Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የድምጻዊ መስፍን በቀለ “ወለላዋ”የሙዚቃ ቪድዮ ክሊፕ ተለቀቀ

$
0
0

የድምጻዊ መስፍን በቀለ “ወለላዋ” የሙዚቃ ቪድዮ ክሊፕ ለቀቀ (ዘ-ሐበሻ) አሁን ካሉት ወጣት ድምፃውያን መካከል የአድማጭን ጆሮ በማግኘት በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ የሆነው ድምጻዊ መስፍን በቀለ ወለላዋ ለተሰኘው ዘፈኑ አዲስ የሙዚቃ ክሊፕ ሰርቶ ለቀቀ። መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ ባደረገው ምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት አማካኝነት የቀረበውና በእውቁ ካይሮግራፈር አብዮት (ካሳነሽ) ደመቀ አማካኝነት በተዘጋጀ ውዝዋዜ አዲሱ ወለላዋ የተሰኘው ክሊፕ ታጅቧል።
በዚህ ክሊፕ ላይ እውቁን ካይሮግራፈር አብዮት ደመቀን ጨምሮ ሌሎች በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ተወዛዋዦች የተሳተፉበት ሲሆን ፊልሙ የተቀረጸውም በዛጎል ፊልምስ አማካኘት መሆኑን በክሊፑ ላይ ተገልጿል።
መስፍን በቀለ እና አብዮት ደመቀ ከ”ወለላዋ” ክሊፕ በፊት የሰሩት “እሹሩሩ” የሙዚቃ ክሊፕ ተወዳጅነትን አስገኝቶላቸው እንደነበር ይታወቃል። ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አዲሱን ወለላዋ የሙዚቃ ክሊፕ ጋብዘናል። ክሊፑን ለማየት እዚህ ይጫኑ


“‘አማራ ኬላ’የሚባሉ አምስት ቦታዎች አሉ፣ የአማራ ተወላጆች በነዚህ ኬላዎች አያልፉም”–ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል

$
0
0

(የፎቶ ምንጭ፡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ)

(የፎቶ ምንጭ፡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ)

(ዘ-ሐበሻ) በክልሎች ስለሚፈናቀሉ አማሮች ጉዳይ ምን አስተያየት አለዎት? በሚል በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ የተጠየቁት የመኢአድ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል “አሁን ቤንች ማጂ ዞን ብትሄጂ አሠቃቂ ነገሮች አሉ፡፡ እኔ አሁን ጉዳዩን እንዲያጣሩ የላኳቸው፣ የአማራ ተወላጆች አይደሉም፡፡ ለምን ብትይ “አማራ ኬላ” የሚባሉ አምስት ቦታዎች አሉ፣ የአማራ ተወላጆች በነዚህ ኬላዎች አያልፉም፡፡ ስለዚህ ጉዳዩን እንዲያጣሩልኝ የደቡብ ሠዎች ነው የላኩት፡፡ መረጃ የደረሠኝም በደቡብ ተወላጆች በኩል ብቻ ነው፡፡ አማራ ቢሄድ በመታወቂያው ይያዛል፡፡” በማለት አጋለጡ።
አዲስ አበባ ላይ ታትሞ ከወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ሰፊ ቃለምልልስ ያደረጉት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል “አምስቱም ኬላዎች ላይ ፖሊስ ቆሞ ይጠብቃል፡፡ምን ምን የሚባሉ ኬላዎች?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ “አሁን ዝርዝሩን አምጡልኝ አላልኩም ግን እነዚህ ኬላዎች አሉ፡፡ በእያንዳንዱ ኬላም ጠባቂ ሚሊሻዎች ቆመዋል፡፡ አንዳንድ አማራ ወደዛ የቢዝነስ ሥራ ኖሮት ለማለፍ ቢፈልግ “ አንድ ሺ ብር ክፈል” እንደሚባልም ደርሠንበታል፤ ጉቦ ነው እንጂ መቸስ ደረሠኝ አይሠጠውም እኮ፡፡ ህዝቡ ተስፋ ቆርጧል፣ ሠልችቶታል፣ ከኢህአዴግ ጥሩ ነገር አይጠብቅም ብለውኛል፡፡” ሲሉ ተናግረዋል።
“ከእንግዲህ ወዲህ ይሄ ህዝብ ወያኔ እድል ይሠጠኛል ብሎ እንደማይጠብቅ እርግጠኛ ነኝ፡፡” ያሉት ኢንጂነር ኃይሉ “የቀረው ሆ ብሎ መብቴን አስከብራለሁ ብሎ ሲነሣ፣ ያን ጊዜ ማን መልስ እንደሚሠጥ አናውቅም፡፡ በቃ ይሄው ነው፡፡” ብለዋል። በተለይም በተቃዋሚ ድርጅቶች መብዛት ዙሪያ ሰፊ ገለጻ የሰጡት ኢንጂነሩ “ይህን ሁሉ ፖለቲካ ፓርቲ የሚያራባው ማን ይመስልሻል፡፡ ዘጠና እና ዘጠና አምስት ፓርቲ አለ እኮ ነው የሚባለው፡፡ ለምሣሌ ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲ ሲመሰረት ሌላ አራት ይፈጠራል። ማን ነው የሚፈጥራቸው ካልሽ ራሱ ወያኔ ነው የሚፈጥራቸው፤ ደሞዝ እየከፈለ የሚያኖራቸው ፓርቲዎች አሉ አይደለም እንዴ፡፡” በማለት ከመንግስት ደመወዝ የሚቆረጥላቸው በተቃዋሚ ፓርቲ ስም የተመዘገቡ ድርጅቶች እንዳሉ አጋልጠዋል።
በቃለ ምልልሳቸው “እውነት ለመናገር ቅንጅትን ወያኔ ራሱ ነው ያፈራረሠው፡፡” ያሉት ኢንጂነሩ “አሁንም እያፈረሠ ነው፡፡ እያንዳንዱ ፓርቲ ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ አስርና አስራ አምስት ያህል ሠላዮች አሠማርቷል፡፡ እኛም ወስጥ ተሠማርተው ስራቸውን ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ የእኛ ጥፋት ምኑ ላይ መሠለሽ፣ ዴሞክራሲ ብለን ስለተነሣን በየአካባቢው ያለው ሁኔታ ዴሞክራቲክ ነው በሚል ራስን በሚደልል ሁኔታ ግልፅ ሆንን እና ምስጢር የሚባል ነገር መያዝ አልቻልንም፡፡ በፊት ለፊት ስንሠራ ስለነበር ለወያኔ ተመቸነው፡፡” በማለት አብራርተዋል።
በቅርብ ቀን “ህይወቴና የፖለቲካ እርምጃዬ” በሚል መጽሐፋቸውን ሊያወጡ በዝግጅት ላይ ያሉት እንጂነር ኃይሉ “መፅሀፉ ስለቅንጅት መፍረስ፣ በአጠቃላይ ስለ ፖለቲካው ሁኔታ የሚዳስስ እንደመሆኑ፣ ከመነሻው ጠቅላላ ሂደቱን ይተነትናል፡፡ መጀመሪያውኑ ቅንጅትን ስንመሠርት አንዳንድ ችግሮች መኖራቸውን ሳላስተውል ቀርቼ አልነበረም። ነገር ግን “ግዴለም አብረን ስንሠራ ቀስ በቀስ ይስተካከላል” በሚል አምኜ አብሬ ተጉዣለሁ። ያንን ጉዳይ አሁን ላይ ሆኜ ወደ ኋላ ሳየው “ለምን ሳናጣራ ሄድን” ብዬ እጠይቅና እቆጫለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ግዜው አይፈቅድም ነበር፡፡ ህዝብ ከእኛ ብዙ ይጠብቅ ነበር፡፡ የጋዜጦችም ግፊት ከፍተኛ ነበር፡፡ የዛን ጊዜ ወደ ኋላ ብንል ኖሮ “መኢአድ እንደልማዱ ቅንጅት አንፈጥርም ብሎ ነገር አበላሸ” ይባላል በሚል ነው የቀጠልነው፡፡ ምክንያቱም መኢአድ ባይኖር ቅንጅት አይፈጠርም ነበር፡፡ ይሄ ግልፅ ነው።” ሲሉ ስለመጽሐፋቸው ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል።

‎የአንድ ጎልማሳ ገንዳ ወግ‎

$
0
0

ከዓለማየሁ ገበየሁ
(በአዲስ አበባ በቁምነገር መጽሔት ላይ ታትሞ የወጣ)

‹‹ እረ ለአንተው ቱ ! ባለጌ ! መተፋት ያለበት ለአንተው ዓይነት ነበር ፡፡ . . . እረ እባክህ አፍንጫህንም መያዝ ትችላለህ እንዴ ? አሁን እንዲህ ለብሰህ ላየህ አዋቂና ጨዋ ትመስላለህ ፤ ይሄኔ ስለ ቆሻሻ ጎጂነት የምታስተምር የሳይንስ መምህር ትሆን ይሆናል . . . ነጭ ጋዋን ለብሰህ ምድረ በሽተኛን የምታመናጭቅ ድሬሰር ወይም ነርስ የማትሆንበትም ምክንያት አይኖርም ፡፡ የዚችን ከተማ ቆሻሻ ነቃቅለን እናጠፋለን ከሚሉ ዲስኩረኛ ፖለቲከኞች ተርታም የምትሰለፍ ቢሆንስ ምን ይገርማል ፡፡ እረ ማዘጋጃ ቤት የጽዳት ፣ ውበትና መናፈሻ ስራ ሂደት መሪም ብትሆን ማን ያውቃል ?
Ye koshaha Genda
‹‹ እኔ ግን በዚች ሰፈር ካወቅኩህ ስንት ዘመን ተቆጠረ ? ቀን ቀን ‹ ይሄ ገንዳ ሸተተ ! › እያልክ ምራቅህን ትተፋብኛለህ ፤ ገልምጠኀኝ ትሄዳለህ ! አንዳንዴ ደግሞ እንደ ማስቲሽ ንፍጥህ ተጣብቆ አልከፈት በሚለው የተዥጎረጎረ መሀረብህ አፍና አፍንጫህን ለመደበቅ ትጣጣራለህ ፡፡ በል ሲልህ ደግሞ ‹ ቅርናታም ገንዳ ! › እያልክ በብልግና መፈክር ትለማመዳለህ ፡፡ ማታ ማታ ግን ከእኔ በላይ በመጠጥ ቀርንተህ በሁለት እጆችህ ጥርቅም አድርገህ ይዘኀኝ ገላዬ ላይ ስትሸና አንዳችም ነገር አይከረፋህም ፡፡ አስመሳይ – ሰው መሳይ በሸንጎ ! እንዳንተ ዓይነቱን ስንት የሰው ገንዳ ታዝቤያለሁ መሰለህ ?! ይሄኔ የቆለጥህ ማስቀመጫ ጨርቅና ካልሲህን በተናጥልም ሆነ በጥምረት የሚያሸታቸው ቢኖር ‹ እረ ተመስገን ! › የሚባልልኝ እኔ ነበርኩ ፡፡ እውነት እልሃለሁ አንድዬ ለአፍታም ቢሆን እጅ ቢያውሰኝ እንዲህ በነጋ በጠባ ቁጥር ቆሽቴን አታሳርረውም ነበር ፡፡ በሚያምረው ከረባትህ ጎትቼ አስጠጋህና እንደ አርጋው በዳሶ በጭንቅላትህ እቀብርህ ነበር ፡፡ ይሄ የሰው አህያ ! እንደ ወሎ ፈረስ መልክህን ብቻ ከማሳመር ቀፎ ጭንቅላትህ ውስጥ ንቦች ምግብ እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ ብትፈጥርላቸው አይሻላልም ?

‹‹ ጆኒ ቀዌ መጣች ፡፡ ዛሬ ደግሞ እነዚህ የጎዳና ልጆች እያዋከቡት ነው ፡፡ እንደው እኔም ርስት ሆኜ የሰው ዘር በይገባኛል ሲጣላብኝ ያመኛል ፡፡ ይህን ያወኩት እዛ ቆሼ የተባለ ሰፈር ነው ፡፡ ቢያንስ በዓመት ሶስትና አራቴ ቆሼ እንድሄድ ይፈቀድልኛል ፡፡ ለነገሩማ በየሁለት ቀናትና በሳምንት ሂሳብ ነበር ቆሻሻዬ ሊራገፍ የሚገባው ፡፡ አልፎ አልፎ ስሄድ ታዲያ የሰው ልጅ የገንዳ ቆሻሻን የቦሌ – የጉለሌ ፤ የሸራተን – የሂልተን … በሚል ስያሜ ለፍቶ እንዳገኘው ርስት ሲራኮትበት ፤ ጦር ሲማዘዝበት እመለከታለሁ ፡፡ በእውነት ይሄ የዘርና የጎሳ አስተሳሰብ ቆሻሻ ድረስ መዘርጋቱ ያሰቅቃል ፡፡ ማቲው ብቻ ሳይሆን ነፍስ ያወቀው ሁሉ ‹ ምርጥ ምግብና ምርጥ ዕቃ › ለመሰብሰብ ዘወትር ቡጢውን ሌላው ላይ መወርወር ግዴታው ሆኗል ፡፡ አንዱ አገልግሎቱ ስላበቃ ወይም ስለቆሸሸ ብሎ የጣለውን ሌላው እንደ ብርቅ ማዕድን ቆፍሮ ለማውጣት መታከቱ ያስቆዝማል ፡፡

‹‹ ታዲያ ጆኒ የሚገርመኝ የሚፈልገው የብዕር ቀፎና ማስመሪያ መሆኑ ብቻ ነው ፡፡ እነዚህ ኩይሳዎች እንኳ ላዬ ላይ ወጥተው የሚቦጠቡጡት የተራረፈ ምግብ ፍለጋ ነው ፡፡ ታዲያ ለማይገናኘው ፍላጎታቸው ለምን አጉል ይናከሳሉ ? እውነት ይሁን ውሸት ያበደውም ከቆሻሻ ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው ይባላል ፡፡ ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እንደተመረቀ የከተማው ቆሻሻ እንደ ችግር ሳይሆን እንደ ድሃ አጋር ሊታይ የሚችልበትን ‹ አንድ – በአራት › የተባለ ልዩ የፈጠራ ፕሮጄክት አቅርቦ ነበር ፡፡ ከቆሻሻ አግሮ ስቶን ፣ ነጭ ከሰል ፣ ባዮ ጋዝ እና የካኪ ፌስታል ለመስራት ፡፡ ጉዳዩን ያዳመጡት የሚመለከታቸው ወገኖች ‹ ፕሮጄክትህ ግማሽ እውነት – ግማሽ እብደት የተቀላቀለበት ነው › በማለት አጣጣሉበት ፡፡ እየቆየ ሲሄድ ግን አንዳንድ የፈጠራ ሰዎችና ባለሀብቶች ከጥቅሉ ፕሮጄክት አንድ አንዱን እየመዘዙ ጥቅም አነደዱበት ፡፡ ቀስ በቀስ ደግሞ ‹ ለምን ? እንዴት ? ፍትህ የለም ! › ማለት ያበዛው የጆኒ ጭንቅላት ነደደ አሉ ፡፡ ጆኒ ግን ያሳዝነኛል ፡፡ የጸዳ ነጭ ወረቀት ማለት ነው – ተንኮል ፣ ጥላቻም ሆነ እብሪት አይንጸባረቅበትም ፡፡ በዚህ ለጋ እድሜውም ማበድ አልነበረበትም ፡፡ በርግጥ በሽተኛን ደጋግሞ በማመናጨቅ የሚታወቁት ሀኪሞች በትኩረት ደጋግመው ቢያክሙት ይድናል ፡፡ ጆኒን በትኩረት ቢያጤኑት ሊማሩበትም ይችላሉ ፡፡ ምነው ብትሉ አንድም ቀን ተሳስቶ በአካባቢዬ ሽንቱን ሸንቶ አያውቅም ፡፡

‹‹ ምስኪን ! ከእነዚህ እርጉሞች ጋር ላለመጣላት ነው መሰለኝ አቅጣጫውን ቀየረ ፡፡ መጡ እነዚህ ከፈሳቸው ጋር የተጣሉ ! ዘለው አናቴ ላይ ወጡ ! መነቀሩኝ ! አቤት አስፋልቱ በአንድ አፍታ ቄጤማ ተጎዘጎዘበት ፡፡ ፈንዲሻ ተረጨበት . . . ዕጣን ተለኮሰበት . . . ደስ ይላቸዋል ልበል ?! አልናገርም ፣ አልሰማም ፣ አላይም በሚል ፍልስፍናው የሚታወቀው የአዲስ አበባ ነዋሪም ይፈራቸዋል መሰለኝ አይገስጻቸውም ፡፡

‹‹ ታዲያ ምነው ሮጡ ? . . , አሃ ! ድንጋይ ወርዋሪዋን ወይዘሮ ተካበች አይተው ነው ፡፡ የእኚህ ሴትዮ ልብና በሁለት ገጹ የሚለበስ ጃኬት አንድ ናቸው ፡፡ ሴትየዋ ቀን ቀን ሰው እንዲያያቸው ይህን የመሰለ ልማታዊ ተውኔት ይሰራሉ ፡፡ ሰው አይደለም ውሾች ቆሻሻውን ሲመነቅሩ ዝም አይሉም ፡፡ በጩኀትም ሆነ በፉጨት በል ሲላቸውም ድንጋይ በመወርወር ያካልቧቸዋል ፡፡ ይህ ተግባራቸው ግን አንዳንዴ የከፋ ጉዳት ይዞ ሊመጣ ይችላል ፡፡ አንድ ግዜ የሆነውን ማንሳት ጥሩ ነው ፡፡ የተራቡ ይሁኑ ስሪያ የጨረሱ በርካታ ውሾች ገንዳውን ሲሞነጭሩ በመድረሳቸው ድንጋይ ማዝነብ ጀመሩ ፡፡ ኤፍ ኤም 97.1 ጠዋት ጠዋት ከሳጅን መዝገቡ ጋር አዘውትሮ የሚያሰማውን የትራፊክ ዘገባ ማዳመጥ ከማይመቻቸው ውሾች መካከል ሶስቱ በደመነፍስ ሲካለቡ የትልቅ መኪና ጎማ ደፈጠጣቸው ፡፡ አንድ ቀን ሙሉ ከአስፋልት ማንም ሳያነሳቸው ከተዘረሩ በኃላ መሽተት ሲጀምሩ ወይዘሮ ተካበች የጎዳና ተዳዳሪዎችን አሰባስበው እኔ ጀርባ ላይ እንዲወረወር አደረጉ ፡፡ አቤት ለአንድ ሳምንት የነበረው የአካባቢ ቅርናት ! አቤት ጭንቅላቴን የወረረው የግማት ጥቃት ! ያኔ ጋዜጠኞችን ጠርቼ ጥልቀት ያለው መግለጫ ብሰጥ እደሰት ነበር ፡፡ እረ የሬዲዮ የአየር ሰዓት ገዝቶ የመዘባረቅ ሀሳብ ሁሉ የመጣብኝ ያኔ ነው ፡፡

‹‹ ታዲያ እኚህ ተዋናይ ሴትዮ ዱሪዬዎችንም ሆነ ውሻዎችን ካባረሩ በኃላ ወጪ ወራጁ እንዲሰማቸው የፈጸሙትን ገድል ለደቂቃዎች ይተርካሉ ፡፡ የንግግራቸው ቃናም ሆነ የአካላቸው እንቅስቃሴ ግዜያዊ መድረክ ላይ ያለ አይመስልም ፡፡ በጣም የሚገርመው መነባንቡን የትና መቼ እንደሚያጠኑት ነው ፡፡ ማታ ማታ ሌላ ናቸው ፡፡ የራሳቸውን የጠላ ድፍድፍ ፣ ለሌሎች ተቀጥረው ደግሞ የአትክትልና ፍራፍሬ ልጣጭና ብስባሽ በኔ ዙሪያ ይቆልላሉ ፡፡ ጠዋት ሲነጋ ከሁሉ ቀድመው ‹ አበስኩ ገበርኩ › ን የሚያዜሙት እሳቸው ናቸው ፡፡

‹‹ እኔ የምለው ይህ የከተማ ህዝብ እስከመቼ ነው የምናገባኝ ፖሊሲውን የሚያራምደው ? አንድ ሰሞን በጉንፋንና ኮሌራ ፣ በትውከትና ተቅማጥ ልጆቻችንና እኛ ማለቅ የለብንም ፣ በየአካባቢያችንም በቂ ገንዳ ሊቀመጥ ይገባል በማለት ጩኀቱን አቀለጠ ፡፡ ፊደል የቆጠሩትም ለከተማ እድገት የጽዳት አጠባበቅ አስፈላጊ መሆኑን የሌሎች ሀገሮችን ልምድ በመጠቃቀስ መንግስት ከእንቅልፉ እንዲነቃ ጎተጎቱ ፡፡ የሁሉም ሀሳብ ትክክል ስለነበር እኔና ጓደኞቼ ሰፈር ከተማውን አጥለቀለቅነው ፡፡ ምን ዋጋ አለው ታዲያ ? ጩኀቱ ቆሻሻውን ለመድፋት ብቻ ሆነ ፡፡ ገንዳው ሲሞላ እንዲነሳ ማን ይጩህ ? በግምና ክርፋት አየር ውስጥ ያለመኖር መብታችን ይከበር ! ማን ይበል ?

‹‹ አስተዳዳሪዎቹ በምርጫ ሰሞን ‹ መልካም አስተዳደር እናሰፍናለን ! ህዳሴውን እናረጋግጣለን › ሲሉት ለምን በተጨባጩ ቆሻሻ አያፋጥጣቸውም ፡፡ ሚዛን አትደፋም ተብላ በማትጠቀሰው ቆሻሻ ተግባራዊ ማንነትን መለካት ይቻላል ፡፡ ለምሳሌ አስተዳደሩ የከተማውን ጉድፍ አይደለም በማዘጋጃ ዙሪያ የሚታየውን ሽንትና አይነምድር ማጽዳት አልቻለም ፡፡ የአውሮፓዎችን መንግስታዊ አስተዳደር ቀምሮ ቢያስፋፋ ኖሮ ስንት ግዜ ስልጣኑን በፈቃዱ በለቀቀ ነበር ፡፡

‹‹ ይኀው ስንትና ስንት ዓመት በጀት መመደቢያና መዝጊያ ላይ ፣ የግማሽ ዓመት ስራ አፈጻጸም ላይ አዳዲስ ነገሮች እናዳምጣለን ፡፡ መፍትሄው እጃችን ሊገባ አንድ ሀሙስ ቀርቶታል ይሉናል ፡፡ በምን ይሆን ከተባለ
. የውበትና ጽዳት ተቋም መፈልሰፉ
. የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር መቋቋሙ
. ባለ በርና ባለጎማ ገንዳዎች እየተሰሩ መሆናቸው
. ገንዳ የማንሳት ተግባር 24 ሰዓታት ሙሉ እንደሚከናወን
. ደረቅ ቆሻሻ ወደ ጠቃሚ ግብዓት የሚቀየርበት አሰራር መፈጠሩ
. የደረቅ ቆሻሻ የቆየ ችግር በተደራጁ ማህበራት እንደሚንበረከክ ይነገራል ፡፡ ይህ ዓይነቱ የወረቀት ዲስኩር ከጆኒ ቀዌ ፕሮፖዛል በምን ይሻላል ? አስተዳደሩ ከጆኒ ቀዌ የሚለየው አንደኛውን ጨርቁን ጥሎ አለመታየቱ ነው ፡፡

‹‹ በርግጥ አስተዳደሩ ከተማዋ ለአፍሪካ ህብረት መቀመጫነት አትመጥንም የሚል የሰላ ትችት በውጭ ሰዎች ድንገት ሲቀርብ የሆነ ነገር ለመስራት ተፍ ተፍ ይላል ፡፡ ለልምድና ተሞክሮ ልውውጥ የጽዳት ሰራዊቱን በምድረ አፍሪካ ይበትናል ፡፡ አንድ ሰሞን ኪጋሊ ደርሶ የመጣው ልዑክ ጆሮአችንን አደንቁሮት ነበር ፡፡ ‹ እውነት ሰው በላዋ የሩዋንዳ ከተማ እንደዚህ ውብ ናት ? › የሚለው ግርምት ከልክ በላይ ተጭኖብን ነበር ፡፡ ሰው በጦርነት ሲበላ የከረመ ከተማ የኃላ ኃላ በውበት የሚልቅ እስኪመስል ድረስ ፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ አዲስ አበባ የኪጋሊ አቻ ለመሆን የቀረበች ናት ፡፡ የቀይና ነጭ ሽብር ባለታሪክ ናትና ፡፡

‹‹ የጽዳት ሰራዊቱ ግብም በአንድ ተጨባጭ ለውጥ እንደሚደመደም ተገምቶ ነበር ፡፡ ግን የዚህን ሀገር ተግባር አውሎ ንፋስና ማዕበል ሳይሆን ወሬ ነው የሚበላው ፡፡ ይባስ ብሎ በቅርቡ ደግሞ በጥናት ሳይሆን በአውሎ ንፋስ የመጣ የሚመስል ዜና የከተማዋን ኃላፊዎች አሙቋቸዋል ፡፡ ሎንሊ ፕላኔት የተባለ ዓለማቀፍ የጉዞና አስጉበኚ መጽሀፍ ካምፓኒ አ/አ በ2013 ሊጎበኙ ከሚገባቸው አስር የዓለማችን ከተሞች አንደኛዋ ናት በማለት ምስክርነቱን ሰጥቷል ፡፡ ይሄን ያልኩትም ከተማዋ ፈጣን እድገት እያሳየች በመሆኑ ነው ብሏል ፡፡ መቼም ይህ ድርጅት የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ቢሆን ኖሮ ሚዛን ያልጠበቀ ዜና በማሰራጨቱ ፍ/ቤት ሊቆም አሊያም ሊታገድ በቻለ ነበር ፡፡ ደግነቱ ስምን መልዓክ ያወጣዋል የሚል አባባል መኖሩ ፡፡ ሎንሊ ወይም ብቸኛው ድርጅት ያወጣውን ዘገባ ሌሎች አልደገፉትም ፡፡ ‹ ብቻህን ተወጣው ! › የተባለ ይመስላል ፡፡ እረ ‹ ፈረንጁ ዋልታ ማዕከል ! › ያሉትም ሳይኖሩ አይቀርም ፡፡ ብቻ ብዙ የሚጋጩ ነገሮች ስላሉ ከእንቅፋቱም ከነገሩም ላለመላተም ግራና ቀኝ እያስተዋሉ መጓዝ ይበጃል ፡፡ ለምሳሌ ባለስልጣኖች የሚፈሩት ፎርበስ / Forbes / አዲስ አበባ የዓለማችን ስድስተኛዋ ቆሻሻ ከተማ መሆኗን ነው በቅደም ተከተሉ የሚያሳየው ፡፡ ይህ አይነቱ መረጃ ከሎንሊ አይደለም ከሞተው ብሩስሊ ጋር ካራቴ አያማዝዝም ?

‹‹ አዲስ አበባ ትንሳኤ ማግኘቷን ታረጋግጥ የነበረው ያ ማነው ; . . . ጉዳዬ ሳይሞላ እያለ ያዜመው . . . እ . ጋሽ አበራ ሞላ እንዳጀማመሩ ቢዘልቅበት ነበር ፡፡ ልብ በሉ ! አበራ ሞላ ሲያንጽ የነበረው ጽዳት ብቻ አልነበረም ፡፡ የአስተሳሰብ ለውጥና ውበትንም ጭምር እንጂ ፡፡ በከተማችን ስንት ሞተው ኀውልት የቆመላቸውን ቦታዎች አይደለ አንዴ እንደ ፈጣሪ . . . ‹ እፍ ተነሱ ብርሃን አግኝታችኃል › እያለ ያነቃቸው ፡፡ ካድሬዎች ግን በግምገማቸው አበራ ሞላ በከተማዋ ያበዛው ማሰሮና መፈክር ነው ማለታቸው ተሰምቷል ፡፡ እረ በሀገራችን ታሪክ መፈክር አብዝቶ የማያውቅ መንግስት ነበር እንዴ ? መፈክሩስ ያን ያህል እየበሉ የተኙ አስተዳዳሪዎችን አብሽቋል ? ግራ የሚያጋባ ነው ፡፡ እስኪ አንድ አራቱን እናስታውስ !
. ቆሻሻ ወዮለት !
. የሸና ይሸነሸናል !
. ጽዳት ሲለካ ስልጣኔ ነው ለካ ?!
. የአበራ ሞላ እንባ ፈሶ አይቀርም !

‹‹ ምናልባት የመጨረሻዋ ?! ድርጅቱ አንደኛ ከሰብዓዊ ሰዎች ይልቅ ግእዙ ግንባር ደምቆ እንዲጠራ ነው የሚፈልገው ፡፡ በግምገማው ላይ ለመሆኑ እንዲህ ከመሬት ተነስቶ የጀገነው አበራ ማነው ? የት ነበር ? የኃላ ታሪኩ ምን ያመለክታል ? እውነተኛ ፍላጎቱ ምንድነው ? የሚሉ ጥያቄዎች በጉልህ ተነስተው የማያዳግም ምላሽ እንዳገኙ ይገመታል ፡፡ ሁለተኛ ጋሽ አበራ የሚዳክረው በሀገር ተቆርቋሪነት እንጂ በድርጅት መስመርና አቅጣጫ አይደለም ፡፡ ታዲያ ይህን በፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በህዝብ ያልተመረጠ ዜጋ ለማድነቅ እንዴት ይመቻል ? ውጤቱስ ከአሳጭነቱ አኳያ እንዴት ይመዘናል ? ጥያቄው እነዚህና የመሳሰሉት ናቸው ፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ ለበኃላ የተሞክሮ ቅመራ እንዲያመች ሳያደናቅፉት መመልከት አሊያም ቀረብ ብሎ መደገፍ ሲገባ ጠላልፈው ጣሉት ፡፡ የተቀደሰ ሀሳቡን ቀምተውት እንኳ የእሱ ጎዳናን መጨረስ አለመቻል ያሳዝናል ፡፡

‹‹ የከተማው አስተዳደር መቋቋምና ማሸነፍ ካልቻለባቸው ጉዳዮች አንዱ ጽዳት መሆኑ ይታወቃል ፡፡ ብሎ ብሎ ሲያቅተው ደጋግሞ የሚያነሳት ምክንያት ‹ ህዝቡ የአስተሳሰብ ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም ! › የምትል ናት ፡፡ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዴት ሊመጣ እንደሚችል ግን የጠለቀ ግንዛቤ ያለው መሆኑ ያጠራጥራል ፡፡ ገንዳዎች በየአደባባዩ ከተቀመጡ ሰዎች በአካባቢው ይሸናሉ በሚል ወደ መንደር ማራቅ ተጀምሮ ነበር ፡፡ ግን ገንዳዎች ባይኖሩም የከተማችን ግንቦች ዛሬም በቀንም ሆነ ማታ እንደጉድ ይሸናባቸዋል ፡፡ ይህን ችግር ጠልቆ ያለመረዳት ነው ስንኩልና ፡፡ እንኳን ሽንት ቤት መኖሪያ ቤት የሌለው የከተማ ህዝብ ጭንቀቱን የት ይክፈል ? አስተዳደሩ በየቀበሌውና በየሰፈሩ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃ ቤቶችን መገንባት ቢኖርበትም አላደረገውም ፡፡ ጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆችን በየቦታው እንደ አሸን ሲያፈላ ለሽንት ቤት ግን ቦታ የለኝም ይላል ፡፡ ያሉትን ክፍት ቦታዎች በሙሉ በሰብዓዊነት ሳይሆን በገንዘብ ጭንቅላት እያሰበ ግንባታ እንዲጥለቀለቅባቸው ያደርጋል ፡፡ ለልማት ግንባታ የማይደረግ ነገር የለም በሚል ለመንገድ ግንባታ ቤቶችን ያፈርሳል ፡፡ ሽንት ቤት ለመገንባት ለምን ቤቶች እንዲፈርሱ አይደረግም ? ይህ ነው የአስተዳደሩ የአስተሳሰብ ችግር ፡፡ ልማት ማለት አስፓልትና ኮንዶሚኒየም ብቻ ነው ? በአምስት ዓመቱ እቅድ ላይ የጤና ነገር ትልቅ ቦታ እንዳለው ነው የሚታየው ፡፡ በጤና ፖሊሲው ላይ 16 የሚደርሱ ትላልቅ የጤና ፓኬጆች ተቀምጠዋል ፡፡ የግለሰብና የአካባቢ ጤና ጉዳይ ከዚህ ውስጥ በመፍራሙ ደምቆ ይታያል ፡፡ ይህ ማለት ታዲያ በቂ መጸዳጃ ፣ በቂ ገንዳ ፣ በቂ የጽዳት አስተዳደር ማለት አይደለም ፡፡ ይህን ድብቅ ማንነት ሳይገላለጹ ህዝብን በአስተሳሰብ ችግር መገሰጽ የት ያደርሳል ? ይኀው እንደምናየው የትም ! እረ ልማትስ የሚፋጠነው ጤነኛ ዜጋ ሳይፈጠር ነው ? ጽዕዱ ማህበረሰብም በፖለቲካው ረገድ ክብር እንዳለውም መገንዘብ ያስፈልጋል ፡፡

‹‹ ለማንኛውም ገንዳን ለማጽዳት ፍትሃዊ ፣ ግልጽና የጸዳ አስተሳሰብ ያስፈልጋል ፡፡ ይህን ሃሳብ በተጠማዘዘ መንገድ ላስረዳ ፡፡ አስተዳደሩ በስሪቱ ውስጥ የወይዘሮ ተካበች አይነቶችን በብዛት ከመቆለልና ከመካብ ፤ የጆኒ ቀዌ አይነቱን እያከመ ፣ እየደገፈና የስራ ነጻነታቸውን እያረጋገጠ ቢቀጥል ያዋጣዋል ››

Health: ጤናማ ሆኖ ለመቆየት 6ቱ ምርጥ ጥቆማዎች

$
0
0

ከግርማ ብርሃኑ
eyehealthእርጅናን መዋጋት
በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል በሳምንት ለ3 ወይም 4 ቀናት የእግር ጉዞ ማድረግ ብቻ እርጅናን ለመዋጋት በቂ መሆኑን ያውቃሉ? በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው በሰውነታችን የሚገኝን የጉልኮስ መጠን ማቃጠል መቻል ከምንም ነገር በላቀ እርጅናን መከላከል እንደሚያስችል ያረጋገጠ ሲሆን በተለይ ቀኑን ሙሉ ቢሮ ተቀምጠው የሚውሉ ሰው ከሆኑ የእግር ጉዞ ማድረጉ ሌሎች የበሽታ አይነቶችን ከመከላከል አንፃር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
በአንዳንድ የጃፓን ከተማ ታላላቅ ድርጅቶች ውስጥ የቡድን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ባህል እየሆነ መጥቷል። በእነዚህ ድርጅቶች በ20 ደቂቃው ደወል የሚደወል ሲሆን በዚህ ጊዜ ማንኛውም ሠራተኛ ስራውን አቁሞ ሰውነቱን ማፍታታትና ማሳሳብ ይገባዋል። ይህን ካደረጉ በኋላ ግን ምንም እንዳልተፈቀረ ወደ ስራቸው ይመለሳሉ። የጃፓን ስ/አስኪያጆች ሠራተኞቻቸውን ውጤታማ ለማድረግ ይህን ሲያቅዱ እግረ መንገዳቸውንም የሠራተኞቻቸውን እርጅና እየተዋጉ መሆኑን ልብ ይበሉ።
ጭንቀትን መዋጋት
ጭንቀት የዕለት ተዕለት ተግባርዎ ነው? መልካም። እንግዲያውስ ዛሬውኑ ከጭንቀትዎ ሊፈወሱ ይገባል። በእርግጥ የሰው ልጅ ከጭንቀት ሊርቅ አይችል ይሆናል ነገር ግን ጭንቀት በትክክለኛው ጊዜና ቦታ መሆን ይገባዋል። የፒንሴልቫኒያ ዩኒቨርሲቲ ሳይኮሎጂስቶች በዚህ ችግር ተጠቅተው ያገኟቸውን ሰዎች አንድ ምክር ይለግሳሉ። ይኸውም በጭንቀት የተጠቁት ሰዎች በየቀኑ ለ20 ደቂቃ ያህል ‹‹የጭንቀት ክፍለ ጊዜ› እንዲመድቡና ይህንንም በተመሳሳይ ሰአትና በተመሳሳይ ቦታ እንዲተገብሩት ነበር የመከሩት። በእነዚህ 20 ደቂቃዎች ልጨነቅባቸው ይገባኛል ጥቆማዎች ያሏቸውን ጉዳዮች አሰባስበው መጨነቅ የሚገባዎትም በእነዚህ 20 ደቂቃዎች ውስጥ
ብቻ ሲሆን ከዛ ውጭ ካሉት ጊዜያት በምንም ምክንያት ለመጨነቅ ዝግጁ መሆን/መፍቀድ/ አይኖርብዎትም። ይህን ልማድ ማዳበር ‹psychosomatic› ከሚባሉ ስነ-ልቦናዊ ችግሮች ለመዳን ብሎም ቀስ በቀስ ጭንቀትዎን በቀላሉ መቆጣጠር የሚችሉባቸውን መንገዶች መረዳት ያስችልዎታል። ይሞክሩት።
የልብዎ ጉዳይ
አተኛኘትዎ ምን ይመስላል? በሆድዎ አልያም በግራ ጐንዎ የሚተኙ ከሆነ ልብዎ የሰውነትዎን ክብደት እንዲሸከም እያደረጉት ሲሆን ይህም ልብዎ ደም በመርጨት ረገድ በምታደርገው ጥረት ላይ አሉታዊ ችግር ይፈጥራል። እንግዲህ ያስቡት የዕድሜዎትን 1/3 ያህሉን ጊዜ የሚያሳልፉት ተኝተው ሲሆን በዚህ ሁሉ ጊዜ ልብዎ እንድትጨነቅ መፍቅድ አይኖርብዎትም። እንግዲያውስ በጀርባዎ ወይም በቀኝ ጐንዎ የመተኛት ልማድ ያዳብሩ።
በሲጋራ አመጣሽ ካንሠር
አለመሞት

የሚያጨሱ ከሆነ ማጨስ ቢያቆሙ መልካም ነው። አይሆንልኝም፣ ካሉም በሲጋራ ከሚመጣ ካንሠር ለመዳን የካሮት ጁስ ይጠጡ። እንደ ጀርመን የህክምና ባለሙያዎች ገለፃ በካሮት ውስጥ የሚገኘው ‹Carotene›የተሰኘ ንጥረ ነገር ካንሠርን በመከላከልም ሆነ አልፎ አልፎም በማዳን ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
እንደየህክምና ባለሙያዎቹ ገለፃ 60 ሲጋራ በቀን የሚያጨስ ሰው 4 ብርጭቆ የካሮት ጁስ ቢጠጣ ለካንሠር የመጋለጥ እድሉ የማያጨሱ ሰዎች ያህል የቀነሰ እንደሚሆን ይናገራሉ። በእርግጥ የካሮት ጁስ ለመጠጣት የግድ አጫሽ መሆን አይገባዎትም። ለጤንነትዎ ቢጠጡት ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም።
አይንዎን ይጠብቁ
የአይናችን አፈጣጠር ቅርበት ባለው ነገር ላይ ለረጅም ሰዓታት ማተኮርን አይፈቅድም። ምናልባት በስራዎ ጠባይ ረጅም ሰዓታትን የኮምፒውተር መስኮት ላይ አተኩረው መዋልን የሚጠይቅዎ ከሆነ ወይም ረጅም ሰዓት ቴሌቪዥን መመልከት የሚያዘወትሩ ከሆነ በየመሀሉ ቴሌቪዥኑን /ኮምፒውተሩን መመልከት ያቁሙና አይንዎትን ያፍታቱ። ለምሳሌ አይንዎትን በትልቅ ክብ ቅርፅ እንዲያይ ማሽከርከር። ወደ ግራና ወደ ቀኝ እንዲሁም ወደ ላይና ወደታች መመልከት ይመልከቱ። ወይም በመስኮትዎ አሻግረው ራቅ ያለ አካባቢን በአይኖችዎ ለመቃኘት ሙከራ ያድርጉ። በዚህም መንገድ አይኖችዎን በቀላሉ ከጉዳት መታደግ ይቻልዎታል። ይህ ሁኔታም ከአይኖችዎ በተጨማሪ አዕምሮዎ ዘና እንዲል ምክንያት ይሆናል።
ውፍረትን ይከላከሉ
የፓኪስታን ሴቶች ውፍረትን ለመከላከል የሚጠቀሙበት አስገራሚ መንገድ አለ። ይህን መንገድ ሲሰሙ በውጤቱ ላይ ጥርጣሬ ሊያድርብዎ ቢችልም ይሞክሩት። አስገራሚ ለውጥ ያያሉ።
የፓኪስታን ሴቶች እንደላስቲክ (የብር ላስቲክ) ያለ ነገር በእጃቸው ላይ ያደረጋሉ። ይህ በእጅ ላይ የሚደረግ ላስቲክ ዘላቂነት ያለው ጫና በነርቭ ስርዓታችን ላይ ስለሚያስከትል ሰውነታችን ክብደትን ለመከላከል አስተዋፅኦ ያላቸውን ኬሚካሎች ማመንጨት ይጀምራል። ላስቲኩን አንዱን ከክንድዎ ዝቅ ብሎ ሌላውን ከእጅዎ መታጠፊያ በታች ያድርጉት። ይህ ዘላቂነት ባለው ሁኔታ መደረግ ሲኖርበት በጣም ጠብቆ የደም ዝውውርን የሚገታ ወይም በጣም ላልቶ ቦታውን የሚለቅ እንዳይሆንም ጥንቃቄ ያድርጉ።

ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 50 – PDF

ጥላሁን ገሠሠና የትንሳዔ በዓል

$
0
0

(ቅዱስ ሃብት በላቸው)

tlahoun_gessesse
የትንሳዔ በዓል ሲመጣ ትውስ ከሚሉኝ ሰዎች አንዱ ምትክ የለሹ ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ንጉስ አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ ነው። በኢትዪጵያውያን የሙዚቃ አፍቃሪዎች ልብ ውስጥ ታላቅ ስፍራ የሚሰጠው ይህ የዘመናችን ታላቅ የኪነጥበብ ሰው ድንገት በሞት የተለየን ከአራት ዓመታት በፊት ሚያዝያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም የትንሳዔ ዕለት ነበር። በዚህም የተነሳ የፋሲካ ሰሞን ድብልቅልቅ ባለ ስሜት መዋጡን እየተለማመድኩት መጥቻለሁ። የእምባ ከረጢቴ ባዶ እስኪሆን ድረስ ቢያነፋርቁኝም የጥልዬን ዘፈኖች ማድመጥ አብዝቶ ይመቹኛል። ዛሬም በዚሁ የመንፈስ ባህር ላይ እየተንገዋለልኩ ነው!!
ጥላሁን ለ53 ዓመታት በዘለቀው የመድረክ ቆይታው በሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ዘላለማዊ የሆነ ስም ለመትከል ያስቻለው ልዩ ጣዕም ያላቸው ሙዚቃዎቹ፤ እንዲሁም በመድረክ ላይ በሚያሳየው ማራኪ እንቅስቃሴው ብቻ ሳይሆን ለአድናቂዎቹ በሚሰጠው አክብሮት ጭምር እንጂ!!
ጥልዬ! … በተለይም በዓል ሲመጣ ትውስ ከሚሉኝ ነገሮች አንዱ በልጅነት ዕድሜዬ ቤተሰቦቼም ሆኑ ጎረቤት ወዳጅ አዝማዶቻችን በጉጉት ከሚጠብቁት ነገር አንዱ የጥላሁን ገሰሰን አዲስ የሙዚቃ ስራ ነበር። የዋህ፣ ቅን፣ ደግ፣ ሩህሩህ፣ የዕውነት ጠበቃና እጅግ መልካም ሰው ነበርክና እግዚአብሔር አምላክ ነፍስህን ለገነት ያበቃልን ዘንድ ዘንድሮም ሆነ ወደፊት ስላንተ እንፀልያለን!! ስራዎችህም የትናንት፤ የዛሬ፤ ወይንም የነገ የሚባሉ ሳይሆኑ ዘላልማዊ ናቸውና በማይቀረው ሞት ተለይተኸን ስጋህ አፈር ቢለብስም ምንጊዜም እናስታውስሃለንና በመንፈስ ተለይተኸን አታውቅም!!

ሰዎች ስለ ጥላሁን ምን ብለው ነበር? ለትውስታም ይረዳ ዘንድ እስኪ አንዳንዶቹን ዛሬ ላካፍላችሁ!
«ጥላሁን ገሰሰ በአገራችን የሙዚቃ ድርጅት እንደተዓምር የተፈጠረ የአዕምሮ ሃኪም ነው» (ስሙ ያልታወቀ ሰው ከተናገረው)

«ጥላሁን ገሰሰ ለተፈጠረለት ዓለም፤ ግዴታውን በተሰጥዖው ተወጥቷል። ሕይወት ክቡር መሆኗን መስክሯል፤ እንግዲህ በዝች ምድር ይህን ያሕል የጣረ ሰው ምን አለ ደጋጉን ዳግመኛ ቢፈጥረው በማለት ያንጎራጎረው ታዲያ እንደርሱ ግምት ቢሆንማ ኖሮ እኛም ጥሌን በየዘመኑ ደግመን ደጋግመን ባገኘነው ነበር»፡አንጋፋው የዜማ ደራሲ አቶ ተስፋዬ ለማ 1985 ዓ.ም)

«ጥላሁን ከአባቶቼና ከእናቶቼ ጊዜ ጀምሮ፤ የኛ ሁሉ ታናናሾች ትንንሽ ልጆች ድረስ መወደድ የቻለ ታላቅ ሰው ነው። ለአንድ አርቲስት ደግሞ ከዚህ የበለጠ ትልቅ ስጦታ የለም። (አርቲስት ኩኩ ሰብስቤ)

«ጥላሁን ዘፈኑ ቀርቶ ለቅሶው ያረካኛል።» (ታላቁ ጋዜጠኛና ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ)

«በዘመናችን ውስጥ ዋይ! ዋይ! የተሰኘውን የለቅሶ ቃል፤ ለዘፈን ቅላጼ ሆኖ ሲዘፈን የሰማነው በዘመናዊው የጥላሁን ድምፅ ነው። (ኣዲስ ዘመን ጋዜጣ 1956 ገብረ-አብ ተፈሪ)

«ጥላሁን አርቲስት አይደለም፤ ራሱ አርት ነው፤ ጥላሁን ሳይዘፍን የሚደመጥ ሰው ነው። እርሱን ገና መድረክ ላይ ሲያዩት ማልቀስ የሚቃጣቸው ብዙዎች ናቸው። ብቻ ጥላሁን የሰራቸው ስራዎችም ሆኑ ሌሎቹም ነገሮች ተደማምረው አንድ ትንሽዬ የመድረክ አምላክ ፈጥሯል» (ጋዜጠኛ ደረጄ ደስታ)

«ጥላሁን ነፍስ ያለው ሕያው ሃውልት ነው። በተለያየ ርዕስ የሁሉንም ህይወት እየዘፈነ ብዙ የኖረ ሰው ነው። ለዚህ ነው ጥላሁን ብዙ፤ ለኛ ደግሞ አንድ ስሙ ጥላችን ነው፤ በርሱ ተወደናል፤ በርሱ ተከብረናል » (አርቲስት ነዋይ ደበበ)

«ዘወትር ወደ መኝታዬ ከመሄዴ በፊት አንድ የጥላሁንን ሙዚቃ መስማት አለብኝ።» (ድምፃዊ ታምራት ሞላ)

«ከብዙዎቹ የአገራችን ታዋቂ ድምፃውያን ጋር አብሬ ሰርቻለሁ። ጥላሁን አንድ ካሕን ቤተ መቅደስን የሚያከብረውን ያህል መድረክን የሚያከብር ድምፃዊ ነው፤ ከመድረክ በፊት ሳጫውተው ቆይቼ ልክ ሙዚቃው ሲጀመርና መድረኩን ሲረግጥ ይቀየርብኛል። ሰውነቱም፤ ውስጡም፤ አይኑም ይለወጣል። ይህንን ሌሎቹ ላይ አይቼው አላውቅም።

«ሁሉም አርቲስቶች በየራሳቸው ችሎታና በየራሳቸው የድምፅ አወጣጥ በመዝፈን አድማጭን ይማርካሉ። ጥላሁን ገሰሰ ግን ድምፁን ከግጥሙ፤ ግጥሙን ደግሞ በውስጥ መንፈሱ አዋሕዶ ከአካላቱ እንቅስቃሴ ጋር አቀነባብሮ ሶስቱን በአንድ ጉልበት እንደመብረቅ የሚያሰራጭ ስሜት ያለው ድምፃዊ አላየሁም »

«ጥላሁን ገሰሰ ፈፅሞ የጥቅም ሰው አልነበረም፤ በጣም የሚገርመኝ ነግር ይህ ነው። አንድ ወቅት ላይ ሳናግረው አንተ እኮ ንጉስ መሆንህን ታውቀዋለህ? አልኩት። እርሱ ግን የምቀልድበት ነው የመሰለው። በዚህ የድምፃዊያን ንጉስነቱ ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም ለማግኘት እንኳን የሚጓጓ ሰው አልነበረም። ይህ ባህሪው በጣም ይገርመኛል። ብዙዎቹ የአገራችን አርቲስቶች ብልጭ ብለው ድርግም የሚሉት ቶሎ ገንዘብ፤ ሃብት፤ መኪና አግኝቶና ተዝናንቶ ይከስማል። አብዛኞቹ የጥቅም ጉዳይ ይጥላቸዋል። ጥላሁን ገሰሰ በዚህ ድምፁ ገንዘብ ለማግኘት የጓጓበት ጊዜ እኔ እስከማውቀው ጊዜ ድረስ አልነበረም። (ታዋቂው የቲያትር ደራሲ፤ አዘጋጅና ተዋናይ ጌታቸው አብዲ)

«ጥላሁን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሱዳን፤ በሱማሊያ፤ ባጠቃላይ በምስራቅ አፍሪካ እጅግ ተወዳጅ የነበረ ታላቅ የሙዚቃ ሰው ነበር።
(የቀድሞ የስራ ባልደረባው ታዋቂው ኤርትራዊ ድምፃዊ በረከት መንግስተ አብ)

(የ ኤርትራ ቴሌቭ ዥን የጥላሁንን ሞት አስመልክቶ ከሰራው ድንቅና የተዋጣለት ዘገባ የተቀነጨበ)

(ይህን አርቲክል ቢያነቡት ይጠቀማሉ – እዚህ ጋር ይጫኑ)

አባይ፤ የኢህአዴግ አባል ነውን!? –ከአቤ ቶኪቻው

$
0
0

አቤ ቶኪቻው

አቤ ቶኪቻው

“አባይ ማደሪያ የለው ደሞዝ ይዞ ይዞራል…” የምትለው አባባል ከተፈጠረች እነሆ ሁለት አመት አለፋት፡፡ ግዜው ይሮጣል፡፡ ሶስት፣ አራት፣ እና አምስት አመትም እዝችው አጠገባችን ቁጭ ብለው የምናወራውን እየሰሙ ነው፡፡

ከሶስት አመት በፊት መንግስታችን የትራንስፎርሜሽን እቅድ የሚባል ወደ አስማት ቀረብ የሚል ዕቅድ አውጥቶ “ወተት በቧንቧ በየቤቱ እናቀብላለን” አይነት ነገር ሲነግረን ይቺ ነገር የየትኛው “እንትን” ውጤት ትሆን ብለን ስንጨነቅ ሰንበተን ነበር፡፡ ከዛ ወድያው ትራንስፎርሜሽኑን አባይ አጥለቀለቀው፡፡ ከዛስ…. ከዛማ ትራንስፎርሜሽን ተረስታ አባይ አባይ ይዘፈን ጀመር፡፡ ከዛስ…. ምን ከዛስ አለው… አባያችን ከእያንዳንዳችንን ኪስ ውስጥ ዘው ብሎ ገባ….ታ!

ሰላም ወዳጄ እንዴት ሰነበቱልኝ አውዳመቱ እንዴት አለፈ… እንኳንስ አውዳመቱ እና ስንቱ አያልፍም የተባለ ክፉ ቀን አልፏል… አሉኝ እንዴ! አዎ ጥሩ ነገር ብለውኛል፡፡ ቀጥሎም ገና ብዙ ቀኖች ያልፋሉ ዕድሜውን የሰጠን ሰዎችም ቁጭ ብለን እንታዘባለን፡፡ ስለዚህ ዕድሜውን ይለምኑ…! በቅጡ ካወጋን እኮ ሰነባበትን መሰል…! አንዳንድ ወዳጆቼም “በአነስተኛ እና ጥቃቅን ፅሁፎች አደከምከን እኮ” ሲሉ በውስጥ መስመርም በአደባባይም ተግሳጽ ልከውልኛል፡፡ ሰዉ ቀላል ተናጋሪ ሆኗል እንዴ…!

ለማንኛውም ዛሬ በአባይ ጉዳይ ላይ ትንሽ እናውጋ ብዬ ተከስቻለሁ…! ይቺ ፅሁፍ ለላይፍ መፅሄት እና እና ለ abetokichaw.com ድረ ገጽ ተብላ የተሰናዳች መሆኗንም እናገራለሁ፡፡ ከላይ በተንደረደርኩት መሰረት ስቀጥል እባክዎን ወዳጄ አብረውኝ ይዝለቁ ብዬ በመጋበዝ ነው፡፡

ለአባይ መዋጮ መዋጮ መባል የተጀመረ ሰሞን እኔ እሰራበት የነበረ የትምህርት ተቋም ከመንግስት ከፍተኛ አካላት ከፍተኛ ቁጥጥር ተጥሎበት ነበር፡፡ ቁጥጥሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአግባቡ ግልጋሎት ለህዝቡ እንዲሰጡ ተብሎ የተወሰደ ነበር፡፡ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እና አለቃችን በዚህ ቁጥጥር የተነሳ የእለት እንጀራችንን እንዳይቆጣጠር፣ እንዳይወሳሰብ፣ ብሎም እንዳይቋረጥ ተጨንቀን፡፡ ተጨንቀንም፤ መስሪያ ቤታችንን በማፀዳዳት ስንተጋ በነበረበት ወቅት፤ የአባይ መዋጮ ነገር እየጠነከረ መጣ… እናስ… እናማ አለቃችን መጀመሪያ የስራ ሃላፊዎችን ሰበሰበ ሰብስቦም ሰራተኛው በሙሉ የአንድ ወር ደሞዙን ለአባይ እንዲለቅ የማሳመን ስራ እንዲሰሩ ተማፀነ፡፡

The Nile River has become a point of contention between Egypt and Ethiopia.

አባይ የኢሕ አዴግ አባል ነውን?


ሃላፊዎቹም ወደ ሰራተኛው ሄደው “ዛሬ የአንድ ወር ደሞዛችንን ባንለቅ ነገ ሁሉንም ደሞዛችንን ስራችንንም ጭምር እንደምንለቅ” አስረዱን እኛም ነገሩ ሲገባን ቃል ገባን፤ “ከነገሩ ጦም ይደሩ” ነውና፤ “ከጠቀመው ይውሰደው” ብለን የአንድ የአንድ ወር ደሞዛችንን እነሆ በረከት አልን፡፡ አቶ በረከትመን አቶ መለስም ፈገግ አሉልን፤ ያኔም መንግስት በመስሪያ ቤታችን ላይ ያሰበውን የጥራት ቁጥጥር ተወልን “እንዳሻሽ ሁኚ” የሚለውን ሙዚቃም ጋበዘን እኛም በደስታ ደነስን….! ጥራት ምናባቱ ጥሪት ነው ዋናው! ለአባይ በሰጠነው ጥሪት የጥራት ቁጥጥሩ ቀረልን እስይ እልልል…. አለልን!

የአባይ መዋጮ ነገር በሁሉም መስሪያ ቤቶች በተለይም በግል ቤቶች እንዲሁ ነበር፡፡ መስሪያ ቤቶች ከመንግስት ጋር አጓጉል ከመሳፈጥ ብለው፤ ለስራ ሃላፊዎች መመሪያ ያስተላልፋሉ፤ የስራ ሃላፊዎች ደግሞ በአለቆቻቸው ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ብለው፤ ሰራተኞቻቸውን እጅህ ከምን ይላሉ፤ ሰራተኞችም ጠቅላላ ደሞዝ ከማጣ የአንድ ወር ደሞዜን ባጣ ይቀለኛል እና ይሁን ብለው ይለግሳሉ፡፡

ይህ በእንዲህ አንዳለ፤

ይቺ አባይ ትልቅ መሸቀያ ሆናለች፡፡ ደግሞ እኮ ሽቀላዋ ይሉኝታ አልባ መሆኗ ነው የሚገርመው፡፡ አንድ ወዳጄ አሁን ላለንበት “ግሎባል ዋርሚንግ” ስጋት ጭስ አልባ መሆን እንጂ ይሉኝታ አልባ መሆን ጠቀሜታ የለውም ብሎኛል፡፡ የኢህአዴግ ባለስልጣናቱ ግን በይሉኝታ አልባ ገንዘብ ስብሰባ ከሀገር ይወጡ እና አጓጉል የሆነ የቅስም ስብራት ሲደርስባቸው በንዴት የሚያወጡት ጭስ “ለግሎባል ዋርሚንጉ” ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን ልብ አላሉትም… ስለዚህ እኛ ልብ እናስብላለን

ሰሞኑን የአባይ ወሬ በከፍተኛ ደረጃ እየተርገበገበ ይገኛል፡፡ በተለይ ኢህአዴግን ወክለው ፌስ ቡኩን የተቀላቀሉ ተበካዮች… (ይቅርታ የፊደል ግድፈት አለ እናርማለን…) በፌስ ቡክ የኢህአዴግ ተወካዮች… ነጋ ጠባ አባይ አባይ እያሉ በጎርፍ ሊያስወስዱን ምንም አልቀራቸው፡፡ እኔ የምለው አንዳንድ ከእኛ የበለጡ የኢህአዴግ ካድሬዎችን ግን ልብ ብላችሁልኝ ከሆነ አባይ ራሱ በአንድ ለ አምስት አደረጃጀት ውስጥ የገባ የኢህአዴግ አባል አድርገው እኮ ነው የሚያዩት፡፡ እውነቱ ግን የታወቀ ነው፤ እንኳንስ ወንዙ እና ሰዉ እራሱ የኢህአዴግ አባል የሚሆነው ለአበሉ ብሎ ነው፡፡ (የዘንድሮ ኑሮ እንደሆነ በአበልም አልተቻለም!) እናም ያለ አበል የኢህአዴግ አባል የሚሆን ከተገኘ አስይዛለሁ… (በቅንፍም የማስይዘው ለፖሊስ ነው ብዬ ማብራሪያ እሰጣለሁ!) የምር ግን አንድ እኔ ነኝ ከአገር ተባርሬ እንኳ ኢህአዴግዬ እያልኩ የማቆላምጣት… እና አንድ እርሳቸው ነበሩ… እንጂ ሌሎቹ በሙሉ ለአበላቸው ሲሉ ነው…! ይቺ አስተያየት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝን እንኳ ሳይቀር ትመለከታለች፡፡ ድሮ የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት… ይባል አንደነበረው የአሁኑን የኢህአዴግ ሰራዊት ግን የሚወልደው የኑሮ ውድነቱ ነው፡፡ አባል ካልሆኑ መብል የለማ!

ታድያ አባይ ለየትኛው አበሉ ብሎ ነው በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ውስጥ የሚገባው…! የትኛው የኑሮ ውድነት አላስቆም አላስቀምጥ ብሎት “ከመሞት መሰንበት” ብሎ በአባልነት ይጠመቃል፡፡ በእውኑ ራሱ ጠማቂ ሆኖ ሳለ ይጠመቅ ዘንድስ እንዴት ይሆንለታል…!

ለማንኛውም አባይ ኢህአዴግ አይደለም፡፡ አባይ አንድነትም አይደለም፡፡ አባይ ኦነግም አይደለም አባይ ግንቦት ሰባትም አይደለም፡፡ አባይ ኢትዮጵያ ነው፡፡ አባይ ወንዝ ብቻም ሳይሆን ሀገር ነው፡፡ አባይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀብት እና ጸጋ ነው፡፡

በቅርቡ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከአውሮፓ ሀገራት ዩሮ ከምድረ አሜሪካ ደግሞ ዶላራቸውን ከአረብ ሀገራትም ድርሃማቸውን አፈስፈስ! አድርገው ለመውሰድ ትልልቅ ቦርሳ ይዘው ሄደውም አልነበር…? ሲመለሱ ግን ትልቁ ቦርሳቸው ብቻ ሳይሆን አነርሱም ሽምቅቅ ብለው ተጣጥፈው እና አንሰው ነበር፡፡ “እኔን ያሳንሰኝ” አይባልም መቼም ከዚህ በላይ የት ልነስ…!

ለዚህ ዋነኛ ሰበቡ ውጪ ሀገር በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያጋጠማቸው ተቃውሞ ነው፡፡ ባለስልጣናቱ ኢትዮጵያ እንደተለመደው፤ “ታመጫለሽ አምጪ አለበለዛ ቤቱን ለቀሽ ውጪ” ማለት የሚሳካ መስሏቸው ቢሄዱም ኢትዮጵይውኑ “አንሰማችሁም” አሏቸው! እውነትም አላቸው፤ እነርሱ ስንት ጊዜ “ድምፃችን ይሰማ” ቢሉ እሺ ብሎ አንድም ቀን ያልሰማቸው መንግስት ገንዘብ አምጡ ሲላቸው እንዴት ሊሰሙት ይችላሉ…!

በውጪ ሀገር ያሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለይም ሀገር ቤት ከመንግስት መሬት ወስደው ቤት መስራት ያልጀመሩቱ… ከአባይ በፊት በርካታ መገደብ ያለባቸው ነገሮች አንዳሉ ጮክ ብለው እየተናገሩ ነው፡፡ ያ ማለት ግን አባይን መቃወም ማለት አይደለም፡፡ አባይ ይገደብ የሰብአዊ መብጥ ጥሰትም ይገደብ፡፡ አባይ ይገደብ እስርም ይገደብ፡፡ አባይ ይገደብ ስልጣንም ይገደብ፡፡ አባይ ይገደብ የእምነት ጣልቃ ገብነትም ይገደብ፡፡ አባይ የግደብ የፕሬስ አፈናውም ይገደብ፡፡ ያኔ የምናመነጨው ሃይል ለጎረቤት ሀገር ብቻ ሳይሆን ለመላው አለም ይበቃል… ስለዚህ ስሙን… ነው የሚሉት፡፡

ይህንን በቅጡ ያልሰሙ የኢህአዴግ የስጋ ዘመዶች ግን በአባይ ላይ ትንፍሽ የሚለውን ሁሉ የኢትዮጵያ ጠላት ማድረጋቸው ሳያንስ ራሱ አባይን በአንድ ለአምስት አደረጃጀት የታቀፈ የኢህአዴግ አባል አድርገውት ቁጭ አሉ! ይሄንን አባይ ቢሰማ ከአጠገቡ የበቀለች ዛፍ ላይ ይሰቀል ነበር፡፡

ከዚች ጋ የምትመሳሰል አንዲት ጨዋታ እነሆ እንደማሳረጊያ ትሁን!

ሰውዬው ሀገር ያስቸገረ ዘራፊ ነበር፡፡ ታድያ የሆነ ጊዜ በቁጥጥር ስር ይውል እና ስቅላት ሊከናወንበት ህዝብ የተሰበሰበበት አደባባይ በአንገቱ ሸምቀቆ ገብቶ ሳለ፤ ንጉሱ አንድ ዕድል ሰጡት “እስቲ እዚህ ከተሰበሰባችሁት ውስጥ እኔ ይሄንን ሰው ባል አድርጌ መክሬ ገስጬ እመልሰዋለሁ፤ የምትል ሴት ካለች ትምጣ” አሉ፡፡ ይሄን ጊዜ አንዲት በሀገሩ የታወቀች እና በዘርፈ ብዙ ችግቿ የምትተች ቢመክሯትም አልሰማ ያለች (ስናጠጋጋም እንደ ኢህአዴግ ያለች ሴትዮ እንበላት) በጥቅሉ በክፉ አመሏ የተነሳ ባል አጥታ ቁማ የቀረች ሴት፤ “እኔ አድነዋለሁ… እኔ መክረዋለሁ…” ብላ ወደ ንጉሱ ዘንድ ቀረበች፡፡ ወንጀለኛውም ወደ ሴትዮዋ ዘወር ብሎ ቢያይ ያውቃታል… አትሆነውም፡፡ አንገቱ ከገመድ ውስጥ ነው… በልቡም የእርሷ ባል ከመባልስ… አለና በአንደበቱ ደግሞ “አጥብቀው…!” አለ!

እና ወዳጄ ኢህአዴግዬ ያለውን ይበለኝ እንጂ ይህን ግን እነግርዎታለሁ፤

አባይ የማንም ባል የማንም አባልም አይደለም፡፡ እርሱ የኢትዮጵያ አብራክ ክፋይ ነው! የማይሆን ጋብቻ ከሚፈፅም…. “አጥብቀው” ብሎ ጥልጥል ቢል ይመርጣል፡፡ አባይ የኢትዮጵያ ነው፡፡ የኢትዮጵያውንን ድምፅ የማሰማ አባይን ሊደፍርም፣ ሊወሽምም፣ ሊያገባም፣ ሊያግባባም ይከብደዋል፡፡

ስናበቃም እንላለን…

ከባዱን ነገር እንደማመጥ እና እናቅልለው!

ወዳጄ ይበሉ ይቺን ታኸል ካወጋን የጤና ያድርግልን፤ ይበሉ ያሰናብቱኝ!

አማን ያሰንበተን!

ዚምባብዌና ሶማሊያ በኢትዮጵያ

$
0
0

ይነጋል በላቸው

እስከ ዳግማይ ትንሣኤ ድረስ ብዙም ረፍዷል አይባልምና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለ2005ዓ.ም የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፡፡ ለቀጣዩ በዓልም ሁላችንንም በሰላም ያድርሰን፡፡
ዛሬ ዕለቱ የፋሲካ ማግሥት ነው፡፡ ያ ሁሉ ግር ግርና ወከባ የታየበት ሃይማኖታዊ በዓል የአንድ ዓመት ዝግጅት የፈጀ እንዳልመሰለ በአንድ ቀን ማግሥት አለቀና ብዘውን ሰው ኦና ቤት አሸክሞ አለፈ፡፡ የወጉን ለማድረስ ከዘመድ አዝማድ የተበደረውንና የተለቀተውን፣ ከመሥሪያ ቤቱ ብድር በመጠየቅ ተዝቆ የማያልቅ ዕዳ ውስጥ የገባውን፣ በውጪም በሀገር ቤትም ከሚገኝ በሀብት የተሻለ ዘመድና ጓደኛ ገንዘብ ቀለዋውጦ ቤቱን እንደጎረቤቱ ለማድረግ የባዘነውን፣ በልመናም በዝርፊያና በስርቆትም በሙስናና በወንጀል ድርጊትም ከሰው ላለማነስ ሲል ዕለቷን አሸብርቆና ደምቆ ለማለፍ የዋተተውን ሁሉ ዛሬ ብናየው ‹እንዲህ ልጠግብ በሬየን አረድኩ› እንዳለችው ሴት በባህል ተፅዕኖ ምክንያት በሠራው አልባሌ ነገር ትናንትን የኋሊት እየተመለከተ ሲጸጸት ልናስተውል እንችል ይሆናል፡፡ ዋናው ጉዳይ ግን ፋሲካም ብዙዎችን ዕዳ ውስጥ ነክሮ ሌሎች 364 ቀናትን ዐርፎ ሊመለስ – እንደገናም በተለመደው የሺዎች ዓመታት አዚሙ ጅሎችንና ከሃይማኖት ያፈነገጠ የሆድ ተዝካር አምላኪዎችን ሊያቂያቂል ወደሰገባው ተመልሷል፡፡ እንደወትሮው ሁሉ በሰሞኑ በዓልም ብዙ አየን፡፡
beg market ethiopia
ሰውነት ሳይላላጥ፣ ኪስ ሳይራቆት፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰላም የሰፈነባት ሀገር ስትኖር ሃይማታዊንም ይሁን ሕዝባዊ በዓላትን ማክበር ደስ ይላል፡፡ በመልካም ዘመን እነዚህ በዓላት እስኪደርሱ ድረስ ያቁነጠንጣል፡፡ ‹መቼ በደረሱ› እያስባለ በደስታና በሃሤት ባህር ያስዋኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሚታየው ሀገራዊ ድባብ ግን የተለዬ በመሆኑ እንዲያ እንድንሆን የሚያደርግ ሳይሆን በተቃራኒው “በዓል ጥንቅር ብሎ ይቅር! ደጉን ዘመን እያስታወሰ በትዝታ ማዕበል ከሚያላጋኝ ይልቅናስ በዓል የሚባል ነገር ከነጭርሱ ባይመጣ ይሻለኛል፡፡ በዓል የሚያምረው ለባለጊዜዎች ነው፡፡ ለእነሱ ደግሞ በዓመት ሦስትና አራት ቀናት ብቻ ሣይሆኑ ሠርክ በዓላቸው ነው፡፡ ምን ሲጎድልባቸው?” በሚል ጥልቅ ሀዘን ውስጥ የሚከት አሰቃቂ ሁኔታ ነው እየታዬ ያለው፡፡
ከፍትህና ፀጥታ ጉዳዮች በተጓዳኝ የአንድ ሀገር የጤንነት ደረጃ ከሚለካባቸው ዋና ዋና መክሊቶች መካከል አንድኛው የገንዘብ የመግዛት አቅም ነው፡፡ የገንዘቡ የመግዛት አቅም እየተልፈሰፈሰ ሄዶ ዜጎች ብዙ ገንዘብ ይዘው የሚገዙት ነገር ግን ጥቂት ከሆነ በዚያ ሀገር ውስጥ አንዳች ትልቅ ችግር ለመከሰቱ ዓይነተኛ ምልክት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የቅርብና የሩቅ ጊዜ የታሪክ መዛግብት ቢፈተሹ ይህን እውነት የሚያጠናክሩ ክስተቶችን አናጣም፡፡ ለምሳሌ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የጀርመን ወንደላጤዎች የመኝታ ቤቶቻቸውን ግድግዳዎች በዚያን ጊዜው ፋይዳቢስ የጀርመን የገንዘብ ኖቶች እየለጠፉ ያሳምሩ ነበር ይባላል – በእጅጉ ጋሽቦ ትርጉመቢስ ሆኖ ነበርና፡፡ ሶቭዮት ኅብረት በምትፈራርስበት ወቅት አንድ ዶላር በዚያን ወቅት ጥምቡን በጣለው ሺዎች ሩብል ይተረጎም ነበር፡፡ በምዕራባውያን ማዕቀብ ክፉኛ የተመታችው ዚምባብዌ የአሁኑን እንጃ እንጂ ቀደም ሲል ከጀርመን በባሰ መልክ አንድ ኪሎ ቲማቲም ለመግዛት የሀገሪቱን ገንዘብ በዶንያ ተሸክሞ መሄድ ያስፈልግ ነበር፡፡ አሁንም የአሁኑን እንጃ እንጂ ሶማሊያ በፈራረሰች የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ውስጥ የዚህችን ሀገር ትላልቅ የገንዘብ ኖቶች እዚህና እዚያ ወዳድቀው ማግኘት ያልተለመደ አልነበረም፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየን በነዚህ ሀገራት ውስጥ የሆነ ተስቦ ወረርሽኝ ገብቶ ሕዝቡንና መንግሥታቱን እያመሰ መሆኑን ነው፡፡ ገንዘብ ዋጋ አጣ ማለት በተዛዋሪ ሕይወት ዋጋ አጣ ማለት ነው፡፡ በምድር ለመኖር ደግሞ የገንዘብ አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ አይገባም፡፡ መሬት የሥጋ እንጂ የነፍስ መኖሪያ አይደለችምና ገንዘብ በቀጥታ ከደም ዝውውር ጋር የተሣሠረ ነው፡፡ ገንዘብ ባይኖር ኖሮ የአሁኑ የዓለም ቅርፅ የተለዬ እንደሚሆን ለመናገር ነቢይ መሆንን አይጠይቅም፡፡ አዳሜ የሚገዳደለውና ትርጉም በሌለው ሁኔታ የሚተላለቀው ከገንዘብ ጋር በተገናኘ ነው፡፡ የድንበር ግጭት፣ የሃይማኖት ልዩነት፣ የዘር መድሎ ወዘተ. ሽፋኖች እንጂ ትክክለኛዎቹ እውነተኛ የጠብ መንስኤ አይደሉም፡፡ ገንዘብና ገንዘብ ሊገዛው የሚችለው ማንኛውም ነገር ሁሉ አስፈላጊነቱ በአንድ ጀምበር ቢያከትም በሃይማኖት ስምም ይሁን በዘርና በቀለም ወይም በሌላ ምክንያት የተቀሰቀሱና አሁን በዓለም የምናያቸው ቁርቋሶዎች ሁሉ በአንድ አዳር እንደጤዛ በረገፉ ነበር፡፡ የሆድ ነገር ሆድን እየቆረጠ አንዱን ከአላስካ ወደ ሣይቤሪያ ይወስዳል፤ ሌላውን ከራስ ዱሜራ ወደራስ ካሳር ይነዳዋል፡፡ ሆድ መጥፎ ነው፡፡ ‹ሆዳም ፍቅር አያውቅም› መባሉም በጣም ትክክል ነው፡፡
የኢትዮጵያን ገንዘብ ስናይ በተለይ በአሁኑ ወቅትና በአጠቃላይ ደግሞ ከግንቦት 97 የጨነገፈ ሀገራዊ ምርጫ ወዲህ እጅጉን አሳሳቢ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ የወያኔውን መንግሥት የውሸት አቅማዳነት የሚገነዘብ ወገን በወያኔ የሚደሰኮረው “ግሽበቱ ከሁለት አሃዝ ወደ አንድ አሃዝ ወረደ፤ ሕዝቦቻችን ሆይ ደስ ይበላችሁ!” ዓይነቱ ይሉኝታቢስ ቱሪናፋ አይታለልም፡፡ እውነቱ እንዲህ ነውና – እቀጥላለሁ፡፡
beg market ethiopiaበሰሞኑ የዓመት በዓል ገበያ ልጀምር፡፡ ደመወዜ ከሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመለስ ዜናዊ ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ ይሁንና እርሱ ከዚያች ከኔ ከምታንስ ወርሃዊ ምንዳው እንደምንም ቆጥቦ እንዳንዳንዶች ተጨባጭ መረጃና ግምት ከሦስት ቢሊዮን የበለጠ ዶላር ማጠራቀም ሲችልና ከዚሁ ገንዘብ የሚበልጥ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት ሲያፈራ እኔ ዓመት በዓሉን የዋልኩት እንደሚከተለው ነው፡፡ የታሪክ ምፀትና አሽሙር ማለትም እንደዚህ ዓይነቱ ገጠመኝ ነው፡፡
ዶሮ 155 ብር – ብዙም ወፍራም አይደለም፡፡ ቀይ ሽንኩርት በጣም ቀንሶ በሰባት ብር ሒሣብ አምስት ኪሎ፡፡ ቅቤ በጣም ከመወደዱ የተነሣ ኪሎው በአማካይ ብር 190 በመግባቱ አልገዛሁም – በዘይት ተሠራ፡፡ ዕንቁላል አንዱን በብር 2፡50 ሒሣብ – ስምንት፡፡ የሥጋ ቅርጫ – ጥሩው ሥጋ – በአማካይ 1800 በመግባቱ ሦሥት ኪሎ ሥጋ በ300 ብር ገዛሁ፡፡ አረቂ ባህል ነውና ለአክፋይ መውሰድ ስለነበረብኝ ከ15 ብር ሽቅብ ወጥቶ በ70 ብር ገዛሁ፡፡ ለልጆች አዲስ ቀርቶ ልባሽ ልብስም መግዛት አልቻልኩም፡፡ በዋዜማው ከጓደኞች ጋር ለመጫወት በ‹ዳች ፔይ ሲስተም›(እኛም – ‹ጨዋታ በጋራ ክፍያ በግል› እንለዋለን) ለሦስት ጃምቦ ድራት ብር 33…
ይህን ኑዛዜ መሰል ንስሃ የምነግራችሁ ወድጄ አይደለም፡፡ እኔ ‹የወፍራም ደመወዝ› ባለቤት ሆኜ በዚህ መልክ በዓሉን በቁጥቁጥ ሳሳልፍ ከኔ የባሰው ድሃማ እንዴቱን ይሰቃይ? ስንቱ ይሆን ጥርኝ ቆሎ እያማረው ቤቱን ዘግቶ በዓሉን ያሳለፈ? እንዳይለምን እያፈረ፣ እንዳይተወው በርሃብ እየተሰቃዬ ለመኖር ሲል ብቻ በሰቆቃ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ስንቱ ይሆን? ማነው የሚያስብለት? ፈጣሪስ የት ገባ? ምን ደበቀው? ምን እያዘጋጀ ይሆን? ቁናውን ሰፍቶ ለመጨረስ ስንት አሠርት ዓመታት ይፈጅበታል?
በመሠረቱ የሀገራችንም ይሁን የዓለማችን ሀብት በሸሃኔና በግራም እየተለካ ለሁላችንም እኩል ይሸንሸን የሚል ፍላጎትም ሆነ ቅዠት የለኝም፡፡ ከፍ ሲል እንደተናገርኩት ምድር የውድድር ቦታ ስለሆነች የልዩነት መኖር የግድ ያህል ነው፡፡ ነገር ግን ሊኖረን በማይገባ የተንቦረቀቀ ልዩነት አንዱ በርሀብ ሊሞት ሲያጣጥር ሌላው በቁንጣን ሊሞት ወረፋ መያዝ ያለበት አይመስለኝም፡፡ የተናግዶታችን(transaction) ትሥሥር ሲፈተሸ በእጅጉ የተፋለሰና ለጥቂቶች ብቻ ክፉኛ ያዘመመ ነው፡፡ ሀብታሙ ለምን ሀብታም ሊሆን እንደቻለ ለማየት አይፈልግም፡፡ በድሃው ትከሻ ሚሊዮኔርና ቢሊዮኔር ከሆነ በኋላ በራሱ ብቸኛ ልፋት የከበረ ይመስለዋል፡፡ ነገር ግን ያ ስህተት ነው፡፡ እንደኔ ሀብታም ጭንቅላት ቢኖረው ኖሮ የዓለማችን ችግሮች በግማሽ መፍትሔ እንደሚያገኙ ይሰማኛል፡፡
የትም እንሂድ ሀብታም በራሱ ጥረት ብቻ ሀብታም አልሆነም፡፡ እየበዘበዘና የድሆችን ጉልበት እያለበ ነው አንድ ሀብታም ሀብታም የሚሆነው የሚል ፅኑ እምነት አለኝ፡፡ አንድ ሰው ምን ቢለፋ 60 ቢሊዮን ዶላር ሊኖረው አይችልም ወይም ቢያንስ ሊኖረው አይገባም፡፡ በፎርብስ ግምት መሠረት በዓለማችን ሊኖሩ እንደሚችሉ ከተገመቱ ሁለትና ሦስት ሺህ ቢሊየኔሮች መካከል በትክክል ሠርቶና ለሚያሠራቸው ሰዎች ትክክለኛ የላባቸውን ዋጋ ከፍሎ የከበረ ሰው ለማግኘት በእጅጉ አስቸጋሪ ነው፡፡ አንድ ቢሊዮኔር ለአንድ ውሻው የሚመድበውን የወር በጀት ለአንድ ሠራተኛው ቢመድብ ሠራተኛው ዕድለኛ ነበር፡፡ ነገር ግን በአራቱም ማዕዘን ብናይ ሰዎች ለሰዎች ሲከፉና ተገቢውን የጉልበት ዋጋ ሲከለክሉ፣ እነሱ ሕዋን ሳይቀር ሲጎበኙ ሠራተኞቻቸው ግን አስፕሪን እንኳን መግዛት እያቃታቸው በህመም ሲሰቃዩ ለመመልከት ተገድደናል፡፡ ለዚህ ሳይሆን ይቀራል ክርስቶስ ‹ ሀብታም መንግሥተ ሰማይ ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይቀላል› ማለቱ?
ነገር በነገር እየተጣለፈ የት ጀምሬ ምንን ይዤ ወደየት መሄድ እንዳለብኝ ዘነጋሁት እንጂ አነሳሴ ስለኢትዮጵያ ገንዘብ መጋሸብ በመጠኑ ለማውራት ነበር፡፡ ይሁን፡፡ ዋናው ቁም ነገር፣ ቁም ነገር መናገሬ ነው – ቁም ነገር ተናግሬ ከሆነ፡፡
በሀገራችን ገንዘቡ የማሽላ እንጀራ ከሆነ ቆይቷል፡፡ ሀገሪቱ ባለቤት የሌላት እስክትመስል ድረስ በኳስ አበደች ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን፡፡የፖለቲካውን አመራር ማን ይያዘው ማን ሌላ ነገር ነው፡፡ ማንም ይያዘው ለጊዜው እሱ የማያሳስበን ዜጎች እየበዛን መጥተናል፡፡ ዝንጀሮዋ ‹ቀድሞ የመቀመጫየን› እንዳለችው ቀምሶት የሚያድረው ምናምኒት የሌለው ዜጋ ቁጥር ሀገር ምድሩን እያጥለቀለቀው በሚገኝበት ሁኔታ የፖለቲካውን ልጓም ወያኔ ይያዘው ቻይና ትጋልበን አናውቅም(ቻይና በማይረባ ሸቀጦቿ አጥለቀለቀችን! በጣት በሚጠረቆስ ቱቦላሪ ብረት፡፡)፡፡ ኢኮኖሚው ግን ክፉኛ በመናጋቱ የገንዘባችን የመግዛት አቅም ቃላት ከሚገልጹት በላይ ወድቋል፡፡ ገንዘብ ወድቆ ኢኮኖሚው ጠንክሯል የሚባለው ፈሊጥ አይገባኝም፤ ‹የኑሮ ውድነቱ መንስኤ የኢኮኖሚው ዕድገት ነፀብራቅ ነው› መባሉም መራራ ቀልድ ነው፡፡ አዲስ አበባና አካባቢዋ በወያኔ ሀብታሞችና በጫማ ላሾቻው የተገነቡ ሕይወት አልባ ባዶ ሕንፃዎች፣ የዱርዬው መንግሥት በብድርና በተራድዖ ከሚያገኘው ብዙ ገንዘብ ውስጥ ጥቂቱን በማውጣት የሚሠሩ የአስፋልት መንገዶች የኑሮ ውድነቱን ረገብ ሊያደርጉት አልቻሉም፡፡
ተመልከቱ እንግዲህ፡፡ የአንድ ሰው ዝቅተኛ መንግሥታዊ ደመወዝ ብር 400 አካባቢ ነው፡፡ በየሻይ ቤቱና ቡና ቤቱ የሚሠሩ ወገኖቻችን ደመወዝም በመጠነኛ ቲፕ ይደጎማሉ እንጂ ከዚህ የሚበልጥ አይደለም፡፡ ከጉለሌ ተነስቶ ሜክሲኮ የሚሠራ የጥበቃ ሠራተኛ አራት መቶና አምስት መቶ ብር በወር ደርሶት ምኑን ከምን እንደሚያደርገው አስቡት፡፡ ግዴለም በሌላው ትርፍ ሰዓቱም ይህንኑ ያህል ገንዘብ ሠርቶ (ሠርቆ አላልኩም!) ያገኛል ብለን እናስብና በስምንትና ዘጠኝ መቶ ብር ወርሃዊ ጥቅል ገቢ እንዴት ሊኖር እንደሚችል እናስበው፡፡
ትራንስፖርቱ ብቻ በከተማ አውቶቡስ ተጓጉዞ በወር ከ300 ብር በላይ ይፈጅበታል፡፡ ጥቁር ጤፍ 1600 ብር ነው – በኩንታል፡፡ ድሃ ደግሞ ልጅ መውለድ ይወዳልና የቤተሰቡን ብዛት አስቡት፡፡ ቤት ኪራይ በቀላሉ አይገመትም – አዲስ አበባ ላይ አንዲት ሦስት በአራት የሆነች መናኛ ክፍል ቤት ከ800 ብር በታች ማግኘት አይሞከርም፡፡ ሰው እርስ በርሱ ተባልቶ ሊያልቅ ነው፡፡ መብራት፣ ውሃ፣ ስልክ፣ ተቀማጭ፣ ሕክምና፣ ልብስ፣ የልጆች ትምህርት፣ መዝናኛ… የመሳሰለው ለአንድ ተቀጣሪ ኢትዮጵያዊ የህልም ያህል እንጂ እውን ሊሆን አይችልም፡፡ አመጋገቡም እጅግ የወረደ በመሆኑ በቁሙ ሞቱን ተሸክሞ የሚዞርና ትንሽ በሽታ ዘወር ብትልበት መቋቋም የሚያቅተው ተንጠራዋዥ ነው፡፡ የአብዛኛው ሕዝብ ችግር እንግዲህ ይታያችሁ፡፡ ብዙው ዜጋ በምጽዋትና በዲያስፖራው ድጋፍ እየኖረ እንጂ በእውነተኛው ደመወዙ መኖር ካቆመ ቆይቷል፡፡ ሠርቶ ከሚኖረው ይልቅ እንዲሁ በተዓምር የሚኖረው ይበልጣል – ብቻ ግን ይመሻል ይነጋል፡፡ ይህ የተፈጥሮ ሕግ እስካሁን አልተቀየረም፡፡ ይህን ዓይነት በመንፈስም በሥጋም በአእምሮም የደከመ ሕዝብ ማስተዳደር ለአምባገነኖች በጣም ቀላል ነው፡፡ ነገሩ የቁጥር ጉዳይ አይደለም፡፡ የደከመን ሕዝብ መቶ ሚሊዮንም ይን አንድ ቢሊዮን በቀላጤም በወንጭፍም ማስተዳደር ይቻላል፡፡ በሌሎች ሀገሮች በአንድ ወር ደመወዝ ስድስት ወራትን መኖር ይቻል ይሆናል፤ በኢትዮጵያ ግን በአንድ ወር ደመወዝ በጣም ጎበዝ የሆነ ዜጋ ለሦስት ቀናት ሊኖር ይችላል – ከልደታ እስከ ባታ፡፡ ቀሪዎቹን 27 ቀናት በምትሃት የሚኖር ሕዝብ በመንግሥት ላይ እንዲያምጽ መጠበቅ አስቸጋሪና ተዓምር መሥራትን ይጠይቃል፡፡ ተስፋ ሁሉ ተሟጦ የመጨረሻው የምፅዓት ዘመን ሲመጣ ግን መተንበይ የሚያስቸግር ሊቢያ-ሦርያዊ ዕልቂትና ትርምስ እንደሚፈጠር ከወዲሁ መገመት አይከብድም፡፡ ያ ጊዜ መምጣቱ ለማይቀረው እስኪያልፍ ያለፋል፡፡

ለዚህ ነው አባቶች በሥነ ቃላቸው፤

“እንዲህ ጨሶ ጨሶ የነደደ እንደሆን፤
ያመዱ ማፍሰሻ ሥፍራው ወዴት ይሆን?”
በማለት የአንድን ክፉ ድርጊት የመጨረሻ መጥፎ ውጤት የሚጠቁሙት፡፡

ተቀጣሪው ዝቅተኛ ደመወዝተኛ የሚኖረው ሞቶ ነው፡፡ እኛም አለን የምንለው የምንኖረው ሞተን ነው፡፡ የሞተውን ካልሞተው ለመለየት ምናልባት ዘርህን መጠያየቅ ሳያስፈልግ የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ኅሊና ያለህ ካልሆንክ በስተቀር ከገዢው መደብ ተፈጥረህ አትራብም ብቻ ሳይሆን ዓለም ልታቀርብ የምትችለው መልካም ነገር ሁሉ ይኖርሃል፡፡ አንፋሽ አከንፋሽ ከሆንክም በመነጽር ውስጥ እየታየህ ሊኖርህ የሚገቡ የተወሰኑ ንብረቶች እንዲኖሩህ ይደረጋል፡፡ ሀብት ንብረት ብቻ ሳይሆን መላው እስትንፋስህ በወያኔዎች ቁጥጥር መሆኑን መዘንጋት የለብህም፡፡ አንተ ምንም እንኳን ታማኝ ሎሌ ብትሆንም ‹እባብ የወጣበትን ጉድጓድ አይስትም› በሚለው ነባር ብሂል የሚያምኑት ወያኔዎች የአንተን ዘላቂ ወዳጅነትና ቀናነት የሚያዩት በጥርጣሬ ነው፡፡ እንደትሮይ ፈረስ ከተጠቀሙብህ በኋላ አሽቀንጥረው የሚጥሉበት ብልሃት አላቸው – ጥፋት ባይኖርህም እንኳን፡፡ ያም ጥፋትህ ምናልባት አማራ ሆነህ መገኘትህ ሊሆን ይችላል፡፡ አለዚያም ተስቶህ የኢትዮጵያን ስም በስስት አንደበት አቆላምጠህ አንስተህም ሊሆን ይችላል፡፡ ብቻ የዐይንህ ቀለም ካስጠላቸው የሚመዙብህ ካርድ አያጡም – ያም ካርድ የተዘጋጀልህ ገና በጧት ነው፡፡ በአሁኒቷ ኢትዮጵያ ለአስተማማኝ ብልጽግናህና ኩፍስ ሕይወትህ ዋናው መሠረት የዘርህ ማንነት ነው ወዳጄ፡፡
በተረፈ ጉዳችን ብዙና እየተንተከተከም ያለ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ገቢህን በራስህ የምትወስን ከሆንክ ጌታ ነህ፡፡ ሊስትሮ ከኔ ይሻላል፡፡ ለአንድ ጫማ ከሦስት ብር ጀምረው ያስከፍላሉ፤ ግንበኛና አናጢን አረቂ ቤት የምታገኛቸው ከስንት አንዴ ነው – ‹የጥንቱ ትዝ አለኝ› ብለው ሲመጡ፡፡ ዛሬ እነሱ በቀን ከ200 በታች አይገኙም – ቢራና ድራፍት ቤት ነው መዝናኛቸው፡፡ አንተ ወደታች አንዳንዶች ወደላይ፡፡ ጊዜ ነው፡፡ አንስቶ ያፈርጥሃል ወይ አንፈራፍሮ ሲያበቃ ያነሳሃል፡፡ ተራ የጉልበት ወዛደር በቀን ከ60 ብር በታች አይቀመስም፡፡ እንዲቀንሱልህ ብትጠይቅ ‹እንዴት እንኑር?› ይሉሃል፡፡ እውነታቸውን ነው፡፡ ተራ ሽሮ በተራ ቡና ቤት 40 እና 50 ብር ነው፡፡
ሀኪም ቤት ብትሄድ ዘረፋ ነው፡፡ የመንግሥት ሀኪም ቤት በቁሙ ሞቷል፡፡ ለምትቀደድበት ሰንጢና አልኮል ራስህ ግዛ ልትባል ትችላህ፡፡ አለቃ የለ – ምነዝር የለ – ሁሉም ዘበናይ ነው፡፡ አዛዥና ታዛዥ የለም፡፡ ሰው ቢሞት ግድ ያለው የለም፡፡ የትም ሂድ ሆስፒታሉ ሁሉ ትርምስ ነው፤ በሀገሪቱ አንድም ሰው ጤናማ አይመስልህም፡፡ ልክ እንደፖሊስ ጣያውና እንደፍርድ ቤቶች ሁሉ ሀኪም ቤቶችም በሰው ጢም ብለው ነው የሚውሉ፤ ሀኪም የለም በሽተኛ ግን ሲጉላላና ሲሞት ይውላል፡፡ በግዴለሽ ህክምና የሚሞተው ደግሞ አይነሣ፡፡ አንተው ግዴለህም ተበለሻሽተናል፡፡
የግሎቹ ጋ ከሄድክ ተኝተህ ለመታከም ለአንድ አዳር የሚያስከፍሉህ የአልጋ ኪራይ ከሼራተን አዲስ ሱትሩም ዋጋ ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ ሀኪም ወደክፍልህ በገባ በወጣ ቁጥር ትራስጌህ በሚቀመጥ ወረቀት ላይ ምልክት እየጫረ ሒሣብህን ያንረዋል፡፡ ጉንፋን አሞህ ብትገባ ቁርጭምጭሚትህን ራጅ እንድትነሣ ሊያዝዙህ ይችላሉ – ‹ምክንያቱም› ይልሃል ዶክተሩን ስትጠይቀው – ‹ምክንያም የጉንፋን ጥንተ አመጣጥ ሲጠና አነሳሱ ከቁርጭምጭሚት ነው፤ እዚያ ላይ ካጣነው ብብትህ ሥር ሊገኝ ስለሚችል እሱን ራጅ እናነሳዋለን› ሊልህ ይችላል፡፡ ዋናው ለደልቃቃ ኑሯቸው የሚሆናቸውን ወፋፍም ገንዘብ ለነሱ መስጠትህ ነው፡፡ ሙያዊ ሥነ ምግባር ተቀብሯል፡፡ በነዚህ ሀኪም ቤቶች ሌላው ቀርቶ ለካርድ የምትከፍለው ብቻ የትዬለሌ ነው – ልጅህ እንዲወለድ ብትሄድባቸው ልጁን ራሱን የሰጡህ ይመስል – አንተ ከመነሻው እንዳልለፋህበት – ለአምስት ደቂቃ የማዋለድ አገልግሎት በአሥር ሺዎች እንድትከፍል ብትጠየቅ አንተም እነሱ በመሥሪያ ቤትህ መጥተው ግልጋሎትህን እንዲያገኙ ከመዛት በስተቀር የምትከስበት የሕግ አንቀጽ የለም፡፡ ሕጉ ለሌቦች ያመቸ ነው – ዘመነ ብላ ተባላ፡፡ ለጠላትህም አይሁን እንጂ ሞተህ ሬሣህ እንኳን ቢወጣ ያለ የሌለ ሒሣብ ቆልለው ሀዘንተኛን ሲያስጨንቁ ፈጣሪ መኖሩን የረሱ ሊመስሉ ይችላሉ፡፡ ሁሉም ተያይዞ ሆዳም – አጋሰስ ሆኖልሃል፡፡ ይሉኝታ ጠፍቶ ሆድ ነው የነገሠው፡፡
በዚህ መሀል እየተጎዳ ያለው ድሃው ነው፡፡ በዚአከ ለዚኣየ ሀብታሙና አጭበርባሪው ርስ በርስ እየተጠቃቀመ ሲኖር መድረሻ ያጣውና የፖለቲከኞቹና የነጋዴዎቹ የአልጠግብ ባይነት ደዌ ሰለባ ሆኖ ለማያባራ እዬዬ የተጋለጠው ቀድሞ ንዑስ ከበርቴ ይባል የነበረውን የማኅበረሰብ ክፍል ጨምሮ ወደታች ያለው ሕዝብ ነው፡፡ የንግድ ሥርዓት የለም፤ የመንግሥት ሥርዓት የለም፤ ሀገሪቱ በደመነፍስና በስሜት ብቻ እየተነዳች ናት፡፡ ይህ የዕውር ድንብር ጉዞ እስከመቼ እንደሚቀጥል በግልጥ አናውቅም፡፡ ግን ይህም የሚያልፍ መሆኑ እርግጥ ነው፡፡ ሲያልፍ ግን ወዮ ለመዥገሮችና ለትኋኖች! የአልቅቶች ዘመን ያቃል፡፡ የፍየል ዘመን እያበቃ ነው፤ የበጎች ዘመን እየመጣ ነው፡፡ ያኔ በሠፈሩት ቁና መሠፈር አይቀርምና ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ሆድ መጥፎ ነው፡፡ የሚያስርበንም ሆነ የሚያጠግበን ሆዳችን ነው፡፡ ለሆድ መኖርን አቁመን ለኅሊናችን መኖርን ካልጀመርን ቆመንም ሞተንም ሙታን ነን፡፡ በአንዲት እንጀራ ለሚቆዘር ሆድ ብለን ሚሊዮኖችን ብናስለቅስ መጨረሻችን እንደማያምር ግልጽ ሊሆንልን ይገባል፡፡ በድጋሚ መልካም ዐውዳመት፡፡


Sport: ቅዱስ ጊዮርጊስ የራሱን እድል በራሱ አሳልፎ ሰጥቷል (አስተያየት)

$
0
0

kidus georgis
ከይርጋ አበበ
ዛማሌኮች በጽናት እስከመጨረሻው በመጫወታቸውና የጊዮርጊሶችን መዘናጋት በመረዳታቸው ጨዋታውን በአሸናፊነት አጠናቅቀዋል፤
የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ከግብፁ ዛማሌክ ጋር ባደረገው ጨዋታ ሙሉ ሦስት ነጥብ ማግኘት ወይም ግቡን ሳያስደፍር አቻ መውጣት ባለመቻሉ ወደ ቀጣዩ ዙር ሳያልፍ ቀረ።
ትናንት በአዲስአበባ ስቴዲየም 10 ሰዓት ላይ በተካሄደው የመልስ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስና የግብፁ ዛማሌክ ሁለት ለሁለት በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በጨዋታው በአንድ ግብ ብልጫ አለያም ዜሮ ለዜሮ በሆነ ውጤት ቢለያይ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ይችል የነበረ ቢሆንም ይህንን ውጤቱን ማስጠበቅ ባለመቻሉ አሳዛኝ ተሸናፊ ለመሆን ተገድዷል።
በተለይ ሁለት ለአንድ መምራቱን ማስጠበቅ እንዲያም ሲል ተጨማሪ ግብ በማከል የበላይነቱን ማረጋገጥ ሲገባው በተከተለው የታክቲክ ስህተት ሁለት አቻ በመውጣቱ በሰው አገር ብዙ ግብ ባስቆጠረ በሚለው ስሌት መሠረት ዛማሌክ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድሉን አስጠብቋል።
ጨዋታው በተጀመረ ገና የመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች የጊዮርጊስ ተከላካዮችን መዘናጋት ተጠቅሞ የዛማሌኩ ተጫዋች አብዱላዬ ሲሴ ዛማሌኮችን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጥሯል።
በእዚህ ወቅት ጊዮርጊሶች የነበራቸው አቋም መልካም በመሆኑ በአሥራ አራተኛው ደቂቃ ላይ ሽመልስ በቀለ ከያሬድ ዝናቡ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብ ቀይሮ አቻ መሆን ቻሉ። የመሐል ሜዳ የበላይነቱ በእንግዳው ቡድን ቢወሰድባቸውም በ43ኛው ደቂቃ በተከላካዩ አይዛክ ኡሴንዴ አማካኝነት ተጨማሪ ግብ አስቆጥረው በስቴዲየም ይገኝ የነበረውንና ጨዋታውን በየቤቱ ይከታተል የነበረውን ስፖርት አፍቃሪ ማስደሰት ችለዋል።
የመጀመሪያው ግማሽ ጨዋታ ብዙም የኃይል አጨዋወት ያልተስተዋለበት ቢሆንም የዛማሊኩ 25 ቁጥር መሐመድ ኢብራሂም የመጀመሪያውን ቢጫ ካርድ ሲመለከት፣ ሌላኛው የቡድን ጓደኛው ኑሬ ሰዒድ በ44ኛው ደቂቃ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።
ከዕረፍት መልስ ጊዮርጊሶች ጫና ፈጥሮ ከመጫወት ይልቅ ኳስን ወደ ኋላ እየመለሱ ሰዓት ማባከንን በመምረጣቸው የጨዋታ ብልጫ ተወስዶባቸዋል። የጊዮርጊሶቹን ወደ ኋላ አፈግፍገው መጫወት የተመለከቱት የዛማሌክ አሠልጣኝ የበለጠ ጫና ለመፍጠር እንዲቻላቸው የተጫዋች ቅያሬ አካሄዱ። መሐመድ ኢብራሂምን አስወጥተው ዘጠኝ ቁጥሩን መሐመድ ፋቲ አብዱል ሳሚርን በማስገባት ይበልጥ ተጭነው መጫወት ጀመሩ።
በአንፃሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ የአንድ ግብ ብልጫውን አስጠብቆ ለመውጣት አጥቂውን ዮናታን ብርሃኔን በተከላካዩ አሉላ ግርማ በመቀየር ይበልጥ ወደ ኋላ ተመልሶ መጫወት ጀመረ። አሉላ ግርማ ተቀይሮ ከገባ በኋላ አስር ደቂቃ ሳይጫወት ተጐድቶ በመስመር አማካዩ ምንተስኖት አዳነ ተቀይሮ ሊወጣ ችሏል። ኮከቡን አዳነ ግርማን በጉዳት ያጣው ቅዱስ ጊዮርጊስ የግብ መስመሩ ጠፍቶበት ታይቷል።
kidus georgisበጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ ካይሮ እና አዲስ አበባ ላይ የጊዮርጊሱ ሮበርት ኦዶንካራ መረብ ላይ ሁለት ግቦችን ያስቆጠረው አብዱላዬ ሲሴ ጊዮርጊሶችን አንገት ያስደፋች በአንፃሩ ግብፃውያንን ወደ ቀጣዩ ዙር ያሳለፈች ግብ አስቆጠረ። በጨዋታው ሙሉ ጊዜውን ምርጥ ሆኖ ያመሸው ብቸኛው ጥቁር የዛማሌክ ተጫዋች የቡርኪናፋሶ ዜጋ አብዱላዬ ሲሴ በድምሩ ሦስት ግቦችን በጊዮርጊስ መረብ ላይ በማሳረፍ ለዛማሌክ ባለውለታ ሆኗል።
በቅዱስ ጊዮርጊሶች በኩል አበባው ቡጣቆና አማካዩ ተስፋዬ አለባቸው ጥሩ ሲንቀሳቀሱ ያመሹ ሲሆን፣ በቀኝ መስመር ተከላካይ በኩል የተሰለፈው ቢያድግልኝ ኤልያስና ወጣቱ ዮናታን ብርሃኔ ብዙ ስህተቶችን ሲሠሩ አምሽተዋል።
ጊዮርጊሶች ሙሉ 45 ደቂቃውን ሰዓት በማባከን ውጤት ለማስጠበቅ መሞከራቸው ደግሞ ሌላው የክለቡ ድክመት ሆኖ ታይቷል። ፈርኦኖቹ ሁለተኛውን ግብ ካስቆጠሩ በኋላ ጊዮርጊሶች በኡሞድ ኡኩሪ እና ሽመልስ በቀለ አማካይነት ሁለት ያለቀላቸው ዕድሎች አግኝተው የበረኛ ሲሳይ አድርገዋቸዋል። በእነዚህ ስህተቶች የተነሳ ጊዮርጊሶች የማለፍ ዕድላቸውን አበላሽተው ወደ ቀጣዩ ዙር ሳያልፉ ቀሩ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ም/ቤት ለዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ምላሽ ሰጠ

$
0
0

entc-logo-5የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት የሕወሓት የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዋሽንግተን ዲሲ ለሚተላለፍ ራድዮ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ምላሽ ሰጠ። ምክር ቤቱ በዋሽንግተን ዲሲ የወያኔ ኢሕአዴግ ኤምባሲ እየሸጠ ያለውን ቦንድ ህጋዊነት በተመለከተ ለአሜሪካው የገበያ ልውውጥ ኮሚሽን ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ዶ/ር ቴዎድሮስ በራድዮ ላይ ቀርበው ተናግረዋል። (መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)

ቴዎድሮስ አድሃኖም በራድዮ ቀርበው የተናገሩት የሚከተለው ነው፦

ሸንጎ “የፍትህ አካላት የመጨቆኛና የማፈኛ መሳርያዎች መሆናቸው ያብቃ!”አለ

$
0
0

shengo(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) “የፍትህ አካላት የመጨቆኛና የማፈኛ መሳርያዎች መሆናቸው ያብቃ!” መግለጫ አወጣ። ሸንጎው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው ላይ እንዳስቀመጠው ” አቶ እሰክንድር ነጋና አቶ አንዱአለም አራጌን ጨምሮ በሽብርተኛነት የፈጠራ ክስ ውንጀላ በረጅም እሰራት የሚማቅቁትን ውድ የኢትዮጵያ ልጆች በቀጣይነት ለማሰቃየት የአዲስ አበባ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰደውን እርምጃ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣በጥብቅ ያወግዛል።”
“በመላው ዓለም የነፃ ፕሬስ መብት በሚከበርበት ቀን ዋዜማ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ በእውቅ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች ላይ ካሁን በፊት የበታች ፍርድ ቤት ጥሎባቸው የነበረውን ፍርደ ገምድል ብይን እንዲጸናና የስቃይ ዘመናቸው እንዲቀጥል መፍረዱ አገዛዙ ነፃ ፕሬስንና የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት ለ21 ዓመታት እንዳደረገው ሁሉ አሁንም በዚያው አጥፊ ጎዳና እየቀጠለ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። የሀገሪቱ የፍትህ አካላትም ይህንኑ እኩይ ተግባር ለማሳካት ሙሉ በሙሉ የአገዛዙ የፖለቲካ መሳሪያ እንደሆኑ መቀጠላቸውን የሚያመለክት ነው።” ያለው የሸንጎው መግለጫ “የፍትህ አካላቱ የዜጎችን መብት ማሰከበርና መብታቸው የተረገጠባቸው ግለሰቦችም አለኝታ መሆን ሲገባቸው፣ ተራ የፖለቲካ መሣሪያ ሆነው መቀጠላቸው ለሀገሪቱ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በሙያው ለተሰማሩትም ሁሉ እጅግ አሳፋሪና አሳዛኝ ነው።” ብሏል።
ሸንጎው መግለጫውን በመቀጠል ” እራሱን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫነው አገዛዝ፣ ሁሉንም ተቋማት ለአምባገነን ስርዓቱ እድሜ ማራዘሚያ አድርጎ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ድምጽ የሚያፍን፣ የሀገሪቱን ልዖላዊነት የካደና በተግባርም በመንቀሳቀስ አካሏን ያስቆረሰ፣ ያለባህር በር ያስቀረ፤ ደንበራችንን አሳልፎ ለጎረቤት ሀገር በገጸበረከትነት የሰጠ፤ በህዝብ መካከል የተለያዩ ልዩነቶችን እየፈለገ ግጭቶችን ሆን ብሎ የሚያራግብ፤ በሃይማኖት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ምዕመናኑን ያሰቃየ፣እምነታቸውን የተፈታተነ፤ በሚናገሩት ቋንቋና በዘውጋቸው እየነጠለ ዜጎችን ለዓመታት ከኖሩበትና ህይወት ከመሰረቱበት ቀያቸው እያፈናቀለ የሚገኝ ፍጹም አምባገነናዊና ጎሰኛ ቡድን ነው። ባጭሩ የሀገራችንና የህዛባችን አበይት ችግሮች ዋናው ምንጭ ይኀው ስርአትና አገዛዙ ናቸው፣ በመሆኑም ከዚህ አስከፊ ስርዓት ፍትሃዊነትን መጠበቅ የሚቻል አይደለም።” ካለ በኋላ “ስለሆነም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ከዓመት ዓመት እየከፋ የመጣውን የመብት ረገጣና ፈላጭ ቆራጭ አምባገነናዊ ስርአት በአንድነት በመቆም አምርሮ እንዲታገል አሁንም ደግመን ጥሪ እናቀርባለን ። በተቃዋሚነት የተሰለፉ የፖለቲካ ሀይሎችም በህዝባችን ላይ የተጫነውን የጨለማ ዘመን ለማሳጠር በአንድነት ቆመን በጋራ ለመታገል እንችል ዘንድ ጊዜ ሳንወስድ ወደ ተግባር እንድናመራ አሁንም ጥሪያችንን እናቀርባለን።” በሚል መግለጫውን ቋጭቷል።

የቃሊቲው ደብዳቤና የርዕዮት እውነቶች (በስለሺ ሀጎስ)

$
0
0
ጀግናዋ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

ጀግናዋ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

ሚያዝያ 23 2005 ዓ.ም ሪፖርተር ጋዜጣ በቅጽ 18 ቁጥር 44/1356 ዕትሙ “በህግ ታራሚ ርዕዮት ዓለሙ ላይ የደረሰ አንዳችም አይነት ችግር የለም!” በሚል ርዕስ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር የተላከ ደብዳቤ አስነብቧል፡፡ ደብዳቤው በቅጥፈትና በክህደት የተሞላ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ባልተነሳ ጥያቄና ባልተባለ ነገር ላይ በማተት የተነሳበትን ሀቀኛ ጥያቄ አደናብሮ ለማለፍ ከአንድ ህገ መንግስታዊ ተቋም የማይጠበቅ ጥረት አድርጓል፡፡
ይህ የሆነውም ርዕዮት ራሷን በማትከላከልበት ሁኔታ ውስጥ መሆኗን እንደ መልካም አጋጣሚ በማየት ይመስላል፡፡ በመሆኑም በደብዳቤው ላይ የሰፈሩትን አብዛኞቹን ጉዳዮች በቅርብ ስለማውቃቸው የርዕዮትን እውነቶች የማስረዳት ሞራላዊ ኃላፊነት እንዳለብኝ በማመኔ ይህን ጽሑፍ ለማዘጋጀት ተገድጃለሁ፡፡
በደብዳቤው ከታጨቁ ቅጥፈቶችና ማወናበዶች መሐከል ጸሐፊውን ጠልፈው የሚጥሉ እውነቶች ተሸሽገው ቀርበዋል፡፡ ከነዚህም መሐከል አንደኛው ርዕዮት ለብቻዋ እንድትታሰርና በጠያቂዎቿ እንዳትጎበኝ ለማድረግ ማረሚያ ቤቱ እንደተዘጋጀ ማረጋገጡ ነው፡፡ በደብዳቤው መጨረሻ ላይ፣
‹‹በማረሚያ ቤት አብረዋት ከሚኖሩ ታራሚዎች ለመረዳት እንደቻልነው ርዕዮት ያለምንም ጥረትና ልፋት ዝናን ለማግኘት በመሻቷ ከታራሚዎችና ከጥበቃ አባሎች ጋር በየጊዜው ትጋጫለች፡፡ ጤናማ የሆነ ግንኙነት የላትም፡፡ በተለያየ ጊዜ በታራሚዋ ላይ የዲሲፒሊን ግድፈት በመታየቱም ማረሚያ ቤቱ ጥፋቱን በማጣራት ላይ ይገኛል፡፡ ጥፋተኛ ሆና ከተገኘችም በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የሕግ ታራሚዎች መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር 138/1999 መሠረት ተገቢውን የዲሲፒሊን እርምጃ ተቋሙ እንደሚወስድ ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡››
የሚል ሀሳብ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
በጽሑፉ ላይ እንደሚታየው ርዕዮት የዲሲፒሊን ግድፈት ማሳየቷን ማረሚያ ቤቱ ደምድሟል፡፡ ከዚህም በላይ ከጥበቃ አባሎችና ከታራሚዎች ጋር እየተጋጨች የዲሲፒሊን ግድፈቱን የምትፈጽመው ለምን እንደሆነ ሲገልጽ “ያለምንም ጥረትና ልፋት ዝናን ለማግኘት በመሻቷ ከታራሚዎችና ከጥበቃ አባሎች ጋር በየጊዜው ትጋጫለች፡፡ ጤናማ የሆነ ግንኙነት የላትም፡፡” በማለት በልቧ ምን አስባ ድርጊቱን እንደምትፈጽም ሁሉ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኖ ነግሮናል፡፡
ታዲያ ማረሚያ ቤቱ የሚያጣራው ምንድን ነው? ጥፋተኝነቷን ከነ መንስዔው እርግጠኛ ሆኖ እየነገረን፤ መልሶ ደግሞ ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች እርምጃ እወስዳለሁ ማለቱ አልሞ ለመተኮስ ሳይሆን፣ የሚፈልገው ላይ ተኩሶ ዒላማ ለማክበብ መዘጋጀቱን ያሳብቃል፡፡
አርሶ መራብና ተኩሶ መሳት፣
እያደር ይፈጃል እንደእግር እሳት! ሆነበት እንጂ ነገሩ፡፡
ማረሚያ ቤቱ ከሳሽም፤ አጣሪም፤ ፈራጅም፤ እርምጃ ወሳጅም ሆኖ መቅረቡ ደግሞ “በህግ ሽፋን ርዕዮት ብቻዋን እንድትታሰርና ጠያቂዎቿ እንዳይጎበኟት ለማድረግ እየሰራ ነው” የሚለው ስጋት እውነት መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ሲፒጄም ቢሆን ያለው ይህንኑ ነው፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደብዳቤው ላይ፤
“በአንዳንድ ሚዲያዎች የተገለጸው ሌላው ጉዳይ ለሁለት ወራት በአንድ ክፍል ውስጥ ለብቻዋ እንደታሰረች የሚገልጸው ዘገባ ነው፡፡ ይህ ዘገባ ከርዕዮት ጋር የሚኖሩ የህግ ታራሚዎችን ከመናቅ ወይም እንደሰው ካለመቁጠር የመነጨ ይመስለናል፡፡ ሀሳቡ የርዕዮት ከሆነም ለራሷ ካላት የተጋነነ ግምት ወይም ማንነት የመነጨ ሊሆን ይችላል፡፡”
የሚል ውንጀላ ቀርቧል፡፡
እግዜር ያሳያችሁ! “ሊሆን ይችላል” ነው ያለው፡፡ ግምት ብቻ ተይዞ “ለራሷ ካላት የተጋነነ ግምት… እንደሰው ካለመቁጠር የመነጨ” የመሳሰሉ ሥነልቡናዊ ትንታኔዎች ውስጥ እንዴት ይገባል? ኧረ ጎበዝ አታሳፍሩን!
እርግጥ ነው ርዕዮት ለብቻዋ እንድትታሰር ሊያደርጋት በሚችል አንቀጽ (በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የሕግ ታራሚዎች መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር 138/1999) ክስ ተመስርቶባት ውሳኔውን (ውሳኔው ተግባራዊ የሚሆንበትን ዕለት) በመጠባበቅ ላይ ናት እንጂ በአሁኑ ሰዓት ለብቻዋ አልታሰረችም፡፡
ለዚህ ጉዳይ ሽፋን ከሰጡ በርካታ የሀገር ውስጥ የህትመት ውጤቶች መሐከል አንዱ (ሪፖርተር ጋዜጣ ቅጽ 18 ቁጥር 42/1352) ‹‹ርዕዮት ለብቻዋ ታስራ ትገኛለች›› ብሎ ሲፒጄ መናገሩን ጽፏል፡፡ ማረሚያ ቤቱን ለግምታዊ ስህተት የዳረገውም ይሄው ዘገባ ነው፡፡ ነገር ግን እንኳን አንድ ትልቅ ተቋም ቀርቶ፤ የዘገባው ስህተት ከምን የመነጨ እንደሆነ ማረጋገጥ የሚፈልግ ሰው የሲፒጄን ኦርጂናል መግለጫ ማንበብ፤ አሊያም ጋዜጣውን መጠየቅ ብቻ ይበቃዋል፡፡
እኔ ያነበብኩትና ለፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በአድራሻው የተላከት የሲፒጄ ደብዳቤ “ርዕዮት ለብቻዋ ታስራለች” አይልም፡፡ በጉዳዩ ላይ መረጃ የሰጡ የርዕዮት ቤተሰቦችም በአንድም ሚዲያ ላይ ይህን አላሉም፡፡ ታዲያ ሪፖርተር ከየት አመጣው? የሚለውን ጥያቄም ከጋዜጣው በስተቀር ርዕዮትም ሆነች ማንም ሰው ሊመልሰው አይችልም፡፡
ከዚህ ሌላ ርዕዮት ማረሚያ ቤቱ እንዳለው አይነት ሰው አለመሆኗን ዓለም የሚያውቀው እውነት በመሆኑ ይህን ለማስረዳት አንዲትም ቃል ሳላባክን ወደ ቀጣዩ ርዕሰ ጉዳይ ልለፍ፡፡
ህክምናዋን በተመለከተም ምንም አይነት ችግር እንዳላጋጠማት በደብዳቤው ላይ ተገልጿል፡፡ “ማረሚያ ቤት በቆየችባቸው ጊዜያት በተለያዩ ቀናት ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተልካ ሕክምና ማግኘቷን ከግል ማህደሯ ማረጋገጥ ይቻላል” በማለትም እማኝ ይጠቅሳል፡፡
በተለያዩ ቀናት፣ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መሄዷ እውነት ነው፡፡ ነገር ግን በጡቷ ላይ ሕመም እንደሚሰማት ተናግራ ሪፈር እንዲጻፍላት ብትጠይቅም፣ ከመንፈስ ጭንቀት ውጪ ምንም በሽታ እንደሌለባትና የእጅ ሥራ እንድትሰራ፤ ጥልፍ እንድትጠልፍ ስትመከር መሰንበቷ፤ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሄዳ ህክምናዋን ለመከታተል የቻለችውም ከብዙ አቤቱታ በኋላ ኦማር የተባለ የአፍሪካ ጋዜጠኞች ፌዴሬሽን ተወካይ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ጋር ቃሊቲ ድረስ ሄደው በጎበኟት ወቅት በእነሱ በኩል በቀረበ አቤቱታ በማረሚያ ቤቱ ዋና አስተዳዳሪ ትዕዛዝ መሆኑ ቢታከልበት የተሻለ እውነት ይሆን ነበር፡፡
ሕክምናዋን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መከታተል ከጀመረች ወዲህም ብዙውን ጊዜ በቀጠሮዋ መሠረት ተገኝታ መታከም አለመቻሏ፤ ህመሟ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ የተለየ ህመም ካጋጠማት ቀጠሮዋን ሳትጠብቅ ወደ ሆስፒታል እንድትመጣ በሀኪሞቹ ቢታዘዝም፤ ከጥር 10 ቀን ጀምሮ ክፍተኛ ደም ከጡቷ እየፈሰሰ እስከ የካቲት 07 ድረስ ህክምና ሳታገኝ በስቃይ መክረሟ፤ ከዚያ በኋላም ሀኪሟ በአስቸኳይ የናሙና ምርመራ ተደርጎ የዕጢው ደረጃ ከታወቀ በኋላ መለስተኛ ቀዶ ጥገና ማድረግ እንደሚኖርባት በመግለጽ ለየካቲት 13 ቀጠሮ ቢሰጥም መኪና የለም በሚል ሰንካላ ሰበብ እስከ መጋቢት 2 ድረስ፣ ከነስቃይዋ እንድትቆይ መደረጓና ሌሎች ታራሚዎች ህክምናቸውን ሲከታተሉ የቀጠሯቸው ቀን ከፍርድቤትና ከሌሎች ቀጠሮዎች ጋር እንዳይጋጭ የህክምና ቀጠሯቸውን እዚያው ሆስፒታል እያሉ እንዲያውቁት የሚደረግበት አሰራር የተለመደ ሆኖ እያለ ርዕዮት ከመጋቢት 2 ወዲህ መቼ ምን አይነት የሀኪም ቀጠሮ እንዳላት ለማወቅ ብትጠይቅም፣ በግልጽ ‹‹ለአንቺ አይነገርሽም›› መባሏ ተገልጾ ቢሆን ኖሮ ሙሉ እውነት ይሆን ነበር፡፡
ፍጹም እውነት እንዲሆን ደግሞ…
እንጂማ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መሄዷ ብቻ ሳይሆን መለስተኛ ቀዶ ጥገና አድርጋ ከጡቷ ላይ ዕጢ ማስወጣቷም ጭምር ከወራት በፊት ሁሉም የሰማውና ያረጀ ዜና ነው፡፡
የትምህርቷን ጉዳይ በተመለከተ ከመነሻው ጀምሮ እስከ ክልከላው ድረስ እኔ ራሴ ስከታተለው የነበረ በመሆኑ፣ ማረሚያ ቤቱ ላከ በተባለው ደብዳቤ ላይ ያነበብኩት ነገር ክፉኛ አስደንግጦኛል፡፡ ጸሐፊው ትክክለኛ መረጃ ሳያገኝ በየዋህነት ተሳስቶ ካልሆነ በቀር እንዲህ አይነት አይን ያወጣ ቅጥፈት በአደባባይ እንዲነበብ ለመጻፍ በገዛ ህሊናው ላይ የሰለጠነ ልዕለ ኃያል ሰው መሆን ይጠይቃል፡፡
የሆነው ሆኖ “ትምህርቷን እንድትከታተል የሴቶች ቀጠሮና ማረፊያ ቤት ተገቢውን ድጋፍ እያደረገላት ይገኛል፡፡” ተብሎ የተገለጸው ፍጹም ሀሰት ሲሆን እውነቱ የሚከተለው ነው፡፡
የማረሚያ ቤቱን ይሁንታ ጠይቃ ካገኘች በኋላ ህዳር 29 2012 እ.ኤ.አ ያስመዘገብኳት እኔው ራሴ ነበርኩ፡፡ መመዝገቧን ካሳወቀች በኋላም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የማረሚያ ቤቱ ባልደረቦች ት/ቤቱ ድረስ በመሄድ እንዳረጋገጡ የሰማሁት ከራሳቸው አንደበት ነው፡፡ በየካቲት ወር መጨረሻ ትምህርቱ ሲጀመር የመማሪያ መጻህፍቶቿን ይዤ በሄድኩበት ጊዜ ግን የተሰጠኝ “እሷ እንድትማር አልተፈቀደላትም” የሚል ምላሽ ነው፡፡ ጉዳዩ እስካሁን ድረስ እልባት ባለማግኘቱ ትምህርቷን መጀመር አልቻለችም፡፡ የመማሪያ መጻሕፍቱም እስከ ዛሬ ድረስ በእጄ ይገኛሉ፡፡
በመጨረሻም መሽቶ በነጋ ቁጥር በሁሉም መስክ የባሰ ነገር መጋፈጥ ልማዳችን ነውና ለማረሚያ ቤቱ ደብዳቤ ይህን ያህል ጊዜና ጉልበት ከፈጀን በቂ ነው፡፡ ነገ ለሚመጣው የባሰ ነገር ጊዜና ጉልበት መቆጠብ፣
ያምናን ቀን አማሁት ላፌ ለከት የለው፤
የዘንድሮው መጣ እጅ እግር የሌለው፡፡
የሚል ቁዘማ ውስጥ ከመዘፈቅ ሳያድነን አይቀርም፡፡
ቺርስ!!

ሰላማዊ ትግላችንን ከፍ አድርገን እንቀጥላለን!!!

$
0
0

semayawi

ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ ጊዚያት በሐገራችን የሚፈፀሙ የተለያዩ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶችና ህገ ወጥ ድርጊቶች ኢንዲቆሙ ለመንግስት የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቢቆይም ከመንግስት የተሰጡት ምላሾች ግን ጥያቄዎቻችንን ማንቋሸሽና ማጣጣል ወይም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ማለፍ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ፓርቲያችን ጥያቄዎችን የሚያቀርበው መንግስት አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው ቢሆንም ችግሮቹ እስካሁንም ሳይፈቱ አንዳንዶቹም እየተባባሱ ቀጥለዋል፡፡ በመሆኑም ፓርቲያችን ከዚህ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጥሪ ለመንግስት አቅርቦ መልስ ከተነፈጋቸው መካከል፤

1ኛ. ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና
አባላትን በአሸባሪነት ስም ማሰርና ማሰቃየትን አጥብቀን የምንቃወም መሆኑንና እስረኞችንም እንዲፈታ የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን ምንም መልስ ያልተገኘ በመሆኑ፤
2ኛ. የዜጎችን ሰብዓዊና ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ኢሰብዓዊ በሆነ ድርጊት በታጠቁ ኃይሎች እንዲፈናቀሉ ማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሆኑ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡና የተፈናቀሉት ዜጎችም በአስቸኳይ ወደየመኖሪያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ በመንግስትም ሆነ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው የጠየቅን ቢሆንም አሁንም ገና የሚፈናቀሉ ዜጎችን ስም ዝርዝር በየማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ ተለጥፎ እያየን በመሆኑ፤
3ኛ. መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ፣ የእምነት ስርዓታችንና የሃይማኖት መሪዎቻችንን እምነታችን
በሚፈቅደው ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን በአሸባሪነት ወንጀል በመክሰስ በእስር እንዲማቅቁና ሰብዓዊ መብታቸው እንዲጣስ መደረጉ እንዲቆምና ያነሷቸውም የእምነት ነፃነት ጥያቄዎቻቸው እንዲከበር የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን የተገኘ መልስ ባለመኖሩ፤
4ኛ. መንግስት የኑሮ ዉድነትን፣ የሥራ አጥነትንና በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሌቦችን የሚቆጣጠርባቸውን
መንገዶችና ፖሊሲዎች በማዉጣት ሐገራችንን ከቀውስና ዜጎችንም ከሰቆቃ እንዲያወጣ በተደጋጋሚ ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ሰሚ አጥተው በመቆየታቸው እነዚህ ችግሮች እንዲፈቱ አሁንም አጥብቀን የምንጠይቅ መሆኑ እና ሌሎችም፤

በመንግስት ምላሽ የተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብን ትኩረት የሚያገኙበትን መንገድ መፈለግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚሁ መሰረት ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች በሚገኙበት ድምፃችንን ለማሰማት ከግንቦት 15 – 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስና ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ከላይ ያነሳናቸውና ሌሎችም ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ ሰማያዊ ፓርቲ ለመጠየቅ ወስኗል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ጥያቄዎች እንዲመለሱ የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበራትና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእነዚህ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ሚያዚያ 29 ቀን 2005 ዓ. ም
አዲስ አበባ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤቱን እንዲለቅ ተገደደ

$
0
0

 

ኢሳት ዜና:-ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለኢሳት በላኩት መረጃ እንደገለጹት ጋዜጠኛ ተመስገን ተከራይቶ በሚኖርበት ቀበና አካባቢ ያለው ቤቱን እንዲለቅ በአከራዩ የተነገረው አንድ የመስተዳድሩ ባለስልጣንና አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ አከራዩ ቤቱን እንዲያስለቀቁት ማስጠንቀቂያ ከሰጡዋቸው በሁዋላ ነው።

የቤት አከራዩ “  ሁለቱ ሰዎች መጥተው ለመሆኑ ተመስገን ምን እንደሚሰራ ያውቃሉ ወይ? ተመስገን ማን እንደሆነስ ጠንቅቀው ያውቃሉ ወይ?  ለማንኛውም ዛሬ የምናሳውቅዎት እርሱ ለአካባቢው ሰላም ያሰጋል፣ ከዚህ በሁዋላ እንዳያስቀጥሉት ” ብለው እንዳስጠነቀቁዋቸው ለጋዜጠኛው በመንገር በአስቸኳይ ቤት እንዲፈልግ ተማጽነዋል። ጋዜጠኛ ተመስገንም ቤቱን በፍጥነት ለቆ ለመውጣት እንደሚቸገርና የአንድ ወር የቤት መፈለጊያ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጆች ለራሳቸው አሲምባ የሚል ስም በሰጡት የጋዜጠኛው መኖሪያ ቤት ውስጥ የኢዲቶሪያል ስብሰባዎችን እና ጽሁፎችን ያዘጋጁ እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።

ጋዜጠኛ ተመስገን የሚያዘጋጀው ፍትህ ጋዜጣ በመንግስት ጫና እንዲቋረጥ ከተደረገ በሁዋላ ጋዜጠኛው ህተመቱን ሊያስቀጥል የሚችልበትን ፈቃድ እስካሁን አላገኘም። ከ106 በላይ ክሶች ያሉበት ተመስገን ፣ አሁንም ጽሁፎችን በፌስቡክና በተለያዩ ድረገጾች በመጻፍ ላይ ይገኛል።

የወያኔ የዘር ማጥራት ዘመቻ

$
0
0

amharaBy Dawit Melaku ( Germany)     

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ላለፉት 38 ዓመታት  አንግቦት የተነሳው አንድን ብሔር ለይቶ የማጥራት(Ethnic cleansing) ዘመቻ  ዛሬም ቀጥሎበታል፡፡ይህ ቡድን በስልጣን እስካለ ድረስም ወደፊት ይቀጥላል፡፡ዜጎች በገንዛ ሀገራቸው ከእንስሳት ያነሰ ክብር ተነፍገው ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ፣ ንብረት እንዳያፈሩ፣ ያፈሩትንም ንብረት በተደራጁ ዘራፊዎች እንዲነጠቁ እየተደረገ  ነው፡፡በተለያዩ ሀገራት የእንስሳት መብት ተከራካሪ ወገኖች ስለእንስሳት አያያዝ እና እንክብካቤ ተደራጅተው በጋራ እየተንቀሳቀሱ  በሚገኙበት ባሁኑ ወቅት ከጊዜው ጋር አብሮ መራመድ የተሳናቸው ዘረኛ ቡድኖች በተለያዩ ጊዜያት በአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኞቻችን ላይ የሚፈጽሙት ጭካኔ የተሞላበት ግፍ  የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልብ የሚያደማ ነው፡፡

“ዶሮን አስረዝሞ ሲያስፘት የፈቷት ይመስላታል” እንደሚባለው የኢትዮጵያ ህዝብ አጋጣሚዎችን እየጠበቀ እስካሁን በትግስት ስለጠበቃቸው ከስተታቸው መማር የማይችሉት እና ትግስትን ከፍራቻ የሚቆጥሩት ወያኔዎች ዛሬም ከተጠናወታቸው የጥላቻ ዛር መላቀቅ አልቻሉም፡፡ይሁን እንጂ ይህን የመሰለ አሳፋሪ እና ትውልድ የማይረሳው ወንጀል የፈፀሙ የወያኔ ባስልጣናት እና ጉዳይ አስፈፃሚ የክልል ጀሌዎቻቸው ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡የወያኔዎች ግፍ በዝርዝር ለመጥቀስ ብዙ ጊዜ እና ራሱን የቻለ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ የሚጠና ቢሆንም በጉልህ ከሚጠቀሱት መካከል የጎንደር እና የወሎን ለም መሬቶች ወደ ትግራይ ክልል ለመቀላቀል በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ አማርኛ ተናጋሪዎች ቤታቸው በእሳት እየጋየ አብረው ሲለበለቡ በተደራጀ መልኩ አልተቃወምናቸውም፡፡በሀረር፣በበደኖ፣ በአርሲ፣ በአርባጉጉ፣ወዘተ ወያኔዎች በለኮሱት እሳት ወገኖቻችን ሲታረዱ፤አይናቸው እያየ በገደል ሲወረወሩ እያንዳንዱ በግሉ ከማዘን ባለፈ የተወሰደ ስር-ነቀል  እርምጃ አልነበረም፡፡ዶሮ ጫችቶቹዋን በጭልፊት ስትነጨቅ ለጊዜው ስትጮህ ትቆይእና ድጋሜ መጥታ እስክትነጥቃት ዝም ብላ እንደምትጠብቀው እኛም ያለፉትን በደሎች በሆዳችን አምቀን እንደያዝነው የቀደመው ጠላት አሁንም ለድጋሜ ጥፋት ይዘጋጃል፡፡

“ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም፡፡” እንደሚባለው ዘረኛው ቡድን አላማየ ብሎ የተነሳው እና አሳካዋለሁ ብሎ የሚያልመው አማርኛ ተናጋሪዋችን በሙሉ ማጥፋ እና የሀገሪቱን ብሄራዊ ቋንቋ ሳይቀር ምርጥ ብሎ በሚጠራቸው በታላቋ ትግራይ ቋንቋ መተካት ነው፡፡ በ1993 ዓ.ም 25,000 አማራዎች ከምስራቅ ወለጋ እንዲፈናቀሉ ተደርጉዋል፡፡ምናልባት እነዚህ አማራዎች እንደሌሎች ሁሉ ብዙ ያልተነገረላቸው በመሆኑ እና ወደፊትም ወያኔዎችን ለፍረድ በሚቀርቡበት ሁኔታ ላይ ይበልጥ ሊረዳ ስለሚችል ባይኔ ያየሁትን እና ነገ ተዳፍኖ እንዳይቀር በማሰብ ዘርዘር አድርጌ አቀርበዋለሁ፡፡ ተፈናቃዮች ለበርካታ ዓመታት በአካቢው ይኖሩ የነበሩ እና እዚያው ቦታ ተወልደው ለአቅመ-አዳም እና ለአቅመ-ሄዋን የደረሱ ሁሉ ይገኙበታል፡፡እነዚህ ተፈናቃዮች ከምስራቅ ወለጋ ሲፈናቀሉ መጥተው ያረፉት ምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ ነበር፡፡ለበርካታ ቀናት እዚህ ቦታ ሲሰቃዩ ከቆዩ በኋላ ወደ አዊ ዞን በዳንግላ ወረዳ ስር በሚገኘው ጃዊ በረሃ እንዲሰፍሩ ተደረገ፡፡ጃዊ   በበረሃማነቱ የሚታወቅ፤ቢጫ ወባ ተብሎ የሚጠራው የወባ ዝርያ አመቱን ሙሉ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰትበት፤ ለሰው መኖሪያ የማይመች ምንም አይነት መሰረተ-ልማት  የሌለበት ፣ረግረጋማ ፤   በጫካ  የተሸፈነ ቦታ ነው፡፡ያኔዎች እነዚህን ተፈናቃዮች ጃዊ እንዲሰፍሩ ያደረጓቸው መፈናቀላቸው ተገቢ ስላልሆነ ለወደፊቱ ቤት ሰርተው ንብረት አፍርተው እንዲኖሩ በማሰብ አደለም፡፡ነገር ግን እነዚህን ሰዎች  ለማጥፋት  የተሻለ አማራጭ ስላገኙ ነው፡፡ይኸውም አማራጭ ሁለት ዓይነት ጠቀሜታ ያስገኝላቸዋል፡፡ የመጀመሪያው ጠቀሜታ ከቡሬ በማራቃቸው ተፈናቃዮችን በተመለከተ በውጭ ለሚኖሩት ኢትዮጵያውያን እና ለመገናኛ ብዙሀን መረጃ እንዳይወጣባቸው  በማድረግ ይረዳቸዋል፡፡በዚህም በውጭው አለም ያላቸውን በውሸት የታጀለ ዲፕሎማሲያዊ ጠቀሜታ ሊያተርፉ እንደሚችሉ ይገምታሉ፡፡ ሁለተኛው እና ትልቁ ጠቀሜታቸው ግን እነዚህን ተፈኛቃዮች በወያኔዎች ተገደሉ ከሚባል በገዳይነቱ በሚታወቀው  በተለምዶ ቢጫ ወባ(Phalisipharum malaria) ተብሎ በሚጠራው የወባ በሽታ በማስጨረስ   በህመም  ሞቱ መባል የተሻለ የተቀነባበረ ሴራ መሆኑን በመረዳታቸው ነው፡፡በዚህም መሰረት ሰፋሪዎቹ በቂ ህክምና በማይገኝበት ለስሙ ብቻ የተቋቋመች አንዲት አነስተኛ ክሊኒክ፤ በግዳጅ መልክ ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የጤና ባለሙያዎች፤የተወሰኑ የሚዋጡ እንክብሎች ብቻ እየቀረቡ ፤በሽተኞች በድንኳን ውስጥ እየተኙ እንዲታከሙ ተወስኖባቸዋል፡፡ በዚህም ያልተሟላ ህክምና በየቀኑ በግምት ከ20-30 ሰዎች የሞትን  ጽዋ ይጎነጩ ነበር፡፡

 

 

በተለይ ነፍሰ-ጡር እናቶችና ህፃናት ወዲያውኑ ለእልቂት ተዳርገዋል፡፡በቦታው አንቡላንስ ስላልነበር ሰዎችን ወደ ህክምና መስጫ ቦታው ለማምጣት በቃሬዛ ተሸክመው ነበር የሚያመጧቸው፡፡የወባው ገዳይነት አስታማሚ ሁኖ ተሸክሞ የመጣው ሰው ያመጣው በሽተኛ ምርመራ ተደርጎለት የተወሰኑ የሚዋጥ መድሃኒቶች እስኪሰጠው ድረስ የብርድ ስሚት ተሰምቶት ጸሀይ ልሙቅ ብሎ በደቂቃዎች ውስጥ በዚያው ህይወቱ ያልፍል፡፡በጣም የሚገርመው እና የወያኔዎችን  አረመኔነት የሚገልጸው ደግሞ በህይወት ያሉት ሞትን ሸሽተው እግር አውጭኝ በማለት ወደሚያውቋቸው ዘመዶቻቸው እና ወዳጆቻቸው ህይወታቸውን ለማትረፍ ቦታውን ለቀው ሲሄዱ በአካባቢው በሚኖሩ የወያኔ ታጣቂዎች ተይዘው እንዲመለሱ እየተደረገ ፤ሆን ተብሎ የመድሀኒት እጥረት እንዲከሰት በማድረግ፤ፈዋሽነታቸው አጠራጣሪ የሆኑትን የአዲግራት መድሀኒት ፋብሪካ ምርቶች ብቻ በማቅረብ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡እነዚህን ወገኖቻችን በግፍ ሲያስጨርሱ ለፍርድ እንዲቀርቡ አላደረግንም፡፡  ሃላፊነትንን ባግባቡ አለመወጣትም በወያኔዎች መንደር ስለማያሰጠይቅ በወቅቱ በስልጣን ላይ የነበሩ ባለስልጣናትም ምንም አልተባሉም፡፡ይልቅስ በወያኔዎች ዘንድ የሚያስጠይቀው ለህዝብ መቆርቆር ፤ሰባዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ  ፤ፍትህ እንዲሰፍን መጠየቅ ነው፡፡ለዚህም ነው ለነፃነት የሚታገሉ ጀግኖት በቃልቲ እስርቤት እየማቀቁ የሚገኙት፡፡አንዱአለም አራጌ መቼ ነው ኢፍትሃዊነቱን የምታቆሙት፤መቼ ነው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ የምትወርዱት ፤መቼ ነው ማሰቃየት የምታቆሙት መቼ ነው ማሰር  የምታቆሙት ነበር ያለው ፡፡ሙሉውን ቃል ይህን ይመልከቱ፡፡http://www.youtube.com/watch?v=eIAewbwI9oo፡፡  ይህን የመሰለውን የመብት ተከራካሪ ነው በግፍ አስረው የሚያሰቃዩት፡፡ይህ ነው ለወያኔዎች ሽብርተኝነት፡፡

በ2004 ዓ.ም 30,000 አማራዎች ከደቡብ ክልል ጉራፋይዳ ወረዳ ተፈናቅለዋል፡፡እነዚህን ተፈኛቃዮች በተመለከተ የዘረኛነት መሀንዲስ የሆነው፤ አሁንም በሙት መንፈስ ሀገሪቱን የሚመራው አቶ መለስ ዜናዊ  ተፈናቃዮችን በተመለከተ ለይሰሙላ ለተቋቋመው ምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ” ከምስራቅ ጎጃም የመጡ ቁጥራቸው 30,000 የሚሆኑ አማራዎች ተፈናቅለዋል፡፡እነዚህ አማራዎች በአንድ አጋጣሚ  በሰፈራ ምክንያት ወደክልሉ የመጡ፤ ከ10 አመት በላይ የተቀመጡ ፤ጉራፋይዳ ምስራቅ ጎጃም እስኪመስል ድረስ አስተዳደሩም ሁሉም አማራዎች ናቸው፡፡ችግሩ አማራዎች መሆናቸው አይደለም! የእነዚህ ሰዎች ስለተፈናቀሉ አማራው ተነክቷል ወይ?; አማራው ቀርቶ ምስራቅ ጎጃም ተነክቷል ወይ” ችግሩ ያለው አንዳንድ በኢትዮጵያ አንድነት እንታወቅ ፤ መለያ ባህሪያችን የኢትዮጵያ እንድነት ነው የሚሉ የመንደርተኝነት ጥያቄ ያነገቡ ቡድኖች የሚያናፍሱት አሉባልታ ነው፡፡ በማለት ነው የመለሱት፡፡የሪፖርቱ ሙሉ ማብራሪያ ይኸን ይመስላል http://www.youtube.com/watch?v=H-dqM6Iq6ck እንግዲህ 30,000 ሲፈናቀል አማራው አልተነካም ማለት ምንያክል መጠነ ሰፊ የጥፋት ድግስ እንደደገሱ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ እነዚህ ተፈናቃዮች የት እንደገቡ ማንም እርግጠኛ ሁኖ መናገር የሚችል የለም፡፡አንድም በጅምላ ጨርሰዋቸዋል አለያም ሰው በማያያቸው ቦታ ወስደው እንደ በፊቶቹ በበሽታ እንዲያልቁ አድርገዋል፡፡

በቅርቡ ቁጥራቸው ከ10,000 የማያንሱ የአማርኛ ተናጋሪዎች ከቤኒሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን በግፍ ከቀያቸው ከተፈናቀሉ በኋላ በመላው ዓለም ውግዘት እና ተቃውሞ ሲገጥማቸው  ወደመጡበት ተመልሰው እንዲሰፍሩ ተደርጉዋል፡፡እነዚህ ተፈኛቃዮች ንብረታቸውን ተዘርፈው ቤታቸው ተቃጥሎ የእለት ምግብ እንኳን ያልያዙ እንደመሆናቸው አሁንም ለከፋ ችግር ተጋልጠው ይገኛሉ፡፡ተፈኛቃዮች ህይወታቸው አደገኛ ሁኔታ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል መገመት ያቻላል፡፡ካለፈው ልምድ በመነሳት ወያኔዎች እንዚህን ወገኖቻችንን ህክምና እንዳያገኑ በማድረግ ሊያጠፏቸው ስለሚችሉ  አስፈላጊውን እርዳታ በማሰባሰብ ልንደርስላቸው ይገባል፡፡

በመጨረሻም መጠኑ ይለያይ እንጂ የወያኔ  የብሔር ፖለቲካ ያላፈናቀላቸው ፤እስራት እና ግድያ ያልደረሰባቸው  ብሄሮች እና ብሄረሰቦች አይገኙም፡፡እያናዳንዳችን በተደራጀ እና በተቀናጀ መልኩ እነዚህን ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ በማድረግ እና ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሀገራችን ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ለማውጣት በጋራ መቆም ያገባናል፡፡ የአቶ መለስን ራዕይ እናስፈጽማለን እያሉ አሁንም በቀቢጸ-ተስፋ ከወዲያ ወዲህ የሚባዝኑትም ሆኑ እንደ አቶ ታምራት ላይኔ ያሉ በስደት ላይ የሚገኙ ወንጀለኞች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እነሱ በሚሰጡት ቀጥተኛ ትእዛዝ መሰረት ለሞቱት ፣ለተፈናቀሉት፤ለወደመው ንብረት፣ለደረሰው ስነልቦናዊ በደል ቀጥተኛ ተጠያቂዎች በመሆናቸው በዓለም አቀፍ ፍርድቤት ጉዳያቸው እንዲታይ እና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኑ እንዲደረግ ለመላው  ወገን ወዳድ ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!


Hiber Radio: “ኢትዮጵያውያንን በአውሮፕላን መርዝ እየረጨ ያስጨረሰው ግራዚያኒ ሐውልት ሲቆምለት እሱ ያስገደላቸው አቡነ ጴጥሮስ ሐውልታቸው መፍረሱ ያሳዝናል”ኪዳኔ ዓለማየሁ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ሚያዚያ 27 ቀን 2005 ፕሮግራም

>
አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የግራዚያኒ ሐውልት እንዲፈርስ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ የሚያስተባብረው ግብረ ሀይል ቦርድ ም/ሰብሳቢ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
በዓሉና የኑሮ ውድነቱ ያስመረረው ኢትዮጵያዊ ህይወት ቅኝት (በመረጃ ላይ የተመሰረተ ትንታኔ)
ሌሎች ቃለ መጠይቆች አሉን
የቬጋስ የስራ ማቆም አድማ መንታ ገጽታዎች አሸንፈው ወደ ስራ የገቡና ዛሬም በትግል ላይ ያሉ
ዜናዎቻች
- ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ለመደራደር ዝግጁ ነኝ ትላለች ፡አስመራ በበኩሏ ቅድመ ሁኔታ ጠይቃለች
- የእነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ መደረግ ተከትሎ በአገዛዙ ላይ አለማቀፍ ውግዘቶች እየወረዱ ናቸው
- ጋዜጠኛ እስክንድር የዋል ይደር እንጂ እውነት ትወጣለች ብሏል
- ግብጽ “በኢትዮጵያ ላይ የጠመንጃ ቃታዮን እልስብም “አለች ካይሮ በዲፕሎማሲ እሩጫው መግፋቱን የመረጠች ትመስላለች
- የኑሮ ውድነቱን ተከትሎ በአገር ቤት የበዓል ገበያ ቀዝቅዞ እንደነበር ተዘገበ
- የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት መነሳት በኢትዮጵያውያን ላይ ቅሬታ ፈጠረ
- የአገዛዙን ለአገሪቱ ታሪክና ቅርስ ያለውን ጥላቻ ያሳየበት ሒደት ነው ተብሏል

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

ሰማያዊ ፓርቲ በአፍሪካ ሕብረት 50ኛ አመት ክብረ በአል ዕለት በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ

$
0
0

*ሰልፈኞች ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ
በዘሪሁን ሙሉጌታ
(ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ዕትም)

semayawi partyከመጪው ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ አመት የወርቅ እዮቤልዩ በአል ላይ ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ተደረገ።

ሰልፉን ያዘጋጀውና የሚመራው በቅርቡ የተመሰረተው ሰማያዊ ፓርቲ ሲሆን የሰልፉም አላማ ፓርቲው ከዚህ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ለመንግስት ጥሪ አቅርቦ መልስ ያላገኙ አራት ርዕሰ ጉዳዮች ትኩረት እንዲያገኙ ለማድረግ መሆኑን ተገልጿል።

የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ስለሺ ፈይሳ፣ የፓርቲው የሕግ ጉዳይ ኃላፊ ወጣት ይድነቃቸው ከበደ እና የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አሮን ሰይፉ በጋራ በፓርቲው ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳመለከቱት የተቃውሞ ሰልፉ የሚደረገው የተለያዩ ሐገራት፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና መሪዎች በሚገኙበት ድምፃችን ለማሰማት ነው ብለዋል።

በዚሁ መሠረት ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ጥቁር ልብስ በመልበስና ግንቦት 17 ቀን 2005 ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ጽሕፈት ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ አራቱን ጥያቄዎች እንዲመለሱ ፓርቲው ግፊት እንደሚያደርግ አመራሮቹ በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል።

የፓርቲው አመራሮች መመለስ ይገባቸዋል ያሉዋቸው አራቱ ጥያቄዎች መካከል፣ ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባላትን በአሸባሪነት ስም ማሰርና ማሰቃየትን አጥብቀን የምንቃወም መሆኑንና እስረኞችንም እንዲፈቱ የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን ምንም መልስ ያልተገኘ በመሆኑ፤ የዜጐችን ሰብዓዊና ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ኢሰብዓዊ በሆነ ድርጊት በታጠቁ ኃይሎች እንዲፈናቀሉ ማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሆኑ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡና የተፈናቀሉት ዜጎችም በአስቸኳይ ወደየመኖሪያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ በመንግስትም ሆነ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው የጠየቅን ቢሆንም አሁንም ገና የሚፈናቀሉ ዜጎችን ስም ዝርዝር በየማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ ተለጥፎ እያየን በመሆኑ፤ መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ፣ የእምነት ስርዓታችንና የሃይማኖት መሪዎቻችንን እምነታችን በሚፈቅደው ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን በአሸባሪነት ወንጀል በመክሰስ በእስር እንዲማቅቁና ሰብዓዊ መብታቸው እንዲጣስ መደረጉ እንዲቆምና ያነሷቸውም የእምነት ነፃነት ጥያቄዎቻቸው እንዲከበር የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን የተገኘ መልስ ባለመኖሩ፤ መንግስት የኑሮ ውድነትን፣ የሥራ አጥነትንና በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሌቦችን የሚቆጣጠርባቸውን መንገዶችና ፖሊሲዎች በማውጣት ሐገራችንን ከቀውስና ዜጎችንም ከሰቆቃ እንዲያወጣ በተደጋጋሚ ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ሰሚ አጥተው በመቆየታቸው እነዚህ ችግሮች እንዲፈቱ አሁንም አጥብቀን የምንጠይቅ መሆኑ ለማስገንዘብ ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ፓርቲው በጣሊያን ሀገር ለፋሺስት ግራዚያኒ መናፈሻና ሐውልት መቆሙን ተከትሎ በፓርቲውና ከሌሎች የሲቪክ ማህበራት ጋር ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራቱ የተወሰኑ የፓርቲው አመራሮችና የሰልፉ አስተባባሪዎች ታስረው መለቀቃቸው አይዘነጋም።n

ጥንታዊው ባንኮ ዲሮማ ሕንፃ የመደርመስ አደጋ ተጋርጦበታል

$
0
0

ከረጅም ዓመታትበፊት በልዩ ዲዛይን በአፄ ሀ/ስላሴና በምስካየ ህዙናን መድሃኒአለም የጋራ ገንዘብ የተሰራውና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሆነው ባንኮ ዲሮማ ሕንፃ ያለበቂ ጥናትና ጥንቃቄ በተያዘ የሌላ ሕንፃ ግንባታ እቅድ ለመደርመስ አደጋ መጋለጡን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ።

በሀገሪቱ በስነሕንፃው ዘርፍ ቅርስ የሆነው ፒያሳ አካባቢ የሚገኘው ባንኮ ዲሮማ ሕንፃ የመደርመስ አደጋው የተጋረጠበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሕንፃው ቅጥር ግቢ በስተሰሜን በኩል በሚገኘውና ከህንፃው መሠረት ጋር ይገናኛል ተብሎ በሚገመተው ባዶ ቦታ ላይ ለመስራት በተያዘው የሌላ ህንፃ ግንባታ የመሰረት ቁፋሮ ጋር በተያያዘ ነው። ከሕንፃው 10 ሜትር እንኳን በማይርቅ ክፍት ቦታ /የህንፃው ፓርኪንግ/ ላይ ቁፋሮ ለመጀመር ማሽነሪዎች የገቡ ሲሆን ቁፋሮው ወደ መሬት 10 ሜትር ጥልቀት እንዳለው ከባለሙያዎች ለመረዳት መቻላቸውን ተናግረዋል።

በተለይ ከተወሰኑ ሜትሮች ጥልቀት በኋላ አለት /ድንጋይ/ ይገኛል የሚል ግምት መኖሩን፣ በቁፋሮ ወቅት የአለቱ መገኘት እውን ከሆነ የነባሩን ባንኮ ዲሮማ ሕንፃ መሰረት ሊያናጋውና ለመደርመስ አደጋ ሊያጋልጠው እንደሚችል በሕንፃ ግንባታ ሙያተኞች ጭምር እንደተገለፀላቸውና በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ሥጋት ላይ መውደቃቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። የግንባታ ሥራውን የወሰደው ተቋራጭ ድርጅትም ባለው ከፍተኛ ሥጋት የተነሳ ለባንኮ ዲሮማ ሕንፃ ቀድሞ ኢንሹራንስ የገባለት መሆኑ ተሰምቷል። ኢንሹራንስ ቀድሞ መግባቱ ደግሞ ሕንጻው ለአደጋ የመጋለጥ ሥጋቱ ምንያህል ከባድ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ነው።

በመዲናችን በስነ ሕንፃው ዘርፍ ቀደምት ከሆኑት ሁለት ሕንፃዎች አንዱ የሆነው ባንኮ ዲሮማ ህንፃ ሊደርስበት ለሚችለው ጉዳት ኢንሹራንስ መገባቱ ከቅርስ ጥበቃ አኳያ ሲታይ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

ምክንያቱም ሕንጻው ከተደረመሰ በኋላ በተገባለት ኢንሹራንስ መሠረት ሊገነባ ቢችልም እንኳን ታሪካዊነቱንና ቅርስነቱ ሙሉ ለሙሉ የሚያጣ በመሆኑ ነው።

ስለዚህ እንዲህ አይነት የሀገርና የሕዝብ ሀብት የሆኑ ቅርሶችን የመጠበቅ፣ ታሪካቸውን አፈላልጎና አደራጅቶ የመመዝገብ ኃላፊነት ያለበት የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ተቋም ይህንን በህዝብ ልብ ውስጥ በቅርስነት ተመዝግቦ እንደ አይን ብሌን የሚታይ ሕንፃ ከውድመት ለማዳን ፈጥኖ እንዲንቀሳቀስ ጥሪ አቅርበዋል።

“ሕንጻው በቅርስነት ተመዝግቧል? ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ “ዋናው ቁምነገር በቅርስነት የተመዘገበ ያልተመዘገበ የሚለው ሳይሆን የሀገር ቅርስ መሆኑ በሕዝቡ መታመኑ ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ከመዲናችን አዲስ አበባ ቀደምት ከሆነውና ባንድ ወቅት ትልቅ ፎቅ ነው ተብሎ ጉዳት ደርሶበት ከነበረው ገብረ ወልድ ሕንፃ ተመጣጣኝ እድሜ ያለው ባንኮ ዲሮማ ሕንፃ ያለበቂ ጥናት በሚደረግ የሌላ ሕንፃ ግንባታ ምክንያት እንዳይደረመስና ቅርስነቱ እንዳይጠፋ የሚመለከተው አካል ሁሉ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ተቋም ፈጥነው ሊደርሱለትና ከግንባታ በፊት ለነበሩ ህንፃ ደህንነት ሲባል በቂ ጥናት ሊደረግበት ይገባል። ከጥቂት ዓመታት በፊት ተፈጥሮአዊ ቀለሙን ሊያሳጣ የሚችል ቀለም የመቀባት እድሳት ሊደረግ ሁሉ ነገር ካለቀ በኋላ ታሪካዊነቱን ወይም ቅርስነቱን ያጣል በሚል የነበረውን የቀለም ይዘት ይዞ እንዲቀጥል መደረጉን አስታውሰዋል።

ሌላው ስጋት ከሕንፃው መሰረት ስር መነሻው ያልታወቀ ከፍተኛ የውሃ ክምችት መኖሩ አሁን ከታቀደው ሥራ ጋር ተያይዞ ሕንጻውን ለውድመት ይዳርገዋል የሚል ነው።

በባንኮዲሮማ ፓርኪንግ ውስጥ ሊሰራ ስለታቀደው አዲስ ሕንፃ እና ነዋሪዎች ያቀረቡትን ስጋት በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ

ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ መታዘዙ በአካባቢው ቁጣን ቀሰቀሰ

$
0
0

(ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው) በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቦረና ዞን ቡሌሆራ/ ሀገረ ማርያም/ ከተማ የምትገኘው ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ መታዘዙ በአካባቢው ቁጣ መቀስቀሱን ታወቀ፡፡ የአካባቢው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት “የከተማው ከንቲባ ሀላፊነት በጎደለው እና በማን አለብኝነት ቤተክርስቲያኑን አፍርሰው ቦታውን ለባለሀብት ለመሸጥ መወሰናቸው ለሀይማኖቱም ለህዝቡም ያላቸውን ንቀት ያሳዩበት ነው፡፡” ሲሉ አውግዘዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች አሁን የወሰዱትን አቋም ሲገልጹ የከተማው ከንቲባ በድፍረት ቤተክርስቲያኑን አፍርሰን እንጨትና ቆርቆቆውን እንድናነሳ አዘዋል ፡፡
“እኛ የእግዚያብሄርን ቤት አናፈርስም ፡፡ እሳቸው ከፈለጉበት በሚረፈልጉት ኃይል ሊያስፈርሱ ይችላሉ ፡፡ ለወረዳው አስተዳደር አመልክተን የወረዳው አስተዳዳሪ በስፍራው ተገኝተውተ ተመልክተውታል ፡፡ ቤተክርስቲያኑ እንዳይፈርስ የሚያስችለው ውሳኔ ይሰጣሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ ተናግረተዋል ፡፡
አስተያየት ሰጪዎቹ በመጨረሻ በሰጡት አስተያየት በዚሁ ከተማ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አለ፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን ካለፈው መንግስት ጀምሮ በከተማው ማስተርፕላን መሰረት ፍቃድና ካርታ አለው ይሁን እንጂ እኚህ የከተማው ከንቲባ ቦታውንና ከቦታው ላይ ያለውን ባህርዛፍ አላስረክብም ብለው ችግር ፈጥረውብን እስካሁን ችግሩ ባልተታበት
ሁኔታ እንደገና አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ ቅድስት አርሴማ ማዘወራቸው ገርሞናል ብለዋል ከተማውን ከንቲባ አቶ ቡሌ ገመዳ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡበት በተንቀሳቃሽ ስልካቸው እና በጽ/ቤታቸው ስልክ ለማግኘት ያደረግነው መከራ ለጊዜው አልተሳካም ፡፡

ከዋሽንግተንና አካባቢዉ የጋራ ግብረሃይል የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

Moving-picture-Ethiopia-flag-flapping-on-pole-with-name-animated-gif

የዋሽንግተንና አካባቢዉ የጋራ ግብረሃይል

Email: dcjointtaskforce@gmail.com

አምባገነኑ እና በፍጹም ማናለብኝነት የኢትዮጵያን ህዝብ ስብእና በመርገጥ፤ በማፈናቀል፤ በመግደል፤ ነጻነቱን በመቀማት፤ ሀገራችንን እየጠፋት የሚገኘዉ የወያኔ ስርአት ከእለት እለት እየፈፀመ ያለዉ ግፍ እየከረረ መጥቷል። ለነጻነታቸዉ ሚታገሉ ዜጎችን በሀገራቸዉ አሸባሪ እያለ እያሰረ ይገኛል። ድምጻችን ይሰማ፤ የእምነት ነጻነት ይጠበቅ፤ ህገ መንግስቱ ይከበር እያሉ የሚታገሉ ወገኖቻችንን አክራሪ እያለ ሲሻዉ በየእስር ቤት ያጉራል፤ አልያም ይደበድባል ወይም ይገድላል። የተከበሩ የእምነት ተቋማትን በኢንቨስትመንት ስም አያጠፋ ይገኛል። የሀገሪቱን መሬት ነዋሪዉን በማፈናቀል ለዉጭ ባለብቶች በዉዳቂ ዋጋና የህብረተሰቡንና ሀገርን ጥቅም በማያስጠብቅ ሁኔታ ሸንሽኖ እየሸጠ ይገኛል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እህቶችችንን በአረብ ሀገራት ከባርነት ባልተናነሰ ሁኔታ እየሸጠ ይገኛል። የሀገሪቱን አንጡራ ሀብት በስርአቱ በሚመሩ ኩባንያዎችና በዙርያቸዉ በተሰበሰቡ ፍርፍሪ ለቃሚዎቻቸዉና አጫፋሪዎቻቸዉ አንጠፍጥፎ በመዝረፍ ላይ ነዉ። የህዝቡን በነጻ የመደራጀትና የመምረጥ መብቱን በመግፈፍ ዲሞክራሲን ሙሉ በሙሉ አጥፍቷል፤ በተጨማሪም ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶችንም የማጥፋት ዘመቻዉን እያጧጧፈ ይገኛል። የሀገራችን ዜጎችም በሚደርስባቸዉ እንግልት፤ ኑሮ ዉድነትና፤ ተስፋ አጥነት በመማረር ከመቹዉም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ሀገራቸዉን በመጣል ወደ ጎረቤት ሀገራት በመሰደድ ለእጅግ ከፍተኛ ስቃይና መከራ በመዳረግ ላይ ይገኛሉ። ይሀ ሁሉ አልበቃ ብሎ በሀገራችን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በፍጹም ዘረኝነት ላይ በተመረኮዘ መርህ የአማራ ተወላጆች የሆኑ ወገኖቻችንን ግልጽ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈጸም ከቀያቸዉ አፈናቅሏል። ባጠቃላይ ዘረኛዉና ሀገር አጥፊዉ የወያኔ ስርአት በሃገራችንና በወገናችን ላይ እየፈጸመ ያለዉን ግፍ ዘርዝሮ ለመግለጽ እጅግ ያዳግታል።

ግፈኛዉ የወያኔ ስርአት በሀገራችን እያደረሰ ያለዉን ግፍና ዘረፋ ሳያበቃ፤ የማይጠረቃ የዘረፋ ቋቱን በመያዝ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ላይ ለዓባይ ግድብ ማሰርያ በሚል ሽፋን ገንዘብ ለመሰብሰብ ጥረት እያደረገ ይገኛል። ነገር ግን የወያኔ ስርአት ባሁኑ ወቅት ያልተረዳዉ አንድ ገሃድ የሆነ አዉነታ አለ። የኸዉም ወቅቱ አብዛኛዉ በዉጭ የሚኖር ሀገር ወዳድ ዜጋ ሁሉ ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ግፈኛዉ ስርዓት በሚፈጽመዉ ግፍ በመማረር በአንድነት በመቆም ሀገሩንና ወገኑን ከወያኔ የግፍ ቀንበር ለማላቀቅ በቁርጠኝነት በመነሳት እየታገለ ሚገኝበት ጊዜ መሆኑን ነዉ። በመሆኑም ዓባይ ከመገደቡ በፊት ነጻነት፡ በሚል የጋራ መርህ አንድ በመሆን፤ የስርአቱን ህገወጥ የሆነ የገንዘብ ማሰባሰብ ጥረቶች እያከሸፈ ይገኛል። በተከታታይም በሳኡዲ አረቢያ፤ በደቡብ አፍሪካ፤ በኖርዌይ፤ በስዊድን፤ በአሜሪካ የወያኔዉ ዘራፊ ደም መጣጮች ገንዘብ ለመዝረፍ ያረደጉትን ሙከራዎች በማክሸፍ ቅሌት አከናንቦ ወደ መጡበት መልሷቸዋል። በዚህም ሳያበቃ በሀገሩ ህገ ወጥነትን የተካነዉ ስርአት የህግ የበላይነት ባለባቸዉ ሀገሮች ዉስጥ ያለፍቃድ እያከናወነ የሚገኘዉን የቦንድ ሽያጭ ለየሀገራቱ በማሳወቅ የክስ ዘመቻዉን እያጧጧፈዉ ይገኛል። በዚህም የተደናገጠዉ ስርአት ያካሄድ ለዉጥ በማከናወን በቅርቡ እኤአ ሜይ 11 ቀን 2013 ዓ/ም በአሜሪካን ሀገር በኒዉዮርክ ከተማ ህዝቡን ወገኑንና ሀገሩን በመክዳት የግፍ፡ የግድያ፤ የዘረኝነት፤ የዝርፍያና፤ የእስር አምባሳደሩ ለመሆን በመረጠዉ ድምጻዊ ንዋይ ደበበ ዋና አቀንቃኝነት ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቋል።
ይህን ህዝባችን ቁስል ላይ እንጨት የሚሰነቁር፤ እስካሁን ባደረግነዉ ትግል ላይ ደሞ ያላቸዉን ንቀት የሚያሳይ እኩይ ተግባር እኛ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢና በኒዉ ዮርክ አካባቢ የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን አጥብቀን እንቃወመዋለን። በዚህም መሰረት፡
1. በእለቱ ዝግጅቱ በሚከናወንበት ቦታ እጅግ ከፍተኛ የተቃዉሞ ሰልፍ የምናደርግ ስለሆነ ሁሉም ሀገር ወዳድ የሆነ ወገን ሁሉ በመገኘት ሆዳምነትን፤ ባንዳነትንና፤ አድር ባይነትን አጥብቀን ለመቃወም እንድንሰባሰብ ጥሪ እናቀርባለን።
2. ሌሎች በዝግጅቱ ለመሳተፍ የሚያስቡ ካሉም ዉሳኔያቸዉን ከሃገርና ከወገን ደህንነት አኳያ ደግመዉ እንዲያጤኑ ወገናዊ ማሳሰብያችንን እናስተላልፋለን።
3. በእለቱም በዝግጅቱ ላይ የሚሳተፉትን በቪዲዮና በካሜራ በመቅረጽ በተለይ እዚህ አገር የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ ስርአቱን በሚደግፉት ላይ በሌሎች ሀገሮች በህግ እንደ ተጀመረዉ እኛም ማንነታቸዉን በማጣራት ለሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት የምናስተላልፍና ጉዳዩም ዉሳኔ እስኪያገኝ አጥብቀን የምንከታተል መሆኑን እናሳዉቃለን
4. በዚህ ዝግጅት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ አፍቃሪ ወያኔ / ፀረ ህዝብ ድምጻዉያን ላይ ካሁን በሗላ በዓለም ዙርያ በሚያዘጋጇቸዉ ማናቸዉም ዝግጅቶች ላይ ላለመገኘት የጋራ ማእቀብ ጥሪ እናቀርባለን። ይህም በመሆኑ በእለቱ እነማን እንደተሳተፉ በማጣራት ወደፊት ለህዝቡ የምናሳዉቅ ይሆናል።
የወገናችን ሰቆቃ በጋራ እንደሚወገድ ስለምናምን እስካሁን በጋራ ያከናወናቸዉ እጅግ አርኪ ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ ወገናችን ያደረገዉን ከፍተኛ ተሳትፎ እናደንቃለን። ሃገራችንና ወገናችንን ነጻ የማድረጉ ትግል በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ የጀመርነዉን ትግል በጽናት እንድንገፋበት ጥሪያችንን እያቀረብን በኒዉ ዮርክ በሚደረገዉ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ በ dcjointtaskforce@gmail.com በመጻፍ ተጨማሪ ማብራርያ ማግኝት የሚቻል መሆኑን እናሳዉቃለን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

የዋሽንግተንና አካባቢዉ የጋራ ግብረሃይል
Email: dcjointtaskforce@gmail.com

Ethio Flag

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live