Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

“የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ አይደለም”–አብርሃ ደስታ (ከአዲስ ጉዳይ መጽሔት ጋር ያደረገው ቃለ-ምልልስ)

$
0
0

abreha desta
አዲስ ጉዳይ መጽሄት ቅጽ 8 ቁ. 205/ የካቲት 2006

አዲስ ጉዳይ፡- የህወሓት የ39 ዓመታት ጉዞ በግልህ እንዴት ታየዋለህ?

አብርሃ ደስታ፡- በእኔ አመለካከት የህወሓት ጥረት ከመጀመሪያ አንስቶ ስልጣን ለመያዝ ነው፡፡ አሁንም በስልጣን ለመቆየት ሲሉ ኢኮኖሚውን እየተቆጣጠሩት ነው፡፡ የህዝቡን መረጃ የማግኘት መብት፤ የህዝቡን አስተሳሰብ ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ነው ያሉት፡፡ ጉዞው ስልጣን የመያዝ እና በስልጣን የመቆየት ጉዳይ ነው።

አዲስ ጉዳይ፡- ፓርቲው ግን ‘‘ለመመስረቴ ምክንያቱ የህዝብ ብሶት ነው’’ ይላል፡፡

አብርሃ ደስታ፡- ይህ ፕሮፓጋንዳ ነው። መጀመሪያ ለትግል ሲነሱ ህዝቡ የስርዓት ለውጥ ፈልጎ ታግሏል። ነገር ግን የህወሓት መሪዎች ስልጣን የመያዝ ዓላማ እንጂ ህዝቡን የስልጣን ባለቤት ማድረግ አልነበረም። በመሆኑም የህዝቡን ብሶት ስልጣን ለመያዝ ተጠቅመውበታል። ከዚህ ውጪ ለእኔ የእነርሱ ደርግን አስወግደው ስልጣን መያዝ የደርግን ሚና ለመጣወት እንጂ ህዝቡን ለመጥቀም አልነበረም።

አዲስ ጉዳይ፡- አንዳንዶች ህወሓት ወደ ኋላ አካባቢ የትግል መስመሩን ስቷል ሲሉ ሌሎች ደግሞ ፓርቲው ከመመስረቱ አንስቶ ዓላማው ስህተት ነበር ይላሉ። የአንተ አስተያየት ምንድነው?

አብርሃ ደስታ፡- እዚህ ላይ እኔ ህወሓትን የማየው በሁለት ከፍዬ መሆኑ ይታወቅልኝ። ስልጣን ፈላጊው የህወሓት አመራር እና ነፃነት ፈላጊው የህወሓት ታጋይ፡፡ ደርግ ገና ስልጣኑን ከያዘ ከወራት በኋላ ወደ ጫካ ገቡ። ስለዚህ የህወሓት አመራሮች ጫካ የገቡት የደርግ መንግስትን ጭካኔ ስላዩ ወይም የደርግን አምባገነንነት ስለተገነዘቡ ነው ለማለት አልደፍርም። ምክንያቱም በጥቂት ወራት ውስጥ ብቻ የህወሓት አመራሮች የደርግን ጨቋኝነት የሚያውቁበት ሁኔታ አለ ማለት በጣም አስቸጋሪ ነው። ዓላማቸው ስልጣን ነበር። ሲነሱም እንደሚታወቀው ትግራይን ለማስገንጠል ነበር፡፡ ይሄም ሆኖ ህወሓቶች ሲንቀሳቀሱ የደርግ መንግስት የወሰደው የኋይል እርምጃ ነበር። ይሄ እርምጃ ግን በጣም በስህተት የተሞላ ሆነ፡፡ ደርግ ጫካ የገቡትን ሰዎች ለማንበርከክ ሲል ህዝቡን በማስፈራራት ብሎም የመግደል እና ሌሎችም እርምጃዎችን ይወስድ ነበር፡፡ ይሄን ተከትሎም ህዝቡ የደርግን ግፍ በመቃወም ተነሳስቷል። ህዝቡ ለትግል በተነሳበት ወቅት ህወሓትን ተቀላቅሏል፡፡ የአብዛኛው የህወሓት ታጋይም ሆነ የትግራይ ህዝብ ዓላማ ከጭቆናና ከግድያ ለመዳን እንጂ ስለ ትግራይም ሆነ ስለ ኤርትራ መገንጠል ምንም የሚያስቡበት ጊዜ አልነበራቸውም፡፡ ይሁን እንጂ ይሄን የኅብረተሰቡን ጭቆና የማስወገድ እንቅስቃሴ ለራሳቸው ፍላጎት አውለውታል፡፡

አዲስ ጉዳይ፡- ኢህኣዴግ የአራት ፓርቲዎች ግንባር ቢሆንም ፍፁም የህወሓት የበላይነት በግንባሩ ነግሷል የሚሉ አሉ። ይህን ሀሳብ እንዴት ታየዋለህ?

addis guday magazine
አብርሃ ደስታ፡- አብዛኞቹ የኢህኣዴግ አባል ፓርቲዎች የህወሓት ውጤቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች ህወሓት እንዲመሰረቱና እንዲደራጁ ያደረጋቸው ናቸው፡፡ በዚህ አምናለሁ፡፡ ይህንን ሃሳብም እቀበለዋለሁ፡፡ ነገር ግን እዚህ ላይ አንድ ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ ህወሓት ራሱ የጥቂት ግለሰቦች ስብስብ መሆኑ ነው።

አዲስ ጉዳይ፡- ይህንን ሃሳብ ዘርዘር አድርገህ ብታብራራው?

አብርሃ ደስታ፡- በትግሉ ወቅት በጊዜው በነበረው ጨቋኝ ስርዓት የተነሳ ህዝቡ ሌላ የተሻለ አማራጭ ስላልነበረው ህወሓትን ደግፏል፡፡ ይሁን እንጂ ህወሓት ስልጣን ከያዘ በኋላ በሺኅ የሚቆጠሩ ታጋዮችን ሆን ተብሎ እንዲባረሩ ተደርገዋል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ገና ፓርቲው ስልጣን እንደያዘ የአመራሩ ተነኮሎች ግልፅ እየሆኑ ሲመጡ የህወሓት ታጋዮች መቃወም በመጀመራቸው ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ነው ህወሓት የተወሰኑ ግለሰቦች ስብስብ መሆኑ መረሳት የለበትም የምለው፡፡

አዲስ ጉዳይ፡- አንድ ወቅት ህወሓት በትግራይ የሚከተለው የፖለቲካ ስልት ‘‘እኔ ከሌለሁ ደርግ ይመጣባችኋል’’ ዓይነት መሆኑን ተናግረህ ነበር።

አብርሃ ደስታ፡- አዎ! ይሄ እውነት ነው፡፡ እንደውም ዋናው የህወሃት የትግራይ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያው እኔ ከሌለሁ ሌሎች መጥተው ይበሉሃል የሚሉት ሃሳቦች ናቸው፡፡ በእርግጥ የደርግ ስርዓት እንዳይመለስ መፈራረሱ የታወቀ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ግን በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይሄ ፕሮፖጋንዳ እየሰራ አይደለም። በትግራይ ውስጥ ብዙ ተቃውሞ አለ። በእርግጥ ይሄ ‘‘ደርግ መጣ’’ የሚለው ቃል የትግራይን ህዝብ ማስደንገጡ አይቀርም። በጊዜው ብዙ ስቃይና ግድያ ያየ ህዝብ ስለሆነ ማለቴ ነው፡፡ ስለዚህ ይደነግጥና ‘‘ከደርግማ ህወሓት ይሻለናል’’ ይላል፡፡ ይሁን እንጂ ደርግ ሊመለስ እንደማይችል ከዚህ በኋላ በጥቅሉ ወደ ወታደራዊ ስርዓት ልንመለስ እንደማንችል ለህዝቡ በማስረዳት ለውጥ የምናመጣበትን መንገድ እናመቻቻለን የሚል ዕምነት ነው ያለኝ፡፡ ይሄ ፕሮፖጋንዳም ካሁን በኋላ አይሰራም።

አዲስ ጉዳይ፡- ይህን የምትልበት ምክንያትህ ምንድነው?

አብርሃ ደስታ፡- ለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ህዝቡ ደርግ ሊመለስ እንደማይችል በሚገባ እያመነ መምጣቱ ነው። እኛም በዚህ ላይ በስፋት እንሰራበታለን። ህዝቡም ዲሞክራሲያዊ አሰራር እና ዲሞክራሲያዊ መንግስት እንደሚያስፈልገው እየተረዳ ነው። ይሁን እንጂ የህዝቡ ግንዛቤ እያደገ በመጣ ቁጥር የህወሓት አፈናም በዚያው መጠን እያደገ መምጣቱ አይቀርም። በዚህ የተነሳም ህዝብ እየታፈነ ነው። የመሰብሰብ፤ የመደራጀትና የመናገር ዲሞክራሲያዊ መብቶቹን አሁን እየተነጠቀ ነው። በዚህ ላይ ተገቢውን መልካም አስተዳደር እያገኘ አይደለም። በዚህ የተነሳም ህወሓት ደርግ ይመጣል ብሎ ለሚነዛው ፕሮፖጋንዳ የትግራይ ህዝብም ‘‘እናንተም እኮ ሌላው ደርግ ናችሁ’’ እያለ ነው። ‘‘ደርግም የሚደበድበንና የሚገድለን ስንናገር መብታችንን ለማስከበር ስንሞክር እንጂ እናንተም ማፈኑንና መግደሉን ጀምራችኋል። እናንተ እራሳችሁ እያፈናችሁ በመሆኑ ደርግ መጣ አትበሉን፡፡ እናንተ እራሳችሁ እንደ ደርግ እየሆናችሁ ነው’’ በማለት ህዝቡ ግልፅ መልዕክት አስተላልፏል። በዚህ የተነሳ ይህ ደርግ ይመጣባችኋል የሚለው ፕሮፖጋንዳ የሚሰራ አልሆነም።

አዲስ ጉዳይ፡- ብዙዎች በትግራይ የህወሓት ደጋፊ እንጂ ተቃዋሚ አለ ብለው አያምኑም። አንተ ደግሞ ተቃውሞ አለ እያልክ ነው . . . .

አብርሃ ደስታ፡- አዎ! በትግራይ ተቃውሞ አለ ብዬ ለእነዚህ ሰዎች ላረጋግጥላቸው እፈልጋለሁ። እንደውም በሙሉ ነፃነት ህዝቡ ምርጫ ማድረግ ቢፈቀድለት ህወሓት በትግራይ ይመረጣል የሚል እምነት የለኝም። ለምን ብትል እኛ በተለያዩ ቦታዎች ተዟዙረን ህዝቡን በደንብ አናግረናል። በሄድንበት የትግራይ አካባቢ በሙሉ ግን ተቃዋሚ አለ። ህዝቡ እኛን እንደሚደግፍ እየገለፀልን ነው። ነገር ግን ህዝቡ የሚጠራጠረው ‘እኛ ሰው እንፈልጋለን ነገር ግን ህወሓት በምርጫ ቢሸነፍ ስልጣን ያስረክባል የሚል ግምት የለንም። እናንተን ሆነ ሌሎች ተቃዋሚዎችን ያፍናል። ከዚህ በባሰ መልኩም ሊያጠፋችሁ ይችላል። በተለይ ለዲሞክራሲያዊ አሰራር ዕድል መሆኑን ስለምናውቅ በዚህ መንገድ ለውጥ ለመምጣቱ እርግጠኞች አይደለንም’ እያሉ ነው ያሉት። ስለዚህ እኔ ከዚህ ሃሳብ የወሰድኩት ከሌሎች ግምት በተቃራኒው አፈናው በትግራይ የባሰ መሆኑን ለማሳየት ነው። ይብዛም ይነስ በሌሎች አካባቢዎች እኮ ሰላማዊ ሰልፍ እየተፈቀደ ነው። በትግራይ ግን ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ መሰብሰብ እንኳን እየተከለከለ ነው።

አዲስ ጉዳይ፡- አፈናው ባይበዛ በትግራይ ተቃዋሚዎች በብዛት ይኖሩ ነበር ብለህ ታስባለህ?

አብርሃ ደስታ፡- በየትኛውም የትግራይ አካባቢ ከተወሰኑ ካድሬዎች በቀር ህወሓትን የሚደግፍ የለም። ጥቂት ደጋፊዎችን ፖሊስንና መከላከያውን ይዞ ነው ህዝቡን በዘዴ የሚያቀናው እንጂ እንደ ህዝብ የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ ነው የሚለው ለእኔ አሁን የማይሰራ ሃሳብ ነው።

አዲስ ጉዳይ፡- መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመደመር ህወሓት/ኢህኣዴግ እስከ 40 ዓመት በስልጣን መቆየት እንዳለበት እየተናገረ ነው።

አብርሃ ደስታ፡- ህወሓት ገና 50 ዓመት ይገዛል የሚለውን ነገር በትግራይ አዘውትረው በአደባባይ የሚናገሩት ነው። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን እንዲህ ያለው አቋም የተሳሳተ ነው። በእርግጥ የእነርሱ ኋይማኖት በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችላቸውን ነገር ብቻ ማድረግ ነው። ልማት ያለ ዲሞክራሲ አይመጣም። ልማትን የሚያመጣው መንግስት ብቻ ሳይሆን ህዝቡ ነው። ህዝቡ የልማቱ አምጪ እስከሆነ ድረስ በሙሉ ነፃነት ህዝቡ መስራት፤ በማንኛውም ቦታ በእኩልነት የመታየት መብቱ መከበርና ሰው በስራው እንጂ በሌላ አመለካከት መገምገሙ መቆም አለበት። ይሄ ነገር እስካልመጣ ድረስ ዘላቂ ልማት አይኖርም።አሁን ባለው ሁኔታ እንኳን ለውጥ ሊመጣ ቀርቶ ለውጡ እንዳለ እንኳን ለመቆየት የሚችል አይደለም፡፡

አዲስ ጉዳይ፡- ህወሓትን ለረጅም ዓመታት ከመግዘት የሚያግደው ምንድን ነው?

አብርሃ ደስታ፡- ህወሓት በከፍተኛ ደረጃ በሙስና የበሰበሰ ነው። እንኳን በውጪው ህዝብ ይቅርና በራሱ ውስጥ እንኳን በጣም ብዙ ቅሬታዎች አሉ። በዚህ መሰረት ህወሓት ጊዜ ቢሰጠውም ለውጥ ሊያመጣ የሚችል አይደለም። ምክንያቱም ሙስናና አድልዎ በቡድኑ ውስጥ ተበራክቷል። በህዝቡም ያለው ተቀባይነት ዝቅ በማለቱ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ እየቀነሰ ነው።

አዲስ ጉዳይ፡- የተለያዩ ሰዎች በህወሓት የተነሳ የትግራይ ህዝብ በሃብት ክፍፍሉ የተለየ ተጠቃሚ እንደሆነ ያምናሉ።

አብርሃ ደስታ፡- ምን አለ መሰለህ። በእርግጥ በህወሓት የስልጣን ዘመን እየበለፀጉ ያሉ ግለሰቦች አሉ። ነገር ግን እነዚህ የበለፀጉ ግለሰቦች ለባለስልጣነቱ የቅርብ የስጋ ዝምድና ያላቸው ናቸው። ወይም ራሳቸው ባለስልጣናቱ ናቸው። በመሆኑም በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች እነዚህ ትግርኛ ተናጋሪዎች ፎቅ ሲገነቡ ወይም የተለያዩ ቢዝነሶችን ሲሰሩ እያዩ የትግራይ ተወላጆች ሃብታም እየሆኑ ነው ብለው ቢናገሩ አይፈረድባቸውም። ምክንያቱም እነማን መሆናቸውን አያውቁም። ከዚህ ውጪ አብዛኛው የትግራይ ህዝብ በድህነት ውስጥ ስለመኖሩም መረጃ ላይኖራቸው ይችላል። ስለዚህ አብዛኛው የትግራይ ህዝብ በድኅነት እየኖረ የባለስልጣናት ዘመዶች ሃብት እየሰበሰቡ መሆናቸውን በደንብ የምናውቀው እኛ የትግራይ ሰዎች ነን። በሌላ ቦታ በአማራ፣ በኦሮሚያም ሆነ በሌላው ክልል ሃብት የሚሰበሰብ ትግርኛ ተናጋሪ ብታይ አንተም የትግራይ ሰው ሃብት እያካበተ ነው የሚል ሃሳብ ልታዳብር ትችላለህ። በመሆኑም የሌላው ክልል ነዋሪ እንዲህ በማለቱ ሊፈረድበት አይገባም። ጉዳዩን በሚገባ ማስረዳት የሚኖርብንም እኛው የትግራይ ህዝቦች ነን። ባለስልጣናቱና ዘመዶቻቸው ከህዝብ የተሰጣቸውን ሃላፊነት አላግባብ በመጠቀም ሃብት እየሰበሰቡ መሆናቸውን ማጋለጥ ያለብን እኛው የትግራይ ሰዎች ነን።

አዲስ ጉዳይ፡- ህወሓት በኢኮኖሚው ላይ በበርካታ ድርጅቶች መሳተፉ፣ የደህንነት ኃይሉን መጠቀሙና ነፃ ሚዲያውንም ማዳከሙ ለሰላማዊ ትግሉ ተስፋ አስቆራጭ ነው የሚል ሃሳብ ይነሳል . . .

አብርሃ ደስታ፡- እውነት ነው። እንደተባለው ህወሓት ኢኮኖሚውን በስፋት መቆጣጠሩ ሚዲያውንም መቆጣጠሩ ወይም የግል ሚዲያውን አለመፈለጉ፤ በሰላማዊ ትግሉ ላይ እንቅፋት ይፈጥራል። ነገር ግን እንቅፋት ስለሚፈጥር፤ መንግስት አፋኝ በመሆኑ እና ለሰላማዊ ትግሉ በሩን በመዝጋቱ የተነሳ ተቃውሞ እንዳስፈለገ መታወቅ አለበት። እኛም እየተቃወምን ያለነው ይህንኑ አካሄድ ነው። እኛ እንደምናምነው ሚዲያውን ስለተቆጣጠረ፣ ህዝቡን ስላፈነ የሰላማዊ ትግል መንገድ ችግር ሊያደርስበት ይችላል እንጂ ሊያስቆመው አይችልም። ህዝቡ ለውጥ እስከፈለገ ድረስ መንግስት የፈለገውን አፈና ቢያካሂድ አስፈላጊን መስዋዕትነት በመክፈል ህዝቡን እያደራጀንና እያስተማርን ለውጥ ማምጣት ይቻለናል የሚል እምነት ነው ያለኝ።

አዲስ ጉዳይ፡- የህወሓት ምስረታ ሲታሰብ የተለያዩ መስዋዕትነት የከፈሉ ታጋዮች ስማቸው አብሮ ይነሳል። አንተ በግልህ መስዋዕት የሆኑት ታጋዮች ዓላማ ዳር ደርሷል ትላለህ?

አብርሃ ደስታ፡- ይሄ ነገር ሲነሳ ጉዳዩን በጥንቃቄ በሁለት ከፍለን ማየት ይኖርብናል። የመሪዎቹ ዓላማ ስልጣን መያዝ ነበረ ብዬ ነው የማምነው። የእኛ ወላጆች ዓላማ ግን ነፃነት ነበር። ስለዚህ ለእኔ የትግሉ ዓላማ አልተሳካም ባይ ነኝ። ምክንያቱ ደግሞ የታጋዮቹ ዓላማ ለሰው ነፃነትን ማምጣት ነበር። አሁን ግን ነፃነት የለም። አፈና ነው ያለው። ስለዚህ የታጋይ ወላጆቻችን ዓላማ ህዝቡን ለማፈን እስካልነበረ ድረስ ዓላማው አልተሳካም የሚል እምነት ነው ያለኝ።

አዲስ ጉዳይ፡- የትግራይ ህዝብ እና የህወሓት መሪዎች በኤርትራ መገንጠልም ሆነ በኢትዮጵያዊ ህብረብሄራዊ ስሜት የተለያየ አቋም ያላቸው መሆኑ ይነገራል። እውነት ነው?

አብርሃ ደስታ፡- አዎ! የህወሓት መሪዎች ዓላማ ኤርትራን ማስገንጠልን የሚጨምር ነበር። ይሄን አቋማቸውን ደግሞ የተለያዩ ዶክመንቶች ጭምር ይመሰክሩታል። ህዝቡም ሆነ ታጋዮቹ ግን የኤርትራን መገንጠል የሚደግፉ አልነበሩም። ይሄን የህወሓት ኤርትራን ማስገንጠል ዓላማ የማይደግፉ ታጋዮች ሲገኙ ይቀጡ እና ይባረሩ ነበር። በተለይ ለኤርትራ ህዝብ ባርነት ወይስ ነፃነት የሚል ሪፈረንደም ሲቀርብ ብዙ ታጋዮች ተቃውመውታል። ይህ የህወሓት አመራር ድጋፍ ያለውን ሃሳብ በመቃወማቸው፤ የአሰብ ወደብ ጉዳይንና የዲሞክራሲ ጥያቄን በማንሳታቸው ባንድ ጊዜ ወደ 32 ሺኅ የሚጠጉ ታጋዮች ከህወሓት ተባረዋል። ከእነዚህ ውስጥ የታሰሩም የተገደሉም አሉ።

አዲስ ጉዳይ፡- ህወሓት የኢትዮጵያን የባህር በር አስነጥቋል ብለህ ታምናለህ?

አብርሃ ደስታ፡- አዎ! በትክክል አስነጥቋል ነው የምለው። ህወሓት ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታጣ ምክንያት ሆኗል።

አዲስ ጉዳይ፡- የህወሓት አመራሮች የአማራ ህዝብን ከገዢው መደብ ጋር ደብሎ በመሳል የብሄር ጥላቻ እንዲከሰት አድርገዋል ተብለው ይተቻሉ። አንተ ምን ትላለህ?

አብርሃ ደስታ፡- የህወሓት አመራሮች የአማራ ህዝብን ከገዢው መደብ ጋር አንድ አለመሆኑን ያውቃሉ። ነገር ግን ሆን ብለው ህዝቡንና ገዢ መደብን አንድ አድርገው የሚያቀርቡት ደግሞ ህዝቡ ተባብሮ በአንድ ላይ መቆም ከቻለ ለስልጣናቸው ስለሚያሰጋቸው ጭምር ነው። ይህ ዓይነቱ አቋም ደግሞ ከድሮም ጀምሮ የሚያራምዱት ነው። እኛ ልጆች ሆነን የሚነገረን ደርግ ማለት አማራ ማለት ነው ተብሎ ነበር። አማራ ማለት ደግሞ ደርግ ነው። በመሆኑም አማራ ገዢና ጨቋኝ ነው የሚሉ ነገሮች ናቸው። እስካሁን ድረስ ፀረ አማራ የሆኑ ዘፈኖች አሉ። ምክንያቱም ፀረ አማራ ማለት ፀረ ደርግ እንደማለት ስለነበር ነው። ይህ አስተሳሰብ የከፋፍለህ ግዛ ስትራቴጂ እንጂ የትግራይ ህዝብ በሙሉ ህወሓት አለመሆኑ እንደሚታወቅ ሁሉ የደርግ ስርዓት እና የአማራው ህዝብ አንድ አለመሆናቸው ይታወቃል። እነርሱ ግን ይሄን ይጠቀሙበታል፣ ከስልጣን በላይ የሚያስቡት ነገር ስለሌለ ማለቴ ነው።

አዲስ ጉዳይ፡- ያለህበት አረና ፓርቲ በትግራይ ውጤታማ የሚሆን ይመስልሃል?

አብርሃ ደስታ፡- በእርግጥ ብዙ አፈናዎች እየተካሄዱ ነው። ህዝቡን ለማወያየት ስንሞክር ስብሰባ እየተሰረዘብን፤ ከዚያም አልፎ ድብደባ እየደረሰብን ነው። ይሁን እንጂ የትግራይ ህዝብ ለውጥ እንደሚፈልግ ለእኛ ተስፋ ስጥቶናል። በመሆኑም እኛ ውጤታማ እንሆናለን ብዬ ነው የማስበው።

አዲስ ጉዳይ፡- አቶ ስብሃት ነጋ ‘‘አረናዎች የተቆጡ ህወሓቶች ናቸው’’ የሚል ሃሳብ ሰንዝረዋል። በእርግጥ አረና ህወሓት ነው?

አብርሃ ደስታ፡- አረናን እንደ ፓርቲ ከህወሓት ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። ነገር ግን ጥቂት የቀድሞ የህወሓት ሰዎች ወደ አረና ስለገቡ በቂም ተበሳጭተው ነው በሚል ነገር ያነሳሉ። እነዚህ ሰዎች በእርግጥ ህወሓት ነበሩ። ነገር ግን ህወሓት ችግር እንዳለበት ሲረዱ ከፓርቲው በመውጣት አረና የተሻለ አካሄድ እንዳለው ሲረዱ የእኛን ፓርቲ ተቀላቀሉ። ከዚህ ውጪ ከፖለቲካ ርዕዮተ ዓለምም ሆነ ከአሰራር አንፃር በዓረናና ህወሓት መካከል ብዙ ልዩነቶች አሉ።

አዲስ ጉዳይ፡- ልዩነታችሁን በምሳሌ ልታስደግፍ ትችላለህ?

አብርሃ ደስታ፡- ለምሳሌ በእኛ ፓርቲ ውስጥ ማዕከላዊ ዲሞክራሲያዊነት ብሎ ነገር የለም። ሌሎች አካሄዶቻችንም በስፋት ከህወሓት የሚለዩ ናቸው። እነርሱ ወደ ኃይል እርምጃ የገቡት እኮ ለህዝቡ የእኛን አቅጣጫ በዝርዝር ስናስቀምጥ ጎልቶ በወጣው ልዩነት የተነሳ ነው። ስለዚህ ህወሓት ለስልጣን የሚቀናቀነውን ማንኛውንም ፓርቲ ማጥላላት ልማዱ ነው። ይህንን እኛም ስለምናውቀው ከህወሓቶች ለሚሰነዘር አስተያየት እኛ ያን ያህልም የምንጨነቅበት ጉዳይ አይሆንም።

አዲስ ጉዳይ፡- ህወሃት በትግራይ ወይም ኢህአዴግ በኢትዮጵያ በምርጫ ስልጣን የሚለቅ ይመስልሃል?

አብርሃ ደስታ፡- ህዝቡን መቀየር ከቻልንና ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብለን ህዝቡን ካስተባበርን በምርጫ ፓርቲው ስልጣን ሊለቅ ይችላል። በእርግጥ ፓርቲው በምርጫ ስልጣን ለመልቀቅ ፍቃደኛ አይደለም። የፈለገውን ያህል ኀይል ተጠቅሞ ህወሓት በስልጣን ላይ ለመቆየት እንደሚፈልግ ይታወቃል። ነገር ግን በምርጫ ተቀጥቶ ስልጣን እንዲለቅ ማስገደድ ይቻላል። ምርጫውን የሚሰርቅበት መዋቅሩን በማሳጣት ለህዝብ ድምፅ የሚንበረከክበት ዕድል አሁንም አለ።


ኢትዮጵያ እየከሳች አላሙዲ በሃብት እየወፈሩ ነው፤ የዓለማችን 61ኛው ቢሊየነር ሆኑ

$
0
0

alamudi 1
(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው የዓለማችን የቢዝነስ መጽሔት ፎርብስ በየዓመቱ የዓለማችንን ቢሊየነሮች ደረጃ የሚያሳውቅበትን መረጃ ይፋ አደረገ። ባለፈው ዓመት የዓለማችን ሁለተኛው ሃብታም የነበሩት የማይክሮሶፍት ባለቤት ቢል ጌትስ የዓለማችን አንደኛ ቢሊየነር ሲሆኑ የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙከምበርግ 21ኛው የዓለማችን ቢሊየነር ሆኗል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በመሬት ነጠቃ የሚከሰሱት ሼህ መሀመድ አላሙዲ የዓለማችን የሃብታምነት ደረጃቸው ከዓመት ዓመት እድገት እያሳየ አምና ከነበሩበት የ65ኛ ደረጃ 4 ደረጃዎችን በማሻሻል የዓለማችን 61ኛው ሃብታም ሆነው በመጽሔቱ ተቀምጠዋል። እንደ ፎርብስ ገለጻ የ8 ልጆች አባት የሆኑት በአባታቸው የሳዑዲ፤ በእናታቸው ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሆኑት አላሙዲ $15.3 ቢሊዮን አላቸው።

ከሳዑዲ አረቢያ ሃብታሞች መካከል ሁለተኛው የሆኑት አላሙዲ የወያኔ/ኢሕአዴግ ደጋፊ ከመሆናቸውም በላይ፤ ከስር ዓቱ ጋር በፈጠሩት ስር የሰደደ ወዳጅነት በአድልዎ አብዛኛው የኢትዮጵያ ወሳኝ የንግድ ተቋማት በርሳቸው ስር እንዲያዙ ትልቅ ውለታ እንደተዋለላቸው በተደጋጋሚ እንደሚተቹ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ። ምንም እንኳ ሼኩ በነዳጅ ዘይት ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ቢሆኑም በተለይም የኢትዮጵያን ወርቅ በእርሳቸው ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የሰውዬው ሃብት ከእለት ወደ ዕለት እንዲጨምር አስችሎታል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።

የፕላኔታችን 10ሩ ቢሊነሮች የሚከተሉት ናቸው።

1ኛ. ቢል ጌትስ 76 ቢሊዮን ዶላር
2ኛ. ቻርሎስ ሳሊም ሄሉ 72 ቢሊዮን ዶላር
3ኛ. አማሪኮ ኦርቴጋ 64 ቢሊዮን ዶላር
4ኛ. ዋረን ብፌት 58.2 ቢሊዮን ዶላር
5ኛ. ላሪ ኤልሰን 48 ቢሊዮን ዶላር
6ኛ. ቻርለስ ኮች 40 ቢሊዮን ዶላር
7ኛ. ዳቪድ ኮች 40 ቢሊዮን ዶላር
8ኛ. ሼልደን አንደርሰን 38 ቢሊዮን ዶላር
9ኛ. ክርስቲ ዋልተን እና ቤተሰቦቿ 36.7 ቢሊዮን ዶላር
10ኛ. ጂም ዋልተን 34. 7 ቢሊዮን ዶላር

የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ በ28.5 ቢሊዮን ዶላር 21ኛ፣ አላሙዲ በ15.3 ቢሊዮን ዶላር 61ኛ፣ ቸልሲ ስፖርት ክለብ ባለቤት ኢብራሞቪች በ9.2 ቢሊዮን ዶላር 137ኛ ሆነዋል።

(ሰበር ዜና) አንድ ሰው ከተገደለ በኋላ ሹፌሮች ባደረጉት አድማ ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የሚወስደው መንገድ ከተዘጋ 3 ቀን ሆነው

$
0
0

Zehabesha 2(ዘ-ሐበሻ) ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የሚወስደው መንገድ ከተዘጋ 3 ቀን እንደሞላው በአካባቢው የከባድ ሹፌር አሽከርካሪዎች ለዘ-ሐበሻ ገለጹ። እነዚህ ሹፌሮች እንዳስታወቁት ይህ መንገድ የተዘጋው የከባድ መኪና ሹፌሮች ባደረጉት አድማ የተነሳ ነው።

ለዘ-ሐበሻ መረጃ ያቀበሉት ሹፌሮች እንደገለጹት ለከባድ መኪና አሽከርካሪዎቹ የሥራ ማቆም አድማ ምክንያት የሆነው አንድ ሹፌር ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ መንገድ ላይ በመገኘቱ የተነሳ ነው። በገዋኔ አካባቢ ይህ መንገድ እንደተዘጋ የገለጹት ሾፌሮቹ መንገዱ በመዘጋቱ የተነሳ የቆሙት መኪኖች ብዛት በኪሎ ሜትር እንደሚቆጠር አስታውቀዋል።

የስራ ማቆም አድማ ያደረጉት እነዚሁ ሹፌሮች ጥያቄያቸው የደህነንት ዋስትና እንደሆነ የገለጹት ምንጮቹ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ተከበው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

Sport: ከሶፖት ሻምፒዮና ከአትሌቶቻችን ምን እንጠብቅ?

$
0
0

ከቦጋለ አበበ

በቀጣዩ ወር መጀመሪያ በሚካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ አስራ አንድ አትሌቶችን ወደ ፖላንድ ሶፖት እንደምትልክ ይጠበቃል። ከአስራ አንዱ አትሌቶች በተጨማሪ ሁለት ተጠባባቂ አትሌቶች ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑም ታውቋል።
በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ ካሠማራቻቸው አትሌቶች ጥንካሬና አቋም በመነሳት በትንሹ አራት ሜዳሊያዎች ሊመዘገቡ እንደሚችል መገመት ይቻላል።

መሐመድ አማን

ሙሃመድ ድል አድርጎ ሲገባ!

ሙሃመድ ድል አድርጎ ሲገባ!

የዓለም የስምንት መቶ ሜትር ሻምፒዮኑ ወጣት አትሌት መሐመድ አማን ያለፈውን ዓመት በስኬት ያጠናቀቀ አትሌት ነው። ከዳይመንድ ሊግ እስክ ዓለም ሻምፒዮና ያሉ ውድድሮችን ጠራርጎ በማሸነፍም በርቀቱ ኮከብ መሆኑን አሳይቷል።
መሐመድ በዘንድሮ ዓመት ያካሄዳቸውን ውድድሮችም በጠቅላላ በማሸነፍ የአምናው ብቃቱ አብሮት እንደሚገኝ አሳይቷል። ኢትዮጵያ በሶፖት የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ ከምትጠብቅባቸው አትሌቶች መካከል መሐመድ ግንባር ቀደሙ ነው።
መሐመድ ከሁለት ዓመት በፊት እንዲህ በርቀቱ ስሙ ገናና ሳይሆን ቱርክ ኢስታንቡል ላይ በተካሄደ ተመሳሳይ ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ ማስመዝገብ ችሏል። መሐመድ ያኔ ያስመዘገበው የወርቅ ሜዳሊያ በታላላቅ ዓለምአቀፍ መድረኮች የመጀመሪያው ነበር። በዘንድሮው ሻምፒዮናም መሐመድ ያለፈውን ክብሩን አስጠብቆ እንደሚመጣ እርግጠኛ መሆን ይቻላል። ለእዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳየው የሚገኘው ድንቅ አቋም ምስክር ይሆናል።

ገንዘቤ ዲባባ

በለንደን ኦሊምፒክና በሞስኮው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተደብቃ የነበረችው የጥሩነሽ ዲባባ ታናሽ እህት ገንዘቤ የዘንድሮው የውድድር ዓመት «የእኔ ነው» እያለች ትገኛለች። ያለፈውን ዓመት እዚህ ግባ በማይባል ውጤት ብታጠናቅቅም ዘንድሮ ለማመን የሚከብድ አቋም በማሳየት ጀምራዋለች።
ገንዘቤ በሁለት ሳምንት ውስጥ ሦስት የዓለም ክብረወሰኖችን በማሻሻል የስፖርት ቤተሰቡን አስደምማለች። በቤት ውስጥ አንድ ሺ አምስት መቶ፣ ሦስት ሺ ሜትርና በሁለት ማይል ውድድሮች በእያንዳንዳቸው የዓለም ክብረወሰን ያስመዘገበችው ገንዘቤ አሁን አስፈሪ አትሌት ሆናለች።
ገንዘቤ የዓለም ሻምፒዮኗን አበባ አረጋዊን በማሸነፍ ጭምር ክብረወሰን ያስመዘገበች አትሌት እንደመሆኗ መጠን ሶፖት ላይ አዲስ ነገር ካልተፈጠረ የወርቅ ሜዳሊያ የማታስመዘግብበት ምክንያት አይኖርም።
ገንዘቤ ሦስቱን ክበረወሰኖች ባስመዘገበችበት ወቅት በአንድ ሺ አምስት መቶ ብቻ ሳይሆን በሦስት ሺ ሜትርም የወርቅ ሜዳሊያ ማስመዝገብ እንደምትፈልግ መናገሯ ይታወሳል። ገንዘቤ ከሁለት ዓመት በፊት በኢስታንቡል በተካሄደ ተመሳሳይ ሻምፒዮና የአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት እንደነበረች ይታወሳል።
genzebe d

ሐጎስ ገብረህይወት

«ትንሹ ቀነኒሳ በቀለ » በሚል እየተሞካሸ የሚገኘው ሐጎስ ገብረህይወት ሶፖት ላይ ከሚነግሱ አትሌቶች መካከል አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል። በሞስኮው የዓለም ሻምፒዮና ትልቅ ጥረት አድርጎ የብር ሜዳሊያ በአምስት ሺ ሜትር ማስመዝገብ የቻለው ሐጎስ በእዚህ ዓመት በሦስት ሺ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ድንቅ ብቃት በማሳየት አሸንፏል።

ሐጎስ የዓለም ወጣቶች የሦስትና አምስት ሺ ሜትር ባለ ክበረወሰን ሲሆን በተለያዩ ውድድሮች የሚያሳየው ጥንካሬ የሶፖት የሦስት ሺ ሜትር ንጉስ እንደሚሆን ይጠበቃል። ከእዚህ ባሻገር ያለፈው ዓመት የአምስት ሺ ሜትር የዳይመንድ ሊግ አሸናፊው የኔው አላምረውና ደጀን ገብረ መስቀል በርቀቱ ከሐጎስ ጋር ይወዳደራሉ።

ሦስቱ አትሌቶች በእዚህ ወር የቤት ውስጥ ውድድር በሦስት ሺ ሜትር ተገናኝተው ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ደረጃ ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። እነዚህ አትሌቶች ልዩ ብቃት ያላቸው ብቻም ሳይሆኑ አሁን ላይ እየበሰሉ መጥተዋል። ከእዚህ ቀደም በተለያዩ ዓለምአቀፍ ውድድሮች በጥቃቅን ስህተቶች የሚገባቸውን ሜዳሊያ ያጡበት አጋጣሚ ሶፖት ላይ ይደገማል ተብሎ አይታሰብም። እንዲያውም የሦስቱ አትሌቶች ጠንካራ ፉክክር በመረዳዳት ላይ ያተኮረ ከሆነ አረንጓዴውን ጎርፍ ሶፖት ላይ የምናይበት አጋጣሚ እንደሚፈጠር ጥርጥር የለም።

የአልማዝ አያናና ህይወት አያሌው ጥምረት

በሴቶች ሦስት ሺ ሜትር በእርግጠኝነት ከአንድ በላይ ሜዳሊያ ሊመዘገብ እንደሚችል መናገር ይቻላል። የርቀቱን የዓለም ክብረወሰን ካሻሻለችው ገንዘቤ ዲባባ በተጨማሪ አልማዝ አያናና ህይወት አያሌው በርቀቱ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው።
አልማዝ አያና በቅርቡ መታየት የጀመረች ወጣትና ባለ ድንቅ ተሰጥኦ አትሌት ነች። በሞስኮው ሻምፒዮና መሠረት ደፋር በአምስት ሺ ሜትር ላስመዘገበችው የወርቅ ሜዳሊያ ወጣቷ አትሌት ምንያህል አስተዋፅኦ እንደነበራት ይታወሳል። አልማዝ ለመሠረት የወርቅ ሜዳሊያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከማበርከቷ በተጨማሪ የነሐስ ሜዳሊያ ያሸነፈች አትሌትም ነች። አልማዝ ሞስኮ ላይ ከነበራት ብቃት ተነስቶ ሶፖት ላይ ሜዳሊያ ውስጥ እንደምትገባ እርግጠኛ መሆን ይቻላል።

በመሰናክል ውድድሮች የምናውቃት ህይወት አያሌው በዘንድሮው የውድድር ዓመት መነጋገሪያ ከነበሩ የአትሌቲክሱ ዓለም ክስተቶች አንዷ ነች። ህይወት በግል አገር አቋራጭ ውድድሮች አምስት ጊዜ በተከታታይ በማሸነፍ አስገራሚ ብቃት ያሳየች አትሌት ነች። በእዚህ ርቀት ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ትጠብቃለች። ከአትሌቶቹ ጥንካሬ አንፃር የትኛዋ አንደኛ እንደምትሆን መገመት ቢከብድም የሦስቱ አትሌቶች ውህደትና የቡድን ስራ ለሜዳሊያ ያበቃቸዋል ተብሎ ይታሰባል።

መኮንን ገብረመድህን

በኢስታንቡሉ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት የነበረው መኮንን ገብረመድህን ወደ ሶፖት ይጓዛል። መኮንን በርቀቱ ካለፈው የተሻለ ሜዳሊያ ይዞ እንደሚመለስ ተስፋ ተጥሎበታል። በእዚህ ርቀት ሌላው አትሌት አማን ወጤ ከመኮንን ጋር በርቀቱ ኢትዮጵያን ይወክላል። ሁለቱ አትሌቶች ጠንካራ ተፎካካሪዎች እንደሚሆኑም ይጠበቃል።

በሴቶች አንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር ከገንዘቤ ዲባባ በተጨማሪ አክሲማይት አምባዬና ጎድፋይ ፀጋዬ ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢሕአዴግ መንግስት ህጋዊ በሆነ መንገድ ለዕረፍት ከሳውዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡ ወገኖቻችን ላይ የጉዞ እገዳ ጣለ

$
0
0

ኢትዮጵያ ሃገሬ ከጂዳ

(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)

ኢትዮጵያውያኑ የእረፍት ግዜያቸውን ዱባይ እና ባህሬን ለማስላፍ ተገደዋል!

ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ለዕረፍት አሊያም ለተለያዩ አስቸኳይ የስራ ጉዳዮች በሚጓዙ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ መጡበት እንዳይመለሱ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግመ ንግስት የጉዞ እገዳ መጣሉን ምንጮች አስታወቁ። የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት እየወስደ ያለው እርምጃ አያሌ ወገኖቻች በሰው ሃገር ያፈሩትን ቀዋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቻቸውን ያሳጣ ዜጎች ህጋዊ ሆነው ለመኖር የሚያስችሉ መብቶቻውን የነፈገ ከመሆኑም በላይ አብዛኛውን ተጓዥ ለምዝበራ እና ለተጨማሪ ወጪ የዳረገ አሰራር መሆኑንን የሚገልጹ እነዚህ ምንጮች በባዕዳን ሃገር ህጋዊ በሆነ መንገድ የሚኖረውን ወገናችንን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ እርምጃ መሆኑ አክለው ገልጸዋል።

አዲስ አበባ ኤርፖርት ላይ በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ደህንነት ሃይሎች እየተፈጸመ ያለው የጉዞ እገዳ ህጋዊ የሆነ መስረት የሌለው መሆኑን የሚናገሩ የእገዳው ሰላባዎች አንዳንድ ተጓዦች የቪዛ ግዜያቸው መቃጠሉን ተከትሎ ህገወጥ፡ በሆነ መንገድ ባህር አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመግባት መገደዳቸውን ተናግረዋል። መንግስት አዲስ አበባ ኤርፖርት ላይ እyeተፈጸመብን ያለው ወከባ ሳውዲያኑ ከሚፈጽሙብን ግፍ እና በደል የከፋ መሆኑንን የገለጹ አንድ ተበዳይ ለይለፍ 5 ሺህ ብር እጅ መንሻ መክፈላቸውን ጠቅሰው ወደ ሳውዲ ዓረቢያ ህጋዊ በሆነ መንገድ መግባት የሚያስችለን ህጋዊ ቪዛ እያለን ከሃገር ሃገር የመጓጓዝ ህገ መንግስታዊ መብታችን በህገወጦች ተጭፍልቋል ብለዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ለዕረፍት ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት እቅድ ይዘው የነበሩ ወገኖቻች በጉዞ እግደዳው ምክንያት የእረፍት ግዚያቸውን ጓረቤት ሃገራት ለማሳለፍ መገደዳቸውን በማውሳት ኤርትራውያንን ጨምሮ የሌላ ሃገር ዜግነት ያላቸው ተጓዦች ያለምንም ስጋት በነጻነት ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡም ሆነ ሲወጡ ኤርፖርት ላይ በደህንነት ሃይላቱ የሳውዲ የመኖሪያ ፈቃድ (ኢቃማ) እንደማይጠየቁ ጠቅሰው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግንስት እገዳውን የጣለው በኢትዮጵያን ላይ ብቻ መሆኑንን አረጋግጠዋል ።

መንግስት የሳውዲን መኖሪያ ፈቃዱ (ኢቃማ) ያልያዘ ኢትዮጵያዊያን ላይ የጉዞ እገዳ መጣሉ በጣም አሳፋሪ እና እርምጃው ጥናት ያልተደረገበት መሆኑንን የሚናገሩ ምንጮች የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.መንግስት በሳውዲ አረቢያ ስለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አኗኗር በቂ ግንዛቤ እና መረጃ የሌለው መሆኑንን ያሳያል ብለዋል ። በሳውዲ አረቢያ ህግ አንድ የውጭ ሃገር ዜጋ የስራ ግዜውን ጨርሷ አሊያም ለእረፈት ወደ ሃገሩ ሲመለስ የመኖሪያ ፈቃዱን (ኢቃማውን) ለአሰሪው (ለከፊሉ) የማስረከብ ግዴታ እንዳለበት የሳውዲ አረቢያ ህግ ይደነግጋል ።

የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ቅሬታቸው ገለፁ (ከአብርሃ ደስታ)

$
0
0

ባሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል የዉኃና አፈር ጥበቃ (Water and Soil Conservation, ማይን ሓመድን ዕቀባ) ተግባራት የሚከናወኑበት ግዜ ነው። ህዝብ ስራው ትቶ ተገዶ በፕሮግራሙ ይሳተፋል። ለፖለቲካ ሲባል ህዝብ በፍላጎቱ ተሳተፈ ተብሎ ሪፖርት ይቀርባል። እውነታው ግን ሌላ ነው። በየዓመቱ ህዝብ ሳያምንበት ተገዶ ይሰራል። በግዜው ያልሰራ እስከ ሦስት መቶ (300) ብር ተቀጥቶ ይሰራል። በዚሁ ምክንያት ብዙ ሌሎች የግል ሥራዎች ይቆማሉ። ዜጎች ብዙ ኪሳራ ይደርስባቸዋል።
አብርሃ ደስታ
የዉኃና አፈር ጥበቃ ሥራ የጉልበት ስራ ነው። መስራት የሚችል ይሰራል፣ ወይ እንዲሰራ ይገደዳል። በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ጣብያ ሩባ ፈለግ ግን ለየት ያለ ጉዳይ ተከስቷል። የዓፅቢ ወንበርታ ህዝብ በህወሓት የትጥቅ ትግል ወቅት ንቁ ተሳታፊ የመኖሩ ያህል ባከባቢው ብዙ አካል ጉዳተኞች (የቀድሞ ታጋዮች) አሉ። በጉልበት ስራ መሰማራት አይችሉም። ምክንያቱም አካላቸው ጎድሏል። እናም በጡረታ ገንዘብ በገጠር ህይወት ነው የሚኖሩ። የአካል ጉዳተኞች መሆናቸው ታውቆ ላለፉት ሃያ ሦስት (23) ዓመታት በዉሃና አፈር ጥበቃ ሥራ ተሳትፈው አያውቁም። ምክንያቱም አካላዊ ቁመናቸው አይፈቅድላቸውም፤ ግማሾቹ ዓይናቸው የጠፋ ግማሾቹ እግራቸው የተቆረጠ ወዘተ ናቸው።

አሁን ግን ለመጀመርያ ግዜ በተለየ ሁኔታ አካላቸው የጎደሉ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች በዉኃና አፈር ጥበቃ ፕሮግራሙ እንዲሳተፉ በመንግስት አካላት እየተገደዱ ይገኛሉ። ለምን አሁን እነሱን ማስገደድ ተጀመረ? የአፅቢ ወንበርታ ህዝብ በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት በመንግስት አካላት ላይ ተቃውሞ አስነስቶ ነበረ። ህወሓቶች የቀድሞ ታጋዮቹ ዒላማ አድርገው በዉኃና አፈር ጥበቃ እንዲሳተፉ ያስገደዱበት ምክንያትም ህዝብ ፀረመንግስት ሲነሳ የቀድሞ ታጋዮቹ ከመንግስት ጎን ከመሰለፍ ይልቅ የህዝቡን ጥያቄ በመደገፋቸው ነው። ታጋዮቹ ዓፈና በዝቷል፤ ለዚህ አይደለም መስዋእት የከፈልነው፣ ፍትሕ ጠፍቷል ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች በማንሳታቸው ነው።

አሁን የድሮ ታጋዮቹ በግዝያቸው በፕሮግራሙ ባለመሳተፋቸው የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸው ለብቻቸው እንዲሳተፉ ይደረጋል። የገንዘብ ቅጣቱ እስከ ሦስት መቶ ብር ይደርሳል። ሦስት መቶ ብር ደግሞ መክፈል አይችሉም፤ ግድቡም መገደብ አይችሉም። ምክንያቱም ታጋዮቹ የሚተዳደሩት በጥሮታ ገንዘብ ነው። የጥሮታ ገንዘቡ ደግሞ ከሦስት መቶ ብር በላይ አይደለም። ታድያ ሦስት መቶ ብር (የጥሮታ) ለመንግስት ከፍለው በምን ሊተዳደሩ? ምን በልተው ሊገድቡ? በግድቡ ለመሳተፍም ይከብዳቸዋል። ምክንያቱም ግድብ የጉልበት ስራ ስለሆነ። አካላቸው አይፈቅድላቸውም፤ ምክንያቱም አካል ጉዳተኞች ናቸው።

በዚሁ ምክንያት በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ሩባፈለግ ጣብያ ከባድ ዉጥረት ነግሷል። በጣብያው (ንኡስ ወረዳ) እስካሁን ድረስ 963 ዜጎች በፕሮግራሙ ባለመሳተፋቸው ምክንያት ክስ ተመስርቶባቸዋል። ክስ ከተመሰረተባቸው ዜጎች ከ100-150 የሚደርሱ ሰዎች ተቀጥተዋል። ሌሎችም ቅጣታቸው እየተጠባበቁ ነው። የአከባቢው ህዝብ የካቲት 13, 2006 ዓም ይህ የመንግስት ካድሬዎች ተግባር በመቃወም “ሰሚ የለም ወይ?!” በማለት በጭኾት ተቃውሞውን አሰምቶ ነበረ።

የቀድሞ ታጋዮቹ ግን መንግስትን ክፉኛ እየወቀሱ ነው። አካላቸው በመጉደሉ ምክንያት ምንም ዓይነት የጉልበት ስራ መስራት የማይችሉ የመንግስት ተግባር ስለተቃወሙ ብቻ አሁን በፕሮግራሙ እንዲሳተፉ እየተገደዱ ካሉ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች መካከል ስማቸው እንዲጠቀስ ፍቃደኛ ከሆኑ (1) ሃምሳአለቃ ሃይለማርያም ገብረእግዚኣብሄር፣ (2) ሃምሳአለቃ አታኽልቲ ገብረኪሮስና (3) አስራአለቃ ወልዴብርሃ ገብረመድህን ይገኙባቸዋል። እነዚህ ሰዎች ደርግ ከወደቀ ከ1983 ዓም ጀምሮ በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት በምንም ዓይነት የመንግስት የጉልበት ስራ ተሳትፈው አያውቁም። አሁን መቃወም በመጀመራቸው ግን እየተገደዱ ይገኛሉ። አሁንም ቢሆን በጉልበት ሊገድቡ እንደማይችሉ የታወቀ ነው። የመንግስት ጥረት ግን ታጋዮቹ መንግስትን መቃወም እንደማያዋጣቸው ተገንዝበው ተቃውሞአቸውን እንዲያቆሙ ለማስገደድ ብቻ ነው። መንግስትን ከደገፉ ግን ነፃ ይሆናሉ። አይገደዱም። እንዲህ ነው የህወሓት ተቃውሞን የማፈን ስትራተጂ።

ቀደም ሲል የህወሓት ካድሬነታቸው በማቆማቸው ምክንያት መሳርያቸውን (ጠመንጃቸውን) በመንግስት አካላት ተነጥቀዋል። በአካላዊ ጉዳት ምክንያት ከህወሓት ዉትድርና ቢወጡም ጠመንጃቸው ግን ይዘውት ነበር የሚኖሩ። ጠመንጃቸው ይፈልጉታል። ምክንያቱም (አንድ) ራሳቸው የሚከላከሉበት ነው። ለብዙ ዓምታት ከነሱ ጋር የኖረ ስለሆነ ማንነታቸው አድርገውታል። እናም ጠመንጃቸውን ሲነጠቁ insecurity ይሰማቸዋል። ትልቅ የሞራል ውድቀት ይሰማቸዋል። የሞራል ኪሳራ ይደርስባቸዋል። ህወሓትም ይህን ያውቃል። እናም ነጠቃቸው። (ሁለት) ጠመንጃቸው በትንንሽ ከተሞች የሚገኙ ሃብታም የህወሓት ካድሬዎች የቤት ዘበኞች በመሆን ስራ የሚያገኙበት ነው። ጠመንጃ ከሌላቸው በዘበኝነት የመቀጠር ዕድል አያገኙም። ስለዚህ ስራ እንዳያገኙ ስለተፈለገ ነው። ስራ ካላገኙ በመንግስት ጥገኛ ይሆናሉ። ጥገኛ ከሆኑ ደግሞ መንግስትን ይደግፋሉ እንጂ አይቃወሙም። መንግስትን ካልተቃወሙ ደግሞ ህወሓት የፈለገውን ዓፈና የማድረስ መብት አገኘ ማለት ነው። ስለዚህ የዚህ ሁሉ ዓላማ ተቃውሞውን በማዳከም ህዝብን መጨቆን የሚቻልበት መንገድ ማመቻቸት ነው።

በብዙ የትግራይ አከባቢዎች የዉኃና አፈር ጥበቃ ፕሮግራም እየተሰራበት ያለ ሲሆን ባከባቢው ተገኝቶ በፕሮግራሙ ያልተሳተፈ ገበሬ መሬቱ እየተነጠቀ ይገኛል (እንደ ቅጣት መሆኑ ነው)። ነገሩ እንዲህ ነው። የህወሓት ካድሬዎች ማዳበርያ ለመሸጥ ሲባል ገበሬውን በአስገዳጅ እንዲገዛ ያደርጋሉ። ማዳበርያ ካልገዛ ይታሰራል፣ የመንግስት አገልግሎት አያገኝም፣ መሬቱም ይነጠቃል። ገብሬውም እነዚህ ሁሉ ቅጣቶች መሸከም ስለማይችል የማዳበርያ ዕዳ ይገባል። ማዳበርያውን ለመግዛት ገንዘብ ከተለያየ ተቋማት ይበደራል። ብድሩ ለመመለስ በከተሞች አከባቢ ወይ ሌላ ራቅ ያለ ቦታ በመሄድ ተጨማሪ ስራ ይፈልጋል። ዕዳውን ለመክፈል ስራ ፍለጋ ከቀዩ ይርቃል። ካድሬዎች ደግሞ “ባከባቢው እያለማ አይደለም” በሚል ምክንያት መሬቱ ተወስዶ ለሌላ ካድሬ ይሰጣል። ገበሬው ለዘላለሙ ከቀዩ ይፈናቀላል። ምክንያቱም መሬት የመንግስት ነው። መሬት የኔ ነው ብሎ ፍርድቤት ሂዶ መከራከር አይችልም። ሁሉም ነገር በሕግ ሳይሆን በመመርያ ነው የሚሰራው። እናም ህዝብ ችግር ላይ ወድቋል።

የታጋዮቹ ጉዳይ ግን አሳሳቢ ነው። ታጋዮቹ አካላቸው ጎድሏል። እኛን ከጨቋኞች ነፃ ለማስወጣት ሲሉ መስዋእት ከፈሉ። ለኛ ሲሉ አካላቸው ጎደለ። አሁን መስራት አይችሉም። መቃወምም እንዳይችሉ እየተደረጉ ነው። እነሱ የቤት ስራቸው ጨርሰዋል። ለኛ ሲሉ አካላቸው የጎደሉ ወገኖች አሁን እኛ ልንተባበራቸው ይገባል። እኛ ልንታገልላቸው ይገባል። እኛ ነፃ ልናወጣቸው ይገባል። ምክንያቱም እነሱ ዓቅሙ የላቸውም፤ እንደ ድሮ ሩጠው ጫካ መግባት አይችሉም። ከዚሁ ዓፋኝ ስርዓት እንገላግላቸው።

It is so!!!

በኢሕ አዴግ ውስጥ አለመተማመኑ በዝቷል፤ አንድነት በመዋቅሬ ውስጥ ገብቷል በሚል ግምገማ ሊጀምር ነው

$
0
0

Bahr dar 7
ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንደዘገበው፡

ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲ ኃይሎች በአደረጃጀቴ ሰርገው ገብተተዋል በሚል ግምገማ ለጀምር መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮች በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች የሚገኙ የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮችን በመሰብሰብ “አንድነት ፓርቲ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀታችን ውስጥ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች በጊዜ በግምገማ ካልተራገፉ ቀጣዩ ምርጫ ከቁጥጥር ውጪ እንደማይሆን ማንም እርግጠኛ መሆን አይችልም፡፡” ማለታቸውን በስብሰባው ላይ የተሳተፉ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ተናግረዋል፡፡

eprdf UDJ ምንጮቹ ጨምረው እንደተናገሩት ኢህአዴግ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀቱን የሚያስተባብሩ ከፍተኛ ካድሬዎችን አንድ-ለ-ሰላሳ ማደራጀት መጀመሩን ተከትሎ አንድነት ፓርቲ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች አሉ በመባሉ ካድሬዎች እርስ በእርስ መሰላለል እና አለመተማመን ጀምረዋል፡፡ ይህ በካድሬዎቻቸው መካከል የተጠፈጠረው ትርምስ ያሰጋቸው የኢህአዴግ የአዲስ አበባ ጽ/ቤት አመራሮች ለክፍለ ከተማ አመራሮቻቸው አንድነት ሊይዝብን የሚችለው 30 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ነው የተቀረውን በኮንዶሚኒየም ፣ በአነስተኛ ጥቃቅንና በየአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀት ይዘነዋል ብለዋቸዋል፡፡ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ መረጃ የሰጡት የስብሰባው ተሳታፊዎች 750ሺ የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢ፣ 30ሺ የኮንዶሚኒየም እጣ ተጠባባቂዎች ኢህአዴግን ነው የሚመርጡት በሚል ከመድረክ የቀረበው መደምደሚያ እንዳላሳመናቸውም ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን በሚመለከት ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የደረሰው ዶክሜንት እንደሚያስረዳው ፓርቲው የአዲስ አበባ አደረጃጀቱን ኢህአዴግ በዘረጋው ልክ 138 ያደረሰ ሲሆን በአሁኑ ጊዜም የወረዳ ደረጃና የሴል አደረጃጀቶቹን በኢህአዴግ የአደረጃጀት ቁጥር ልክ የማድረግ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ያመለክታል፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ የመንግስት ታጣቂው የባለ3 ልጆች ባለትዳሮችን በጥይት ደብድቦ ገደለ

$
0
0

የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ (ፎቶ ከፋይል)

የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ (ፎቶ ከፋይል)


ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው

በንፋስ ስልክ ላፍቶ የመንግስት ታጣቂው የ3 ልጆችን ባልና ሚስትን በጥይት ደብድቦ መግደሉ ተሰማ። ድርጊቱ የተፈፀመው ትላንት ከቀኑ 9.30 አካባቢ ነው ተብሏል።

አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ውስጥ ልዩ ስሙ መካኒሳ አቦ ማዞሪያ በሚባል አካባቢ አንድ የመንግስት ታጣቂ የሶስት ልጆች ወላጆች የሆኑትን ባልና ሚስት በአውቶማቲክ መቺንገን በጥይት ደብድቦ ገድሏቸዋል።

የአካባቢው ሰዎች እና የሟች ዘመዶች በጋራ በመሆን የቀብሩን ስነ- ሥርዓት ለማስፈጸምና የመንግስት ታጣቂው የወሰደው እርምጃ ለማውገዝ እና በየጊዘው በአካባቢው የሚፈጸመውን የመንግስት ታጣቂዎች እርምጃ እና በህብረተሰቡ ላይ የደረሰውን ግፍ በጋራ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ለማጋለጥ በህብረት ድምጻቸውን ለማሰማት ሲሞክሩ በፈደራል ፖሊስ የተበተኑ ሲሆን በአካባቢው ላይ የአዲስ አበባ የፖሊስ ሃይሎች ተሰማርተዋል።

የፈደራል ፖሊስ አመራሮች የአከባቢውን ህዝብ የፖለቲካ አጀንዳ ያለው ሲሉት የፈረጁት ሲሆን ቀብሩ ሳይፈጸም ህዝቡን በማስፈራራት እና በዛቻ ያባረሩት ሲሆን የሟች ዘመዶች የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ጉዳችንን ሳይሰማና ሳያውቅልን አንቀብርም ብለው አስከረኖቹ ወደ መኖሪያ ቤት ተመስልሷል።

ለዘ-ሐበሻ ዘግየት ብሎ በደረሰን መረጃ ቀብሩ በነገው እለት ይፈጸማል።


አስተያየት፣ በሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ “እኛና አብዮቱ” መጽሀፍ ላይ

$
0
0

ከፈቃደ ሸዋቀና

የሻምበል ፍቅረ ስላሴን ባለ 440 ገጽ መጽሐፍ ላነብ ስነሳ ጸሐፊው በሃያ ዓመታት የእስር ቤት ቆይታቸው በስልጣንና የሃላፊነት ዘመናቸው የነበሩትን ብዙ ክንዋኔዎች ፣ ውሳኔዎችና ተዋናዮችን አስመልክቶ የነበራቸውን እይታ እንደገና ለማጤንና ለማሰላሰል እድል አግኝተው የጻፉት ሊሆን ስለሚችል ሚዛናዊ የሆነ ዕውቀት፤ እንዲሁም የመንግስታቸውን የውስጥ ለውስጥ ሥራዎች ከሩቅ እናይ የነበርን ተራ ዜጎች ሳናውቃቸው የቀሩ ነግሮችን የምናገኝበት ይሆናል የሚል ጉጉት ነበረኝ። በተጨማሪም በመግቢያው ሊተርኩልን ቃል የገቡትን የደርግን የግዛት ዘመን ዋና ዋና ቁም ነገሮችና ክንዋኔዎች እንደወረደ አቅርበውልን አንባቢዎች የሁሉንም ነገር ፋይዳ የራሳችንን ሚዛን ተጠቅመን እንድንረዳው ይተውልናል ብዬ አስቤም ነበር። ይህ ከንቱ ምኞት መሆኑን ወደ ገጾቹ ውስጥ ርቄ ሳልሄድ ነው ያረጋገጥኩት። በሁሉም የደርግ የግዛት ዘመን ክንዋኔዎችና የፖለቲካ ተዋናዮች ላይ የራሳቸውን ዳኝነቶች አመለካክቶችና ግለ-አይታዎች (bias) ጨምረውበታል።

fikresilase wegderese new book cover
ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ከእስር በወጡ ባጭር ጊዜ ውስጥ ጊዜያቸውን ወስደው ይህን መጽሀፍ በመጻፋቸው ሊመሰገኑ ይገባል። ወደፊትም ሌሎች መጽሐፎች እንደሚጽፉ ቃል ገብተዋል። የሚቀጥሉት ላይ በበለጠ የሃላፊነት ስሜት እንዲጽፉ ለማሰቢያ የሚረዳ ነገር ካስተያየቴ ሊያገኙ ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ። እውነት በመናገርና በሀቅ በመመስከር ከሚገኘው ብዙ ጥቅም ውስጥ አንዱ ለተናጋሪው የህሊና ፈውስ የሚያስገኝ መሆኑ ነው። ለሻምበል ፍቅረስላሴና ለቤተሰባቸው መልካሙን ነገር ሁሉ እመኝላቸዋለሁ። መጽሀፋቸው ላይ በማቀርበው አስተያየት ላይ ግን ርህራሄ የለኝም። የምንሟገትበት ጉዳይና ታሪክ ከያንዳንዳችን ስብዕና በላይ ስለሆነ።

የዚህን ጽሁፍ ርዕስ ግምገማ (Review) ከማለት ይልቅ አስተያየት(Observation) ያልኩት እውቄ ነው። መጽሀፉ እንደመጽሀፍ የሚገመገም ባህርይ የለውም። ብዙው የደራሲው ነጻ እይታ ዘገባ ነው። ትልልቅ ድምዳሜዎች ላይ የደረሱባቸውን ነጥቦችና በፖለቲካ ባላንጦቻቸው ላይ የሚያቀርቡትን ክስ ተዓማኒ የሚያደርግ ወይም የሚያረጋግጥ ወይም ደርግን ከክስ የሚያነፁበት ማስረጃ የሚሆን የግረጌ ማስታወሻም (Footnote) የዋቢ ዝርዘርም (Reference list) የለበትም። መጽሀፉ ባቀራረቡ ከሞላ ጎደል የደርግ በተለይም የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም ገድል ነው። ለበርካታ ደርግ ላይ ለሚቀርቡ ወንጀሎችና ጥፋቶች ሁሉ የተገቢነት ማረጋግጫ (justification) ለመስጠት ደራሲው ሙከራ ሲያደርጉ ይታያል። ስለዚህ ግምገማ የሚገባው መጽሀፍ ነው ማለት ለመጽሀፉ የማይገባውን ነገር ማድረግ መስሎ ታይኝ። ማድረግ የሞከርኩት ፈጣን ወፍ በረር ቅኝት ብቻ ነው። ምሳሌ የሚሆኑ ነገሮችን አሳይቼ ብዙውን ነገር ትቼዋለሁ።

በደርግ የግዛት ዘመን ከደረሰው የጥፋት ከምር ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ሀይሎችና ተራ ዜጎች የሚወስዱት የተለያየ መጠን ያለው ድርሻ እንዳለ ብዙ የሚያከራክር አይመስለኝም። ከዚህ የጥፋት ከምር ላይ እያንዳንዱ የደርግ አባልና በተለይ በከፍተኛ ሀላፊነት ላይ የነበሩ ደራሲውን የመሰሉ መሪዎች የሚያነሱት ትልቅ ድርሻ አለ። በሚያሳዝን ሁኔታ ሻምበል ፍቅረስላሴ ለይሉኝታ ያህል ብለው እንኳን በግልም ይሁን በጋራ ምንም ሀላፊነት አይወስዱም። የመንግስታቸውን ጥፋት ሁሉ በሌላ ያመካኛሉ። ኢህአፓን አጥብቆ በመወንጀል የደርግን ለመሸፈን ይቻላል በሚል ሀሳብ ይመስላል ኢህአፓ ገደላቸው የሚሏቸውን 271 ሰዎች ዝርዝር ከምጽሀፉ 21 ገጾች ሰጥተው አስፍረዋል። (ከገጽ 275 – 296). ዝርዝሩ ደርግ ራሱ እየገደለ ኢህአፓ ገደላቸው የሚባሉ ሰዎች ስም ሁሉ ይዟል። ለምሳሌ ዶክተር መኮንን ጆቴን የገደላቸው ራሱ ደርግ መሆኑን እንደሚያምኑ የመኢሶን አባላት የነበሩ ጓደኞቼ ነግረውኛል። በአጸፋው ኢህአፓ ብለው የፈጁትን ሰው ዝርዝር ይቅርና ጠቅላላ ቁጥር እንኩዋን ሊነግሩን ፈቃደኛ አይደሉም። ተራ ተመልካች ካለችግር የተረዳውንና ብሎ ብሎ የጨረሰውን የኮሎኔል መንግስቱንና የደርግ መንግስት ጥፋቶችና ሀገርን አደጋ ላይ የጣለ ግትርና እምባገነናዊ አመራር በጨረፍታ እንኩዋን ለመተቸት አለመሞከራቸው ወይ ቀጥተኛ ክህደት ፣ ወይም የውሻ አይነት ቅድመ-ሁኔታ አልባ ታማኝነት ፣ ከዚህ ከዘለለ ደግሞ “በምኒልክ ጊዜ የደነቆረ ምኒልክ ይሙት እንዳለ ይኖራል” የሚባለው አይነት ነገር አስመስሎባቸዋል።

በመከረኛይቱ ሀገራችን ላይ ብዙ መታከም የሚገባው ትልልቅ ቁስል አለ። የሚሻለው ወደማከሙ መዞር እንጂ ቁስሉ ላይ ጨው መነስነስ አይደለም። ሻምበል በመጽሀፋቸው ብዙ ቦታ ይህንን ጨው ቁስላችን ላይ ካለሀሳብ ነስንሰውታል። በህይወት የሌሉና ሊከራከሯቸው የማይችሉ ሰዎችን ሳይቀር በስልጣን ዘመናቸው ጊዜ እንደሚደረገው አሁንም በመደዳው ይወነጅሏቸዋል። ይህ አጻጻፍ በውድቀታቸው ላገኛቸው ለራሳቸው ቁስል ፈውስ ይሆነኛል ብለው አስበው ከሆነም ተሳስተዋል። ንጹህ ራስን እንደገና ማግኘት (redemption) የሚቻለው ለዕውነት ክብር በመስጠት ብቻ መሆኑን የተረዱት አልመሰለኝም። ዛሬ የሚገዙንን ገዥዎች እካሄድና አገዛዝ ስለጠላን የደርግን ዘመን ግፍ እንዳለ የረሳነው መስሏቸው ከሆነም በጀጉ ተሳስተዋል። የወጋ እንጂ የተወጋ አይረሳም። ደጉ፣ ቸሩና አስተዋዩ የአትዮጵያ ህዝብ በወደቀ እንጨት ምሳር ማብዛት አይገባም ብሎ ስለተወውና እነሻምበል ፍቅረስላሴ ትተውለት በሄዱት ምስቅልቀል ላይ በመጠመዱ እንጂ የደረሰበትን ግፍ ረስቷል ማለት አይደለም። ወዳጅ ዘመድ በግፍ የሞተበት ፣ ጧሪ ልጃቸውን ያጡ እናት አባቶች ፣ ቤቱ የፈረሰበት ቤተሰብ ፣ ከነጠባሳው የሚኖር ዜጋ፣ ከገበያ ላይ ሳይቀር ካለፈቃዱ ታፍሶ ጦር ሜዳ የተማገደው ማገዶ ትራፊ አሁንም አለ እኮ!

በመጽሀፉ ላይ የምሰጠው አስተያየት ርሳቸው የሚወነጅሏቸውን ድርጀቶች ወይም ሰለባዎች ወይም ግለሰቦች ወክዬ ለመሟገት አይደለም። ከሻምበል ፍቅረስላሴ መጽሀፍ ጋር ያጣላኝ አንዳንዱ ነገር በቅርብ በምናውቀው ታሪክ ላይ ያሳዩት ይሉኝታ የሌለው አጻጻፋቸው ነው። በጊዜው ያልተወለደውና ለዕውቀት ያልደረሰው ትውልድ የተሳሳት ግንዛቤ እንዲወስድ ሲጋበዝ ዝም ብሎ ማየትም ተገቢ አልመሰለኝም። ስለዚህ በዚህ መጽሀፍ ላይ የምሰጠው አስተያየት ጨከን ያለ መስሎ ታይቷችሁ ከሆነ ከዚህ አቅጣጫ እዩልኝ። ሌላ የግል ወይም የቡድን ሂሳብ የማወራርደው የለኝም። የኛ ሀገር ሰው እንደሚለው ከጅብ የሚያጣላ ጓሮዬ ያሰርኩት አህያ የለኝም።

እኔ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት ተፈንቅሎ ደርግ ስልጣን ሲወስድ 19 ሊሞላኝ ጥቂት ወራት የቀሩትኝ የአዲስ አበባ ዩኒቭርሲቲ የሁለተኛ አመት ተማሪ ነበርኩ። በደርግ ዘመን ለነበረው ሁሉ እንግዳ አይደለሁም ማለት ነው። እንደብዙ ወጣቶች ኢህአፓ አካባቢ ልሳተፍ እንጂ ያደረኩት ተሳትፎ ብዙ አልነበረም። ካስተዳደጌ ይሁን ከሌላ በልጅነቴ ጀምሮ አንዳንድ ገዜ አስተማሪና ጉዋደኛ እስቲጠላብኝ ድረስ ጨቅጫቃ ተማሪ ነበርኩ። አንድ ነገር እስኪገባኝ ድረስ ሰው አስቸግር ነበር። በ1968 ዓም መጀመሪያ ኣካባቢ አንድ የኢህአፓ የጥናት ክበብ ላይ ስሳተፍ ደርግ የወዛደሩ ፣ ኢህአፓ ደግሞ የላብ አደሩ እምባገነንነትን እናሰፍናለን በሚሉት ነገር ላይ ችግር ነበረብኝ። ለካርል ማርክስ ጭንቅላት እስከዛሬ ድረስ ትልቅ አድናቆት ቢኖረኝም የሶሻሊዝም ሳይንስነትም አይገባኝም ነበር። የጥናት ቀጠሯችን ዕለት በኢትዮጵያ ያለውን የላባደር ቁጥር ፈልጌ ጠቅላላ ከ45ሺ እንደማይበልጥ አረጋግጬ መጣሁ። አዲስ አበባና አቃቂ አካባቢ ያለው ብቻ 20 ሺ አይሞላም ነበር። 35 ሚሊዮን ህዝብ ባለበት አገር ላይ ሀምሳ ሺ ለማይሞላ ሰው ሺ ጊዜ ተበዝባዥ ሲሆን ቢውል አምባገነን እንዲሆን የምንታገልበት ምክንያት እልገባ ብሎ አስጨንቆኝ ነበር። ይህን ነገር ሳነሳ ሰብሳቢያችን የነበረው ልጅ ሳቀብኝ። ከማርክስ እየጠቀስ ሊያስርዳኝ ሲሞክር ይበልጥ አዞረብኝ። ማርክስ የሚያወራው አይነት ላባደርማ ጭራሹኑ እዚህ አገር የለም ብዬ ድርቅ እልኩ። የኛ አገር ላባደር ማርክስ እንደሚናገርለት እንዳውሮፓው ሳይሆን እንዴውም የተፈናቀለ (depeasantised) ገበሬ ነው ብዬ ተከራከርኩ። ሰብሳቢያችን ስደብ አዘል ሽሙጥ አሽሟጠጠኝና ተጣላን። ከዚያ ሴል ውስጥም ወጣሁ። እዚያ ሴል ውስጥ አብረውኝ የነበሩ ልጆች የነበራቸውን የህዝብና ሀገር ፍቅር በፍጹም አልጠረጥርም። እኔ የህዝብና ያገር ፍቅራቸውን እንደሆን እንጂ በጀግንነትና በመስዋዕትነት ስሜት አልወዳደራቸውም። እነሱ ለህዝብ ሲሉ ለመግደልም ሆነ ለመሞት ዝግጁ ነበሩ። እኔ የሚያገዳድል ነገር ባለበት አካባቢ መገኘት አልወድም። ሰው የሚገድል ሰው ምን አይነት ህሊና እንዳለው እስከዛሬ አይገባኝም። ሁሉም ማለት ይቻላል በኋላ አልቀው ተገደሉ። ብዙ ሊሞቱ የማይገባቸውና በህይወት ቢኖሩ ትላልቅ ሳይንቲስት የሚወጣቸው የቅርብ ጉዋደኞቼ በደርግ ተገለዋል። እኔ ቀጭኑን የቀይ ሽብር ዘመን አስተማሪ ሆኜ ገጠር ውስጥ አለፍኩት። መጨረሻ ላይ የቀይ ሽብሩ ዶፍ ሊያባራ አካባቢ ያበዱ ካድሬዎችና ባለስልጣኖች ርዝራዥ ኢህአፓ ብለው እኔንና ጥቂት ጉዋደኞቼን ሊበሉን የምኖርበት ወረዳ አብዮት ኮሚቴ ውስጥ መዶለታቸውን ሰማሁ። አምልጬ ባንድ ትልቅም ባይሆን ጠቃሚ ስልጣን በነበረው አጎቴ ርዳታ ተረፍኩ። አጎቴ ለኔና ለታናሽ ወንድሜ ብቻ ሳይሆን ለጓደኞቼም መዳን ረዳ። ከሁሉ በላይ አብዱል ቃድር የሚባል የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የደሴ ልጅ፣ አሁንም በህይወት አዲስ አበባ የሚኖር የጓደኛዬ ጓደኛ ባጎቴ ርዳታ ሞት ከሚጠብቅበት እስር ቤት ለማውጣት ስለቻልኩ እስከዛሬ ደስ ይለኛል። ከዚያ በኋላ ያለውን የደርግ ዘመን አጎንብሼና ትምህርት ላይ አተኩሬ የሆዴን በሆዴ ይዤ ባድርባይነት ነው ያሳለፍኩት። ስለዚህ የብዙ ሰው ያህል ቂም የለኝም። እነሻምበል ፍቅረስላሴ ላይ አሁን ከደረሰባቸው በላይ እንዲደርስባቸው አልፈልግም። ጉዳያቸውን ያየው ዳኛ እኔ ብሆን ኖሮ የሀያ ዓመት ቀርቶ የሁለት ወር እስራትም እልፈርድባቸውም ነበር። ሰው ሲዋረድና ሲሰቃይ ማየት አልወድም። የሰሩትን ስራ አልቅሼ ነግሬና ወቅሼ ንስሀ እንዲገቡ መክሬ ነበር የምለቃቸው። ግፈኛን በደግነት እንጂ በግፍ በመቅጣት ርካታ የሚገኝ አይመስለኝም።

ሻምበል በመጽሀፋቸው ሊሰጡን የሚሞክሩትን የማህበራዊ ሳይንስ ትንታኔ ቢተውት ይሻል ነበር። ኮሎኔል መንግስቱም መጽሀፋቸው መጀመሪያ ላይ እንዲህ አይነት የምሁር ተግባር ውስጥ ሲንጠራሩ ተመልክቼ ነው ሳላነብላቸው የወረወርኩት። ሻምበል ፍቅረስላሴ ሊቃውንት ተንታኞችን ሊጠይቅ የሚችለውን ማህበራዊ ሳይንስ ቀርቶ በተመክሮ እንኳን ሊታወቁ የሚችሉ ነገሮችን ስተዋቸዋል። ለምሳሌ በጊዜው ተነስቶ ስለነበረው ስለጊዚያዊ ህዝባዊ መንግስት ጥያቄ አንስተው በተቹበት ክፍል ውስጥ ጊዜያዊ ህዝባዊ መንግስት ሊመሰርቱ ይገባል ተብለው የተጠቀሱትን የህብረተሰብ ክፍሎች በየተራ እያነሱ እንዴት እንደማይችሉ ያስረዳሉ። የገበሬውን ተሳትፎ በተመለከተ፣

“ገበሬው ንቃቱ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ የመንግስትን አወቃቀርና አሰራር ማወቅ ቀርቶ የሚኖርበትን አካባቢ እንኩዋን እንዴት እንደሚተዳደር ለይቶ ለማወቅ ችሎታ የሌለው መደብ ነበር” ይሉናል። (ገጽ 226)።

ተማሪዎችን አስመልክቶ ሲናገሩ ደግሞ፥

“ተማሪዎች የስራም ሆነ የኑሮ ልምድ የላቸውም። ቤተሰብ ማስተዳደር እንኩዋን በቅጡ አያውቁም። . . . . . . . መንግስት ስልጣን ውስጥ ተካፋይ መሆን አለባቸው የሚል ሀሳብ ማቅረብ ከግዴለሽነት ወይም ግራ ከመጋባት የመነጨ ይመስላል” ይላሉ። (ገጽ226)”.

ይህን የሚጽፉት ሻምበል ፍቅረሰላሴ ከስልጣን አባሮ እስር ቤት ያጎራቸው ተማሪዎች የነበሩ ልጆች አደራጅተው ያሰማሩት የገበሬ ሰራዊት መሆኑን ፈጽሞ ረስተውታል። በታሪካችን ውስጥ ትንሽ ወደኋላ መለስ ብለው ቢያዩ ሀገሪቱን ለየዘመናቸው እንዲመች አድርገው አደራጅተው ፣ ሕግ አውጥተው ፣ ዳኝነት አይተው ፣ ገበያ አቋቁመው፣ ሲያስፈልግ የጎበዝ አለቃ መርጠው ፣ ጦርነት ተዋግተው ያቆዩልን አባቶቻችን ገበሬዎች መሆናቸውን መገንዘብ ይችሉ ነበር። የገዳን ስርዓት የሚያክል አስደናቂ የመንግስት ዘይቤ የፈጠሩት ያገራችን ከብት አርቢዎች እንደነበሩ ሻምበል የሚያውቁ አልመሰለኝም። ደርግን ከመሰረቱትና ሻምበል በመጽሀፉ እንደሚነግሩን አህያ የከበቡ የጅቦች ስብስብ በሚመስል ጉብዔ ላይ 60 ሰዎች ላይ እጅ እያወጡ ካለፍርድ ይገደሉ ብሎ ከሚወስን ወታደር የተሻለ ፍርድ ሊሰጡ የሚችሉ ብዙ ያገሬ ገበሬዎች እንዳሉ አውቃለሁ።

በደርግ የግዛት ዘመን ብዙ ሰው ከሀገር የሚሰደደው ደርግ ሀገሪቱን ለልጆችዋ የሲዖል ጎሬ ያደረጋት በመሆኑ መሆኑን ከሀያ አመት በሁዋላ እንኩዋን ማየት አለመቻላቸው ገርሞኛል። ገጽ 440 ላይ ሻምበል እንዲህ ይላሉ።

የኛን መንግስት ለማዳከም ታዋቂና የተማሩ ግለሰቦችን ጠላቶቻችን አስከድተዋል። የአሜሪካ መንግስት የስለላ ድርጀት (ሲ አይ ኤ) ከፍተኛ በጀት በመመደብ የመንግስት ባለስልጣናትን ፣ ይዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ፣ ታዋቂ ስፖርተኞችን በብዛት አስኮብልሏል”።

ሻምበል ስደቱን ነው ኩብለላ የሚሉት። አሜሪካ ተሰዶ መኖር ለግል ኑሮ የሚጠቅም መሆኑ ከደርግ በፊት የማይታወቅ ነገር አስመሰሉት። በደርግ ጊዜ የነበረውን አንድ ከስደት ጋር የተያያዘ ቀልድ ሻምበል አልሰሙም መሰለኝ። ቀልዱ እንዲህ ነው። አንድ ቀን ቦሌ አይሮፕላን ጣቢያ የሚጀምር ብዙ ሺ ህዝብ ተሰልፎ ኮሎኔል መንግስቱ አዩና “ይህ ሁሉ ህዝብ ምንድነው” ብለው ጠየቁ አሉ። “ጓድ መንግስቱ ከሀገር ሊወጣ የተሰለፈ ህዝብ ነው” ብሎ አንድ ባለሙዋል ይነግራቸዋል። ታዲያ ይህ ሁሉ ሰው ከወጣ እኛስ ምን እንሰራለን ብለው ከኋላ ተሰለፉ አሉ። ሰልፈኛው ቅድሚያ እየሰጠ ስላሳለፋቸው መጨረሻ ላይ ከፊት አንደኛ ሆነው ተሰለፉ አሉ። ያን ጊዜ ያ ሁሉ እልፍ ሰው ሰልፉን ትቶ የበተናል። ኮሎኔል ግራ ገብቷቸው “ምን ሆኖ ነው ሰልፈኛው የሚበተነው” ብለው ባለሙዋሉን ሲጠይቁት “አይ እርሶ መጀመሪያ ከተሳፈሩና ከሄዱማ ለምን እንሄዳለን ብለው ነው” አላቸው ይባላል። ከደርግ በፊት ውጭ ሀገር ትምህርታቸውን የጨረሱ ምሁራን ዲግሪያቸውን እስከሚረከቡበት ድረስ ላለመዘግየት በፖስታ እንዲላክላቸው ጠይቀው ወደ ሀገራቸው ይመለሱ እንደነበር የማናውቅ አስመሰሉት።

ሻምበል መጽሀፉ ውስጥ የነበረውን የኢኮኖሚ ችግር በሙሉ እንዱን እንኳን እኛ ስለተሳሳትን የተፈጠረ ነው እይሉም። በራሳቸው የፖሊሲና የማኔጅሜንት ችግር በጊዜው በነበሩት የመንግስት እርሻዎችና ሌሎች የኢኮኖሚ ተቋሞች ላይ የደረሰውን ውድቀትና ኪሳራ ሁሉ በኢህአፓ ላይ ለጥፈውታል። በጊዜው ኮሎኔል መንግስቱና ተራው የደርግ አባል ሁሉ የኤክስፐርት ቦታ ተክተው ካልሰራን ሲሉ እንደነበር እዚህ ጊዜና ቦታ የለኝም እንጂ ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ እችል ነበር። አንዲት እንኳን ምስሌ ሳይሰጡን በደፈናው ኢህአፓ “በተለያዩ የተንኮል ዘዴዎች የማምረቻ መሳሪያዎች በማበላሸት ወይም በማቃጠል የምርት እንቅስቃሴ እንዲቋረጥ አድርጓል”። ይሉናል። (ገጽ 253)

ሻምበል ከ1967 ዓም ጀምሮ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ያመጹባቸውንና የደመሰሷቸውን ሰዎች ሁሉ ጨፍልቀው መሬታቸው የተወረሰባቸው የመሬት ከበርቴዎች ይሏቸዋል። ያመጹ ባለመሬቶች መኖራቸው እውነት ነው። ታሪኩ ግን ይህ ብቻ አይደለም። ጠመንጃቸውን እንደጌጥ የሚወዱ በርካታ ድሀ ገበሬዎች መሳሪያ አስረክቡ ሲባሉ እንደውርደት ቆጥረው ለወንድ ልጅነት ክብራቸው ሲሉ የሸፈቱ ብዙ ነበሩ። እኔ በግል ጅባትና ሜጫ አውራጃ ውስጥ ጀልዱ በሚባል አካባቢ አስተማሪ በነበርኩበት ቦታ የሆነውን አውቃለሁ። አማራና ኦሮሞ ገበሬዎችና አነስተኛ ነጋዴዎች ናቸው። መሳሪያችንን ተውልን ብለው ለምነው ሲያቅታቸው የሸፈቱ ሰዎች በስም የማውቃቸው ነበሩባቸው። የተወሰነ ጊዜ ቢሆንም ተዋግተው የሞቱት ሞቱ። የመሬት ከበርቴ በሌለበት ሰሜን ሸዋም ተመሳሳይ ነገር መሆኑን አውቃለሁ።

ደርግ ገበሬዎችን መሳሪያ ሲገፍ ትልቅ ጠቃሚ የህብረተሰብ ባህሪ እየቀየረ መሆኑ አልገባውም። በየጥምቀቱና በየበአላቱ በዘፈን ላይ “ምንሽሬ ፣ ቤልጅጌ” የሚባሉ ዘፈኖችና “መራዥ ተኳሹ” የሚባሉት የጀግንነት ፉከራዎች ቆሙ። የጀግንነት መንፈስም አብሮ ተሰበረ። እሱ ዱሮ ቀረ ተባለ። የወያኔ ጦር ሰሜን ሸዋ ከደረሰ በኋላ ኮሎኔል መንግስቱ ደብረ ብርሃን ሄደው “ጀግናው የመንዝ የመራቤቴና የቡልጋ ህዝብ ሲዘምት እንጂ ሲዘመትበት አይተን አናውቅምና ተነስ” የሚል ሰበካ ካካሄዱ በሁዋላ አንድ ዘመዴ ገበሬ ያለኝን አልረሳውም። “ይቺ ሰውዬ” ፣ አለ መንገስቱን። ፊቱ ላይ የንቀትና የጥላቻ ገጽታ አይበት ነበር። “ያኔ መሳሪያችንን ገፍፋ ሴት አድርጋን ስታበቃ ዛሬ ባንድ አዳር ወንድ ልታደርገን ፈለገች አይደል? እንግዲህ እንደፎከረች ራሷ ትቻለው። እኛማ አንድ ጊዜ ቁጭ ብለን ሸንተናል” ነበር ያለኝ። ትንሽ ማሰብ የሚችል አንጎል ያለው ሀገር እመራለሁ ፣ አገር እወዳለሁ የሚል ሰው አንድ ሶሺዎሎጂስት ወይም ከባላገሮቹ መሀል ሽማግሌዎች ጠርቶ የሚሰራው ስራ ምን እንደሚያስከትል ይጠይቅ ነበር። እርግጠኛ ነኝ ብዙ ዓመታት ከደርግ ቀደም ብለው ሀገራችንን የመሩት አፄ ምኒልክ ቢሆኑ ኖሮ አዋቂ ሳያማክሩ እንዲህ አይነት ነገር አይሞክሩም ነበር። ሕዝቡን ቢፈሩት እንኳን እንደማትነካኝ ማልልኝ ብለው መሳሪያውን ይተውለት ነበር።

ደርግ በችሎታ ማነስና በማያውቀው ነገር ገብቶ ሳይሳካለት የቀረውን ነገር ሁሉ ሻምበል ፍቅረስላሴ በተለይ በኢህአፓ ላይ ብዙ ጊዜም ከተጠቀሙባቸው በሁዋላ በፈጁዋቸው መኢሶንን በመሳሰሉ ደርጅቶችና መሪዎቻቸው ላይ እየወስዱ የለጠፉት ነገር አስተዛዛቢ ነው። ለምሳሌ በሶማሊያ ወረራ ጊዜ ደርጉ ውስጥ የነበረውን ያመራር መዝረክረክና የሰራዊት ሽሸት ሁሉ በኢህአፓ ያመካኛሉ።እንዲህ ይላሉ፤

“የኢትዮጵያ ጦር የያዘውን ቦታ እየለቀቀ እንዲያፈገፍግ የተደረገው በሶማሊያ ጥንካሬና ግፊት ብቻ ሳይሆን በጦሩ ውስጥ የተሰገሰጉት የኢህአፓ አባላት ጦሩን በማሸበራቸውና እንዲሸሽ ቅስቀሳ በማካሄዳቸው ጭምር ነው። ……………… የኢህአፓ አባላት በጦሩ ውስጥ ሽብር ነዙ።….. ከዚህም አልፈው በግርግርና በተኩስ መሀል መሪዎችን ከጀርባቸው እየተኮሱ ገደሉ” (ገጽ 364)

በመጽሀፉ ውስጥ ብዙ ቦታ እንደሚያደርጉት ይህን ከባድ ክስ ያስቀምጡና ክሱን የሚያስረዳላቸው አንዲት መረጃ ወይም ምሳሌ አይሰጡም። ነገሩን በደርግ ዘመንም ሰምተነዋል። ይህ የተደረገበት ልዩ ምሳሌ (specific case) በጊዜ ፣ በቦታ ፣ በስም ተለይቶ ሲሰጥ ሰምተን እናውቅም። የሻምበል አይነት ስልጣን የነበረው ሰው ደግሞ ለመረጃ ቅርብ ስለሚሆን ማስረጃ ማቅረብ ሊቸገር አይገባም።

ሻምበል ፍቅረ ስላሴ በስልጣን ዘመናቸው የደረሰውን ታሪካችን የማይረሳውን ግፍ ሁሉ እንዳለ በኢሕፓና ትግሉን እናግዛለን ብለው ከውጭ ሳይቀር በረው ሀገር ገብተው ሂሳዊ ድጋፍ በመስጠት ትግሉን ለመምራት በተሳተፉ ወግኖቻችን ላይ ካለምንም ይሉኝታ ለመደፍደፍ ያደረጉት ሙከራ በጣም ያሳዝናል። ተገኘ የተባለ ጥሩ ነገር ሁሉ የደርግና የመንግስቱ ኃይለማሪያም ይሆንና የተበላሸ ነገር ሁሉ ደግሞ በነዚህ ሀይሎች ላይ ይላከካል። ሐላፊነት መውሰድ ብሎ ነገር የለም። ሌላው ቀርቶ ደርግ ከውስጥ ኢህአፓ ከውጭ አጣብቀው መከራቸውን በሚያሳዩዋቸው የመኢሶንና የሌሎች ደጋፊዎቻቸው ድርጀት መሪዎችንም ካለይሉኝታ ይከሷቸዋል። መንግስቱና ደራሲው ራሳቸውን ሳይቀር የሚመጻደቁበትን የሶሻሊዝም ሀሁ እጃቸውን ይዘው ያስቆጠሩዋቸውን ደርጅቶች መሪዎች እነ ኃይሌ ፊዳን ስልጣን ባቁዋራጭ ሊይዙ ሲሉ ደርሰው እንደገደሏቸው እያማረሩ ይነግሩናል። ካለፍርድ የተገደሉበትን ሁኔታ ሁሉ ተገቢ አስመስለው ያቀርቡታል። ከአምቦ ከተማ አለፍ ብሎ ቶኬ ከምትባል ቦታ ተደብቀው የተያዙትን የመኢሶን መሪዎች እስር ቤት እንኩዋን ሳያደርሷቸው ሜዳ ላይ እንዳረዷቸው በዚያው አካባቢ እኖር ስለነበር እየተሸማቀኩ ሰምቻለሁ። የደርግ ሎሌ ሆነው ሲያገለግሉ ጥሩ ይሆኑና በነጻነት ለመንቀሳቀስ የዜግነት መብታቸውን የተጠቀሙ ዕለት ርኩስ ይሆኑባቸዋል ለሻምበል።

ሻምበል ፍቅረስላሴ ደርግ በጥይት የፈጀውን ሠራተኛና ወጣት ሁሉ ኢህአፓ አስገደላቸው ይላሉ እንጂ እኛ ገደልናቸው አይሉም። ያየር መንገድ ሰራተኞች መንግስት ያገተባቸውን የስራተኛ ማህበር መሪ ይለቀቅልን ብለው በተነሳ ግርግር ላይ 6 ሰራተኞች በመንግስት መገደላቸውን ይነግሩንና ይህም ስለሆነ “ኢህአፓ ድል አድራጊ ሆኖ ወጣ” ብለው ያሽሟጥጣሉ። እንዴውም ግርግር ላይ “የመጀመሪያውን ተኩስ የተኮሱት የአህአፓ አባላት እንደነበሩ በተደርገ ማጣራት ተረጋግጧል” ይሉናል (ገጽ 251) ። የተጣራበትን መንገድም ይሁን ሰነድ ላንባቢው ዋቢ ለመስጠት አይጨነቁም። ደርጎቹ ከስዎቹ መሀል የተወስኑ ሰዎች አስረው ዘቅዝቀው እየገረፉና ጥፍር እያወለቁ የመረመሩዋቸው ሰዎች እንደሚኖሩ የምንገምት ሰዎች አለን። ከዚያ ያገኙትን ማስረጃ ይሆን ወይ ብዬ ለማሰብ እንድገደድ አደረጉኝ። ሻምበል ፈቅረስላሴን አወዛጋቢና አከራካሪ ሊሆን የሚችል መጽሀፍ መጻፍ ያማከራቸው ሰው ዋቢ መጥቀስና ማስቀመጥ ተገቢ መሆኑን የነገራቸው አልመሰለኝም።

ደርግ የገደላቸውን የመኢሶን አባላትም በራሱ በመኢሶን ያመካኛሉ። ለምሳሌ እንዲህ ይላሉ።

“የመኢሶን መሪዎች ከኮበለሉ ብኋላ በርካታ አባሎቻቸው ላይ የመጉላላት ፣ የመታሰርና ከሥራ መባረር በሎም የመገደል አደጋ ደርሶባቸዋል። ይህ የመኢሶን የስልጣን ጉጉትና የአመራር ድክመት ውጤት መሆኑ ነው”። (ገጽ 342)

የመሪዎቹ መኮብለል በምን ተአምር ነው ደርግ ካለፍርድ ተራ አባሎቹን እንዲፈጅ ምክንያት የሚሆነው? መሪህ ስለኮበለለ ተብሎ ተከታይ የሆነ ያገር ዜጋ ካለፍርድ ይፈጃል እንዴ? ሻምበል አንዳንዱ ሎጂካቸው የተዘቀዘቀ ነው። የደርግን ወንጀል በዚህ አይነት የተውገረገረ ዘዴ ለመሸፈን መጣር በታሪክ ላይ ትልቅ የሽፍትነት ስራ መሆኑ ሻምበል የገባቸው አልመሰለኝም።

ሌላ አንድ ልጨምር። የጄነራል ተፈሪ በንቲ፣ የሻምበል ሞገስ ወልደሚካኤልና መቶ አለቃ አለማየሁ ሀይሌ በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም የተፈጸመባቸውን ዘግናኝ አገዳደል ድራማ ይተርኩልንና መደምደሚያ ላይ እንዲህ ይላሉ።

“የኢህአፓ መሪዎች በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ጉዳዮች ላይ የመወሰንና የማዘዝ ሙሉ ስልጣን ያለውን መንግሥት በመለመሏቸው ጥቂት የደርግ አባላት አማካይነት አንበርክከው ስልጣን ለመያዝ ይቻላል ብለው በቀየሱት ከጀብደኝነት የመነጨ ስልት ምክንያት የደርግ አባላትን ለእሳት ዳረጉ” ይሉናል(ገጽ 127)።

በራሱ በደርግ አሰራር ተመርጠው ሀላፊንት ላይ የተቀመጡትን የደርግ መሪዎች በግል ውሳኔ ከደርግ ውጭ አሲረው የገድሉዋቸውን ኮሎኔል መንግስቱን አረዷቸው እንደማለት ኢህአፓ ለሳት ዳረጋቸው ሲሉ ትንሽ አያፍሩም። የሚገርም ነው። የቀድሞ የጃንሆይ የመኪና ማቆሚያ ጋራጅ ውስጥ ከታሰሩ በሁዋላ ድምጽ በማያወጣ ጠመንጃ አስቀድመው አዘጋጅተው የረሸኗቸውን መንግስቱን ነፃ አውጥቶ ሌላ የሚከስ ሰው ምን አይነት ህሊና እንዳለው ለመገመት ይከብዳል። ጄኔራል ተፈሪ ፣ መቶ አለቃ አለማየሁና የሻምበል ሞገስን በጊዜው የነበረውን የርስበርስ መጨፋጨፍ ለማስቆም መላ ያሰቡና በስልጣን ጥም ያበዱትን ኮሎኔል መንግስቱን ገለል ለማድረግ ህልም የነበራቸው ቅን ሰዎች ነበሩ፣ ሆኖላቸው ቢሆን ኖሮ የተሻለ የሰላምና የእርቅ አቅጣጫ ሊመጣ ይችል ነበር፣ ብለን የምናስብ ብዙ ኢትዮጵያዊያን መኖራችንን እንዳይገምቱ ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ህሊና ላይ አንዳች የሚያህል መርግ የተቀመጠበት ይመስላል። ለነገሩ ሶስቱንም የደርግ አባሎች የኢህአፓ ስርጎ ገቦች ይሉዋቸዋል እንጂ ለመሆናቸው ወይም ያደረጉትን ያደረጉት ከኢህአፓ በተሰጠ ትዕዛዝ ስለመሆኑ ምንም የቀረበ መረጃ የለም። ሙዋቾቹ የደርግ አባሎች በጊዜው የያዙትን ስልጣን ያገኙት ግን በዚያ ጨለማ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ በምትመስል የምርጫ አካሄድ መሆኑን ደራሲው ራሳቸው አልደበቁም። ሙዋቾቹ የሰሩት ነገር ጥፋት ነው ብለን ብንስማማስ እንኩዋን በዚያ ሁኔታ ከሚታረዱ ለምን ታስረው ቃላቸውን ሰጥተው ለፍርድ መቅረብ ነበረባቸው ብሎ የሚከራክር ህሊና አጡ። ያን ጊዜ ህሊናው ባይኖራቸው አይገርመኝም። ዛሬ ከብዙ ዘመን በኋላ ይህን ማሰብ አለመቻላቸው ግን ይገርማል።

ሻምበል ሁሉንም የደርግ መንግሥት ክንዋኔ በዚህ መጽሀፍ ላይ ማጠቃለል እንደማይቻል መጽሀፉ መጨረሻ ላይ ነግረውናል። ሳይነግሩን የቀሩት ነገሮች ግን ሊያልፉዋቸው የማይገቡና እዚህ መጽሀፍ ላይ የደርግ ጥሩ ተግባራት አድርገው ከነገሩን ስራዎች ጋር የሚነጻጸሩ ትልልቅ ነገሮች ናቸው። በደርጉ የመጨረሻ እድሜ አካባቢ ተነስቶ የነበረውን የከሸፈ መፈንቅለ መንግስት በተመለከተ ምንም አልነገሩንም። በጃንሆይ ጊዜ ስለደረሰው ችጋር በሰፊው ተርከዋል። በ1977 ዓ.ም ስለደረሰው ዘግናኝ የችጋር እልቂት ትንፍሽ አላሉም። የሚያመካኙባቸውን ሁሉ ጨርሰው ስለፈጁ የሚለጥፉበት አካል ስላጡ አስመሰለባቸው። አከራካሪ ስለነበረው ቤተሰብን መተከልና ጋምቤላ እስከመክፈል ስለደረስው ቅጥ ያጣ የሰፈራ ፕሮግራም ምንም አላሉም። ስለዚያ በጅጉ በድንቁርና ላይ ስለተጀመረ መንደር ምስረታ ስለሚባል የዕብደት ስራ ምንም አላሉም። እኔ ከገበሬዎች እንደተማርኩት ገበሬዎች ዳገታማና ጭንጫማ ጥግ እየፈለጉ መኖሪያ ቤት የሚሰሩት መሬቱ ጭንጫማ ስለሚሆንና ተፋሰስም ስለሚኖረው በክረምት ከብቶቻቸው አረንቋ እንዳይገቡ ፣ የማይታረስ መሬትም ላይ ስለሚሰፍሩ የርሻ መሬት ለማትረፍ ፣ ለጥ ያለው ሜዳ ደግሞ ውሀ ስለሚተኛበት ለሳርና ለግጦሽ እንጂ ተፋሰስ ስለሌለው ለቤት መስሪያና ለከብት በረት ስለማይሆን ነው። ይህን ነገር አቅርበው መንደር ምስረታውን ስለሞገቱ የታሰሩ ገበሬዎች አጋጥመውኛል። ደራሲው የደርግን ጥፋቶች ላለመንካት ሲሉ ብዙ ትንንሽ ነገሮችን እንድናስታውስ የሚወተውቱተን ያህል እነዚህን ትልልቅ የጥፋት ተግባራት ወደጎን የገፏቸው ይመስላል።

የፖለቲካ አመራር በውሱን አቅም ውስጥ ማድረግ የሚቻለውን ነገር ባግባቡ የማድረግና በተለይም አስቸጋሪ ቅራኔን የመፍታትና ስምምነት የመፍጠር (compromise) ጥበብ ነው። ይህንን የማያውቁ ፣ አንዴ እንዲቀናቸው የጠቀማቸው ዘዴ ለሁሉም ችግር መፍቻ የሚጠቅም የሚመስላቸው የፖለቲካ መሪዎችና ሀይሎች ከውድቀት አያመልጡም። ብዙ የፖለቲካ መሪዎች የሚፈልጉትን ነገር ወይም ለፕሮፓጋንዳ ብለው የሚያወሩትን ነገር ራሳቸው ደጋግመው ይሰሙና እንደውነት ያምኑታል። ያን ጊዜ ነገር ይበላሻል። ማስተዋል ሁሉ ቦታውን ለዕብሪት ይለቃል። በደርግም ላይ ሆነ በሌሎች አምባገነኖች ላይ የሆነው ይህ ነው። የደርግ ታሪክ ባጭሩ ሲጠቃለል ይኸው ነው። ሌተና ኮሎኔል መንግስቱን ሀገር ወዳድ እያሉ ሊሸጡልን የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። ሻምበልም ሊሸጡልን እንደሚሞክሩት ኮሎኔል መንግስቱ ከስልጣናቸው በላይ ሀገራቸውን የሚወዱ ሰው አልነበሩም። በግትር አምባገነንነትና ራስ ወዳድነት ሀገርና ህዝብ ክፉኛ የጎዱ አምባገነን ናቸው። በተግባር ያየነው ይህንን ነው።

ስላለፈ ነገር መጻፍ ጥሩ የሚሆነው መማሪያና ማስተማሪያ የሆነ እንደሆን ነው። ሻምበል ስለደርግ ይኖራቸዋል ብለን የገመትነውን የሚያክል ከደርግ ጥፋትና ልማት የምንማርበት መማሪያ ነገር በዚህ መጽሀፍ ላይ አልሰጡንም። ወደፊት ይክሱን ይሆናል የሚል ተስፋ አለኝ።

Fekadeshewakena@yahoo.com

“በዜጎች ላይ የመብት ጥሰት እየፈጸሙ ያሉ የመንግስት ተቋማት አና አስፈጻሚዎች በህግ ሊጠየቁ ይገባል”–አንድነት

$
0
0

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት እ.ኤ.አ በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተፈፀሙ ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርት ተመልክተነዋል፡፡ በሪፖርቱ የተካተቱት የመብት ጥሰቶች አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በተደጋጋሚ ያጋለጣቸው እና ከፍተኛ ትግል እያደረግንባቸው የሚገኙ አስከፊ ተግባራት እንደሆኑ ቢታወቅም የቆምንለት ዓላማ እና እየታገልነው ያለው ስርዓት በሌሎች ዘንድም ድርጊቱ የታወቀ መሆኑን ያረጋገጥንበት ነው፡፡ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በሪፖርቱ ያካተታቸው እንደተጠበቁ፣ የተፈጸሙ እና እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከዚያም የላቁ እንደሆኑ አንድነት በተጨባጭ ያውቃል፡፡

UDJ የኢህአዴግ መንግሥት ዜጎችን በማፈን፣ ሚዲያዎችን በመዝጋት፤ ለህግ የበላይነት ቁብ በማጣት፤ ድብቅ በሆኑ እስር ቤቶች ዜጎችን በማጎር፤ በጥርጣሬ ያዝኳቸው የሚላቸውን ዜጎች በራሳቸው ላይ እንዲመሰክሩ በማስገደድ፤ በማሰቃየት፤ በማስፈራራት፤ በመግደልና አስገድዶ ከሀገር በማሰደድ የተመሰከረለት ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከገዥው የኢህአዴግ መንግሥት የተለየ አመለካከት ያላቸውና ስርዓቱን የሚተቹ ዜጎች የመከራ ገፈት የሚጋቱባት ሀገር እንደሆነች መቀጠሏም ከዜጎቿም ሆነ ከዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ የተሰወረ አይደለም፡፡

ቀደም ሲል በግፍ ታስረው ከሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አንዷለም አራጌ እና ናትናኤል መኮንንን ከመሳሰሉ ብርቱ ሰላማዊ ታጋዬቻችን በኋላ እንኳን በቅርቡ የፓርቲያችን የቀድሞ ዋና ፀሐፊና የአሁኑ የብሔራዊ ም/ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ ሃሳባቸውን በመጽሔት ጽፈዋል ተብለው ለእስር መዳረጋቸው የስርዓቱ አፋኝነት መቋጫ ያጣ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ሌላኛው አባላችን አቶ አለማየሁ ለፌቦ ከፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ማግስት ጀምሮ ወደ ደቡብ ክልል ሲመለሱ የፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ለ27 ቀናት መታሰራቸው፤ በኦሮሚያ በደቡብ እና በሰሜናዊት ኢትዮጵያ በተለየ ሁኔታ አባሎቻችን በአመለካከታቸው ብቻ ከስራ እየተፈናቀሉ መሆኑ፤ ጋዜጠኞች እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ዛሬም በእስር ላይ መሆናቸው፤ ከዚህ በተጨማሪ ሙስና፤ የመሬት ቅርምት፤ የዜጎች መፈናቀል እና ህገ ውጥ አሰራር በበኩሉ ከስርዓቱ ጋር የተገነባ መሆኑ ሀቅ ነው፡፡

በሪፖርቱ የተዘረዘሩትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መድገም ባያስፈልግም በዚህች ሀገር የተንሰራፋው ህገ ወጥነት ይቀየር ዘንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የሲቪክ ተቋማት፤ ድፕሎማቲክ ማህበረሰቡ እና የሚመለከተቸው አካላት ህጋዊ በሆነ ሁኔታ በመንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድሩ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ይህ ሁሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ባለበት ‹‹ጤነኛ እንደሆነ መንግሥት ›› ራሱን ለመቁጠር እንደሚያስቸግረው እንረዳለን፡፡ በመሆኑም የፖለቲካ ምህዳሩን ለሁሉም እኩል በማድረግ፤ የፀረ ሽብር፤ የፕሬስ፤ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ማደራጃ፤ ህጎችን በመቀየር፤ የሊዝ አዋጁን እና በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ የተካተተውን የፕሬስ ነጻነት የሚገፋ አንቀጽ በመሰረዝ፤ ከዴሞክራሲና የፍትሕ ተቋማት ላይ እጁን በማንሳት ከሚመጣበት የህዝብ ቁጣም ሆነ የታሪክ ተወቃሽነት ቢያመልጥ መልካም ነው እንላለን፡፡ አንድነት፣ በሀገራችን ያሉትን የፖለቲክ ችግሮች በዉይይት ለመፍታት በኢሕአዴግ እና በተቃዋሚዎች መካከል ሁሉም አሸናፊ የሆኑበትና ቅንነት ያለበት ውይይት እንዲደረግ፣ ፍላጎት እንዳለው በተደጋጋሚ በገለጸው መሰረት፣ ኢሕአዴግ ወደ መሃል ሜዳ መጥቶ ለዉይይት እንዲዘጋጅም እንጠይቃለን።

በሪፖርቱ የተዘረዘሩ እና ሌሎችም የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በሚመለከት ግን በተለይ የተወካዮች ምክር ቤት፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮምሽንና የእንባ ጠባቂ ተቋማት ከፓርቲ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ መርምረውና አጣርተው የመብት ጥሰት የፈጸሙትን የመንግስት አካላት ለፍትህ ማቅረብ ግዴታቸው መሆኑን አንድነት ፓርቲ ያሳውቃል፡፡

ከሁሉም በላይ ዋነኛ የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆናችሁ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ያላችሁ መላው የሀገራችን ዜጎች ሰፊው ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት እንጂ ከጥቂት አምባገነን መሪዎች መብት የሚለምን አለመሆኑን በመገንዘብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ስርዓቱን ለመታገል በአንድ ድምጽ ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የአሜሪካ መንግሥትም ቢሆን አንዲህ ዓይነቱን ከአሜሪካ ባህልና እሴት ጋር የሚቃረኑ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተደጋጋሚ በየዓመቱ ሪፖርት ከማውጣት ባሻገር ትርጉም ያለው ጫና በማሳደር ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ለዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብት መከበር ሊቆም ይገባል ብለን እናምናለን፡፡

ዘለዓለማዊ ክብር ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
የካቲት 26 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት ከወጣ በኋላ በኢትዮጵያ የፀረ-ሽብር፣ የፕሬስና የሲቪል ማኅበረሰብ ሕጎቹ ማወዛገባቸውን ቀጥለዋል

$
0
0

press
ዘሪሁን ሙሉጌታ/ሰንደቅ ጋዜጣ

“መፈክር በተሰማ ቁጥር መፈክሩን ተከትለን አንነጉድም” አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒሰትሩ ቃል አቀባይ

የ2013 የስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት መውጣትን ተከትሎ ባለፉት አምስት ዓመታት ሲያወዛግቡ የነበሩት የፀረ-ሽብር፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የበጎ አድራጎትና ማኅበራት (የሲቪል ማኅበረሰብ) ሕጎች ማወዛገባቸውን ቀጥለዋል።

John Kerryየአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) በየዓመቱ በሚያወጣው ሪፖርት ላይ በሕጎቹ የሀገሪቱን ሕዝቦች ስብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ ጫና እንደሚያደርጉ ሲጠቅስ መቆየቱ ይታወሳል። መንግስት በበኩሉ የፀረ-ሽብር ሕጉ በሀገሪቱ ላይ ያንዣበበውን የሽብር አደጋ ለመግታት አስፈላጊ መሆኑን፣ የፕሬስና ሕጉም ሀሳብን የመግለፅ ነፃነትን ለማስፋት እንዲሁም የሲቪል ማኅበረሰብ አዋጁም በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ የውጪ ጣልቃ ገብነትን ለመግታትና ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበራትን ለማበረታታት መሆኑን ሲገለፅ ቆይቷል።

ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጎች የሀገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሂደት እያሽመደመደና የፖለቲካ ዓላማ ያዘሉ፣ የገዢውን ፓርቲ የስልጣን ዘመን የሚያረዝሙ በማለት ሲቃወሙ ቆይተዋል።

ከሰሞኑንም ይሄው ጉዳይ እንደ አዲስ ተነስቶ እያወዛገበ ነው። በመንግስት በኩል ሕጎቹን የማሻሻል ሁኔታ በራሱ መንገድ የሚያየው መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል።

“በእኛ እምነት ሕጎቹን መቀየር የሚያስፈልግ ከሆነ በሂደት ከታለመላቸው ዓላማ አንፃር ያመጡት ስኬት ተመዝኖ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በራሱ መንገድ (Organic Process) መልሶ የሚያያቸው ይሆናል” ያሉት አቶ ጌታቸው ከዚህ ውጪ ሕጎቹን በደፈናው ከመቃወም በስተቀር በዝርዝር የመጣ ጉዳይ የለም ብለዋል። ከዚህ ይልቅ ሕጎቹን ለማስቀየር መፈክር ማሰማቱ እንደማይጠቅም ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው “መፈክር በተሰማ ቁጥር መፈክሩን ተከትለን የምንነጉድበት ምክንያት የለም” ብለዋል።

ሃብታሙ አያሌው

ሃብታሙ አያሌው

በአንድነት ለዴሞክራሲ ለፍትህ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው በበኩላቸው ፓርቲያቸው ገዢው ፓርቲ በሕጎቹ ላይ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመነጋገር ፈቃደኛ ከሆኑ በደስታ እንደሚቀበሉት ተናግረዋል።

ምንም እንኳ ፓርቲያቸው ለስርዓት ለውጥ የሚታገል ቢሆንም፤ ኢህአዴግን ጨምሮ በውጪ ሀገር በሚገኙ በሕግ ካልተከለከሉ በስተቀር ከማንኛውም የዴሞክራሲ ኃይል ጋር ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ገንቢ ውይይት ማድረግ እንፈልጋለን። ኢህአዴግም በማንኛውም የሕግና የፖሊሲ የሀሳብ የበላይነት ለማግኘት ፍረጃውን በመተው፣ ፓርቲዎችን በማናናቅና ሕዝባዊ መሠረታቸውን ሳይክድ እስከመጣ ድረስ በሕጎቹ ላይ ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለመነጋገር እንዲያመችም ሕጎቹን በጅምላ ከመቃወም ባለፈ በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ለመነጋገርም እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። ሕጎቹን በጅምላ የሚቃወሙትም አዋጆቹ የወጡበትን መሰረታዊ ፍላጎት (Intention) ዴሞክራሲንና ሕገ-መንግስቱን የሚጥሱ በመሆኑ ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ሊዘጋ ነው፤ ዘንድሮ አንድም ተማሪ አልተመዘገበም

$
0
0

ዘሪሁን ሙሉጌታ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው፦

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎችን በማጣቱ የትምህርት ክፍሉ አደጋ ላይ መውደቁን እያሳዘናቸው መሆኑን የታሪክ መምህራንና ተመራማሪዎች ገለፁ። ሀገሪቱ ጥንታዊና መካከለኛ ታሪኮች ባለቤት ብትሆንም በአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የታሪክ የትምህርት ክፍል ሊዘጋ መቃረቡ እያነጋገረ ነው።
addis ababa un
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል የሚያስተምሩ መምህራንና የታሪክ ተመራማሪዎች “ታሪክ ዳቦ አይሆንም” በሚል የተሳሳተ አመለካከትና የ70/30 የትምህርት ፖሊሲ የፈጠረው ችግር መሆኑን በመግለፅ አሰራሩን አምርረው ተችተዋል። ከታሪክ በላይ ዳቦ የሚሆን የለም። ታሪክ የአንድ ሀገር የማንነትና የእውቀት መሠረት መሆኑ እየታወቀ የትምህርት ክፍሉ በተማሪ እጦት በአደጋ ላይ መገኘቱ እንደሚያስቆጣቸው መምህራኑና የታሪክ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።

ሰሞኑን ዩኒቨርሲቲው የታሪክ ትምህርት የተከፈተበትን 50ኛ ዓመት ባከበረበት ወቅት በ2006 ዓ.ም አንድም የታሪክ ተማሪ ያልተመዘገበበት መሆኑ አሳፋሪም አሸማቃቂም መሆኑን የጠቀሱት ባለሙያዎቹ ችግሩን ለማስተካከል ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ፕሬዝዳንት ዶ/ር በለጠ ብዙነህ ስለጉዳዩ ተጠይቀው የታሪክ ትምህርት ክፍሉ እየተዳከመ መምጣቱን አምነዋል። ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው ምክንያት በታሪክ ትምህርት የሚመረቁ ተማሪዎች በመስኩ ስራ አናገኝም በሚል አመለካከት ዲፓርትመንቱን ባለመምረጣቸው ነው ብለዋል። ከዚህ ባለፈ በታሪክ ትምህርት የተመረቁ ተማሪዎች የታሪክ መምህር የመሆን ፍላጎት ባለማሳደራቸው ወደ ሌሎች ትምህርቶች እያተኮሩ በመሆኑ ነው ብለዋል።

ዩኒቨርስቲው በ70/30 ፕሮግራም መሰረት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጠቅላላው በማኅበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ በ2006 የትምህርት ዘመን ወደ 600 ብቻ ተማሪ መመዝገቡን ያስታወሱት ዶ/ር በለጠ እነዚሁ 600 ገደማ ተማሪዎች በሶሻል ሳይንስ ለ20 ዲፓርትመንቶች መከፋፈላቸውን ነው ያስረዱት። ከዚህም ውስጥ ተማሪዎቹ የተሻለ የሥራ ዕድል ወደሚያስገኝላቸው የትምህርት አይነት ነው የሚያተኩሩት ብለዋል።

የታሪክ ትምህርት መዳከም እንደ ሀገር ስለሚያመጣው ተፅዕኖ የተጠየቁት ዶ/ር በለጠ፤ ተፅዕኖ መፍጠሩ አይቀሬ መሆኑን ይስማሙበታል። ነገር ግን በመላው ሀገሪቱ በቅርቡ በተከፈቱ 32 ገደማ ከሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ወደ 17 ዩኒቨርሲቲዎች የታሪክ ትምህርት ስላላቸው በዘርፉ የሚመረቁ ተማሪዎችን ቁጥር በአንፃራዊነት ሊደግፈው እንደሚችል ተናግረዋል። ነገር ግን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያለው ሁኔታ ግን የታሪክ ትምህርት የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር ማነስ ግን አስጊ መሆኑ ተናግረዋል። ሁኔታውም በዚሁ ከቀጠለ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ የታሪክ መምህራን ላናገኝ የምንችልበት አደጋም ይታየኛል ብለዋል። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የታሪክ ትምህረት እንደ አንድ የትምህርት አይነት እየተሰጠ በመሆኑ በዩኒቨርሲቲዎች ያለው የታሪክ ተማሪዎች እጥረት መታየቱ ወደፊት የታሪክ መምህራን ላናገኝ እንችላለን ሲሉም ዶ/ር በለጠ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

ከአመለካከት ጋር በተያያዘ “ታሪክ ዳቦ አይሆንም” የሚለው አተያይ ችግር መፍጠሩን የጠቀሱት ዶ/ር በለጠ የታሪክ ትምህርት ከገበያና ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጋር ብቻ የተያያዘ በመሆኑ ይሄንን አመለካከት ለመለወጥ ብዙ መስራት እንዳለብን እንረዳለን ብለዋል። በቀጣይም የክፍለ ትምህርቱን ህልውና ለማስቀጠል የmajor/miner ፓኬጅ ማጠናቀር እንደሚገባ ጠቅሰዋል። ለምሳሌ ታሪክን በዋናነት ተምሮ ጋዜጠኝነት ወይም ቋንቋን በሁለተኛ ደረጃ እንዲማር በማድረግ የስራ አማራጭን ለመፍጠር መሞከር አለበት ብለዋል። አሁን ባለው የካሪኩለም ሁኔታ የmajor/miner ፓኬጅ አለመኖሩ ለተማሪዎቻችን አማራጭ እንድንሰጣቸው አላደረገም ብለዋል።

የሀገሪቱ ታሪክ በአግባቡ ባልተጠናበትና ባልተተነተነበት ሁኔታ የታሪክ ትምህርቱ መዳከሙ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ገዢው ፓርቲ ከሚመራበት ልማታዊ አቅጣጫም ጋር በማያያዝ የታሪክ ትምህርት መዳከሙን የሚተቹም አካላት አሉ።

[የረዳት ፓይለቱ ጉዳይ] ጀግናችን አጀንዳችን!

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

በትርጉም የሚቃኑትን ወልቻማና የተወኩ ዕሳቤዎች በትርጉም ፋክት በማንጠር ለሚነሱ ማናቸውም ጥያቄዎች የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች መልስ መስጠት ግድ ይላቸዋል። ለዚህም ነው ሥርጉተና ብዕሯ ታጥቀው በጀግናቸው ዙሪያ ትንሽ ማለት የወደዱት። ለሚሰጠን ጊዜ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ምስጋናችን ፍቅር ሰንቆ ይደረስ እንላላን – ጥንዶች።

የዝምታ ድል ባለቤት ረዳት አውሮፕላን አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ተገኘ።

ሥም።

ረዳት የአውሮፕላን አብራሪ ኃይለመድህን አበራ፤ ይህ ሥም የወጣት ጀግናችን ሥም ነው። ወላጆቹ መንፈስ ቅዱስ አቅብሏቸው በጥንቃቄ የሰዬሙበት። ደፍረን ስሙን እንጥራው። ድህነት ነው። ኃይል ያለው መድህን የሚበራ ስለ መገኘቱ ያበሥረናል – ይፈውሳልም!

በዚህ ሥም ፓል ላይ የሚጠሩ ወንድሞቼን አመስግናለሁ። በሌላ በኩል ግን ሺ ሚሊዮን ጊዜ „ኮ ፓይለት፤ ረዳት አብራሪ“ እያሉ የሚጠሩትን ቅን ወገኖቼ እንዲያስተካክሉ በትሁት ቅን መንፈስ አሳስባለሁ።፡ሥሙን ቅርባችን አድርገን እናስጠጋው። ከማንነታችን ጋር እናዋህደው። „ረዳት አውሮፕላን አብራሪ፣ ወይንም ኮ ፓይለት“ የወል ሥም ነው። ልክ „ሰው“ በሰውነት ለተፈጠረ ሁሉ የተጸዎ ሥም እንደሆነው ሁለ። እኔ አንድ „ሰው“ መጣ ብል። የምነግረው ሰው „የትኛው ሰው?“ ብሎ ማንነቱንና ልዩ የሚያደርገው ሥም ይጠይቀኛል „አቶ ሀ“ ጎረቤታችን ሃኪሙ በማለት መልስ እሰጣለሁ። „ረዳት አውሮፕላን አብራሪ ወይንም ኮ ፓይለት“ የሙያ የተጸዎ የወል ሥም ነው። „እሱ“ ስል ተወላጠ ሥም ይሆናል። ነገር ግን እንዲህ ላላ ለበቃ ተግባርና ተልዕኮ የተፈጠረን ወጣት የወሰደውን ልዑቅ እርምጃ ለመደገፍም ሆነ ለመቃወምም ስንነሳ ድርጊቱን ፈጻሚ ባለቤቱ መለያ ሥም አለው። እጅግ የሚያመራምር የሚያምርም „ኃይለመድህን አበራ“ አሁን በቤተሰብ ሥም ስለሚጠር ለሰላማዊ ስለፍና ለፒቲሽን „አበራ ኃይለመድህን“ ይህ በዚህ እንዲስተካክል አበክሬ ላሳስብ እወዳለሁ። እርግጥ ነው የገዢው የጎሳ ፓርቲ ተጠሪዎች ወይንም ደጋፊዎች በሽታችሁ እንደሚሆን አስባለሁ። ተፈጠረ ጀግና ባላሰባችሁት – ባላቀዳችሁት ሁኔታ …. ምን ትሆኑ? ፈጣሪን ጠይኩት …. አቤ ሄሮድስን ከነ ከነጓዙ ገርድሷል ማን ያውቃል ኃይሌ ደግሞ እነ ይሁዳን …. ቡሉ ወደ ሁለተኛው ጉዳዬ … ለእኔዎቹ
ethio airlines
የነፃነት ትግል እርምጃን ቅንጦተኞች ዝነጣቸው አላማረባቸውም።

ባልተለመደ ሁኔታ፤ ዓለም በሌላ ወጣ ገብ ጉዳይ ሲባዝን ከኢትዮጵያ አንድ የቆረጠ ወጣት የተዘገን መከራን ለመግለጽ የተሳነውን የሚዲያ አንደበት በዝምታ አስገድዶ አስከፈተ። የትግሉ አይነት ሰላማዊ ነበር። ለነገሩ “ትግል“ ብሎ ሰላማዊ የለም የሚሉም አሉ። ቀደም ያሉትን የነፃነት ትግሎች ታሪክ መጸህፍት እንዲያነቡ እዬገባዝኩ፤ በተጨማሪም በህይወታችው ውስጥ ትዳር መስርተው ሲኖሩ ያለውን የመንፈስን የአካል መስከም ዳሰስ አድርገው ስለትግል ትምህርት እንዲወስዱ እጠቁማለሁ ያው በትህትና።

የነፃነት ትግል፤ አንቢተኛነት ነው። አሻም ማለት ነው። ለገዢው ለመገዛት ፈቃድን መንሳት ነው። አሻም ደግሞ በውድ ሊጀመር ይችላል። አድማጭ ካጣ ግን በህግ ጥላ ሥር ህግ መጣስ ግድ ይላል። አሁን ራህብ አድፍጦ ቹፌውን ወያኔን እዬጠበቀ ነው። „ዝምታ“ በእናት ሀገራችን በኢትዮጵያ „ልብን የሚሰነጥቅ የብዙኃን ዝምታ“ በእጅጉ ሰፍኗል። ኑሮው ራህብ ሆኖ አብሮ ከራህቡ ጋር በዝምታ የታመቀ ቃጠሎ አለ። ይህ ዝምታ ሲገነፍል ግን ምድር ቀውጢ ይሆናል። „ሀገርን ህዝብ ካልጠበቀ ሰራዊቶች በከንቱ ይደክማሉ“ ይለናል አካል የሌለው የመዳህኒተዐለም አገልጋይ ቃለ ወንጌል። ዛሬ ያለው የአጋዚ በላህሰብ ሞገዱ የተነሳ ዕለት መግቢያ ያጣል። ወያኔን በልስሉስ ቅምጥል ፈሰስ ባላች መንገድ እንታገል፤ ግን ይህችን ሳትነኩ፤ በዚህ አልፋችሁ፤ ያቺኛዋን ብቻ …. ራህብ ላይ ተሆኖ፣ ሞትም ላይ ተሆኖ፣ ዕንባ ላይ ተሆኖ፣ ሳቅ የለም እንጂ ይህ ቀበጥ ያለ የዝነጣ ትችና አገላለጽ አንድ የኮሜዲ ትራጄዴ በቅይጡ ልዩ ኪኖ ሆኖ ባሰራ ….. ነበር። አዬ! ዘማናይነት … የደላው ገንፎ ….

በመጀመሪያ ነገር በጫካ ተመክሮ የነፃነት ትግል አይመራም። ጎጥ ላይ ተሁኖም አይታሰብም። በንክኪ ፖለቲካም አይታሰብም። በቆረጠ ሥልጡን ዕይታን የነቃ ግንዛቤን ከዘመኑ ጋር እራስን በማቀራረብ መለወጠን አብስሎ ይጠይቃል። ለዚህ ደግሞ አይደለም ኢትዮጵያን አኽጉሩን ዓለምንም ቆሞ የሚያስተምር፤ የሚሰበክ ለሁለት ዓመት የዘለቀ የምንም ዓይነት ግድፈት ያልታዬበት ድንቁ “የድምጻችን ይሰማ“ እጅግ ብቁ ሥልጡን የእምነት የነፃነት ሰላማዊ ጥያቄና ግብዕቱ ከበቂ በላይ ትዕግሥትን አምርቶ ያቀና ገድል ነበር። ከዚህ በላይ ምን መረጃ እንድናቀርብ ይሆን የቅንጦት ፖለቲከኞች የሚጠይቁን?! …. ሰማያዊ ፓርቲ በቢሮ ሰልፍ በጠራ ዋዜማ ተደብድቦ ተገርፎ መዘረፉስ? የአንድነት ከፍተኛ አመራር በግልና በጋራ የሚደርስባቸው መራር እጅግ አሰቃቂ በሀገር ኢትዮጵያ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅው ድፍረትስ ምን ይባል ይሆን? ጻፋችሁ ተብለው የካቴና ጓደኛ የሆኑት ቅኖችስ? እኔ አንዳንድ ጊዜ ይህ ህሊና የሚባለው ነገር በምን ላይ እንዳለ ይገርመኛል …. ግን የእውነት እንደ ሰው ማሰብ እንዴት …. አይቻልም ….

ሰማቱ አሰፋ ማሩ በጠራራ ጸሐይ በባሩድ የተቃጠለው ይረሳልን?! የኔሰው ገብሬ በቤንዚን እራሱን አመድ ማድረጉስ ህሊናን አይፈትሽምን? ያቺ ምስኪን ሴት ባልሽ መሳሪያ ደብቋል ተብላ የባለቤቷን ምንድ ነው በትርሷ እንድተጊትት ብቻ ሳይሆን የነገ ተስፋ ጥንስስ በግፍ ሲያሰወርዳት የት ነበርን? ስንቱ …. በእውነት ይህን እውነት ስንዳፈር ጠረናችን ባዕድ ሆኗል። ባላፈው ሳምንት አንድ ወጣት እራሱን በመዲናዋ ላይ ሲያጠፋስ ከቶስ የሥርዓቱን ገነትን ይነግረን ይሆን? በሳውዲ በግፍ ደማቸው በባዕድ ሀገር የጎረፉት ደመ ከልብ ወጣቶችን አቤቱታ በግል ኃላፊነቱን ወስዶ ሰማያዊ የጠራው ሰልፍ በምን አይነት ዱላ ነበር የተወራረደው? አለን ወይንስ የለንም?!

….. እራቅ ብልን ምልስትን ስንቃኝ ለእርቀ ሰላም ከውጪ ሀገር የሄዱት ወገኖች ምን ጠበቃቸው? ቅንጅናትና ቃሊቲ፤ ብዕርና እግር ብረት …. ህም! አለም ያወቀውን የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ህልፈት ዘገበች ተብላ 30000 _የፍትህ“ ጋዜጣ የእሳት እራት የሆነቸው …. ምንድን ነው ነው የሚፈለገው?! …. አይደለም አቅጣጫን ቀይሮ በሰላም ያረፈ አውሮፕላን ቀርቶ ነገ ከዚህ የከፉ ያልታቀዱ ጨርሶም ያልተሳቡ የፋሙ ጥቃቶችን ወያኔ መጠበቅ ግድ ይላዋል። ቀለደ – ዘፈነ – ደለቀ – ዳነሰ …. ኢትዮጵያ እንደ ጥንቸል ማንኛውም ዓይነት መሞከሪያ ጣቢያ አድርጎ መሰረቷን ነቀለ። ዕንባ እያለ እንቅልፍ የለምና ነገም ሌላም ይጠበቅ ሙጃው ወያኔ። ከዚህም ባለፈ ይጋያል። እደግመዋለሁ ከዚህ ያለፈ ይጋያል። የአሽዋ ድርድሮች ላንቲካ የጨው ሃውልት ሆነውም ይቀራሉ ….. „ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው“

የትም ቦታ፤ በእጅ በገባ ማናቸውም መሳሪያ „እንቢተኝነት ይሞሸራል“ ነገ አይቀሬ መሆኑን ሙጃው ወያኔና ደጋፊዎቹ ብትረዱት እጅግ መልካም ነው። በዚህ ዙሪያ ቃል፣ ድምጽ፣ ክብር፣ ተቀባይነት፣ ሚዛን አያነሱም። ዜሮ ሲባዛ ዜሮ ዜሮ ይሆናል። የሃሳብ ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ መስመር የሳቱ ሂደቶች ግን ሊቀ ይገባቸዋል። ወያኔ ሃቅን ተጭኖ እንዲቀብል ማሰገደድ አይቻልም። ፈጽሞ! ወያኔ ያለወቀው ይህን ነው። ቀድሞ ነገር ወያኔ የብዙኃኑ አንጡራ ጠላት ነው። ሀገርን ያህል ታላቅ ክብር ለቀደመ ጠላት የሚሸልም አሽኮኮ … ይጠብቅ ጊዜውን። „እፉኙቱ ወያኔ“ ራሱን ሳይደግም አመድ ይሆናል ከነምናምቴው – ድሪቶው። ኢትዮጵያዊነት ፈተና የደረገው እሱ በሰራው ሴራና ደባ ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያዊነት ህሊናን ተውሶ ወይንም ተበድሮ የሚኖሩበት ማንነት አይደለም – በፍጹም። ለዚህ ደግሞ አልተማረበትም እንጂ ወያኔ የሰማዩ ታምር ከአናቱ ነበር ግማቱን በአንድ ሰሞን ትቢያ ያደረገው። አሁንም ይቀጥላል ፈንግል ይፈነገላል …. ግፍና እንባ ባክነው አይቀሩም … አስከ ልጅ – ልጅ ….

ከዚህ ጋር የሚነሳው ነገ አንድም አብራሪ ታምኖ አውሮፕላን አይሰጠውም፤ መልሱ ነገን የሚያውቅ መዳህኒአለም ብቻ ነው። የታፈነ ህዝብ ግን በር ሲዘጋ በመስኮት፤ መስኮት ሲዘጋ በጣሪያ፤ ጣሪያ ሲዘጋ በምድር ድምጹን እንብተኝነቱን በማንኛው ጊዜና ሁኔታ ያፈነዳዋል። ፉኛ ታውቃላችሁ? ከልክ ባላይ ከተነፋ ይፈነዳል …. ከፈነዳ የሚተርፍ አንድም የቅንጦት ምናንምን አይኖርም።

ወ/ሮ ዘነቡ

ወ/ሮ ዘነቡ

ወይ መዳህኒታአለም አባቴ ደግሞ ከመቼ ወዲህ ነው ስለ ኢትዮጵያዊነት ተቋማት ስብከት የተጀመረው? የወያኔ ጠላቱ ማንና ምን ሆነና?! ለመሆኑ ዬት አሉና ጥብቅና የሚቆምላቸው ተቋማት፤ ቀፏቸውን የቆሙት። ካላ ቀለም እስክርቢቶ አይጽፍም ሞክሩት …. በዘመነ ወያኔ አለን የምንለው የኢትዮጵዊነት ተቋም፤ ቅርስና ውርስ፤ ትውፊትም የለንም። የሰሞኑ የወ/ሮ ዘነቡ መልእክት ምን ይመስላችኋል? እስከዚህ ድረስ የገማ ነው ወያኔ! ከዚህ በላይ ምን እርቃን መቅረት አለና?
ክብሮቼ – ስለዚህም የቤት ሥራችን ጥልቅና የገዘፈ መሆኑን ልብ ልንለው ይገባል። መርዝ ያልተነሰነሰበት አንዳችም ፃዕዳ ቦታ የለንም። በተረፈ የጀግኖች ጀግና! የተስፋ ተስፋ! የብርኃን ብርኃን መድህናችን ኃይላችንና ጉልበታችን እንደ ሲዊዝ ሰልፈኞች አገላለጽ „ሃይለመድህን አበራ የነፃነት መጸሐፋችን ነው።“ በጀግናችን ኮርተንበታል። በዚህ ጀግንነት መንፈስ ኢትዮጵያ ዳግም ታበራለች። ህሊና ተሸጠ እንጂ እነ ወያኔ ትውልዱ ባገኘው አጋጣሚ እኮ ማንፌስቶችሁን እዬቀጠቀጣ አመድ ዱቄት እያደረገላችሁ ነው። የጎጥ ረግረግ ለጨፈረበት መንፈሳችሁም ሽንፈትን አስገድዶ እዬጋታችሁም ነው።

ወይ ዘመናይነት …. ቅድመ መሰናዶ አስፈላጊ አይደለም፣ ሂደቱን ታከሩበታለችሁ የሚሉም አዳመጥኩ … ከእንቅልፎች … አይገርሙም? እኮ! ጅሎች እንዲህ ይሉናል። ቂሎች እንዲህ ይቀልዳሉ። „ልብ ያለው ሸብ“ ይላል ጎንደሬ። እኛ ስለምንሰራው ተግባር ለእኛ ተውሉን እነ ውሽልሽል የሙጃ አጨብጫቢዎች። የእናንተን የፍርሰት ቲወሪ ተንዶ አፈሩ እብቅ እስኪያድረጋችሁ ድረስ። መሬት የያዘ፤ መሰረት ያለው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገን የሚሞሽር ተግባር በግልና በጋራ ተግተን እንሰራበታለን። እዬተኛን ሳይሆን የምንኖረው እዬኖርን እናበራለን – ብርኃን አለንና። ሥጦታውም የመዳህነታችን ነው። „ቁርጥ ያጠግባል“ ቁርጣችሁን ታውቁ ዘንድ ሊነገራችሁ ይገባል። አዲሱ ዓምት የፈረንጆች እንዴት ነበር ዶልታችሁ በአዲስ ትወና ቃጠሎ የነበር — አሁን እኮ ከጀግንነት መልስ ረብ አለና አታሞው ተዘቀዘቀ -። ኢትዮጵያ አምላክ አላት። ኢትዮጵያዊነትም ታግላችሁ የማታሸንፉት ሚስጢር ነው – ተግባባን?!

ህም!

“ሊያመልጥ ሲል ተያዘ፡“ ወይ ጉድ! — ይህ ደግሞ የዓይን እከክ ነው። ለመሆኑ ታድኖ የተያዘው ምን ከሚባል ጫካ ውስጥ ነው? ቀድሞ ነገር በአደጉት ሀገሮች እኮ ጫካዎችም የእረፈት ጊዜ ማሳለፊያ፤ መዝናኛዎች ሲሆኑ በአቅራቢያቸው ለሰው ልጅ የሚስፈልጉ ነገሮች ሁሉ የተሟላባቸው፣ የሰው መኖሪያ አካባቢዎች ናቸው። ሌላው የዱር አራዊት መኖሪያዎችም ቢሆኑ ለዱር አራዊቶች ጥበቃ የሚደረግላችው የተከለሉ አካባቢዎች ሆነው፤ ነገር ግን በአቅራቢያቸው ሁለመናቸው ሙሉ ነው። በመሆኑ የሰው ልጆች ለሰላማዊ ኑሯቸው ለመኖሪያ የሚመርጧቸው ቦታዎች ናቸው። „መሳቂያው ፓርላማ“ አለ አቤ ቶኪቻው መሳቂያዎች ለነገሩ በረቀቀ በሰማይ ታምር፤ እኛ ልንፈታው በማንችል ሁኔታ በፈረንሳይና በኢጣሊያን አውሮፕላን በክብር ታጅቦ በመስኮት በገመድ እወርዳለሁ፤ ከዛ ጠብቁኝ ሲል በግልጽና በልበ ሙሉነት፤ በረጋ መንፈስ ነበር የገለጸው። ወረደ – ፈቅዶ እራሱ እጁን ሰጠ። በቃ! ጀግናው ኃይለመድህን አበራ። „ያዙት“ የሚለው ቃል ለሂደቱ ሆነ ለሰብዕናው ከእውነት ውጪ ነው። ጄኔባ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጫካ የለም። ጫካ ያለው በደመንፈሶች ህሊና በነወያኔ ብቻ ነው … እንደ አውሬ እንዲያስቡ ስለሚያግዛቸው፣ ተፈጥሯቸውም ስለሆነ፣ እንኳንስ ከድርጊቱ ከቃሉ ጋር ከ40 ዓመት በኋላ መፋታት አልቻላችሁም … እም!

እገታ ወይንስ ጠለፋ ወይንስ አቅጣጫ ቅይራ ….

ብብዙ ሚዲያዎች እመሰማው „ጠለፋ“ ነው። የሃሳብ ልዩነቱን አክብሬ እኔ እንደማስበው ግን ረዳት አውሮፕላን አብራሪው ሀይለመድህን አበራ እንደ ጣሊያናዊ ባእድ አብራሪ ሙሉ መብት አለው በአውሮፕላኑ ደህንነት ጉዳይ። ረዳትም የሚመደበው ዋናው ቢታመም ወይንም በረራ ላይ እያለ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ቢገጥመው ተክቶ እንዲያበር ነው። ሊቀመንበሩ ሳይኖር ምክትሉ ተክቶ እንደሚሰራው፤ ስለዚህ ኃላፊነቱን ወስዶ በንብረትና በተጓዦች ላይ ምንም የመንፈስ ጫና ሳይፈጥር እቅጣጫ መቀዬሩ „ጠለፈ“ ሊያሰኘው አይችልም ባይ ነኝ።

በሌላ በኩልም „ተሳፋሪን አገተ“ ለማለትም የሚያስችል ሂደት አላዬሁበትም „ አዬር ላይ እያለ ለቅድመ ሁኔታ ተሳፋሪውን አቅርቦ ቢሆን ኖሮ“ „አገተ“ የሚለውንም መጠቀም ባስቻለ። ባለሙሉ መብት ስለነበር አቅጣጫውን ቀይሮ ከታቀደው ቦታ ሳይሆን ሌላ ቦታ አሳረፈ። ይህ ደግሞ የአዬር ሁኔታ ቢዛባ፣ ሊያርፍበት የታሰበው አውሮፕላን ጣቢያ በጊዚያው ምክንያት ሊያሳርፍ ባይችል መሰሉ ተግባር ይፈጸማል።
በአውሮፕላኑ ላይ ሙሉ መብት ያለው አብራሪ በኢትዮጵያ ያለው የአንድ ዘር ተኮር የጎጥ ሥርዓት ጫናን በቃኝ ብሎ እንቢተንኝነቱን በእጁ በገባ አጋጣሚ ገልጦበታል። ወይንም ሰላሙን የነሳውን የጎሳ አስተዳደር አሻም ብሎ ገፍትሮበታል። እንዲያውም ከዚህ ጋር ተያይዞ በ28.02.2014 „የጀግናችን ድምጽ ድምጻችን ነው“ ለሚሉ ወገኖች ሲዊዘርላንድ በርን ላይ በተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ቀድም ብዬ ሄጄ ሰለነበር ከሁለት ኢትዮጵያዊ እህቶቼ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ለመወያዬት ዕድሉን አግኝቼ ነበር።

ወ/ሮ/ት እዬሩስ የምትባል ሰልፈኛ ስትነግረኝ እ.ኤ.አ በ1970 ከፖላንድ ወደ ሲዊዝ አንድ አብራሪ መሰል ተግባር እንደ ፈጸመና በዛን ወቅት ሲዊዞች ለዲክታተር አልገዛም ብሎ በመምጣቱ አጨብጭበው እንደተቀበሉት የሰማችውን አጫውታኛለች። ታሪክን ያጫወታት ሰው „ዛሬ ሲዊዝ ስደተኛ በመብዛቱ እንጂ እኔ እጠብቅ የነበረው አጨብጭበው እንደሚቀበሉት ነበር“ ሲሉ አንድ የሀገሬው ሰው እንደ አጫዋቷት ገለጸችልን። በዚህ መንፈስ ወስጥ ሆኜ እኔ ስለማስበው ጋር ግጥም ስለነበር ተስፋን ሰነቁኩኝ። እኔ ደግሞ „በዝምታ ዲክታተርን ያንበረከከ ለድልም የበቃ የጀግንት የላቀ ተግባር ስል አዘከርኩት። የጥንቃቄው ልባምንት ፍልስፍና ነው – ልእኔ። ሌላው ቀርቶ አውሮፕላን ውስጥ ሆኖ አውሮፕላኑ የማረፍያ ቦታውን እንደቀዬረ እንጂ በምን ምክንያት ዬት ለማረፍ እቅድ እንደነበረው፤ ፈጻሚውም ማን እንደሆነ እንኳን ፈጽሞ ፍንጭ አልሰጠም። ጠንቃቃነቱን በ30 ዓመት ዕድሜ ሲሰላ ታምር ነው። ይህም ስለሆነ ነው ተሳፋሪዎች መንፈሳቸው ሳይታወክ ጄኔባ የገቡት። ረቂቅ።

ስለምን በመስኮት?

ይህንንም ሲያጣጥሉት አድምጫለሁ። ረዳት አውሮፕላን አብራሪ ኃይለመድህን አበራ በመስኮት መወረዱ የተጓዡንም ሰላም ጠብቋል። ለሲዊዝ የደህንነት ቢሮም ብዙ ያላዬናቸው ተግባራትን ቀድሞ ሰርቶላቸዋል፤ አስተካክሎላቸዋል። ግብግብ ተፈጥሮ ቢሆን ብዙ ነገር መልኩ በተቀዬረ ነበር። ኃላፊነት በብቃት ያቀለመ ወርቅ ህሊና ማስተዋልን ፈጥሮ በህይወትም አቁሞ አሳይቷል። በሌላ በኩል በበሩ ሲወጣ ችግር ባይፈጠር እንኳን፤ የአውሮፕላኑ ውስጥ ከኢትዮጵያ ደንበር ጋር በብዙ መልኩ የተቆራኘ ሊሆን ይችል ስለነበረ፤ ለሙጃው ወያኔ ዬይገባኛል ጥያቄም ትንፋሽ በዘራለት ነበር። ይህን ሁሉ ብልሁ ቀድሞ ደፍኖታል እራሱ የሚስጢር ቁልፍ ነውና። እኔስ እላለሁ … ምነው ስትወለድ አስር ሆነህ በነበር … የኔ ጌታ!

ሥነ ምግባርና ኑሮውን

ይህን በሚመለከት ወላጅ እናቱ የተከበሩ ወ/ሮ የህዝብአለም ሥዩም „ብሩክ“ ሲሉ ገልጸውታል። ከዚህም በላይ በመኖሪያ አካባቢው የእረፍት ጊዜውን እንዴት ያሳልፍ እንደ ነበር አዲስ አድማስ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ አንብቡት። ጫማ ሲያስጠርግ፤ ኢንተርኔት ካፌ ተጠቃሚነቱ፤ የሚያዘወትራቸው ሱቆች፤ ጎረቤቶቹ፤ እቃ እዬጋዘ የሚቀርብለት ወጣት የሰጡት አስተያት እጅግ ያኮራል። ሁሎቹም የሰጡት አስተያዬት ወጥና የውስጡን ንጽህና ፍንተው አድርጎ ያሳያል። እኔ በዚህ ዕድሜ የማይታሰብ ብቃት ቡሁሉም ዘርፍ ከመልስ ሰጪዎች መገንዘብ ችያለሁ። እኛም ታድለናል፤ ተተኪዎቻችን በዚህ የኢትዮጵያ ጠላት በሆነ የጎጥ አስተዳደር በወያኔ ዘመን ተፈጥረው ግን በድርጊት እንደወርቅ እዬነጠሩ በሚወጡ ጀግኖቻችን ተስፋችን ልንጥል ይገባል። ኃላፊነቱንም ቀድመን ልንለቅላቸውም ይገባል። በምስከርነት በተሰጡት አስተያቶች ምርኩዝነት ወልገድጋዳ መላመቶች ሃግ ሊሉም ይገባሉ ….. ፎቶውንም የወሰድኩት ከዛው ነው ሊስቅም ይገባል የዝምታው ድል ዘመንን ሰርቷልና! ገዢ መሬቱን በሙሉ ተቆጣጥሮታል – ካለ ባሩድ ጢስ …

ጀግናችን አጀንዳችን ነው!

hero ጀግንነት ታሪክ ነው። ጀግንነት ትውፊት ነው። ጀግንነት ማንነት ነው። ስለሆነም ማንነታችን ዘለን ሌላ ነገር ማቀድ አንችልም። የፍላጎታችን እንብርት፤ የራዕያችን መሰረት፤ የተስፋችን ማረፊያ ሟተት ማንታችን በጀግንነት የጠለፈው የአድዋ፣ የማይጨው ወዘተ ታሪካችን ነው። የማንነታችን ምንጭና ግኝት ማህጸን የቀደምት ታሪካችን በተጋደሎ የቀለመ ከመሆኑ ላይ ነው። ስለ ትናንት ጀግኖቻችን ስናነሰ ይህ ብቻ በቂ አይደለም፤ በታሪካችን እኛም የእነሱን የሚመጥን ተግባር ዘመኑ በፈቀደው ልክ መሆን አለበት ብለን ተስማምተናል። ትናንት በፈረስ በበቆሎ ዛሬ ደግሞ ምዕቱ በፈቀደው በሠለጠነ እምቢተኝነት የተዘከረው የወርኃ የካቲት ደማቅ ገድል የጀግናችን የኃይለመድህ አበራ ታሪክ ታሪካችን ነው። ምዕራፉ በሰለጠነው ዐለም በሀገረ ሲዊዘርላንድ ጀኔባ ላይ ነው የተፈጸመው። እቅዱና ስኬቱ በትርጉም ሲለካ ጣሊያንን፤ እንግሊዝን፤ ፈረንሳይን፤ ቱርክን ፖረቹጋልን ቀደምት ሆነ ዛሬ አቅደው እያጠቁን ያሉትን ሁሉ ጠላቶቻችን ድል ያደረገ ምንም ብክነት ያልዞረበት ገድል ነው። ተፈታተሸን – ጣሊያን ዳግም ታሸ …. በአኽጉሩ። አሽከርነቱን የተቀበሉት ባንደዎችም አንገታቸው ተቀረቀረ፤ አንደበታቸው ተለሰነ።

ስለሆነም አጀንዳችን ከዚህ ገናና ገድል ይነሳል። አቅጣጫችን በዚህ ይመራል። ይዘከራል – ይወደሳል – ይከበራል። ለትውልዱ መንፈስ የሚስማማ፣ የሚጥን ፣የሚመችም ወርቅ በእጅ ገብቷል። ለመሆኑ መቼ ነው መኢህድንና አንድንት በጋራ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ አቅደው የሚያውቁት? ይህን ጥበብ መርምሩት። የጀግና እትብት በተቀበረበት ቦታ በዕለተ ሰንበት በሰባተኛው ቀን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በአኃቲ ድምጽ „ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል „ ሲሉ አረሙ ወያኔ ከመጣ የተወለዱ ታዳጊዎች፤ ወጣቶች ታሪክንንና ማንንትን ያከበረ የወል ፍላጎትን በቁርጠኝት ሃዲድ በመንፈስም ጄኔባና በባህርዳር፤ ባህርዳር በጄኔባ ቃል አሰሩ — ውል ተዋዋሉ ኢትዮጵያዊነት ታተመ በመንፈስ ማህጸን! የበቃ የተግባር አብነት ተፈጸመ። ይህንስ ሰው ሰራሽ ነው ትሉት ይሆን …. እነ እንቶ ፈንቶ? ….

መቋጫ። ሁለት የዳዊት ፍሬዎች የተከበሩ የወ/ሮ የህዝብአለም ሥዩምን ቃለ ምልልስ ከባህርዳር የተጠነቀረውን ቃለ ምልሱን እጅግ በሚገርም ፍጥነት ቃል በቃል በ አማርኛ ከአትላንታ ጋዜጠኛዳዊትተሰርቶ እንደዛ መቅረቡ እጅግ ያኮራል። እንዲህ ብንደጋገፍ እንዴት መንገዳችን ቅርብ፤ ተስፋችን በመዳፋችን ውስጥ ተደላድሎ በገባ በነበረ …. እኔ የሲዊዝን ዘገባ ፃፍኩ ፎቶውን አርቲስት ሚሊዮን ላከልኝ … እስኪ ይህን አምሮት በመሆን እናክብረው … እባካችሁ?!

ቆዬን በጀግናችን ዙሪያ። የሀገሬ ልጆች ጀግና ነፍሳችሁ ነው። ስለምን? እናንተም አጋጣሚውን ካገኛችሁ ጀግንነቱን በድርጊት ትጠልፉታላችሁና … አትርሱት ጀግናችን አቡነዘሰማያታችን – ድርሳናችን ይሁን! አቅም ያለን ሱባኤ ላይ ስለሆን እንሰበው … ኃይልዬን! ሱባኤ ላይ ባንሆንም እንደ እምነታችን ከልባችን ውስጥ ካላቸው ሙዳይ መስጥረን ቸር ወሬ እንዲያሰማን ፈጣሪያችን እንጠይቅ የሁሉ ጌታ ይሰማናል። ሲዊዝዬ በመሆኑ በግሌ ተመችቶኛል። እኔ በተረጋጋ መንፈስ ሐሤትን እዬጠበኩ ነው። „ቸር ተመኝ ቸር እንድታገኝ“ …. ከሁሉ በላይ ሲዊዝ ሁሉም እንዳሻው የሚፈልገውን የሚዝቅበት ሀገር ስላለሆነ „የተከደነ ሲሳያችን ይፈልቃል“

ብልህ – ቆረጠ
ስልትነን – ታጠቀ
ተባይ ተጣበቀ
ትእቢት ተወቀጠ
ትንቢት – ተመረጠ።

በጀግኖቻችን ከጠላት የሚነሱ ማናቸውም ወጀቦች ሁሉ በድል ይሰክናሉ!
ኢትዮጵያዊነት ከቀስት እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ልዩ አቅም ነው።
ፈተናን ከመፈጠሩ በፊት አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ኢትዮጵዊነት!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

በዳላስ የምትነዳው መኪና ከባቡር ጋር ተጋጭቶ ሕይወቷ ያለፈው ኢትዮጵያዊት ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈጸማል

$
0
0

melat mamo
(ዘ-ሐበሻ) በዳላስ ቴክሳስ ባለፈው ቅዳሜ ማርች 1 ቀን 2013 ዓ.ም የምትነዳው መኪና ከባቡር ጋር ተጋጭቶ ሕይወቷ ያለፈው ወጣቷ ኢትዮጵያዊት ሜላት ማሞ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ረፋዱ ላይ እንደሚፈጸም ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል።

ከባቡር ጋር ተጋጭታ ሕይወቷ የማለፉ ዜና በዘ-ሐበሻ ከተዘገበ በኋላ በዓለም የተለያዩ ክፍሎች ተሰራጭተው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሃዘናቸውን በስፋት ሲገልጹ የሰነበተ ሲሆን በዳላስም ኢትዮጵያውያኑ በከፍተኛ ሃዘን ላይ እንደሚገኙ የደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል። በጣም ተግባቢና ሃገር ወዳድ እንደነበረች የሚነገርላት ወጣቷ ሜላት ሕይወቷ በአሰቃቂ ሁኔታ ማለፉ ከተሰማ በኋላ ባለፈው እሁድ በዳላስ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ ም ዕመናን በለቅሶና በጸሎት አስበዋት ውለዋል።

የወጣት ሜላት ማሞ የቀብር ስነሥርዓት ዛሬ የሚፈጸም ሲሆን ከጠዋቱ በ10 ሰዓት በዳላስ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ ፍትሃት ስነስርዓት ከተካሄደ በኋላ ረፋዱ ላይ ከጠዋቱ 11 ሰዓት በሬስትላንድ የመቃብር ሥፍራ የቀብር ስነስርዓት ይደረጋል። ምናልባት በዳላስ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በቀብሩ ላይ መገኘት ከፈለጋችሁ አድራሻው፡ Restland Cemetary – 13005 Greenville Ave, Dallas, TX 75243 መሆኑን ዘ-ሐበሻ ከሥፍራው ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

ዘ-ሐበሻ የሜላት አደጋ እንደተሰማ የዘገበችውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ቀብሩ የሚደረግበት ቦታ ካርታው የሚከተለው ነው፦

13005 Greenville Ave Dallas, TX 75243 (Photo Credit Google Map)

13005 Greenville Ave Dallas, TX 75243 (Photo Credit Google Map)

የአፍሪካ መሪዎች ለምን ቶሎ ይሞታሉ? –በ6 ዓመት ውስጥ 10 የአፍሪካ መሪዎች ሞተዋል

$
0
0

meles zenawi
ቢቢሲ እንደጻፈው – አድማስ ሬዲዮ እንዳቀናበረው።

አንድ የአገር መሪ ፣ ገና በሥልጣን ላይ እያለ መሞቱ የተለመደ አይደለም። ነገር ግን ካለፈው 2008 ዓ.ም ወዲህ በዓለም ላይ 13 የአገር መሪዎች ገና ቢሯቸው እያሉ ሲሞቱ፣ ከዚያ ውስጥ 10 ያህሉ የአፍሪካ መሪዎች ናቸው። አፍሪካ ውስጥ መሪዎች ለምን ሥልጣን ላይ እያሉ ይሞታሉ?

በ 2012 ዓ.ም ብቻ አራት የአፍሪካ መሪዎች ቢሯቸው ውስጥ እያሉ ህይወታቸው አልፏል (የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የጋናው ፕሬዚዳንት፣ የማላዊ ፕሬዚዳንት፣ የጊኒ ቢሳዎ ፕሬዚዳንት) ። የመሪዎቹ ሞት ለጋዜጠኞች ደግሞ አዲስ የምርምር መንገድ ከፍቷል፣ – የአፍሪካ መሪዎች ለምን ቢሯቸው እንዳሉ ይሞታሉ?

“ሌሊት ስልክ ከተደወለልኝ፣ በቃ አንድ የአፍሪካ መሪ ሞቷል ማለት ነው ብዬ ማሰብ ጀምሬያለሁ” የሚለው የደቡብ አፍሪካው ዴይሊ ማቭሪክ ዜና አውታር ጋዜጠኛ ሲሞን ኤሊሰን ነው። እናም ይህን ጥያቄ ይዞ የትኛው መሪ በስንት ዓመቱ፣ በምን ምክንያት ሞተ? የሚለውን ምርምር ማድረጉን ቀጠለ።

ከ 2008 ወዲህ ብቻ 10 የአፍሪካ መሪዎች ሥልጣን ላይ እንዳሉ ህይወታቸው አልፏል። እነሱም ….
1- የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ፣ ዕድሜ 57 የሞት ምክንያት ድንገተኛ ኢንፌክሽን፣ የሞቱበት ወር ኦገስት 2012
2- የጋናው ፕሬዚዳንት ጆን አታ ሚልስ ፣ ዕድሜ 68፣ የሞት ምክንያት የጉሮሮ ካንሰር፣ የሞቱበት ወር ጁላይ 2012
3- የማላዊው ፕሬዚዳንት ቢንጉ ዋ ሙታሪካ ፣ ዕድሜ 78፣ የሞት ምክንያት ካርዲያክ አሬስት፣ የሞቱበት ወር ኤፕሪል 2012
4- የጊኒ ቢሳዎ ፕሬዚዳንት ኤም ቢ ሳኒሃ ፣ ዕድሜ 64፣ የሞት ምክንያት የቆየ በሽታ፣ ለረዥም ጊዜ ታመው ቆይተው። የሞቱበት ወር ጃንዋሪ 2012
5- የሊቢያው ፕሬዚዳንት ሙ አመር ጋዳፊ ፣ ዕድሜ 69፣ የሞት ምክንያት በአማጺዎች ተገድለው፣ የሞቱበር ወር ኦክቶበር 2011
6- የናይጄሪያው ፕሬዚዳትን ኦማሩ ያር አዱአ፣ ዕድሜ 58፣ የሞት ምክንያት የኩላሊትና የልብ ህመም፣ የሞቱበት ወር ሜይ 2010
7- የጋቦን ፕሬዚዳንት ኦማር ቦንጎ፣ ዕድሜ 73፣ የሞት ምክንያት የልብ ድካም፣ የሞቱበት ወር ጁን 2009
8- የጊኒ ቢሳዎ ፕሬዚዳንት ጄ ቢ ቪየራ፣ ዕድሜ 69፣ የሞቱበት ምክንያት ተገድለው፣ የሞተበር ወር ማርች 2009
9- የጊኒ ፕሬዚዳንት ላንሳና ኮንቴ፣ ዕድሜ 74፣ የሞቱበት ምክንያት እስካሁን አልተነገረም፣ የሞቱበር ወር 2008፣
10- የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሌቪ ማዋናዋሳ፣ ዕድሜ 59፣ የሞቱበት ምክንያት ስትሮክ፣ የሞቱበት ወር 2008

እንግዲህ ከየትኛውም የዓለማችን አህጉር በአፍሪካ ተቀማጭ ፕሬዚዳንቶች በብዛት ህይወታቸው አልፏል። ከአፍሪካ ውጭ፣ በተመሳሳይ ወቅት ህይወታቸው ያለፈው የዓለም መሪዎች ሶስት ብቻ ሲሆኑ እነሱም የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ታመው፣ የፖላንድ ፕሬዚዳንት ላች ካሲንኪ በአውሮፕላን አደጋ እና የባርባዶስ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ቶምሰን በካንሰር በሽታ ናቸው።

ከዝርዝሩ እንደሚታየው አፍሪካውያን መሪዎች ከሌሎቹ የዓለማችን አገሮች ይልቅ ዕድሜያቸው የገፋ ነው። ምናልባት አፍሪካውያን መሪዎቻቸው ሸምገል ያሉ እንዲሆኑ ይፈልጉ ይሆን? ሲል ይኸው ጋዜተኛ ሲሞን ኤሊሰን ይጠይቃል።

በዓለም ላይ ያሉ መሪዎችን ዕድሜ በአማካይ አውጥተን ስንመለከት፣ አፍሪካውያን ሸምገል ያሉ ሆነው ይገኛሉ። የዓለም መሪዎች በአህጉር ተከፋፍለው አማካይ ዕድሜያቸው ሲሰላ አፍሪካውያን መሪዎች በአማካይ ዕድሜያቸው 61፣ ኤዥያውያን 61፣ አውሮፓ 55፣ ሰሜን አሜሪካ 59፣ ደቡብ አሜሪካ 59፣ እንዲሁም አውስትራሊያ 58 ሆነው ተገኝተዋል።

በሌላ በኩል በአፍሪካ ለረዥም ጊዜ በህይወት የመቆየት መጠን (ላይፍ ኤክስፔታንሲ) አነስተኛ መሆኑ ይታወቃል። ይህም ከአህጉሪቱ የድህነት እና የበሽታ ታሪክ ጋር ይያያዛል። መሪዎች ሥልጣን ከያዙ በኋላ የተመቻቸ ኑሮ ቢኖራቸውም፣ ያደጉበት ህይወት በችግርና በሽታ የተጠቃ የድህነት ኑሮ ከሆነ እስከመጨረሻው ለረዥም ጊዜ የመቆየት ዕድላቸው ላይ ለውጥ እንደሚኖረው በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዘር ጉዳይ ጥናት ሃላፊ ዶክተር ጆርጅ ሌሰን ይናገራሉ። ስለዚህም አፍሪካውያን መሪዎች በጊዜ ህይወታቸው ቢያልፍ፣ ከአህጉሪቱ ችግር ጋር የተያያዘ ምክንያት ሊኖረው ይችላል ማለት ነው።

በ2009 ዓ.ም በተደረገው ጥናት የአፍሪካውያን አማካይ በህይወት የመኖርያ ዕድሜ 75 ሲሆን፣ የየአሜሪካውያን 82፣ የአውሮፓውያን 81፣ የፓስፊክ አገሮች 80፣ የ ኤዥያውያን 77 ነው። ስለዚህ የአፍሪካ መሪዎች በጊዜ ሞት ቢያጠቃቸው ላይገርም ይችላል።

እንግዲህ የአፍሪካ መሪዎች በሥልጣን ላይ እያሉ የመሞታቸው ነገር አዲስ ባይሆንም፣ ብዙዎቹ በህይወት እያሉ ያስተካከሉት ነገር ከሌለ ድንገት ሲሞቱ ሥልጣኑን ለመያዝ የሚደረግ ሽኩቻ በህዝቡና በአገሪቱ ላይ ችግር ይፈጥራል .. ሲሉ ተንታኞቹ ይናገራሉ።


[የኦሞ ወንዝ ጉዳይ] በግድቡ ሕይወታቸው የተገደበ ኢትዮጵያውያንን ለማትረፍ የሚደረገው እርብርብ –ከፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

Omo River

ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም

ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ከሁለት ዓመታት በፊት በዚህ በያዝነው ወር “ግድቡ እና አደጋው፡ ግልገል ጊቤ ሦስት በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ በደቡብ ኢትዮጵያ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ከሚካሄደው ልማት ጋር በተያያዘ መልኩ ግድቡ ሊያስከትል በሚችለው እንደምታ ላይ ትኩረት በማድረግ ትንታኔ አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትንታኔዬ በዚህ የልማት ሰበብ እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ በአካባቢው ስነምህዳር ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽእኖ እና ግድቡ በአካባቢው ለዘመናት ሰፍረው በሚኖሩት ህዝቦች ህይወት ላይ የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ከግምት ውስጥ በማስገባት በተለያዩ ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የአካባቢ ጥበቃ ድርጅቶች መንግስት ከዚህ ድርጊቱ እንዲታቀብ ድምጻቸውን ሲያሰሙ እኔም የሀሳቡ ተጋሪ በመሆን የነበረኝን ጥልቅ ስጋት በተደጋጋሚ አሰምቸ ነበር፡፡

ከዚህም በተጨማሪ “በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ያለውን ምቹ ያልሆነ ሁኔታ እና ተጋርጦ የሚታየውን የወደፊት አደጋ አስቀድመው ግንዛቤ በመውሰድ ታላላቆቹ ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቃቸውን በማስመልከት የነበረኝን ልዩ አድናቆት እና ምስጋና አቅርቤ ነበር፡፡“ በይበልጥም ደግሞ የዓለም አቀፍ ወንዞች/International Rivers፣ የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች/Human Rights Watch፣ የኦክላንድ ተቋም/Oakland Institute፣ የዓለም አቀፉ የኑሮ ዋስትና/Survival International፣ እና የአፍሪካ ሀብቶች የስራ ቡድን/the Africa Resources Working Group በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የአካባቢውን የተፈጥሮ ስነምህዳር ለመጠበቅ እና ለዘመናት ሰፍረው የኖሩትን ህዝቦች ህይወት ለመታደግ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ላይ ለመተግበር የተያዘው መጠነ ሰፊ ዕቅድ ወደ ተግባር እንዳይሸጋገር ባደረጓቸው እና አሁንም በማከናወን ላይ ባሏቸው ጉልህ እና አንጸባራቂ ተግባራት ላይ የተሰማኝን አድናቆት እና ጥልቅ የሆነ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ እነዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በግልገል ጊቤ ሦስት የሀይድሮኤሌክትሪክ ግድብ ግንባታ ምክንያት ህይወታቸው ለከፋ አደጋ ተጋልጦ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን/ት ህይወት ለመታደግ በሚደረገው የህይወት ማዳን እርብርብ ለዓመታት በመጀመሪያው ረድፍ ላይ በጽናት ተሰልፈው የሚገኙ ናቸው፡፡

የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የህዝቡን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ እና የቅስቀሳ ዘመቻዎችን በማካሄድ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ላይ ሊከሰት በሚችለው የከፋ የአካባቢ ስነምህዳር አደጋ ላይ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የጠራ አቋም እንዲይዝ በማድረግ እረገድ በርካታ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት በጥንቃቄ የተዘጋጁ ዘገባዎችን፣ የጥናት ውጤቶችን እና ዝርዝር የፖሊሲ ትንተናዎችን እንዲሁም ሌሎች ሳይንሳዊ እና አሀዛዊ ዘገባዎችን በማዘጋጀት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው ገዥው አካል በሚተገብራቸው “የልማት መርሀግብሮች” ሰበብ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ግራ እና ቀኝ ለዘመናት ሰፍሮ በሚኖረው ህዝብ የዕለት ከዕለት ኑሮ እና አጠቃላይ ህልውና ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ውጤት በሰነድ አስደግፈው አቅርበዋል፡፡ እነዚህ ዓለም አቀፍ የአካባቢ ስነምህዳር ጥበቃ እና የመብት ተሟጋች ድርጅቶች በጊቤ ሦስት የሀይድሮኤሌክትሪክ ግድብ ግንባታ አማካይነት በወንዙ ሸለቆ የሚገኙትን የተለያዩ ጎሳዎች መሬት በማይመጥን የኪራይ ተመን ሰበብ ገዥው አካል በመንጠቅ ለወጭ ገበያ ምርትነት የሚውሉ የስኳር እና ሩዝ ልማቶች ዘርፍ ተግባራዊ በማድረግ በሸለቆው ግራ እና ቀኝ ሰፍሮ ለዘመናት ሕይወቱን ሲመራ የኖረውን ህዝብ በግዳጅ “የመንደር ሰፈራ” (“villagization”) በሚል ከቀየው ለማፈናቀል እያደረገ ባለው ጭካኔ የተሞላበት አካሄድ ላይ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የጋራ ግንዛቤ እንዲጨብጥ እና የኗሪውን ህዝብ ተጠቃሚነት አሽቀንጥሮ የጣለው የስመ ልማት ከንቱ ሙከራ ተግባራዊ እንዳይሆን ለማስቆም እና ተጽዕኖ መፍጠር እንዲችል በመፈጋቻቸው ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2012 ባቀረብኩት ትችቴ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና የአካባቢ ስነምህዳር ጥበቃ ድርጅቶች እንዲሁም ቡድኖች በኦሞ ወንዝ ሸለቆ የልማት መርሁግብር ሰበብ ህልውናቸው ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጦ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን/ት ህይወት ለመታደግ ከልማት ሰለባው ህዝቦች ጎን በመሰለፍ ድርጊቱን በማውገዝ እና ለመቀልበስ እንዲቻል የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ባሉበት ወቅት እኛ ኢትዮጵያውያን/ት በተለይም ደግሞ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት እጃችንን አጣጥፈን ከዳር የመቆማችን እውነታ ለምን እንደሆነ በመጠየቅ ለዚህ አንገብጋቢ አደጋ ልዩ ትኩረት ባለመሰጠቱ ጉዳይ ላይ በማብሰልሰል የተሰማኝን ቅሬታ ለወገኖች በይፋ ገልጨ ነበር፡፡ እነዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ተቋማት እና ቡድኖች ለእኛ ብለው እንደዚህ ያለ ከባድ እና ቀጣይነት ያለው ስራ እያከናወኑ እያሉ እኛ ግን በጸጥታ እየተመለከትን ነው፡፡ በዚያን ጊዜ “ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና ከአካባቢ ስነምህዳር ጥበቃ ድርጅቶች ጋር በመቀላቀል ለአካባቢያችን ለመሟገት እራሳችን ንቁ ተሳታፊ በመሆን እገዛ እናድርግ በማለት ለኢትዮጵያውያን/ት ወገኖቸ ሁሉ የተማጽዕኖ ጥያቄ አቅርቤ ነበር፡፡” እንዲሁም “በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገው እና የተለያዩ ብዝሀ ህይወት ዝርያዎችን አካትቶ የያዘው የኢትዮጵያ ሀብት አሁን ላለው እና ለወደፊቱ ትውልድ ጠቀሜታ እንዲውል ክብካቤ እና ጥበቃ እንዲደረግለት የእራሳችንን የአካባቢ ጥበቃ ሲቪል ድርጅት እኛው ኢትዮጵያውያን/ት በተለይም የዲያስፖራው ማህበረሰብ እናቋቁም” የሚል የተማጽዕኖ ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ የሁኔታውን አሳሳቢነት በመገመትም እንዲህ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቸ ነበር፣ “ይህንን ማድረግ ካልቻልን በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ግራ ቀኝ በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ ግድቡ እያደረሰ ያለው አደጋ ዓይነት እጣ ፈንታ ውስጥ እራሳችንን ማግኘት እንደምንገደድ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡“

ያንን ትችት ጽፌ ካቀረብኩ ከሁለት ዓመታት በኋላም ቢሆን እስከ አሁን ድረስ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መበቶች እና የአካባቢ ስነምህዳር ጥበቃ ድርጅቶች ለእኛ ብለው ያንን ሁሉ እልህ አስጨራሽ ትግል እና ጥረት እንዲሁም የእኛን ወገኖች ህልውና ለመታደግ እርብርብ እያደረጉ ባሉበት ወቅት እኛ ከዳር ቆመን እየተመለከትን የመገኘታችንን ሁኔታ ሳስበው ለመቀበል በጣም ይቆጠቁጠኛል (በግልጽ ለመናገር ሀፍረት ይሰማኛል፡፡) እነዚህ ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ተመሳሳይ ጥያቄዎች ምንም ምላሽ ባይኖራቸውም ደግሜ ደጋግሜ እንዳነሳቸው እገደዳለሁ፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የአካባቢ ስነምህዳር ጥበቃ ድርጅቶች በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ላይ እየተካሄደ ላለው የከፋ አደጋ የሚያመጣ መርሀግበር መቀልበስ ለእኛ ሲሉ ሁሉንም እልህ አስጨራሽ ስራዎች እንዲሰሩ መጠበቅ በእውነቱ ፍትሀዊ ነውን? እነዚህ ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ለወጎኖቻችን እና ለሀገራችን ሲሉ ይህንን የመሰለ ጥንቃቄ እና ክብካቤ ሲያሳዩ እኛ የጉዳዩ ባለቤቶች ምንም ዓይነት ትኩረት ያልሰጠነው ለምን ይሆን?

ለወገኖቻችን ህልውና ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ከሚያሰሙት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የማንቀላቀል እና ድጋፍ የማናደርግላቸውስ ለምን ይሆን? ጨቋኙ ገዥ አካል የጭቃ ጅራፉን እያጮኸ በእነዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ ቅጥፈት የተሞላበት እና አሳፋሪ መግለጫ እየሰጠ መልካም ስራቸውን እና ስማቸውን ሲያጠለሽ ለምንድን ነው ወደ እነዚህ ድርጅቶች በመጠጋት የማናግዛቸው እና የማንከላከልላቸው? ተመሳሳይ የአካባቢ ስነምህዳር ጥበቃ ወንጀሎች እና የሰዎችን ሰብአዊ መብቶች የመደፍጠጥ ወንጀሎች በስመ “ልማት” ሰበብ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ቢፈጸሙ ኖሮ በእውነት ግድየለሾች እና በዝምታ የምንመለከተው ይሆን ነበርን? በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ግራ እና ቀኝ የሚኖሩ ወገኖቻችን የተገለሉ አናሳ ጎሳዎች በመሆናቸው ብቻ ለእነርሱ መብቶች መደፍጠጥ ግድየለሾች መሆን ይኖርብናልን? በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ግራ እና ቀኝ የሚኖሩ ወገኖቻችን እንደሌሎቻችን ሁሉ “ዘመናዊነትን” የተላበሱ ባለመምሰላቸው በእነርሱ አፍረንባቸው ወይም ደግሞ በቅርቡ ያረፉት አቶ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት የእነዚህ ህዝቦች አኗኗር “ኋላቀር ስልጣኔ“ ነው በማለት በግልጽ እንደፈረጇቸው ቆጥረነው ሊሆን ይችል ይሆን? በምን ዓይነት ሁኔታ ነው እረፍት በሌላቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከፍተኛ ተጋድሎ አማካይነት በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ግራ እና ቀኝ ለሚኖረው ህዝብ የተገኘ የአካባቢ ክብካቤ እና ጥበቃ ቅርስ ነው እናም ኑ ተረከቡን ብለን የወደፊቱን ትውልዶች ለማሳምን የምንሞክረው? ውድ አንባቢዎች በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ በአንክሮ እንድታስቡ እጠይቃለሁ፡፡

እኛን እየረዱን ያሉትን ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቢያንስ በገንዘብ ልናግዛቸው የሚገባ መሆኑ ፍትሀዊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ግራ እና ቀኝ ለሚኖሩት ወገኖቻችን ሰብአዊ መብት ጥበቃ ይህን ያህል ተጋድሎ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ እኛ ድጋፋችንን በተጨባጭ ሁኔታ ለወገኖቻችን የማናሳይበት ምክንያት ሊኖር አይችልም፡፡ ከእነርሱ ጋር በጋራ መቆም ይገባናል እናም ከዳር ቆመን የእነርሱ ተመልካች መሆን አይኖርብንም፡፡

የግልገል ጊቤ ሦስት ግድብ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ግራ እና ቀኝ በሚኖሩ ህዝቦች ላይ የሚያስከትለው ግልጽ እና ወቅታዊ አደጋ፣

የጊቤ ሦስት ግድብ ግንባታ በአሁኑ ወቅት በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ግራ እና ቀኝ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ወገኖቻችን ማለትም በቦዲ፣ ካሮ፣ ሙጉጂ፣ ሙርሲ፣ ኒያንጋቶም እና ዳሰነች ከብዙዎች ጥቂቶቹ ሲሆኑ ለሺህ ዓመታት “ባህረ ሸሽ ግብርና” እየተባለ የሚጠራውን የግብርና ስራ በመስራት ህይወታቸውን ሲመሩ በኖሩት ላይ ግልጽ ወቅታዊ አደጋ አንዣቦ ይገኛል፡፡ የዝናብ ወራት ከተጠናቀቁ በኋላ ውኃው ሲሸሽ በወንዙ ዳርቻዎች አካባቢ ተሸፍኖ የነበረው መሬት ለም የሆነ ደለል በርካታ የአዝዕርት ዓይነቶችን ማለትም ማሽላ፣ በቆሎ እና ባቄላ ለማምረት ያስችላል፡፡ የእነዚህ ኢትዮጵያውያን ህልውና የተመሰረተው በየጊዜው በሚለዋወጡት የጎርፍ ወቅቶች አማካይነት ነው፡፡ የጊቤ ሦስት ግድብ የወንዙ የላይኛው ክፍል ወደ ውጭ አገር ለሚላክ የኤሌክትሪክ ምርት ማመንጫነት ሲባል በሚገደብበት ጊዜ ወንዙ በሸለቆው ውስጥ የሚያደርገውን የተፈጥሮ የውኃ ፍሰት መጠን በመሰረታዊ መልኩ ያናጋዋል፡፡ ወደግድቡ ማጠራቀሚያ እና ለስኳር ልማት የመስኖ ስራ ለሚውለው ውኃ ፍጆታ ሲባል የውኃው የፍሰት አቅጣጫ ሲቀየር አጠቃላይ የኦሞ ወንዝ የውኃ መጠን ዘለቄታዊ ባለው ሁኔታ በእጅጉ እንደሚቀንስ በመስኩ የተሰማሩ ባለሙያዎች አሳማኝ በሆነ መልኩ ሞግተዋል፡፡

በዚህም ምክንያት በሸለቆው ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች በእርግጠኝነት ባህረ ሸሽ እየተባለ የሚጠራውን የግብርና ዘይቤ ለማካሄድ አይችሉም፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 በዓለም ዕውቅናን ያተረፉት የተፈጥሮ ሀብት ክብካቤ እና ጥንታዊ የሰው ዘር ተመራማሪ የሆኑት ባለሙያ ዶ/ር ሪቻርድ ሊኬይ የጊቤ ሦስት ግድብ ግንባታ የግል ጥቅም ማሳደጃ “ሳይንሳዊ” ጥናት በስነምህዳሩ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን ውጤቶች አሳንሶ የሚያይ መሆኑን የምር በመሞገት “ግድቡ በርካታ የሆኑ አሉታዊ ውጤቶችን እንደሚያስከትል እንዲያውም አንዳንዶቹ በሁለቱም በኩል ማለትም በአካባቢው ስነምህዳር እና ለዘመናት ህይወቱን በዚህ ወንዝ የታችኛው ክፍል ላይ መስርቶ ለሚኖረው ማህበረሰብ ህይወት ውድመት እና ዕልቂት“ ሊሆን እንደሚችል አስረግጠው ተንብየዋል፡፡

የኦሞን ወንዝ “ማልማት”፣

እ.ኤ.አ በ2011 መጨረሻ አካባቢ አቶ መለስ ዜናዊ በደቡብ ኦሞ ዞን በጅንካ ከተማ በመገኘት ንግግር አድርገው ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ አቶ መለስ ረዥም እና የማስመሰያ፣ እንዲሁም ጠንከር ያለ እና እብሪት የተሞላበት ንግግር ነበር ያደረጉት፡፡ “በኋላ ቀር ስልጣኔ” ተተብትበው የሚገኙት ላሏቸው በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ግራ እና ቀኝ ለሚኖሩ ህዝቦች ከሰማይ መና እንደሚያወርዱላቸው ነበር ቃል የገቡት፡፡ እነዚህን ህዝቦች ከድንጋይ ዘመን መንጥቀው በማውጣት ወደ ስልጣኔው ዘመን በእልልታ በማምጣት “የፈጣን ልማት ምሳሌ” እንደሚያደርጓቸው ምለው ተገዝተው ነበር፡፡ እንዲህ በማለት ነበር ለማህበረሰቡ የመተማመኛ ንግግር ያደረጉት፣ “በኦሞ ወንዝ የሚገነባው ግድብ የጎርፍ አደጋውን ያስወግድላችኋል፣ ግዙፍ የሆነ የመስኖ ልማት ስርዓት ይዘረጋል፣ እናም ከቦታ ቦታ የምትዘዋወሩት የማህበረሰብ አባላት (pastoralists) ዘለቄታዊ የሆነ ገቢ ያስገኝላችኋል፣ እንዲሁም ደግሞ ዘመናዊ ህይወት ትኖራላችሁ”::

ለጊቤ ሦስት ግድብ ግንባታ ሂደት ጥንቃቄ እና ትኩረት በመስጠት እንዲከናወን እና ለዘመናት በኦሞ ሸለቆ ግራ እና ቀኝ ኑሮውን በመግፋት ላይ የሚገኘውን ህዝብ የህይወት ዘይቤ እና ባህል በጠበቀ መልኩ የልማት ስራው እንዲከናወን ተማዕጽኗቸውን ላቀረቡ ዓለም አቀፍ የአካባቢ ስነምህዳር ጥበቃ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አቶ መለስ በአጻፋው ጥላቻ በተሞላበት መልኩ ስራቸውን ስማቸውን በማጠልሸት እና በነገር በመሸንቆጥ የአቅማቸውን ያህል ተግትገዋቸዋል፡፡ እነዚህን ዓለም አቀፍ ድርጅቶች “ወንዞቻችንን የመጠቀም ነጻነታችንን ለመገደብ እና ህዝቦቻችንን ከድህነት እንዳናወጣ“ ሁልጊዜ ለተቃውሞ የተዘጋጁ እና እልቂት ናፋቂ ሟርተኞች ናቸው በማለት ፈርጀዋቸዋል፡፡ እንዲሁም አደገኛ የልማት አደናቃፊዎች የሚል ታርጋ ለጥፈውላቸዋል፡፡ እንዲህ በማለትም አክለውላቸዋል፣ “ግዙፍ የሆነ ፕሮፓጋንዳ በመፍጠር ላይ ናቸው… የልማት ፕሮጀክቶቻችንን እንዳናጠናቅቅ ከውጭ የገንዘብ ብድሮችን እንዳናገኝ መሰናክል በመፍጠር ላይ ናቸው፡፡“ እንዲህ ሲሉም ተሳልቀውባቸዋል፣ “የኋላቀርነት እና የድህነት ሁነኛ ጓደኞች…በእርግጥ ምንም ዓይነት ተጨባጭነት ያለው ነገር የማይሰሩ” ብለዋቸዋል፡፡ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ለእራሳቸው ጥቅም ብቻ የቆሙ ዘረኞች ብለዋቸዋል፣ ምክንያቱም ይላሉ፣ “ሁሉም እንዲሆን የሚፈልጉት ነገር እነዚህ ዘላኖች የቱሪስት መስህብ ሆነው እንዲቀሩ ነው፡፡“ እናም የኦሞ ወንዝ ሸለቆ ህዝቦች፣ “ለሳይንቲስቶች እና ለተመራማሪዎች ለጥንታዊ የሰዎች የአኗኗር ዘይቤ የተናጠል ጥናት“ ማድረጊያ ማዕከል ሆነው እንዲቀሩ ለማድረግ አስበው ነው ብለዋል፡፡

አቶ መለስ እና ሎሌዎቻቸው ከዚህ ቀደም የተደረገውን እና በአሁኑ ጊዜም በጊቤ ሦስት ግድብ እና ሸለቆውን “ለማልማት” በሚል ሰበብ እየተደረገ ያለውን የአካባቢ ውድመት ለመደበቅ ብዙ ርቀቶችን ተጉዘዋል፡፡ እ.ኤ.አ በጁላይ 2008 በግድቡ ላይ የግንባታ ስራ ከተጀመረ ከሁለት ዓመታት በኋላ እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና የአካባቢ ስነምህዳር ጥበቃ ድርጅቶች ዓለም እንዲገነዘብ ደወሉን ማሰማት ከጀመሩ በኋላ አቶ መለስ “የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን መስሪያ ቤታቸው” የጊቤ ሦስትን ፕሮጀክት የአካባቢ ስነምህዳር እና ማህበራዊ እንደምታ ጥናት አሳትመው እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ ያ የጥናት ዘገባ ለማስመሰያነት የአቶ መለስን የማይቀየር ጽኑ ውሳኔ ህጋዊ በማስመሰል ወዲያውኑ በህገወጥ መልክ የፕሮጀክቱን የወደፊት ስራ ለማስቀጠል የተደረገ አሳፋሪ ክንውን ነበር፡፡ ያ ዘገባ ዓይን ያወጡ ቅጥፈቶች የታጨቁበት ነበር፡፡ የጊቤ ሦስት ግድብ የውኃ ማጠራቀሚያ አካባቢ ለሰው ልጅ መኖሪያነት ምቹ አይደለም፣ ምክንያቱም ገዳይ በሆኑት የወባ ትንኝ እና የቆላ ዝንቦች/tsetse flies (“ለእንቅልፍ በሽታ” የሚዳርጉ) ተህዋስያን የተወረረ አካባቢ መሆኑን ሀፍረተቢስ በሆነ መልኩ ያቀረበ ዘገባ ነበር፡፡

ዘገባው እንዲህ ይላል፣ “ወደፊት በግድቡ የውኃ ማጠራቀሚያ አካባቢ ምንም ዓይነት ሰፈራ አይኖርም፣ እናም ሰፈራዎች የሚኖሩት በላይኛው ከፍታ ቦታዎች ከሸለቆው ውጭ በሆኑ አካባቢዎች ብቻ ነው… በታችኛው የኦሞ ወንዝ ሸለቆ የመጨረሻ ጠርዝ አካባቢ መሬቶች ላይ በጣም ውስን የሆነ የእርሻ ስራ አለ… በመርሀግበሩ በተያዘው ግድብ ዙሪያ የሚኖረው ህዝብ እና በውኃ ማጠራቀሚያው መካከል ያለው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት/UNESCO ከያዘው የባህል ቅርስ ቦታ በቅርብ ርቀት የሚገኙ አይደሉም፡፡ በግድቡ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ሳይንሳዊ፣ ባህላዊ፣ የዘር እና የታሪክ ጠቀሜታ ያላቸው በግልጽ የሚታዩ ቅሬተ አካሎች የሉም፡፡“

የአቶ መለስ የኦሞ ወንዝ ሸለቆን “ኋላቀርነት” ወደ “ዘመናዊነት” ኑሮ የመቀየር ዘይቤ ሸለቆውን ለሳውዲ አረቢያ እና ለሌሎች የውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች እና ለጓደኞቻቸው ለማዛወር የታቀደ ነበር፡፡ አቶ መለስ በንግግራቸው በመቀጠል “መንግስት ዕቅድ ያወጣል፣ እናም 150,000 ሄክታር የስኳር አገዳ ልማት ከዚህ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ያደርጋል“ በማለት መንግስታቸው ጠንክሮ እንደሚሰራ ገልጸው ነበር፡፡ በእርግጠኝነት እንደ አይሲ/IC የተባለው መጽሔት ከሆነ “የሳውዲ አረቢያው ባለሀብት አልሙዲ በከፍተኛ ደረጃ ካሉት የመንግስት አመራሮች ጋር ጥብቅ የግንኙነት ትስስር ስላለው ለሩዝ ምርት የሚሆን 10,000 ሄክታር መሬት ተሸንሽኖ ተሰጥቶታል፡፡“ የእርሱ ግዙፍ ፕሮጀክት በአካባቢው ስነምህዳር ማለትም በብሄራዊ ፓርኩ እና በዱር እንስሳት መጠለያ ላይ እንዲሁም ለዘመናት በአካባቢው ሲኖሩ በነበሩ ትውልዶች ማህበረሰብ አባላት ላይ ታላቅ ጉዳትን አስከትሏል፡፡”

አቶ መለስ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ በኦሞ ኩራዝ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ስር አምስት የስኳር ፋብሪካዎች ይቋቋማሉ በማለት ተናግረው ነበር፡፡ እንደ “ኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት” ከሆነ “መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ/Mesfin Industrial Industry (MIE) የተባለው ድርጅት በአማራ ክልል ከሚገኘው ጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ልማት ፕሮጀክት እና በኦሞ ሸለቆ ከሚገኘው ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከሚባሉ መንግስታዊ ድርጅቶች ጋር የብር 3 ቢሊዮን (162.2 ሚሊዮን ዶላር) የሚያወጣ ዋጋ ያላቸው ማሽነሪዎችን ለማቅረብ የስምምነት ውል ተፈራርሟል…“ መስፍን ኢንዱስተሪያል ኢንጅነሪንግ “ከድሬዳዋ እስከ አዲስ አበባ ለሚዘረጋው የባቡር መስመር ግንባታ ፕሮጀክት እና በተመሳሳይ መልኩ ከጅቡቲ በአፋር በኩል አድርጎ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ለሚዘረጋው የባቡር መስመር አገልግሎት የሚውሉ የባቡር ሃዲዶችን የመዘርጋት የማጠናቀቅ ስራ ያከናውናል፡፡“
እ.ኤ.አ በጁን 2011 “የጊቤ ሦስት ግድብ በቱርካና ሐይቅ ላይ ጉልህ የሆነ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል አስተማማኝ ያልሆነ የውኃ መጠን በመልቀቅ በውኃ ውስጥ ያሉ ህይወት ያላቸው ዝርያዎችን እና ከእርሱ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የስነሕይወት ስርዓቶች ለአደጋ እንደሚጥል“ እናም “በኢትዮጵያ ያለው መንግስት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በሌላ መንግስት ግዛት ውስጥ የተመለከተን ባህላዊ ቅርስ ከጉዳት ላይ ላለመጣል በጊቤ ሦስት ላይ የጀመረውን የግንባታ ስራ በአስቸኳይ እንዲያቆም“ በማለት የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት/UNESCO ከድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡

በአቶ መለስ “የልማት” ዕቅዶች በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ግራ እና ቀኝ የሚኖረው በድህነት የሚማቅቀው እና ተከላካይ የሌለው ህዝብ ፍትሐዊነት በጎደለው መልኩ ግፍ የተፈጸመበት ሲሆን የእርሳቸው ሞራለቢስ ጓደኞች ግን የናጠጡ ሞራለቢስ ሀብታሞች ሆነዋል፡፡ እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 2014 የታተመ አንድ የአካባቢ ምህዳር ጥናት ከሆነ “የኩራዝ ስኳር ልማት (161,285 ሄክታር መሬት ይሸፍናል ተብሎ ይገመታል) ግንባታ እና ከዚህ ጋር የተያያዙ የመሰረተ ልማት ስራዎች የስኳር ማምረቻ መሳሪያዎችን ጨምሮ እና በመንደር የማሰባሰብ ስራዎች የጊቤ ሦስት ግድብ ከመጠናቀቁ በፊት ቀደም ሲል የተጀመሩ ስራዎች ናቸው፡፡ የኩራዝ ስኳር ልማት እና ሌላ ተጨማሪ ለሸንኮራ አገዳው ልማት እርሻ አገልግሎት ምቹ የሆነ የተጠና መሬት (47,370 ሄክታር) እንደ መስኖው ሀብትን በአግባቡ የመጠቀም ባህሪ በእርግጠኝነት የኦሞ ወንዝን 50 በመቶ የውኃ ፍሰት ይፈልጋል፡፡“

የአቶ መለስ የኦሞ ወንዝ ሸለቆ “ስልጣኔ” መርሀግብር ለጓደኞቻቸው ነፋስ አመጣሽ ዘረፋ ነው፣ ሆኖም ግን የኦሞ ወንዝ ሸለቆን ኗሪ ህዝቦች ያነጠፈ እና ያደረቀ ዕቅድ ነው፡፡ የአቶ መለስ ስለኦሞ ወንዝ ሸለቆ እና ህዝብ ራዕይ “ለሳውዲ አረቢያው ባለሀብት ለአላሙዲ እና ለመስፍንኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ ጥሩ የሆነ ነገር ሁሉ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ህልውናቸውን መስርተው ለሚኖሩ ህዝቦችም ጥሩ ነው“ በሚል ዕይታ ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ ለዚህም ነው በኦሞ ወንዝ ሸለቆ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ለስግብግብነት እና ከሀዲነት ዓላማ መጠቀሚያ እየሆኑ ያሉት!

የኦሞን ወንዝ እና የኗሪውን ህዝብ ህልውና ለመታደግ ቀጣይ እርብርብ፣

ባለፈው ሳምንት ዓለም አቀፋዊ ወንዞች/International Rivers የተባለው ድርጅት በለቀቀው የቪዲዮ መልዕክት መሰረት ግድቡ እና የመከነው ያልታሰበበት “የልማት” ፕሮጀክት ተብሎ የቀረበው ዕቅድ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው ገዥው አካል እንደገና ካላሰበበት እና ካልተቋረጠ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ የሚያስከትለው ከፍተኛ ስጋት እና በሸለቆው ግራ እና ቀኝ በሚኖረው ህዝብ እና ስነምህዳር ላይ ሊቀለበስ የማይችል አደጋ እንደሚያስከትል አስጠንቅቋል፡፡ ቪዲዮው በአሁኑ ጊዜ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ላይ የተጋረጠውን አደጋ በግልጽ የሚያሳይ ስለሆነ መመልከቱ ጠቃሚነት አለው፡፡

የጊቤ ሦስት ግድብ ግንባታ እና ለመስኖ ስራ ተብሎ የኦሞን ወንዝ ውኃ አቅጣጫ ማስቀየስ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሰሜን ኬንያ በሚኖሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦች ህልውና ላይ ግልጽ እና ከፍተኛ የሆነ አደጋን ሊያስከትል እንደሚችል ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የወንዙን የተፈጥሮ የውኃ ፍሰት ኡደት ማቋረጥ ማለት ከዓለም በትልቅነቱ ከፍተኛ የሆነው የቱርካና የበረሀ ሐይቅን ህልውናው አድርጎ የተመሰረተው የእርሻ፣ የግጦሽ መሬት፣ እስከ ቱርካና ሐይቅ ድረስ በወንዙ ዳርቻ የሚገኘው የዓሳ ሀብት ሁሉ እንዳለ ይወድማል፡፡ ግድቡ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ እና በቱርካና ሐይቅ ሁለቱም በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት/UNESCO የዓለም የልዩ የባህል እና ስነምድር ቅርስነት የተመዘገቡትን ሀብቶች ሙሉ በሙሉ ያጠፋል፡፡

“የጊቤ ሦስት ግድብ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት/UNESCO በዓለም የቅርስነት መዘገብ የሰፈረውን ቦታ፣ ለ300,000 ተጨማሪ ህዝብ ህልውና መሰረት የሆነውን እና እስከ ቱርካና ሐይቅ ድረስ የተዘረጋውን እንዲሁም፣ 90 በመቶ የሚሆነውን የውኃ ፍላጎቱን የሚያገኘው ከኦሞ ወንዝ የሆነውን” የተፈጥሮ ስነምህዳ በቋፍ ላይ ሊጥለው እንደሚችል የመስኩ ባለሙያዎች ያላቸውን ስጋት ይገልጻሉ፡፡

በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ሊደርስ የሚችለውን የአካባቢያዊ ስነምህዳር አደጋ መጠን እና በግድቡ መሰራት ምክንያት በሰው ላይ የሚደርሰውን ኪሳራ ኢትዮጵያውያን/ት ሁሉ እንዲገነዘቡት ማድረግ ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ አለው፡፡ በተለይም ኢትዮጵያውያን አንባቢዎቸ የዓለም አቀፍ ወንዞች ቪዲዮንን ( የአማርኛውን ትርጉም አዚህ ይጫኑ ወይም http://www.internationalrivers.org/amharic-video-translation-omo-cascade ) አንድትመለከቱት እጠይቃለሁ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ/USAID እና በኢትዮጵያ የለጋሽ ድርጅቶች እገዛ ቡድን/Donors Assistance Group (በኦሞ ወንዝ ሸለቆ የሚኖረውን ህዝብ ህልውና ከአደጋ ለመታደግ ከሚደረገው እርብርብ ጋር በተያያዘ መልኩ “ምንም ዓይነት መከራ የማይታያቸው፣ ምንም ዓይነት ስቃይ የማይሰማቸው፣ ስለምንም ዓይነት መከራ የማይናገሩ” ሆኖም ግን ለህዝብ መብት እና እድገት የቆሙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ናቸው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) እና የ26 አገሮች ስብስብ የሆነው በኢትዮጵያ የለጋሽ ድርጅቶች እገዛ ቡድን (DAG) ከኦሞ ወንዝ ሸለቆ ጋር በተያያዘ መልኩ በኗሪው ህዝብ ላይ በሚፈጸሙት የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች ከሚነሱ ጥያቄዎች ጋር ላለመተባበር ጆሮ ዳባ ብለው ተቀምጠዋል፡፡ በጨዋ አነጋገር እነዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚያራምዷቸው አቋሞች በሚከተለው መልክ ሊመሰሉ ይችላሉ፣ “ምንም ዓይነት መከራ አላየንም፣ ምንም ዓይነት ስቃይ አልሰማንም፣ እናም በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ምንም ዓይነት የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ የለም፡፡“
እ.ኤ.አ ኦክቶበር 2010 በዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በሂዩማን ራይትስ ዎች/HRW በኢትዮጵያ እርዳታ ለሰብአዊ መብት ድፍጠጣ መዋል የሚለው ዘገባ ከመውጣቱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) እና በኢትዮጵያ የለጋሽ ድርጅቶች እገዛ ቡድን (DAG) በሰብአዊ መብት ድርጅቱ “በኢትዮጵያ የተስፋፋው ስልታዊ ሙስና በልማት እርዳታ“ በሚል የወጣውን ዘገባ በመካድ እንዲህ የሚል መግለጫ አውጥተው ነበር፣ “የእኛ ጥናት ምንም ዓይነት ሙስናን የሚያመላክት ስልታዊ ወይም የተስፋፋ ሙስና መረጃ አላገኘንም፡፡“ እ.ኤ.አ በ2012 የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) የሚከተለውን ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “ደቡብ ኦሞን በጎበኘሁበት ወቅት [የሰብአዊ መብት ረገጣን] የሚያጠናክር ምንም ዓይነት መረጃ አላገኘሁም፡፡“ እ.ኤ.አ ጃኗሪ 17፣ 2014 በተጻፈ ደብዳቤ የዩኤስኤአይዲ/USAID በኢትዮጵያ የአሁኑ ተልዕኮ ዳይሬክተር ዴኒስ ዌለር ድርጅታቸው እና ሌሎችን በሚመለከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ድርጅቴ እና ሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች በጋራ ሆነን በደቡብ ኦሞ ያለውን ሁኔታ ስንከታተል ነበር“ እናም “ከእነዚህ ጉዞዎች የተገኘው ዋና ግኝት የሚያመለክተው ምንም ዓይነት የተስፋፋ ወይም ስልታዊ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዘገባ አልተገኘም፡፡ የእኛ ምልከታዎች ቀደም ሲል በአጽንኦ ሲባሉ እና ሲነገሩ የነበሩትን…ማለትም በሰፈራ የማሰባሰብ ሂደቶች በስልታዊ እና በተስፋፋ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች የታጀቡ ናቸው የሚባለውን ነገር የሚደግፉ ሆነው አልተገኙም፡፡“

የሚገርመው ነገር ግን በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ኗሪ ህዝቦች ላይ የተፈጸሙት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደሌሉ የዌለር ትችቶች ያጣጣሉትን ከእርሳቸው ቀደም ብለው በእርሳቸው ቦታ ከነበሩት ከቶማስ ስታል አስተያየቶች ጋር ፍጹም በተቃራኒው መሆናቸው ነው፡፡ ከኢትዮጵያ በእራሳቸው ፈቃድ ወደ ባግዳዳድ ለመሄድ ከመነሳታቸው በፊት እ.ኤ.አ በኦክቶበር 2010 ቃለመጠይቅ የተደረገላቸው ስታል እንዲህ የሚል ትኩረትን የሚስብ የእምነት ቃል ሰጥተው ነበር፣ “የፖለቲካ ተሳትፎን በሚመለከት ጥሩ ስራ አልሰራንም፡፡ በተለይም ከሁለት ዓመታት በፊት የተካሄደውን ምርጫ በሚመለከት ዴሞክራሲን ለማስፋፋት ምንም ብዙ የሰራነው ነገር የለም…ይህ ደረቅ እውነታ ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጎናል፡፡“ ለዌለር ግን በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ኗሪዎች ላይ የሚካሄደው የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ “ተስፋ የሚያስቆርጥበት” ምንም ዓይነት ምክንያት አይኖርም!

በኦሞ ወንዝ ሸለቆ በሚኖረው ህዝብ የሚካሄደውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) እና በኢትዮጵያ የለጋሽ ድርጅቶች እገዛ ቡድን (DAG) ይፋ አቋም በሁለት ሀሳቦች ሊጠቃለል ይችላል፣ 1ኛ) በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና የአካባቢ ስነምህዳር ጥበቃ ተሟጋች ድርጅቶች በግድ ስለማፈናቀል፣ ስለመንደር ምስረታ፣ ስለሰፈራ ፕሮግራም፣ ለህልውና የሚሆንን መሬት ስለመነጠቅ፣ ድብደባዎች፣ ግድያዎች፣ አስገድዶ መድፈር፣ እስራት፣ ማስፈራራት፣ የፖለቲካ ጭቆና እና የመንግስት እገዛ ያለማድረግ የሚወጡ ዘገባዎች ሁሉም አስመሳይ ፍብረካዎች እና ተራ ቅጥፈቶች ናቸው፡፡ 2ኛ) ዘገባዎቹ ትክክለኛ ቢሆኑም እንኳ የተዘጋጁት በተበጣጠሱ እና የሁለተኛ የመረጃ ምንጭን መሰረት አድርገው ስለሆነ “ለስልታዊ እና የተስፋፉ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች“ ተጨማሪ ግብዓት ሆነዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) በኢትዮጵያ “ስልታዊ እና የተስፋፉ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች“ እንደሌሉ መካዱ ማንንም ሊያስደንቅ አይችልም፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) ለዓመታት “ለስልታዊ እና የተስፋፉ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች“ የሚለውን እውነታ እንደ ባዶ ሀረግ በመቁጠር ሀቅን በመሸፋፈን ከለላ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 አቶ መለስ ፓርቲያቸው በ99.6 በመቶ በፓርላሜንታዊ ምርጫ ድል ተጎናጸፍኩ ብለው ሲያውጁ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) ምንም ዓይነት “ለስልታዊ እና የተስፋፉ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች“ የመብት ጥሰቶች አላገኘም፣ አላየም፣ አልሰማምም፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ በጋምቤላ እና በኦጋዴን አካባቢዎች በሰው ልጅ ዕልቂት ወንጀል በፈጸሙበት ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) የሚለውን የተከበረ መጠሪያ ስሙን እራሱ ወደ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ ክህደት (USA In Denial) በሚል ስያሜ ቀይሮታል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተሟጋቾች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የፍትሀዊነት አመጸኞች፣ የድረገጽ አዘጋጆች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በጅምላ ለእስር ወደ ዘብጥያ ሲጣሉ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) ምላሽ “ስልታዊ እና የተስፋፉ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች“ የሉም የሚል ነበር፡፡ ምንም! ጭራሽ! በፍጹም! “የተስፋፉ እና ስልታዊ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች“ ማለት በእርግጠኝነት ምን ማለት ነው? የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) “ነጠላ ሞት አሰቃቂ ነው፣ የሚሊዮኖች ሞት ግን ለቁጥር ያህል ነው“ ለማለት ፍልጎ ነውን? ምናልባትም ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) በኦሞ ወንዝ ሸለቆ የአንድ ሰው ሰብአዊ መብት መደፍጠጥ አሰቃቂ ነው፣ ነገር ግን በኦሞ ወንዝ ሸለቆ የሚኖረው የጠቅላላው ህዝብ ሰብአዊ መብት መደፍጠጥ ለቁጥር ነውን?!

እውነታው ግን የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) እና ሌሎች እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 2012 የኦሞን አካባቢ የጎበኙት ሰዎች በግዳጅ “በተለያዩ የታችኛው ኦሞ ማህበረሰብ የተደረጉትን የቪዲዮ ቃለመጠይቅ ቅጂዎች“ እንዲሰጣቸው ተደርጓል፡፡ እነዚህ ቅጅዎች “ለጥርጣሬ ቦታ አይሰጡም፣ ለጋሽ ድርጅቶች ለሰብአዊ መብት ጥሰት በጣም አስተማማኝ የሆነ የመጀመሪያ የመረጃ ምንጭ አድርገው ስለወሰዱት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያ (USAID) እና በኢትዮጵያ የለጋሽ ድርጅቶች እገዛ ቡድን (DAG) የመስክ ጉብኝ አድርገው“ ካጠናቀቁ በኋላ ጉዳዩን ችላ እንዲሉት አስችሏል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ የሚኖሩ ህዝቦችን ህልውና ለመታደግ ከሚደረገው እርብርብ ጋር ተቀላቅሏል፣

እ.ኤ.አ በጁላይ 2013 ሴናተር ፓትሪክ ሊሂ (ዲ ቬርሞንት) በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ እርዳታ አስተዳደር ላይ የተወሰኑ ማብራሪያዎች በሴኔት ቢል 1372 ላይ እንዲጨመር አድርገዋል፡፡ የሊሂ ማብራሪያ “በ2014 የተጠናከረው የድርጊት መርሀግብር“ እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 3፣ 2014 ሁለቱንም ምክር ቤቶች በመዝለል በሰነድ ላይ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ የሰነዱ ክፍል የሆነው ቁጥር 7042 (d) የድርጊት መርሀግብሩ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የመንግስት ጽ/ቤት “በድርጊት መርሀግብሩ ኮሚቴ አማካይነት የኢትዮጵያ መንግስት 1ኛ) የፍትህ ነጻነት፣ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ፣ በነጻ የመደራጀት መብት፣የመሰብሰብ እና የእምነት ነጻነት፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መብቶች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ጋዜጠኞች ያለምንም መሸማቀቅ ወይም ጣልቃገብነት እና የህግ የበላይነት መንቀሳቀስ የሚችሉ መሆናቸውን፣ 2ኛ) የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና የሰብአዊ እርዳታ በኢትዮጵያ ወደ ሶማሊ ክልል እየገቡ መጎብኘት እንዲችሉ የመፍቀድ“ የሚሉትን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በኦሞ ወንዝ የታችኛው ክፍል እና በጋምቤላ አካባቢዎች ላይ የዩናይትድ ስቴትስ “የልማት እርዳታ” እና “የኢኮኖሚ ድጋፍ ገንዘብ” ሀ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አስገድዶ ማስፈርን ለሚተገብሩ እንቅስቃሴዎች ሊውል እንደማይችል፣ ለ) የአካባቢ ማህበረሰቦችን ህይወት ሊለውጡ ለሚችሉ ተነሳሽነቶች ማዋል እንደሚቻል እና ሐ) ጉዳት ከመድረሱ በፊት ከማህበረሰቦች ጋር ለሚደረግ ምክክር በማለት በማያሻማ መልኩ በግልጽ ተቀምጠዋል፡፡ ህጉ የሚጠይቀው “የገንዘብ ግምጃ ቤቱ ዋና ጸሀፊ የዩናይትድ ስቴትስ የእያንዳንዱ የገንዘብ ተቋም ኃላፊ የሆኑት ሁሉ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በኢትዮጵያ ዜጎችን ሊያፈናቅሉ ለሚችሉ ተግባራት መዋል እንደሌለበት መቃወም እንዳለበት“ ያመላክታል፡፡ “የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና የአካባቢ ስነምህዳር ጥበቃ ድርጅቶች በኦሞ ወንዝሸለቆ እና በጋምቤላ ተፈጥሯዊ ስነምህዳር እና ለዘመናት የህልውናቸው መሰረት አድርገው በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦች መብቶቻቸውእንዲጠበቁላቸው ሲያደርጉት የቆዩት ጥረት ፍሬ ያፈራ ይመስላል፡፡!!

የኦሞ ወንዝ ሸለቆን እና በዚያ ሰፍሮ የሚኖረውን ህዝብ ህልውና ለመታደግ በሚደረገው እርብርብ ኢትዮጵያውያን/ት የት ላይ እንገኛለን?

የይስሙላው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስለውኃ ልማት እና ስለአካባቢ ንፅህና እውቀት እንዳላቸው ይነገራል፡፡ እንደሚቀርቡት ዘገባዎች ከሆነ በአርባ ምንጭ የውኃ ቴክኖሎጂ ተቋም “የድህረ ምረቃ የአካዳሚ ቦታ“ ይዘው እንደነበር ይነገራል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የእርሳቸው የዘር ግንድ “ዋናው የህብረተሰብ ምድብ ከሆነው ከደቡብ ብሄሮች ብሄር እና ብሄረሰቦች ክልል ከኦሞቲክ ማህበረሰብ“ የመጡ እንደሆኑ ይነገራል፡፡

አቶ ኃይለማርያም በኦሞ ወንዝ ሸለቆ እየተከሰተ ስላለው አካባቢያዊ የስነምህዳር ውድመት እና “ከልማት” ጋር በተያያዘ መልኩ እየደረሰ ስላለው የማህበራዊ ኪሳራ የግል እና የሙያ ፍላጎት እንዲኖራቸው ሀሳብ ማቅረብ ምክንያታዊ ነው፡፡ ሆኖም ግን አቶ ኃይለማርያም በተደጋጋሚ “አገሪቱን ወደ እድገት ለማሸጋገር የአቶ መለስን ራዕይ ለማስፈጽም ነው ያለሁት“ በማለት በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡ እናም ከዚህ መንደርደሪያ መርሀቸው በመነሳት አቶ ኃይለማርያም የኦሞ ወንዝ ሸለቆ የአካባቢ ስነምህዳር ውድመት እና በሸለቆው ውስጥ የሚኖሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦች ህልውና አደጋ ላይ መውድቅን ከላይ ከቀረበው አስተሳሰባቸው ጋር አቆራኝቶ ማየት ይቻላል፡፡
እርግጥ ነው በዚህ ጉዳይ ላይ የማደርገው ትግል ባልጬት ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍስስ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን አቶ ኃይለማርያም እና ገዥው አካል በኢራን አገር ከሚገኘው ኦሮሚህ/Oroumieh ከሚባለው ሐይቅ አሰቃቂ ተውኔት ትምህርት እንዲቀስሙ አጥብቄ እማጸናለሁ፡፡ ያ ሐይቅ ዕውቀትን ባላካተተ መልኩ በተፈጸመበት የግድብ እና የመስኖ ስራ ፕሮጀክት ምክንያት በ10 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የውኃው መጠን በ80 በመቶ በመቀነስ ተኮማትሯል፡፡ የኢራን አዲሱ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሮሃኒ በሐይቁ መንጠፍ ስለደረሰው አካባቢያዊ ውድመት የሰጡት ምላሽ “ለችግሩ መፍትሄ ለመፈለግ እንዲቻል በአስቸኳይ ቡድን ማቋቋም እና በዘርፉ ክህሎት ያላቸውን ምሁራን መጋበዝ“ ነበር፡፡

አቶ ኃይለማርያም እና የስራ ጓዶቻቸው የኦሞ ወንዝ እንዲነጥፍ ሲደረግ ስለቱርካና ሐይቅ መድረቅ ወይም ደግሞ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ላይ ስለሚደርሰው አካባቢያዊ እና ስነምድራዊ እንዲሁም ማህበራዊ ውድመት ደንታ የላቸውም፡፡ በእብሪት እና በድንቁርና የታወሩ የገዥ አካል መሪዎች ምሁራንን እና በመስኩ ተፈላጊው ክህሎት ያላቸውን ባለሙያዎች በመጋበዝ ለተደቀነው አደጋ ዘለቄታዊ መፍትሄ ይሰጣሉ የሚል እምነት እንደሌለኝ አውቃለሁ፡፡ የገዥው አካል አመራሮች የወሰን ልክን እንደሰበረ ሁሉ በእራሳቸው የይሆናል ባዶ ተስፋ ከሚቦርቅ፣ ስለኦሞ ወንዝ ሸለቆ ጥንቃቄ እና ክብካቤ እንዲደረግ በተደጋጋሚ የሚማጸኑትን ወገኖች ከማውገዝ የዘለለ እርባና የሌለው ንግግር ከመደጋገም ውጭ የገዥው አካል አመራሮች የሚቀይሩት ነገር አይኖርም፡፡ ያም ሆነ ይህ አቶ ኃይለማርያም እና የተግባር ጓዶቻቸው በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ላይ የሚደረገውን የአካባቢያዊ ስነምህዳር ውድመት እና የማህበራዊ ቀውስ መግታት እንዲችሉ የህግ ኃላፊነት ያለባቸው የመሆኑን እውነታ ለታሪክ ተመዝግቦ ለተተኪው ትውልድ እንዲቀመጥ ሰለፈለግሁ ነው፡፡ ከዚህም በላይ “እውነት በመቃብር ለዘላለም ተቀብራ እንደማትቀር፣ሁሉቅጥፈትም ለዘላለም በዙፋን ላይ ተሰይማ እንደማትኖር“ ከአንገት ሳይሆን ከአንጀት መገንዘብ አለባቸው፡፡

የኢትዮጵያ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላትስ ምን እያደረጉ ነው?

የዲያስፖራው ማህበረሰብ ኢትዮጵያውያን/ት ወገኖቻችንን በጊቤ ሦስት ግድብ ምክንያት ህልውናቸውን ለመታደግ ከሚደረገው እርብርብ ጋር እንቀላቃለለን? በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ለሚኖሩ ድምጽ፣ መጠለያ፣ አቅም እና ድጋፍ ለሌላቸው ወገኖቻችን በአንድ ላይ ቆመን ልንናገርላቸው አንችላለን? ከኦሞ ወንዝ ሸለቆ ህዝቦች ጋር በአንድ ላይ ቆመን እንሟገትላቸዋለን ወይስ ደግሞ አቶ መለስ ዜናዊ እንደተናገሩት “በኋላቀር ስልጣኔ” ውስጥ ያሉ በመሆናቸው ምክንያት ጆሮ ዳባ ልበስ እንላቸዋለን? ዓለም አቀፍ ወንዞችን/International Rivers፣ ሂዩማን ራይትስ ዎችን/Human Rights Watch፣ ዓለም አቀፍ የኑሮ ዋስትናን/Survival International፣ እና የአፍሪካ ሀብቶች የስራ ቡድን/the Africa Resources Working Group በመቀላቀል የኦሞን ወንዝ ሸለቆ ኗሪን ህዝብ ህልውና ለመታደግ እና በላያቸው ላይ የተጫነውን ታላቅ መርግ ከጫንቃቸው ላይ ፈንቅሎ ለማንሳት ጥረት ልናደርግ እንችላለን?
የእነዚህን ጥያቄዎች መልሶች አላውቅም፣ ሆኖም ግን ሁልጊዜ እንደማደርገው አደርጋለሁ፡ ትልቁን ሸክም ተሸክመው በመታገል ላይ ላሉት እናአቀበቱን ለመውጣት እየተፍጨረጨሩ ላሉት ውኃ እናቀብል (ከኦሞ ወንዝ ባይሆንም እንኳ)!

“እንደስብስብ ወይም ደግሞ እንደ ግለሰቦች በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ/Universal Human Rights Declaration of Human Rights እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህግ መሰረት ለዘመናት የኖሩ የአንድ አካባቢ ቋሚ ዝርያ ያላቸው ህዝቦች ባሉበት ቦታ ተደስተው የመኖር መብት እና መሰረታዊ ነጻነቶቻቸው ተከብረውላቸው የመኖር መብት አላቸው፡፡“ (የተባበሩት መንግስታት ድንጋጌ የአንድ አካባቢ ዝርያ ያላቸው ህዝቦች 61/295)
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር! የካቲት 25 ቀን 2006 ዓ.ም

Sport: የስፔን ላሊጋ ፉክክሩ ከወትሮው ለየት ብሎ ቀጥሏል

$
0
0

barcelona
ከዳዊት በጋሻው

የዓለም ውድና ኮከብ ተጫዋቾችን የያዘው የስፔን ላሊጋ የሁለቱ ክለቦች ማለትም የባርሴሎናና የሪያል ማድሪድ ሩጫ እየተባለ በተደጋጋሚ ቢታማም በዚህ የውድድር ዓመት ግን ሀሜቱ ትንሽም ቢሆን ረገብ ያለ ይመስላል።

በዚህም የስፔን ላሊጋ በ2013/14 የውድድር ዘመን ከወትሮው በተለየ መልኩ ፉክክሩ ጠንካራ እየሆነ ነው።የዋና ከተማዋ ክለብ ሪያል ማድሪድና የካታሎናውያን ባርሴሎና ብቻቸውን ሲፎካከሩበት የነበረው ሊግ ዘንድሮ አትሌቲኮ ማድሪድን በመሃል አስገብቷል። ከሪያል ማድሪድ በተጨማሪ ሌላው የማድሪድ ከተማ ክለብ የሆነው አትሌቲኮ ማድሪድ ከባርሴሎናና ከሪያል ማድሪድ ጥሩ እየተፎካከረ መሆኑን በርካታ የስፖርት መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ናቸው።

አትሌቲኮ ማድሪድ፣ባርሴሎናና ሪያል ማድሪድ ተከታትለው እየመሩት የነበረው ላሊጋ አሁን ማድሪድ ተረክቦታል። ሪያል ማድሪድ የላሊጋው መሪ እንዲሆን የሦስቱ ወሳኝ ተጫዋቾች ጥምረት ማለትም የጋሬዝ ቤል፣የካሬም ቤንዜማና የክርስቲያኖ ሮናልዶ(BBC) አስተዋጽኦ የላቀ ነበር።
ሌላውና በዚህ የውድድር ዓመት ተፎካካሪ ሆኖ የተከሰተው አትሌቲኮ ማድሪድ በዲያጎ ኮስታ አስፈላጊውን ጥቅም እያገኘ ነው።ዲያጎ ኮስታ ከአትሌቲኮ ማድሪድም አልፎ ስፔንን ያጓጓ ሲሆን «ብራዚላዊነቴን ትቼ ለስፔን እጫወታለሁ» እስከማለት ደርሷል።
የካታሎናውያን ባርሴሎና በአንጻሩ ወሳኝ አጥቂው ሊኦኔል ሜሲን በጉዳት ያጣ ቢሆንም በኔይማርና ሴስክ ፋብሪጋዝ ተገቢውን ጥቅም እያገኘ ነው። ሊኦኔል ሜሲም ከጉዳቱ ካገገመ በኋላ ወደ ሜዳ በመመለስ መደበኛ የግብ ማግባት ስራውን ጀምሯል። በአጠቃላይ የሦስቱ ክለቦች ፉክክር ዘንድሮ የሊጉ ድምቀት መሆን ችላል።

ባለፈው ሳምንት በተካሄዱት የ25ኛው ሳምንት የስፔን ላሊጋ የጨዋታ መርሀ ግብር ባርሲሎና ሲሸነፍ፣ ማድሪድ የላሊጋውን መሪነት መረከብ ችሏል። ባርሲሎና ባልተጠበቀ ሁኔታ በሪያል ሶሴዳድ 3ለ1 ሲሸነፍ ፣ ሪያል ማድሪድ ኢልቸን 3ለ0 በመርታት ከዚያን ቀን ጀምሮም የላሊጋው መሪ ሆኗል።
ባርሲሎና በሳምንቱ በሻምፒዮንስ ሊግ ማንቸስተር ሲቲን 2ለ0 በመርታት ጣፋጭ ድል ቢቀዳጅም በሊጉ የደረሰበት ሽንፈት መሪነቱን ለሪያል ማድሪድ እንዲሰጥ አድርጎታል።

Ronaldo Christianoበዲያጎ ኮስታ የሚመራው አትሌቲኮ ማድሪድና በዓለም ኮከቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሚታገዘው ሪያል ማድሪድ ባሳለፍነው ሳምንት በቪሴንቴ ካልደሮን ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት የተለያዩ ሲሆን፤ ባርሴሎና በማሸነፉ ከመሪው ሪያል ማድሪድ ያለውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ ችሏል።
በስፔን ላሊጋ እስካሁን 26 ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ በ64 ነጥቦች ሲመራ ፣ባርሴሎና በ63 እንዲሁም አትሌቲኮ ማድሪድ በ61 ነጥቦች ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።ሪያል ቫያዶሊድና ራዮ ቫይካኖ በ23 ነጥቦች እንዲሁም ሪያል ቤቲስ በ15 ነጥቦች ወራጅ ቀጠና ውስጥ ገብተዋል።
የስፔን ላሊጋ የኮከብ ግብ አግቢነቱን (ፒቺቺ) የዓለም ኮከቡና የሪያል ማድሪዱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ23 ግቦች፣ብራዚላዊውና በቅርቡ ለስፔን ሊጫወት ከጫፍ የደረሰው የአትሌቲኮ ማድሪዱ ዲያጎ ኮስታ በ21፣የባርሴሎናው አሌክስ ሳንቼዝ በ16 ፣የሪያል ሶሲዳዱ ግሪዝማንና የባርሴሎናው ሜሲ በ15 ግቦች ይከተላሉ።

የጋዜጠኛ ብርቱካን ሃረገወይን ባለቤት የሆኑት ከፍተኛው የመንግስት ፕሮቶኮል ሹም ከስልጣናቸው ተነሱ

$
0
0

tplf ከኢየሩሳሌም አረአያ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት ከፍተኛ የፕሮቶኮል ዋና ሹም ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ በላይ ግርማይ ከስልጣን መነሳታቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። የሕወሐት አባል የሆኑትና ከ1990ዓ.ም ጀምሮ የጠ/ሚ/ሩ እንዲሁም የፕሬዝዳንቱ ፕሮቶኮል ሹም ሆነው በአቶ መለስ ዜናዊ ተሾመው ሲያገልግሉ መቆየታቸውን ያስታወቁት ምንጮች የአቶ በላይ ቢሮ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ውስጥ እንደነበረ ጠቁመዋል።

የቀድሞ ፕ/ት ነጋሶ ጊዳዳ፣ የጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ እንዲሁም የፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የፕሮቶኮል ሹም ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን ያስታወሱት ምንጮቹ፣ የውጭ አገር ባለስልጣናት፣ አምባሳደራትና ሌሎች አካላት ወደ ጠ/ሚ/ሩም ሆነ ፕሬዝዳንቱ ከመግባታቸው በፊት ጉዳያቸው በአቶ በላይ ግርማይ በኩል ያልፍ እንደነበር አያይዘው ገልፀዋል። ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ለ14 አመት በከፍተኛ ፕሮቶኮል ሹምነት ሲያገለግሉ ዘ-ሐበሻ የቆዩት አቶ በላይ ለአቶ መለስ ከነበራቸው ታማኝነትና ቀረቤታ አንፃር ከጠ/ሚ/ሩ ሞት በኋላ በነበራቸው ስልጣን ብዙም ደስተኛ እንዳልነበሩ የጠቆሙት ምንጮች አክለውም በሕወሐት ውስጥ ተፈጥሮ ከቆየው የቡድን ልዩነት ጋር በተያያዘ አቶ በላይ ግርማይ ከሃላፊነት እንዲነሱ በነደብረፂዮን መወሰኑን አስታውቀዋል።

በሌላም በኩል ለአቶ በላይ ግርማይ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ ይጠቁማሉ። የአቶ መለስና የወ/ሮ አዜብ ታማኝ ከሚባሉት የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ከስልጣን ተነስተው በሙስና እስር ቤት መወርወራቸውን፣ እንዲሁም የቤተመንግስት የደህንነትና ጥበቃ ዋና ሃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈሪ ቀጥሎ ከስልጣን የተነሱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን አቶ በላይ ግርማይ እንደሆኑ ምንጮቹ ገልፀዋል።

አቶ በላይ ግርማይ የጋዜጠኛ ብርቱካን ሃረገወይን ባለቤት ሲሆኑ፣ ጋዜጠኛ ብርቱካን በኢትዮጲያ ራዲዮና ቴሌቪዥን በሃላፊነት ተመድባ የምትሰራና አቶ መለስ ዜናዊን ብዙ ጊዜ ለብቻዋ ቃለምልልስ ታደርግ እንደነበረ፣ እንዲሁም ከጠ/ሚ/ሩ ጋር ወደ ተለያዩ አገራት አብራ ትጓዝ እንደነበረ ምንጮቹ አመልክተዋል።

የምትነዳው መኪና ከባቡር ጋር ተጋጭቶ ሕይወቷ ያለፈው ኢትዮጵያዊት ወጣት ቀብር በዳላስ ተፈጸመ (የቀብር ፎቶዎች ይዘናል)

$
0
0

melat mamo 11(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ቅዳሜ ሕይወቷ በአሰቃቂ ሁኔታ ያለፈው ኢትዮጵያዊቷ ሜላት ማሞ ዛሬ በዳላስ ከተማ የቀብር ሥነ-ሥርዓቷ ተፈጸመ። በወጣቷ ቀብር ላይ ከ500 ሰው በላይ መገኘቱንም የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከስፍራው አስታውቀዋል።

ዘ-ሐበሻ በሁለት ዜናዎች እንደገለጸችው ከባቡር ጋር የምትነዳው መኪና ተጋጭቶ ሕይወቷ ያለፈው ሜላት ማሞ በዳላስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ፍትሃት ከተደረገላት በኋላ በበሪ’ስላንድ የመቃብር ቦታ (Restland Cemetary) አስከሬኗ አርፏል።

በስፍራው የነበረው ሕዝብ በከፍተኛ ሃዘን ተውጦ ሃዘኑን ሲገልጽ እንደነበር የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በተለይም በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ጥቃትና ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመውጣት ለወገኖቿ ያላትን ፍቅር መግለጿን በማስታወስ ሃዘናቸውን በጥልቀት ሲገልጹ እንደነበር ጠቅሰዋል።

ወጣቷ ሜላት ማሞ የ4 ዓመት ወንድ ልጅ እናት እንደሆነችም ተያይዞ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ዛሬ የቀብር ስነስርዓቷ ሲፈጸም የሚያሳየውን ፎቶዎች ከዳላስ የዘ-ሐበሻ ተባባሪዎች ልከውልናል – እነሆ።

ስለሜላት ከዚህ ቀደም የዘገብናቸውን 2 ዘገባዎች ተጨማሪ መረጃዎች ይሰጧችኋል፤ ሊንኮቹን እነሆ

1ኛ. በዳላስ የምትነዳው መኪና ከባቡር ጋር ተጋጭቶ ሕይወቷ ያለፈው ኢትዮጵያዊት ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈጸማል

2ኛ. በዳላስ የምትነዳው መኪና ከባቡር ጋር ተጋጭቶ ሕይወቷ ያለፈው ወጣት ኢትዮጵያዊት ናት ተባለ

melat mamo memorial 1

melat mamo memorial 3

melat mamo memorial 4

melat mamo memorial 5

melat mamo memorial 6

melat mamo memorial 7

melat mamo memorial 8

ሰላማዊ ወይስ የትጥቅ ትግል ወይስ ማንፈራጠጥ –ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

$
0
0

Pro Mesfin
የተማረ ወይም የእውቀት ባለቤት እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍል ከወያኔ ጋር የሚደረገው ትግል ሰላማዊ ይሁን ወይስ በትጥቅ ትግል የሚለውን የጦፈ ክርክር ሲያደርግ ሃያ ሁለት ዓመታት ሆነው፤ ዳኛ የሌለበት ክርክር ስለሆነ የመደማመጥ ግዴታ ታይቶበት አይታወቅም፤ ስለዚህም በሁለቱ መሀከል ያለው ልዩነት ግልጽ ሆኖ አያውቅም፤

አንድ፣ ከሁሉ በፊት ሰላማዊ ትግል በሀሳብ ደረጃ መሆኑንና የትጥቅ ትግል ደግሞ በተግባር መሆኑን ለይቶ ለመረዳት ችግር ሆኖ ቆይቶኣል፤ በሌላ አነጋገር ሰላማዊ ትግል በሀሳብ፣ በንግግር፣ በተለያዩ ሀሳብን ለማስለወጥ መቀስቀሻ በሚሆኑ መንገዶች ተቃውሞን መግለጽ ነው፤ በአንጻሩ የትጥቅ ትግል በጠመንጃ ወይም በጉልበት ያለውን የአገዛዝ ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ ሙከራ ነው፤

ሁለት፣ እንዲህ ከሆነ በሰላማዊ ትግል ለሚያምኑ ሰዎች ያለምንም ጥርጥር በተለያዩ ዓላማዎችና ዘዴዎች ላይ መከራከርና ሀሳብን ማጥራት አስፈላጊ ነው፤ በሰላማዊ ትግል ተግባር አለ ቢባልም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ ወይም የተቃውሞ አቅዋሞችን ከማሳየት አያልፍም፤ አገዛዞች ጃዝ! ብለው ውሻና ፖሊስ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ሲለቁ የጉልበት ጥርስና ዱላ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያርፋል፤ ጉዳት ይደርሳል፤ ሰላም ይቃወሳል፤ በሕዝብና በአገዛዙ መሀከል ቂም ይጀመራል።

ሦስት፣ የትጥቅ ትግል ደግሞ በተዋረድ በሚተላለፍ ትእዛዝ የሚፈጸም ግዴታ ነው፤ በትጥቅ ትግል ጉልበተኛ ከጉልበተኛ ጋር፣ ብረት ከብረት ጋር ይጋጠማል፤ የሰው ልጅ ለእርድ ይቀርባል፤ በሕይወታቸው በልተው ያልጠገቡ ምስኪኖች ለጥቂት ሰዎች የሥልጣን ጉጉት ይታረዳሉ፤ ያለቀባሪ በጅብና በአሞራ ይበላሉ፤ ዕድለኞች የሚባሉት እጆቻቸው፣ ወይም እግሮቻቸው ተቆርጠው፣ ወይም ዓይኖቻቸው ጠፍተው፣ ወይም ከዚህ ሁሉ የባሰ ጉዳት ደርሶባቸው በሕይወት የሚቀሩት ናቸው፤ ከነዚህ በሕይወት በቀሩት የጦር ጉዳተኞችና በጦርነቱ ላይ በሞቱት መሀከል የትኛው የተሻለ አንደሆነ የሞቱት ባይናገሩም ጉዳተኞቹ ይናገራሉ፤ ‹የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!› እያሉ።

አራት፣ ሁለቱ የትግል ስልት ዓይነቶች በባሕርይ የተለዩ ናቸው፤ አንዱ ሌላውን የሚደግፍ አይደለም፤ ሰላማዊ ትግል የትጥቅ ትግልን ለመደገፍ ሰላማዊ የሚለውን ስያሜ መጣል አለበት፤ የትጥቅ ትግልም ሰላማዊ ትግልን ለመደገፍ ትጥቅ የሚለውን ስያሜ መተው አለበት፤ ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል አራማጆች ድል ቢያደርጉ ማን ወንበሩ ላይ እንደሚወጣ ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ጠመንጃ የያዘው ሥልጣኑን ሲይዝ ሰላማዊ ትግሉ ይቀጥላል! ያውም ከተፈቀደለት!

በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ታሪክ አርበኞች ሳይቀሩ በሩ ተዘግቶባቸው ለደጅ ጥናት እንደተዳረጉ አይተናል፤ መልኩን ለወጥ ቢያደርግም ደርግን ከተፋለሙት ውስጥ በአዲስ አበባና በአስመራ ወንበሮች ላይ ሲወጡ የተሸነፉት ወይ ለወያኔ ገብረው ሎሌነት ገቡ፤ ወይም በአሜሪካ መሽገው ያቅራራሉ፤ ዘመኑ እንዳለፈባቸውም ገና አልተረዱም።

አምስት፣ ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል ሁለቱም ብርቱ ቃል ኪዳንን ይጠይቃሉ፤የቃል ኪዳናቸው ልዩነት አንዱ እስከሞት ለመታገል፣ ሌላው ደግሞ እስከመግደልና እስከመሞት ለመታገል መሆኑ ነው፤ ለሰላማዊው ትግል ከፍተኛ መንፈሳዊ ወኔ የሚያጎናጽፈው ለመግደል ያለው ተቃውሞ ነው፤ ሕይወትን ለማልማት ሕይወትን መቅጠፍ የአስተሳሰብም የመንፈስም ጉድፍ ያለበት ሥራ ነው።

የሰላማዊ ትግል ዋናውና ቀጥተኛው ተልእኮ ሕዝብን ለሥልጣን ባለቤትነት ማብቃት ነው፤ ሥልጣንን ለመያዝ አይደለም፤ ስለዚህም ኢላማው ሕዝብ ነው፤ በሥልጣን ወንበሩ ላይ ያሉት የሰላማዊ ትግሉን የሚቃወሙት በሕዝብ ዘንድ ተሰሚነትና ተቀባይነት እንዳያገኝ ለማድረግ ነው፤ ሰላማዊ ትግሉ የሚያተኩረው በሕዝቡ ጆሮ፣ አእምሮና ልብ ላይ ነው፤ አገዛዙ በበኩሉ ጸጥ-ለጥ ብሎ የሚገዛለት ሕዝብ እውቀቱ ዳብሮ፣ መብቶቹን ሁሉ ተገንዝቦ፣ በሕግ ለሕግ እንጂ ለሰው አልገዛም በማለት ልቡ እንዳይሸፍት አፈናውንና ማነቆውን በማጠናከር እያደነቆረ ለመግዛት ይፈልጋል፤ የሰብአዊ መብቶችን የሚያስተምሩና በአገዛዙ አካላት የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያጋልጡ ድርጅቶችን ማዳከም ወይም ማጥፋት ለአገዛዙ አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው፤ ኢሳት የሚባለው የቴሌቪዥንና የራድዮ ፐሮግራም ለወያኔ የውስጥ እግር እሳት የሆነበት ለዚህ ነው፡፡ በሰውነት ደረጃ ሕዝቡ መብቶቹን ሁሉ እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ፣

በዜግነት ደረጃ ሕዝቡ ለሥልጣን የሚያበቃውን የዜግነትና የፖሊቲካ መብቶች እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ፣ ሕዝቡ የሰውነትና የዜግነት መብቶቹን ተገንዝቦ በአገዛዝ ስር አልተዳደርም የማለት መንፈሳዊ እምቢተኛነት እንዲያድርበት ማድረግ፣ በግልጽ ጭቆናን የሚጠላና ለመብቶቹና ለነጻነቱ በቆራጥነት የሚቆም ሕዝብ እንዲፈጠር ማበረታታት፣ መብቶቹንና የሥልጣን ባለቤትነቱን የተረዳና ከጭቆና ጋር የተጣላ ሕዝብ በፖሊቲካ መስመር ቡድኖችን እየፈጠረ እንዲደራጅ ማድረግ፣ ያወቀና የነቃ፣ በፖሊቲካ መስመር የተደራጀና ማናቸውንም ዓይነት ጭቆና የሚጠላ ሕዝብ ለማንም ጉልበተኛ የማይንበረከክ ሕዝባዊ ኃይል እንዲሆን መጣር፣

የትጥቅ ትግል ዋናውና ቀጥተኛው ተልእኮ በሥልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ አውርዶ ወንበሩን ለራሱ ለመውሰድ ነው፤ ይህንን ሲያደርግ ሕዝቡን ወደጎን ትቶ ወይም ዘልሎ ነው፤ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ በጠመንጃ ሥልጣን የሚይዙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥልጣኑን ለሕዝብ እናስረክባለን፤ ትክክለኛ ምርጫ እናካሂዳለን በማለት ሕዝቡን በተስፋና በጠመንጃ ይዞ ነው፤ ነገር ግን ሥልጣንን ሕዝብ ለፈቀደው አስረክበው ከቤተ መንግሥት ሲወጡ አናይም፤ ሲሸሹ ወይም ሬሳቸው ሲወጣ እንጂ።

ብዙውን ጊዜ የማይታሰብ ወይም ብዙዎች የሚዘነጉት የሁለቱ ትግሎች የገንዘብ ወጪ በጣም ከፍተኛ ልዩነት ያለው መሆኑን ነው፤ ሰላማዊ ትግል በሕይወትም፣ በንብረትም፣ በመሣሪያም በዝግጅትም የሚያስከፍለው ዋጋ ከትጥቅ ትግል ጋር ሲወዳደር በጣም አነስተኛ ነው።

ስለዚህም በሁለቱ በተለያዩ ስልቶች አራማጆች መሀከል የሚደረግ ክርክር ምን ዓይነት ነው? የሰላማዊው የመጀመሪያ ደረጃ ኢላማው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፤ የትጥቅ ትግል የመጀመሪያ ደረጃ ኢላማው የወያኔ አገዛዝ ነው፤ በሌላ አነጋገር በሰላማዊ ትግል ሕዝቡ በሰላማዊ ትግል ትንሽም ቢሆን የነጻነትን አድማስ ለማስፋት እንዲችል ድፍረትን በማስተማር በኩል የማይናቅ አስተዋጽኦ ቢያደርግም አገዛዙን የመነቅነቅ ኃይል ገና አላዳበረም፤ አንድም ውጤት አላሳየም፤ የትጥቅ ትግሉ ከፉከራና ከሽለላ እስካሁንም አልወጣም፤ የሰላማዊ ትግል ዓላማ ሕዝቡ መብቶቹን እንዲያውቅ ለማንቃትና ለመብቶቹ እንዲታገል የሚያስችለውን ብቃት ለማስጨበጥ ነው፤ ስለዚህም ዘዴው በሕዝቡ ላይ ነው፤ የትጥቅ ትግሉ ዘዴ አገዛዙን በጉልበት ገልብጦ በዚያው ባልተለወጠ ሕዝብ ላይ ሌላ አገዛዝ ለመመሥረት ነው።

በኢትዮጵያ ለውጥ እናመጣለን የሚሉ ሁሉ የቆሙበትንና የቆሙለትን ዓላማና ዘዴ በግልጽ ተገንዝበው ካልተሰለፉ በተንፈራጠጠ አስተሳሰብ የተባበረ ተግባር ሊገኝ አይችልም።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live