Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የክልል እና የፌዴራል ምርጫ 2007! (ግርማ ሞገስ)

0
0

Girma Moges

ግርማ ሞገስ

ምርጫ 2005 የአካባቢ (የክልል ቀበሌ፣ ወረዳ እና ከተሞች) እንዲሁም የእራስ ገዞቹ የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ  ምክር ቤቶች ምርጫ ነበር። ብዙ የተወራለት የ33ቱ ተቃዋሚዎች ህብረት ቢያንስ ቢያንስ በአዲስ አበባ  ከተለመደው የተቃዋሚዎች ምርጫ ሽሽት የተሻለ ነገር ሊሰራ ነው ብለን በተስፋ ስንጠብቀው ምርጫው ሲቃረብ  ስለ ህውሃት/ኢህአዴግ አምባገነንነት የማናውቅ ይመስል እንደ አዲስ ዜና በህውሃት/ኢህአዴግ ስር ምርጫው ነፃ  አይሆንም አለን። ወዲያው እራሱን ከምርጫ ማግለሉን ገለጸለን። በዚህ አይነት የአዲስ አበባን ምክር ቤት 138  መቀመጫ እና የከንቲባውን ቦታ ካለምንም ፉክክር ተቃዋሚው በነፃ ለህውሃት/ኢህአዴግ በማስረከቡ ዛሬ ሰላማዊ  ሰልፍ ለማድረግ እውቅና ለማግኘት ሳይቀር በዚህ ምክር ቤት ስር በመጉላላት ላይ ይገኛል።  ….….ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ…….

 

 

 

 


የጃኪ ጎሲ አዲሱ ነጠላ ዜማ “ፊያሜታ”ን ያድምጡ [Video]

0
0

ጎሳዬ ቀለሙ “ጃኪ ጎሲ” በአማርኛ እና በትግርኛ ቋንቋ የሠራው አዲሱ ፊያሜታ ነጠላ ዜማ ያድምጡ። ዜማው ገና ከመለቀቁ በሶሻል ሚድያዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሲሆን ዘፈኑ ቀይባህርን ዞሮ ይመለሳል ልቤ እያለ ያቀነቅናል፤ ተስፋ እንደማይቆርጥና እንደተከፋ እንደሚኖር በዘፈኑ ይናገራል።

Jacky gosee

Hiber Radio: ኢትዮጵያውያን ሴት እስረኞች በሳዑዲ እስር ቤት ተገረፉ፤ ድረሱልን አሉ [ልዩ ዘገባ]

0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 5 ቀን 2006 ፕሮግራም

<... ...>

በሳውዲ በእስር ላይ እየተሰቃዩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

ሸንጎው የቀጣዩን ዓመት ምርጫ አስመልክቶ ምን አሳሰበው? እውን ምርጫ 2007 ከቀደሙት ምርጫዎች የተለየ ይሆናል?

ፕ/ር አቻምየለህ ደበላና ዶ/ር ደምሴ ኦሉማ ለህብር ጥያቄዎች የሸንጎውን ወቅታዊ መግለጫ አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል(ሙሉውን ያዳምጡት)

ኦቲዝም ምንድነው? እውን ልጆቻችንን አውቀን በጊዜ ተገቢውን ቴራፒ እንዲወስዱ እናደርጋለን?

በኦቲዝም ውስጥ ያሉ ልጆች ያሏቸው ልጆች ወላጆች ምን ይላሉ?

ዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ከአትላንታ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል

ወ/ሮ ፌበን ፋንቱ ወላጅ ከሎስ አንጀለስ ማብራሪያ ሰጥተውናል (ሙሉውን ያዳምጡ)

ግብረ ሰዶማዊነትና ኢትዮጵያ (ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

ኢትዮጵያውያን ሴት እስረኞች ከሳውዲ የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ

ባለፈው ሰኞ ተቃውሞ አቅርበው በእስርቤቱ ጠባቂዎች ግርፋት ደረሰባቸው

ኢትዮጵያውያን ኤምባሲ የላችሁም እንደሚባሉ ገልጸዋል

የሊቢያ የባህር ላይ ጠባቂዎች ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከአራት መቶ በላይ ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዳይሻገሩ አገቱ

75 የሚሆኑትን ከመስጠም ታደጉ

ሱዳን በመገንባት ላይ ያለውን የህዳሴውን ግድብ የመጠበቅ ሀላፊነት የለብኝም አለች

በትግራይ የገጠር መንደር በአገዛዙና በሕዝቡ መካከል በተነሳ ግጭት ሁለት የአገዛዙ ሚሊሻዎች ሞተው አንድ መቁሰሉ ተገለጸ

ሒላሪ ክሊንተን ቬጋስ ላይ ጫማ ተወረወረባቸው

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ እና ጸጋዬ ከበደ በለንደን ማራቶን ሶስተኛ ወጡ

ኬንያውያን በሴቶችና በወንዶች ድል ተቀዳጁ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ፪ (ተመስገን ደሳለኝ )

0
0

በዚህ ርዕስ ሥር ባለፈው ሳምንት በይደር ካቆየሁት ተከታይ ጽሑፍ በፊት አንድ እርምት የሚያሻው ጉዳይን በአዲስ መስመር ላስቀድም፡፡

ሬዲዮ ፋና እና “አምደኞቹ”

Temesgen-Desalegn4

ተመስገን ደሳለኝ

በ1988 ዓ.ም በኤፈርት ባለቤትነት ስርጭቱን አሀዱ ያለው “ሬዲዮ ፋና”፣ ከምስረታው አንስቶ ዛሬም ድረስ ልክ እንደ በረሃው ዘመን ሁሉ የሥርዓቱ ቀኝ እጅና የርካሽ ፕሮፓጋንዳው ማስተላለፊያ ቱቦ ሆኖ መዝለቁ ለወዳጅም ለጠላትም የማያከራክር ገሀድ የወጣ ሐቅ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተወሰኑ የግል ሚዲያዎች ላይ የርግማን ዘመቻ የታወጀ ይመስል ለተከታታይ ሳምንታት “ስመ-ጥር” ረጋሚዎችን ጣቢያው ድረስ ጋብዞ ማብጠልጠልና ማውገዙን ቀንደኛ ሥራው አድርጎ ይዞታል፡፡ በርግጥ ይህ ዘመቻ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የፕሬስ ድርጅት በኩል በ“ጥናት” ስም የወጣው ውንጀላ ቅጥያ ሲሆን፣ በቅርቡ ኢቲቪ ሰርቶ እንዳጠናቀቀው የሚነገርለት ዶክመንተሪ ፊልም ደግሞ “ሳልሳዊ” ዘመቻ ሆኖ ለጥቆ የሚቀርብ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ሰሞነኛውን የፋና ዘመቻ ከተለመደው አቀራረብ የተለየ የሚያደርገው ከህወሓት ከበሮ መቺነት መሻገር የተሳነው ዛሚ ሬዲዮ ጣቢያን ከወከለው አቶ ዘሪሁን ተሾመ በተጨማሪ፣ የኢዴፓው አቶ ሞሼ ሰሙ እና የ‹‹ፎርቹ››ኑ ጋዜጠኛ ታምራት ወልደጊዮርጊስ በውጋ-ንቀል ስልት የርግማኑ ቡራኬ ሰጪ ሆነው መቅረባቸው ነው፡፡ ‹‹አዲስ አማኝ ከጳጳስ በላይ ልሁን ይላል›› እንዲሉ ሩቅ አላሚው የሕዳሴው ግድብ የሕዝብ ተሳትፎ አስተባባሪ ም/ቤት ምክትል ዳይሬክተር የሆነው ዛዲግ አብረሃም ሆነ ሚኒስትር ዴኤታው ሽመልስ ከማል የረከሰውን የአፈና መንፈስ ‹‹ለማቀደስ›› በቁርጠኝነት መሰለፋቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው፡፡ በርግጥ እነዚህ ሰዎች በቀጥታ ከስርዓቱ ህብስት ተቋዳሽ በመሆናቸው በዚህ ደረጃ ‹‹ማሸብሸባቸው›› ብዙም አያስገርምም፤ አስገራሚው ነገር ታምራት ወልደጊዮርጊስ ‹‹እንቁ›› እና ‹‹ፋክት›› መጽሔቶችን በአንድ ሰው የሚዘጋጁ አስመስሎ ከማቅረብም አልፎ፣ ማሕበረ ቅዱሳን የገጠመውን የመበተን አደጋን በተመለከተ የወጣውን ዘገባ እስከማውገዝ የደረሰበት ጽንፍ ነው፡፡

በወቅቱ ዛዲግ አብረሃ ሚዲያዎቹ እንዲደመሰሱ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ፣ ታምራትም የማሕበረ ቅዱሳን አባላት ተቋማቸውን ከመንግስታዊ አፈና መከላከል እንዳለባቸው የምትመክረውን የ‹‹ፋክት›› ዘገባ ቃል በቃል ጠቅሶ ሲያበቃ ‹‹ቋቅ እያለኝም ቢሆን ከዛዲግ አብረሃ ጋር የምስማማበት ጉዳይ ይህ ነው›› በማለት ከፕሬስ አፈናው ጎን መቆሙን አስረግጦ ተናግሯል፡፡ በአናቱም መጽሔቶቹ ‹‹አብዛኛው ህዝብ የሚፈልገውን መርጠው የሚዘግቡ ናቸው›› ያለበት አውድ ነቀፋ ይሁን ምስጋና ግልፅ ባይሆንም፣ ቢያንስ አምባገነኑን በረከት ስምኦን እና ጋሻ-ጃግሬዎቹን ከማስደሰት፤ ብዙሃኑን ግፉአን ማገልገል የተሻለ ብቻ ሳይሆን የተቀደሰ ተግባር ስለመሆኑ በረከትም በልበ-ሙሉነት እሰጥ-እገባ ሙግት የማይሞክርበት ነጭ እውነት እንደሆነ ታምራት ቢያስተውለው የተሻለ ይመስለኛል፡፡ ግና፣ ሐቁ ይህ ቢሆንም ወንድም ታምራት ራሱ ብቻ ሙያውን አክብሮ የሚሰራ ጋዜጠኛ፤ ሌላውን ደግሞ ኃላፊነት የማይሰማው ከማድረጉም በዘለለ፣ እነዚህን ሚዲያዎች ከአርበኝነት ጋር አዳብሎ ለማውገዝ መሞከሩ የተኮረኮርኩ ያህል ሳልወድ በግድ ያሳቀኝ ጉዳይ ሆኖብኛል፡፡ ምክንያቱም በእኔ እምነት በኢትዮጵያችን ላለፉት ሁለት ዓስርታት ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ለሕግ የማይገዛ እና በሙስና የተጨማለቀ ሥርዓት ከመሆኑ አኳያ በጋዜጠኝነትም ሆነ በየትኛውም ሙያ ለሚንፀባረቅ አርበኝነት የተሻለው ብያኔ፣ ሀገርን ከፍርሰት መታደግ ማለት ነውና፡፡

ደግሞም በዚህች ሀገር ዝግመታዊ-ሞት ፊት ላይ ቆሞ የኮሪደር ሐሜቶችን ከመዘገብ በእጅጉ ለቆና ረቆ በመሻገር የውደቀታችን ምክንያት የሆነውን አገዛዝ በሕዝባዊ እምቢተኝነት ማስወገድ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ብዙ ጊዜ በእንዲህ አይነት ውይይቶች ላይ ሚዛናዊ ለመሆን ይሞክር የነበረው ታምራት (ለዚያኛውም አቋሙ በግሌ አመስግኘው አውቃለሁ)፣ ማሕበረ ቅዱሳንን በተመለከተ የወጡ ዘገባዎችን ባወገዘበት አዛው ሬዲዮ ጣቢያ ስቱዲዮ ውስጥ ተቀምጦ፣ ሽመልስ ከማል አንድ እንኳ የታሰረም የተሰደደም ጋዜጠኛ እንደሌለ ጠቅሶ አይኑን በጨው አጥቦ ሲከራከር ትንፍሽ አለማለቱ የቀራኒዮ መንገድ እና የንግድ ስራ ፍፁም የማይተዋወቁ ሆድና ጀርባ መሆናቸውን የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡

በነገራችን ላይ በዚህ ውይይት የአደባባይ ምሁሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እና የኢትዮ-ምህዳሩ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ መሳተፋቸው ከሞላ ጎደል ከዘመቻው ጀርባ ያለውን ኢህአዴጋዊ ሴራ አጋልጦታል ብዬ አስባለሁና ባርኔጣዬን ከፍ አድርጌ አክብሮቴን ልገልፅላቸው እወዳለሁ፡፡ በተለይ ጉምቱ የፍልስፍና መምህር ዶ/ር ዳኛቸው፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቶችን ብቻ ሳይሆን የሥርዓቱን ሃሳብ አልባነት ለመሞገት ለሚያደርገው አበርክቶ በድጋሚ አመሰግነዋለሁ፡፡…ከዚህ ሁሉ ሰበር ሐተታ በኋላ ወደ ክፍል ሁለቱ ዋናው አጀንዳችን ዘልቀን፣ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ለፍትሕ መበላሸት የዳኝነት ሥርዓቱ ብቻ ሳይሆን ፖሊስ እና ዐቃቤ ሕግም የአንበሳውን ድርሻ ስለመውሰዳቸው ለማመልከት እሞክራለሁ፡፡
ፖሊስ ሲባል…

…የተወሰኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት ዝሆን አድነው እንዲያመጡ በአለቃቸው ይታዘዛሉ፡፡ ከሰዓታት በኋላም ፖሊሶቹ ግዳያቸውን አምጥተው ለአለቃቸው ያስረክባሉ፡፡ ይሁንና አለቅየው ግዳያቸውን ባየ ጊዜ ባለማመን ዓይኖቹ ፈጥጠው ሊወድቁ ደረሱ፤ ለምን ቢሉ፣እሱ ያዘዛቸው ዝሆን፣ እነርሱ ያመጡት ግን ሁለት ጥርሱ የወለቀ፣ አንድ ቀንዱ የተሰበረ፣ አንድ አይኑ የጠፋ፣ ምላሱ የተቆረጠ… ብቻ ምን አለፋችሁ በድብደባ ብዛት ሊሞት የተቃረበ ፍየል ነበርና፡፡ እናም በቁጣ፡-
‹‹ዝሆን አይደል ወይ አምጡ ያልኳችሁ?›› ሲል ያፈጥባቸዋል፤
‹‹ጌታዬ፣ ዝሆን ነኝ ብሎ እኮ አምኗል!›› በማለት ቆፍጣና ፖሊሶቹም በሕብረት መለሱለት፡፡

…ይህችን ቀልድ ለዚህ ንዑስ-ርዕስ መግቢያ ያደረኩት፣ በነባሩ ባሕል እንዲህ ያሉ ጉዳዮች በቀልድ፣ በግጥም፣ በምሳሌዊ አባባል… መገለፃቸው የተለመደ ከመሆኑ አኳያ ስለሀገራችን የፖሊስ አባላት ስንነጋገር ከቀልዷ ጀርባ መራራ እውነት ማድፈጡን አምነን እንድንቀበል ገፊ-ምክንያቶች በመኖራቸው ነው፡፡

እንደሚታወሰው በየትም ሀገር የተፈፀመ ወንጀል ከዐቃቤ ሕግም ሆነ ከፍርድ ቤት በፊት በፖሊስ የምርመራ ሂደት ውስጥ ማለፉ የግድ ነው፡፡ የዘርፉ ምሁራን ‹‹የፖሊስ ምርመራ ሳይንስ ነው›› እንዲሉ ሙያው ክህሎት የሚጠይቅ መሆኑ አይካድም፡፡ ይሁንና ተጨባጩ እውነታ የሚነግረን የ83ቱን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ በዘርፉ እንዲሰማሩ የተደረጉት አብዛኞቹ መርማሪዎች ድርጅቱን ለቡሕተ-ሥልጣን ያበቁ ታጋዮች መሆናቸውን ነው፡፡ በርግጥም በረባውም ባልረባውም ወንጀል ተጠርጥሮ እጃቸው የገባውን ሁሉ አፈር-ድሜ በማስጋጥ የ‹‹ሚመረምሩበት›› መንገድ ኩነቱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ ይህ ሁናቴም ይመስለኛል የፖሊስን ሙያ ከሳይንሳዊ ጥበብ ወደ አሳረ-ፍዳ ማሳያ አውርዶ የተጠላ ያደረገው፡፡ ለዚህም ኩነና በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ የሩቁን ትተን የቅርቡን እንኳ ብንመለከት የህዝበ-ሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ችሎት ላይ ቀርበው በማዕከላዊ ምርመራ እስር ቤት መርማሪ ፖሊሶቹ ሰብዓዊ መብቶቻቸው ተገርስሶ ሲያበቃ ምን ያህል አካላዊና መንፈሳዊ ስቅየት እንደደረሰባቸው ከተናገሩት መሀል የሚከተሉትን በዋናነት እናገኛለን፡-

‹መርማሪ ፖሊሶቹ እንቅልፍ ከልክለው የተዳከመ አካልን ልብስ አስወልቆ እርቃን በማስቀረት መግረፍ፣ የዘር ፍሬ ብልት ላይ በውሃ የተሞላ ጠርሙስ ማንጠልጠል፣ በኤሌክትሪክ ገመድ የውስጥ እግርን መግረፍ፣ ጢምን በአሰቃቂ ሁኔታ መንጨት፣ እጅና እግርን ሰብዓዊነት በጎደለው መልኩ ለረጅም ሰዓታት ማሰር፣ ጭንቅላትን በቆሸሸ ውሃ ውስጥ መንከር፣ ከ24 ሰዓታት በላይ ቀጥ ብሎ እንዲቆሙ ማስገደድ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል ሾክ ማደረግ እና የመሳሰሉት፡፡› በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማትም በተደጋጋሚ ጊዜ በተለይም ከደርግ ስርዓት ጀምሮ ዋነኛ ማሰቃያ በሆነው ማዕከላዊ የምርመራ ጣቢያ የሚፈፀመውን ተግባር በሪፖርት መልክ ማውጣታቸው ይታወሳል፡፡ ከወራት በፊት ሂዩማን ራይትስ ዎች ይህንን የስቃይ ጣቢያ አስመልክቶ ‹‹They want a confession: Torture and Ill-treatment in Ethiopia’s Makelawi Police Station›› በሚል ርዕስ ባሰራጨው ሪፖርት በጣቢያው የሚፈፀመውን ግፍ ከመግለፁም በተጨማሪ፣ ታሳሪዎች እንዴት ባለ ሁኔታ ‹‹የእምነት ቃል››እንደሚሰጡ አመላክቷል፡፡ ለማሳሌም አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ፤ ነገር ግን በጣቢያው ታስሮ የነበረ ሰው ገጠመኝን ከሪፖርቱ እንደሚከተለው ልጥቀሰው፡-

‹‹ወደ ጣቢያው የገባሁ ቀን ኢ-ሜይል አድራሻዬን ከነምስጢር ቁልፉ እንድሰጣቸው ጠየቁኝ፤ ሰጠኋቸው፡፡ በውስጡም ምንም አይነት የፖለቲካ አንድምታ ያለው መልዕክት አልነበረም፡፡ ይሁንና ከሶስት ቀን በኋላ በዛው አድራሻዬ ‹ከኦነግ የተላከ መልዕክት ተግኝቷል› ብለው ጠየቁኝ፡፡ ሆኖም ነገሩን እንደማላውቅ እያወቁ ‹ለእኔ የተላከ መልዕክት ነው› ብለህ ፈርም ሲሉ አዘዙኝ፡፡ እኔም ከታሰርኩ በኋላ የተገኘ በመሆኑ አልፈርምም አልኩ፡፡ በዚህም የተነሳ ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመውብኛል፡፡››

በርግጥም የሀገሪቱን የወንጀል ምርመራ ስራን ተነቃፊና ተወጋዥ ያደረገው በእውቀት ማነስ፣ በስቅየት (በቶርቸር) እና በሙስና የተተበተበ መሆኑ ብቻ አይደለም፡፡ በአደረጃጀቱም ነው፤ ለምሳሌ ከፌዴራልና ክልል ፖሊስ በተጨማሪ ግምሩክ የራሱ እስር ቤት፣ የራሱ መርማሪና ዐቃቢ-ሕግያን አሉት፡፡ ፀረ-ሙስናም እንዲሁ የጠረጠረውን ሁሉ አስሮ ይመረምራል፤ ይከስሳልም፡፡ አንዳንድ ምንጮቼ እንዳቀበሉኝ መረጃ ከሆነ ደግሞ በሽብር ጉዳይ የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን (ቡድኖችን) ራሱን ችሎ አስሮ የሚመረምር እና የሚከስ ተቋም በቅርቡ በአዋጅ ሊቋቋም ዝግጅቱ ተጠናቅቋል፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሁሉ መዋቅራዊ ትስስር በሌለው ሁኔታ በፖሊስ ስራ የመሰማራታቸው ምስጢር፣ አንድም ሳይንስ እንጂ አሳር ዕውቀት ባለመጠየቁ፣ ሁለትም ንፁሀንን ከወንጀለኛ ጋር ደባልቆ ለመውቀጥ ስለሚመች፣ ሶስትም ስርዓቱ ተቀናቃኞቹን ለመደፍጠጥ በ‹‹ሕጋዊ አሠራር›› ሽፋን ተጨማሪ ጡንቻ እንዲኖረው ማስቻሉን በማስላት ይመስለኛል፡፡ በዚህ አይነት ምርመራ የተገኙ መረጃዎችም ፍርድ ቤት ቀርበው እንደሕጋዊ ማስረጃ እየተቆጠሩ እስከ ዕድሜ ልክ የእስር ቅጣት ሲያስበይኑ ደጋግመን ተመልክተናል፡፡

ይህም ሰፊው ሕዝብ በፍርሃት እየተርበደበደ ሰጥ-ለጥ ብሎ እንዲገዛ፤ አሊያም እንደ ጥንቸሊቷ አገር ጥሎ እንዲጠፋ ለማድረግ ያለው ጉልበት በግልፅ ተተግብሮ የታየ የሥርዓቱ የዕለት ተዕለት ምግባር ነውና ከዚህ በላይ ትንታኔ አያሻውም፡፡ ከዚህ ይልቅ የጥንቸሏ አፈ-ታሪክ ተብሎ የሚነገረው ነባራዊ እውነታውን በሚገባ ያንፀባርቃልና እንደወረደ ልጥቀሰው፡-…ከለታት አንድ ቀን አንዲት ጥንቸል ከመጣባት የመዓት ናዳ ማምለጥ የምትችለው ቀዬዋን ጥላ ስትሰደድ እንደሆነ ብቻ በማመኗ ልቧ እስኪፈነዳ ድረስ ጋራ-ሸንተረሩን እያቆራረጠች ስትሮጥ ድንገት ከሀገሪቱ ድንበር አጠገብ ከሚኖር አንድ ግድንግድ ጦጣ ጋር ፊት-ለፊት ተፋጠጠች፣ በድካም ዝላም ቁና ቁና እየተነፈሰች ‹‹ይህ ጦጣ ፖሊስ ይሆን እንዴ?›› ብላ እየተጠራጠረች ማምለጫ ዘዴ ስታውጠነጥን፣አያ ጦጣ፡- ‹‹ወይዘሪት ጥንቸል፣ ለመሆኑ ምን የከበደ ጉዳይ ቢገጥምሽ ነው እንዲህ ልብሽ እስኪፈርስ ድረስ የምትሮጪው?›› ሲል ይጠይቃታል፤‹‹የዝሆን ዘር በሙሉ ከያለበት ተለቅሞ በቁጥጥር ስር እንዲውል አስቸኳይ ትዕዛዝ መውጣቱን እስካሁን አልሰሙም እንዴ?›› ብላ በጥርጣሬ ትክ ብላ እያስተዋለችው ጥያቄውን በጥያቄ ስትመልስለት፣

አያ ጦጣ፣ እጅግ በጣም ከመደነቁም በላይ ግራ ግብት እያለው ‹‹ታዲያ አንቺ ምን አገባሽ፤ ዝሆን አይደለሽ?›› ሲል መልሶ ይጠይቃታል፤ ‹‹ወይ አያ ጦጣ! ዝሆን ባልሆንስ?! አለመሆኔ ተጣርቶ እስክለቀቅ ድረስ ለምን ብዬ ታስሬ ልገረፍ? ደግሞስ በዱላ ብዛት ዝሆን ነኝ ብዬ ያመንኩ እንደሆነ መጨረሻዬ ምን ሊሆን እንደሚችል አስበውታል? ይልቅ እርስዎም አይሞኙ! በጊዜ አብረውኝ ከመዓቱ ዘወር ብለው ቢቆዩ ይሻሎታል፤ ኑ እንሂድ›› ብላ በፍርሃት የተዋጠችው ምስኪኗ ጥንቸል ሩጫዋን ቀጠለች፡፡ …በእኛይቱ የመከራ ምድርም፣ እኛና ኢህአዴግ በዚህ ደረጃ ፍፁም የማንተማመን፣ በጎሪጥ የምንተያይ ሆነን ከቀረን እንደ ዘበት ሃያ ምናምን አመታት ተቆጥረዋል፡፡

ዐቃቢ ሕግ ሲባል….

በዚህ አውድ ሌላው ተጠቃሽ ተቋም፣ ፖሊስ በ‹‹የትም ፍጪው…›› መንገድ ያመጣለትን ‹‹መረጃ›› ሳያላምጥ በመዋጥ ለክስ የሚያበቃው ዐቃቤ ሕግ ሲሆን፣ ለአጠቃላዩ የፍትሕ መዛባትና መጨማለቅም በዕኩል ደረጃ ተጠያቂ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ለአደባባይ ያልበቁ አያሌ የዐቃቢ-ሕግያን ሸፍጦችን ትተን በድህረ ምርጫ 97 የተከሰተውን አለመግባባት ተከትሎ ለእስር ከተዳረጉት የቅንጅት ለአንድነትና ለፍትህ ፓርቲ አመራሮች ጋር የተያያዘውን እንመልከት፡፡ እንደሚታወሰው መጀመሪያ የቀረበባቸው ክስ ‹‹የዘር ማጥፋት›› የሚል የነበረ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያን በተመለከተ ለረዥም ዓመታት ጥናት ያደረገው አሜሪካዊ ፕ/ር ዶናልድ ሌቨን፣ አቶ መለስን ‹‹ዘር ማጥፋት እኮ ቀልድ አይደለም›› በማለት አጥብቆ ከወቀሰው በኋላ ክሱ ‹‹ሕገ-መንግስቱን በኃይል የመናድ እና ዘር የማጥፋት ሙከራ›› ወደሚል መቀየሩን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ፡፡

የሆነው ሆኖ ጉዳዩ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ዐቃቢ-ሕግያኑ በተከሳሾቹ ላይ በ‹‹ማስረጃ››ነት ካቀረቡት ሰነዶች መካከል የአባላዘር በሽታ የህክምና ምርመራ ወረቀትን ጨምሮ፣ ሀሰተኛ (ፎርጅድ) ደብዳቤዎች እና ከክሱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው የቪዲዮ ፊልሞች እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ‹‹የቃሊቲው መንግስት›› በሚለው መጽሐፉ፣ በጥቅምት 25/1998 ከ‹‹አዲስ አበባ ፖሊ ከፍተኛ ክሊኒክ›› ቢኒያም (የአባቱም ስም ተጠቅሷል) ለተባለ ሰው የአባላዘር ምርመራ አድርጎ የተሰጠው የሕክምና ምስክር ወረቀት ‹‹ሕገ-መንግስቱን በኃይል ለመናድ ሞክረዋል›› በተባሉት የቅንጅት መሪዎች ላይ በ‹‹ማስረጃ››ነት መቅረቡን ከመጥቀሱም በላይ ሰነዱን በገጽ 444 ላይ እንዳለ በማተም ለታሪክ ምስክርነት አብቅቶታል፡፡ መቼም ይህ ሁናቴ አቶ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ጦር ሶማሊያን የወረረው የአሜሪካንን ተልዕኮ ለማስፈፀም ነው? ተብሎ ለቀረበበት ወቀሳ አከል ጥያቄ፣ አሜሪካ የምትሰጠው ዕርዳታ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን መከላከል ላይ ያተኮረ እንደሆነ ከገለፀ በኋላ ‹‹ሶማሊያ ውስጥ ደግሞ በኮንዶም አንዋጋም!›› ብሎ እንደመለሰው አይነት ቧልት አቅልለን እንዳናልፈው የሚያግደን ጉዳዩ ‹‹አንድ ንፁህ በሀሰት ከሚፈረድበት፣ ሺ ወንጀለኞች በነፃ ቢለቀቁ ይመረጣል›› ከሚባልለት ፍትሕ ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ነው፡፡

በጥቅሉ ላለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ ለእስር የተዳረጉ ንፁሀንም ሆነ በሙስና የተወነጀሉት ላይ እየቀረበ ያለው ክስና ማስረጃዎችን ሥራዬ ብሎ ለመረመረ ሰው፣ የፍትሕ መዛባቱን ደረጃ ፍንትው አድርገው ያሳዩታል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለምሳሌም ከወራት በፊት ‹‹በገቢዎችና ግምሩክ ባለሥልጣን የአ/አ ኤርፖርት ቅ/ጽ/ቤት የመንገደኞች ጓዝ የሥራ ሂደት መሪ›› ባለሥልጣን ላይ የተመሰረተውን ክስ ብናየው እንዲህ የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡-

‹‹ከአሜሪካና ከአውሮፓ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ መንገደኞች ዕቃዎቻቸውን አስፈትሸው ቀረጥና ታክስ ሊከፈልባቸው የሚገቡት ላይ መክፈል እንዳለባቸው ኮንትሮባንድም ከሆነ እንደሚወረሱ እያወቀ ማንነታቸውና ብዛታቸው ያልተለዩ መንገደኞች ዕቃቸው እንዳይፈተሽ ማድረግ፡፡››

መቼም ይህ አይነቱ ክስ በምድራችን የመጀመሪያው ሳይሆን አይቀርም፡፡ ምክንያቱም ማንነታቸውና ብዛታቸው፣ ቀኑና ወሩ ተለይቶ ባልታወቀበት ጊዜ ከመንገደኞች ጋር በመመሳጠር የተሰራ ወንጀል አለ ብሎ ክስ መመስረት ከጥንቆላ በምንም ሊለይ አይችልምና ነው፡፡ ኧረ ለመሆኑስ! የሰዎቹ ቁጥርና ያስገቡት የዕቃ ዓይነት ካልታወቀ ባለሥልጣኑ ‹‹ፈፀመ›› በተባለው ሙስና ሀገሪቱ ከቀረጥ ማግኘት የነበረባትና ያሳጣት ገቢ ምን ያህል ነው? አንድ ብር? አንድ ሺህ? አንድ ሚሊዮን ወይስ አንድ ቢሊዮን? ይሁንና የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ በዚህ መልኩ መቅረቡን በፍርድ ቤት በመቃወማቸው ዐቃቢ ህግ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ይታዘዛል፡፡ ተሻሽሎ የቀረበው ደግሞ ባጭሩ እንዲህ ይጠቀሳል፡-

‹‹ቀኑና ወሩ ተለይቶ ባልታወቀበት በ2002 ዓ.ም ዜግነታቸው አሜሪካዊ የሆነ ሁለት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሁለት ሻንጣ የመኪና መለዋወጫ ከተያዘባቸው በኋላ አስለቅቋል፡፡ ግንቦት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የሰንሻይን ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ ከዱባይ ሀገር ያስገቡት የመኪና መለዋወጫ ዕቃ እንዲያልፍ ሲያስደርግ በሌላ ባልደረባው ተይዟል፤ ከሐምሌ ወር 2002 ዓ.ም እስከ ነሐሴ ወር 2003 ዓ.ም ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ባለው ጊዜ ከተለያዩ ሀገራት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ መንገደኞች ሠልፍ ይዘው እያለ ከዚህ መለስ ያሉት መንገደኞች ሻንጣቸውን ሳያስፈትሹ፣ ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሉ እንዲያልፉ ማድረግ፡፡››

እነሆም እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ሀገሪቱ እንዲህ ባሉ የሕግ ባለሙያዎች ስር ወድቃለችና ‹እግዚኦ በሉ›፡፡ እግዚኦታው ግን የሁለቱ እንስቶች ስም እና ያሳለፉት ዕቃ ተመን ባለመታወቁ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም በጽሁፍ በቀረበ ክስ ላይ ከሠልፈኞቹ መካከል ‹‹ከዚህ መለስ ያሉት መንገደኞች…›› ተብሎ ድፍን ያለ ነገር ‹‹መረጃ›› ሆኖ መቅረቡ ነው፡፡ ግና፣ ይህ ምን የሚሉት መረጃ ነው? ያውም ለፍርድ ቤት! እናም ጥያቄያችን እንዲህ እያለ ይቀጥላል፡- የትኛው ሠልፍ ጋ ያሉ መንገደኞች ናቸው በሕገ-ወጥ መንገድ ያለፉት? የቀኙ? የመሀለኛው? የግራው? የሠልፉስ ርዝመት ምን ያህል ነው? የሠልፈኞቹስ ብዛት? አምስት? ሀምሳ ወይስ አምስት መቶ? በርግጥ ክሱ ለአንዱም ጥያቄያችን ምንም አይነት ምላሽ አይሰጥም፡፡ ጉዳዩን ይበልጥ የሚያወሳስበው ደግሞ ይህ ‹ሾላ በድፍን› የሆነ ወንጀል የተፈፀመው ከሐምሌ ወር 2002 ዓ.ም እስከ ነሐሴ ወር 2003 ዓ.ም ድረስ በየቀኑ መሆኑ ነው፡፡ መቼም እነዚህ ሁሉ ጉዶች እውነት ከሆኑ በዚህች ሀገር፣ ማፍያ እንጂ መንግስት አለ ብሎ የሚመሰክር ደፋር ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡

በጥቅሉ የፖሊስም ሆነ የዐቃቢ-ሕግያኑና የዳኞቹ እንዲህ ሙያውን እና ተቋሙን የማራከስ አካሄድ ከአንድ ገፊ-ምክንያት የዘለለ ሌላ መነሾ የምናገኝለት አይመስለኝም፡፡ ይኸውም ሥልጣኑን ለማራዘም ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሰው ኢህአዴግ፣ በዋናነት ዋስትና የሚሆኑትን ፖሊስ፣ ዐቃቢ-ሕግ እና ፍርድ ቤቶችን በታጋዮች እና በካድሬዎች በመሙላት፣ በተለየ የፖለቲካ አቋም ከፊቱ የሚቆሙትን እየጨፈለቀ ለማለፍ አስልቶ የቀመረው በመሆኑ ነው፡፡

ኦርዌላዊ ስርዓት

የዚህን ስርዓት ቅጥ ያጣ አምባገነንነት ማብራራት አድካሚ እየሆነ ነው፡፡ የሚፈርሰው ማህበራዊ ዕሴት፣ የሚናደው ሀገራዊ ማንነት፣ እንደ አምባሻ የሚቆራረሰው መሬት፣ አልፎ ተርፎም እየጠፋ ያለው ትውልድ እና መሰል ጉዳዮችን ጠቃቅሶ፣ የነገይቷ ድህረ-ኢህአዴግ ኢትዮጵያ በገዢው ስብስብ ክፉ መዳፍ ሳቢያ ህልውናዋ ከገደሉ ጠርዝ ላይ ስለመቆሙ ማተት መደጋገም ነውና እንለፈው፡፡ ይህም ሆኖ ግን አገዛዙ በፍትሕ ስርዓቱ በኩል የሚያካሂዳቸው ዘግናኝ ድርጊቶች የመዓቱን ጊዜ ቅርብ የሚያደርጉ መሆናቸውን ማስታወስ (የሚሰማ ባይኖርም) የዜግነት ግዴታ ይመስለኛል፡፡ የአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንትን ጨምሮ፣ ቁጥራቸው የበዛ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋማት በተደጋጋሚ እንደዘገቡት፣ የዚህች አገር ምስኪን ልጆች በማይታወቁ ድብቅ እስር ቤቶች ጭምር መከራ እየወረደባቸው ነው (እኔ ይህንን ጽሑፍ በማዘጋጅበት፣ እናንተም አሁን በምታነቡበት ሰዓትም ቢሆን ለይተን በማናውቃቸው በርካታ የስቃይ እስር ቤቶች፣ በእልፍ አእላፍ ወገኖቻችን ላይ ግፍ እየተፈፀመ መሆኑን መካድ አይቻልም)፡፡

እነዚህ ማሰቃያ ቦታዎች ከምስራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከደቡብ እስከ ሰሜን ባሉት የሀገሪቱ አካባቢዎች ተሰበጣጥረው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ በነዚህ ካምፖችም የሚታጎሩት ዜጐች በዋነኝነት ከገዢው ግንባር የተለየ (የሚቃረን) ፖለቲካዊ አመለካከት ያላቸው ስለመሆኑ የተቋማቱ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡ በተለይም ብረት አንስተው የሚታገሉ ኃይሎች የተነሱባቸው ክልል ተወላጆችን ማሰቃያ ካምፖቹን የሚያደልቡ ‹የተመረጡ› መከረኞች ሆነዋል፡፡ ኢህአዴግ እንጥፍጣፊ ለሕገ-መንግስቱ አክብሮት ቢኖረው፣ የዜጎቹ ወንጀሎች የቱንም ያህል ቢከፉም እንኳ፣ በግልጽ የፍርድ ሂደት ተገቢ የሆነ ተመጣጣኝ ቅጣት ማግኘት በተገባቸው ነበር፡፡

የዚህ አይነቱን የፍትህ ምኩራቡ አስፀያፊ እርክስናን፣ በግላጭ የሚያሳየን ሌላኛው ጭብጥ በኦጋዴናውያኑ ላይ እየወረደ ላለው ግፍ ተጠያቂ ተቋምም ሆነ ባለሥልጣን እስካሁን ድረስ አለመኖሩ ነው፡፡ የስዊድናውያኑን ሁለት ጋዜጠኞች መታሰርና በይቅርታ መፈታት ተከትሎ፤ በክልሉ ያለው ፍርድ ቤት ስለማያውቀው ዝርፊያ፣ እስርና ግድያ በምስልና በድምፅ የተደገፉ ማስረጃዎች ከጥቂት ወራት ወዲህ ተሰምተዋል፡፡ የአካባቢው የቀድሞ ባለስልጣን ወደስዊድን በተሰደደ ማግስት ያቀረባቸውን እነዚህን ማስረጃዎች ኢህአዴግ እንደለመደው የኦብነግ ከንቱ ውግዘት አድርጎ ማለፍ አይቻለውም፡፡ በዚህ ሰው ማስረጃም ሆነ ክልሉን ባጠኑ ምሁራንና ተቋማት ዘገባዎች መሰረት የጠቀስኳቸው ዘግናኝ ክስተቶች ማህበረሰቡን እየናጡት ነው፡፡

በተለይ ልዩ ሚሊሺያ የሚባለው ሕገ-ወጥ ሀይል፣ በሱማሌ ክልል ጎዳና ላይ ያሻውን እያነቀ እንዲያስር፣ ልጃገረዶችን እንዲደፍር፤ ገፋ ካለም በጥይት አረር እንዲረሽን የተተወበት አግባብ የሚመሰክርልን የፍትሕ ስርዓቱ ድምጥማጡ ስለመጥፋቱ ብቻ ነው፡፡ በዚህ መልኩ በሌሎቹም የሀገራችን ክፍሎች ካለዘውግ፣ ሐይማኖት እና ዕድሜ ልዩነት፤ ካለፍርድ ቤት እውቅና እየተፈፀመ ያለው ግፍ፣ የፍትህ ተቋሙ የዜጎችን ህልውና ለመጨፍለቅ ከገዢዎች ጋር በጥብቅ የተጋመደ ስለመሆኑ ያስረግጡልናል፡፡ እንግዲህ ፍትሕና ርትዕ የሰማይ ላይ ሩቅ ተስፋዎች እንዲሆኑብን የፈቀደውን ስርዓት እስከ መቼ መታገስ ይቻለናል? ስለርትዕ በኢትዮጵያ ምድር ላይ መስፈን ሲባልስ፤ የኢህአዴግን ቅፅር በህዝባዊ ሰላማዊ አብዮት ብንንደው፣ መስዋዕትነታችን ሀገርን ከመዓት ለማዳን ሲባል በፈቃደኝነት የሚከፈል ትውልዳዊ ግዴታ አይደለምን?! (በቀጣዩ ከአራጣ ማበደር ወንጀል እስከ መንግስታዊ ሙስና ላሉ ጉዳዮች እና ለፍትሕ ሥርዓቱ ሞቶ መቀበር ማሰሪያ አበጅቼ አጀንዳውን ለጊዜው እደመድመዋለሁ)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

አዲስ አበባ

 

የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እና የዲያስፖራውን ሚና በተመለከተ በኖርዌይ ኦስሎ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ

0
0

Nor1

በዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ  የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት አፕሪል ቅዳሜ 12/2014  በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ  የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እና የዲያስፖራውን ተሳትፎ በተመለከተ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ተካሄደ:: በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ቁጥራቸው ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ከኦስሎ እና ከተለያየ ከተማ  በመምጣት በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን  የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር አባል አቶ ቡዙነህ ፅጌ የስብሰባው ተጋባዥ እንግዳ በመሆን ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል::

ሕዝባዊ ስብሠባው በኖሬጅያውያን የሰአተ አቆጣጠር ከቀኑ 15:00 እስከ ምሽቱ 21:00 ሰዓት የተካሄደ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ  አቶ አቢ አማረ በኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ አረመናዊ ስርአት በጭካኔ በግፍ ለተገደሉ እና በተለያዩ አስር ቤቶች በፖለቲካ ኣስተሳስባችው ምክንያት ያለወንጀላች የሚስቃዩ ውድ ኢትዮጵያዊን ወገኖቻችን በማስብ  በዚሁ ዘረኛ ቡድን አስቃቂ የኣካል ጉዳት ለተፈጸባቸው ኢትዮጵያዊን  የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማስደረግ ስብሰባውን አስጀምረውታል::

 Nor2

በመቀጠለም አቶ ዮሀንስ አለሙ የዴምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር የመግቢያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው ስለ ዲምክራሲያዌ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አመሰራረት እና ስለ ድጋፍ ድርጅቱ አላማ በማብራራት የድጋፍ ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት በሀገር ቤት በሰላማዊ ትግል የወያኔን መንግስት ለመጣል እየታገሉ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶችን እየረዳ እንደሚገኝ እና ከሀገር ውጭ ደግሞ የወያኔን መንግስት  በሁለገብ ትግል  ለማስወገድ እየሰራ ያለውን የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሴ ንቅናቄ የፖለቲካ ድርጅትን በግንባር ቀደምነት እየረዳ እንዳለ በመግለጽ  የወያኔን ዘረኛ ስርአት ለመጣል ሁሉም ሰው አስተዋጿ ማድረግ እንደሚጠበቅበት እና ማንኛውም  ኢትዮጵያዌ ዜጋ በሀገራችን የጋራ ጉዳይ ስለሆነው  የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ሀሳብ በመለዋወጥ ፣በመካከላችን ያሉትን ማንኛውንም የሃሳብ ልዩነቶች ወደ ኋላ በመጣል ፣ በመቻቻል፣ ሀገር እያፈረሰ እና ሕዝብ እያዋረደ ያለውን የዘረኛውን የወያኔን መንግስት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሁለገብ ትግል ለማስወገድ መረባረብ እንዳለበት አጽኖት ሰተው ንግግር አድርገዋል::

በመቀጠለም ዲምክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ድጋፍ ከሚሰጣቸው ድርጅቶች መካከል አንዱ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር አባል የሆኑት አቶ ቡዙነህ ፅጌ የስብሰባው ተጋባዥ እንግዳ ሰፊውን ጊዜ በመውሰድ ከንጉሱ ስርአት ጀምሮ በደርግ መንግስት ዘመንም በሀገራችን የተደረጉ የፖለቲካ ንቅናቄዎችንና ለውጦችን አንድ በአንድ በመዘርዘር አሁን ካለው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ጋር በማነጻጸር ሰፋ ያለ ትንታኔ ያቀረቡ ሲሆን አሁን ላይ ሀገሪቱን እየመራው ነው የሚለው የወያኔ መንግስት ከዚህ ቀድሞ ኢትዮጵያን ከመሩት ከሁለቱ መንግስታቶች ማለትም ከንጉሱም ከደርግም መንግስት ጋር ሲነጻጸር ፈጽሞ እንደማይገናኝ የወያኔ መንግስት ዘረኛና የዘረኝነት ፖለቲካ እያራመደ ያለ አረመናዊ መንግስት እንደሆነ አብራርተዋል::

የግንቦት 7  የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር አባል አቶ ቡዙነህ ፅጌ አክለውም ከወያኔ በፊት የነበሩ ሁለቱ መንግስታቶች ለውድቀት የዳረጓቸውን ምክንያቶች በመጥቀስ የወያኔን አንባ ገነናዊ መንግስት ለአፋጣኝ ውድቀት ሊዳርጉት ይችላሉ የሚሉትን ግልጽ ምክንያቶች በመዘርዘር አስቀምጠዋል:: አቶ ቡዙነህ በሁለት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በማንሳት እና በማብራራ ከሕዝብ ውይይት እንዲያደርጉበት ለመወያያ ያቀረቡ ሲሆን እነዚህም

1, በሙስሊሙ ማህበረሰብ እና በወያኔ መካከል ያለው ግጭት

2, የህዳሴ ግድብን  በማስመልከት ያለው ተቃውሞ

ስለሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቃውሞ ሲናገሩ የሙስሊሙ ትግል በሁለት አመታት ውስጥ የተደረገው ሰላማዊ ትግል በጣም የተሳካና ወያኔ በቀላሉ ሊያዳፍነው ያልቻለው ሰላማዊ መብትን የመጠየቅ ትግል እንደሚያደንቁ በመናገር ነገር ይህ በሙስሊም ማህበረሰብ በኩል እየተደረገ ያለው ትግል እስከ አሁን ድረስ ከመንግስት በኩል ምንም አይነት መልስ ሊያገኝ እንዳልቻለ እና ወደፊትም ከወያኔ መንግስት በኩል ምንም አይነት መልስ ያገኛል የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል:: ለዚህም ማስረጃው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከጠየቋቸው አራት የመብት ጥያቄዎች አንዱም ካለመመለሱ በተጨማሪ እስካሁን መሪዎቻቸውም በሃሰት ውንጀላ በእስር እየማቀቁ ያለፍርድ እየተንገላቱ መሆናቸው ነው፥፥

ነገር ገን አሁን እየሆነው ባለው ሁኔታ በእንደዚህ አይነት መንገድ እስከመቼ ድረስ የሙስሌሙ ትግል ይቀጥላል በማለት የተናገሩ ሲሆን አሁን እየሄደ ባለው አካሄድ የሙስሊሙ ተቃውሞ የትግል አቅጣጫውን እስካልቀየረ ድረስ ረጅም ርቀትን ትግሉ ሊቀጥል ይችላል የሚል እምነት እንደሌላቸው እና ነግር ግን የሙስሊሙ ጥያቄ ከእምነት መብት ጥያቄ ባሻገር ወደ የዜግነትን መብት ወደ ማስከበር መለወጥና መሸጋገር  እናደለበት በመናገር የሙስሊሙ ማእበረሰብ ጥያቄ ፍሬ ሊያፈራ የሚችለው  ትግሉ በዚህ መልኩ ሲቀጥል እንደሆነ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰተዋል:

 

በሁለተኛም የህዳሴ ግድብ በሚመለከት  ያቀረቡት ሀሳብ ወያኔ የራሱን የፖለቲካ ኪሳራና በህዝቡ ላይ እያደረሰ ያለዉን ግፍ በዕድገት ስም ለመሸፈን ያመጣዉ እንጂ ታቅዶበትና ለህዝቡ በማሰብ እንዳልሆነ በኢትዮጵያና በህዝቡ ላይ እያደረሰ ያለዉ ግፍ እንደ ማስረጃነት በማቅረብ ያብራሩ ሲሆን እንደ ምሳሌም ወያኔ ሃገራዊ የሆነ አላማ ይዞ ካለመነሳቱ አንፃር የሃገርን ድንበር አሳልፎ እስከመስጠት እየሄደ ያለበትን ሁኔታ ጠቅሰው ይህ አሰራር ደግሞ የዲክታተሮች ባህሪ እንደሆነ አብራርተዋል፥፥

 

የወያኔ መንግስት በህዳሴ ግድብ ሰበብ ምክንያት በማድረግ በመላው አለም ኢትዮጵያኖች በሚኖሩበት ሀገሮች በመዞር የዲያስፖራውን ቀልብ ለመውሰድ የሚያደርገው የአባይ ቦንድ ሽያጭ ሩጫ በዲያስፖራ ተቃዋሚዎች አማካኝነት በፍጹም እንዳልተሳካለት ይህንንም የወያኔ በአባይ ቦንድ ሽያጭ ስም ገንዘብ ዘረፋ በመቃወም ወያኔን አሳፍረው ከመለሱት መካከል በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች እንደሆኑ በማስታወስ  የዚህ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰበብ የወያኔን መንግስት ወደ መጥፎ ውድቀት ላይ ሊጥለው እንደሚችል በማመን የወያኔ መንግስት በአሁን ሰአት ከግብጽ መንግስት ጋር እየገባ ያለው ሰጣ ገባ ለኢትዮጵያ መጥፎ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ ንግግራቸውን አጠቃለዋል፥፥

 

በመቀጠልም አቶ ብዙነህ ባነሷቸው ነጥቦችና እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ከስብሰባው ተሳታፊዎች ለቀረበላቸው በርካታ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሰፋ ያለ ውይይትም ተደርጓል፥፥ ከውይይቱም በማስቀጠል የዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዳንሄል አበበ የዲምክራሲያዌ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የአቋም መግለጫ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ድርጅታቸው ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና በደል ፈጽመው እንደሚያወግዙ እና ዴምክራሲያዌ ለለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሁል ጊዜ ከግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሴ ንቅናቄ ጎን እንደሚቆም ቃል በመግባት የአቶ ቡዙነህ ፅጌን በኖርዌይ በመገኛት ለህዝቡ ለሰጡት ገለጻ አመስግነዋል፥፥

በዝግጅቱ መጀመሪያና ማጠቃለያ ላይ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል መዝሙር በመዘምራን የተዘመረ ሲሆን በየጣልቃው የተለያዩ የባህል ዘፈኖች በተወዛዋዦች ታጅቦ የቀረበ ሲሆን ጣእም ያለው ባህላዊ ምግብም በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የሴቶች ክፍል ተስተናግዷል፥፥ ስብሰባውን ተጀምሮ እስኪያልቅ አቶ ፍቅሬ አሰፋ መርተውታል::

 

በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ለዝግጅቱ መሳካት የበኩላችሁን ላበረከታችሁና ከተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች ረዥም ርቀት በመጓዝ የዝግጅቱ ታዳሚ ለነበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን እና እንዲሁም የድርጅቱ አባላቶች ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን፥፥

 

 

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

 

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

 

 

የኢህአዴግ “አሸባሪነት”በ2007 ምርጫ ማንን ያስር ይሆን?

0
0

ሳሙኤል ተወልደ በርሔ/ሃርስታድ ኖርዌይ/

2007 electionሰው በላው የኢህአዴግ “አሸባሪነት” ለ2007 ምርጫ ምን እየቆመረ ይሆን?…ኢህአዴግ  ስልጣኑን ከተቃውሞም ሆነ ከነፃው ፕሬስ ወቀሳ የሚያረጋጋበት በርካታ ኢ-ፖለቲካዊ (ኢ-ዴሞክራሲያዊ) አካሔዶች አሉት፡፡ ኢህአዴግ እንደቀደምቶቹ የኢትዮጵያ መንግስታት ሁሉ የተቃውሙትን ፖለቲከኞች አስሯል፤ በዩኒቨርስቲ ውስጥ የአካዳሚ ነፃነታቸውን የጠየቁ ተማሪዎችን በፖሊስ አስደብድቧል፤ ከፍ ሲልም በእስር አሰቃይቷል፡፡ ብዙዎችንም በፖለቲካ አመለካከታቸው (በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ) ከገዛ ሀገራቸው እንዲሰደዱ አድርጓል፡፡ ንቁ  የፖለቲካ ተሳትፎ በሚያደርግ አባወራ ምክንያት የቤተሰቡ አባላት ከፍተኛ ወከባ እና እንግልት እንዲደርስባቸው አስደርጓል፡፡

የ1997 ዓ.ም ምርጫ ውጤት ፍፁም ወደተቃዋሚዎች ማጋደሉን የተመለከተው እና ስልጣኑ አደጋ ላይ መውደቁን የተገነዘበው ኢህአዴግ ከ97 ዓ.ም በኋላ እስከአሁን ድረስ ያለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ እጅግ አስጨናቂ ማድረጉ የአደባባይ ሐቅ ነው፡፡ ከአስጨናቂ እና ከኢ-ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ርምጃው መካከል በዋነኝነት ሊጠቀስ የሚችለው ደግሞ “አሸባሪነት” የሚለው ታፔላው ነው፡፡

በዚህ ሰው በላ ሐሳዊ ፍረጃውም ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ ተቃዋሚዎችን፣ ሞጋች የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞችን፣ የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞችን…ባጠቃላይ ስልጣኔን በዓይነ ቁራኛ ይመለከቱብኛል ብሎ ቀይ መስመር ያሰመረባቸውን ሰዎች አስሮ አስቀምጧቸዋል፡፡

በዚህ ስጋቱ የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ በ2007 ዓ.ም በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ንቁ ተሳታፊ ይሆናሉ ብሎ የሚገምታቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም የነፃው ፕሬስ  ሞጋች ጋዜጠኞችን በ“አሸባሪነት” ሰበብ እየቀፈደደ ወህኒ ሊያወርዳቸው እንደሚችል የማይጠረጥር የኢህአዴግን አስከፊ የፖለቲካ ስነ-ባህሪ የማያውቅ ብቻ ነው፡፡

ይህን ያልኩት ያለ በቂ ምክንያት አይደለም፡፡ በ1997 ዓ.ም የምሁራን ስብስብ በነበረው ቅንጅት የደረሰበት ወደር አልባ ሽንፈት ዳግም እንዲደገምበት ስለማይፈልግ ለስልጣኑ የሚያሰጉ ፓርቲዎችን (አመራሮቻቸውን) አነፍንፎ ከመያዝ ወደ ኋላ አይልም፡፡

በዚህም የተነሳ የ2007ቱን ብሔራዊ ምርጫ ተቃዋሚዎች እንደፈለጉ እንዲሆኑበት እና የነፃው  ፕሬስ አባላት በነፃነት እንዲዘግቡት ሁኔታዎችን ያመቻቻል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ እናም በ97  ዓ.ም ምርጫ ለወህኒ ቤት እንደተገበሩት ተቃዋሚዎች እና ጋዜጠኞች ለ2007ቱም ምርጫ እንደ አድባር የሚገበሩ ተቃዋሚዎች እና ጋዜጠኞች አይጠፉም፡፡ ጥያቄው ይገበራሉ ወይስ አይገበሩም? የሚለው ሳይሆን፤ እነማን ይገበራሉ? የሚለው ነው፡፡

ደርግ በዘመነ ስልጣኑ የተቃውሞ ድምፅ ሲያሰሙት የነበሩ ሰዎችን “አድኃሪ፣ አወናባጅ…” ወዘተ እያለ ይፈርጅ ነበር፡፡ ፈርጆ ሲያበቃም “አድኃሪዎች” ምኖች፣ ምናምኖች ያላቸውን ሰዎች  ከማሰርና ከመደብደብ አልፎ እስከ መግደል የደረሰ እርምጃ ይወስድባቸው ነበር፡፡ ደርግ እንዲያ ሲፈርጅ፣ ሲገድል፣ ሲያስር፣ ሲደበድብ የነበረው ለህልውናው ስለሚሰጋ ነበር፡፡

እየፈረጀ ባያስር፣ እያሰረ ባይገድል…የተቃውሞ ድምፅ የሚያሰሙ ወገኖች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ስልጣኑ (ህልውናው) አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ስለሚያምን የስልጣን ትንኮሳ ለሚያደርጉበት ሰዎች እንቅልፍ የለውም ነበር፡፡ ጃንሆይም ተቃውሞ ያሰሙባቸው የነበሩ  የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን “ፀረ ዘውድ፣ ፀረ ንጉስ…” እያሉ በመፈረጅ ለህልውናቸው ማቆያ  ወይም ለስልጣን ማረጋጊያ የሚያግዙ ርምጃዎችን ይተገብሩባቸው ነበር፡፡

እነሆ ኢህአዴግም “ከማን አንሼ” በሚል ስሜት የሰላ ሂስ የሚያቀርቡ ጋዜጠኞችን፣ ለስልጣኔ  (ለወንበሬ) ያሰጉኛል የሚላቸውን ጠንካራ ተቃዋሚዎችን እያደነ በ“አሸባሪነት” ስም ወህኒ ያወርዳቸው  ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ በጋዜጠኞቹ በእነ እስክንድር ነጋ እስር (“የአሸባሪነት ታፔላ”)  ነፃውን ፕሬስ ለማስበርገግ፣ በፖለቲከኞቹ በእነ አንዷለም አራጌ ተመሳሳይ ታፔላ የተቃውሞውን መንደር ለማስደንበር መላ ዘይዶ የተነሳው ገዢው ፓርቲ “አሸባሪ” የሚለውን ሰበብ የህልውናው ማስጠበቂያ “ዘበኛ” ሳያደርገው የቀረ አይመስለኝም፡፡

ጋዜጠኞች በ“አሸባሪነት” ስም ወህኒ በወረዱ ቁጥር መንግስት የሰላ ሂስ ከሚሰነዝሩ የነፃው  ፕሬስ አባላት ሂስ “ነፃ” እየወጣ ይሄዳል፡፡ እንዲሁ ከፍተኛ የህዝብ ቅቡልነት የተቀዳጁ  የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች “አሸባሪ” በሚል ሰረገላ ወህኒ ሲወርዱ ገዥው ፓርቲ የስልጣን ማገሩን ይበልጥ እየተከለው እና እያጠበቀው ይመጣል፡፡ ታዲያ ከ”አሸባሪነት” በላይ  የመንግስትን ህልውና (ስልጣን) እያስጠበቀ ያለ ዘብ ይኖር ይሆን?

ኢህአዴግ “አሸባሪነት”ን ለብቻው የሚረዳበት (የሚተረጉምበት) የተለየ መዝገበ ቃላት እንዳለው የምናውቀው የነ አሜሪካን አቋም በአንክሮ የገመገምን ዕለት ነው፡፡ እንደሚታወቀው አሜሪካና  ኢትዮጵያ “የጸረ ሽብር” አጋር ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት “አሸባሪ” እያለ የሚያስራቸውን ጋዜጠኞች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አሜሪካ “አዎ! አሸባሪ ናቸው” ብላ አታምንም፡፡

ይባስ ብላ “በሽብርተኝነት” ስም የታሰሩ ጋዜጠኞችን እና ፖለቲከኞችን በአስቸኳይ ይፈታ ዘንድ የኢትዮጵያን መንግስት ያሳሰበችበት ጊዜ በርካታ ነው፡፡ የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማትም የኢትዮጵያ መንግስት “ሽብርተኛ” እያለ ወህኒ የወረወራቸውን ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች  “ጀግና” እያሉ ሲሸልሟቸው ነው የምናስተውለው፡፡

ከዚህ እውነታ የምንገነዘበው ኢህአዴግ ራሱ በፈለሰፈው እና የተቀረው አለም በማይስማማበት “ሽብርተኝነት” ስም እየነገደ መሆኑን ነው፡፡ አዎ! ሽብርን እና አሸባሪዎችን የማይጠየፍ ጤነኛ  ሰው የለም፡፡ ነገር ግን ኢህአዴግ “አሸባሪ” የሚለውን ቃል የሚተረጉምበት መዝገበ ቃላቱ  ከሌላው አለም የተለየ በመሆኑ ሰርክ እንደተወገዘበት ነው የሚገኘው፡፡

አንድ የማውቃቸው ባለትዳሮች ነበሩ። ምንም እንኳን ዛሬ ተነጣጥለው ለየብቻ መኖር ቢጀምሩም፤ ሚስትየው ባሏ መጠጥ እንዲያቆም ያልተሳለችው ስለት እና ያላንኳኳችው የቤተክርስቲያን በር የለም። ከዚህም ሌላ ጠዋት ከቤት ሊወጣ (ወደ ስራ ሊሄድ ሲል) እግሩን ከመላስ በማይተናነስ መልኩ ማታ ጠጥቶና ሰክሮ እንዳይመጣ ትወተውተዋለች፣ ትለምነዋለች፣ ታስጠነቅቀዋለች።

ውትወታዋም ሆነ ልመናዋ እንዳልሰመረ የምትረዳው ማታ ወደ ቤት ሲመጣ ሰክሮ እየተንገዳገደ  መሆኑን ስትመለከት ነው። ጠዋት ሲወጣ አስጠንቅቃው ማታ ሲገባ የሚሰክረው ለምንና ምን በድላው እንደሆነ ስትጠይቀው `ሰይጣን አሳስቶኝ ነው` ይላታል በመጠጥ የተላወሰው ምላሱ  እየተደናቀፈበት። እሱ እየሰከረ እሷ እየመከረችና እየለመነች ለአንድ አመት ያህል አብረው ቢኖሩም, መፋታታቸው ግን አልቀረም ነበር። አብረው በኖሩባቸው ወቅቶች ጠጥቶ ሲመጣ `ለምን?` ማለቷን አትተውም ነበር። `ሰይጣን አሳስቶኝ ነው` የሚለው ቃል የዘወትር መልሱና ሰበቡ መሆኑን የተገነዘበችው ሚስት `ምን አለበት ለአንድ ቀን እንኳን ሰበብህን ለወጥ ብታደርገው? ሁልጊዜ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው እያልክስ ለምን ታሞኘኛለህ?` ብላ በተናገረች ማግስት እቃዋን ይዛ ላትመለስ ተለየችው።

እውነት ነው! አመቱን ሙሉ ወይም ለአመታት በአንድ በማይለወጥና በማይሻር ሰበብ  አድራጎታችንን (ስህተታችንን) እየሸፋፈንን ለመቀጠል የምናደርገው ሙከራ ሰበባችንን  በሚያደምጠው ሰው ላይ የማይሰረይ መሰላቸት ይፈጥራል። ሁልጊዜ በአንድ ሰበብ ለመጓዝ መሞከር ፋራነታችንን እና አራዳ አለመሆናችንን ያሳብቅብናል።

በማይለወጥ ሰበባቸው (ምክንያታቸው) ልንጠቅሳቸው ከምችላቸው አካላት ደግሞ ገዥያችን ኢህአዴግ አንዱ ነው። ኢህአዴግ መንግስት እንደመሆኑ የአገሪቱን ፀጥታና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት አለበት። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ (አንዳንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በርከት ለሚሉ አንዳንድ ጊዜዎች) ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ሙስሊሙን ወክለው የሚንቀሳቀሱ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ሲከስስ ወይም ሲያስር እንደ ምክንያት (ሰበብ) የሚያስቀምጣቸው መልሶች  እጅግ ተመሳሳይ እና ማሻሻያ የማይደረግባቸው ናቸው። ጋዜጠኛን ሲያስር ‹‹ህገ-መንስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በሀይል (በሽብር) ለመናድ ሲቀሳቀስ…›› የምትል የተለመደችውን ምክንያት ያስቀምጣል። ይህ ምክንያት ጋዜጠኛውን ለመክሰሻ አገልግሎት ብቻ የሚውል አይደለም። ተቃዋሚዎችን ሲያስርም ‹‹ሽብርተኛ›› የምትለውን ቃል ለመክሰሻ ፍጆታው ያውላታል። በአሁን ሰአት በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊሙን ተወካዮች ሲያስር እንደ ምክንያት የተጠቀመው ጋዜጠኞችንና ተቃዋሚዎችን ለመክሰስ የደረደራቸውን ሰበቦቹን ነው።

ከላይ የባለትዳሮቹን የህይወት ተሞክሮ ያነሳሁት ያለ ምክንያት አይደለም። ከኢህአዴግ ምክንያት ድርደራ ጋር ተቀራራቢ (ተመሳሳይ) ባህሪ ስላለው ነው እንጂ። ሚስት ‹‹ሰይጣን አሳስቶኝ ነው›› በሚለው የባሏ ቋሚ ተሰላፊ ሰበብ ትዳሯን እስከመናድ ያደረሰ መሰላቸት  አሳድሮባታል።

የ1997 ዓ.ም የምርጫ ውጤቱ ወደ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካጋደለና ሁኔታዎች ወደአላስፈላጊ አቅጣጫ ከዞሩ በኋላ በርካታ ተቃወሚዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች ወህኒ ወርደዋል። የዛን ጊዜ የታሰሩበት ምክንያት ‹‹ህገ-መንግስቱን እንደ ሾላ በድንጋይ ለማውረድ…›› የሚል ነበር። 1997 ዓ.ም ጥሎን ከነጎደ ዛሬ ወደ ስምንት አመት ሆኖታል። በነዚህ ስምንት አመታቶች ውስጥ ፖለቲካው፣ ኢኮኖሚው፣ ኑሮው፣ የሰው አስተሳሰብ… በውድቀትና በእድገት ምህዋር ውስጥ ወይ ወደ ላይ ወጥቷል፤ አሊያም ወደታች ወርዷል። በአጠቃላይ ሁኔታው ተለውጧል፤ ተለዋውጧል። “ህገ-መንግስቱንና ህገ-መግስታዊ ስርዓቱን በሀይል (በሽብር) ለመናድ ሲንቀሳቀሱ…›› በመንግስታችን ቋንቋ፤ የቁመት፣ የወርድ፣ የመጠን ለውጥ ሳይደረግባት ይኸው እስከዛሬ እንዳለች አለች። ኢህአዴግ ወደፊት እስከሚኖርበት ጊዜ ድረስም አብራው ትኖራለች፤ ሰንደቁና አርማው ናትና አትጠፋም። ጋዜጠኞች፣ ተቃዋሚዎች፣ ‹‹እምቢየው›› መብቴን የሚሉ ዜጎች ከኢትዮጵያ ምድር  ሲጠፉ ብቻ ነው ያቺ የኢህአዴግ ምክንያት ‹‹በክብር›› ወደ ማህደሯ የምትመለሰው። እስከዚያው ድረስ ግን፤ እንደ ርዕዮተ አለም የተያዘችው ምክንያት ሳትከለስ፣ ሳትበረዝም ሆነ ተሐድሶ ሳይደረግባት በዶግማ (Doctrine) መልክ ትቀጥላለች።

የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች ‹‹መንግስት በሽብርተኝነት ሊያስረን እንደሆነ ከታማኝ ምንጮቻችን ሰማን›› ብለው አገር ጥለው ከተሰደዱ በኋላ፤ እንዳሉትም በሌሉበት በሽብርተኝነት ተከስሰውና ‹‹ሽብርተኛ›› ተብለው ተፈርዶባቸዋል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ርእዮት አለሙ ተከስሰው የተፈረደባቸው ‹‹ሽብርተኛ›› በምትለዋና ለአዲስ ነገር ጋዜጣ ባልደረቦች በተለጠፈችው ቦሎ ነው። አንድ ጋዜጠኛ ሲታሰር የክሱ ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ የግድ የሚመለከተው አካል መግለጫ እስኪሰጥ መጠበቅ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። አሁን አሁን እከሌ የሚባል ጋዜጠኛ ታሰረ የሚል ወሬ ሲሰማ፤ ያው ‹‹በሽብርተኝነት›› እንደሚከሰስ አስቀድሞ ማረጋገጥ እየተለመደ መጥቷል። ይህ እንዲሆን በር የከፈተው መንግስታችን በተለይም ከ1997 ምርጫ በኋላ እየተከተለው የመጣው ተሐድሶ አልባ ምክንያቱ (ሰበቡ) ነው።

ለአዲስ ነገር ጋዜጠኞች ክስ የተጠቀመውን ምክንያት ለእስክንድር ነጋ፣ ለእስክንድር ነጋ  የተጠቀመውን ለርዕዮት አለሙ… ለውብሸት ታዬ… ነገ  ደግሞ አንድ ጋዜጠኛ ሲታሰር፤ ለእሱም ፍጆታ ያውለዋል።

በአንድ ተመሳሳይ ምክንያት የተለያዩ ጋዜጠኞችን ማሰር አይሰለችም? የሰው ልጅ አንዴ፣ ሁለቴና ሶስቴ በሰይጣን “ሊሳሳት” ይችል ይሆናል። ግን እንዴት ዘለአለአም በሰይጣን እየተሳሳተ ይኖራል?  እያንዳንዱ ጋዜጠኛስ እንዴት ‹‹ሽብርተኛ›› ሊሆን ይችላል?

በደርግ ጊዜ ነው አሉ፤ ‹‹አንድ ሰው አይደለም በጤናው ሰክሮ እንኳን የመንግስቱ ኃይለማርያምን አስተዳደር መውቀስም ሆነ መተቸት አይችልም ነበር ይባላል። “ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል” የሚለው አባባል በደርግ ጊዜ አይሰራም ነበር።” ሲሉ አንድ አባት አጫውተውኛል። ደርግ ከተገረሰሰ ከሃያ ሁለት አመታት በኋላ ማለትም ዛሬ፤ ያውም “ዴሞክራሲና ነፃነት ያለገደብ መስፈኑ” በሚነገርበት በዚህ ጊዜ ሳይሰክሩ መንግስትን መተቸት ከባድ እየሆነ መጥቷል። ከባዱን መከራ እጋፈጠዋለሁ ያለ ጋዜጠኛም ‹‹ያቺ ነገር›› ትመዘዝለታለች።

እንግዲህ በደርግና በኢህአዴግ መካከል ያለውን ልዩነት እንመርምር። በደርግ ጊዜ ተሰክሮም ሆነ ሳይሰከር ትችት እሰነዝራለሁ ማለት ከባድ ነበር። በኢህአዴግ ጊዜ ዲሞክራሲው “ያለ ገደብ”  በመንሰራፋቱ፣ በገደብ ሰክረው ያለገደብ የመንግስትን ስህተት መተቸት ይቻላል። ታዲያ  በመጠጥ ስካር እንጂ በኑሮው ንረት፣ በመልካም አስተዳደር ችግር፣ በመኖሪያ ቤት እጥረት ስካር መንግስትን ማማረር፣ ከማማረርም አልፎ ለተቃውሞ መውጣት “ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች…” ለሚል የክስ ፋይል አሳልፎ ይሰጣል። መቼም አሜሪካና አውሮፓ የሽብርተኞች ደጋፊና አፍቃሪ ስለሆኑ አይደለም-የኢትዮጵያ መንግስት “አሸባሪ” ያላቸውን እነ እስክንድርን እየሸለሙ ያሉት፡፡ እናም ኢህአዴግ ሆይ! የተበላች ዕቁብ የመሰለችውን ምክንያትህን (አሸባሪነትን) ቀየር ብታደርጋትስ?!…

 

 

በኖርዌ ያሉ ኢትዮዽያውያን የወያኔን የስለላ መረብ በመቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

0
0

ETH Norበ11-4-2014 በኖርዌ ያሉ ኢትዮዽያውያን የወያኔን የስለላ መረብና ኖርዌ በስደተኛው ላይ ያላትን ፖሊሲ በመቃወም    የተቃውሞ ሰልፍ አረጉ።  23 ዓመት እራሱ መራጭ እራሱ ተመራጭ ሆኖ በጠመንጃ አፈሙዝ ህዝቡን እያንቀጠቀጠ የኖረው ወያኔ

አንድ ቀን ሕዝብ በቃኝ ብሎ አንቅሮ እንደሚተፋውና ንብ ሆኖ ለነፃነቱ እንደሚነሳ ማወቅ ነበረበት።

ግን አልሆነም ዜጎች እንደዜጋ በሐገራቸው መኖር ቀርቶ በስደትም ሰላማቸውን ማግኘት አልቻሉም።

እስርና እንግልት፣ረሐብና ሰቆቃ፣ስደት የእያንዳንዱ እጣ ፋንታ ሆነ፤በወያኔ ዘመን ሰው ብቻ አይደለም መሬትም መሰደድ ጀምሮ የግል ጥቅሙን ለማስጠበቅ ሲል የኢትዮዽያን ለም መሬት ለሱዳን በመሸጥ ላይ ይገኛል

ኢትዮዽያንና ኢትዽያዊነትን ያሉ ሁሉ አሸባሪ እየተባሉ በየእስርቤቱ ታጉረው እጣ ፈንታቸው እስርና እንግልት ሆነ

ሐገራቸውን ጥለው በባሕርና በየብስ አቆራርጠው የሞተው ሞቶ የተረፈው በአለም ዙሪያ ተበትኖ ጥገኝነት  በመጠየቅ ይኖራል.

በዚሕም የተሳካላቸው ጥቂቶች ሲሆኑ ባብዛኛው ወያኔ ለውጩ አለማት በሚያሳየው ሁለተኛው ፊቱ ምክንያትና ምእራባውያን ከሐገሪቱ ከሚያገኙት ጥቅም የተነሳ ሐገርህ ዲምክራሲ ነው እየተባለ ፍትሀዊ ያልሆነ መልስ እየተሰጠው በመጉላላት ላይ ይገኛል።

ያም ሆኖ የሐገሩ ጉዳይ በደም ስሩ ሰርጎ የገባው ኢትዮዽያዊ ሁሉ ጠዋት ማታ ኢትዮዽያዬ እያለ ይጮሀል። ይህ የህዝብ ቁጣ ያስፈራው ወያኔ ያለ የሌለ የሐገሪቱን ኢኮኖሚ እየመዘበረ ዜጎችን ይሰልላል ያሰልላል፣አልፎ ተርፎም ዜጎችን ከመሰሎቹ ጎረቤት ሐገሮች ድረስ በመሄድ ጎትተው እስርቤት ያስገባሉ።

ይህንን ለመቃወምና ለማውገዝ ነበር የኢትዮዽያ ስደትኞች ማህበር በኖርዌ ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጅቶ ኢትዮዽያውይኑ ዛሬም ስለ ሐገራቸው ሊጮሁ የወጡት፤ ሰልፈኞቹ ድምፃቸውን እንዲህ በማለት ነበር ድምፃቸውን ያሰሙት እኛ ስደተኞች እንጅ ወንጀለኛ አይደለንም፣ኖርዌ ለማፊያው ወያኔ የምታደርጊውን እርዳታ አቁመሽ ከኢትዮዽያ ሕዝብ ጋር ቁሚ፣ወያኔ የሚያደርገውን ተግባር እናወግዛለን፣ሼም ኦን ዩ ሳውዝ ሱዳን ኦኬሎን አሳልፈሽ የሰጠሽ፣ወያኔ አሸባሪ ነው፣ለውጥ እንፈልጋለን፣ኖርዌ የዩኤንን ህግ ታክብር የሚሉትን የመሳሰሉ ሲሆን

በሰልፉ ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮች መልክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን የኢትዮዽያ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ተወካይ አቶ ዳንኤል የወያኔን ጀሌዎች የማጋለጡ ስራ በሚገባ እየተሰራበት መሆኑን ሲገልጡ ሰልፈኛው በጭብጨባ የተቀበላቸው ሲሆን የስደተኛ ማህበሩም ተወካይ ኖርዌ ነፃ እንድታወጣን ሳይሆን ለወያኔ የምትሰጠውን እርዳታ አቁማ ድጋፍ እንድትሰጠን ነው፤ በተጨማሪም ኖርዌ አቶ ኦኬሎን ታስለቅቅ በማለት  ተጠይቃለች። በሰልፉ ላይ የኖርዌ ሊብራል ፓርቲ ተወካይ ከሰልፈኛው ደብዳቤ ተቀብለው መልክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን

የኖዋስ ፣አንቲረሲስት ተወካዮችም እንዲሁ ይዘውት የመጡትን መልክት ለሰልፈኛው አስተላልፈዋል።

ከዚያ በቀጥታ ወደሶፊን በርግ ሎካል አዳራሽ ሰልፈኛው አምርቶ ምሳ  ከተበላ በሁዋላ ኮሚቴው ካባላቱ ጋር ሰፊ ዉይይት ያደረገ ሲሆን የ፫ወር የስራ ሪፖርትም አቅርቦአል።

የኢትዮዽያ ስደትኞች ማህበር በኖርዌ

 

ድምጻዊ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) ከተሾመ አሰግድ ለሰረቀው ዘፈን ይቅርታ ይጠይቅ ይሆን? ወይስ ማን አለብኝነት ያልፈዋል?

0
0


ይታየው ከሚኒያፖሊስ

ከዓመት በፊት በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 38  ነዋሪነቱ ሚኒሶታ የሆነው ስመ ጥሩው ድምጻዊ ተሾመ አሠግድ “በጠራራ ጸሐይ ተዘረፍኩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ” ሲል ለዘ-ሐበሻ ጋዜጣ በሰጠው መግለጫ ላይ አስታውቆ ነበር። ካለፈቃዱ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) የተባለው ድምጻዊ የተሾመን “የኔ አካል” ወስዶ መሥራቱን አምርሮ መቃወሙንም አንብበን ነበር። “አንድ ዘፋኝ የአንዱን ወስዶ ለሕዝብ ሲያቀርብ ባለቤቱን ማስፈቀድ ይኖርበታል” ያለው ተሾመ “ጎሲ ከ20 ዓመት በፊት የተጫወትኩትን፦ “የኔ አካል የኔው ነሽ፤ ምን አወርስሻለሁ፤ አንጀቴና ልቤን ያው ትቼልሻለሁ”” ዘፈኔን ካለፈቃድ በክሊፕ ጭምር ማውጣቱ ክፉኛ በድሎኛል” ካለ በኋላ “ድምጻዊው ጎሳዬ ቀለሙ የኔን ብቻ ሳይሆን ዘፈኑን የደረሱልኝን ገጣሚው ይልማ ገብረአብን እና የዜማ ደራሲውን አበበ መለሰን ሁሉ ተዳፍሯል። ይህንን ዘፈን በፈረንጆች በ1987 ዓ.ም አካባቢ ከነራሄል ዮሐንስ ጋር በጋራ ባወጣሁት አልበም ውስጥ ሳካትተው ግጥሙን እና ዜማውን የሰጡኝ እነርሱ ናቸው። በሙዚቃ ክሊፑ ላይ የነዚህ ስም አልተጠቀሰም። ይልቁንም የሌላ ሰው ስም በመጻፍ የኛን ሥራ የራሱ በማስመሰል አቅርቦ ሥራዬን ዘርፏል” ሲል ቅሬታውን አሰምቶ እንደነበር አንበበናል።
jacki gossee
“ወደ ሕግ ጋር መሄዴ የማይቀር ነው። ጉዳዩን ፍርድ ቤት አድርሼ እሞግተዋለሁ” ያለው ድምጻዊ ተሾመ አሰግድ “የኔ አካል” የተሰኘውን ሥራዬን ካለፈቃዴ ተነጥቂያለሁና ከዚያ በፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ፤ በጠራራ ጸሐይ ነው የተዘረፍኩት።” በማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰረቁ ዘፈኖች ሲወጡ ከኦርጂናሉ ዘፋኝ በይሁንታ መገኘቱን እና አለመገኘቱን ማረጋገጥ ይኖርበታል ሲል ጥሪውን አቅርቦ ነበር። “ድምጻዊ ጎሳዬ ቀለሞ (ጃኪ ጎሲ) የተሾመ አሰግድን ዘፈን መሥራቱን አምኖ በቪድዮ ክሊፑ ላይ ምስጋና አቅርቧል” በሚል የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ለተሾመ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ተሾመም “ይሄ ገሎ ማዳን ነው። ነጮጭ ሲናገሩ መጀመሪያ አቁስለውና ከዛ ለቁስሉ ማበሻ ጨርቅ ስጠው ይላሉ። ጎሳዬም ያደረገው ያ ነው። ዘፈኑን ካለፈቃዴ ወስዶ፤ ክሊፑም ከመልዕክቱ ጋር የማይገናኝ አድርጎ ሰርቶ በመጨረሻ ተሾመ አሰግድን አመሰግናለሁ ብሎ ቢጽፍ ምን ዋጋ አለው? ከገደለኝ በኋላ ማርኩህ ቢለኝ ምን ዋጋ አለው?” በማለት አምርሮ ሲናገር መስማታችን ይታወሳል።

በኢትዮጵያ ስመ-ጥር ከሆኑ ድምጻዊያን መካከል የሆነውና ብዙዎች “ኢትዮጵያዊው ስቲቭ ዎንደር” የሚሉት ተሾመ አሰግድ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በመስከረም ወር 1945 ተወልዶ በተወለደ በ5 ወሬ ዓይነ ስውር መሆኑን በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 2 ላይ በሰጠው ቃለ ምልልስ መናገሩ ይታወሳል። የመጨረሻ ካሴቱን ካወጣ 17 ዓመት ያለፈው ይህ ድምጻዊ እስካሁን ስንት ካሴቶችን ሰርተሃል በሚል ጥያቄ አቅርበንለት “ጥቂት ካሴቶችን አውጥቻለው:: ትዝታና ባቲ በሚባለው የሙዚቃ ቅኝት በፊሊፕስ አሳታሚነት በ1960ዎቹ አንድ ሸክላ አውጥቼ ነበር:: ከዛ በተረፈ ያልተሳካለት አንድ ካሴት ሰርቼ ነበር:: ከዛ ወዲህ ግን ጅቡቲ ለ5 አመታት ከቆየው በሗላ ከሮሀ ባንድ ጋር በመሆን ‘የኩባያ ወተት”ን ሰራሁኝ:: ይበልጥ ከሕዝብ ጋር ያስተዋወቀኝም ይሄ ሥራ ነው:: በሌላ በኩል ከነራሄል ዮሐንስ; አሰፉ ደባልቄ እና ኬኔዲ መንገሻ ጋር አንድ ካሴት; እንዲሁም ከማርታ አሻጋሪ; በዛወርቅ አስፋው እና ኤልያስ ተባባል ጋር በመሆን አንድ ኮሌክሽን ሰርቼ ነበር:: በራሴ በኩል 2ኛውን ሙሉ ካሴቴን “ደርባባዬ’ን አውጥቼ ነበር:: ብዙም በሕዝብ ዘንድ አልገባም:: ግን አልፎ አልፎ ሰዎች ያውቁታል::” ሲል መልሷል። 

ተሾመ ጎሳዬ ሰረቀኝ ባለው ዘፈን ዙሪያ ይህን ቢናገርም ጆሲ ሾ ላይ የቀረበው ጃኪ ጎሲ በማን አለብኝነት እንደውም ተሾመ ስለዚህ ዘፈን አያገባውም ሲል መናገሩ ይታወሳል። ጎሳዬ ቀለሙ ይህን ያለው ለደራሲው እንደገና ስለከፈልኩት ተሾመ ይህ ዘፈን የኔ ነው ብሎ መከራከር አይችልም ሲል በቲቪ መድረክ መናገሩ ይታወሳል። ይህን ያለው ሃገር ቤት ሆኖ ነበር። ዛሬ ተሾመ አሰግድ በሚኖርበት ሰሜን አሜሪካ ጎሳዬ ቀለሙ መጥቷል። ተሾመ ፈቃድ ይፈልጋል። ሆኖም ግን ጃኪ በማን አለብኝነት “ድምጻዊው የለፋበትን ሥራ አያገባውም” ሲል ተናግሯል። ጃኪ እነ ምነው ሸዋ ላይ እንዳሳየው በግትርነቱ ይቀጥል ይሆን ወይስ ተሾመ እንዳለው ወደ ሕግ በመሄድ ጃኪን በስርቆት ይከሰው ይሆን? አብረን የምናየው ይሆናል።


ሰማያዊ ፓርቲ ሕዝቡ በሚያዝያ 19ኙ ሰልፍ በመውጣት የወቅቱን አሳሳቢ ጉዳይ እንዲናገር ጥሪ አቀረበ

0
0

semayawi party(ዘ-ሐበሻ) “ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልሳለን” በሚል ሰማያዊ ፓርቲ ባወጣው መግለጫው ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም በጃንሜዳ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የሕዝቡን ብሶት እናሰማለን አለ።

“ሰማያዊ ፓርቲ በመንግስት የሚፈጽሙ ሕገ ወጥ ድርጊቶች የሠብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ለመንግስት አካላት በተደጋጋሚ ጊዜያት ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ መንግስት እነዚህን ተከታታይ ጥሪዎች ተቀብሎ የማሻሻያ እርምጃ ከመውሰድና ችግሮችን ከመቅረፍ ይልቅ ጉዳዩን ችላ በማለት ችግሮቹ የበለጠ እየተባባሱ እንዲሄዱ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡” ያለው መግለጫው “በመሆኑም እነዚህ ችግሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ለማድረግ ሠማያዊ ፓርቲ እሁድ ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት የሚቆይ ከፓርቲ ጽ/ቤት እስከ ጃንሜዳ የሚደርስ ታላቅ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ያዘጋጀ ሲሆን የሠላማዊ ሰልፉን ቀንና ሰዓትም በአዋጅ ቁጥር 031983 መሠረት ለሚመለከተው አካል በደብዳቤ በማሳወቅ ሰልፉን ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡” ብሏል።

“በዚህ ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ ላይም ከዚህ ቀደም ተነስተው የነበሩ መንግስት በእምነት ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆም፣ ዜጎች ከቀያቸው ማፈናቀሉ እንዲቆምና ዜጎቹ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ የሚሉ ጥያቄዎች የሚነሱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በገዢው ፓርቲ ስልጣን እንጅ ለህዝብ የማይጨነቁት ተቋማት ስራቸውን በሚገባ ባለመስራታቸው ሕዝብ ለከፈለው ክፍያ አገልግሎት እያገኘ አለመሆኑም እያገኘ አለመሆኑም የወቅቱ አሳሳቢ ጉዳይ ሲሆን በተለይ የውሃ የመብራት የቴሌ ኮሚኒኬሽንና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ሕዝብን እያመማረረ መሆናቸው በሠላማዊ ሠልፉ ላይ የሚነሱ ወሳኝ ጥያቄዎች ናቸው፡፡” የሚለው ሰማያዊ ፓርቲ “ይህን ታላቅ ሠላማዊ ሠልፍ የተሳካ እንዲሆን ለማድረግ የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልስ ዘንድ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ሲቪክ ማህበራትና ሚዲያው ከሚደረገው ጥረት ጎን መቆም ሀገራዊ ግዴታ እንዲወጡ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡” በማለት ለዘ-ሐበሻ የላከውን መግለጫ ቋጭቷል።

በባሌ 2 ሙስሊሞች በመንግስት ቅጥር ነብሰ ገዳዮች ሕይወታቸው መጥፋቱ ተዘገበ

0
0

(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)

በባሌ ዞን ጊኒር ከተማ 2 ሙስሊሞች በመንግስት ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች መገደላቸውንና ህዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ ቁጣውን እየገለጸ እንደሆነ ቢቢኤን ራድዮ ዘገበ።

እንደራዲዮው ዘገባ ችግሩ የተከሰተው ሁለት የመንግስት ፖሊሶች በትላንትናው እለት ሰይፉ የተባለ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ በጊኒር ከተማ በሚገኝ ሆቴል መኝታ ክፍል ይዘውት ከገቡ በኋላ በገመድ አንቀው የገደሉት ሲሆን የሆቴሉ ሰራተኛ መኝታ ቤቱን ሲከፍት ሟችን በማየት ለዘመዶቹ ጥቆማ ሰጥተዋል፡፡

ራድዮው ጨምሮም ሁኔታውን የሰማው ያካባቢው ነዋሪ በነቂስ በመውጣት ግርግር የተፈጠረ ሲሆን አስተዳደሩንም በመውረር ልጁን ይዘው ሲሄዱ የነበሩ ፖሊሶችን እንዲያቀርቡዋቸው፤ አልያም ሌላ ነገር እንደ ሚከሰት በመግለጽ ቢጠይቁም የመንግስት ቅጥረኞች ህዝቡን ከማረጋጋት ይልቅ ህዝቡ ላይ የተኩስ እሩምታ በመክፈት አብዲ በያን የተባለን በመግደል ቀውሱን አባብሰውታል ሲል ዘግቧል።

ቢቢኤን እንዳለው የሟቾቹም ሬሳ ለምርመራ በሚል አዲስ አበባ በሚገኘው ሚኒልክ ሆስፒታል ተልኳል፡፡

የበድር አመራሮችን አስመልክቶ የወጣ መግለጫ –ከፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን

0
0

ጥቂት የበድር አመራሮች በሰሜን አሜሪካ የሚገኘዉን የሙስሊሙን ማህበረስብ ስም በመጠቀም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለመነጋገር ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉዞ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ

ፈርስት ሒጅራህ ፋዉንዴሽን ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የሚያደርጉትን ሰላማዊ የመብት ትግል መዳረሻዉ ድል እስኪሆን ድረስ በማንኛውም ጉዳይ በጽናት ይደግፋል። በህዝብ የተመረጡት የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ያሳዩት ቁርጠኝነትንና ጽናትን ፈርስት ሒጅራህ በእጅጉ የሚያደንቅም ብቻ ሳይሆን በነዚህ የሰላም አምባሳደሮች ላይ የኢትዮጵያ መንግስት እየፈጸመ ያለዉን ግፍ በማንኛዉም መልኩ የሚፋረደዉ ዘግናኝ እዉነታ ነዉ። እነዚህ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆች የሆኑት ኮሚቴዎች ዛሬም በእስር ቤት ውስጥ ያሳዩት የአመራር ብቃትና ጥንካሬ በአለማችን የታሪክ መዝገብ ላይ የሚሰፍር አኩሪ ታሪክ በመሆኑ ፈርስት ሒጅራህ ኮሚቴዎቹን ከመደገፍም ባሻገር የሚከተል መሆኑን ሲገልጽ በታላቅ በደስታ ነዉ።

የታሰሩት ኮሚቴዎች

የታሰሩት ኮሚቴዎች


የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ላይ እያደረሰ ያለዉን ቀጣይ በደል ለመታደግ የታሰሩትን አሚሮችን (መሪዎችን) በመከተልና ድምጻችን ይሰማ የሚያወጣዉን ትእዛዝ ለመተግበር ፈርስት ሒጅራህ ወደ ሗላ የማይል መሆኑን እያስገነዘበ፤ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የሚያደርጉትን ሰላማዊ ትግል ለማኮላሽት የሚደረግ ማንኛዉንም እንቅስቃሴ ለማጋለጥ ፈርስት ሒጅራህ እምርታዊ በሆነ ትጋት የሚሰራ መሆኑንም ለመግለጽ ይወዳል። እንደ አገር መሪ ሳይሆን እንደ አሸባሪ የሚንቀሳቀሰዉ የኢትዮጵያ መንግስት የፈርስት ሒጅራህ ፋዉንዴሽንን እስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ከግምት ዉስጥ በማስገባት ድርጅቱ የሚያደርገዉን ጠንካራ የመብት ትግል ለማርገብ ያደረጋቸዉ ጥረቶች ሁሉ የመከኑበትን እዉነታ ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ማድረጉም ግድ ይላል።

ፈርስት ሒጅራን ጨምሮ ሌሎች በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ማህበራት የመሰረቱት በድር አለምአቀፍ የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ድርጅት የተመሰረተለት አላማን በማፋለስ፤ በድርጅቱ ምስረታ እና አወቃቀር ብሎም አመራር ላይ ወሳኝ ሚና ያለዉንና ለወደፊቱም በድርጅቱ ህልዉና ላይ አይቀሬ ተሳትፎና ድርሻ ያለዉን ፈርስት ሒጅራን በማግለል፤ የኢትዮጵያን መንግስትና የሙስሊሙን ማህበረሰብ እናደራድራለን በማለት አብዛኛዉ ያልወከላቸው ጥቂት የበድር አመራሮች በቅርቡ ስኬት አልባ የሆነን ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ ማድረጋቸዉ ይታወቃል። ይህንን ሙሉ ህዝባዊ ይሁንታ ያላገኘዉን ጉዞ ፈርስት ሒጅራህ ፋዉንዴሽን ከዚህ ቀደም እንደተቃወምነዉ አሁንም ሙሉ በሙሉ የሚቃወም መሆኑን እየገልጸ ያለዉንም አቋም ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ማድረግ ይፈልጋል።

ቀደም ሲል በመንግስትና በሙስሊሙ ጉዳይ ላይ ገለልተኛ(ኒውትራል) የሆነ አቋም ነዉ ያለን በማለት በይፋ ይናገሩ የነበሩ ግለሰቦች፤ ዛሬ የኢትዮጵያ መንግስት አትኩሮት ሰጥቶ በልዩ አቀባበል(VIP)አስተናግዶናል፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በከፈትነዉ መስመር መስራቱን እንቀጥላለን፤ ሙስሊሙ ህብረተሠብ አንቅሮ የተፋውን የመንግስት መጅሊስን የሙስሊሙ ጉዳይ ያገባዋል (stakeholder) ነው በማለት እዉቅና በመስጠት አነግረናል፣ኢትዮጵያ ዉስጥ ቢሮ ከፍተናል በማለት ያለ ምንም እፍረት ሙስሊሙን ማህበረሰብ እያወናበዱ ይገኛሉ። እነዚህ ግለሰቦች ባስቸኳይ የያዙትን የህዝብ አደራ አስረክበዉ የድርጅቱ መመሪያ ተተግብሮ ህዝብ ያመነበት ምርጫ እንዲደረግ ፈርስት ሒጅራህ በአጽኖ ይጠይቃል።

የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሙ ማህበረስብ ላይ የሚያደርሰዉን ጭቆና ለማዉገዝ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ወኔ የሌላቸዉ የመንግስትን ጥቅም አስከባሪና መንግሥት በሙስሊሙ ህብረተሰብ መካከል የተፈጠረውን አስጊ አለመግባባትን መፍትሄ ለማስገኘት ነዉ በማላት የተሳሳተ አመለካከታቸዉን ሲያራምዱ የነበሩ ግለሰቦች ዛሬ አስታራቂ መስለዉ ኢትዮጵያ መሔዳቸዉ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ንቃተ ህሊና እንደናቁ የሚቆጠር እጅግ አሳፋሪ ስራ በመሆኑ ባስቸኳይ ከበድር ድርጅታዊ አሰራር ገለል እንዲሉ ፈርስት ሒጅራህ የጠይቃል።
ፈርስት ሒጅራህ ከጅማሮዉ አንስቶ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በአያሌ መስዋእትነት የገነባዉ በድር፤ ከመስመር በወጡ ጥቂት መሪዎች ግላዊ ፍላጎት የሚፈርስ አይደለም። በመሆኑም ፈርስት ሒጅራህ በመላዉ አለም ከሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ጋር በመጻጻፍና በመዘዋወር ግንዛቤን የማስጨበጥ ስራ ይሰራል።

ለፊትና (መከፋፈል)የሚለዉን ቃል ብዙ የግል ጥቅም አስጠባቂ አካላት የሚጫወቱበት ካርድ በመሆኑ፤ ፈርስትሒጅራህ በወሰደዉ አቋም ፊትና ፈጣሪዎችን መንቅሮ ለማዉጣት የሚያደርገው ጥረት መላዉ የኢትዮጵያ ሙስሊም ምንም አይነት ግራ መጋባት ሳይስተዋልበት ጥረታችን ከስኬት ይደርስ ዘንድም በዱዓ (በጸሎት) ይበረታ ዘንድም ፈርስት ሒጅራህ ይጣራል። ቀድም ሲል በኢትዮጵያ የሚገኙ ታዋቂ ዳኢዎች እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ሰላማዊ ትግሉን ለመቀልበስ ያደረጉት ሙከራ በተባበረዉ የሙስሊሙ ማህበርሰብ ክንድ እንደከሸፈዉ ሁሉ ተመሳሳይ ሴራን ለማክሸፍ ፈርስት ሒጅራህ የሚያደርገዉን ጥረት ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንዲረዳዉ ያሳስባል።

ኮሚቴዎቻችንና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች የታሰሩበት፣ የተገረፉበት፣ የተሰቃዩበት፣ የሞቱበትና ብዙዎች የተሰደዱበትን ትግልን ከንቱ ለማድረግ ለሚነሳ ማንኛዉም ሐይል ታጋሾች አንሆንም። በየአደባባዩና በተለያዩ የዲፕሎማሲ መድረኮች በግልጽ ወጥተን ህዝብ ከወከላቸዉ አሚሮቻችን ጎን ቆመን ለመብት ለነጻነት በመታገላችን አንገት ደፊና ይቅርታ ጠያቂዎች አንሆንም። በድር ድርጅታችን ነዉ፦ በድርን ለማዳን ቆርጠን በመነሳታችን መላዉ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም በዱዓ (በጸሎት) እንዳይረስን እንማጸናለን።

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በአስቸኯይ ከእስር ይለቀቁ፦

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

አላሁ አክበር

ሰማያዊ ፓርቲ የሚታገለው ማንን ነው ? (ግርማ ካሳ)

0
0

ግርማ ካሳ

blue partyሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እንደጠራ አነበብኩ። ገረመኝ። መጋቢት 28 ቀን በአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕጉን ባፈረሰ መልኩ በመጋቢት 28 ቀን ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል ገለጸ። የሰልፉ ቀን ወይንም ቦታ እንዲቀየር የመጠየቅ እንጂ በጥቅሉ ለቀረቡት የሰልፍ ጥያቄዎች እውቅና አንሰጥም የማለት መብት አስተዳደሩ እንደሌለው በመጥቀስ፣ በአስተዳደሩ የተላከዉን ሕገ ወጥ ደብዳቤ አንድነት እንደማይቀበል አሳወቀ። አንድነት ተለዋጭ ቀን እንዲያቀርብ የሚጠይቅ፣ ሕጉን የተከተለ ሁለተኛ ደብዳቤ፣ አስተዳደሩ፣  ላከ። የአንድነት ፓርቲ መጋቢት 28 ቀን ሊደረግ የታሰበውን ሰልፍ ወደ ሚያዚያ 5 ቀን ለማድረግ እንደሚፈልግ አሳወቀ። በሚያዚያ 5 ቀን፣ የሩጫ ዝግጅት ስላለ፣  ቅዳሜ ሚያዚያ 4 ቀን ሰልፉን ማድረግ እንደሚቻል፣ አስተዳደሩ በደብዳቤ  ገለጸ። ግምሽ ቀን የሚሰራበት እንደመሆኑ፣ ቅዳሜ ቀን ሰልፉን ማድረግ እንደማይስማማው የአንድነት ፓርቲ ገልጸ። በሳምንቱ እሁድ ፋሲካ፣ በአስራ አምስት ቀኑ ደግሞ ዳግማይ ትንሳኤ በመሆኑ ፣ ለክርስትና እምነት ተከታዮች አክብሮቱን በመግለጽ፣ ሁለት እሁዶችን (ሚያዚያ  12 እና 19) አልፎ በሚያዚያ 26 ቀን ሰልፉን ለማድረግ ወሰነ።

 

ምንም እንኳን የአዲስ አበባ አስተዳደር መጀመሪያ ላይ የጻፋቸው ሕግ ወጥ ደብዳቤዎች አሳዛኝ የነበሩ ቢሆንም፣ የአንድነት ፓርቲ ሕግ ወጥ ደብዳቤዎችን እንደማይቀበል ካሳወቀበት ጊዜ በኋላ ግን፣ በአንድነት እና በአስተዳደሩ መካከል ሲደረጉ የነበሩት የደብዳቤ ልዉዉጦች ጤናማ መሰሉኝ። ያሉ ልዩነቶችን በሰለጠነ መልኩ ለመፍታት መሞከር ሊበረታታ የሚገባዉ ነው።

 

የአንድነት ፓርቲ ከአስተዳደሩ ጋር በዚህ ሁኔታ እየተነጋገረ ባለበት ሁኔታ፣ ሳይታሰብ የሰማያዊ ፓርቲ ፣ የተለየ ጥያቄዎች ቢኖሩት እሺ፣ ግን አንድነት ባቀረባቸው ጥያቄዎች ዙሪያ፣ ሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ ጠራ።  ይሄም ሰማያዊ ፓርቲን በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎችን እንድጠይቅ አደረገኝ።

 

የአንድነት ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀንን ያለፈው ዳግማይ ትንሳኤ ስለሆነ ነው። ሰማያዊ ፓርቲ እንደ አብዛኞቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ አካባቢ እየወሰደ ስላለው አቋም ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ፣ የታሰሩ ሙስሊም እስረኞች እንዲፈቱ፣ ጠይቋል። በዚህ ሁኔታ ለሙስሊሙ ማህብረሰብ ከበሬታ መሰጠቱ ተገቢ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ለክርስትና እምነት ተከታዮችም ከበሬታ ማሳየት አልነበረበትምን?  በክርስቲያኖች ዘንድ ትልቅ አመት በዓል በሆነበት፣ በዳግማይ ትንሳኤ ቀን፣  ሰልፍ መጥራት ተገቢ ነዉን ?  ፈረንጆች እንደሚሉት «ሴንሲቲቭ» መሆን አልነበረበትምን ?  ሁሉም እምነቶች መከበር አለባቸው ባይ ነኝ። ሰማያዊ በዚህ ረገድ ትክክል አደረገ አልልም። ይሄ የመጀመሪዉ ነጥቤ ነው።

 

ሰማያዊ ፓርቲ ያነሳቸው ጉዳዮች፣ የአንድነት ፓርቲም ያነሳቸው ጉዳዮች ናቸው። የሕዝቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው። ሰማያዊና አንድነት ቢዋሃዱ ጥሩ ነበር። ግን ሰማያዊ ለብቻው መጋለብ የሚፈልግ በመሆኑ፣ ተመሳሳይ የፖለቲካ ፕሮግራም ቢኖርምም፣ መዋሃድ አልተቻለም። ነገር ግን የቀረቡ ጥያቄዎች ተመሳሳይ በሆኑበት ሁኔታ፣ ሰማያዊ የራሱን ሰልፍ፣ አንድነት ሊጠራ ባሰበበት ወቅት ለማድረግ ከሚሞክር፣ ከአንድነት ጋር ተነጋግሮ፣  ቢያንስ በጋራ ሰልፍ ቢጠራ መልካም ነበር። ለምን ያ እንዳለሆነ አለገባኝም። ሰልፍ ሲጠራ እኮ አላማ ሊኖረውና ዉጤት ሊያስመዘግብ ይገባል። እንደው ዝም ብሎ ሰልፍ ማድረግ በራሱ የትም አያደርስም። ሰልፍ የሚደረገው ትልቅ መልእክት ለማስተላለፍ ነው። ሰልፉ የተሳካ የሚሆነውም በተቻለ መጠን ብዙ ሕዝብ ሲገኝ ነው።

 

ሰልፉ በጋራ በመጠራቱ፣ እርግጥ ነው ሰማያዊ ለብቻው የተለየ ክሬድት አያስገኝለትም። አንድነትም የተለየ ክሬድት አያገኝም። ክሬድቱን የሚወስዱት በጋራ ነው የሚሆነው። ያ ደግሞ ችግር አለው ብዬ አላስብም። ለሕዝብ የሚያስብ ድርጅት፣  «ድርጅቴ ብቻ ለምን አልተጠቀመም ?» የሚለውን ሳይሆን «ሕዝብን ይጠቅማል ወይ ?» የሚለዉን ጥያቄ ነው የሚያቀርበው። ከድርጅት በላይ የአገርን ጥቅም ያስቀድማል። በዚህ ረገድ ሰማያዊ መጠይቅ አለበት። ይሄ ሁለተኛ ነጥቤ ነው።

 

ሌላው ያስገረምኝ ነገር ቢኖር፣ ሶስተኛ ነጥቤ የማደርገው፣ የአንድነት ፓርቲ በባህር ዳር ሲያደርግ በነበረ ጊዜ፣ ማለት  ሁለት ወራት ገደማ በፊት፣ ለምን ሰማያዊ  በአዲስ አበባ ሰልፍ እንዳልጠራ ነው። ወይንም ደግሞ አንድነት በአዋሳ፣ ድረደዋ በመሳሰሉት ከተሞች ወደፊት ሰልፎች ለማድረግ ባሰበበት ወቅት፣ በአዲስ አበባ ሌላ ሰልፍ ስለማይኖር፣ ያኔ ለምን ሰልፍ እንደማይጠራ ነው።  ለምን ቢያንስ ፣ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተላበሰ፣ ፕሮፌሽናል፣ አክብሮት፣ ለአንድነት ፓርቲ አሳይም ? ለምን አንድነት ሊያደርግ ባሰበበት ወቅት  ሰልፍ ይጠራል ? ባልጠፋ ጊዜ ለምን በዚህ ወቅት ሰማያዊ ጣልቃ ይገባል ? ይህ በአንድነት ፓርቲ ላይ፣ በአገር ዉስጥም ሆነ በአገር ዉጭ ባሉ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ንቀት እንዳላቸው አያሳይምን ? «ሰማያዊዎች የሚታገሉት አገዛዙን ሳይሆን አንድነትን ነው» የሚል ስሜትስ ሰዎች ቢኖራቸው ያስገርማልን ?

 

እንግዲህ ለማጠቃለል ይሄን እላለሁ። ሰማያዊዎች በዚህ ረገድ ትልቅ ስህተት እየሰሩ በመሆናቸው ልብ ይገዙና ቆም ብለው ያስቡ ዘንድ እመክራለሁ። እላለሁ። የአንድነት ፓርቲ ትልቅ መሰረትና ድጋፍ ያለው ድርጅት ነው። አንድነትን ለመደፍጠጥ አስብው ከሆነ፣ የራሳቸው እግር ላይ እንደሚተኩሱ ማወቅ አለባቸው። የአንድነት ፓርቲ የሚያራምደው የሰለጠነ ፖለቲካ የማይመቻቸው፣ «የአገርን ችግር ለመፍታት፣ አንድነት ከኢሕአዴግ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ» ማለቱ ያበሳጫቸው፣  በዉጭ ያሉ ጥቂት ጽኝፈኞችና አክራሪዎች ፣ አንድነት ፓርቲ ተዳክሞ፣  ሰማያዊ ፓርቲ አይሎ እንዲወጣ ከመፈለጋቸው የተነሳ፣ ሆይ ሆይ ፣ እንደሚሏቸው ይገባኛል። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ አገራችን የምትፈልገው እንዲሁ በስሜት የመጋለብ ፖለቲካን ሳይሆን፣ ሕዝቡን በአራቱም ማእዘናት የሚያደራጁ፣ ብስለትና እርጋታ የተሞሉ አመራሮች ያሏቸው፣ በሚስማሙባቸው ጉዳዮች አብሮ ለመስራት የተዘጋጁ፣ የሚከባበሩና የሚቻቻሉ ድርጅቶችን ነው። የጀብደኝነት ፖለቲካን ሕዝቡ አይፈልግም። «እኔ ብቻ ነኝ የማወቀዉ» የሚል ግትር ፖለቲካ ቦታ አይኖረዉም።

 

 

ህወሓት ይቅርታ እየጠየቀ ነው!

0
0

Abrha Destaህወሓቶች ከትግራይ አከባቢዎች ባሰባሰቡት መረጃ መሰረት የትግራይን ህዝብ ልብ ሸፍቷል፤ የህወሓት የስልጣን ዕድሜ ከአንድ ዓመት እንደማያልፍ ታውቋል። አሁን ህወሓት በምንም ምክንያት የትግራይን ህዝብ ድጋፍ ማግኘት ስለማይችል ያለው ብቸኛ አማራጭ ለትግራይ ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ ነው። የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት እነ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሓየ፣ ስዩም መስፍን፣ ፀጋይ በርሀና ሌሎች በህወሓት ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ በትግራይ ገጠር ወረዳዎች እየተዘዋወሩ በአርሶአደሩና ወጣቱ ላይ ለፈፀሙት በደል በግልፅ ቋንቋ ይቅርታ እየጠየቁ ነው። ይቅርታ መጠየቅ ጥሩ ነው። ግን ምነው ከረፈደ? በህወሓቶች የዐዞ እንባ የሚሸወድ ወጣት ካለ እስቲ እናያለን። ለማንኛውም ትዕቢተኞቹ ህወሓቶች ለይቅርታ የተዳረጉ ባሰማነው (ባጋለጥነው) ተቃውሞ ነው። በትግራይ የሚደርስ ዓፈና ላጋለጣችሁ ሁሉ ምስጋናየ ተቀበሉ

አንቀላፍቶ የነበረውን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ያነቃቃው የብዙአየሁ ደምሴ “ሳላይሽ”አልበም

0
0

Bizuayehu Dimesse – Bewalashebet [New Single]በተስፋሁን ብርሃኑ

አሁን አሁን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ጉዞ እጅግ እየቀዘቀዘና እድገቱ እምብዛም የማይታይበት እየሆነ የመጣ እንደሆነ በርካታ ነባር ድምፃውያን፣የግጥምና ዜማ ደራሲዎችና የሙዚቃ አፍቃሪያን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

ምክንያታቸው ደግሞ የሁሉም ማለት ይቻላል ሙዚቃ ሳትጠራቸው ወቅቱና ገንዘቡን ብቻ ያገኙ በርካታ ወጣቶች ወደሙዚቃው በመግባታቸውና ለግጥሙና ዜማው እምብዛም የማይጨነቁ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው መታየት የሚፈልጉ በብዛት መምጣታቸው የሙዚቃውን እድገት ቁልቁል ያስኬደው ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በሁለተኛ ደረጃ ያስቀመጡት ምክንያት የኮፒ ራይት ጥሰት ሲሆን ነባርና የብዙ የሙዚቃ አፍቃሪያን ቀልብን ገዝተው የዘለቁ ድምፃውያን ካሴቶቻቸውን ቶሎ ቶሎ ባለማውጣታቸውና አንዳንዶቹም ከነአካቴው ከሙዚቃው በመራቃቸው የሙዚቃ እድገቱን አስተጓጉሎታል ይላሉ፡፡

አዳዲስና ወጣት ድምፃውያን በብዛት እየመጡ ነው፡፡ አብዛኞቹ ታዲያ የነባር ድምፃውያንን ሙዚቃ ዳግሞ በመጫወት ድምፃቸውን እያሟሹ ዘፋኞች ለመሆን በቅተዋል፡፡ ምን ያህልም እንደተሳካላቸው ፍርዱን ለሙዚቃው አፍቃሪ እንተዋለን፡፡

ከነዚህ የነባር ድምፃውያን ሙዚቃዎች ተጫውተው ከተሳካላቸው ድምፃውያን መካከል አንዱ ብዙአየሁ ደምሴ አንዱ ነው ብንል ማጋነን አይሆንብንም ምክንያቱም ከአራት ዓመታት በፊት የታዋቂውን ድምፃዊ ሙሉቀን መለሰን ዘፈኖች ሙሉ ካሴት በመስራት የሙዚቃ አፍቃሪያንን አስደምሟልና ነው፡፡ በዚህ አልበሙ አብዛኛው የሙዚቃ አፍቃሪ ከሙሉቀን ያልተናነሰ ብቃት እንዳለው መስክረው ለታል፡፡ ምንም እንኳ “አስፈቅጃለሁ” “አላስፈቀደኝም” በሚል ያለመግባባት በሁለቱ ድምፃውያን መካከል ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም በኋላም በሰይፉ ፋንታሁን አማካኝነት ሊታረቁ ንደቻሉ ሰምተናል፡፡ በዚህ ካሴቱ በርካታ ነባርና አዳዲስ ድምፃውያን አድናቆትን ችረውታል፡፡ ትንሽ ዝምድና ከድምፃዊው ጋር ያለው ቴዲ አፍሮ ሳይቀር ምስክርነቱን የሰጠበት አጋጣሚ ነበር፡፡

ከሁለት ወራት በፊት ዜማ አማን በተባለ ከበርካታ ድምፃውያን ጋር በአማኑኤል ይልማ የተዘጋጀው ካሴት ላይ ባወጣቸው ሁለት ዘፈኖች በርካታ አድናቆትን ተችሮት ነበር፡፡ ከአንድ ወር በፊት የራሱን ሁለተኛ ካሴት “ሳላይሽ” በሚል መጠሪያ በናሆም ሪከርድስ አማካኝነት ከሚኖርበት ካናዳ አድናቂዎቹ አበርክቷል፡፡ በዚህም የራሱን የአዘፋፈን ስልት እንዲሁም ከአንድ የሙሉቀን መለሰ ዘፈን በስተቀር ሁሉም አዲስ ግጥምና ዜማ በማቅረቡ እጅግ ተወዶለታል፡፡ ካሴቱም በወጣ በአጭር ቀናት በብዙ ሺህ ኮፒዎች እንደተሸጡለት ተነግሯል፡፡

አሁንም በበርካታ መዝናኛ ስፍራዎችና በተለያዩ ቦታዎች የዚህን ድምፃዊ ሙዚቃዎች መደመጥን ቀጥለውበታል፡፡ በዚህም እጅግ እንደተሳካለት መመስከር ይቻላል፡፡ ብዙአየሁ ደምሴ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን ከአንድ ዓመት በላይ በካናዳ እየኖረ ይገኛል፡፡ ከመላው ዓለም የኮንሰርት ጥሪ እየቀረበለት ያለው ወጣቱ ድምፃዊ ምናልባትም ከፋሲካ በኋላ ጥሪውን ተቀብሎ ኮንሰርቶችን ሊያቀርብ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ የነባር ድምፃዊያንን ሙዚቃ በመጫወት በርካታ ድምፃውያን የራሳቸውን ችሎታ ሳያሳዩ ተውጠው የቀሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ነገር ግን ብዙዓየሁ ደምሴ በመጀመሪያ አልበሙ ተጠቅሞበት የነበረውን ሙሉቀን መለሰን በመተው በራሱ የአዘፋፈን ስታይል ጥሩ ካሴት ለአድማጩ አበርክቷል፡፡ ይህም ወጣቱን በእጅጉ ያስመሰግነዋል፡፡ በዚህ በያዝነው 2ዐዐ6 ዓ.ም ከሸዋንዳኝ ኃይሉ ካሴት በኋላ የአድማጭን ቀልብ ገዝቶ እስከ አሁን የቆየውና በእጅጉ እየተደመጠ ያለው “ሳላይሽ” የብዙዓየሁ ደምሴ ካሴት ነው በዚህም አንቀላፍቶ የነበረውን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ጉዞ መነቃቃትን
ፈጥሮለታል ለማለት ይቻላል፡፡ ብራቮ ብዙዓየሁ!!

ዘ-ሐበሻ በኪነጥበብ ዙሪያ የሚሰጡ አስተያየቶችን ለማስተናገድ ሁሌም ዝግጁናትና ይሳተፉ።

የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ

0
0

-ፍርድ ቤት ቀርበው ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል

አቶ ጥዑም ተኪዔ

አቶ ጥዑም ተኪዔ

የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡርን ላለፉት በርካታ ዓመታት በዋና ሥራ አስኪያጅነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ጥዑም ተኪዔ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከሚያዝያ 2 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታወቀ፡፡

በሥራ ምክንያት ወደ ድሬዳዋ መሄዳቸው የተገለጸው አቶ ጥዑም፣ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ሥር የዋሉት ባረፉበት ሆቴል መሆኑን የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ለአቶ ጥዑም በቁጥጥር ሥር መዋል ዋናው ምክንያት በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘው የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ስፖርተኞች (ሠራተኞች) ክበብ ጋር የተገናኘ ሳይሆን እንደማይቀር ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡ ላለፉት ዓመታት ክበቡን በኮንትራት ይዘውት የነበሩ ግለሰብ የኮንትራት ጊዜያቸው በሰኔ ወር 2006 ዓ.ም. የሚያበቃ ስለሆነ፣ ኮንትራት እንዲያራዝሙላቸው ዋና ሥራ አስኪያጁን ሲለማመጡ እንደነበር ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡

አቶ ጥዑም ያረፉበት ሆቴል እንዲፈተሽ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፀረ ሙስና መርማሪ ፖሊስ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ አውጥቶ ሲፈትሽ፣ ክበቡን በኮንትራት የያዙት ግለሰብ ለመርማሪ ፖሊሶች ያስመዘገቡት 2000 ብር በመገኘቱ፣ አቶ ጥዑም በቁጥጥር ሥር ሊውሉ መቻላቸውን አስረድተዋል፡፡

አቶ ጥዑም ሚያዝያ 5 ቀን 2,006 ዓ.ም. ድሬዳዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸው፣ በድጋሚ ሚያዝያ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. መቅረባቸው ታውቋል፡፡ ፖሊስ ምርምራ እንደሚቀረው ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት ተጨማሪ የ14 ቀናት ጊዜ ጠይቆ እንደተፈቀደለትና ለሚያዝያ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱም ታውቋል፡፡ አቶ ጥዑም የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የሚከለክል በመሆኑ የዋስትና መብታቸው መታለፉም ተገልጿል፡፡

 

ምንጭ ሪፖርተር ጋዜጣ


ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 8 –ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ይዛ ቀርባለች

0
0

NE8በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ በፒዲ ኤፍ ለቀናታል፡፡
- ፕሮፈሰር አለማየሁ፣ ታምራት ታረቀኝ፣ ግርማ ሞገስና ታዲዮስ ታንቱ ጥልቅ ትንታኔዎችን ሰጥተውባታል፡፡
- የተማሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ ማቆም አድማ፣ የአርሶ አደሮች ሰቆቃና ሌሎችም አዲስ ወሬዎች ተካተውባታል፡፡
- በላይ ማናዬ የብሄርፌደራሊዝሙን ቅዝምዝሞሽ ይተነትንልናል፡፡
- ዮናታን ተስፋየ ለምን ፈራን ይለናል፡፡
- እያስፔድ ተስፋዬ የስርዓቱን ሰለባዎች (ከማሞ መዘምር እስከበቀለ ገርባ ዳስሷል፼፡፡ -
- ጌታቸው ሺፈራው ኢህአዴግ ምንም እንደማያሟላ ይሞግታል፡፡
- ብርሃኑ ተክለ ያሬድ የእስር ቤት ትዝታውን አቅርቦባታል፡፡ ወጣቱ አቃቤ ህግ የፍትህ ስርዓቱ ፍትህ ያስፈልገዋል ብሏል፡፡
- የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ስራ አስኪሃጅ በደሎች ተዘርዝረውበታል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 8 ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

 

ሰማያዊ በፌደራል መንግስቱና በቡለን ወረዳ የመሰረተው ክስ ሀሙስ ፍርድ ቤት ይቀርባል!

0
0
ethiopia-blue-party-300x164ሰማያዊ ፓርቲ በቤንሻንጉል ጉምዝ በህገ ወጥ መንገድ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ወደ ቦታቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱና ተገቢው ካሳ እንዲከፈላቸው በተደጋጋሚ ባካሄዳቸው ሰላማዊ ሰልፎችና ባወጣቸው መግለጫዎች የጠየቀ ሲሆን መንግስት ለጥያቄው ምላሽ ባለመስጠቱ ዜጎቹ የተፈናቀሉበትን ቡለን ወረዳና የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ላይ ክስ መስርቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ክሱን ታዋቂው የዓለም አቀፍ የህግ ባለሙያ ዶክተር ያእቆብ ኃይለ ማሪያም ይዘውት የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ቢሮክራሲያዊ ምክንያቶች መዝገብ ሳይከፈትለት እንደቆየ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ ሰማያዊ ፓርቲ ባደረገው ተደጋጋሚ ግፊት ክሱ በአሁኑ ወቅት መዝገብ ተከፍቶለት፣ የዳኝነት ክፍያ ተከፍሎ በቀጣይ ሀሙስ ሚያዝያ 9/2006ዓ/ም ክሱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስምንተኛ ፍትሃብሄር ችሎት ላይ መታየት እንደሚጀምር ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
‹‹ሰማያዊ ፓርቲ በጉዳዩ ላይ አቋም ወስዶበት ከሰላማዊ ሰልፉም ባሻገር ዜጎቹ ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱና ካሳ እንዲሰጣቸው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ እስካሁንም ድረስ በዜጎች ላይ በሚደርሰው ችግር ከጎናቸው ሆኖ የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡›› ያሉት አቶ ብርሃኑ ፓርቲው ኢትዮጵያውያኑ በመፈናቀሉ ሂደት በደረሰባቸው ችግር ልጆቻቸው የታመሙባቸውን ለህክምና እንዲሁም ለመጓጓዣም ፓርቲው እገዛ ሲያደርግ መቆየቱንና አሁንም ዜጎቹ ፍትህ እስኪያገኙ ድረስ ከጎናቸው እንደሚሆኑ አሳውቀዋል፡፡
በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸው ትክክል ነው ወይ ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ ‹‹አሁንም ማፈናቀሉ ቀጥሏል፡፡ አሁንም ዜጎች እየተፈናቀሉ ስለመሆኑ በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡ አሁንም ሰልፉን የጠራንበት ምክንያት ይህ የማፈናቀል ህገወጥ ድርጊት ባለመቆሙ ነው፡፡ እኛ እየከሰስን ያለነው ባለፈው የመፈናቀል ህገወጥ ተግባር በተፈጸመባቸው ላይ ነው፡፡ የቡለን ወረዳ ቀኑን ጠቅሶ ‹‹ስለምትፈናቀሉ ልቀቁ!›› ያለበትን ማስታወቂያና ማስጠንቀቂያዎች በመረጃነት ይዘናል፡፡ ይህ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ጥያቄ ማንሳት ደግሞ ዋነኛው ስራችን ነው፡፡›› ብለዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም ‹‹አሁን ይህ ድርጊት ከወረዳና ከክልሎች አልፎ የመንግስት ፖሊሲ ወደመሆን በመሸጋገሩ በተደራጀና ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ መታገል አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡›› ብለዋል፡፡ የሰልፉ አላማም በኢህአዴግ የፖሊሲ ችግር ላይ መሆኑን የገለጹት የህዝብ ግንኙነቱ ‹‹ኢህአዴግ መሬት የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ንብረት ነው፡፡›› በሚል ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ተዘዋውረው የመስራትና የመኖር መብታቸውን ስለገደበና በዚህ የተሳሳተ ፖሊሲ ኢትዮጵያ እንደ አገር ትልቅ ችግር እየገጠማት በመሆኑ ችግሩ ከሚደርስባቸው ዜጎች ጎን በመሆንና ሌላውን ህዝብ በማንቀሳቀስ ኢህአዴግ ሃገር የማስተዳደር አቅምም ሆነ ችሎታ እንደሌለው በማጋለጥ ስልጣኑን እንዲለቅ ግፊት ለማድረግ እንደሆነ አቶ ብርሃኑ ለነገረ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል፡፡ የክሱን ሂደትም ሚዲያውያና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲከታተሉት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Source: Negere Ethiopia

ጓዶች በአፅቢ ከተማ አራት የዓረና አመራር አባላት ከያዙት አልጋ እንዲለቁ ተጠይቀው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ታስረው አደሩ

0
0

Abrha Destaጓዶች በአፅቢ ከተማ አራት የዓረና አመራር አባላት ከያዙት አልጋ እንዲለቁለት ጠይቆ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ፖሊስ ጠርቶ ያሳሰራቸው የፌደራል መንግስት ባለስልጣን አቶ ተፈራ ደርበው (የግብርና ሚኒስተር) ነው። የፌደራል ባለስልጣን ሊይዘው የሚገባ አልጋ ይዛችኋል ተብለው ነበር ታስረው ያደሩ። ከአፅቢ የዓረና ስብሰባ በኋላ በአባይ ፀሓየና ስብሃት ነጋ የሚመራ የፌደራል መንግስት ልኡኳን የአፅቢን ህዝብ ችግር ለመፍታት (ወይ ለማባባስ) ተልከዋል። መሬት የህዝብ ይሆናል፣ ብድር በነፃ ነው ወዘተ እያሉ ዓረና ሲያስተምረው የነበረውን ሲሰብኩ ሰንብተዋል። ዛሬ ሰኞ መጋቢት 06, 2006 ዓም ደግሞ አስራአለቃ ስንታየሁ ይመር የተባሉ የዓረና አባል “ዓረና” የሚል ፅሑፍ ያለው ቲ-ሽርት በመልበሳቸው ምክንያት በፖሊስ ታስረው ከሰዓታት በኋላ ተለቀዋል

 

የአንበጣ መንጋ በሶማሌ፣ በኦሮሚያና በድሬደዋ ባሉ 13 ወረዳዎች ስጋት ሆኗል

0
0

news(ዘ-ሐበሻ) የአንበጣ መንጋ በሶማሊያ፣ በኦሮሚያና በድሬደዋ ባሉ 13 ወረዳዎች ስጋት ሆኗል ሲል የኢትዮጵያ የግብርና ሚኒስቴር በመንግስታዊ ሚዲያዎች በኩል አስታወቀ። እንደ መግለጫው ከሆነ የአንበጣው መንጋ በቅድሚያ የታየው በሶማሊያ ክልል ቶጎ ጫሌ አካባቢ ቢሆንም ወደ ሌሎች ክልሎችም እየተዛመተ መጥቷል።

የአንበጣ መንጋው ከሶማሊላንድ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ሲሆን በሶማሌ፣ በኦሮሚያና በድሬደዋ አስተዳደር ባሉ ወረዳዎች 14 የሚሆኑ የአንበሳ መንጋዎች መግባታቸውን አረጋግጫለሁ ሲል የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤትቱ “የአንበጣ መንጋውን 95 በመቶ መከላከል ችያለሁ፤ በሰብል ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰም” ቢልም የአካባቢው ነዋሪዎች ግን መንግስት አፋጣኝ እርምጃ አልወሰደም በሚል ይወቅሳሉ። የአንበጣ መንጋው ወደ ሌሎች ከተሞች እንዳይዛመትም ከፍተኛ ስጋት አለ ተብሏል።

የሁለት መቶ ሁለት ነፍስ የታደገ ማስተዋል –ማህበራዊ ኑሮንም ያዳመጠ ብልህነት። (ከሥርጉተ ሥላሴ)

0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 17.04.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
«ማስተዋልን ገንዘቡ የሚያደርግ፣ በወርቅና በብር ከመነገድ ይልቅ በእርሷ መነገድ ይሻላልና። ከቀይ ዕንቁም ትከብራላች፤ የተከበረም ነገር ሁሉ አይተካከላትም። በቀኛዋ ረጅም ዘመን ነው፣ በግራዋም ባለጠጋነትና ክብር። እርስዋን ለሚይዟት የሕይወት ዛፍ ናት። የተመረኮዘባት ሁሉም ምስጉን ነው። እግዚአብሄር በጥበብ ምድርን መሠረተ በማስተዋልም አጸና። ምሳሌ ም.3 ቁ. 13 እስከ 19 »

PLTበቅድሚያ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አምንያን እንኳን ለ2006 ፀሎተ ሃሙስ አደረሳችሁ – አደረሰን። ልክ የዛሬ ሁለት ወር በዚህች ዕለት የሰማይ ታምር በማስተዋል ተገለጠ። ዓለምም ታደመ – በአጽህኖት በአንክሮ ተደመመ። የወያኔ ገዢ መሬትም ተደፈረ – በጎጥ የጎረና የዘበጠ አስተዳደሩም አፈረ – ተመዘነ።

ማስተዋል የሰማይ ጸጋ ነው። ማስተዋልን እግዚአብሄር አምላክ መርቆ ሲሰጠን እንድናስተውለው ነው። ማስተዋል „ማስተዋልን“ አብክሮ የሚጠይቅ መክሊትና ክህሎት ነው። ክህሎት ነው ያልኩበት ምክንያት ሰው በዕድሜው ተመክሮ ያገኛቸው ትምርቶች ተግባሩን መካሪ እንዲሆኑ መፍቀዱ ብቻ ሳይሆን፤ ከዕድሜ ጋርም በርካታ ባህሪያት እዬሰከኑ ስለሚሄዱ ማስተዋል የበለጠ እያማረበት እዬተዋበ ይሄዳል ለማለት ነው። ማስተዋልን የሰነቀ ግለሰብ፣ ድርጅት ወድቆ አይወድቅም፤ ጉዞው ሁሉ መጪ ነገሮችን አስቀድሞ ዬሚይበት መሳሪያ በመንፈሱ ስላለው የተግባሩ ትልም ሆነ መቋጫው አቅም ያለው እርግጠኝነትን የጠጣ ይሆናል። የፈለገ ዓይነት ያልተጠበቀ ሁኔታ ቢመጣም ይቋቋመዋል። ማስተዋል እኛ እንደምናስበው ለተለዩ ፍጥረቶች አምላካችን የሸለማቸው ሳይሆን ሁላችንም ያለን ሀብት ሆኖ፤ ግን ያላዬነው መሪ ሥነ – ምግባር ነው። ማስተዋልን „የማስተዋል“ የመቻል አቅም ግን ተለይቶ መቀባት ይመሰለኛል።

በማስተዋል የተመራ „ሰላማዊ እንቢተኝነት“ ካዬን ልክ ዛሬ ሁለት ወራችን ነው። „ሰላማዊ እንቢተኝነት“ ከባሩድ በስተቀር በማናቸውም በእጅ በገባ አምክንዮ ሊከወን ይችላል። ክወናው መስዋእትነቱን ሊያቀለው ወይንም ሊያከብደው ይችላል። የጀግናዬ የረ/ አውሮፕላን አብራሪ ኃይለመድህን ወይንም እንደ ሲዊዞቹ ረ/ አውሮፕላን አብራሪ አበራ ኃይለመድህን የማስተዋል ልክ መለካት ያለበተ እጅግ በዳበረ ማስተዋል የተከወነ መሆኑ ነው። ካለምንም ንብረት ውድመትና ካለምንም ህይወት ጥፋት ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ጫና ሳይፈበረክ የተከወነ ጉልበታም ደፋር „የሰላማዊ እንቢተኝነት“ አብነት ነው። የታሪኩ ሂደት ልብ አንጠልጣይ ከመሆኑ ጋር ይህን ተከትሎ በአለማችን በጉልህ የቀጠሉ ተግባራትን ስንመለከት እውነትም እርምጃውና ጥበቃው የአምላካችን የመዳህኒተአለም ስለመሆኑ እንገነዘባለን። 202 ነፍስን በማስተዋል የታደገው ይህ ድንቅ ተግባር ዘመናትን ሊያሻግር የሚችል የብቃት ልቅም – ልቅናም ነው።

ከዬካቲቱ የብልሁ „ሰላማዊ እንቢተኝነት“ በኋላ በአውረፕላን ዙሪያ  ሰማይ ላይ ሆነ የብስ ላይ የተከሰቱ ተግባራት  የእሱን የማስተዋል ብቃት እኛ ካለን የማስተዋል ሃብት ጋር ፍተሻ እንድናደርግበት በሚገባ ያስተምራል። በተጨማሪም ዓለም በሁለት ረዳት አውሮፕላን አብራሪዎች መሃከል ያለውን ብቃትና የብልህነት ደረጃ እንዲገመግም በራሱ ጊዜ በፈቃደ እግዚአብሄር አቅም እዬተለካ ነው። እኔን ስትሞግተኝ የነበረች ባልደረባዬ „ አበራ ሊደነቅ ይገባል“ አለችኝ። ለነገሩ ለእሷም ማስተዋሉ ተገልጦላት።

 

ሀ. የጀግናዬን ማስተዋል የበለጠ የሚያብራራ፤ የሚያበለጽግ አጋዢ ሰሞንተኛ የሰማይና የምድር „እንቢተኝነት“

 

  1. ወርኃ መጋቢት —- እኔ እንደማስበው ረዳት አውሮፕላን አብራሪ ኃይለመድህን አበራ „ማስተዋሉ“ ያሰቀረውን ዓለም አቀፍ እንግልት፣ ጥፋት፤ የመንፈስ ጭንቀት፤ የማህበራዊ ኑሮ ቀውስ፤ የፖለቲካ ትርምስ ማስተዋልን አለብን ባይ ነኝ። እኛ ብቻ አይደለም እያንዳንዱ ሰው ዓለም ዓቀፍ ድርጅትም። እኔ አስቀድሜ በጻፍኳቸው ጹሑፎች አንድ ነገር ተማጽኜ ነበር። „በአዎንታዊ“ እንድንመለከተው …. ይሄው የማላዥያ አውሮፕላን 26 ሀገሮች ቀንና ሌት  በአውስትራልያ በፐርዝ ውቅያኖስ ማሰኑ … ስንት ገንዘብ? ስንት ነርብ? ስንት ሴል? ስንት ጊዜ? ስንት ዕንባ ፈሰሰበት? ስንት ቤተሰብ ተበተነበት? ሳይንስን ያሸነፈ ጥረት ባተለ። እንዲሁም የቀዝቃዛው ጦርነት አካል ሆኖ ዓለምን እያመሰ ነው። ከሁሉ በላይ „ከሞቱ አሟሟቱ“ ይላል የቀደመው ብሂል፤ ዬሂደቱን ወጥ መረጃ ለመስጠት እንኳን ያላስደፈረ በመሆኑ ተሳፋሪዎች የደረሰባቸው አለመታወቁ ብቻ ሳይሆን፤ ዬታላላቅ ሳይንቲስቶች ጠበብት ሊቃናተ – ሙሁራን የትንበያ ሆነ የጥበብ አቅም ፈተነ – ገመደ።
  2. ወርኃ ሚያዚያ — ከሚዚያ መግቢያ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በጎረቤት ሀገር በጀርመን ታዋቂው የሉፍታንዛ አውሮፕላን ከቱርክ አዬር መንገድ በእጥፍ፤ ከሌሎችም የተሸለ ትርፍን የሚዝቅ ድርጅት፤ ለአብራሪዎቹ የሚከፈለው  ማህያ ጋር ሲነፃፀር አይመጥንም ሲሉ የኖሩ ኖረው በሚዚያ መግቢያ በ2014 ለተከታታይ ቀናት ሞተራቸውን ረ አድርገው ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። ሉፍታንዛ ተጓዡን ሲያዘገይ እንኳን ድጎማ የሚያደርግ ሲሆን፤ ያ … ሁሉ በረራ ተጓጉሎ ቀጥ በማለቱ የጀርመን መንግሥት ስንት መዋለ ንዋይ ከሰረ?  ስንት ቀጠሮ ተሰረዘ? የሚችሉ ወደ ፈረንሳይ፣ ወደ ኦስትራሽ ፣ ወደ ሲዊዝ በመሄድ ተጨማሪ ጊዜና ገንዘብ አፈሰሱ። ይህ „የሰላማዊ እንቢተኝነት“ በዚህ መልክ የተካሄደው ጀርመን ተቃውሞን ለማሰማት ዴሞክራሲ ያለበት ሀገር ስለሆነ ነው። የእኛ ግን ሃሳቡን ማሰብ እንኳን አይቻልም፤ እንኳንስ እንዲህ ለተከታታይ ቀናት አውሮፕላን አቁሞ አመጽ ማካሄድ ቀርቶ። አግባብነት ያለው ጥያቄ በግል ለማቅረብ እንኳን ጋዳ ነው። ከዚህ አንጻር ፈቃደ እግዚብሄር በሁሉም አቅጣጫ ሰማይ ላይ ሆነ ምድር ላይ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥ ነገሮችን እዬፈጠረ ወጣቱ ፓይለት የወሰደውን  ውሳኔ፣ የማስተዋልና የብልህነት ብቃት በአዎንታዊነት እያበሰለው ይገኛል። ትርፍ!

 

ለ. የወያኔ መደፈር እልህና ቁጣ ተከታይ እርምጃ።

ይህን በሚመለከት ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ የተበራራ ቀዳሚ የማሳሰቢያ ጭብጥ አቅርቧል። ስለምን በሚስጢር ተያዘ ለሚለው እኔ እንደማስበው ከሆነ —

  1. የሲዊዝ መንግሥት ተጠይቆ አዎንታዊ መልስ እስኪሰጥ ድረስ መጠበቅ ግድ ይል ነበር። ፍርዱን ሊያከብድ የሚችል የወንጀል ክስ አስቀድሞ ወያኔ ቢያሳውቅ፤  የሲዊዝ መንግሥት „አሻም“ ሊል ስለሚችል፤ ምንም ያልተፈጠረ አድርጎ አለሳልሶ ለመስለብ ነበር የጫካው ተመክሮ – የመከረው። ግን ይህ አልተሳካም።
  2. ድርጊቱ ሲከወን በጓዳ ስላልነበር የክሱ መሰረት ተምታቶም ይሁን ቅጥፈት ተሸምቶ መቀነባበር ነበረበት። ለዚህም ወያኔ በቂ ጊዜ ያስፈልገው ነበር። ልክ ሄሮድስ መለስ ሲሞቱ እንደ ተሰራው ድንባስ ትእይንት ቀድሞ መዘጋጀት አለበት ወያኔ ገርድፎ ይሁን ሸርክቶ።
  3. የጀግናው የኃይለመድህን ተግባር ወያኔ ባላለመው፤ ባላሰበው፤ እጅግም ባልገመተው ነበር። ጥቃቱን ያደረሰበትን የመንፈስ ትርትርና ትርምስ መልሶ ለመቋቋም ገዢው ፓርቲ ወያኔ  አቅሙ አልነበረውም። ስለሆነም ወያኔ ትንፋሽ መሰብሰብ ነበረበት። የሚርገበገብ መንፈሱ ተግ ማለት ነበረበት። ደፋር እርምጃ ያስታጠቀውን መንፈሳዊ ቁስለት ለማገገም ጊዜ ማግኘት ለወያኔ በእጅጉ ያስፈልገው ነበር። አዬር ላይ የተወሰደው እርምጃ እንዲህ በግልብ፤ በግብታዊነት የተከወነ አልነበረምና። ሲዊዝ ከገባ በኋላ እንኳን ፎቶውን ለማግኘት አልተቻለም። ስለዚህ ይህን ለመሞገት ልጥፍና ዝግ መሳናዶ አስፈለገው – ወያኔ።

አስተዋዩ አውሮፕላን አብራሪ አበራ ሀይለመድህን መነሻውን፤ መድረሻውን ያወቀ፤ መሬት ላይ የሚጠብቀውን ማናቸውንም ነገሮች ሁሉ ጠንቅቆ የተረዳ። ወቅት የሰጠውን ዕድልም ያላሾለከ የማስተዋል ፍሬ ነው። ክንውኖቹ ሁሉ የማስተዋል ማህጸነ – ሚስጢር ናቸው።

 

ሐ. ለቤተሰቦቹ እኔ እምለው።

ውጬ ሀገር የሚኖሩ የፖለቲካ መሪዎች፤ ጋዜጠኞች፤ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቾች ሁሉ አስከ 18 ዓመት እስር፤ የእድሜ ልክ እስር፤ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው አሉ። ይህ ወያኔ አቅሙን አለማዋቁን ነው የሚመለከተው እንጂ የሚያመጣው አንዳችም ነገር የለም። ስለዚህ የፈለገውን አይነት ክስ ወያኔ መስርቶ የሚፈልገውን አይነት ውሳኔ ቢሰጥ ወገኖቼ ቅጭጭ አይበላችሁ። ማስተዋልን ወልዳችሁ አሳደጋችሁ። ማስተዋሉ የሸለመው ደህንነት አለና አትስጉ – ለደቂቃ አደራ! ሲዊዝ እንደተፈለገ ተገብቶ የሚዛቅ ምንም ነገር የለም።

ይልቅ አራዊት ስለሆነ ወያኔ ለእናንተ ለራሳችሁ ጥንቃቄ አድርጉ። ጥቃት ሊሰነዝርባቸው የሚችሉ እጅግ በርካታ መስኮች አሉት። ግንኙነትን መወሰን፤ ከተገኘው ቤት አለመመገብ፤ የተገኘውን ሥጦታ አለመቀበል። በፖስታ የሚላኩ ነገሮችን ሁሉ በጥንቃቄ ማዬት ይገባል። በተረፈ „በማስተዋል“ ላይ የወያኔ ማናቸውም ዓይነት ፍርድ ሊያደርስ የሚችለው ምንም ነገር የለም። ከተጀመረ ጀምሮ ያለው የሂደቱ ጠረን ምላሽ ሆነ አዬሩም፤ እንዲሁም አካባቢውም፤ ተያያዥ ነገሮችም እርምጃውን – ውሳኔውን – ማስተዋሉን እንደ ታቦት የሚከበክቡ ናቸው።

አዬር ላይ ሳይቀር የጣሊያንና የፈረንሳይ አውሮፕላኖች እኮ አጀበውታል። ይህ በሰው ሃይል የተከወነ አይደለም። በሳምንቱ እትብቱ በተቀበረበት የተከናወነው ድንቁ የባህርዳሩ የመኢህድና የአንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ቀድሞ የተሰናዳ ግን የጄኔቡን ድል ያጀበ ነበር። በጣም ዕንቁ መረጃ ነበር። ከዚህ ሰልፍ በኋላ የሁለቱ ፓርቲዎች ሁኔታስ …? ይህም ሌላ ታምር ይነግረናል። ዙሪያ ገባው በአባታችን በመዳህኒአለም ጥበቃ የሚደረግበት ክንውን ሰለሆነ ጉዳዩን ለፈጣሪ መስጠት ነው። የእውነት ወላጆቹም ቅኖች ናችሁ። እንደገና በማህበራዊ ህይወትን ያቆሰለ ቋሳ አልተከለም። አንድ ነፍስ አልጠፋም። ደም አላጋባም። የማህበራዊ ኑሮን ሥነ -ምግባር በቅጡ ያደመጠ ብልህነት- ልዕለ ምህረት።

 

መ. ባለቤት ስላልነበረው ወቅታዊው ሲዊዛዊ ዘገባው ትንሽ ልበል።

መቼም ጀግናዬ ኃይለመድህነ አበራ በጣም ያስተማረን ነገር ማስተዋልና ትርፉን ነው። ስለዚህ በእሱ ዙሪያ የሚፈሱ መረጃዎች ሁሉ እጅግ በጣም የጥንቃቄን ጥበቃ ይሻሉ። አሁን ሀገር ቤት ያለውን በማስተዋልና በጥንቃቄ መረጃውን ያቀበለን የጋዜጠኛ ተመስገን ዘገባ ዘርጋ አድርጋችሁ ስትመልከቱት „የጉዳዩን ደህንነት“ በሚገባ ጠብቆለታል። ስሜቱን ለመግለጽ እንኳን እራሱን ቀጥቶ በተረጋጋ ቀለማዊ ስክነት ነበር ዕይታውን የገለጸው። ወሸኔ ነው ማለፊያ ወንድምዬ።

ወደ ጉዳዬ ስመጣ አሁን ሲዊዝ ላይ ስላለው ሁኔታ መረጃ ያቀበለን  ዘገባ ባለቤት ቢኖረው መልካም በሆነ ነበር። ተጠያቂነት ሆነ ተመስጋኝነት ጥግ ይኖረዋል። ለማንኛውም ዘጋቢው ማን? መሆኑን ባላውቅም ሊስተካከሉ በሚገባችው ጉዳዮች ላይ ትንሽ ማለት ወደድኩኝ። ስለምን ነገም ሌላ ዘገባ ሊቀርብ ስለሚችል መስተካከል አለበት ብዬ ስለማምን። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/28770 መነሻዬ ይህ ነው።

 

በቅድሚያ ግን የተከበሩ(ችሁ) የመረጃውምንጭዘጋቢ(ዎች) አመሰግናችኋለሁ – የወያኔህልምመክሰሩን፤የወያኔህልም  ውሃበልቶትመቅረቱን፤የወያኔየበቀልቀጣይትልሙአከርካሪውእንኩትኩትማለቱን ስለነጋራችሁን ወይንም ስላበሰራችሁን እግዚአብሄር ይጠብቃችሁ። እግዚአብሄርም ይስጥልን። አሁን ወደ አስተያዬታዊ ማሳሰቪዬ።

 

1       በነገራችን ላይ ሚዲያ ላይ የሚወጣ ማናቸውም ዘገባ ባለቤት እንዲኖሩ የሚዲያ ህግ ያስገድዳል። ነገሩ የኃይልዬ ጉዳይ ሆኖ እንጂ እኔ እራሴ አላነበውም ነበር። የሆነ ሆኖ የእሱን ጉዳይ በባለቤትነት የሚከታተል ሰው ወይንም ቡድን የቆረጠ መሆን አለበት። ምንም ዓይነት ቅንጥብጣቢ ቅሬት ሊኖረው አይገባም። አቋሙ ግልጽና አንድና አንድ መሆን ይኖርበታል። ምክንያቱም በውስጡ ብዙ ነገሮች የተከተቡበት በአጽህኖት የቆረጠ ብልጹግ እርምጃ ነውና። እውነት ለመናገር የዘገባው እርእስ ነርብ ይበጥስ ነበር። „ኢህድግ“ ይህ ቃል ጀግናችን ለወሰደው ለድርጊቱም ክብር የሚመጥን አልነበረም። የተጎመደ ጉድ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ላይ ያለው ህብረ ብሄር ፓርቲ አይደለም። የአንድ ጎሳ ድርጅት ቲፒኤልኤፍ ነው። ይህ ደግሞ አለም ያወቀው ነው። ይህ ወጋ ጠቀም ያለ አገላለጽ እኔ በግሌ ፈጽሞ አይመቸኝም። ጎሰኝነት መርዝ ነው። ወያኔ ስለሆነ ሳይሆን ሌላም ጎሳም እድሉን ቢገኝ የሚያድርገውን ነው ዛሬ ወያኔ እዬፈጸመ ያለው ዕንባን የመርገጥ ተግባር። የህግ ሆነ የተፈጥሮ ጥሰት  መሰረቱ ይሄው ነው። አንድ ጎሳ ሥልጣን ከያዘ ጨቆነ ያለውን ይቀጠቅጣል፤ ተጨቆነ ያለውን ጥበቃ ያደርግለታል። አናሳዎችም ቢሆን ልክ ብዙ ቁጥር እንዳላቸው ይፈለጣሉ – ካለርህራሄ።

ይህ የሚመነጨው ደግሞ የዘር ፖሊሲዎቹ ከተነሱበት ከዞግ ማኒፌስቶው ነው። አንድ የጎሳ ድርጅት ወሳኝ የሆነውን የፖለቲካ ተቋማት በእጁ ካስገባ፤ ዜጎች በዜግነት በሐገራቸው የመኖር መብታቸው ይጠቀጠቃል። ዜግነት ዳር ደንበሩ ይጣሳል። የዜግነት መብት በግፍ ተጥቅልሎ ይጣላል፤ ዜግነት ይደፈራል። ዜግነት ዋጋው ይረክሳል – ይሰረዛል። ከዚህም ባለፈ ለዬጎሳው አጥር ተሰርቶ ግርዶሽ ይበጃል። ቅራኔውም እንዲፋፋም ሁኔታዎች ይመቻቻሉ።

ስለምን? ሥልጣን ላይ ያለው ገዢ ጎሳ ትንፋሹ ጥበቃ የሚያገኘው በዚህ ግጭት ውጤት ነውና። ሌላውን እያተራመሰ እሱ ንጹህ አዬሩን ለሽ ብሎ ይመገባል። አይደለም ሀገር ውስጥ ውጭ ሀገር ያለው የነፃነት ትግሉ ቤተሰብ በጠላታችን ላይ ተስማምተን፤ ነገር ግን ውስጥ ውስጡን ያለው መታመስ መስከን ያልቻለውም ለዚህ ነው። ይህ በግልብ ተሂዶ የሚደረስበት ሳይሆን፤ መሬት ዬያዘ የመንፈሳዊ ጥሪቶች አቅም በተጠና ሁኔታ መገንባትን ይጠይቃል። ድልዳል ያለው ተከታታይነት ያለው ተግባርን መከወን ይፈልጋል። ሳናውቀው እኛም የዚህ ኮስማና የጎሳ ፍቅር ሰለባ ስለሆን፤ እራስንም ታግሎ ማሸነፍ። የወያኔ ትልም ተጠቂ እኛ ብቻ ሳንሆን ዘመኑ እራሱ ሆኗል። አንዱን ዘለን ሌላው ላይ ስንደርስ፤ ቀጥ እንላለን። ምሳሌ በወያኔ አባገነንነት ላይ ተስማምተን ወደ ታሪክ ወይንም ወደ ሃይማኖት አሁን ደግሞ ወደ ፆታዊም እዬዘለቀ ነው ስንደርስ እራሳችን ከዋናው አስኳል ፍላጎታችን መንበር እናወርዳለን። ይህ ደግሞ ለጣሊያን የረጅም ጊዜ ትልም ላደረ ዬጎሳ ድርጅት ህይወቱና የሚፈልገውም ነው።

በጎሳ ማኒፌስቶ  የዘር አድሎ፤ የዘር ግለት፤ የዘር ፍልሰት፤ የዘር መፈናቀል፤ በዘር መጥቃት፤ የዘር የበታችነት፤ የዜግነት ዋጋ ዕጦት መታዬታቸው ግድ ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ እዬታመሰችበት ያለው ይህ ነው። ወያኔ ይህን ማራገቢያ ይዞ ያፋፍመዋል። የደጋፊዎችም መደበኛ ተግባር ይኽው ነው። ስለዚህ የመሰረታዊ ችግራችን ምንጩ አናቱ ጉዳይ የጎሳ አስተዳደር ዘረኛ ፋሽስታዊነት ወይንም ሌሎችን በኃይል መጫን ማድቀቅ ነው። (Diskrimnation + rascism = TPLF) ስለዚህ የጀግና ኃይለመድህን ጉዳይ የሚታዬውም ከዚህ አንጸር ነው። «ረዳትፓይለትሃይለመድህንአበራንለማስመለስየኢህአዴግልኡካንበጄኔቫ» ብሎ ርእስ መስጠት አያስኬድም የተዘጋ – የታነቀ መንገድ ነው፣ ለጉዳዩ ፍትህ አሰጣጥ። ለነጻነት ትግሉም ቢሆን ቦንብ የማጉረስ ያህል እጅግ አስጊ አካሄድ ነው። ለብልሁ አውሮፕላን አብራሪም ከጉዳዩ ጋር ያሉ ተያያዥ አንቀፆችን ካል ይግባኝ ይገድላል። አውነት ለመናገር ለዚህ ሥልጡን – ንጡር ድርጊትም እርእሱ ውስጥ ያለው ለወያኔ የህብረ ብሄር ፓርቲነት እውቅና መስጠት የተገባ ፈጽሞ አይደለም። ለቀጣይ ትግላችንም በዚህ መስማማት ካልቻልን የትም አንደርስም።

ለማንኛውም ጉልበት ሊሰጡ የሚችሉ (Siwiss Criminal Cod (STGB) Art. 173, 174, 177, 261)  እነዚህአንቀፆችወያኔንበፍርድአደባባይሲዊዝላይሊሞግቱትየሚችሉናቸው። በእንግሊዘኛ እንዳለያቀርብኩት የህግ ባለሙያዎችለቃልቀርቶ ለአንድ ፊድልእንኳንያላቸውንየከበደየጥንቃቄ ዕይታስለምገነዘብነው “እኔ” ለሚለው አገናዛቢ ቃል „ለእኔ” ከእኔ” ተእኔ” „በእኔ“ አንዲት  ፊደል ከፊት ስትታከል የትርጉሙ መልክ ሆነ አቅጣጫ ይቀዬራል። ስለሆነም ባለቤት ነን ካልን፤ ለምንጽፋቸው ማናቸውም ነገር ሁሉ ጥንቃቄ ማደረግ ግድ ይላል። ሕይወትም ታሪክም ነው። ትርፍ የሚገኘው ከጠንቃቃነት ነው።

2      „ጀግና ሀይለመድህን በቤተሰብ እንደተጠዬቀ“ ዘገባው አመለክቶ ነበር። ይህ በ28.02.2014 የበርኑ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገልፆ ነበር። እኔ የሰላማዊ ሰልፉን ዘገባ ስሠራ መረጃውን ዘልዬ ነበር ሪፖርቱን ያጠናቀርኩት። ፖለቲካ ግርድፍ አይደለም ልም ነው። ደህንነት የሚባል ነገር አለ። ቤቱ ብቻ ሳይሆን ጓሮውና አካባቢው ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል። ለእንሰሳ አስተዳደር ይህን መሰል መረጃ ማቀበል ሆነ መቀለብ አይገባም። ጊዜውን ቢጠብቅ መልካም በሆነ ነበር። መጠበቅ – ማሸነፍ ነው።

3.     ውጭ ስለሚገኙ የህግ ባለሙያዎች በአሉታዊ አስተያዬት ዘገባው ነበረው። ቃሉን በትርጉም ላቃናውና እንዳለ ማቅረብ ስለሚከብደኝ። “ኢትዮጵያዊ የህግ ጠበቆች የሲዊዝ ጠበቆች ለጠዬቋቸው ጥያቄዎች አቅም ያነሰው መልስ እንደሰጡ።” ዘገባው ጠቁሟል። ይህን በሁለት መልክ ማዬት ይገባል።

3.1   መዘርዘር ባልፈልግም ጫና በሁሉም ላይ አለ። ይህን ጥሶ መውጣት መቻል መታደል ነው፤ ባይሆንም መብት ነውና ብዙ መጋፋት አያስፈልግም። የሥራ ክፍፍልም ስለአለ ለሥራው ቅርበት ያላቸው ወገኖች ተግተው በጀመሩት ይቀጥሉ ባይ ነኝ።

3.2  ወቀሳ ላይ ደፈር ብለን ከገባን ሁሉንም አካባቢ መዳሰስ ያስፈልጋል። ጉዳዩ የተፈጸመው ሲዊዝ ሆኖ በተመሳሳይ ቀን በ28.02.2014 ሁለቱም የኢሳት ስቲዲዮዎችና ሪፖርተሮች የተገኙት ኖርዎይ ነበር።

ፀሐፊ ገዛህኝ አበበ ከኖርዎይ እንደዘገበው ቅኒት ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላና ጋዜጠኛ ደረጀ ደስታ መገኘታቸውን ዘግቧል http://ecadforum.com/Amharic/archives/11253/ ሪፖርቱን ለኢሳት ያቀበለውም ጋዜጠኛ ደረጀ ስለመሆኑ አዳምጫለሁ። እኛስ ነው ጥያቄው? ማዳላት ጥሩ አይደለም።

 

ከዚህም ባለፈ “የሲዊዝ ሹሞኞቹ አክቲቢስቶች፤ የነፃነት ትግሉ ኤክስፐርቶች” አልነበሩም። ሁልጊዜም ታች ሆነው ሥራውን የሚጋፈጡትን ብቻ ነው ጉሮሯቸው እስከደርቅ ድረስ መፈክር ሲያስተገቡ ያዬሁት። እርግጥ የሰለጠነ መሳሪያና ታታሪ ቪዲዮ ቀራጭ አይቻለሁ። ሰላማዊ ሰልፉን ዬጠሩት ወገኖች ወንዝ ላይ፤ ዛፍ ጥላ ሥር፤ መንገድ ላይ ብቻ ከሆነ ቦታ በጋራ እንግዳችን እንቀበል ሲሉ መገኘት መልካም ነበር። ከሁሉም የላቀ ፈታኝ ጥሪ ነበር። ግን አልሆነም። ታሪክን ለሚጽፉት ይከብዳል። ስንት ቀንስ በትርጉም ተቃንቶ፤ ተሽፍኖ ሃቅን ከናንቦ ይዘለቃል?! እኔማ ያው ዬቤቴን የከረንትን እንዲሁም  የአንድነትን ናፍቆቶቼን ስለአገኘሁ በመንፈሴ ላይ ምንም ዓይነት ግልምጫም ሆነ ፍጥጫ በሹም ሳይደርስብኝ በሰላም ተግባሬን ከውኜ ነበር የተመለስኩት።

እርግጥ ኖርወዬ ጥሩ እረኛ አባት ስላላቸው እድለኛ ናቸው። ለመታገል የወደዱ ሁሉ ፍቅርና እቅፍ መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ተከታታይነት ያለው ቋሚ  ድርሻንም ለመወጣት ሆነ ለመታገል ይችሉ ዘንድ ተመርቀዋል። እኔም እማደንቀው አመራር ነው ኖሮይ ያለው። አጋጣሚ ሰጥቶኝም በ2009 የታህሳሱ የጂ20 ዓለም ዓቀፍ ስብሰባ ላይ ሄሮድስ መለስ ተገኝተው ስለነበር  ከኮፐን ሀገን የተቃውሞ ስልፍና ስብሰባ ላይ እናቱን ውስጡ ጽላቱ ያደረግ፤ ንቁ አሰባሳቢ እንዳላቸው ዓይኔ አይቷል፤ እንዴትም እንደሚደንከባከባቸው ተመልክቻለሁ። ያን ጊዜ አዎንታዊ ቅናትም ብልት አድርጎኝ ነበር የተመለስኩት። ዶር/ ሙሉአለም አዳሙ ወቅቱ ለሚጠይቀው የትግል መስመር አስቀድሞ የተሰናዳ ወርቅ ወንድም ነው። ለዚህም ነው  የትግል መስመሩ ሁሉ በእኩልነት እንደ ወቅቱ ባህሪና ይዘት በነፃነት ቋሚ አድማጭ ኖሪዎይ ላይ ያለው። አቅማቸውም ጉልበታም የሆነው።

የሆነ ሆኖ ለ28.02.2014 ነገር  ኃይለመድህን አበራ ግን ከዬትኛውም ቦታ የተፈጥሮ ጠረን ለኢሳትና ሆነ “ለኢሳት አክቲቢስቶቹ” ሲዊዝ ይቀርብ ነበር …. አስተካክሉ፣ እረሙ፣ ታዝበናችኋል እንላለን እኔና ብእሬ …. በስንት ወጨፎና ግርፋት ነው እኛ እንኳን ሥራ ያውጣው ብለን ሳንቀመጥ ሁሉንም ታግሰን እኔም ሆንኩ ብዕሬም እንዲሁም እምሳሳለት ጥንቁቅ ሰብዕናዬም እዬተረገጥን የምንታደመው —- እንኳንስ ፍቅርና ክብር፤ እልልታ በገፍ በሩን ቧ አድርጎ ፈክቶ የሚጠብቀው ኢሳት —- የእውነት መገኘት ነበረበት። ኢሳትም በስሚ ስሚ — ቀኑን አሾለከ —– ታሪክ ተከዘ።

4     የዘጋቢ ፊልሙም ጉዳይ የበለጠ ድንቅ ሊሆን የሚችለው ተከድኖ ቢቆይ ነበር። ሲዊዝ መኖር እኮ እጅግ ተዝቆ የማያልቅ ዕውቀት የሚሸመትበት ሀገር ነው። እጅ ስንሰጥ ወደ 8 ወር 300.00 የማይሞላ ወደ ሌላ ካንፕ ስንሸጋገር 400.00 መኖሪያ ፈቃድ ስናገኝ 960.00 ፍራንክ ለወር ይሰጠናል። ያው ከጤና ኢንሹራንሱና ከቤት ኪራዩ ሌላ። ደረጃ በደራጃ ኑሮን እንዴት መኖር እንደሚቻል በረቀቀ ሁኔታ ብልሆቹ ያስተምሩናል። ከካንፑ ውስጥ ልብስም በጣም በርካሽ ይሸጣል። በ1.00 በ5.00 የሲዊዝ ፍራንክ ወዘተ …. መንገድ ላይ ሆነ  ገብያ ላይ ቀለል ያለ እቃ ለያዘ ቅድሚያ ይሰጣሉ። ሐብታቸው – ደስታው – ድሎታቸው ልክና ደንበር አለው። እኛም ያስተማሩንን በመተግበር በራችን እስከ አንቃሩ ሳንከፍት ስሜታቸውን እዬተከተልን መረጃውን ብናቀብል መልካም ነው።

 

5.        ትእግስትን ገርገጭ ያደረገ አስተያዬታዊ ማሳሰቢያ – ለሲዊዝ የሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጆች።

 

- በሀገረ ሲዊዝ የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ መጠዬቅ ሆነ የማሳወቅ ጉዳይ በደብዳቤ እንጂ በኢሜል የሚታሰብ አይደለም። መልሱም በደብዳቤ መሆን አለበት። አይደለም እኛ ሲዊዞች ከህጋቸው በታች በታች ናቸው። ስለዚህ መጀመሪያ መጨረስ የሚገባነን ሳንጨርስ በተደጋጋሚ ከሥራዓት አስጠባቂዎች ጋር መጋጨት ለሁልጊዜ ለኢትዮጵውያን ሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ሊነሳ የሚችል ይሆናል። ተሳታፊውም ይቀራል። ይህ ትብስብስ ያለ ጉዳይ ፍርጥርጥ አድርጋችሁ ተወያይታችሁ መልክ ልታስይዙት የሚገባ ጉዳይ ነው።

- ጥሪው በኢሜል፤ በሁሉም ሆም ፔጆች፤ በኤስኤምኤስ በተጨማሪነት መጠቀሙ መሰረታዊ ነው።  በኢሳትና በፌስ ቡክ እንደምትጠቀሙት ሁሉ። በአንዱ መረጃውን ማግኘት ይቻላል።

- ጥረው ሲተላለፍ ባለቤት ሊኖረው ይገባል፣ ቋሚ የመገናኛ ቦታ መታወቅ አለበት፤ ተሳታፊ ከዋናው ባቡር ጠቢያ ወርዶ የትኛውን አውቶብስ፣ ትራም፣ እንደሚይዝ መብራራት አለበት፤ የሚወርድበት ስቴሽንም ሆነ በእግር የሚያስኬድ ከሆነም ግልጽ መረጃ ሊሰጥ ይገባል። የአድራሻ ለውጥ ሲኖር ሲቀዬርም በ አስቸኳይ በማናቸውም መንገድ ለተጠሪው በሙሉ መረጃ የማሳወቅ ግዴታ ነው። እኔ በግሌ የስልክ ቁጥር አያሰኜኝም። ደጅ ጥናት ስለማልፈልግ። የምፈልገው ትክለኛ ግልጽ መረጃ ወረቀት ላይ የተጻፈ።

- ተሳታፊውን በሙዑሉ አክብሮትና ፍቅር “እንኳን ደህና መጣችሁ” ሰልፉ ሲያበቃ ደግሞ “እግዚአብሄር ይስጥልን፤ በሰላም ያግባችሁ” መባል አለበት። የመንፈስ ስንቅ አይነት – ለቀጣዩ ጥሪ ምቹ ሁኔታም ማሰናዳት ያስፈልጋል። ለአንድ ሰላማዊ ሰልፍ ጊዜው ገንዘቡ አቅሙ ጤናውም አለ —- በጣሙን አብዝቼ የምጠይቀው – ድካሙን ከብክነት የሚያድን የተደራጀ አቅም፤ ብቃታዊ አመራር።

- ስብሰባም ሲጠራ ማስታወቂያው ይወጣል የሚገኘው የፖለቲካ ሰው ግን አይገለጸም። ለምን? አይገባኝም። ጭራሽም የመረጃ ፍሳት ሳይኖር ይቀራል። ለምሳሌ ኢንጂነር ይልቃል ሲዊዝ መጡ ጄኔባን ብቻ አይተው ተመለሱ። ቢሰማ ቢያንስ እዛው አካበቢ ያሉ ወገኖች መገኘት ይችሉ ነበር።

- በርን ማዕከላዊ ቦታ ከመሆኑም በላይ ፍቅር ናቸው እዛ ያሉ ወገኖች። ሁሉንም ቀዳዳ በተግባር እዬሸፈኑ ያሉትም እነሱ ናቸው። ለማናቸውም ኃላፊነት በቂ ተከታይነት ያለው አቅምም አለ። ስለዚህ የሲዊዝ የነፃነት እንቅስቃሴ በርንን ማዕከል ቢያደረግ መልካም ይመስለኛል። የሲዊዝ ዋና ከተማም ነው።

- ጠሪው በሌለበት ተጠሪው የመገኘት ይህም ያዬሁት ነገር ነው። ከዚህ በላይ የወቅቱን የሰልፈኛውን ሙቀት፤ ፍላጎት፤ ቁጣ ሊያስተናገድ የሚችል አቅም ሊኖር ይገባል። ኤክለፕተስ ዛፍ ፍሬ ሲያፈራ ቅርንጫፉ ፍሬውን የመሸከም አቅም ስለማይኖረው ይዘነጠላል። የሳውዲ ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ግልብጥ ብሎ ተወጥቶ ነበር በግምት ከ300 እስከ 400 ሊሆን የሚችሉ ቅኖች ነበሩ። ተሳትፎው ልባዊ ሀገራዊ – ፍቅራዊ ነበር። እኔ ሲዊዝ ውስጥ አይቼ አላውቅም። ግን ያን ፍል እንባ በሥርዓት መርቶ ለቀጣይ ኃይላፊነት በቋሚነት ለማቆዬት የሚችል የተደራጀ አመራር አልነበረም። በቀጣይ የረዳት አውሮፕላን አብራሪ ጉዳይ ጥሪ ቢኖር ለመሳተፍ እነዚህ ነጥቦች በአግባቡ ሊስተካከሉ ይገባል። በስተቀር ግን ለብክነት ጊዜ የሚሰጥ ሰው አይኖርም።

በመጨረሻ — ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ካሰኛችሁ የቀደምት አንድነቶችን በስተቀር ብሄራዊ ጉዳይን የማስተናገድ አቅም ያላቸው እንደ ሙንሽን፤ ኖርወዬ፤ ሲዊዲንና ፍራንክፈርት የዳበረ ልምድ ስላላቸው በዝግጃታችሁ ቅድሚ ምክር ጠይቁና እናንተ ካላችሁ ተመክሮ ጋር አጋባታችሁ ጥሪያችሁን አክብሮ የሚመጣውን ኃይል በብቃትና በፍቅር ብታስተናግዱ መልካም ነው። አልመለሰብተም ጨረስኩኝ።

 

በመጨረሻ – ለጀመርነው አጠቃላይ አቅጣጫ ጠላትን በስልት ሊረታ የሚችል ሥልጡን – ጥንቁቅ ዘገባዊ አቀራረብ ነበርው የነገረ ኃይለመድህን በወያኔ ጓዳ ያለውን ጭብጥ የጠቆመን የጋዜጠኛ ተመስገን ጥንቅር። እጅግ ለሚዲያ ሰዎች ይረዳልና ደግመን ብናነበው ምርጫዬ ነው ከትህትና ጋር። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/29045

 

እንደ መከወኛ። ናፍቆቶቼ የሀገሬ ልጆች ይሄውላችሁ በገባሁት ቃል መሰረት “የተስፋ ማህጸን” የመጀመሪያ ዝግጅትን በ10.04.2014 ደስ ብሎኝ ድልን እያሰላሁ  ሰራሁት። የተላለፈውን አርኬቡ ላይ አለላችሁ። ቀጣዩ ደግሞ በ27.04.2014 ይሆናል። እያሰባችሁ በዬ15 ቀኑ  በዕለተ ሃሙስ ከ15 እስከ 16 ሰዓት አዬር ላይ ከቻላችሁ፤ ካልቻላችሁ አርኬቡ ላይ አዳምጡ – ጀግና ፍለጋ ጋራ ሸንተረር ከምትጠብቁ ሲዊዝ ላይ የተገኘውን የጀግና ድጋፋዊ መንፈስ አዳምጡ በትህትና። www.lora.ch.tsegaye ወይንም Aktuell Sendung www.tsegaye.ethio.info።ይህንሊንክከአጀንዳችሁብትመዘግቡት አመሰግናለሁ። እኔአልመለሰበተም።የዘርፖለቲካናጦሱለጎረበጠውተቆርቋሪይህችን በመንፈሱ ሰሌዳ ማስቀመጥ ቀላሏ የቤት ሥራ ናትና። በተረፈ የጀግናችን ሁለተኛ ወር ምክንያት በማድረግ ጸልዩለት፤ በፌስ ቡካችሁ በቲተር አካውንታችሁ ላይ እሱን እሰቡት። ቀኑን ለእሱ ስጡት አሁንም ዝቅ ብሎ በሚለምን ትህትና። “ሰላማዊ እንቢተኝነትን በዝምታ የሞሸረ” የእኛ ልዩ ስጦታ ነው ረ/ አውረፕላን አብራሪ ኃይለመድህን አበራ።

 

መልካም የትንሳኤ በአል ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማንያን ተመኘሁ። እንዲሁም መልካም በጸሎት የመረዳዳት የመተሳሰብ ጊዜ – ይሁንልን። የወንድማችን፤ የልጃችን፤ የጀግናችን፤ የሽልማታችን ቸር ወሬ አምላካችን ያሰማን። አሜን!

 

 

የጀግና ተግባሩ መንበሩ!

የጀግና ውበቱ ተግባሩ!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ!

 

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live