Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ግልጽ መልእክት ለአገራችን የታሪክ ፀሃፊዎችና ፖለቲከኞች !

$
0
0
የታሪክ ተወቃሽነቱን ከራሳችን እንጀምር !
በመንገሻ ሊበን
እኛ ኢትዮጵያዊያን የአኩሪ ታሪክ ባለቤቶች እንደሆን ከልጅነት እድሜያችን ጀምሮ እየተነገረን ያደግን ህዝቦች ነን ። የሰው ልጅ መገኛ ፤የቅዱሳን አገር ፤የጀግኖች መፍለቂያ ምድር ፤ መቅደላ ፤አድዋ፤ ማይጨው ወ.ዘ.ተ የሚሉት ቃላት በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አእምሮ ውስጥ የሚያቃጭሉ የታሪክ ፀፊዎቻችን የብእር ትሩፋቶች ናቸው ። እጅግ የሚገርመው ግን ፣ የአፄ ቴድሮስ እጅና እግር ቆራጭነት ፤ የአፄ ዮሃንስ አንገት ቀንጣሽነት የአፄ ምኒልክ ጡት ዘልዛይነት እንደዚሁም የአፄ ኃይለስላሴ ፤ የኮሎኔል መንግስቱና የአቶ መለስ ዜናዊ አሰቃቂ ወንጀሎች የታሪካችን አንድ አካል መሆናቸው እየታወቀ በታሪክ ፀሃፊዎቻችን ዘንድ ግን ብዙም የሚዳሰሱ ነገሮች አለመሆናቸው ነው ።
እንደዚህ ፅሁፍ አቅራቢ እምነት ፣ መልካሙን ታሪካችን እንዴት አቅበን መጓዝ እንዳለብንና ከመጥፎ ታሪካችንም ምን ዓይነት ልምድ መቅሰም እንደሚገባን መማር የምንችለው ታሪክ ፀሃፊዎቻችን ትክክለኛውን ታሪካችንን ያለምንም መዛነፍና ወገንተኝነት በሃቀኛ ብእራቸው ሲከትቡልን ብቻ ነው ።መረረም ጣፈጠም የኛ ታሪክ የኛ የራሳችን ነውና ።
ለመንደርደሪያ ያህል ይህን ካልኩ በቀጣይነት ላነሳው ወደፈለኩት ርዕሰ ጉዳይ ላምራ።
አውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች እንደ ቅርጫ በተከፋፈሏት የጥቁሮች ምድር፣ በጀግኖች አባቶቻቸን ከፍተኛ መስዋእትነት ብቸኛዋ የነፃነት ቀንዴል የሆነችው እናት አገራችን ኢትዮጵያ፣ ካለፉት 50 እና 60 ዓመታት በተለይም ደግሞ ካለፉት 22 ዓመታት ወዲህ እያጋጠማት ያለው ህልውናዋን የሚፈታተን ኩነት የቱን ያህል ከባድና አሳሳቢ እንደሆነ ብዙዎቻችን የምንገነዘበው ነገር ይመስለኛል።
እንደ እኔ እምነት ለዚህ የአገርን ህልውና በቀጣይነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየጣለ ለሚገኘው የተወሳሰበ ችግር ተጠያቂዎቹ፣ ከ1983 በኋላ መንበረ ስልጣኑን የተቆጣጠረው የወያኔ ስርዓትና ከእርሱ በፊት የነበሩት ሁለት መንግስታት ብቻ ሳይሆኑ፣ የሃገራችን ታሪክ ፀሃፊዎች፤ ሙሉ እድሜያቸውን በተቃዋሚነት ጎራ ተሰልፈናል የሚሉ ሃይሎችና የኢትዮጵያን ችግር እንደ እጃችን መዳፍ ጠንቅቀን እናውቀዋልን እያሉ በየአደባባዩ የሚመፃደቁት ፖለቲከኞቻችን ጭምር ናቸው።
በእርግጥም እነዚሁ ሃይሎችና ተመፃዳቂ ግለሰቦች ፣ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ፣ ያልነበረን ታሪክ የነበረ አስመስሎ በማቅረብና ፣ “ታሪክ እንደፀሃፊው ነው” እንዲሉ ፣ ከሞላ ጎደል ሁሉንም ታሪካችንን (መጥፎም ይሁን ጥሩ ታሪክ ) ለፀሃፊው ወይም ለገዥው አካል በሚመች መንገድ በማቅረብ ፣ አንዳንዴም ኢምንቱን ፍፃሜ እጅግ በተጋነኑ የማንህሎኝነት ቃላት በመጀቦን ወይም ደግሞ ትውልድ ሊማርበት የሚገባውን አንኳር ፍፃሜ ምንም እንዳልተፈፀመ በማስመሰል፣ አላስፈላጊ የህይወትና የጊዜ መስዋእትነት እንድንከፍል ከማድረጋቸውም በላይ … በአገራችን ኢትዮጵያ ላይም አሳፋሪ ውድቅት እንዲከተልና ትውልድም ያለፈ ታሪኩን በሚገባ እንዳይገነዘብ የየራሳቸውን ድርሻ አበርክተዋል ብቻ ሳይሆን እስከ ዛሬም እያበረከቱ ይገኛሉ ።
ስለሆነም ታሪክን በማፋለስ ረገድ ፣ የታሪክ ተወቃሽነቱ መጀምር ያለበት፣ ይህንን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተፈጸመ በደል ይፋ አውጥቶ በግልፅ በመወያየትና በመመካከር እንጅ፣ በተፋለሰ ታሪክ ላይ ተንተርሶ በጥፋት ላይ ጥፋት በመስራት አልያም ደግሞ የራስን ሌባ ጣት ወደ ሌላ በመቀሰርና ተጠያቂነቱን በሌሎች ላይ በመለደፍ መሆን የለበትም።
እንደሁሉም የአለም አገራት ፣ አገራችን ኢትዮጵያም በተለያዩ ፍፃሜዎች መጥፎና ደግ ኩነቶችን ያስተናገደች ምድር ናት ። ይህ ሁለት ተፃራሪ ኩነት በታሪክ መዝገብ ላይ በሚገባ ሊሰፍርና ትውልድም በጥልቀት ሊማርበት የሚገባው ነገር ይመስለኛል ። አስቀድሜ በፅሁፌ መግቢያ ላይ እንደጠቀስኩት ከመጥፎ ታሪካችን ምን ዓይነት ልምድ መቅሰም እንደሚገባንና መልካሙን ታሪካችን ደግሞ እንዴት አቅበን መጓዝ እንዳለብን መማር የምንችለው ታሪካችን ያለምንም መዛነፍና ወገንተኝነት በሃቀኛ ፀሃፊዎች ተከውኖ ሲቀርብልን ብቻ ነው። ከዚያ ውጭ ግን መነገር ያለበት ሃቀኛው ታሪካችን በግለሰቦችና የፖለቲካ ሃይሎች አስተሳሰብ ፤ ስሜትና ፍላጎት ላይ ብቻ ተመርኩዞ መፃፉን ከቀጠለ ፣ የታሪክ መፋለስ እንዳያስከትል በእጅጉ ሊያሰጋን የሚገባ ነገር ነው ።
ለመንደርደርያ ያህል አንድ አንኳር ነጥብ ላንሳ ። ይህ አንኳር ነጥብ ፣ ላለፉት 50 እና 60 ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ዓመታት ፣ የህዝባችንና የፖለቲካ ሃይሎቻችንን ቀልብ በከፍተኛ ደረጃ ከሳቡት የአገራችን የፖለቲካ አጀንዳዎች መካከል አንዱ ነው። ይህ አንኳር ጉዳይ በአገራችን የታሪክ መዝገብ ላይ ያለምንም መዛነፍና ወገንተኝነት በሚገባ ሰፍሯልን…? ወይም ደግሞ ከእስካሁኑ ፍፃሜ በኋላስ ትውልድ ሊማርበት የሚገባው ሃቀኛ ታሪክ ያለወገንተኝነት እየተፃፈ ነውን…? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ይሰጥበት ዘንድ አንባቢን በአክብሮት እጋብዛለሁ ።
ሁሉም እንደሚያውቀው በአገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻን ከሚይዙት አንኳር ጉዳዮች መካከል አንዱ የኤርትራ ጉዳይ ነው። ፖለቲከኞቻችንና ፀሃፊዎቻችን ይህንኑ አንኳር ጉዳይ አስመልክተው ከደርዘን በላይ የሆኑ መጣጥፎችን ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወቅ ነገር ቢሆንም “ታሪክ እንደፀሃፊው ነው” የተሰኘው ብሂል ግን በመጣጥፎቻቸው ላይ መንፀባረቁ አልቀረም ። ለምሳሌ ያህል በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ፤ በደርግና በወያኔ ዘመነ-መንግስታት የኤርትራን ጉዳይ በሚመለከት በፖለቲከኞቻችንና ፀሃፊዎቻችን አማካኝነት ለንባብ የበቁ መጣጥፎችን ብንመለከት ፣ ትውልድ ሊማርበት የሚገባው ታሪካችን የቱን ያህል እየተፋለሰና ያለጥልቅ ጥናት በፀፊው ፍላጎትና ስሜት ላይ ብቻ ተንተርሶ እየተፃፈ እንደሆነ ለመገነዘብ የግድ ተመራማሪነትን አይጠይቅም ። ያም ሆነ ይህ ነገር ከማንዛዛትና አንባቢን ከማሰልቸት በቀጥታ በቀዳሚነት ላነሳው ወደፈለግኩት ርእሰ ጉዳይ እናምራ ። በዚህ ጉዳይ ላይ ሶስቱን መንግስታት ጨምሮ ፖለቲከኞቻችንና ፀሃፊዎቻችን ሲከተሉት የነበረውን አቋም በመጠቃቀስም፣ ከእውነተኛው የታሪክ ፍፃሜ አኳያ የየራሳችንን ድምዳሜ ለመስጠት እንሞክር።
እስካሁን ድረስ በግብታዊነት ስንከተላቸው ከቆዩት የታሪክ ፀፊዎቻችንና ፖለቲከኖቻችን መጣጥፍ አንፃር ከዚህ በታች የሰፈሩት እውነታዎች ለመቀበል የሚያዳግቱና እንደ እሬት የመረሩ መሆናቸው አሌ ባይባልም ፣ የኛ ታሪክ የኛ የራሳችን ነውና ለትውልድ ይበጅ ዘንድ ያለምንም መሸፋፈን መነገርና መፃፍ አለበት የሚል ፅኑ እምነት አለኝ ። ይህ የኔ ብቻ ሳይሆን የብዙዎቻችንም እምነት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ።
በበርካታ የታሪክ ድርሳናት ላይ ከሰፈሩ መጣጥፎች መገንዘብ እንደሚቻለው ፣ የኤርትራ ጉዳይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንደከፍተኛ አገራዊ አጀንዳ በተደራጀ መልኩ ተጋግሎ መስተጋባት የጀመረው በአጼ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ነው ። ከንጉስ ሃይለስላሴ በፊት የነበሩት የአገራችን ነገስታት (ንጉሰ ነገስታት ምኒልክን ሳይጨምር) ኢትዮጵያን አሁን በያዘችው የሉዓላዊነት ቅርፅ የማስተዳድር እድሉን ስላላገኙትና (የኢትዮጵያ ግዛት አንዴ ይጠብ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይሰፋ እንደነበረ ልብ ይሏል) የግዛት ጠረፋቸውም በነበራቸው የሃይል ሚዛን ላይ የተመረኮዘ ስለነበረ፣ በማስገበርም ይሁን በሌላ ምክንያት (ለምሳሌ አፄ ዮሃንስ መጥቀስ ይቻላል ) አልፎ አልፎ ወደ ደጋማው የኤርትራ ግዛት ከመዝለቅ ባሻገር ኤርትራን እንደ ክፍለ-አገር ወይም እንደ ጠቅላይ ግዛት አሁን በያዘችው ቅርጽና ይዞታ የኔ ናት ብሎ የተነሳ አንድም የኢትዮጵያ ንጉስ በታሪክ አልተመዘገበም። ይህ ማለት ግን የባህር በር ጥያቄ አይነሳም ነበር ማለት አይደለም። የባህር በር ጥያቄው ግን አሰብና ምጽዋን ብቻ ሳይሆን ጁቡቲንና ሶማሊያንም ያካትት እንደነበር መዘንጋት ታሪክን ማፋለስ ነው ።
የግዛት ጅማሮውን አሰብና አካባቢዋን በማድረግና ወደተቀረው የኤርትራ ግዛት በፍጥነት በመዛመት ለ60 አመታት ያህል የቅኝ ግዛት ቀንበሩን በኤርትራ ህዝብ ላይ የጫነው የጣሊያው ፋሽስት ስርዓት፣ የመስፋፋት ህልሙን እውን ለማድረግ በኢትዮጵያም ላይ ተደጋጋሚ ትንኮሳዎችንና የወረራ ሙከራዎችን ማድረጉ ይታወቃል ። ነገር ግን በተለያዩ የማደናገርያ ስልቶችም ሆነ በሃይል የኢትዮጵያን ህዝብ እንደሌሎች የአፍሪካ ህዝቦች አንበርክኮና ረግጦ መግዛት እንደማይቻል ፣ በጀግኖች አያቶቻችን ብልህነት ፤ አርቆ አስተዋይነትና ከፍተኛ መስዋእትነት በታሪካዊው የአድዋ ጦርነት ላይ ሲረጋገጥ ፣ ወራሪው የባእድ ሃይል ያለውድ በግዱ ኢትዮጵያን እንደ ሉዓአላዊት አገር ተቀብሎ ከአፄ ምኒልክ ጋር የተለያዩ ስምምነቶችን ለማድረግ ተገደደ ።
ከነዚህ ስምምነቶች መካከል ተጠቃሾቹ የጣልያን ቀኝ ግዛትንና (ኤርትራን) የኢትዮጵያን ድንበር በተመለከተ በ1900 ፤ በ1902 እና በ1908 (እ.ኤ.አ) በሁለቱ አገሮች መካከል የተፈረሙ የስምምነት ሰነዶች ናቸው ። በነዚህ የስምምነት ሰነዶች መሰረት ፋሽስት ጣሊያን የኢትዮጵያን ዳር-ድንበር በምንም አይነት መልኩ ላለመጣስና የአገሪቱንም ሉዓላዊነት ለመቀበል ስትገደድ፣ ኢትዮጵያ በፊናዋ ከጣልያን ጋር በምንም አይነት መንገድ በጠብ ላለመፈላለግ የውል ቃል ኪዳን አስራለች ።
በአድዋው ጦርነት የጣሊያውን ፋሽስት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ወራሪ ሰራዊቱን ከአገራችን ሉዓላዊ ግዛቶች ጠራርጎ ያባረረው የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት፣ በጀግኖች አያቶቻችን የማያዳግም ምት ተደናግጦ የተበታተነውንና የመዋጋትና የመከላከል አቅሙ ከዜሮ በታች የወረደውን የፋሽስት ሰራዊት እስከ አስመራ ድረስ ዘልቆ ከምንጩ የማድረቅ…ብቃትና ሞራል ቢኖረውም ፣ ያልነበረን ታሪክ እንደገና መፍጠርና የክብር ስሙን በወራሪነት መዝገብ ላይ ማስፈር አልፈለገም ። እንዲያውም ንጉሰ ነገስታት ምኒልክ አሸናፊ ሰራዊታቸው ድንበሩን ተሻግሮ እንዳይገሰግስ መመርያ ሲያስተላልፉ “ የአገሩ ዛፍ የለው ፤ የወንዱ ባት የለው ፤ የሴቱ ጡት የለው። ከዚህ በኋላ አገሬ አይደለምና ፣ ተመለስ !! ” በማለት እንደተናገሩ እስካሁን ድረስ በእድሜ ጠገብ አያቶቻችንና አባቶቻችን የሚነገርና የሚተረክ እውነታ ነው ። ይህ ታሪካዊ ፍፃሜ የጀግኖች አያቶቻችንን ህግ አክባሪነት የሌሎችን ግዛት ያለመመኘት ጨዋነት በተጨባጭ ያሳየ ተግባር ነው። ከታሪካዊው የአድዋ ጦርነት በኋላ የተፈረሙት ሶስቱ ታሪካዊ ስምምነቶች ደግሞ የኢትዮጵያዊያኑን የአልገዛም ባይነትና የአገርን ዳር-ድንበር አሳልፎ ያለመስጠት አኩሪ ታሪክ ያስመሰከረ አንኳር ፍፃሜ ነው ።
ነገር ግን ስለኤርትራ ጉዳይ ቀን ከሌት የሚሰብኩን የዘመናችን ፖለቲከኞች ይህንን እውነታ በትክክለኛ ታሪክነቱ ሲያስነብቡን አልታዩም ። እንዲያውን ይባስ ብለው በወቅቱ የነበሩ ሁኔታዎችን ሸፋፍነው በማለፍና የኢትዮጵያውን ንጉሰ-ነገስት መንግስት ህግ አክባሪነት በማጣጣል ለጀግኖች አርበኞቻችን መረብን ተሻግሮ አለመሄድ የተለያዩ ምክንያቶችን ከመፍጠር ባለፈ የወቃሽነት ጣታቸውን በአፄ ምኒልክ ላይ ሲቀስሩ ይስተዋላሉ ። የታሪክ መዝጋቢዎች ወይም ነጋሪዎች ስራ እውነተኛውን ታሪክ በተገቢው መንገድ በመዝገብ ላይ ማስፈር ሆኖ እያለ ፣ የኛዎቹ ጸሃፊዎችና ፖለቲከኞች ግን፣ ባልነበሩበትና ባልተካፈሉበት ታሪክ ውስጥ ሆነው የታሪክ ፈጻሚዎችን ስራ በማጣመምና የየራሳቸውን ትርጉም በመስጠት ፣ የምኒልክን ወደ ኤርትራ ግዛት ዘልቆ አለመግባት፣ አንዴ ከሰራዊታቸው በረሃብና በውሃ ጥም መድከም ጋር፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከመሃል አገር የሰራዊት ሃይል መሳሳት ጋር እያዛመዱ በመግለፅ ፣ እስካሁን ድረስ መፍትሄ ላልተገኘለት ውስብስብ ችግራችንና የህይወት፤ የንብረትና የግዜ ኪሳራችን የበኩላቸውን አሉታዊ አስተዋፅዖ አበርክተዋል ።
እዚህ ላይ መጠቀስ ያለበት ሌላም ታሪክ አለ ። እርሱም፣- በታሪክ ፀሃፊዎቻችን ዘንድ ብዙም የማይወሳውና አፄ ምኒልክ በአድዋው ጦርነት ወቅት በተማረኩት የኤርትራ ተወላጅ የጣልያን ወታደሮች ላይ የፈፀሙት እጅግ አሰቃቂ በደል ነው ። አፄ ምኒልክ ድል የነሷቸውን የጣልያን ምርኮኞች ሰብአዊነት በተመላበት ሁኔታ ተንከባክብው በክብር እንደሸኟቸው በታሪክ ፀሃፊዎቻችን መጣጥፎች ላይ ተደጋግሞ የተነገረን ነገር ቢሆንም … በጦርነቱ ላይ የማረኳቸውን የኤርትራ ተወላጆች ግን እንዴት እጆቻችውን እየቆረጡና በአንገታቸው ላይ እንደሚዳሊያ እያንጠለጠሉ ወደ አገራቸው ኤርትራ እንደሸኟቸው በታሪክ ጸሃፊዎቻችን ብእር ብዙም የተነገረለትና የተወሳለት ጉዳይ አይደለም ። ለምን…?
እርግጥ ነው ይህ እውነታ ለብዙ አመታት ስንጋተው ከቆየነው የተፋለሰ ታሪክ አንፃር ለብዙዎቻችን የማይዋጥና እንደ ኮሶ የመረረም ሊሆን ይችላል ። ነገር ግን ጣፈጠም መረረም የኛ ታሪክ የኛ ነውና ሁሉም ይማርበት ዘንድ በሚገባ መፃፍ አለበት ። ያም ሆነ ይህ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ጊዜ ከማባከን አሁንም ወደ ዋናው ነጥቤ ልመለስ ።
ቅድም እንዳልኩት ካለፉት 50 ወይም 60 ወይም ደግሞ ከዚያ በላይ ከሆኑ ዓመታት ጀምሮ እስከአሁን ድረስ የመላው ህዝባችንን ቀልብ በመሳብና በአገራችን የፖለቲካ አጀንዳ ውስጥም ጉልህ ድርሻ በመያዝ የሚታወቀው ርእሰ ጉዳይ ኤርትራን የሚመለከተው ክፍል ነው ።
ፋሽስቱ የጣልያን መንግስት በአድዋው ጦርነት ድል ተነስቶና በነጮች አለም አሳፋሪ የውርደት ሸማን ተከናንቦ ከድል ነሽዋ ኢትዮጵያ ጋር ሶስት የተለያዩ ስምምነቶችን ከተፈራረመ በኋላም ቢሆን የተስፋፊነት አባዜውን እርግፍ አድርጎ ለመተው አልፈለገም ። እንዲያውም ይባስ ብሎ በአድዋው ጦርነት የደረሰበትን አሳፋሪ ውርደት ለማካካስ ለረጅም አመታት የዘለቀ ሁለንተናዊ ዝግጅት ሲያደርግ ነበር የቆየው ። በዚህ የረጅም አመታት ዝግጅቱ ነው እንግዲያውስ ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ መጠነ-ሰፊ የሆነና በከፊልም ቢሆን ስኬታማ የሆነበትን ወረራ ያካሄደው ። (በዚህ ርእሰ ጉዳይ ዙርያ ብዙ ስለተባለና ስለተነገረ…ወደ ዝርዝሩ ገብቼ በመፃፍ የአንባቢዎችን ጊዜ ማባከን አስፈላጊ አይመስለኝም።)
ያም ሆነ ይህ በዚህ ጉዳይ ላይ መጠቀስ ያለበትና በታሪክ ፀሃፊዎቻችንና ፖለቲከኞቻችን አንደበት ብዙውን ጊዜ በግልፅ የማይነገረን አንድ ነጥብ አለ ። ይሄውም የጣልያን የአምስት አመታት የቅኝ ግዛት ዘመን በማንና በምን መልኩ እንደተቋጨ ተድበስብሶ የሚፃፈው ታሪካችን ነው ። እርግጥ ነው ጀግኖች አያቶቻችንና አባቶቻችን በፋሽስቱ ጣልያን የተደፈረውን የአገራቸንን ክብር ወደ ነበረበት ለመመለስ ለአምስት አመታት ያህል ያደረጉት አኩሪ ተጋድሎ ሁሌም ሊዘከር የሚገባው ነው። ነገር ግን በፋሽት ጣልያን የተደፈረው የኢትዮጵያ ክብር ዳግም ወደ ነበረበት የተመለሰው ያለማንም እርዳታና ድጋፍ በጀግኖች አባቶቻችን ቆራጥ ተጋድሎ ብቻ ነው ብሎ መፃፍ ታሪክን ማፋለስ ነው ።
የእንግሊዝን ወረራ ለመመከት በመቅደላ አፋፍ ላይ ህይወታቸውን እንደሰዉት አጼ ቴድሮስ (በእርግጥ አፄ ቴድሮስ በራሳቸው ሽጉጥ ወይስ በጠላት ጥይት ተገደሉ የሚለው ታሪክ አወዛጋቢ ቢሆንም) ፣ ስለ ኢትዮጵያ ክብር እስትንፋሳቸውን ይሰጣሉ ተብለው ሲጠበቁ ጭራቸውን ቆልፈው በመፈርጠጥ ለንደን ላይ የታዩት የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ አሳፋሪ ታሪክና ፣ የጣልያንን ፋሽስት ጦር ከኢትዮጵያ ምድር ጠራርጎ ያወጣው የእንግሊዝ ሰራዊት ከፍተኛ ሚናም የታሪካችን አንዱ አካል በመሆኑ ፣ እንደ እሬት ቢመረንም የግድ መፃፍ አለበት። (ስለአዲስ አበባዎቹ የጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት ፤ የዊንስተን ቸርችልና የኮለኔል በርኒንግሃም መንገዶች ፣ የስም አወጣጥ መነሻ ታሪክ የሚያውቀው ኢትዮጵያዊ ወጣት ስንት ነው…..? )
ከፍጻሜ ማህደሮቻችን ውስጥ ምርጥ ምርጡን ብቻ እየለቃቀሙ በታሪክ ድርሳናት ውስጥ ማስፈር ፣ ትዝብት ብቻ ሳይሆን ትውልድንም ማሳሳት ነው ። የታሪክ ድርሳን ማለት አኩሪ ፍፃሜ ብቻ የታጨቀበት መዝገብ አይደለም። ጣፋጭና መራራውም በአንድ ላይ ተቀይጦ የሰፈረበት የእውነተኛ ፍፃሜዎች ሰነድ እንጅ ። ስለዚህ ለትውልድ ይበጅ ዘንድ ያላንዳች መሸፋፈን ሁሉም መፃፍ አለበት።
ወደ መነሻ ነጥቤ ልመለስ………
በሁለተኛው የአለም ጦርነት በአክሲስ ሃይሎች ላይ የደረሰውን ሽንፈት ተከትሎ ፣የጣሊያው ፋሽስት ጦር እንደ ሊቢያና ሶማሊያ ግዛቶቹ ሁሉ ለአምስት አመታት ከገዛት ኢትዮጵያና ለ 60 አመታት ከአስተዳደራት ኤርትራ ጠቅልሎ ለመውጣት ሲገደድ ፣ ኢትዮጵያ ከስደት በተመለሱት ንጉስ ገዥነት በነፃነት ፣ ኤርትራ ደግሞ ጣልያንን አሸንፈው በመጡት እንግሊዞች ስር በሞግዚትነት መመራት ጀመሩ ። ከዚህን ጊዜ በኋላ ነው እንግዲህ የኤርትራ ጉዳይ በአገራችን የፖለቲካ አጀንዳ ውስጥ በተደራጀ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ መራገብ የጀመረው ። ይህ ጉዳይ ከአገራችን ባሻገር አለማቀፋዊ ደረጃ እንዲይዝና ይበልጥ እንዲቀጣጠል ካደረጉት መካከል ደግሞ አፄ ኃይለስላሴና በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው የነበሩት አቶ አክሊሉ ሃብተወልድ በቀዳሚነት ቢጠቀሱም፣ ኤርትራን በሞግዚትነት ስም የተረከበው አዲሱ የእንግሊዝ አስተዳደርም ቢሆን ከራሱ የፖለቲካ ጥቅም አንፃር ጉዳዩን ይበልጥ በማቀጣጠልና አለማቀፋዊ ትኩረት በማሰጠት ረገድ የተጫወተው ሚናም በቀላሉ የሚገመት አይደለም ።ይህም የታሪካችን አንዱ አካል ነውና….ያለምንም መሸፋፈን አሁንም መፃፍ አለበት ።
ይቀጥላል…….
መንገሻ ሊበን
ማንኛውንም አስተያየት ለመቀበል የፀሃፊው የኢሜል አድራሻ ሁሌም ክፍት ነው ። mengeshalibenn@yahoo.com
↧

↧

በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ ሲያጠምቁ የከረሙት አነጋጋሪው መ/ር ግርማ ወንድሙ እንዳያጠምቁ ታገዱ

$
0
0


በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ ሲያጠምቁ የከረሙት አነጋጋሪው መ/ር ግርማ ወንድሙ እንዳያጠምቁ ታገዱ (ዘ-ሐበሻ) በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ የማጥመቅ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩት መምህር ግርማ ወንድሙ ካሁን በኋላ በደብሩ ውስጥ እንዳያጠምቁ በደብሩ አስተዳደር መልአከ ኃይል አባ ሚካኤል ታደሰ (ቆሞስ) ሚያዚያ 28 ቀን 2005 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ታገዱ። የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ምንጮች ደብዳቤውን አግኝተው አድርሰውናል። ለ እገዳው ምክንያትነት የቀረቡት አካባቢው የቱሪስት ቦታ ስለሆነ ለጸጥታ እና ለንጽህና የሚሉ ይገኙበታል።

“በደብሩ ውስጥ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ እየፈጸሙ ያለውን የማጥመቅ ሥራ ማገድን ይመለከታል” በሚል ለመምህር ግርማ በተጻፈው ደብዳቤ ላይ ከዚህ በፊትም መምህሩ እንዳያጠምቁ ታግደው የነበረ ቢሆንም ጉዳዩ ሳይፈጸም መቆየቱንና ከሚያዝያ 28 ጀምሮ ግን መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው እስጢፋኖስ ቤ/ክ እንዳያጠምቁ ታግደዋል።

እገዳው ለምን እንዳስፈለገ ደብሩ በጻፈው ደብዳቤ ላይ “የብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ በ/አ/አ/ሀ/ስ የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሰኔ 8 ቀን 2003 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር 4290/90/03 የሰጡት የእገዳ ትዕዛዝ ያልተነሳና ያልተሻረ በመሆኑ፤ በግቢው ውስጥ ያለው ሁኔታ ለሃገርም ሆነ ለቤተክርስቲያኒቱ ሰላም አስጊ በመሆኑ፣ በተጨማሪም ደብራችን የአዲስ አበባ እንብርት በሆነው በመስቀል አደባባይ አካባቢ፣ በአፍሪካ ህብረት እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤትና በታላቁ ቤተመንግስት አካባቢ በመገኘቱ ምክንያት ሰላማዊ ቦታ መሆን እንዳለበት ከዚህም ሌላ በብዙ የውጭ ሃገር ዜጎች ቱርስቶችም በተደጋጋሚ ቦታው ስለሚጎበኝ በሰላም ገብተው እንዲገለገሉ እና እንዲጎበኙ፤ ንጽህናው የተጠበቀ፣ ሰላም እና ጸጥታ የተሞላ የጸሎት ስፍራ መሆን እንዳለበት ሰበካ ጉባኤው ስላመነ፤ አሁን እየተፈጠረ ካለው ችግር አንጻረና የተጀመረውም የማጣራት ሥራ ተጠናክሮ የማያዳግም ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ከዛሬ ሚያዝያ 28 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ለጊዜው የማጥመቅ አገልግሎትዎን እንዲያቆሙ የደብሩ አስተዳደር ሰባካ ጉባኤ ጽ/ቤት የ እግዳ ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔውን ባለማክበር በቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ዋነኛ ተጠያቂ መሆንዎን እናስታውቃለን” ይላል።

የዘ-ሐበሻ ምንጮች ደብዳቤውን አድርሰውናል ይመልከቱት፦
memeher girma

↧

ዴቪድ ሞይስ ሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ተኩ

$
0
0

fergusen davids moyesአብርሃም አያሌው

ማንችስተር ዩናይትድ ስኮትላን ዳዊውን ዴቪድ ሞይስን የሰር አሌክስ ፈርጉሰን ምትክ አድርጐ ሰየመ።
የቢቢሲ ዘገባ እንዳ መለከተው የ50 ዓመቱ ዴቪድ ሞይስ እ.ኤ.አ ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለስድስት ዓመታት ክለቡን እንዲያሰ ለጥኑ ተቀጥረዋል።
ሞይስ የኤቨርተን ክለብን እ.ኤ.አ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ላለፋት 11 ዓመታት አሰልጥነዋል።
ያልተጠበቀውን ከአሠልጣኝነት የመሰናበት ዜና ከትናንት በስቲያ ይፋ ያደረጉት የ71 ዓመቱ ሰር አሌክስ «በዴቪድ ሞይስ ሁላችንም ያለልዩነት ተስማምተናል» ሲሉ ተናግረዋል።
«ዩናይትድን ሊያሰለጥን የሚገባው አንድ አሠልጣኝ ሊያሟላው የሚገባው ብቃት ሁሉ ከሞይስ ዘንድ አለ» ሲሉም ተሰናባቹ አሰልጣኝ አዲሱን የኦልድ ትራፎርድ መሪ አሞካ ሽተዋል።
በክለቡ ቦርድ የተሾ ሙት ሞይስ በበኩ ላቸው «ይህ ታላቅ ክብር ነው፤ ሻምፒዮን ቡድንን ለማሰል ጠን በታላቅ ሰው ተመ ራጭ መሆን ያስደ ስታል፤ ሥራው እንደሚ ከብድ አውቃለሁ ፤ ያም ሆኖ በሆነው ሁሉ ተደስ ቻለሁ» በማለት ሃሳባ ቸውን ገልጸዋል።
27 ለሚጠጉ ዓመታት ዩናይትድን ያሰለጠኑት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ክለቡን ለ13 የፕሪሚየር ሊግ ፤ አምስት የኤፍ ኤ ካፕና ለሌሎችም ለበርካታ ዋንጫዎች ክበር አብቅተዋል።
ከመጪው የውድድር ዘመን ጀምሮም በክለቡ ዳይሬክተርነትና አምባሳደርነት እያገለገሉ በኦልድትራፎርድ እንደሚቆዩ ታውቋል።

↧

ወያኔ ባለስልጣናቱን አቶ መላኩ ፈንታን እና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን አሠረ

$
0
0

አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ

አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ

ብአዴኑ መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።

ብአዴኑ መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።


(ዘ-ሐበሻ) የወያኔ ሥርዓት በኢትዮጵያ ብቻውን ያሸነፈበትን ምርጫውን ሙሉ በሙሉ አሸንፌያለሁ በሚል ከማወጁ አስቀድሞ የሕዝቡን ስሜት ለመቀየር አቶ መላኩ ፈንታ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርን እና ምክትላቸውን አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ 12 ሰዎችን በሙስና ጠርጥሮ ማሰሩን በሰበር ዜና አብስሯል።
መላው የወያኔ/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት በሙስና የተጨማለቁ መሆናቸው በይፋ የታወቀ ሲሆን ስርዓቱ የጸረሙስና ሕጉን የፖለቲካ ልዩነት በሚያሳዩ ባለስልጣናት ላይ ብቻ ተግባራዊ በማድረግ ሲተች ቆይቷል የሚሉ ታዛቢዎች ከዚህ ቀደም አቶ ታምራት ላይኔ በሙስና ሲታሰሩ፣ አቶ ስዬ አብርሃ ከነቤተሰባቸው ዘብጥያ ሲወርዱ፣ አቶ ቢተው በላይ እና አባተ ኪሾም እንዲሁ ከርቸሌ ሲወረወሩ የጸረሙስና አዋጁ ተግባራዊ የሆነባቸው ከድርጅታቸው ጋር የፖለቲካ ልዩነት በማምጣታቸው እንጂ እውን አዋጁን ተግባራዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ አለመሆኑን በአስተያየታቸው ላይ ተናግረዋል።
አቶ ይሁን ተድላ የተባሉ ታዛቢ የዛሬውን የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣናት መታሰርን ተከትሎ የሰጡት አስተያየትም ከዚሁ የሚለይ አይደለም። እኚህ አስተያየት ሰጪ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ “አቶ መላኩ ፈንታ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለእስር የተዳረጉበት ወቅታዊ ምክንያቱ በ አማራው ብሔር ከደቡብና ከቤንሻንጉል ክልል መፈናቀል ጉዳይ ላይ በብአዴን ውስጥ በተፈጠረ የተለያየ አቋም ድርጊቱን በተመለከተ ግለሰቡ ህወሃት ላይ ጣታቸውን በመቀሰራቸው ነው የሚል ጥርጣሬ አለ። ወያኔ ታማኝ አገልጋዮቹን ለክፉ ጊዜ ብሎ ባሰናዳላቸው ወጥመድ በቀላሉ ወንጅሎ ወደ ወህኒ ሊያወርዳቸው እንደሚችል የተረጋገጠ ነው። በመሆኑም የአቶ መላኩ ፈንታ አሁን ተይዘው ወደ እስር ቤት የተወሰዱበት ምክንያት ሁሉም የኢህአዴግ አባላት ንጹህ በማይሆኑበት ሙስና ተጠርጥረው ነው የሚለው ፕሮፓጋንዳ ሚዛን የሚደፋ አይደለም። ከደብረፅዮን ቢሮ ሾልኮ የወጣው ወሬ እንደሚያመለክተው ከሆነ አቶ መላኩ ፈንታ ለጊዜው ወደ አልታወቀ ሀገር ለመኮብለል ሲዘጋጁ ኤሌክትሮኒክ መልዕክታቸው በመጠለፉ ነው።በዚህ ላይ አቶ መላኩ ፈንታ በሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በሃላፊነት ሲሰሩ የሚያውቁት የደህንነትና የድርጅት ሚስጥሮች ስላሉ የግለሰቡ ከሀገር መኮብለል ተመጣጣኝ ስልጣን እንደነበራቸው አቶ ጁነዲን ሳዶ ኩብለላ በቀላሉ የሚታይ አይደለም በሚል የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።አብረዋቸው የተያዙት የህወሃቱ እና ሌሎች ባለስልጣናት ግልፅና ተጨባጭ ከሆነው የባለሥልጣኑ መስሪያ ቤት የሙስናና የአሰራር ንቅዘት አኳያ አቶ መላኩ ፈንታ ለታሰሩበት እውነተኛ ምክንያት ጥሩ የወያኔ ሽፋን እና ማጭበርበሪያ እንደሚሆኑ ታዛቢዎች ይገልፃሉ።” ይላሉ።
የኢቲቪን ዜና ይመልከቱ፦
↧

የታሰሩት ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች ስም ዝርዝር (ይዘናል)

$
0
0

ብአዴኑ መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።

የአማራ ሕዝብ መፈናቀልን ተቃውመዋል በሚል በወያኔ ጥርስ ውስጥ እንደገቡ የሚነገርላቸው ብአዴኑ መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።


(ዘ-ሐበሻ) በትናትናው የዜና ዘገባችን አቶ መላኩ ፈንታ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርን እና ምክትላቸውን አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ከነዚህ ሁለት ባለስልናት ጋር የታሰሩት ሌሎች 11 ባለሃብቶችና ባልስልጣናት ስም ዝርዝር ድርሶናል። ለግንዛቤዎ ያንብቡት።
1.እሸቱ ወልደሰማያት – በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
Eshetu Wodesmayat – Prosecutor Directorate Director at ERCA
2.አስመላሽ ወልደማሪያም- የቃሊቲ ጉምሩክ ኃላፊ
Asmelash Woldemariam- Kaliti Customs Head
3.ጥሩነህ በርታ- በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቡድን መሪ
Tiruneh Berta – ERCA Confiscation Admin Group Head
4.አምኘ ታገለ- የናዝሬት ጉምሩክ ኃላፊ
Amogne Tagele – Nazret Customs Head
5.ሙሉጌታ ጋሻው- በኦሮሚያ ልዩ ዞን መሀንዲስ
Mulugeta Gashaw – Oromia Zone Engineer
6.ከተማ ከበደ- የኬኬ ትሬዲንግ ባለቤት
Ketema Kebede – Owner of KK Trading
7.ስማቸው ከበደ- የኢንተርኮንቴንታል ሆቴል ባለቤት
Semachew Kebede – Owner of Intercontinental Hotel
8.ምህረት አብ አብርሀ- ባለሀብት
Mehreteab Abraha – Investor
9.ነጋ ገብረእግዚአብሄር- የነፃ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤት
Nega G/Egziabher – Owner of Netsa Trading PLC
10.ዘሪሁን ዘውዴ -ትራንዚተርና ደላላ
Zerihun Zewede – Transistor and Broker
11.ማርሸት ተስፉ – ትራንዚተርና ደላላ ናቸው፡፡
Marishet Assefa – Transistor and Broker
↧
↧

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደርግ አልነበረችም፤ የወያኔም አይደለችም፤ የቅንጅትም አትሆንም

$
0
0

የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ

የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ

አብርሃም ሰሎሞን ግንቦት ፫/፳፻፭ ዓ.ም.
መለያየት ይብቃ፤ ገለልተኛ ሆኖ መቀመጥም ይቅር። ቅዱስ ሲኖዶስ አንድ ነው፤ መንበሩም ያለው ኢትዮጵያ ነው። ሃያ ዓመታት ያስቆጠረው የመለያየት ግድግዳ ይፍረስ፤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር አንድ እንሁን። ልጆቻችንን አንድነት እንጂ መለያየትን አናስተምራቸው፤ አባቶቻችን ያቆዩልንን ሥርዓትም አናጥፋው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከእራስዋ ልጆች ፓትርያርክ ለመሾም የወሰደባት ጊዜ ምን ያህል አድካሚ እንደነበር እናስብ፤ የተከፈለውንም የጊዜ፣ የገንዘብ፣ የጉልበት እና የሕይወት መሥዋዕት አንዝንጋ። ወ.ዘ.ተ. በማለት የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት አባቶችና መምህራነ ወንጌል አብይ ጾም ከመግባቱ በፊት በነበሩት ተከታታይ ሳምንታት በአውደ ምሕረት ላይ ስብከት መስበክ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ “ቤተ ክርስቲያናችንን ለወያኔ አሳልፈው ሊሰጡ ነው።” የሚል ዜና አልፎ አልፎ ከመሰማቱ ባሻገር በሚኒሶታ ውስጥ ባሉ የመገናኛ አውታሮች፣ በድረ-ገጽ፣ በኢሜል እና በጽሑፍም ሲሰራጭ ቆይቷል። በተለይም በሰሞነ ሕማማት ጊዜ የጌታን ነገረ ስቅለት እያሰቡ ሰዎች በጾም፣ በጸሎት እና በስግደት ሳምንቱን እያሳለፉ ባሉበት ወቅት የካህናተ ቤተ ክርስቲያኑን ፎቶግራፍ በድረ-ገጽ ላይ እና በኢሜል ላይ አውጥቶ “እሪ በል ሚኒሶታ ቤተ ክርስቲያንህ ለወያኔ ሊሰጥ ነው” በሚል ቅስቀሳ ጽሑፍ መበተኑም አይዘነጋም፤ ሁኔታውም እጅግ ያሳዝናል።
ከላይ በርእሱ ላይ እንደገለጽኩት ማንም ሰው እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባልነቱ ሊቀበለው የሚገባው ጉዳይ እና እውነታ ቢኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደርግ አልነበረችም፤ የወያኔም አይደለችም፤ የቅንጅትም አትሆንም የሚለውን ኃይለ ቃል ነው። ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ዘመን ተቆጥሮላቸው የሚያልፉ የፖለቲካ ድርጅቶች ወይም የመንግሥት አካሎች ሳትሆን ዘላለማዊት ናትና። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስንም ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ቤተ ክርስቲያን ሲያስተምረው፦ ጴጥሮስ አንተ አለት ነህ በአንተ ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሀነም ደጆችም አይችሉአትም ብሎ ተናግሮታል። አንግዲህ ጌታችን ቤተ ክርስቲያኔን እያለ ከተናገረና ካስተማረን ስለ ምንድን ነው ቤተ ክርስቲያንን ለወያኔ ሊሰጡት ነው እየተባለ አባላቱን ግራ ማጋባት የተፈለገው? ቤተ ክርስቲያን ያዘነ የሚጽናናባት፣ የደከመ የሚበረታባት፣ የወደቀ የሚነሳባት፣ ንስሐ የሚገባባት፣ ቅዱስ ሥጋው እና ክቡር ደሙ የሚሰጥባት በአጠቃላይ ነፍስ የሚድንባት እንጂ የምድራዊ ፖለቲካ የሚነግርባት እና የእነእገሌ ድርጅት ናት የምትባል አይደለችም።
ቅዱስ ዳዊት አእምሮ ያለው ክቡር ሰው እንደሚጠፋ እንስሳ መሰለ ብሎ እንደተናገረው ተነጋግረን መግባባት ስንችል ውይይትን እንደ ጦር ፈርተነው “ከተነጋገርን እንለያያለን፤ እንበታተናለን” በሚል ፍራቻ ገለልተኛ እንደሆንን እንቀመጥ ማለቱ አግባብ አይደለም። እኛ እንደ ሰውነታችን “ከተነጋገርን እንግባባለን፤ እንስማማለን” ብለን በማሰብ ለውይይት መቀመጥ ይኖርብናል። ከቤተ ክርስቲያን ሕይወት የተለየ አመለካከት ከሌለው ሰው በቀር መንፈስ ቅዱስ ሆይ አንተ እርዳን ሕፃናት የሚያድጉባት፣ ልጆች የሚማሩባት፣ ሃይማኖት የሚሰበክባት እና ፍጹም ኦርቶዶክሳዊት አስተምህሮ የሚሰጥባትን ቤተ ክርስቲያንህን ልንሠራ ተዘጋጅተናልና በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልዩነትን አጥፍተን በአንድነት የምንጓዝበትን መንገድ አቅናልን ብለን በተሰበረ ልብ ለውይይት ከተቀመጥን ከሳሻችን ዲያብሎስ ያፍራል፤ እግዚአብሔር በግብራችን ይደሰታል። አላማችን ግን የፖለቲካ አመለካከትን ከቤተ ክርስቲያን አመለካከት ጋር አንድ አድርገን እናራምዳለን ከሆነ ሁለት የማይገናኙ ሐሳቦችን ለማገናኘት እየተሞከረ በመሆኑ ድካማችን ከንቱ ይሆናል፤ ጥረታችንም ይመክናል። ዓለም በምድራዊ ፖለቲካ ትመራለች፤ በዓለማችን ውስጥም ፖለቲካ የእራሱ የሆነ መንገድ እና ግንዛቤ ኖሮት በትምህርት ታግዞ ብዙኻን እየሠሩበት ይገኛል። በመሆኑም ፖለቲካ በቦታው መልካም እንደሆነ እናምናለን፤ ተቃውሞም አይኖረንም። በየትኛውም ቦታ ያሉ አካላት ግን ቤተ ክርስቲያንን የፖለቲካ ድል ማግኛ ሊያደርጉ አስበው ከሆነ ትክክለኛ መንገድ ላይ አለመሆናቸውን ሊረዱት ይገባል። ምክንያቱም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፖለቲካ እና ጫማ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መግባት የለበትም።
ኢትዮጵያ ለጠላት ያልተንበረከከች አገር እንደሆነች ታሪክ ሲያስተምረን ቆይቶ በርስ በርስ ጦርነት ግን ስትጠፋ አየናት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ባለ ታሪክ ሆና ከሐዋርያት ጀምሮ ትክክለኛውን መንገድ ስትመራ ቆይታ አሁን ዘመን ሰለጠነ ሲባል ልጆቿ ከሰላም ይልቅ ጦርን ከአንድነት ይልቅ መለያየትን መርጠን የአገር ውስጥ እና የውጭ ሲኖዶስ በማለት ተለያየን። ቤተ ክርስቲያንን መደበቂያ አድርገው ፖለቲካቸውን ለማስፋፋት የሚሞክሩትን ሁሉ ልብና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ መልሱን ይሰጣቸዋል። በቅንነት ቤተ ክርስቲያን ተገፍታለች ልናድናትና ልንደርስላት ይገባናል ብለው ለተነሱትም እግዚአብሔር ያግዛቸዋል። የሰው ዝምታ ፍርሐት መስሎ ሊታይ ይችላል፤ የእግዚአብሔር ዝምታ ግን ያስፈራል። ለቤተ ክርስቲያን አምላክዋ ነውና ቤተ ክርስቲያን ስትገፋ ዕለት ዕለትም ስትታወክ ያለ መልስ ዝም አይልም። እግዚአብሔር ሲወረውር አይታይም ሲጥል ግን ይታያል። የሰላም መድረክ እንዳይፈጠር ስምን ደብቆ በብዕር ስም መዋጋት አይጠቅምም። ሁላችን ከአንድ ገበታ ቆርሰን የበላን ወንድማማቾች እና እኅትማማቾች ሆነን ሳለ እንደ ጠላት ልንተያይ የምንዘጋጅበት ወቅት መሆንም ባልተገባ ነበር። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በግልጽ ካልተነጋገርን በየትኛው ስፍራ ተወያይተን ወደ አንድነት እንመጣለን? አንተ ማነህ? አንቺ ማነሽ? እናንተስ ማናችሁ? እኛስ ማነን? ሳንደባበቅ በገሐድ እንወያይና ቤተ ክርስቲንን የሰላም ቤት እናድርጋት።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ መልእክቱ ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ። ያለው ቃል እንዲፈጸምብን አያስፈልገንም። ጌታችን በወንጌል እንዳስተማረን እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ልንሆን ይገባል። ልባሞች ብቻ ሆነን የዋህነትን ሳናክልበት ከቀረን አስተዋይ እንደ እኛ ከየት ይመጣል በሚል ትዕቢት እንወድቃለን። የዋሆችም ብቻ ሆነን ሥርዓት ሲፈርስ፣ ሃይማኖት ሲጠፋ፣ ፍርድ ሲሳሳት እና ፍትህ ሲመዘበር ዝም ካልን ቤታችንን እናፈርሳለን። በመሆኑም እርስ በርሳችን ስንነካከስ እንዳንጠፋፋ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሚመራት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከጸሎት ጋር የተሰበረው እንዲጠገን፣ የተበላሸው እንዲስተካከል፣ የተጣመመው እንዲቃና እና የተለያየው አንድ እንዲሆን በውጭ ሆነን ሳይሆን በውስጥ ገብተን ተሰልፈን ቤተ ክርስቲያንን ወደ ቀደመ ክብርዋ እንመልሳት። ይኽም ማለት በውስጥዋ አባት እና ልጆች ተከባብረውባት፣ ወንድማማቾችና እኅትማማቾች ተፈቃቅረውባት እንመልከታት ማለት ነው። ቀርበን ሳንወያይ በስማ በለው ብቻ አንተ እንዲህ ነህ፤ አንቺ እንዲያ ነሽ ብንባባል የሰይጣን ዲያብሎስ መሳለቂያ ከመሆን በቀር ሌላ አንዳች ነገር አናመጣም። እውነት ገንዘባችን ሃይማኖት ከሆነ ስለ ምንድን ነው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለውይይት ቀርበን ችግራችንን ተነጋግረን ቤተ ክርስቲያንን ለተተኪው ትውልድ በፍቅር ለማስረከብ የማንዘጋጀው? ነቢዩ ኢሳይያስ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? ብሎ የተናገረው ቃል በገሐድ ሲፈጸም እያየነው ዛሬም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ብቻ በእኛ የርስ በርስ ችኩቻ አዛውንቱ፣ ወጣቱ እና ታዳጊ ሕፃናቱ በመናፍቃን ሲወሰዱ እየሰማን ብቻ ሳይሆን እያየንም ባለንበት ሰዓት የእነእገሌ ሐሳብ እኛን አያሸንፈንም ተባብለን በእልህ መንገድ ስንጓዝ ቤቱ ባዶውን እንዳይቀር ያስፈራል። ሁለት ሰዎች ሳይነጋገሩ ተፈራርተው ብቻ ያኛውም መጣብኝ ብሎ ወደ ኋላው ሲያፈገፍግ ይኽኛውም ያጠቃኛል ብሎ አስቦ አካባቢውን ሲለቅ ምድሪቱ ብቻዋን ያለ ሰው ቀረች ይባላል። እኛም ተፈራርተን የእኛ ሰዎች እነእገሌ ብቻ ናቸው ስንባባል በመሐል ሃይማኖታችን፣ ፍቅራችንን እና አንድነታችን አጥተን እንኖራለን።

ስለዚህም የቤተ ክርስቲያናችን ሽማግሌዎች አሁን ወቅቱ ልዩነትን አጠንክራችሁ የምትሰብኩበት እና የምትነጋገሩበት ሳይሆን በቀሪው ዕድሜአችን ለወጣቱ ምን እናስተምረው የምትሉበት በመሆኑ በምትገናኙበት ሁሉ ስለ ሰላም መክራችሁ ቤተ ክርስቲያንን የሰላም መድረክ ለማድረግ ተዘጋጁ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ብሎ እንዳስተማረን በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይጥለቅባችሁ። የቃሉ ምስጢር ጠዋት ጀምበር ሲወጣ የተጣላን ማታ ጀምበር ሳይጠልቅ በአንድ ቀን ውስጥ እንታረቅ ሳይሆን ሞት መጥቶ ሳይወስደን እና ለዘላለም ጀምበር ሳይጠልቅብን እንታረቅ ማለት ነው። ስንቶች አባቶቻችን፣ እናቶቻችን፣ ወንድሞቻችን እና እኅቶቻችን የጥሪያቸው ቀን ደርሶ ቤተ ክርስቲያን እንደተለያየች ጀምበር ጠለቀባቸው!!!! ይኽ ሊያሳዝነን ይገባልና አሁንም ልባሞች ሆነን በዚሁ ትውልድ ወደ ሰላም መንገድ እናቅና። የዕድሜ ባለፀጋ አባቶቻችን በዚህ ነገር እርዱን። እንባችሁ እንደ ራሔል እንባ ፀባኦት የሚደርስ እናቶቻችን ከጸሎት እና ከልመናችሁ ባሻገር የቤተ ክርስቲያን ውስጥ መለያየት እንዲወገድ በየቤታችሁና በያላችሁበት ተነጋገሩ። የእምነት ጽናታችሁ የሚለካበት ሚዛን የሚሰፈርበት መስፈሪያ የለውምና። ወጣቶች ሁላችሁ እንደየዕድሜ ደረጃችሁ የመለያየት ነገር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምን ያህል እንዳቆሰላችሁ ታውቁታላችሁና ምንም እንኳን መንገዱ አልጋ በአልጋ ሆኖ ያረማምደናል ብለን ባናስብም ለዘመናት ተለያይተን ያመጣነው ነገር ስለሌለ ቤተ ክርስቲያንን ሌላ አንዳች ነገር ሳንጨምርባት እንደ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ተመልክተናት በቀኖናም፣ በሥርዓትም፣ በዶግማም፣ በዶክትሪንም አንድ ሆነን መራመድ የምንችልበትን ጉዳይ አጥብቃችሁ እሹ። ሕፃናቱ በእጃችን ስለወደቁ የሕፃናቱን ነገር እኛ እናስብላቸው፤ ያልተለያየች ቤተ ክርስቲያን ተመልክተው በጳጳስ ተባርከው ይኑሩ። ይኼንን ባናደርግላቸው ለውደቅታቸው ምክንያት እኛ መሆናችንን አንዘንጋው። አገራችን ኢትዮጵያ ፈተና ገጥሟታል፤ ልጆች ሞተውባታል፣ የንጹሐን ደም ፈስሶባታል፤ በእስር ቤት ውስጥ ያለ ፍርድ የተዘጉ ኢትዮጵያውያን ሞልተውባታል። ለዚህና ይኼን ለመሳሰለው ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች እናዝናለን። ሆኖም ከችግር ለመውጣት ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ተለይቶ ለብቻ መሆን መፍትሔ አያመጣም። መለያየት የሥጋ ሥራ ነውና እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እንጓዝ። ይቆየን!!

↧

የፍትህ ሚ/ሩ ብርሃን ኃይሉ ከስልጣናቸው ተባረሩ

$
0
0

አቶ ብርሃን ኃይሉ ስዊድናዊያኑ ጋዜጠኞች በይቅርታ ተለቀዋል በሚል መግለጫ የሰጡ ዕለት የተነሱት ፎቶ ነው።

አቶ ብርሃን ኃይሉ ስዊድናዊያኑ ጋዜጠኞች በይቅርታ ተለቀዋል በሚል መግለጫ የሰጡ ዕለት የተነሱት ፎቶ ነው።

(ዘ-ሐበሻ) በዚህ ዓመት ማርች 2005 ዓ.ም ባህርዳር ላይ በተደረገው የኢሕአዴግ ጉባኤ ላይ ከ255ቱ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚዎች መካከል ብአዴንን ጥላቸው አድርገው በድጋሚ ተካተው የነበሩት የፍትህ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ሃይሉ የአቶ መለስን የሕወሓት የበላይነት ሌጋሲ አስፈጻሚው ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ፊርማ መባረራቸው ተሰማ።
ቃሊቲን ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች በሃሰተኛ ሕወሓት ሠራሽ ክሶች ወደ ዘብጥያ ሲወረወሩ ይህን ሃሰተኛ ክስ በማስፈጸም ታማኝነታቸውን ሲያሳዩ የከረሙት አቶ ብርሃን ሃይሉ ከስልጣናቸው መነሳት አሁንም ለሆዳቸው አድረው ከመንግስት ጎን በመቆም የሕወሓትን የበላይነት ለማንገሥ እየሰሩ ላሉት ባልሰልጣናት ትምህርት ይሆናቸዋል የሚሉ አስተያየቶች እየተሠነዘሩ ነው።
በአሁኑ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ በአንካሳ ሕግ እስር ቤት ለሚማቅቁት ወገኖች አናካሳውን ሕግ በማስፈጸም ረገድ ተጠያቂ እንደሆኑ በህዝብ ዘንድ የሚመሰከርባቸው አቶ ብርሃን ሃይሉ ከዚህ ቀደምም በፈረሰው ማስታወቂያ ሚ/ር በሚኒስትርነት ማዕረግ በመሥራት የሕወሓት መንግስት የነደፈውን የመናገር መብትንመንፈግን ሲያስፈጽሙ ቆይተዋል።

ሚንስትሩ እ.አ.አ በ2005 ዓ.ም. በማስታወቂያ ሚንስትርነት ሲሰሩ ነበር። ሆኖም ማስታወቂያ ሚንስትር እንዲፈርስ ሲደረግ፤ በቀጥታ ሌላ ሹመት በማግኘት የፍትህ ሚንስትር ሆነው ኢህአዴግን በታማኝነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ከሰሞኑ የባልስልጣናት በሙስና መታሰር፤ የአቶ ብርሃን መባረር ኢሕአዴግ ውስጥ ያለውን ሽኩቻ ያሳየ ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎ አብዛኛው የኢሕ አዴግ ባልስልጣናት በሙስና ተጨማልቀው እያለ እነዚህ አሁን የታሰሩትን፤ ሁሉም የኢሕ አዴግ አመራሮች የአምራርነት ብቃት የሌላቸው መሆኑ እየታወቀ ጊዜ ጠብቆና ባልስልጣናቱ ለምን? ማለት ሲጀምሩ እንደብርሃን ኃይሉ ከስልጣን ማሰናበት የተለመደ የወያኔ የፖለቲካ አካሄድ ነው ሲሉ ሃሳባቸውን ይሰነዝራሉ።

አቶ ብርሃን ኃይሉ ሥልጣን ላይ በነበሩ ጊዜ ስለ እስክንድር ነጋ ጠረጴዛ እየመቱ የተናገሩትን ለግንዛቤ እንደሚከተለው ቪድዮውን አቅርበነዋል።

↧

ተገፊዎች የባህሪ ለውጥ ኣምጡ እንጂ! ከገለታው ዘለቀ

$
0
0

ከ ገለታው ዘለቀ

comment_stage_5ልትታተም ካሰበች ኣንዲት ልቦለድ ጽሁፍ ላይ ኣንድ የምናብ ሰው ከተገረመበት ነገር ተነስተን ኣጭር መልእክት ለማቀበል እንሞክራለን። ይህ የምናብ ሰው ወደ ኣንድ ሃገር ይሄድና በዚያ በኣንድ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ ናሽናል ጂኦግራፊ የተሰኘውን የ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ያያል። በወቅቱ ይተላለፍ የነበረው ፕሮግራም የዱር እንስሶች ኑሮ ነው። ይህ የምናብ ሰው ከኣልጋው ጫፍ ላይ ቁጢጥ ብሎ ረጃጅም ጢሙን ቁልቁል እየላገ ይህን ፕሮግራም ያያል። የሚያማምሩ የሜዳ ኣህያዎች መንጋ ረጋ ብሎ ሳሩን ይግጣል። ጥቂት ሳይቆይ ከረጃጅሙ ሳር ውስጥ ሲሹለከለኩ የነበሩ ሶስት ጅቦች መጡ። ኣንዱን ጅብ ቀድሞ ያየው የሜዳ ኣህያ ሩጫውን ሲቀጥል ሌላው ነገሩ ያልገባው ሁሉ ተከትሎ ይሰግር ጀመር።

የሜዳ ኣህያዎቹም ተፋፍገው ሲሮጡ ኣንድ ወደ ሁዋላ ቀረት ያለ የሜዳ ኣህያ  ነበርና ኣንዱ ጅብ ከሆዱ ቆዳውን ሊዘነጥል ይጥራል። ይህ የሜዳ ኣህያ እግሮቹን እያወራጨ ለማምለጥ ይጥራል። ትግሉ ከሚሮጡት ጋር ሩጫውን ለመቀጠል እንጂ የሚነክሰውን ጅብ ለመጉዳት ኣይደለም።

ሌሎቹም ጅቦች ተጋገዙና ምን ዋጋ ኣለው ይህን የሜዳ ኣህያ ሆዱን ዘረገፉት።

ያ የምናብ ሰው ተገረመ። ኣየ ኑሮ…………

ወደ ሌላ ኣንዲት ወንዝ ስር ጥሙን ሊያረካ ውሃ ከሚጠጣ ሌላ ያማረ የሜዳ ኣህያ ጋር ካሜራው ወሰደው። ይህ የሜዳ ኣህያ ሁለት የፊት እግሮቹን  ፈርከክ ኣርጎ እንዴው እግዜር የሰጠውን ውሃውን በፍቅር ይስባል። ጥቂት ሳይቆይ ኣንድ ሌላ ጅብ ከሁዋላው ዘሎ ከሆዱ ቆዳውን ሊዘነጥል ትግል ጀመረ። ይህ የሜዳ ኣህያ ከወራጁ ወንዝ ጫፍ ላይ ተክሎት የነበረውን ኣፉን ነቀል ኣረገና ወደ ሁዋላ በቅጽበት ዞረ። የሚታገለውን ጅብ እንደሌሎቹ የሜዳ ኣህያዎች በርግጫ ብሎ ለማምለጥ ኣይጥርም። ኣንገቱን ጠምዝዞ ኣንድ ሁለቴ ዞረና ወደ ሆዱ ገብቶ ቆዳውን ሊዘነጥለው የሚታገለውን ጅብ ጉሮሮ ኣስግጎ ኣገኘውና በዚያ ላይና ታች ክችም ባለ ጥርሱ የጅቡን ጉሮሮ ቀርጥፎ ይዞ ትግል ተጀመረ። ኣሁን ጅብ ማጥቃቱን ትቶ ራሱን ለማዳን እየታገለ ነው። ነገር ግን ኣልሆነም።  ይህ የሜዳ ኣህያ የዋዛ ኣልነበረም። ጥቂት ደቂቃዎች ከታገሉ በሁዋላ ጅቡ መታገሉን ሲያቆም የሜዳው ኣህያ ሙሉ በሙሉ ከሜዳው ላይ ኣንጋለለውና ያየው ጀመር። ጥቂት ኣሸተተውና ጥሎት ለመሄድ ርምጃ ሲጀምር ኣንድ ሌላ ጅብም መጣ።  ያ  የሜዳ ኣህያ በሃይል ወደ ጅቡ መሮጥ ሲጀምር ጅቡም ቂጡን ጥሎ ሮጠ።

የምናቡ ሰው ይህን ነገር እያየ ተገረመ። ለካ ይሄ የሜዳ ኣህያ ብቻውን በዚህ ጠራራ ጸሃይ በዚህ ወንዝ ሥር የሚያንቀባርረው የባህሪ ለውጥ ኣምጥቶ ነው። እየተራገጡ መሮጥን ኣቁሞ መናከስ ጀምሩዋል። ይህ የባህሪ ለውጡም ከተጠቂነት ወደ ኣጥቂነት ኣሸጋግሮታል እያለ ይደነቃል…………

በኣንድ ሃገር የሚኖሩ ህዝቦች ኣንዳንዴ ጅብ በሆነ ስርዓት ይጠቃሉ። ጥቂት ቡድኖች ያለውን የሃገሪቱን ሃብት ተቆጣጥረው ኣብዛኛውን ሰው ጦሙን ያሳድሩታል። የኢኮኖሚው ሰፊ ልዩነት ሌሎች የህይወት ዘርፉን ሁሉ ያጠቁትና ያልተመጣጠነው እድገት በፍትህ ፊት፣ በባህልላዊ ቡድን፣ በኣጠቃላይ በኑሮ ዘየ ሁሉ ከባድ የእኩልነት እጦትን ይስብበታል።

ዛሬ ኢትዮጵያ ቢሊየነር ሁሉ ያላት ኣገር ናት። በሌላ ጥግ ደሞ የ ዓለምን የመጨረሻ ድህነት የሚኖሩ ብዙ ህዝቦችም ኣሉባት፣ ይህ ሰፊ ያልተመጣጠነ እድገት በተወሰነ ደረጃ ቢሳለጥ ኣሁን ያለው የድህነት ገጽታ መልኩን ይቀይር ነበር። የገቢ ኣለመመጣጠን ስንል ሁሉ እኩል ይካፈል ማለታችን ኣይደለም። ሁላችን እኩል በመካፈላችንም ፍትህ ኣይሰራም። ግን ደሞ ለሃብታሙ ህንጻ የሚሰራው ወዛደር ቢያንስ ቤት ኣከራይቶ የቀን ኑሮውን የሚገፋበትን ሊከፍለው ይገባል። ቀን ቀን ኣሸዋና ሲሚንቶ ሲያቦካ ውሎ ለምን ጎዳና ላይ ይወድቃል? መንግስትስ እንዲህ ያለውን ኣስከፊ ስርዓት ለምን በተወሰነ ደረጃ ኣያጠብም? ለምን ፖሊሲ ኣያወጣም?። የካፒታሊዝም ጽንሰ ሃሳብ እኮ እንደዚህ ኣይደለም።  ካፒታሊዝም ፍትህ ኣለው። ዜጎች ባላቸው የሥራ ኣቅም እየሰሩ የተለያየ የገቢ መጠን መኖሩ ትክክል ነው። ይሁን እንጂ ድሃውን ያለልክ ጎድቶ ሃብታሙን ያለልክ ማበልጸግ የካፒታሊዝም ስርዓት ልብ ኣይደለም።

የሚገርመው ስርዓቱ ፍትሃዊ ባይሆንም እነዚህ ዜጎች ኣይናከሱምና ኑሮኣቸው ሁሉ የሚያሳዝን ይሆናል::

ደሞ መንግስት ሥራ ጠፋ ሲሉት ሥራ ንቃችሁ ነው ኣይነት ይናገራል። ተናቀ የተባለው ስራ ምንድን ነው? ብላችሁ ብትጠይቁ ያው የወዛደርነት ሥራ ነው። የመጀመሪያው ጥያቄ ታዲያ ኣሁን ይህ ሚሊዮን ሥራ ኣጥ በቃ ሥራ ኣንንቅም እሺ ወዛደርነቱን እንሥራ ብሎ ቢወጣ ይህንን የሚያስተናግድ ኢንዱስትሪ ወይም የኮንስትራክሽን ስራስ የታለና ነው? የትኛው የፋብሪካ ስራ ወይም የኮንስታራክሽን ስራ በወዛደር እጦት ስራ ኣቆመ?

እውነቱን ለመናገር ኣንዳንድ ሰው ወደ ወዛደርነት ስራ የማይሳበው ገቢው ስላነሰ ወይም ስለማያኖረው ነው። በሃገራችን ውስጥ የሲቪል ኤንጂኔር ስራ ስለምን ተከባሪ ሆነ? ባህላዊው ሲቪል ኤንጂነር (ኣናጺው) የተከበረ ነበር ወይ? ብለን ብንጠይቅ ኣልነበረም:: “ኣናጢ መናጢ” ነበር የሚባለው። ምንም የሌለው ድሃ ማለት ነው መናጢ ማለት። ሁዋላ ላይ ታሪክ ተቀየረና ዘመናዊ ትምህርት ተምረው የመጡ ኣናጺዎች (civil engineers) ገቢያቸው ዳጎስ ያለ በመሆኑና የነሱን ኑሮ ብቻ ሳይሆን የቤተሰባቸውን ህይወት የሚቀይር ገቢ ስላላቸው ተወደዱ።

በድሮ ጊዜ፣

“የኛ ሙሽራ ኩሪ ኩሪ

ወሰደሽ ኣስተማሪ…” ይባል ነበር ኣሉ።

በኔ ጊዜ ኣስተማሪ ለትዳር የማይመረጥበት ጊዜ ስለምን ሆነ? ያው ከኑሮው ጋር ከገቢው ኣቅም ጋር ተያይዞ ነው።

ያ የሜዳ ኣህያ ዘይዱዋል። የባህሪ ለውጥ በማምጣቱ ተከብሮ ከተባራሪነት ወደ ኣባራሪነት ተሸጋግሩዋል። የተባረከ ነውና የጅቡን ስጋ ግን ኣይበላም። እነዚህ እንስሳት እንደዚህ የሜዳ ኣህያ የባህሪ ለውጥ ቢያመጡ ያ ጅቡም ቅጠላቅጠል መብላት ይጀምርና የነዚህ እንስሶች መንደር ሰላም ይወርድበታል።መከባበር፣ መተሳሰብ ይመጣና ኣብረው ይኖራሉ። ጅብና የሜዳ ኣህያ ሳይጠራጠሩ ተቃቅፈው ያድራሉ::

ድሆች በኢትዮጵያ ውስጥ የባህሪ ለውጥ ሊያመጡ ይገባል። እነዚህ በሙስና የከበሩ ሚሊየነሮችና ቢሊየነር ኢትዮጵያ ውስጥ  ስንት ፊላንትሮፒክ ወይም ሰባዊ የሆነ ድርጀት እንዳላቸው ወይም እንደሚረዱ  ኣላውቅም። ርሃብ ሲመጣ ኣለማቀፍ ድርጅቶች ናቸው ስንዴና ዘይት ለማቅረብ ሲሮጡ የሚታዩት።

ዛሬ ሃገራችን ባልተመጣጠነ እድገት ጎዳና ላይ እየነጎደች ነው። ያለው እየጨመረ፣ የሌለው የሚበላው እያጣ ወጣቱ ጢሙን ኣንዠርግጎ የጡረታ ኣባቱን ቤት ሳይለቅ እየኖረ ነው። ካልተናከሰ እንዲሁ ይኖራል።መናከስ ከጀመረ የባህሪ ለውጥ ካመጣ ግን ተከብሮ፣ መብቱ ተጠብቆ ይኖራል።

ኣንድ ጊዜ ትዝ ይላችሁ እንደሆነ የ ኢትዮጵያ ጦር ላይቤሪያ ዘምቶ ነበር። በዚያ ቆይታው ዩናይትድ ኔሽን (UN) ዳጎስ ያለ ኣበል ያስብለት ነበርና ይህንን ኣበሉን የኢትዮጵያ መንግስት እኔ ኣከፋፍላለሁ ብሎ ነው መሰለኝ ይቀበላል። ተቀብሎ ለወታደሮቹ ማካፈል ነበረበት። ይሁን እንጂ ይሄ የጅብ ባህሪ ያለው ኣሰራራቸው ባህሪ ሆኖባቸዋልና ያንን ገንዘብ ቆይ ዛሬ ቆይ ነገ እያሉ ያቆዩባቸዋል። መንግስትን የሚያህል ትልቅ ነገር የነዚያ የድሃ ወታደሮች ኣበል ኣጓጉታው ኣልሰጥም ብሎ ቆየ። ከተዘራፊዎቹ ኣንዱ መንግስት ዘረፈኝ ብሎ ኣስቆናል። እንግዲህ ይታያችሁ ዩናይትድ ኔሽን ለሰጠው መንግስት ቀንቶ እነዚያን ድሆች ቀማ። ሁዋላ ላይ ግን እነዚህ ወታደሮች ኣምጸው እንደነበር ዜና ሰምተናል። መንግስትም ደንግጦ እሰጣለሁ ብሎ ነበር መሰለኝ። መናከስ በመጀመራቸው እንጂ መንግስት የልፋት ዋጋቸውን ነጥቆ ኣፍንጫችሁን ላሱ ብሎ ነበር።በጠራራ ጸሃይ መንግስት እንዲህ ኣድርጎ ድሆችን የሚቀማባት ኣገር ናት ኢትዮጵያ።

ቸሩን ያሰማን ጃል!

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

geletawzeleke@gmail.com

↧

የ2012/2013 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አስሩ መጥፎ የተጫዋች ዝውውሮች

$
0
0

ከይርጋ አበበ
piremier legueበ2012 ክረምት የተጫዋቾች ይዝውውር መስኮት ከተከናወኑ ዝውውሮች መካከል ለአዲሱ ክለባቸው ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ያልቻሉትን አስር ተጫዋቾች የእንግሊዙ ዘሰን ጋዜጣ ለአንባቢያን አቅርቧል። እኛም ይህንኑ ለአንባቢያን በሚመች መልኩ አሰናድተን አቅርበናል ።
1. ክርስቶፎር ሳምባ (ከአንዚማካቻክላ ወደ ኪው ፒ አር 12ነጥብ5 ሚሊዮን ፓውንድ)
ብላክ በርን ሮቨርስ ወደ ታችኛው ሊግ መውረዱን ተከትሎ ወደ ምስራቅ አውሮፓው ሀብታም ክለብ የሩሲያው አንዚ ማካቻክላ የስድስት ወር ጊዜ ቆይታ ያደረገውን የኮንጎ ብሄራዊ ቡድን አምበል ሳምባ በጥር ወር የተጫዋቾች ዝውውር ነበር ከለንደኑ ክለብ ጋር የፈረመው። የመውረድ ስጋት ፊቱ ላይ የተደቀነበት ኪው ፒ አር አሰልጣኙን ሲቀይር እግረ መንገዱን ተጫዋች ግዥ ፈፅሞ ነበር። ክልባችንን ይታደግልናል ብለው ያሰቡት አፍሪካዊ ተከላካይ የታሰበውን ያህል መስራት ሳይችል ክለቡንም ከመውረድ ሳይታደግ በመቅረቱ የዓመቱ ቀጥር አንድ መጥፎ ግዥ ለመባል የቀደመው አልተገኘም ።
2. ጃቢ ጋርሽያ ( ከቤነፊካ ወደ ማንቸስተር ሲቲ 16 ሚሊዮን ፓውንድ)
ጉልበተኛው ነይጂል ዲዮንግ ወደ ጣሊያኑ ታላቅ ክለብ ኤሲ ሚላን መሰደዱን ተከትሎ ወደ ሀብታሙ ክለብ ዝውውር ያደረገው የቤኒፊካ ተጫዋች ሌላኛው ያልተሳካ ዝውውር ተብሏል። ከፖርቹጋሉ ታላቅ ክለብ ወደ ሀብታሙ የማንቸስተር ክለብ ሲዘዋወር በያያ ቱሬ እና እንግሊዛዊው ጋሬት ባሊ የተያዘውን የሰማያዊዎቹን የመሃል ሜዳ ክፍል የግሉ ለማድረግ ከባድ ፈተና የገጠመው ጋርሺያ ለ22 ጊዜያት ብቻ ለሰማያዊዎቹ መጫወት የቻለ ቢሆንም በነዚህ ጨዋታዎቹ የደጋፊዎቹን ፍላጎት ማሟላት ባለመቻሉ የሳምባን እግር ተከትሎ የመጥፎ ዝውውሮችን የፊት መስመር ሊቆጣጠር ችሏል።
3.ጆ አለን(ከስዋንሲ ሲቲ ወደ ሊቨርፑል 15 ሚሊዮን ፓውንድ)
ዌልሳዊው ኮከብ በ2011/12ለብሬንዳን ሮጀርስ ቡድን ቁልፍ ሰው ነበር። ይህንን ችሎታውን የተገነዘቡት አየርላንዳዊው አሰልጣኝ ከስዋንሲ ወደ ሊቨርፑል ሲዘዋወሩ ጆንም አብሯቸው እንዲጓዝ የ15 ሚሊዮን ፓውንድ ቼክ ከአሜሪካውያኑ የሊቨርፑል ባለቤቶች አስከፍለው ነበር ያዘዋወሩት። ጅማሬው ጥሩ የነበረው ዌልሳዊ ኮከብ ውድድሩ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሸጋገር ብቃቱን ጠብቆ አለመዝለቁ ሌላኛው ያከሰረ ተጫዋች የሚል ስያሜን ዘሰን ሰጥቶታል።
4.ማርኮ ማሪን ( ከቬርደር ብሬመን ወደ ቸልሲ 6 ሚሊዮን ፓውንድ)
ጀርመናዊው ጥበበኛ ወጣት ችሎታውን ማንም አይጠራጠርም። ነገር ግን እሱ ሮማን አብራሞቪቹ ክለብ ከመፈረሙ በፊት የፈረሙት ኦስካር እና ኤዲን ሃዛርድ ከሁዋን ማታ ጋር የፈጠሩትን የተዋጣለት ጥምረት ሰብሮ መግባት ባለመቻሉ የመጥፎ ዝውውሮችን ስም ዝርዝር ከያዘው የዘሰን ማስታወሻ ላይ የሱም ስም ከሶስት ተጫዋቾች ቀጥሎ በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
5. ኢማኑኤል አዲባዬር (ከማንቸስተር ሲቲ ወደ ቶተንሃም ሆትስፐርስ 5 ሚሊዮን ፓውንድ)
በማንቸስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ ከተንከራተተ በኋላ በቶተንሃምም አንድ የውድድር አመት የተሳካ የውሰት ውል ያሳለፈው ማኑ በቋሚነት ለኋይት ሃርትሌኑ ክለብ ሲፈርምም የመጀመሪያ አመት ብቃቱን እንዲደግም በማሰብ ነበር። ነገር ግን የሃሪ ሬድናፕን መሰናበት ተከትሎ ክለቡን የተረከቡት አንድሬ ቪያስ ቦአስ ለቀድሞው የአርሴናል ተጫዋች የሚመች የአጨዋወት ፍልስፍና ይዘው አለመምጣታቸው አዴ ለተቀያሪነት ተዳረገ። ዕድሉን አግኝቶ በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ጥሩ ግልጋሎትን ቢሰጥም ብዙ ጊዜ አለመሰለፉ እንደ ድክመት ተቆጥሮ አምስተኛው መጥፎ ዝውውር ከመሆን አላዳነውም።
6.ዳኒ ግርሃም(ከስዋንሲ ሲቲ ወደ ሰንደርላንድ 5 ሚሊዮን ፓውንድ)
አሜሪካዊው አጥቂ በስዋንሲ ቆይታው የግብ ሪከርዱ ጥሩ የሚባል ነበር። ነገር ግን ዴንማርካዊው ቴክኒሽያን ብሬንዳን ሮጀርስን ተክተው ክለቡን ሲረከቡ ከስፔን የገዙት ሚጉኤል ሚቹ ዳኒን ወደ ተጠባበቂ ወንበር እንዲያወርደው ተደረገ። 90 ደቂቃ ሙሉ ተቀያሪ ወንበር ላይ መቀመጥ ያልተመቸው ግርሃም ወደ ጥቋቁር ድመቶቹ በጃንዋሪ የዝውውር ወቅት ይሄዳል ። በሰንደርላንድ የመሰለፍ እድል ቢያገኝም የግቡን መስመር ማግኘት አለመቻሉ መጥፎ የግብ ሪከርዱ ያልተሳካለት ተዘዋዋሪ እንዲሆን አድርጎታል።
7. እስቴባን ግራኔሮ ( ከሪያል ማድሪድ ወደ ኪው ፒ አር 9ሚሊዮን ፓውንድ)
የቀድሞው የብላክ በርን እና ማን ሲቲ አሰልጣኝ የነበረው ዌልሳዊው ማርክ ሂውዝ በሪያል ማድሪድ የተሰላፊነት ዕድል በማጣቱ የተሰላቸውን ስፔናዊ 9 ሚሊዮን ፓውንድ ክፍያ ከፍለው ወደ ለንደን ያመጡት ታላቅ ተስፋ ሰንቀው ነበር። ዳሩ ግን ክለቡም ሆነ ግራኔሮ የኋልዮሽ በመጓዛቸው በአመቱ መጨረሻ ክለቡ ወደ ታችኛው ዲቪዚዮን ልጁ ደግሞ የአመቱ ሰባተኛው ደካማ ዝውውር ለመባል ቻሉ።
8. አሉ ዲያራ ( ከኦሎምፒክ ማርሴይ ወደ ዌስትሃም ዩናይትድ 2 ሚሊዮን ፓውንድ)
አወዛጋቢውን እንግሊዛዊ አማካይ ጆይ ባርተን ከኪው ፒ አር በውስት ያገኘው የፈረንሳዩ ክለብ ጠንካራውን አማካዩን ለዌስትሃም ሲሰጥ የቋሚ ተሰላፊነት ቦታውን እንደማያገኝ አስቦ አልነበረም። ነገር ግን ዲያራ በለንደን የጠበቀው ያልታሰበው ሆነ። እሱም የመዶሻዎቹ አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ ከአሉ ዲያራ ይልቅ ሴኔጋላዊውን ዲያሚን በማስቀደማቸው ተጠባባቂ መሆን የሰለቸው ፈረንሳዊው በጥር ወር ወደ ፈረንሳይ ተመልሶ ለትውልድ ከተማው ክለብ ሬን ፊርማውን አኖረ።
9.ስኮት ሲንክሌር ( ከስዋንሲ ሲቲ ወደ ማን ሲቲ6 ሚሊዮን ፓውንድ)
በዚህ ስም ዝርዝር ውስጥ የሚበልጠውን ድርሻ የያዙት የቀድሞ የስዋነሲ ሲቲ ተጫዋች እንደሆኑ የቀድሞው የቼልሲ ተጫዋች ስኮት ሲንክሌር አስተዋጽኦ አድርጓል። ስኮት በቼልሲ የተደበቀውን ችሎታውን በዌልሱ ክለብ መልሶ ማግኘት ቢችልም ወደ ማንቸስተር ሲቲ ያደረገው ዝውውር ራስን ከተራራ ላይ ወደ መሬት እንደ መወርወር ያስቆጠረውን ስህተት የፈጸመበት ነበር። በሮቤርቶ ማንቺኒ ቡድን ውስጥ እንደ ሳሚር ናስሪ፣ ዴቪድ ሲልቫ እና ጄምስ ሚልነር ዓይነት ኮከብ ተጫዋቾች መኖራቸው የተጠባባቂ ወንበርን በመደበኛነት እንዲያዘወትር አድርጎታል።
10. ማይኮን ( ከኢንተር ሚላን ወደ ማን ሲቲ 3 ሚሊዮን ፓውንድ)
ማንቸስተር ሲቲ ያለፈውን የዝውውር መስኮት ብዙ የከሰሩ ዝውውሮችን የፈፀመ ክለብ ሆኗል። በኢንተር ሚላን ጉልበቱን የጨረሰውን ብራዚላዊ በዝቅተኛ ዝውውር ሰማያዊውን ማሊያ ማልበስ ቢችልም ያሰበውን ግልጋሎት ማግኘት ሳይችል ቀርቷል። በብራዚል ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ቦታውን በባርሴሎናው ኮከብ ዳኒ አልቬስ የተወረሰው ግዙፉ ብራዚላዊ በእንግሊዝም የጠበቀው ከብራዚል የተለየ አልነበረም። ያለፉትን ሁለት ዓመታት በጥሩ አቋም ላይ ያሳለፈው አርጀንቲናዊ ፓብሎ ዛባሌታ ቦታውን የግሉ አድርጎት ስለነበር ከዛባሌታ ቀድሞ መሰለፍ ለማይኮን የሚቻል አልሆነለትም። እናም ዓመቱን ሙሉ ተጠባባቂ ወንበር ላይ ተቀምጦ የዛባሌታን ምርጥ እንቅስቃሴ ሲመለከት ከረመ። ከእንግሊዛዊው ሚካህ ሪቻርድስ መጎዳት በኋላ ማንም እንዳይቀማው አድርጎ ቦታውን ያስከበረው አርጀንቲናዊ ረፍት ሲያስፈልገው ብቻ በካፒታል ዋን ጨዋታዎች የሚሰለፈው ብራዚላዊ አንድ ያልተሳካ የውድድር ዓመት በእንግሊዝ ሲሰልፍ ዘሰን ጋዜጣም አስረኛው ያልተሳካለት የዓመቱ ፈራሚ የሚል ስም ሰጥቶታል።

↧
↧

ሁለት እግርና አንድ እጅ አልባዋ የዋና ሻምፒዮን

$
0
0

ከኡመልኸይር ቡሎ
ካዬላ ዊህለርካዪላ ዊህለር የተወለደችው ሁለት እግርና አንድ እጅ ሳይኖራት ነው:: ሐኪሟም ዋናን እንደ አንድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንድትጠቀም ይመክራት ነበር። በእዚህ መሠረት ባደረገችው ጥረት ዊህለር ግን በ16ዓመቷ በዋና የዓለምን ሪከርድ ለመስበር ችላለች፡፡
ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው ታዳጊዋ በብራዚል ሜክሲኮና ኔዘርላንድ ውድድሯን ያደረገች ሲሆን፤ በ2016 ፓራኦሎምፒክ ለመወዳደር እቅድ ይዛለች። በ2013 በተካሄደው50 ሜትር የሴቶች ሻምፒዮን ተወዳድራ አዲስ ሪኮርድ አስመዝግባለች፡፡
«ነገሩን ሁሉ ለመግለፅ አስቸጋሪ ነው። ስሟ ሲጠራና ዩናይትድ ስቴትን መወከሏን ሳውቅ በጣም ተገረምኩ፣ ማመን አቃተኝ፣ ከደስታ ብዛት የምይዝ የምጨብጠውን አጣሁ። ይች እኮ የእኔ ድንቅ ልጅናት አልኩኝ» ይላሉ እናቷጆሲ ዊህለር፡፡
«ሁሌም ምንም ማድረግ የማትችይው ነገር የለም እያልን እንነግራታለን። ነገር ግን ነገሮችን ላንቺ ማድረግ እንዲመቹ ማመቻቸት ይጠበቅብናል ስለምንላት እርሱዋም በጥረቷ ቀጠለች» ሲሉ አክለዋል።
ዊህለር በማትዋኝባቸው ጊዜያት ቤዝቦል እና ቦውሊንግ በመጫወት ጊዜዋን ታሳልፋለች በትምህርቷም ከፍተኛ ውጤት የምታስመዘግብ የደረጃ ተማሪ ስትሆን፤ በኮምዩኒቲ ኮሌጆች አድቫንስድ ኮርሶችን ትወስዳለች፡፡ ንቁ ተሳተፎም ታደደርጋለች፡፡
በእዚህ ዓመት ባስመዘገበችው ከፍተኛ የአትሌቲክስና የአካዳሚክ ውጤት «ስኩላ ስቲክ» የተባለ የክብር ስያሜ አግኝታለች፡፡
በርግጥ ዊህለር በ2012ም ፓራኦ ሎምፒክ ለመወዳደር ተመርጣ ነበር። ነገር ግን እንዳጋጣሚ ሆኖ አብሯት የሚወዳደር ሰው ባለመኖሩ ሳትወዳደር ቀርታለች። ምክንያቱ ደግሞ በፓራኦሎምፒክ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች የሚመደቡት እንደ አካል ጉዳታቸው ደረጃ በመሆኑ በእርሷ የጉዳት ደረጃ የሚወዳደር ሰው ባለመኖሩ ነው፡፡
« አምና በፓራኦሎምፒክ አልተወ ዳደርኩም ነበር። ምክንያቱም በእኔ ምድብ የምትወዳደር ሌላ ሴት ተወዳዳሪ አልነ በረችም። የእኔ ምድብ ኤስ ዋን ሲሆን፤ በእዚህ ምድብ የሚካተቱ ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው» ትላለች ዊህለር።
«ሃገሬን በመወከል መወዳደር እፈል ጋለሁ። አዲስ ሪኮርድ ማስመዝገብና ሜዳሊያ ማግኘት በጣም የሚያስደስትና የሚያስገርም ነገር ቢሆንም እኔ ግን ከውድድሩ ባሻገር አርዓያ በመሆን እዚያ ቦታ መገኘት እፈልጋለሁ» ብላለች።

↧

የአቶ አስገደ ልጆች ምን ወንጀል ሠሩ? (አሕለፎምና የማነ አስገደ) –ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

$
0
0

ክፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ግንቦት 2005

Pro Mesfin አቶ አስገደ ከቀደሙት የወያኔ ታጋዮች አንዱ ነው፤ ወያኔ ለሥልጣን እስከበቃበትና ከዚያም አልፎ አባል ሆኖ ቆይቶአል፤ በኋላ ግን የተመለከተውን አሠራርና አካሄድ እየተመለከተ ወያኔ ዱሮ የነበረውን ዓላማ በሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ከሚደረገው ጋር ሲያነጻጽር መነሻውን እየሳተ መሆኑን በመገንዘቡ የወያኔን አሠራር በቁጭት መተቸትና መንቀፍ ጀመረ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ መጽሐፎችንም ደረሰ፤ አጫጭር ጽሑፎችም በጋዜጦችና በመጽሔቶች ላይ ጻፈ፤ ከጓደኞቹ ከቀድሞ የወያኔ አባሎች ጋር በመሆን አሬና የሚባል ተቀናቃኝ ፖሊቲካ ፓርቲ አባል ሆነ፤ ይህ ሁሉ እንደሰውም፣ እንደዜጋምየአቶ አስገደ መብቱ ነው፤ ወያኔን በመተችትና በመንቀፍ አቶ አስገደ የመጀመሪያው አይደለም፤ የመጨረሻውም እንደማይሆን እየታየ ነው፤ ከዚህ በፊት አቶ ገብረ መድኅን አርአያ ወያኔን ሲያጋልጥ ቆይቷል፤ አሁንም እየቀጠለ ነው፤ አሁን ደግሞ ከአቶ አስገደ ጋር ኤንጂኒር አብደልወሃብ ቡሽራ አለ፤ … እውነት የብረት ግንብም ቢሆን ሰርስሮ የመውጣት ኃይል አለው፤ እየወጣም ነው፡፡ በሚያዝያ (2005) ውስጥ የአቶ አስገደ ሁለት ወንዶች ልጆቹ ከተለያዩ ከተሞች ተይዘው ታሰሩ፤ አቶ አስገደ እንዳለው አንዱ ልጁ፣ አሕለፎም አስገደ ሚያዝያ 16/2005 ‹‹በአንድ ሻይ ቤት ቡና ሲጠጣ›› ተያዘ፤ ሌላው ልጁ ደግሞ፣ የማነ አስገደ የሚባለው የሶፍትዌር ኤንጂኒር ታሞ ስለነበረ ጠበል ለመጠመቅ ወደአያቱ መኖሪያ ሄዶ ሳለ በሚያዝያ መጨረሻ ሳምንት አካባቢ ተይዞ ታሰረ፤ የሁለቱ የአቶ አስገደ ልጆች በሚያዝያ 16ና ምናልባትም 25 መሀከል በሁለት በተለያዩ ከተሞች ተይዘው መታሰር አድፍጦ የሚጠብቃቸው ኃይል የነበረ ያስመስለዋል፤ ልጆቹ ከወያኔ ድርጅት ጋር ያላቸው/የነበራቸው ግንኙነት አይታወቅም፤ አባታቸው አቶ አስገደ ግን ወያኔ የነበረ የወያኔ ነቃፊ መሆኑ ይታወቃል፤ የሁለቱ ወጣቶች መታሰር ምክንያት ከመንግሥት ጋር ሳይሆን ከወያኔ ጋር የተያያዘ መሆኑን የሚያመለክተው አሕለፎም የሚባለው በመጀመሪያ የታሰረው በመደበኛ ፖሊስ ጣቢያ ወይም ቀበሌ ሳይሆን 06 በሚባል የወያኔ እስር ቤት መሆኑ፣ የፖሊስ ጣቢያውን ኃላፊ አቶ አስገደ ሲጠይቀው የሰጠው መልስ ‹‹አስገደ እራስህ ተበክለህ እየጮህክ እዚህ ያለውን ሰው እየበከልክብን ነው›› ማለቱ የልጆቹ መታሰር የተያያዘው ከአባታቸው ጋር እንደሆነ የሚያመለክት ያስመስለዋል።

የአክሱም ጽዮን የሃይማኖት አባቶች እንዳስተማሩን ‹‹አዳም በበደለ መድኃኔ ዓለም ካሠ፤›› የተባለበት ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ከድንግል ማርያም ተወልዶ፣ የሰው ሥጋ ለብሶ፣ ተደብድቦ፣ ተሰቅሎ፣ ተቀብሮ፣ ተነሥቶ ወደሰማይ ያረገውና በገሃነመ እሳት ያሉትን ነፍሳት ነጻ ያወጣቸው የሰውን ልጅ ከኃጢአት ውርስ ነጻ ለማውጣት ነው፤ በአዳም ኃጢአት የሰው ልጆች አይቀጡም፤ እያንዳንዱ ሰው ለሚሠራው ራሱ ኃላፊ ይሆናል፤ ስለዚህም አዳም ዕጸ በለስን በልቶ በበደለ መድኃኔ ዓለም (ኢየሱስ ክርስቶስ) በሞቱ የሰውን ልጅ ነጻ አወጣው፤ ካሠው፤ ይህ የሐዲስ ኪዳን መልእክት ነው፤ በአጼ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ዘመናዊ ሕግ እስቲወጣ ድረስ የሕግ መሠረት የነበረው ፍትሐ ነገሥት ልጆች በአባታቸው ወንጀል አባትም በልጁ ወንጀል እንዳይከሰሱ ይደነግጋል፤ የኦሪት ሕግ በሐዲስ ኪዳን ተሸሮአል፤ ወያኔ ይህንን ሁሉ የሕግ አስተሳሰብ እድገት አያውቅም፤ ሊያውቅም አይፈልግም።

ስለዚህ በዘመነ ኦሪት በነበረ አስተሳሰብ እንገዛለን፤ የአቶ አስገደ ልጆችም በዘመነ ኦሪት አስተሳሰብ እንደተያዙ ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ያስረዳሉ፤ ከዚህም በፊት እናት በልጅዋ ምክንያት እንደተገደለች፣ ሚስቶች በባሎቻቸው ምክንያት እንደተደበደቡ እናውቃለንና ነገሩ አዲስ አይደለም፤ እንኳን ከወያኔ ውጭ ባሉ ሰዎችና በወያኔዎችም ላይ ይኸው የኦሪት ሕግ በወንድማማቾች ወያኔዎች ላይ ሲፈጸም አይተናል፤ ነገር ግን ከጫካ በኋላ በሃያ ዓመታት የሥልጣን ዘመንም ይቺን ቀላል የፍትሕ ትምህርት አለመማራቸው የሚያስገርም ብቻ ሳይሆን የሚያሳፍርም፣ የሚያስፈራም ነው፤ ሥልጣን የኃላፊነት ሸክም በመሆኑ ያስተምራል፤ በሥልጣን መማር የማይቻል ሲሆን ሥልጣን የውድቀት ምክንያት ይሆናል።

በቅንነትና በእውነት ላይ ያልተመሠረተ ኃይል የጭቆና መሣሪያ እንደሚሆን የታወቀ ነው፤ በልጅነትና ባለመብሰልም ይሁን በእውቀት ማነስ ትንንሾች ልጆችና ወጣቶች በስሜት ብቻ በአንዳንድ መፈክሮች ተማርከው አጥምደው ለሚጠብቋቸው ቡድኖች ሲሳይ ይሆናሉ፤ ይህ ተደጋግሞ የታየና እየታየ ያለም እውነት ነው፤ ‹‹አታስቡ – እኛ እናስብላችኋለን፤›› በሚሉ ቡድኖች ውስጥ ገብተው የሰውነት ባሕርያቸውን ሁሉ ያጣሉ፤ ከብዙ ዘመናት በኋላ እየነቁ ማሰብ ሲሞክሩና የራሳቸውን አስተያየት መስጠት ሲጀምሩ አንድ ወንጀል ይለጠፍባቸዋል፤ የታወቁትን ብቻ ለማስታወስ ያህል ታምራት ላይኔንና ስዬ አብርሃን መጥቀስ ይቻላል፤ በሁለቱም ላይ የተለጠፉባቸው ወንጀሎች የግል ሳይሆኑ ቤተሰቦቻቸውን የሚጨምሩ ነበሩ፤ አንድ የቡድኑ አባል እኔም ማሰብ እችላለሁ ሲል መሠረታዊውን ሕግ ይጥሳል፤ ሁሌም ቅጣቱ በማራቆትና ደሀ በማድረግ ከጥቅልነት ወደሰውነት የተመለሰውን አስጨንቆ እንዳያስብ ለማድረግ ነው፤ የከፈተውን የአእምሮውን በር እንደገና ዘግቶ አንዲያፍነው ለማድረግ ነው።

ብሩኅ አእምሮ ያላቸውን ልጆች እየለቀሙ አምጥቶ አንድ ከፍተኛ ስም ያለው የትምህርት ተቋም ውስጥ አስገብቶ ዘመኑ ያፈራውን የእውቀት ጥበብ አንዲማሩ አድርጎ ታዛዥ ሎሌ ለማድረግ መሞከር የትምህርትን ባሕርይ አለማወቅ ነው፤ የትምህርትን ባሕርይ በጫካ ውስጥ መማር አይቻልም፤ የትምህርትን ባሕርይ በሥልጣን ወንበር ላይ ተቀምጦና በዕብሪት ተወጥሮ መማር አይቻልም፤ በኢትዮጵያ ባህላዊ ትምህርት ብዙ ልፋት አለበት፤ ከሞቀ ቤት ርቆ፣ በቀፈፋ ተመግቦ፣ ከሌሎች ትምህርት ፈላጊዎች ጋር እየተንከራተተ ብዙ ዓመታት አሳልፎ ነው የትምህርት ባሕርይ የሚገለጠው፡፡ በዘመናዊው ትምህርትም መንከራተቱና ልፋቱ ይቀንስ እንጂ ከባድና አድካሚ ነው፤ በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የትምህርት ሚኒስትር ከነበሩት ከአቶ አካለ ወርቅ ጋር ስለወጣቶች ችኩልነት ስንነጋገር አንድ ነገር ነገርኋቸው፤ ‹‹ተማሩ ብላችሁ ትምህርት ቤቶች ከፈታችሁልን፤ ለአንዳንዶቻችን የአዳሪነት ምቾትም ሰጠታችሁን፣ ከዚያም በኋላ በየፈረንጅ አገሩ እየላካችሁ አስተማራችሁን፤ ተማርን፤ መማር ማለት መለወጥ ነውና እኛ ተለወጥን፤ እናንተ ግን አልተለወጣችሁም፤ መሠረታዊ ችግራችን ይህ ነው፤›› የተናገርሁት ነገር በጣም ተሰምቶአቸው ለጥቂት ሰኮንዶች ትክዝ አሉ፤ ‹‹እውነትህን ነው፤ ታዲያ ይህንን ቸግር ማን ይፍታው?››
ወያኔ/ኢሕአዴግ እየጠበበ ሲሄድ ከውስጥ እየነቃ ነው፤ አንዳንድ አባሎቹ ነጻነታቸውን እያወጁ ነው፤ የሰው ልጅ ነጻነትን ከቀመሰ በኋላ የማሰብ ችሎታው እያደገና እየሰፋ ይሄዳል፤ በዚያው መጠን የሰውነቱን ልክ ይረዳል፤ የወያኔ መሪዎች ይህንን እውነት ቢረዱና አገሪቱንና ሕዝቡን ከመከራ ቢያድኑ ለራሳቸውም ይጠቅማቸው ነበር።

↧

የእነ መላኩ ፈንታ ጉዳይ… ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

ከተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ከአንድ ወዳጄ ጋር ሃያ ሁለት አካባቢ ምሳ በልተን ስናበቃ እንደሌላው ቀን ሹፌሬ ስላልነበር በኮንትራት ታክሲ ወደቤቴ (አሲምባ) አመራሁ፡፡ ታክሲው በውለታችን መሰረት የቀበናን አደባባይ ዞሮ ሲቆም፣ እኔም ሂሳቤን አወራርጄ ወረድኩ፡፡ ሆኖም ጥቂት እርምጃ እንደተራመድኩ ያላስተዋልኳቸው ሁለት ሰዎች አጠገቤ ደርሰዋል፡፡ በዕድሜ እኩዮቼ ይመስላሉ፡፡ አንዱ ቀጭንና ቀውላላ ነገር ነው፤ ሌላኛው ደግሞ ቁመቱ መካከለኛ ሆኖ፣ ደልደል ያለ ሰውነት አለው፤ ሁለቱም ‹‹ጠይም›› የሚባሉ ናቸው፡፡ ቀውላላው፡-
‹‹ሰላም ተመስገን!›› አለኝ፣
‹‹ሰላም!›› መለስኩኝ፡፡
‹‹ልናናግርህ ፈልግን ነበር?››
‹‹ይቅርታ አላወኳችሁም፡፡››
‹‹አንተ አታውቀንም! እኛ ነን የምናውቅህ››
‹‹የት ነው የምታውቁኝ? ማለቴ በምን መልኩ…››
‹‹እሱን ተወው! የእኛ ማንነትንም እንድንነግርህ አትጠብቅ፣ ይገባሃል ብለን እናስባለን!›› አለ እስከአሁን ዝም ብሎ የነበረው ደልዳላው ሰው፡፡ ሆኖም ቀውላላው ጓደኛው አቋርጦት ቀጠለ፡-
‹‹ ምን መሰለህ? ሰሞኑን እነ መላኩ ፈንታ እንደታሰሩ ታውቃለህ፤ እናም የእነርሱ ጉዳይ የእኛ ብቻ ነው፤ አንተን አይመለከትህም፡፡››
‹‹አልገባኝም! ይህ ምን ማለት ነው?››
‹‹በቃ! በዚህ ጉዳይ ላይ ትንተና፣ ማብራሪያ እፅፋለሁ ምናምን እያልክ አትድከም ለማለት ነው!›› ቆጣ ባለ መልኩ መለሰልኝ-ደልዳላው ሰው፡፡
ከትከት ብሎ መሳቅ አማረኝ፤ በጣም መሳቅ! ሆኖም ለምን እንደሆነ አልውቅም-አልሳቅኩም፡፡ በግልባጩ ድንገተኛ ንዴት በመላ ሰውነቴ ሲሰርፅ ታወቀኝ፡፡ ከሰከንዶች በኋላም እስከአሁን ሲናገር ትህትና ያልተለየው ቀውላላው ሰው እንዲህ ሲል አግባባኝ፡-
‹‹እየውልህ፣ መንግስት ሰዎቹን ያሰረው በወንጀል ላይ በመሰማራታቸው ከመሆኑ በተጨማሪ ለህዝብና ለሀገር ጥቅም ነው፤ ስለዚህም ገና ፍርድቤት ስለሚቀርቡ፣ ምርመራውም ስላላለቀ አንተ በፅሁፍህ ተሳስተህ፣ ለሌሎችም የተሳሳተ መረጃ እንዳታስተላልፍ ለመምከር ነው፡፡››
‹‹ስለምክራችሁ በጣም አመሰግናለሁ! ነገር ግን እኔ የምሰራውን አውቃለሁና ለስራዬ መካሪ አያስፈልገኝም›› ስል ባለመካከለኛ ሰውነቱ አቋረጠኝና፤ ከቅድሙ በባሰ የቁጣ ቃል መናገሩን ቀጠለ፡-
‹‹ስማ! ልንመክርህ ወይም ልናባብልህ አይደለም የመጣናው፤ በቃ በማያገባህ ጉዳይ መግባት እንደሌለብህ ልንነግርህ ነው!››
ይህን ጊዜም አነጋገሩ በስሱ አስቆጣኝና፡-
‹‹እየወልህ! እናንተ ማንም ብትሆኑ ግድ አይሰጠኝም፤ ኋላ ኪሳችሁ ያለው መታወቂያም አያሳስበኝም፡፡ እስከዛሬ ድረስ የማደርጋትን እያንዳንዷ ነገር አስቤበትና አምኜበት ነው፤ ማስፈራሪያችሁ እኔ ጋ ቦታ የለውም፡፡ ምናልባት ‹ይህንን ጻፍ፤ ይህንን አትጻፍ› ስትሏቸው ትዕዛዛችሁን በመፈፀም ያስለመዷችሁ ጋዜጠኞች ካሉ ወደእነርሱ ልትሄዱ ትችላላችሁ›› ብዬ መንገዴን ልቀጥል ስል፣ ትሁቱና ቀውላላው ሰው፡-
‹‹ተመስገን ብታስብበት መልካም ነው!›› አለ፣
 መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።

መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።

‹‹ምንም የማስብበት ነገር የለም፤ ይልቅ አለቃችሁን ንገሩት፣ ሰሞኑን እንደናንተ አይነት ፀጉረ ልውጦች በቤቴ አካባቢ በዝተዋልና ሰብስብልኝ፣ ይሄ አንድም ስራ መፍታት ነው፤ ሁለትም የሀገር ሃብት ማባከን ነውና! ብሎሀል በሉት››
…ከዚህ በኋላ ቤቴ ገብቼ ስለገጠመኜ ማሰብ ስጀምር መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች በአእምሮዬ ተመላለሱ፡- በዚህች ሀገር ላይ ምን እየተደረገ ነው? እነማን፣ በእነማን ላይ እያሴሩ ነው? መላኩ ፈንታ የታሰረው እውነት በሙስና ብቻ ነውን? ኢህአዴግስ ዕውን ሙስናን ለመከላከል ቆረጦ ተነስቷል?አሁን ማ ይሙት በሙስና መጠየቅ ከተጀመረ መላኩ ነው የመጀመሪያ የሚሆነው? ወይስ…
አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ

አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ

(የሆነ ሆኖ ይህችን የሞነጫጨርኩት ‹‹አይመለከትህም!›› ያሉኝ ሰዎች እንደሚመለከተኝ ይረዱ ዘንድ ነውና፣ በቅርቡ በስፋት የምመለስባቸውን የመነሻ ሃሳቦች አስቀምጬ ልሰናበት)
1. መላኩ ፈንታ በባህርዳሩ ስብሰባ ላይ ‹‹የህወሓት ስውር እጆች›› እንደሚደግፋቸው የሚነገርላቸውን ሁለት መቶ ነጋዴዎች በስም ጠቅሶ ‹‹አላሰራ አሉኝ፤ አስቸገሩኝ!›› ብሎ ሪፖርት ማቅረቡ ያስቆጣው አካል በእስሩ ላይ መኖር አለመኖሩን፤ አዜብ መስፍን በዛው ጉባኤ ላይ ‹‹መለስ ብቻ ነው በደሞዝ የኖረው›› የሚል ጥቆማ ከማቅረቧ ጋር ተያያዥነት አለው ወይስ የለውም?
(ስለሰውየው ብቃትና ከሙስና የፀዳ ስለመሆኑ በስፋት ይነገር እንደነበር አውቃለሁ፤ በአናቱም የኢህአዴግ አመራር ሆኖ ከሙስና የራቀ ይኖራል ብሎ ማሰብ በእጅጉ ይከብዳል፡፡ በእርግጥ ‹‹የመላኩ ችግር›› ተብሎ ሲነገር እስማ የነበረው ከመልከ መልካምነቱ ጋር ተያይዛ የምትነሳ ጉዳይ ነች-ቶሎ በፍቅር መሸነፍ፡፡ በነገራችን ላይ መላኩ ከሆኑ ጊዜያት በፊት ዱባይ ውስጥ የመኪና አደጋ ደርሶበት እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ለስራ ጉዳይ ሄዶ ግን አልመሰለኝም)
2. መቼም የማይካደው ሀቅ መላኩ ፈንታ ለፓርቲው ባለውለታ መሆኑ ነው፡፡ ይኸውም በተለይ ከምርጫ 97 በኋላ ኢህአዴግ ‹‹አይደግፉኝም›› ያላቸውን ነጋዴዎች የተለያየ ምክንያት እየለጠፈ እንደአኮሰመናቸው ይታወሳል፡፡ ይህንን የስራ ሂደት ካሳኩት ‹‹ዋነኞቹ አስፈፃሚዎች›› መካከል ደግሞ እርሱ ይመራው የነበረው መስሪያ ቤት ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ እናም እዚህ ጋር የሚነሳው ጥያቄ ዛሬ መላኩ ፊቱን ከጠላት ወደወዳጅ (የስርዓቱ አውራ ጣት ወደሆኑ ነጋዴዎች) ማዞሩ የመዘዘው ጦስ በድርጅቱ ውስጥ ለተፈጠረው ልዩነት ‹‹መያዣ›› (የአብርሃም በግ) አድርጎት ይሆናል ብሎ መከራከር ይቻል ይሆን? መላኩስ ይህንን ጥያቄ ያቀረበው በራሱ ተነሳሽነት ነው? ወይስ ‹‹አይዞህ›› ብሎ አደፋፍሮት ሲያበቃ የከዳው ቡድን አለ?
3. በኢህአዴግ ውስጥ የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ልዩነት ፈጥሯል፡፡ እነ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ እንዲፈታ ይፈልጋሉ፡፡ ብአዴንም ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ይህንን ሃሳብ ይደግፋል፡፡ እናም እነዚህ ልዩነቶች መስፋታቸው ይሆናል ሁለት የብአዴን አመራር አባል የሆኑ ሚንስትሮችን በአንድ ሳምንት ውስጥ ‹‹የነቀላ››ው ሰላባ አድርጓቸው ይሆን?
4. እንዲህ አይነቱ እስር እና ድንገት ከሃላፊነት መባረር በመላኩና በብርሃን ብቻ ይቆማል? ወይስ ይቀጥላል? ከቀጠለስ ወደ እነማን ያመራል?

ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለማስከበር ማንኛውንም መስዋዕትነት መክፈል የሁላችንም ግዴታ ነው!

↧

ዶ/ር አድሃኖም ስለሃገር ጥቅም ይከበር ብለው ያሉት ደስ ሲል

$
0
0

ከዓቢቹ ነጋ

የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ከጫካ ከመጡት የወያኔ ጀሌወች በትምህርትም ሆነ በአስተሳሰብ የተሻሉና በደም ያልተጨማለቁ ናቸው ሲባል ብዙ ሰምተናል። በመሆኑም ያስታርቂነትና የመልካም አስትዳደር ሚና ሊጫወቱ ይችሉ ይሆናል አያሉ ብዙ ሰውች ገምተው ነበር። አስተዋይና የምሁርነት ባህሪ እንዳላቸውም ይነገራል።

አዲሱን ሥልጣን እንደያዙ የሰከነ ፖለቲካና በሎጂክ የተደገፈ የውጭ ፖሊሲ ነድፈው በውጭ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ የሚአቀራርብ የፖለቲክ መርሃ ግብር ያሳዩ ይሆናል ብለን ጠብቀን ነበር። በቅርቡ በውጭ ሃገር ጉብኝታቸው ጊዜ ዲያስፖራውንና የዓባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭን አስመልክቶ በዩቲውብ የሰጡትን ማስጠንቀቂያ በጥሞና አዳምጠነዋል ። የንግግራቸው አንኵኣር መልእክት አንድና አንድ ነው። ኢትዮጵያኖች የሃገር ጥቅምን ፤የኢኮኖሚ እድገትን፤ የማህበራዊ ስራዓትና ብልጽግናን ከሚጎዳ ተግባር እንዲታቀቡ ለዘብ ባል መልኩ አሳስበውናል።

አክለውም በፖለቲካ ልዩነቶች አኣንዱ በግራ ሌላው በቀኝ መሰለፍ ይችላል ብለዋል አውቁ የፖለቲካ ዶክተር። የህ ካንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አና ምሁር የሚጠበቅ የዲፕሎማሲ ቍዋንቍዋ ስለሆነ እንቀበለዋለን። ዲያስፖራው በየጊዜው በሰላማዊ ሰልፍ፣ በጽሁፋ፤ በመግለጫ፤ በመገናኛ ብዙሃን ወዘተ ወያኔን የሚነግረውና የሚቃወመውም ለዚሁ ዓላማ መሆኑ ይታወቅ። በዚህ ብዙ ጠብ አይኖርም።

ነገር ግን በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በቦንዱ ሽያጭ፤በፖለቲካ፤ በኢኮኖሚና በልማት ጉዳዮች ላይ ተቃውሞ የሚአሰማው ለምን ይሆን ብለው ዶክተሩ እራሳቻውን መጠየቅ ይኖርባቸዋል።የህክምና ሙያዎን አልረሱት ከሆነ ለአንድ በሽተኛ ወይም ታካሚ መድሃኒት ከመታዘዙ በፊት ለበሽታውና ለህመሙ መንስዔ የሆኑት ጉዳዮችን መጀመሪያ ማጠናትና ግድ ይላል። የበሽታውን አይነትና በሽታው የተከሰተበት ምክንያት ከታወቀ በህዋላ ህክምናው ይሰጣል። እንደህክምና ጠበብትነትዎ መልሱን ማፈላለግና ታካሚዉን መርዳት የርሶ ፋንታ እንጂ የታካሚዉ አይሆንም። በርግጥ ህክምናው የተሳካ እንዲሆን በሽተኛውም መተባበር የኖርበታል ።

በሃገርቤትም ሆነ በውጭ ተስዶ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለሃገሩ ነፃነት፤ ኣንደነት፤ ፍቅር፤ ሰላምና ብልጽግና ሁሉም ቀናኢ መሆኑ በውል የሚአውቁት ይመስለናል። በተደላደል ሃገር እየኖረ፤ ሶስት ጊዘ በቀን እየተመገበ፣ በመኪና እየተንደላቀቀ ፤በጥሩ ቪላ ቤት እየኖረ ፤የተፈጥሮ መብቶቹ ማለት የመጸፍ፤ የመናገር፤ የመቃወም፤ የመሰብሰብ፤ የመሰለፍ፤ በፈለገበት አካባቢ እየተዘዋወረ መኖርና መሰራት እየቻለ በወያኔ ጨምላቃ ፖለቲካ የሚነንጋገረውና የሚቃወመው ለምን ይመስለዎታል። እትበቱ የተቀበረችበት ዉድ ሃገሩ ኢትዮጵያ በገንዛ ልጆችዋ እየተጠቃችና እየፈራረሰች መሆኑን ስለተረዳ ጨርሳ ሳትወድም ከውድቀትዋና ከመፈራረስዋ በፊት ህዝቤንና ሃገሬን ልታደግ ብሎ እንጅ የኢትዮጵያን ጥቅም ለመጉዳት ከመነሳሳት የመነጨ ስሜት እንዳልሆነ ዶክተሩ ሊገነዘቡት ይገባል። ኢትዮጵያዊው ለሃገሩ ቀናኢ ለመሆኑ የድሮ ታሪኩና ያሁን ተግባሩ ምስክር ናቸው። የተማሩት ድክተር አድሃኖም ይህን የኖረ እውነታ ያጡታል ተብሎ አይገመትም።

በህክምና ሙያ አንደተመረቁ ይነገርልዎቀታል። ዳያስፖራው ለዚህ ኣድናቆቱን የሚነፍግዎ አይሆንም።በአንፃሩ አብዛኛው ዳያስፖራ በተላያየ ሙያ ከፍተኛ ትምህርት፤እውቀትና ልምድ ያካበተ መሆኑን የሚዘነጉት እንደማይሆን ተስፋአለን። የዕድሜዎን ክልል ስናሰላስል በኀይለሥላሤ ዘመን እንደተማሩ እንገምታለን። እስኪ በዚያን ጊዜ የነበረውን የትምህርት ደረጃና በርስዎ መንግስት ጊዜ ያለውን የትምህርት ጥራት አነጰጵረው ፍርድ ይስጡ።

ሐገርም በተስቦ፤ በኤድስ፤ በሳንባ ነቀርሳ ፤በወባ በሽታወች አይታመም እንጂ በማህበራዊ፤ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ስነምግባር አካሄድ ትታመማለች። ኢኮኖሚው ሖዋላቀር ሲሆን ፤ የሃገር ብልጽግና ባለበት ሲረግጥ ፤ አንዳድ ግዜም ወደ ሁዋላ ሲሄድ፤ የህዝብ ኑሮ ሲጎሳቆል፣ ስራጥነትና ቦዘኔነት ሲሰፍን፤ ዜጎች በሃገራቸው አንደሁልተኛ ዜጋ ሲቆጠሩ፤ በማንኛም የሃገሪቱ ክፍሎች አየተዘዋወሩ መስራትና መኖር ሲከለከሉ፤ ህዝብ መፈናቀል አፈናና እንግልት ሲበዛበት ወይ ወደ ዓመፅ ያመራል ውይ የስራ እድልና አንፃራዊ ሰላም አገኛለሁ ብሎ ወደ አመነበት ሃገር ይሰደዳል። በሃገራችን እየሆነ ያለውም ይኸው ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በቁንጮነት የሚመሩት በየኣመቱ ወደ አረብ ሃገራት፣ አፍሪካ፣ አዎሮፓ፣ አሜሪካ፤ ካናዳ፤ አውስትራሊያ፣ አስያ የመሰደደውን የህዝብ ቁጥር በውል የሚአውቁት ይመስለናል። በተባበሩት መንግስታት ግምት 2 ሚሊዮን የሚበልጡ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ አሃጉራት ተበትነው እነደሚገኙ ይዘግባል። በርግጥ እርስዎና ግብራበሮችወ የሃገርን አንጡራ ሃብት እየዘረፋችሁ በተልያዩ የዓለም አቀፍ ባንኮች ካሸሻችሁት ንብረት ጋር ሲነጻጸር ቁጥሩ ኢምንት መስሎ ይታየዎት ይሆናል። አገር የሚገነባውን ኢኮኖሚ የሚፈጥረውን ህዝብ ማጣት ግን እጅግ የከፋ ጥፋት ነው። ይህ ለምን አንደሆነ የሚረዱት ይመስለናል።

ዶ/ር አድሃኖም የዚህ ሁሉ ችግር መንስዔ የሆኑትን ላእላይና ታህታይ (Basic and Super Structure) ምክንያቶችን መጠየቅና ማወቅ ተገቢ ይመስለናል። ከሙያዎም ሆነ ከሃላፊነትዎ አንጻር ጉዳዩን መመርመርና መረዳት ይጠበቅብዎታል። ለማስታወስ ያህል የሚከተሉትን በጥሞና ይመለክቱና የትኛው ነው የሃገርን ጥቅም የሚጎዳ ሃገርን የሚአጠፋ ስራ እየሰራ ያለው ብለው ይጥይቁ። አስር ሽህ ኪሎሜትር በድሪም ላይነር መጙዝ ሳያስፈልግዎ መልሱን አዲስ አበባ ላይ ያገኙታል።

በመጀመሪያ ሁሉም የሃገርን ትቅም ማስቀደምና ማስጠበቅ እንዳለበት እንስማማለን። ከሁሉም በላይ ግን ይህ ሃላፊነት ሃገሪቱንና ህዝብን እናስተዳድራለን በሚሉት መሪወችና ሃልፊወች ላይ አጅግ የገዘፈ መሆኑን ያለመጠራጠር መቀበል ያስፈልጋል። በኢትዮጵያ ላይ በጉልበት ነግሳችሁ የምታስተዳድሩትንና የምትገዙትን ህዝብና የሃገር ጥቅም የከዳችሁ የመጀመሪወችሁ ተጠያቂ አርስዎና ግብራአበሮችዎ ናችሁ። የመጀመሪያው ሃገር ሻጭና የህዝብ ጥቅም ነጣቂ ማነው ቢባል መልሱን ከጉያው ያገኙታል። ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ፀረ ህዝብና ፀረ ሃገር ድርጊታችሁን እንመለከት።

ለረዥም ዘመናት ነፃነቷዋንና አንድነቷዋን ጠብቃ የኖረችውን ሃገር አካልዋን ገንጥሎ ወደብ አልባ ያደረገ ወያኔ ወይስ ዲያስፖራ። በግራ ወይም በቀኝ አስተሳሰብ ከርስዎና ከቡድንዎ የተለየውንና የተቃወመውን ሁሉ የሚአስር፣ የሚገል የሚአሳድድ ማነው ወያኔ ወይስ ዲያኣስፖራ።

እርስዎ በኤርትሪዊነትዎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 1.9 GPA አግኝተው መግባት ሲፈቀድልዎ አማራዉና ሌላው ህብረተሰብ 2.2 GPA ካላመጣ የዩኒቨርሲቲ በራፍዋን ይረግጥም ነበር። ታዲያ ይህ አማራ ነው ሲጨቁን የኖረ። ይህነው ነፍጠኝነት። ለኀይለሥላሤ መንግሥስት ዕድሜ መለመን የነበረባችሁ አናንተ መሆን አልነበርባችሁም።

ከሃገሪቱ የቀላልና የከባድ ኢንዱስትሪዎች ዉስጥ 45% በአስመራ አልነበረምን። ከፒአሳ እስከ ብሄራዊ ቲያትር፤ከመርካቶ እስክ ኮተቤ፤ከብሄራዊ ቲአትር እስከ ደብረዚይት ይምግብ ቢቶችን፤የአልባሳትና የወርቅ መሸጫ ሱቆችን፤ ቡናና ሻሂ ቢቶችን፤ የትራንስፖርት ድርጅቶችን በአብዛኛው በኤሪትራዊያንና በወያኔ የተያዙ አይደሉምን። ማነው ኤርትራኖች ናቸው ትግሬዎች ናቸው ብሎ የጠየቀ። ይህ ሁኔታ በኃይለሥላሤም ሆነ በደርግ ጊዘ የነበር ሃቅ ነው። በርስዎና በወንበዴው ድርጅትዎ አማካይነት አማራውን፣ ኦረሞውን፣ ጉራጌውን፣ ቤንሻንጉሉን፣ አፋሩን፣ከምባታውን፤ሃድያውን፤ ሲዳማውን ወዘተ በጎሳው እያሳደዳችሁ የምታፈናቅሉና በሃገሩ ሰርቶ አንዳይኖር የምታደርጉ የመንግሥስት ቀማኞች አይደላችሁምን። ከዚህ የበለጠ የሃገር ትቅምን፤አንድነትንና እድገትን የሚጎዳ ነገር ምን ሊኖር ይችላል። ዲያስፖራው ይህን ሰርቶአል ካሉ ከነማስረጃዉ ያቅርቡልንና እንተማመን።እኛ እስከምናዉቀዉ ዲያስፖራ ያደረገው ይህን እኩይ ተግባራችሁን የተቃዉሟል። ዲያስፖራው አገርን ከጥፋትና ከዉድመት ለማዳን የሚንቀሳቀስ ይመስለናል ።

አማራው ኦረሞው ወዘተ ልዩ ተጠቃሚ አንደሆነ አድርጋችሁ በመንግሥት ፕሮፖጋንዳ ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ፣ በቡድን፤ እንዲሁም መዋቅርና መመሪያ ዘርግታችሁ የጥላቻ ዘር የምትዘሩና የምታናፍሱ አናንተ አይደላችሁም። በመንግሥት አዋጅና መመሪያ የሃገርን ጥቅም እያፈረሰ አገር ማስገንጠሉ አንሶ መሬት እየቆረሰ ለሱዳንና ለሶማሊያ በእጅመንሻነት የሚሰጥ ማን ሆነና ነው ዲያስፖራዉ የሚወቀሰዉ። ነፃነት ባለበት ሃገር ስለሚኖር እኩይ ተግባራችሁን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይቃወማል ለዓለም ህዝብም ያስረዳል። ይህ የሃገርን ጥቅም ማጥፋት ነው የሚባል ከሆነ ዲያስፖራው በጸጋና በኩራት የሚቀበለው ወቀሳ ይሆናል።ይሄ ሁሉ ሃቅ ማይከብድዎት ቢሆን የተሸከሙት የዶክትሬትና የመንግስት ስልጣንና ህሊናዎ እንዴት አይወቅስዎትም ።

ተፋቅሮ ፤ ተጋብቶ፤ተዋልዶ በአንድነት የኖረውን ህዝብ በዘር ሃረጉ በቁዋንቁው እየለያችሁ ለማተራመስ ድፍት ቀና የምትሉ እርስዎና ግብረአበሮችዎ አይደላችሁም እንዴ። ክዚህ የበለጠ የአገረ ጥቅምን ማፈራረስ ሌላ ምን ሊኖር ይችላል። ዲያስፖራውማ ተው ይህ ትክክል አይደለም አገረ ይበተናል፤ የአገር ጥቅም ይጎዳል እያለ ይጮሃል ። የማንኛው ተግባር ነው የሃገር ጥቅምን የሚጎዳው። ፍርዱን ለርስዎና ለቡድንዎ ከመተው ሌላ አምራጭ የለም።

በቤንሻንጉል፤በጉራፈርዳ፥ በአፋር፥ በኦረሞ ወዘት በመሳሰሉት ክልሎች እና አካባቢወች አማራውን፤ኦረሞውን፣ ጉራጌውን አፋሩን፣ አኝዋኩን እየነጠላችሁ የምታፈናቅሉ፣ ንብረቱን በመንግስት መምሪያና ልዩ ትእዛዝ የምትቀሙ ህጋዊ ቀማኞች አርስዎና ቡድንዎ አይደሉምን። የሃጋሪቱን ከፍተኛ ስልጣን ይዛችሁ ኣብዛኛውን የኢኮኖሚ፤ የማህበራዊና የፖለቲካ ተቁኣማትን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደራጃ ይዛችሁ ይህን ሁሉ ግፍና ኢሰበአዊ ድርጊት በንፁሃንና ሰላማዊ ዜጎችና በሃገሪቱ ላይ የምታዘንቡት ምን ለማትረፍ ነው። እርስዎና ግብረአበሮችዎ የምትፈጽሙት ወንጀልና ግፍ ሞልቶ ከፈሰሰ ውሎ አድሮኣል። አገሪቱ በግፋ ጨቅይታ ልትፈራርስ ተቃርባለች።የአገርን ጥቅምና ህልውና የሚፈታተን ተግባር አየፈጸማችሁ ዲያስፖርውን የሃገር ጥቅም አፍራሽ አድርጋችሁ ራሳችሁን እንደጲላጦስ ከደሙ ነፃነን ልትሉ ትፈልጋላችሁ። እንደርስዎ ያለ ተማርሁ የሚል ሰው ሎጂክና ፕሪንሲፕለ ትቶ ደም ከውሃ ይወፍራል አያል ዘር የማጽዳት ዘመቻ ሲካሄድ ጀሮዳባልበስ አያለ የሚጎዝ ምንዓይነት ህሊና ነው።

ኤርትራን ያስገነጠላችሁ አናንተ በሁአላም ከኤርትርዊያን ጋር ጦርነት ከፍታችሁ ህዝቡን ያስጨፈጨፋችሁ አናንተ። እምቢ ላገሬ እምቢ ለነፃነቴ ብሎ የዘመተውን አማራ ፣ ኦሮሞ፣ አፋር፣ ጉርጋጌ፤ ሲድማ፣ ከምባታ ወዘተ ከፊትለፊት አሰልፋችሁ ከ 70-100,000 ሕዝብ አላስጨረሳችሁም አንዴ። ሕዝቡ በደሙ ያስቀራትን ባድመን መልሳችሁ ለሻብያ አልሰጣችሁምን። በዛንጊዜ ኤርትራኖችን ከኢትዮጵያ ምድር ንብረታቸውን ቀምታችሁ ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ወደ አስመራ አልመለሳችሁምን።

አሁን ደግሞ አነዚህኑ ኤርትራኖች ከአስመራ ወደ ኢትዮጵይ አንዲመለሱ አድርጋችሁ በመንግሥት መስሪያ ቤት አንዲመለሱ፣ ንብረታቸው ከነወለዱ አንዲመለስ አላደረጋችሁምን። ማነው በኢትዮጵያ ህዝብና ንብረት ላይ አየቀለደ የሚገኘው። ይህ ሁሉ ተግባር የሃገር ጥቅምን መጉዳት አይደለምን። ለነገሩ በአመራር ላይ ያላችሁት አብዛኞቻችሁ ኤርትራኖች ስልሆናችሁ የኢትዮጵያን ጥቅም ታስተብቃላችሁ ተብሎ አይጠበቅም። ዲያስፖራው የሃገር ጥቅምን የሚጎዳ ነገር እንዳይሰራ ታስጠነነቅቃላችሁ። የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብያደርቅ ማለት ይህ ነዉ።

በስልጣን ወንበር ከትቆናጠጣችሁ በሁአላ እንደ መንግሥት ሀገ መንሥት ኣወጣችሁ። ማንም ሳይጠይቃችሁና ሳያስገድዳችሁ እናምንበታለን ብላችሁ ያወጣችሁትን ሀገመንግሥት አንድ አራተኛወን እንኹዋን በተግባር አልፈፀማችሁም ። በሃገራችን ታሪክ ኢትዮጵያ ያለህግ የምትተዳደርው ክ1991 ዓማተ ምህረት ጀምሮ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለህግ ተገዥ የነበረን ህዝብ ወደኾላ አየወሰዱ በህግ አልባ ስርዓት ከማስተዳደር የበለጠ ወራዳ ስራና ሕገአራዊትነት ምን ሊኖር ይችላል።ከዚህ የበለጠ የሃገረንና የህዝበን ጥቅም የሚጎዳና የሚአፈርስ ምን ነገር ይኖራል ።

በቅርቡ ወደ ሃገርቤት ጎራ ብዬ ሃገሪቱን በሰፊው አይቸ ተምልሻለሁ። እርግጥ ነው ሕንጻ ተቆልልዋል መንገድ ተሰረቶአል፤ የዝቅተኛና የከፍተኛ ትምህርት ቤቶችና ተቐማት እንዳሸን ፈልተዋል፤ ጤና ጣቢአወች ተሰርተዋል፤ የመብራትና የስልክ መስመሮች ተዘርግተዋል፤ የውሃ ቡአንቡወችና የስልክ መስመሮች ጨምረዋል። ይህን ስናይ እሰየው እንላለን። የሚገርመው የሚጠጣ ውሃ የለም፣ ህዝቡ የኤሌክትሪክ መብራት አጦ በሻማ ያመሻል፣ ተማሪወች ከከፍተኛ ትምህርት ተቅዋማት ተመርቀው በቅጡ ስማቸውን መጻፍ አይችሉም ተመርቀውም ቦዘኔ ናቸው፤ምርት ተመርቶ ህዝብ ፆሙን ያድራል። ሁልጊዜ በግብረሰናይ ድርጅቶች እርዳታ ከመጠየቅ አልወጣም።ጤና ጣቢወች ተሰርተው ባልሙያወች የሉም ህዝቡ በበሽታ ይሰቃያል።

ሖስፒታሎቻችሁ የመፀዳጃ ቤት ይመስላሉ።እንዲአውም በአሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙ መጸዳጃ ቤቶች በሃገር ቤት ካሉት ሆስፒታሎቻችሁ በንጽህና ሳይሻሉ አይቀሩም። የጎዳና ተዳዳሪው ቁጥር በየቀኑ ይጨምራል አሁንማ የመንግሥት ሰራተኛውም ተረጂ ሆንዋል። የዛሬ ሃይ ዓመት 85% የሆነው ህዝባችን በቀን ከ$1 ዶላር በታች በሆነ ገቢ ይኖር ከነበረበት ዛሬም የተቀየረ ነገር የለም። የትላይ ነው የ 11% ኢኮኖሚ እድገቱ። መቸም ምሁሩና ዶክተሩ አድሃኖም ይህን እውነታ በቀላሉ የመረዳት አቅም ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ግዴታም ስላለባችሁ ይህን ሃቅ ያስተባብላሉ ብለን አንጠብቀም።

የሃገር ቅርስና ታሪክ የሃይማኖት ትቁዋማትን፤ ባህልንና ታሪክን ማጥፋት የሃገርን ጥቅምና ማንነት ማጥፋት አይደለምን። ማነው የእስላሙን ህብረተሰብ ከኦርቶዶክሱ ጋር የሚአናቁር። ሌላዉ ቢቀር ከዛሬ ሽሕ ዓመት በፊት ባሕረ ነጋሽ ወይም ነጋሺ የሰራውን እንኩአን ማሰብ እንዴት ያቅታችሁኣል። ማነው አማራውንና ኦርቶዶክሱን እንዳይንሰራራ አድርገን አከርካሪውን ሰብረነዋል ብሎ በኦፊሲየልና በመገናኝ ብዙሐን ወጦ በዝና መልክ እያወራ ያለው። ከዚህ የበለጠ የሃገረ ጥቅምንና አንድነት ማጥፋት የበለጠ ምን ይኖራል ይላሉ። አገር ከፈረሰ እኮ አማራውና ኦሮሞው ብቻ አይደለመ የሚጠፋው እንናንተም ጭምር መሆኑ እንዴት አይታያችሁም። የሌሎች ጉአደኞችዎ አርቆ የማሰብ አድማስ የተወሰነ ቢሆን እንደርስዎ ያለ ምሁር እንዴት አደጋዉ አይታየዉም። ይህን ከመሰለ የሃገር ጥቅምን ማወደም የበለጠ ምንሊኖር ይችላልና ነው ዲያስፖራውን የምትወቅሱት።

በሃገርቤትና በውጭ ሃገር ያለው ተቃዋሚና ህዝብ በተደጋጋሚ የሚአቀርበው ጥያቄ የብሔራዊ እርቅንና ሠላምን የአንድነት መንግሥት እናቕቁም እያለ ሲለፍ ይኸው ሃያ ሁለት ዓመት አስቆጠረ። ይህን የተቀደሰ ሃሳብ በእምቢተኝነቱ ፀንቶ የሚገኘው ማነው ። ሃገርን ለአንድነትና ለትብብር የጠራ ተቃዋሚን ዲያስፖራ እንደሽብርተኛ የሚቆጥር መንግሥትና ዶክትሬት ምን ዓይነት ጭንቅላትና መሪ ነው። ዶር አድሃኖም አሁንም ጊዜ አለ አልመሸም ማስተካከል ይቻላል። ከርስዎና ከግብረአበሮችዎ የሚፈለገው ቅን ልቦናና ለሃገር ጥቅም አስቦ መንቀሳቀስ ነው። ለጥፋቱ ደረጃው ይለያይ እንጂ ሁሉም ሃላፊነት ወስዶ ለማስተካከል መስራት ይኖርበታል። ሐላፊነቱ መንግሥት ነኝ በሚለዉ ላይ የከበደ ነዉ።

ሕዝብና ኢግዚአብሔር ሁሉጊዜ ይቅር ባዮችናቸዉ። የሃገር ጥቅም ማጥፋቱን አቁማችሁ የሃገር አንድነትና ጥቅም ማስጠበቅን ቅድሚያ ሰጣችሁ ከሕዝብ ጋር ታረቁ። ካልሆነ ሃገር አገር ሲአርጅ አሜኪላ ይወልዳል እያልን ተቃውሞኣችንን እንቀጥላለን። ለዶ/ር አድሃኖም ካልነቁ መንጋቱን የሚኣበስር መልክተኛ አንልክባቸዋለን።

ቸር ይግጠመን
ዓቢቹ ነጋ ነኝ
ማይ 12, 2013

↧
↧

የወያኔ ፖሊስ አባል 12 ንጹሃን ዜጎችን ባህርዳር ላይ ረሸነ

$
0
0

Bahir dar(ዘ-ሐበሻ) በባህር ዳር ከተማ ልዩ ስሙ አባይ ማዶ በተባለ አካባቢ አንድ የወያኔ ፖሊስ አባል 12 ሰዎችን ገደለ፤ የመንግስት ሚዲያዎች ፖሊሱ ሰክሮ ነበር በሚል ዜናውን ለማለዘብ ቢሞክሩም አስተያየት ሰጪዎች ግን ጉዳዩን በጥርጣሬ እየተመለከቱት ነው።

የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ደረጀ አቻምየለህ “ግለሰቡ በውል ባልታወቀ ምክንያት በመንገድ ላይ በከፈተው ተኩስ ከሞቱት 12 ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል።” ካሉ በኋላ ገዳዩን የወያኔ ፖሊስ አባል ክትትል በማድረግ ልንይዘው ብንሞክርም ራሱን ወንዝ ውስጥ በመወርወር ሕይወቱን አጥፍቷል በማለት ተናግረዋል።

ይህ የወያኔ ፖሊስ አባል በትናንትናው ዕለት 12ቱን ንጹሃን ዜጎች ሲረሽን ከሟቾቹ ውስጥ ሴቶች ፣ ህፃናትና አዛውንቶች እንደሚገኙበት ሲታወቅ ፖሊሱ ይህን ወንጀል ለምን ሊፈጽም እንደቻለ የታወቀ ነገር አለመኖሩን መርማሪዎች አስታውቀዋል።

ትናንት ከተገደሉት ግለሰቦች መካከልም የአስከሬን ምርመራና ሌሎች ምርመራዎች በደንብ ሳይጠናቀቁ በጥድፊያ የሰባቱ የቀብር ስነ ስርዓት በአንድ ላይ በአስቸኳይ ዛሬውኑ እንዲፈጸም መደረጉና ከግድያው በስተጀርባ ያሉት ጉዳዮች ከወዲሁ አነጋጋሪ ሆነዋል።

↧

የ«ኢሕአዴግ ደጋፊዎች» መልካም እንቅስቃሴ –ግርማ ካሳ

$
0
0

ግርማ  ካሳ
Muziky68@yahoo.com

ግንቦት 6 ቀን 2005 ዓ.ም

EPRDF-supportrsበዳያስፖራ ቀንደኛ የኢሕአዴግ ደጋፊና የኢሕአዴግ ደጋፊዎች አስተባባሪ የሚባሉት፣ የሲቪሊቲ ፓልቶክ ክፍል ዋና አድሚን፣ አቶ ብርሃኑ ዳምጤ (አባ መላ) ከአዉራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ አደመጥኩ። አባ መላ ጠንካራ ትችት በኢሕአዴግ ላይ ሰንዝረዋል። ይሄም ብዙዎችን ሳያስገርም አልቀረም።  «አባ መላ፣ አራዳ ነዉ፤  ወያኔ ሊወድቅ ሲል ፍሬቻ አብሮቶ ታጠፈ» ያሉም አሉ። ፡) ፡) እኔ ግን ብዙ አላስገረመኝም። አባ መላን ጨምሮ በርካታ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች  ገዢዉን ፓርቲ የሚደግፉት በሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎች እንጂ፣  በዴሞክራሲና በሰብአዊ መብት መከበር ረገድ ብዙ ቅሬታዎች እንደነበሯቸው ስለማወቅ።

አባ መላን ጨምሮ በርካታ የሲቪሊቲ ክፍል አድሚኖች፣ ገዢዉን ፓርቲ ይደግፉ እንጂ፣  ገዢዉ ፓርቲ በሚያደርጋቸው የተሳሳቱ ተግባራት ላይ ተቃዉሟቸውን ያሰሙበት ጊዜ ጥቂት አይደለም።  ኢሕአዴግ በልማቱ ረገድ የሚያደርገዉን እየደገፉ፣ በዲሞክራሲና በሰብአዊ መብት ረገድ የሚደረጉትን ስህተቶች ግን  ብዙ ጊዜ ሲቃወሙ ሰምቻቸዋለሁ። ፓርቲዉ እንዲያሻሻል፣ አንዳንድ ጎጂ ፖሊሲዎቹንም እንዲቀይር፣  ዉስጥ ዉስጡን ግፊት ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው።

አንድ ምሳሌ ልጥቀስ። ከአራት አመታት በፊት ሰኔ ወር 2001 ዓ.ም ላይ ነዉ። ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በግፍ የታሰረችበት ወቅት። አቶ ስብሐት ነጋ በሲቪሊቲ ፓልቶክ ክፍል እንግዳ ሆነው ይቀርባሉ። በወ/ት ብርቱካን መታሰር ደስተኛ ያለሆኑትና ለመፈታቷ አጥብቀዉ ዉስጥ ለዉስጥ ሲታገሉ የነበሩት አባመላ፣ በገዢዉ ፓርቲ ላይ ያለቸዉን ተቃዉሞ በይፋ ገለጹ። ብዙ ታዳሚ ባለበት፣ አቶ ስብሃት ነጋን የሚከተለዉን ጠየቁ ፡

«አንዳንድ ጊዜ ከኢሕአዴግ በኩል፣ በዳያስፖራዉ የኢሕአዴግን ደጋፊዎች ሁሉ ሳይቀሩ፣ criticise የሚያደርጉት popular ያልሆኑ ነገሮችን ትወስዳላቹህ። አላስፈላጊ የሆነ። ለምሳሌ በቅርቡ በብርቱካን ሚደቅሳ ላይ የተወሰደዉ እርምጃ ምንም እንኳን ጥፋት አጥፍታለች ቢባልም ቴክኒካሊ፣ አስፈላጊ ያልሆነ confrontation ነዉ። ብዙ የምንሰራዉ፣ እንደ አገር የምንሰራዉ ብዙ ነገር አለ። በሕግ አንጻር ሁሉን ነገር እንደ ሌጦ መተርጎም የለብንም። ሌሎች moral values የሕዝብ አስተያየት የመሳሰሉ ነገሮችን ግምት ዉስጥ አስገብቶ ማየት ይገባል። የአንድ ጠንካራ መንግስት መለኪያዉ እርሱ ነዉ ብለን እናምናለን። ምን አልባት እነዚህን የመሳሰሉ ነገሮች፣ implication ያላቸዉን ጉዳዮች avoid ለማድረግ በኢሕአዴግ በኩል አንዳንድ ድክመት አለ። በሕዝብ ታዋቂ የሆኑ፣ በጥሩም ሆነ በመጥፎ ተወዳጅነት ያላቸዉ የሙዚቃ ሰዉ ሊሆን ይችላል። ስፖርተኛ ሊሆን ይችላል። ወይም የፖለቲካ ሰዉ። በተለይ የብርቱካን ጉዳይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ዉስጥ እርስዎም እንደሚያወቁት፣ የሴቶች ታጋዮች ሚና በጣም በጣም ትንሽ ነዉ። በተቃዋሚም እንኳን ብትሆን «በሕጋዊና በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ» ብላ የገባች እስከሆነች ድረስ፣ በአምጽ የሚታገሉትን ተቃዉመን፣ ጠመንጃ ከሻቢያ ጋር አንስተዉ ግለሰቦችን ለመግደል፣ ተቋሞችን ለማፍረስ፣ የሚንቀሳቀሱትንም እያወገዝን፣ በሰላም «አገሬ ዉስጥ ሕግና ሕገ መንግስት አለ። መንግስትን ፊት ለፊት እታገላለሁ» ብሎ የገባዉንም ኃይል እኩል treat ማድረግ የለብንም። በተለይ ሴት በመሆኗ፣ የልጅ እናትም በመሆኗ፣ በኢትዮጵያ ዉስጥ የሴቶችን ሚና ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ እምነት አለዉ ብዬ ስለማምን፣ ኢሕአዴግ በእንደዚህ አይነት ሰዎች ላይ የምትወስዱት እርምጃ በምንም መልክ defend ልናደርግ፣ justify ልናደርግ እያቃተን ነዉ። ከእንደዚህ አይነት unpopular ድርጊት መቼ ነዉ ኢሕአዴግ የሚገደበዉ? ይሄን ጉዳይ በቅርቡ ለመፍታት የታሰበ ነገር አለ ወይ ?»[1]

አንድ የሕወሃት ታጋይ የነበረ ወዳጅ አለኝ።  በእስረኞች መታሰር ዙሪያ ያለኝን ምሬት አደመጠና እንዲህ  አለኝ «ወንድሜ ግርማ፣ አንተ በምትለው እስማማለሁ። ኢሕአዴግ ዉስጥ ብዙ ችግር አለ። እኔ ጦርነት ላይ ጓደኞቼ ሲሞቱ አይቻለሁ። በርሃ ገብተን የታገልነው  ግፍን በመቃወም ነዉ። አሁን ግፍ በሕዝብ ላይ እንዲሰራ አንፈልግም። ኢሕአዴግ ለዉጥ ማድረግ አለበት። ኢሕአዴግ ማሻሻያ እንዲያደርግ ሁላችንም እንጣር። አንዳንች አንዳችንን እንደጠላት በማየት ሳይሆን  ለአገራችን የጋራ ጥቅም አብረን እንስራ» ነበር ያለኝ።  እኔም ተስማማሁ።

እንግዲህ እነዚህ የሚያሳዩት ብስለት ከማጣት የተነሳ፣ የኢሕአዴግ ደጋፊዎችን ሁሉ በአንድ ጨፍልቆ ማየት ትክክል እንዳልሆነ ነዉ። በጣም ብዙ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች፣ ኢሕአዴግ የሚያደርጋቸውን የልማት እንቅስቃሴች እየደገፉ በዴሞክራሲና በሰብአዊ መብት መከበር ዙሪያ ለዉጦች እንዲደረጉ፣ ዉስጥ ዉስጡን ግፊት የሚያደርጉ አሉ። በባለስልጣናቱ «እናሻሽላለን፣ ድክመታችን እናርማለን …» እየተባሉ፣  ከዛሬ ነገ መሻሻሎች ይመጣሉ በሚል ሲጠባበቁ የነበሩ ናቸው። ለዚህም ነዉ አብዛኞቻችን «በኢሕአዴግ ዉስጥ ለዉጥ እንዲመጣ ለማድረግ ከኢሕአዴግና ከደጋፊዎቹ ጋር መሰዳደብ ሳይሆን በጨዋነት መነጋገር አለብን። በኢሕአዴግ ዉስጥ ለዉጥ ለማምጣት የሚሰሩ ኢሕአዴጎችን ማበረታታ አለብን» ስንል የነበረዉ። ይሄ ጥረታችንም ነዉ «ወያኔ» ሲያስብለን የነበረዉ።

በነአባመላ እንዳየነዉ፣ የብዙ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች  ትእግስት እየተሟጠጠ የመጣ ይመስለኛል። በተለይም በሰብአዊ መብት መከበርና በዴሞክራሲ ዙሪያ፣ እንኳን መሻሻል ሊኖር፣ እየበሳስበት መምጣቱን፣ በፓርቲዉ ያሉ የበሰሉ ሰዎች ወደ ጎን እየተገፉ በአንጻሩም የጫካ አስተሳሰብ ያላቸዉ፣ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝንም አላሰራም ያሉ፣ የአስተሳሰብ እንጭጮች አይለው መዉጣታቸውን እና ኢሕአዴግ በራሱ ሰዎች ከሕዝብ ጋር በየጊዜው እየተጋጨ፣ በዉስጡ እየተሸረሸረ አደገኛ ሁኔታ ላይ መሆኑን የታዘቡ ይመስላል። የታቀዱ የልማት እንቅስቃሴዎች ከግቡ እንዲደርሱ፣ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ፣ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ.፣ የታሰሩ የሕሊና እስረኞች እንዲለቀቁ፣ ከሙስሊሞች ጋር ያለዉ ችግር በሰላም እንዲፈታና በአገራችን እርቀ ሰላም እንዲወርድ ለማድረግ፣ ኢሕአደግ ዉስጥ ያሉ እንክርዳዶች መወገድ እንዳለባቸው የተረዱ ይመስላል።

በመሆኑም በኢሕአዴግን ዉስጥ ያሉ ስልጣን የጨበጡ አክራሪዎችን ለመታገል፣ ከወሬ ያለፈ፣  አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን  ጀምረዋል። ከፍተኛ ገንዘብ የማሸሽ እንቅስቅሴ እየተደረገ እንዳለ የጠቆሙት፣ የሲቪሊቲ አድሚኖች በዴንቨርና በዲሲ፣  1 ዶላር በ27 ብር እንደሚመነዘር፣ አገር ቤት ያሉ አንዳንድ ግለሰቦችም እስከ 1 ሚሊዮን ዶላር ወደ ዉጭ ለማሸሽ፣  በአገር ቤት 27 ሚሊዮን ብር ለመክፈል እየሞከሩ እንደሆነ ይናገራሉ።

በአሜሪካና በካናዳ እንዲሁም በለንደን ፣ በዚያ መኖር ከጀመሩ አንድ አመት ባልሞላቸው ሰዎች የተገዙ ከ300 ሺህ ዶላር በላይ የሚያወጡ በርካታ ቤቶች ፣ (ሃብታሞች በሚኖሩባት በኦሬንጅ ካዉንቲ ካሊፎርኒያ ብቻ የታወቁ፣  ወደ አራት የሚሆኑ ቪላ ቤቶች) እንዲሁም የተከፈቱ በርካታ ቢዝነሶች እንዳሉ ያስረዱት የሲቪሊቶ ክፍል አድሚኖች፣ እነዚህን ከሕዝብ በተዘረፈ ገንዘብ፣ የተገዙ ቤቶችንና ቢዝነሶችን በተመለከተ ያሰባሰቧቸው፣ በፎቶ ግራፍ ላይ የተመረኮዘ መረጃዎች በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ይፋ እንደሚያደርጉ አሳዉቀዋል። (በነገራችን ላይ የሕወሃት ነባር ታግይ ያልኩት ከላይ የጠቀስኩት ወዳጄ የሚኖረዉ፣ እየሰራ፣ እንደማንኛዉም ሌላው ኢትዮጵያዊ መለስተኛ በሆነ አፓርተማ ዉስጥ ነው።  የ300 ሺህ ዶላር ቤት አልገዛም። ስለዚህ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ደጋፊ ሁሉ ገንዘብ በልቷል፣ ሰላይ ነዉ ወዘተረፈ  የሚል የተሳሳተ አስተያየት አይኑረን። ስንከስ በስሜት ሳይሆን በመረጃ ይሁን። እንሰልጠን።)

ይህ የተዘረፈዉን የሕዝብ ገንዘብ ለማስመለስ በ«ኢሕአዴግ ደጋፊዎች» የሚደረገዉን ጥረት፣  አገሩን በሚወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሊደገፍ ይገባዋል ባይ ነኝ። ይህ መልካም እንቅስቃሴ፣ ትምህርት ሆኖን፣ ዜጎችን «ወያኔ፣ ሆዳም» እያሉ የመስደብ አመላችንን አቁመን፣ «በምንስማማባቸው ነጥቦች ከኢሕአዴግ ደጋፊዎች ጋር አብረን መስራት መልመድ» አለብን እላለሁ።

በርካታ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች ፣ እኛ እንዲኖር የምንፈልገዉን መልካም ለዉጥ፣ በኢሕአደግ ዉስጥ ይፈልጋሉ። የሕሊና እሥረኞች በሙሉ እንዲፈቱ ይፈልጋሉ። የዲሞክራሲ ስርዓት እንዲገነባ ይፈልጋሉ። እርቀ ሰላም እንዲወርድ ይፈልጋሉ። አሁን በአገዛዙ እየተደረገ ያለዉ የልማት እንቅስቃሴ እንዲቀጥልም ይፈልጋሉ።

እንግዲህ ለመልካም ለዉጥ፣ ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣ ለእርቅ ፣ ለሰላም፣ ለልማት አብረናቸው የማንሰራበት ምክንያት የለም። የሚያሳዝነው አሁን ስልጣን ከበስተጀርባ የጨበጡትና በኢሕአዴግ ዉስጥም ችግር የፈጠሩት ጥቂት ጨካኝ፣ ዘረኛና ክፉ ባለስልጣናት መሆናቸው ነዉ። «EPRDF is controlled by hateful elements» [2]በሚል በቅርብ ጊዜ ይሄንኑ እዉነታ ለማንጸባርቅ ሞክሪያለሁ።

ለምሳሌ ጋዜጣኛ ተመስገን ዳሳለኝ እንደዘገበዉ፣ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንዲሁም አቶ ደመቀ ብርሃኑ፣  እነ እስክንድር ነጋ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ይፈልጋሉ። ዶር ቴዎድሮስ አዳኖም እና ከሃላፊነታቸው የተሰናበቱት፣ በአዲስ አበባ ከተማ በሰሩት ሥራ የማከበራቸው፣ አቶ አርከበ እቁባይ ተመሳሳይ አመለካከት እንዳላቸው ፣ ካሉኝ አንዳንድ መረጃዎችም ፍንጭ ለማግኘት ችያለሁ። ፕሬዘዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፣ የአጼ ኃይለስላላሴ ሃዉልት በአፍሪካ ሕብረት ከጋናዉ ንክሩማ ጎን እንዲቆም ደብዳቤ ጽፈዋል።

ነገር ግን ለእስረኞች መፈታትም ሆነ ለአጼ ኃይለስላሴ ሃዉልት መሰራት፣ መሰናክል የሆኑት፣ እነ እስክንድርን  «መለስ ዜናዊ አደገኛ ብሎ አስሯቸዋል። እዚያዉ ቃሊቲ  ይበስብሱ» የሚሉ ፣ እነ ደምቀ ብርሃኑን  አላሰራም ያሉ፣ ሚሊተሪዉንና ደህንነቱን የሚቆጣጠሩ፣ እፍኝ የማይሞሉ ጥቂት ግለሰቦች ናቸው። እርግጠኛ ነኝ አብዛኛዉ የኢሕአዴግ ደጋፊ፣ እነ አባመላ እንዳደረኩት፣ ከተነሳ፣ በአጭር ጊዜ ዉስጥ እነዚህ እፍኝ የማይሞሉ እፉኞች ታሪክ ይሆናሉ።

ምንም እንኳን በነአባ መላ እያየን ያለነዉ አስደሳች ዜና ቢሆንም፣ የተቀረዉ የተቃዋሚ ኃይል ግን የበለጠ እራሱን ማደራጀት ይጠበቅበታል። ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት በኢሕአዴግ ዉስጥ ለዉጥ እንዲመጣ መጠበቁ፣ ለዚያም መስራቱ  ተገቢ ቢሆንም፣ ያንን ብቻ ጠበቆ ግን ቁጭ ብሎ መቀመጥ ትልቅ ስህተት ነዉ። የተቃዋሚዉ ኃይል እራሱን ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ ፣ በቲቪና በስብሰባዎች ቀርቦ ከማዉራትና፣ መግለጫዎች ከማውጣት ያለፈ፣  በተጨበጡ ስራዎች ዙሪያ እራሱን የማሰማራት እንቅስቃሴ ይጠበቅበታል። ለዚህም ነዉ እንደ አንድነት ፓርቲና መኢአድ ያሉ፣ አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች ሆነ፣ ከአገር ዉጭ የሚገኙ፣ እንደ ሽግግር መንግስት ምክር ቤትና አዲሱ የኦሮሞ ዴሞክራሲያ ግንባር ያሉ ድርጅቶች፣ እንዲሁም  ኢትዮጵያዉያን ሁሉ፣  አገር ቤት ያለዉ የሰማያዊ ፓርቲ፣  ግንቦት 17 ቀን  2005 ዓ.ም በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ ፊት ለፊት በጠራዉ የሰላማዊ ሰልፍና ከግንቦት 15 እስከ ግንቦት 17፣ ጥቁር አልባሳት በመልበስ፣ ለሚደረገዉ የሰላማዊ ተቃዉሞ ወቅታዊ ጥሪ፣  ሕዝባዊ ምላሽ መስጠት ያለባቸው። ማንም ይጠራዉ ማንም፣ መልካም እስከሆነ ድረስ መደገፍ አለበት። የምንፈልገዉ በአገራችን ለዉጥ እንዲመጣ እንጂ ድርጅት አምላኪዎች አይደለንም። (በዚህ ረገድ እንደ ቃሌ ፓልቶክ ክፍል፣ ኢትዮጵያ ሪቪው፣ ዘሃበሻ፣ ኢኤም.ኤፍ የመሳሰሉ ድህረ ገጾች፣ እንዲሁም ኢሳት፣  ይሄንን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማገዝ እያደረጉ ያሉትን ጥረት ለማበረታት እወዳለሁ። በዚህ ጉዳይ በሰፊዉ የምመለስበት ይሆናል። እስከዚያም በቸር እንሰብት።

 


↧

ኢትዮጵያ በፍጥነት ወደኋላ እየገሰገሰች ነው!

$
0
0

ጌዲዮን ከኖርዎይ

Gedeon

ጌዲዮን ከኖርዎይ

የኢትዮጵያ እድገት መቼም በጣም አስገራሚና አነጋጋሪ መሆን ከጀመረ ሰነባበተ፥፥ ውሸት ሲደጋገም ውነት ይሆናል አለች ቻይና! አቶ መለስ ዜናዊ እንደቀልድ የተናገሩት ነገር ስር ሰዶ አሁን አሁን በሳቸው አጠገብ ያለፉት ሁሉ አብረው አጮሁት፥፥ የሚገርመው ነገር ግን አውሮ ፓውያንም አብረው አጮሁት እንደውም ስራቸውን በርዳታ ስም እንደፈለጋቸው እንዲያሮጡ መልካም አጋጣሚን የፈጠረላቸው ይመስላል፥፥

ግንቦት 13,2013 ቀን በኦስሎ ከተማ ሊተራቱር ህውስ በተባለው አዳራሽ ውስጥ ይህንኑ የኢትዮጵያን እድገት ለማስተጋባት በኖርዌጂያን ዴቨሎፕመንት ፈንድ በተባለ ድርጅት አማካኝነት Ethiopia – the reality behind the media በሚል ርእስ በተጠራው ስብሰባ ላይ ኖርዌጂያን ፖለቲከኞችና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች በእንግድነት በተገኙበት የውይይት መድረክ ላይ በርካታ ወድ ኢትዮጵያውያን በኖርዎይ እንዲሁም ኖርዌጂያን በቦታው ላይ ተገኝተው ነበር፥፥

ተጋባዥ ከነበሩት እንግዶች መካከል፥Gedeon2

  • ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ሚኒስቴር ሃይኪ ሆልሞስ ከሶሻል ሌፍት ፓርቲ
  • ፒተር ጊትማርክ የኖርዌጂአን ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ የኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ዋና ቃልአቀባይ እና
  • ዶክተር ሚሊዮን በላይ ኢኮሎጂካል ለርኒንግ እና ኮሚዩኒቲ አክሽን ዳይሬክተር ከኢትዮጵያ ሲሆኑ ስብሰባውን የመሩት አቶ አንድሪው ክሮግሉንድ የኖርዌጂያን ደቨሎፕመንት ኤንፎርሜሽን ኤንድ ፖሊሲ ዋና ክፍል ሃላፊ ነበሩ፥፥

ውይይቱን በይበልጥ ያተኮረው በስልጣን ላይ ባሉት አቶ ሃይኪ ሆልሞስ የኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ሚኒስቴር እና በአቶ ፒተር ጊትማርክ የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ የኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ዋና  ቃል አቀባይ መካከል ቢሆንም ዶክተር ሚሊዮን በላይ ብዙ ለመናገር ከኢትዮጵያ መንግስት ብዙም ፍቃድ የተሰጣቸው አይመስልም ነበር፥፥

Gedeon3

ይሁን እንጂ አቶ ሃይኪ ሆልሞስና በአቶ ፒተር ጊትማርክ መካከል የነበረው የልዩነት አቋም አቶ ሃይኪ ሆልሞስ ኢትዮጵያ ውስጥ እድገት አለ ስለሆነም የገንዘብ እርዳታ ማድረጋ እንቀጥላለን የሚል ሲሆን አቶ ፒተር ጊትማርክ በበኩላቸው አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ስለሚባለው እድገት ጥርጣሬ እንዳላቸውና እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ከግዜ ወደጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱ ኖርዎይ የምታደርገውን የገንዘብ እርዳታ እንድታቆም እንዲሁም እርዳታው አስፈላጊ ከሆነም በስልጣን ላይ ላለው መንግስት ሳይሆን ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚደርስበት መንገድ መፈለግ አለበት ሲሉ የሳቸው ፓርቲም በስልጣን ላይ ከወጣ ይህው እርዳታ እንደሚቌረጥና በማንኛውም ጊዜ ይህ ሁኔታ ሲሻሻል እርዳታው እንዴት እንደሚቀጥል የሚታይ ይሆናል ብለዋል፥፥Gedeon4

እንዲሁም ከተሳታፊዎች መካከልም ብዙ ጥያቄዎች ለዶክተር ሚሊዮንና ለአቶ ሃይኪ ሆልሞስ የተሰነዘረ ሲሆን የተሳታፊው አቋም የነበረው፥ የኖርዎይ መንግስት እየሰጠ ያለው የገንዘብ እርዳታ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግስት ህዝቦችን ለማፈን እያተጠቀመበት ነው፥ እርዳታው መረዳት ላለበት ህዝብ አልደረሰም፥ የሚሉና በርካታ የተቃውሞ መልክቶችን ያዘኡ ነበሩ፥፥

በመጨረሻም ምንም እንኳን ከተሰብሳቢው በርካታ የወቅታዊ የሃገራችን አንገብጋቢ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለውይይቱ ተጋባዥ እንግዶች የቤት ስራ የሚሆኑ በርካታ ጥያቄዎች በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል፥፥

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

↧

የናዝሬት ጉምሩክ የህግ ማስከበር ኃላፊ አቶ ተመስገን ጉልላት ታሰሩ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የወያኔ ሥርዓት ሰሞኑን በህግ ቁጥጥር አውያቸዋለሁ ካላቸው ተጠርጣሪዎቸ ጋር ሲፈለጉ ነበር የተባሉት አቶ ተመስገን ጉልላት ከአዲስ አበባ ወደ ጋምቤላ በመሸሽ ሱዳን ለመግባት ሁኔታዎችን ሲያመቻቹ ሊያመልጡ ሲሉ ተያዙ ሲል የወያኔ ሚድያዎች ሲገልጹ ተጠርጣሪው በእጃቸው የተለያዩ ሰነዶችና 160 ሺህ ብር ይዘው ሊሰወሩ ሲሉ ተይዘዋል ብለዋል።

 መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።

መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።

የጋምቤላ ጉሙሩክ ስራ አስኪያጅ ለሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ 80 ሺህ ብር በመስጠት ወደ ሱዳን ለመግባት ጥረት አድርገዋል በማለት የዘገቡት የወያኔ ሚዲያዎች ወደ ሱዳን ለማስገባት ተባብሯቸዋል ያሏቸውንም፡ አቶ ጌታቸው አሰፋንም በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተዘግቧል።
በተጨማሪም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታስረዋል የተባሉት 24 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዛሬ በዋለው ችሎትም ተጠርጣሪዎቹን በሶስት የክስ መዝገብ በመከፋፈል ፍርድ ቤቱ የተመለከተ መሆኑን የዘገቡት መንግስታዊ ሚድያዎች በእነ መላኩ የክስ መዝገብ ውስጥ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች መካተታቸውን አስታውቀዋል። አንደኛው ተጠርጣሪ አቶ መላኩ ፈንታ ጠበቃ ደንበኛቸው በዋስ ለመለቀቅ ያስችሏቸዋል ያሏቸውን ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ በቃል ማቅርባቸውም ታውቋል።
የሁሉንም ሀሳብ ያደመጠው ፍርድ ቤቱም በጊዜ ቀጠሮ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ ለነገ ቀጠሮ ይዟል። በተመሳሳይ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር፣ በአስርሺዎች የሚቆጠር ዶላርና ዩሮ ቤታቸው ሲበረበር ተገኘ በተባሉት በነገብረዋህድ የክስ መዝገብ ውስጥ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችንና የአቃቢ ህግ መከራከሪያን ያደመጠ ሲሆን መደበኛ የስራ ሰዓት በመጠናቀቁ በጊዜ ቀጠሮው ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ ይዟል ሲሉ የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።
በእነመላኩ የክስ መዝገብ ውስጥ የሚገኙ 7 ተጠርጣሪዎች
1.መላኩ ፋንታ
2.እሸቱ ወልደሰማያት
3.መርክነህ አለማየሁ
4.አስመላሽ ወልደማርያም
5.ከተማ ከበደ
6.ስማቸው ከበደ
7.ዶክተር ፍቅሩ ማሩ
ከተከሰሱባቸው ወንጀሎች መካከል ቀረጥና ታክስ በማጭበርበር እንዲሁም አራጣ በማበደር የተከሰሱ ግለሰቦች ክስ ስልጣንን በመጠቀም እንዲቋረጥ በማድረግና በዚህም ያልተገባ ሀብትን መሰብሰብ የሚል ይገኝበታል ።

በእነገብረዋህድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 11 ተጠርጣሪዎች
1.ገብረዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ
2.በላቸዉ በየነ
3.ጥሩነህ በርታ
4.ተስፋዬ አበበ
5.ነጋ ገብረ እግዚአብሄር
6.ምህረተአብ ካሳ
7.ሙሌ ጋሻው
8.አሞኘ ታገለ
9.ኮለኔል ሃይማኖት ታፈሰ
10. ሀብቶም ገብረ መድህን
11. ወይዘሮ ንግስቲ ተስፋዬ

ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ የተከለከለ ሲሚንቶ እንዲገባ ማድረግ ፣ በኮንትሮባንድ የተሰማሩ ግለሰቦችን በማገዝ ፣ ከተጠርጣሪዎች መካከል የሁለቱን ክስ የሚደግፉ ሰነዶችን ማሸሽ የሚል ይገኝበታል ።
በሶስተኛው የናዝሬት ጉምሩክ ባልደረቦች በሆኑት በነ መሀመድ ኢሳ የክስ መዝገብ ውስጥ የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎች
1.መሃመድ ኢሳ
2.ሰመረ ንጉሴ
3.ዘሪሁን ዘውዴ
4.ማር እሸት ተስፋዬ
5.ሙሉቀን ተስፋዬ
6.ዳኜ ስንሻው

የተከሰሱባቸው ወንጀሎች ደግሞ በኮንትሮባንድ የተለያዩ እቃዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረግና ያልተገባ ሀብት መሰብሰብ የሚሉ ናቸው።

↧
↧

Hiber Radio: የስዬ አብርሃ ወንድም ዳግም በሙስና ታሰረ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ!
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ግንቦት 4 ቀን 2005 ፕሮግራም
> አቶ መስፍን (በዲሲ የአቶ መለስን ልደት ሊከበር አይገባም ያለውን ተቃውሞ ካስተባበረው ግብረ ሀይል አስተባባሪዎች አንዱ ለህብር ከሰጡት)
> ከሰልፈኞቹ አንዱ (ሙሉውን ያዳምጡት)
> ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከቃሊቲ የጻፈው ደብዳቤን ተርጉመን ይዘናል
>
አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የግራዚያኒ ሐውልት እንዲፈርስ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ የሚያስተባብረው ግብረ ሀይል ቦርድ ም/ሰብሳቢ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
ሌሎች ቃለ መጠይቆች አሉን
ዜናዎቻችን-
– የስዬ አብርሃ ወንድምን ጨምሮ ከሙስና ጋር በተያያዝ የተጠረጠሩ 16 ከፍትኛ ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች ታሰሩ
- አገሪቱ በእስር አመታታ ውስጥ ከ11 ቤሌዮን ዶላር በላይ አጥታለች
- ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በሙስና ተጠርጥረው ስለታሰሩት እንዳይጽፍ በደህንነቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጠው
- ለአጼ ሀይለስላሴ ሐውልት ሊቆም ይገባል ሲሉ ፕ/ር ግርማ ወ/ጊዮርጊስን ጨምሮ ታዋቂ ሰዎች የፈረሙበት ጥያቄ ለሀይለማሪያም ደሳለኝ ቀረበ
- ለአቶ መለስ ልደት ሊከበር አይገባም ያሉ ኢትዮጵያውያን ዋሽንግተን ኤምባሲ ፊት ለፊት ተቃውኦ አደረጉ
* ፕ/ር ኤፍሬም ይስሐቅ ልደቱን ለማክበር ከመጡ የስርዓቱ ደጋፊዎች መካከል ነበሩ
- አቶ ሃይልማሪያም ደሳልኝ የፍትህ ሜኔስትራችውን አባረሩ እርምጃው ከአማራ ተወላጆች የዘር ማጽዳት ዘመቻ ጋር ያያዙት ወገኖች አሉ
- በኢትዮ ኬኒያ ድንበር ላይ በተቀሰቀሰ የጎሳዎች ግጭት 8 ሰዎች ሞቱ
- በቬጋስ በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ የፍሪያስ አሽከርካሪዎች ለገቨርነሩ ድምጻቸውን ለማሰማት
ሌሎችም ዜናዎች አሉን
↧

ሰውየው –ክፍል 1

$
0
0
ከይገርማል ታሪኩ 
Pen-4

ሰውየው

መካከለኛ ቁመና አላቸው: ሰውነታቸው ሞላ ደልደል ያለ ወንዳወንድ:: እድሜአቸው ወደ 70 አመት የሚጠጋ ቢሆንም የሰውነት አቋማቸውና ጥንካሪያቸው ሲታይ ሀምሳም የደፈኑ አይመስሉም:: የእግር መንገድ ይወዳሉ:: በውትድርና ያሳለፉት ዘመን ጥንካሪያቸው ላይ አሻራውን አሳርፏል:: እና አሁንምንቁ: ቀልጣፋ: ደፋርና ጠንካራ ናቸው:: ለሽርሽር ብሎ አብሯቸው የወጣን ሰው በላብ እስኪጠነፍር ድረስ ያሽከረክሩታል:: ደከመኝን ብዙም አያውቁም:: ቁጥብ አንደበት አላቸው:: በቁም ነገር ጊዜ ቁምነገር መናገር በቀልድ ጊዜም መቀለድ ይችላሉ:: ቁምነገራቸው ከመሬት ጠብ አይልም:: ጨዋታቸውአይጠገብም:: ካገኙት ጋር ሁሉ አፍ የሚካፈቱ ግን አይደሉም:: ከማን ጋር መዋልና ምን መስራት እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ:: ውለታ መዋል ይችላሉ:: ለተቸገረ ደራሽ: አሳቢና ተቆርቋሪ ናቸው:: ቤታቸው የሄደን እንግዳ ጠብ እርግፍ ብለው ያስተናግዳሉ:: ሰው በልቶ የጠገበ አይመስላቸውም:: አንድነገር ብቻ አይወዱም “ጥቃት”:: ጥቃትን ከምንም በላይ: ከራሱ ከሞትም ቢሆን አብልጠው ይጠላሉ:: ያላግባብ ጥቃት የፈጸመባቸውን ሰው ልኩን ሳያሳዩ አይለቁም:: ያም ሆኖ አጥቂው ጥፋቱን አውቆ ይቅርታ ከጠየቃቸው ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርገው ወደቀድሞው ለስላሳ ማንነታቸው ይመለሳሉ::የቤተክርስቲያን ሰው ስለሆኑ ይቅርታን የእግዚአብሄር መቅረቢያ መንገድ አድርገው ይወስዳሉ:: “ሽህ ጊዜ ኧረ ከዚያም በእጅጉ ለሚበልጥ ጊዜ ጥፋት እያጠፋን: ከፈቃዱ እየወጣን: በእብሪትና በትእቢት ስንት በደል ከፈጸምን በኋላ ‘በመጥፎ ስራችን ተጸጽተናል ማረን’ ብለን እግዚአብሔርን ይቅርታስንጠይቀው ይቅርታ ያደርግልናል አይደል? ይቅርታ እየለመንንና ይቅርታ እየተደረገልን እያለ በድያለሁና ይቅርታ አድርጉልኝ ብሎ የሚመጣን ሰው አይ አይሆንም ብለን እንዴት ልንገፋው እንችላለን:: ይቅርታ ካላደረግን ይቅርታን መጠየቅ የለብንም:: ይቅርታ የእግዚአብሔር ነው” ይላሉ ከዚህ ጋርየተያያዘ ጉዳይ ሲነሳ ከሰሙ::

ወደውትድርናው የገቡት በቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት ነው: በ1950ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ:: ትውልዳቸው ከደህና ቤተሰብ ቢሆንም አስተዳደጋቸው ግን እንደማንኛውም ተራ ኢትዮጵያዊ ነው:: ማንኛውም ህጻን ሆኖ ያደገውን ሆነው ነው ያደጉት:: ትምህርት ቤት ገብተው ተምረዋል:: ወጣትነትሁሉን አስፈሪ ነገር ለመድፈር ያስችላል:: ውትድርና ቀላል ነገር አይደለም:: ጨዋታው ከህይወት ጋር የተያያዘ ነው:: በዚያን ጊዜ የነበረ ወታደር ደረቱን ለጦር ግንባሩን ለጥይት ለመስጠት የቆረጠ እንደባህታዊ በየበረሀው በቀበሮ ጉድጓድ ለመኖር: ራሱን አሳልፎ አገርንና ህዝብን ከጥቃት ለመከላከል የተሰለፈነበር:: ኢትዮጵያ ሀገራችን የጠላት ችግር የለባትም:: ከአሁኑ የሶማሊያ ክልል አልፎ እስከ አዋሽ አርባ ድረስ ያለውን መሬት ከኢትዮጵያ በሀይል ነጥቆ ታላቋን የሶማሊያ ግዛት ለመመስረት ያለመው የዚአድባሬ መንግስት: ኤርትራን ከኢትዮጵያ አስገንጥለው የአረቡ ዓለም አካል ለማድረግ በግብጽፊታውራሪነት የተሰለፉት የአረብ ሀገሮች: የኢትዮጵያን ሰላምና እድገት የማይፈልጉት ሁሉ ጀብሀንና ሌሎች ሀገር በቀል አፍራሽ ሀይሎችን አሰልፈው ዙሪያ ገባውን የሚያቆስሉበት ዘመን ነበር:: ያኔ ነው ሰውየው ይህን ራስን ለመሰዋእትነት አሳልፎ በመስጠት ሀገርንና ህዝብን ለመታደግ የሚል አላማአንግበው ወደ ውትድርና የገቡት::

እኒህ ሰው ሻለቃ ሀይለየሱስ እጅጉ ይባላሉ:: ብዙ የሀገር አውራወች ከበቀሉበት ደቡብ ጎንደር ነው ትውልዳቸው:: የያኔው የ1950ዎቹ ወጣት ሀይለየሱስ ፈጣንና ቀልጣፋ ነበሩ:: በልጅነታቸው ከእኩዮቻቸው ጋር ሲጫወቱ ሮጦ የሚቀድማቸው: ታግሎ የሚጥላቸው አልነበረም:: ሽንፈትን አይወዱም: እናይታገላሉ ታግለውም ያሸንፋሉ:: በዚያን ወቅት የነበረው ይህ ለጥቃት ያለመንበርከክ ስሜት: ከራሳቸው አልፈው ለህዝብና ለሀገር እንዲሰለፉ አስገደዳቸውና ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደውትድርናው ገቡ:: በተራ ውትድርና ለአመታት ካገለገሉ በኋላ ለምክትል መቶ አለቅነት ተወዳድረው ከጓደኞቻቸውየተሻለ ውጤት አምጥተው በማለፋቸው ሆለታ የመኮንኖች ማሰልጠኛ ተቋም ገብተው በምክትል መቶ አለቅነት ተመረቁ::

የምክትል መቶ አለቅነት ማእረግ ካገኙ በኋላ በተለያዩ የጦር አውድማወች ከጓድ መሪነት እስከሻምበል አዛዥነት አገልግለዋል:: ያን ያገጠጠ የኤርትራ ተራራ እንደዝንጀሮ እየቧጠጡ በመውጣት ሻቢያንና ጀብሀን እያሳደዱ አይቀጡ ቅጣት ቀጥተዋል:: ወታደሮቻቸው በበሰለ አመራራቸውና ወታደራዊስልታቸው ያደንቋቸዋል:: ለሀገርና ለወገን ባላቸው ፍቅር ያከብሯቸዋል: በጀግንነታቸው ይመኩባቸዋል:: ዘመድ ወዳጆቻቸው እንዲሁም ጓደኞቻቸው ይኮሩባቸዋል:: የኤርትራን ደጋና ቆላ መሬቶች ጀብሀንና ሻቢያን ሲያሳድዱ ረጋግጠውታል:: ከተሰነይ እስከናቅፋ: ከአከለጉዘይ እስከምጽዋ ቆንጥሩንእየመነጠሩ አሜካላውን እየጠረጉ: ረሀብና ጥምን ተቋቁመው ድካም ሳያዝላቸው ተመላልሰውበታል:: በተደጋጋሚ በደረሰባቸው የመቁሰል አደጋ ምክንያት በምድር ጦር መምሪያ ውስጥ እንዲሰሩ ሲደረግ ደስተኛ አልነበሩም:: እኒያ በኤርትራ መሬቶች ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት እየተናነቁ ጥለውየሚወድቁት የትግል አጋሮቻቸው ሁኔታ በምናባቸው እየታያቸው ወደዚያው ሂድ ሂድ የሚል ስሜት ይተናነቃቸዋል:: ግን ምንም ማድረግ አልቻሉም: የበላይ ውሳኔ ነዋ!

የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ጸር የሆነው ወያኔ መራሹ ኢህአዴግ ስልጣን ሲቆጣጠር ሻለቃ ሀይለየሱስ ለተሀድሶ ከጓደኞቻቸው ጋር ወደጦላይ ተወሰዱ:: በጦላይ ቆይታቸው ብዙ አሳዛኝና አሳፋሪ ድርጊቶች አይተዋል:: በአንድ ወቅት አንቱ ተብሎ ይፈራና ይከበር የነበረ የጦር መሪ ባልሰለጠነ የዘር ሰራዊትከፍ ዝቅ ሲደረግ ማየትና መስማት ከምንም በላይ ያማል:: እንዳይቻል የለምና ይህም ታለፈና ሀይለየሱስ ከማጎሪያ ካምፑ ተሰናብተው ወያኔ ባስቀመጠው የእድሜ ገደብ ተጠቅመው የጡረታ መብታቸውን አስከብረው ኑሯቸውን ከአዲስ አበባ ወደባህርዳር አዙረው ቤት ሰርተው ልጆቻቸውን እያሳደጉመኖር ጀመሩ:: ወቅቱ እንዲህ እንዳሁኑ አልከፋም ነበርና ሻለቃው በጡረታ በሚያገኙት 400 ብር የማይሞላ ገንዘብ ልጆቻቸውን ለማሳደግ ብዙም አልቸገራቸውም::
ይህ በእንዲህ እንዳለ የወያኔ የጫካ ፖሊሲ በከፋ መልኩ መተግበር ጀመረ:: “አማራ የትግራይ ጠላት ነው:: አማራ መጥፋት አለበት” ብለው ወያኔዎች በመተዳደሪያ ደንባቸው ያስቀመጡትን ፖሊሲ በተግባር መተርጎም ጀመሩ:: አማሮች ቡና ለቅመው: እህል ሰብስበው: ወይም በማንኛውም የጉልበት ስራተሰማርተው ያገኟትን ጥሪት ለዘመመ ጎጇቸው ማቃኛ ለኑሮ መደጎሚያ ለማድረግ እግር ወደመራቸው አሊያም ስራ ይገኛል ብለው ተስፋ ወደአደረጉበት አካባቢ እንደሄዱ ሳይመለሱ በዚያው ወድቀው ቀሩ:: ነፍጠኛ መጣብህ እየተባሉ ብሄር ብሄረሰቦች እየተቀሰቀሱ በየአካባቢው አማሮች እየታደኑእንዲገደሉ ተደረገ:: አንገታቸው ተቆረጠ ሆዳቸው በሳንጃና በገጀራ ተቀደደ:: በደህናው ጊዜ ሁሉም አገሬ ብለው ከቦታ ቦታ መርጠው ለጤናቸው ወይም ለስራቸው የሚስማማ ነው ብለው ባመኑበት የሀገሪቱ ክፍል ካካባቢው ህዝብ ጋር ተዋልደውና ተስማምተው የኖሩት አማሮችና የአማራ ዝርያያለባቸው ሰዎች ሁሉ ይህ ቀረ የማይባል ግፍ ተፈጸመባቸው:: ም/ጠ/ ሚኒስትር የነበረው ታምራት ላይኔ በጅጅጋ ተገኝቶ ‘እዚህ ያሉት አማሮች ሊገዟችሁ: ሊዘርፏችሁ: ሊገድሏችሁ የመጡ ናቸው:: ለምን ዝም ብላችሁ ታይዋቸዋላችሁ:: ዱላው በእጃችሁ ጠላቶቻችሁ በደጃችሁ’ አይነት ንግግር አደረገናየአማሮችን የስቃይ ደረጃ በእጅጉ አናረው:: በአሶሳ: በወተር: በበደኖ (የየአካባቢውን ሰለባ እግዜር ይቁጠረው) አማሮች ከነነፍሳቸው በገደል ተጣሉ: እንደበግ ታረዱ:: አዛውንቶች: ህጻናት: ወንዶች ሴቶች: ሁሉም ተረሸኑ:: አማራነት ብቻውን ለሞት ዳረገ:: አቅም ያገኙ ሀብት ንብረታቸውን ሳይይዙነፍሳቸውን ለማትረፍ የተወለዱበትና ያደጉበትን: ሀብት ንብረት አፍርተው ይኖሩ የነበረበትን አካባቢ ጥለው ባዶ እጃቸውን ተሰደዱ:: ‘አማሮች ወደመጡበት ሲመለሱ ምንም ነገር እንዳያንጠለጥሉ:: ባዶ እጃቸውን ነው የመጡት: መመለስ ያለባቸውም ባዶ እጃቸውን ነው:: ቤታቸውን: ድርጅታቸውንእንዳትገዟቸው:: ምን ያደርጉታል:: ይዘውት አይሄዱ ተብሎ በየሰፈር ተሿሚወች እንዲለፈፍ ተደረገና አማሮች ባዶ እጃቸውን ‘በለው በለው’ እየተባሉ የወደቁት ወድቀው የተረፉት እንዲሰደዱ ተደረገ::

ኢትዮጵያ የምትባለዋ ሀገር ታሪክና ስም የሚያንገሸግሻቸው ወያኔወች ኢትዮጵያን ለማጥፋት በቅድሚያ አማራውን ማጥፋት ብለው ወስነው የጥፋት ዘመቻውን አጧጧፉት:: አማሮች በየቦታው የጣእር ድምጽ አሰሙ:: በረጅም ዘመን የሞት የሽረት ትንቅንቅ ያቆያትን: በጥቁሮች ታሪክ ያልታየ ገድል ፈጽሞ ከነጮች ጋር ድንበር ተካሎ በደምና በአጥንቱ መሰረት የገነባትን ኢትዮጵያን ያወረሰ ኩሩ ኢትዮጵያዊ እየታደነ ታረደ:: ለደርቡሾች: ለግብጾች: ለቱርኮች: ለሶማሊያወች: ለጣሊያኖችና ለእንግሊዞች ያልታጠፈ ክንድ በገዛ ልጆቹ ዛለ:: የወራት የእግር መንገድ እየተጓዘ ደረቅ ዳቦቆሎና እንጎቻ እየገመጠ በዚያመንገድ ባልነበረበት ዘመን እባቡ እየነደፈው: ወባው እየጣለው: የዱር አውሬው እያጠቃው: ይኸ ሁሉ የሚያጎድልበት ሳይበግረው ረሀብና ጥሙን ችሎ በጦር በጎራዴ ከዳር ዳር እየዞረ: የሀገር ትርጉም ቀደም ብሎ ገብቶት ‘እኔ ለሀገሬ’ ብሎ ከጠላት ጋር ተናንቆ በደምና በአጥንቱ አስከብሮ ባቆያት ኢትዮጵያላይ የተቀመጡ የጊዜው ሰዎች የዚያን አንበሳ ኢትዮጵያዊ ልጆች እየለቀሙ በመፍጀት ውለታውን ከፈሉ:: ከኢትዮጵያዊነት ደረጃው ዝቅ ብሎ የማያውቀው አማራ ሀገሬ እንዳለ የሀገር ትርጉም ባልገባቸው ርጉም ልጆቹ ሀገሩን አጣ:: ‘የአማራው ሀገር የት ይሆን?’ ሲልም ጠየቀ:: አማራ ተብለው በብአዴን ስርየተሰባሰቡ ከንቱወች ‘ከክልላቸው የወጡት አማሮች ጉዳይ አይመለከተንም’ አሉ:: በዚህ ጊዜ ነበር ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ የሚወተውተውን አማራ ‘እስቲ መጀመሪያ ለራሳችን እንሁን- እያጠፉንኮ ነው’ በሚል መልክ እንደራጅ ብለው ጥቂት መሰሎቻቸውን ይዘውመዐሕድን የመሰረቱ::

ሻለቃ ሐይለየሱስ እጅጉ ጡረታ የወጡት ከትግል አይደለም:: በዚያም ላይ እየተጠቃ ያለው ወገናቸውና በደም እየታጠበች ያለች ሀገራቸው ጉዳይ ሰላም ነስቷቸዋል:: እናም የወያኔን ወደስልጣን መምጣት ተከትሎ ጠበንጃቸውን የሰቀሉት ሻለቃ ጠበንጃቸውን አውርደው ና ወልውለው በሚያውቁበትናወያኔን በሚገባው መንገድ ሊያነጋግሩ አልፈቀዱም:: የአለም ሁኔታ ለእንደዚህ አይነት ትግል አመች አይደለም:: ወያኔና ሻእቢያ ደርግን አሸንፈው ስልጣን እንዳልነጠቁ አሳምረው ያውቃሉ:: ‘ኢምፔሪያሊዝም ይውደም’ እያሉ የሰው ምስል ቀርጸው በእሳት ሲያቃጥሉ የነበሩትን ደርጎች ለመበቀል: በምትኩምየራሷን ተላላኪወች ለማንገስ አሜሪካ በነደፈችው መርሀ ግብር መሰረት የጦር ጀኔራሎች እንዳያዋጉ በተለያየ ነገር በመደለል ውጊያውን እንዳበላሹትና ሁሉም ነገር በወያኔና በሻእቢያ የበላይነት እንዲደመደም እንዳደረጉ ያውቃሉ:: የኢትዮጵያ ጦር ‘ይህንን ቦታ አጥቅተህ ያዝ’ ይባላል:: ጦሩ የተባለውን ቦታአጥቅቶ ሲይዝ ምክንያቱን በማያውቀው ሁኔታ ወደኋላ አፈግፍግ ይባልና እንደገና ሌላ ትእዛዝ ይመጣበታል:: በዚህም ምክንያት በስንት መስዋእትነት የያዘውን ምሽግ እንደቀላል ነገር ለቆ እንዲመለስ ይደረጋል:: ብዙም ሳይቆይ ‘ተለዋጭ ትእዛዝ’ ተብሎ አጥቅተህ ይዘኸው የነበረውን ምሽግ በአፋጣኝመልሰህ በእጅህ አድርግ ይባላል:: ይህ ሲሆን ግን የሻእቢያ ጦር በውጊያ ተሸንፎ ለቆት የነበረውን ምሽግ ቀድሞ እንዲገባበት ተደርጎ ነው:: ከጠላት ማስለቀቁን እንጅ ተመልሶ በጠላት እጅ መውደቁን ያልጠረጠረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ወደምሽጉ ሲመለስ የመሸገው የጠላት ጦር በሩምታ ተኩስ ይቀበለዋል-በዚህ አይነት የተበላሸ አመራር የሰራዊቱን የውጊያ ፍላጎት አሟጠው አጠፉት:: ይህን ሀይለየሱስ ጠንቅቀው ያውቃሉ:: ሶሻሊስት ርእዮተአለምን ይከተሉ የነበሩ ሀገሮች ሁሉ እጣ ፈንታ ይኸው ሆኗል:: የሶቭየት ህብረትን መፈራረስ ተከትሎ ‘ኢምፔሪያሊዝም ይውደም’ እያሉ ኢምፔሪያሊዝምን ይወክላልብለው ሆዱ የተንዘረጠጠ: ጥርሱ ያገጠጠ: የዶላር ምልክት በተነፋ ሆዱ ላይ የተለጠፈበት የካርቶን ስእል እየሰሩ ሲያቃጥሉና ኢምፔሪያሊዝምን ያጠፉ ያህል በደስታ ሲቃ በእሳቱ ዙሪያ ክብ እየሰሩ ሲጨፍሩ የነበሩትን ሶሻሊስቶች አሜሪካ በአካል ተበቀለቻቸው- ብትንትናቸውን አወጣቻቸው- ሀገራቸውንጭምር:: የኢትዮጵያም ታሪክ ያው ይህንን የተከተለ ነው:: ይህ ለሀይለየሱስ እንግዳ ነገር አይደለም:: ሶሻሊዝም እንደስርአት ካከተመ በኋላ ሁሉም ነገር በአሜሪካ በጎ ፈቃድ ስር ወደቀ:: ወዲያ ወዲህ ማለት አልተቻለም:: ችግር አለብኝ የሚል ወገን ሁሉ በሰላማዊ ሰልፍ የአሜሪካና የአውሮፓ ሀገሮችኤምባሲወች ባሉባቸው ከተሞች ‘እግዚኦ’ ብሎ በደልን ማሰማት ብቸኛ አማራጭ ሆነ:: በስሜት ተነሳስቶ ‘ዘራፍ’ ብሎ ጫካ የሚገባ ሰው ቢኖርም ትርጉም የለውም:: የያዘውን ጥይት አስጨርሰው ካስተኮሱ በኋላ በዱላ አባሮ መያዝ ይቻላል:: ውጊያ ለመጀመር የሎጀስቲክስ ተከታታይ አቅርቦት: የስልጠናናየቴክኒክ እርዳታ: የመረጃና የነጻ መሬት መኖር ወሳኝ ነው:: ያንን ማግኘት እጅግ ከባድ ነው:: አንደኛ ወያኔ ማንኛውንም የኢትዮጵያ ጥቅም አሳልፎ በመስጠት ከበፊት የኢትዮጵያ መሪወች ሁሉ በተለየ ለጎረቤት ሀገሮች ተመችቷል:: ሁለተኛ ወያኔ የአሜሪካ ተላላኪ በመሆኑ ሁለንተናዊ ድጋፍ ይደረግለታል-መረጃን ጨምሮ:: ስለዚህ የተሻለው መንገድ በደልን በእግዚኦታ ማሰማት ነው:: ይህንን የተረዱት ሻለቃ የአማራውን ጩኸት ለመጮህ መዐሕድን ተቀላቀሉ::

ይቀጥላል

↧

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ የሰማያዊ ፓርቲን የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ደገፈ

$
0
0

EYNM New Logo(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 29 2005 ዓም የአፍሪካ ህብረት የወርቅኢዮቤልዮ በአል በሚከበርበት ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ተከትሎ ”የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው!” ያለው የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ “ሰማያዊ ፓርቲ በመግለጫው የጠቀሳቸው አራት ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ መልስ እንዲያገኙ ከሚታገልላቸው ዋና ዋና የህዝብ ጥያቄዎች መካከል ውስጥ የሚገኙና ዘረኛው የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በዘረጋው የጭቆናና የግፍ መረብ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በግዴለሽነት በግልፅ በአደባባይ ከሚፈፅመው ስቃይ ፣ መከራና ፣ እንግልት ጥቂቶቹ በመሆናቸው ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረበው ወቅታዊና ተገቢ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪን ሙሉ ለሙሉ የተቀበለው መሆኑን በአፅንዎት ይገልፃል::” ሲል ባወጣው መግለጫ ላይ አስታወቀ።

ንቅናቄው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው “የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ህዝባዊ በመሆኑ ፤ በዚህ ዘረኛ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ከልክ ያለፈ ጭቆና ፣ ረገጣና ፣ እንግልት ደርሶብኛል የምትሉ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ፣ በምንወዳት ሃገራችን ለህዝብ የሚበጅ ቀና ለውጥን የምትመኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ፤ እንዲሁም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ የሃይማኖት ተቋማትና ፣ የሲቪክ ማህበራት ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነትና የህዝብ አደራ በጫንቃችሁ እንደተሸከማችሁ በመገንዘብ ፤ የሚጠበቅባችሁን ህዝባዊ ተልኮ መፈፀም ታሪካዊ ግዴታችሁ መሆኑን በመረዳት ፤ ከሰማያዊ ፓርቲ ህዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ጎን እንድትቆሙ ሲል በጥብቅ እያሳሰበ ፤ ሃገራዊ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል:: የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው!” ብሏል።

Download (PDF, 291KB)

 

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live