Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ቆንጨራ አከፋፋዩ ማነው!? አብይ ስልጣንዎን ይጠቀሙ ወይ ለሕዝቡ ቁርጡን ይንገሩ!! –ሀብታሙ አሰፋ

0
0
የሕወሓት መሪዎች ከስልጣን እንደወረዱ ሰሞን ቆንጨራ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ያከፋፍሉ ነበር። ከዚህ ሁሉ የሚታወሰው አባይ ጸሐይዬ በቤንሻንጉል ድብቅ ስብሰባ አድርጎ በወጡ ማግስት ለዕቅዱ ተግባራዊነት አንድ መኪና ቆንጨራ በክልሉ ፖሊስ ተይዙዋል።ይሄ አብይ ስልጣን ላይ የወጡ ሰሞን የሆነ ነው። ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ፣በድሬዳዋ እና በሐረር ጥቃት አድራሽ አሸባሪዎች በጭካኔ ያጠፉት ሕይወት ሳያንስ ሌላ ንጹሃንን የመቅጠፍ […]

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፈቱ! –ያሬድ ኃይለማርያም

0
0
መቼም ይህ ሁሉ ውርጅብኝ በአገር እና በሕዝብ ላይ እንደማያባራ ዝናብ ሲወርድ ዝም ማለትዎ አንድም አቅም ማጣት፣ አንድም በፓርቲ ሰንሰለት ተጠርንፈው፣ አንድም ከብሽቀት፣ አለያም ምን ይዤ ነው ሕዝብ ፊት የምቀርበው ከሚል በሰዋዊ ስሜት ተውጠው ይሆናል። ወይም እኛ ልንገምተው ያልቻልነው ሌላ ችግር ገጥሞዎት ይሆናል። ለማንኛውም ግን ዝምታዎ እስከ አሁን ግርምታን ፈጥሯል። ከዚህ ካለፈም እና በዚሁ ከዘለቁም ውስጣችን […]

ወራሪውን የጣሊያን ጦር ለመመከት አርበኞች ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰባሰቡባት ስፍራ –“አንዲትግራር”

0
0
(ኢፕድ) “አንዲትግራር” በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ እንግዳ ዋሻ አንቀላፊኝ ሜዳ በተባለች ስፍራ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድ ተሰባስበው ወራሪውን የጣሊያን ጦር ለመዋጋት የጦር ስትራቴጂ ቀይሰው የመጀመሪያው የአርበኞች ማህበር የመሰረቱባት ታሪካዊ ስፍራ ነው። ወደ አንዲትግራር ለማቅናት ከደብረሲና ተነስተው እስከ ታሪካዊው ስፍራ ለመድረስ የአካባቢው ፒስታ መሰል አቧራማ ወጣ ገባ መንገድ ማቆራረጥ የግድ ይላል። አካባቢው ተፈጥሯዊ […]

የለውጥ አረማሞ ! –የጎንቻው!!

0
0
የለውጥ አረማሞ ! – የጎንቻው!!

ስለ ብሔረተኝነት –ታየ ደንድአ

0
0
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ብሔረተኝነት ትልቁን ስፍራ ይዟል። ሆኖም ይህ አንገብጋቢ ጉዳይ በብዙዎች ዘንድ ግልፅነት የለዉም። ምሁራን እንደሚሉት ብሔረተኝነት የተለያዩ ትርጉሞች አሉት። በጥቅሉ ግን የራስን ብሔር መዉደድ ተብሎ ሊገለፅ ይችላል። ይህ ደግሞ የብሔሩ ክብር እና ጥቅም እንዲረጋገጥ ከልብ መታገልን ያጠቃልላል። . በመሠረቱ የራስን ብሔር መዉደድ ሌላ ብሔርን መጥላት አይደለም። ይልቁንም ትክክለኛ ብሔረተኝነት ስለሌሎች ማሰብን ያማክላል። መጀመሪያ […]

የ ዶ/ር አቢይ ኢትዮጵያ ወይም ሞት ጥሪ ክፍል ፪ (ከአባዊርቱ)

0
0
ይህንን አባሪ ያስከተበኝ ነገር እባክዎ ይፍቀዱ የልቤን ልናገር በባለፈው ሳምንት የሆነው ሁኔታ ዛሬን ላይ አድሬ ሳይኖረኝ ብዥታ ፍንትው ብሎ ታየኝ የሆነው ሁኔታ። ለካንስ ጉዳዩ ሌላ ነገር ነበር ጉዳዩን ሳጠናው የሆነውን ነገር ወያኔና ጁዋር ብሎም እነንቶኔ ለካስ ሞክረዋል አወይ ሰው መሆኔ ስሜታዊ ሆኜ እርሶን በመኩነኔ ዋናው ጽልመት ሳለ የሚሉት ወያኔ። አቢይ ወዴት ጠፉ፣ አይ ሰው ደንታቢሱ […]

ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ብዙ ዋጋን የከፈለው ጀግናው አንዱዓለም አራጌ በቦስተንና አካባቢዋ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ብርቱ ቀጠሮ

0
0
ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ብዙ ዋጋን የከፈለው ጀግናው አንዱዓለም አራጌ በቦስተንና አካባቢዋ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ብርቱ ቀጠሮ

መንግሥት የህግ የበሊይነት የማስከበር ኃሊፊነቱን መወጣት አልቻለም የብሔራዊ መግባባትና እርቅ ሰላም መድረክ በአስቸኳይ –ኅብር ኢትዮጵያ

0
0
መንግሥት የህግ የበሊይነት የማስከበር ኃሊፊነቱን መወጣት አልቻለም የብሔራዊ መግባባትና እርቅ ሰላም መድረክ በአስቸኳይ – ኅ ብር ኢትዮጵያ ዴሞክ ራሲያ ዊ ፓር ቲ[ኅ ብር ኢትዮጵያ Hibir press release Final Oct 31-2011 —–ሁሉንም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ—–      

እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን… ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው –ሰርፀ ደስታ

0
0
ይህ ቃል በመጻፈቅዱስ ተጽፎ  ያለ ሁሌም በስታወስኩት ቁጥር በጣም የሚገርመኝና ሁኔታዎችንም ሳስተውል የሚያስደነግጥ ሆኖ አገኘዋለሁ፡፡ ቃሉ የት ምህራፍና ቁጥር ላይ እንዳለ አላውቅም ግን ሙሉው እንደሚከተለው ነው የሚለው፡፡ አስታውሰዋለሁ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ነው የሚለው፡፡ እግዚአብሔር እውነት ነው! እውነትን (እግዚአብሔርን) ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን ማለት ነው፡፡ አንዴ ለማይረባ አእምሮ ተላልፎ […]

የማያዛልቅ ባል ቅንድብ ይስማል –ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

0
0
ሽሉም ገፍቶ ቂጣውም ጠፍቶ የተፈራው ነገር ሁሉ ደርሶ እዚህ ደርሰናል – ጥቅምት 22 ቀን 2012ዓ.ም. ፡፡ ማታም ሆነ፤ ቀንም ሆነ አንድ ዓመት ከስድስት ወርና ከ22 ቀን፡፡ እውነት ነው – የማያዋጣ ባል ቅንድብ ይስማል፡፡ የማያዛልቅ ባልም ይሁን ጓደኛ የሚፈልገውን እስኪያገኝ የሚያሳየው መቅመድመድ አይጣል ነው፡፡ ይሉኝታን አውልቆ ይጥላል፡፡ ሀፍረት ሲያልፍ አይነካውም፡፡ አንጎሉን አስቀምጦ በስሜቱ ብቻ ዕውር ድንብሩን […]

ዜጎችን ለሰብአዊ መብት ጥሰት ተጋላጭ ያደረገው ፌዴራላዊ ስርዓቱ የተተገበረበት መንገድና የፌዴራል ስርዓቱ የመንግስት አወቃቀር ነው ተባለ

0
0
ዜጎችን ለሰብአዊ መብት ጥሰት ተጋላጭ ያደረገው ፌዴራላዊ ስርዓቱ የተተገበረበት መንገድና የፌዴራል ስርዓቱ የመንግስት አወቃቀር አንዱ ችግር መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ተናገሩ:: በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ፌዴራላዊ ስርዐቱ የተተገበረበት መንገድ ዜጎችን ለሰብአዊ መብት ተጋላጭ ማድረጉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ተናገሩ:: ዶክተር ዳንኤል በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳብራሩት፤ ዜጎችን ለሰብአዊ መብት ጥሰት […]

የአማራን ሕዝብ ማዕከል አድርገው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደረሱ

0
0
አዴፓ፣ አብን እና የአምስቱ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ጥምረት የያዘው የአማራ ድርጅት የስምምነቱ አካል ሆነዋል፡፡ የአማራ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች እና ጥቅሞች ምላሽ እንዲያገኙም ፓርቲዎቹ በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡  በአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ አዘጋጅነት በአማራ ክልል እና በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ በውይይት መድረኩ በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው የአማራን ሕዝብ አማክለው የሚቀሳቀሱት አዴፓ፣ አብን እና […]

“አብይ የሚጨነቀው ስለ ኦሮሞ ህብረት እንጅ በግፍ ስለተጨፈጨፉ ንጹሀን አይደለም”–አቶ ያሬድ ጥበቡ

0
0
“ከጃዋር የጥበቃ ችግር ጋር በተያያዘ የተነሳውን የኢትዮጵያውያን በግፍ መጨፍጨፍ በተመለከተ ሁሉ ነገር እስኪጠራ በሚል ዝምታን መርጬ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከሩሲያ ጉብኝታቸው ሲመለሱም በመፅሀፋቸው ካስነበቡን ኢትዮጵያዊ ህልማቸው ጋር በሚመጥን መንገድ አመራር ይሰጣሉ ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር። ሆኖም፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ በወጣው መግለጫ፣ ሐረርና አምቦ ካደረጉዋቸው ስብሰባዎች፣ የፕሬስ ሃላፊያቸው እሳቸውን ተክተው የሰጡት መግለጫ፣ አንዳቸውም ሀላፊነት ከሚሰማው መሪ […]

አቶ ኤሊያስ ሽኩር የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

0
0
አቶ ኢሊያስ የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን የተሾሙት በቅርቡ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው የተሾሙትን አቶ ርስቱ ይርዳን በመተካት ነው ። አቶ ኤሊያስ ሽኩር ከአሁን በፊት የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል ። ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ጌታቸው ባልቻ የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው የሚቀጥሉ ይሆናል ። (ኢ.ፕ.ድ)

በሰሜን አሜሪካ ሦስት ገዳማትን ለማቋቋም ታስቧል፤ በውጭ አህጉረ ስብከት አደረጃጀት ደንብ ረቂቅ ላይ ተጨማሪ ጥናት ይደረጋል

0
0
ሐራ ተዋሕዶ በሰሜን አሜሪካ ዩናይትድ ስቴትስ፣ በተመረጡ ሦስት ቦታዎች ገዳማትን ለማቋቋም፣ የአህጉረ ስብከቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በጋራ፣ ትላንት ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ምክረ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡ ዋሽንግተን፣ ሜሪላንድ እና ካንሳስ፣ ሦስቱን ገዳማት ለማቋቋም የተመረጡ ቦታዎች ሲኾኑ፣ የሚጠይቁት ወጪም በምክረ ሐሳቡ ተካቶ ቀርቧል፡፡ በአጀንዳው ተ.ቁ.(10) ጉዳዩን ይዞ የተወያየበት ምልአተ ጉባኤው፣ ከዘላቂ የመተዳደርያ ኹኔታ፣ ከቦታ አቀማመጥ ምቹነት፣ ከቦታዎቹ ግዢ […]

‹‹ኢህአዴግ ወጥ ፓርቲ ለመመስረት መንቀሳቀሱን እንደ ጥሩ አጋጣሚ እወስደዋለሁ›ዶክተር ዲማ ነገዎ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁር

0
0
አዲስ አበባ፡- የቀድሞው የኦነግ መሪ የነበሩት የፖለቲካል ሳይንስ ምሁር ዶክተር ዲማ ነገዎ‹‹ኢህአዴግ በመዋሃድ ወጥ ፓርቲ ለመመስረት መንቀሳቀሱን እንደ ጥሩ አጋጣሚ እወስደዋለሁ›› ሲሉ ገለፁ፡፡ ዶክተር ዲማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤በአሁኑ ወቅት በየትኛውም ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ የላቸውም፡፡ነገር ግን እንደ አንድ ምሁር ማለት የሚችሉት ኢህአዴግ በውስጡ ያለውን አደረጃጀት የመወሰን የራሱ መብት ነው፡፡በመዋሃድ ወጥ ፓርቲ ለመመስረት መነሳሳቱም መልካም ተግባር […]

የአማራን ሕዝብ ማዕከል አድርገው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደረሱ

0
0
 የአማራን ሕዝብ ማዕከል አድርገው የሚንቀሳቀሱት አዴፓ፣ አብን እና የአምስቱ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ጥምረት የያዘው የአማራ ድርጅት በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደረሱ፡፡ በአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ አዘጋጅነት በአማራ ክልል እና በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ በውይይት መድረኩ በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው የአማራን ሕዝብ ማዕከል አድርገው የሚቀሳቀሱት አዴፓ፣ አብን እና የአምስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት የአማራ […]

ከአንድ ላም በአማካይ የሚገኘውን 1.8 ሊትር ወተት ወደ 30 ሊትር ለማሳደግ እየተሰራ ነው

0
0
በኢትዮጵያ ከአንድ ላም በአማካይ የሚገኘውን 1.8 ሊትር ወተት በቴክኖሎጂ በመደገፍ ወደ 30 ሊትር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። በአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የተደገፈ የእንስሳት ሀብት ልማት ፕሮጀክት ለመጀመር የሚያስችል የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈርሟል። ስምምነቱን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ፣ የአማር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህና የጎንደር ዩንቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር አስራት […]

ወያዖ (ወያኔና ዖነግ) –ከአባዊርቱ

0
0
ይድረስ ልክ እንደኔ እርር ድብን ላልከው ግራግብት ብሎህ አንገት ለደፋኽው። የሰሞኑ ውጥረት በደም የጨቀየ ካይምሮ ሳይጠፋ አንድ ነገር ታየ። ዛሬ በጠዋቱ አይን የገባው ዜና እስቲ ወገን ሁላ  ስሜቱን ተውና ለምን እንደወጣ መርምር እንደገና የ “ወዳጅ” ጠላቱ ከዚሁ ጉድ ነውና። እንዲህ ነው ጉዳዩ ስሙኝ ወገኖቼ ያለውን ሁኔታ ሁሉዋንም  ከፍቼ ላስረዳችሁ በግልጽ ዜናውን ለይቼ። ወያኔና ዖነግ (ወያዖ) […]

እስክንድርንማ ተውት! –መስከረም አበራ

0
0
ሰሞኑን ከአንድ ወዳጄ ጋር በስልክ እናወራለን፡፡ እሱ በጠ/ሚ አብይ አስተዳደር ላይ ተስፋ ቆርጦ ጨርሷል፤እኔ ደሞ ደፍርሶ ሲጠራ የሚመጣ ነገር ካለ እንይ ባይ ነኝ፡፡ በክርክራን መሃል “አንድ ቀላል ጥያቄ ልጠይቅ” አለኝ፡፡መጠባበቅ ጀመርኩ፡፡ ቀጠለ “ሌላ ሌላውን ተይውና በአሁኑ ሰዓት በእኩልነት የምንጨቆንበት ሁኔታ እንኳን እንደሌለ አይታይሽም? በዚሁ ሁኔታ እንዴት ያለ ተስፋ ነው የሚኖረኝ?!” ሲል ምርር አለ፡፡ ለዚህ አባባሉ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live