Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በትግራይ አለመረጋጋት አለ!

$
0
0

Abrha Destaጓዶች ህወሓቶች በጣም ደንግጠዋል። ባሁኑ ሰዓት በብዙ የሑመራ አከባቢዎች፣ ማይጨው (ሽኮማዮ)፣ ዓዲጎሹ (ተከዘ)፣ ሐውዜንና አፅቢ ህዝቡን ለመቆጣጠር ፖሊሶችና ምልሻዎች ተሰማርተዋል። ትናንት ማታ (ቅዳሜ ማታ) አቶ መሰለ ገብረሚካኤል (የዓረና ስራ አስፈፃሚ አባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና አስተባባሪ) ፊታቸው በሸፈኑ ታጣቂዎች ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወስደው ምርመራ ተደርጎባቸዋል። ትናንት ቅዳሜ በእንዳ አብርሃ ወ አፅብሃ የዓረና ልሳን ለህዝብ ሲያድሉ የነበሩ የዓረና አመራር አባላት አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሞገስ ፣ አቶ ኃይለኪሮስ ታፈረና መምህር ይልማ ኩኖም በህወሓት አስተዳዳሪዎች ክፉኛ ተደብድበው ሆስፒታል ገብተዋል። አቶ ቴዎድሮስ ሞገስ ተደብድቦ በፖሊስ ታስረዋል። አቶ ገረችአል ግደይ (አባ ሐዊ) የተባለ ያከባቢው አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስን እንዲታሰር ስለወሰነ በሚል ምክንያት በዉቅሮ ከተማ ታስሮ ይገኛል። አሁን የእንዳ አብርሃ ወ አፅብሃ አከባቢ በፖሊሶች እየተጠበቀ ነው። ሁለትና ከሁለት በላይ ሁኖ መንቀሳቀስ ተከልክሏል። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ አይፈቀድም። በአፅቢ ወንበርታ ላለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመግታት የተቃውሞው መሓንዲስ የተባለውን አቶ ሕድሮም ሀይለስላሴን በሰበብ አስባቡ ለማሳሰር ዝግጅት መጀመሩ ከህወሓት ፅሕፈትቤት መረጃ ደርሶኛል። በሐውዜን ከተማ ዓረና ተብሎ የተጠረጠረ ሁሉ ድብደባ ተፈፅሞበታል። ከሐውዜን እንዲወጣም እየተደረገ ነው። አሁን እሁድ ግንቦት 24, 2006 ዓም ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ በእግሪሓሪባ መንደር ብዙ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች ተሰማርተዋል። አቶ ሙኡዝ ፀጋይ የተባለ ያከባቢው የዓረና አስተባባሪ ቤት ተከቧል። መንቀሳቀስ አይችልም። በያንዳንዱ የእግሪሓሪባ መኖርያቤት በር ሦስት ፖሊሶች ይገኛሉ። ዛሬ በህዝቡና አስተዳዳሪዎች አለመግባባት ተፈጥሮ ነበረ። ባጠቃላይ ባሁኑ ሰዓት በትግራይ አለመረጋጋት አለ። ይህን ሁሉ ችግር እየፈጠረ ያለ ግን ህወሓት ራሱ ነው። ከሰለማዊ ተቃውሞ ዉጭ ምንም ዓይነት ዓምፅ በሌለበት ህዝቡ ሊያምፅ ይችላል በሚል ስጋት ብቻ የፀጥታ ሃይሎች እያሰማራ ነው። ህዝቡም ተደናግጧል። እኛ ግን ብዕር እንጂ ጠመንጃ አልያዝንም።

በትግራይ አስቸኳይ መፍት ሄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ተባራክተዋል። መነጋገር ይኖርብናል።


ትህዴን በሺህ የሚቆጠሩ ታጋዮችን ማስመረቁን አስታወቀ (የሠራዊቱን ቪድዮ ይዘናል)

$
0
0

ለበርካታ ወራት ሲሰለጥኑ የቆዩ ብዛት ያላቸው ረመፅ በሚል ስያሜ የሚታወቁ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ሰልጣኞች የድርጅቱ ሊቀመንበር ታጋይ ሞላ አስገዶምና ሌሎችም የሰራዊት አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ መመረቃቸውን ድርጅቱ አስታውቆ ቪድዮውን ልኳል።

ትህዴን በሺህ የሚቆጠሩ ታጋዮችን ማስመረቁን አስታወቀ (የሠራዊቱን ቪድዮ ይዘናል)

የሚሊዮኖች ድምጽ ግብረ ኃይል በዳያስፖራ –ዝምታችን እስከመቼ ?

$
0
0

በቅርቡ አንዲት ታላቅ ጥቁር አሜሪካዊት የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ከዚህ አመት በሞት አልፈዋል። ማያ አንጀሎ ይባላሉ። እኝህ ታላቅ ሴት ጸሃፊ፣ ገጣሚም ነበሩ። አንድ ጊዜ ማያ አንጀሎ ሲናገሩ ፡ “We may encounter many defeats but we must not be defeated.” ብለው ነበር።

በዚህ አለም ስንኖር፣ በግለሰብ ደረጅ፣ በቤተሰብ፣ በአገር የተለያዩ ፈተናዎች ያጋጥሙናል። ስህተቶች እንሰራለን። እንወድቃለን። ሽንፈቶች ያጋጥሙናል። የምናቀርቅርበት፣ የምናዝንበት፣ የምናለቅሰበት ጊዜ አለ። በአገር ጉዳይ ያለውን ሁኔታ እንኳን ስንመለከት፣ ከስድሳዎች የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ ፣ በተለይም በአገራችን እኩልነት፣ ዴሞክራሲ፣ ሰላም፣ የሰብአዊ መብቶች መከበር፣ የሕግ የበላይነትን በተመለከተ ፣ ከተገኙት ድሎች ይልቅ፣ ሽንፈቶቻችን በጣም ይበዛሉ። በስድሳዎቹ የነበረው የለዉጥ እንቅስቃሴ መስመር ስቶ ወደ ማይሆን ቦታ ወሰደን። በዚያ ጠባሳ ምክንያት ፖለቲክ እንደ ኮረንቲ ይፈራ ጀመር።ደርግ ወድቆ ኢሕአዴግ ሲተካ፣ «አዲስ ንጉስ እንጂ ለዉጥ መቼ መጣ» እንዳለው ዘፋኙ የታሰበለትም የተጠበቀው ሳይሆን ቀረ። በዘጠና ሰባት ታሪካዊ የሆነ የቅንጅት እንቅስቃሴ ታያ። የኢሕአዴግ ዱላ ተጨምሮበት፣ በመሪዎቹ መካከል የተፈጠረው ልዩነት የትግሉን ግለት አወረደው። እንደገና ሽንፈት አጋጠመን። እንደገና አምባገነኖች ለጊዜ ተሳካላቸው።

ላለፉት አንድ አመት፣ የሚሊዮኖች ንቅናቄ በሚል መርህ ፣ የወዳደቀዉን በማንሳት ፣ የተሰባበረዉን በመጠገን፣ ብዙዎች ለአሥርተ አመታት መስዋእትነት የተከፈለበትን ትግል ከግብ ለማድረስ፣ ተጨባጭ የሆኑ ሥራዎችን መታየት ጀምረዋል። ለዉጥ ሊያመጣ የሚችለው ኃይል የህዝብ ኃይል ብቻ ነው። ይህንን ኃይል ከማደራጀት፣ ከማንቃት፣ ከማሰባሰብ ዉጭ ሌላ የተሻለ አማራጭ የለም። ሕዝብን ከጎኑ ያላደረገ ትግል ዋጋ የለውም። የሚሊዮኖች ንቅናቄ ሕዝብን ማእከል ያደረግ የሚሊዮኖች ንቅናቄ ነው።

ብዙዎች ከጊዜ ወደ ጎዜ ከሚሊዮኖች አንዱ ነን እያሉ ትግሉን እየተቀላቀሉ ነው። የሶሊዳሪቲ ንቅናቄ፣ የብዙ ደርጅቶች ስብስብ የሆነው ሸንጎ፣ የሽግግር ምክር ቤቱ እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶች የሚሊዮሞች ንቅናቄ አካል ሆነው በጋራ እየሰሩ ነው። በሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል ዙርያ መሰባሰቦች እየታዩ ነው። ይህም አስደሳች ዜና ነው።

ነገር ግን አሁንም ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆነ ወገኖቻችን ያለፉትን ጠባሳዎችን እየተመለከቱ፣ ተስፋ ቆርጠው፣ እጃቸውን ለፍርህትና ለባርነት አሳልፈው ሰጠው፣ ዝም ማለትን የመረጡ አሉ። ለነዚህ ወገኖቻችን የማያ አንጀሎ አባባል ልናካፍላቸው እንወዳለን። “We may encounter many defeats but we must not be defeated.” እንላቸዋለን። «ዝምታችን እስከመቼ ነው ?» እንላቸዋለን።

የሚሊዮኖች ንቅናቄ መጪው እንቅስቃሴዎች በአዳማ/ናዝሬት፣ በደብረ ማርቆስ፣ በደብረ ታቦር ይሆናል። ከነዚህ ከሶስት ከተሞች በተጨማሪም፣ ከሃላፊዎች እውቅና ከተሰጠ ፣ በአርማጭሆ፣ በወገራ እና በቁጫ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ። ቢያንስ በአንድ ቀን ብቻ፣ ከሶስት እስከት ስድስት ባሉ ከተሞች የአንድነት ፓርቲ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው። ሕዝቡ ፍርሃትን አውልቆ፣ ያለፉት ሽንፈቶች ተስፋ ሳያስቆርጡት፣ ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለሕግ የበላይነት፣ ለፍትህ ፣ ለዲሞክራሲና ለእኩልነት ድምጹን ለማሰማት መዘጋጀቱ ትልቅ ድል ነው።

እንግዱህ ይሄንን ታሪካዊና አገራዊ እንቅስቃሴ እንቀላቀል። ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ። ነጻነት ዋጋ ያስከፍላል። ሌሎች ትልቅ ደረጃ የደረሱት ጥረው ግረው ነው። ሌሎች ነጻነታቸው ያገኙት መስዋእትነት እከፍለው ነው። እኛም እንደዚሁ ዋጋ ለመክፈል እንዘጋጅ። ለኛ መብት ሌሎች እንዲጮሑልን መጠበቅ የለብን። ለመብታችን እያንዳንዳችን እንነሳ ።ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን።

MILLIONS OF VOICE FOR FREEDOM !

 

ሁለት አዳዲስ የራድዮ መርሃግብር ስርጭቶች በኢንተርኔት አገልግሎታቸውን ጀመሩ።ይበርቱልን!

$
0
0

ሚልዮኖች እንደመሆናችን በተለያዩ አቀራረቦች እና  ስልቶች የሀገራችን ምሁራን ሊያንፁን ይገባል።ያደጉትን ሀገሮች ትተን የአፍሪካ ሃገራትን ለምሳሌ እንደ ዑጋንዳ ያሉ ሀገሮች በዋና ከተማቸው ብቻ ከሃምሳ በላይ ኤፌ ኤም ራድዮኖች አሉ።ሕዝብ እንደምርጫው ይሰማል እራሱን ያይበታል።መገናኛ ብዙሃኗ በአፈና መንግስት በታገተባት ሀገራችን ኢትዮጵያማ ምን ያህል እንደሚቀረን ከእዚህ መረዳት ይቻላል።ኢትዮጵያ ወጣቶቿ እየደረሱላት ነው።ሁለት አዳዲስ የራድዮ መርሃግብሮች ወደ መስመር ገብተዋል።የመገናኛ ብዙሃን በተለያየ አቀራረብ እና ፈጠራዎች በተለይ በዲያስያስፖራው እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች ለሚሰማው የሃገርቤት ነዋሪ የራሳቸውን በጎ ተፅኖ መፍጠራቸው ሳይታለም የተፈታ ነው።እናም እናበረታታቸው።አይዟችሁ ምን እናግዝ? እንበላቸው።እኛ መናገር ቢያቅተን የሚናገሩልንን ሃሳብ የሚያመነጩትን ማበረታታት ተገቢ ነው።

ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ቀደም ብለው ለነበሩ ኢትዮጵያውያን የብሮድካስት ስርጭቶች ተጨማሪ እገዛ የሚያደርጉ ግን ደግሞ አስፈላጊ የሆኑ አዳዲስ የራድዮ መርሃግብር ስርጭቶች ተጀምረዋል።

የመጀመርያው ”ዋዜማ” የተሰኘ ራድዮ ሲሆን ስለ ዋዜማ / About Wazema በሚለው አርዕስት ስር እንዲህ ይላል -



“ዋዜማ ሬዲዮ” በስደት ባሉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ ሳምንታዊ የፖድካስት ሬዲዮ ስርጭት ነው። ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ልንጨዋወት መክረናል። እግረመንገዳችንን ጎረቤቶቻችንን የሚመለከቱ ጉዳዮች ስናነሳ ብንገኝም የእንግዳ ተቀባይነት ወጋችን ሆኖብን ነው።
አዘጋጆቹ መስፍን ነጋሽ፣ ደረሰ ጌታቸው፣ አርጋው አሽኔ እና መዝቡ ኃይሉ ነን። ብቻችንን ግን አይደለም፣ አብረውን የሚጓዙ መደበኛ ተሳታፊዎችም ይኖሩናል።
ዝግጅቶቻችን አገራችን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ለማድረግ እንድትችል የሚመኙ ናቸው። ዓላማችን ማንኛውም የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም ሌላ አይነት ቡድን የማይቆጣጠረው አንድ ተጨማሪ የውይይት መድርክ መፍጠር ነው።
ዋዜማ ሬዲዮ!

”ዋዜማ” ራድዮ ከፖለቲካዊ ጉዳዮች በተጨማሪ ማኅበራዊ እና ኪነጥበባዊ ዝግጅቶችም ተካተውበታል።
ድረ-ገፁን ከእዚህ በታች ያለውን በመንካት ማዳመጥ ይችላሉ http://www.wazemaradio.com 

ሁለተኛው በተለይ በኖርዌይ እና አካባቢ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴ ላይ የሚያተኩር ነገር ግን ለመላው ዓለም በኢንተርኔት የሚዳረሰው ‘‘የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ” በተሰኘ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ለማምጣት የሚሰሩ ግለሰቦችንም ሆነ ድርጅቶች በተለያየ መንገድ የሚደግፍ ድርጅት የተጀመረ ነው።



በድረ-ገፁ ላይ  ”የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ” እንዲህ የሚል አረፍተ ነገር አለ -
”ሰላም ጤና ይስጥልኝ መላው የስርጭታችን ታዳሚዎች ዛሬ ወረሃ ግንቦት 23ኛ ቀን ላይ እንገኛለን የዴሴሶን ራዲዮ የሙከራ ፐሮግራም ለመጀመሪያ ግዜ ለአድማጭ የሚደርስበት ቀን ነው ::ክብራትና ክቡራን ኢትዮጲያውያን ወገኖቻችን ለዘመናት ያጣነውን ስላምና እኩልነት ለማስመለስ የሚታገለው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የራዲዮ ስርጭቱን ለአየር ማዋል የቻልበት የመጀመሪያ ቀን ላይ በመድረሳችን በመላ ኖርዌይ ለሚገኙ አባላትና ለደጋፊዎቻችን የደስታ መልእክታችን ይደረሳችሁ::
ዝግጅቶቻችን ዘወትር ቅዳሜ ለአድማጭ ይደርሳል በቅርቡ ቆሚ ዝግጅቶቻችንን እናቀርብላችኋለን ይጠብቁን !!”
”የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ” ራድዮ ድረ-ገፅ http://www.dceson.no/news/2014/05/31/dceson-radio-opening-program-may-31-05/ ነው።

ከላይ የተጠቀሱት ራድዮኖች ለኢትዮጵያውያን በጎ መንገዶችን ማመላከት ብቻ ሳይሆን ቀደም ብለው ለነበሩ የብሮድካስት አገልግሎቶችም ሆነ በኢትዮጵያዊነት ዙርያ የተሻለ ለሚያልሙ ሁሉ አጋዥ፣መንገድ አመላካች፣እና አዳዲስ ሃሳቦች አመንጪ እንደሚሆኑ ይታሰባል።ይበርቱልን!

ጉዳያችን 
ግንቦት 25/2006 ዓም (ጁን 02/2014)

Hiber Radio: ኃይለመድህን አበራ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው፤ * ክርስቲያን በመሆኗ ሞት የተፈረደባት ትውልደ ኢትዮጵያዊት ልትፈታ ነው

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ግንቦት 24 ቀን 2006 ፕሮግራም

> ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የቀድሞ የዓለም ባንክ አማካሪ እና ተመራማሪ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሸንጎ በሲያትል ላዘጋጀው ስብሰባ የሚያቀርቡትን የመፍትሄ ሀሳብ መሰረት አድርጎ ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ(ሙሉውን ያዳምጡት)

ኢትዮጵያውያን በምግባረ ሰናይ ተግባራቸው የሚዘክሯቸው የሰዎች ለሰዎች መስራች ካርል ሲዘከሩ (ልዩ ዝግጅት)

ግንቦት ሃያ ይዞት የመጣው ምስቅልቅል እና ሰብዓዊ ውርደታችን በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሪፖርት ሲዳሰስ( ልዩ ዘገባ አለን ሙሉውን ያዳምጡት)

>

አቶ ጴጥሮስ አሸናፊ የረዳት አብራሪውን ጉዳይ ከሚከታተሉት አንዱ ከሲዊዝ ጄኔቫ ለህብር ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

ውይይት እንደገና ዩኒየን እንደገና መደራጀት ?

ዜናዎቻችን

- በትግራይ አለመረጋጋት መኖሩ ተገለጸ

* የአረናን ልሳን ያደሉ ተደብድበው ሄስፒታል ገብተዋል

- ከአውስትራሊያ የሶማሌ ክልል ተወላጆች አዜብ መስፍን ከውጭ ኩባንያ ጋር ሆነው ከክልሉ ለተወሰደ መሬት ተጠያቂ መሆናቸውን ገለጹ

- ጅቡቲ አጥፍቶ መጥፋት በአገሬ ፈጸሙ ካለቻቸው ሁለቱ አንዱ ከኢትዮጵያ የሄደ መሆኑን ገለጸች

- የክርስትና እምነት ተከታይ በመሆኗ በሱዳን ሞት የተፈረደባት ትውልደ ኢትዮጵያዊትን የአገሪቱ ባለስልጣናት ልንለቅ ነው አሉ

- ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡትን ጦማሪያን ፖሊስ መንግስት ሊገለብጡ ነበር ሲል ቀጠሮ ጠይቆ ተፈቀደለት

_ ፍርድ ቤቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ሽብር የለም ሲል ውድቅ ያደረገውን የ28 ቀን ቀጠሮ መቀበሉ ህጋዊ መሰረት እንደሌለው ታውቋል

_ ኤርትራ ወጣት ዜጎቼ በህገወጥ ደላሎች ሳቢያ ከአገር እየወጡብኝ ነው አለች

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

የሕዳሴ አብዮት! (ተመስገን ደሳለኝ)

$
0
0

ተመስገን ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ)

የዛሬይቱ ኢትዮጵያችን ‹‹አብዮታዊ ሁኔታ›› ላይ ለመድረሷ በብዙሃን ዜጐች ዕይታም ሆነ፤ ሂደቱን በተከታተሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ምሁራን ምልከታ የማይታበል ሐቅ ሊሆን መቃረቡ በዚህ ተጠየቅ ለማነሳው አጀንዳ ገፊ-ምክንያት ነው፡፡ በአናቱም ባለፈው ሳምንት ‹‹የ‹ቀለም› አብዮት ናፍቆት›› በሚለው መጣጥፍ ላይ ለማሳያነት የጠቀስኳቸው ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ነገረ-ንዋያዊ ችግሮች ተደማምረው፣ ሀገሪቷን በርቀት እንደታዘብናት ሶቪየት ሕብረት፣ አሊያም በቅርበት እንዳስተዋልናት ሶማሊያ በመጪዎቹ ጥቂት ጊዜያት የመፈራረሷን አይቀሬነት ማስረገጣቸውን ልብ እንላለን፡፡ ከዚህ ክፉ የታሪክ ዕጣ ለመታደግም ከሁለት አስርታት በላይ ያስቆጠረውን ይሄን አሮጌ ሥርዓት መቀየር ብቻውን ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ እንደማይችል ዛሬ ግልፅ እውነታ ሆኗል፤ ምክንያቱ ደግሞ ለዘመናት በገዥነት የተንሰራፋው የፖለቲካ ባሕልም አብሮ ካልታደሰ ነገሩ-ሁሉ ‹‹ታጥቦ ጭቃ…›› ከመሆን አለመዝለሉ ነው፡፡

እናም ወደዚህ ከፍታ ለመሻገር ሶስተኛው አብዮት ብቸኛ መፍትሔ የመሆኑ ጉዳይ አከራካሪ አይደለም፤ ይህ ታላቅ ንቅናቄ ‹‹የሕዳሴ አብዮት›› በሚል ስያሜ ቢጠቃለል፣ ሂደቱ አንድም ኢህአዴግን ከክፉ ስራዎቹ ከመግታት ባለፈ፣ ኢትዮጵያን በሁለንተናዊ መልኩ የማደስና የተረጋጋ የፖለቲካ ማሕበረሰብ መፍጠርን የመሳሰሉ ተልዕኮዎችን በቀላሉ ወደ መሬት ለማውረድ ያስችላል፤ ሁለትም ከለውጡ ጋር የተያያዙ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ከስያሜው አንድምታ አንፃር እየቃኙ በቀላል መንገድ ለመተንተን ጠቀሜታ ይኖረዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ አምኜም በአዲስ መስመር የሕዳሴን ታሪካዊ ዳራ፣ አተገባበር እና ተያያዥ ጉዳዮችን እየጠቃቀስኩ ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡

 ‹‹ህዳሴ›› ሲባል…

በ5ኛው ክፍለ ዘመን ከጀርመን የተነሱ ጎዝ፣ ቫንዳልና ቡርጉንዲያኖችን ጨምሮ ሰባት ጎሳዎች፣ በወቅቱ ከፊል አውሮፓን ያስተዳድር የነበረውን ልዕለ-ኃያል የምዕራብ ሮማ ኢምፓየር አንኮታኩተው ግብዓተ-ፍፃሜውን ዕውን አደረጉት፡፡ ይህም የኃያሉ አገዛዝ ፍፃሜ ፕላኔታችን በአዲስ የፖለቲካ ባሕል እንድትዋጅ ሌላ የታሪክ ምዕራፍ ከፈተ፡፡ የዚህ መነሾም አሸናፊዎቹ ጀርመናውያን ጎሳዎች የአስተዳዳሪነት ችሎታም ሆነ ልምዱ ስላልነበራቸው የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም የሮማ ቤተ-ክርስቲያን እና ፊውዳሎቹ ሥልጣኑን ሙሉ በሙሉ በመቀራመታቸው ነበር፡፡ መላ ግዛቱም ሥልጣኔ-ጠል (Barbarism) እየተባለ የሚጠራውንና እስከ 15ኛው ክፍለ ጊዜ ድረስ በዘለቀው ‹‹የጨለማው ዘመን›› ውስጥ ያልፍ ዘንድ ተገደደ፡፡ ይህን ተከትሎ ትምህርትም ሆነ መንግስታዊው አስተዳደር በኃይማኖታዊ ቀኖና እንዲበየን ተፈረደበት፡፡ በወቅቱ አብያተ-ክርስቲያናት በብዛት ከመታነፃቸው ባለፈ አይን የሚሞላ መሰረታዊ ልማት ባለመዘርጋቱ፣ ከተሞች እጅጉን ቆርቁዘው የገጠሩን ገፅታ እስከመላበስ ደርሰው ነበር፡፡ ከሁሉም የከፋው ደግሞ መመራመር፣ መጠየቅና አለማዊ እውቀትን መፈለግ ከደመ-ቀዝቃዛዎቹ ‹‹መንፈሳዊያን›› አስተዳዳሪዎች ዘንድ ምድራዊ ፍዳን ለመቀበል መዳረጉ ነበር፡፡

በዚህ መልኩ ክፍለ-አህጉሩ ሰባትና ስምንት መቶ የመከራ ዓመታት ካሳለፈ በኋላ፣ የጣሊያኖቹ ፍሎረንስ፣ ቬነስ እና ሮማ ከተሞች ከዘመኑ በተለየ እውቀት ፈላጊና አንሰላሳይ ልጆቻቸው መናጥ ጀመሩ፡፡ ይህንን የመነቃቃት መንፈስ በሥራዎቹ በማካተት የዘመኑ ዝነኛ ባለቅኔ ዳንቴ አሊጋሪ በቀዳሚነት ይታወሳል፡፡ በ15ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ደግሞ መነቃቃቱ መላ ጣሊያንን በማዳረስ በምርምር ውጤት (በሳይንስ) መቃብር ላይ ተንሰራፍቶ የነበረውን ኃይማኖታዊ አስተዳደር ዳግም እንዳያንሰራራ አድርጎ አፈራረሰው፡፡ ይህ አይነቱ የለውጥ መንፈስ ከጣሊያን ባሻገር ከአልፕስ ተራሮች ጀርባ ባሉ የአውሮፓ ሀገራት ድረስ በመዛመቱም ታሪክ ይቀየር ዘንድ ግድ ሆነ፡፡ ለሁነቱም ዋናው ተዋናይ ሕዝባቸውን ከተዋጠበት የጨለማ ዳዋ ለማላቀቅ ሲሉ የጥንታዊያኑ ግሪክ እና ሮማ የተዘነጉ የአሰላሳዮችን የአእምሮ ውጤት መመርመር ቀዳሚ ስራዎቻቸው ያደረጉት የጊዜው ጠቢባን እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ ታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ባህል፣ ስነ-ጽሁፍ፣ ሞራል እና መሰል ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ እውቀቶችን መልሶ በመመርመር ጠቃሜታውን ለይቶ ማሰራጨትን የቀን ተቀን ሥራ ማድረጋቸው የማታ ማታ ለስኬት አብቅቷቸዋል፡፡ እነሆም የታሪክ ምሁራን ‹‹ሕዳሴ›› (Renaissance) ብለው የሚጠሩት ይህንን ሁነት ነው፡፡

በርግጥም ሕዳሴ የታሪክ ሀዲድን ተከትሎ የኋሊት በመመለስ የማንፃት (የመታደስ) ተግባር የሚያከናውን የሳይንስ ዘርፍ ነው፡፡ ይህም ጥንታዊውን ዘመን ዛሬ ላይ እንዳለ ማንበር ሳይሆን፤ የቀደመውን ሥልጣኔ የወደቀበትን ህፀፅ መርምሮ ለዘመኑ የሚበጀውን አንጥሮ በማውጣት፣ ያረበበውን ማሕበራዊ ፍዝነት እና ኋላቀርነት አንገዋሎ በመጣል ላይ የሚያተኩር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፍልስፍና መሆኑ አፅንኦት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ምዕራባውያን ለደረሱበት የሥልጣኔ ከፍታ ዋናው መሰረት የተጣለው በሕዳሴው ዘመን ስለመሆኑ ራሳቸው ይመሰክራሉ፡፡ ኮፖርኒከስ፣ ጋሊሊዮ፣ ቦይል፣ ሀአርቬይ፣ አይዛክ ኒውተን፣ ሊዎናርዶ ዳቪንቺ፣ ሚካኤል አንጀሎን የመሳሰሉ ጉምቱ ጠቢባን የሥራ ውጤትም አብርሆት (ኢንላይትመንት) የሚባለውን ዘመን ወልዷል፤ ይህም ወደ ኢንዱስትሪ አብዮት አሸጋግሮ ለዛሬው ዘመናዊነት መደላድልን ስለማመቻቸቱ የታሪክ ድርሳናት ያትታሉ፡፡

በወቅቱ የሕዳሴው መንገድ ቀያሽ ተደርጎ የሚጠቀሰው ገዥ-ሃሳብ፣ የሰውን ልጅ በቀዳሚነት በሚያጠናውና ሰዋዊነት (Humanism) ተብሎ በሚጠራው ዘርፍ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ ይህ አስተሳሰብ በሀገረ-እንግሊዝ በተስፋፋበት በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተነሳው ፀሐፌ-ተውኔት ዊሊያም ሼክስፒር፣ ኃይማኖታዊ ክብረ በዓላትን፣ ስሜት-ተኮር እንቅስቃሴዎችንና ሥነ-ምግባር ላይ ብቻ ያውጠነጥን የነበረውን የድራማ ዘውግ፣ ወደ አለማዊ ይዘትነት በመቀየር ለሀገራዊ ፍቅር መነቃቃት እና የአርበኝነት መንፈስን በማስረፅ ረገድ ወደር የማይገኝለት ሚና ለመጫወቱ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቹ ግንባር ቀደም ምስክሮች ናቸው፡፡ በጥቅሉ የ‹‹ሕዳሴ›› (Renaissance) ፅንሰ-ሀሳብ የግሪክና የላቲን ብሉይ መድብሎች ላይ ቆሞ ፍልስፍናን እና መሰል የእውቀት ዘርፎችን መተርጎምን የያዘ የብርሃን ንቅናቄ በመሆኑ፤ የግለሰብን አለማዊ ከፍታ ለማስረገጥ፤ የሰውን ልጅ ምክንያታዊነት፣ የምርምር ክሂልና የኪነ-ውበት ፈጠራ ማሳደግን ዋነኛ ማዕከሉ ያደረገ ብርቱ የለውጥ መንፈስ ነው ተብሎ ቢደመደም ማጋነን አይሆንም፡፡

 የኢትዮጵያ ህዳሴ

በሚሊኒየሙ አከባበር ዋዜማ ይህንን ቃል በጥራዝ ነጠቅነት የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ መጠቀሙን ተከትሎ፣ ከክቡራን ሚንስትሮች እስከ የቀበሌ ካድሬዎች የንግግር መክፈቻና መዝጊያ ሆኖ ዛሬም ድረስ በማጭበርበሪያነት እያገለገለ ይገኛል፡፡ በአባይ ወንዝ ላይ እየተሰራ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫንም «የሕዳሴ ግድብ›› ሲሉ ሰይመውታል፤ ምንም እንኳ የትኛውን ያለፈ ታሪካችንን እንደሚያድስ አፍታተው ባይነግሩንም፡፡ ሰሞኑን የተከበረውን የግንቦት ሃያ በዓል በማስመልከት በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ በወሬ ደረጃ የሚያውቀውን ገድል እየተደነቃቀፈ የተረከልን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም ቢሆን ‹‹የግንቦት ሃያ ድል ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ገናናነቷ እንድትመለስ /እንድትታደስ/ የጠቀመ ነው›› ከሚል መታበይ አልፎ፣ የትኛውን የገናናነት ዘመናችንን ለመመለስ እንደተቻለ ለይቶ አላስቀመጠልንም፡፡ በርግጥ እርሱ እያወራ የነበረው የአክሱም ስልጣኔን በተመለከተ ከሆነ፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ታላቁ ስላቅ ተብሎ በታሪክ ማህደር ሊመዘገብ ይገባል፤ በተለይም የአቶ መለስ ዜናዊን ‹‹የአክሱም ሀውልት ለወላይታው ምኑ ነው?!›› ሽርደዳን ስናስታውስ፡፡ በተቀረ ‹‹ሕዳሴ›› ብሎ ለመሰየም በቅድሚያ መታደስ የሚገባው ጥንታዊ ሥልጣኔ ስለመኖሩ ማመን እንደሚጠይቅ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፕሬዚዳንት ለነበረ ሰው ይጠፋዋል ብዬ አላስብም፡፡

በአናቱም ጀግናው ኢህአዴግ ከምንሊክ በፊት የነበረችዋን ኢትዮጵያ እንደማያውቃት ሲለፍፍ እና የኢትዮጵያ ታሪክን በ100 ዓመት ገድቦ፣ የቀደመው የሥልጣኔ አሻራ የአንድ ወይም የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ማሕበረሰብ ግንጥል ውበት እንደሆነ ለሃያ ሶስት አመት ሙሉ ሲሰብክ ኖሮ፣ ዛሬ ‹የጥንቱን ገናናነት እንመልሳለን› ማለቱ፤ ራሱ ካነበረው የሥርዓት አወቃቀር ጋር ፊት ለፊት እንደሚያላትመው የዘነጋው ይመስለኛል፡፡ ይህም ሆኖ ‹‹ስለሕዳሴ የማወራው ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ አይደለም!›› ካለን ደግሞ፣ የኢትዮጵያን የ3ሺህ ዘመን ቀደምት ታሪክ በይፋ አምኖ መቀበሉን ያወጀ ያህል አድርገን ልንወስደው እንችላለን፤ ግና፣ ይህ አይነቱ አቋም ድንገት በሞቅታ የሚለወጥ ሳይሆን፣ ብዙ ማብራሪያዎችን እና ደም ያፋሰሱ ጠማማ ታሪኮችን የማቃናት ከባድ ሥራ የሚጠይቅ ነው፡፡ በተረፈ የሕዳሴው ልፈፋ በታሪክ ብያኔው ያኮረፉትንና ‹ቅድሚያ ኢትዮጵያዊነት› የሚሉትን ስብስብ በሀሳዊ የፕሮፓጋንዳ ማግኔት ወደፓርቲው ለመጎተት የሚጠቀምበት ተራ የማጭበርበሪያ ስልት ከመሆን የሚዘል አይመስለኝም፡፡

የሆነው ሆኖ በዚህ አውድ መከረኛይቷን ኢትዮጵያ ከአደገኛው ማዕበል የሚታደጋት ቀጣዩ ሕዝባዊ ንቅናቄ ‹‹የሕዳሴ አብዮት›› በሚል ማዕቀፍ ስር ይወድቅ ዘንድ ገፊ-ምክንያቱ፣ የሥርዓት ለውጥ ብቻውን ለሀገሪቱ ትንሳኤ በቂ አለመሆኑን አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡ ስለምን? ቢሉ፣ በተለይም ከ1983ቱ የመንግስት ቅያሬ በኋላ የተከሰቱ አስጨናቂ ችግሮች መፍትሄ ያገኙ ዘንድ ዳግም የመታደስ (እንደገና የመወለድ) አስፈላጊነትን አማራጭ አልባ ምርጫ በማድረጋቸው ነው፡፡ በተለይም የብሔር ፖለቲካው የወለደው የጎሳ ክፍፍል፣ ከባህላዊ እሴቶች ማፈንገጥ፣ የትምህርት ጥራት ማሽቆልቆል፣ የኃይማኖት መቻቻል ወደ ታሪክነት መቀየር፣ የህሊና ታማኝነት መደብዘዝ እና ከሰው ልጅ ይልቅ ቁስ መከበሩ… ከሞላ ጎደል አብዮቱን በታሪክ ማንፃት መካከል የማለፍ ተልዕኮ እንዲያነግብ ገፍቶታል፡፡ በተጨማሪም የቀድሞ የታላቅነት መገለጫችን የሆነው የአክሱም ሥልጣኔ ክቡድ መንፈስ ለዚህ ዘመን መዋጀት የሚበቃ ሽራፊ ምስጢረ-ጥበብን ሸሽጎ ስለመያዙ ከቶም ቢሆን ቅንጣት ታህል የማንጠራጠር መሆናችን ሕዳሴን አጀንዳ እንድናደርገው ያስገድደናል፡፡

ከላይ እንዳየነው የአውሮፓን ሥልጣኔ በፅኑ መሰረት ላይ ያስረገጡት አሰላሳዮቻቸው እንደሆኑ ሁሉ፤ በእኛም አውድ ሀሳቦቻቸውን ወደ አደባባዩ ተዋስኦ አብዝተን ልናካትትላቸውና የሕዳሴያችን ምሁራን ሊሆኑ ይገባል ብዬ የማምንባቸው ሶስት መምህራን አሉ፡፡ መስፍን ወልደማርያም፣ መሳይ ከበደና ተከስተ ነጋሽ፡፡  አዛውንቱ ጠቢብ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በተለይም ‹‹መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ›› በሚለው መጽሐፋቸው፣ የኋላው መዘንጋቱ የችግሮቻችን ምንጭ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡ በገፅ 12 ላይም እንዲህ በማለት በቁጭት ይጠይቃሉ፡-

‹‹ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዓመታት በፊት ሰረገላ ነበር፣ የመስኖ እርሻ ነበር፣ የግንብ ቤት ነበር፣ ሕዝብ የሚገበያየው በገንዘብ ነበር፤ ከአራት መቶ ዓመታት በፊት ጋሪ ነበር፣ ድልድይና የግንብ ቤቶች ተሰርተው ነበር፤ የዚህ ሁሉ የሥራ ጥበብ ለምን ከሸፈ? የአክሱም ሀውልቶችን የመስራት ጥበብ ለምን ከሽፎ ቀረ? የላሊበላን ከድንጋይ የተፈለፈሉ አብያተ ክርስቲያናት የመስራት ጥበብ ለምን ከሸፈ? የጎንደርን ቤተ-መንግስቶች የመስራት ጥበብ ምን አክሽፎ አስቀረው? እነዚህ ሁሉ የድንጋይ ስራ ጥበቦች በሚታዩበት አገር በደሳሳ ጎጆ ውስጥ መኖር ከትውልድ ወደትውልድ የሚተላለፍ ባሕል መሆኑ በምን ምክንያት ነው?››

ቀድሞ ግራ-ዘመም የነበሩት የፍልስፍና መምህር ፕ/ር መሳይ ከበደ ደግሞ ሌላኛው የሕዳሴው ምሁር ይሆናሉ ብዬ አስባለሁ፤ በተለይም ከ40ዎቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን ጋር በተባረሩ ማግስት ባሳተሟቸው መጻሓፍት፣ የቀደሙ ሀገር-በቀል የኢትዮጵያ ሊቃውንትን ሙግቶች በማብራራት ይታወቃሉ፡፡ ‹ወደ ምንጫችን የመመለስን› ጥሪ የሚያስተጋቡት ፕሮፌሰሩ፣ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ማጥ ለመውጣትም ሆነ ወደፊት እንድትገፋ፣ ለረዥም ዘመን ካስተናገደቻቸው ዕሴቶች መካከል ረብ ያላቸውን መመለስ እንደሚገባት አብዝተው ተከራክረዋል፡፡

አስመራ የተወለዱት የታሪክ አጥኚው ፕ/ር ተከስተ ነጋሽም ሌላው ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የትምህርት ስርዓቱ ላይ ባደረጉት አበርክቶ በዚህ አውድ የማነሳቸው እኚህ ምሁር፣ እንደ ፕ/ር መሳይ ሁሉ፣ ዘመናዊው የትምህርት ስርዓት አውሮፓ ተኮር እና ኢትዮጵያ-ጠል በመሆኑ ወደፊት መራመድ እንዳላስቻለን ደጋግመው ከመናገር ባለፈ፤ ቋንቋ የሚሸከመውን ሀገራዊ ማንነት ከመረዳት አኳያ አማርኛን እና ኦሮምኛን የስርዓተ-ትምህርቱ ቋንቋዎች ማድረግ ብቸኛው ከውድቀታችን መውጫ መንገድ መሆኑን ያምናሉ፡፡ …በጥቅሉ እነዚህ አንጋፋ ጠቢባን (ያልጠቀስኳቸው ሌሎችም እንደሚኖሩ ሳልዘነጋ) አውሮፓውያን ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ከጨለማ የወጡበትን ብልሃት መመርመርን ይበልጥ አጠንክረው በመከተል፣ ሀገር የመታደግ ተልዕኮዎቻቸውን ከዳር ያደርሳሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ይሁናቸውና!

መጪው የሕዳሴ አብዮት በዋናነት የሚያተኩርበት ሌላው ጉዳይ፣ ከአራት አስርታት በፊት በያ ትውልድ ፈታኝ የትግል ጉዞ ላይ ትልቅ ተሳትፎ የነበራቸውን እንስቶች የተኳቸው የዛሬዎቹ የፆታ አቻዎቻቸው ለምን ከእንቅልፍ በከበደ አርምሞ ውስጥ ሰጠሙ? የሚለው ነው፡፡ ከአውሮፕላን ጠላፊዋ ማርታ መብራቱና ታደለች ኪዳነማርያም እስከ የመኢሶኗ ወሳኝ መሪ ንግስት አዳነ፤ እንዲሁም ከእልፎቹ የኢህአፓ ትንታግ ጓዲቶች እስከ ወያኔዎቹ አረጋሽ አዳነ እና ቀሺ ገብሩ ያሉ ተዘርዝረው የማያልቁ የዚያ ዘመን የአናብስት እንስቶች እንቅስቃሴ እንደዋዛ አክትሞ፣ በብርቱካን ሚደቅሳ፣ ርዕዮት አለሙና ፈቲያ መሀመድን በመሰሉ ጥቂት ጀግኖች ተገድቦ መታየቱ፣ በቀድሞው ታሪክ መታደስን አማራጭ የለሽ ያደርገዋል፡፡ በርግጥ የእንስቶቻችንን ፊኒክስነት ለመመለስ ከጥንቱ ይልቅ የትላንቱ የእናቶቻችን ጊዜ በተምሳሌነቱ ተስተካካይ የለውም፡፡ እነርሱ በያ ትውልድ ተጋድሎ የጊዜውን ጎታች የፆታ አመለካከት በመጋፋትና የወንዶችን ትምክህታዊ ዓለም በመነቅነቅ ታሪክ ለመስራት የታደሉ ፈርጦች እንደሆኑ አስመስክረዋል፡፡

የእኔ ዘመን አብዮተኛ ሴቶችም፣ በኮታ ሳይሆን በእውነተኛው እኩልነት እንዲገለጡ ግዴታቸውን ከወዲሁ መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ከወቅታዊው የሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር እኩሌታውን የሚይዙት እንስቶቻችን በነቂስ ያልተሳተፉበት አብዮት በየትኛውም መስፈርት ውጤታማ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በግልባጩ እነርሱን በዕኩልነት ማካተቱ ካልተሳካ ለውጡ ሊዘገይም ሆነ ክፉ ጠባሳ ሊኖረው ስለሚችል፣ ‹‹ያለሴቶች ተሳትፎ የኢትዮጵያ ሕዳሴ እውን አይሆንም!›› ከሚለው ዘመነኛ ኢህአዴጋዊ ቧልት እና ፕሮፓጋንዳ በተለየ መልኩ ተግባራዊ የሚሆን የንቃት ሕዳሴ ትኩረት ሊሰጠው ይገባዋል ብዬ አምናለሁ፡፡

ሌላው ጉዳይ ኢትዮጵያ በ66ቱ እና በ83ቱ የአብዮት ሀዲድ ላይ የመጣችበትን የማሕበረ-ፖለቲካ ታሪኳን ግድፈቶችና ስኬቶች በምክንያታዊነት መመርመር ለሁለንተናዊ ዳግም ልደት (ሕዳሴ) እንድንዘጋጅ መደላድል የመፍጠሩ እውነታ ነው፡፡ ይህ የዳግም ልደት አብዮታዊ ጉዞ ደግሞ በዋነኝነት የሁለት ማሕበረሰቦችን ቅሬታ የሚያቅፍ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይኽን የምለው የሌሎቹን ዋጋ በመዘንጋት ሳይሆን፣ በቀዳሚነቱ ስለማምን ነው፡፡

የብሔር ጥያቄ የኢትዮጵያን ማዕከላዊ መንግስት ለመናድ ቅርብ የነበረባቸው ዘመኖችን ተመልክተናል፡፡ በዚህ መንገድ አልፈንም በዋናነት በአግባቡ መመለስ ካቃቱን ጥያቄዎች መካከል በኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚነሳው ዋነኛው መሆኑ አያከራክርም፡፡ ይህ ጥያቄ ጠርዘኛ ልሂቃኑ በሚያቀርቡት ልክ ባይሆንም፤ መሬት የረገጡ ማንነታዊ ቅሬታዎችን ተንተርሶ መነሳቱ ግን መካድ የለበትም፡፡ እናም ኢትዮጵያችንን በማደስ ጉዞ፤ ኦሮሞነት ከሀገሪቱ ምንነት ብያኔ የተነጠለ ሆኖ የመጣበትን የታሪክ አጋጣሚ ሂደት በመግታት፣ የብሔሩን መለዮዎች የኢትዮጵያዊነት ብያኔ ገዢ መተርጎሚያና መዳረሻ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ሌላኛው ጭብጥ ደግሞ የኢትዮጵያን እስልምና ነባራዊነት ማፅናት ነው፡፡ ኃይማኖቱም ሆነ ተከታዮቹ በአፄያዊዎቹ አፈና ውስጥ ለሺ ዓመታት የመቆየታቸውን እውነታ ተቀብለን፤ በኢትዮጵያዊነት ትእምርታዊ ገፆች ውስጥ ቀዳሚ አዋጭነታቸውን መቀበል የመታደሳችን ግብ ሊሆን ይገባል፡፡ ለነዚህና ለሌሎች መዘርዘር ለማይቻሉን የሀገሪቷ መከራዎች፣ መውጫው ኢትዮጵያን በማደስ የሚደመደም አብዮት ከሆነ ዘንዳ፣ የብሔራዊ ዕርቅ ጉዳይ ከዋነኛ የሽግግር ሂደቶች መካከል ከፊት የሚቆም እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ በእርግጥ ርዕሰ-ጉዳዩ በተነሳ ቁጥር፣ ‹ማን ከማን ጋር ነው የሚታረቀው?› እያለ የሚቀልድ ኢህአዴግ መራሹን መንግስት የመሰለ ቢኖርም፤ እየመጣ ካለው መዓት ሀገሪቷን ለማዳን፣ ብሔራዊ እርቅ ምቹ ድልድያችን መሆኑን ማመን ያስፈልጋል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በበላይነት የሚዘውሩት ልሂቃንን በአንድ የጋራ መድረክ ላይ ማሰባሰብ፣ በቀጣይ እንድትኖረን በምንሻት ሀገር ምንነት ማዕቀፍ ውስጥ የሚያርፉ ተመጋጋቢ አመለካከቶችን ለመቅረፅ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

የሆነው ሆኖ ይህን ተምኔት የመሰለ፣ ነገር ግን ሊከወን የሚችል የሕዳሴ አብዮት ያለእንቅፋት ለማሳለጥ፣ በቅድሚያ ገዥዎቻችን ‹በአንድ ክፉ አጋጣሚ ስልጣኑን ብናጣ ያበቃልናል› ከሚለው ነቢባዊም ሆነ ተጨባጭ ስጋት እንዲላቀቁ ዋስትና መስጠት ላይ መግባባት የግድ ይላል፡፡ በመገዳደል ከተበከለው የግራ-ቀኝ ፖለቲካ ለመንፃት፤ ከነነውረኝነታቸው ሀገሪቷ የእነርሱም እንደሆነች አምነው እንዲቀበሉ ማድረግ ብቸኛው መፍትሔ ነው፡፡ በመጪዋ ኢትዮጵያ አንዱ ልዩ ቀናዒ፣ ሌላኛው ደግሞ ተጠርጣሪ እንደማይሆንባት መተማመን፣ ለሕዳሴው የሚኖረንን ተስፋ ያጎለብታል የሚል ፅኑ እምነት አለኝ፡፡

(የሕዳሴው አብዮትን ማስፈፀሚያ ሃሳብን በተመለከተ ሳምንት እመለስበታለሁ)

ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ እንዴት በምግብ መመረዝ ሊሞቱ ይችላሉ? –በምግብ መመረዝ የሚከሰቱ 4ቱ ገዳይ በሽታዎች

$
0
0

የምግብ መመረዝ ለበርካታ ሰዎች የሞት መንስኤ ሲሆን ይስተዋላል፡፡ በቅርቡ እንኳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ በምግብ መመረዝ እንደሞቱ ሲነገር እንሰማለን፡፡ ውድ አዘጋጅ፤ የምግብ መመረዝ እንዴት ይከሰታል? በምን ያህል ጊዜስ ይገድላል? ሰዎች በምግብ ተመረዙ ሲባል ምን ማለት ነው? የምግብ መመረዝ አይነቶች ስንት ናቸው? በምግብ መመረዝ የተጠቃ ሰው የመዳን ተስፋስ ይኖረዋል? ሰዎች በምግብ የሚመረዙት ባለማወቅ ነው ወይስ ሆን ተብሎ በሰዎች በተቀነባበረ ዘዴ? የምግብ መመረዝ ችግር በእኛ ሀገር Food Poison የሚባለው ነው ወይስ ይለያል? በዓለማችን በምግብ መመረዝ ለሞት ወይም ለህመም የተዳረጉ ሰዎችስ ይኖሩ ይሆን?
በጥቅሉ የምግብ መመረዝ ችግርን በሚመለከት ለሌሎች ትምህርት ሊሰጥ በሚችል መልኩ ማብራሪያ ብትሰጡኝ ደስተኛ ነኝ፡፡
ጫላ ዋቆ ከሚኒያፖሊስ

Alemayehu Atomsa
ከዶ/ር ዓብይ ዓይናለም የተሰጠ ምላሽ፦

በእንግሊዝኛው Food poisoning ወይንም Food borne illness ተብሎ የሚጠራው የምግብ መመረዝ በሽታ ሰዎች የተመረዘ ወይም በባክቴሪያ፣ በቫይረስና በፓራሳይቶች የተጠቃ ምግብን በሚመገቡበት ጊዜ የሚከሰትና ሰዎችን ከቀላል በሽታ አንስቶ እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል ህመም ነው፡፡ ይህ በሽታ ምግቡ በሚመረትበት ጊዜ ወይንም በቤት ውስጥ በሚበስልበት ጊዜ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደ ውስጡ በሚገቡ መርዛማ ነገሮች ምክንያት ሊከሰት የሚችል ነው፡፡
ሰዎች በምግብ መመረዝ በሚጠቁበት ጊዜ ትውከት (nausea)፣ ማቅለሽለሽና ተቅማጥ (vomiting or diarrhea) ወዲያውኑ የሚከሰቱ ምልክቶች ናቸው፡፡ እነኚህ ምልክቶች ደግሞ ምግቡን ከተመገብን በሰዓታት ጊዜ ውስጥ የሚታዩ ናቸው፡፡ በእርግጥ ብዙውን ጊዜ የምግብ መመረዝ ቀላል እና ያለ አንዳች የህክምና ክትትል ሊወገድ የሚችል ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዶቹ ከባድና የረዥም ጊዜ የህክምና ክትትልን የሚጠይቁ ናቸው፡፡ እንደተወሰደው መርዛማ ንጥረ ነገር ህመሙ ስር እየሰደደ እስከ ሞትም ሊያደርስ የሚችል ነው፡፡

የምግብ መመረዝን የሚያስከትሉ ነገሮች

በመላው ዓለም በየጊዜው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በምግብ መመረዝ በሽታ ይጠቃሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ ለምግብ ደህንነትና ንፅህና ከፍተኛ ትኩረት በሚሰጡ በአውሮፓና በአሜሪካ ውስጥ በሚገኙ ሀገሮች ውስጥ በዚህ ችግር የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ለበሽታው በዋነኛነት የሚጠቀሰው ምክንያት ደግሞ የምግብ በመርዛማ ነገሮች መበከል (contaminated food) ነው፡፡
የምግብ መመረዝ የተለያዩ ህመሞችን ያስከትላል
- የጨጓራ ህመም (upset stomach)
- የሆድ መነፋት (abdominal cramps)
- ማቅለሽለሽና ተውከት (nausea and vomiting)
- ተቅማጥ (diarrhea)
- ትኩሳት (fever)
- የሆድ ድርቀት (dehydration)
በምግብ መመረዝ ምክንያት ከሚከሰቱ የህመም አይነቶች ውስጥ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ህመሞቹም እንደ ሰውነታችን መመረዝ ቀላል እና ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡

ባክቴሪያ እና ቫይረስ

ባክቴሪያ እና ቫይረስ የምግብ መመረዝን ከሚያስከትሉት ነገሮች ውስጥ በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የህመሙ ምልክትና የፅናቱ መጠን ምግቡ እንደተበከለበት ባክቴሪያ ወይም ቫይረስ መጠንና አይነት ሊለያይ ይችላል፡፡

ፓራሳይትስ (ጥገኛ ህዋሳት)

ፓራሳይቶች በሆድ ውስጥ የሚፈጠሩና ምግብን እና ደህንነትን ከሌሎች ህዋሳት በመውሰድ የሚኖሩ ጥገኛ ህዋሳት ናቸው፡፡ እነኚህ ህዋሳት ደግሞ የምግብ መመረዝን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ በጥናት ተረጋግጧል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከዋናዎቹ ምግብ ወለድ ጥገኛ ህዋሳት መካከል ባለ አንድ ሴል ህዋስ (protozoa) ክብ ህዋሳት (roundaxnmt) እና የኮሶ ትሎች (topwarm) ይገኙበታል፡፡

መርዛማ ንጥረ ነገሮች

በእርግጥ ብዙውን ጊዜ የምግብ መመረዝ የሚከሰተው በባክቴሪያ፣ በቫይረስ እና በፓራሳይትስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አልፎ አልፎም ቢሆን በተፈጥሮ ወይም በኬሚካል መርዛማ ነገሮች ምግብ ውስጥ መጨመር የተነሳ አደገኛና ገዳይ የምግብ መመረዝ ሊከሰት ይችላል፡፡

አለርጂ

አንዳንድ ሰዎች ለተለያዩ ምግቦች ባላቸው አለርጂነት የተነሳ የምግብ መመረዝ ችግር ሊከሰትባቸው ይችላል፡፡ ብዙውን ጊዜ ለአለርጂነት ከሚያጋልጡት የምግብ አይነቶች መካከል ለውዝ፣ ወተት እና እንቁላል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ከባድ የምግብ መመረዝ
በአሜሪካ ውስጥ ከስድስት ሰዎች መካከል አንዱ በየዓመቱ በምግብ መመረዝ ችግር ይጠቃል፡፡ ይህም ማለት 48 ሚሊዮን አሜሪካውያን በየዓመቱ የዚህ ችግር ሰለባዎች ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ ይህም ሆኖ አብዛኛዎቹ ሰዎች ህመሙ ብዙም ጉዳት ሳያስከትልባቸው ያለ ህክምና ክትትል ወይም በቀላል ህክምና ይፈወሳሉ፡፡ ይህም ሆኖ ጥቂቶችና ህመሙ ከፍተኛ ህመም ሊያስከትልባቸውና እስከሞትም ሊያደርሳቸው እንደሚችል ተረጋግጧል፡፡ በምግብ መመረዝ ምክንያት ከሚከሰቱና እስከ ሞት ሊያደርሱ ከሚችሉ ህመሞች መካከል የሚከተሉት በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡

1. የኩላሊት በሽታ

ሄሞላይቲክ ዩሪሚክ ሲንድሪም (Hemolytic uremic syndrome (HUS)) በምግብ መፈጨት ሂደት ውስጥ መርዛማ ነገሮች ሲፈጠሩና ቀይ የደም ሴሎች በሚድሙበት ጊዜ የሚከሰት አደገኛ በሽታ ነው፡፡ በሽታው አደገኛ የሚሆነው በኩላሊት ላይ ቁስለትን የሚያስከትል በመሆኑ ነው፡፡ HUS የሚከሰተው ኢ-ኮሊ (E-coli) በተባሉት የባክቴሪያ አይነቶች ምክንያት ነው፡፡ ሄሞላይቲክ ዩሬሚክ ሲንድረም ብዙውን ጊዜ ህፃናትን የሚያጠቃ ቢሆንም በአዋቂዎች ላይ የሚከሰትና ኩላሊትን የሚያጠቃ የህመም አይነት ነው፡፡

strong>2. የአጥንት መገጣጠሚያ በሽታ (Chronic Arthritis)

ሺጌሳ ወይንም ሳላሞኔላ በተሰኙት ህመሞች የተጠቁ ሰዎች አንዳንዴ በአጥንት መገጣጠሚያዎቻቸው ላይ ህመም ሊሰማቸው ይችላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እነኚህ ሰዎች የአይን እብጠት እና ሽንት በሚሸኑበት ጊዜ የህመም ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ይህ የህመም አይነት የሚከሰተው በአጥንት መገጣጠሚያዎች አካባቢ በሚፈጠር የህመም ስሜት (reactive arthritis) ምክንያት ነው፡፡ ይህ ህመም እንደ ሁኔታው ለወራት ወይንም ለዓመታት ሊዘልቅ የሚችል ሲሆን ስር የሰደደ የአጥንት መገጣጠሚያ አካባቢ ችግርን ሊያስከትል የሚችል ነው፡፡ ህመሙ አንዴ ከተከሰተ በህክምና ለመዳንም ያስቸግራል፡፡
3. የአዕምሮና የነርቭ ችግር
የምግብ መመረዝን የሚያስከትሉ የባክቴሪያ ዝርያዎች (Listeria) ወዲያውኑ ካልተወገዱ የአንጎል ገለፈትን በማጥቃት Meningitis የተባለውን አደገኛ አእምሮ ነርቭ ህመም ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ አንድ ጨቅላ ህፃን ገና እንደተወለደ በሊስቴሪያ ባክቴሪያዎች ከተጠቃ የህፃኑ የወደፊት እጣ ፈንታ የአእምሮ ህመም (mental retardation) በሚጥል በሽታ፣ የአካል መሽመድመድ፣ አይነ ስውርነት፣ ወይም መስማት የተሳነው ሊሆን ይችላል፡፡

ጉሌይን ቤር ሲንድረም (Guillain Bare Syndrome) የሰውነታችንን ነርቭ የሚያጠቃ የህመም አይነት ነው፡፡ ይህ በሽታ የሚከሰተው ደግሞ የሰውነታችን ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል ሲስተም የራሳችንን ነርቭ በሚያጠቃበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ የህመም አይነት ከፍተኛ የህክምና ክትትልን የሚጠይቅና በጊዜው መፍትሄ ካላገኘ የአካል መሽመድመድንና አልፎም ተርፎ ህልፈተ ህይወትን ሊያስከትል የሚችል ነው፡፡

በአሜሪካ ውስጥ በየዓመቱ 3,000 የሚሆኑ ሰዎች ከምግብ መመረዝ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ህመሞች ምክንያት ይሞታሉ፡፡ ከእነኚህ ሟቾች ውስጥ 88 በመቶ የሚሆኑት የህመማቸው ምክንያት ሳልሞኔላ፣ ቶክስፕላዝማ፣ ሊስቴሪያ፣ ኖርቫይርስ እና ካምፓይሎባክተር ተብለው የሚጠሩት ህዋሳት ናቸው።
ሌሎች ሞትን የሚያስከትሉና ምግብ ወለድ የሆኑ የህመም አይነቶችም አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህልም ጥሬ ዓሣን በመመገብ ምክንያት የሚከሰተውን ቫይብሮ ኢንፌክሽን የተባለውን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይህ የህመም አይነት የደም ዝውውር ሂደትን በመመረዝ እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል ነው፡፡ በዚህ በሽታ ከሚጠቁ ሰዎች መካከል ግማሽ ያህል የሚሆኑት እንደሚሞቱና ህመሙም አጣዳፊና በሁለት ቀናቶች ውስጥ የሚገድል እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡
4. በምግብ መመረዝ የተጠቁ ታዋቂ ሰዎች
ባክቴሪያ ድሃ ሆነ ሀብታም፣ የተማረ ይሁን ያልተማረ፣ ታዋቂ ይሁን አንዳችም እውቅና የሌለው ሰው በአጠቃላይ ለማንኛውም የሰው አይነት ደንታ የሌለው ህዋስ ነው፡፡ አንድ ሰው ሆን ተብሎ የተመረዘም ይሁን በተለያየ ምክንያት በባክቴሪያ፣ በቫይረስ በፓራሳይት ወይም በመርዛማ ንጥረ ነገሮች የተሞላ ምግብን ከተመገበ ይታመማል፣ ህመሙ በቀላሉ ሊድን አሊያም እስከ ሞት ሊያደርሰውም ይችላል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ታዋቂ ሰዎች በምግብ መመረዝ ከተጠቁት ዝነኞች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

- ክራንቤረስ የተባለው ታዋቂ የሙዚቀኞች ቡድን በማርች 2012 አንደኛው ዘፋኝ በምግብ መመረዝ በመጠቃቱ ምክንያት በአውስትራሊያ ሊያቀርብ የነበረውን ዝግጅቱን ለመሰረዝ ተገዷል፡፡
- ዝነኛው ድምፃዊ ኤልተን ጆን በዚሁ በሽታ በመጠቃቱ ምክንያት በፌብርዋሪ 20 2012 በላስ ቬጋስ ሊያቀርብ የነበረውን ዝግጅት ሰርዞታል፡፡
- የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት የነበሩት ኒኮላስ ሳርኮዚ ወንድ ልጅ የሆነው ፔሪ ሳርኮዚ በምግብ መመረዝ ምክንያት በጃንዋሪ 26 2012 በብላክ ሲ ከተማዋ ኦዴሳ ውስጥ ሆስፒታል ገብቶ ነበር፡፡
- የሀገረሰብ ሙዚቃ አቀንቃኟ ኬሊ ፒክለር በጃንዋሪ 2012 በአሪዞና ፍኒክስ ከተማ ውስጥ የምግብ መመረዝ ህመም አጋጥሟት ነበር፡፡
- ሌላዋ የሀገረሰብ ሙዚቃ አቀንቃኟ ሚራንዳ ለምበርቶ በጃንዋሪ 2012 በተመሳሳይ መንገድ በአደገኛ የምግብ መመረዝ ተጠቅታ ነበር፡፡ ‹‹ለሞት ተቃርቤ ነበር›› የሚል የትዊተር መልዕክቷን ያስተላለፈችው ሚራንዳ ህመሙ የጀመራት ‹‹ሽሪምና›› የተሰኘ የዓሣ አይነት በመመገቧ ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
- የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኙ ጆይ ጆፐስ በዲሴምበር 2011 በተመሳሳይ ችግር ተጠቅቶ በአስቸኳይ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ተገድዶ ነበር፡፡
- ራፐሩ ዲ.ኤም ኤክስ በጃንዋሪ 25 2012 በምግብ መመረዝ ተጠቅቶ ሆስፒታል ገብቶ ለመታከም ተገዷል፡፡ በDMX ችግሩ የተከሰተው ሸሪምፕ የተባለውን የዓሣ አይነት በመመገብ ምክንያት እንደሆነም በወቅቱ ተጠቅሶ ነበር፡፡
- በኦክቶበር 2011 ዝነኛው የሮክ ሙዚቃ አቀንቃኝ ስቲቨን ቴይለር በምግብ ወለድ ህመም ተጠቅቶ በመንገድ ላይ በመውደቁ በአስቸኳይ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ነበር፡፡
- የቼልሲው የመሀል ሜዳ ኮከብ ፍራንክ ላምፓርድ ባለቤት የሆነችው እና ‹‹Dancing on Ice›› የተሰኘውን የቴሌቪዥን ሾው የምታቀርበው ክርስቲን ብሊክሊ በቅርቡ በምግብ መመረዝ ተጠቅታ ሆስፒታል ተወስዳ ነበር፡፡ ለእሷም ህመም በምክንያትነት የተጠቀሰው ‹‹ሽሪምፕ›› የተሰኘው የዓሣ አይነት ነው፡፡
- በዲሴምበር 5 2011 የቀድሞው ብራዚላዊ የእግርኳስ ኮከብ ሶቅራትስ በ57 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ቀደም ሲል በተመገበው የተመረዘ የበሬ ሥጋ ምክንያት ለረዥም ጊዜ በሆስፒታል ውስጥ የህክምና እርዳታ ከተደረገለት በኋላ ነው፡፡
ወደኛ ሀገር ስንመለስ ደግሞ ነፍሱን ይማረውና ዝነኛው ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ በተለያዩ ወቅቶች ከስራው ጋር በተያያዘ የምግብ መመረዝ አጋጥሞት እንደነበር ይነገራል፡፡
ውድ ጫላ፡- ከላይ በመጠኑ ለማብራራት እንደሞከርነው የምግብ መመረዝ በሽታ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰትና እንደ ሁኔታው እስከ ህልፈተ ህይወት ሊያደርስ የሚችል የህመም አይነት ነው። ምግብ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ በሆነ ምክንያት ሊመረዝ እና የሰውን አካል ሊጎዳ ይችላል፡፡ ባክቴሪያ፣ ቫይረስ፣ ፓራሳይትስ የተባሉት ህዋሳቶችና መርዛማ ንጥረ ነገሮች ምግብን መርዛማ ከሚያደርጉት ነገሮች ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡

በእርግጥ በምግብ መመረዝ ከሚጠቁት ሰዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ ያለ አንዳች ህክምና ወይንም ቀለል ባለ የህክምና ክትትል የሚወገዱ ናቸው፡፡ ለህልፈተ ህይወት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ቢሆን ቀላል አይደለም፡፡

ሰኔ 1 ቀን ትኩረቱ አዳማና ደብረ ማርቆስ ላይ ነው -አማኑኤል ዘሰላም

$
0
0

የአሥራ ስድስት አመት ወጣት ነበረች። ይሄን ጊዜ ከኮሌጅ ተመርቃ፣ ሥራ ይዛ ምናልባትም ተድራ፣ የልጆች እናት ትሆን ነበር። አሁን ግን የለችም። ኮተቤ አካባቢ ነበር፤ ከአጋዚ ጦር አንዱ በተተኮስ ጥይት ተመታ ወደቀች። ሰኔ አንድ ቀን 1997 ዓ.ም።

shibre-desalegn

የአሥራ ስድስት አመት ወጣት ነው። በእጆቹ ድንጋይ አልያዘም። ተማሪ ነበር። ወደቤቱ ሲመለስ፣ በአካባቢዉ ግርግር ተፈጠሮ ስለነበረ፣ ሰላምና መረጋጋት እናመጣለን ባሉ ታጣቂዎች ተገደለ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት በጊምቢ ወለጋ። ያኔ ደም ፈሰሰ። አሁንም ደም እየፈሰሰ ነው። ያኔም ድብደባ ነበር አሁን ድብደባ ነው።፡ያኔ መታሰር፣ መታፈስ ነበር፣ አሁንም መታሰር፣ መታፈስ ነው። ያኔም አንገት ደፍቶ አቀርቆ ባርያ ሆኖ መኖር ነበር። አሁን አንገት ደፍቶ መኖር ነው። ያኔም ዜጎች ከቅያቸው ይፈናቀሉ ነበር። አሁንም ዜጎች እየተፈናቀሉ ነው። አይበቃም እንዴ ወገን ? ?

አንድ ነገር መርሳት የሌለብን ነገር አለ። ይሄ ሁሉ በአገራችን እና በሕዝባችን ላይ እንዲኖር የፈቀድነው እኛዉ እራሳችን ነን። አምባገነኖችን ማማረርና መራገም ማቆም አለብን። እነርሱ አሁን እያደረጉት ያለውን እንዲያደርጉ የፈቀድንላቸው እኛው ነው።

አንዳንዶቻችን ትችት እንወዳለን። «ይሄ ለምን አልተሰራም፣ ተቃዋሚዎች እንደዚህ ናቸው….» ማለት እንወዳለን። አገር ቤት ያሉ ታጋዮች ትንሽ ስህተት ከሰሩ ፣ ስህተታቸውን አጋነን እናወራለን። የተሰሩ መልካም ስራዎችን ላይ አናተኩርም። ነጻነትን እንፈልጋለን። ግን ሌሎች ታግለው ነጻነትን እንዲያመጡልን ነው የምንጠብቀው። ይሄ አይሆንም !!! ይሄ አይሰራም። ዳር ቆም ትችት ያለፈበት ፖለቲካ ነው።

ለዉጥ ከፈለግን ፣ ሌሎች ለምን ይሄን አያደርጉም ማለት አቁመን፣ እኛ ምን እያደረግን ነው ብለን መጠየቅ አለብን። ያልተሰራ ነገር ካለ፣ ሰብሰብ ብለን፣ ጓደኞቻችን ይዘን እኛው እንስራው። በአገራችን ጉዳይ ላይ ነጋሪና ጎትጓች ሊኖረን አይገባም። ትግሉን ለመርዳት ተሯሩጠን መምጣት አለብን እንጂ መለመን የለብንም። በአገራችን ሰለምና ደሞክራሲ ኒኖር እኮ፣ እስክንደር ነጋ ወይንም አንዱዋለም ወይንም አገር ቤት እየተጋሉ ያሉቱ ብቻ አይዴልም የሚጠቀሙት። እያንዳንዳችን ነው የምንጠቀመው። ኢትዮጵያ ስትመነጠቅ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነው የሚመነጠቀው። ስለዚህ የምንታገለው ፣ ባናስተዉለው ነው እንጂ፣ ለራሳችን ነው።

ለበርካታ አመታት የአንድነት ፓርቲ ላይ ከፍተኛ ትችት ይቀርብ ነበር። «ምን እየሰሩ ነው ? ለምን አያታግሉንም ? ..» እያሉ የሚጮሁ ጥቂት አልነበሩም። እነሲህ ሰዎች ያኔ ትክክል ነበሩ። አዎን አንድነት ተኝቶ ነበር። ግን ያለፈው አመት የተለየ ሁኔታ እያየን ነው። ባህር ዳር፣ ደሴ፣ ጊዶሌ አዲስ አበባ ….ይመስክሩ። አንድነት አስደሳች በሆነ ሁኔታ የተጨበጡ ስራዎችን እየሰራ ነው። ታዲያ ትላንት አንድነትን ለምን አልሰራም ብለን ስንተች የነበረን፣ ዛሬ ድምጻችን ለምን ጠፋ ? ታዲያ የኛንስ ድርሻ ለመወጣት ለምን ዘገየን ?

እንግዲህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከራሱ ጋር እንዲነጋገር እጠይቃለሁ። የፊታችን እሁድ ሰኔ 1 ቀን በአዳማና በደብረ ማርቆስ ታልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል። ባለስልጣናት ለሰልፉ እውቅና ሰጥተዋል። እንግዲህ በአዳማ እና በደብረ ማርቆስ ያለን በነቂስ እንወጣ። ድምጻችንን እናሰማ። «ነጻነት ፣ ነጻነት፣ ቢሊሱማ ! ቢሊሱማ» እያለን እንጩህ። በራሳችን እንተማመን። እነርሱ ምንም ማድረግ እንደማንችል ነው ደጋግመው ሊነግሩን የሚፈልጉት። ያንን ከማለትና ልቦናችንን ለመስለብ ከመሞከር ዉጭ ሌላ አማራጮች የላቸውም። እኛ ግን ልባሞች እንሁን። አንፍራ። በደብረ ማርቆስና በአዳማ የነጻነት ደዉል ይሰማ።

በተቀረው የኢትዮጵያ ግዛት እንዲሁም በዉጭ አገር ያለን፣ በመንፈስ ሰልፉን እንቀላቀል። በሶሻል ሜዲያዎች ዘምቻዉ ፣ ቅስቀሳው ይጧጧፍ። በስካይፕ፣ ቫይበር፣ ኢሜል ወዳጅ ዘመዶቻችንን ወደ ሰልፉ እንዲወጡ እናበረታታ። እንነቃነቅ!!!!!!

በዉጭ አገር ላለን በተለየ ሁኔታ ሌላ ትልቅ ሃላፊነት አለብን። ገዢው ፓርቲ እንዳለ ኢኮኖሚዉን ተቆጣጥሯል። የአገሪቷ ካዝና በ እጃቸው ነው። የህዝብን ጥያቄ አንግቦ የሚንቀሳቀሰው የሚሊዮነሞች ንቅናቄ፣ የጀርባ አጥንቱ ህዝብ ነው። እኛ ነን። በዚህ ጊዜ አገር ቤት ያለው ሕዝባችን ፈታኝ ትግል እያደረገ ባለበት ወቅት፣ በዉጭ ካለን ብዙ ይጠበቃል። ለሌሎች ፣ ሌሎች ጉዳዮች ብዙ ገንዘብ እየተሰበሰበ ባለበት ሁኔታ፣ ወሳኝ ለሆነው ነገር ዝምታዉና መቀዝቀዙ ትክክል አይደለም። ዳያስፖራው ፕራዮሪቲዉን ማስተካከል አለበት።


እረ ለመሆኑ ከአንድነት ወዲያ ለኦሮሞ ማን ሊመጣ ነው? 

$
0
0

ተስፋዬ ዋቅቶላ (የአዳማ አንድነት ፓርቲ የሕ/ግንኙነት)

“….ያኔ እንተያያለን…”

በትላንትናው ዕለት የአዳማ አንድነት ሰልፍ ፈቃዳችንን ከ20ቀናት ደጅ ጥናት በኋላ ወስደናል፡፡ግን ከአስገራሚ ገጠመኞቹ ጥቂቱንም ቢሆን ማካፈል ግድ ይለናልና እነሆ፡፡ፈቃዱን ከመስጠታቸው በፊት ከከተማው ጸጥታ ክፍል ሶስት ሰዎች መጥተው ከንቲባው ጽ/ቤት ተጠርተው ገቡ፡፡እኛ በዚህ ዕለት ካልተሰጠን ላንወጣ ተነጋግረን ገብተናልና “ቶሎ ድረሱልኝ” ያላቸው ሰዎች መምጣት ደስ ብሎናል እንጂ አልፈራንም፡፡ሆኖም ነገርየው ለካ ማስፈራራት ነበር፡፡

በተለያዩ መንገዶች ትንኮሳ ቢደረግብንም ለትንኮሳው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ህጋዊውን ወረቀት መያዝ ቅድሚያ ሰጥተን ይዘን ወጥተናል፡፡ከትንኮሳዎቹ ሁለቱን ልጥቀስ፡፡

1. የጸጥታው ክፍል ኀላፊ ሻ/ቃ ዘሪሁን የመረጣችሁት መንገድ ትራፊክ የሚበዛበት ማደያዎች፣ባንኮች እና ገበያዎች ያሉበትበመሆኑ አንፈቅድላችሁም ልሂድ ብትሉ ያኔ እንተያያለን በማለት ሊያሰገድደን ሞክሯል፡፡

2. ልትይዙ ካስገባችኋቸው መፈክሮች “ ‘የኦሮሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥያቄ በሕጋዊ አግባብ ይመለስ!’ የሚለው ተሰርዞ መውጣት አለበት::” በማለቱ ከፍተኛ ክርክር ገጥመን ልንግባባ አልቻልንም፡፡በዚሁ የተነሳ ሻለቃው “ይህን መፈክር ይዘህ ብትወጣ አስገባሃለሁ!” በማለት ዝቶብኛል፡፡በተጨማሪም አብራ የነበረች ሴት “እናንተ ስለኦሮሞ ምንአገባችሁ!” በማለት ልታጣጥለን ሞክራለች፡፡

እረ ለመሆኑ ከአንድነት ወዲያ ለኦሮሞ ማን ሊመጣ ነው?…ደግሞስ ሕብረብሔራዊ ፓርቲ አንተ ለዚህ ብሄር አያገባህም ሊባል የሚያስችለው ምን መንገድ አለ?…እረ ኢህአዴግ ሆይ በህገ መንግስታዊ መብትና ዲሞክራሲዊ መብታችን ላይ የሚጣልብንን ማዕቀብ በሕግ አምላክ ጠብቅልን-ኋላ የመንግስትነትህ ድርሻ የት ገባ ተብለህ ቀንህ ሲደርስ ትጠየቃለህ !

ተስፋዬ ዋቅቶላ (የአዳማ አንድነት ፓርቲ የሕ/ግ)

UDJ Head

የቴዲ አፍሮ እና የኮካ ጉዳይ

$
0
0

ሁኔ አቢሲኒያዊ

ይህንን ፅሁፍ ከጥቂት ወራት በፊት ዘሐበሻ ድሕረ ገፅ ላይ ፅፌው የነበረ ሲሆን ኮተታም ካድሬዎች ስላልተስተካከሉ ከጥቂት ማስተካከያዎች ጋር እነሆ በድጋሚ ለጥፌዋለው
ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) በብዙዎች ሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ወጣት ከያኒ ነው፤ በሙዚቃዎቹ በሚያነሳው ሀገራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ታሪካዊና ወቅታዊ ጉዳዮች የተነሳ የብዙዎችን ቀልብ ለመግዛት የቻለ ይመስለኛል፡፡ የእርሱን ታላቅነት መግለፅ የዚህ ጹሑፍ ዓላማ፣ ጥያቄም፣ የማወቅም ፍላጎት አይደለም፡፡

teddy afroይልቁንም ለዚህ አጭር መጣጥፍ መነሻ የሆነኝ ከሰሞኑ በአንዳንድ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኮካዎች(ኮተታም ካድሬዎች) የቴዲ አፍሮን ከብራዚል መቅርት ምክንያት አድርገው ሰሞንኛ ትችታቸውን በመሰንዘራቸውን ምክንያት እኔም የተሰማኝን ልጨምር በሚል ነው፡፡
እኛ ሐገር እንደፋሽን ከተያዙት ፖለቲካዊ እሳቤዎች መካከል ዋነኛው ጠርዝ ይዞ የመከራከር ልማድ ነው ይህ መንገድ የት እንደሚያደርሠን ባይታወቅም እንደኢትዮጵያዊ ግን አሳፋሪ እና የአለም ጭራ ሆነን እንድንቀር እያስደረገ ያለ ተግባር ነው፡፡ ከሠሞኑ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለ2014ቱ የብራዚል የአለም ዋንጫ ማጀቢያ የሚሆን ከሌሎች የአፍሪካ ድምፃውያን ጋር በመሆን እየሠራ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ነገር ግን እስከአሁን ምክንያቱ ምን እንደሆነ ባልታወቀ ጉዳይ ቴዲ ከኮካ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻሉን ከቴዲ ህጋዊ ድህረ ገፅ ላይ ማንበብ ችለናል ይህም በበርካታ የማህበራዊ ድሕረ ገፅ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ የመወያያ አጀንዳ ሆኗል፡፡

በተለይ በኮካዎች ዘንድ (በነገራችን ላይ ኮካ ኮተታም ካድሬ እንደማለት ነው) የቴዲን ከአለም ዋንጫ ውጭ መሆን እንደትልቅ እድል በመቁጠር ፌስቡካዊ በዓል እያከበሩ ይገኛሉ፡፡ ቴዲ አፍሮ መጥላትም ሆነ መውደድ መብት ቢሆንም ሐገራዊ ጉዳዮችን የምንመለከትበት መነፀር መስተካከል እንዳለበት ይሠማኛል፡፡

ቴዲ አፍሮ ብቻ አይደለም ከብራዚሉ የአለም ዋንጫ ውጭ የሆነው የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ፣ ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያም ነች ከውድድሩ ውጭ የሆነችው ነገር ግን ይህንን የቴዲ አፍሮን ከብራዚሉ የአለም ዋንጫ ውጭ መሆን አጋጣሚ በመጠቀም የእንኳን ደስ አላቹህ መልዕክት መለዋወጥን የመሠለ አሳፋሪ ተግባር የለም ነገር ግን ይህ ጉዳይ ዞሮ ዞሮ መድረሻውን ወደ አንድ ቦታ ይወስደዋል ወደጠባብነት ኢህአዴግን ከምቃወምበት ጉዳይ መካከል አንዱ ይህንን ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ ሴራው ነው ለዚህ ሴራው ውጤታማ መሆን ደግሞ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን በአደባባይ የሚናገሩ እና የህዝቡ icon የሆኑ ሠዎች በድብቅ መምታት አንዱ ነው የዚህ ሠለባ ከሆኑት መካከል እንደ ታማኝ በየነ፣ አስራት ወ/የስ፣ ብርሐኑ ነጋ፣ ጥላሁን ገሠሠ እና ቴዲ አፍሮ የመሣሰሉት ተጠቃሾች ናቸው ሆኖም ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ ሊጠፋ አልቻለም አይችልም፡፡

በአንድ ወቅት ቴዲ አፍሮ ስለምን ስለ አክሱም ሐውልት መመለስ አልዘፈነም ብሎ የፃፈ አንድ ኮካ ፌስቡከኛ (ኮካ ፌስቡከኛ ያልኩት ስሙን መጥራት ስላፈርኩኝ ነው) ሠሞኑን ቴዲ ከብራዚል በመቅረቱ ውስጡ በሐሴት ተሞልቶ ደስታውን እየዘረገፈልን ነው፡፡ አሁን እንደዚህ አይነት ሠው ባንዳ ቢባል መቀየም ይኖርበታል፡፡
ለማንእንደምናውቀው ቴዎድሮስ ካሣሁን በዚህች የሙዚቃ ህይወቱ ከዛቻ እስከመታሰር ድረስ የደረሰ መሆኑ እሙን ነው ይህም የደረሰበት የተለየ ሰው ስለሆነ ነው
ቴዲ ሺህ ዘመናት ስልጣኔያችንና ታሪካችን፣ ጥበባችን በፍቅር፣ ፍቅራችን በጥበብ የተገመደበት ውሉ ከየት ተጀምሮ የት እንደተቋረጠ ታሪክን እንጠይቅ ዘንድ እንዲህ ሲል በቅኔው ተመራምሮ ያመራምረናል፡-
ብራናው ይነበብ ተዘርግቶ ባትሮኖሱ ላይ፣
የእነ ፋሲለደስ የእነ ተዋናይ፣
የት ጋር እንደሆነ ይታይ የእኛ ጥበብ መሰረቱ…፡፡

እናም እስቲ ታሪክ ይታይ፣ ይመርመር፣ ዘመናትን ያስረጁና የተሻገሩ ብራናዎቻችን ይውጡ፣የሺህ ዘመን የሃይማኖት፣ የጥበብ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔና የፍልስፍና ድርሳኖቻንን ይታዩይመርመሩ… በአክሱም ስልጣኔ፣ በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ትንግርት፣ በጎንደርበእነ ፋሲለደስ የስልጣኔ አየር ዝናዋ የናኘላት፣ እነዛ ፍቅርን በጥበብ አስውበው በቅኔያቸውናበማኅሌታቸው ሰማይ ሰማያትን ሰንጥቀው በመንፈሳቸው ጸባዖት የደረሱ፣ በፍቅር ጧፍ የነደዱበማሕሌታዩ ያሬድ መንፈስ የተነሱ እንደ ተዋናይ ያሉ የቅኔ የጥበብ ጉልላቶች እንደ አጥቢያኮከብ በደመቁባት ምድር ዛሬን ፍቅር የተራብን፣ ጥበብን የተራቆትን፣ ስለ ፍቅር የደከመንምንድነው ምክንያቱ የሚል ይመስለኛል ቴዲ…፡፡

ቴዲ በሙዚቃው ለታሪክ ያለውን ስሱነትና (sensitivity) እውቀትም (Indigenous Knowledge)አሳይቶናል፡፡ ተዋናይን ስንቶቻችን እናውቀዋለን ተብለን ብንጠየቅ የሚያስተዛዝበን ሳይሆን ይቀራል፡፡ በተለይ ደግሞ ለዘመናችን ትውልድ ለአፉም ለልቡም ቅርቦቹ እነ አርሴናል፣ቼልሲ፣ ሜሲ፣ ሮናልዶ፣ እነ ፊፍቲ ሴንት እነ ቢዮንሴ፣ ወዘተ… የባሕር ማዶዎቹ ዝነኞች ናቸውእንጂ እነ ተዋናይን እነ ቅዱስ ያሬድን፣ እነ አጼ ፋሲልን ሊያስባቸው ወኔው ያለውአይመስልም፣ ኅሊናውንም ይደክመዋል እናስ እንዴት፣ ምን ሲደረግስ ሊያስባቸው ይችላል የኔትውልድ፡፡ በቅኔው የተራቀቀና በመንፈሳዊ እውቀቱ አንቱ ስለተባለው ስለ ተዋናይለመስማትም ሆነ ለማወቅ የታሪክ መዛግብትን ማገላበጥ ግድ ይላል፡፡ አሊያም ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት አባቶች እግር ስር ቁጭ ማለት ያስፈልግ ይመስለኛል፡፡

ቴዲ በየትኛው መንገድ የሀገሩንና የቤተ ክርስቲያኑን የጥበብ እና የሥልጣኔ ከዋክብቶችን ሊያውቅ እንደቻለ ባይነገረንም የትናንትናዎቹን የሀገራችንን ባለውለታዎችና የዘመንፈርጦች ማንነት ለማወቅ እና እንዲሁም ታሪኩን ለመመርመር ግን የተጋና የሰላ አእምሮ እንደተቸረው/እንዳለው የግጥሞቹ መልእክቶች ይነግሩናል፡፡ እናም ከታሪካችንና ከስልጣኔያችን መሰረት ከአክሱም ተነስቶ በጊዜና በታሪክ ሃዲድ ላይ አሳፍሮን በትላንት ታሪካችን ውስጥ ራሳችንን እንድንመረምር፤ ራሳችንን እንድናይ ይወተውተናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ይለናል ቴዲ ስለ ፍቅር ዜማው ውብ የግጥሞቹ ስንኞች፡-
. . .የኋለው ከሌለ የለም የፊቱ፣
ሳይራመድ በታሪክ ምንጣፍ፣
ሰው አይደርስም ከዛሬ ደጃፍ፡፡
በማለት ከታሪካችን ጋር እጅ ለእጅ በምናብ ሊያጨባብጠንና ሊያስተያየን ይፈልጋል፤ እናምያለ ትላንት ዛሬ የለም፣ ያለ ዛሬ ደግሞ ነገ አይታሰብም በሚል የመጣንበትና የተጓዝንበትንአኩሪና አሳፋሪ የታሪካችንን ምእራፍ ለማገላበጥ ለደከምን ለእራሱ እና ለእኛ ትልቅ ቁም ነገርያለው ምክር ያስተላልፋል፡፡ ይህ የከያኒው የግጥም ስንኝ የሮማውን ታላቅ የሕግ ሊቅ፣ፈላስፋና አስተማሪ የሆነውን የሲስሮን አባባል አስታወሰኝ፡- ‹‹ከመወለዳችን በፊት ያለውንታሪክ ካላወቅን ዕድሜ ልካችንን ሕጻን ሆነን እንቀራለን፡፡›› ታሪካችንን ለመመርመር እናከታሪካችን ለመማር የደከምን እኛ ዛሬም እንደ አዲስ ሰናፈርስ ስንጀምር ከመጀመር ሀ ሁሳንወጣ እንደ ህጻን ባለህበት እረገጥ የሆንበትና ታሪክን እንድንደግም የተፈረደብን ምስጢሩምን ይሆን በማለት ታሪክ ጠያቂ፣ የታሪክ ወዳጅ፣ ከታሪክ የምንማር እንድንሆን ያተጋናል፡፡
ከምንኮራበት ታሪካችንና ስልጣኔያችን ባልተናነሰ አንገት የሚያስደፋ ስማችንና ማንንታችን በዓለም ፊት በቀየረብን በበርካታ የራብ፣ የእርስ በርስ ጦርነትና መበላላት ታሪክ ዘመናትን ውስጥ አልፈናል፡፡ እናም የመጣንበት መንገዱ ረጅም ዘመናቶቻችንም መከራ ሰቆቃና ዋይታ የነገሰባቸው ናቸው ሲል የትናንቱን ታሪክ ለመድገም የተፈረደብን ይመስል ታሪክ ደጋሚዎች እንድንሆን የሆንበትን እውነታ መመርመርና ማየት እንችል ዘንድ ትልቅ ጥያቄ ያጭርብናል፡፡ ዛሬም እግራችን መሄድ ተስኖት ቆመናል የእርሱ ደጋፊዎች እንዳሉ ሁሉ የእርሱ ተቃዋሚዎች መኖራቸው ተፈጥሮአዊ ነው ነገር ግን በአሉባልታ የቴዲን ስራዎች ጥላሸት ለመቀባት የሚደረግ ትግል ወይ ቅናት ነው አልያም ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው እንደሚባለው ይሆናል፡፡
ደበበ ሠይፉ ቀጣይ ግጥሙን ለኮካዎች የፃፈው ይመስለኛል
ጥሬ ጨው – ደበበ ሰይፉ
————
መስለውኝ ነበረ ፣
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች ፣
ለካ እነሱ ናቸው ፣
ጥሬ ጨው..ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች ፣
መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ-
መታሸት-መቀየጥ
ገና እሚቀራቸው ፣
“እኔ የለሁበትም !”
ዘወትር ቋንቋቸው ።
………. እኔም የዘመኑ ካድሬዎችን ጥሬ ጨው ብያቸዋለው

ሕወሓት ስድስት የኦሮሞ ተወላጆች አለባቸው ጫካ ወስዶ እንደረሸናቸው ተጋለጠ፤ በትግራይ 14 የኦሮሞ ተወላጆች ከጨለማ ክፍል ታስረዋል

$
0
0

ወጣት አራርሳ ኤዴሳ የተባል የጅባት እና ሜጫ ሰው በቶርች እንዲሞት ተደርጓል።

ከምኒልክ ሳልሳዊ

አምባገነኑ የሕወሓት ጁንታ ቢትዮጵያውያን ኦሮሞዎች ላይ የሚያደርሰው አድገኛ የሆነ ዘረኝነትን ያዘለ የጥላቻ መከፋፈል እና እንዲሁም የተማሩ የኦሮሞ ወጣቶችን ለማጥፋት የሚደረገው ሩጫ እየተጋለጠበት መሆኑን የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
የኦሮሞን ሕዝብ ነጻነት እና የመብት እኩልነት ጥያቄዎችን የሚያነሱ ለሕወሃት አስጊ ናቸው ሕዝብን ይቀሰቅሳሉ ተብለው የሚፈሩ እና ከየመንገዱ እና ጎረቤት አገሮች ታፍነው የተወሰዱ የኦሮሞ ተወላጆች በትግራይ ክልል ውስጥ በከፍተኛ ጥበቃ በ እስር ቤት ስቃይ ላይ መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ ቁጥራቸው 14 የሚሆኑ ታሳሪዎች የደረሱበት አይታወቅም ተብሎ ነገሩ ተደፋፍኖ ሕወሓት በከፍተኛ ደረጃ እያሰቃያቸው መሆኑ ታውቋል። ከ እስረኞቹ መካከል ከዚህ ቀደም ወጣት አራርሳ ኤዴሳ የተባለ እና ከበጮ አከባቢ ታፍኖ የተወሰደ ተማሪ በግርፋት እና በድብደባ ሕይወቱ እንዳለፈ ታውቋል። እንዲሁም እስር ቤቱ ውስጥ ከየመንገዱ ታፍነው የተወሰዱ የኢሕኣፓ የቀድሞ አባላት እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
news
ይህ በኢንዲህ እንዳለ በሰሜን ሸዋ አለባቸው ጫካ ውስጥ ሕወሓት ስድስት የኦሮሞ ተወላጆችን እንደረሸናቸው መርጃዎች አጋልተዋል። ወያኔ በተለያየ ጊዜያት ለኦሮሞ ህዝብ መብት የሚከራከሩ እና ከጅቡቲ እና ኬንያ ታፍነው የመጡ እነዚህን 6 የኦሮሞ ተወላጆች ሰብስቦ በመውሰድ ከገደላቸው በኋላ በጅምላ እንደቀበራቸው ታውቋል። አለባቸው ጫካ ማለት የወያኔ እስር ቤቶች እና የማሰቃያ ቦታዎች አንዱ ሲሆን በትግሉ ወቅት የተለያዩ የደርግ መኮንኖች እንዲሁም የሻእቢያ ተቃዋሚዎች እንደተረሸኑበት ይታወቃል። አሁንም በከፍተኛ ጥበቃ ብዛት ያላቸው ዜጎች ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል።
ዚጎቻችን ደብዛቸው ጠፋ እንደወጡ አልተመለሱም ወዘተ እየተባለ በተለያየ ጊዜ ሮሮ ቢሰማም ምንም አይነት ፍንጮች እንዳልነበሩ ሲታወቅ በአሁን ሰአት ግን የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ኢትዮጵያውያን ክየመንገዱ እና ጎረቤት አገር እየታፈኑ ካለፍርድ በምስጢራዊ ወህኒ ቤቶች እየተሰቃዩ እንደሆነ ተጋልጧል።

የዳቦና የዱቄት ጉዳይ እያወዛገበ ነው

$
0
0

በጸጋው አለሙ

በሀገሪቱ ተከስቶ የነበረውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት መንግስት ለተወሰኑ ዱቄት ፋብሪካዎችና ዳቦ አቅራቢዎች የድጎማ ስንዴን በማቅረብ ዳቦን በቁርጥ ዋጋ ለተጠቃሚው እንዲያቀርቡ ሲያደርግ ቢቆይም ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ ግን ቃሉን ጠብቆ የስንዴ ምርቱን እያቀረበ ባለመሆኑ ችግር ላይ መውደቃቸውን አንዳንድ በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል። መንግስት የተወሰነ ዱቄት ፋብሪካዎችና ዳቦ አምራቾችን በራሱ የአቅርቦት ትስስር ውስጥ በማስገባት ባለፉት አመታት የዳቦ ግራምን ወስኖ ባስቀመጠው ዋጋ እንዲሸጡ ሲያደርግ ቆይቷል።

newsሆኖም መንግስት ለዳቦ ቤቶችና ለዱቄት ፋብሪካዎች ስንዴን በማቅረቡ ረገድ እስካለፉት አራት ወራት ድረስ ቢቀጥልም ካለፉት አራት ወራት በኋላ ግን በገባው ቃል መሰረት በቂ ስንዴ ማቅረብ ባለመቻሉ የዳቦ እጥረት እየፈጠረ መሆኑን በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች ገልጸውልናል። እንደነጋዴዎቹ ገለፃ መንግስት በአሁኑ ሰዓት እያቀረበ ያለው የስንዴ መጠን መቅረብ ከሚገባው ሁለት ሶስተኛን እጅ በመቀነስ ነው።

በዚሁ ዙሪያ ካነጋገርናቸው በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል አንዱ የሆኑት የሮዚታ ዳቦ መጋገሪያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተሾመ ተዘራ መንግስት በገባው ቃል መሰረት የተፈለገውን የስንዴ መጠን ሊያቀርብላቸው ባለመቻሉ ከተቀመጠው ዋጋ በተጨማሪ 5 መቶ ብር በኩንታል አውጥተው ከግለሰብ አቅራቢዎች ስንዴ ለመግዛት መገደዳቸውን ገልፀውልናል። በዚህም አንዳንድ ዳቦ ፋብሪካዎች ክስረት እየደረሰባቸው በመሆኑ ከዘርፉ ለመውጣት እየተገደዱ መሆኑን አንዳንድ ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችም ገልፀውልናል።
መንግስት ባስቀመጠው የዋጋ ተመን መሰረት ዳቦ ቤቶች ምርታቸውን እንዲሸጡ ቢገደዱም ግን መንግስት በገባው ቃል መሰረት በቂ የስንዴ አቅርቦትን ባለማቅረቡ ከሌላ ነጋዴ በ1300 ብር እየገዙ በተተመነው ዋጋ ዳቦ መሸጣቸው በቀን የዘጠኝ ሺ ብር ክስረት እየደረሰባቸው መሆኑን አቶ ተሾመ ገልፀውልናል። መንግስት በገባው ቃል መሰረት አንድ ኩንታል ዱቄትን በ796 ብር ሲያቀርብ የቆየ መሆኑ ታውቋል።

በነጋዴዎቹና በመንግስት የስንዴ አቅርቦት መካከል የተፈጠረውን ክፍተት ተከትሎ በአዲስ አበባ በድጎማ ለህብረተሰቡ የሚቀርበው የአንድ ብር ከሃያ ዳቦ እጥረት እየታየበት ነው።
በዚህ ዙሪያ ያነጋገርናቸው በንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማከል ይማም መንግስት በአንድ ወቅት የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ስንዴ በድጎማ ማቅረብ የጀመረበት ሁኔታ ቢኖርም በዘለቄታው ግን በዚህ ይቀጥላል የሚል አስተሳሰብ መያዝ የሌለበት መሆኑን አመልክተዋል።

እንደ አቶ አማከል ገለፃ ዳቦ አቅራቢዎች በሁለት ተከፍለው ሊታዩ የሚችሉ ናቸው። የመጀመሪያዎቹ መንግስት በአንድ ወቅት የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት በስንዴ አቅርቦት ትስስር ውስጥ በማስገባት የተደጎመ ዳቦ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ የተደረጉ ሲሆኑ ከዚህ ውጪ ያሉት ግን የድጎማ ስንዴን ስለማይወስዱ ዳቦን በፈለጉት ዋጋ የሚያቀርቡ ናቸው። በትስስሩ ውስጥ የገቡት የዳቦ ቤት በአሰራሩ አምነውበት መሆኑን የገለፁት አቶ አማከል መንግስት የሀገር ውስጥ ስንዴ አቅርቦት የተረጋጋ በሚሆንበት ወቅት የውጪ የስንዴ ግዢውን የሚቀንስበት ሁኔታ መኖሩን ገልፀውልናል።

ነጋዴዎቹ ከሰርን ቢሉም ነጋዴው እየከሰረ መሸጥ ስለሌለበት መድረኮች ተፈጥረው ውይይት ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ መኖሩንም አቶ አማከለ ገልጸውልናል። በነጋዴዎቹ ከሚገለፁት ቅሬታዎች መካከል አንደኛው መንግስት የዳቦ ተመኑን ሲያወጣ ታሳቢ ያደረገው የስንዴ ዋጋን ብቻ ሲሆን ይሁንና ከዚህ ውጭ ግን የእርሾና ተያያዥ ግብአቶች ዋጋም በየጊዜው እየናረ የመሄድ ጉዳይ ታሳቢ ያልተደረገ በመሆኑ ይህ ሁኔታ ለተጨማሪ ክስረት የዳረጋቸው መሆኑን ነጋዴዎቹ ተናግረዋል። አቶ አማከል በበኩላቸው በአጠቃላይ ነጋዴዎቹ ላቀረቡት ጥያቄ መንግስት ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በመጀመሪያ ጥናት መደረግ ያለበት መሆኑን አመልክተዋል።

ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተላለፈ ጋዜጣዊ መግለጫ “ሕዝባዊ አንድነት ለነፃነት

$
0
0

udJ&AEUPለአለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት የሕዝብን መብት በመቀማትና አፍኖ በሥልጣን ላይ የሚገኘው የህወሃት/የኢህአዴግ መንግሥት ዜጐች በአገራቸው ውስጥ በመዘዋወር ሰርተው እንዳይኖሩ ያገደ ብቻ ሳይሆን በተወለዱበትና እየኖሩበት በአለው ቀያቸውም የገዠው ፓርቲ አባል ካልሆኑ ወይም ደግፈው ካልቆሙ ይሰደዳሉ፣ ይበታሰራሉ፣ ይደበደባሉ፤ በተለያዩ ምክንያቶችም ንብረታቸውን ይቀማሉ፡፡ የተቀዋሚ ፖለቲካ ድርጅት አባል ከሆነ ደግሞ ጫናው ምን ያህል እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ በዚሁ መመሪያቸው መሠረትም በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የመኢአድ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡ ከሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከልም ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህልም፡-


1. በደቡብ ክልል በሰሜንአሪ ወረዳ በጉዛ ዚፍቲ ቀበሌያት የሚኖር ሕዝብ ሕገ-መንግሥታዊ መብቻውን ተጠቅመው በመኢአድ ጥላ ሥር ስለተደራጀና ጽ/ቤት ስለከፈቱ ብቻ ሦስት (3) አመራሮቻቸው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍትህም ተከልክለው ሰሚ አካል ሊያገኙም አልቻሉም፡፡


2. በጐፋ ልዩ ዞን የሚገኙ የመኢአድ አመራሮችና አባላት ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ስለተደራጁ ብቻ ከፍተኛ ድብደባና እስር ደርሶባቸዋል፤ የፓርቲው መታወቂያቸውንም እንዲነጠቁ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ጊዜም አስራ ሁለት (12) የመኢአድ አባላት በሳውላ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡


3. በደቡብ ክልል በደራሼ ልዩ ወረዳ የመኢአድ የወጣቶች የአመራር አባል በጩቤ ተወግተው ለፍትህ አካላት አቤት ቢሉም መልስ አጥተው በችግር ላይ ይገኛሉ፡፡
4. በአማራ ክልላዊ መንግስት በአንካሻ ወረዳ የሚገኙ የመኢአድ አመራር በኢህአዴግ ካድሬዎች ተደብድበው በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ከትናንት በስቲያ ማለትም ሚያዚያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በጐንደር ከተማ በመንግሥት ታጣቂዎችና በሕዝቡ መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የብዙ ዜጎች ሕይወት እንዲጠፋ ሆኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ብዙ ዜጎችም ከቤታቸው እየታፈኑ ወደ አልታወቀ ቦታ እንዲወሰዱ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡


5. በተለያዩ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር በአደረጉት ግጭት ምክንያት ብዙ ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተው፤ ብዙ ንብረትም ወድሟል፡፡


ይህ የሚያሳየን የህወሃት/ኢህአዴግ መንግሥት የማስተዳደር ስልት ችግሩን በዘዴ በመፍታትና በማግባባት ሳይሆን ኃይልን በመጠቀም ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑን ነው፡፡
በአጠቃላይ እንደዚህ ያሉ የከፉ የሰብአዊ መብት ረገጣ አገር ተረካቢውን ወጣት ምሁር ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፡፡


ስለዚህ የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመቃወምና ከተበዳዮች ጐን የቆመ መሆኑን ለማሳየት “ሕዝባዊ አንድነት ለነፃነት” በሚል መሪ መፈክር በመላ አገሪቱ ሕዝባዊ ንቅናቄ ለመፍጠር ከዜጎች ጐን የቆመ ድርጅት መሆኑን ለማሳየት ሰላማዊ ሰልፎችን አዘጋጅቷል፡፡ በዚሁ መሠረትም እሁድ ግንቦት 3 ቀን 2006 ዓ.ም በጐፋ ልዩ ዞን በሳውላ ከተማ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አድርጓል፡፡


ስለዚህም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነት ሲል ከጐናችን እንዲሰለፍ ታላቅ ሕዝባዊ ጥሪ ያስተላልፋል፡፡
አንዲት ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ እና የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት አቶ ድሪባ ኩማ ከስልጣናቸው ሊባረሩ ነው ፓስፖርታቸውንም እንዲያስረክቡ ተጠይቀዋል።

$
0
0

አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ እና የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት አቶ ድሪባ ኩማ ከስልጣናቸው ሊባረሩ ነው ፓስፖርታቸውንም እንዲያስረክቡ ተጠይቀዋል።አባ ዱላ ገመዳና የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው የቁም እስረኞች መሆናቸው ከተለያዩ ምንጮች እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመልከተዋል። የጎልጉል ምንጮች ግን ኦህዴድ ውስጥ በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ እየተካሄደ ያለው ግምገማ ሲጠናቀቅ በርካታ ባለስልጣኖች ክስ እንደሚመሰርትባቸው ተናግረዋል።

በቀድሞው የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አባ ዱላ ገመዳና በአቶ ድሪባ ላይ ይህ ውሳኔ የተላለፈው አገር ጥለው እንዳይወጡ በሚል ነው። ጎልጉል በቅርቡ ካገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣኖች እንዳሉ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። ውሳኔው የተላለፈው ሰሞኑን የአዲስ አበባን አዲስ ማስተር ፕላን ለመተግበር የኦሮሚያ ክልል ከተሞች መካተታቸው ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ነው። ከሁለቱ ባለስልጣናት በተጨማሪ ከፍተኛ የክልልና የዞን የኦህዴድ አመራሮችም በደህንነት ቅርብ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑ ተሰምቷል። ካገር መውጣት የማይችሉም አሉ።

አባ ዱላ /ጃርሳው/

አባ ዱላ ኦሮሚያን ሲረከቡ በማክረር አካሄድ የሚታወቁት አቶ ጁነዲን ያዋቀሩትን ካቢኔ በመበተን ሥራቸውን አንድ ብለው ጀመሩ። አዲስ ካቢኔ ሲገነቡ የመረጡት አዲስ የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎችንና በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቀናቃኝ (የተቃዋሚ) ፓርቲ አባላትን በማስኮብለል ነበር። ህወሃት ለሁለት በተበረገደበት ወቅት ለአቶ መለስ ቡድን ድጋፍ በመስጠት ቅድሚያ የያዙት አባ ዱላ ባስቀመጡት ውለታ መሰረት ኦሮሚያ ላይ ያሻቸውን እንዲያደርጉ የሟቹ መለስ ድጋፍ ነበራቸው። በዚህም ድጋፍ ሳቢያ ኦሮሚያ ላይ የሚፈልጉትን ሲያደርጉ ከተባረሩት መካከል የአሁኑ ፕሬዚዳንት ሙክታር ከዲር ይገኙበታል።

“አትደግፉን ነገር ግን የክልሉን ልማት አታደናቅፉ” በማለት አዲስ የመለመሏቸው የተለያየ አመለካከት ያላቸው አዳዲስ የኦህአዴድ አባላት ኦሮሚያን ከአባ ዱላ እጅ ተረከቡ። አባ ዱላ ፍጹም ነጻነት ይሰጡ ስለነበር ካድሬው ወደዳቸው። ስማቸው ተቀይሮ መለያ ተሰጣቸው፤ “ብራንድ” ሆኑ – “ጃርሳው” ተባሉ። በካቢኔያቸውና በሳቸው መካከል የነበረው ፍቅር በነደደበት ወቅት አባ ዱላ ክልሉን እንደሚለቁ ተሰማ። ባለፈው ምርጫ አባ ዱላ ለፌዴራል እንጂ ለክልል እንደማይወዳደሩ ይፋ ሲደረግ ካድሬው ገነፈለ። “የኢህአዴግ ምክር ቤትን ውሳኔ አንቀበልም” በማለት ተቃወመ። ከአንዴም ሁለት ጊዜ ስብሰባ ቢካሄድም ከስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ተበተነ። በመጨረሻም ራሳቸው አባ ዱላ በመሩት ስብሳባ ካድሬውን ተማጽነው ነገሩ ረገበ። ይሁን እንጂ ቅርሾ ግን ነበር። ይህንኑ አስመልክቶ “ኦህዴድ/ኢህአዴግ በመደብ ትግል መተላለቅ ጀመረ” በማለት ዘግበን ነበር።

አባ ዱላ ኦሮሚያን ሲመሩ ቆይተው ሲመሻሸ “ይህንን ቤት ይዤ ለመታገል አይመቸኝም” በማለት ቦሌ ያስገነቡትን አስገራሚ ህንጻ ለኦህዴድ አስረከቡ። በከፍተኛ ሙስና ይታሙ ስለነበር ተናዘውና ገብረው ታለፉ። ለፌዴራል ተወዳድረው አፈ ጉባኤ ለመሆን በቁ። በወቅቱ የወ/ሮ አዜብ ድጋፍ ቢኖራቸውም የሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን የቀኝ እጅ የሆኑ ባለስልጣኖች ግን ጠምደዋቸው ነበር። ሙክታር አህመድ አንዱና ዋናው ነበሩ። ከላይ በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ አባ ዱላን ከሚቃወሙ መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚቀመጡ ናቸው።

በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ አልፈው እዚህ የደረሱት አባ ዱላ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ተማሪዎች ህይወት የቀጠፈውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አስመልክቶ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ተማሪዎችን ከወ/ሮ አስቴር ማሞ ጋር በመሆን አነጋግረው ነበር። በወቅቱ የተማሪዎቹ ጥያቄ ፍትሃዊ እንደሆነ ሲመሰክሩ፣ ይህንኑ ምስክርነታቸውን ለተለያዩ የአገር ውስጥና የውጪ አገር ሚዲያዎች አሳውቀውም ነበር። አያይዘውም ነፍስ ያለ አግባብ ያጠፉ እንደሚጠየቁ ቃል ገቡ።

የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት አባ ዱላ ይህንን ከተናገሩ በኋላ ከፍተኛ ወቀሳ ተሰንዝሮባቸዋል። “ረብሻውን ያስነሱት ራሳቸው የኦህዴድ ካድሬዎች ናቸው” ከሚል ድምዳሜ የደረሰው ኢህአዴግ ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ ሰፊ የስለላ ስራ አከናውኗል። “ጥፋተኞቹን ለህግ እናቀርባለን” በማለት መግለጫ ያወጣው ኢህአዴግ በቀጣይ የሚያስራቸውና የሚከሳቸው ባለስልጣኖች አሉ። ምንጮቹ በተለይ አባዱላና የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት አቶ ድሪባ ኩማ ላይ ስለሚወሰደው ርምጃ ያሉት ነገር ግን የለም። ክስ ከተመሰረተባቸውና ምርመራው በሰንሰለት ታች ድረስ ከዘለቀ የኦህአዴድ የታችኛው መዋቅር ሊናጋ እንደሚችል ግን ግምታቸውን አኑረዋል። ለምሳሌ ያነሱት ሽፈራው ሽጉጤን ነው። ሽፈራው ሽጉጤ በሙስና እንዲከሰሱ ከተወሰነ በኋላ የታለፉት “የሲዳማ ብሔረሰብ ይነሳል” በሚል እንደሆነ ያወሱት ምንጮች “ክስ ተመስርቶ ምርመራው ቢካሄድባቸው ወ/ሮ አዜብም አሉበት ሲሉ አስቀድመው በምክር ቤት ይፋ በማድረጋቸው ዝምታ ተመርጧል”።

ኦህዴድን ወደ ታች ማዘዝ እንደ ቀድሞው አይቀልም

አዲስ አበባን የሚያሰፋው አዲሱ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዲሆን ሀሳብ ሲቀርብ ድፍን የኦህዴድ ምክር ቤትና ካቢኔ ተቃውሞ አሰምቷል። በክልሉ ምክር ቤት ደረጃም የተያዘው አቋም ተመሳሳይ ነው። ይህንን እውነት የሚያነሱ ክፍሎች ኢህአዴግ/ህወሃት ስንቱን አስሮና ለፍርድ አቅርቦ ይችለዋል ሲሉ ጥያቄ ይሰነዝራሉ” ቀደም ሲል በምርኮኞች ስብስብ የተቋቋመው ኦህዴድና አሁን ያለው ኦህዴድ የተለያዩ መሆናቸውን ኢህዴግ ችግር ሊገጥመው እንደሚችልም ግምታቸውን ያስቀድማሉ።

አሁን ያለው ኦህአዴድ ከምርኮ አስተሳሰብ የተላቀቀ። አዲስ ትውልድ የተካተተበት፣ በጎሳ አስተሳሰብ የተቃኙ፣ ህወሃት በሚፈልገው መጠን ከመታዘዝ በላይ ወደ ራሳቸው ደምና ጎሳ የተሳቡ፣ ይህንኑ አስተሳሰብ እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ የተከሉ በመሆናቸው የተወሰኑ የበላይ አመራሮችን በማሰር ችገሩ ሊፈታ እንደማይችል ሰፊ አስተያየት እየተሰጠ ነው። ለዚህም ይመስላል ኢህአዴግ በመደብ መተላላቅ መጀመሩ ይፋ እየሆነ የመጣው።

የመጨረሻው መጀመሪያ

ለጊዜው ይፋ ሆኑ መረጃዎች እንደሚያመክቱት አባዱላና አቶ ድሪባ ኩማ ካገር መውጣት አይችሉም። የተጀመረው ግምገማ ተጠናቆ የሚሆነው ሳይታወቅ በቅርብ ክትትል ስር ናቸው። የጎልጉል ምንጮች እንደጠቆሙት የዞንና ወረዳ መዋቅሮች ላይ ርምጃ ለመውሰድ ስጋት አለ። ካድሬው ዘንድም መደናገጥ ተፈጥሯል። ህወሃት ውስጥም የአቋም መለያየት ተከስቷል፡፡ በአንድ ወገን ካድሬው እንዳይሸፍትና በቀጣዩ ምርጫ ኢህአዴግን አሳልፎ እንዳይሰጠው ርምጃው የተለሳለሰ መሆን አለበት እየተባለ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ግለ ሂስ በማካሄድ ነገሩን የማርገብና ምርጫውን የማለፍ ስልታዊ አካሄድ አለ። ይሁን እንጂ ኦህዴድ እየተለማመደ ያለው አካሄድ ሌሎችን ትምህርት በሚሰጥ መልኩ ካልታረመ ወደ ፊት ችግሩን ያገዝፈዋል የሚል አቋም የሚያራምዱ መኖራቸው ታውቋል። ህወሃት በዚህ ደረጃ አቋም ለመያዝ አለመቻሉና በርዕዮተ ዓለም መከፋፈል መጀመሩ ለዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የዘራው መርዝ መልሶ ራሱን ሊያጠፋው አፉን መክፈቱ የሚጠቁም ነው፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት “ኢህአዴግ በርዕዮተ ዓለም መበላላት መጀመሩ ይፋ እየሆነ ነው” የሚለው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚነሳ ዓቢይ ጉዳይ ሆኗል፡፡

source: goolgul.com

ከኬንያ የተነጠቀው የሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው

$
0
0

-የኬንያ የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት ከ575 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያጣሉ

መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገውና ቤንች ኢቨንትስ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም አዘጋጅ፣ በመጪው መስከረም በናይሮቢ ኬንያ ሊያካሂደው የነበረውን የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም


ወደ አዲስ አበባ ማዘዋወሩን ባለፈው ሰኞ ማስታወቁን ሐን ጊስካ አፍሪካ ኦንላይን ገለጸ፡፡ ይህንን ተከትሎም በኬንያ የሚገኙ የሆቴል ባለቤቶች፣ የቱሪዝም ባለሙያዎችና የጉዞ ወኪሎች ከኬንያ ተነጥቆ ለኢትዮጵያ በተሰጠው ዕድል ላይ ቅሬታቸውን መግለጻቸውንም የዜና ምንጩ ገልጿል፡፡

ይህ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም መነቃቃትን እንደሚፈጥር አስተያየታቸውን የሚሰጡት የዘርፉ ባለሙያዎችም፣ በዚህ መልካም አጋጣሚ ምክንያት የአገሪቱ ቱሪዝም አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ ብሎ ሊቀመጥ እንደሚችልም ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ በአንፃሩ ኬንያውያን የዘርፉ ተዋንያኖች ግን አምስት ቢሊዮን ሺልንግ ወይም ከ575 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያላነሰ ገቢ እንደሚያጡ ተንብየዋል፡፡ ከዚህም በላይ የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይና የአውስትራሊያ መንግሥታትን የሰሞኑን የጉዞ ማስጠንቀቂያ ተከትሎም የኬንያ ቱሪዝም በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዳ እንደሚችልም ተንብየዋል፡፡

በምሥራቅ አፍሪካ ዋነኛ የቱሪዝም መዳረሻ መሆኗ የሚነገርላት ኬንያ በዓመት ከ66 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ በሚያስገኝላትና ሁለተኛው ትልቁ የአገሪቱ የገቢ ምንጭ በሆነው ቱሪዝሟ ከፍተኛ ዕውቅና ቢኖራትም፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተከታታይ በተፈጸሙባት የሽብር ጥቃቶች ምክንያት የቱሪዝም ገቢዋ እያሽቆለቆለ እንደሚገኝ ምንጮች ያስረዳሉ፡፡ ከሰሞኑ የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግሥታትም አልሸባብ በኬንያ ተጨማሪ ጥቃቶችን ሊሰነዝር እንደሚችል በመጠቆም ዜጎቻቸው ወደ አገሪቱ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲገቱ ማስጠንቀቃቸው፣ የኬንያን ቱሪዝም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳ ተጠቁሟል፡፡

5945654dfa99f60bd6ab567c6edde3e0_Lእንደ አብዛኞቹ የኬንያ የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት አስተያየት የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም ከኬንያ ተነጥቆ ለኢትዮጵያ የተሰጠውም በዚሁ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ምክንያት ነው፡፡ የቤንች ኢቨንትስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማቲው ዊህስ ግን የቦታ ቅያሪው የመጣው ኢትዮጵያ ከኬንያ በተሻለ ለተሳታፊዎች ሰፊ ቦታ ስላላት ነው ብለዋል፡፡ ‹‹ናይሮቢ በርካታ የተሳትፎ ጥያቄ ላመጡ ደንበኞቻችን የሚበቃ ቦታ ስለሌላት አዲስ አበባ ትሻላለች፡፡ በመሆኑም በናይሮቢ ኢንተርኮንትነንታል ሆቴል ሊካሄድ የታቀደው መርሐ ግብር በሸራተን አዲስ ይከናወናል፤›› ሲሉ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

‹‹በዚህም ምክንያት ሌሎችን እናስቀይማለን ብለን አንጠብቅም፤›› የሚሉት ዳይሬክተሩ፣ በቀሩት የአራት ወራት ጊዜ ውስጥ መርሐ ግብሩን በአዲስ አበባ በስኬት ለማካሄድ ጥረቶች መጀመራቸውንም አስረድተዋል፡፡ በናይሮቢ የሚገኘው ኢንተርኮንትነንታል ሆቴል 350 የመኝታ ክፍሎች እንዳሉት፣ ሸራተን አዲስ ግን 293 ክፍሎች ያሉት በመሆኑ የቦታ ጥበት ነው የሚለውን ምክንያት የማይቀበሉት ኬንያውያን የቱሪዝም አካላት፣ ተደጋጋሚ የሽብር ጥቃቱን ማስጠንቀቂያ ሰበብ አድርገው በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

‹‹በተለያዩ ጊዜያት በጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያና በዌስት ጌት የገበያ ማዕከል የደረሰውን የሽብር ጥቃት አስመልክቶ የተፈጠረውን አሉታዊ ሁኔታ ለመቀየር መንግሥት የደኅንነት ሁኔታውን በጥብቅ እየተከታተለ መሆኑን ተረድተው፣ በርካታ ቱሪስቶችን ፊታቸውን መለስ ማድረግ ጀምረው ነበር፡፡ አሁን ምን ተፈጥሮ ነው እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው? ለማንኛውም መልካም ዕድል፤›› ሲል አንድ ኬንያዊ ስሜቱን ገልጿል፡፡

ይህን ዜና ተከትሎ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም ለመታደም የሚመጡ እንግዶች ቁጥር ከፍ እንደሚልና እስከ ሰኔ 2 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስም ባለው የምዝገባ ጊዜ ተሳታፊዎች ቅናሽ የተደረገበትን አንድ ሺሕ ዶላር ክፍያ መፈጸም እንደሚገባቸውም አዘጋጁ አካል ገልጿል፡፡ የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም ከመጪው መስከረም 19 እስከ መስከረም 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በሸራተን አዲስ የሚካሄድ መሆኑንም አዘጋጁ አሳውቋል፡፡

ከአራት መቶ በላይ ልዑካንና 27 ኩባንያዎችን እንዳስተናገደ በተነገረለት የአምናው የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎረም የኬንያ ትልቁ ባለአምስት ኮከብ ሆቴልን ተጠቃሚ እንዳደረገ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ይህን መሰሉ መልካም አጋጣሚ በአዲስ አበባ እንደሚጠበቅ አዘጋጁ ገልጿል፡፡ በሌላ በኩል በአፍሪካ በርካታ መዳረሻዎች ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ የውሳኔ ሒደት ውስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳሳረፈ ተገልጿል፡፡ የሸራተን አዲስን ተወዳዳሪ የዋጋ አቅርቦት ተከትሎ ተሳታፊዎች የጉብኝቱ አካል ብቻ ሳይሆኑ፣ የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ተገኝተው ስለአፍሪካ ያላቸውን እይታ እንዲያሰፉ ተጨማሪ ዕድል የሚፈጥርላቸው መሆኑን ዘገባው ይጠቁማል፡፡

ኬንያ ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝግጅቱን በተሳካ ሁኔታ ያዘጋጀች በመሆኗና ሁሉንም አቅርቦቶች በአማራጭነት የያዘች መሆኗን የሚገልጽ አንድ ተሳታፊ፣ በውሳኔው መበሳጨቱንና ውሳኔው የማይቀየር ከሆነም ወደ አዲስ አበባ እንደማይጓዝ መግለጹን ከኬንያ የወጡ ዘገባዎች ገልጸዋል፡፡ አዘጋጁ ቤንች ኢቨንትስ ግን ጊዜው የኢትዮጵያ ነው እያለ ነው፡፡

Source: Ethiopian Reporter


ግዮን ሆቴል እንዳይሸጥ ተወሰነ

$
0
0

Gihonለሽያጭ ከሚቀርቡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ ግዮን ሆቴል እንዲወጣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ትዕዛዙ የተሰጠው የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ግዮን ሆቴልን ከሽያጭ ውጪ አድርጐታል፡፡

የኤጀንሲው ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ግዮን ሆቴል እንዳይሸጥ መመርያ መሰጠቱን ገልጸው፣ ነገር ግን ስለሆቴሉ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ አንጋፋውን ግዮን ሆቴል ለመሸጥ ለበርካታ ጊዜያት ጨረታ አውጥቷል፡፡ ከጨረታ በተጨማሪም ሆቴሉን ለመግዛት ፍላጐታቸውን ካሳዩ ኩባንያዎች ጋር ሲደራደር ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ሆቴሉን የሚገዛ በመጥፋቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሽያጭ ሒደቱ እንዲቋረጥ ማድረጉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የፕራይቬታይዜሽን ምንጮች እንደሚሉት ግዮን ሆቴልን ለመግዛት የተካሄዱት በርካታ ድርድሮች የከሸፉት፣ በዋጋ ውድነትና በተለያዩ መደራደሪያ ነጥቦች ምክንያት ነው፡፡

በ1950 ዓ.ም. የተመሠረተው ግዮን ሆቴል በ123 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ነው፡፡ ሆቴሉ 191 መኝታ ክፍሎች፣ ሰባት የመሰብሰቢያ አዳራሾችና አንድ የመዋኛ ገንዳ አለው፡፡ የተለያዩ ሬስቶራንቶችም አሉት፡፡

የአፄ ኃይለ ሥላሴ ልጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አክሊለ ብርሃን መኰንን 8.3 ቢሊዮን ብር በማቅረብ የሆቴሉን 80 በመቶ ድርሻ ለመያዝ ከፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ቢፈራረሙም፣ ተግባራዊ መሆን አልቻለም፡፡

ሆቴሉ ያሉት ሕንፃዎች አሮጌ የሚፈርሱ በመሆናቸው ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ያስቀመጠው መነሻ የመሸጫ ዋጋ ከፍተኛ ነው የሚሉ በርካታ ናቸው፡፡

በመጨረሻ ግን ግዮን ሆቴል የመንግሥት ይዞታ ሆኖ እንዲቀጥል የተወሰነ በመሆኑ፣ መንግሥት ተጨማሪ ወጪ በማውጣት ማሻሻያ ካደረገለት በኋላ ሆቴሉን በአምስት ኮከብ ደረጃ ለማሳደግ ዕቅድ አለው፡፡

ሆቴሉ በአመቺ ቦታ ላይ ሰፊ ይዞታ ያለው በመሆኑ የማሻሻያ ሥራ ከተሠራበት ትልቅ ገቢ የሚያስገባና አትራፊ የመንግሥት የልማት ድርጅት እንደሚሆን ለሆቴል ሥራ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ያስረዳሉ፡፡

Source: Ethiopian Reporter

የአልሸባብን የሽብር ተልዕኮ ሊፈጽም ነበር የተባለ ግለሰብ ተያዘ

$
0
0

በአዲስ አበባ ከተማ የአልሸባብን የሽብር ተልዕኮ ለመፈጸም ሲዘጋጅ ነበር የተባለ ግለሰብ መያዙን፣ የብሔራዊ ደኅንነትና መረጃ አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ ግብረ ኃይል ማክሰኞ ምሽት አስታወቀ፡፡

ግብረ ኃይሉ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ተያዘ የተባለው ግለሰብ በአዲስ አበባ ከተማ የሽብር ጥቃት ለማድረስ የሚያስችል ዝግጅት ሲያደርግ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡ ኅብረተሰቡ የተለዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያስተውል ለሚመለከተው አካል በፍጥነት እንዲያሳውቅ የጠየቀው ግብረ ኃይሉ፣ ስለግለሰቡ ዝርዝር መግለጫ አልሰጠም፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ አልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ በተደጋጋሚ ከሚያደርገው ዛቻ የዘለለ ጥቃት በኢትዮጵያ ላይ ሊፈጽም እንደማይችልና የሚያሰጉ ሁኔታዎች በኢትዮጵያ አለመኖራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአሜሪካ መንግሥት በአዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲው አማካይነት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩና ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ አሜሪካውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ አስታውቋል፡፡

አልሸባብ በኢትዮጵያ ጥቃት ለመፈጸም እንደሚችል የሚያስረዱ ታማኝ መረጃዎች እንደደረሱት በመጠቀስ ነው የጥንቃቄ ማሳሰቢያውን ኤምባሲው በድረ ገጹ ላይ ይፋ ያደረገው፡፡

ጉዳዮችን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ምንም ዓይነት የፀጥታ ሥጋት እንደሌለበት አስታውቀዋል፡፡

አልሸባብ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ላይ እንደሚዝት የጠቆሙት ቃል አቀባዩ፣ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ምንጊዜም ዝግጁና ጥንቁቅ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ያወጣው የጥንቃቄ ማሳሰቢያን በተመለከተ፣ በራሳቸው መንገድ የተለመደ አሠራር ነው ብለዋል፡፡

news‹‹በኢትዮጵያውያና በምዕራባውያን ማዘውተሪያዎች ላይ አልሸባብ የፈጠረው ሥጋት›› በሚል የወጣው ይኼው የአሜሪካ መንግሥት የጉዞ ማስጠንቀቂያ፣ ‹‹ኤምባሲው አልሸባብ በኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያንንና ምዕራባውያንን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ለመፈጸም መዘጋጀቱን ታማኝ የሥጋት ማስጠንቀቂያ ሪፖርቶች ደርሰውታል፤›› ይላል፡፡

ኤምባሲው በደረሰው መረጃ መሠረት የአልሸባብ አባላት በቅርብ ሳምንታት ውስጥ፣ በኢትዮ ሶማሊያ ድንበር አካባቢ ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው መግባታቸው ታውቋል፡፡

ኤምባሲው ጥቃቱ የሚፈጸምበትን ጊዜና ቦታ በግልጽ ባይጠቅስም፣ በኢትዮጵያ አሜሪካውያንና ሌሎች ምዕራባውያን በብዛት ተሰባስበው የሚገኙባቸው ሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶች፣ የገበያ ማዕከላትና የእምነት ቦታዎች ላይ ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል በማመላከት፣ በእነዚህ ሥፍራዎች የሚንቀሳቀሱ አሜሪካውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስጠንቅቋል፡፡ ማስጠንቀቂያው በኢትዮጵያ የሚኖሩና ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጐች፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጉዞ ማስጠንቀቂያ ፕሮግራምን በተጠንቀቅ እንዲከታተሉ አሳስቧል፡፡

የአፍሪካና የአሜሪካ ኢነርጂ ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ ስብሰባቸውን እያካሄዱ ሲሆን፣ በመዲናው እንግዶች ሲበዙ በሆቴሎች ከአባባቢ ጠበቅ ያለ ፍተሻና ጥበቃ ማድረግ የተለመደ ቢሆንም ሪፖርተር ተዘዋውሮ ማረጋገጥ እንደቻለው፣ በበርካታ ሆቴሎችና ሥፍራዎች የአሜሪካ መንግሥት የጉዞ ማስጠንቀቂያ መውጣትን ተከትሎ እጅግ የተጠናከረ ፍተሻ እየተደረገ ይገኛል፡፡

አልሸባብ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ስታዲየም በእግር ኳስ ተመልካቾች ላይ ለማፈንዳት ያዘጋጀው ቦምብ ድንገት ፈንድቶ ሽብር ሊፈጽሙ የተዘጋጁ አባላቱ መሞታቸው የሚታወስ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ወታደሮች በቅርቡ በሶማሊያ የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ኃይል (አሚሶም) ከተቀላቀሉ ጊዜ ጀምሮ፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ በርካታ የአገሪቱ ከተሞች ከአልሸባብ ነፃ መውጣታቸው በስፋት እየተዘገበ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ ሲዝት ቆይቷል፡፡ ሰሞኑን የኢትዮጵያና የሶማሊያ ወታደሮች በከፈቱት ጥቃትም 74 የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን ከሶማሊያ የወጡ ዘገባዎች ያስረዳሉ፡፡

Source: Ethiopian Reporter

ፕሮፌሰር መስፍን ለሰማያዊ ፓርቲ እራት ግብዣ የ20 ሰው ትኬቶችን እንደገዙ የፌስ ቡክ ጉዋደኞቼ ጽፈው አነበብኩ

$
0
0

 

Prof. Mesfin Woldemariam

Prof. Mesfin Woldemariam

ከልጅነታቸው እስከ ሽምግልናቸው ለዚች ሀገር ያላቸውን ሁሉ ሳይሰስቱ የሰጡት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ሌላው ቀርቶ የግላቸው የሆነ መኖሪያ ቤት እንደሌላቸው የምናውቅ ስንቶቻችን እንሆን?
አዎ! ለነ አባዲ ዘሙ ድንቅ ቪላ የገነባች ሀገር ባለፉት ረጅም ዓመታት ለፕሮፌሰር መስፍን አንድ ክፍል ቤት አልሰጠቻቸውም። ለአያሌ ዓመታት የኖሩት እና አሁንም እየኖሩ ያሉት ፒያሳ በሚገኝ የኪራይ ቤቶች ህንጻ ውስጥ ተከራይተው ነው።
ይህ ስለሆነ ፕሮፌሰር ፦ “ኢትዮጰያ ሀገሬ ሞኘ ነሽ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ፣ የገደለሽ በላ” እያሉ በቁጭት አላንጎራጎሩም። ይልቁንም በምርጫ 97 ወቅት ለወጣቶች ባደረጉት አንድ ገለጻ ላይ ፦”እቤቴ ስገባ አፍራለሁ”ሲሉ ነው የሰማሁዋቸው። የገረመኝም ይኸው ነው።
“ማደሪያ የሌላቸው በርካታ ዜጎች መንገድ ላይ ወድቀው እያየሁ ማታ እቤቴ ስገባ አፍራለሁ፣ ጎዳና የሚያድሩትን እያሰብኩ እንቅልፍ አይወስደኝም፣ አሁን የምኖርበት የኪራይ ቤት በዝቶብኛል” ነው ያሉት ፐሮፌሰር መስፍን።
ጤና እና ረጅም እድሜ ለጋሽ መስፍን!

Dereje Habtewold

በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ወራሪው ማን ነው? ተወራሪዎቹስ? – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ታላቅ የሕዝብ ቅልቅል ተካሂዷል። ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል፦ የአህመድ ግራኝ ወረራ፣ የኦሮሞ ወረራ፣ በዘመነ መሣፍንት የነበሩት የእርስ በእርስ ጦርነቶች፣ ፈፃሜ-ዘመነ መሣፍንትን ያበሠሩት የማዕከላዊ መንግሥትን እንደገና የማዋቀር ጦርነቶች እንዲሁም ሁለቱ የኢጣሊያ ወረራዎች የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚያ ጦርነቶች እና የእርስ በእርስ ግጭቶች ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የሕዝብ ክፍል ሕይዎት እንዳሣጡ አይካድም። ያንንም ተከትሎ ከኑሮ አስገዳጅነት እና በአገዛዝ ኃይሎች የበላይነት የያዘው አካል በሚፈጥረው የፖለቲካ አሠላለፍ መለዋወጥ ምክንያት የአንዱ ጎሣ ወይም ነገድ አባሎች በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመጥፋት ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዚህ ረገድ ከኢትዮጵያ ዋና ዋና ነገዶች እና ጎሣዎች መካከል፦ በምዕራብ ኢትዮጵያ ነዋሪ የነበሩት የጋፋት ነገድ በኦሮሞ ወረራ ሙሉ በሙሉ እንዲጠፉ ሆነዋል ወይም ማንነታቸውን ተገድደው ለውጠው «ኦሮሞዎች» ወይም «ዐማራዎች» ወይም በሌላ ነገድ ስም ይጠራሉ፤ የሜያ ነገድ ተወላጆች ደግሞ በግራኝ አህመድ እና በኋላም ተከትሎ በመጣው በኦሮሞዎች ወረራ ምክንያት ቁጥራቸው በእጅጉ ተመናምኖ ዛሬ በዝዋይ ኃይቅ ውስጥ በሚገኙ ደሴቶች እና አካባቢው ብቻ ተወስነው ይገኛሉ። ጥንት በባሊ (ባሌ) እና ፈጠጋር (አርሲ) ተስፋፍተው ይኖሩ የነበሩት ሐዲያዎች እና ከንባታዎች በኦሮሞዎች ወረራ ተጨፍልቀው «ኦሮሞዎች» ሲባሉ ቀሪ ወገኖቻቸው በደቡብ ምዕራብ ሸዋ በአንድ ጠባብ አካባቢ በተጨናነቀ ሁኔታ እንዲኖሩ ተገድደዋል። ከዚህ በተጨማሪም፦ አርጎባዎች፣ ቀቤናዎች፣ ወርጂዎች፣ አላባዎች፣ ሲዳማዎች፣ ወዘተርፈ በኦሮሞዎች ወረራ ምክንያት ማንነታቸውን እንዲቀይሩ ተገድደዋል፤ ከዚያም አልፎ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። በእናርያ ንጉሥ ግዛት ሥር የነበሩት ጃንጀሮዎች (የም) በኦሮሞ ቆሮዎች (በእነ አባ ጅፋር) በገፍ በባርነት ተፈንግለዋል። የዳውሮ እና የገሙ ሰዎች ደግሞ ግዛታቸውን በኦሮሞ ወራሪዎች ተነጥቀዋል። በመሆኑም የዘመናዊት ኢትዮጵያን የሕዝብ አሠፋፈር ጥንቅር ለውጥ ለመገንዘብ ከአህመድ ግራኝ ወረራ ጀምሮ ማዬቱ ለበለጠ ግንዛቤ ይረዳል።

ግራኝ አህመድ በኢትዮጵያ ላይ ወረራውን የጀመረው የንጉሡ የአፄ ልብነድንግል ሹም እና የደዋሮ (ምዕራብ ሐረርጌ) ገዢ ከነበረው ከአዛዥ ፋኑኤል ጋር በ፲፭፻፲፯ ዓ.ም. ባደረገው ውጊያ ነበር። ግራኝ አህመድ ዘንተራ (ደንቢያ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ጣና ሐይቅ አጠገብ) በአፄ ገላውዲዎስ ሥር ሲዋጉ በነበሩት የፖርቱጋል ወታደሮች የጥይት አረር ተመትቶ በየካቲት ፳፯ ቀን ፲፭፻፴፭ ዓ.ም. እስኪገደል ድረስ ኢትዮጵያን ለ፲፱ ዓመታት ያህል በጦርነት አመሠቃቅሏታል፤ ዜጎቿን ኍልቆ-መሣፍርት ለሌለው ግፍ እና በደል ዳርጓቸዋል። የእርሱን የወረራ ፍፃሜ እግር በእግር ተከትለው የመጡት የኦሮሞ ወራሪዎች ደግሞ ከ፲፭፻፵ዎቹ ጀምረው ከደቡብ ከነጌሌ ቦረና አካባቢ ተነስተው ከፊታቸው የነበረውን የሌላውን ነገድ እና ጎሣ ሕዝብ ዕድሜ እና ፆታ ሣይለዩ በጅምላ እየፈጁ እስከ ትግራይ ድረስ ዘልቀዋል። ኦሮሞዎች አብዛኛውን የኢትዮጵያ ክፍል በተከታታይ ወረራዎች ለመያዝ የፈጀባቸው ጊዜ ከ፫፻ ዓመታት ይበልጣል። ስለዚህ ዛሬ ያለውን የኢትዮጵያን የሕዝብ አሠፋፈር በቅጡ ለመረዳት ያለፈውን የ፩፻፳ ያመታት ብቻ ታሪክ ሣይሆን አህመድ ግራኝ ኢትዮጵያን ከወረረበት ከ፲፭፻፲፯ ዓ.ም. ጀምሮ የነበረውን ሁኔታ መመርመር የግድ ያስፈልጋል። ሆኖም ባለፉት ፵ እና ፶ ዓመታት በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ «መሪዎች ነን» ብለው የተነሱ ልሂቃን የኢትዮጵያን የረዥም ዘመን የታሪክ ጉዞ በ፻ ዓመታት ብቻ በመገደብ በጉንጭ አልፋ ውዝግብ ሕዝብን ሲያተራምሱ ይታያሉ። በተለይም ለዚህ ውዝግብ ቀዳሚዎቹ የትግሬ እና የኦሮሞ ልሂቃን ሲሆኑ እንደ ዋለልኝ መኮንን ዓይነቶቹ ጥራዝ ነጠቅ የዐማራ ልሂቃንም በዚህ ክበብ ውስጥ ይገኙበታል።

ታሪካቸውን በቅጡ ያልተረዱ ጥቂት፣ አክራሪ እና ዘረኛ የሆኑ የኦሮሞ ልሂቃን፣ ከጀርመናውያን የኃይማኖት ሠባኪዎቻቸው የተጋቱትን ለኢትዮጵያዊነት እና ለዐማራ ያላቸውን ጥላቻ እንደበቀቀን ደግመው፣ ደጋግመው ሲጮኹ ይሰማሉ። ለመሆኑ የዚህ አስተሣሰብ ምንጩ ከዬት ነው? በዘመነ ቅኝ አገዛዝ የአፍሪካ ቅርምት ወቅት፣ እንግሊዞች፥ «ግብፅን መቆጣጠር ማለት ቀይ ባሕርን መቆጣጠር ማለት ነው፤ ቀይ ባሕርን መቆጣጠር ማለት ደግሞ መላውን የመካከለኛውን ምሥራቅ መቆጣጠር ነው፤» ብለው በማመን ግብፅን «የገንዘብ ብድር ዕዳን» ሠበብ በማድረግ ከቱርኮች ነጥቀው ቅኝ ግዛታቸው አደረጓት። እንደዚያም ሁሉ፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሠባኪዎች «ቻይናን ስጡን እና እስያ የእኛ ትሆናለች» ብለው ሰላዮቻቸውን በኃይማኖት ሠባኪነት ሽፋን በቻይና አሠማሩ፥ ቻይናም ቀስ በቀስ በምዕራባውያን ተፅዕኖ ሥር ወደቀች። የኦነግ እና የኦሕዴድ የንስሃ አባታቸው የሆነው ጀርመናዊው ሰላይ ዩሓን ክራፍ በበኩሉ «ጋሎችን ስጡን እና መላው የመካከለኛው የአፍሪቃ ክፍል የኛ [የጀርመኖች] ይሆናል፤» በማለት ጀርመን የኦሮሞን ነገድ ተጠቅሞ ምሥራቅን እና መካከለኛውን የአፍሪቃ ክፍል በቅኝ ግዛቱ ሥር የሚያውልበትን መንገድ መጥረጉን እናያለን። ስለሆነም «የነፃ ኦሮሚያ» ዓላማ አራማጆችም «ኦሮሚያ» ከሚባለው አዲስ ወያኔ-ሠራሽ ግዛት ጀምሮ የሚያራግቡት ተግባር ሁሉ፣ በ፲፱ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሠፊውን የኢትዮጵያ አካል ቆርሶ ለጀርመን የቅኝ ግዛት ለማድረግ የታቀደው ሤራ በዚህ በእኛ ዘመን ታድሶ መቅረቡን መገንዘብ ያስፈልጋል።

ከዚህ በተጨማሪ ዩሓን ክራፍ፣ ጀርመን በአውሮፓ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ የበላይነቱን እንድትይዝ ያለውን ፍላጎት እንደሚከተለው ገልጿል፥ «“ጋሎችን” መያዝ መካከለኛው አፍሪቃን ለመቆጣጠር ከማስቻሉም ሌላ፣ በቀይ ባሕር ዳርቻ የሚገኙትን አገሮችን መያዝ ከንግድ መቆጣጠሪያነት ባሻገር፣ ጀርመን በአውሮጳ ያላትን የበላይነት ማረጋገጥ እና የጀርመንን ሥልጣኔ በዐረቦች ምድር፣ በአበሻ እና በመላው ምሥራቅ አፍሪቃ ማስፋፋት ነው። የጀርመን በምሥራቅ አፍሪቃ መስፋፋት፣ የእስልምና ኃይማኖት በዐረብ ምድር እና በአፍሪቃ ጠረፎች የሚያደርገውን መስፋፋት የሚያዳክም፣ የዐረቦችን የባሪያ ንግድ የሚቀንስ፣ እንዲሁም የምሥራቅ አፍሪቃን ሕዝብ አረመኔነት በክርስትና ሥልጣኔ መዋጋት ነው። ከአበሻ በስተደቡብ ያሉት “ጋሎች” የሠፈሩበት ቦታ ለአውሮጳውያን ሠፋሪዎች ምቹ ቦታ ነው፤» በማለት ጀርመን የኦሮሞዎችን ልብ ከኢትዮጵያዊነት ስሜት በማውጣት ምሥራቅን እና መካከለኛውን አፍሪቃ እንዴት በቁጥጥሩ ሥር ማዋል እንደሚችል «ወንጌላዊው» ክራፍ ምክሩን ለግሷል፤ ምክሩም የመከነ አይመስልም፤ ኦነግን እና መሰል ድርጅቶችን አፍርቷል። ለአብነትም ያህል ለኦነግ መመሥረት እና መጎልበት የስካንዴኔቪያን አገሮች፣ ጀርመኖች እና ሌሎችም የቅኝ ገዢነት ቅዠታቸው ያልለቀቃቸው አውሮጳውያን የሚያደርጉትን ሁሉን-አቀፍ ድጋፍ ልብ ይሏል!

በማስከተልም ዩሓን ክራፍ፣ ከሸዋ በስተደቡብ የሚኖሩት “ጋሎች” ብዛት ያላቸው መሆኑን ገልጦ፣ የእስላሞችን የመሥፋፋት ወረራ ሊመክቱ እንደሚችሉ እና የአፍሪቃ ጀርመኖች ሊሆኑ እንደሚችሉ ዕምነቱን አስረድቷል። ዩሓን ክራፍ ምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪቃ በጀርመን ቁጥጥር ሥር እንዲውል የነደፈው አንዱ ሥልት፣ ሚሽነሪዎችን በወንጌል ማስፋፋት ስም በአካባቢው በማሠማራት፣ የየአገሮቹ ልዩ ልዩ ነገዶች እና ጎሣዎችን ሊለያዩበት እና ሊናቆሩበት የሚችሉበትን ዘዴ ማጥናት፣ እንዲሁም ያገኟቸውን የማናቆሪያ ቀዳዳዎች ማስፋት ነበር። ለዚህም ዩሓን ክራፍ ያቀረበው ኃሣብ፦ «በደቡብ እና በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆችን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ነገዶች በመለዬት፣ በተቃራኒው ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን የኦሮሞ ጎሣዎች አንድ የሚያደርግ አዲስ መጠሪያ ስም በመስጠት፣ በዚህ አዲስ ስም የሚታወቅ የአካባቢ ስም ፈጥሮ፣ ያን አካባቢ ከቀረው የኢትዮጵያ የሚገነጥል ብሔርተኛ ቡድን በጀርመን ሁለንተናዊ ርዳታ ማጠናከር፤» የሚለው ነበር። ለዚህም «“ጋላ” የሚለው ስም ሁሉንም የነገዱን አባሎች አጠቃሎ ለመጥራት አያስችልም» የሚል ምክንያት በመስጠት፣ «ኦርማኒያ» ከሚለው ስም «ኦሮሚያ» የሚል ቃል በማውጣት ጥንት “ጋላ” በመባል የሚታወቀው ነገድ በዚህ እርሱ ባወጣው አዲስ ስም እንዲጠራ እና «ኦሮሚያ» ለሚባል ክልል ነፃ መውጣት እንዲታገል በወንጌል ማስፋፋት ስም አስተማረ፣ ሰበከ። በዚህ መሠረት ዩሓን ክራፍ ራሱ «ኦሮሚያ» ብሎ የሰየመውን የኢትዮጵያ አካል መቆጣጠር ማለት፣ ምሥራቅን እና መካከለኛውን አፍሪቃ መቆጣጠር እንደሆነ በማመን የጀርመን ተስፋፊዎች ዓይናቸውን ኢትዮጵያን በማፍረስ ላይ እንዲያነጣጥሩ ምክር ለገሠ።

የዩሓን ክራፍ እና የመሠሎቹ ምክር በጀርመን ቅኝ ገዢዎች ልብ ውስጥ መስረፁ ማስረጃው ጀርመን በአፍሪቃ አኅጉር ላይ ትከተል በነበረው የቅኝ ግዛት ፖሊሲ ላይ ጉልህ አሻራ አኑሯል። በዚህ ረገድ እስከ ፩ኛው የዓለም ጦርነት ድረስ ጀርመኖች ከምሥራቅ አፍሪቃ፥ ታንዛኒያን፣ ሩዋንዳን እና ብሩንዲን፤ ከምዕራብ አፍሪቃ ቶጎን፣ ከፊል ጋናን እና ካሜሩንን፤ ከደቡባዊ አፍሪቃ ደግሞ ናሚቢያን በቅኝ ግዛትነት በያዙበት ወቅት ከእንግሊዞች፣ ፈረንሣዮች እና ጣሊያኖች በከፋ ሁኔታ ያካሄዱት የከፋፍለህ-ግዛው የቅኝ አገዛዝ አካሄድ አይረሣም። ከሁሉም መዘንጋት የሌለበት አብይ ነጥብ፥ በ፲፱፻፹፮ ዓም በሩዋንዳ በሁቱዎች እና በቱትሲዎች መካከል የደረሠው የዘር ዕልቂት እና በብሩንዲም በየጊዜው በዘር ልዩነት ምክንያት የሚደረገው መተላለቅ ሠንኮፉ በጀርመን ቅኝ ገዢዎች የተተከለ እና በኋላም ጀርመኖቹን በተኩት ቤልጂጎች ዳብሮ በዘመናችን ደግሞ በፈረንሣዮች የተተበተበ የተንኮል ድር ድምር ውጤት መሆኑን ነው። በእኛም አገር በኢትዮጵያ፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት በዩሓን ክራፍ መሠሎቹ አመለካከት ተኮትኩተው ያደጉ የኦሮሞ ልሂቃን የሚያቀነቅኑት አስተሣሰብ አለ። ይኼውም፥ የያዙትን የኢትዮጵያዊነት ማንነት ለማስጠበቅ ሣይሆን ለማጣት በሚያስገድድ መልክ በራሣቸው ላይ ዘመቻ ከፍተው፣ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ቀርቶ ለራሳቸው ሊሰሙት የማይፈቅዱትን ጩኸት ሲያሰሙ ይደመጣሉ።

ለመሆኑ ጥቂት የኦሮሞ ልሂቃን ነገዳቸውን “ጋላ”፣ ቋንቋቸውን “ጋልኛ” የሚለውን ዐማሮች እንደሰጡዋቸው አድርገው የሚያቀርቡት ታሪካዊ መሠረት አለው? በመሠረቱ “ጋላ” እና “ጋልኛ” የሚሉትን ስሞች ዐማራው አላወጣቸውም። እንዲያውም የኦሮሞን ታሪክ በስፋት እና በጥልቀት ያጠኑ ሰዎች እንደሚያስገነዝቡት “ጋላ” ማለት እስላምም፣ ክርስቲያንም ያልሆነ ማለት እንደሆነ ያብራራሉ። የቃሉም ምንጭ ሶማሊኛ እንደሆነ ያስገነዝባሉ። በሌላ በኩል “ጋላ” ማለት ግመል ማለት ነው የሚሉም አሉ። ሌሎች ደግሞ “ጋላ” የሚለው ቃል «ገላ» ከሚለው የኦሮሚኛ ግሥ የወጣ መሆኑን እና ትርጉሙም «ወደ ቤታችን መሄድ ፈለግን፣ ወደ ቤታችን ሄድን ወይም ገባን» ማለት እንደሆነ ያስረዳሉ። ይህም ትርጉም ኦሮሞዎች በሶማሌና በባንቱ ጎሣዎች ተገፍተው፣ ከነበሩበት ከምሥራቅ አፍሪቃ የሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻዎች ፈልሰው ወደ ደቡብምሥራቅ ኢትዮጵያ ግዛት፥ ወደ ባሌ፣ የተጠጉበትን ዘመን በማውሣት፣ በሰላም ተረጋግተው የሚኖሩበትን ሥፍራ ፈልገው ማግኘታቸውን የሚያመለክት ስያሜ እንደሆነ ብዙዎች በትርጉሙ ይማማሉ። ስለዚህ ጥቂት ዘረኛ የኦሮሞ ልሂቃን «“ጋላ” የሚለውን የስድብ ስያሜ የሰጠን ዐማራው ነው፤» የሚሉት የራሣቸው የማንነት ቀውስ ያስከተለባቸው ግራ መጋባት ከመሆን ውጭ ሌላ አሣማኝ ምክንያት የላቸውም። «ዐማራ ይህንን መጠሪያ ሰጠን» የሚሉትም ውንጀላ ፍፁም መሠረተ-ቢስ ሐሰት ነው። በአንፃሩ «ኦሮሞ» እና «ኦሮሚያ» ለሚሉት መጠሪያዎች የታወቀ ፈጣሪ አላቸው፦ እርሱም አፍቃሬ ቅኝ ገዢዎች የነበረው ጀርመናዊው ዩሓን ክራፍ ነው።

ዩሓን ክራፍ «ጋላ» የሚለውን ቃል ለመቀየር ያነሣሣውን ኃሣብ ሲያስተነትን፦ «ጋላ» የሚለውን ቃል ሲተረጉም «ስደተኛ» ማለት እንደሆነ እና ይህም መጠሪያ በዐረቦች እና በ«አበሾች» የተሰጠ እንደሆነ ይገልፃል። በአንጻሩ እርሱ የፈጠረው «ኦርማ» ወይም «ኦሮማ» ማለት ትርጉሙ «ጎበዝ» ማለት እንደሆነ ያምናል። በእርሱ አባባል «ጋሎች» ለራሣቸው እና ለሚኖሩበት አካባባቢ አጠቃላይ የወል መጠሪያ ስለሌላቸው «ኦርማኒያ» ተብለው እንዲጠሩ ኃሣብ አቅርቧል። ሆኖም ይህንን የዩሓን ክራፍን ኃሣብ የእርሱ-ቢጤ የሆኑ የዘመኑ ሚሽነሪዎች እና ተመራማሪዎች እንኳን አልተቀበሉትም። ለምሣሌም ያህል፦ ኢትዮጵያን ያጠኑ እንደ ዶክተር ቻርለስ ቴ ቢክ ያሉ የመልከዐምድር ተመራማሪዎች፣ ለኦሮሞዎች «ጋላ» የሚለውን ስም የሰጡዋቸው ዐረቦች እና «አበሾች» አለመሆናቸውን እና ስሙ ከራሣቸው ቋንቋ የተገኘ እንደሆነ ይሞግታሉ። ይሁን እንጂ፣ ዕውነቱን ትተው ውሸቱን፣ ሠፊውን ጠልተው ጠባቡን፣ የሚያኮራውን ንቀው የሚያቀልለውን፣ የሚያስከብረውን አውግዘው የሚያዋርደውን፣ የመረጡት ጥቂት «ተማርን ያሉ» የኦሮሞ ልሂቃን፣ የዩሓን ክራፍን ስብከት አምነው ተቀብለው፣ ዐማራን እና ኢትዮጵያን ከምድረ-ገፅ በማጥፋት፣ «ኦሮሚያ» የተባለ አዲስ አገር በመመሥረት እንቅስቃሴ ላይ ከተሠማሩ ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ አድርገዋል። ወራሪ የሆኑትን ኦሮሞዎችን እንደ ተወራሪ በመቁጠር፣ ወያኔም ዮሓን ክራፍ የሰጠውን የአካባቢ መጠሪያ በማፅደቅ፣ ዐማሮችን እና ሌሎችን ኢትዮጵያውያን ከአፅመ-ርስታቸው በማባረር፣ «ኦሮሚያ» የሚል አዲስ ግዛት ፈጥሮላቸዋል።

«እንግዳ ሲሰነብት፣ ባለቤት የሆነ ይመስለዋል፤» የሚሉት አባባል አለ። እንግዶቹ እና ወራሪዎቹ ኦሮሞዎች፣ የነባሮቹን የኢትዮጵያ ነገዶች እና ጎሣዎች ግዛቶች በወረራ ይዘው፣ የገደሉትን ገድለው፣ የሠለቡትን ሠልበው፣ ጡት ቆርጠው ሲያበቁ፣ ተበዳዮቹ «ይህ በደል ተፈፀመብን» ሣይሉ፣ እንዲያውም እነርሱ «ተበደልን» ብለው በወረራ የያዙትን አገር እንገንጥል ይላሉ፣ ነባሮቹን ኢትዮጵያዊ ነገዶች እና ጎሣዎች ያፈናቅላሉ። እነርሱው ነባር የአካባቢ ስሞችን ለውጠው እና በነገዳቸው ስም ቀይረው መያዛቸው እየታወቀ፣ «ዐማራው ስማችን እንድንቀይር አስገደደን፤ ቋንቋችንን፣ ባህላችንን እና የየአካባቢ ስሞችን ለወጠብን» እያሉ ስም ሲያጠፉ ይሰማሉ። ሃቁ ግን የአካባቢ ስሞችን በመለወጥና በራሱ ነገድ ስም በመጥራት የሚታወቀው የኦሮሞ ወራሪ ኃይል ነው። የታሪክ ሠነዶችን ማጣቀስ ካስፈለገም፥ በ፲፮፻ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን ከጎበኙት እና በአገሪቱም ተቀምጠው የሕዝቡን የአኗኗር ልማድ እና ዘይቤ በቅርበት እያጠኑ የታሪክ መድበሎችን ካበረከቱልን የአውሮፓ ሊቃውንት መካከል ፔድሮ ደ-ኮቪልኻም፣ አባ ፍራንሴስኮ አልቫሬዝ እና ሌሎችም የፖርቱጋል ዜጎች አያሌ ጠቃሚ የታሪክ ማስረጃዎችን ትተውልን አልፈዋል። እንዲሁም አህመድ ግራኝን ተከትሎ የዘመተው፣ እርሱ ባደረጋቸው ወረራዎች ሁሉ የቅርብ ተሣታፊ የነበረው የመናዊው ሺሃብ አድ-ዲን አህመድ ቢን አብድልቃድር ቢን ሣሌም ቢን ዑትማን፣ «ፉቱህ አል-ሓበሻ» በተባለው የታሪክ ድርሣኑ የዚያን ዘመን የኢትዮጵያን የሕዝብ አሠፋፈር ቅጥ በዝርዝር መዝግቦት ይገኛል። በእነዚያ ጽሑፎች ውስጥ «ጋላ» ወይም ኦሮሞ የሚባል ነገድ ዛሬ «ኦሮሚያ» ተብሎ በተከለለው አብዛኛው የኢትዮጵያ ግዛት ስለመኖሩ በአንዱም ጭራሽ አልተጠቀሰም። ስለዚህ የዛሬው ዘመን የኦሮሞ ልሂቃን የጥንት አባቶቻቸው በወረራ የያዙትን ግዛት እንደ አፅመ-ርስት ቆጥረውት ሌላውን ኢትዮጵያዊ ሲያፈናቅሉ ሃግ ሊባሉ ይገባቸዋል። ከኦሮሞ ወረራ በፊት ዛሬ ወለጋ፣ አርሲ፣ ወሎ፣ ኢሉባቡር፣ ወረኢሉ፣ ወረሂመኖ፣ ወዘተርፈ በመባል የሚታወቁት የቦታ (የአካባቢ) ስሞች የሚታወቁት እና የሚጠሩት በሌሎች ስሞች ነበር። የሚከተለውን ሠንጠረዥ እንዲሁም አባሪ ካርታዎችን ፩ እና ፪ ልብ እንበል።

ከኦሮሞ ወረራ በፊት ዛሬ ወለጋ፣ አርሲ፣ ወሎ፣ ኢሉባቡር፣ ወረኢሉ፣ ወረሂመኖ፣ ወዘተርፈ በመባል የሚታወቁት የቦታ (የአካባቢ) ስሞች
ተ/ቁ ነባር ስም በኦሮሞዎች የተሰጠው ስም የትኞቹን አካባቢዎች እንደሚገልጽ በአካባቢው ነዋሪ የነበሩ ነገድና ጎሳዎች
1 ቢዛሞ ቄለም ምዕራብ ወለጋ ጋፋት፣ ዐማራ፣ ሽናሻ፣ ቤንሻንጉል፣ አንፊሎ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
2 ዳሞት ሌቃ ምሥራቅ ወለጋ ጋፋት፣ ዐማራ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
3 እናርያ ኢሉ አባቦራ ኢሉባቦር ዐማራ፣ ከፊቾ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
4 ገሙ ጂማ ጂማ የም (ጃንጀሮ)፣ ገሙ፣ ዳውሮ (ኩሎ)፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
5 ገንዝ ጅባት እና ሜጫ ምዕራብ ሸዋ ጋፋት፣ ዐማራ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
6 ግራርያ ሰላሌ ሰሜን ሸዋ ጋፋት፣ ዐማራ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
7 እንደጥና እንጦጦ፣ ጉለሌ፣ የካ አዲስ አበባ ዙሪያ ሜያ፣ ዐማራ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
8 ኦ(ወ)ይጃ የረር እና ከረዩ ምሥራቅ ሸ ሜያ፣ ሐዲያ፣ ዐማራ፣ ከምባታ፣ ሲዳማ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
9 ፈጠጋር አርሲ አርሲ ሐዲያ፣ ከንባታ፣ ሜያ፣ ዐማራ፣ አዳል (አፋር)፣ ሲዳማ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
10 ደዋሮ ጭሮ ምዕራብ ሐረርጌ ሐዲያ፣ ከምባታ፣ ዐማራ፤ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
11 ላኮመልዛ ወሎ ደቡብ ወሎ ዐማራ፤ አዳል (አፋር)፣ አገው፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
12 ቤተ-ጊዮርጊስ ወረኢሉ ወረኢሉ ዐማራ
13 ቤተ-ዐማራ ወረሂመኖ ወረሂመኖ ዐማራ
14 አንጎት ራያ ሰሜን ወሎ ዐማራ፣ አገው፣ አዳል (አፋር)
15 ባሊ ባሌ ባሌ ሐዲያ፣ ከንባታ፣ ሜያ፣ ዐማራ፣ ሲዳማ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች

ስለዚህ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባን «ፊንፊኔ»፣ ናዝሬትን «አዳማ»፣ ደብረዘይትን «ቢሾፍቱ በሉ» እያሉ ለማስገደድ ለሚሞክሩት ዘመነኞች እኛም፥ ወለጋን ቢዛሞ እና ዳሞት፣ ኢሉባቡርን እናርያ፣ ወሎን ላኮመልዛ፣ አርሲን ፈጠጋር፣ ሐረርጌን ደዋሮ፣ ወዘተርፈ ብለን በጥንቱ ስማቸው የምንጠራ መሆናችንን እንዲያውቁት እንሻለን። ወደፊት ካላረፉም በእንግድነት ከኖሩበት አገር «ውጡ» የምንል መሆኑን ሊያውቁት ይገባል። የኦሮሞ ቀለም-ቀመስ ትውልድ ዐማራን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ፣ ክንዱን አስተባብሮ ሊያጠፋው ሲነሣ፣ ዐማራው በተቃራኒው እጁን አጣጥፎ ተቀምጦ ይጠብቀናል ብለው ካሠቡ በእጅጉ ተሣስተዋል። በመሆኑም ለማንኛችንም የሚበጀው እኛ ኢትዮጵያውያን በጠቅላላ አንዳችን ለሌላችን ቀና መተሳሰቡ እንጂ፣ ፍጭው ፈንግጭው ከሆነ ዬትም አንደርስም። እንዲያውም ከኖረው መልካም ባህላችን ውስጥ የቀረንን አብሮ እና ተቻችሎ የመኖር መልካም ባህላችንን እንኳን ለማጣት እንገደዳለን። ስለሆነም ከዚህ ተነስተን «ወደፊት እንዴት እንጓዝ?» የሚለውን ጥያቄ አንስቶ በጋራ በሚደረስበት ውሣኔ የተሻለች ኢትዮጵያን በመገንባቱ ላይ ማተኮሩ ዐዋቂነት ብቻ ሣይሆን ብልኅነትም ነው። በየትኛውም መልኩ የትናንት ኢትዮጵያን ካነሣን፣ በዳዩ «ተበደልኩ» ባዩ፣ ወራሪውም «ተወረርኩ» የሚለው የኦሮሞው ልሂቅ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ሞረሽ ወገኔ በተለይ በአሁኑ ወቅት ራሱን በኢትዮጵያዊነት ጭንብል ውስጥ ሸፋፍኖ፣ ለጥፋቱ ሁሉ የሩቅ ተመልካች ሆኖ ለሚታዘበው የተማረው የዐማራ ተወላጅ የሚያስተላልፈው ግልፅ መልዕክት አለ፦ ወገናችን ከምድረ-ገፅ እየጠፋ ዝምታው እስከመቼ ነው? «ትውልድ ትውልድን ተክቶ ያልፋል፣ ታሪክም ይመዘገባል» ተብሏልና ዛሬ ለወገኖቻችን ካልደረስን ነገ እያንዳንዳችን የትውልድም፣ የታሪክም ተጠያቂ ከመሆን እንደማንድን መካድ አይቻልም። ስለዚህ በወገኖቻችን በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ በትግሬ-ወያኔ እና በተባባሪዎቻቸው ላይ የሚደርሰው ሠቆቃ ከዚህ በላይ በዝምታ እና በቸልተኝነት ሊተው ከማይችልበት ምዕራፍ ላይ መድረሱን ተገንዝቦ ለወገን ጥሪ ተጨባጭ የተግባር ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል።

ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደግ!

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!

ኢትዮጵያ በታማኝ ልጆቿ መስዋዕትነት እና ትግል ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ወራሪው ማን ነው? ተወራሪዎቹስ? – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ( PDF)

MWAO_V2No23_map1

ካርታ ፪፦ (ምንጭ፦ ፕሮፌሠር ጌታቸው ኃይሌ፣ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም.። የአባ ባሕርይ ድርሰቶች፤ ኦሮሞችን ከሚመለከቱ ሌሎች ሰነዶች ጋራ። ገፅ ፲፪።)

 

moreshሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

“በቅሎ አባትህ ማነው ቢሉት ፈረስ አጎቴ ነው አለ” የኢህአዴግ የሃያ ሶስት ዓመት ጉዞ –ከሙሼ ሰሙ

$
0
0

mushe semu“ከአዲስ ጉዳይ መጽሄት የተወሰደ”

ለ23 ዓመታት የዘለቀው የኢህአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ስር ከሰደደ ድህነት፣ ከኑሮ ውድነት፣ ከረሃብ፣ ከሰብአዊ-መብት ረገጣ፣ ከእስርና እንግልት በተለይ ደግሞ ከመበታተን ስጋትና አደጋ ሊታደገን እንዳልቻለ የእለት ተእለት ኑሮችን በቂ ምስክር ነው፡፡ ከሃያ ሶስት ዓመታት አንጻራዊ የሰላም ጎዞ በኃላ በየክልሉ የሚታዩት ግጭቶች፣ መፈናቀልና መሰደዶች ዛሬም እጅግ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ የመበታተን አደጋ እንደጃበብን እያረጋገጡ ነው፡፡ እዚህም እዚያ ብልጭ ድርግም የሚሉት ልማቶችም ከኢቲቪና ሬድዮ ዲስኩር አልፈው የኑሮውድነቱን፣ ግሽበቱን፣ ሙስናውን፣ ስራ-አጥነቱንና ስደቱን ማስቀረት አልቻሉም፡፡

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live