Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

እልህ ያረገዘው –ያለወለደው። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ 13.06.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

2005

ከዬት መጀመር እንዳለብኝ ሳላውቅ እንሆ ጀመርኩት። ለሁለተኛ ጊዜ እርእስ ሰጥቼ ለመጻፍ ተሰናደሁ። ግን ይቻለኝ ይሆን? አላውቀውም። ጉዴ ይታይ።

በጓጉሎ ቀናት መታሸት – እንደ ተልባ። በወለምታ በወላላቁ ፍላጎቶች መሾክሾክ – እንደ አጃ። ባለተደላደለ አለሎ መዳጥ – እንደ ጥጥ። በላተገራ መቀንጠቢያ መነን – እንደ ባዘቶ። ለቅሞ ማፍስስ አፍሶ መልቀም። እልህ ያረገዘው ግን ያልወለደው ትዕይንት የእኛ ሃብታችን መሆኑ። እም!

„ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“  በምላስ መጋዘን ስትደገም – ስተሰለስ። ስትሞሸር – ዘውድ ስትጭን። ስትሽሞነሞን መንበር ላይ ከፍ ብላ ስትታይ ፍላጎት- ምኞት ህልም። መመኘት መልካም። ደስ ይላል። ይህን ቀን  ምኞት ማግኘት የሚቻለው ግን ማሸነፍ እራስን መርታት ሲቻል ብቻ ነው። ለማሸነፍ እልህን አግብቶ እልህን ማርገዝ። ማርገዙ ብቻውን ደግሞ ሸክም ነው። እልህ ያረገዘውን መገላገል ነው ብልሃቱ። በስተቀር ብልሃት የሌለው ቅላት።

ሰለ ወያኔ አስከፊነት ቀን እራሱ ከአመት አስከ አመት ታዳሚ ነውና ይናገራል;። ነገም ይናገራል ቢሄድም ተከታዩ ነገ መምጣቱን ስለሚያውቅ። ደንበሩም ወሰኑም ይናገራል – በቁሙ ታርዷልና። ዱሩ ጫካው ይናገራል – እርቃኑን ነውና። ካቴናው ይናጋራል ከእልፍ ጋር አብሮነቱ አና ብሏልና። ባሩዱም ይናገራል ሰፊ የሥራ መስክ ተክፍቶለታልና። መገፋቱም ይናገራል ከዳር እስከ ደንበር ተካልሏልና። ራህቡ ይናገራል ሁሉም ዓይነት ራህብ ድንኳን ጥለው ሃዘን ላይ ቁጭ ብለዋልና። መጠቃቱም ይናገራል ማህጸን ተቀጥቅጧል – አብራክም ተመትሯልና። መዋረዱም ይናገራል ክብር ተጥሷልና። ታሪክም ይናገራል – ምድማዱ ጠፍቷልና። እንዲያውም ብራና ላይ ያሉት ባህርማዶ የተሻገሩት ሳይቀሩ ሳንከሰል ድረሱልን እያሉ መልእክት እዬላኩ ነው።

ማንነታቸውን የተገፈፉት ትውፊት ገብ ቦታውች ትናንሽ መንዶሮች ሳይቀሩ ስማቸውን ተልጧል፤ እነሱም እራሳቸው አቤት ባዮች ናቸው ለሰማዩ ዳኛ። ቋንቋ የለም ጠፍቷል። ቋንቋው ጎሳ ሆኗል። ቅርሱ ተጥሷል ስለሆነም ይጮኃል ሰሚ ቢያገኝ። ይህ ሁሉ ሆኖ ግን እልሁ መጋኛ መሆን አልቻለም። እልሁ በሽታ መሆን አልቻለም። እልሁ በሽታ ከሆነ ለመዳን ትታገላለህ። ለመዳን የምትታገለው በሃኪም የተሰጠህን መዳህኒት ሳታቅማማ ተከታትለህ ከወሰድከው ብቻ ይሆናል። በስተቀር እንዲያውም ሌላ ጠንቅ ይዞ ከች።

ወይ መዳህኒተአለም አባቴ አሁን ደግሞ አንድ ነገር ነሰተኝ – መንፈሴ። ግን እሺ ንገረኝ አልኩት። „ዋናውን መሳሪያ አትዝለይ“ እያለኝ ነው። አስከትሎም እንዲህ አለኝ። …. „እልሁ እራሱ ከቦታው ስለመኖሩ አረጋግጪ“ እለኝ። እውነቱን።“ ግን ግን ጥቃቱን እንደ ክኒኗ ዋጥ ሰልቀጥ ሲደርግ የጤና ነውን? ይህም ሌላው ጉዳይ ነው። አፋቸውን ሞልተው ወያኔ ይሻላል። ይሄኛው በደል በዚህ ይካካሳል ይሉናል የጎጥ ጠበብቶች። ወያኔ „ኦሮምዬ“ የምትባል ክልል ፈጥሮልናል ቢያንስ በቋቋችን እዬተናገርን ነው በማለት በፍቅር ድብን ሲሉ አስተውላለሁ። ተጠቂሚ ነን ባዮች አልገባቸውም እንጂ እራሱ „የኦሮምያ ክልል“ የሚለው ስያሜ እኮ አንባገነን ነው። „የአማራ ክልል“ የሚለውም እንደዚሁ። „የደቡብ ህዝቦች ክልልም“ የሚለውም እንደዚሁ ወዘተ። ስለምን? በስውር ደባ፤ በረቂቅ ቋሳ የዋጣቸው ማንነቶች አሉና። የደፈጠጣቸው ማንነቶች አሉና። በእርህራሄ አልቦሽ የዳጣቸው ማንነቶች አሉና። ወለጋ እኮ የለም ወይንም አዋሳ፤ ወይንም ወሎ። እንደገና በቁጥራቸው አናሳም ቢሆኑ በአንድ ብሄረሰብ ልዩ ሥም በተከለሉ ቦታዎች ቁጥራቸው ያነሱ ኢትዮጵያዊ  ብሄረሰቦች አሉ። አሁን ወሎ አገው፣ ኦሮሞ አለ። ጎንደር ቅማንት ሽናሻ ወይጦ አለ። እኔ እንደማስበው እልሁ የሴራውን ሥር አላገኘውም። እልህ የለሾችም ቢሆኑ በወያኔ ቀለብ የሚሰፈርላቸው ከዘመንተኛው ጋር የመደቡት እራሳቸውን እዬፋቁ ስለመሆኑ አልተገለጠላቸውም። በነጠፈ ህልም ላይ እዬዳከሩ ነው ያሉት። ግርዶሽ ነገር አለባቸው። ወይንም እንደ አባት አደሩ ዓይነ ጥላ ነገር። እራሳቸው እኮ የለም። በሌለ ውስጥነት አለመኖርን እንደ መኖር አድርጎ መቀበል። የመንፈስ ድህነት ወይንም የተፈጥሮ ስጦታን ዝለት …. ዝግተም።

ክልል የሚለው ቃል እራሱ የሚከፍል የሚተረትር የሚሰነጥቅ ዲዲቲ ነው። አዲስ አበባ ክፈለ ከተማ በዚህ ስያሜ መንፈስ እንደ አወጣ ተሸኝሽኗል። ወረራው መጠነ ሰፊ፤ ወረደ ሰፊና ቁመተ ረጅም ነው።

በዚህ ስሌት በቦታ ስያሜ እንኳን ሳይቀር መብቱ የተጠበቀለት „የትግራይ ክልል“ ብቻ ይሆናል። ይህ ባለ ጊዜነትን የሚያውጅ ይመስለኛል። „ትግሬነት’ ቀን አልከዳውም እንደ ‚ኢትዮጵያዊነት“ የዚህ ሁሉ ደባ ፍሰት መነሻ መሠረታችን ያፈልሰዋል። ምድረበዳ ያደርገዋል። ይህን በትክክል ተረድትን ስንመረምረው መዳኛችን አንድ ብቻ ነው። ቀረመቱ ሳይሆን መሠረቱ ይሆናል – የፍላጎታችን አውራ ድልዳል። የመንፈሳችን ዓይነ ልቦና ሆነ እዝነ ህሊና መንሹ መሰረቱን ያውጃል። ፍሬ ዘር፤

ሥር ያለው የጥቃት ዓላማ እልህን ጠንስሶ ስለምን መገላገል አላስቸለንም? ምን አልባት በደሉ ግጥግጥ ሆኖልን? ወይንም ቅልቅል? ለዛውም በግንቦት ኢትዮጵያ ሠርግ አልተለመደም። ካልቸገረ በስተቀር … መሰረቱ መርዝ – ጣሪያው መርዝ -ግድግዳው መርዝ – ማገሩ መርዝ – መግቢያ መውጫ በሩ መርዝ።  በመርዝ ላይ ቁጭ ያለ ሰብእና እልህ ሰውነቱ እንዲፈጥር በማደረግና ባላማደረግ መሃከል ያለው ልዩነት እንደ ሰው መሆን ወይንም ይህን ጸጋና መክሊት ከመተላለፍ ይመነጫል።

ከዚህስ በኋላ ለእንጉልቻ የተፈጠረ ወይንም ቀንናና ሌሊት የእንቅልፍ ክኒኑን ወስዶ ለሽ፤ ወይንም የእልህን ትልሞች መቆጣጠር ተስኖት የዛለ አካል ተሸክሞ መኖር ዕጣው ይሄ ነው፤ እንደ እኔ እንደ ሥርጉተ ይህ አርበኝነትን ቅንቅን እዲበላው በሙሉ ድምጽ መፍቀድ ነው። አርበኝነት የግድ ነፍጥ ማንሳት ብቻ አይደለም። በሸር ላይ በመንፈስ መሸፈት። ልብን ቅርቅር አድርጎ በዳይን ፊት በመንሳት አርበኝነት አንቱ ይሆናል። መንፈስን አሸፍቶ በልብ ውስጥ ጫካን ማደራጀት፤ በተገኘው አጋጣሚ ፍቅርን ነፍጎ በቃህንን እያንቦለቦሉ ሰንጎ ማጉረስ። ለጠላትም ለግል ኢጎም። ልምምጥ ጎንበስ ቀና አያስፈልግም የዚህን ጊዜ እልህ ተፈጥሯል – የተፈጠረውም እልህ ተገላግሏል ማለት ያስቻላል። በስተቀር ኤሉሄ ነው።

እልህ የግል ሃብት ነው። የግል ንብረት ነው። እልህ እራስ ለራስ ችሎ የሚሰጠው ነፃነትም ነው። እልህ የድል መንበርም ነው። እልህ የራዕይ ጉልላትም ነው። በተለይ ተበደልኩ ለሚል ዜጋ እልህ የበሽታው ሁሉ መፈወሻ ነው። እልህ የቋሳ ሃጢያት የፈጠራቸውን ስንክሳሮች ሁሉ ይፍታህ ይላል እንደ አባቱ እንደ ጴጥሮስ። ስለሆነም የጡሑፉ ወጋግራ በሽታውን ለመፈወስ መጀመሪያ ከራሱ ይነሳ ነው አብዩ ዓምድ። በዙሪያው ያለውን ይቃኝ። እልሁን የሚመሳሳሉትን ደስ ብሎት ማቄን ጨርቄን ሳይል ይቀላቀል። ሲቀላቀል ግን ለማጥመድ ወይንም ለመጠመድ መሆን አይኖርበትም። እልሁን ለማድመጥ የእልህ ዘብ አደር ለመሆን እንጂ።

ይህም ማለት እልሁን ለመገላገል የእልሁን ሥነ ምግባር መፈጸም ግድ ስለሚለው፤ ቅንነነት – እውነት – ንጹህ ልብ – ግልጽነት – ቀጥተኝነት – ታማኝነት – አክብሮተ – ዕሴት – ውል – ለኪዳን ማደር – መሆን – ፈርኃ እግዚአብሄር –  ሁሉንም የመንፈስ ሃብቶች ሳይለግሙ ለማህበርተኞች ፈቅዶና ወዶ ግዙት – ንዱት በማለት መፍቀድ ይኖርበታል። ተጻራሪ ዕኩይነትን በመጸዬፍ መገፍተር —-

ይህን ጊዜ በደል ይረታል። መበደል ያሸንፋል። ግን ችለናል? ወይንስ ገና ታቱ ነው? የተሻለ ወያኔ ነው የሚሉ ጹሑፎችን አነባለሁ እንዲሁም አንደበቶችን አደምጥ ነበር አሁንስ? ቀንበጥ ከትምህርት ቤት ወጥቶ ሲቀር ይመቻልን? የጫጉላ ሽርሽር ነውን? እልሁ የት ላይ ይቀመጥ? የት ነው ያለው ባላንባራስ እልህ? ዳጥ። በኢትዮጵያዊነት ማእቀፍ ግን ጎጤን። „ስንት ጊዜ በንግግሩ ላይ „ኢትዮጵያን“ አነሳ“ ይህ ለአንድ በጎጡ ለሚያምን ታላቅ የተከበረ ሰው እንደ ብርቅና ድንቅ ይነገርለታል። ለእኔ ግን ስለጎጥ የሚያስብ  – የሚደክምም መንፈስ „ኢትዮጵያዊነትን“ ባያነሳ – ሳይፈጠር ቢቀርም ይሻለዋል። ውሃ መልኩ ምን ይመስላል?!!!! የእኔ ክብሮች? መልስ –  ውሃማ። ኢትዮጵያዊነትም እንደዛ ነው።

 

ክወና – ትናንትና 12.06.2014 ብራዚል ላይ አለምአቀፍ ድርጊት ተከወነ – ከተለመደው ውጪ። ነፃነቱን የተቀማ ህዝብ ባላበት ቦታ አንተ ባላህ ጉልበትና አቅም እንኳን አንደበትህን ማዘዝ እንደሚሳነህ ሃቅ እራሱን አስከበረ – አስረከበ። ገድል ነው። የፊፋው ፕሬዜዳንት ሆነ የሀገሪቱ መሪ ወሮ እዬቻሉ ግን ልሳናቸውን ማን ዘጋው? ነፃነት የሚገዛ ሸቀጥ አይደለም። ወይንም የምተሸጠው ሸቀጥ ወይንም በችርቻሮ የመትሸቅጠው – የምትሸቅጥበትም።

የእግር ኳስ እስፖርት አፍቃሪን በምልአት በመሩበት በድንቆቹ በነፔሌ በሀገረ – በብራዚል አንደበት ተከርችሞ የአሻንጉሊት ትርዒት ብቻ ቀረበ። ዳመናማ ነበር። ይህንን ዘመናችን ያበረከተልንን ትልቅ አጋጣሚ ሳናከባልለው ወይንም በኢጎ መርዝ ሳንበክለው ከራሳችን ጀመርን ይህን እናንብበው  - እንተርጉመው – እናመሳጠረው። ጩኸቱ ሌላው ላይ ሲሆን ወይንስ ከእኔም ላይ ባላው!?! ….. እንለካው።

የሬግኑ የ2012ቱ የክብር ጉባኤ አባልና የመንበር ተናጋሪ አፈሩ ይከብዳቸውና ሄሮድስ መለስ ዜናው ነበሩ። ግን ከታች የተቀመጠው ከብላቴናው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ንግግር በኋላ ያ – ክብር ልብን ነፍቶ መንቀሳቀስ፤ ያ ካለቦታ ተኮፍሱ እዩዩኝ ማለት-  ኩምሽሽ ብሎ ተኮመታተረ። የሚገርመው መሰንበት አልችል በሎ ጠንዝሎ ትንሽ ቀናት በደመንፈስ ዕብኑን ሞካከረ። ይህም አልሆነም ሰኔልና ቹቻን አዳብሉኝ ብሎ አለፈ …. ። የዚህ ዓመት የአቤዋ ድምጹም የዓለሙን መሪ ፕ/ ባራክ ኦባማን የቀጣይ የመሪነት ክብርና ዝና በምን ይዋጀዋል? መጠበቅ።

ይህ ሁሉም ሰው ባለው መድረክ፤ ባለው ዕድል፤ በእጁ በገባ ሥልጣን፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሊያስተውለው ዬሚገባ ዘመን ያፈራው ትልቅ አመክኖዊ – ክስታታዊ – ተቋም ነው። ለዛውም የዶግማ። በእጅህ ያለውን ነገር የምታከብረው ስታጠው መሆን አይገባውም። ይልቁንም ልብህ ከአንተ ጋር መሆኑን ካረጋጋጥክ ከማጣትህ በፊት ለሥነ ምግባሩ ፈቅደህ – ወደህ – ደስ ብሎህም መገዛት አለበህ። አፈና …. ለፈርዖን ለሄሮድስ – ለጋዳፊ – ለሙጋቤ – ለናዚ – ለሂትለር ለማንም አይሆንም ….። ማበጥ ——- መተርተርን – መፈንዳትን ያልማል። ጌጦቼ የእኔ ውቦች ይሄው ነው ዛሬ እኔና ብራናዬ የምናወጋችሁ።

መልካም የልደት በዓልን በፍቅር – በአክብሮት – በትህትና – ተመኘሁ ነፃነትን ለዛውም ለሴት ሳልጠብቀው ግን በተባረከች ቀን አገናኝቶ ላጎናጸፈኝ ለዘሃበሻ ድህረ ገጽ ዝግጅት ክፍል እና ታዳሚዎች።  እንኳን ለ6ኛ ዓመት ምስረታ ልደታችሁ አደረሳችሁ – አደረሰን። አዝመራማ አመትም ተመኙሁ  ከልብ – ለልቤዎቹ።

በተረፈ Radio Tsegaye Aktuell Sendungn ወይንምwww.tsegaye.ethio.info ጎራእያላችሁጊዜስታገኙበድምጽደግሞእንገናኝናፍቆትንእናወጋጋ።ኑሩልን – የኔዎቹ።

 

እልህን የምወደው የቆሰለውን ውስጤን ለመፈወስ አቅም እንዲኖራው አድርጌ መምራቴን ሳረጋግጥ ብቻ ነው!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ለመኾን እንደማይችሉ ያምናሉ

$
0
0

በአብዮቱ መባቻ ዓመታት ከደርጉ ‹‹የለውጥ ሐዋርያት›› ጋራም በቁርኝት ሠርተዋል
ከደርግ ጋራ አብሮ በመሥራትና ደርግን በማውገዝ መካከል የሚታዩት የፓትርያርኩ የአቋም ጽንፎች ፀረ አማሳኝ መስሎ የአማሳኞች ከለላ ኾኖ የመገኘት ፍፃሜ ነው!!
(ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፵፱፤ ግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም.)

ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤተ ክርስቲያኒቱና መሪዎቿ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ሊኾኑ እንደማይችሉና መንግሥት በቤተ ክርስቲያኒቷ የአስተዳደር ጉዳይ ጣልቃ ቢገባ ሕገ መንግሥቱን እንደማይፃረር አቋም ይዘው መከራከራቸው ተገለጸ፡፡

የፓትርያርኩ አቋም የተንጸባረቀው፣ ከአንድ ሳምንት በፊት በተጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖዶሱ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ለቀናት ውይይት ባደረገበት ወቅት እንደነበር የስብሰባው የፋክት ምንጮች ተናግረዋል፡፡
abune matias
የሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ማሻሻያ ለካህናት ስለተከለከሉ ተግባራት አስመልክቶ፣ ጳጳሳትና በቤተ ክርስቲያኒቱ በሓላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ ካህናት ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ አባልነት ወይም አራማጅነት ነፃ መኾን እንደሚገባቸው ይደነግጋል፡፡

ስለ አንቀጹ አግባብነትና አስፈላጊነት በተሰጠ ማብራሪያ፣ ‹‹እስከመቼ ድረስ አንድ ላይ ተጣብቀን እንኖራለን፤ ሕገ መንግሥቱ እንደሚለው ነፃ መኾን አለብን፤ ነፃ መኾናችንን ለማረጋገጥ ጳጳሳትና በሓላፊነት ደረጃ ያሉ ካህናት ከፖሊቲካ እንቅስቃሴ አባልነትና አራማጅነት ነፃ እንዲኾኑ መከልከል አለብን፤›› መባሉ ተዘግቧል፡፡

ፓትርያርኩ አንቀጹን በመቃወም ‹‹ከመሐንዲስ፣ ከዶክተር ነፃ ልንኾን እንደማንችለው ከመንግሥት ጥገኝነትም ነፃ ልንኾን አንችልም፤›› የሚል አስተያየት መስጠታቸው ተዘግቧል፡፡ አያይዘውም በሕገ መንግሥቱ የተደነገገው መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ እንጂ በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ጣልቃ ቢገባ ድንጋጌውን እንደማይፃረር የሚያሰማ አቋም አራምደዋል ተብሏል፡፡

አቡነ ማትያስ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ የመጨረሻ ወሳኝና ላዕላይ የሥልጣን መዋቅር ከኾነው ከቅ/ሲኖዶሱና አባላቱ ይልቅ ከመንግሥት ጋራ አላቸው የሚባለው ያልተገራና ያልተገደበ ግንኙነት የሊቃነ ጳጳሳቱን ቁጣ ቀስቅሷል በተባለበት ኹኔታ ይህን አቋም ማራመዳቸው እያነጋገረ እንደሚገኝ ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

Patriarch Abune Mathias formerly known as Aba Teklemariam with Dergue’s Renewal committee membersሌሎች የፋክት ምንጮች በበኩላቸው፣ ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጋራ አላቸው በሚል በተቺዎቻቸው የሚጠቀሰው ልክ ያልኾነና ያልተገራ ግንኙነት ጵጵስና ከመሾማቸው አስቀድሞ የሦስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ቀሲስና ምክትል ልዩ ጸሐፊ በነበሩባቸው የአብዮቱ መባቻ ዓመታትም፣ የወቅቱን የሥርዓት ለውጥ በቤተ ክህነቱ ለማሥረጽና ተቃዋሚዎች (በተለይ ኢዲዩ) የሕዝብ ተቀባይነት እንዳያገኙ ወደ ስሜን ኢትዮጵያ ተጉዘው የፈጸሙትን ተግባር በአስረጅነት ይጠቅሳሉ፡፡*

›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››
*YeTahisas Girgir ena Mezezuበግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ከ፲፱፻፵፰ – ፶፫ ዓ.ም. በአገር ግዛት ሚኒስቴር የሕዝብ ፀጥታ ጥበቃ መምሪያ ሓላፊ ሌተና ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ ልዩ ረዳት የነበሩት አቶ ብርሃኑ አስረስ ‹‹ማን ይናገር የነበረ… የታኅሣሥ ግርግርና መዘዙ›› በሚል ርእስ በቅርቡ ለኅትመት ባበቁት መጽሐፍ፣ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የፊት ስማቸው አባ ኃይለ ማርያም እንደነበር የጠቀሱት በስሕተት ይመስላል፡፡

በ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. በወልቃይት፣ በፀገዴና በአርማጭሆ ቆላ ደርግን በመቃወም የተንቀሳቀሰውን የኢዲዩ ኃይል ለማቆምና ደገኛው ከቆለኛው ጋራ እንዳይተባበር ለመምከር በደርግ ተመልምለው ወደ በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ካቀኑት መካከል በወቅቱ አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት አኹን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አንዱ የቡድኑ አባል እንደነበሩ የመጽሐፉ አዘጋጅ ገልጸዋል፡፡

አባ ተክለ ማርያም በወቅቱ ‹‹የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አቡነ ቀሲስ፣ በኋላ አቡነ ማትያስ ናቸው›› የሚሉን ጸሐፊው፣ ከአባ ተክለ ማርያም ጋራ አለቃ ቀለመ ወርቅ(የቤተ ክህነት ደብተራ ይሏቸዋል) በቡድኑ ውስጥ የተካተቱት ‹‹ለሃይማኖት ነክ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደነበር›› አስፍረዋል፡፡

የሕዝብ ተሰሚነት አላቸው በሚል ከጠቅላይ ግዛቱ ሰባት አውራጃዎችና የጎንደርን ከተማ በመወከል ከተመረጡት መካከል በወቅቱ የደብረ ታቦር አውራጃ ተወካይ አቶ(በኋላ ሊቀ ማእምራንና ደርግ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደር በኅብተረሰብ ተሳትፎ ላይ መመሥረት በሚል ሐዋርያዊ አገልግሎቷን በሶሻሊስታዊ መንፈስ ለመቃኘት ያቋቋመው ጊዜያዊ ጉባኤ ጸሐፊ) አበባው ይግዛው አንዱ እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡

Patriarch Abune Mathias with renewal committeesከዘመቻው ጉዳይ ጋራ በተያያዘ ስብሰባ የተደረገው በጎንደርና ደብረ ታቦር ላይ ብቻ እንደነበር የሚገልጹት አቶ ብርሃኑ፣ ‹‹ኢዲዩ እየበረታ መጥቷል፤ እኛም በሰላም ተነጋግረን ደገኛውንና ቆለኛውን እንዳይተባበር ማድረግ አልቻልንም፤›› በማለት ዘመቻው ስኬታማ እንዳልነበር ጠቅሰዋል፤ አያይዘውም ‹‹ኹለቱ የሃይማኖት ሰዎች የተመለሱት አንድም አስተያየት ወይም ማብራሪያ ሳይሰጡ ነበር፤›› ብለዋል፡፡ (ገጽ 400 – 421)
***************************************************

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር ዶ/ር ውዱ ጣፈጠ ካሱ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ በሠሩት ጥናት፣ የሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ቀሲስ የነበሩት አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት (በኋላ ብፁዕ አቡነ ማትያስ) ደርግ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የለውጥ ጊዜያዊ ጉባኤ›› (the EOC provisional council or Renewal Council) በሚል ያቋቋመው ጊዜያዊ ጉባኤ አባል የነበሩ ባይኾኑም የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር ከነበሩት ዶ/ር ክነፈ ርግብ ዘለቀ ጋራ በጥብቅ ቁርኝት መሥራታቸውን ገልጸዋል፡፡

ጊዜያዊ ጉባኤው በነሐሴ ወር ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ምክትል ሊቀ መንበር ኮሎኔል አጥናፉ አባተ ቀጥተኛ መመሪያና ቁጥጥር የተቋቋመ ነበር፡፡ ከኹለተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ጋራ ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ የገባው ጊዜያዊ ጉባኤው፣ ቅዱስነታቸው በአራት መዋቅሮች(የፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት፣ የስብከተ ወንጌልና ማስታወቂያ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ፣ የውጭ ጉዳይና ልማት ኮሚሽን) የቤተ ክህነቱን አስተዳደር ለማጠናከር ያቋቋሙትን ኮሚቴ በመጋፋት ለውጥና መሻሻል ያመጣል ያለውን የራሱን ባለአምስት ኮሚቴዎች (የሕግና አስተዳደር፣ የስብከተ ወንጌልና ትምህርት፣ የኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ የታሪክና ባህል ጉዳዮች እና የአቤቱታ ሰሚ) መዋቅር ዘርግቷል፡፡

ከጊዜያዊ ጉባኤው ጋራ ያልተግባቡትና የማሻሻያ መዋቅሩን ያልተቀበሉት ቅዱስነታቸው በወርኃ የካቲት ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. ጊዜያዊ ጉባኤው ለደርጉ ባቀረበው የክሥ ሪፖርት ‹‹ሲጠበቅ የቆየ ፍርድ›› በሚል ዐዋጅ ከመንበረ ፕትርክናው ተገፉ፡፡ በቅዱስ ሲኖዶሱና በጊዜያዊ ጉባኤው መካከል ሽኩቻ የተካሔደበት ቀጣዩ የፕትርክና ምርጫ በጊዜያዊ ጉባኤው በኩል ታጭተው የቀረቡትን ሐዋርያዊውን ባሕታዊ አባ መላኩ ወልደ ሚካኤል – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በመንበሩ ሠየመ፡፡

ጊዜያዊ ጉባኤው በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫና ሹመት፣ በአህጉረ ስብከት ዝውውር እንዲሁም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሹመት በቀጥታ ይቆጣጠር የነበረ ከመኾኑም በላይ ከደርጉ ጋራ እጅና ጓንት ኾነው በአባልነት የሠሩ አባላቱ በዋና ሥራ አስኪያጅነትም ተቀምጠው ነበር፡፡ ጵጵስና እስኪሾሙ ድረስ የቅዱስነታቸው አቡነ ቀሲስና ምክትል ልዩ ጸሐፊ የነበሩት አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት ከጊዜያዊ የሃይማኖት ጉባኤው ጋራ በጥብቅ ቁርኝት መሥራት ብቻ ሳይኾን ወደ ስሜን ኢትዮጵያ ተነቃንቀው ስለ አብዮቱ ካስተማሩና የሥርዓት ለውጡን የሚቃወሙ እንደ ኢዲዩ ያሉ ኃይሎች የሕዝብ ተቀባይነት እንዳያገኙ ከቀሰቀሱ የደርጉ ‹‹የለውጥ ሐዋርያት› አንዱ ነበሩ፡፡

“Before his appointment as bishop, Matyas had been Abune Qasis of Patriarch Abune Takla-Haymanot. Though not a member of the provisional council, he had closely worked with Dr. Kenafe-Regeb Zallaqa, chairman of the council, and was mobilized to northern Ethiopia with members of the council to teach and explain about the revolution.”(WUDU TAFETE KASSU,PhD; THE ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH,THE ETHIOPIAN STATE AND THE ALEXANDRIAN SEE: INDIGENIZING THE EPISCOPACY AND FORGING NATIONAL IDENTITY,1926 – 1921; p.366)

ቴዲ አፍሮና ውዝግብ ያልተለየው ዝና

$
0
0

በአዲስ አበባ ታትሞ ከተሰራጨው ቁምነገር መጽሔት የተወሰደ

ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ወደ ሙዚቃው ዓለም ተቀላቅሎ ወደ ዝና ማማ መውጣት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ መነጋገሪያ ከመሆን ያመለጠ አርቲስት አይደለም፡፡ በ1993 ዓ.ም ማብቂያ ላይ ባወጣው የመጀመሪያ ‹አቦጊዳ› አልበሙ የሙዚቃ አድማጩን ጆሮ ለመቆጣጠር የቻለው ቴዲ አፍሮ በወቅቱ በአለቤ ሾው ፕሮግራም ላይ በእንግድነት ቀርቦ ‹25 ዓመቴ ቢሆንም ፍቅረኛ ገና አልያዝኩም › ባለ ማግስት የከተማው ወጣት ሴቶች አይን ማረፊያ ሆኖ ነበር፡፡ ከዚሁ ይፋ ካልወጣ የሴቶች አደን ጋር ተያይዞ የመጀመሪያውን ውዝግብ አስተናገደ፡፡ ‹በሴት ልጅ ጡት ላይ ፊርማ ፈርሟል› በሚል ተሰራጨው ወሬ ከከተማ ወሬነት አልፎ የአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ገበያ መጥሪያና ማሻሻጪያ ሆኖ ነበር፡፡‹የተባለውን ነገር አላደረኩም፤ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ኩሩዎች ናቸው፡፡ ይህንን ነገር እንዳደርግ አይጠይቁኝም ፤ እኔም አላደረኩትም› ብሎ በወቅቱ ለታተመችው ቅፅ 1 ቁጥር 1 ቁም ነገር መፅሔት ላይ ቢናገርም አድናቂዎቹን ከማሳመን በቀር የወሬ ማጣፈጫነቱን አላስቀረውም ነበር፡፡
TeddyAfro_NYC-12
ቴዲ አፍሮ የመጀመሪያ ውዝግቡን በዚሁ መልኩ ለመቋመጨት ጥረት ቢያደርግም ከዚሁ አልበሙ በፊት በሰራው የመጀመሪያ ካሴቱ ሳቢያ ለሌላ ውዝግብ የተዳረገው ብዙም ሳይቆይ ነው፡፡ የመጀመሪያ ካሴቱን ሳያወጣ ለዓመታት አስቀምጦት የነበረው ቮይስ ሙዚቃ ቤት የአቦጊዳ አልበሙ የአድማጭን ጆሮ መቆጣጠር ተመልክቶ አዲሱን አልበም ለገበያ ያቀረበው ወዲያውኑ ነበር፡፡ በዚህ ሳቢያም ‹የአቦጊዳን አልበም ሽያጭ ብቻ ሳይሆን አሁን ያለበሁበት ደረጃ ፈፅሞ የማይመጥን› ያለውን ከዓመታት በፊት የተሰራውን ካሴት ‹ሳያስፈቅደኝ መልቀቅ የለበትም› በሚል ሌላ ውዝግብ ተፈጥሯል፡፡ ተፈጠረው ውዝግብ መሀል ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ ገብቶ በሽምግልና ጉዳዩን እንዲፈታ እስኪያደርግ ድረስ በመገናኛ ብዙሃን ዘንድ መነጋገሪያ ነበር፡፡

ቴዲ በሙዚቃ ስራው ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ ህይወቱና በሚያደርጋቸው ቃለ ምልልሶቹ ዝናውን ከፍ እያለ ቢመጣም ምርጫ 97 ተከትሎ ገበያ ላይ በዋለሁ ሶስተኛ ‹ጃ ያስተሰርያል› አልበሙ ሳቢያ ውዝግቡ ከግለሰብ ወደ መንግስት ዞሮ ነበር፡፡ ይፋዊ በሆነ መንገድ መንግስት ተቃውሞውን ባይገልፅም ዘፈኑ በማንኛውም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ላይ እንዳይተላለፍ ከመከልከል ጀምሮ ለጉዳዩ ሌላ ፓለቲካዊ መልክ በመስጠት የውዝግቡን ጡዘት እንዳከረረው እናስታውሳለን፡፡ ከምርጫው ጋር የተያያዘው ውጥረት ቀስ እያለ ቢረግብም ከመንግስት ጋር ያለው ውዝግበ ከአንድ ዘፈን ወደ ሶስት አድጎ ከ‹ካብ ዳህላክና› እና ‹ሼ መንደፈርን› ጨምሮ ታይቷል፡፡ መንግስት በወቅቱ ከነበረው ፖለቲካዊ ራስ ምታት ተረጋግቶ ሚሊኒየሙን ለመቀበል ሽር ጉድ በሚልበት ወቅት ቴዲ አሁንም የህዝቡን የልብ ትርታ ያዳመጠ ‹አበባ አየሽ ሆይ› የተሰኘውን ተወዳጅ ባህላዊ ዜማ ለእርቅ አውሎት ብቅ አለ፡፡ ከፓለቲካ እስረኞች መፈታት ጋር ተያይዞ የእርቅ መንፈሱ በሁሉም ሙዚቃ አድማጭ ጆሮ ማንቃጨል ቢጀምርም መንግስት ግን ዘፈኑን ዘወትር በየሚዲያው ላይ ሲለቀቅ ሁኔታውን በዝምታ ከመመልከት ውጪ ‹ሆ በል ከበሮ ሆ በል አንተ ማሲንቆ ስታይ ሰው ታርቆ› በሚለው ስንኝ ከህዝቡ ጋር እስክስታ ለመውረድ ሳይችል ቀርቷል፡፡የቴዲ አፍሮ የእርቅ መንፈስ ሚሊኒየሙን ብቻ ሳይሆን ባህር ማዶ ተሻግሮ ለመዝፈንና ለማስጨፈር ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ከሚሊኒየሙ ጋር ታኮ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ቢዮንሴ ኖውልስ በቴዲ አፍሮ ‹አበባ አየሽ ሆይ› ዜማ ወገቧን ይዛ ስትጨርፍር ታይታለች፡፡

ቴዲ በዘፈኑ የሀገሩን ልጆች አልፎ የውጪ ሰዎችን ማማለል ቢችልም ከመንግስት ጋር የገባው ውዝግብ ከዚህ ቀደም ከግለሰቦች ጋር እንዳለው አይነት ተራ የሚባል አልነበረምና ወደ እስር ቤት የሚገባበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ በብዙዎቹ አድናቂዎቹ ዘንድ አሁንም ድረስ እንደሚታመነው ‹ቴዲ አፍሮ በመኪና ሰው ገጭቶ አምልጧ› የሚለውን የአቃቤ ህግ ክስ ለመቀበል ዳግም መወለድ የሚያስፈልጋቸው ይመስላል፡፡ ‹ደጉ ይበልጣል› የተባለውን የ18 ዓመት የጎዳና ተዳዳሪ ገጭቶ ስለመግደሉና ስለማምለጡ በወቅቱ መነጋገሪያ የነበረው ክስ ከብዙ የፍርድ ቤት ቀጠሮና ምልልስ በኋለ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ ሲቋጭ ‹ቴዲ እንደ በፊቱ ተወዳጅ ሥራዎቹን ይሰጠን ይሆን ›የሚል ጥርጣሬ መኖሩ አልቀረም፡፡ የፈጠራ ስራ ችግር የሌለበት ቴዲ ከእስር ቤት በወጣ በሶስተኛው ወር ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ኮንሰርት በማዘጋጀት ገቢውን በልመና ሥራ ላይ ለተሰማሩ ወገኖች ማቋቋሚያ አደረገ፡፡ በዚህ ኮንሰርት ላይም ያገኘውን ከአንድ ሚሊየንም ብር በላይ ገንዘብም ለኤልሻዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር አስረከበ፡፡

ከሚያወጣቸው አልበሞች ጋር ተያይዞ ውዝግብ የማያጣው ቴዲ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋርም ውዝግብ ውስጥ መግባቱ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ከዘፈኖች መመሳሰል ጋር በተያያዘ በሰይፉ ፕሮግራም ላይ በቀረበ ዘገባ ሳቢያ ጉዳዩ በስምምነት እስኪፈታ ድረስ ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ጫፍ ደርሶ ነበር፡፡ ቴዲ የሌሎቹን ያህል አይሁን እንጂ ከረዥም ጊዜ ማናጀሩ አዲስ ገሠሠ ጋርም ውዝግብ ውስጥ ገብቶ የተለያዩ ሲሆን በተደጋጋሚ ተሰርቀው በወጡ ነጠላ ዜማዎቹ ሳቢያም የመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ የቴዲ አራተኛ ካሴትም ውዝግብ መፍጠሩ አልቀረም፡፡ ‹ጥቁር ሰው› በሚል ርዕስ ያወጣው አልበም ከፍተኛ የሙዚቃ ችሎታውን ያሳየበትና አዳዲስ የአዘፋፈን ስልቶችን ያካተተበት ሥራው ቢሆንም ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ፓለቲካዎ አቋም ጋር ተያይዞ ተቃውሞ የገጠመው ወዲያውኑ ነበር፡፡ ጉዳዩ ከታሪክ አንፃር መታየት ያለበትና የአድዋ ጀግኖችን ለመዘከር በሚል የተሰራ ሙዚቃ እንደሆነ የተለያዩ ሰዎች የየራሳቸውን አስተያየት በማከል በየመገናኛ ብዙሃኑ ላይ ለመከራከር መሞክሩም ፓለቲካዊ መልክ የተሰጠውን ውዝግብ ለማብረድ ሳይቻል ቀርቷል፡፡ ከዚህ ውዝግብ ቀጣይ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችለው ‹ወደ ፍቅር ጉዞ› የሚል ስያሜ የተሰጠው የሙዚቃ ኮንሰርትም በበደሌ ቢራ ስፖንሰር አድራጊነት ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ክልሎች በመጓዝ ለማሳየት ፕሮግራም ቢዘረጋም ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ጋር ተያይዞ ‹ሰጠ› በተባለ ቃለ ምልልስ ሳቢያ በደሌ ቢራ ኮንሰርቱን ሰርዞታል፡፡ በደሌ ኮንሰርቱን ለመሰረዝ ምክንያት የሆነው ቴዲ ሰጠ በተባለው ቃለ ምልልስ ሳቢያ የተቆጡ ወገኖች ‹በደሌ ቢራን እንዳይጠጡ!› የሚል የቅስቀሳ ዘመቻ በመጀመራቸው እንደሆነና ከንግድ ስራ አንፃር ኮንሰርቱን መሰረዝ አዋጭ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡ ቴዲ የተባለውን ቃለ ምልልስ እንዳልሰጠ፤ ይልቁንም በመፅሔቱ የተፈጠረ ተራ ስህተት እንደሆነ ገልጾ ለመከራከር ቢሞክርም ሰሚ
ያገኘ አይመስልም፡፡ ጉዳዩ ስር እየሰደደ የመምጣቱ አንዱ ማሳያ ተደርጎ የሚወደሰደውም የዘመቻው ቀስቃሾች የቴዲን ኮንሰርት በማሰረዝ ብቻ ሳይገቱ ሌላም የመልስ ምት መሰጠት እንዳለበት የሚያሳስቡ ቅስቀሳዎች ተጠናክረው በመሰጠታቸው የጥቁር ሰው ተነፃፃሪ ተቃራኒ ነጠላ ዘፈን በአንድ አርቲስት
ተሰርቶ ተለቋል፡፡

ይህ የውዝግብ አዙሪት ባልተቋጨበት ሁኔታ ኮካ ኮላ ለብራዚሉ የዓለም ዋንጫ በየሀገሩ ከሚያሰራቸው አርቲስቶች መሀከል አንዱ አድርጎ ቴዲን እንደመረጠው ተሰማ፡፡ቴዲም ከሶስት ወራት በላይ በአዲስ አበባና በኬኒያ እየተመላለሰ የሙዚቃ ስራውን ሰርቶ ቢያጠናቅቅም ተመሳሳይ ችግር መከሰቱ ተነግሯል፡፡ በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ብራዚል እየተካሄደ የሚገኘውን የዘንድሮውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ምክንያት በማድረግ እንደተለመደው ግዙፍ የቢዝነስ ተቋም የሆነው ኮካ ኮላ በተለያዩ ድምጻውያን ሙዚቃዎችን አዘጋጅቶ ራሱን እያስተዋወቀ ነው፡፡ ሙዚቃዎቹ የተሰሩት በብዙ ዓይነት ቋንቋዎችና ከተለያዩ ሀገራት በተውጣጡ ድምጻውያን ሲሆን የተቀረጹት በኮካኮላ ስቱዲዮ /Coke Studio/ ነው፡፡ ከ30 በላይ ከሚሆኑ ሀገራት የተመረጡ ድምጻዊያን የሠሩት የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ አፊሲያላዊ የኮካ ኮላ ሙዚቃ ‹‹The world Is our›› /አለም የኛ ናት/ የሚል ርዕስ አለው፡፡ ይሄንን ሙዚቃ በድምፅ ለመስራት ከተመረጡት በርካታ ዘፋኞች መካከል ኢትዮጵያዊው ቴዲ አፍሮ ይገኝበታል፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 መገባደጃ አካባቢ ቴዲ ለሙዚቃ ኮንሠርት ወደ ኳታር ባቀናበት ወቅት ከኮካ ኮላ ካምፓኒ ስልክ ተደውሎ በዓለም ዋንጫው ሙዚቃ ላይ እንዲሳተፍ ተጠየቀ፡፡ በዚህ መሠረት ከሌሎች አፍሪካውያን ድምጻውያን ጋር በጋራ ካቀነቀነው ዘፈን በተጨማሪ በአማርኛ ቋንቋ የተሰራና በግሉ የተሳተፈበት ሙዚቃ በኮካ ኮላ ስቱዲዮ መቀረጹ ተነገረ፡፡ ሙዚቃውም በ2014 የመጀመሪያ ወራት ላይ ለህዝብ እንደሚቀርብ ተገልጾ ነበር፡፡ ይሁንና በተባለበት ጊዜ የቴዲ አፍሮ ዘፈን አልተለቀቀም፡፡

tedddyበሌሎች ሀገራት ድምጻውያን የተሰሩ ዘፈኖች ግን በይፋ ተለቀው እየተደመጡ ይገኛሉ፡፡ በአማርኛ ቋንቋ የተሰራው የቴዲ ዘፈን ግን መዘግየቱ ሳያንስ በቅርቡ ደግሞ ሙዚቃው ከነአካቴው ከስቱዲዮ እንደማይወጣ ተሰማ፡፡ ይህን ተከትሎ ቴዲ አፍሮ በድረገጹ ላይ ወጣ በተባለ ጽሁፍ ድርጊቱን ኮነነ፡፡ የኮካ ኮላ ካምፓኒ ድርጊት ‹‹ሀገራችን ያዋረደ›› ጭምር መሆኑን በመግለጽ ጉዳዩን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚከታተለው ገለጸ፡፡ የኮካ ኮላ ዘመቻ በአብዛኛው የዓለም ክፍል የሚታወቀው ኮካ ኮላ በዓለም ላይ 200 ከሚበልጡ ሀገሮች ውስጥ ፋብሪካውን ተክሎ በቀን ከ1.7 ቢሊዮን በላይ የሚሆን ጠርሙስ ኮካ ይሸጣል፡፡ መመረት የተጀመረበትን 128 ኛ ዓመት በማክበር ላይ ያለው ኮካ ኮላ ካለፈው ጥር አንስቶ እስከ መጋቢት ባለው ሶስት ወራት ብቻ 1.5 ቢሊዮን ዶላር አትርፏል፡፡ ኮካ ኮላ በዓለም ዙሪያ የተለያዩ ተቃውሞዎች ገጥመውት የሚያውቁ ሲሆን ሁሉንም በማይበገረው የገንዘብ ሀይሉ አሸናፊነቱን አረጋግጦ ነው የተወጣው፡፡ ከአረብ እስራኤሎች ጦርነት በኋላ በአረቡ ዓለም በታየው የፀረ እስራኤል ዘመቻ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የአብዛኛዎቹ አረብ ሀገራት ኮካ ኮላን ባለመጠጣት ለፍልስጤሞች ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ጥረዋል፡፡ አረቦቹ ኮካ ኮላን ባለመጠጣት ብቻ ሳይወሰኑ ፊታቸውን ወደ ፔፕሲ አዙረዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን ይህ ዘመቻ የኮካ ኮላን ገበያ የሚፈታተንና ከገበያ የሚያስወጣ ስላልነበረ በማስታወቂያው ላይ ባፈሰሰው ከፍተኛ በጀት የዓለማችን ቀዳሚ ለስላሳ መጠጥነቱን አስከብሮ ለመቆየት ችሏል፡፡ እ.እ.አ በ1950ዎቹ አጋማሽ ላይም የህንድ ገበሬዎች ኮካ ኮላ ለማሳችን የሚያስፈልገንን ውሃ ተሸማብን በማለት ኮካ ኮላን ባለመጠጣት ተቃውሟቸውን ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ በዓመት 11 ቢሊዮን ዶላር ለማስታወቂያ ብቻ የሚያወጣው ኮካ ኮላ ንፁህ የመጠጥ ውሃን በማውጣትና ዙሪያ ለሚሰሩ ፕሮጀክቶች የሚመድበውን ማህበራዊ በጀት ወደ 50 ሚሊዮን ዶላር በማሳደግ ራሱን ከህንድ አርሶ አደሮች ዘመቻ ተከላክሏል፡፡

የኮካ ኮላ የአቀማመም ምስጢር ድብቅነቱን ተከትሎ ሱስ አስያዥ ቅመም እንዳለውና ለጤናም አደገኛ ስለመሆኑ የተወራበት ጊዜ ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶም ሰዎችን ሱስ የሚያሲይዝ የኮኬይን ቅመም እንዳለው ሲነገር ኮካ ኮላ ግን ይህ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው ሲል አስተባብሏል፡፡ያም ሆኖ ኮካ ኮላ አሁንም
ድረስ በብዙ ሀገሮች ውስጥ ተወዳጅ መጠጥ ቢሆንም እንደ ሰሜን ኮሪያ በርማና ኩባ አይነት ሀገሮች ኮካ ኮላ ፋብሪካ በሀገሮቻቸው እንዲቋቋም ያልፈቀዱ ሀገራት ናቸው፡፡እ.ኤ.አ በግንቦት 8 ቀን 1886 በአትላንታ ጆርጂያ ለራስ ምታት መድሃኒት ይሆናል ብሎ መድሃኒት ቀማሚው ጆን ኤስ ቴምበር ከካካዋ ፍሬ በሶዳ ውሃ በጥብጦ ያዘጋጀው ኮካ ኮላ የተባለው መጠጥ ይኸው ዛሬ በመላው ዓለም ይጠጣል፡፡ በወቅቱ ድካምንና ራስ ምታትን እንዲሁም ድብርትንና የወንዶችን የወሲብ ፍላጎት ያነሳሳል በሚል የተቀመመው ኮካ ኮላ በአዲስ መልኩ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ምስጢራዊነቱን ጠብቆ መመረት ከጀመረ እነሆ ዘንድሮ 120 ዓመታት ሆኖታል፡፡
ዘመቻ ‹‹ኮካ አትጠጡ››የድምጻዊው አድናቂዎችና በሁኔታው ስሜታችን ተነክቷል ያሉ ሰዎች በማህበራዊ ድረገፆች አማካኝነት በኮካ ኮላ ካምፓኒ ላይ መቀየማቸውን የሚያሳዩ ምስሎችንና ጽሁፎችን ለጠፉ፡፡ የካምፓኒውን ምርቶች ባለመጠጣት ተቃውሞአቸውን ለማሰማት ዛቱ፡፡ በተግባር ጉዳዩ ለመፈጸሙ
ማረጋገጫ ባናገኝም በቴዲና በኮካ ኮላ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ አበሳጭቷቸው ከኮካ ምርቶች የታቀቡ ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ግን አያዳግትም፡፡ በተለይ በማህበራዊ ገፆች ላይ በተደጋጋሚ ሲጻፍ የነበረውን ‹‹ፀረ-ኮካ›› ዘመቻ የቅስቀሳ መልዕክቶች ስንመለት የተባለው ድርጊት መጨረሻው የት ነው እንድንል ይገፋናል፡፡ የሙዚቃው አለመለቀቅ ‹‹ሀገራችን ከመናቅ›› የመጣ ነው ከሚል ሀሳብ ጋር አያይዞ ድምፃዊው ቅሬታውን መግለጹ ተቃውሞውን እንዲደምቅ አድርጎታል፡፡ በቴዲ አፍሮ የግል ድረገጽ ላይ ወጣ የተባለው መግለጫ እንዲህ ይላል፡፡‹‹ስለ ዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ
የተሰጠ መግለጫ ባለፉት ወራቶች ቴዎድሮስ ካሳሁን ወይም ‹‹ቴዲ አፍሮ›› ከኮካ ኮላ እና በስፋት ሲወራ ከከረመው የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ ጋር ስለነበረው ግንኙነት ያለንን አቋም እንድንገልፅ ሚርፍልን ጥያቄዎች ምክኒያት ከፍተኛ ጫና ሲደረግብን ቆይተናል፡፡ በበኩላችን በተገባው የውል ስምምነት ላይ ግንኙነቱን ሚጥራዊነት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን የገባ እና ማክበር የነበረብን ቢሆንም ቅሉ የቴዲ አፍሮ እና የኮካ ግንኙነት ወሬ እንዴት አፈትልኮ ወጥቶ ህዝብ እንዲያውቀወው እንደቻለ ቢያስገርመንም አሁን ለመገንዘብ እንደቻልነው የቴዲ ከኮካ ጋር ያለው ግንኙነት ኢትዮፒካል ንክ
በተሰኘ የሀገር ውስጥ የኤፍ.ኤም ሬዲዮ የመዝኛ ፕሮግራም አዘጋጆች አማካኝነት ያወጀው እና በሚያስገርም ሁኔታ ለኮካ የቲቪ ሥራም አድናቆቱን በመስጠት ያረጋገጠው የኮካ ኮላ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ብራንድ ሥራ አስኪያጅ የሆነው አቶ ምስክር ሙሉጌታ መሆኑን መረዳት ችለናል፡፡

ያለጥርጥር በኮካ ኮላ ስም ቴዲ አፍሮ ለኮካ የቴሌቪዥን ስራ በማገናኘት እና በዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ተነሳሽነቱን የወሰደው የብራንዱ ሥራ አስኪያጅ ነበር፡፡ እኛም ጥያቄን ውድ አገራችንን በመላው የዓም ዋንጫ ተመልካቾች ዘንድ አዎንታዊ ገፅታ የትኩረት እይታ ስር የሚያውላት በመሆኑ እና በዚህ በጉጉት በሚጠበቀው ታላቅ ዓለም አቀፍ የስፖርት ከንዋኔ ግዙፍ ቁጥር ያለው የዓለም ህዝብ ዘንድ የአገራችንን እና የህዝባችንን መልካም ገፆች ለማሳየት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ከተሟጠጠ በኋላ ነበር፡፡በመጨረሻም ምንም እንኳን በጉዳዩ ጭብጥ ዙሪያ በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ስለተያዘው አቋም የተወሰነ መግባባት ላይ መድረስ ቴሌኮንፈረንስ የሚመለከታቸው ወገኖች እንደሚገኙበት ቃል ተገብቶበት የተዘጋጀ ቢሆንም ውይይቱ ሙያዊ በሆነ መልኩ ያልተዘጋጀ፣ ግልፅነት የጎደለው፣ አለመግባባት እንዳይከሰት ለማድረግ የጋራ መፍትሔ ለመሻት ሳይሆን ቅንነት በጎደለው መልኩ የኛን ሐሳብ ለመረዳት ነበር፡፡ ቴሌኮንፈረንሱ ሆነ ተብሎ ህጋዊ ወኪል የሆነውን ሥራ አስኪያጃችንን በጭብጦቹ ላይ ለመወያየት እንዳይሳተፍ በማግለል መካሄዱ በራሱ ሂደቱ በቅን ልቦና ላይ ያለተመሰረተ መሆኑ ግልፅ ማስረጃ ነው፡፡ በመሆኑም የአርቲስቱ አድናቂ ለሆኑት ኢትዮጵያዊያን እና የውጪ አገር ዜጎች በሙሉ ከኮካ ኮላ ጋር የነበረንን ግንኙነት ያቋረጥን መሆናችንን ለመግለፅ መገደዳችን እያዘንን ስንገልፅ የዓለም ዋንጫ እስከሚከፈትበት ዕለት ድረስ ኮካ ኮላ የወሰደውን እርምጃ በድጋሚ እንዲያጤነው ያደርግ ዘንድ በተደጋጋሚ ጥሪያችንን ስናቀርብ ብሔራዊ ጠርዝ ባለው እና በውድ አገራችን፤ በህዝባችን እና አድናቂዎቻችን ላይ ጭምር የተቃጣውን የፈሪ እና ሀገር ወዳድነት የጎደለው አሳፋሪ የክህደት እና ክብር የሚያጎድፈውን ተግባር ግን ይቅር ላለማለት ወስነናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አስከመጨረሻው ዕለት ድረስ ኮካ ኮላ የተጠናቀቀውን ሥራ እንዲያሰራጨው እና እንዲለቀው ግፊት ማድረጋችንን እንደምንቀጥልበት ለአድናቂዎቻችን እያረጋገጥን ከዚህ ጎን ለጎንም ከሁኔታዎች ጋር አግባብነት ያላቸው ሰላማዊ እርምጃዎችን በመውሰድ የሁለቱንም ወገኖች ገፅታን እና ጥቅምን የሚጎዳ ማናቸውም ውዝግብ በማስቀረት በአድናቂዎቻችን የተጣሉብንን አደራ መተማመን እና እምነት ለመመለስ የሚያስችል እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡›› ቢቀር ምን ይቀርበታል? ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ከኮካ ኮላ የቀረበለትን ጥያቄ በደስታ ተቀብሎ የዓለም
ዋንጫውን የኢትዮጵያ ቅጂ ሙዚቃ ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ በሚገኘው የኮካ ኮላ ስቱዲዮ ተቀርጿል፡፡ ታድያስ መጽሔት ከአሜሪካ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ሙዚቃው እንደማይለቀቅ ከተነገረ በኋላም ኮካ ለድምጻዊው ተገቢውን የካሳ ክፍያ ለመፈጸም መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ የተቀረፀው ሙዚቃ ንብረትነቱ የኔ ብቻ ነው የሚለው ግዙፉ የለስላሳ መጠጥ ካምፓኒ ለጊዜው ዘፈኑ ባይለቀቅም ለድምፃዊው ግን ተገቢውን ነገር እናደርጋለን የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ ከዚህ አንፃር ከተመለከትነው ቴዲ ሙዚቃው ባለመለቀቁ ምንም አይቀርበትም ማለት እንችላለን፡፡ ነገር ግን ድምጻዊው ከሚያገኘው ገንዘብ ባሻገር ኢትዮጵያ በዓለም ፊት የምትታወቅበትን ዕድል አጥታለች፡፡ ቴዲም ቢሆን የደከመበት ሙዚቃ ከስቱዲዮ አለመውጣቱ ምቾት ይነሳዋል፡፡ ለምን ብሎ መጠየቁም ተገቢ መሆኑን የብዙዎቹ አድናቂዎች ሀሳብ ነው፡፡

‹‹ሾላ በድፍን››
ኮካ በዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ ራሱን ለማስተዋወቅ የሚረዱ ሙዚቃዎች ሲያዘጋጅ የዘንድሮው ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ደቡብ አፍሪካ ላይ ለተከናወነው የዓለም ዋንጫ ‹‹waving Flag›› በሚል ርዕስ ሶማሊያዊው ድምጻዊ ኬናንን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ድምፃውያን አሰርቷል፡፡
በወቅቱ ይህ ሙዚቃ ተወዳጅ እንደነበር ይታወሳል፡፡የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር አጋር የሆነው ኮካ ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ማጀቢያ የሚሆን ሙዚቃ በራሱ ስቱዲዮ መቅረጽ የጀመረው ባለፈው ዓመት ነበር፡፡ ሳምባ በሚባለው የብራዚሎች ባህላዊ የሙዚቃ ስልት የተሰራው ‹‹The World Is Our›› የተሰኘው ሙዚቃ በተለያዩ ሀገራት ሙዚቀኞችና በተለያዩ ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል፡፡ የዚህ ሙዚቃ ዋና አቀንቃኝ በትውልድ ብራዚላዊ በዜግነት ደግሞ አሜሪካዊ የሆነው ዴቪድ ኮሬይ ሲሆን ካለፈው መስከረም ጀምሮ ከ90 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ተዘዋውሮ ሙዚቃውን መድረክ ላይ ተጫውቷል፡፡
በዲቪድ ኮሬይ በዋናነት የተሰራው ይህ የኮካ ኮላ ሙዚቃ በሌሎች ሀገራት ድምጻውያን በተለያዩ ቋንቋዎች ተቀርጾ ለጆሮ በቅቷል፡፡ ከስቱዲዮ ያልወጣው የቴዲ አፍሮ ብቻ ነው፡፡ ለምን? እስካሁን መልስ የለውም፡፡ የኮካ ኮላ ሰዎች ከአትላንታ ሰጡት በተባለው መግለጫና ቴዲ አፍሮ በድረ ገፁ ባሰፈረው ጽሁፍ ሙዚቃው ስላለመለቀቁ እንጅ በምን ምክንያት እንደሆን አይጠቅሱም፡፡ ነገሩ ‹‹ሾላ በድፍን›› ሆኗል፡፡ ስለዚህ ከሁሉም ነገር በፊት ሙዚቃው ያልተለቀቀው በምን ምክንያት ነው? ብሎ መጠየቅ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

‹ኮካ ሀገሪቷን ደፍሯል?›
ቴዲ አፍሮ በርካታ አድናቂዎች ካሏቸው አትዮጵያዊያን የሙዚቃ ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ለኮካ ኮላ ሙዚቃ ሊሠራ ነው ተብሎ ሲነገር እንደ አንድ በሀገር ኩራት ተቆጥሮ በመገናኛ ብዙሀን ሲዘወርለት ነበር፡፡ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ተጠግቶ ከነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ጋር ተነጻጽሮ ሲቀርብ ነበር፡፡ ‹‹ኢትዮጵያን በብራዚሉ የዓለም ዋንጫ የሚወክለው›› የሚል መንደርደሪያ ከስሙ በፊት መጠቀስ ጀምሮ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ሙዚቃው አለመለቀቁ በዚያ ሁሉ ሙቀት ላይ በረዶ እንደመጨመር ነው፡፡ ለዚያምነው በማህበራዊ ድረገፆች ‹‹ኮካ ኮላ አትጠጡ›› የሚሉ ኢትዮጵያዊያን በብዛት ብቅ ማለታቸው፡፡ ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያን ወክሎ ከተጋዘበና ሙዚቃው በስቱዲዮ ከተቀረጸ በኋላ እዚያው ታፍኖ መቅረቱ ‹‹ክብረ ነክ›› መሆኑን እየገለጹ ነው፡፡ ‹‹ሀገር ተደፍራለች›› የሚሉ ሀሳቦች በስፋት እየተነሱ ነው፡፡ በጉዳዩ ላይ መንግስት እጁንእንዲያስገባ የጠየቁም ነበሩ፡፡ ጉዳዩ ግን የሁለት አካላት ስምምነት የሚጠይቅ ነው፡፡ ሀገራዊ አጀንዳ ለመሆን ግን አይበቃም፡፡ ተራ የቢዝነስ ስምምነትና ከዚያ ጋር ተያይዞ የተከሰተ የውል መፍረስ ነው የሚሉም ወገኖች አሉ፡፡

ኮካ ኮላ እንደአንድ የንግድ ተቋም ከድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ጋር የስራ ስምምነት አድርጓል፡፡ በስምምነቱ መሠረት ተፈጻሚ ያልሆኑ ነገሮች ካሉ ቴዲ አፍሮ ህጋዊ ጥያቄ ማንሳት ይችላል፡፡ ይሄን ለማድረግም ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡ እንዴት ተሠራ?ኮካ ኮላ ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ሙዚቃ መሪ ድምጻዊ አድርጎ የመረጠው ዴቪድ ኮሬይን ነው፡፡ ይህ ድምጻዊ ከተለያዩ ሀገራት ድምፃዊያን ጋር የየሀገራቱን ቋንቋ በመጠቀም በጋራ ሙዚቃውን ሰርቷል፡፡ ከ30 በላይ ከሚሆኑ ድምጻውያን ጋር በዚያው ቁጥር ልክ አንዱን ሙዚቃ ደጋግሞ ተጫውቷል፡፡ ይሄን ዕድል ካገኙ ድምፃዊያን መካከል ቴዲ አፍሮ አንዱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቅጅ የሆነውን ሙዚቃ ዴቪድ ኮሬይና ቴዲ በጋራ ቀርፀዋል፡፡ ኮካ ኮላ በተለያዩ ሀገራት የሙዚቃ ስቱዲዮዎች አሉት፡፡ የቴዲ አፍሮና የሌሎች አፍሪካውያን ድምጻዊያን ሙዚቃ የተቀረፀው ናይሮቢ በሚኘው የኮካ ኮላ ስቱዲዮ ሲሆን ጉዳዩን የሚከታተለውና የሚያስፈጽመው ደግሞ ማንዳላ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው፡፡ ጣቢያው ግን ሙዚቃውን ‹የውሀ ሽታ› አደረገው፡፡መጨረሻው ምን ይሆን?

ለዚህ ጥያቴ ምላሽ መስጠት ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ ሙዚቃው ከስቱዲዮ እንዳይወጣ የተደረገበትን ምክንያት አለማወቃችን ከግምት ያለፈ እንዳንናገር ያስገድደናል፡፡ኮካ ኮላ ትልቅ የንግድ ስም ነው፡፡ በሀገራችን በብዛት ከሚዘወተሩ የለስላሳ መጠጦች መካከል አንዱ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ድምጻዊ ቴዲ
አፍሮ ደግሞ ብዙ አድናቂዎች ካሏቸው የሙዚቃ ሰዎች አንዱ እንደመሆኑ መጠን ኮካ ኮላ በገበያው ላይ የሚደርስበትን ተጽዕኖ በመፍራት ችግሩን እልባት ይሰጠዋል ብለን መገመት እንችል ይሆናል፡፡በማህበራዊ ድረገፆች ‹‹ፀረ ኮካ›› ዘመቻ የጀመሩ የቴዲ አድናቂዎች የካምፓኒውን ስም ሊጎዱ የሚችሉ ሀተታዎችንም ደጋግመው እያስነበቡ ነው፡፡ ኮካ ለጤና ጠንቅ የሆነ ንጥረ ነገሮች እንዳሉት በመግለጽና የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ያልተለቀቀው ካምፓኒው ለኢትዮጵያ ካለው ንቀት የተነሳ መሆኑን በመዘርዘር አድማ እየቀሰቀሱ ነው፡፡

ይህን ስንመለከት ካምፓኒው በኢትዮጵያ ያለውን ተቀባይነት ላለማጣትና ስሙን ለመጠበቅ ሲል ‹የታፈነውን ሙዚቃ› ሊለቀው ይችላል፡፡

ማን ይንገርልን – ማን ይመስክርልን – (ከጸጋዬ ገብረመድህን አረአያ)

$
0
0

እንደ ልጄ የምቆጥረውና ከበኩር ልጄ ከዩሐንስ ጋር ያደገው ሳምሶን በሕክምና ኮሌጅ ይማር በነበረበት ዘመን በምሽቱ ሰዓት ላይ የ‹‹ፈገግታ ጊዜ›› በምንለው ግማሽ ሰዓት ያጫውተን ነበር፡፡ አዎን ሕይወት ውጥርጥር ባለበትና ጭንቀት ከቀበሌ ከሚወረወር ቀስት፣ ጭንቀት ከየካድሬውና ከየፖለቲካው ኅቡዕ ድርጅት ከሚወረወር ሌላ ቀስት፣ ጭንቀት፣ ከመስሪያ ቤት ጭንቀት፣ ከበላይ አካል ጭንቀት፣ ከበታች አካል ጭንቀት፣ ጭንቀት —- አንድ የድሮ ማስታወቂያ ሚኒስትር እንዳሉት ከላይ ከመሳፍንቱና ከመኳንንቱ በሚለቀቅብህ እሳት፣ ከታች ከሕዝቡና ከሠራተኛው ከሚነድድብህ እሳት የገና ዳቦ ትሆናለህ፡፡ ስለዚህ ‹‹በታይም አውት›› (ፋታ ልበለው) መልክ ከሳሚዬ ጋር የማደርገው የግማሽ ሰዓት ውይይት (ጨዋታ) ለእኔ “ማሳጅ” ነበር፡፡ መታሻ!
ethiopian flag
እንደ ወትሮው የዛሬው ወጋችን በክፍል ውስጥ ስለነበረው አጋጣሚ ነበር፡፡ በዚያው ዕለት በሕክምናው ኮሌጁ የመጀመሪያው ሰዓታት (ሦስት) አስተማሪው ዶክተር አሥራት ወልደየስ ነበሩ፡፡ “ዛሬ የማስተምራችሁ ስለ ጦር ሜዳ አነስተኛ የቀድዶ ሕክምና ነው” ይላሉ፡፡ አከታትለውም የጦር ሜዳውን “ሰገሌ እንበለው” ይላሉ፡፡ ይቀጥላሉ፡፡ ተፋላሚዎች በወሎው ጦር በኩል “ንጉሥ ሚካኤል” —- ይሉና ቆም ብለው ይመለከቱ ጀመር፡፡ እንዳጋጣሚ ከፊት ለፊት የተቀመጠውን አንዱን ተማሪ “ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስን ታውቃቸዋለህ? ብለው ይጠይቁታል፡፡ “አንተዋወቅም” ይላል፡፡ ሁለተኛው ጊዜ ሳይፈጅ ወደ መርካቶ ሲኬድ መግቢያው ላይ ድልድይ ያላቸው ሰውዬ ናቸው” ይላቸዋል፡፡ ሦስተኛው በሙሉ የአዋቂነት ኩሩ ስሜት ‹‹የአጤ ኃይለሥላሴ ቅድመ አያት ናቸው፡፡ ከአያቴ ጋር በጣም ይተዋወቁ ነበር›› አለ፡፡ ሌላው የፕሮፌሰር አሥራትን ከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት የበለጠ ለማጋጋል ፈለገና ይልቁንም እሳቸው በዛሬው ፕሮግራማቸው ስለጦር ሜዳ ሕክምና ለማስተማር የተዘጋጁ መሆናቸውን ስለተናገሩ “ኢትዮጵያ ከእንግሊዞች ጋር በተዋጋች ጊዜ የጦር መሪ የነበሩት አጭር፣ ፉንጋ ሰው ነበሩ፡፡ አጤ ኃይለ ሥላሴ ሠላሳ ዓመታት አሠሩአቸው” ይላል፡፡ ፕሮፌሰሩ ትንሽ ይደንቃቸውና “ኢትዮጵያ ከእንግሊዞች ጋር የተዋጋችው ትራፋልጋር ላይ ነበር ወይስ ወተርሉ ላይ ነበር?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ አራዳው ተማሪ “የለም ሰገሌና አንኮበር ላይ ነበር” ይላቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ እንግሊዞች በወተርሉና በትራፋልጋር ላይ ጦርነት የገጠሙት ከፈረንሳዩ መሪ ከናፖሊዮን በናፖርት ጋር ነበር፡፡) ፕሮፌሰሩ ቀልዱንም ሞክረውት ጥርሳቸው ሊላቀቅ አልቻለም፡፡ በጎጃም ቅኔ ቤት የሚወራ ጨዋታ ነበር፡፡ በጎንጅ የሚታወቁ አንድ የቅኔ መምህር ነበሩ ይባላል፡፡ እንደአጋጣሚ ሆኖ ጥርሶቻቸው ሽግናም ነበሩ፡፡ አንድ ቀን አንድ ወዳጃቸው ሰውን ሁሉ በጨዋታው ሲያስቅ ውሎአል፡፡ መምህር ሞገሴ ግን አንድም ጊዜ ፈገግ ሲሉ አልታዩም፡፡ ወደማታ ላይ ሰውየው “አባ ሞገሴ አንድ ደቂቃ እንኳ ሲስቁ አላየሁዎትም›› ይላቸዋል፡፡ ጥርሰ ሽግናሙ መምህርም ‹‹መቼ የምስቅበት ጥርስ ስጠኝና?” አሉ ይባላል፡፡ ለመሆኑስ በዚህ አገር ከማስለቀስ አልፎ የሚያስቅ ነገር ከወዴት መጥቶ! አባ ሞገሴ ጨርሰውታል፡፡ መቼ ለፈገግታ ታደልን፡፡

ሳምሶን (ከብዙ ዓመታት በፊት ጀምሮ ዶክተር) እንዳጫወተኝ ዶክተር አሥራት ወረቀቶታቸውን ሰበሰቡና፣ በጥቁር ሰሌዳው ላይ የጻፉትንም አንዳንድ የህክምና ዓይነቶች ጠራረጉና “በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ካሉ ተማሪዎች ጋር አገርን በተመለከተ መነጋገር የሚያስቸግር አይመስለኝም ነበር፡፡ በተለይም ሀብተ ጊዮርጊስን ከማያውቅ የዩኒቨርሰቲ ተማሪ ጋር ምን ጉዳይ አለኝ?” በማለት ክፍሉን ጥለው ወጡ፡፡ ከዚያ ወደ ቢሮአቸው ሄደው በትካዜ ባሕር ይሰጥማሉ፡፡ ያለፉትን ዘመናት ጦርነቶች፣ የጦር አገዛዦቹን ከነጀብዱዎቻቸው፣ በድል ጊዜ የነበረውን ሽለላና ፉከራ፣ የዘመቻ ባህልና የጦርነት መንፈስ አንብበዋል፤ ሰምተዋል፡፡ ፋሽስት ኢጣልያ አገራችንን በወረረችበት ዘመን የነበረውን ውጣ ውረድ፣ ማን ከማን ጋር እንደቆመ፤ ስለጀግንነትና ስለክህደት ሰምተዋል፡፡ ተከታትለዋል፡፡ ሲናገሩ ኖረዋል፡፡ እያደር አገሪቱን የጀግና ድርቅ እንደመታት፣ የእምነት ድቀት እንደወረደባት ብዙ የሚናገሩና ቁጭታቸውም የማይገታ መሆኑን ሰው ሁሉ የሚያውቅላቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ ከክፍል ገብተው “ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስን ታውቃላችሁ አይደል?” ሲሉ የተሰጧቸው (እዚህ ላይ ያልተጠቀሱም አሉ) መልሶች አስደነቁአቸው፡፡ በእንግሊዝ አገር ይማሩ በነበረበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን እንደ ብርቅ ሕዝብ፣ እንደ ሰማያዊ ተዋጊ ኋይላት፣ የጥቁር ሕዝብ እንቁና እግዚአብሔር ለራሱ መከበርያ አድርጎ —– የፈጠረው ተደርጎ በብዙዎች ይታይ እንደ ነበር አስታወሱ፡፡ የአድዋው ጀግና መሪ የወቅቱን የአውሮፓ ኃያል መንግሥት ያንኮታኮተበትንና ጥቁሩን ሕዝብ እንዳኮራው ሁሉ ተፈሪ መኮንን ወደ ሥልጣን ሲመጡ ‹‹ይኸ ደግሞ ለእኛ ሁሉ የተወለደልን ነፃ አውጫችን ነው›› ብለው እንደ አዳኝና የአርነታቸው ምልክት አድርገው እንደ ተቀበሉአቸው አሰቡ፡፡ ራስ ተፈሪን እንደ አምላክ እንደሚያዩአቸውም አሰቡ፡፡ አድዋን እንደገና፣ ተድአሊን፣ ጉዳጉዲን በአእምሮአቸው አሰሱ፡፡ አጼ ኃይለሥላሴን የሚያደንቁአቸውን ያህል በእነ በላይ ዘለቀ፣ በእነ አቶ ፈጠነ፣ በአፈንጉሥ ታከለ—– በእነ ልጅ እያሱና በአባታቸው በንጉስ ሚካኤል ሞት የነበራቸው ቅሬታ ትዝ አላቸው፡፡ አጼ ኃይለሥላሴ ይቺን አገር ያስከበሩአት መሪ መሆናቸውን እያሰላሰሉ ደግሞ አወዳደቃቸውን፣ አሟሟታቸውንና አብሮአቸውም የሦስት ሺህ ዓመት የዙፋን አገዛዝ ምዕራፍ መዘጋቱን በአእምሮአቸው አወጡ አወረዱ፡፡ ሳያስቡት እንባ ወርዶአቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ታላቅነትና የሕዝብዋ አንድነት ግዙፍ ታሪክ እየወደቀ ይሆን? ብለውም መጨነቅ ያዙ፡፡

ይህ ትውልድ በዚህ ዓይነት ውጣ ውረድ ውስጥ አላለፈም፡፡ ወይም ያንን ዘመን በታሪክ ቅብብሎሽም አላወቀውም፡፡ በአንድ ወቅት እንደ ገለጡልኝ “ጀግና ስንፈልግ ባጀን” የሚለውን የእኔን የጦቢያ መጣጥፍ ካነበቡ በኋላ በአካል የሚያውቁአቸውን ቀኝ ጌታ ዩፍታሔ ንጉሤን አስታወሱ፡፡ ከዚያ በኋላ ቀኑን ሙሉ ተበጥብጠው ውለዋል፡፡ “ስማ! አሉኝ” አቤት አልሁ፡፡ “የሼክስፒየርን ሐምሌት አንብበሃል” አሉኝ፡፡ አዎን ብዙና ዋነኛ ስንኞቹ አሁንም በአእምሮዬ ውስጥ ቀርተዋል፡፡ በቃሌ ነበር የማንበለብላቸው አልኋቸው፡፡ ያነሱብኝ ሐምሌት ከመቃብር ቆፋሪው ሰውዬ ጋር ያደረገውን ንግግር ነበር፡፡ በቁም የሞቱ፤ ሞተው ያልተቀበሩ፤ ሞተውም አለን የሚሉ፤ አለንም የሚሉ ምውታን! ዶክተሩ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔን ያነሱበት ምክንያት ገብቶኛል፡፡ ዩፍታሔን እንደ ሼክስፒየሩ መስፍን (ልዑል ሐምሌት) በመቃብር ሥፍራ የሚባዝን ፍጡር አድርገው ነበር ያዩአቸው፡፡ አዎን ከሐምሌት የሚለዩት ዩፍታሔ ከሙታን መካከል ሕያዋንን የሚፈልጉ በመሆናቸው ነው፡፡ ዮፍታሔ ጀግና ናፈቃቸውና “ዓይኔን ሰው አማረው” አሉ፡፡ ባበደ ቅኔ

‹‹አጥንቱን ልቁጠረው መቃብር ቆፍሬ
ጎበናን ከጋላ አሉላን ከትግሬ
ስመኝ አድሬአለሁ ትናንትና ዛሬ ——
“ዓይኔን ሰው አማረው” አሉ?

የአገር ናፍቆት፣ የጀግና ረሃብ፣ የታሪክ ምርምር ፣ የእኔነት ፍለጋ አንድ ሕዝብ ከከፍተኛ ብሔራዊ ውድቀት ላይ በሚገኝበት ሰዓት የሚያጋጥም አባዜ ነው፡፡ የታሪክ ክፍተት፣ የእኔነትና የጋራ አገር ሳይታሰብ ከትልቅ እንቆቅልሽ ውስጥ መውደቅ፣ ወደማይታወቅ፣ ጉዞውም ወዳልለየ አቅጣጫ ይወስደዋል፡፡ ይህንን ወቅት ያሰላስሉአል፡፡ በነገራችን ላይ በብዙዎች መጣጥፎቼ ውስጥ ሐምሌትን ሳልጠቃቅስ አልቀረሁም፡፡

በቅን የኢትዮጵያ ልጅነት ከሚታወቁት ዶክተር ጋር የምር ንግግር ነበረኝ፡፡ ባለፈው መጣጥፌ (ጅብ ቲበላህ በልተኸው ተቀደሰ) ላይ ለማመልከት እንደሞከርሁትም በመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት ምክትላቸው ከነበሩት (በኋላ የቅንጅት ሊቀመንበር) ከአቶ ኃይሉ ሻውልም ጋር ስለዚህ አገር የጉዞ አቅጣጫ ቀን ከሌት የምንወያይባቸው ጊዜያት ነበሩ፡፡ ዋናው ጉዳይ አንደኛ የመጣውን አደጋ መመለስ ነው፡፡ ሁለተኛ ኢትዮጵያን በተመለከተ እዚህ ስንደርስ የተቀረጸውን ታሪክ ማቃናት ነው፡፡ ሦስተኛ በየትም አገር በማንኛውም ዘመን ብቅ የሚል ሥነ መንግሥት አለ፡፡ በእኛ እምነት በዚህ ወቅት የመጣብን ሥነ መንግሥት ጤና ጉዳይ አጠያያቂ ከመሆኑ ላይ ነው፡፡ ከሥርዓቱ ጋር ሊግባባ የሚችል ማን ጤነኛ ሰው አለ? ምን እናድርግ? ከዜሮ መነሳት ሳያስፈልገን አይቀርም፡፡

የትናንቲቱ ኢትዮጵያ የዛሬውና የነገይቱ ኢትዮጵያ መሠረት ናት፡፡ የዛሬ ኢትዮጵያውያንም በትናንቲቱ ኢትዮጵያ መሥራቾችና የመሠረት ድንጋይ አቀባዮች ትከሻ ላይ የቆምን ነን፡፡ ይህን በመካድ አዲስ ታሪክ እንመሰርታለን ለሚሉ አጥፊ ኃይላት ሶማሌዎች አንድ አባባል አላቸው፡፡ “አዲስ ጫማ ከመግዛትህ በፊት አሮጌውን አትጣለው” ይላሉ፡፡ የወደፊቱን ተስፋ ሊያሳጡን የሚፈልጉት የዚህ መንግሥት ባለቤቶች የትናንት ደሆችና የዛሬ ውርስ የሌለው ሕዝብ አድርገው ፈርደውብናል፡፡ የሚያሳዝነው ለዚህ ሁሉ ሴራ የራሳቸው ትረካ፣ አዲስ ታሪክና ድርሰት ይዘው ሲቀርቡ የቅጥፈታቸው ሰለባ አለመታጣቱ ነው፡፡ አንድን ሕዝብ የጋራ ታሪክ አልባ ማድረግ፣ መነሻና መድረሻ የሌለው —— መሠረትና መንደርደሪያ አልባ ማድረግ በቀላል ቋንቋ የሚገለጥ ኃጢአት አይመስለኝም፡፡ በአንድ ሐረግ ለመግለጥም ሁላችንም እየተገረፍን እንደ ከብት ወደ ቄራ እየተወሰድን ነው፡፡ በጉልበት የምንጋተው መርዝ! ከዚህ ቀደም በተጠቀምሁበት ቋንቋ እንደገና እመለስበታለሁ፡፡ ለእነዚህ ነፍሳት እግዜሩም ሌላ ገሐነም ማዘጋጀት አለበት፡፡

minilikበመጀመሪያዎቹ አንቀጾች ለማመልከት እንደ ሞከርሁት የቅርቡንም ሆን የጥንቱን የኢትዮጵያ ታሪክ እኛም ከሰባው ዓመት ባሻገር የዘለልነው እምብዛም ክትትል በማጣት በተጨማሪም ወደ ሥልጣን እርካብ ላይ የወጣ ሁሉ ፀሐይ ብርሃንዋ መስጠት የጀመረችው በእነሱ አገዛዝ ጀምሮ መሆንዋን ለማስረገጥ ብዙ ትርምስ ሲፈጠር ኖርዋል፡፡ እውነት ነገር ይነገር፡፡ በአጼ ኃይለሥላሴም ዘመን ቢሆን የምኒልክም፣ የቴዎድሮስም፣ የዩሐንስም ታሪክ ጉልህ ሆኖ እንዳይወጣ ይፈለግ እንደነበረ ምስክር ነኝ፡፡ የዚህም ምክንያት በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመንና ታሪክ ላይ ምንም ጉዳይ ወይም ግለሰብ ጥላውን እንዳይጥል ስለሚፈለግ ነበር፡፡ በዘመናቸውም የነበሩትን አርበኞች ሁሉ ታሪክ ለቅመን በንጉሠ ነገሥቱ ትከሻ ላይ በመቆለል እውነተኞቹ አርበኞች ሳይታወቁ፣ ታሪካቸውን፣ በአፍ በመቀባበል እንጂ ተነግሮ ሳንጠግበው ሰዎቹ ወይ ተገድለዋል፡፡ በገመድ ተንጠልጥለዋል ወይም የእርሳስ ሲሳይ ሆነዋል፡፡

ያለፉትን መንግሥታት በመጠኑና ምናልባትም ይበዘባቸዋል በማይባል ሁኔታ ጀግንነትና ጀግናን ባለማክበር የተሰለፉትን አገር ሻጮችንና ለአገር ክብርና ሰማዕትነት የቆሙትን ወገኖቻችንን ሲገድሉና ሲያስገድሉ የኖሩትን ስንተች በጅተናል፡፡ አዝናለሁ፡፡ በባንዳነትና በአገር ጠላትነት የቆሙትን በየጊዜው ስናሳቅል (እኔን ጨምሮ) የቆየነውን ያህል ለዛሬውና ተረካቢው ስለ ጦርነቶታችን፣ ስለ መሪዎቻችን በጎ በጎ ምንባብ አቅርበን የምናውቅ አይመስለኝም፡፡ በዚህ የተነሳ እንደምትከታተሉት ሁሉ ውሸት ይነግሥ ዘንድ፣ የፈጠራ ታሪክ ተአማኒነት ያገኝ ዘንድ አስተዋጽኦ አድርገናል፡፡ የእውነት አለመነገር ለቅጥፈት ተቀባይነት አስተማማኝ ሁኔታዎችን አስገኝቷል፡፡

ውሸትን የመሰለ ጨካኝ ነገር የለም፡፡ ውሸት ደግሞ ሰው ሳይሆን ባሕርይ ነውና ያንን ገፋ አድርግን ካየነው እንደ ዋሾ ሰው ጨካኝ የለም ለማለት ይቻላል፡፡ ትንሽ ዕድሜህ ገፋ ሲልና በመሠረቱም በቤተሰብ በሚሰጥ ትምህርትና ግብረ ገብነት ተኮትኩተህ ካደግህ ተራራ የሚያካክለው የወያኔዎች ቅጥፈት ያሳብድሃል፡፡ ቀደም ሲል እንዳልሁት ደግሞ ይቺ አገር ከምንም ምንም የበለጠ ሀብትዋና ኩራትዋ የዘመናት ጀግንነትና ለአንድነትዋ የተከፈለው መስዋዕትነት ሆኖ ሳለ ያለንን አውቀን ያለማሳወቁ ጎዳን፡፡ ጎድቶናል፡፡ ሌላው ቀርቶ ልጆቻችን እንኳ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን እየተመለከቱ “የፕሮፓጋንዳውን እውነት” ወደ ማመኑ አዘንብለዋል ባይ ነኝ፡፡ በተለይም መንግሥት ይዋሻል ብሎ ለማመን የማይፈልገው የዋሕ ሁሉ ደህና የፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆኖአል ባይ ነኝ፡፡ የማላስባቸው ሰዎች ሳይቀሩ እኔን አዋቂ አድርገው “ጋሽ ጸጋዬ ይኸ ቴሌቪዥን ላይ የሚቀርበው የምኒልክ ጭካኔ ምን ያህል እውነት ነው?” ብለው ይጠይቁኛል፡፡ እንደአጋጣሚ ደግሞ መኪናዬ ውስጥ በተለዋዋጩ የአየር ጠባይ የወየበች መጽሐፍ አለችኝ፡፡ Who will tell the people? የምትል፡፡ ለሕዝቡ ምን እንንገረው? የሚሉ ፋይዳዎችን የሚነካካ ነው፡፡ አዎን ለሕዝባችን —— በተለይም ለአዲሱ ትውልድ ምን እንንገረው? የእነማን ልጅ መሆኑን ——- በምን መሠረት ላይ የበቀለ መሆኑን እንዴትና በማን ይነገረው? አዎን ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላይ ምኒልክንና የአድዋ ጦርነትን ምኒልክንና አርሲን ——- በጠቅላላውም ምኒልክንና የታሪክ ዘመኑን በተመለከተ የሚቀርበው ፕሮግራም ደሙን ያላፈላው ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ የፈጠራ ድርሳንና በአሁኑ ጊዜ ደግሞ እየሰጠመ የሚገኘውን የወያኔ መርከብ ለማዳን ሲባል የተፈበረከው ቅጥፈት መልስ የሚገባው አይመስለኝም፡፡ በእኔ በኩል ውሸትን ማስተባበል ሥራዬ ነው ብዬ አላውቅም፡፡ እውነትን በእውነቱና በሐቀኛ ቅርጹና መልኩ ማሳየት እርግጥ የአደጋ ጊዜ ግዴታ ይሆናል፡፡ አለዚያ ለፈጠራ ድርሳን ሁሉ እንደ አስተባባይና ተቃዋሚ ሆኖ መጮህ ተገቢ አይደለም፡፡

ፋሽስቶችና ናዚዎች አብረው የሚጓዙባቸው የጋራ ባሕሪያት አሉአቸው፡፡ ይኸውም በተደጋጋሚነትና በአሰልቺነት የሚቀርበው የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ የደገምሁት ካልሆነ በቀር ሙስሊኒ ራሱ “ማይክሮፎኑን” ከያዘ የሕዝብን ቀልብና ልብ መማረክ ዕዳው ገብስ ነበር፡፡ (ለእኔ ተውልኝ ነበር የሚለው) በዚህም የተነሣ የኢጣልያ ጎረምሶች ለእሱ ፕሮፓጋንዳ፣ የጀርመን ወጣቶች ከሒትለር ለምትወጣ አንዲት ቃል ተገዥ ሆኑ፡፡ ሕዝቦቻቸውም ወደ እልቂትና አገሮቻቸውም ወደ ፍጹም ውድመት መሩ፡፡

ሁላችሁም ልትስማሙኝ እንደምትችሉ አምናለሁ፡፡ በአንዲት ነጥብ ላይ ማለቴ ነው፡፡ ወያኔ በመጣበት እግር መውጣት ሳይሆን መጽሐፋችን እንደሚለው “በታላቅ መንቃቃት” የሚያልፍበት “የታላቁ መልአክ” እንቢልታ ከሚጮኽበት ደረጃ ላይ ደርሶአል፡፡ ይኸን ራሱም አላወቀውም አይባልም፡፡ ከሁለት ባላ ላይ ተንጠልጥሎ ሁለት አደጋ በማድረስ “የመጣው ይምጣ” ላይ ይገኛል፡፡ የጨረሳቸውን የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ፈለግ ተከትለው አመጹን የሚያፋፍሙ ወጣቶችን ጥያቄዎች ለማስተኛት ኦሮምኛ የሚናገሩ የመንደሩን ሰዎች የቴሌቪዥን እንግዶች እያደረገ ነው፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ በማድረግ “የምኒልክ ሐውልት በፊንፊኔ መቆም ይገባዋል ወይ? የናዚ ሐውልት በለንደን እንዲቆም ይፈቀዳል ወይ?” በማሰኘት የዛሬን ጥያቄ በሌለ ታሪክ ሊለውጠው እየሞከረ ነው፡፡ በሌላም በኩል በአማራውና በኦሮሞው መካከል ያለውን የማያረጅና የማይፈርስ ድልድይ ለማቃጠልና ደም ለማፋሰስ እየሞከረ ነው፡፡ እውን ለዚህ ዓይነቱ ተለማማጅ ፕሮፓጋንዳ የምንፈታ ተራ ሕዝብ ነን?

በዚያን ሰሞን የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ መሪ ለሆነ ወዳጄ ስልክ ደውዬለት ነበር፡፡ “ምን እየተፈጠረ ነው?” አልሁትና “እባክህ በአገር ሽማግሌ ጠፍቶአል የማይባል ነገር የለም፡፡ የማይሰማ ታሪክ፣ የማይሰደብ ጀግና፣ ስለኢትዮጵያ አንድነት የማይነገር ተረት የለም” አለኝ፡፡ በዚህ መጣጥፍ ላቀርበው ላሰብሁት አሳብ ተጨማሪ ግፊት ፈጠረብኝ፡፡ የሽማግሌ ከአገር (በአገር) መጥፋት፣ የታሪክ ምስክሮች ከአገር (በአገር) አለመኖር፣ ሕሊና ያላቸው ሰዎች ወጣ ብለው ለመናገር ያለ መቻል (ጥቂቶችን በማኅበራዊ ድረ ገጽ ብናነብብም) በአገር ላይ እየደረሰ ያለውን አደጋ ምን ያህል ጎድቶታል? ብዙ ብዙ እንደሚባለውም አንድ አገር ላይ ሕሊና ቢሶች ከሚያደርሱባት አደጋ ይልቅ ተከናንበው የተኙ የእውነት ምስክሮች በዝምታቸው የሚያደርሱት አደጋ መቶ እጥፍ ነው፡፡

“ሽማግሌ ዜጋ ጠፋ” አለኝ ወዳጄ፡፡ ወያኔ እንደ መጣች ታሪክ መዘበራረቅና የጥላቻን ዘር መበተን እንደ ጀመረች “ኢትዮጵያን በትክክለኛ ቅርጽዋና ይዘትዋ የሚያውቁአት አረጋይ ዜጎች ነበሩ፡፡ በሚኒስትርነት፣ በአምባሳደርነት፣ ሕዝብን በማስተባበርና በጦር ሜዳም ውሎ የታወቁ አባቶች ነበሩ፡፡ እነዚህ አባቶች ሁኔታው ሁሉ አገርን የሚያዋርዱና ቀስ በቀስም የእያንዳንዱን ዜጋ ሕልውና የሚጻረሩ መሆኑን በመረዳት ባለቀ ዕድሜያቸው ላይ “የኢትዮጵያዊነት ማኅበር” አቋቁመው ነበር፡፡ እነዚህም አቶ ሐዲስ ዓለማየሁ፣ ቢትወደድ ዘውዴ ገብረሕይወት፣ ደጃዝማች ዶክተር ዘውዴ ገብረሥላሴ፣ ልጅ ሚካኤል እምሩ፣ ደጃዝማች ወልደሰማያት ገብረ ወልድ ፊታውራሪ ገብረሕይወት፣ አቶ በለጠ ገብረጻድቅና ዋናው ጸሐፊ አቶ ሳሙኤል ዓለማየሁ ነበሩ፡፡ የፖለቲካ ሥልጣንን አይተውትና ጠግበውት በመጨረሻ ዘመናቸው ላይ የነበሩትን እነዚህን አባቶችና ሁለት ሦስት ወጣትነት ያላቸው ቅን ዜጎችን ለማየት ያስደነገጣቸው ወያኔዎች ይኸ አጀንዳ ይፈርስ ዘንድ ያልጣሩት መስክ አልነበረም፡፡ በዚህም በስደቱ ዓለም ተመሳሳይ ጥረቶች መደረጋቸውን አውቃለሁ፡፡ ልብ በሉልኝና አረቡ ዲታስ አሜሪካ ድረስ መረቡን ዘርግቶ ወጣቶቻችንን ለመከፋፈል የሚያደርገውን ትከታተሉት የለም እንዴ? በስፖርቱ ስም!

“የሽማግሌ” ሚና ምንድን ነው? ታሪክ ሲዛባ፣ ሕግና የታወቀው ሥርዓት ሲናጋ፣ በሕዝብ መካከል ሰላም ሲታጣ መምከር፣ መገሰጽ፣ ማስተማር ነው፡፡ ይኸ ነበር ባህላችን! በዛሬው የእብደት ዘመን ግን እንደምከታተለው በእርግጥ የሽማግሌ ሚና ሊጫወቱ የሚገባቸውና በዚያ ሰልፍም ከመጀመሪያው ረድፍ መገኘት የሚኖርባቸው አንዳንድ ግለሰቦች ከአጥፊዎች ጋር ማኅበር በመጣጣት ላይ መሆናቸውን ተገንዝቤአለሁ፡፡ ይኸ የሚያስታውሰን ፈረንጆች “ንጉሡ ራቁታቸውን ናቸው” የሚሉትን ይትበሐል ነው፡፡ እንደሚባለው የንጉሡ ባለሟሎች በዓይነቱ፣ በጥራቱና በረቂቅነቱ እስከዛሬ የማይታወቅ ልብስ እየተሰራልህ ነው ብለው አእምሮውን አስተውታል፡፡ በመጨረሻም “በዓይን የማይታየውን ልብስ ለብሰሃል” ብለው በዙሪያው እየተሽከረከሩ በወደል ወደሉ ቋንቋ ያደንቁት ጀመረ፡፡ በፊቱ እየተንበረከኩም “ንጉሣችን ለዘላለም ይኑር! ዓይን አይቶት የማያውቀውን ረቂቅ ልብስ ለብሶ ለሕዝብ ይታይ ዘንድ ወደ አደባባይ ይወጣል” ብለው ከፊት ለፊቱ መሮጥ ይይዛሉ፡፡ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ያጨበጭባል፡፡ ሆታው ሌላ ነበር፡፡ ሁሉም አጨብጫቢ ነው፡፡ “ሆ” ባይ ነው፡፡ በመካከሉ አንዲት ትንሽ ልጅ ——– አእምሮዋ በቅጥፈትና በማጭበርበር ኃጢአት ያልተበከለ-ከአባትዋ ትከሻ ላይ እንደታዘለች “ንጉሡ ራቁቱን ነው፡፡ ንጉሡ ራቁቱን ነው” አለች ይባላል፡፡ ታዲያን እንደ የእውነት ምስክሮችና የአገሪቱ ሕሊናዎች አድርገን የምንመለከታቸው (በእኛም አገር ዛሬ) ሰዎች ራቁቱን ያለውን ንጉሥ ሲያቆላጵሱት እየሰማን ነው፡፡

የአድዋ ጦርነትና የምኒልክ ዘመን በሰባትና ስምንት ሺ ዓመት የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደ “ትናንት” ማታ የሚታይ ይመስለኛል፡፡ እኔ አንድ ትሁት ኢትዮጵያ ዜጋ ደግሞ የተወለድሁት ፋሺስት ኢጣሊያ ከተባረረች በኋላ ሲሆን በምኒልክ ዘመን ሁነኛ ሥፍራ የነበራቸው ሰዎችን ለማወቅና ለማነጋገር ዕድል ገጥሞኛል፡፡ እንዲያውም የአክስቴ ባለቤት (የእናቴ ታናሽ እህት) ልጅ ደስታ ምትኬ የእቴጌ ጣይቱ የአክስት ልጅና ጸሐፊያቸውም ነበሩ፡፡ በተደጋጋሚ በመጣጥፎቼ የጠቀቀስኋቸውን ጋዜጠኛና ከንቲባ ደስታ ምትኬ፣ ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለማርያም (ዋየሕ) ደጃዝማች ከበደ ተሰማን፣ ፊታውራሪ እማኙ ይመርን ሌሎችንም አውቃለሁ፡፡ እንደማምነውም ዛሬም ጭምር በዚያ ዘመን የኖሩ ከአምስት እስከ አሥር ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ (ሰሞኑን ባለ 139 ዓመት ዕድሜ ኢትዮጵያዊ ብቅ አሉ ልበል?)

የምኒልክ ዘመን ወደ ኋላ ብዙ የዘመን ርቀት ሄደን በብዙ ውጣ ውረድ ታሪኩን የምንፈለፍልበት ጣጣ ያለው አይደለም፡፡ የኢትዮጵያን ዕድሜ በምኒልክ ዘመን ሲወስኑት የኖሩት ወያኔ ገዥዎቻችን ግን መረጃው ያላረጀውን፣ ብል በልቶ ያላፈጀውን ቁልጭ ያለ ታሪክ በፈጠራ ድርሳን ለምን እንደ ለሰኑት፣ የፈጠራ ታሪክ ደራሲ (እነ ተስፋየ ገብረአብ) ለምን እንደሾሙብን ግልጽ ነው፡፡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን በታላቅና ታሪካዊ ሁኔታ የተመሰረተውን አንድነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ ለማፍረስ ያገኙት ስልት ይኸ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡

ለሕዝባችን ስለዚያ ዘመን ማን ይናገር? ማን የሕዝብ ሕሊና ሆኖ ይመስክር? ታሪክ ምን ይላል? ከመጠነኛ ንባቤ፣ ባለፉት ዘመናት በምኒልክ ዘመን ከነበሩ አዛውንትና አዋቂዎች ወግና ምስክርነት በመነሣት ያቅሜን ትንሽ “እውነት” ብተነፍስ ዛሬ ማታ ጥሩ እንቅልፍ የምተኛ ይመስለኛል፡፡ በቻይናዎቹ የታኦ ፍልስፍና እንደሚነገረው “ማለዳ ላይ ታኦ አንብበህ ማታ ላይ ብትሞት ደስ ይበልህ፡፡ የጽድቅ መንገድ ይኸ ነውና” ይላል፡፡

እምዬ ምኒልክ – ትንሽ ስለ ምኒልክ ስብእና

ስለ ልደታቸው፣ ስለ ትምህርታቸው፣ በአጤ ቴዎድሮስ ተወስደው እንደ አባት እንዳሳደጉአቸውና ልጃቸውን እንደዳሩላቸው ከመቅደላ አምልጠው እንዴት ወደ ሸዋ እንደ ተመለሱ ማውሳት ዝርዝርና መጽሐፍ የሚወጣው ይመስለኛል፡፡ ይልቁንም ስለ መንግሥት አመራር ስታይላቸው፣ ስለሕዝባዊነታቸውና ስለ “አረብ ዘመቻቸው” ብቻ ብናወራስ?

ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት የተባሉበት ጊዜና የአጤ ዩሐንስ መንግሥት ማክተሚያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጭካኔ ይልቅ ርህራሄና ፍቅር የተራበበት ዘመን ነበር፡፡ አጼ ቴዎድሮስን በነበራቸው ታላቅ ብሔራዊ ራእይ እስከ ወዲያኛው የምናከብራቸውን ያህል ወደ መጨረሻው ላይ ጭካኔያቸው ዳር ድንበር አጥቶ ነበር፡፡ በኋላም አጼ ዩሐንስ ጎጃምን በነቂስ አቃጥለው ቀጣሁት ብለዋል፡፡ “እስላም የሆንህ እስከ ሦስት ወር ድረስ ክርስቲያን ሆነህ ካልጠበቅኸኝ ማርያምን በሕይወትህ ቆርጠህ ጠብቀኝ” ስላሉ የወሎ፣ የሸዋ ሙስሊሞች በበኩላቸው ጎራዴ መሳል ጀምረው ነበር ይባላል፡፡ እስካሁን ስላም ጠፍቷል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ምኒልክ “ሁሉም በእምነቱ ይተዳደር፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልጄ ነው ብለው በአዋጅም በግንባርም ለሕዝባቸው በመግለጣቸው “እምዬ ምኒልክ” ሊባሉ ችለዋል፡፡

እውነት ይነገር! ምኒልክ ከመቅደላ አምልጠው ወደ ሸዋ ሲጓዙ በዛብህ አባደክር የተባለ ባላንጣቸው ብዙ ሠራዊት አደራጅቶ ሥልጣን አልለቅቅም ብሎ አፍቀራ (መንዝ) ላይ መሽጎ አስቸግሮ ነበር፡፡ ይሁንና ምኒልክ ጋደሎ እንደ ደረሱ የሱባ፣ የጥሙጋ፣ የአርጤማና የከረዮ ኦሮሞ ባላባቶች በደስታና በእልልታ ተቀብለው ንጉሥነታቸውን አውጀው ታላቅ ግብዣ አደረጉላቸው፡፡ በዚያ ግብዣም ላይ ምኒልክ (ያን ጊዜ ደጃዝማች) በተራቀቀ ኦሮምኛ ንግግር አድርገው ለባላባቶቹ ልዩ ልዩ ሽልማቶች ሰጥተዋቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ አጤ ምኒልክ ብቻ ሳይሆኑ አባታቸው ንጉሥ ኃይለ መለኮት፣ አያታቸው ንጉስ ሳህለ ሥላሴና የእሳቸውን አባት አዝማች ወሰን ሰገድ የተራቀቀ ኦሮምኛ ይናገሩና እድገታቸውና ክፍላቸውም ከኦሮሞዎች ጋር መሆኑ በጹሑፍም በቃልም የተረጋገጠ ነው፡፡

ምኒልክ በአባታቸው ዙፋን ላይ ለመቀመጥ ወደ ሸዋ በመጡ ጊዜ በባላንጣነትና በሥልጣን አላስረክብም መልክ አምጾ የነበረው በዙ አባደክር ኃይል ጠርቀምቀም ያለ ነበር፡፡ ይሁንና ከአባደክር ሠራዊት መካከል በርከት ያሉት በየጊዜው እጃቸውን ለምኒልክ በመስጠት ከሠራዊቱ ጋር ተቀላቅለዋል፡፡ አንደኛውም የበዙ አባደክር ወታደር ጎበና ዳጬ (አባጥጉ) ነበሩ፡፡ እኒህ የወታደርነት ቁመናና ግርማ ሞገስ የነበራቸው የበዙ አባደክር ወታደር ለምኒልክ ከገቡ በኋላ በፍጥነት የቤተ መንግሥቱ ባለሟል ሆኑ፡፡ ታሪካቸው እንደሚለው ደግሞ በዙ አባደክር እጁን ሰጥቶ ምህረት ጠይቆ ሲገባ ከጎበና ጋር ሲገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ፡፡ (በነገራችን ላይ እንደ አስተማሪያችን ልናያቸው እንደ እውነት ምስክር ልንቀበላቸው የምንወድደው ክቡር ኦቦ ቡልቻ ስለምኒልክና ጎበና ግንኙነት የሚናገሩት ታሪክ ከየትኛውም የዘመኑ ፋብሪካ የወጣ መሆኑ አልገባኝም፡፡ የምኒልክና የታላቁ ጎበና ዳጨ ግንኙነት ይህን ሲመስል ከበዛብህ ጋር ሆነው ምኒልክን የወጉ በሙሉ ምሕረት መቀበላቸው እውነት ነው፡፡ በዛብህ ግን መላልሶ ምሕረት እየጠየቀ በመሐሉ እየሸፈተ ጥፋት በማድረሱ፣ ወዲህም ምኒልክን በግብዣ ላይ ለመግደል ሽጉጥ ስለተገኘበት፣ በተጨማሪም ስለ ሥልጣን አያያዝ ከሰዎች ጋር የተላላከው ደብዳቤ ስለተያዘበት መሳፍንቱና መኳንንቱ የሞት ፍርድ ፈረዱበት፡፡ ያን ጊዜ ነው እናት አይዋጁ የተባለች የዘመኑ የቡልጋ አዝማሪ (እንደ ዶክተር ሥርግው አገላለጥ)

“ጋላም አርፈህ ተኛ አውልቅ ጀልዶህን
ያማራውም ጎበዝ ፍታ ኮርቻህን
በእሳት አቃጠሉት የሚያባንንህን
“አንተም ጨካኝ ነበርህ ጨካኝ አዘዘብህ
እንደ ገና ዳቦ እሳት ነደደብህ”
አለች ይባላል፡፡ (እሳት ነደደብህ የተባለው በጥይት ሲደበደብ ከጥይቱ ጋር የሚበተነው አረር ልብሱ ላይ አርፎ እሳት ስለተያያዘ አካሉ በተጨማሪም በእሳት ስለተለበለበ ነው፡፡)

ምኒልክ ለበዛብህ ተደጋጋሚ ምሕረት ሰጥተው በሰላም ይኖር ዘንድ ያሳዩትን ፍቅር በመጣስ እስከ ግድያ ሙከራ መድረሱ የተጠቀሰውን ፍርድ መስጠት ግዴታ ሆኗአል፡፡ አለዚያ አጎታቸው ኃይለ ሚካኤል ሣኅለ ሥላሴ ከባለቤታቸው ከወ/ሮ ባፈና ጋር አድማ አቀነባብሮ በሕይወታቸው ላይ ሲነሳ ምኒልክ የግድያ ትዕዛዝ ወይም በወቅቱ ይደረግ እንደነበረው ንብረት አልቀሙም፡፡ ስለዚህ የምኒልክን ደግነት፣ አዛኝነትና ርኅራሄ የተመለከተው ሰው ሁሉ “እምዬ ምኒልክ” ይላቸው ገባ፡፡

ስለባለቤታቸው ስለ ባፈና ትንሽ ነገር እንጨምርበት፡፡ ወይዘሮ ባፈና ምኒልክን ሲያገቡ ብዙ ልጆች የነበሩአቸውና በዕድሜም ረገድ ምኒልክን በብዙ የሚበልጡአቸው ነበሩ፡፡ (እቴጌ መነን አፄ ኃይለ ሥላሴን ስድስት ዓመት ይበልጡአቸው ነበር – የራስ እምሩን ማስታወሻ ያነብቡአል) ወይዘሮ ባፈና ከምኒልክ ልጅ ለመውለድ ስላልቻሉ አንዲት ልጃቸውን ከሣኅለ ሥላሴ ልጆች ለአንደኛው በመዳር ይህንን ክፍተት ለመሙላት ይሞክራሉ፡፡ ስለዚህ ኃይለ ሚካኤል የተባለውን ያልተሟላ ጤንነት ያለውን የሣኅለ ሥላሴ ልጅ አግባብተው ምኒልክን ለመገልበጥ ሞከሩ፡፡ ምኒልክ ይህን ሁሉ ይከታተሉ ነበር፡፡ በዚህ አድማ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑትን ሁሉ አስሮ መቅጣት የተለመደ በሆነ ነበር፡፡ ዳሩ ግን አጎታቸውንም ሚስታቸውንም አልቀጡአቸውም፡፡ ይልቁንም ባለቤታቸው ወይዘሮ ባፈና ከአፈንጉሳቸው ጋር እንደሚማግጡ ያወቁ ስለነበረ ሁለቱንም ከእልፍኝ አስጠርተው “ሁለታችሁን ልድራችሁ ነው” ማለታቸው በጽሑፍ ጭምር ተረጋግጦአል፡፡ በመጨረሻውም ለባፈና መተዳደሪያ የሚሆን መሬትና ሀብት ሰጥተው ከአፈንጉሥ በዳኔ ጋር አጋቡአቸው፡፡ የምኒልክ አርቆ አሳቢነትና ሰብዓዊነት ይህን መሳይ ነበር፡፡

እንደሚባለው አጼ ምኒልክ አፈንጉሥ በዳኔንና ባፈናን ፊት ለፊት ባነጋገሩበት ጊዜ “ሁለታችሁን ልድራችሁ ነው” ሲሉ ታማኝ አገልጋያቸው የነበሩት አፈንጉሣቸው “እንዴት ሲደረግ ጌታዬ ምኒልክ የገባበትን ጭን እኔ የምደፍረው” ሲሉ “ወስላቴ በምስጢር ስታደርገው ግን መቼ እንዲህ አልህ” በማለት አፊዘው ራሳቸው ደግሰው አጋቡአቸው ይባላል፡፡ አፈንጉሥ በዳኔ ለምኒልክ በሥራ በኩል እጅግ ታማኛቸውና በተሰማሩበት ኋላፊነት እንከን ያልነበራቸው ሰው እንደሆኑ ይወሳል፡፡

ስለ ምኒልክ ሰብዓዊነትና አርቆ ተመልካችነት ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡፡ አንዱም በጦር ሜዳ ያሳዩት የነበረው ምሕረትና ርህራሄ ነው፡፡ እንደሚነገረው በራስ ጎበና የሚመራውን የሸዋ ጦር የጎጃም ጦር መሪ ራስ ደረሶ በየጊዜው ለፍልሚያ ሲፈታተኑት ቆይተው በኋላ እምባቦ ላይ ንጉሦቹ በተገኙበት ትልቅ ጦርነት ተካሂዶ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ቆስለው ተማረኩ፡፡ በዚህን ጊዜ ንጉሥ ምኒልክ የንጉሥ ተክለ ሃይማኖትን ቁስል እየጠረጉ ፋሻ እያሰሩላቸው ጠቦት እያሳረዱ እንዳከሙአቸውና እቴጌ ጣይቱም ታላቅ እንክብካቤ እንዳደረጉላቸው ዜና መዋዕሉ ያወሳል፡፡ ይኸ ብቻ አይደለም፡፡ አጼ ሚኒልክ ከንጉሥ ተክለሃይማኖት ጋር የነበራቸው ቅራኔ በከፋና በወለጋ ግዛቶች ምክንያት ነበር፡፡ በኋላ ግን ከፋን መልሰው እንደ መረቁላቸው ታውቋል፡፡ (ለንጉስ ተክለሃይማኖት የንግሥናን ማዕረግ ንጉሠ ነገሥት ዩሐንስ ሲሰጡአቸው ንጉሠ ጎጃም ወከፋ ብለው ነበር) ንጉስ ተክለሃይማኖት በኋለኛው ዘመን ለወዳጆቻቸው “እባካችሁ ስለምኒልክ አንድም ክፉ ነገር እንዳትነግሩኝ፡፡ የምኒልክን ሞት ሳልሰማ መሞትን እመኛለሁ፡፡ ይሉ ነበር፡፡

በሌሎች መጣጥፎች ላይ እንዳመለከትሁት ምኒልክ ከአድዋ ጦርነት በኋላ የኢጣልያንን ምርኮኞች እያከሙና እያሳከሙ፣ እያስታመሙና እየቀለቡ ባሳዩአቸው እንክብካቤ አለም ዓቀፍ ክብርና ዝና ተቀናጅተዋል፡፡ ይኸ የሰብዓዊነት ማስረጃ በፈንጆቹ በኩል “ከአፍሪካ የማይታኝና የማይታሰብ ሥልጡን መሪ” ተብለው ተደንቀዋል፡፡ (ከተማረኩት የኢጣልያ ሠራዊት መሪዎች መካከል ጄኔራሎች፣ ኮሎኔሎች፣ ማጆሮችና ቲኒንቲዎች በብዛት ይገኙ ነበር፡፡

አጼ ምኒልክ ከሕዝብ ጋር የነበራቸው ትብብርና ፍቅር እጅግ ድንቅ እንደነበር የሚያስረዳ ሌላ ጉዳይ አለ፡፡ እንደሚባለው ንጉሠ ነገሥቱ በየሳምንቱ በበቅሎአቸው አዲስ ዓለም (55 ኪሎ ሜትር ርቀት) እየሄዱ አስቀድሰው ይመለሳሉ፡፡ ይህን ሁሉ ርቀት አብረዋቸው መሣሪያ ይዘው የሚከተሉአቸው በርካታ ሰዎች ደግሞ ነበሩ፡፡ ታዲያ መኪና መጣና ምኒልክም መንዳት በመቻላቸው በአራዳ ጊዮርጊስ የተሰበሰቡ የዘወትር አጃቢዎቻቸውን “እናንተም አርፋችሁ ጠብቁኝ፡፡ በአውቶሞቢል ሄጄ እመለሳለሁ” ብለው ተሰናብተዋቸው መንገዳቸውን ይሄዳሉ፡፡ እነዚያ አዎች ከአራዳ ጊዮርጊስ ሳይለዩ ሲጠብቁ ቆይተው ምኒልክ ሲመለሱ አገኙአቸው፡፡ ሰዎቹ አኩርፈዋቸዋል፡፡ ምኒልክ ቢለማመጡ ቢለማመጡ ሰዎቹ ይቅርታ ማለት አልሆነላቸውም፡፡ ከሕዝቡ ጋር የነበራቸው ግንኙነት የአባትና የልጅ ዝምድና ስለሆነ “እንግዲህ ካሳዘናችሁኝ ሰልሜ ታርፋላችሁ” አሉ ይባላል፡፡ ይኸ በዘመኑ እጅግ ከባድ አነጋገር መሆኑ ነው፡፡ እግረ መንገዳችውን መቀለዳቸው ነው፡፡

ቀደም ሲል እንደ ገለጥሁት ጎበና ለአጼ ምኒልክ የገቡት ከአባደክር ብዙ ሠራዊት ሲሆን ጎበዝና ደፋር ተዋጊ በመሆናቸው ከደጃዝማችም በላይ ራስ ተብለዋል፡፡ ራስ ጎበና ይህን ሹመት ያገኙት በአንድ ቀን ለእሳቸውና ለዳርጌ ሳህለ ሥላሴ በተሰጠው ሹመት ነው፡፡ ከንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ልጅና ከራሳቸው ከምኒልክ አጎት (መስፍን) ቀድመው ራስ መባላቸው ድፍን ኢትዮጵያን ያስደነቀ ሹመትና የምኒልክ ፍትሐዊነት መሆኑ ሲወሳ ኖሯል፡፡ እንዲያውም አጼ ምኒልክ ስለ ጎበና ሲያነሱ “ጎበና ጎበና የእኔ – አንተ የጦር ንጉሥ ያገር ንጉሥ እኔ” ይሉ ነበር ይባላል፡፡ በፍቅር፣ በአክብሮትና በአድናቆት! ታዲያ የራስ ጎበና ልጅ ደጃች ወዳጆ የምኒልክን ልጅ ወይዘሮን ሸዋረጋን አግብተው ልጅ እንደ ወለዱ ይነገራል፡፡ ወጣቶቹ ለምን እንደ ተፋቱና የተወለደውም ልጅ ዕጣ ፋንታ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡

የአረብ ዘመቻውና የኅብረቱ መሠረት

ከዚች አጭር መጣጥፍ ምን ዓይነት ውጤት እንደሚገኝ አላውቅም፡፡ አጀማመሬም ረጅሙን የምኒልክ ታሪክ በአጭሩ ለማስረዳት እችላለሁ ብዬ አይደለም፡፡ በታሪካችን ውስጥ በዚህ ጽሕፈት አማካይነት ምን ያህል ርቀት እንደምንሮጥ ለማየት ብቻ ነው፡፡ እስካሁን የሞከርሁት ምኒልክ የሚለው ስም ከዘመኑ በፊት የተከሰተ፤ ሰውየው ከዘመኑ በፊት የነቃ፣ ሥልጡን፣ በተፈጥሮው ሩኅሩህና ሰብዓዊ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ ዝርዝር ማስረጃውንና ታሪኩን ማንበልበል ቀላል ነው፡፡ እኔም እንዲሁ በአእምሮዬ ውስጥ ከመዘገብኋቸው ዓበይት ነጥቦች መካከል ትዝ የሚሉኝን ብቻ ነው ለዛሬ ያቀረብኩት፡፡ አለዚያ የምኒልክን ሰብዓዊነት በሚመለከት የፈረንጆችንም የኢትዮጵያውያንም ምስክርነት በሰፊው መዘርዘር ቀላል ነው፡፡ እሸት እሸት የሆኑ መረጃዎች አሉ፡፡

አጼ ምኒሊክ ቀደም ሲል ንጉሰ ነገስት ብለው ማሕተም አሳትመው ከአጼ ዮሐንስ ጋር በመጠነኛ ፍጥጫ ላይ ቆይተው ነበር። አጼ ዮሐንስ ምንም እንኩዋን የነጋሲነት ትውልድ ባይኖርባቸውም ጄነራል ናፒዮር በአጼ ቴዎድሮስ ላይ በነበረው ተልእኮ ተባባሪና ደጋፊ ስለሆኑ በርከት ያለ መሳሪያ መሸለማቸው ይታወቃል። እንግሊዞች ለዚህ ተልእኮአቸው ምኒልክም እንዲተባበሩ ቢጠይቋቸው ትብብር ሳያሳዩ ቀርተው ከመሳሪያ እርዳታው ተካፋይ አልሆኑም። ይልቁንም ምኒልክ ቴዎድሮስን እንደአባት ያዩአቸው ስለነበረ ከሴራው አልተሳተፉም። ራስ ጎበና ሁኔታውን ለመሰለል ሞክረው እንደነበረና ከእንግሊዞች ጋር ግን አለመገናኘታቸው ይወሳል። ለማንኛውም ንጉስ ምኒልክ አጼ ዮሃንስን በንጉሠ ነገስትነት በተቀበሉ ጊዜ በተስማሙት መሰረት ተበታትነው የኖሩትን የምእራብ ኢትዮጵያ ግዛቶች ወደ ውህደቱ በማስገባቱ ረገድ በሚያካሄዱት ዘመቻ አንዳች ተቃውሞና ጣልቃ ገብነት እንዳያስገቡ ንጉሠ ነገስቱ ተስማምተውላቸዋል። በሰሜኑ በኩል ውህደቱን በማምጣቱ ረገድ አጼ ቴዎድሮስ ስራውን በአብዛኛው ጨርሰውታል። ስለዚህ በምኒልክ በኩል በራስ ጎበና አዛዥነት በጉድሩና በአዋሽ ወንዝ አካባቢ የነበሩት ቀድሞም በአምሃየስ ፣ በአስፋወሰንና በሳህለስላሴ ዘመን በኅብረቱ ውስጥ ገብተው የነበሩትን ኦሮሞዎች በማስተባበር አንድነቱ የበለጠ ስር እንዲሰዽድ አድርገዋል። በሚቀጥለው ርምጃ የግቤ፣የጎጀብና የዴዴሳ አካባቢ ስፍራዎች በራስ ጎበና ልጅ በደጃዝማች ወዳጆ አማካይነት በውይይትና በድርድር ብቻ የውህደቱ ተሳታፊዎች ሆነዋል።

የጎበና “የአረብ እንቅስቃሴ” የተጀመረው በ1860-1870 ድረስ ባሉት አመታት ነው።በእነዚህም አስር አመታት የሊበንን ነዋሪዎች፣ በሙገር ጅረት አካባቢ ነዋሪዎች ከዚያም ጊቤን ተሻግረው ነዋሪዎቹን እያሳመኑና እያስተባበሩ በፈቃዳቸው ያለ ደም መፍሰስ ከውህደቱ ተሳታፊዎች ለመሆን ተስማምተዋል:: ከነዚህም መካከል የጅማው አባ ጅፋር ይገኛሉ:: የአባ ጅፋር እናት ህብረቱ ለሁሉም ጥቅም እንደሆነ በማወቅ ለልጃቸው በሰላም እንዲገቡ ምክር እንደሰጧቸው ገልጠዋል::

ከዚህ በኋላ ሁለተኛው የራስ ጎበና ውህደቱን የማጠናከር ተግባር የተከናወነውበ 1870 – 1880 ነበር፡፡ በዚህ ዘመቻ ጎበና አባ ጥጉ የሌቃ ነቀምቴና የሌቃ ቄለሞን ባላባቶች (መሪዎች) ኩምሳ ሞረዳና ጆቴ ቱሉን አንዲት ጥይት ሳትተኮስና በሰላም የአንድነቱ አቋም አባላት አድርገዋቸዋል:: የአጼ ምኒልክ የክርስትና ልጅ የሆኑት ደጅ አዝማች ገብረ እግዚአብሄር ሞረዳ (የሌቃ ነቀምቴው) እና የሌቃ ቄለሙ ደጅ አዝማች ጆቴ ቱሉ ከጦር ሚኒስትሩ ከራስ ጎበና፣ ከኢሊባቡር ገዥ ከራስ ተሰማ ናደው ጋር በመመካከር የኢትዮጵያ ዳር ድንበር እስከ ነጭ አባይ መሆኑን በማመን ዛሬ ኡ ጋንዳ እስከሚባለው አገር ድረስ ሄዶ የሚያቀና የጦር አስኳል ልከው ነበር:: ይሁንና አስመራ ላይ አንድ ችግር ተፈጠረ:: ጣሊያኖች ከህንድ ሀገር ያስመጡአቸው ላሞች በሽተኞች ሆነው ተገኙና ከዚያ የጀመረ የከብት በሽታ ወደ ኢትዮጵያ ተዛመተ:: “ ክፉ ቀን ” በተባለው በዚህ በሽታ እስከ ኢሉባቦር፣ ወለጋ፣ ሲዳሞና ከፋ ድረስ አያሌ ሺህ ህዝብና ከብት አለቀ፡፡ ሠራዊቱም የዘመቻ ተግባሩን ማቋረጥ ግዴታው ሆነ:: (የአረብ ዘመቻ ማለት የምእራብ ዘመቻ ማለት ነው፡፡ ቃሉ ግዕዝ ነው) ለነጭ ዓባይ ማስገበሩ ንቅናቄ የተመረጡት የጦር አዛዥ ከራስ ተሰማ ሠራዊት ፊታውራሪ ኀይሌ የሚባሉ ሲሆኑ ስምንት መቶ ወታደሮች ይዘው ዘምተው ነበር፡፡ እርሳቸው እንደ ምንም ብለው ከስፍራው ደርሰው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከሶባት ጅረት በስተግራ ሰቀሉ፡፡ እጅግ የሚጋረፈውን ንዳድ ለጠባቂ ለመተው አላስቻላቸውምና እርሳቸውም ሰው ሳያስቀሩ ወደ ጎሬ ተመለሱ፡፡ እንደሚባለው ከጥቂት ቀናት በኋላ ቢቸነር በሚባለው የጦር አዛዥ ሰራዊቱን አስከትሎ ከስፍራው ሲደርስ የኢትዮጵያን ይዞታ ለማስከበር ሰው ስላላገኘ ሰንደቅ አላማውን አውርዶ የግብጽን ሰንደቅ አላማ ሰቀለ፡፡ (ተክለ ጻድቅን፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይን፣ ሥርግው ሀብለ ሥላሴን፣ ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴን ወዘተ ወዘተ ያነብቡአል)

ዘመቻው በንዳድ፣ በሰውና በከብት እልቂት ብዙ ችግር ስላደረሰ እንደታሰበው እስከ ነጭ አባይ መፍለቂያ ሊሳካ ባይችልም በዚያው አቅጣጫ የሼህ ሆጀሌ ግዛት ቤኒሻንጉልና(ቤላ ሻንጉል) እና ቦረና ወደውህደቱ እንዲገቡ ራስ መኮንን ወልደሚካኤል ጉዲሳና ፊታአውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ የቦረና፣ የጅባትና ጫጫ ገዢ ብዙ ደክመው ተሳክቶላቸዋል። ከነሱም እኩል የወለጋ ባላባቶች ደጃዝማች ጆቴና ደጃዝማች ገብረግዚአብሄር ተሳታፊዎች ሆነዋል። (በነገራችን ላይ ሼህ ሆጀሌ እስከ እድሜያቸው ፍጻሜ ድረስ ጽኑ የሆነ ኢትዮጵያዊ ስሜት እንደነበራቸው ይነገርላቸዋል፡፡)

“በአረቡ ዘመቻ” ውህደቱን በመቃወም ጦርነት የከፈተው የከፋው ንጉስ ጋኪ ሼሮኮ ነው። ጋኪ ሼሮኮ ከአጼ ሰርጸ ድንግል በቀጥታ የትውልድ ሃረግ የሚመዝዝና በማንም ስር ለመሆን አልፈልግም የሚል ነበር።እርሱም ከራስ ወልደጊዮርጊስ ጋር ተዋግቶ ተማረከ። ጦርነቱ አንዳለቀ ግን የከፋ ሴቶች ባሎቻችንን እኛ ባልደገፍነው ጦርነት ውስጥ ማግዶ አስጨረሳቸው በማለት ከስሰው መሰቀል አለበት የሚል አቤቱታ አቀረቡ። አጼ ምኒልክ ግን ጋኪ ሼሮኮን ወደ አንኮበር በመውሰድ በእንክብካቤ አቆዩት ይባላል፡፡

ስለ አርሲ ምን የምንለው አለ? በሳህለ ስላሴና በንጉስ ሃይለመለኮት (የምኒልክ አባት) ጊዜ ጥቂት ኦሮሞዎች መሸፈታቸው ይነገራል። ይሁንና በአዝማች ሰይፉና በራስ ዳርጌ አማካይነት ወዲያው ሰላም መመስረቱ ይወሳል።ራስ ዳርጌ በቅርብ በህዝቡ ዘንድ ባገኙት እውቅና፣ መልካም ስነምግባርና ሃይማኖተኛነት እዚያ በገዢነት ተመድበዋል፡፡ አርሲ ከኢትዮጵያ ክፍላተ ሃገር ጠበብ ያለችና የህዝቡም ብዛት እስካሁን አንድ ሚሊዮን ስላለሆነ የራስ ዳርጌ ወራሾች እነ ራስ ካሳ ሃይሉ ብዙ የሰላሌ ተወላጆችን ወደዚያ በመውሰድ አስፍረዋቸዋል።

እንደ በቆጂ፣ ትንሳኤ ብርሃንና ጢቾ ባሉት ከተማዎችም ብዙሃኑ ነዋሪ ጉራጌ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ከምባታና ኦሮሞ ነው። የምኒልክ ጸሐፌ ትዕዛዞች ባቆዩን መዘክሮች መሰረት አጼ ምኒልክ ወደ አርሲ የሄዱት በጦርነትና ለጦርነት ሳይሆን የሃረሪው መሪ አሚር አብዱላሂ አልገብርም ብሏል በተባለ ጊዜ ወደዚያ ሲዘልቁ ነበር። የጨለንቆ ጦርነት እየተባለ በሚጠቀሰው ዘመቻ ደግሞ ሃሮልድ ማርከስ እንደገለጸው የአሚሩ አመጽ ያለቀው በአስራአምስት ደቂቃ ነው። ይህም በአለም ታሪክ ያልታየና ያልታወቀ ነው። አሚሩ ሁለት ሚስቶቹን ይዞ ሲጠፋ ወዲያው በከተማው ሰላም ነገሰ። ተስፋዬ ገብረአብና ቀደም ብሎም ወዳጄና የድሮ ተማሪዬ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ እንዳሉት ሳይሆን በጨለንቆው ዘመቻ አንድም የኦሮሞ ተወላጅ ተሳትፎ አልነበረውም፡፡ እናት አይዋጁ የምትባል (ስርጕው ሃብተ ስላሴ እንደሚሉት)የቡልጋ የኪነት እመቤት(አዝማሪ) ከገጠመቻቸው ሁለት አናቅጽ ባቀርብላችሁ

ጎበና ጎበና ጎበና ፈረሱን አማን ቢያስነሳው
ዓባይ ላይ ገታው
ጎበና ፈረሱን ፋሌ ላይ ቢያስነሳው
አረብ አገር ገታው
ጎበና ፈረሱን ቼቼ ቢለው
ሱዳን ላይ ገታው
የመዳኒት ጥቂት ይበቃል እያለች
እጅጋየሁ አድያም አንድ ወልዳ መከነች

(እጅጋየሁ አድያም ሰገድ የአጼ ምኒልክ እናት ናቸው።)

የታላቅ ብሄራዊ ቤተሰብ ምስረታ

ጥንታዊት ኢትዮጵያ (“ወያኔዎች አጠራሩን ከፈቀዱልኝ”) ጥቁር አፍሪካን፣ አለዚያም እስከ ነጭ አባይና_ቤናድር (ሞቃዲሾ) የመንና ሐድራሞትን (የማውቀው አካባቢ ነው) ማጠቃለሉ ቀርቶ የአሁኑን ቅርጽ የያዘው በ19 ክፍለ ዘመን ፍጻሜና በሐያኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ ነው። እስካሁንም ይህን አንድነት የፈታው አንዳች ሃይል አልነበረም። የኢትዮጵያ ታሪክ በአጠቃላይና ይልቁንም የምኒልክን ዘመን ታሪክ በመከታተል የታወቁት ዶክተር ሃሮልድ ማርክስ በአንድ ጽሁፋቸው ላይ እንደገለጹት አጼ ሚኒልክ ኢትዮጵያን አንድ በማድረጉ ረገድ “አንድ ታላቅ ብሄራዊ ቤተሰብ” መስርተዋል። የዚህ “ብሄራዊ ቤተሰብ” ስርዓት ደግሞ በግዴታ ወይም በማስፈራት የመጣ አይደለም። በተፈጥሮ መጣ ይሉናል was not the outcome of coercion,it was what came naturally, አዎን እንደተባለውም የሸዋ ነገስታት በአብዛኛው ከምኒልክ ወደኋላ የምንቆጥራቸው ሁሉ ኦሮምኛ ስለሚናገሩ፣ በጋብቻ ከኦሮሞዎች ጋር በመተሳሰራቸውና ለሎችንም በዚህ ረገድ ስላደፋፈሩቸው ወዲህም የሞጋሳ (የጡት ልጅነት) ስርአት ስለተዘረጋ “አንድ ብሄራዊ ቤተሰብ” ሊመሰረት ችሎአል።

በሌሎች መጣጥፎቼ ያነሳኋቸውን ነጥቦች ላለመደጋገም እየሞከርሁ ነኝ። ከመቶ አመት በፊት ተበጣጥሶና በጎሳ መሪዎችና የክፍለ ሃገራት ወቅታዊ ገዢዎች _ዘመነ መሳፍንት _ተበታትኖ የኖረ አገር ወደ ህብረት የመጣበት ዘመንና ያንን ያስፈጸሙ የታሪክ ከዋክብት በአባትነት ሊከበሩ፣ በጀግንነት ሊዘከሩ ሲገባ ዛሬ ላይ የሚጨፈጨፉት ለምንድነው? የታሪክ ክብርና የብሄራዊ አላማ ጉዳይ እንደዘመኑ ገዢዎች ቅኝት ነው። ወዳጆቼና ወገኖቼ ለመሆኑ በህልማችሁም በቅዠታችሁም አገር የሚሸጥ መንግስት ይመጣል —- ይኖራል ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ለመሆኑ ሕዝብን ከህዝብ ለማጫረስ የሚፈልግ መንግስት ይኖራል ብላችሁ አምናችሁ ታውቃላችሁ? ለመሆኑ በሕልምም ሆነ በቅዠት መንግስት ከህዝብ ይቀማል፣ ይሰርቃል፣ ደም ያፈሳል፣ ቀምቶ ራሱን፣ ያበለጽጋል የሚል ወሬ ብትሰሙ ታምናላችሁን በሌላ አለም ማለቴ ነበር። ለመሆኑ ትልቁ ሌባ የመንግስት መሪ መለስ ነው ብሎ ጉግል (Google) ሲገልጥላችሁ ምን ተሰማችሁ? (ሶስት ቢሊዮን ዶላርስ)

በእኔ በኩል የርስበርሱ ጭፍጭፍ መሰናዶ እያስፈራኝ ነው፡፡ “የምኒልክ ሃውልት ይፍረስ” የቴሌቪዥን ጥሪ! “በኦሮሞ ጥያቄ ስም”! የወያኔ የጦር አዋጅ ነው። ከዚያው ከሰፈራቸው “ወያኔ” ከአስራአምስት ከማይበልጡት ሴረኛና ጠንቀኛ ማእከላዊ ገዢዎቻችን የሚገላግለንና ለእኛም ጋር የሚታረቅ ሽምብራ የሚያክል ወያኔ የለም? ኢትዮጵያን የሚያድን! ትግሬውንም የሚያድን?

በነገራችን ላይ የአጼ ምኒልክ ዘመን የኦሮሞ ልጆች ከትልልቁ የመንግስት ሃላፊነት፣የጦር አበጋዝነትና አስተዳደር ስራ ላይ የወሳኝነትን ሃላፊነት የተቀዳጁበት ነበር። ለመሆኑ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ከታሪካዊ የአገር አንድነት ተጋድሎ፣ውጤትና ታሪካዊ በረከት ሊያለያይ ይችላልን? ወያኔኮ ሺህ አመት የመግዛት ዕድል ቢኖረው አንዲት ትምህርት ላለመካፈል ጭንቅላቱን አውቆ የዘጋ የክፋት ሁሉ ምንጭ ነው፡፡ መሄድ ያለበት።

ተክለሃይማኖት አካባቢ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ሊፈርሱ ነው

$
0
0

ተክለሃይማኖት አካባቢ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ብቻ ተለይተው ሊፈርሱ መሆኑን በአካባው ሚገኙ ነጋዴዎች ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ (ፎቶ ከፋይል)

የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ (ፎቶ ከፋይል)


ነጋዴዎቹ እንደሚሉት ከተክለ ሃይማኖት ጀምሮ እስከ ጥቁር አንበሳ የሚገኙ የመኪና ዕቃ መለዋወጫ፣ የጎማ መሸጫ እና ሌሎች የንግድ ሱቆች በአምስት ቀናት ውስጥ እንዲፈርሱ በመንግስት ተወስኗል፡፡ ከንግድ ቤቶቹ በስተጀርባ የሚገኙ የቀበሌ ቤቶች አብረው የማይፈርሱ መሆኑን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ “እኛ ግብር ከፋዮች ሆነን ከሌላው ህብረተሰብ ተለይተን በ5 ቀናት ውስጥ እንድንነሳ መደረጉ ህገወጥ ነው” ብለዋል፡፡

ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ከሚደረግባቸው የአዲስ አበባ አካባቢዎች መካከል በሚጠቀሰው በዚህ ስፍራ በርካታ የንግድ ሱቆች ይገኛሉ፤ በአካባቢው የሚገኙት የንግድ ቤቶች በአማካይ እስከ 4 ሰራተኛ የሚያስተዳድሩ ከመሆኑም በላይ በኮሚሽን ስራ ላይ ለተሰማሩ በርካታ ዜጎች የእለት ጉርስ ምንጭ እንደሆኑ ይታመናል፡፡

ምንጭ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

የዞን 9 ጦማሪዎች እና ጋዜጠኛው ተጨማሪ 28 ቀናት ቀጠሮ ተሰጠባቸው

$
0
0

ካለምንም ክስ ላለፉት 50 ቀናት ፖሊስ የምርመራዬን አልጨርስኩምና ተጨማሪ ቀጠሮ ይሰጠኝ ጥያቄና በፍርድ ቤቱ መፍቀድ የተነሳ እየተጉላሉ የሚገኙት የዞን 9 ጦማሪያን እና ጋዜጠኛው ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ተጨማሪ 28 ቀናት ፖሊስ ጠይቆ ፍርድ ቤቱ መፍቀዱን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ አስታውቀዋል።
zone 9999
በፌደራል ፍርድ ቤት በአራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ የቀረቡት ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ዘላለም ክብረት፣ ኤዶም ካሳዬ፣ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ሲሆኑ ጉዳያቸውን ለመከታተልም በርካታ ሰዎች ፍርድ ቤት መገኘታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል። እንደዘጋቢዎቹ ከሆነ ባልተነገረ ክስ ላለፉት 50 ቀናት በእስር ቤት እየማቀቁ የሚገኙት ታሳሪዎቹ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ መንፈሳቸው ጠንካራ እንደነበር ለማየት ተችሏል።

የታሳሪዎቹ ወላጆችና ሴቶች በፍርድ ቤቱ ሲላቀሱ እንደነበር ያስተዋሉት ዘጋቢዎቻችን ተጨማሪ 28 ቀናት ቀጠሮ መሰጠቱ ብዙዎችን እንዳበሳጨ ጠቁመዋል።

ወጣቶቹና –ቅዳሜ (ጽዮን ግርማ)

$
0
0

አንዷን ቅዳሜ በፍርድ ቤት

በዛሬው ችሎት ፖሊስ የሃያ ስምንት ቀን የምርምራ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደለት

ጽዮን ግርማ

ጽዮን ግርማ tsiongir@gmail.com

ጽዮን ግርማ
tsiongir@gmail.com

 

ለአብዛኛው ወጣት አዲስ አበባ ላይ ”ቅዳሜ” ትርጉም አላት። የሣምንቱን የሥራ ቀናት በየፈርጁ ያሳለፈው ኹሉም ወጣት ”ቅዳሜ”ን ደግሞ እንደየምድቡ ይውልባታል። እንደሰማኹት ከኾነ ለዞን ዘጠኝ አባላትና ጓደኞቻቸውም ቅዳሜ ልዩ ቀን ናት። ለወጣቶቹ አብሮነት የጡመራ መድረኩ ቢያግዛቸውም ከዛ በላይ ግን ጓደኝነታቸው ቤተሰባዊነትን ፈጥሮላቸው አብዛኛውን ቅዳሜ እንደየቅርበታቸው አብረው ያሳልፋሉ።

አብረው እስረኛ ይጠይቃሉ፣ የታመመን ያጽናናሉ፣ በጋራ ምሳ ይቋደሳሉ፣ የተለየ ዝግጅት ካለም አብረው ይሳተፋሉ። ከዚህ የተረፈ ጊዜ ካላቸው ደግሞ ፈጣንንና ነጻ የገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት በሚገኝበት ሆቴል ገብተው ዓለም በምን ኹኔታ ላይ እንዳለች ለመከታተል ይሞክራሉ። አገሪቷ ውስጥ ባለው ከፍተኛ የኢንተርኔት ኮኔክሽን ችግር ምክንያት አብዛኛው ጋዜጠኛና ጥቂት ወጣቶች የእነዚህ ትልልቅ ሆቴሎች ገመድ አልባ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው። በቅዳሜ ወደእነዚህ ሆቴሎች ጎራ ያለ ከጦማሪያኑ ወይም ከጋዜጠኛ አንድ ሰው ሊያገኝ ይችላል። በቃ ሲገናኙ ሰላም ተባብለው መቀላቀል ነው። እናም በአንድ ጉዳይ ጨዋታ ጀመራል። አብዛኛው ጨዋታ በአገር ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሊኾን ይችላል። ኮምፒዩተሮቻቸውን እየነካኩ ስለ አገራቸው ግድ ያላቸውን ይነጋገራሉ፣ ይከራከራሉ አሊያም ይጨቃጨቃሉ። መሄጃው ሰዓት የደረሰበት ደግሞ ተሰናብቶ ይሄዳል። በእነዚህ ሆቴሎች በቀጠሮ የሚገናኝ ሰው የለም። ”የት ነህ? የት ነሽ?” የሚለው የስልክ ጥያቄም ለመገናኘት በቂ ነው።

የተስፋዓለም ቅዳሜ ደግሞ ሌላ ነበረች። ሥራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ አብዛኛውን አርቦች ከእነ ለሊታቸው በሥራ ያጠፋቸዋል። ቅዳሜንም ረፈድ አድርጎ ይነሳል። እናም የመጀመሪያ ሥራው ለሕትመት የበቁ ጋዜጣና መጽሔቶችን አበጥሮ ማንበብ ነው። በማንበብ ብቻም አያቆምም፤ ከዘገባዎቹ አብዛኖቹ የተሠሩት በጓደኞቹ አሊያም በሚያውቃቸው ጋዜጠኞች ስለሚኾን ስልክ ይደውላል። ከዘገባዎች ውስጥ ተስፋዓለምን የሚያስደስቱት በጣም ጥቂቶቹ ብቻ ሊኾኑ ስለሚችሉ የስልክ ልውውጦቹ ”እንዲህ ብታደርግ/ብታደርጊ ኖሮ፣ እንትናን ብታናግረው በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ይሰጥህ ነበር፣ እዚህ ቦታ እኮ እንዲህ ዓይነት መረጃ ነበር፣ ይሄ እኮ ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ሕትመት ላይ ወጥቷል፣ እውነቱን ለመናገር ይሄ ለሕትመት የሚበቃ ዘገባ ነው ብዬ አላምንም” በሚሉ አስተያየቶች የተሞሉ ነበሩ። በዚያው ልክ ደግሞ የሚያስደስተውን ዘገባ ሲያነብ ወይም ፕሮግራም ሲሰማ አዘጋጁን አወቀው አላወቀው ስልክ አፈላልጎ በመደወል ያበረታታል። የተስፋዓለም ግማሽ ቅዳሜ የምታልቀው ይህን ሲያደርግ ነው።

አኹን እነዚህ ወጣቶች ቅዳሜያቸውን በፌደራል ወንጀል ምርመራ መምሪያ (ማዕከላዊ) ፖሊስ ተነጥቀዋል። ሃምሳ ቀናት ታስረው ዘጠኝ ቅዳሜን አጥተዋል። እንዳሻቸው የሚያደርጓትን ቅዳሜ አኹን እነርሱ አያዙባትም። ከጠዋቱ ዐስራ ሁለት ሰዓት ሲል ከእንቅልፋቸው ይቀሰቀሳሉ። ለቁርስ ዳቦ በሻይ ይሰጣቸዋል። (ቤተሰብ የሚያወስድላቸው ምግብ ቁርስ ከበሉ በኋላ ነው የሚደርሳቸው) እናም ተመልሰው ገብተው ይዘጋባቸዋል። አብዛኞቹ ለየብቻ ከሌሎች እስረኛ ጋር የታሰሩ ሲኾን ሁለት፣ ሁለት ተደርገው የታሰሩም አሉ። እናም ከምርመራ የተረፈ ቀናቸውን በዝጉና በጨለምተኛው ክፍል ያሳልፋሉ። በአንዷ ቅዳሜ ደግሞ እንደዛሬው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።

አንዷን ቅዳሜ – በፍርድ ቤት

ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም.፤ ሦስቱ ወጣቶቹ እነርሱ በማያዙባት ቅዳሜ እጆቻቸውን በካቴና ታስረው ፒያሳ በሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ግቢ ውስጥ ሲደርሱ ከሌላው ጊዜ የበለጠ ቁጥር ያለው በዐይን ግምት ሦስት መቶ የሚደርስ ችሎት ተከታታይ በግቢ ውስጥ ተገኝቶ ነበር። የዛሬዎቹ ጠባቂ የፌደራል ፖሊሶች ባለፈው ጊዜ ከነበሩት ሻል ያሉ ስለነበሩ ቤተሰቦች ችሎት ውስጥ ገብተው እንዲታደሙ ባይፈቀድላቸውም ግቢ ውስጥ ከመቆም የከለከላቸው ወይም ያመናጨቃቸው አልነበረም።

ከጠዋቱ አራት ሰዓት ከሃያ ደቂቃ አካባቢ ሲኾን ችሎቱ በሴት ዳኛ በመሰየሙ፤ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎቹ ናትናኤል ፈለቀ እና አጥናፉ ብርሃነ እጃቸውን በሰንሰለት እንደታሰሩ ወደ ግቢው ገቡ። ዛሬ ወጣቶቹ በስስ ፈገግታ ”አይዞአችሁ ደህና ነን” የሚል የተስፋ ምልክት ለቤሰተቦቻቸውና ለጓደኞቻቸው አሳይተዋል። ከእነርሱ ቀጥለው በፖሊስ ታጅበው የገቡት ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስና የሕግ መምሕርና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘለዓለም ክብረት እጆቻቸው በካቴና እንደታሰረ ለቤተሰቦቻቸው ሰላምታን ሰጥተዋል። የእነርሱ ፈገግተኛ መኾን ለቤተሰቦቻቸው፣ ለጓደኞቻቸውና ለወዳጆቻቸው ጥቂትም ቢኾን እፎይታን ሰጥቷል።

ተጠርጣሪዎቹ ችሎት የቀረቡት እንደወትሮው ኹሉ በሁለት መዝገብ ተከፍለው ቢኾንም ፖሊስ ያቀረበው ምክንያትና መከራከሪያ አንድ ዓይነት ነበር። ችሎቱ ከተሰየመ በኋላ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ ቀጠሮ በርካታ ጉዳዮችን ሲመረምር መቆየቱንና አሁንም ያልተጠናቀቀ ምርመራ ስለሚቀረው ተጨማሪ ሃያ ስምንት ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል።

ጠበቃው አቶ አመሐ፤ ”ፖሊስ ከዚህ ቀደም በወሰደው ጊዜ ቀጠሮ ሰነድ ለማስተርጎም፣ የምስክሮችን ቃል ለመቀበል፣ ኢሜሎቻቸውን ለመፈተሽ እንዲሁም ያልተያዙ ግብረአበሮቻቸውን ለመያዝ ብሎ እንደነበርና አሁን ዝም ብሎ በጥቅሉ በርካታ ሥራዎችን ሠርቼያለሁ እንደገና ይጨመርልኝ ማለቱ አግባብ አይደለም” ሲሉ አመልክተው ነበር። ዳኛዋ ፖሊስ የሠራውን ሥራና የሚቀረውን ምርምራ እንዲያስረዳ በማዘዛቸው፣ ”ከሠራናቸው በርካታ የምርመራ ሥራዎች መካከል የተባባሪዎቻቸውን ቤት ፈትሸናል፣ ለተለያዩ ባንኮች የተጠርጣሪዎቹን ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡን ጠይቀን ከተወሰኑት ምላሽ አግኝተናል፣ የተወሱ ምስክሮችን ቃል ተቀብለናል፣ ከትርጉም ሥራውም የተወሰነውን ሠርተናል። ግብረአበሮቻቸው ወደ ክፍለ ሃገርና ወደ ተለያዩ አገራት እየሸሹ መያዝ ስለተቸገርን የፖሊስ ኃይል አሰማርተን እያፈለግናቸው ነው እነርሱንም መያዝ ይቀረናል።” በማለት ተናግሯል።

አቶ አመሐ በበኩላቸው፤ ”ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ ሃምሳ ቀናት ሞልቶታል። እነዚህ የሚላቸውን ነገሮች አጠናቆ ለመጨረስ የነበረው ጊዜ ከበቂ በላይ ነው። አሁንም ቢኾን እነዚህን ምርመራዎች ለማድረግ ደንበኞቼን አስሮ ማስቀመጥ አስፈላጊ አይደለም፤ ስለዚህም ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቻውን ሊያከብርላቸው ይገባል። ይህን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ባይቀበለው እንኳን ከዚህ በኋላ ፖሊስ በሚሰጠው ሃያ ስምንት ቀናት ጊዜ ውስጥ ምርመራውን አጠናቆ እንዲመጣ፤ አጠናቆ ባይመጣ ደግሞ ጥያቄው ተቀባይነት እንደማይኖረው ተደርጎ ይመዝገብልን” በማለት ጠይቀዋል።

ዳኛዋ አቤቱታውን ካደመጡ በኋላ፤ ፖሊስ ከዚህ በኋላ ሲቀርብ ለተጨማሪ የምርመራ ቀነ ቀጠሮ መጠየቂያ አሁን የጠቀሳቸውን ምክንያቶች በምክንያትነት ይዞ እንዳይቀርብ በማሳሰብ የጠየቀውን የሃያ ስምንት ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ፈቅደዋል።

በዛሬው ዕለት ችሎት ከቀረቡት መካከል ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፤ ከፍተኛ የኾነ የጀርባ ሕመም ስላለበት ወንበር እንዲገባለት መጠየቁንና እስካኹን ሊገባለት እንዳልቻለ ጠቅሶ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት አመልክቷል። ዳኛዋ ከምንም ነገር በላይ የጤና ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ በማሳሰብ የጠየቀው ወንበር እንዲገባለት ሲሉ ተናግረዋል። በችሎት የተገኘው መርማሪ ፖሊስ፤ ”በአጋጣሚ የእርሱ መርማሪ እኔ ነኝ የጀርባ ሕመም እንዳለበት ነግሮኛል። ወንበር እንዲገባለት ግን አልጠየቀኝም። አሁንም ቢኾን ይህ በጣም ቀላልና እዛው እኛው ጋር ሊያልቅ የሚችል ነገር ነው። ችግር የለም እናስገባለታለን” ሲል ቃሉን ሰጥቷል።

እስረኞቹ ከችሎት ሲወጡ እንደ አገባባቸው በፈገግታ ሰላምታ እየሰጡ ሲኾን፤ ችሎቱን ለመከታተል መጥቶ ፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ የቆመው ሰውም እጁን በማውለብለብ ተሰናብቷቸዋል።

የሸራተን ሆቴል ሰራተኞችና የማኔጅመንቱ ፍጥጫ ተባብሷል –አዲስ አድማስ ጋዜጣ

$
0
0

ናፍቆት ዮሴፍ – ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ

ኢሰማኮ ማኔጅመንቱ ለድርድር እንዲቀርብ አስጠነቀቀ

ማኔጅመንቱ ህግን በሚጥስ ተግባር ላይ አልደራደርም ብሏል

“የሥራ ማቆም አድማ የመጨረሻ አማራጭ ነው” የሰራተኛ ማህበሩ

የሸራተን አዲስ ሆቴል ሰራተኞችና ማኔጅመንት ፍጥጫ ተባብሶ እንደቀጠለ ነው፡፡ ባለፈው ሀሙስ ከሰዓት በኋላ በፊንፊኔ የባህል ምግብ አዳራሽ በተጠራ አስቸኳይ ስብሰባ፤ ሰራተኞቹ ለቱሪዝም ሆቴሎችና ጠቅላላ አገልግሎት ሰራተኛና ማህበራት ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን የስራ ኃላፊዎች በሸራተን ሆቴል ማኔጅመንት ደረሰብን ያሉትን በደል ያስረዱ ሲሆን “በገዛ አገራችን በ10 ፈረንጆች ቅኝ እየተገዛን ነው” ሲሉ ምሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን በበኩሉ፤ የሸራተን ማኔጅመንት በአፋጣኝ ወደ ድርድር እንዲመጣ የአምስት ቀን ጊዜ በመስጠት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ፅፏል፡፡ ከተመሠረተ አራት አመቱን ያስቆጠረው የሸራተን አዲስ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበርና ሰራተኞቹ ለኢንዱስትሪ ፌደሬሽን በጋራ ባሰሙት አቤቱታ፤ ለበርካታ ጊዜያት በደላቸውን ለሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይና ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ቢያሳውቁም በደሉ እንደቀጠለ መሆኑን ገልፀው፤ ከዚህ በኋላ ያለው ብቸኛ አማራጭ በደላችንን በሰላማዊ ሰልፍ በመግለፅ የኢትዮጵያ ህዝብና ዓለም እንዲሰማው ማድረግ ብቻ ነው ብለዋል፡፡
Sheraton Addis, Addis Ababa, Ethiopia
“ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰላማዊ ሰልፍ እያስፈቀዱ በአደባባይ መንግስት ከስልጣን እንዲለቅ በሚጠይቁበት ወቅት እኛ በአገራችን እንደ ሁለተኛ ዜጋ የምንታይበትን አሰራር ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የምንከለከልበት ሁኔታ አይኖርም” ያሉት ሰራተኞቹ፤ እስከዛሬ የሞከሯቸው አማራጮች አለመሳካታቸውን ጠቁመዋል፡፡ “የሆቴሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ በዘርና በቀለም ልዩነት በማድረግ፣ በጥቅማ ጥቅሞቻችን ላይ እያደረሱት ያለው በደል እስካሁን መፍትሄ አላገኘም” ያሉት የሸራተን መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ዳዊት ሳሙኤል፤ “በምንም መልኩ የስራ ማቆም አድማ አናደርግም፤ ስራችንን እየሰራን ግን መብታችንን ለማስከበር ትግላችንን እንቀጥላለን፤ የስራ ማቆም አድማ የመጨረሻው አማራጭ ነው” ብለዋል፡፡ “ትልቋን ኢትዮጵያ በትንሹ ሸራተን ግፍ ውስጥ እንድናይ እየተገደድን ነው” ያሉት ሌላው የማህበሩ አባል፤ ፈረንጆቹ ቀስ በቀስ ቪዛ እየሰጡ ከአገራችን ሊያባርሩን ስለሆነ መፍትሄ እንሻለን ብለዋል፡፡

ማኔጅመንቱ ወደ ድርድር ለመምጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑና የህብረት ስምምነቱ ጊዜ አብቅቷል ብሎ የሆቴሉ ሰሌዳ ላይ በመለጠፉ፣ የኢንዱስትሪ ፌደሬሽን ለኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህራት ኮንፌደሬሽን በፃፈው ደብዳቤ፤ ኢሰማኮ ጣልቃ ገብቶ ማኔጅመንቱ እንዲደራደርና የህብረት ስምምነቱን እንዲፈርም ካልተደረገ ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስድ ያሳወቀ ሲሆን ኢሰማኮም የኢንዱስትሪ ፌደሬሽኑ ትብብር መፈለጉን ለማኔጅመንቱ ጠቅሶ በፃፈው ደብዳቤ፤ የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበሩን አቤቱታና የኢንዱስትሪ ፌደሬሽኑን የአግዙኝ ጥያቄ ተቀብሎ መመርመሩን ገልጿል፡፡ ድርድርን በተመለከተ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 130 ንዑስ አንቀጽ አንድ እና ሁለት መሰረት “የህብረት ድርድር” ለማድረግ የፈለገው ወገን ሌላውን ወገን በጽሑፍ ሊጠይቅ እንደሚችል የጠቆመው ኢሰማኮ ለህብረት ድርድር የሚሆነውን ረቂቅ አዘጋጅቶ እንደሚሰጥና ተጠያቂውም ወገን ጥያቄው በደረሰው በ10 ቀናት ውስጥ ለህብረት ድርድር እንደሚቀርብ ኢሰማኮ በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ይሁን እንጂ ማኔጅመንቱ የማህበሩን ጥሪ ተቀብሎ በመደራደር ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ የህብረት ስምምነቱ ጊዜውን ጨርሷል በሚል ሰሌዳ ላይ መለጠፉ አለመግባባቱን እያባባሰውና ሰራተኛው ወዳልተፈለገ እንቅስቃሴ እንዲገባ እያደረገው መሆኑን ኢሰማኮ በደብዳቤው ጠቁሞ ማኔጅመንቱን ተችቷል፡፡

ሰፊ ጊዜ ተሰጥቶት እንኳን የማህበሩንና የፌደሬሽኑን የሰለጠነ የድርድር ጥያቄ ወደጐን የተወው ማኔጅመንቱ፤ ሰራተኛውን ወዳልተፈለገ ጫፍ እየገፋና የሰራተኛውን መብትና ጥቅሙን እየሸራረፈ መሆኑን የጠቆመው ኢሰማኮ፤ የተወሰደው ጊዜ ከበቂ በላይ በመሆኑ የሆቴሉ ማኔጅመንት ይህ ደብዳቤ በደረሰው በአምስት ቀናት ውስጥ ለድርድር እንዲቀርብ ያሳሰበ ሲሆን ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ህግ በሚፈቅደው መሰረት ማኔጅመንቱን ለድርድር እንዲቀርብ እንደሚያስገድድ አስታውቋል፡፡ የኢንዱስትሪ ፌደሬሽኑ የህግ ክፍል ኃላፊ አቶ ሰኢድ ይመር በበኩላቸው፤ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግና ለመሰል እንቅስቃሴዎች የሚቀሩ የህግ ጉዳዮች በመኖራቸው ትንሽ ጊዜ እንዲታገሱ ለሰራተኞቹ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፤ ኢሰማኮ ለማኔጅመንቱ በሰጠው የአምስት ቀን ጊዜ ውስጥ ለድርድር ካልቀረበ ግን ሁሉንም የማድረግ መብት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ የኢንዱስትሪ ፌደሬሽኑ ሊቀመንበር አቶ ቶሌራ ደሬሳም፤ ሰራተኞቹ ያላቸውን ትብብርና አንድነት አድንቀው፤ ሰራተኛው ስራውን በአግባቡ እየሰራና ምርታማነቱን እያሳየ የመብት ጥያቄውን ማሰማት እንደሚችል መክረዋል፡፡

የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ዳዊት በበኩላቸው፤ ሰራተኛው ለማህበሩ ሙሉ ስልጣን ከሰጠው፣ ከአሁን በኋላ ማኔጅመንቱ ለሚፈፅመው በደል ከመንግስት ፈቃድ ጠይቆ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚወጡ ቃል ገብቷል፡፡ ሰራተኛውም ሙሉ በሙሉ ለማህበሩ ስልጣን መስጠቱን በአንድ ድምጽ አጽድቆ ቃለ ጉባኤ ተፈርሟል፡፡

የሸራተን ማኔጅመንት በበኩሉ፤ ኢንዱስትሪ ፌደሬሽኑ ለኢሰማኮ የፃፈው ደብዳቤ ማኔጅመንቱን ሳይጠይቅ የአንድን ወገን አቤቱታ ብቻ ማስተናገዱን ገልፆ ፌዴሬሽኑን ወቅሷል፡፡ ማኔጅመንቱ ስራውን የሚያከናውነው ህግን መሰረት አድርጐ እንደሆነ ገለፆ፣ የህብረት ስምምነቱ ስራ ላይ የዋለው እ.ኤ.አ ከማርች 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመሆኑ የአገልግሎት ዘመኑ ማርች 1 ቀን 2014 ዓ.ም መጠናቀቁን እና የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀፅ 3 መሰረት ከጁን 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ደሞዝና ጥቅማ ጥቅምን በተመለከተ በህብረት ስምምነቱ የተሰጡ መብቶች እንዲቋረጡ ማድረጉን ለኢንዱስትሪ ፌደሬሽኑ በፃፈው ደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ የሸራተን ማኔጅመንት አክሎም፤ ለሰራተኛ እቆረቆራለሁ የሚል ወገን መጀመሪያ ድርድሩ ለምን እንደተቋረጠ ካጣራ በኋላ ችግር ፈጣሪውን ወቅሶ ወደ ትክክለኛ መንገድ እንዲመጣ ማድረግና ድርድሩም በሰላም ተጠናቅቆ የኢንዱስትሪ ሰላም በድርጅቱ እንዲሰፍን መትጋት ይጠበቅበታል ብሏል፡፡ ድርጅቱ የሰራተኞችን መብትና ጥቅም ከህግ ውጭ እንደማይነፍግ ጠቁሞ ህግን በሚጥስ ተግባር ላይ ግን እንደማይደራደር አስታውቋል፡፡


በእስር ላይ የሚገኙት የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአቶ አንዷለም አራጌ መልእክት (ሊያነቡት የሚገባ)

$
0
0

Andualem & Eskinder with family

ኤልያስ ገብሩ (ጋዜጠኛ)

“‹‹የታሰራችሁ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች የእኔ ጀግኖች ናችሁ። አከብራችኋላሁ።›› ብለህ ንገርልኝ አለኝ – ደጋግሞ።…”
ከትናንት በስትያ ሰኔ 03 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ከቅርብ ጓደኛዬ እና የሙያ ባልደረባዬ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ጋር ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት [እስር ቤትም ነው] አምርተን ነበር- ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆኑትን አቶ አንዷለም አራጌን ለመጠየቅ። የተለመደውን የፖሊስ ፍተሻ አልፈን ወደ ውስጥ ስንዘልቅ የሰማያዊ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፈ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ፣ አቶ ሳሙኤል የተባሉ አባልና የ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እስክንድርን ሊጠይቁ ቀድመውን ደርሰው ነበር።

…እስክንድርን እና አንዷለምን አስጠራናቸው፡፡ ሁለቱም ሲያዩን ደስ አላቸው፡፡ በተለይ በተለይ የእስክንድር ፈገግታ በጣም ደማቅ ነበር። ተከፋፍለን ከሁለቱም ጋር ሃሳቦችን መለዋወጥ ጀመርን፡፡ እስክንድር በዓለም የጋዜጠኞች እና የዜና አታሚዎች ማኅበር የዓመቱ የወርቅ ብዕር የ “pen Golden of freedom 2014″ ተሸላሚ በመሆኑ

‹‹እንኳን ደስ ያለህ››

አልኩት።

‹‹አመሰግናለሁ። ትናንት አንድ ልጅ ሊጠይቀኝ መጥቶ ነግሮኛል››

ካለን በኋላ ደግመን ስለሽልማቱ በጋራ ሃሳብ መለዋወጥ ቀጠልን። እስክንድር ሽልማቱ አዲስ መሆኑን አላወቀም ነበር።

በመሆኑም ስለሽልማቱ ሁኔታ፣ ማን እንደሸለመው፣ ሽልማቱ የት እንደተደረገ፣ ሽልማቱን ማን እንደተቀበለለት [ሽልማቱን የተቀበለው በኢትዮጵያ በሽብርተኝነት ክስ ወንጀለኛ ተብሎ ከባልደረባው ፎቶ አንሺ ጋር 11 ዓመታት ከተፈረደበት በኋላ በይቅርታ የተለቀቀው ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ ነበር]፣ የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ምን እንደሚመሰል፣ በሽልማቱ እነማን እንደተገኙ …ያወቅነውን ሁሉ ነገርነው።

‹‹ይህንን አላዋኩኝም፣ ሰርካለም (ባለቤቱ) ለምን በቦታው አልተገኘችም?››

በማለት ጠየቀንና በድጋሚ ደስ ብሎት ጣቶቹን በሽቦ ውስጥ አሾልኮ ጨበጠን። ወዲያው ይህቺን መልዕክት ተናገረ፡-

‹‹ይህ ሽልማት የእኔ ብቻ አይደለም። የእናንተም ነው። የኢትዮጵያዊ ጋዜጠኞች ነው። ሁላችንንም ይመለከተናል፡፡ ለሁላንችም ይገባናል። ይሄንን ሽልማት የምመለከተው ሐሳብን በነጻነት ከመግለጽ የመብት ጥሰት አኳያ ብቻ አይደለም። ለሌሎች የዜጎች መብቶች ሲሉ ለታገሉ እና እየታገሉ ላሉ ፖለቲከኞች፣ የሕሊና እስረኞችም ጭምር ነው። ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከሌሎች ከተነፈጉ መብቶች ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡ ሁሉንም መብቶች እናገኛቸዋለን፣ ወይም እናጣቸዋለን። ለዚህ ደግሞ ጸንተን እንታገል፣ ትግላችን ግን ሰላማዊ ብቻ መሆን አለበት። …››

እስክንድር ደስ ብሎት ሃሳቡን መናገሩን ቀጥሏል፡፡ እኔ ለተወሰኑ ቀናት በማዕከላዊ መታሰሬን ሰምቶ ስለነበረም

‹‹ማዕከላዊ እያለህ የታሰሩትን ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች ለማግኘት ችለህ ነበር?››

ብሎ ጠየቀኝ፡፡ እነሱን በአካል ማግኘት አለመቻሌን ነገር ግን ከእነሱ ጋር ታሥረው የነበሩ ሌሎች ተጠርጣሪ ዜጎችን አግኝቼ በእስር ስላሉበት ሁኔታ መጠየቄን ነገርኩት።

የታሰሩት ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖችን ቤተሰብ ማግኘት እችል እንደሆነና ከቻልኩም በእነሱ በኩል መልዕክቱ ይደርስለት ዘንድ በድጋሚ ጥያቄያዊ ሃሳቡን አቀረበልኝ፡፡ የተወሰኑ የእስረኛ ቤተሰቦችን ማግኘት እንደምችል አስረዳሁት።

‹‹የታሰራችሁ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች የእኔ ጀግኖች ናችሁ። አከብራችኋላሁ።››

ብለህ ንገርልኝ አለኝ – ደጋግሞ።… በዕለቱ ከሰዓታት በፊት ሰናይት ታከለ የምትባል ወዳጄም እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ እንደምሄድ በነገርኳት ጊዜ ‹‹እንደማከብረው እና እንደማደንቀው ንገርልኝ›› ያለችኝን መልዕክት ለእስክንድር አደረስኩላት።እሱ ግን ሳቅ እያለ

‹‹ተሳስተሻል! …ተሳስተሻል! …ተሳስተሻል››

ብለህ ንገራት አለኝ።

‹‹ለምን?››

አልኩት፡፡

‹‹ገና ምን ሰርቼ?››

በማለት በዚያ ትሁት አንደበቱ መለሰልኝ፡፡ በእውነት መልሱ አስደመመን። ዋይ እስክንድር፣ ፍጹም የተለየ ታላቅ ሰው!!! እስክንድርን እናናግረው የነበርን ጠያቂዎች ወደ አንዷለም አራጌ ዞርን፡፡ አንዷለም ጋር የነበሩት ደግሞ ወደ እስክንድር።

አንዷለም የስፖርት ቲ-ሸርት ከቁምጣ ጋር ለብሷል። ጥቁር መነጽር አድርጓል። ረጋ ብሎ ፈገግ በማለት

‹‹ምን አዲስ ነገር አለ?››

በማለት ጨዋታ ጀመረ። አንዷለም የእስክንድርን ሽልማት ሰምቶ ኖሮ፣

‹‹አሁን ከምሳ በኋላ ጣፋጭ የለውዝ ሻይ እሱን እና ጓደኞቻችንን በመጋበዝ ‹እንኳን ደስ ያልህ!› በማለት ሰርፕራይዝ አደርገዋለሁ። ምግብ ማብሰል እያለማመድኩት ነው። ብዙ ጊዜ እኔ ነኝ ሰርቼ የማበላው። በልጅነቱ በበርገር ያደገ ልጅ አሁን ሽንኩርት እና ቲማቲም መክተፍ ችሏል …››

በማለት በቀልድ ነገረን።

‹እነማን ከእናንተ ጋር አሉ? በአንድ ክፍል ውስጥስ ስንት ናችሁ? ጊዜያችሁንስ እንዴት ነው የምትጠቀሙበት?››

የሚል ጥያቄ አቀረብንለት።

‹‹ለረዥም ጊዜ፣ በጣም አስቸጋሪ ክፍል ውስጥ፣ መሬት ላይ ስንከባለል ነበር በእስር ያሳለፍሉት፡፡ አሁን አቶ ስዬ አብርሃ ታስሮ በነበረበት ጥሩ በሚባል ክፍል ውስጥ ለአምስት ታስረን እንገኛለን፡፡ አቶ መላኩ ተፈራ፣ አቶ መላኩ ፈንታ ና አንድ ባለሃብት አብረውን ናቸው፡፡ አሁን አልጋ ላይ መተኛት ጀምሬአለሁ፡፡ ይሄ ለእኔ እንደ አዲስ ሕይወት ነው። አሁን ደስተኛ ነኝ። …ጊዜያችንን በጥሩ ሁኔታ ከፋፍለን እየተጠቀምንበት ነው፡፡ እናነባለን፣ እንወያያለን፣ የምንፈልጋቸውን መጽሐፍት ግን በምንፈልገው ጊዜ አናገኝም፣ በዚህ በኩል መጠነኛ ችግር አለ፡፡ በተረፈ ደህና ነኝ። እኔ ተስፈኛ ነኝ። እናንተም በተሰማራችሁበት ዘርፍ የምትችሉትን ሁሉ ለሀገራችሁ ለውጥ መታገል አለባችሁ…››

ከሁለቱም ጋር የነበረንን የ30 ደቂቃ ቆይታ ሳንጠግብ

‹‹በቃችሁ››

የሚለው የፖሊስ ድምጽ ተሰማ።

‹‹እናመሰግናለን፣ በቃ ሂዱ››

ሲል አንዷለም በእርጋታ ተናግሮ በሽቦ ስር አሾልኮ እጆቻችንን ጨበጠን። እስክንድር ደግሞ

‹‹‹ሲመቻችሁ ብቻ መጥታችሁ ጠይቁን፣ ሥራ እንዳይበደል!። ሥራችሁን ሥሩ››

በማለት ለእኛም ያለውን አሳቢነት ከምክሩ ጋር ደጋግሞ ገለጸልን – ሁሉንም ሰላም በሉልኝ በማለት። እንግዲህ እስክንድርን የምትሉ ሁሉ ሰላምታውን በእኔ በኩል አድርሻለሁ።

Health: ብስጭት ይታከማል ወይ?

$
0
0

‹‹ከሁለት ዓመት በፊት በደረሰብኝ ከባድ የመኪና አደጋ ምክንያት በቀኝ እጄና እግሬ ላይ የእንቅስቃሴ ችግር ቢፈጠርብኝም ከቀን ወደ ቀን ግን የእጆቼ መስለል እና መቅጠን የህሊናዬን እረፍት የነሳኝ ስለሆነ አፋጣኝ ምላሻችሁን በመስጠት ከሀሳብ የምፀዳበትን ምክር እንድትለግሱኝ እጠይቃለሁ፡፡

በ2001 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ ዲፓርትመንት የአራተኛ ዓመት ተመራቂ በነበርኩበት ሰዓት የመመረቂያ ጊዜዬን በጉጉት በመጠበቅ ላይ ሳለሁ በድንገተኛ የመኪና አደጋ የከፍተኛ ጉዳት ሰለባ ሆኛለሁ፡፡ በሰዓቱም እጅግ በማዘንና በመከፋት ይህችን ዓለም በክፉኛ ምሬት ያዘንኩባት ወቅት ብትሆንም የነበረኝን የትምህርት ጊዜ ግን በማጠናቀቄ ለፈጣሪዬ ምስጋናን ከማቅረብ አልቦዘነኩም፡፡ ሙያውን በተመለከተ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ጋር በተያያዘም የስነ ልቦና ምክር እንድትሰጡኝ ከአደራ ጭምር አሳስባለሁ››

ኤኬ

angry face ማንም ሰው በህይወት ዘመኑ ሲኖር የዛሬን እንጂ የነገን ስለማያውቅ በደረሰብህ ጉዳት ያሳለፍከውን የህይወት ውጣ ውረድ እንደ ችግር ብታየው ነገ ግን ከፊትህ ያለውን በመልካም እና በጥሩ በማሰብ ራስህን ማፅናናት ግድ ይልሃል፡፡ በዚህም ምክንያት ለአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን በሆስፒታሉ መኝታ ክፍል የህክምና አገልግሎት በማግኘት ያሳለፍክ ቢሆንም በተመላላሽ ህክምና ደግሞ ለስድስት ወራት ያህል እንደቆየህ የላክልን መረጃ ያሳያል፡፡ ነገር ግን በተደረገልህ ቀዶ ጥገና ምክንያት በጤንነትህ ላይ የፈለከውን ያህል ለውጥ ባለማየትህ ሙሉ በሙሉ ደስተኛ አለመሆንህን ያሳያል፡፡ ምናልባትም በቀዶ ጥገና ጊዜ በተፈጠረ የኦፕሬሽን ስህተት ላልተለፈገ ጉዳት ተዳርጌ ይሆን ወይ? በማለት ኦፕሬሽን ካደረገ የህክምና ባለሙያ ጋርም በነበረህ የመጨረሻ ቀጠሮ ላይ ውይይት እንዳደረግህ ብትገልፅልንም ከሐኪምህ የተሰጠህን መልስ ግን በውሉ አላሳወቅከንም፡፡ ከቅርብ ወራት ወዲህ ደግሞ የሽንትና የሰገራ መውጫ ሰዓት የሚሰማኝን ስሜት ማወቅ እየተሳነኝ አይነ ምድሬንም ሆነ ሽንቴን በመፀዳጃ ቤት መጠቀም እስከማልችልበት ድረስ ደርሻለሁ ብለኸኛል፡፡ ምናልባትም ይህ ሁኔታ ለህሊና ረፍት ማጣትህ ትልቁን ድርሻ ይይዛል ብለን እንገምታለን፡፡ ኤኬ የመኪና አደጋ ከደረሰብህ በኋላ ለምን ያህል ጊዜ የህክምና እርዳታውን ሳታገኘ ቆይተሀል የሚለው ጥያቄ በእኛ በኩል ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ ምክንያቱም አደጋ እንደደረሰብህ የሚፈልገውን ምርመራ ሁሉ ተደርጎ የቀዶ ጥገና ስራ እንኳን የሚያስፈልግ ከሆነ በወቅቱ ማድረግ በቀጣይ የሚኖረውን ለውጥ የተሻለ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ያለበለዚያ የተፈለገውን ያህል ውጤት ማግኘት አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡ በአከርካሪ አጥንት (spinal cord) ወይም በአንጎላችን (Brain) አካባቢ የሚፈጠረው አደጋ ከነርቭ ጋር የተያያዘ ስለሚሆን የሰውነት ክፍላችንን ማዘዝና መቆጣጠር ይችላል፡፡

ይሄ የሰውነት ክፍልም የቀዶ ጥገና የሚደረግበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚጠይቅ መሆኑ ከኦፕሬሽን በፊት ሰፋ ያለ ዝግጅት ይደረጋል፡፡ በቀኝ በኩል የእጅህና የእግርህ ክፍል በፈለከው መልኩ አለመታዘዝ ከነርቭ ጋር የተያያዘ ጉዳትን የሚያመላክት ቢሆንም ሐኪምህ በሚሰጥህ ምክር ግን ህክምናህን በአግባቡ ከተከታተልክ የተሻለ ለውጥ ማምጣት ትችላለህ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜም የመስለልና የመቅጠን አይነት ምልክት በተጎዱት የሰውነት ክፍሎቼ ላይ ታይቷል ብለህ የምታምን ከሆነ ግን ዛሬ ነገ ሳትል ወደ ሆስፒታሉ በመሄድ እንደገና መታየቱ ወደ ፊት ሊመጣ የሚችለውን የባሰ ችግር መቀነስ ያስችላል፡፡ ከእንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የሰውነት ማፍታቻ ሊሆን የሚችል ግብአቶችንም በባለሙያ ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ የምንጠቀም ከሆነ ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩትን የአላስፈላጊ የሰውነት መላሸቅን መቋቋም እንችላለን፡፡

ፊዚዮቴራፒ (physiotherapy) ህክምናም ከእንደዚህ አይነት አደጋም ሆነ ህመም ጋር ሊከሰት የሚችል የጤና ችግርን ማዳን ወይንም የጉዳት ደረጃውን መቀነስ ያስችላል፡፡ የህክምና ክትትሉ እንዳለ ሆኖ ግን በተጨማሪነት ለአራት ዓመታት የለፋህበትን የትምህርት ውጤት በስራ ተግብሬ ሀገሬንም ሆነ ራሴን አሁን ላለሁበት የጤንነት ሁኔታም ልጠቅም እችላለሁ ወይ የሚለው የሁለተኛ ጥያቄ ነው፡፡

ለዚህም የአካል ጉዳተኝነት በብዙ አይነቶች ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ እንደ ምሳሌ የእጅ፣ የእግር፣ የማየትና የመስማት መሳን፣ የአዕምሮ ዘገምተኝነት በከፊሉ ሊነሱና ሊጠቀሱ የሚችሉ ሲሆን ከዚህም ባሻገር በህብረተሰቡ ዘንድ ተከስተው የምናያቸው ናቸው፡፡ በአካል ጉዳተኘነት ብቻ ግን ሰው መስራት እየፈለገ ጉዳቱ ምክንያቱ ሆኖብሃል በማለት እራሱን ከስራ የሚያገል ከሆነ ይህ ሰው ከስነልቦና ችግር ጋር በተያያዘ የባለሙያ ምክር አስፈላጊው ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሲባል ደግሞ የአካል ጉዳተኛ የፈለገውን ስራ ሁሉ መስራት ይችላል ማለት እንዳልሆነ ተገንዝበን ማለፍ አለብን፡፡ የስራህ አይነት ሊሆን የሚችለው በተማርከው የትምህርት ዘርፍ እንደሆነ እንገምታለን፡፡ ስለዚህ የጠቀስክልን የህመም አይነት እና ጉዳት አንተ ካሰብከው አላማና ግብ የሚያስተጓጉል ነገር ስለማይኖው ለስራ አመቺ የሆነ ቦታን መምረጥና ማመቻቸት ጠቀሜታ እንዳለው መንገር እንፈልጋለን፡፡ የሰው ድጋፍ ከመሻት እና የሰውን እጅ ከማየት በራስ ሰርቶ ማደር ጠቀሜታው የጎላ ቢሆንም በአቅምህና በደረጃህ ያሰብካቸውን አላማዎች ሁሉ ለማሳካት ግን ጥረትህ ወሳኘ መሆን አለበት፡፡ የደም ግፊት በሽታ፣ የስኳር በሽታ እና የነርቭ በሽታ ከመኪና አደጋ ያልተናነሰ የአካል ጉዳተኝነት ሊያመጡ ቢችሉም የበሽታውን መንስኤ ግን በወቅቱ ማወቅ ከተቻለና አስፈላጊውን ክትትል ከተደረገ ጉዳቱን መከላከልም ሆነ መቆጣጠር የሚቻልበት መንገድ ይኖራል፡፡ አደጋ በራሱ ህመም ቢሆንም ዘወትር ስለደረሰው ጉዳት የምናስብ ከሆነ ግን የህሊና እረፍትን በማጣት ካሰብነው ግብ መድረስ የማንችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ አንድ ሰው የአካል ጉዳተኝነትን በተፈጠሮ ወይም ከውልደቱ በኋላ ባላሰበው ጊዜና ወቅት ሊያገኘው ቢችልም መንፈሰ ጠንካራ በመሆን ግን ሊከሰትበት የሚችለውን ችግር ሁሉ በትዕግስት ማሳለፍ ይችላል፡፡ በአገራችን በመኪና አደጋ የሚከሰተው ቀላልም ሆነ ከባድ የአካል ጉዳት በበሽታ ምክንያት ከሚመጣው የአካል ጉዳተኝነት ይበልጡን ቦታ ይይዛል፡፡ ስለዚህ መስራት ወደ ምትፈልግበት ቦታ እንደልብ በትራንስፖርት ለመንቀሳቀስ የሚያስቸግርህ ባለመሆኑ ለስራህ እንቅፋት ሊሆን የሚችል ነገር ይኖራል ብለን አናስብም፡፡ ከነርቭ ጋር በተያያዘ የሚመጡ የሰውነት ጉዳቶች በወቅቱ የህክምና አገልግሎት ቢደረግባቸውም የለውጥ ሂደታቸውን የሚያሳዩት ግን ቀስ በቀስ ነው የሚሆነው፡፡ እንደሌላው ህመም መድሃኒት ስለተወሰደ ብቻ ብዙውን ጊዜ አፋጣኝ ምላሽ አይታይባቸውም፡፡ በአንጎላችን እና በአከርካሪ አጥንት አካባቢ የሚከሰቱትን የጤና ችግር መለየት የምንችለውም በኤም.አር.አይ (MRI) ወይም ሲቲስካን (CT Scan) በሚባል መሳሪያዎች ይሆናል፡፡ በሀገራችንም እነዚህ ሁለት መሳሪያዎች በግል የህክምና ዘርፍ በሰፊው ይገኛሉ፡፡ በአንጎላችን አካባቢ የሚከሰተው የውስጥ የአንጎል ክፍል እብጠት (Brain Tumoir) ሲሆን በአከርካሪ አጥንት ደግሞ ዲስክ መንሸራተት ነው፡፡ እነዚህ ደግሞ ዋነኛው የነርቭ ስራ መቋረጥን ያስከትላል፡፡

በተለያየ ጊዜ ከሰውነት ጉዳት ጋርም ሆነ ከአየር ንብረት መለዋወጥ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የነርቭ በሽታዎች ወቅታዊ የሚሆኑበት አጋጣሚ ስለሚኖር አስፈላጊው ሁሉ ጥንቃቄ መደረጉ ተገቢ ነው እንላለን፡፡

ውድ የመጀመሪያ ተሳታፊያችን ኤኬ በአካል ጉዳተኝነት በኩል ሊነሱና ልንጠብቃቸው የሚገቡ ብዙ ጉዳዮች እንዳሉ መገንዘብ አለብህ፡፡ የአካል ጉዳተኛ በመሆንህ ብቻም በራሱ አንዳንድ ጊዜ የጥቃት ሰለባ የምትሆንበት ሁኔታ ስላለ እንቅስቃሴህን ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ማድረግ ይገባሃል፡፡ ከዚህም ባለፈ የምትሰራቸው ስራዎች ከጤንነትህ ጋር በአግባቡ ሊዛመዱ የሚችሉ ስለመሆኑ ማሰብ አስፈላጊ ነው እያልን እናጠናቅቃለን፡፡

 

ጄኔራል ሰዓረና ጋዜጠኛ እስክንድር –ከኢየሩሳሌም አረአያ

$
0
0

ሰኔ 1 ቀን 1997ዓ.ም፤ በአዲስ ከተማ ት/ቤት የተጀመረው ተማሪዎችንና ንጹሃን ዜጐችን በግፍ የመግደል እርምጃ ተከትሎ አብዛኛው ባለስልጣናት ልጆቻቸውን ከየት/ቤቱ በአጃቢ ያስወጡ ነበር። ወደ ካቴድራል ት/ቤት በሁለት ኮብራ ተጭነው የተላኩ 20 ልዩ የፌዴራል ፖሊሶች የጄ/ል ሰአረና የጄ/ል ብርሃነ (ወዲ መድህን) ሴት ልጆችን አጅበው ሄዱ። ሁለቱ ሴት ልጆች በማግስቱ አሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ተመቶላቸው ዓርብ ሰኔ 3 ቀን በረሩ። የብዙ ባለስልጣናት ልጆች በተመሳሳይ እንዲወጡ ተደረገ።

jeneral saree and nafkote (2) ..29ሺህ የአሜሪካ ዶላር በተርም እየተከፈለላቸው መማር ቀጠሉ። የአዜብ ልጅና የእህቷ ልጅ፣ (በነገራችን ላይ አርአያ መኮንን ይባላል፤ በ1995ዓ.ም ቦሌ ከሩዋንዳ ፊት ለፊት ጥቂት ገባ ብሎ አዜብ ለዚህ ወጣት በ7 ሚሊዮን ብር ቪላ ቤት ገዝታ በስጦታ አበርክታለች። የቪላው ኪራይ ሂሳብ በስሙ ባንክ ይገባለታል) ..የአርከበና ስብሃት ልጆች በቨርጂኒያ፣ የሽፈራው ጃርሶ ልጆች በካሊፎርኒያ፣ የፖሊስ ኮሚሽነር የነበረው ወንጀለኛውና 5ሚሊዮን ዶላር ሰርቆ የወጣው ተስፋዬ መረሳ ልጆች በኒዮዎርክ….ወዘተ በተቀማጠለ ኑሮና በውድ ክፍያ መማር ያዙ። ባለፈው አመት በነርስ የተመረቀችው የጄ/ል ሰአረ ልጅ ሐመልማል ሰዓረ የምርቃት ፕሮግራም ላይ ጄኔራሉ ተገኝተው ነበር።…ወደ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንለፍ። እስክንድር በላባቸው ሰርተው ሃብት ካፈሩ ጥሩ ቤተሰቦች የተገኘ ልጅ ሲሆን የተማረው በሳንፎርድ ት/ቤት ነው። ከዚያም አሜሪካ መጥቶ ትምህርትና ህይወቱን ቀጠለ። “አገር አማን” ብሎ በዘመነ ኢህአዴግ አገር ቤት ገባ። ተደጋጋሚ እስርና ድብደባዎችን አሳለፈ። እነሆ “አሸባሪ” ተብሎ ከሌሎች ንፁሃን ጋር በእስር እየማቀቀ ይገኛል። እነ ጄ/ል ሰአረና መሰሎቻቸው በመቶ ሺህ በሚቆጠር ዶላር ልጆቻቸውን በአሜሪካና አውሮፓ ሲያስተምሩና ሲያንደላቅቁ፣ እንዲሁም ልጆቻቸውን ለማስመረቅ ሲገኙና ሲደሰቱ በአንፃሩ በመፃፉና ሃሳቡን በመግለፁ ብቻ እስር ቤት የተወረወረውና ናፍቆት ልጁን እንዳያሳድግ የተደረገው እስክንድር ነጋ ጭራሽ ቤተሰቡ ያወረሱትን ቤት በግፍ እንዲነጠቅ ተደረገ። በጄኔራሎቹና ባለስልጣናቱ ሰፈር ግን በሚሊዮን ብር የተገነባ ቪላ፣ ልጆቻቸው የሚንደላቀቁበት በመቶ ሺህ የሚቆጠር ዶላር…ወዘተ አለ። ይህ ከህዝብ የተዘረፈ የአገር ሃብት ነው!! የጄ/ል ሰዓረ ባለቤት ኰ/ል ፅጌ በስማቸው በገርጂ የተገነባውና ሰባት ሚሊዮን ብር የፈጀው ቪላ ሲገኝ የሚገርመው የቅጥር ግቢው ወለል በእምነበረድ መሸፈኑ ነው። ሌላው በሙስና የታሰሩት የደህንነት ሹሞቹ ወ/ስላሴና ገ/ዋህድ..መኖሪያ ቤት ውስጥ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ቦንቦች እንዲሁም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብና የቤት ካርታ ወዘተ መገኘቱን ገዢው ፓርቲ ይፋ አድርጓል። ዛሬ ጠያቂ ባይኖርም ቅሉ ነገር ግን ጄኔራሎቹና ባለስልጣናቱ እንደነ ወ/ስላሴ ዘርፈው ያካበቱት ለመሆኑ አያጠያይቅም። የሚገርመው መፅሐፍትና ጋዜጣ የተገኘበት የእስክንድር ቤት ሲወረስ በአንፃሩ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያና ሚሊዮኖች ተገኘበት ያሉትን የዘራፊዎቹን የሙስና ቤት አልነኩም።… እንደ እስክንድር ሁሉ አቶ አንዱአለም፣ አቶ በቀለ፣ ውብሸት፣ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ተወካዮች እነ አቡበከር.. በሙሉ ልጆቻቸውን እንዳያሳድጉ የተደረጉ የህሊና እስረኞች ናቸው!! እንዲሁም ጄ/ል ሰአረ በምሳሌነት ተጠቀሱ እንጂ የአብዛኛው ባለስልጣን ከዘረፋ የተገኘ ህይወት ተመሳሳይ ነው። የአንዳንዶቹ ባለስልጣናትና ልጆች የአሜሪካ ውሎና ኑሮ የሚያሳይ በፎቶ የተደገፈ ማስረጃ እንዳለ ሳልጠቁም አላልፍም።…

(በፎቶው ጄ/ል ሰዓረ ሴት ልጃቸውን አቅፈው ሲያስመርቁና ሲደሰቱ- በአንፃሩ እስር ቤት ከጋዜጠኛ ሰርካለም የተወለደው ሕፃን ናፍቆት እስክንድር በጨቅላነቱ በስደት ያለ አባት እንዲያድግ ተፈርዶበት ይታያል..)

ሱዳን ሃገር የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይን የሚዳሥስ አራተኛ ፁሁፍ (ካርቱም ሱዳን)

$
0
0

ሰኔ 04/ 2006
ካርቱም ሱዳን

helpባለፉት ሦስት ፁሁፎቻችን እንደገለፅነው ዛሪም የስደተኛው ችገር በመቀፀሉ የተነሳ ይህንን  ፁሁፍ ለመፃፍ ተገደናል አፈሳው ሰሞኑን ጋፕ ብሎ ሰንብቶ ነበር ከሰኔ ሁለት ጀምሮ ግን በጣም ተባብሷል ጭራሽ ህግ  አስከባሪ ነን የሚሉ ፖሊሶች ወደ ተራ ዝርፊያ ገብተው ይገኛሉ። - [ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—–

የአዲስ አበባ የባቡር ሐዲድ በውሉ መሠረት ባለመነጠፉ እየተቀየረ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ አስታወቀ

$
0
0

6cd106c6c9eaae691a91562dec3d04eb_Lበአዲስ አበባ ከተማ ቀላል የባቡር መስመር ላይ ቀደም ብሎ የተነጠፈው ሐዲድ ከውሉ ውጪ የተከናወነ በመሆኑ በመቀየር ላይ እንደሚገኝ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

በምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ከተማ የባቡር ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር በኃይሉ ስንታየሁ ባለፈው ዓርብ በፕሮጀክቱ አካባቢ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራርያ፣ የቻይናው ኩባንያ በኮንትራት ውሉ መሠረት ሐዲዱን እንዲያነጥፍ በኮርፖሬሽኑ አማካሪ ድርጅት በመታዘዙ በመቀየር ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ቀደም ብለው የተዘረጉት ሐዲዶች እርስ በእርስ የተያያዙት በብሎን መሆኑን ያስታወሱት ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹የኮንትራት ስምምነቱ ግን በኃይድሮጅን ብየዳ መከናወን እንደሚገባው ይገልጻል፤›› ብለዋል፡፡

በብየዳ እንዲያያዙ መደረጉ ‹‹ከጥንካሬ፣ ከደኅንነትና ከምቾት አንፃር ጥቅም ስላለው ነው›› የሚሉት ኢንጂነር በኃይሉ፣ በሚነሱትና በሚቀየሩት ሐዲዶች መካከል የምርት እንጂ የጥራት ልዩነት የለም ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት እየተከናወነ ያለው ሐዲዱን የመቀየርና የመበየድ ሥራ እንጂ ‹‹ሐዲዱ የሚያርፍበትን ርብራቦችና ባላንስ ጠጠሩን የማንጠፍ አይደለም፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

‹‹ከቻይናው ኩባንያ ጋር የተፈረመው ስምምነት የኢንጂነሪንግ፣ የግዥና የግንባታ ሥራዎችን አጠናቆ የፕሮጀክቱን ቁልፍ የማስረከብ ኃላፊነት በመሆኑ፣ በዚህ ሐዲድ የመቀየር ሥራ በራሱ ጊዜና የገንዘብ ወጪ የሚሸፈን ነው፤›› ብለዋል፡፡

እስካሁን ድረስ ኮንትራክተሩ ያቀረበው የጊዜም ሆነ የወጪ ኪሳራ አለመኖሩን የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ፣ ቢያቀርብም ከውሉ ውጪ በመሥራቱ የመጣ በመሆኑ አማካሪ ድርጅቱ አያፀድቅለትም ብለዋል፡፡

ሐዲዱን የመቀየር ሥራ እየተከናወነ ያለው ሐዲዱ ቀድሞ በተነጠፈባቸው ቦታዎች በሙሉ መሆኑን ኢንጂነር በኃይሉ አስረድተዋል፡፡

Source: Ethiopian Reporter

ፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ ከጠበቃ አምሐ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

$
0
0

10450846_839629952732672_3428211520770207074_nየስድስቱን ጦማርያንና የሁለቱን (የኤዶምና የተስፋለምን)ጉዳይ በመከታተል በፍርድ ቤት እየወከሏቸው የሚገኙት የህግ ባለሞያ አቶ አምሐ ሁልግዜም የህግ ደምበኞቻቸው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ ግቢው ውስጥ ውጪ ለምንጠብቃቸው ጋዜጠኞች በዝጉ ችሎት ምን እንደተከናወነ ያለምንም መሰላቸት ያስረዳሉ፡፡በትናንትናው የፍርድ ቤት ውሎም ጠበቃው ከዋናው ግቢ ውጪ አሰፍስፈን ለጠበቅናቸው ጋዜጠኞች መረጃ አድርሰውናል፡፡ለተባባሪነታቸው፣ድካም ሳይነበብባቸው፣አንተ ወይም አንቺ ከየትኛው ሚዲያ ነህ/ሽ ሳይሉ ለሚዥጎደጉድላቸው ጥያቄ ምለሽ በመስጠታቸው ምስጋናዬ ይድረሳቸው፡፡

ጥያቄ —በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ፖሊስ አዲስ ያቀረበው ነገር ምንድን ነው ? ጠበቃ አምሐ –አዲስ ያቀረበውን ነገር በዶክመንት መልክ አላቀረበም፡፡በቃል ያሉት የተወሰኑ ምስክሮችን መስማት መጀመራቸውን፣ለባንክ ቤቶች ለጻፍነው ደብዳቤ ከአንዳንዶቹ ምላሽ አግኝተናል፣የተወሰኑ ዶክመንቶችን አስተርጉመናል ነው ያሉት፡፡ነገር ግን ምን ያህል ምስክሮችን ለመስማት አቅደው ምን ያህሉን ማድመጥ እንደቻሉ አልተናገሩም፣ያስተረጎሟቸው ዶክመንቶች ጠረጠርንበት ለሚሉት ወንጀል ያለው አስረጂነት /ተቀራራቢነት ምን እንደሆነም አልገለጹም ፡፡ ጥያቄ– ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ ጊዜያት በፖሊስ ለሚጠየቀው የምርመራ ጊዜ እየፈቀደ ነገር ግን ቀጠሮ የተፈቀደበት ምርመራ ሳይከናወን ሲቀር ፖሊስ መጫን አይችልም ? ጠበቃ አምሐ — የእኛም ትልቁ መከራከሪያ ይህው ነበር፡፡ፖሊስ ቀጠሮ የጠየቀበትን ምክንያት ሳይሰራ የተለያዮ ሰበቦችን እያቀረበ ደምበኞቼን እያጉላላ ነው ብለናል፡፡አሁን ግን ፍርድ ቤቱ ጠንከር ያለ ትዕዛዝ በመስጠት ይህው ትዕዛዝም መዝገቡ ላይ እንዲሰፍር አድርጓል፡፡አሁን የተሰጠው የሃያ ስምንት ቀን የምርመራ ጊዜም የመጨረሻው እንደሚሆን ፍርድ ቤቱ ገልጻል፡፡እኛም ይህ ትዕዛዝ መዝገብ ላይ መስፈሩን አረጋግጠናል፡፡ ጥያቄ– በየቀጠሮው ዳኞች እተቀያየሩ መቅረባቸው አሁን ተስፋ የሚያደርጉት ነገር ላይ ተጽእኖ አይፈጥርም ? ጠበቃ አምሐ — አይፈጥርም በማለት መናገር አልችልም፡፡ለምሳሌ ከዚህ ቀደም አንድ ዳኛ ከመነሻው ክሳችሁን በሽብርተኝነት ያላደረጋችሁት በመሆኑ አሁን መለወጥ አትችሉም በማለት ጉዳዩ በመደበኛ ፍርድ ቤት ሊመራ እንደሚችል ተናግረው ነበር፡፡በሌላ ቀጠር ውሳኔው እንዲለወጥ ተደርጓል፡፡ይህ ግን መዝገብ ላይ የሰፈረ በመሆኑ የዳኛው መለወጥ ለውጥ ይፈጥራል ብለን አንገምትም፡፡ ጥያቄ– አሁን ፖሊስ የሃያ ስምንት ቀን ጊዜ ቀጠሮ የተፈቀደለት በዚህ ግዜ ውስጥ ምን አደርጋለሁ ብሎ ነው? ጠበቃ አምሐ — ፍርድ ቤቱ ተባባሪዎቻቸውን ለመያዝና የትርጉም ስራ ለመስራት ለሚለው ተጨማሪ ጊዜ እንደማይሰጠው አስታውቋል፡፡በተጨማሪው ጊዜ አለኝ የሚለውን ማስረጃ ሰብስቦ እንዲጨርስና ምስክሮቹን እንዲያደምጥ ተነግሮታል፡፡በእርግጥ ፖሊስ ያልያዝኳቸው ተባባሪዎች አሉ ክፍለ ሃገር ስለሄዱብኝ ላገኛቸው አልቻልኩም ብሏል፡፡በነገርህ ላይ ፖሊስ በቀጣዮ ጊዜ ሲቀርብ ፍርድ ቤቱን ጊዜ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ጥያቄ– ምናልባት ፖሊስ የጸረ ሽብር አዋጁን በማስታከክ ይሆን ቀጠሮ እየደጋገመ የሚጠይቀው ጠበቃ አምሐ — አዎን አዋጁ ለአራት ወራት ፖሊስ ቀጠሮ በመጤቅ የምርመራ ስራውን እንዲሰራ ይፈቅድለታል፡፡ይህ ተባለው ግን ለምርመራ ነው፡፡ምንም ሳይሰሩ ምርመራዬን ስላልጨረስኩ እንዲል ግን አይፈቅድለትም፡፡ፍርድ ቤቱም ይህንኑ በመረዳቱ ይመስለኛል ከአሁን በኋላ አልፈቅድም ያለው፡፡ ጥያቄ — ደምበኞችዎ ዛሬ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ በማዕከላዊ ከዚህ ቀደም ተናግረውት ከነበረ ውጪ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ተናግረው ይሆን ጠበቃ አምሐ –ጋዜጠኛ አስማማው ሁለት ነገሮችን ዛሬ ለፍርድ ቤቱ አቅርቦ ነበር፡፡የጀርባ ህመም እንዳለበት በመግለጽ መርማሪው ወንበር እንዲያቀርብለት ነግሮት የነበረ ቢሆንም ይህ አልተደረገልኝም ብሏል፡፡የእህቱ የባንክ ደብተር በፖሊስ በመወሰዱም ቤተሰቡ ችግር ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ ለማዕከላዊ ሰዎች ነግሯቸው ምላሽ እንዳላገኘ አስታውቋል፡፡የአስማማው መርማሪ በበኩሉ ህመምተኛ መሆኑን እንደነገረው ነገር ግን ወንበር ስጠኝ አላለኝም በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የአስማማውን እሀት የባንክ ደብተር ከምርመራው ጋር የሚያገናኘው ነገር ይኖራል በማለት ከጠረጠረ ሊያቆየው እንደሚችል የጠቀሰ ሲሆን ህመምተኛ በመሆኑ ግን ጤንነቱ እንዳይጎዳ ፖሊስ አገሪቱ በምትችለው መጠን ሊያስተናግደው እንደሚገባና ይህንኑ ማግኘትም ህገ መንግስታዊ መብቱ መሆኑን በማውሳት የጠየቀው እንዲፈጸምለት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡መርማሪውም የተባለውን እንደሚያደርግ ለፍርድ ቤቱ ቃሉን ሰጥቷል፡፡ ጥያቄ –ጉዳዮን እንደሚከታተል ጠበቃና ግለሰብ በሂደቱ ላይ ያለዎት ተስፋ ምንድን ነው ጠበቃ አምሐ — ብሩህ ነገር ይታየኛል ማለት ባለመቻሌ አዝናለሁ፡፡ምክንያቱም እንደሚገባን እየተደመጥን አይደለም፡፡ፖሊስ የጠየቀውን እያገኘ ነው፡፡ ይህ ነገር ተስፈኛ እንዳንሆን ያደርገናል፡ ምንጭ፥ – freedom4ethiopian.

የስኳር ፕሮጀክቶች ለተቋራጮች የተሰጡት በህገ-ወጥ መንገድ ነው ተባለ

$
0
0

በጥቅምት 2006 ይጠናቀቃል የተባለው የስኳር ፋብሪካ ግንባታ ገና አልተጀመረም

የፋብሪካ ግንባታ በመጓተቱ፤ የ100 ሚሊዮን ብር ሸንኮራ አገዳ ያለ ጥቅም ተወግዷል

የፕሮጀክቶቹ የገንዘብ ወጪ በውል አይታወቅም፤ ያለ ጥናትና ዲዛይን የተጀመሩ ናቸው

          27 መንግስት በመቶ ቢሊዮን ብር ወጪ የስኳር ምርትን 23 ሚሊዮን ኩንታል ለማድረስ የሚያካሂዳቸው ከአስር በላይ አዳዲስና ነባር የስኳር ፕሮጀክቶች ያለ ውጤት ለአመታት የተጓተቱ ሲሆን፤ የመስኖና የፋብሪካ ግንባታዎቹ ለተቋራጭ ድርጅቶች የተሰጡት በህገወጥ መንገድ ያለጨረታ እንደሆነ የፌደራል ኦዲተር ገለፁ፡፡ አስር የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ ህግን ባልተከተለ መልኩ ያለ ጨረታ ሙሉ ለሙሉ ለብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን መሰጠቱን ኦዲተሩ ጠቅሶ፤ የፋብሪካዎቿ ግንባታ እንደተጓተተ ገልጿል፡፡ ያለ ጨረታ የመስኖና የአገዳ ልማት ፕሮጀክቶችን ወስደው ስራ ያጓተቱ ተቋራጮች፤ በአዲስ አበባና በየክልሉ የሚገኙ የውሃ ስራ ድርጅቶች እንዲሁም የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ናቸው፡፡ ፕሮጀክቶቹ የመንግስትን የግዢ መመሪያ ባልተከተለ መልኩ ያለ ጨረታ ለተቋራጮች መሰጠታቸው፣ በታቀደላቸው ጊዜና ወጪ እንዳይጠናቀቁ ያደርጋል ብሏል – የኦዲተሩ የምርመራ ሪፖርት፡፡

ፕሮጀክቶቹ ለተቋራጮቹ የተሰጡበትን አሰራር በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁት የኮርፖሬሽኑ የስራ ሃላፊዎች፣ በግዢ ክፍሉ በኩል የምናውቀው ነገር የለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የኮርፖሬሽኑን የአምስት አመታት እቅድ አፈጻጸም በተመለከተ የቀረበው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በጣና በለስ እና በኦሞ-ኩራዝ ፕሮጀክቶች፣ የ3 ፋብሪካዎች ግንባታ እስከ ጥቅምት 2005 ዓ.ም እንዲጠናቀቅ እቅድ ወጥቶ እንደነበር የገለፀው የፌደራል ኦዲተር፤ እስከ አመቱ መጨረሻ የተከናወነው ስራ ግን ከ45 በመቶ እንደማይበልጥ ገልጿል፡፡ በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም ይጠናቀቃል የተባለው የወልቃይት የስኳር ፋብሪካ ግንባታም፣ ገና ግንባታው ሳይጀመር የእቅዱ ጊዜ ማለፉ ተገልጧል፡፡

በአገዳ ተክል ልማት፣ በመስኖ ስራና በፋብሪካ ግንባታ በኩል ኮርፖሬሽኑ የሚያዘጋጃቸው የስኳር ፕሮጀክት እቅዶች የሰው ሃይልንና የገንዘብ ምንጭን ያላገናዘቡ፣ ተግባሪ አካላትን ያላሳተፉና በበቂ ጥናት ላይ ያልተመሰረቱ መሆናቸውን በምርመራ እንደደረሰበት ኦዲተሩ ገልፆ፤ በዚህም ምክንያት የኮርፖሬሽኑ ዓመታዊ እቅዶች በአመት ከሶስት ጊዜ በላይ ይከለሳሉ ብሏል፡፡ ይህም ፕሮጀክቶቹ እንዲጓተቱ ማድረጉንና መንግስትን ተገቢ ላልሆነ ወጪ እየዳረገው እንደሚገኝ የኦዲተሩ ሪፖርት ገልጿል፡፡ የተንዳሆ ስኳር ፕሮጀክት የፋብሪካ ግንባታ ስራ በታቀደለት ጊዜ መጠናቀቅ ባለመቻሉ ምክንያት፣ በ5ሺህ164 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የሸንኮራ አገዳ ምርት ጥቅም ላይ ሳይውል እንዲወገድ መደረጉን ኦዲተሩ ጠቅሶ፤ በዚህም ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰ አመልክቷል፡፡

ፕሮጀክቶቹ በትክክል ምን ያህል ገንዘብ ወጪ እንደተደረገባቸው በውል ለመለየት አለመቻሉን የገለጸው የኦዲተሩ ሪፖርት፤ ከአገዳ ልማት፣ ከመስኖ ግንባታና ከፋብሪካ ግንባታ ክፍል ጋር የተቀናጀና የተጠናከረ የፕሮጀክት ክትትልና ቁጥጥር አሰራር ባለመኖሩ ምክንያት በየአመቱ ተደጋጋሚ የዕቅድ ክለሳ በማድረግ የዕቅድ አፈጻጸም መጓተትን፣ የወጪ መጨመርን፣ የጊዜ መራዘምንና የሃብት ብክነትን አስከትሏል ብሏል፡፡ ፕሮጀክቶቹ ለአመታት መጓተታቸው፤ የሃብት ብክነትን ከመፍጠር በተጨማሪ በአምስት አመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ የተቀመጠው ግብ እንዳይሳካ ማድረጋቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡ የአገሪቱ የስኳር ምርት በየአመቱ እንደሚጨምር ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፤ ከ2003 ዓ.ም ወዲህ የስኳር ምርት እየቀነሰ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በአምስት አመት ውስጥ የስኳር አመታዊ ምርት ከ3 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 22 ሚሊዮን ኩንታል እንዲያድግ ታቅዶ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን፤ እስካሁን አራት ሚሊዮን ኩንታል አለመድረሱ ተዘግቧል፡፡

ምንጭ፥ – አዲስ አድማስ


መኢአድና አንድነት በአንድ ወር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ይዋሀዳሉ

$
0
0

በሁለቱም ወገን የተመረጠው ውህደት አመቻች ኮሚቴ ሰኞ ስራ ይጀምራል

      UDJAEUP   የአራት አመት የድርድርና የምክክር ጊዜ የፈጀው የመላው ኢትዮጵያ ድርጅት (መኢአድ) እና የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ቅድመ ውህደት ባለፈው እሁድ የተፈረመ ሲሆን ሁለቱ ፓርቲዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚዋሀዱ የፓርቲዎቹ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ ነገ ብሄራዊ ምክር ቤቱን ለአስቸኳይ ስብሰባ የጠራ ሲሆን የስብሰባው ዓላማም የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴን ለመምረጥ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ኮሚቴው በብሄራዊ ም/ቤቱ እንደሚሰየም የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ተናግረዋል፡፡ የመኢአድ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነህ ለአዲስ አድማስ እንዳብራሩት፤ የመኢአድ ስራ አስፈፃሚ አምስት አባላት ያሉት የውህደት አመቻች ኮሚቴ መርጦ ለአንድነት በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን አባላቱ አቶ ወርቁ ከበደ፣ አቶ ተስፋሁን አለምነህ፣ አቶ ሲራክ አጥናፍ፣ አቶ ሙሉ ጌታ አበበና አቶ ካሳሁን አበባው ናቸው፡፡ በአንድነት በኩል ያሉት አዘጋጅ ኮሚቴው ነገ በብሄራዊ ም/ቤቱ ከተመረጡ በኋላ ይፋ እንደሚሆኑ የተናገሩት አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ ከሁለቱም ፓርቲዎች የተውጣጡ እና 10 አባላት ያሉት ውህደት አመቻች ኮሚቴ ሰኞ ስራውን እንደሚጀምር ገልፀዋል፡፡

በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ውህደቱ እንደሚፈፀም የገለፁት አቶ ሀብታሙ፤ ስለውህዱ ፓርቲ ስያሜ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ስለ አጠቃላይ የውህደቱ ፓርቲ ፕሮግራም፣ አርማና ድርጅታዊ አወቃቀር ውይይት ተደርጎ ሙሉ በሙሉ ውህደቱ ይጠናቀቃል ብለዋል። ባለፈው እሁድ በተደረገው ቅድመ ውህደት ላይ ስለተነሳው ረብሻና ድብድብ የተጠየቁት የመኢአድ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፤ ረብሻ በማስነሳት ቅድመ ውህደቱን ለማሰናከል ሙከራ ያደረጉት ሰዎች የኢህአዴግ ካድሬዎች መሆናቸው በማስረጃ ደርሰንበታል” ያሉ ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ሁሉም ነገር በሰላም እየተከናወነ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

 አዲስ አድማስ

የዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት ዛሬ ጁን 15 በሚኒሶታ ይከበራል * የዓመቱ ምርጥ ሰው ይሸለማል

$
0
0

የሚኒሶታ ምርጥ ሰው ይሸለማል ከተመሠረተች 6ኛ ዓመቷን የምትይዘው ዘ-ሐበሻ በደመቀ ሁኔታ በዓሉን በሚኒሶታ ዛሬ እሁድ ጁን 15 ቀን 2014 ዓ.ም እንደምታከብር የzehabesha LLC መስራችና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ አስታወቀ። ዘ-ሐበሻ በጋዜጣ መልክ በሚኒስታና በአካባቢዋ የምትሰራጭ ሲሆን በድረገጽ ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ አድጋ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያውያን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ መሆኗን የሚገልጸው ሔኖክ “ድረገጹ በየቀኑ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ወገኖች እንደሚጎበኝ ከጎግል የምናገኘው መረጃ ያሳያል፤ ከዚህም በተጨማሪ የሰርቨር ወጪያችን እንዲጨምር ምክንያት ሆኖናል” ይላል። አንድ ድረገጽ ከፍተኛ ተመልካች ሲኖረው ያን ማስተናገድ የሚችል ትላልቅ ሰርቨር ያስፈልገዋል የሚለው ጋዜጠኛው ድረገጹ አንዳንድ ጊዜ በከፍተኛ ተመልካች ብዛት ሰርቨሩ እየተጨናነቀ የመጓተትና አንዳንዴም ሰዎችን አላስገባ እንደሚል ገልጾ ይህን ችግር ለመፍታት አንባቢዎች የዘ-ሐበሻን ወጪዎች እንዲጋራ በድረገጹ ላይ ጥሪ አቅርቦ እንደነበር አስታውሷል። “በድረገጻችን ላይ ባደረግነው የድጋፍ ጥሪ ኢትዮጵያውያን በገንዘብ በኩል ያሳዩን ድጋፍ አነስተኛ ነበር” የሚለው ጋዜጠኛው በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ጊዜያት ድረገጹን ለመረዳትና ብዙ ሰዎችን ካለምንም ችግር ማስተናገድ እንዲችል የገንዘብ ድጋፍ አድርገው እንደነበርና እነርሱንም በዚህ አጋጣሚ እንደሚያመሰግን ገልጿል። 10376341የዘ-ሐበሻ በተለይ የሚኒሶታ ወዳጆች ላለፉት 6 ዓመታት ዘ-ሐበሻን እንዴት መርዳት እንችላለን? ጋዜጣውን በሽያጭ ለምን አታደርጉትም ሲሉ የተለያዩ ወገኖች ሲጠይቁን ነበር የሚለው ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ ያንን ለማድረግ ሳይቻል ቀርቶ ነበር። ሆኖም ግን ዛሬ ጁን 15 ቀን 2014 ዓ.ም በኬሊ ኢን ሆቴል አክቲቪስት ታማኝ በየነን በመጋበዝ የሚኒሶታ ወዳጆቻችን ዘ-ሀበሻን የሚያጠናክሩበት ምሽት አዘጋጅተናል ብሏል። በዚህ የዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት በዓል ላይ ሁሉም የዘ-ሐበሻና የነፃ ሚድያ ደጋፊዎች እንዲገኙ ጥሪ ያቀረበው ሔኖክ አርቲስት ታማኝ በየነም ዘ-ሐበሻ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያከናወነችው የመረጃ መጋቢነት ተግባርን በማድነቅ ሌሎች ፕሮግራሞችን በመሠረዝ ለዘ-ሐበሻ አጋርነቱን በማሳየቱና ወደሚኒሶታ ለመምጣት መወሰኑን በማድነቅ ምስጋና አቅርቧል። በዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት በዓል ላይ የሚኒሶታ የዓመቱ ምርጥ ኢትዮጵያዊ እንደሚሸለም ያስታወቀው ጋዜጠኛው ይህ ሽልማት ወደፊትም እንደሚቀጥል ገልጾ የዘ-ሐበሻ ወዳጆች ዛሬ ጁን 15 በኬሊ ኢን ሆቴል በመገኘት የበዓሉ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጠርተዋል። የዘ-ሐበሻ በዓል የሚከበርበት አድራሻ

Best Western Plus Kelly Inn Address:
161 St Anthony Ave,
St Paul,
MN 55103

ዝግጅቱን ለማገዝና እንዴት ዘ-ሐበሻን ማገዝ እንደምትችሉ ለመጠየቅ የበዓሉን ዋና አስተባባሪ አቶ አልዩ ተበጀን በስልክ ቁጥር 612-986-0557  ያነጋግሩ።

ለዘ-ሐበሻ በቼክ እገዛችሁን ለመላክ
Zehabesha LCC
6938 Portland Ave S
Richfiled
MN 55423

መጠቀም ትችላላችሁ።

ዘ-ሐበሻን በፔይፓል በኩል ማገዝ ለምትፈልጉ የሚከተለውን ሊንክ ላይ ይክፈሉ

እውነት ያሸንፋል!

አሸባሪው አቃቤህግ በአሜሪካ

$
0
0

ህወሃቶች የፈጠራና የሐሰት ክስ እየፈበረኩ በርካታ ለወገንና ለአገር የሚቆረቆሩ ኢትዮጵያውያንን በአገር መክዳት፣ ዘር ማጥፋት እና ሽብር ፈጠራ ወንጀሎች በመክሰስ እና በማሰር ለከፍተኛ ፍዳና መከራ ዳርገዋቸዋል።
የእነ ሽመልስ ከማልን አርአያ እንዲከተሉ ተመልመለው እንደነ እስክንድር ነጋ፣ ርዮት አለሙ፣ ውብሸት ታየ አንዱዓለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣በቀለ ገርባ፣ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያውያንን ለእስርና ለሰቆቃ ከዳረጉት አቀብያነ ሕግ መሃል ቴዎድሮስ በሃሩ፣ ዘርሰናይ ምስጋናው፣ብርሃኑ ወንድምአገኝ በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ቴዎድሮስ በሃሩ በአሁኑ ግዜ በአሜሪካን አገር በሰላም የተረጋጋ ኑሮ ለመመስረት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። ይሁናና በሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ፣ የሚኖረው ግለሰብ ፍርድ ቤት ስላቀረበው መረጃ የሐሰት ክስ ለመናገር ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ይህ ቪዲዮ ቴዎድሮስና ተባባሪዎቹ የህወሃቶችን ግፍ በፍርድ ቤት ሽፋን ለማስፈጸም የሰሩትን ወንጀል፣ በንጹሃን ዜጎች ያደረሱትን መከራና ፍዳ ለማሳየት ይሞክራል። ህወሃቶች እና ሎሌዎቻቸው በጸረ ሽብር ሕግ ሽፋን በሐሰት ክስ በበርካታ ንጹሃን ዜጎች ላይ ሽብርና ግፍ መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ብዙ መረጃዎች መኖራቸውን ግን በቀላሉ መካድ አይቻልም።

አሸባሪው አቃቤህግ በአሜሪካ

Hiber Radio: የወ/ሮ አዜብና የአላሙዲ ተቀባይነት ከመለስ በኋላ ሲቀንስ የእነ ደብረ ጺዮን፣ ዶ/ር ቴዎድሮስና የሌሎቹ እየጨመረ መምጣቱ ተዘገበ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ሰኔ 8 ቀን 2006 ፕሮግራም

እንኳን ለአባቶች ቀን አደረሳችሁ !

<... ...> አቶ ብርሃነስላሴ አሰፋ የኢህአፓ አባላት በአንድ ላይ እንዲቆሙ ትንሳዔ ብሎ መንቀሳቀስ ከጀመረው የእርቅ ቡድን አባል አንዱ ስለ እንቅስቃሴያቸው ለህብር ከሰጡት መግለጫ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

>

ሻለቃ ደምሴ የቀድሞ ሰራዊት አባላትን ለማሰባሰብ ጉባዔ የጠራው አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለህብር ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የዓለም ዋንጫ ልዩ የስፖርት ዘገባ

በፍርድ አደባባይ ብቻውን ተሟግቶ ያሸነፈው የታክሲ ሹፌር እና ድሉ

ውይይት

ዜናዎቻችን

የወ/ሮ አዜብና የአላሙዲ ተቀባይነት ከመለስ በሁዋላ ሲቀንስ የእነ ደብረ ጺዮን፣ ዶ/ር ቴዎድሮስና የሌሎቹ እየጨመረ መምጣቱ ተዘገበ

ኢትዮጵያ ወደ ፖሊሳዊ አስተዳደር መቀየሯን አንድ የውጭ ምሁር ገለጹ

አንድነትና መኢአድ በአንድ ወር ሙሉ ለሙሉ እንዋሃዳለን ማለታቸው ተገለጸ

ውህደቱ የተለመደ የአገዛዙ ዕንቅፋት እንዳይጠብቀው የሚሰጉ አሉ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ማዕከላዊ ሚገኙት ለዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች አድናቆቱን ከእስር ቤት ገለጸ

በኢትዮ ሶማሊያ ድንበር 74 የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ

ጫት አዘዋወረ የተባለን ወጣት አልሸባብ አንገቱን ቀላ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

(ሰበር ዜና) ከ1000 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ቤታችን ፈረሰ በሚል ኢሰመኩ ደጃፍ ተቃውሞ ወጡ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን መስሪያ ቤት ደጃፍ ከ1000 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ቤታችን ፈረሰ፣ የምንሄደበት አጣን በሚል ለተቃውሞ መውጣታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በፎቶ ግራፍ አስደግፈው ዘገቡ።

ከ1000 በላይ የሚሆኑት እነዚሁ ተሰላፊዎች መንግስት አንድ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ በኢሰመኮ ደጃፍ ላይ በመስፈር መፍትሄ ካላገኘን አንነቃነቅም እንዳሉ ነው። አካባቢውን ፌደራል ፖሊስ ከቦታል ሕዝቡ ግን ካለምንም ፍራቻ ተቀምጦ መብቱን እየጠየቅ እንደሚገኝ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል።

ፎቶዎችን ተመልከቱ፤ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን እንመለሳለን። ዘ-ሐበሻ የትኩስ መረጃ ምንጭ።
self addis 1
self addis 2
self 3

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live