Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Health: ራስዎን በሁለት ቦታ የማስገኘት ጥበብ

$
0
0

ከሊሊ ሞገስ

ፈረንጆቹ (በይበልጥ የስነ ልቦና ተመራማሪዎች) ‹‹ቴሌፓርቴሽን›› በማለት ይጠሩታል፤ ስለተመኙ ወይም ስላሰቡ ብቻ የፈለጉት ቦታ የመገኘት ታላቅ ጥበብ ነው፡፡ ደግሞ አስደናቂው ጉዞ የሚከናወነው ከብርሃን ፍጥነት በመጠቀ ቅፅበት እንደመሆኑ መጠን እልህ አስጨራሽ የኤምባሲዎችን የቪዛ ቢሮክራሲ ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የሚችል መሆኑ በጣም አስደሳች ነገር ሆኖ ሳለ፤ ዘመድ አዝማድ ሳይሰናበቱ እንደው በድንገት የሚከናወን ምኞት በቅፅበት ነጥቆ እሩቅ ሀገር መውሰዱ ምናልባት መጠነኛ የሆነ ቅሬታ ሊፈጥር ይችላል፡፡

እንዲያውም ሆኖ ግን የብዙዎች ‹‹ባህር ናፋቂ›› ልቦች ምኞት ከምኞትነት አልዘለለም፣ በተፈጥሯዊው የቴሌፓርቴሽን ጥበብ የታደለ ሆኖ መገኘት ማለት ከባህር ውስጥ መርፌ የመፈለግ ያህል የማይመስል (Rare) ነገር ነው፡፡

በቅርቡ እየተሰሙ ያሉት ሌሎች ግኝቶች ደግሞ ለሰሚ ጆሮዎች አግራሞትም ድንጋጤም ሊፈጥሩ የሚችሉ ናቸው፡፡ ጉዳዩ እንደ ቴሌፓርቴሽን ለሳይንስ ገና ሊታይ ያልቻለ ‹‹ተዓምር›› አይደለም፤ ጉዳዩ የሳይንስ ውጤት ነው፡፡ ሆኖም እንኳን ሳይንስን እንደ ፖለቲካ ለምናገል ብዙሃን ቀርቶ በዘርፉ ተሰማርተው ለሚገኙ ተመራማሪዎችም ግኝቱ ግራ መጋባትን መፍጠሩን መፅሔቱ ዘግቧል፡፡ ይህ አዲስ ፈጠራ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ በእምቡጥ የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ከዚህ በኋላ የሚመጣውን ዘመን አኗኗር ግን በከፊል ወይም በሙሉ ሊቀይር (አሊያም ሊያናጋ) ይችላል ተብሎ ከወዲሁ ተተንብዮለታል፡፡
teleportation
ነገሩ ወዲህ ነው፤ ወደ ቴክኖሎጂያዊ ፈጠራው ውስጠ ምስጢርና ሐተታ ዘው ብለን በደረቱ ከመዝለቃችን በፊት ቴክኖሎጂው ስለሚያስገኛቸው መልካም ትሩፋቶች በጥቂቱ ጀባ እንበላችሁ፡-

ምሳሌ 1፡- ለስራም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ከሚኖሩበት ሞቅ ያለ ከተማ ርቀው ስልጣኔ ወዳልዳሰሰው አካባቢ ተጉዘዋል እንበል፤ ታዲያ ቀድሞ ይከሰታል ብለው ያላሳቡት የጤና ችግር ይፈጠርና ችግር ላይ ይወድቃሉ፡፡ ደሞ አጣዳፊ በሽታ ነው፤ ግን ሐኪም እንደሰማይ ርቆዎታል፡፡ ሆኖም ብዙ ጊዜ ከኪስዎ የያዝዋትን የሞባይል ስልክ በመጠቀም ወደ ሐኪምዎ የያዝዋትን የሞባይል ስልክ በመጠቀም ወደ ሐኪምዎ ጥሪ ያደርሳሉ፡፡ ከዚያም ስልኳ ላይ ያሉትን አንዳንድ ቁልፎች ጫን ጫን ሲያደርጉ በሚያስገርም ሁኔታ መዳፍ የማትሞላው ሞባይል ወደ ዶክተርነት ትቀየራለች፡፡ ዶክተሩ እዚያው ባሉበት አገላብጦ ይመረምርዎታል፤ ያክምዎታልም፡፡

እዚህ ላይ ግን ሞባይልዎ የተለወጠችው ስጋ ወደ ተላበሰ ዶክተር አለመሆኑን አስረግጠው ይወቁ፡፡ ሞባይሏ የተቀየረችው ወደ አርቴፊሺያል ዶክተርነት ነው፡፡ ዶክተሩ ደግሞ ከየትም የመጣ ሳይሆን በሩቅ ትተውት ከመጡት የመኖሪያ ከተማዋ ዘወትር ክሊኒኩ ውስጥ ተቀምጦ በሽተኞቹን የሚያስተናግደው ወዳጅዎ ነው፡፡ በሽቦ አልባው መስመር በአየር ላይ ረዥም ጉዞ ተጉዞ እርስዎ ጋ ይደርስና ሞባይልዎ ውስጥ ዘው ብሎ ገባ፣ በዚያው ቅፅበትም ሞባይልዎ ወደ ‹‹እሱነት›› ተቀየረች፣ ተመረመሩ፣ ተገቢው ህክምናም ተደረገልዎት!

ምሳሌ 2፡- መቼም ‹‹ቪዲዮ ኮንፍረንሲንግ›› የሚባለው የስብሰባ ‹‹ፋሽን›› ሀገራችን ውስጥም ሳይቀር በመስፋፋት ላይ ነው ያለው፡፡ እንግዲህ ቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ በቦታ ተራርቀው የሚገኙ ተሰብሳቢዎች በቪዲዮ ስክሪን አማካኝነት የተለያዩ እሰጥ አገባቸውን የሚያጧጡፉበት ዘዴ ሲሆን ርቆ የሚጓዘው ምስላቸው ብቻ ነው፡፡ በመጪው ዘመን ዓመታት ግን ለተሰብሳቢዎች የሚልኩት በቪዲዮ የተቀረፀ ምስልና ድምፅዎን ብቻ ሳይሆን ተንቀሳቃሽ ሐውልት የመሰለውን ባለሶስት ዳይሜንሽን (3-D) አካልዎን ከነአስተሳሰብዎ ጭምር ነው፡፡

እርስዎ ‹‹እርስዎነትዎን›› ለወዲያኛው ጫፍ በመላክ መልካም ተሳትፎ እንዳደረጉ ሁሉ ከዚያኛው ጫፍ ላይ ያለው አጋርዎም በሽቦ አልባው መገናኛ አማካኝነት ‹‹እሱነቱን›› ይልክልዎታል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም ሌሎች ተሳታፊዎች ካሉም ተመሳሳይ ሂደት ያከናውኑና ስብሰባው በይፋ ይጀመራል፡፡
ለምሳሌ እርስዎ መቀመጫዎት እዚህ መዲናችን ውስጥ ቢሆን፣ ሁለተኛው ተሳታፊ ናይሮቢ፣ ሶስተኛው ጆሃንስበርግ፣ አራተኛው ቦነስ አይረስ፣ አምስተኛው ኒውዮርክ፣ ስድስተኛው ለንደን፣ ሰባተኛው ሲዲኒ፣ ስምንተኛው ዱባይ፣ ዘጠነኛው ቤይጂንግ እንዲሁም አስረኛው ደግሞ ሚላን ቢሆን፣ በአስሩም የተራራቁ ከተሞች ውስጥ ለስራችሁም ጠረጴዛ ከባችሁ ትቀመጣላችሁ፣ አልፎ አልፎ እንደሚታየው በመካከላችሁ ጠና ያለ አለመግባባት ከተፈጠረም እንዳስፈላጊነቱ እርስ በርስ መቧቀስ ትችላላችሁ!

ምሳሌ 3፡- የጤናን ጉዳይ አሁንም እናንሳና (አያድርስብዎትና) በሆድ ውስጥ ህመም ታመው በኦፕራሲዮን ጠረጴዛ ላይ በማደንዘዣ ደንዝዘው የቀዶ ጥገናው ሂደት እየተከናወነብዎት ነው እንበል፡፡ ታዲያ ደዌው የመሸገበት የሆድ ውስጥ ብልትም መጠኑ በጣም አነስተኛ ሆነው ሐኪሞቹ የት ቦታ መቁረጥ እንዳለባቸው ተቸገሩ እንበል፤ ነገር ግን ሐኪሞቹ የመጪው ዘመን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ነበሩና የምስር ፍሬ የምታክለውን ብልት ወደ ግዙፍና ተመሳሳይ ግን አርቴፊሻል ብልት ቀይሯት፤ ደዌው ያለበትን ጥግም ተመለከቱ ከዚያም ይህን ወሳኝ መረጃ በመጠቀም ጥንጥየዋን ብልት ኦፕራሲዮን ለማድረግ ቻሉ!

እነዚህን ሁሉ እውነተኛ ተአምሮች እንካችሁ ብሎ የሚሰጠን ‹‹Claytronics›› ተብሎ የተሰየመው ጥበብ ነው፡፡ ጥበቡ ከቴሌፓርቴሽን ጥበብ የሚለየው በቴሌፖርቴሽን አንድ ሰው ካለበት ቦታ ተነስቶ ሌላ ስፍራ ላይ ሲያርፍ በቦታው የሚገኘው የተፈጥሮ አካሉ ነው፡፡ በክሌይትሮኒክስ ጥበብ ግን በሌላኛው ላይ የሚገኘው ስጋ የለበሰው ተፈጥሯዊው አካል ሳይሆን የእርሱ ሙሉ ቅጂ ነው፡፡ ቅጂው በመልክ፣ በቁመና እንዲሁም በአሰተሳሰብ ከኦርጅናሉ ሰው ጋር ፍፁም ተመሳሳይ ከመሆኑም በተጨማሪ ህይወት በውስጡ ያለ ይመስል የተንቀሳቃሽ አካል ባለቤት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ኦርጂናሉ ሲናገር በሩቅ ያለው ቅጂውም ተመሳሳይ ንግግር ይናገራል፤ ኦርጅናሉ የሚያከናውናቸውን ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች በቅጂው ‹‹ይቀዳሉ››፡፡

ስለዚህም የክሌይትሮኒክስ ጥበብ ከተአምራዊው የቴሌፓርቴሽን ጥበብ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ ነው ተብሎለታል፡፡ በቴሌፓርቴሽን ጥበብ አንድ ሰው በሁለት የተለያዩ ስፍራዎች ላይ መገኘት አይቻለውም፤ ይህ ሁኔታ ግን ለክሌይትሮኒክስ የሚሳነው አይደለም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ የቴሌፓርቴሽን ጥበብ ‹‹የሚታደሉት እንጂ የማይታገሉት›› ሲሆን ክሌይትሮኒክስ ግን እደማንኛውም የቴክኖሎጂ ውጤት ለፈላጊ ተጠቃሚው የሚሸጥ ነው፡፡

ግና ለመሆኑ ‹‹ክሌይትሮኒክስ›› ምን የሚሉት ጥበብ ነው? የመሳሪያው መሰረታዊ አካላት ‹‹Catoms›› በመባል የሚታወቁ ሲሆኑ፤ እያንዳንዱ ካቶም መጠኑ የፀጉርን አንድ ሚሊዮንና የደቀቀ መጠን ያላቸው አነስተኛ ኮምፒውተሮች ናቸው፡፡ በዘርፉ ጠበብት ‹‹ናኖ ኮምፒውትርስ›› በማለት ይጠሯቸዋል፡፡

ናኖኮምፒውተር (የአምስት ሣንቲም አስር ሚሊዮንኛ መጠን ያላቸው ኮምፒውተሮች) ለዘመናችን አዲስ የሚባሉ አይደሉም፡፡ ካተሞች (Catoms) ግን ከሌሎቹ ናኖኮምፒውተሮች በብዙ መልኩ የተለየ ባህሪይ ነው ያላቸው፡፡ ካተሞች እርስ በርስ የመገጣጠም ልዩ ፀባይ አላቸው፡፡ እንደ አስፈላጊነቱም አንዴ ሞባይል ስልክ፣ አንዴ ብዕር፣ አንዴ መነፅር ወይም ሌላ ጊዜ የሰው ቅርፅ መያዝ ይችላሉ፡፡ የተለያየ ቅርፅ እንዲይዙ የሚያስችላቸው ደግሞ የተቀመሩበት ሶፍትዌር (ፕሮግራሚንግ) መሆኑን የቴክኖሎጂው ፈጣሪ ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡

የክሎይትሮንክስ አመጣጥ

በታዋቂው የቴሌኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች አምራች ኩባንያ ‹‹ኢንቴል›› የምርመራ ላብራቶሪ ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሁለት ሰዎች ማለትም ቶድ ሞሪ እና ሴት ጎልድስታይን የተባሉት ሳይንቲስቶች ናቸው፡፡ ከመጀመሪያው ሐሳቡን በማመንጨት በቀጣይነት ወደ ምርምሩ የገቡት፡፡ ጠቢባኑ ‹‹ክሌይትሮኒክስ›› የሚባለው ሃሳብ ጭንቅላታቸው ውስጥ ብልጭ ያለባቸው የዛሬ ስምንት ዓመት ገደማ በተከሰተ አንድ አጋጣሚ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ያኔ ቨርጂኒያ ውስጥ በተዘጋጀ አንድ ኮንፈረንስ ውስጥ እንድንሳተፍ ለሁለታችንም ጥሪ ቀረበልን፡፡ ታዲያ ስብሰባው የሚካሄደው በቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ አማካኝነት ነበርና ቨርጂኒያ ድረስ መጓዝ አላስፈለገንም፡፡ ይህ ሁኔታ በጣም ስላደሰተንም ነበር ለቀጣይ ምርምር የጋበዘን፡፡ ከቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ የተሻለ ነገር ለምን አንፈጥርም? ተባባልን፡፡ ምርምሩ ተጀመረ፣ እናም አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ ደረስን በማለት ነበር የገለፁት፡፡
አነስተኛ መጠን ያላት መሳሪያ ነች፡፡ ቁመቷ 3.4 ሴ.ሜ፣ የዙሪያ ዲያሜትሯ ደግሞ 4.4 ሴ.ሜ የሆነችና የባትሪ ድንጋይ ቅርፅ ያላት ስትሆን ወደ አስር አይነት የተለያዩ ቅርፆች መቀየር ትችላለች፡፡ ቅርፆቿን የሚቀይረው አብሮ የተገጠመላት ኮምፒውተር ሲሆን በሽቦ አልባው መገናኛ አማካኝነት ራቅ ካለ ስፍራ ላይ ባለ ሰው መታዘዝ ትችላለች፡፡ ስሪቷ ከካተምስ የሆነችና የክሌይትሮኒክስ ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ውጤት ነች፡፡ ምርምሩ ግን በአስገራሚ ፍጥነት ቀጥሏል፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥም የታለመለትን ግብ ይመታል ተብሎ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ በተለይም አንድ ሰው በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ሁለት የተለያዩ ስፍራ ሊገኝ የሚችልበት ጥበብ መሆኑ ታላቁ የኢንቴል ኩባንያ ምርምሩን ስፖንሰር እንዲያደርግ አስገድዶታል፡፡

በእርግጥ አንድ ሰው በክሌይትሮኒክስ ወደ ሌላ ስፍራ እንዲጓዝ የአካሉ ቅርፅ በቪዲዮ ተቀርፆ በሽቦ አልባ መገናኛ ወደ ሌላኛው ጫፍ የሚተላለፍበት ሁኔታ መኖር አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ኦርጂናል አካል ባለበት ስፍራ ሆኖ በቪዲዮ ይቀረፃል፡፡ ቪዲዮ የሚቀርፀው መሳሪያ በአይነቱ ለየት ያለና የሰውየውን አካል በ360 ዲግሪ ከሁሉም አቅጣጫ እየቀረፀ በየሰከንዱ የሚያስተላልፍ ነው፡፡ በሌላኛው መሳሪያም ይህን የተሟላ መረጃ በመመርኮዝ የሰውየውን ተመሳሳይ ቅጂ (ኮፒ) ይሰራል፡፡

የክሎይትሮኒክስ ቴክኖሎጂ በጣም ወሳኝ የሚባሉ በጎ ጠቀሜታዎች ኖረውት ሳለ ምናልባት ለጥፋት ተግባር ሊውል ይችላል የሚል ፍራቻ ገና ከአሁኑ እየተንፀባረቀ ነው፡፡

ለምሳሌ ቅጂ ወታደሮችን ለጦርነት በመጠቀም ምንም ሳይጎዱ ሌላውን ብቻ መጉዳት፣ ከዚህም በተጨማሪ ለዝርፊያ ተግባር እና ለመሳሰሉት ወንጀሎች ቢውል የወንጀለኛው ዱካ ወይም አሻራ ሊገኝ በማይችልበት ሁኔታ ከበድ ያሉ የወንጀል ተግባራት ሊፈፀሙ ይችላሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ መቼም መጠቀም ካለ ጉዳት መኖሩ አይቀርምና ገና ለገና ለጥፋት ዓላማ ሊውል ይችላል በሚል ፍራቻ ተመራማሪዎች ከምርምራቸው አልቦዘኑም፡፡ እንደማንኛውም አዲስ ቴክኖሎጂ ክሌይትሮኒክስም በወደፊት ህይወታችን ላይ የሚያስከትለውን ለውጥ ከወዲሁ በትክክል ለመገመት ያስቸግራል፡፡ ወይ ያለማናል፣ አሊያም ያጠፋናል፣ ለውጡ ግን አይቀርልንም፡፡

ናኖቴክኖሎጂና ቴሌፓርቲሽን ሌሎቹ አማራጮች

በክሌይትሮኒክስ በአንድነት ሁለትነት፣ ሁለትም በአንድነት መከሰቱ ላልተመቻቸው ደግሞ ሌላ አማራጭ አለ፡፡ ምን ጠፍቶ፣ የጊዜው መርዘም ካልሆነ በቀር ሁሉ በእጃችን ሁሉም በደጃችን ነው፡፡
ናኖሮቦቲክስ ሁለተኛው አማራጭ ነው፡፡ ይህ ድንቅ ጥበብ የሚያተኩረው ደግሞ በአይን ለማየት እጅግ በሚከብዱና ጥቃቅን በሆኑ ሮቦቶች የሚመራ ቴክኖሎጂ ማስታቀፍም ይከተላል፡፡ ሽሉም የዘጠኝ ወር እድገቱን ጨርሶ እነሆ ይወለዳል፡፡ ሰውዬውም የድሮ ህፃናንቱን ክሎን በተደረገው ህፃን ውስጥ መመልከት ይችላል፡፡ ልጅም ሲያድግ ቁርጥ አባቱን፡፡ በእርግጥ ሴቷ አርግዛ ትውለድ እንጂ የልጁ ባዮሎጂካዊ (የዘር) እናትና አባት የሚባለው ሰውየው ነው፡፡ አባትና እናት ይባልም እንጂ ልጁ ልጅ ብቻ ሳይሆን ቁርጥ የሰውየው መንትያ ወንድም ነው፡፡ የሚበላለጡት በዕድሜ ብቻ!
ይህን ሁሉ ዕድል ይቅርብኝ ላለ ሰው ደግሞ የመጨረሻ ሌላ ዕድል አለ፡፡ ኳንተም ቴሌፓርቴሽን መቼም የእያንዳንዱ ሰው ሴል የተሰራው ከአተሞች ነው፡፡ እያንዳንዱ አተምም የተሰራው ከፓርቲክሎች ነው (ኤሌክትሮን፣ ፕሩቶንና ኒውትሮን)፡፡ እያንዳንዱም ፓርቲክል የኳንትም ባህሪ ያለው በመሆኑ በአንዴ ሁለት ቦታ ይከሰታል፡፡ እያንዳንዱም ፓርቲክል የኳንትም ባህሪ ያለው በመሆኑ በአንዴ ሁለት ቦታ ይከሰታል፡፡ እያንዳንዱም ሰው የኳንትም ባህሪ ካላቸው አተሞች ተገንብቷልና ይሄው በአንዴ በሁለት ቦታ የመከሰት ዕድሉ አይነፈገውም፡፡ ነገር ግን እነዚህን በሁለት ቦታ የመከሰት ዕድል ያላቸውን ፓርቲክሎች ተቀብሎ ልክ እንደ ኦርጂናሉ አይነት ሰው ለመፍጠር ልዩ የሆነ ተቀባይ መሳሪያ ያስፈልጋል፡፡ ይህ መሳሪያ ‹‹ግሪድ›› እየተባለ የሚጠራ ሲሆን በሞገድ መልክ የተከሰቱትን ፓርቲክሎች ሰብስቦ ወደ ፍፁም ሰውነት ይቀይራቸዋል፡፡ ልክ በአየር ላይ የተለቀቀን ድምፅና ምስል ሰብስቦ እንደሚያሳየን ቴሌቪዥን ይሆንና ግሪዱን ግን ለየት የሚያደርገው የሰውየውን አምሳል በስክሪን መልክ ብቻ ሳይሆን ገሃዳዊ ሰው አድርጎ ነው የሚተፋው፡፡ ይህ ሰውም ከኦርጂናሉ ሰው የሚለየው አንዳችም ነገር አይኖርም፡፡ ፍፁም ተመሳሳይ፡፡ ለመሆኑ እርስዎ የቱን ይመርጣሉ?…


ኢ- ፍትሃዊው እስሬ! እየፈሩ ጋዜጠኝነት የለም!

$
0
0

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና

(ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታችን ትልቅ አደጋ ላይ ነው)

elias Gebru

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና

አርብ ግንቦት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ከወዳጄ ጋዜጠኛ ዳዊት ሠለሞን ጋር ቀጠሮ ነበረኝ፡፡ ረፋድ 5፡25 ሰዓት ላይ የሞባይል ስልኬ ጠራች፡፡ ከአምባሳደር ወደአራት ኪሎ በሚጓዝ ታክሲ ውስጥ ተሳፍሬ ነበር፡፡ የመስመር (የቢሮ) ስልክ መሆኑን አየሁትና “ሃሎ” አልኩኝ፡፡ ‹‹አቶ ኤልያስ፣ የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ?›› የሚል የሴት ድምጽ ተሰማኝ፡፡ ‹‹አዎን›› ስል መለስኩላት፡፡ ብዙ ጊዜ አንባቢዎች ስለሚደውሉ፣ ምን ዓይነት ግብረ-መልስ (feed back) ይኖራት ይሆን ነበር ሀሳቤ፡፡ ሳይሆን ቀረ፡፡ ‹‹የምደውለው ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ነው፣ በአንድ ጉዳይ ላይ ስለምንፈልግዎት ቃልዎትን መጥተው እንዲሰጡን ነበር፡፡›› …‹‹እሺ፣ ሰኞ ጥዋት ልምጣ?›› በማለት ጠየኳት፡፡ ‹‹ቆይ አንዴ?›› ብላኝ ባልደረቦቿን ካነጋገረች በኋላ ‹‹ይቻላል›› አለችኝ፡፡ ቀጭን የጌታ ትዕዛዝ፡፡ ከዚህ የስልክ ጥሪ በኋላ የመጽሔቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ (ፍቄ) ደውሎልኝ ስለጉዳዩ ሐሳብ ተለዋወጥን፡፡ ሰኞ በጥዋት ለመገናኘት ተቀጣጥረን ስልኩ ተዘጋ፡፡

ለምርመራ መጠራቴ በኢትዮጵያ የነጻ ፕሬስ ሕይወት ውስጥ የሚያጋጥም፣ የተለመደ ጉዳይ በመሆኑ ብዙ አልተገረምኩኝም፡፡ በቀድሞ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ እሰራ በነበረበት ወቅት አሸባሪ ተብሎ በፓርላማ በተሰየመው የ‹‹ግንቦት 7›› የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች እና በአገር ውስጥ በነበሩ ከፍተኛ ጄኖራሎች፣ የመከላካለያ ሰራዊት አባላትና ሌሎች ዜጎች ላይ ከባድ ክስ ቀርቦ ነበር፡፡ የፍርድ ሂደቱን ተከታትዬ የምዘግበው እኔ ነበረኩ፡፡ እኔ ከሰራሁት ዘገባ ጋር በተያያዘ አቃቤ ሕግ ክስ አቅርቦ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ከባልደረባዬ ጋዜጠኛ ፍጹም ማሞ (ዋና አዘጋጅ የነበረ) ተጠርተን ቃል በመስጠት በ5000 ሺህ ብር ከወጣን በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበን ነበር፡፡ ፍ/ቤቱም ክሱን ተመልክቶ ለእኔ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሰጠኝ አጋጣሚ ስለነበረ ጉዳዩን አስታውሼ በአዕምሮዬ ለአፍታም ቢሆን ማሰላሰሌ አልቀረም ነበር፡፡

ሰኞ ግንቦት18 ቀን 2006 ዓ.ም ጥዋት ከባልደረባዬ ፍቃዱ ጋር ቀጠሮ ስለነበረን ወደ ቢሮ አመራሁ፡፡ በአጋጣሚ ፍቃዱ ያለወትሮው ቢሮ አልነበረም፡፡ ስልኩ ይጠራል፣ ግን አይነሳም፡፡ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ገደማ ፍቃዱ ደወለልኝ፡፡ ሞባይል ስልኩን ያላነሳው ጓደኛው ቤት ረስቶት በመውጣቱ ምክንያት መሆኑን ነገረኝ፡፡ ከሰዓት የተጠራሁበት ቦታ ለመሄድ በድጋሚ ተቀጣጠርን፡፡ ከሰዓት በኋላ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ እና ነብዩ ሐይሉ ተቀላቅለውን አራት ሆነን ወደማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ሄድን፡፡

ምርመራ ቢሮ ቁጥር – 76

እኔ እና ፍቃዱ ተፈትሸን እና ሞባይላችንን ጥበቃ ጋር አድርገን ወደቢሮ ቁጥር 76 አቀናን፡፡ እኔ አንኳኩቼ ወደ ቢሮዋ ገባሁ፡፡ ፍቃዱ ውጭ ቁጭ አለ፡፡ አንድ ወንድ እና ሴት የመ/ቤቱ ባልደረቦች ቢሮ ውስጥ ነበሩ፡፡ ከየት እንደመጣሁ ነገርኳቸው፡፡ ‹‹ቁጭ በል›› ተባልኩ፡፡ ‹‹ጥዋት ነበር እመጣለሁ እኮ ያልከው?›› ብሎ ወንዱ ፖሊስ ሀሳቡን ሰነዘረ፡፡ ‹‹አዎን›› ካልኩት በኋላ ጠዋት ያልመጣሁት በሁኔታዎች አለመመቻቸት መሆኑን አስረዳሁት፡፡ በምን ጉዳይ ልጠራ እንደቻልኩ መረጃው ካለኝ እንድነግረው ፈገግ እያለ ወዲያው እኔኑ ጠየቀኝ፡፡ መረጃው እንደሌለኝ ነገርኩት፡፡ አንድ የክስ መዝገብ ሲገልጥ የመጽሔታችንን ቁጥር 113ኛ ዕትም አየኋት፡፡ በመጽሔቱ ፊት ገጽ ላይ ‹‹በቃን! የጠባብ ብሔርተኝነት ዘመቻ›› በሚል ትልቅ ርዕስ ሥር የቀድሞ ጠ/ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ፣ የቀድሞ ም/ ጠ/ሚንስትር አቶ ታምራት ላይኔ፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የኦነግ መስራች አቶ ሌንጮ ለታ፣ የቀድሞ ም/ ጠ/ሚንስትር እና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ አዲሱ ለገሰ፣ የቀድሞ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር እና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ተፈራ ዋልዋና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን ፎቶግራፎች አለ፡፡ ይህ ጽሁፍ መጽሔቷ ዝግጅት ክፍል የተሰራ እና ከወራቶች በፊት አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ሕዝብ ጸያፍ ስድቦች መሳደባቸውን ተከትሎ መሰል ድርጊቶች ሥርዓቱ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በተለያዩ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት፣ በኤርትራው ፕሬዚዳንት እና በቀድሞ የኦነግ መስራች መደረጋቸውን በማስታወስ ጠባብ ብሄርተኝነትን የሚቃወም እና ለችግሩ መፍትሄ ጠቋሚ ጽሁፍ ነበር፡፡
በዚያን ዕለት ለፖሊስ ቃሌን እንድሰጥ የተጠራሁትም በዚሁ ጽሑፍ መስሎኝ ነበር፡፡ መርማሪ መሆን አለመሆኑን ያላረጋገጥኩት እያነጋገረኝ ያለው ወጣት ግን የተጠራሁት በቅርቡ በኦሮሚያ ክልሎች በተነሳው ግጭት እና ብጥብጥ ጋር በመሆኑ ላይ ጥቁምታ ሰጠኝ፡፡ በአጋጣሚ በእጅ ላይ ሁለት የዕንቁ መጽሔት ዕትሞችን ይዜ ገብቼ ነበር፡፡ ወጣቱ ልጅ ‹‹አንዴ ልመልከታቸው?›› ብሎኝ ግንቦት 20 በተመለከተ ባለፈው ቅዳሜ የወጣውን የመጽሔቱን ዕትም ሰጥቼው እያገላበጠ ተመለከታቸው፡፡ ከሌላ ክፍል የመጣ አንድ መርማሪም ክስ ያቀረበብኝን ዕትም ከፋይሉ ውስጥ ነጥሎ በመውሰድ የሆነ ጽሑፍን በተመስጦ አንብቦ ክፍሉን ለቅቆ ወጣ፡፡

ወጣቱ ልጅ፣ ‹‹ያው ጥዋት እመጣለሁ ብለህ እኛም ስንጠብቅህ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ እኛ በተራችን እናስጠብቅሃለን፡፡›› አለኝ – ፈገግ እያለ፡፡ ፈገግታው ከልብ የመነጨ ነው ለማለት ግን እቸገራለሁ፡፡ ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ አንዲት ወፈር ያለች፣ የፖሊስ ማዕረግ ያለው የደንብ ልብስ የለበሰች ሴት ወዳለሁበት ክፍል መጣች፡፡ ‹‹ኤልያስ አንተ ነህ?›› አለችኝ፡፡

‹‹አዎን›› አልኳት፡፡

‹‹መጣሁ›› ብላኝ ከአፍታ ቆይታ በኋላ ተመልሳ በመምጣት እኔ የተቀመጥኩበት ወንበር ጋር ባለው ሰፋ ያለ ጠረጴዛ ትይዩ ተቀመጠች፡፡

‹‹ጥዋት ለምን አልመጣህም?›› የመጀመሪያ ጥያቄዋ ነበር፡፡

በአጋጣሚ በተፈጠረ ጉዳይ መምጣት አለመቻሌን አስረዳኋት፡፡ በዚህ ጊዜ ወጣቱ ልጅ አድራሻዬን፣ ዜግነቴን፣ የትውልድ ቦታዬን፣ የተማርኩባቸውን ትምህርት ቤቶች እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ የሰራሁባቸውን የሚዲያ ድርጅቶች፣ የትዳር ሁኔታ …እየጠየቀኝ ፎርም ላይ እየሞላ ነበር፡፡

‹‹ብሔርህስ?›› አለኝ፡፡ ‹‹ኢትዮጵያዊ›› አልኩት፡፡

‹‹ያ’ማ ዜግነት ነው፣ መናገር አለብህ›› አለኝ፡፡ በግሌ የማልወደው ጥያቄ መሆኑን ነገርኩት፡፡ [የሰው ልጆች በሙሉ ምንጫችን አንድ ነው ብዬ አጥብቄ ስለማምን የዘር ጥያቄ ከልጅነቴ ጀምሮ የማይመቸኝ እና የማላምንበት የግል ጉዳይ ነው] ስለብሄር ሊያስረዳኝ ሞከረ፡፡ መታወቂያዬ ላይ የተጻፈውን ነገርኩት፡፡
ወ/ሮ በላይነሽ የተባለችው ምርማሪዬ ፋይሉን ተቀብላ እና በመጽሔቱ የተከሰስኩበትን ጉዳይ ነገረችኝ፡፡ በታሪክ አምድ ሥር ‹‹የተገነቡት እና በመገንባት ላይ ያሉት የመታሰቢያ ሐውልቶች የእነማን እና ለእነማንስ ናቸው?›› በሚል ርዕስ ሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን የተባለው ጸሐፊ በጻፈው ጽሑፍ ውስጥ የኦሮሞን ብሔር የሚያጥላላ፣ ዘርን ከዘር የሚያጋጭ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ የመጣ መሆኑን የሚጠቅስ፣ ለኢትዮጵያ እንግዳ ሕዝብ መሆኑን የሚናገር …ወዘተ በጣም ጥሩ ያልሆነ ጽሑፍ መሆኑን ነገረችኝ፡፡ አያይዛም ይህን ጽሑፍ ተከትሎ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ቁጣ መቀስቀሱን፣ ተማሪዎች ጽሑፉን የጻፈው ግለሰብ ለሕግ እንዲቀርብ ሁለት ጊዜ ያህል ለዩኒቨርሲቲው የሚመለከተው አካል በደብዳቤ ቢያሳውቁም መልስ ሳይሰጣቸው በመቅረቱ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸውን፣ መስታወቶች መሰባበራቸውን፣ ንብረቶች መውደማቸው፣ በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ሆስፒታል ገብተው በሞት እና በሕይወት መካከል ያሉ ተማሪዎች መኖራቸውን፣ የመማር ማስተማር ሒደት መስተጓጎሉን …ወዘተ ዘርዝራ አስረዳችኝ፡፡

እኔም እኛ (የመጽሔቱ አዘጋጆች እና ባልደረቦች) ኢትዮጵያን አንድ የሚያደርግ እንጂ ዘርን ከዘር የሚከፋፍል ሥራ አለለመስራታችንን፣ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 29 መሰረት ሕግን በማክበር ጽሑፎችን መጻፋችንን እና የተለያዩ ግለሰቦችን ሐሳቦች ማስተናገዳችንን፣ ይህንንም መመልከት እንደሚቻል ከጠቀስኩላት በኋላ የተባለው ጽሑፍ የመጽሔቱ ሳይሆን የግለሰቡ የግል ግለ-ሀሳብ መሆኑን አሰረግጬ ነግሬያት ነበር፡፡

መርማሪዬም ‹‹ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በሕገ-መንግሥቱ ተደንግጓል ብላችሁ የመጣላችሁን ጽሑፍ በሙሉ ታትማላችሁ ማለት ነው?›› በማለት ቆጣ በማለት ለመናገር ሞከረች፡፡ የመጡልን ጽሑፎች ሁሉ እንደማይታተሙ፣ እንደዋና አዘጋጅነቴ መስተካከል ወይም መታረም ያለባቸውን ጽሑፎች በአግባቡ እንደምመለከት፣ ሌሎች የመጽሔቱ አዘጋቾችም መሰል ሥራዎችን ተጋግዘን እንደምንሰራ ረጋ ብዬ አስረዳኋት፡፡

በክፍሉ ውስጥ ያሉት ሶስቱም የፌዴራል ፖሊስ ባልደረቦች በጽሑፉ ምክንያት የጠፋ ንብረት እና የአካል ጉዳት መኖሩን አጽንኦት በመስጠት ‹‹አጥፍታችኋል›› በሚል ተቆጥተው ሊናገሩኝ ሞከሩ፡፡ የእኔም ስሜት በተወሰነ ደረጃ መቀየር ጀመረ፡፡ እመን አትመን ክርክር ውስጥ ለአፍታም ቢሆን ገባን፡፡ ‹‹እነዚህ ሰዎች የፍርድ ቤትንም ሥራ ደርበው ይሰራሉ ወይ?›› ስል ታዘብኩ፡፡

ንግግሬን ቀጥያለሁ፡፡ በቅድሚያ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተፈጠረ ለተባለው ነገር መጽሔታችን መነሻ መሆኑን ለመቀበል እንደምቸገር፣ መጋቢት ወር ላይ የወጣ ጽሁፍ አደረሰ የተባለውን ችግር ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት እዚህ ምርመራ ክፍል ውስጥ መሆኑን፣ በጽሑፉ የተቆጡ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለዝግጅት ክፍላችን አለመግለጻቸውን፣ ተማሪዎቹ ያቀረቡትን ቅሬታ ዩኒቨርስቲው መደበኛ በመሆነ መልኩ ለመጽሔታችን ዝግጅት ክፍል ምንም ነገር አለማቅረቡን፣ ቅሬታ ቀርቦ ቢሆን ኖሮ ተፈጠረ የተባለውን ችግር ለመፍታት እኛም የራሳችንን ሥራ መስራት እንችል እንደነበረ፣ ማስተባበያ ጽሁፍ ወይም ጽሑፉን የሚተች ሌላ ጽሑፍ ቢመጣ ኖሮ በተመሳሳይ ገጽ እና ይዘት እንደምናስተናግድ፣ ለዚህም ኃላፊነት እና ግዴታ እንዳለብን ተናገርኩ፡፡

በዚህም ብቻ አቆምኩም፣ በዚሁ መጽሔት ላይ የፖለቲካ አቀንቃኑ እና የኦሮሞ ጉዳዮች ዋነኛ ተማጋች መሆኑ የሚታወቀው ጃዋር መሐመድ የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄዎች ከነመፍትሄዎቹ በተመለከተ የሰጠንን ሰፊ ቃለ ምልልስ ማስተናገዳችንን፣ አቶ ኦባማ አንሰርሙ የተባሉ ጸሐፊም ስለኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ ሰፊ ጽሁፍ አቅርበው በመጽሔታችን ላይ ማስተናገዳችንን ዋቢ በማድረግ አስረዳኋቸው፡፡ እኔም ብሆን በግሌ የትኛውም ዘር ከየትኛውም ዘር እንደማይበልጥ እና እንደማያንስ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ረዥም ታሪክ ያለው ትልቅ ህዝብ መሆኑንና ከገዳ ሥርዓትም ዓለም ዴሞክራሲን እንደተማረ የግል ዕምነት እንዳለኝ ሀሳቤን ሰነዘርኩ፡፡
በቢሮው ውስጥ የፖሊስ ልብስ ለብሳ ኮምፒውተር ላይ ጽሑፍ በመተየብ ላይ ያለች አንዷ የተቋሙ ባልደረባ ጽሑፉ ግጭት ማስነሳቱን እና ጉዳት ማድረሱን ደጋግማ በመናገር ጥፋተኛ መሆናችንን ለመናገር ጥረት አድርጋ ነበር፡፡

እዚህ ጋር ለፖሊሷ ምሳሌ አነሳሁላት፣ አቶ መለስ ዜናዊ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ የ100 ዓመት ነው›› ብለው ተናግረዋል በሚል በአንድ ወቅት መስማቴን በመጥቀስ ይህ የግላቸው ዕምነት መሆኑን፣ እኔ ደግሞ ኢትዮጵያ ከ3000 ዓመታት በላይ ታሪክ እንዳላት እንደማምን እና የሳቸውን ሀሳብ መቃወም ካለብኝ መስታወት በመስበር እና ብጥብት በማስነሳት ሳይሆን በሀሳብ ሞግት ብቻ መሆን እንዳለበት አስረዳኋት፡፡ ምሳሌዬ ባይወጥላትም ዝም አለች – ሌላም ምሳሌ አንስቼላት ነበር፡፡ አቶ መለስ ‹‹የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው›› ብለው ነበር፡፡ ስላት፡፡ ‹‹አዎን፣ ምኑ ነው›› ብላ በፈጥነት መለሰችልኝ፡፡ ግን ትሰማኛለች እንጂ አታዳምጠኝም፡፡ ምናልባት እርሷንም ያስከስሳት ይሆን ማድመጧ!

…ሰዓቱ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ሆነ፡፡ መርማሪዬ ወደቤቷ ለመሄድ የቸኮለች መሰለኝ፡፡ ቃሌን ለመስጠት በነጋታው ከእሷ ጋር ተቃጣጠርን፡፡ በዋስ መውጣት እንደማልችል አረዳችኝ፡፡ እኔም በክፍሉ ውስጥ ካደረግነው ንግግር እና ፊታቸውን በማንበብ ቀድሜ ተረድቼ ነበር፡፡ ባልደረባዬ ፍቃዱን አስጠራሁት፡፡ ዋስትና መከልከሌንም ነገርኩት፡፡ ለእናቴ ስለጉዳዩ ነግሮ እንዲያረጋጋት ስልኳን በወረቀት ላይ ጽፌ ሰጠሁት፡፡ የቤቴን ቁልፍ ለአናንያ ሶሪ እንዲሰጥልኝ ነግሬም ቻው ተባብለን ተሰናበትኩት፡፡ እንግዲህ እንዲህ ነው እስር፣ በስልክ ጠርቶ ቡና ከበጋበዝ ይቀላል – ለመንግሥታችን፡፡

…ይቀጥላል!

በሁለት ዙር የሰለጠኑ 235 የድረ ገፅ መረጃ ማዛባት የሚችሉ ፕሮፓጋንዲስቶች በስራ ላይ መሆናቸው ታወቀ፡፡

$
0
0

ethsatኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ በመላ ሐገሪቱ በኢንተርኔት ድረ ገፅ መንግስት እየደረሰበት ያለውን ትችት ለመቀነስና ፤ የተደበቁ መረጃዎች ተጋላጭነታቸውን ለመቆጣጠር በማሰብ የሰለጠኑ ወጣቶች ስራ መጀመራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል፡፡ ኢህአዴግ በአዳማ ናዝሬት በሁለት ዙር ያሰለጠናቸው 235 ብሎገሮች በፊስ ቡክና በተለያዩ የማህበራዊ የመገናኛ መንገዶች፣ተቃዋሚ የሚመስሉ ስያሜዎችን በማውጣት ህዝብ የማደናገር፤ መንግስትን በሚቃወሙ መረጃዎች ላይ ምላሽ የመስጠት ፤ መንግስትን የሚደግፉ መረጃዎች በየጊዜው በመረጃ መረቡ ለህዝብ እንዲደርስ የማድረግ ተልእኮ ተሰጥቷዋል። ስልጠናውን የወሰዱት ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ሲሆኑ፣ ምርጫውን ያካሄዱት የመንግስት ኮሚኒኬሺን እና የኢህአዴግ ሊግ ናቸው፡፡ ሰልጣኞቹ ተጠሪነታቸው በክልሉ ላሉ የኢህአዴግ መሪ ፓርቲዎች ሲሆን፣ የመንግስት ከሚኒኬሺን መስሪያቤት በበኩሉ መረጃዎችን በበላይነት የማረም እና የማስተካከል ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በቅርቡ በተካሄደ የመጀመሪያው ዙር አፈፃፀም የአማራ ክልል መልካም ውጤት ማስመዝገቡን ፤ በፊስቡክ አመራርነት ለቤነሻንጉል ጉሙዝ ተሞክሮ ማካፈሉ መደነቁን የመንግስት ኮሚኒኬሺን ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን በባህር ዳር ላይ በተካሄደው የመንግስት ከሚኒኬሺን ባለሙያዎች ግምገማ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ የኢህአዴግ የስልጠና መምሪያ ሃላፊ አቶ አዲሱ ለገሰ ደግሞ ከኢሳት ከሚወረወረው የጦር ፕሮፓጋንዳ መዳን የምንችለው በኢቲቪ ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ ሚዲያው ነው ሲሉ ለተመራቂዎች ተናግረዋል። እስካሁን ባለው መረጃ ሰልጣኞቹ 2 ሺ 350 የፊስ ቡክ ፤ የቲውተር ፤ እና የብሎግ አካውንቶችን ከፍተዋል።

አበበ ተካ፡ ሀገሩን በሴት ፍቅር የለወጠው ድምፃዊ

$
0
0

abebe teka
ሳምሶን አብ
(በቁም ነገር መጽሔት ቅጽ 13 ቁጥር 178 ግንቦት 2006 ታትሞ የወጣ)

በሀገራችን ጥቂት የሙዚቃ አልበም አሣትመው እጅግ ከፍተኛ ተወዳጅነት ካተረፉ ድምፃውያን መካከል አንዱ ነው አበበ ተካ፡፡ በተለየ የአዘፋፈን ስልቱና ሙዚቃን በእውነተኛ ስሜት ተውጦ በማቀንቀኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም ቀልብ ሳቢ አቀራረቡ በ1989 ዓ.ም የዓመቱ ምርጥ ድምፃዊ ተብሎ የወርቅና የገንዘብ ሽልማት ማግኘት ችሏል፡፡ በእርግጥ ከአዘፋፈን ችሎታው በላይ የዘፈኖቹ በጥልቀት ፍቅርን የመግለፅ አቅምም ከሠው ልብ ውስጥ በቀላሉ መግባት የሚችሉ ሥራዎች እንዲኖሩት ሣይረዱት አልቀሩም፡፡ መድረክ ላይ ዓይኖቹን ጨፍኖ በታላቅ ተመስጦ ሲያቀነቅን የድምፃዊው ልብ ክፉኛ በፍቅር የተጎዳ መሆኑ ከፊቱ ላይ ይነበብ ነበር፡፡ ፍቅር አቅልጦ ቀጥቅጦ የሠራው ድምፃዊ ነው፡፡ በወቅቱ ኑሮን ለማሸነፍ ከአጠገቡ የራቀችው የፍቅር አጋሩ የዘፈኖቹ ዋና ተዋናይ ነበረች፡፡ እነ ‹‹ሠው ጥሩ››፣ ‹‹ምንድነው ቀለበት››፣ ‹‹በይ ካልረሣሽኝ›› እና ‹‹ አገሯ ወዲያ ማዶ›› የመሣሠሉት ድንቅ ሥራዎች የፍቅሩ ትሩፋቶች ናቸው፡፡

በፍቅሯ ጨርቁን መጣሉ፤ በናፍቆቷ መብሠልሠሉ፣ ከእርሷ በመለየቱ ‹‹ቀኑም ጨለማ ሌሊቱም ጨለማ›› የሆነበት መምሠሉ ከኃያል ጭንቀቱ የተፀነሡ ጊዜ አይሽሬ ሙዚቃዎች በግጥምና ዜማ ደራሲዎች እገዛ ለአድናቂዎቹ ጆሮ እንዲደርሱ ምክንያት ሆነ፡፡ አዎ ምናልባትም ከድምፃውያን መካከል የአበበ ተካን ያህል ለፍቅር ታላቅ መስዋዕትነት የከፈለ ያለ አይመስልም፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ህይወትን መለወጥ በጣም ከባድ ነው፡፡ እርሷም ኑሮዋን ለማሻሻል ነው ከሀገር የወጣችው›› የሚለው ትሁቱ አፍቃሪ የተሠበረ ልቡን በዜማ ብቻ እያስታመመ ፍቅረኛው እስከምትመጣ ለመጠበቅ አልወደደም፡፡ እናም እርሷን ፍለጋ ተሠደደ፡፡ ከሀገር ሀገርም ተንከራተተ፡፡ በተጭበረበረ ፓስፖርት በተሠኘ ምክንያትም በአሜሪካ አንድ እስር ቤት ለአምስት ዓመት በእስር አሣለፈ፡፡ ከዚህ ሁሉ መስዋዕትነት በኋላ ምኞቱ ሞልቶ እንደ ዓይኑ ብሌን የሚሳሳላትን ሴት ከእቅፉ አስገባ፤ በትዳር ተጣመሩ፡፡ ልጆችም አፈሩ፡፡ሶስት ጉልቻ ቆመ፡፡

ዛሬ አበበ የወደዳትን ሴት አግብቶ የሞቀ ትዳር ከጀመረ ረጅም ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የሙዚቃው አድናቂዎች ግን የምንወዳቸውን ሌሎች ሥራዎቹን ማግኘት የህልም ያህል ርቆናል፡፡ አበበ ሙዚቃን በትዳሩ ሳይለውጣት አልቀረም፡፡ ለነገሩ የሠው ልጅ እውነተኛ ችሎታ የሚገለጠው በማጣቱ ዘመን ነው ይባላል፡፡ አበበ ፍቅር ያጣ ጊዜ ድንቅ ሙዚቃዎችን ሰርቷል፡፡ ዛሬ ፍቅርን ሲጠግብ ሙዚቃው ቦታ ያጣ ይመስላል፡፡ እንጂማ ሠው እንዴት ከአሥራ አምስት ዓመታት በላይ አድናቂዎቹን ዘንግቶ ይኖራል? ለብዙ አርቲስቶቻችን ያልተመለሠው ‹የአሜሪካ ጅብ›› አበበን ከበላው ረጅም ዓመት አስቆጥሯል፡፡ እነ ‹‹ሠው ጥሩ››፣ እነ ‹‹ወፍዬ››፣ እነ ‹‹ምንድነው ቀለበት›› ተተኪ የማፍራት አቅማቸው መንምኗል፡፡ አዎ አበበ ሙያውን በትዳር ሸጧል፡፡ እንጂማ ከአሥራ አምስት ዓመት በላይ በሆነ ጊዜ እንኳን አንድ አልበም፤ አንዲት ሀገርስ ትሠራ የለም? ታዲያ አበበን ምን ነካው?
የተጣልን ያህል ለሚሠማን አድናቂዎቹ የእርምታህል የለቀቃት ነጠላ ዜማ በቅርቡ በዩቲዩብ ድረገፅ ተጭና እየተመለከትን ነው፡፡ እንደ ማይክል ቦልተን ፍቅርን ጥሩ አድርጎ ለማዜም የተፈጠረ የሚመስል አንደበቱ አሁን ተራውን ለሀገሩ ሰጥቷል፡፡

‹የፍቅር ገዳም የውበት ፍሬ››
ይናፍቀኛል ከአንቺ ማደሬ››
እያለ ያንቆለጳጵሳትም ይዟል፡፡ አበበ የዛሬ እጦቱ ሴት አይደለችም፡፡ ዛሬ ሀገሩን ነው ያጣው፡፡ ፍቅረኛውን ተከትሎ ጥሏት የሄደችው ሀገር ዛሬ የልቡ ሲሞላ ትናፍቀው ጀምራለች፡፡ እናም ውሎ አድሮ በለቀቀው ነጠላ ዜማለ፡-
‹‹ሁሌም ሀገሬን ምድሬን ይለኛል
ሂድ ይለኝና ሆድ ይብሠኛል
አፈር መሬቱም ይናፍቀኛል
ገራገር ህዝቡም ፍቅሩ ይገድለኛል›› እያለ ድለላ የሚመስል ነገር ጀምሯል፡፡

የማለቃቀስ ስልት ባለው በዚህ ዘፈን አበበ ተካ ወደ ሀገሩ እንዳይገባ ማዕቀብ ተጥሎበት ስሞታውን ለሌሎች የሚያሠማ ነው የሚመስለው፡፡ ታዲያ ይህን የድምፃዊውን በቁጭት መብሠልሠል ስመለከት ታዲያ ለምን ወደ ሀገሩ አይመጣም ብዬ ነበር ራሴን የጠየቅኩት፡፡ ለነገሩ ሠው ሀገር ሆኖ ‹‹ሀገሬ ናፈቅሽኝ ልሙትልሽ ልቀበርልሽ›› አይነት ዘፈኖችን ማቀንቀን ሌሎችም ድምፃውያን የበሉበት ሙድ ነው፡፡ አሜሪካ እቅፍ ውስጥ ተቀምጦ ስለ ኢትዮጵያ ‹‹ምድረ ገነትነት›› ማቀንቀን የብዙ ድምፃውያን ልማድ ሆኗል፡፡ አበበ ተካም ገና ወደ ሀገሩ የመመለሱ ደመና እንኳ ሣይታይ
‹‹ይናፍቀኛል መች ያስተኛኛል
ሀገሬን ሀገሬን ይለኛል››
ማለቱ የዚሁ ልክፍት አንድ አካል ነው፡፡ እንጂማ ፍቅረኛውን ፍለጋ ወደ ማያውቃት አሜሪካ የሄደ ሠው የናፈቀውን ህዝብ ፍለጋ ወደ ወጣበት ሀገር መመለስ ባልራቀው ነበር፡፡ ‹‹ያለቃቀሰላትን›› የፍቅር አጋር ዕድለኛ ሆኖ አግኝቷት ሶስት ጎጆ አቁሟል፡፡ ታዲያ መልሶ ላጣት ሀገሩ ‹‹ሌላ ለቅሶ››
ለምን አስፈለገው? ሀገሩ እንደሁ የትም አልሄደችም፡፡ ትላንት ጥሏት የሄደችበት ቦታ ነው ያለችው፡፡ እንዲያውም ከውጪ የሚመጡ ኢትዮጵያውያንን እጅ ስሞ የመቀበል አባዜ ስለተጠናወታት ተንከባክባው ለማኖር አትሠንፍም ነበር፡፡ ታዲያ አበበ ተካ የእውነት ‹‹ሁሌም ሀገሬን ይለኛል›› የሚለን ከልቡ ከሆነ ለምን ወደ ሀገሩ አይመለስም? አንዲትሴት ለመፈለግ ያልሠነፈ ጉልበት እንዴት ሀገርን ያህል የማትጠፋ ግዑዝ አካል መፈለግ ይከብደዋል?

በርግጥ ይሄ የብዙ ድምፃውያኖቻችን ችግር ነው፡፡ ሀገራቸውን ለቅቀው ይወጡናየሌላትን ሁሉ ቅድስና ሠጥተው በዘፈን ያንቆለጳጵሷታል፡፡ ለሀገር የምታስቡ ከሆነ ሆድ የሚያስብስ ዘፈናችሁን ትታችሁ ምናለበት ሆድ የሚሞላ ሥራ ብትሠሩ? የሆነች ገንዘብ አዋጥቶ ኢትዮጵያውያንን የሚረዳ የበጎ አድራጎት ድርጅት ማቋቋምምኮ አንድ መልካም ተግባር ነው፡፡ ለዘፈኑ ከሆነማ ታላላቆቹ ድምፃውያን እነ አልፋ ብሎንዴም ለኢትዮጵያ ዘፍነዋል፡፡ ስለዚህ ‹‹ሀገሬን ሀገሬን ይለኛል›› ማለት ወይ እየሰጡ ወይ እየመጡ ነው እንጂ እንዲሁ ‹‹ሀገሬን ሀገሬን›› ለማለትማ እዚህ ያለነውስ መች አነስን?

በወላይታ አፈናው ቀጥሏል

$
0
0

newsበወላይታ ዞን ተቃዋሚዎች እንዳይንቀሳቀሱ የሚደረገው አፈና ተጠናክሮ መቀጠሉን የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ እንደ ፓርቲው አመራሮች በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎች ተንቀሳቅሰው ለመስራት አለመቻላቸውንና ከፍተኛ ጫና እንደረሰባቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ለአብነት ያህልም በዛሬው እለት ቴዎድሮስ ጌታ የተባለ የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ዳሞቶ ፋላሳ ወደተባለ ወረዳ ለማደራጀት በሚንቀሳቀስበት ወቅት እንደታሰረ ተገልጾአል፡፡

አመራሩ ሶዶ ከሚገኘው የፓርቲው አደረጃጀት በራሪ ወረቀት መመዝገቢያ ቅጾችን ይዞ ሲሄድ ወሎ ዋርዲራ የተባለ ቦታ ላይ ከእሱ ጋር ሲጓዙ ከነበሩ ሌሎች አምስት ጋር መታሰሩ ታውቋል፡፡ ሌሎቹ ሰዎች የፓርቲው አባላት አለመሆናቸው በመታወቁ ሲፈቱ አቶ ቴዎድሮስ በአሁኑ ወቅት ሳንቶ ከተማ ውስጥ ታስሮ እንደሚገኝ ተገልጻል፡፡

በሌላ በኩል በወላይታ የተለያዩ ቦታዎች ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ አለመቻላቸውን አመራሮቹ ገልጸዋል፡፡ የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው አቶ ወጨፎ ታዳሞ ‹‹በሶዶ ከተማ ለበርካታ ጊዜ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ጥረት ብናደርግም አዳራሽ እንዳናገኝ ተከልክለኛል፡፡ ህዝብን ለማደራጀትና ፕሮግራማችን ለማስተማር አልቻልንም፡፡ በወላይታ ያለው አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡›› ብለዋል፡፡

ደብረማርቆስ አዳማ እና ቁጫ ሰኔ አንድ ቀን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ይካሄዱባቸዋል።

$
0
0

አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል ሁለተኛውን ዙር ህዝባዊ ንቅናቄ
በእለተ እሁድ ሰኔ አንድ ቀን 2006 በደብረማርቆስ በአዳማ እና በቁጫ ወረዳ በሰላማዊ ሰልፍ የህዝቡን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ለማሰማት አደባባይ ይወጣል።
ሰላማዊ ሰልፎቹ እንደመጀመሪያው ዙር የሚሊዮኖች ድምጽ … የደመቁ እንድሚሆኑ ሲጠበቅ በከተማው የምትገኙ ነዋሪዎቹምበሰላማዊ ሰልፉ ላይ በመሳተፍ የታፈነ ድምጻችሁን እንድታሰሙ አንድነት ፓርቲ በአክብሮት ጋብዞታል።
ኑና ስለመሬታችን በጋር እንምከር ይላል የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት የሰልፉ አዘጋጅ ።

አንድነት ቅስቀሳውን አፋፍሞታል፤ ፖሊስ 19 አባላትን አስሯል

231
አንድነት ፓርቲ በመጪው ዕሁድ ሰኔ 1 ቀን 2006 በደብረማርቆስ፣ በአዳማ/ናዝሬት እና በቁጫ/ሰላም በር ከተማ የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል ለሚያካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ፤ የቅስቀሳ ስራውን የሚያስተባብሩ ሶስት ቡድኖች ከትላንት ጀምሮ ከዋናው ጽ/ቤት መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡ ዛሬ በቁጫ/ሰላም በር ከተማ የሚደረገውን ቅስቀሳ የሚያስተባብረው ቡድን ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡ በደብረ ማርቆስና በአዳማ የተጠናከረ ቅስቀሳ ከተሰራ በኋላ የፖሊስ የተሟላ የዕውቅና ማስረጃ የያዙት 10 የአንድነትን ደብረ ማርቆስ ላይ እንሁም 9 የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ደግሞ አዳማላይ አስሯል፤ በተጨማሪም የአንድነት ፓርቲ የአዳማ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው አቶ ተስፋዬ ዋቅቶላን ከሌሎች አመራሮችና አባላት ተነጥሎ እንደታሰረም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬‪#‎millionsofvoicesforlandownership‬ ‪#‎Adama‬ ‪#‎Debremarkos‬ ‪#‎Kucha‬

የጎንደር መንፈስ ይጠራል (ክፍል –አራት) ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ጎንር ክፍል – አራት
የጎንደር መንፈስ ይጠራል።
ከሥርጉተ ሥላሴ 05.06.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

Gondor„የበለጠና የከበደ ኃላፊነት እንደሚጠብቀኝ ባውቅም ለእኔ የከበደኝ ግን ከጎንደር ህዝብ መለዬቴ ነው“ጓድ አበበ በዳዳየጎንደር ክ/ ኢሠፓ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ለጂንካ የክ/ ኢሠፓ አንደኛ ጸሐፊ ሆነው ሲሄዱ መሸኛቸው ላይ የተናገሩት ነበር። የጎንደር አቀራረብና የአያያዝ ሙያው ከውስጥና በመሆን ሰንደቅ የከበረ ነው። ጎንደር ኖሮ መለዬት ትዝታዎቹ በቀላሉ ሊፋቁ የማይችሉ፤ እንዲያውም ትውስታዎች እያመረባቸውና ወዘናቸው እዬፈካ በናፍቆት አሳምረው የሚያሹ፤ በራሳቸው ጊዜ በመንፈስ ቤተኛ መሆን የሚችሉ፤ ተመክሮን ያስመቹና ያሰበሉ የመልካምነት ማሳ ናቸው።

የማከብራችሁና የምናፍቅቻሁ የሀገሬ ልጆች ጹሑፉ ተከታታይ ይሆን ዘንድ ክፍል ሦስት ማጠቃለያው እንዲህ ይል ነበር።  — ሌላው ቀርቶ የታሪካችን አካል የሆነው የግራኝ መሐመድ እረፍት እኮ ጎንደር ነበር። ደንቢያ ላይ የግራኝ በር ይባላል። በነገራችን ላይ በዛ ዘመን የትግራዩ እንደርታና የጎንደሩ ደንቢያ በከንቲባ የሚተዳደሩ ዕውቅና የነበራቸው ከተሞች ነበሩ። ዛሬ ግን የእንደርታን ባላውቅም፤ አይደለም ደንቢያ ጎንደር አንዲት መንደር ናት በጨለማው ዘመነ በወያኔ – የታሪክ ረግረግ። ታሪክ ማለት እንደ ሥርጉተ ዕይታ – የህዝብ ወላዊ አዎንታዊና አሉታዊ አምክኖዊ፣ ክስተታዊ ክንውኖች ዕደሜ ጠገብ ሲሆኑ ታሪክ ይባላል። ይህን መክፈል ወይንም እንደ ዶሮ መበለት አይቻልም። ታሪክ ከአንገት በላይና በታች፤ ወይንም ሲሶና እርቦ ተብሎ ሊከፈል ከቶውንም አይችልም። አሉታዊም ሆነ አዎንታዊው ክንውኖች ለታሪክ ወጥ ገፀ – ባህሪው ወይንም ሙሉ ቁመናና መልኩ ነው፤ ታሪክ የትርጉም ሥራ አይደለምና።

ጎንደር ክፍል አራት ማጠቃለያ።

እንደ መግቢያ በር —- ድርጊት በድርጊት ላይ እዬተባ ውጤት ላይ ሲውል በዚያ ስሜት ውስጥ እራስን ማዬትና መመዘን የተገባ ነው። ሃሳብን አዞ ሃቅን በምልሰት በማሰማራት ለህሊና ችሎት ማብቃት የተገባ ትውልዳዊ ድርሻ ይመስለኛል። አንድ የጥበብ ሰው ገጠመኞቹን ገልቦ ወይንም ጨልፎ አላዬሁም አልሰማሁም ማለት አይችልም። ይህን ካደረገ እሱ በመኖር ውስጥ እዬኖረ ሳይሆን መኖር እሱን እዬኖረበት ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ ክስተታዊ ሁነቶች የታላቁን ሰብዕና ጸጋ እንዲጋፉ ፈቅዷል ማለት ይሆናል። ህም! እራስን ይግባኝ አልባ መደፍጠጥ። በተለይም የጥበብ ቤተኛ የማህበረሰቡን ህይወት እንደዋዛ ሳይሆን በጥንቃቄ ያሰተውለው ዘንድ የከያኒነት ገመናው ግድ እንደሚለው አውቆ፤ የህይወቱን ልምድ ለማበልጸግ፤ ያለውንም ለማካፈል መትጋት ከጥበብ ፍቅሩ ተግባር የመጀመሪያው ሊያደርገው ይገባል። አንድ ጸሐፊ ዛሬን ተሻግሮ ትናትንም መኖር አለበት፤ ትናንት የኖረበት ማህበራዊ እውነት ውበት ነውና። ውበት ያለ እውነት፤ እውነት ያለ ውበት አይኖርም። ውበትን ካለ እውነት እውነትን ካለ ውበት ማሰብ የቃር አቸቶ ነው እልለሁ – እኔው።

የጎንደር መንፈስ አሳምሮ ይጠራል።

„ ቡልጋ በሚባለው አገር ይቀመጡ የነበሩ ህዝቦች በ484 ዓ.ም ጥር 11 ቀን በአለ ጥምቀትን ለማክበር ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች ካህናቱ በማኃሌት፤ ጨዋው በዘፈን ሲወዛወዙ ሰዐተ ቅዳሴው አለፈባቸው። በዚህ ጊዜ አንድ ባህታዊ ድንገት ደርሶ ቅዳሴውን ከእግዚአብሄር የታዘዙ ግሁሳን ቀድሰውታል በናንተ ግን ማት ታዞባችኋልና መዳኃኒተ ነፍሳችሁን ፈልጉ ብሎ ስለነገራቸው፤ ምን ብናደርግ ይምረን ይሆን  ብለው ጠዬቁት። እሱም እዬሩሳሌም ሄዳችሁ የጌታችን መቃብር ብትሰሙ ይቅር ይላችኋል አላቸው። እነሱም ወደ ቤታቸው ሳይመለሱ ታቦታቸውን እንደያዙ ለቅን አሳብ ወደ እዬሩሳሌም ለመሄድ ጉዞዋቸውን ቀጥለው ሲሄዱ የእነሱን መሄድ የሰሙ ባጠገባቸው ያሉት ህዝቦች ሁሉ ተከተሏቸው ። “  ዬእግዚአብሄር መንፈስ መንገዱን እንዴት ቀዬሰላቸው? „ መንገዳቸው በቀጥታ ወደ ስሜን የነበረውን ትቶ ወደ ስሜን እዬመራ ጎንደር አድርጎ ስቋር አደረሳቸው። በዓፄ አላሜዳ ቀዳሜ መንግሥት በ485 ዓ.ም መጋቢት 27 ቀን አብርንታት ደረሱ። ከአማራ ሳይንት ጀምሮ ያለፉባቸውን ቦታዎች ሁሉ ሥም እዬሠጡ ነበር የተጓዙት።“  (ገጽ 38 – 39)*  „ እነዚህ አቨው ሥርዓተ ገዳሙን ጠብቀው 278 ዘመን ከቆዩ በኋላ በ852 ዓ.ም ጉዲት በሰይፍ አስፈጃጃቸውና የጉዲት ዘመነ መንግሥት አልፎ አንበሳ ውደም እስኪነግሥ ድረስ በስውር ካሉት ግሑሳን በቀር በቦታው በግልጽ የሚታዩ መነኮሳት አልነበሩም። እግዚአብሄር በቸርነቱ ብዛት የጉዲትን ዘመነ መንግሥት አሳልፎ አንበሳ ውደምን በአባቱ ዙፋን ባስቀመጠው ጊዜ በ891 ዓ.ም ከሽዋ400መናኞች መጥተው ተሰውረው ከቆዩት ከፊተኞች አቨው ምንኩስናን ተቀብለው ተቀመጡ። እነዚህ 400 መናኞች ገዳሙን አጽንተው የመጣውን እያመነኮሱ እነሱ ሲያልፉ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸውን እዬተተኩ 389 ዓመት ያለሁከት በሰላም ከኖሩ በኋላ በ1277 ዓ.ም በዐፄ አግባ ጽዮን ዘመነ መንግሥት ገዳሙ ጠፋ። 40 ዘመን ጠፍ ሆኖ ከቆዬ በኋላ በ1319 ዓ.ም በአንደኛው አምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት ሳሙኤል ዘዋልድባ ወይም ዘገዳመ ዋሊ የተባሉት አቡነ ሳሙኤል መጥተው ገብተው ጠፍቶ የነበረውን ገዳም አቋቁመው 70 ዓምት በገዳሙ ቆይተው በ1389 ዓ.ም በዚሁ ገዳም አረፉ።“ (ገጽ 43)* የማክበርችሁ መግቢያው ላይ በርካታ ዝርዝር ታሪኮችን ዘልያለሁ። እንዳይበዛባችሁ በማሰብ፤ የተወሰነውን ከፊል ክፍል በቀደመው የጸጋዬ ራዲዮ በ2013 አርኬቡ ላይ ትረካው ስላለ ወደ ኋላ ሄዳችሁ የ2013ን በቅደም ተከተል ታገኙታላችሁ። ዋናውመሰረታዊ ሃሳብ ግን ጎንደር ወገኖቹን እቅፍ ድግፍ አድርጎ፤ ጸጋቸውን አክብሮ፤ አባትነታቸውን ከልብ ተቀብሎ፤ ቤተክርስትያን በስማቸው አስቀርፆ ገዳምትን በስማቸው ሰይሞ መኖር ተፈጥሮው ብቻም ሳይሆን የኖረበት መክሊቱ ስለመሆኑ ለማጠዬቅ ነው።

ከገዳመ ዋልድባ ሳልወጣ ማህበረ ምእመናን መጋቢት 27 ማዬ ዮርዳኖስ በዓል ለማክበር ከዬትም የሀገራችን ክፍል ሲመጡ፤ በተጨማሪም ቀብራቸው ከዛ ቅዱስ ቦታ እንዲሆን የወሰኑ ወገኖች እሬሳ ይዘው ሲያልፉ የሚደረገውን ተልምዶዊ ባህል ሊቁ ጸሐፊ አቶ በሪሁን ከበደ እንዲህ ገልጸውታል። „ አባቴ ግራዝማች አስናቀው አበራ ይኖሩ የነበረው ወደ ገዳሙ በሚወስደው መንገድ ዳር ምዝክር አቦ ከተባለው ቦታ ላይ ስለሆነ 3ጋን ጠላ 3 እንቅብ ቆሎ ተዘጋጅቶ ማንም ሰው አስከሬን ይዞ ለቀብር ወደ ገዳሙ ሲያልፍ ይቀርብለታል። እንዲህ የሚደረገው በሳምንት አንድ ቀን ወይንም በወር ሁለት ቀን ሳይሆን ለምሳሌ በ30 ቀን 30 ሬሳ ወደ ገዳሙ ቢያልፍ ለ30ው ቀን ሁሉ የተደገስው ድግስ ያለማቆራጥ ይቀርባል። በዚህ መልክ 25 አምት አገልግለዋል። ምስክሩም ገዳሙና የጠለምት ህዝብ ነው። አባቴ ሲያልፉም ወንድሜ በቦታው ተከትክቶ ተግቶ ይከውናል“ (ገጽ 98 – 99)* ከገዳሙ በእጅ የተጻፈላቸው የምስጋና ደብዳቤም መጸሐፉ ውስጥ ተያይዟል። ለክብረ በዐል የሚመጣውም በሚደርስበት ቦታ ሁሉ ማህበረሰቡ እዬተነጠፈ እዬተጎዘጎዘ ፍቅር በሩን ከፍቶ ይጠብቀዋል።

ክብረቶቼ – ጎንደር እኮ ጥሩ ሰው፣ መልካም ሥነ – ምግባር ያለው እኮ ታጭቶ ነው የሚገባው። ሊቃናት ልቅናቸውን በሚያገኙበት የቅኔ የንባብ የእድምታ የሚስጥራት አብነት ት/ ቤቶች የቆሎ ተማሪዎች ውስጥ አራት ዓይናማዎችን ጎንደር ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ዝም ብሎ አይሸኛቸውም። ሞኝ አይደለም። መምህሩ ሴት የደረሰች ካላቸው የራሳቸውን፣ በስተቀር የቅርብ ዘመድ ተፈልጎ ይህም ሳይሳካ ቢቀር ከሀገሬው ቆንጆ ልጅ ተምርጣ፤ ያ ሙሑር በጋብቻ ታስሮ እንዲቀር ይደረጋል። ይህ ለጎንደር ክህሎቱ ነው – ልዩ ሥጦታው። ታናሼ ተክሌሻ በ2010 በሁለት ክፍል የጻፈው ነበር። ጹሑፉን ሳነብ እስቅበት ነበር …. ምክንያቱም ልጥፍ ግምት ስለነበረ። ሊቃውንት አያቶቼ ቁጭ አድርገው የቆሎ ተማሪነት ጊዜያቸውን እንደ ትልቅ ይነግሩኝ ነበር። ሰፊ ቤተሰብ ውስጥ ለእኔ የተለዬ አያያዝ ነበረኝ። አባቴ እራሱ ሲያሳድገኝ አሳ ዘይት እያጠጣ ነበር። አሁን እኔ ሙሉ ዕድሜ ላይ ነኝ – ምን ያህል የቀደመ ህዝብ ነው – እሰቡት።

ጎንደርና አብነቱ – በጥቂቱ፡

በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ የደረሰው ግፍና መከራ ከቦታው የነበሩ ወገኖች አሉበት። እኔ መግለጽ የምፈልገው ባለቤት ያልነበረው፤ ከእሳት ወጥቶ ቋያ ውስጥ ዬተርመጠመጠው ዬኢትዮጵያ ሠራዊት ሲበተን በለስ በቀናው አኳኋን ተጉዟል። ወደ ጎንደር አቅጣጫ የተጓዙት ወገኖች በምን ሁኔታ ማህበረሰቡ ተቀበላቸው የሚለውን ተከድኖ የተቀመጠ የድርጊት ልዩ ጸጋ መተንፈሻ እስኪ ይሠራለት በማለት ነው።

የሠራዊታችን አባላት ከጎንደር ደንበር ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ህዝቡ በተለዬ ሲቃ በክብር ነበር የተቀበላቸው። አብሶ ወደ ጎንደር ከተማ እዬቀረቡ ሲመጡ የጎንደር ከተማ ህዝብ ከ20 እስከ 30 ኪ.ሜ  እስከ ኮሶዬ ድረስ ተጉዞ ነበር ድንኳን እዬጣለ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ያደረገላቸው። ሁላችሁም እንደምታውቁት በርሃ – ለበርሃ ለረጅም ጊዜ ካለቅያሬ ልብስ ሲከላተም የቆዬ ወገን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚሆን እሰቡት። በመንፈሱ የመሸነፍ – ድቀቱ፤ እልሁ፤  የመስዋዕትነቱ ዋጋ አልባነት፤ የትዳሩ – የቤቱ – የጎጆው – የወጣትነቱ መስዋዕትነትና አዝመራው – ከንቱነት፤ መግቢያ ቤቱም የሚጠብቀው የተቆለፈ የቋሳ ክምችት ሁለመናው ውልቅልቅ ያደረገው የተጎሳቆለ አካል ነበር።

በዚያ የመከራ፤ በዚያ የፈተና ጊዜ ግን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ወገኖቻቸው በመደገፍ፤ በሙሉ አለንላችሁ በማለት፤ መንፈስን በማጽናናት ነበር የተቀበሏቸው። እያንዳንዱ ነዋሪ በነፍስ ወከፍ እስከ 10 የሠራዊቱ አባላት ነበር እየተቀበለ ያሰነበተ። ኑሮው እራሱ ምስቅልቅል ባላበት፤ የራስን ቤተሰብ ለማስተዳደር በተበተነ ሃሳብ በሚባዘንብት፤ ሰላሙ ባልተረጋጋበት ሁኔታ በርሃ የከረመን ጎስቋላ እንግዳን ችሎ ማስተናገድ ከፈተና በላይ ውሃ ያዘለ ተራራ የመሸከም ያህል ነበር። ነገር ግን ጎንደር ተወጣው። ከእኔ ከወላጅ እናቴ ቤት አባትዬው በአባት ጦር፤ ልጅዬው በመደበኛ የሄዱ አባትና ልጁ በተለያዬ አቅጣጫ ተጉዘው እዛው ከእናቴ ቤት ተገናኙ። የልጁ እናት፣ የአባወራው ባለቤት ከአዋሳ ድረስ መጥተው ቤተሰቡን ተዋውቀው መልካም ቀጣይ ግንኙነትም መስርተው በፍቅር ተሰነባብተዋል። ይህ ዘመኑና ታሪክ የፈጠረውን ወላዊነት ኢትዮጵያዊነትን አብዝቶ ያዘመረ የተባ የተግባር ዓዕምድ ዓውድም ነው – እንዳሻው እዬተደፈጠጠ የሚደመጠው።

እንግዳ መጥቶ ወደ ቤቱ ለመሄድ ሲነሳ ጎንደር ላይ አስተናጋጆች በሙሉ ሊሸኙት አብረው ይወጣሉ። ከሊቅ አስከ ደቂቅ፤ ሲወጡ ቤታቸውን ከፍተው ነው። አንዳንድ ጊዜ እንግዳውን ከቤቱ አድርሶ መመለስ አለ። ለዚህም ነው „ሲሻኛኙ አደሩ“ የሚል ብሂል የኖረው። ከተማ ላይ አስፓልቱ ሞልቶ ለአንድ እንግዳ መላ ቤተሰቡ ወጥቶ ይሸኛል። ገጠር ላይ ወንዝ አሻግሮ ነው የሚመለሰው እንግዳ አሰንባቹ። ከእንግዳ ጋር ለመለዬት በጊዜያዊነት እንኳን ፍቅሩ ማህተም ነው። ከዚህ ጋር አንድ በኽረ ጉዳይ ላንሳ። ሻብያና ወያኔ ኢትዮጵያን የማፍረስ የጫጉላ ጊዜያቸውን ዕርገት የተከወነው ኤርትራውያኑን ንብረት አልባ በመመለስ ነበር። ሁሉንም መከራ የኢትዮጵያ ህዝብ በትዝብት አይቶ ቀን ሲሾልክ ግን፤ ንብረታቸውን ተረክቦ በተገኘው መገናኛ ሁሉ እዬሸጠ እዬላከላቸው ነው። ጎንደር ያኖሩበት የሚገኝበት፤ በማተቡብም የጠና ነው የሚባለውም እንዲህ መሰል ፈተና ሲገጥም ግራ ቀኙን አስቀምጦ ፈርኃ እግዚአብሄር ያለው ተግባር ስለሚከውን ነው። ወገኖቼ ተረት ተረት አይደለም የምናግራችሁ የሆነውና የተደረገውን ነው። ቂም ዕዳ ነው – እዳነቱ ደግሞ የነፍስ ነው ብሎ ማህበረሰቡ በጽኑ ያምናል። አሁን ወያኔ ይህን ያህል ቀጥቅጦ እዬገዛ ነው። ቢሰናበትም ጎንደር እንደ ተፍጥሮው ይቀጥላል። አብሮ መብላትና መጠጣት፤ አብሮ መኖርና ሃዘን ተፍሥኃውን መጋራት ሃይማኖት ነው ብሎ ያምናል – ጎንደር።

የጎንደር ያልመከነ መከራው – በጥቂቱ።

እኔ የማውቃቸውን ጥቂት ነገር ልብል። ትግራይን ብቻ አይደለም የደርግ መንግሥት ዬለቀቀው። ሰቲት ሁመራንና አብደራፊንም ጭምር ነበር። ሲለቀቅ የፓርቲው አካላትም አብረው ከህዝቡ ጋር እንዲለቁ ነበር የተወሰነው። ለእነሱ ለብቻ መጓጓዣ አልተላከም ነበር። የሰቲት ወረዳ ኢሠፓ የሥ/አ/ኮሜቴ አባል የሆነ ወጣት አንድ ጹሑፍ ስለ ጉዞው ጽፎ ነበር። ንዑስ እርእሱ „የጎተተኝ“ ይል ነበር። „አንዲት አራስ አብራን ትጎዝ ነበር። አቅም አንሷት ስለነበር ወደ ኋላ ነበረች። ውሃ ጥማቱ መካራ ስለነበር አራስ ልጇን ከግራር ሥር አድርጋ ውሃ ልትጠጣ ሄደች። ስትመልስ አራስ ልጇ አልነበረም። በጣም ስትጮኽ ወደ ኋላ ተመልሰን አገኘናት። የሆነውን ነገረችን። ያለን ምርጫ ወደ ፊት መሄድ ስለነበርን አብራን እንድትመጣ ነገርናት። በርሃ ነው የሚያቃጥል – ቋያ። እሷ ግን አሻም አለች። ልጄን ትቼ አልሄድም አለችን። አራሱ ህፃን የለም አንቺ ከእኛ ጋር ነይ ብለን በዛለ አቅማችን ለመናት። ግን አልቻለችም። አስገድደን ተሸክመን ለመጓዝ እሷን፣ እኛም አቅማችን እዬሟሸሸ ነበር – አልቻልነም። ትናነት መጣን፤ እኔ ብመጣም ግን ወደ ኋላ የሚጎተኝኝን ትቼ ነው። ዓይኗ መከራውን አያይም ነበር። ልጇን ፍለጋ ይማስን ነበር እንጂ። ምንግዜም ጸጸቴ ነው“ ይል ነበር ጸሐፊው። ይህ መከራ በወሎም እንደተፈጸመ አስባለሁ። አሁን የሚያስፈልጉን መሪዎች ይህን የመከራ ጊዜ መርምረው የሚችሉትን ለማድረግ ሰብአዊነት የሚመራቸውን ነው። መንግሥት ህዝብን ከቦታ ሲያስለቅቅ የሚደርሰው ሰቀቀን መከራ በቃላት መንዝሮ ለመግለጽ አይቻለም። ተርፈው የመጡትስ? ይህም ሌላ ጥያቄ ነው።

በተፋፋመ ውጊያ ላይ እያለን ጎንደር የነበሩ የሠራዊቱ ማዕከሎች ተነቅለው ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ተደረገ። የጨለማ – ደባ ነበር። የነበረው ምርጫ በሀገሬው ሃይልን አጠናክሮ መቀጠል ነበር። እርግጥ ሠራዊት ከማዕከል ለማምጣት አንድ እድል ነበር፤ ዳኮታ የሚያሰርፍ ቦታ ማዘጋጀት። ለዛ ደግሞ አዬር ማረፊያውው አይችልም ነበር። ስለዚህ ነዋሪው ጊዜያዊ መጠለያ ተሰርቶለት በፍጥነት የዳኮታ ማረፊያ ማሰራት ነበር። ነዋሪው በድንገት አፈር ለብሶ በዘመቻ በሚሠራለት ጊዜያዊ መጠለያ መጠለል ግድ ሆነ። ፈቃድም – ንግግር የለም። ከዛው እዬታደረ ያለ የሌለው ሃይል ሁሉ ተሰማራ ለድርብ ግዳጅ። ዳኮታ የሚያሳርፍ ጊዜያዊ አውሮፕላን ማረፊያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሰናዳ። እኔ የአንድ ኮሜቴ ሰብሳቢ ነበርኩኝ። አንድ እድል ብቻ ነበር። ምን እንደተላከ ታውቃላችሁ። ዳኮታው እንደተነሳ የራዲዮ መልእክቱ ስንቅ እንደተላከ ነበር መርዶው። ስንቁን እኮ የጎንደር ህዝብ ያቀርብ ነበር። የተፈለገው ሠራዊት ነበር። ብቻችን ነበርን። ደንቀዝ ላይ የሚለቀቀው የጠላት ከባድ መሳሪያ በቀጥታ አውሮፕላን ማረፊያውን ዒላማ ያደረገ ነበር። ከዚያ በኋላ ዳኮታውን ማሳረፍ አልተቻለም።

ያ ንጹህ የአዬር ማረፊያ ኗሪ የጦርነት ጊዜ ስለነበረ ካለ ካሳ ህፃነት – ሽማግሌ – የታመመ – በቃሬዛ፤  ነፍሰጡር ሁሉም ቤታቸው ፈርሶ ሜዳ ላይ እያሉ ወያኔ ገባ። ….. ባለቤት የሌለው ህዝብ በቀን ወደ 20 ቆርቆሮ ማልበስና የመጀመሪያ ምርጊቱን ማጠናቀቅ ነበር ዘመቻው፤ ባዶ ግድግዳ እንደቆመ፤ ወይንም ቆርቆሮ ሳይለብስ በቃ እንደተበተነ ሁሉም ተበተነ። ያ መከረኛ ህዝብ በግራ በቀኝ ተማገደ። በደልጊ በደንቢያ ዞን ክፍት ነፃ መሬት ነበር። የተንጣለለ ቦታም ነበር – አዬር ወለድ ለማምጣት እሱንም ቁብ የሰጠው የበላይ አካል አልነበረም። ለዛውም በደንቢያ በኩል የማልናገረው የተሻለ ሁኔታ ነበር …. አልሆነም። በኢዲዩም፤ በኢህአፓም፤ በደርግም፤ በወያኔም ዛሬም በአርበኛ ያው ቦታው በጦርነት ቀጠናነት ይማገዳል። ከዚህ ሌላ ወያኔ መሽጓል የሚል የተሳሳተ መረጃ እዬተሰጠ ያለቀ መንደር እናቱ ትቁጠረው ….. መናገር የቻለ ሁሉ ደግሞ እስካሰኘው ድረስ ይወቃዋል።

በጦርነቱ ጊዜ በሰማይ የመንግሥት በምድር የወያኔ መሳሪያ ከጫፍ አስከ ጫፍ ገበሬ – መንደር – እርሻ – የተፈጥሮ ሃብት – ነደደ – ተቃጠለ – ተርመጠመጠ። የሰውን ልጅን እራስ ውሻ …. እም ነው! ይህንን የገዘፈ መከራ ይፍታኃ ዬሚል  ቅዱስ መንፈስ መፍጠር የትግሉ መሰረታዊ መንገድ ይመስለኛል።

እንቡጢጣ -ማከያ ። ሻ/ ገብረህይወት የሚባሉ የደርግ አባል ነበሩ። የስሜን አውራጃ አስተዳደሪ ነበሩ። ከመንግሥት መዋቅር ህግና ደንብ ውጪ አስተዳደሪ ያላቸው አውራጃዎች የበላይ ሆነው እንዲያሰተዳድሩ በተሾሙበት ጊዜ፤ ጌታ አልነበራቸውም። ለአሰሳ ሲወጡ ጥቃት የሚሰነዘርበት ኢህአፓ ብቻ ነበር። ለወያኔ ግን አልጋ ባልጋ ነበር። ሹመታቸው ለስሜን – ለጭልጋና – ለወገራ አውራጃዎች ነበር። የሦስቱም አውራጃ ገበሬዎች ሰፊ ቅጣት ነበራቸው። እኔ የማውቀውን ልናገር። ባለፈው ጊዜ ጋዜጠኛ አብርኃም ደስታ ጮንጮቅ ላይ ወያኔ ያደረስውን መከራ ዘግቦ ነበር። እጅግ አመሰግነዋለሁ። ጮንጮቅ በጭልጋ አውራጃ የሚገኝ የምክትል ወረዳ ዋና የገጠር ትንሽዬ ከተማ ናት። 5 ቆርቆሮ ቤቶችና ሌሎች ግን በርካታ ጎጆ ቤቶች ነበሯት። በእግር ከጭልጋ ከተማ 4 ሰዓት ለኮበሌ ነው።  ከዛ የመጡ ገበሬዎች ልጆቻቸውን ይዘው አንድ ቀን እንዲህ አሉኝ „ እሙሃይ ነበር የሚሉኝ፤ እሙኃይ ሁሉን ለገብርህይወት ሰጠን አሁን ሁሉንም ጨረስን፤ የቀሩን ልጆቻችን ነውና ተምኖ ይውሰዳቸው“ አዎን በዬገብያው የሴት ቀሚስ እዬለበሰ የሚንጠለጠለው እጅግ በርካታ ገበሬ ነበር። ሦስት ጓደኞሞች ዘመቻ ጀመርን። አልቻልነም ይህን ተሸክሞ መኖር። ዘመቻችን ጭልጋ አውራጃ ሰላማዊ አስተዳደሪ ስላለው በእራሱ አስተዳደር ይመራ ነበር ፍሬ ነገሩ። ሻ/ ገብረሕይወት ይነሳ ነበር ጉልበታሙ አድማ።

በዛው ሰሞን ሻ/ ገብረህይወት የጭልጋን ህዝባዊ ድርጅቶች ቢሮ ገንዘብ ልመና ወጣቶችን ሰብስቦ ወደ ጎነድር ይዘውን ሄዱ። ቋራ ከሚባል የመንግሥት ሆቴል „ምግቡ በቅደም ተከተል ይቀርብ ነበር“ ለእኔ የቀረበውን አልበላሁም። የወጣልኝ ደፋር ነበርኩ። ብይ ስባል ደም አልበላም አልኩኝ። በህይወት ያሉት ይመሰክራሉ። በጥርስ የገባሁበት ቀንም ነበር። በቃ እኔ ብቻ ነበርኩኝ ያልበላሁት። ደግሞም ልክ ነበርኩ ጽዕዱ መሆን የልብ ያደርሳል – እንደ ልብም እንዲህ ያናግራል። አንዱ የሰከነው ጓዴ በህይወት የለም ኬኒያ ላይ አልፏል። ጓድ ዬኋንስ የኋላ ይባል ነበር። እንዳንታፈን ሻ/ ገብረህይወት ከመምጣታቸው በፊት መረጃ ለሦስታችንም ይሰጠን ነበር። ወጥተን እንድናድር፤ በኋላ ብልሁ ጓድ ገ/መድህን በርጋ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊና ጓድ ወንደወስን ኃይሉ የርዕዮተ ዓለም ጉዳይ ኃላፊ የወቅቱ የፓርቲው አደራጆች ሁለታችን የካቲት 66 ፓለቲካ ኢንስትቲዩት አንዱን ጀርመን ሀገር ላኩት። ከትምህርት በኋላ ወደ ጎንደር እንዳልመለስም የተደረገው ምክንያትም በዚህ ነበር። ጥሩ እድል ነበር አርሲን ዬመሰለ ሀገር፤ ያን ፍቅር የሆነ የጢቾ አውራጃ ህዝብ ጋር እንድሰራ አጋጣሚ አገኘሁ። በተጨማሪም ጓድ ስለሺ መንገሻን የመሰለ ለስላሳ – ሥልጡን – ፈጣን የአርሲ ክ/ ኢሠፓ ኮሜቴ ተጠሪ ለማዬት በቃሁ። በእውነት የተለዩ ነበር። እሳቸውን የሚያጅብ አንድም ስፔሻል የሚባል አልነበረም። እንዲያውም ተንጠልጥለው „አንተ“ ነበር የሚባሉት።  ጠባቂያቸው ህዝቡ ነበር። እሳቸውም ወጣት ነበሩ። ከወጣቶች ጋር ኳስ የሚጫወቱ፣ ሙዚቃ መኪና ውስጥ የሚያዜሙ ነበሩ። ልጅ ስለነበርኩ ናፍቆቱን ስላልቻልኩ ብቻ በለቅሶ በሃዘን በዬቦታው ልዩ ዝግጅት ተደርጎልኝ ተሸልሜ ወደ ጎንደር ተመልስኩኝ። ዕድለኛ ወጣት ነበርኩኝ። ሁሉም የሚሳሳልኝ።

እንዲህ ሆነላችሁ — ሻ/ ገብረህይወትም  ከሰቲት ሁመራ ወደ ጎንደር በጦር ኤሊኮፍተር ሲበሩ ሰማይ ላይ አመድ ሆኑ – በሁለት ቢላዋ እንደበሉ ነደዱ። ሬሳቸው እራሱ አልተገኘም። የጭልጋ፤ የወገራ፤ የስሜን አውርጃ ህዝብ አረፈ – ተገላገለ ከሃሞራቢ የቋሳ ሽምቅ ቅጣት – ተመስገን! ምንም እንኳን ዛሬም መከራው ተግ ባይልም።

እርገት ይሁን። ግለሰብ ጥፋት ወንጀል ሊፈጽም ይችላል። አጥፊውን ነጥሎ መውቀስ መንቀስ ይቻላል። የአካባቢው ህዝብና የአለም ውርስና ቅርሶች ያሉበትን የታሪክ ማህደርን ግን ግፍ ነው። ትውፊቱ ህዝቡ ቅርሱ የመንፈስ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል። ጎንደር በዚህ ዘመን እልፈቴ ነበር ብሎ የሚናገረው የሰላም ጊዜ ታሪክ የለውም። ይህም ሆኖ ባህሉን፤ ልማዱን፤ ወጉን፣ ትውፊቱን፤ ታሪኩን፤ እምነቱን ጠብቆ የኖረ ህዝብ ነው። „በሚስትና በሀገር ቀልድ የለም“ እዬተባለ ያደገ ስለሆነ ትንፋሹ ድፍረት፤ ትጥቁ ጽናት የሆነ። በማተቡ አዳሪ። ለቃሉ ተገዢ። አደራ አውጪ። ፍቅሩ ጽኑ የሆነ ህዝብ የመብቱ ዳር ድንበር ሊከበርለት እንደሚገባ በአጽህኖት እያሳሰብኩ ጹሑፌን እደምድማለሁ።

የእኔ ክብሮች ትእግስታችሁን ሳተሰስቱ ሸልማችሁ አብረን በአንድ መሰረታዊ ጉዳይ ዙሪያ ሰነበትን። እግዚአብሄር ያኑርልኝ። አምላኬ ይጠብቅልኝ። የ05.06.2014 የጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራሜ ዘና ያለ ናፍቆትን ብቻ ያጫወተ፤ የመግቢያ ትውውቁ – የዝግጅቱ ሆድ ዕቃ፤ ስንበቱን አክሎ በሥነ ግጥም ነበር። ትንሽ ግር እንዳይላችሁ እንደዚህም ዓይነት መንገዶችም መለመድ አለበት ነው ቁም ነገሩ። ኩምትርትር ያለ መንፈስ አስቲ በአመት አንዲት ሰዓት እንኳን የእርፍት ቀን ሊኖረው ይገባል ብሎ  የአብርኃሙ የጸጋዬ መሠሪያ የሥነ ግጥም ቀን ነበረው Tsegaye Radio Lora Aktuell Sendungen ብላችሁ ለጉግል ነፍሱ ስትነግሩት፤ ወይንም በቀጣዩ ሊንክ አምጣልን ብላችሁ ስታዙት ይዞ ከች ቀልጣፋው።  www.tsegaye.ethio.info ነገ ፓስት ያድርጉታል፤ ጊዜው ሲኖራችሁ ጎራ በሉ …. ደግሞ በቀጣዩ ለምለም ዝግኗን እንደትጠብቅ ….. ቸር ያገናኘን።

የቀደሙት ሊንኮች ….

ክፍል አንድ http://en.wikipedia.org/wiki/User:Aatebeje

ክፍል ሁለት http://www.zehabesha.com/amharic/archives/30526#respond

ጎንደር ክፍል ሦስት http://www.zehabesha.com/amharic/archives/30763

  • ኮከብ ያለባቸው አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ መጸሐፍ በሊቁ ጸሐፊ ከአቶ በሪሁን ከበደ የተወሰደ ሲሆን፤ መጸሐፉም ተሽጦም ገቢ የሆነው  ለአብረንታት ዋልድባ ገዳም ነው።
  • ዓ.ምህረቱ በግእዝ ስለሆነ ብዙ ነገር ስለረሳሁ ግድፈት ካለ ይቅርታ ዝቅ ብዬ ሎሌያችሁ እጠይቃለሁ።
  • ግሑሳን – በአይን ማይታዩ የተሰወሩ ግን ለአግልግሎት በቋሚነት የተሰማሩ ንዑዳን፤

 

ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር ኢትዮጵያዊነት።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

Ethiopian-American author Dinaw Mengestu and the aura of estrangemen

$
0
0

Hannah Black
June 5, 2014 

 

140609417The Ethiopian-American author Dinaw Mengestu’s third novel, All Our Names [Amazon.com], tells the story of Isaac, a name stretched to fit not one but two characters whose lives unfold in alternating narratives. In one of these narratives (Isaac), two men form a close friendship in Kampala during a coup, and in the other (Helen), set a year or two later, one of them attempts a love affair with an American woman in a small town in the Midwest. 

 

In the Isaac narrative, we are guided around the revolutionary foment of Amin-era 1970s Kampala by a young man who will eventually take the name of his best friend Isaac when he leaves Uganda for the US. He is a foreigner in Kampala, recently arrived from Ethiopia with ambitions to become a university student and a writer. Over the novel’s first few pages, Mengestu gradually draws out the revelation that even the first of these dreams is impossibly unrealistic.

 

Mired in poverty, neither of the two friends has the means to do more than spectate at the edges of a college scene that is already a palimpsest of imitations. Real and aspiring students alike model themselves on famous figures. The narrator cannot afford even this imitation, but there is some comfort, in this novel, in the fact that imitations are all there is to be had. The dreams of the immediate aftermath of colonialism are turning sour and in the new postcolonial mode, students imitate revolutionaries, the state imitates a state and the narrator simply follows his friend around as he lives out his fantasies.

 

Helen’s town, where she and the man she knows as Isaac meet after he leaves Uganda, is also freighted with unreality. The location is obviously intended to convey the purest essence of Middle America, so much so that the character herself often refers to “the rural mid-west” in a way that could reflect not just the structural needs of the novel but a not-implausible self-­consciousness about her origins. Her relationship with Isaac gives her a new vision of herself, as if from outside; she reflects on how her life would have been had he not arrived, as if this unlived life remains palpable to her. Mengestu sketches out the love affair between Helen and Isaac with the same hazy mix of broad strokes and sharply rendered detail that characterises the Kampala scenes.

 

In Mengestu’s Uganda, everything is constantly, violently changing, so much so that specific events blur and lose distinction. There are struggles to survive poverty, an attempt to overthrow a dictatorship, a bloody civil war, but all these unfold gently, without dramatic tension. As nameless corpses pile up in nameless villages, the narrator notes down his observations of the landscape. Mengestu zooms in on details: a grey suit that matches the grey radio on which a state of emergency is announced over and over again; the wet towel with which the narrator cleans his face after being beaten.

 

But one senses that Mengestu’s intentions have defeated him a little. The attempt to render both the voice of a traumatised refugee with literary ambitions and that of a white American woman who has never left her home state is virtuosic in intention, but not quite in execution. Both characters seem to remain far away from us, and from themselves. Perhaps this poor rendering of character is itself a kind of virtuosity, reminding us that vehicles like literature, or even language, are imperfect vessels for conveying a world of wildly different real experiences, whether those of a frustrated Midwestern social worker or of a helpless witness to atrocities.

 

The novel’s most impressive quality is this pervasive aura of estrangement, as if reality were interchangeable for some other state of affairs, and therefore only minimally possible to describe. But this effect is also a kind of failure. Poor black Africans are only too often represented in this way, as remote and essentially unknowable. Western media coverage of events in ­Nigeria or the Democratic Republic of the Congo, for example, tends to paint specific political formations as if they were incomprehensible eruptions of evil. Africans, we are led to believe, are subjects of trauma so great that it exceeds even the limits of the concept of trauma. Their names change, they appear in one place and disappear in another. Against this erasure, it feels important to remember the former Haitian president Jean-Bertrand Aristide’s dictum that “every person is a person”. Mengestu’s rendering of this hovers in a fascinating limbo, at times seeming to resist the pervasive negation of African subjectivity and at times coming uncomfortably close to simply repeating it.

 

Hannah Black’s writing has been published in Mute, Dazed Digital and The New Inquiry, where she is also a contributing editor.

 

thereview@thenational.ae

 


“ወጣቶች ለትግል እየመጡ ነው”–ግንቦት 7 ወቅታዊ ርዕሠ አንቀጽ

$
0
0

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ “ወጣት፤ የነብር ጣት!” በሚል ርዕስ ጥር 26 ቀን 2003 ዓ.ም. በቁጥር 142 ባወጣው ርዕሰ አንቀጹ “ወጣት በነብር ጣት መመሰል ያንሰው እንደሆን እንጂ አይበዛበትም። የኢትዮጵያም ወጣት የነብር ጣት ሆኖ ያውቃል … አሁንም ነው” ብሎ ነበር። በዚያ ጽሁፍ እና በሌሎችም አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ እንዳብራራው ግንቦት 7 በወጣቱ ችሎታና ተነሳሽነት ላይ ከፍተኛ እምነት አለው። የወደፊቷ ብቻ ሳይሆን የአሁኗ ኢትዮጵያም የወጣቱ መሆኗን ግንቦት 7 ያምናል። ግንቦት 7: ወጣቶችን ለማሳተፍና ለመሪነት ለማብቃት የሚጥር፤ ራሱም በወጣቶች የተገነባ ድርጅት ነው።
Ginbot_7_Logo_L
ኢትዮጵያ አገራችንና ሕዝቧን ከወያኔ አደንቋሪ አገዛዝ ለማላቀቅ ቆርጠው የተነሱ ወጣቶች እየበረከቱ መምጣታቸው የግንቦት 7 እምነትን የሚያጠናክር ሆኗል። አምባገነኑን የወያኔ አገዛዝን በትጥቅ ትግል መፋለም ይኖርብናል ብለው የተነሱ ወጣቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተደራጁ መሆናቸውን እንሰማለን። እድሜያቸው በሀያዎችና በሠላሳዎች መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ለጋ ወጣቶች ናቸው የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የሚባለውን የትግል ድርጅትን የፈጠሩት። ይህ ኃይል ሰሞኑን ለአራተኛ ጊዜ እጩዎችን አሰልጥኖ ማስመረቁን በተለያዩ ሚዲያዎች ባሰራጨው ዜና ገልጿል። በተመሳሳይም የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን አሰልጥኖ ለወሳኝ ትግል ዝግጁ መሆኑን አብስሯል። የኢትዮጵያ አርበኖች ግንባርም በወጣቶች የተሞላ ለትግል የተዘጋጀ ድርጅት ነው። ሌሎችም አሉ። እነዚህን ድርጅቶች ድርጅት ያደረጓቸው ወጣቶች ናቸው።

በሰላማዊ የትግል ዘርፍም ወያኔ የሚያደርስባቸው እስር፣ ዱላና እንግልት እየተቋቋሙ በየእለቱ እየበረቱ የመጡ ጀግኖች ወጣቶችን ማየት ችለናል። ወያኔ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ብሩህ አዕምሮና ልብ ያላቸው ወጣቶችን አስሬ፣ አሸማቅቄ ጨረስኩ ሲል ከዚያ የባሱ እየፈለቁ ነው። በነፃነት ሲጽፉ የነበሩ እነ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታየ እና ርዕዮተ ዓለሙ በሀሰት ክስና ምስክር ሲታሰሩ ወያኔ ተስፋ እንዳደረገው ወጣቶች በፍርሃት ተሸማቀው ልሳኖቻቸውን አልዘጉም። እንዲያውም ከነሱ የባሱ፣ የበሰሉ ጦማርተኞች መጡ። ሰላማዊ ታጋዮቹ እነ አንዱ ዓለም አራጌና ናትናኤል መኮንንን ሲያስር ከእነሱ የበለጡ ወጣት ወንድና ሴት ታጋዮች መጡ። እስከ ድል ድረስ ይህ ዑደት ይቀጥላል፤ ኢትዮጵያ ወጣት ጀግኖችን ማፍራቷ አያቋርጥም።

ወያኔ “ኢህአዴግ” በሚባል ቀፎ በሰበሰባቸው አድርባይ ድርጅት ውስጥ የተሰባሰቡ ወጣቶችም ወደ ህሊናቸው እየተመለሱ፣ ድፍረት እያገኙና እየከዱት ነው። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች በወያኔ ድርጅቶች ውስጥ የገቡ ህሊና ያላቸው ወጣቶች “ምን እናርግ?” እያሉ ነው። ለእነዚህ ወገኖቻችን ግንቦት 7 አጭር ምላሽ አለው – “ከቻላችሁ ጥላችሁ ውጡና የነፃነት ትግሉን በይፋ ተቀላቀሉ፤ ካልቻላችሁ ኢህአዴግን ከውስጥ ሆናችሁ ውጉት፣ አዳክሙት፣ ግደሉት” ።

በሁሉም ረገድ በኢትዮጵያ ወጣት ላይ ያለ ተስፋን የሚያጠናክሩ ነገሮችን የምናስተውልበት ወቅት ላይ መሆናችን የሚያስደስት ነገር ነው። “እንዴት ልታገል? ከማን ጋር ልታገል?” የሚሉ ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተዋል። ነፃነቱን የሚወድ ወጣት ሁሉ እንደ ፍላጎቱና ዝንባሌው የሚሳተፍበት መድረክ ተዘጋጅቶለታል።

ወያኔ፣ ወጣቱን ያህል የጎዳው የኢትዮጵያ የኅበረተሰብ ክፍል የለም። የህወሓት መሪዎች በወጣትነታቸው ዘመን “መብት ተነፈግን” ብለው ብረት አንስተዋል፤ የዛሬው ወጣት ግን እነሱ ያኔ የነበራቸውን እኩሌታ ያህል እንኳን መብት እንዳያገኝ አድርገዋል። የህወሓት ሁሉንም ጠቅልሎ የመግዛት ፍላጎት ወጣቱን መናገርም ሆነ መፃፍ ብቻ ሳይሆን ማሰብ እንኳን እንዳይችል ለማድረግ እየሞከረ ነው።

የኑሮ እድሎች የሚከፋፈሉት በዘርና በፓለቲካ ወገንተኝተኝነት በመሆኑ ከሁለቱም ያልሆነው ወጣት ኑሮው የተጎሳቆለ፤ የነገ ተስፋውም የጨለመ ሆኗል። ስደት የኢትዮጵያ ወጣት እጣ ፈንታ ሆኗል። ዛሬ የተማረውና ከተሜው ብቻ ሳይሆን በትምህርት ያልገፋውና በገጠር በግብርና የሚተዳደረውም ወጣት ስደተኛ ሆኗል። አረብ አገራት፣ ሱዳን፣ ኬኒያ፣ ደቡብ አፍሪቃ በኢትዮጵያውያን ወጣት ወንዶችና ሴቶች ተጨናንቀዋል። ወያኔ ወጣቱን በእድሜና በዝንባሌ ሳይሆን በዘር በማደራጀት የጎንደሩ ለባሌ፤ የሸዋው ለአሩሲ፤ የትግራዩ ለባህርዳር፣ የደሴው ለለቀምት ፈጽሞ ባዕድ እንዲሆን፤ በጥርጣሬም እንዲጠባበቅ፤ በሰበብ አስባቡም እንዲቆራቆስ አድርጓል። ወያኔ፣ የኢትዮጵያን ወጣት በኢትዮጵያ ወጣት ላይ እንዲዘምት አድርጓል።

ያም ሆኖ ግን የወያኔ ፋሺስታዊ የጥፋት ፕሮጀክት እየተናደ ነው። በተስፋና በወኔ የተሞሉ ከሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተውጣጡ ወጣቶች በበረሃዎችና በሜዳዎች ላይ በአንድነት ሲዘምሩ ስናይ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቅርብ መሆኑ ይሰማናል። አዎ!!! የኢትዮጵያ ወጣቶች ከየአቅጣጫው እየመጡ ነው። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ህልማቸውን ያልማል፤ ዜማቸውን ያዜማል። ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሁሌም አብሯቸው ነው። ኢትዮጵያ በወጣቶቿ ብርቱ ትግል ከአገዛዝ ነፃ ትወጣለች።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

“እምቢ!!! መሬታችን ለሱዳን አይሰጥም”በሚል በእስራኤል የተጠራ ሕዝባዊ ስብሰባ

“ያመመኝ በእሙ የተነሳ ስለሆነ ‘ያመመኝ በሷ ነው’የሚል ነጠላ ዜማ ሰርቻለሁ”–ድምፃዊ ጌድዮን ዳንኤል

$
0
0

ቁም ነገር፡- ድምፃዊ ጌዲዮን በቅድሚያ ጥሪያችንን ተቀብለህ በመገናኘታችን በጣም አመሰግናለሁ፤የዛሬ አምስት ዓመት ሁለተኛ አልበምህን ካወጣህ በኋላ ጠፍተህ ነበር፤ ምንድነው መንስኤው?

ጌዲዮን፡- እኔም በጣም አመሰግናለሁ ታሜ፤እንግዲህ እንዳልከው በ2001 ዓ.ም ‹አንደኛ ናት› የተሰኘውን ሁለተኛውን አልበሜን ካወጣሁ በኋላ ትንሽ ችግር ገጥሞኝ ነበር፤

ቁም ነገር፡- ምንድነው የገጠመህ?አልበምህ እንደጠበቅከው አልሆነልህም ወይስ ?

gedion daniel
ጌዲዮን፡- እሱም አንዱ ምክንያት ነው፤ ግን ጊዜው ራሱ ጥሩ አልነበረም ለኔ፡፡የጤና ችግር ገጠመኝ፡፡ምን እንደሆንኩ እንደነካኝ አላውቅም፤ መንፈሴ ትክክል አልነበረም፡፡አልበሙ በጣም አሪፍ ስራ ነበር፤ ብዙዎቹን ኤልያስ መልካ ነበር ያቀናበረልኝ፡፡ ከኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ጋር በ1998 ዓ.ም ስለነበር የተዋዋልነው በዛን ወቅት ሲወጣ
ብዙም አልተደመጠም፡፡

ቁም ነገር፡- ከዛ በኋላ ምን ትሰራ ነበር?
ጌዲዮን፡- ከቤትም አልወጣም ነበር፤ሥራ ሁሉ መስራት አልቻልኩም፡፡ ነገሮች ሁሉ ለኔ በጣም ከብደውኝ ነበር፡፡ ምን እንደነካኝ አላውቅም፤ ደንዝዤ ነበር፡፡

ቁም ነገር፡- ታዲያ ምን አደረግህ?

ጌዲዮን፡- ወደ ፀበል ቦታ ነው የሄድኩት፤
ቁም ነገር፡-የት?
ጌዲዮን፡-ሽንቁሩ ሚካኤል ፤ ቅዱስ ኤልያስ፤ማርያም ነው ለረዥም ጊዜ ሄጄ የተቀመጥኩት፡፡ ለአንድ ዓመት ያህል ሽንቁሩ ሚካኤል ነበር የተቀመጥኩት፡፡ ሁኔታው በጣም ከባድ ነበር፤ ሥራ ሁሉ መስራት እንዳልችል ተደርጌ ነበር፡፡

ቁም ነገር፡-ማን ነበር ፀበል ቦታ የሚወስድህ?
ጌዲዮን፡- ከጓደኞቼ ጋር ነበር እየሄድኩ እዛ ተቀምጩ እጠመቅ የነበረው፡፡ በተለይ ሽንቁሩ ሚካኤል ስሄድ ሰላም ነበር የማገኘው፡፡

ቁም ነገር፡- በመሀል እኮ ተሽሎህ ነበር ተብሎ ነበር?

ጌዲዮን፡- ልክ ነው፤ ከሽንቁሩ ሚካኤል  ዓመት ያህል ተቀምጬ ከተመለስኩ በኋላ ትንሽ ለውጥ ነበረኝ፤ባህሬን ሁሉ ሄጄ ለሁለት ወራት ሥራ ሰርቼ ነበር የተመለስኩት፤ የሚገርምህ በዛን ወቅት ምን ሆነ መሰለህ፤ ሐመልማል አባተ ስልኬን አፈላልጋ ትደውልልኛለች፤የሆነች ልጅ በህልሟ አይታኝ ነው ለእሷ የነገረቻት፡፡ ልጅቷ እንደዚህ
አይነት ልጅ ጌዲዮን የሚባል ታውቂያለሽ ወይ? ትላታለች፤ አዎ ስትላት፤ ታሟል አፈላልገሽ ሽንቁሩ ሚካኤል ሂድ በይው ትላታለች፡፡ እሷም ይህንን ትነግረኛለች፡፡ ከዛ እንደገና ተመልሼ ሄድኩ ማለት ነው፡፡መገጣጠሙ በጣም ይገርማል፡፡

ቁም ነገር፡- በመሀል ግን ከአርቲስቶች ጋር አትገኛኝም ነበር?
ጌዲዮን፡-ከማንም ጋር አልገኛኝም ነበር፤ ሰው አያገኘኝም፤አልፎ አልፎ ሮባ ነበር የሚያገኘኝ፡፡
ቁም ነገር፡- ጉዳዩ ከፍቅር ጋር  የሚያያዝ ነው ይባላል?
ጌዲዮን፡- እንደዛም ነገር አለበት/ሳቅ/

ቁም ነገር፡- እሙ ናት?
ጌዲዮን፡- አዎ ያው እሙን የማያውቃት የለም፡፡ እሙ በጣም ጥሩ ልጅ ናት፤ እሷን ማጣቴ በህይወቴ ውስጥ ትልቅ ነገር ጎድሎኛል ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም ከልጅነት ጀምሮ ነው የምንተዋወቀው፤ማንም ቤተሰብ አጠገቤ ስለሌለኝ ያለችኝ እናቴም አባቴም እሷ ነበረች፡፡ብዙ ነገር አብረን አሳልፈናል፡፡
ቁም ነገር፡-ምን አጣላችሁ ታዲያ?
ጌዲዮን፡- የመጣላት ጉዳይ አይደለም፡፡
እሷ ትኖር የነበረው ዱባይ ነበር፤ ወደ አሜሪካ ነው የሄደችው፤ ግን አልቀርም እመጣለሁ ብላኝ ነበር፡፡ ከሁለተኛው አልበሜ በኋላ ድምጿን አጠፋችብኝ፡፡

ቁም ነገር፡- አሁን ስለ እሷ ምን መረጃ አለህ?
ጌዲዮን፡- ያው አሜሪካ ነው ያለችው፤

ቁም ነገር፡- ትዳር መያዝ አለመያዟንስ?
ጌዲዮን፡- ደህና መሆኗን እንጂ ስለዚህ ጉዳይ አልጠይቃትም፤ ማወቅም አልፈልግም፤በነገራችን ላይ አልፎ አልፎ ትደውልልኛለች፤ አይዞህ በርታ ጠንክር ትለኛለች፤

ቁም ነገር፡-እንዴት ነው ወደ አሜሪካ የሚያስኬድ ሥራ አልመጣልህም እስከዛሬ?
ጌዲዮን፡- አሁን በቅርቡ የእስራኤል ስራ አለኝ፤ ከዛ በኋላ ወደ አሜሪካ የሚያስኬደኝ ስራ እየተነጋገርኩ ነው፤

ቁም ነገር፡- ድምፃዊ አበበ ተካ እንኳ ሚስቱን እዛው ድረስ ሄዶ ፈልጎ አግኝቷታል፤ አንተስ ምን ታስባለህ?
ጌዲዮን፡- እንግዲህ እኔም ሀሳቡ አለኝ፤ ሰዎቹ እያነጋገሩኝ ነው፤ ከተሳካ …

ቁም ነገር፡- ያለችበትን ስቴት ታውቀዋለህ?
ጌዲዮን፡-አዎ ዋሽንግተን ዲሲ ነው ያለችው፡፡
ቁም ነገር፡- ምናልባት ይህንን መፅሔት የምታነብ ከሆነ/በፌስ ቡክም ቢሆን/ ምላሿን ትሰጥሃለች ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤በነገራችን ላይ ባለፈው አልበምህ ላይም አሁንም ነጠላ ዜማ ለእሷ የዘፈንከው አለ አይደል?
ጌዲዮን፡- አዎ፤ ‹እሙ አይኔን› የሚለው የመጀመሪያ አልበሜ ላይ ያለው ለእሷ ነው፤ አሁን ደግሞ የለቀቅሁት ‹ያመመኝ በእሷ ነው›የሚለው ነጠላ ዜማ ለእሷ ነው፡፡
ቁም ነገር፡- ግጥሙን ሰምቼዋለሁ፤ በጣም ስሜት የሚነካ ነው፤ እስኪ ትንሽ ስንኙን በልልኝ
ጌዲዮን፡- ያመመኝ በእሷ ነው
እንዴት ብወዳት ነው
ያየሁትን መአት ችዬ አለሁኝ በእውነት
ያመመኝ በእሷ ነው
እንዴት እንዴት እንዴት
እንዴት ብወዳት ነው
እኔማ ኪሴን ልቤን
ፈትሼ ዝር የሚል ሳጣ ለነፍሴ
የሰው ልጅ እንዲህ ይሆናል
ስል ወደ ቀራኒዮ አዬ መንፈሴ› ነው
የሚለው፡፡ ከግል ህይወቴ ጋር የሚገናኝ በመሆኑ  በዚሁ መልኩ ክሊፕ እየሰራሁለት ነው፡፡

ቁም ነገር፡- አሁን በመልካም ጤንነት ላይ ነው የምትገኘው፤ እንዴት ወደዚህ ህይወት ተመለስክ?
ጌዲዮን፡- እኔ ወደ ሽንቁሩ ሚካኤል ከገባሁ ጊዜ ጀምሮ በሚዲያ ላይ ምን እንደሚነገር እንደሚወራ አላውቅም፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ከዛ ከቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ስወጣ አንድ ሰው ያገኘኝና ሰይፉ ፋንታሁን በሬዲዮ ስላንተ ሲናገር ሰምቻለሁ፡፡ ያገኛችሁት ሰዎች ካላችሁ ጠቁሙን ብሏል ስለዚህ አሁን በስልክ ላገናኝህ ብሎ ደውሎ አገናኘኝ፡፡ በእውነት ሰይፉ ፋንታሁንን በጣም ነው የማመሰግነው፡፡ እግዚአብሔር ይባርከው፡፡ ከሱ ጋር መነጋገር ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ ነገሮች ሁሉ እየተለወጡ መጡ፡፡ ያኛውን ጌዲዮን ረስቼ አዲስ ሰው እንድሆን ነው ያደረገኝ፡፡ከዛ በሬዲዮ አነጋገረኝና ጤነኛ መሆኔን ከተናገረ በኋላ ኢቢኤስ ቲቪ ላይ መቅረብ አለብህ ህዝብ ሊያይህ ይገባል ብሎኝ ጥሩ ፕሮግራም ተሰራ፤ሰዎችም አርቲስቱም አይዞህ አሉኝ ማለት ነው፤ እንግዲህ አስበው ፤ የወጣሁት ከፀበል ቦታ ነው፤ ግን በአንድ ጊዜ ወደ ስራ የምገባበትና አሁን ያለሁበትን ጎተራ ኮንዶሚኒየም ተከራይተው አዲስ ህይወት ውስጥ እንድገባ አድርገውኛል፡፡

ቁም ነገር፡- ምንድነው ያገኘከው ድጋፍ?
ጌዲዮን፡- እንግዲህ የገንዘብ መዋጮ ያደረጉልኝ ሰዎች አሉ፤ ጎሳዬ ተስፋዬ ፤የክለብ ኤችቱኦ ባለቤት፤ የኪንግ ሲልቨር ባለቤት እንዲሁም ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ አንድ ባለሀብት ድጋፍ አድርገውልኛል፡፡ በሙያ በኩል አቀናባሪዎቹ ኤልያስ መልካ፤ ካሙዙ ካሳ፤ አማኑኤል ይልማ፤ አበጋዙ ክብረወርቅ ሁሉም ሊሰሩም ቃል ገብተዋል፡፡ እንዲሁም ሄኖክ ነጋሽ ከአሜሪካ ደውሎ አንድ ዘፈን ግጥምና ዜማ ጨርሼልሃለሁ እልክልሃለሁ ብሎኛል፡፡ ሌሎችም ጓደኞቼ ታደለ ሮባ ያው የታወቀ ነው ከሰይፉ ጋር ሆነው አሁንም አንዳንድ ነገሮችን እያሟሉልኝ ነው፡፡ የአዲሱ አልበሜም ፕሮውዲውሰሩ ሮባ ነው፡፡ ማዲንጎ ፤ ጆሲ፤ ዳዊት ፅጌ፤ ሳምሶን ማሞ፤ሰራዊት ፍቅሬ፤ ቴዲ አፍሮ ከነባለቤቱ ትልቅ ተስፋ ነው የሰጡኝ፡፡ ቴዲ እንደውም ግጥምና ዜማ እሰጥሃለሁ ምንም ነገር እንዳታስብ ነው ያለኝ፡፡ሀይልዬ ፤ፀጋዬ እሸቱ ብቻ በጣም ሁሉንም በስም ያልጠቀስኳቸውንም በሙሉ እግዚአብሔር ያክብርልኝ ነው የምልው ፡፡ ተቦርነም አሜሪካ ካሉ አድናቂዎቼ ጋር አገናኝቶኛል፤ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ በዛወርቅ አስፋው አክስቴ ነች፤ የእናቴ እህት ናት፡፡ ደውላ አናግራኛለች፡፡ ቴዲ የማርሸት ልጅም አግኝቶኛል፡፡ መንግስቱ አሰፋንና አለምነህ ዋሴን፤ሁሉንም በጣም አመሰግናለሁ፡፡

ቁም ነገር፡-ስራስ አልጀመርክም?

ጌዲዮን፡- እየሰራሁ ነው፤ ሐረር መሶብ ሀሙስ፤አርብ፤ቅዳሜና እሁድ እሰራለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- የድሮውን ጌዲዮን አሁን ድጋሚ እናገኘዋለን?
ጌዲዮን፡-በበለጠ ሁኔታ ይገኛል፡፡ በጣም ብዙ ነገሮችን ስላሳለፍኩ ጠንካራ ሆኛለሁ ብዬ ነው የማስበው፡፡ ብዙ ነገር ተምሬያለሁ፤በህይወቴ ውስጥ ያየሁትን ከባድ ነገር ወደ ጥሩ ነገር መቀየር እፈልጋለሁ፡፡ ከዚህ የበለጠ ከባድ ነገር ከዚህ በኋላ ቢገጥመኝ እንኳ በቀላሉ አልሸነፍም፡፡ ስለዚህ በአዲስ መንፈስ ነው ወደ ስራ
የተመለስኩት፡፡ በዚህ አጋጣሚ በየሄድኩበት ቦታ ሁሉ ህዝቡ ለሚሰጠኝ ፍቅና አክብሮት ምላሽ ለመስጠት ቃላት የለኝም፡፡ እግዚአብሔር ያክብርልኝ ብቻ ነው ለማለት የምችለው፡፡
ቁም ነገር፡- ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔርን በመዝሙር ለማመስገን አላሰብክም?

ጌዲዮን፡- በደንብ ነዋ፤የኔ ፍላጎትማ ሙሉ ካሴት መዝሙር ለመስራት ነው፤ቢፈቀድልኝ አምላኬን በዚህ መልኩ ባመሰግን ደስ ይለኛል፡፡ ግን በቅድሚያ በነጠላ መዝሙር ላደረገልኝ የማይመለስ ውለታው እግዚአብሔርን ለማመስገን እፈልጋለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- ከዚህ በፊት ቃለ ምልልስ ስናደርግ ወደ ፊልም ስራ የመግባት ሀሳብ እንደነበረህ ነግረከኛል፤አሁንስ እንዴት ነው?
ጌዲዮን፡- በፊት እኮ የመጀመሪያ አልበሜን ካወጣሁ በኋላ ‹የማያልቀው መንገድ› የሚል ፊልም ላይ ሰርቼ ነበር፡፡ እንደ አሁኑ በየሲኒማ ቤቱ መታየት ሳይጀመር በቪዲዮ ሲዲ ነበር የወጣው፡፡ አሁን እንግዲህ የሚያሰራ ካለ እናያለን..

ቁም ነገር፡- በመጨረሻስ
ጌዲዮን፡- ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ የሙያ ጓደኞቼን ጋዜጠኞችን በሀገር ውስጥም በውጪም አረብ ሀገራትም አውሮፓና አሜሪካ ያሉ የሙዚቃ አድናቂዎቼን በሙሉ አመሰግናለሁ፡፡በጥሩ የሙዚቃ ሥራ አስደስታችኋለሁ ነው የምለው፡፡

ቁም ነገር፡- አመሰግናለሁ፡፡

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በጨለማ ክፍል መታሰራቸው ተሰማ

$
0
0

በአቡ ዳውድ ኡስማን -

(ድምጻችን ይሰማ እንደዘገበው)

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በሃሰት በሽብርተኝነት ተወንጅለው በእስር የሚገኙት ኮሚቴዎቻችንን የማረሚያ ቤቱ አስተዳር ሆን ብሎ የማሸማቀቅ እና የማዋከብ ተግባር እየፈፀመባቸው እንደሚገኝ መዘገባችን ይታወቃል::

abubeker

በማረሚያ ቤቱ ከሚገኙ ህግ ታራሚዎች እና እስረኞች በተለየ መልኩ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በኮሚቴዎቻችን አመራሮች እና አብረዋቸው በታሰሩት ወንድሞች ላይ ትኩረት በማድረግ አቃቂር የ መፈለግ እና ባገኙትም ነገር ጉዳዩን በማግነን ለማሸማቀቅ እና ለማንገላታት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር አቶ አምባዬ እና የደህንነት ሃላፊ አቶ ኤርሚያስ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸወ የተገለፀ ሲሆን ሲዝቱባቸው በነበረው መሰረትም የህዝበ ሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑትን ኡስታዝ አቡበከር አህመድን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሰሩ መደረጉን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በኮሚቴዎቻን እና በወንድሞቻችን ላይ ልዩ ክትትል በማድረግ በጨለማ ክፍ ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ ከበላይ የደህንንት አካላቶች ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆን ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ድንገተኛ ፍተሸ በማድረግ ማንኛው እስረኛ ጠያቂዎች ሊሰጡት የሚችሉትን ገንዘብ ይዛችሁ ተገኝታቹሃል በሚል ኡስታዝ አቡበከር አህመድን እና ሼህ መከተ ሞሄን የማስፈራራት እና ቃላቸውን እንዲሰጡ የማድረግ እንቅስቃሴ ሲየደርጉባቸው ቆይተዋል፡፡በትላንትናው ዕለት ሃሙስም ኡስታዝ አቡበከር አህመድን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሰር ማድረገቻውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ከሌላ እስረኞች በተለየ ሁኔታ ኮሚቴውን የማዋከቡ እና በጨለማ ቤት ለመቅጣት የማስፈራቱ ድርጊታቸው ህገ ወጥ መሆኑን ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ለማረሚያ ቤቱ ደህንነት ሃላፊዎች ሲያሳስቡ ቢቆዩም የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ግን ኡታስዝ አቡበከርን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሰር ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከህግ እና ክፍርድ ቤቱ ተዕዛዝ ሁሉ የበላይ በሆኑ የደህንነት ሃይሎች በኮሚቴዎቻችን አመራሮች ላይ እና በተወሰኑ ወንድሞች ላይ እየተደረገ ባለው ጥብቅ ክትትል እና የዚህ መሰሉ የጨለማ ቤት ቅጣት የሚፈፀም ከሆነ ኮሚቴዎቸችን ለፍርድ ቤቱ እያቀረቡ የሚገኙትን የመከላከያ ምስክር እስከማቆም ሊደርሱ እንደሚችሉ ታውቋል፡፡ ህግ ተፅፎ ባለበት ሃገር ህጉ እየተጣሰ ንፁሃን እንዲንገላቱ መደረጉ የፍርድ ቤቱን ሚና ከቁብ የማያስገባ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ በችሎቱ የመቀጠሉ ሁኔታ አጠያያቂ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ሼህ መከተ ሞሄ እና ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ላይ በጨለማ ክፍል አስገብተው እንደሚቀጧቸው የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ሲዝቱባቸው የቆዩ ሲሆን ዛቻቸውን በተግባር በመለወጥ በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዳስገቧቸው ታውቋል፡፡

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እየተፈጸመባቸው የሚገኘውን ህገ ወጥ ተግባር ለፍርድ ቤቱ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኡስታዞቻችንን እና ወንድሞቻንን አላህ ይጠብቅልን!!!

Health: አልጋ ላይ በባልሽ ላይ ጠ/ሚ/ር መሆን የምትችይባቸው 5 ዘዴዎች

$
0
0

5 ways to be more attractive to your husband

ከሊሊ ሞገስ (አፕል ቫሊ)
giftየውጭ አገር ሴቶችን እንተዋቸው እና ወደ ሀገራችን ስንመጣ በትዳር ውስጥ ያሉት ወይም ያልተጋቡ ሴቶችን ብናይ ብዙውን ጊዜ ከመናገር ይልቅ ማዳመጥ፣ ከመወሰን ይልቅ ውሳኔ ተቀባይ መሆን፣ ከማዘዝ ይልቅ ታዛዥ መሆን ይታይባቸዋል፡፡ ወደ ፍቅር ህይወታቸው ስንመጣ ደግሞ ከወንድ ጓደኛቸው ብዙ የሚፈልጉት ነገር እያለ ነገር ግን በውስጣቸው አፍነው ይይዙታል፡፡ በተለይ በወሲብ ጉዳይ ላይ ሁሌ የወንዱን ስሜት ብቻ ይቀበላሉ፡፡ እርካታ ቢያገኙም አኩርፈው ከመተኛት ውጭ የሚያመጡት ነገር የለም፡፡ ይህ ደግሞ በግልፅ ካለመወያየት መፍትሄ የለውም ብሎ ከመገመትና ከእውቀት ማነስ የሚመጣ ችግር ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ የዚህን ችግር መፍትሄ አንድ በአንድ እናያለን፡፡
በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ዝምታ ወርቅ ነው የሚለው አባባል ቦታ የለውም፡፡ ባለቤትሽ አልጋ ላይ ስህተት ቢሰራ እንኳ ስሜቱን ላለመጉዳት ስትይ ዝም ትያለሽ፡፡ ታዲያ እርካታ ካላገኘሽ ‹‹ዛሬ ምንም አልረካሁም›› ትያለሽ ወይስ አትዪውም?
1. ማነቃቃቱ ከአንቺ ይጀምር
መኝታ ቤት ብዙ ጊዜ ፊሽካ ነፍቶ ጨዋታው እንዲጀመር የሚያደርገው ወንዱ ነው፡፡ ባለቤትሽ መኝታ ቤት ውስጥ ስሜት አልባ ሆኖ እንደ በረዶ ከቀዘቀዘብሽ ምክንያቱን በግልፅ ጠይቂው፡፡ ምናልባት ያን ቅዝቃዜ አጥፍተሽ መኝታ ቤቱን የሰሐራ በረሐ የማድረጉ ስራ የአንቺ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ቀስ በቀስ ስሜቱ እንዲነሳሳ የማድረግ ግዴታ አለብሽ፡፡ ቀለሽ ጀርባሽን በመስጠት መተኛቱ ዋጋ የለውም፡፡
2. ፍላጎትሽን ግለጭ
ለምሳሌ የእርሱ አሳሳም ሊደብርሽ ይችላል፡፡ ይህን ጊዜ በቀጥታ ጥፋቱን አትናገሪ፡፡ ቅሬታዎችሽን የምትገልጭበት መንገድ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ምን እንደምትፈልጊ ስትናገሪ የአንቺን ፍላጎት ብቻ አትከተይ፡፡ ይህን የምታደርጊ ከሆነ ወደ ጠብ ሊያመራ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ‹‹አንተ ስትስመኝ መንግስተ ሰማያት የገባሁ ይመስለኛል ግን ደግሞ አንገቴንም ብትስመኝ ዛሬውኑ ብሞት አይቆጨኝም ነበር››
3. በቃላትና በአካልሽ ባልሽን ምሪው
አንቺ ብልጥ ከሆንሽ በቀላሉ መቆጣጠር ትችያለሽ፡፡ ውብ ቃላትን ሁሌ መናገር ይልመድብሽ፡፡ እርሱ ለምን ቀድሞ እንዲስምሽ ትፈቅጂያለሽ? ቀድመሽ አንቺ ጀምሪው፡፡ ለምሳሌ ባለቤትሽ ፀጉርሽን ሲዳስስ ደስተኛ ከሆንሽ ደስተኛ እንደሆንሽ የሚገልፅ ድምፅ ብታሰሚው የበለጠ በራሱ እንዲተማመን ታደርጊዋለሽ፡፡ እጆቹ በማይመችሽ ቦታ ላይ ካረፈ ቀስ ብለሽ በእጆችሽ ቦታ ላይ ካረፈ ቀስ ብለሽ በእጆችሽ ወደ ምትፈልጊው ቦታ መውሰድ ትችያለሽ፡፡ ለምሳሌ በእጁ ጀርባሸን እየዳሰሰ ከሆነ ቀስ ብለሽ እጆቹን ወደ ታች እንዲንሸራተት ማድረግ ትችያለሽ፡፡
4. ትክክለኛ ሙድ ፍጠሪ
ግንኙነታችሁ ሁሌ ደረቅና ሲሪየስ መሆን የለበትም፡፡ ከጓደኛሽ ላይጥሩ ሙድ በፈጠርሽ ጊዜ ተመሳሳይ ቋንቋ ትነጋገራላችሁ፡፡ አለባበስሽ ቋንቋ ያለው ቢሆን ይመረጣል፡፡ መኝታ ቤት ብትገቢ ሱሪ (ጅንስ) ለብሰሽ የምትገቢ ከሆነ ተሳስተሻል፡፡ ይልቁንስ የውስጥ አካላቶችሽን ግልፅ አድርጎ የሚያሳይ የሌሊት ልብስ ብትለብሽ የባለቤትሽን ስሜት በቀላሉ ትስቢዋለሽ፡፡ ጉርድ ቀሚስ በራሱ ጥሩ ሙድ የመፍጠር ሀይል አለው፡፡ የምትቀበያቸው ሽቶዎች፣ ሙዚቃዎች የመብራቱ አይነት የዕቃዎች አቀማመጥ እነዚህ ሁሉ ልዩ ሙድ ይፈጥራሉ፡፡
5. ባልሽን በስጦታ አስደንግጭው
ወንዶች ብዙ ጊዜ ስጦታ ሊሰጣቸው በቃ የተፈቀዱ እንደሀኑ ይሰማቸዋል፡፡ አንድ የሚወደውን ነገር ገዝተሽ ማታ በጣም ከጓጓሽ በኋላ ያኔ ስጦታ አበርክችለት፡፡ አቤት ያ ምሽት እንዴት እንደሚያስደስት ባየሽው፡፡ በመሆኑም ሁሌ ወንዶችን ፍፁም አድርገሽ አትመልከቻቸው፡፡ ሰው ናቸውና ሊሳሳቱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ መፍትሄው ያለው በአንቺ እጅ ላይ ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ተግባራዊ አድርጊያቸው፡፡ በተለይ በዚህ ዙሪያ የተፃፉ መጽሐፍትን በሚገባ አንብቢ፡፡ ያለ ጥርጥር መኝታ ቤት ውስጥ ዋና ኤክስፐርት ትሆኛለሽ፡፡ ይህን በማድረግሽ ፍቅራችሁን ዘላለማዊ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

በአዲስ አበባ የህዝብ መፈናቀል እንደሚቀጥል መረጃዎች አመለከቱ

$
0
0

ethsatግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ማደስና ፕላን ዝግጅት በሚባለው ፕሮግራሙ በመሃል አዲስ አበባ የሚገኙ ኪስ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን በስፋት እንደሚያፈናቅል የሚነገርለትን እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የአስተዳደሩ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ አካባቢን መልሶ የማልማት ገጽታ አለው በሚባለው ሥራ ውስጥ ዘንድሮ ከተካተቱ አካባቢዎች መካከል በካዛንቺስ 26 ሄክታር፣በደጃችውቤ 11.6 ሄክታር፤በሸበሌሆቴልዙሪያ 10.4 ሄክታር፣አሜሪካንግቢ 16 ሄክታር፣በአፍሪካህብረትቁጥር 2 ወደ 15 ሄክታር፣ተክለሃይማኖት 33 ሄክታር፣አሮጌውቄራቁጥር 1 እና 2እንደቅደምተከተሉ 14 ሄክታርእና 54 ሄክታር፣ባሻወልዴቁጥርየፓርላማማስፋፊያ 4 ሄክታርቤት የማፍረስ እቅድ መኖሩን ተከትሎበአንዳንድአካባቢዎችለነዋሪዎችካሳየመክፈል፣በአንዳንዶቹምየማፍረስሥራዎችእየተከናወኑመሆኑን ምንጮቹጠቅሰዋል፡፡ አስተዳደሩበመልሶማልማትፕሮግራሙበተለይየቀበሌቤቶችውስጥየሚኖሩነዋሪዎችምትክየኮንዶምኒየምቤት የሚሰጥቢሆንምበወቅቱናበሰዓቱየሚከናወንባለመሆኑነዋሪዎችለእንግልትናለተጨማሪወጪእየተዳረጉነው፡፡ በተለይየግልቤቶችምትክቦታበተመሳሳይሁኔታበፍጥነትየሚከናወንአለመሆኑ፣በቂየዝግጅትጊዜሳይሰ ጥነዋሪዎችእንዲነሱመገደዳቸውበየአካባቢውያላቸውንማህበራዊትስስርየሚያናጋናልጆቻቸውንምትምህርታቸውን ለማስቀጠልየሚቸገሩበትሁኔታተፈጥሮአል በተለይበግለሰብቤቶችተከራይተውየሚኖሩበርካታነዋሪዎችበምትክቤቶች አሰጣጥውስ

ጥየማይካተቱመሆኑማህበራዊቀውስእየፈጠረእንደሚገኝታውቋል የከተማአስተዳደሩበተለይበሊዝጨረታቦታዎችንአወዳድሮሲሰጥየመሬትአቅርቦቱእጅግአነስተኛከመሆኑጋርተያይዞ በአንድካሬሜትር10ሺብርእናከዚያበላይየሚሰጡጥቂትሐብታሞችተጠቃሚየሚሆኑበት፣በአንጻሩአነስተኛናመካከለኛገቢዎችያላቸው

ነዋሪዎች የማይጠየቁበትሥርዓትመፈጠሩይታወቃል፡፡ የኢህአዴግ መንግስት እጅግ በውድ ዋጋ የሚሸጠው መሬት በሙስና እየተበላ መሆኑንም የሚደረሱት መረጃዎች ያመለከታሉ። የኢሳት ምንጮች እንደሚገልጹት ከመሬትና ከታክስ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ የዝሪፊያ መረብ የተዘረጋ ሲሆን፣ ምርጭ የሚባሉ ቦታዎች በእነዚህ ጥቂት ግልሰቦች እጅ እየገባ ነው። እነዚህ ሰዎች ገቢዎችንና ጉሙሩክን ከጀርባ ሆነው በመቆ|ጣጠርና ስራቸውን በንጽህናና በሃቀኝነት የሚሰሩ ሰራተኞችን በተለያዩ ወንጀሎች በመክሰስከስራ እንዲባረሩ በማድረግ ከፍተኛ ሃብት እየመዘበሩ መሆኑን ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ታክስ ማጭበርበርና መሬት በህገወጥ መንገድ መዝረፍ በኢትዮጵያ አቋራጭ የመክበሪያ ስልት እየሆነ ነው።

በሰላም በር ከተማ ቁጫ ወረዳ 12 የአንድነት አባላት ታሰሩ

$
0
0

ፍኖተ ነፃነት

Fnoteበራሪ ወረቀት በማደልና የመኪና ላይ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የነበሩት 12 የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ በቁጫ ወረዳ፣ ሰላም በር ከተማ በሕግ ወጥ መንገድ ታሰሩ። የቁጫ ወረዳ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች፣ ጌታቸው ኮይራ፣ ኢሳያስ ሉቃስ፣ ጋሰላ ጋሌቦ፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ሰልፉን ለማስተባበር የሄዱት ስንታየሁ ቸኮል፣ ደረጄ ጣሰው፣ ኃይሉ ግዛው እና የቅስቀሳ መኪናዉን ሲያሽከርክር የነበረዉ ነጻነት ዘገየን ጨምሮ 12 የፓርቲዉ አመራሮችና ባላትን ፖሊስ በሕገ ወጥ ሁኔታ አስሮ ቃላቸዉን እንዲሰጡ በመጠየቅ ላይ መሆኑን ከስፋራዉ የደረሰን ዜና ያመለክታል።

የታገቱ የአንድነት ቀስቃሾች፣ የወረዳው ፖሊስ ቃል እንዲሰጡና እና ብሄራቸዉን እንዲናገሩ ለማስገደድ ቢሞክሩም፣ ሁሉም ቃል ለመስጠጥ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። «ብሄራችን ኢትዮጵያዊ ነው» በማለታቸው ፖሊስ ታሳሪዎቹን ምን ማድረግ እንዳለበት የበላይ ትእዛዝ እየጠበቀ መሆኑን፣ ታጋቶቹ ከመርማሪዉ ተረድተዋል።

በተያያዘ ዜና አብዛኞቹ የቁጭ ወረዳ የካቢኔ አባላት፣ ቢሯቸዉን ለቀዉ በአስቸኳይ ሰብሰብ ላይ እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን፣ የአካባቢው ሕዝብ በመንግስት እየደረሰበት የሚገኘዉን መጠነ ሰፊ ግፍ፣ በአደባባይ ለመቃወም በነቂስ እንደሚወጣ መገመቱ የካቢኔ አባላቱን ሲያሰጋ እንደቆየ የቅርብ ምንጮች ለፍኖት ነጻንት ገልጸዋል።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በቁጫ ወረዳ አጎራባች በሆነችው ደራሼ ወረዳ፣ በጊዶሌ ከተማ፣ በተደረገው ሰልፍ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ፣ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ እያወለበለበ፣ ተቃዉሞዉን ማሰማቱ ይታወሳል።

የቁጫ ወረዳ አጎራባች ደራሼ/ጊዶሌ የተደረገ ሰልፍ


ስለ የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያዊው ቅጂ ሙዚቃ ከቴዲ አፍሮ የተሰጠ መግለጫ፡ “ጉዞው ይቀጥላል!”

$
0
0

ስለ የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ
የተሰጠ መግለጫ

ባለፉት ወራቶች ቴዎድሮስ ካሳሁን ወይም “ቴዲ አፍሮ” ከኮካ ኮላ እና በስፋት ሲወራ ከከረመው የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ ጋር ስለነበረው ግንኙነት ያለንን አቋም እንድንገልፅ በሚጎርፍልን ጥያቄዎች ምክኒያት ከፍተኛ ጫና ስደረግብን ቆይተናል፡፡ በበኩላችን በተገባው የውል ስምምነት ላይ የግንኙነቱን ሚስጥራዊነት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን የገባን እና ማክበር የነበረብን ቢሆንም ቅሉ የቴዲ አፍሮ እና የኮካ ግንኙነት ወሬ እንዴት አፈትልኮ ወጥቶ ህዝብ እንዲያውቀው እንደቻለ ቢያስገርመንም አሁን ለመገንዘብ እንደቻልነው ቴዲ ከኮካ ጋር ያለውን ግንኙነት ኢትዮፒካ ሊንክ በተሰኘ የአገር ውስጥ የኤፍ ኤም ሬዲዮ የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጆች አማካኝነት ያወጀው እና በሚያስገርም ሁኔታ ለኮካ የቲቪ ሥራም አድናቆቱን በመስጠት ያረጋገጠው የኮካ ኮላ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ብራንድ ሥራ አስኪያጅ የሆነው አቶ ምስክር ሙሉጌታ መሆኑን መረዳት ችለናል፡፡
teddy afro
ያለጥርጥር በኮካ ኮላ ስም ቴዲ አፍሮ ለኮካ የቴሌቪዥን ስራ በማገናኘት እና በዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ተነሳሽነቱን የወሰደው የብራንዱ ሥራ አስኪያጅ ነበር፡፡ እኛም ጥያቄውን ውድ አገራችንን በመላው የአለም ዋንጫ ተመልካቾች ዘንድ አዎንታዊ ገፅታ የትኩረት እይታ ስር የሚያውላት በመሆኑ እና በዚህ በጉጉት በሚጠበቀው ታላቅ ዓለምአቀፍ የስፖርት ክንዋኔ ግዙፍ ቁጥር ያለው የዓለም ህዝብ ዘንድ የአገራችንን እና የህዝባችንን መልካም ገፆች ለማሳየት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ለምናደርገው ጥረት ሲባል በፍፁም ቅን ልቦና ተቀብለናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሚለቀቅበት ወቅት የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ የቴዲ አፍሮን ዓለም አቀፍ እውቅና እና ዝና፣ የሥነ ጥበብ ገፅታ እና ስብዕና የበለጠ ከፍ እንደሚያደርገው እና እንደሚያጠናክረው በሚገባ እንገነዘባለን፡፡

ለታፈረችው አገራችን፣በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ለሚገኙት ለውድ አድናቂዎቻችንና ለሰው ልጆች ሁሉ ባለን የማይታጠፍ ታማኝነት በኮካ ፕሮጄክት ተሳታፊ መሆናችን ትክክለኛ እና አግባብነት የነበረው ውሳኔ ነው፡፡ በዚህም ምክኒያት የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ የቴሌቪዥን ቀረፃው የተሻለ ውጤታማነት ይኖረው ዘንድ ቴዲ አፍሮ በበኩሉ አቅሙ የቻለውን ያህል ጊዜውን፣ጉልበቱን እና ስነ ጥበባዊ ክህሎቱን በመጠቀም አስፈላጊውን ጥረት አድርጓል፡፡ በኮካ ሰቱዲዮ ፕሮጄክት ተሳታፊ የመሆኑ ዋነኛው ፋይዳ አለም አቀፍ ተዋቂነት ባለው ብራንድ በመጠቀም የኢትዮጵያን አዎንታዊ ገፅታ ለማጉላት የመላውን ዓለም ህዝብ ትኩረት ለመሳብ የሚያስችል ከባድ ያለ ተልዕኮ ለመወጣት እንጂ የንግድ ዕቃ በማስተዋወቅ ለሚያስገኘው እምብዛም ያልሆነ ጥቅም አልነበረም፡፡
tedddy
በመሆኑም ሙዚቃ ነክ ንብረቶችን በማዘጋጀት እና በማሰራጨት የተለያዩ አገልግሎቶችን ለኮካ ኮላ የማዕከላዊ ምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ለመስጠት ወኪል የሆነው ማንዳላ ቲቪ የዝግጅት ሥራ አስኪያጅ ሚ/ር ዴቪድ ሣንደር፣ በኮክ ስቱዲዮ የተሰራው የቴዲ አፍሮ ስራ በሚያስደንቅ እና በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን የሚገልፀውን ስሜት ቀስቃሽ እና አጓጊ ዜና እና ብስራት የተቀበልነው በከፍተኛ ክብር፣ ኩራት እና እርካታ ሲሆን ይህው ሰው ከዚያም አልፎ “የአለም ዋንጫ ቪዲዮው ተዘጋጅቶና ተከፋፍሎ ምናልባት በጥር ወር በኮካ ኮላ ይለቀቃል” በማለት አረጋግጦልናል፡፡ ከሥራው መጠናቀቅ በኋላ በውጤቱ የተደሰቱት የቴሌቪዢን አዘጋጆች እዚያው ላይ ቴዲ አፍሮ በአንድ የኮካ የሙዚቃ አልበም ተሳታፊ ይሆን ዘንድ ያቀረቡለትን ጥያቄ ወዲያውኑ በመቀበል በሥራው የተሳተፈ ሲሆን ይህም ስራ “የአዲስ አመት ክንውን” ሆኖ ባለፈው “ታህሳስ 22 ቀን በአራት አገሮች ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እንዲጫወት ተደርጓል፡፡”

ከበርካታ ቀናት በኋላ፣ የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ መለቀቅ በጉጉት በምንጠባበቅበት ወቅት አቶ ምስክር የተጠናቀቀውን የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ እንድንመለከተው የጋበዘን ሲሆን በአርቲስቱ ሥራም እንደ ቴሌቪዢን አዘጋጆች ሁላችንም በጣም ደስተኛ ነበርን፡፡
ከጥቂት ጊዜ ባኃላ ግን ከባዶ መነሻነት አስደናቂ መጠማዘዝ ያሳየው አቶ ምስክር ፍርሐት በሞላው ድባብ በተጠናቀቀው ሥራ ላይ የነበረው የቴዲ አፍሮ ተሳትፎ እና ሽፋን “ዝናውን የሚመጥን አይደለም” በሚል የተጠናቀቀው ሙዚቃ እንዳይለቀቅ ድጋፍ እና ተቀባይነት ለማግኘት የሙከራ ጥረት አደረገ፡፡ ይህንን አቋሙን እንቀበልለት ዘንድ ለማሳመን ያደረጋቸው ሁሉም ጉዞዎች እና ኩነቶች በጉዳዩ ላይ “የቴሌኮንፈረንስ” እንዲካሄድ በመጠየቅ ከመታጀቡ በተጨማሪ በእርሱ አስተሳሰብ “ውድቀት” ሊሆን ስለሚችለውና የያዘውን አቋም አስመልክቶ ቴዲ አፍሮ ለህዝብ እንዳይገልፅበት እንድንታቀብ አስከማስፈራራት የደረሰ ነበር፡፡ ከዚህም በላይ ከመነሻው ጀምሮ በኮክ ፕሮጄክት ተሳታፊ እንዳልነበረ እና የኮካ ወኪል ከሆነው ከማንዳላ ቲቪ ጋር እንድንገናኝ ለማድረግ እና እኛን ለማሳመን እንዳልተሳተፈ ሁሉ አቶ ምስክር ከስራው ጋር በተያያዘ ከኮካ ኮላ ጋር የነበረን ግንኙነት በማስተባበል ራሱን በማራቅ ብሔራዊ እና ህዝባዊ ሃላፊነቶችን በተጋረደ ጠባብ የግል ጥቅም ለመለወጥ በፈፀመው አሳፋሪ፣ አገር ወዳድነት በሌለው የፈሪ ተግባሩ ኃላፊነትን ላለመሸከም በማሰብ ራሱን የማሸሽ እንቅስቃሴ አደርጓል፡፡

በኮካ ሰቱዲዮ የዝግጅት ሥራ አስኪያጅ በኩል ከቴክኒክ አኳያ የተጠናቀቀው ስራ የላቀ ጥራት እንዳለው በተደጋጋሚ ተረጋግጦልናል፡፡ በመሆኑም የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃን ይዞ በማቆየት እንዳይከፋፈል እና እንዳይለቀቅ የተደረገበት ምክኒያት እና የመጨረሻ ውሳኔ ከአርቲስቱ ወይም ከሥራ አስኪያጁ ጋር ምንም ውይይት ሳይደረግ እና ሳያውቁት በአቶ ምስክር ሙሉጌታ እና በኮካ ወኪል ማንዳላ ቲቪ የተሰጠ የጋራ ውሳኔ ነው፡፡

የተጠናቀቀው ሥራ ተሰራጭቶ እንዲለቀቅ በተደጋጋሚ የጠየቅን ቢሆንም፣ ከወኪሉ በመጨረሻ ላይ ያገኘነው ምላሽ ግን “በዚህ ደረጃ የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ ለጊዜው አንለቀውም” በሚል የተገለፀልን ከመሆኑ በላይ በእኛ ዘንድ የተፈጠረውን ሃያል ቁጣ በማባበል ለማቀዝቀዝ የሚሞክር እና ሥራውን ወደፊት ሊለቁት እንደሚችሉ ለማሳመን የሚጥር ማታለያ እና ለምንወዳት አገራችን፣ ለሁሉም ራሱን ለሚያከብር ኢትዮጵያዊ፣ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የአገር ውስጥ እና የውጪ አድናቂዎች እና ለአርቲስቱ በቁስል ላይ እንጨት የመስደድ ያህል ሆኖብናል፡፡

በበኩላችን በተጠናቀቀው ሥራ ላይ ስለተወሰደው ተገማችነት ላልነበረው የዱብዳ እርምጃ ለአቅረብነው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው በርካታ ጥረት ትኩርት የተነፈገው ወይንም ከነጭራሹ ችላ ከመባሉ ውጪ ምላሽ የተሰጠውም ትዕግስታችን ከተሟጠጠ በኋላ ነበር፡፡

በመጨረሻም ምንም እንኳን በጉዳዩ ጭብጥ ዙሪያ በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ስለተያዘው አቋም የተወሰነ መግባባት ላይ ለመድረስ ቴሌኮንፈረንስ የሚመለከታቸው ወገኖች እንደሚገኙበት ቃል ተግብቶበት የተዘጋጀ ቢሆንም ውይይቱ ሙያዊ በሆነ መልኩ ያልተዘጋጀ፣ ግልፅነት የጎደለው፣ አለመግባባት እንዳይከሰት ለማድረግ የጋራ መፍትሔ ለመሻት ሳይሆን ቅንነት በጎደለው መልኩ ይኛን ሐሳብ ለመረዳት ነበር፡፡ ቴሌኮንፈረንሱ ሆነ ተብሎ ህጋዊ ወኪል የሆነውን ሥራ አስኪያጃችንን በጭብጦቹ ላይ ለመወያየት እንዳይሳተፍ በማግለል መካሄዱ በራሱ ሂደቱ በቅን ልቦና ላይ ያለተመሰረተ መሆኑ ግልፅ ማስረጃ ነው፡፡
teddy-afro
በመሆኑም የአርቲስቱ አድናቂ ለሆኑት ኢትዮጵያዊያን እና የውጪ አገር ዜጎች በሙሉ ከኮካ ኮላ ጋር የነበረንን ግንኙነት የቆረጥን መሆናችንን ለመግለፅ መገደዳችን እያዘንን ስንገልፅ የዓለም ዋንጫ እስከሚከፈትበት ዕለት ድረስ ኮካ ኮላ የወሰደውን እርምጃ በድጋሚ እንዲያጤነው ያደርግ ዘንድ በተደጋጋሚ ጥሪያችንን ስናቀርብ ብሔራዊ ጠርዝ ባለው እና በውድ አገራችን፣ በህዝባችን እና አድናቂዎቻችን ላይ ጭምር የተቃጣውን የፈሪ፣ እና አገር ወዳድነት የጎደለውን አሳፋሪ የክህደት እና ክብር የሚያጎደፈውን ተግባር ግን ይቅር ላለማለት ወስነናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አስከመጨረሻው ዕለት ድረስ ኮካ ኮላ የተጠናቀቀውን ሥራ እንዲያሰራጨው እና እንዲለቀው ግፊት ማድረጋችንን እንደምንቀጥልበት ለአድናቂዎቻችንን እያረጋገጥን ከዚሁ ጎን ለጎንም ከሁኔታዎች ጋር አግባብነት ያላቸውን ሰላማዊ እርምጃዎችንም በመውሰድ የሁለቱንም ወገኖች ገፅታን እና ጥቅምን የሚጎዳ ማናቸውም ውዝግብ በማስቀረት በአድናቂዎቻችን የተጣሉብንን አደራ መተማመን እና እምነትን ለመመለስ የሚያስችል እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡
ጉዞዉ ይቀጥላል!

ሸንጎ በሲያትል ዋሽንግተን የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አካሄደ

$
0
0

ትልቁ  የኢትዮጵያ አንድነት ኃይሎች ስበስብ የሆነው የኢትዮጵያ  ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሽንጎ) የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት የሁኑት ፕሮፊሰር አቻምየለህ ደበላና ዶ/ር አክሎግ ቢራራ እሁድ ግንቦት24 ቀን2006  (ጁን1፣2014) ፣በሲያትል(አሜሪካ) ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ አካሂደዋል።

2014-06-06_10-44-27በዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ሁለቱም የሽንጎው ተወካዮች  በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ፣ በሽንጎው ራዕይና እንቅሰስቃሴ እና በዜጎች ተሳትፎ ላይ ሰፊ ገለ ጻአድርገዋል። የፕሮፊሰር አቻምየለህ ደበላና የዶ/ር አክሎግ ቢራራን ገለጻ በማስከተልም ስፊ ጥያቄና መልስ እና አርኪ  ውይይት ተካሂዷል።

ሸንጎ ተመሳሳይ ህዝባዊ ስብሰባዋችን በተለያዩ ሀገሮችና ከተሞች ውስጥ በማካሄድ  በአለም ዙሪያ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በሀገሩ ላይ የተደቀነውን አደጋ ለማስወገድ የሚስችል ሚና እንዲጫወት ለማድረግ ኢትዮጵያውያንን ማሰባሰቡን እንደሚቀጥል ታውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ ሸንጎው ዲፕሎማቲክ እንቅስቃሴ በማካጠናከር ከአለም አቀፉ ህብረተሰብ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ከፍተኛ ድጋፍን ለማስገኘት ሰፊ እንቅስቃሴ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል።

በስያትል የተካሄደውን ስብሰባ ላሰተባበሩ እንዲሁም በስብሰባው ላይ  ለተገኙ ሁሉ ሽንጎ ምስጋናውን አቅርቦ፣ ይህ ትብብር ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ እንደሚያደርግ ገልጧል። በሲያትል የኢትዮጵያ ወጣቶች ስብስብ፣ እንዲሁም ሞሲሊም ወገኖቻችን በተለይ ደግሞ ነጃሽ ጀስቲስ በመባል የሚታወቀው ድርጅት አባላት ላደረጉት ትብብር ሁሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ፍቅረኛሞች በአዲስ አበባ – [አሪፍ የፍቅር ታሪክ)

$
0
0

በአዜብ ታምሩ

ወጣቶች ናቸው፡፡ ዓለምፀሀይ ዘላለምና አበራ ተካ ይባላሉ፡፡ ኑሮን በጎዳና የሚገፉ፤ ተቃቅፈው ውለው ተቃቅፈው የሚያድሩ፤ ማንንም ለመስማት ጊዜ የሌላቸው፤ ከጥቂት ቡቱቶዎቻቸውና ከትንሿ ውሻቸው ውጪ ምሳ ካገኙ ስለራት የማያስቡ ከፍቅር ሌላ ምንም የሌላቸው ወጣቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ወጣቶች በአዲስ አበባ ከተማ መሀል አውቶቡስ ተራ አዲስ ከተማ መሰናዶ ት/ት ቤት ጀርባ ከሚገኘው መንደር የኢትዮጵያ ህፃናት መርጃ ድርጅትን አጥር ተገን አድርገው የሚኖሩ ፍቅረኛሞች ናቸው፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ነጋ ጠባ የሚገረሙባቸው፤ ቤት ውስጥ ያጡት አንዱ ላንዱ መስዋዕትነት የሚከፍልለት ፍቅር እዚህ መገኘቱ አጀብ የሚያሰኛቸው፡፡
179 - Kumneger Cover
በነዚህ ወጣቶች ፍቅር ከሚገረሙት ሰዎች መካከል አንዱ አቶ በላይ ይባላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ህፃናት መርጃ ድርጅት የቴአትር ክፍል ሀላፊ የሆኑት እኒህ ሰው ናቸው ስለወጣቶቹ የነገሩኝ፡፡ ከእለት ጉርሳቸው ውጪ ሌላ የሌላቸውና ከማንም ምንም እንደማይፈልጉ የሚናገሩት ወጣቶቹ በቀላሉ ያዋሩኛል ብዬ
አልጠበኩም፡፡ እንዳሰብኩት ግን አልሆኑም፡፡ ከኔ ጋር ለማውራት ፍቃዳቸውን አልከለከሉኝም፡፡ ጥግ ይዘን ማውራት ጀመርን፡፡ እየሆነ ያለውን የሰሙ የአካባቢው ወጣቶች ተሰበሰቡ፡፡ ግርግሩን ፈራሁ፡፡ ወደ ድርጅቱ ግቢ ተያይዘን ገባን፡፡ የአካባቢው ልጆች ግን ‹‹ስለነሱ እኛን ጠይቂን፤ ነጋ ጠባ የምናያቸው የሚያስፈልጋቸውን የምናውቅ እኛ ነን›› አሉኝ፡፡ ያለ ምክንያት አይደለም እንዲህ ማለታቸው፤ እንደኔ ለአካባቢው እንግዳ የሆነ ሰው በመጣ ቁጥር ፍርሀታቸውን ያውቁታልና ሁሌም እንዲያ ይላሉ፡፡

“ፈራን መለያየት ፈራን” ይላል የሁለቱ ወጣቶች ልብ፡፡ የከበቡዋቸው የዚያ ሰፈር ልጆችም ‹‹እናንተን የሚለየው ሞት ብቻ ነው፡፡›› ይሏቸዋል፤ ግን ከዕለት ያለፈ ነገር ሊያደርጉላቸው አልቻሉም፡፡ እሱ ለሷ፤ እሷ ለሱ በሚሆኑት ነገር ተደንቀው የቀን ትዕይንት ካደረጓቸው ግን ከራረሙ፡፡ ዓለምፀሀይ ዘላለም ‹‹እድሜዬ 27 ነው›› አለችኝ፡፡ በደንብ ተመለከትኳት፤ ከዚህ አታልፍም፤ ጥቂት እውነት ብዙ መዘባረቅ የተቀላቀለበት ንግግሯ ከሚደጋገሙት መሀል እውነቶቹን እንድመርጥ አስገድዶኛል፡፡ በንግግሯ መሀል የእንግሊዝኛው ቃላት መደጋገም ሌላ ጥያቄ ያጭራል፡፡ አለምፀሀይ ጎበዝ ተማሪ ነበረች፤ ደብረ ማርቆስ ከተማ በሚገኘው ዋሸራ ብሮድቪው ኮሌጅ የሁለተኛ ዓመት የሴክሬተርያል ሳይንስ ተማሪ ሳለች የአእምሮ ህመም ስለገጠማት ትምህርቷን አቋርጣለች፡፡ (እሷ“ነቅዬ” ነው ትለኛለች ደጋግማ) አክስቶቿ ለማስታመም በሚል ወደ አዲስ አበባ ካመጧት በኋላ ረስተዋታል፡፡ ሄድ መለስ እያለች
ነገሮች እየተደበላለቁባት ስትነግረኝ አዲስ አበባ ከመጣች ሦስት ዓመት አልፏታል፡፡

ዝም ብለው ሲመለከቷት ከንግግር ቅልጥፍናዋና ጥንቅቅ ከማለቷ የአእምሮ ችግሯን ታስረሳለች፡፡ በቀላል ህክምና ለውጤት የምትበቃ ትመስላለች፡፡ ነገሩን የሚያውቅላት ይኑር አይኑር እንጃ እንጂ ብዙ ያነበበችም ለመሆኗ በንግግሯ የምታነሳሳቸው የዓለማችን ፀሀፍትና ፈላስፋዎች ምስክር ናቸው፡፡ እነሶቅራጥስ፣ አርስቶትልና ሌሎችም በአንደበቷ ሲጠቃቀሱ ይቺ ልጅ የሆነ ከአቅሟ በላይ የሆነባት፤ ሰው አልረዳ ያላት ነገር ቢኖርስ ብዬ ገመትኩ፡፡ ደግሞም ጠየኳት “በልጅነትሽ ምን መሆን ትፈልጊ ነበር?” ስል፡፡ ‹‹ሳይንቲስት መሆን፣ የፊዚክስ ሊቅ መሆን ፣ጠፈር ላይ መውጣት…” ለምጠይቃት
የምትሰጠኝ መልስ መጨረሻው ብቻ ነው ፈሩን የሚለቀው፡፡ በአብዛኛው በትክክል እየነገረችኝ ቆይታችን ቀጠለ፡፡

በወጣትነት እድሜ በተለይ በሃያዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የውስጥ ፍላጎቶቻችን የሚጋጩ ይመስለኛል፡፡ የሚያደምጥ የሚረዳ ሲጠፋ የሚፈልጉት ሳይገኝ ሲቀር ደግሞም የሚናገሩት ከማህበረሰቡ ለየት ሲል ‹‹ለየላት›› መባል ከዚያም ቤተሰብ መፍትሄ የሚለውን ሲያደርግ የአእምሮ ውጥረት ሲባባስ ጭንቀት ሲበረታ የባጥ የቆጡን መቀባጠሩ ቢያይል አይገርምም፡፡ በአለም ፀሀይ ህይወት ውስጥ ተመሳሳይ ነገር እንደተከሰተ ለመገመት አይከብድም፡፡ እሷንና ተወልጄ አድጌበታለሁ ያለችኝን ደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ ሰባት ሸዋ በር ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ከፖሊስ ጣቢያው ወረድ ብሎ ያለውን መንደር አስተያየኋቸው፡፡ የእሷ ፍላጎት ከማህበረሰቡ አመለካከት ጋር ሲጋጭና የምታነሳቸው የተለዩ ሃሳቦች ‹አበደች. እያስባላት በድግግሞሹ ተገፍታ ለአዕምሮ ህመም እንደተዳረገች ያስታውቃል፡፡

አበራ አጠገባችን ተቀምጧል፡፡

የምናወራውን እየሰማ ነው፡፡ አንዳንዴ በወሬያችን መሃል ሳቅ ይላል፡፡ ቀይ ረዥም ቆንጆ ወጣት ነው፡፡ “አበራ ተካ እባላለሁ፡፡ ተወልጄ ያደኩት አዲስ አበባ መነን አካባቢ ነው፡፡ እድሜዬ አስርን ሳይዘል ከቤተሰቦቼ ጋር ጥሩ ኑሮ ስንኖር ከሌሎች ዘመዶቻችን ጋር ተቀላቅለን መኖር ጀመርን፤ ያኔ ወላጆቼ ለዘመዶቻችን ጥለውኝ ሲሄዱ እኔም ከቤት ወጣሁ፤ የጎዳና ተዳዳሪ ሆንኩ፡፡ ዛሬ እድሜዬ ሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ይገኛል፡፡ አብዛኛውን እድሜዬን ያሳለፍኩት ጎዳና ላይ ነው፡፡” እያለ ስለራሱ አጫወተኝ፡፡ በአዲስ አበባ የተለያዩ ሰፈሮች፣ በባህርዳር፣ ምዕራብ ሸዋ ጎዳናዎች ብዙ ክረምትና በጋዎች ዝናብና ፀሀዩ ተፈራርቆበታል፡፡ የሌት ቁሩ የቀን ወበቁ ገርፎታል፡፡ እናም ዛሬ ከተላመደው የጎዳና ህይወት ከመውጣት ሞት የሚሻል የሚመስለው አበራ ቀለል አድርጎ ‹‹ቀን ያገኘሁትን እሰራለሁ፤ ማታ ማታ እዚህ አድራለሁ›› በማለት የየዕለት ኑሮውን በአጭር ዓረፍተነገር ገለጸልኝ፡፡ በነአበራ ህይወት ውስጥ ማንም አብሮ ከሚኖረው የተለየ ብዙዎች ያጡትን የማፍቀርና የመፈቀር ህይወት በፍቅር ውስጥ ቢታመሙ አስታማሚ፣ ቢራቡም ቢጠግቡም የሚያወሩት የማያልቅ፣ ደስታ የማይለየው ለሌሎች ቦታ የሌለው መሆን ብዙዎች ያልታደሉት እንዲህ ባዶቤት እንዳንለው ጎዳናላይ ሲገኝ ለየት ያለ ስሜት መፍጠሩ አይቀርም፡፡ሁለቱ ወጣቶች ስለተገናኙበት አጋጣሚ አበራ ያስታውሳል፡፡ “ አውቶቡስ ተራ ጀርባ ሰላም ጂም አካባቢ ቁጭ ብዬ መጣችና አጠገቤ ቁጭ አለች፡፡ ከዚያ ካንተ ጋ መሆን እፈልጋለሁ፤ አለችኝ ተግባባን፤ አብረን መኖር ጀመርን” ይላል፡፡ እሷም “በቃ ስለወደድኩት አብረን መኖር ጀመርን” ትላለች፡፡ የዚያ መንደር ወጣቶችም “እዚህ አካባቢ የመጡ ሰሞን ማንም ትኩረት አይሰጣቸውም ነበር፤ እየቆየ ግን እንደሌሎቹ የጎዳና ልጆች አለመሆናቸውን ስናይ በነሱ ተሳብን” ይላሉ፡፡

እሱ ማንም እንዳይነካት ጠባቂዋ ነው፡፡ የመንፈስ ጭንቀቷ አይሎ መረበሽ ስትጀምር ወደ ደረቱ አስጠግቶ ወደ ራሷ ይመልሳታል፤ አብረው ያገኙትን ተቃምሰው ተቃቅፈው ውለው ያድራሉ፡፡ ‹አንድም ቀን ከዚህ የተለየ ነገር አላየንባቸውም› ሲሉ ይናገራሉ ነጋ ጠባ የሚያዩዋቸው፡፡ እሱም “ ታሳዝነኛለች፤ ታውቂያለሽ ይቺ ልጅ ትረበሻለች፡፡ እኔ ሳባብላት ነው ዝም የምትለው፡፡ ደግሞ እወዳታለሁ” ይላል፡፡ ይህንን የተመለከቱ እውነተኛ ፍቅር ማለት ይሄ ነው አሉኝ፡፡ ከነሱ ውጭ የሆኑ የትዳርና የፍቅር ሕይወቶችን እያነሳሱ፡፡

እንደ ምሳሌ ከጠቀሱልኝ መሀል የሰሞኑን ሰርጎች ከውጥን እስከመጨረሻቸው ለተመለከተ የትዳር መሰረት የሆነውን ፍቅራቸውንም ለመዘነ በየፍርድ ቤቱም ሳይጋቡ ተፋቱ አይነት የፍቺ ጥያቄዎችን መብዛት ላየ ደግሞም የፍቺ ጥያቄ የሚቀርብባቸው ምክንያቶች ግልፅ የማይሆኑና ስስ መሆናቸውን ለሰማ
የጋብቻ ትርጉም ቢደናገረው አይገርምም፡፡ ሲዘፈን እንደምንሰማው ተፅፎም እንደምናነበው የትዳር መሰረቱ ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር ደግሞ ብዙውን ጊዜ ሳይታሰብ አንዳንዴም በመላመድ ይፈጠራል፡፡ የቱ ከልብ የሆነ የትኛው እውነተኛ ነው የሚለው በእያንዳንዱ ሰው ልብ የሚመዘን ነው፡፡ ፍቅር ሲታሰብ ምን አላት? ምን አለው? ከሚሉት ጀምሮ ከአቋም እስከ ዘሩ ከእውቀት እስከ አስተሳሰቡ ለክተው እስከሚጠብቁት ብዙዎችን አይተናል፡፡ ኑሮን ሀ ብለው ሲጀምሩም እንዲህ መሆኑን ባውቅ መች እገባበት ነበር? የሚሉት ብዙዎች ናችው፤ የሰው ባህሪ የጎደለውን መፈለግ ስለሆነ ሲይዙት ባዶ ቢመስል አይገርምም፡፡ ኑሮ ካሉት ሁለቱ ይስማሙ እንጂ የትም ቦታ በማንኛውም ሁኔታ ለመመስረቱ ብዙዎችን ስንሰማ ኖረናልና የእውነተኛ ፍቅር ምሳሌዎች ይኸው እነዚህ ተገኝተዋል፡፡ ለመገናኘትም አብሮ ለመኖርም ምክንያታቸው ፍቅራቸው ነውና ፡፡

“አንድ ቀን” አለኝ አብዲ የተባለ ወጣቶቹን የሚያውቅ የዚያ ሰፈር ወጣት፡፡ ‹‹ሀይለኛ ዝናብ እየዘነበ ወደቤት ለመግባት እየሮጥኩ ስመጣ እነሱ ግን ድንጋይ ላይ ተቃቅፈው ቁጭ ብለው ዝናቡ በላያቸው ላይ ይወርዳል፡፡ በጣም ደነገጥኩ፤ እነሱ ጋ የማይዘንብ ሁሉ መሰለኝ፡፡ ቀስ እያልኩ መራመድ ስጀምር ተመስጠው እያወሩ መሆናቸውን ልብ አልኩ፡፡ በፍቅራቸው እንደሁልጊዜው ቀናሁ፡፡ ፅናታቸውም አስገረመኝና ምነው በሞቁት ቤቶች መሀልም ይህን መሰሉ ፍቅር በሞላ አልኩ፡፡” ሌላዋ ወይዘሮ ደግሞ በትዳር መሀል ሳይቀር የሚያጋጠሙትን እያነሳን ሁሌም እንገረምባቸዋለን አለች፡፡ ”ዛሬ ማነው የአእምሮ ህመምተኛ የሆነችኝ ሴት እንዲህ በትዕግስት ተንከባክቦ ከችግር፣ ከረሀብና ከጥማት ጋር ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ እየኖረ የሚያስታምም? ከሞቀ ቤታቸው እንኳ ብዙዎች የጎደለባቸውን ፍለጋ ሲሄዱ ነው የምናየው፡፡ እነዚህ ወጣቶች ግን ሲያማት እዚሁ እያስታመመ አብረው እየኖሩ ነው፡፡ነገረ ስራቸው ሁሉ እውነት ነው፡፡ እሱም መስራት የሚችል ቆንጆ ወጣት ነው፡፡ እሷም የተማረች ቀልጣፋ ወጣት ናት፡፡ ትንሽ ህክምናና ምክር ድጋፍ ቢያገኙ ተቆርቋሪ ሀላፊነት የሚሰማው ሰው ቢያግዛቸው በቀላሉ ራሳቸውን ችለው የሚያስመሰግኑ ወጣቶች ይሆኑ ነበር” አሉኝ፡፡

እነዚህ ወጣቶች በተለይ እሷ አዲስ አበባ ጉለሌ አካባቢ አክሰቶች እንዳሏት ትናገራለች፡፡ በየጊዜው መንገድ ላይ እንደምታገኛቸው ስትነግረኝ በአካባቢው ያሉ ወጣቶች ደግሞ በአንድ ወቅት ዘመዶችዋ መጥተው የተፈጠረውን አወጉኝ ፡፡ “አንድ ቀን ሁለት አክስቶችዋ መጡ፡፡ ከዚያ ልጃችንን ይዘን መሄድ እንፈልጋለን አሉ፡፡ እና ምን እናድርግላችሁ ስንላቸው ከሱ ነጥሉልን አሉን፤ መጀመሪያ ደብቆ ያመጣት መስሎን ውሰዷት ብለን ነበር፡፡ በፍፁም እሱንና ውሻዬን ትቼ አልሄድም፡፡ ስትል የሆነ ብር ወርውረውላት ሄዱ፡፡ ከዚያ በኋላ ለበዓል እንኳን መጥተው አላዩዋትም፡፡ ስለዚህ ቢወስዷትም የሱን ያህል ስለማያስታምሟት እሱ ይሻላታል›› ይላሉ፡፡

በነበረን ጥቂት ቆይታ ስለጎዳና ህይወት አስከፊነት አበክሬ ለመናገር ብሞክርም ሀሳቤ መፍትሄ መፈለግ መሆኑ ያልገባቸው ሁለቱ ወጣቶች በጥላቻ የተመለከቱኝ መሰለኝ፡፡ እሱን ወደ ስራ እሷን ወደ ህክምና የሚወስዳቸው ቢገኝ የሚለውን የልቤን ሀሳብ ካወቁ ቢታዘቡኝ አይገርምም፡፡ እነሱ የዘወትር ፍርሀታቸው መለያየት ነውና፡፡ እናም የዛሬው ፀሀይ የመጪው ክረምት ዝናብና ጎርፍ ቢያሰጋቸውም ይኸው አሉ፡፡ ለኛ ብዙ ነገር የጎደላቸው ቢመስለንም ፍቅር ህይወታቸውን ሙሉ አድርጎላቸዋል፡፡ የአብሮነት ኑሮአቸውን ይቀጥላሉ፤ መለያየትን ብቻ እንደፈሩ፡፡

(በአዲስ አበባ የሚታተመው ቁምነገር መጽሔት ላይ ታትሞ የወጣ)

ፕረዘዳንት ባራክ ኦባማ ከ 10 አመት አስከ እድሜ ልክ እስራት ሊፈረድባቸው ይችላል

$
0
0

 ውንጀላውም ታሊባን የተባለውን አሸባሪ ድርጅት በሰው ሃይል መርዳት (የታሊባን እስረኞችን መልቀቅ) የሚል ነው። ፎክስ ኒውስ ነው የዘገበው።

 

 

ሚሊዮኖች ድምጽ – ኢሕአዴግ የቁጫ ሕዝብን መብት እንደገና ረገጠ – የቁጫው ሰልፍ ታገደ

$
0
0

የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ በሚል መርህ በቁጫ ሊደረግ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ መተላለፉ ታወቀ። ከአዲስ አበባ የቅስቀሳ መኪና፣ ሜጋፎኖች፣ በራሪ ወረቀቶችና ፖስተሮች ይዞ ወደ ቁጭ የሰማራዉ ቡድን ከትላንት በስቲያ ሰላም በር ከተማ የደረሰ ሲሆን፣ ከዞኑና ወረዳዉ የአንድነት አመራርና አባአት ጋር በመሆን፣ ትላንት በማለደ ወደ ቅስቀሳ በሚሰማራበት ጊዜ፣ ፖሊሶች ቅስቀሳዉን አስቆመዋል። ከአዲስ አበባ የሄደው ቡድን እንዳለ እና የወረዳው አስተባባሪዎች በሙሉ ታስረዉ ዉለዋል።

Kucha

የቁጭ ህዝብ በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ብሶት ያለው እንደሆነ ይታወቃል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ 400 የሚሆኑ የወረዳው አባዎራዎች እስከአሁን ድረስ በእሥር ላይ እንዳሉ ይታወቃል። የሕዝቡን ብሶት የሚያወቁት የወረዳዉ ባለስልጣናት አስቸኳይ ስብሰባ ትላንት ጠርተው፣ ከዞኑ መመሪያ ካላገኝን የታሰሩትን አንፈታም በሚል ቀኑን ሙሉ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ የሰልፍ ቅስቀሳ እንዳይኖር አድርገው ዉለዋል።

kucha1

ትላንት ሲመሽ፣ ከአዲስ አበባ ለቅስቀሳ የተሰማሩ የአንድነት አባላትን ፣ በጉልበትና በወታደር አጅበው ከወረዳው እንዲወጡ አድርገዋቸዋል። በሕዝቡና በባለስልጣናቱ መካከል ከፍተኛ ዉጥረት የሰፈነ ሲሆን፣ ከቁጫ ወረዳ እንዲወጡ የተገደዱት፣ ከአዲስ አበባ የሄዱ የአንድነት አባላት ይዘው የመጡትን የቅስቀሳ መኪናና ሜጋፎኖች ይዘው ወደ አዳማ ናዝሬት ተሰማርተዋል።

የአንድነት ፓርቲ ላለፉት አንድ አመት በደሴ ሁለት ጊዜ፣ በአዲስ አበባ ሁለት ጊዜ፣ በባሕር ዳር ሁለት ጊዜ፣ በጋሞ ጎፋ፣ በጂንክ፣ በፍቼ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በጎንደር፣ ፣ በአዳማ ሰልፎች ያደረግ ሲሆን፣ እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ በአዳማ እንዲሁም በደብር ማርቆስ ነገ ሰልፍ ያደርጋል። በመቀሌ ለሳምንት ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲደረግ ቆይቶ፣ ሰልፉ ነገ ሊደረግ ዛሬ ፣ «መቀሌ እንኳን አንድነት ቅንጅትም አልደፈራትም» በሚል እበ አባይ ወልዱ የአንድነት የቅስቀሳ መኪናዎችን በማገት፣ የአመራር አባላቱን ሁሉ በማሰር ሰልፉ እንዲጨናገፍ ማድረጋቸው፣ በተመሳሳይ ሁኔ በባሌ/ሮቢ ሰልፉን ካደረጋችሁ ከፍተኛ ደም መፋሰ ይኖራል የሚል ዛቻ ባለስልጣናቱ በማቅረባቸው፣ ለሕዝብ ደህንነት ሲባል ሰልፉ ነገ ሳይደረግ መቅረቱ ይታወሳል።

የሚሊዮኖች ንቅናቄ ነገ ከሚደረጉት የደብረ ማርቆስና የአዳማ ሰልፍ ቀጥሎ በነቀምቴ፣ በድረዳዋ፣ በአዋሳ፣ በመቀሌ፣ በደብረ ታቦር፣ በወገራ፣ በአርማጭሆ፣ በአሶሳ ፣ በለገጣፎ እና ለሁለተኛ ጊዜ በጂንካ ሰልፎች ለማድረግ እቅድ አለው።

ምንጭ-  andinet.org

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live