ይቋረጣል:: “ሌባ ሌባ” ሲል ሕዝቡ ይጮሀል:: ብአዴኖች ወያኔ የሚሆነውን የሚሆኑ: አድርጉ የሚባሉትን የሚያደርጉ ሮቦቶች ናቸው ብሎ ስለሚያምን ሁሌም ይጠራጠራቸዋል:: መብራት የሚያጠፉ ቀድመው ባዘጋጁት የተሞላ የምርጫ ኮሮጆ ሕዝብ ድምጽ የሰጠበትን ኮረጆ ለመቀየር ነው ብሎ ይጠረጥራል:: እና መብራት ሲጠፋ “ሌባ ሌባ” እያለ ግር ብሎ ወደየምርጫ ጣቢያዎች ይተማል::  አንዳንድ ባለመኪኖች የመኪናዎቻቸውን የፊት መብራቶች ወደምርጫው ቦታ ቦገግ አድርገው በማብራት ሌብነቱን ለመከላከል ይጥራሉ:: በጥበቃ ብዛት ሕዝቡ ተሰላችቶ ወደየቤቱ እንዲመለስ ይመስላል ጊዜን በአግባቡ አለመጠቀም ይታያል:: እሁድ በጠዋት ወረፋ ይዞ ቀድሞ መርጦ ወደጉዳዩ ለመሰማራት ያሰበው ሕዝብ ወረፋው አልደርስ ብሎ እስከእኩለ ሌሊት ድረስ ተጉላላ:: ቢሆንም ሁሉም በእልህ: በጽናትና በትእግስት የፍላጎቱን አሳካ- መረጠ::

 

ሻለቃ ልጃቸውን እንደሚድሩ አባት በደስታ ብዛት የሚይዙትን የሚጨብጡትን አሳጥቷቸዋል:: ይህን ይዘው ያን ይጥላሉ:: ወዲያ ሄድው ወዲህ ይመለሳሉ:: ሳያስቡት ብድግ ይሉና ተመልሰው ቁጭ ይላሉ:: እርሳቸው የሚወዳደሩበት የምርጫ ክልል መራጭ ወገኖቻቸው አይዞህ ብለዋቸዋል:: ደራወች ጥለው አይጥሏቸውም:: ምእራብ ጐጃም በርሳቸው የተደራጀ በመሆኑ በአሸናፊነት እንደሚወጡ ሙሉ እምነት አላቸው::

 

ሰኞ እለት ከጠዋት ጀምሮ የቅንጅት የምርጫ ታዛቢወች እየተንጠባጠቡ ወደቅንጅት ጽ/ቤቶች መምጣት ጀመሩ:: የየምርጫ ጣቢያው ማህተም ያለበት የድምጽ ውጤት በእጃቸው ይዘዋል:: የቅንጅት አስተባባሪወች የየምርጫ ክልሎችን አሸናፊ ለማወቅ ከየምርጫ ጣቢያወች የመጡትን ውጤቶች መደመር ቀጠሉ:: ለማመን ይከብዳል:: ምእራብ ጐጃም ላይ መቶ በመቶ (100%) ቅንጅት አሸንፏል:: ቅንጅቶች ብዙ አይነት ስሜት እየተሰማቸው ነው:: ደስታ: ስጋት: ፍርሀት:: ደስታቸው:- የትግላቸው ፍሬ መልካም ከመሆኑ የመጣ ነው:: ስጋታቸው:- ምእራብ ጐጃም ላይ የተገኘው ውጤት በሌሎች ዞኖችና ክልሎች ያልተገኘ እንደሆነ ከሚል የመነጨ ነው:: ፍርሀታቸው:- ሕዝብ በድምጹ የጣለው መንግስት ምላሹ ምን ሊሆን እንደሚችል ካለማወቃቸው የተነሳ ነው:: ምናልባት ምክንያት ፈጥረው በድርጅቱና በአባላቱ ላይ የጥፋት ስራ ቢሰሩስ? ሕዝቡንስ ይበቀሉት ይሆን? ወይስ ምን?

 

ሻለቃ ወታደር በመሆናቸው ጠርጣራ ናቸው:: በተለይ ወያኔ ከቶውንም ሊታመን የማይችል ድርጅት ነው:: ብአዴኖች ደግሞ የራሳቸው ህሊና የላቸውም:: አስፈራራ ሲባሉ የሚያስፈራሩ: ደብድቡ ሲባሉ ሙልጭ አድርገው የሚገርፉ: እሰሩ ሲሏቸው የሚያስሩ: ግደሉ ሲባሉ የሚገድሉ ናቸው:: ለእነርሱ ሕዝብ: ሞራል: ምናምን ቦታ የላቸውም:: ስለዚህ ወያኔ ሱርፍ ብሎበት ‘ለየታዛቢወች የሰጣችኋቸውን የውጤት መግለጫ ሰነዶች በአስቸኳይ ቀሙ’ ካላቸው እሳት ጐርሰው እሳት ለብሰው እንደሚመጡባቸው ያውቃሉ:: አሁንም ፍጥነት ያስፈልጋል:: የውጤት መግለጫ ሰነዶችን ሰብስቦ ማራቅ::

 

የምእራብ ጐጃም አርሶ አደር ታሪክ ሰራ:: እንዲህ ያለ ውጤት በየትኛውም የሀገሪቱ የየክልል ዞኖች አልታየም:: ሻለቃ በምእራብ ጎጃም ኮርተዋል:: ቃሉን የማያጥፍ: ለእውነት የቆመ: የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች ስብስብ ሲሉ ያሞካሻሉ:: ወያኔ ደግሞ ‘ጐጃም በከፋ ሁኔታ አጠቃን:: ጉድ ሰራን:: ጐጃምና ተልባ እያደረ ሸርተት ነው የሚባለው ተረት ሀሰት መስሎን ነበር’ ሳይል አይቀርም:: ጐጃም በፍርሀትና በጥቅም ቃሉን አይለውጥም:: በነጻነት ለመወሰን እድሉን ሲያገኝ ሁሌም ከእውነት ጐን የሚሰለፍ ባለማተብ ሕዝብ ነው:: ’ውሻ በበላበት ይጮሀል’ የጎጃሞች መለያ አይደለም::

 

ቅንጅት በበርካታ የምርጫ ክልሎች ተጭበርብረናል ባለበት ወቅት አያልቅበት ወያኔም “ካላችሁስ ኧረ እኔም ተጭበርብሬአለሁ” ብሎ ቀረበ:: ይሉኝታና ሀፍረት አልፈጠረበትም:: ለነገሩ ይሉኝታና ሀፍረት የፋራ ነው: ወያኔ ደግሞ አራዳ:: ቅንጅት ቅሬታ ካቀረበባቸው የምርጫ ክልሎች በዳግም ምርጫው አንድም ሳያገኝ ቀረ:: ወያኔዎች ተጭበርብረናል ብለው ቅሬታ ያቀረቡባቸውን ቦታወች አስመለሱ:: እንዲህ ናቸው ወያኔዎች:- ታግለው የሚጥሉ: አባረው የሚይዙ: ሮጠው የሚያመልጡ: ተናግረው የሚያሳምኑ: ተከራክረው የሚረቱ:: እና ሁሉም ሆነ:: በዳግም ምርጫው ምእራብ ጐጃም በድምጹ አስከብሮት የነበረውን አንድ ወንበር አጣ:: ም/አፈ ጉባኤ ሽታየ ምናለ በዳግም ምርጫው በክንዳሙ ወያኔ እገዛ አንድ የፓርላማ ወንበር ከህዝብ ነጠቁ::

 

-ጐጃም በመጀመሪያወች የወያኔ የግዛት አመታት በተጭበረበረ ገንዘብ ምርቱን ተነጥቋል::

-በ1989 ዓ.ም አካባቢ የጐጃም ሕዝብ ‘የደበቅኸው መሳሪያ አለ’ ተብሎ ታስሯል: ተገርፏል: ተገድሏል::

-ከምርጫው በኋላ ኢሕአዴግ የአማራ ክልልን እንደተሸነፈ አምኖ ሊለቅ ነው የሚል ወሬ ባ/ዳሮች ዘንድ ደረሰ:: ቀጥሎ “እስከቀበሌ ድረስ የሚዘልቅ የክልሉን መንግስት መዋቅር ሰርታችሁ በቶሎ አቅርቡ:: ከዘገየን ቅንጅት ሊያስተዳድር አልቻለም ብለው ተመልሰው ሊወስዱብን ይችላሉ” የሚል መልእክት ከቅንጅት ላእላይ ምክር ቤት መጣ በመባሉ: ኮሚቴ ተቋቁሞ ኰሚቴው የክልሉን መንግስት አስተዳደራዊ መዋቅር ሰርቶ ሰነዱ ፋክስ ተደርጐ ነበር:: ፋክስ የተደረገው ጊዮን ሆቴል በሚገኘው የፋክስ ሜሽን ነበር:: ፋክሱ ለቅንጅት ላእላይ ምክር ቤት መድረስ አለመድረሱ አልተረጋገጠም:: ብአዴኖች ግን እንዴት እንዳገኙት ሳይታወቅ ኮፒው ደርሷቸዋል:: እና በሰነዱ ላይ ፊርማቸውን ያስቀመጡትን ሁሉ ሰብስበው አሰሩ:: እስረኞች ሌሊት ሌሊት በሽፍን መኪና ወደመሸንቲ መንገድ እየተወሰዱ ጫካ ውስጥ ተገረፉ::

-በጥቅምት 1998 የባሕርዳር ኗሪዎች በጥይት ተደበደቡ::

-በሚኒሊክ ጊዜ በደል ተፈጽሞብናል በሚል በአሁኑ ዘመን ያለውን አማራ ለመበቀል ያላፈረው ወያኔ የትናንቱን የምእራብ ጐጃም ጥቃት እንዴት ሊረሳው ይችላል? እና ጐጃሞች ዛሬም በሰበብ አስባቡ እየተሳደዱ ነው::

 

ሻለቃ ሀይለየሱስ እጅጉ በሀላፊነታቸው ስር የተቀመጡትን ባ/ዳር ልዩ ዞንና ምእራብ ጎጃም ዞንን እድሜና ተሞክሮ ባጐናጸፋቸው ዘዴ ተጠቅመው ከሁሉም አባላት ጋር አሸንፈዋል:: የድሉ ባለቤትና የትግሉ አራማጅ የነበሩትን መላው የቅንጅት ቤተሰቦች: መላው የባህርዳርና የምእራብ ጎጃም እንዲሁም የራሳቸውን መራጭ የደራ ህዝብ ከልባቸው የክብር መዝገብ ላይ አስፍረዋል:: የቅንጅት አባላትም ሻለቃን በክብር ያስቧቸዋል::

አማሮች ዛሬም ሁነኛ ሰው ያስፈልጋቸዋል::

ረጅም እድሜ ለሻለቃ (ሻቃ) ሀይለየሱስ እጅጉ!

 

 

 

↧

በላተኛው አባ-መላ ከያሬድ አይቼህ

$
0
0

ከያሬድ አይቼህ ፤ ሜይ 20፥2013

Aba Mela

Ato Birhanu Damte (Aba mela)

የፓልቷኩ አባ-መላ ሰሞኑን ገኗል። መግነኑ አልከፋኝም … ይግነን … ለሁሉም ጊዜ አለውና። ግን አባ-መላን ብዙ ጊዜ አዳምጨዋለሁና የአባ-መላን ነገር መዳሰስ ፈለኩ። ሰሞኑን አባ-መላ ገዢውን ፓርቲ መተቸት ጀምሯል። ይህንን የሰሙ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች በጣም ፈንጥዘዋል ፡ እኔ አልፈነጠዝኩም። ለምን?

አባ-መላ የሚናገረውን ነገር በየሳምንቱ ፡ አንዳንዴ አልፎ አልፎም ቢሆን ፡ አዳምጨዋለሁ። አባ-መላ የሚያረገውን የሚያረግው ለአንድ አበይት ምክንያት ብቻ ነው፦ የግል ጥቅም። አባ-መላ ሌላ ንዑስ ምክንያት የለውም። የሚያደርገው ፡ የሚናገረው ፡ የሚተነፍሰው ፡ የሚስቀው ፡ የሚያለቅሰው … ወዘተ … ለግል ጥቅሙ ነው (ለግል ጥቅሙ መቆሙ መጥፎ ነው ማለቴ አይደለም ፡ ያ ምርጫው ነው)።

በ2008 እ.አ.አ. አባ-መላ ክፍል ውስጥ አስተዳዳሪ የነበረ ሰው (“addis_ababa_1”? በሚል መጠሪያ ስም ሚሳተፍ) ክፍሉ ውስጥ በተነሳ ቅራኔ ምክንያት የክፍሉን ሚስጥር በተቃዋሚ ክፍሎች ውስጥ ገብቶ ሲናገር ሰምቻለው። ከተናገረው ሚስጥር አንዱ ፡ ቃል በቃል ባላስታውስም ፡ አባ-መላ ከሚድሯክ ወይም ከሼህ መሃመድ አልሙዲ በአመት $50,000 ዶላር እንደሚከፈለው ነው። ይሄ ነገር የአባ-መላን ባህሪ እና የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ ትኩሳት ለመረዳት ወሳኝ መረጃ ሆኖ አገኝቼዋለሁ።

አባ-መላ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ከሚድሯክ ጥቅም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ነው ብዬ አምናለሁ። የሚድሯክ ጥቅም ሲከበር ፡ አባ-መላ ለኢህአዴግ እስክስታ ይወርዳል። የድርጅቱ ጥቅም ስጋት ላይ የወደቀ ሲመስል ፡ አባ-መላ ደረቱን ይመታል።

አባ-መላ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆኖ አያቅም። አባ-መላ የሚድሯክን ገጽታ የሚያሽሞነሙን ፡ የደርግ ስርዓት ያፈራው ፡ አንደበተ ምላጭ ፡ የሚያደርገውን የሚያቅ ፡ ፕሮፓጋንዲስት ነው።

ታዲያ ምነው ሰሞኑን የፓልቷክ ተቃዋሚ ክፍሎች ባዶ ሆነው የሲቪሊቲ ክፍል ሞልቶ የፈሰሰው? ተቃዋሚ ባካችሁን በአባ-መላ አትበሉ። አባ-መላ ሚያደረገው ሁሉ ለአገራዊ ጥቅም ብሎ ሳይሆን ለግል ጥቅሙና ለሚያገለግለው ድርጅት ጥቅም ብቻ ብሎ መሆኑን እንገንዘብ።

ሚድሯክ ለብዙ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል የከፈተና ፡ አያሌ ካፒታል ያፈሰሰ ድርጅት በመሆኑ ድርጅታዊ ገጽታውንና ጥቅሙን መንከባከቡ ተገቢና የሚጠበቅ ነው። ሆኖም ግን የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎች በሚድሯክ እና በኢህአዴግ መካከል ሆነን ልንፈጭ ነውና ፡ በአባ-መላ የፓለቲካ ስልት እንዳንበላ ጠንቀቅ እንበል።

አባ-መላንም ሆነ ሌሎች ገዢው ፓርቲን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደግፉ ሰዎችን ተስገብግበን ወደ ተቃዋሚው ጎራ መጨመር የለብንም። በጊዜ ውስጥ ሊፈተኑ ፡ አመኔታችንን ቀስበቀስ ሊያገኙ ይገባል እንጂ ተንሰፍስፈን መርዝ ይሁን መድሃኒት እንደያዙ ሳናቅ አንቀበላቸው።

ወቅቱ የህወሃት/ኢህአዴግ መጨረሻ ወቅት ነውና የሚደናበሩትን የገዢውን ፓርቲ በላተኞች ለጥቅማችን እንጠቀምባቸው እንጂ እነሱ አይጠቀሙበን።

_ _ _ _ _ _

ጸሃፊውን ለማበረታታት ፡ ለመውቀስና ለማስፈራራት በዚህ ይጻፉ፦ yared_to_the_point@yahoo.com

 

↧

ባህርዳር ከተማ የጅንአድ እየተቃጠለ ነው

$
0
0
↧
↧

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የአዲስ አበባው ሕገ ወጥ ሲኖዶስ ለበተነው የሐሰት ጽሑፍ የተሰጠ መልስ

$
0
0

Tewahdoቅዱስ ዳዊት እናንተ የሰው ልጆች እስከ መቼ ድረስ ልባችሁን ታከብዳላችሁ በማለት ለንስሐ ስፍራ ሳይኖራቸው ሐሰትን ፀንሰው አመፃን የወለዱትን ሰዎች የገሠጸበትን የቅዱስ መጽሐፍን ኃይለ ቃል መነሻችን ያደረግነው አለምክንያት አይደለም ።

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

↧

ወይ መላ ነሽ አሉ ወይ መላ አባ መላ!

$
0
0

aba mela

ከሎሚ ተራተራ

እነደምን ከርማችሁ ወዳጆች ? እኔ አምላክ ይክበር ይመሰገን ደህና ነኝ። ሰሞኑን ከወደ ትውልድ አገር የመጡን አዛውንት እንኳን ደህና መጡ፤ የሰሜን አሚሪካ አየርሰ እንዴት ተቀበሎት ለማለት ወደ ጎረቤት ቤት፤ ጎራ ብዪ ነበርና፤ አረፍ እንዳልኩ አንድ ቀደም ብሎ ባለሁበት ከተማ ለጥቂት ወራት በርቀት ዝቅ ብለው እጅ በመንሳት የሃገሬን ተናፋቂ ባህል የሚያሰታውሱኝና እጀግም የማከብራቸውን አባት ድምጥ ሰማሁ።

እንድምነ ዋላችሁ አሉ አቶ በልሁ፤ ድምጣቸውን ያለወትሮዎቸው ለዘብ አድረገው፤ ;;’’’’’ እግዚአብሒር ይመሰገን”’ እንደምን ዋልክ በልሁ ግባ፣ ምነው ? ምን አዲሰ ነገር ሰማህ ደግሞ ድምጥህ ያለወትሮው ለዘብ ብሏል አሉ አቶ ታከለ፤ የዛሪን አያረገወና ልጆቻቸውን ለማየት ወደ ሰሜን አሜሪካ ከመጡ ወዲህ ቀረ እንጂ ድሮማ ሰው ሁሉ የሚጠራቸው “ አልሞ ተኳሸ” እያለ ነበር አሉ።

አቶ በልሁና አቶ ታከለ ለረጅም ግዜ ወዳጆች ከመሆናቸውም ሌላ በወቅቱ የሀገራችን ጉዳይ ዙሪያ ዘወትር በቁጭት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ካላቸው ሃገራዊ ፍቀር በመነሳት መደረግ ሰለሚገባው የሃገር ጉዳይ ፤ በተለይም እንዴት አንድነታቸንን መገንባት እንደሚገባን አበክረው ከሚናገሩት የአካባቢያቸን የሰሜን አሜሪካ አዛውንቷች ዋናዎቹ ናቸው።

ወዲያዉ እግራቸው እንደገባ ወንበርም ላይ ሳይቀመጡ አዬ…; ተወኝ እባክህ…..ሲሉ የሰሙትን ለማጫወት ጀመሩ።, እኔም ኖር;……. በዪ እጅ ከነሳሁ በሗላ ጆሮዪን ሰጥቼ ማዳመጥ ቀጠልኩ፣…… ይገርምሃል ሰሞኑን በዚህ በ “ቡል” ቶክ…ነው.. ”ፓል”ቶክ,,….የሚባል…. የመወያያ መደረክ….. አዪ……ለነገሩ እኔ ይሔንን የመወያያ መድረክ ሳይሆን….”የወሬ ቋት” ነው የምለው። አሉና… ቀጠሉ.. አንድ “አባ…መላ….የሚባል….የ..ወያኔዎቹ አፈቀላጤ.. ሚሰጥር አጋለጠ።……የወያኔን..የግፍ ሰራ መደበቅ (መሸፈን) ደከመኝ..ብሎ ተቃውሞ ሲያሰማ ዋለ። ብዙም ሚሰጥር የማወቀው አለ ብሏል..’…. እያለልሕ …..አዳሜ ተሰበሰቦ ….”ውይ መላ ነሸ አሉ ወይ መላ አባ መላ እያለልህ” ከበሮ፤ ይደልቃል።

ሲሉ ከልቤ ሳቅኩና፤ ፈጠን በዪ ማጋለጡ፣ መልካም አይደለምወይ ብዪ ? ጠየቀኳቸው? ሲመልሱ….እሱማ..መልካም..ነው። አሰገራሚዉ ነገር እኮ አራት ቀን ሙሉ..እንደውም አምሰተኛው ቀን ይኸው መጣ ተሰበሰቦ ማዳነቅ ምን ይሰራል? የተገኝወን መረጃ ሰበሰቦ ተግባራዊ ሰራ ላይ ማተኮር ነው የሚበጀው።

ብለው ሲሉ. በዚሁ ቃላቸው ተሰማምቼ እቸኩል ሰለነበር የሚጣፍጠውን ጫዋታ ገና በእፍታው፤ ትቼ በሉ ደህና ይዋሉ ብዪ ተሰናብቼ ወጣሁና፤ እቤቴ እሰክደርሰ” ወይ መላ ነሸ አሉ ወይ መላ አባ መላ” አሉ አቶ በልሁ፤ እያልኩ እያሰላሰልኩ እቤቴ ደርሰኩና ይቺን ለመጫጫር በቃሁ እላችኸላሁ።

ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነው “ወይ መላ ነሸ አሉ፣ ወይ መላ አባ መላ” እያሉ ከበሮ መደልቅ; አባታችን አቶ በልሁ እንዳሉት አይጠቅመንምና መላው ዳይሰፖራውን ይታሰብበት እያለኩ፤ ከዚህ የሚከተለውን ይበጀናል ያልኩትን ብትጠቀምም ባትጠቅምም መፍትሄ ነው። ብዪ ሰለማምን ጀባ እላለሁ።

ዳይሰፖራው ማተኮር የሚገባው፦

1ኛ) በተገኝው ማንኛውም ይጠቅማል የተባሉትን ኢንፎረሜሸኖች በማሰባሰብና በማጠናከር ላልሰማውና ላልተረዳው፣ የህበረተሰብ ክፈል እነዲደርሰ ማደረግና ለውጤቱም ተግቶ መሰራት።

2ኛ) ከማንኛወም አይነት የጥላቻና የ መጎነታተል ወይም የመናናቅ የ ትግል ሰልት መራቅና ወቅታዊና አንገብጋቢው በሆነው የሃገራችን ቸግርላይ በማተኮር ሳንሰልችና ሳንታክት እያንዳንዳችን የድርሻችንን በቅንነትና በኢትዮጲያዊ ጨዋነት ማበርከት።

3ኛ) በወቅታዊው የሃገራቸን የፖሎቲካ፣ የ ኢኮኖሚም ሆነ የመሃበራዊ ችግሮቻችንን እና መፍትሄዎቻቸውንም ጭምር ባለሞያ ወንድሞቻችንንም ሆነ እህቷቻችንን በመጋበዝ ህብረተሰባችን ሰለወቀታዊው የሃገር ችግርና መፍትሄው ማወያየት።

4ኛ) የፖሎቲካ ድረጀቶችም የኔ የፖሎቲካ ፐሮገራም ነው ለወቀታዊው የሃገራችን ችግር ብቸኛ መፍትሄ የሚሆንው። ከሚል አሰተሳሰብ ወጥተን የጋራ የሆነወን የገጠመንን የሃገር ችግር በጋራ አፋጣኝ መፍትሄ ለማምጣት በመቻቻል፤ ተግቶ በጋራ በመሰራት አገር ወሰጥ ላሉት ለፖሎቲካ ድረጅቶች መልካም ኢትዮጲያዊ ሰሜትን በሁሉም መሰክ በመተግበር አጋርንትን በተገበር ማሳየት።

5ኛ) ከሁሉም በላይ ለምናልመውና ለማይቀረው የህዝብ የሃግር ባለቤትነት እያነዳንዱ ዜጋ ድርሻዪ ምንድነው ? በማለትና ለተግባራዊነቱም እውቀቱንም፤ ጉልበቱንም፤ ገንዘቡንም ህይወቱንም ሳይቅር ለመሰዋት የተዘጋጀ መሆን እንዳለበት ማረጋገጥ ነው።

ይህንን ካልተረዳና ለተግባራዊነቱም ካልተዘጋጀን በሰተቀር ቀደም ብዪ በመግቢያዪ ላይ እንደገለጥኩተ ትርፉ አቶ በልሁ እናዳሉት”…

ሆይ… መላ… ነሸ… አሉ… ሆይ,,.. መላ… አባ… መላ…

ነውና… እነዲህ አይነቱን… ባዶ… ከበሮ… ከመደለቅ… ያውጣን! አሜን!!!

በተመሳሳይ መጣጥፍ እሰክንገናኛ ደህና ሁኑ በቸር ይግጠመን! ችርም ያሰማን!

ከሎሚ ተራ ተራ

Wednesday, May-22-13

አሰተያየትዎን/ነቀፊታዎንም ቢሆን: mwl200825@yahoo.com

↧

በጎንደር ህዝቡ ደፍሮ በአደባባይ ተቃውሞውን አሰማ (VIDEO)

$
0
0
↧

አቡነ ሕዝቅኤል የ6ኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ድጋፍ ነፍገውኛል ያሏቸውን እየተበቀሉ የሚያስመስል ድርጊት እየፈጸሙ ነው ተባለ

$
0
0
  • በሀ/ስብከቱ የአቡነ ሕዝቅኤል አስተዳደር ሙስናና ጎጠኝነት ባስነሣው ቀውስ ተዘፍቋል
  • የሊቀ ጳጳሱ ዘመዶች ከደብር እልቅና እስከ ዕቅብና በከፍተኛ ደመወዝ ተቀጥረዋል
  • ሊቀ ጳጳሱ ሼል አስኪያጁን ያገዱበት ርምጃ የሀ/ስብከቱን አድባራት ተቃውሞ ቀስቅሷል
  • ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በታገዱት ሼ/አስኪያጅ ምትክ ለመመደብ ከሊቀ ጳጳሱ ጋራ እየተሸማገሉ መኾናቸው ተሰምቷል
  • ፓትርያሪኩ እግዱ ተነሥቶ ሼ/አስኪያጁ ወደ ሓላፊነታቸው እንዲመለሱና የእግዱ አግባብነት እንዲጣራ ለጠ/ቤ/ክህነቱ ጽ/ቤት የሰጡት መመሪያ አልተፈጸመም፤ ዋ/ሼ/አስኪያጁ እግዱን ለማስፈጸም ዳተኛ ሲኾኑ ሊቀ ጳጳሱ ደግሞ ላልተገባ ርምጃቸው ድጋፍ ለማግኘት የሀ/ስብከቱን አጥቢያ አብ/ክርስቲያን ሓላፊዎች ነገ ስብሰባ ጠርተዋል
  • አቡነ ሕዝቅኤል በዕጩነት በቀረቡበት የስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ድጋፍ ነፍገውኛል ያሏቸውን እየተበቀሉ ነውን?

abune-hizekel1-221x300የጥቅምት 2005 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በአራት አህጉረ ስብከት እንዲከፈል ሲወስን በሀ/ስብከቱ የተንሰራፋውን የሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር በዘላቂነት እንደሚፈታው በመታመኑ ነበር፡፡ ምልአተ ጉባኤው ስለ ውሳኔው ያወጣው መግለጫ ቃል የሚከተለውን ይላል፡-

በቅ/ሲኖዶስ የተቋቋመው ኮሚቴ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከትን ችግር ለመፍታት አጥንቶ ያቀረበውን ጥናታዊ ጽሑፍ የመረመረው የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጥናቱ መሠረት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በአራት አህጉረ ስብከት ቢከፈል ለአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ቅርበት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚችል ከመኾኑም በላይ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አካባቢ የሚታየው የአስተዳደር ችግር በዘላቂነት እንደሚፈታው በመታመኑ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን፣ በደቡብ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት እንዲደራጅ ወስኗል፡፡

የምልአተ ጉባኤውን ውሳኔ አስመልክቶ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከብዙኀን መገናኛ ለቀረበላቸው ጥያቄ በወቅቱ በሰጡት ምላሽ÷ ‹‹አቤት ባዩ በዛ፤ ጩኸት በዝቷልና ሁሉም በአካባቢው እንዲስተናገድ በሊቃውንትም በአባቶችም ተጠንቶ ቀጠሮ ተይዞበት የቆየ ነው፤›› ብለው ነበር፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት አራቱን የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት የሚመሩ ሁለት ሊቃነ ጳጳሳት በምልአተ ጉባኤው፣ ሥራ አስኪያጆችና ጸሐፊዎች በቋሚ ሲኖዶሱና ቋሚ ሲኖዱሱን ለማጠናከር በተመረጡት ሰባት ብፁዓን አባቶች ተመድበው ነበር፡፡ ይኹንና ከኅዳር ወር መጀመሪያ አንሥቶ ተግባራዊ በኾነው የአዲስ አበባ በአራት አህጉረ ስብከት መደራጀት አድባራትና ገዳማት መልካም አስተዳደር አግኝተዋልን? የተንሰራፋው ሙስናና ብልሹ አሠራር ተወግዷልን?

ምላሹ ግልጽ ነው፤ ለውጡ የቅርጽ እንጂ የይዘትም ባለመኾኑ ተጠያቂነትና ግልጽነት የሰፈነበት መልካም አስተዳደር ላም አለኝ በሰማይ ኾኗል፤ የዘመድ አዝማድ አሠራሩና ጎጠኝነቱ አልተገታም፤ ሞያና ሞያተኛው አልተገናኘም፡፡

አሁንም ሹመት፣ ቅጥር፣ ዕድገትና ዝውውር እየተፈጸመ የሚገኘው በውድድርና በፍትሐዊነት ሳይኾን በኔትወርኪንግ /በደላሎች እና አቀባባዮች/ነው፤ ለደብር እልቅና በአነስተኛ ግምት እስከ ብር 80,000፣ ለጸሐፊነት እስከ ብር 30,000፣ ለስብከተ ወንጌል ክፍል ሓላፊነት ሳይቀር እንደ ደብሩ ገቢ ከብር 10,000 – 15,000 ይጠየቃል፡፡ መዝገብ በሚያውቀው ደመወዝ ከቶም የማይታሰበውን መሬት መያዝ፣ ሁለት ቤት መሥራት፣ የግልም የንግድም መኪኖችን መሸመት ብርቅ አይደለም፡፡

አዲስ አበባ የመንበረ ፓትርያሪኩ መቀመጫና የሁሉም አህጉረ ስብከት ማእከል በመኾኑ ያለውን ቅምጥ አቅም ያህል፣ ይቅርና በመልካም አስተዳደር (ቅጥር፣ ዕድገት፣ ዝውውር) በቅጽ አሟላልና በፐርሰንት አሰባሰብ እንኳ የአህጉረ ስብከቱ ሁሉ አርኣያ ሊኾን አልቻለም፡፡

ይህ አህጉረ ስብከት ቀድሞም÷ ብር 64,000 እጅ መንሻ ሲቀበሉ (አንዱን በደብር እልቅና ለማሾም፣ የደብሩን የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ለማጸደቅ፣ የካህናቱንና ሠራተኞችን በጀት ለማጸደቅ) እጅ ከፍንጅ የተያዙት የቀድሞው ምክትል ሥራ አስኪያጅ ርእሰ ደብር በሪሁ አርኣያበሙስና ወንጀል ከመጠየቅ ይልቅ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ትምህርትና ሥልጠና መምሪያ በምክትል ሓላፊነት በማዘዋወር በጎጠኝነት ከተጠያቂነት የማራቅ ሥራ የተሠራበት ነው፡፡

ይህ አህጉረ ስብከት ቀድሞም÷ በአድባራትና ገዳማት በልማት ስም ጉብኝት ሲያካሂዱ ከብር 30 – 50 ሺሕ እየተቀበሉ፣ በታወቁ የጥቅም አቀባባይ ደላሎቻቸው ቅጥር፣ ዕድገትና ዝውውር እየፈጸሙ የቆዩት፣ ከሁሉም በላይ በ2004 ዓ.ም የበጀት ዓመት በቀረበው ሪፖርት ከብር ስድስት ሚልዮን በላይ ጉድለት የተገኘባቸው የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ ለዓመታት ድኻውን እየበደሉ ፍርድ እያጓደሉ ተቋማዊ ለውጥን የማምከን ሚናቸውን ሲጫወቱ ወደኖሩበት ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅነትያለአንዳች ተጠያቂነት የተዘዋወሩበት ነው፡፡

በዚህ አህጉረ ስብከት÷ ርእሰ ደብር በሪሁን በሰንዳፋ፣ ንቡረ እድ ኤልያስ በሰንዳፋና በሌሎች ከሁለት ባላነሱ የከተማ ቦታዎች በገንዘብም በዐይነትም እየዘረፉ ስለሠሯቸው የመኖሪያና የንግድ ቤቶች፣ ስለወሰዱት የቤተ ክርስቲያን መሬቶች የጠየቃቸው የለም፡፡

ዛሬም÷ አዲስ አበባ ለአራት አህጉረ ስብከት ከተከፈለ በኋላ ሙስናው፣ ጎጠኝነቱና ብልሹ አሠራሩ በሰሜንና ምሥራቅ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት መጠነኛ መሻሻል ቢያሳይም በደቡብና ምዕራብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ግን ተባብሶ መቀጠሉ ነው የተዘገበው፡፡ በተለይምበምዕራብ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት በአስከፊ ደረጃ የተስፋፋው የጎጠኝነትና ሙስና ተግባር በቀጥታ ከሊቀ ጳጳሱ ጋራ የተያያዘና በእርሳቸው ዙሪያ የሚያጠነጥን እንደኾነ መገለጹ ሊቀ ጳጳሱን በሚበዛው ምስጉን አቋማቸው የሚያውቋቸውን ብዙዎች አሳዝኗል፡፡

በሀ/ስብከቱ ሥር የሚገኙ 33 ያህል አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አስተዳደሮች ግንቦት 12 ቀን 2005 ዓ.ም ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ እንዳስገቡት የተዘገበው ባለአራት ገጽ አቤቱታ እንደሚጠቁመው÷ ከጠቅላላው የሀ/ስብከቱ 21 የክፍል ሓላፊዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች መካከል 13 ያህሉ ከሊቀ ጳጳሱ ጋራ በአንድ ይኹን በሌላ መንገድ የቅርብ ዝምድና ያላቸው የአካባቢ ተወላጆች ናቸው፡፡ ፊት በአዲስ አበባ አድባራትና በትውልድ ቦታቸው ከብር 300 – 400 በማይበልጥ ደመወዝ ይሠሩ የነበሩ የሥጋ ዘመዶቻቸው በታላላቅ አድባራት ከዐቃቢነት እስከ ዋና ጸሐፊነትና አስተዳዳሪነት በከፍተኛ ደመወዝ ተቀጥረዋል፤ በደብር እልቅና የሚገኙ ቀራቢዎቻቸው (ለምሳሌ፡- በጠሮ ቅድስት ሥላሴ) ከደመወዛቸው ወጪ ከፍተኛ አበል (እስከ ብር 2600) እንዲከፈላቸው ተወስኖላቸዋል፤ በዚህም መንገድ በተዘረጋ የጎጠኝነትና ጥቅመኝነት ሰንሰለት በተለይ ግራር ደብረ ዐባይ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በየሳምንቱ ከ5 – 12,000 ብር በብፁዕነታቸው ስም ይባክናል፤ ሊቀ ጳጳሱም ‹‹የልማት አባት›› እያሉ ሸልመዋቸዋል፡፡ የጋዜጠኝነት ልምድ የሌለውን ዘመዳቸውን በቀድሞው የሀ/ስብከቱ ማኅተምና ፕሮቶኮል ደብዳቤ በሀ/ስብከቱ ልሳን ኆኅተ ጥበብ ጋዜጣ ላይ በምክትል አዘጋጅነት አስቀጥረዋል፡፡

‹‹ሁሉ ቤቱን ሠርቶ እኔ ብቻ ቀርቻለኹ›› በማለት ማማረር ጀመረዋል የሚባሉት ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከዚህ ቀደም÷ ‹‹ለጳጳስ ቍሪት/ንብረት የለውም – ጎመን የሚዘራበት፣ ሽንኩርት የሚተክልበት፤ ንብረቶቹ ምእመናን ናቸው›› በማለታቸው የተደሰቱባቸው ወገኖች በቡራዩና በሰሚት(?) በሚገኙ የከተማ ቦታዎች ቤት እየሠሩ የመኾናቸው ወሬ ሲሰሙ ‹‹ኧረ ምን ሊኾናቸው›› ብለው ማዘናቸው አልቀረም፡፡ ‹ሥራውን›ም የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎች እንዲያስተባብሩላቸው ያዝዟቸዋል ተብሏል – ልክ እነንቡረ እድ ኤልያስ ‹‹አምስቱ ከለባት››የሚባሉትን የደብር አለቆች፣ ጸሐፊዎች፣ ሒሳብ ሹሞች፣ ቁጥጥሮችና ገንዘብ ያዦች ቢያጆ አሸዋና ሲሚንቶ እያስገለበጡ እንዳሠሩት ማለት ነው፡፡

ሊቀ ጳጳሱ ለቤት ሥራው እንዲተባበሯቸው ከሚያገብሯቸው የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎች አንዱ ሥራ አስኪያጁ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው ናቸው፡፡ በሀ/ስብከቱ የሰፈነውን የሙስናና የዘመድ አዝማድ አሠራር ወደ ዐደባባይ አውጥቶ አነጋጋሪ ያደረገው አጋጣሚ፣ ሊቀ ጳጳሱ የምዕራብ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ በመኾን በቋሚ ቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ የተመደቡትን መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይን ባለፈው ሳምንት፣ በቁጥር 765/4/05 በቀን 07/09/2005 ዓ.ም ከሓላፊነታቸው ከማገዳቸው ተያይዞ ተነሥቷል፡፡Aba Hiruy complaints

የእግዱ ምክንያት ‹‹ከሊቀ ጳጳሱ ዕውቅና የተሠሩ ሥራዎች ናቸው›› ቢባልም ከሊቀ ጳጳሱ ዕውቅና ውጭ አንዳችም ነገር አለመፈጸማቸውን ነው አባ ኅሩይ ሲናገሩ የሚደመጡት፡፡ ‹‹እርሳቸው ያልመሩትን ሥራ አልሠራኹም፤›› የሚሉት ሥራ አስኪያጁ፣ በሀ/ስብከቱ የተሰገሰጉና የጥቅም ሰንሰለት የዘረጉ ‹‹የሊቀ ጳጳሱ ቤተሰቦች›› በሊቀ ጳጳሱ ስም የሚፈጽሙትን ሕገ ወጥ ተግባር እንዲጠነቀቁበት ገልጠው መናገራቸው ከበደል እንደተቆጠረባቸው ያስረዳሉ፡፡

በሥራ አስኪያጅነት የተመደቡት በቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ እንደኾነ ያስታወሱት መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ፣ ከሓላፊነት የታገዱበት ርምጃ በራሱ ‹‹አቡነ ሕዝቅኤል በሌላቸው ሥልጣንና ሓላፊነት›› የወሰዱት ነው፡፡ በመኾኑም‹‹ይህ ዐይነቱ አሠራር ለቤተ ክርስቲያኗና ለእምነታችን አደጋ ኾኖ ከመገኘቱም ባሻገር በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል ለቆሙና ለሚቆሙ ሰዎች የሞራል ስሜት የሚያሳጣ ስለሆነ ያለሥልጣንና ያለሕግ የተጻፈብኝ ደብዳቤ ይነሣልኝ›› ሲሉ በሊቀ ጳጳሱ የተላለፈባቸውን እግድ በመቃወም ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ የጻፉት ደብዳቤ ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል ሊቀ ጳጳሱ በሥራ አስኪያጁ ላይ ያስተላለፉትን እግድ ተቃውመዋል የተባሉት የሀ/ስብከቱ አድባራት አስተዳደሮች፣ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ በጽሑፍ ባስታወቁት ዝርዝር አቤቱታቸው÷ ሊቀ ጳጳሱ ሥራ አስኪያጁን መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይንና የቀድሞውን ጸሐፊ መጋቤ ሥርዐት ደስታ ጌታሁንን ከሓላፊነት በማገድና በማንሣት የወሰዷቸው ርምጃዎች መንሥኤ ‹‹ጎጠኝነትና ሙሰኝነት ነው›› በሚል እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል፡፡

በተቃውሞ አቤቱታው ላይ የተጠቀሰውና በሊቀ ጳጳሱና በሥራ አስኪያጁ መካከል ለተፈጠረው አለመግባባት ዋነኛ መነሻ የተባለው ግን፣ በስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ጋራ ከሀ/ስብከቱ በመራጭነት እንዲሳተፉ የተለዩት ሰዎች ትውልዳዊ ማንነት መኾኑ በእጅጉ አሳዛኝ ነው፡፡ በአቤቱታው እንደተመለከተው፣ ከሀ/ስብከቱ ተወክለው በፓትርያሪክ ምርጫው እንዲሳተፉ ከተለዩት 13 ልኡካን 12ቱ(ሥራ አስኪያጁ ሲቀሩ)የምርጫ ሕጉ ድንጋጌ እንደሚያዝዘው ሊቀ ጳጳሱ በሚመሩት የአስተዳደር ጉባኤ ሳይሆን በሊቀ ጳጳሱ ቀጥተኛ ውሳኔ የተመረጡ ቀራቢዎቻቸውና ዘመዶቻቸው ናቸው፡፡

South and West A.A Diosces manager

መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው

12ቱ መራጭ ልኡካን ሀ/ስብከቱ ካሉት 33 ያህል አጥቢያዎች  መካከል ከስድስት አጥቢያ ብቻ የተመረጡ ነበሩ የሚሉት የዜናው ምንጮች፣ ሥራ አስኪያጁ እንደ ሊቀ ጳጳሱ ቃል በሊቀ ጳጳሱ ቀጥተኛ ውሳኔ የተመረጡትን ልኡካን በቃለ ጉባኤ አስደግፈው ለአስመራጭ ኮሚቴው እንዲልኩ የተላለፈላቸውን ትእዛዝ አለመቀበላቸው ግልጽ ግጭት ውስጥ እንደከተታቸው ያብራራሉ፡፡ በምትኩ የሀ/ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ባካሄደው‹‹የብሔር ተዋፅኦ የጠበቀ›› የመራጮች ልየታ በፓትርያሪክ ምርጫው የሊቀ ጳጳሱ ደጋፊዎች እንዲኾኑ የተዘጋጁት ልኡካን በቁጥር በማነሳቸው ለሥራ አስኪያጁ‹‹ከምርጫው በኋላ እንገናኝ›› የሚል ዛቻ እንዳተረፈላቸው ምንጮቹ አልሸሸጉም፡፡

የአቤቱታው አቅራቢዎች እንደሚያምኑት፣ አሁን መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይን ከሥራ አስኪያጅነት ሓላፊነት በማገድ የተገለጸው ርምጃ ‹‹የአቡነ ሕዝቅኤል የፓትርያሪክነት ሥልጣን ጥማት የወለደው በቀል›› ነው፤ ሊቀ ጳጳሱ ከምደባቸው ጀምሮ የጠሏቸውን አባ ኅሩይን ከሥራቸው ሊያሳግድ የሚያስችል በቂ ምክንያት ይነቀስ ቢባል ከስም ማጥፋት ያለፈ አንድም ነጥብ እንኳ ማቅረብ እንደማይቻልም ርግጠኞች ናቸው፡፡ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ያቀረቡትን አቤቱታ ሲያጠቃልሉም ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠባቂዋና መሪዋ እንደመኾንዎ መጠን ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል እያራመዱ ያሉት ግፍና በደል ሙስናና ዘረኝነት ቆሞ ከዚህ ሁሉ የጸዳ ሥራ እየሠሩ ያሉት አባ ኅሩይ ከቅዱስነትዎ መመሪያ ወርዶ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እስኪዛወሩ ድረስ አቡነ ሕዝቅኤል በሰብል መሰብሰቢያ ወቅት የሰጧቸው እግድ ተነሥቶላቸው የዘሩትን ዘር ምርቱን እንዲሰበስቡ እንዲደረግ ቅዱስነትዎ ቆራጥ አመራርና ርምጃ ወስደው መመሪያ እንዲሰጡልን ከእግረ መስቀልዎ ዝቅ ብለን እናመለክታለን›› በማለት ጠይቀዋል፡፡

የሥራ አስኪያጁ ማመልከቻ የደረሳቸው ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ÷ የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት ውዝግቡን እንዲያጣራ፣ የማጣራቱ ተግባር እስኪጠናቀቅ ድረስ በሊቀ ጳጳሱ የተላለፈው እግድ ተነሥቶ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወደ ሓላፊነታቸው ተመልሰው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ አባታዊ መመሪያ መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ መመሪያው በብፁዕ ዋ/ሥራ አስኪያጁ ወይም በጽ/ቤታቸው ተፈጻሚ እንዳልኾነ የተገለጸ ሲሆን ይህም የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ በኾኑት ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልና በብፁዕ ዋ/ሥራ አስኪያጁ አቡነ ፊልጶስ መካከል ባለው ተዘምዶ የመረዳዳት ኹኔታ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

ለፓትርያሪኩ እንደ ልዩ ሀ/ስብከት በሚቆጠረው አራቱ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት በአንዱ በተፈጠረው በዚህ አለመግባባት፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሰጡት መመሪያ ቅር የተሰኙት አቡነ ሕዝቅኤል በበኩላቸው÷ ለእግድ ርምጃቸው ድጋፍ ለማሰባሰብ ይመስላል የምዕራብ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችን፣ ጸሐፊዎችን፣ ሒሳብ ሹሞችን፣ ቁጥጥሮችንና ገንዘብ ያዦችን በነገው ዕለት በጽ/ቤታቸው ለማነጋገር ስብሰባ መጥራታቸው ተዘግቧል፡፡

*             *            *

በብፁዕነታቸው ጥንተ ሀ/ስብከት – ከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት – ጎልተው የሚሰሙ መሰል የመልካም አስተዳደርና ሙስና ችግሮችን ለጊዜው እናቆያቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በአዲስ አበባ ደርበው በያዟቸው ሁለት አህጉረ ስብከትና እንደ ቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚስተዋልባቸው አስተዳደራዊ ውሳኔ÷ በሐቀኝነት በሚወሰዱና በጥቅመኞች ተጽዕኖ በሚገለባበጡ አቋሞቻቸው መካከል የሚዋልልና ምልስ ቅልስ የበዛበት እንደኾነ ተጨማሪ ማሳያዎች እየተነቀሱ የሚቀርቡባቸው ትችቶች ጥቂቶች አይደሉም፡፡

ትችት (፩)፤ አባ ዮናስ መልከ ጼዴቅ ይባላሉ፡፡ በምዕራብ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት የቶታል ሰፈረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ናቸው፡፡ ደብሩ ለሚያሠራው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልገውን ሞያዊ አበርክቶ አቅሙና በጎ ፈቃዱ ባላቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች በማሟላት ከ20 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ ለማዳን ከምእመናን የቀረበላቸውን ሐሳብ በተለያዩ ስልቶች ውድቅ በማድረግ፣ በጥቅም ለተሳሰሩት አካል ያለግልጽ ጨረታ ይሰጣሉ፡፡ ምእመናን አካሄዱን ተቃውመው አምስት ጊዜ ወደ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል እየተመላለሱ አቤት ቢሉም የብፁዕነታቸው አቋምና ውሳኔ ከአስተዳዳሪው ጋራ ነበር፡፡

ይኹንና ምእመናኑ አቤቱታቸውን አጠንክረው ለበላይ አካል በማሰማታቸው ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ለመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ምክትል ሥ/አስኪያጅ በሰጡት መመሪያ አላግባብ በጥቅም ትስስር የተሰጠው የሕንጻ ግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም ውሳኔ ተሽሮ ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ሞያዊ በረከት እንድትገለገልና ከከፍተኛ ወጪ እንድትድን ተደርጓል፡፡

ብፁዕነታቸው ግን በውሳኔው ደስ አልተሰኙም፡፡ እንዲያውም እልክ በመጋባት ይመስላል ከደብረ ሣህል ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም እስከ መርካቶ ደ/ኀ/ቅ/ ራጉኤል የቤተ ክርስቲያንን መሬትና ንብረት እየሸጡ የግል ጥቅማቸውን በማካበት፣ ከዚህም ጋራ በተያያዙ የፍ/ቤት ክሦችና ንጽሕ ከመጠበቅ አኳያ በሚቀርቡባቸው አቤቱታዎች የሚታወቁትን የደብሩን አስተዳዳሪ በጅቡቲ ደ/ፀ/ቅ/ገብርኤል አስተዳዳሪነት ለማሾምጥረው አድርገው የነበረ ቢኾንም ይህም አልሠመረላቸውም – ከፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ግንኙነት የበላይ ሓላፊ ቢሮ የወጣው ትእዛዝ እንደሚያመለክተው ጥቅመኛው አባ ዮናስ ለጊዜውም ቢኾን ለዚህ ሓላፊነት የተገቡ ኾነው አልተገኙም፡፡

ትችት (፪)፤ ይኼኛው ትችት ብፁዕነታቸው በቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት ካለባቸው ሓላፊነት ጋራ የሚያያዝ ነው፡፡ ችግሩ በአጭሩ ሲገለጽ በድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ሥራ የተፈጸመውን ሙስናና ምዝበራ ይመለከታል፡፡ በውለታ ከተያዘው ጊዜ  በአምስት ዓመት በዘገየው የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ በአነስተኛ ግምት ከስድስት ሚልዮን ብር በላይ የምእመናን ገንዘብና የቤተ ክርስቲያን ንብረት ለተቋራጩና ለጥቅመኛ የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላት ሲሳይ እንደተዳረገ ታምኗል፡፡

ይህም በቀደመው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት ኦዲት ሪፖርትና ቅ/ሲኖዶስ ዳግመኛ በላከውና በም/ሥ/አስኪያጁ በተመራው አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት መረጋገጡ ተነግሯል፡፡ በተለይም ከመቶ በላይ በሚቆጠሩ ገጾች የተጠናቀረው የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ከአባሪ ማስረጃዎች ጋራ የቀረበላቸው የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ፣ ለሚመለከተው አካል በአጀንዳ አስይዘው እንዲያስወስኑ በተለያየ ጊዜ ከተደረጉት ጥረቶችና ማሳሰቢያዎች በተፃራሪ ሪፖርቱን ለወራት አግተው የመያዛቸው ምስጢር ለኮሚቴውና ለፍትሕ ፈላጊ የሀ/ስብከቱ ምእመናን ግርታን የሚፈጥር ኾኗል፡፡

*             *            *

ብፁዕነታቸው በመልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ላይ ባስተላለፉት የእግድ ርምጃና እግዱ ተነሥቶ መንሥኤው እንዲጣራ ቅዱስነታቸው በሰጡት አባታዊ መመሪያ መካከል የታየው ልዩነት የመጀመሪያ እንዳልኾነ የሚናገሩት የመንበረ ፓትርያሪኩ ምንጮች፣ ኹኔታው በአንድ በኩል÷ ብቁ አመራር ከመስጠት አንጻር ብፁዕነታቸው በመሠረቱ ያለባቸውን ውስንነት ያሳያል ይላሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይህን ውስንነት የሚበዘብዙቀራቢና ዘመድ ነን ባይ ጥቅመኞች በብፁዕነታቸው ዙሪያ መበራከታቸውን እና ብፁዕነታቸውም በማወቅም ይኹን ባለማወቅበተጽዕኗቸው መጠለፋቸውን እንደሚያረጋግጥ ያምናሉ፡፡

Ab Hizkielብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል

አሁን በአባ ኅሩይ ላይ የተላለፈውን እግድ መጽናት የሚጠባበቁ ሁለት ግለሰቦች እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡ አንዱ፣ የፓትርያሪኩን ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ግንኙነት መምሪያ በሓላፊነት የመቆጣጠር ተስፋቸው የጨለመባቸውና ለአራት የተከፈለውን የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት በአንድነት ይዞ ጥቅምን የማስፋት ሌላ ከንቱ ተስፋ መሰነቃቸው የሚነገርላቸው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ናቸው፡፡ ሌላው÷ በቀድሞው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሒሳብና በጀት ክፍል ሓላፊ የነበሩቱ ናቸው፡፡ ግለሰቡ የሀ/ስብከት ሓላፊነታቸውን እንደ ትርፍ ጊዜ ሥራ ይሠሩ የነበሩ፣ በሙሉ ጊዜያቸው ግን በአንድ የግል ባንክ ውስጥ በአካውንቲንግ ሞያ በመደበኛ ሠራተኝነት የተቀጠሩ፣ በዓለ ሆቴል መኾናቸው ተገልጧል፡፡

ሁለቱም በብፁዕነታቸው ዙሪያ በብፁዕነታቸው ስም ተጽዕኗቸውን ያጠናከሩ ግለሰቦችን በተላላኪነትና በሽምግልና እየተጠቀሙ መኾናቸው ተገልጧል፡፡ በዚህም እንደተባለው በወቅቱ የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ላይ ያለማስረጃ ተላልፏል የተባለው እግድ ከጸና በቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ በብፁዕነታቸው ለሥራ አስኪያጅነት የመጠቆም ዕድል እንደሚያገኙ ተስፋ ያደርጋሉ¡¡

ይህና ይህን የመሳሰሉት የጥቅመኞች ተስፋዎች ግን÷ በመጪው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከመንበረ ፓትርያሪኩ ጀምሮ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን አስተዳደር በተዋረድ በዘመናዊ መልክ ለማዋቀርና ዘመኑን የዋጀ ቀልጣፋ አሠራር ለመዘርጋት በሚያስችል የባለሞያ ጥናት ላይ ለመወያየት ከጥቅምት ምልአተ ጉባኤ ያደረ አጀንዳ ለያዘው ቅዱስ ሲኖዶስና የቅዱስነታቸው አስተዳደር አንዱ መፈተኛው ይኾናል፡፡

እኒህን የመሳሰሉ የጥቅመኞችን ተስፋዎች መሥመር ማስያዝ÷ በፀረ ሙስናና በልማት እንዲሁም በሰላምና በመልካም አስተዳደር ዙሪያከሚመለከታቸው አካላት ጋራ የተጠናከረ ሥራ ለመሥራት ከምንጊዜውም በላይ የተዘጋጀች እንደኾነች በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔዎች መግለጫ ላይ ያስታወቀችው ቤተ ክርስቲያናችን ዝግጁነት የሚለካበት እንደኾነ ጥርጥር የለውም፡፡

ምዕራብ÷ ‹‹ዕርበተ ፀሓይ›› የሚፈጸምበት ዐቢይ ማእዘን የመኾኑን ተፈጥሯ ሥራት በምሳሌነት በመያዝ በምዕራብ አዲስ አበባ ሀ/ስብከትአስተዳደር የተቀሰቀሰው ውዝግብ አፈታት÷

  • የቤተ ክርስቲያናችን የፀረ ሙሰኝነትና ፀረ ጎጠኝነት አቋም ትርጉም ባለው ደረጃ የሚታይበት፣
  • አዲስ አበባ በአራት አህጉረ ስብከት የመደራጀቱ ፋይዳ በቅርጹም በይዘቱም የሚፈተሽበት፣
  • ከሁሉም በላይ ያዘቀዘቀችውና ድልህ የመሰለችው የሙሰኞችና ጎጠኞች ‹ጀንበር› ዳግመኛ ላትወጣ ግባቷ (መጥለቋ) የሚረጋገጥበት እንዲኾን እንመኛለን፡፡

‹‹የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ለአራት መከፈል ሙስናውን ጨርሶ ባያስወግደውም ይቀንሰዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ ጥቅምት 2005 ዓ.ም/፡፡

 

በመልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው ላይ የተላለፈውን እግድ በመቃወም ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ የቀረበው የጽሑፍ አቤቱታPetition by west A.A Dioseces 00Petition by West A.A Diseces 01West A.A Petition 03Petition by West A.A Dioseces 03

 

ምንጭ፡ ሐራ ተዋሕዶ

↧
↧

ፓትርያሪክ መርቆርዮስ ለምን እንደተሰደዱ ምላሽ የሚሰጥ ባለ 63 ገጽ መጽሐፍ ታትሞ ወጣ (ይዘነዋል)

$
0
0

abune-merekoriwos-150x150(ዘ-ሐበሻ) ማርች 5 ቀን 2013 በአዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስ “ቤተክህነታዊ ሃረካት” ሲሉ ምእመናን የተቹትን ባለ 52 ገጽ መጽሐፍ በስደተኛው ሲኖዶስ ዙሪያ አሳትሞ መበተኑን በወቅቱ ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም። በስደት የሚገኘው ሲኖዶስም ለዚህ መጽሐፍ ምላሽ የሆነ ባለ 63 ገጽ ትንሽ መጽሐፍ አሳትሞ በትኗል። ይህ መጽሐፍ በኢሜይል፣ በድረ ገጽ እንዲሁም ታትሞ እየተሠራጨ ሲሆን አቡነ መርቆርዮስ ለምን ሊሰደዱ እንደቻሉና እንዴት እንደተሰደዱ? ለቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊና ታምራት ላይኔ ጽፈዋቸው የነበሩ ደብዳቤዎች፣ እንዲሁም ሕወሓት በበርሃ በነበረበት ወቅት ለሰላም እንዲሰሩ የጻፏቸውን ደብዳቤዎች ሁሉ ይዟል።

በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ይህን ለአዲስ አበባው ሲኖዶስ ላሳተመው “ቤተክህነታዊ ሃረካት” ምላሽ የሚሆን መጽሐፍ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች እንዲያነቡት ልኮልናል እንደሚከተለው አስተናግደነዋል።

መጽሐፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (PDF)

↧

ሕገ ወጥነት ከዓላማችን አይገታንም!!! (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ማብራሪያ)

$
0
0

ሕግ ምን ይላል?
አዋጅ ቁጥር ፫/፲፱፻፹፫ ዓ.ም
ስለ ሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት የወጣ አዋጅ፤ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው አካል ስላለበት ግዴታ በአንቀጽ ፬ ላይ እንዲህ ይላል
አንቀጽ ፬፤የማሳወቅ ግዴታ፤
፩/ ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ህዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ የሚያዘጋጀው ማንኛውም ግለሰብ፣ ቡድን ወይም ድርጅት የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ከሚካሄድበት ጊዜ ቢያንስ ከ፵፰ ሰዓታት በፊት በጽሑፍ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
፪/ የማሳወቂያው ጽሑፍ ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ በከተማ ከሆነ የሚደረገው ለከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት፤ ከከተማ ውጭ ከሆነ ለአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
መልስ ሰጪው አካል የከተማ ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ያለበትን ግዴታና ኃላፊነት አንቀጽ ፮ ላይ እንዲህ ብሎ ደነግጋል፡፡
አንቀጽ ፮፤ የከተማው ወይም አውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊነት፣
፩/ ከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ጥያቄ በጽሑፍ ሲቀርብለት ሰላምን ከማስፈን ጸጥታን ከማስጠበቅና የሕዝቡን ዕለታዊ ኑሮ እንዳይሰናከል ከማድረግ አንጻር አስፈላጊውን ዝግጅት ሁሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
፪/ ከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተመለከቱትን ሁኔታዎች በማገናዘብ ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ በሌላ ጊዜ ወይም በሌላ ሥፍራ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያየት ካለው ምክንያቱን በመግለጽ ይህንኑ ጥያቄው በደረሰው በ፲፪ ሰዓት ውስጥ በጽሑፍ ለአዘጋጁ ማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም የከተማው ወይም አውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው ምን ጊዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ማለት አይችልም፡፡

semayawi partyምን ተደረገ?
ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ማወቅ የሚገባው በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የሰላማዊ ሰልፍና የህዝባዊ ስብሰባ ማሰወቂያ ቢሮ እንዲያውቅ የሚያደርግበትን ደብዳቤ ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ሰዓት የተጠቀሰው ቢሮ ድረስ አቅርቧል፡፡ የቢሮው ኃላፊ ደብባቤ አልቀበልም በማለታቸው ከሰዓት በኋላም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ደብዳቤውን እንደገና አቅርቦ አሁንም አልቀበልም በማለታቸው ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ የተለያዩ አካላት እስከ ከንቲባው ፅ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉጋዮች ምክትል ኃላፊ ድረስ በመሄድ ደብዳቤውን እንዲቀበሉ ቢጠየቁም “ደብዳቤ እንዳንቀበል ከበላይ ታዘናል” በማለት በቃል ተመሳሳይ የአንቀበልም መልስ ሰጥተዋል፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ ከፓርቲው በኩል ሦስት ሰዎች ከማዘጋጃ ቤቱ ደግሞ ሦስት ሰዎች የአይን ምስክርነት ባሉበት በሰላማዊ ሰልፍና የህዝባዊ ስብሰባ ማሰወቂያ ቢሮ ኃላፊ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ወጥተዋል፡፡ ከዚህም በጠጨማሪ ደብዳቤው በፖስታ ቤት በኩል በሪኮመንዴ እንዲደርስ ተልኳል፡፡
ምን ይደረጋል?
ሰማያዊ ፓርቲ በሕግ የተቋቋመ ህግ የሚያከብር ፓርቲ ነው፡፡ ፓርቲው የሚገዛው ለህግ እንጅ ለውንብድና ባለመሆኑ ሰልፉን በዚህ መልኩ ለማሰናከል የማይቻል መሆኑን የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዲያውቁት ማሳሰብ ይፈልጋል፡፡ ሰልፉን ለማድረግ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በህግ በኩል የጎደለ አንድም ቅንጣት ነገር ባለመኖሩ ሰልፉ በታቀደው ቦታና ስዓት የሚካሔድ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

ግንቦት 15 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

↧

ፀረሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናትን የሀብት ዝርዝር ላለማሳወቅ እያንገራገረ ነው

$
0
0

ፍኖተ ነፃነት

የፌደራል ስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣኖችን የሀብት በዝርዝር ይፋ ለማድረግ ማመንታቱ በፓርላማ መነጋገሪያ ሆነ፡፡

321589_109993089111063_1484315227_aየፌደራል ስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ባለፈው ሳምንት ግንቦት 6 ቀን 2005 ዓ.ም ለፓርላማ ባቀረቡት የ2005 በጀት የአስር ወር የዕቅድ አፈፃፀም ባቀረቡበት ወቅት የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት በዝርዝር ይፋ ለማድረግ ማመንታታቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ኮሚሽነሩ ባለፈው አመትም ተመሳሳይ ሪፖርት ሲያቀርቡ “በቅርቡ የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት በዝርዝር ይፋ እናደርጋለን” ቢሉም በያዝነው አመትም ይፋ አለመደረጉ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ኮሚሽነሩ ሲመልሱም በአስደንጋጭ ሁኔታ “የሚገለፅና የማይገለፅ አለው” ብለዋል፡፡
ብቸኛው የተቃዋሚ ወኪል የሆኑ አቶ ግርማ ሰይፉ “የተሽዋሚዎች ሀብት የሚገለጽና የማይገለፀው ምንድነው?” የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም በቂ ምሳሽ እንዳላገኙ ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡ ጨምረውም “ፀረ ሙስና ኮሚሽን አሁንም የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብትና መረጃ ይፋ ለማድረግ ተጨማሪ ጊዜ መውሰድ የለበትም” ካሉ በኋላ፣ ባለስልጣናቱን በሚመለከት የሚገለፅና የማይገለፅ መረጃ ሊኖር እንደማይገባ አሳስበዋል፡፡

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live