Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመቃወም የሚንቀሳቀሰው የአዲስ አበባ አስተባባሪ ኮሚቴ ሒደታዊ መግለጫ፤

0
0
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአሥሩ ማኅበራት ኅብረት በየሁለት ሳምንቱ የደረሰበትን ለምዕመናን ለማሳወቅ በገባው ቃል መሠረት ባለፉት አስር ቀናት ከመንግሥት ጋር የተወያየባቸውን ጉዳዮች በመግለጫ አሣውቋል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመቃወም የሚንቀሳቀሰው የአዲስ አበባ አስተባባሪ ኮሚቴ ሒደታዊ መግለጫ፤ በኢትዮጵያ […]

ባህር ትራንስፖርት ሜቴክ የ2 ቢሊዮን ብር እዳ አልከፈለኝም አለ

0
0
የሜቴክ የዱቤ አገልግሎት ክፍያ እዳን አለመክፈል የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የ2 ቢሊዮን ብር የዱቤ አገልግሎት ቢሰጥም ክፍያው እንዳልተፈፀመለት ገለፀ፡፡ የወጪና ገቢ እቃዎች ማጓጓዝ ላይ የሚሰራው መንግሥታዊው የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽንም በዚሁ ዘርፍ የዱቤ አገልግሎትን እንደሰጠ ይናገራል፡፡ በጉዳዩ ላይ አሐዱ ቴሌቪዥን ማብራሪያ የጠየቀው የብረታ […]

የኢትዮጵያ ክፍላተሃገር ህብረት ወቅታዊ መግለጫ

0
0
መስከረም 16 ቀን 2012 ዓም(25-09-2019) የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ የነጻነትና የአንድነት ምሰሶ ናት አገራችን ኢትዮጵያ ባስመዘገበችውና ባለፈችበት የረጅም ዘመን ታሪኳ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለአገራዊ ምስረታ፣ለሕዝብ ሰላምና አንድነት ከፍተኛውን ድርሻ አበርክታለች።የቦታ እርቀት፣የተፈጥሮ ውጣ ውረድ፣የጎሳና የቋንቋ መሰናክል ሳያግዳት አቅም በፈቀደው መጠን ከዳር እስከዳር ተንቀሳቅሳ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ብቻ ሳይሆን በፋሲፊክ ዳርቻ ለሚገኙ አገሮች ምእመናን ጭምር የፈጣሪን ቃልና ትእዛዝ፣የብሉይና […]

የደመራና መስቀል በዓል የአንድነት ተምሳሌትነቱን በሚያጎላ መልኩ ይከበራል – የሀይማኖት መሪዎች

0
0
የደመራ እና መስቀል በዓል ሀይማኖታዊ አስተምህሮው በሚፈቅደው መንገድ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመቻቻል እና የአንድነት ተምሳሌትነቱን በሚያጎላ መልኩ ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የሀይማኖት መሪዎች እና መምህራን ተናገሩ። መስቀል እየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ያዳነበት ምልክት ተደርጎ እንደሚወሰድ የምስራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አህጉረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል እና መምህር ምህረትአብ አሰፋ ገልጸዋል። የዘንድሮው የበዓል አከባበርም የእምነቱ […]

የአማራ ብሄርተኝነት ስንክሳር እና ያዘለው አደጋ (በመስከረም አበራ)

0
0
በመስከረም አበራ መስከረም 14 2012 ዓ ም በተማሪዎች እንቅስቃሴ ተፀንሶ የተወለደው የሃገራችን የፓርቲ ፖለቲካ ታሪክ መሰረቱን ያደረገበት ስታሊናዊ ርዕዮተ-ዓለም የዘመኑን ታጋዮች ቀልብ ከሃገራቸው የፖለቲካ አድባር አፋትቶ ከሩሲያ እና ቻይና ጋር ያዋደደ ነበር፡፡ይህ ወደ ራስ ልዩ ሁኔታ በጥልቅ ለመመልከት ፋታ ያልተወሰደበት የፖለቲካ ግልቢያ ነው እስከዛሬ ያላባራ የመከራ ዶፍ በሃገራችን ሰማይ ላይ አዳምኖብን የሄደው፡፡መሰረቱ የተበላሸ ቤት አይፀናምና […]

ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ተጽዕኖ ለማሳረፍ የሚደረጉ መሯሯጦች ተቀባይነት የላቸውም – ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ

0
0
የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ዛሬ (መስከረም 14 ቀን 2012 ዓ.ም) ታላቁ የኢትየጵያ ህዳሴ ግድብን በመጎብኘት ላይ ናቸው። የአባይን ወንዝ በተመለከተ እ ኤ አ የ1959 ስምምነት ተቀባይነት እንደሌለው ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ከጎበኙ ብኋላ ገልጸዋል። እንደ ሚኒስትሩ ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ተጽዕኖዎችን ለማሳደር […]

በ17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የመጀመሪያው ልዑክ ዶሃ ገብቷል

0
0
ባሕር ዳር፡ መስከረም 14/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኳታር አስተናጋጅነት የፊታችን ዓርብ መስከረም 16/2012 ዓ.ም 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ይጀመራል፤ በዚህ ውድድር የሚሳተፉ የስፖርት ልዑካን የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ልዑክ ኳታር ዶሃ መግባቱ ነው የተገለጸው። የአትሌቲክስ ልዑኩ ከሌሊቱ 8፡00 ላይ በዶሃ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የጽሕፈት ቤቱ […]

በሐረሪ ክልል ህገወጥ የመሬት ወረራ

0
0
በሐረሪ ክልል የሚገኝ የማኅበረሰብ የትምህርት ተቋም በይዞታው ውስጥ በሚፈፀም ህገወጥ የመሬት ወረራ የተነሳ የመማር ማስተማር ሥራ መጀመር አልቻልኩም አለ። ድሬዳዋ — የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንም በህገወጥ መሬት ወረራው እየተቸገርኩ ነው ብላለች። የክልሉ ፀጥታ ምክር ቤት ችግሮቹን ለመፍታት ዝርዝር መርኃ ግብር አውጥቼ እየተንቀሳቀስኩ ነው ብሏል። የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በስቶኮልም የሚገኘው የባለአደራው ምክር-ቤት ቻፐተር ቦርድ አባል ተወካዬች የሕሊና እስረኞች  በአስቸኳይና ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ እንዲፈቱ የሚጠይቅ ደብዳቤ አስገቡ

0
0
በዛሬው እለት ማለትም 2019/09/26 በስቶኮልም የሚገኘው የባለአደራው ምክር-ቤት ቻፐተር ቦርድ አባል ተወካዬች ኢትዬጵያ ኢምባሲ በመገኘት ደብዳቤ አስገብተዋል።   ደብዳቤው የባለአደራው ምክር-ቤት አባላት የሆኑት የሕሊና እስረኞች  በአስቸኳይና ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ እንዲፈቱ የሚጠይቅና በቅርቡ የአዲስ አበባ መስተዳድር በ”Reform” ሰበብ በመስተዳድሩ ሠራተኞች ላይ የወሰደው ሕገ-ወጥና ኢ-ፍትሐዊ ከሥራ የማፈናቀል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲስተካከል የሚያሳስብ ነው። –ሙሉውን ደብዳቤ ያንቡቡ—–  

የቤተ መንግስቱ መታደስ –ወድሰው ዋለ

0
0
ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባን ያየኋት በመስከረም ወር 2000 ዓ.ም ነው፡፡ ሀገሬን ስለምወድ የሀገሬን ታሪክ ስለማደንቅ አስቀድሜ አስጎብኙኝ ያልሁት የሀገሪቱ መገለጫ የሆነውን የመንግስቱን ዋና መቀመጫ ቤተ መንግስቱን ነው፡፡ የውጭ አጥሩን እና ጥበቃዎችን አይቸ በጣም ደስ አለኝ፡፡ የውጭ አጥሩ ዘውድ፣ ጦርና ጋሻ አለበት፡፡ በሆነ ወቅት ዋና መግቢያ እና መውጫ በሚመስለው በር ካናቱ ላይ የአናብስት ምስል እና ዘውድ […]

“Fly out of Ethiopia while you can.” ማለትስ አሁን ነው –አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

0
0
አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ) ከተማ ይፍሩ የተባሉ የደርግ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር(?) ለሥራ ጉብኝት ወደ ውጭ ሄደው በዚያው ቀሩ አሉ፡፡ ለምን እንደቀሩ ሲጠየቁ በርዕሴ የጠቆምኩትን የእንግሊዝኛ ዐረፍተ ነገር እንደተናገሩ ይወሳላቸዋል – “አጋጣሚ ባገኘህ ጊዜ (ሁሉ) ከኢትዮጵያ አጥብቀህ ሽሽ!” ተብሎ ቢተረጎም ያስኬዳል-  ህልምና እንግሊዝኛ ደግሞ እንደፈቺው ነው አሉ፡፡ ሀገራችን ካለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት ወዲህ […]

የሌለውን ፈላስፋ ፍለጋ ሳይሆን የጠፋውን ፈላስፋ ፍለጋ ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት የተሰጠ ምላሽ –በመ/ር አበባው አሰፋ[1]  

0
0
ጎንደር ዩኒቨርስቲ ስለ ፈላስፋው ዘረ-ያዕቆብ ሙህራንና ጻህፍት በሁለት ተከፍለው ኢትዮጵያዊ ነው፣ ኢትዮጵያዊ አይደለም በማለት ይከራከራሉ። ኢትዮጵያዊ ነው ከሚሉት ውስጥ ዋናዋናዎች ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ አብርሃም ደሞዝ፣ የኔታ አለማየሁ ሞገስ፣ ፈንታሁን ጥሩነህ፣ ብሩህ አለምነህ ይጠቀሳሉ። ኢትዮጵያዊ አይደለም ከሚሉት ውስጥ ዋናዋናዎች ኮንቲ ሮሲኒ፣ ዲ/ን ድንኤል ክብረት፣ ፍስሐ ታደሰ፣ ሰሎሞን አበበ ቸኮል፣ ካሳሁን አለሙ፣ ታሪኩ ውብነህ […]

የመስቀል ደመራ በአል በ9 አጥቢያ ቤተክርስቲያን በዳላስና አካባቢው በጋራ ይከበራል

0
0
የመስቀል ደመራ በአል በ9 አጥቢያ ቤተክርስቲያን በዳላስና አካባቢው በጋራ ይከበራል

በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር 55 ሰዎች መታሰራቸውን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስታወቀ

0
0
በዛሬው የመስቀል ደመራ በአል አከባበር ላይ 55 የበዓሉ ታዳሚዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት እና ጉዳይ አስፈፃሚ መላከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ ሰይፉ ለቢቢሲ ገለፁ። መላከ ህይወት አባ ወልደየሱስ እንደገለፁት 33ቱ ምእመናን በቁጥጥር ስር የዋሉት ቤተክርስትያኗ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት እንዲቆም የሚያወግዝ ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ለብሰው በመገኘታቸው ነበር። ምእመናኑ […]

የደመራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማንያን ዘንድ ተከበረ

0
0
ይህ በዓል የሚከበረው በ326 ዓመተ ምህረት መስከረም 17 የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ፍለጋ የጀመረችበት ዕለት በመሆኑ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በተለይ የደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በመከበር ላይ ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳን ጨምሮ ፣ በርካታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት […]

“ተራማጁ” እና “አድኀሪው” ኢሕአዴግ –በፈቃዱ ኃይሉ

0
0
ኢሕአዴግ ከስሞ ውሕድ ፓርቲ ሆኖ እንዲመጣ የሚፈልገው ቡድን በአንድ በኩል በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተመራ ነው፤ ከተቃዋሚ ወገን ደጋፊዎችም አሉት። በሌላ በኩል ደግሞ «ፌዴራላዊ ስርዓቱን እና ሕገ መንግሥቱን ማስጠበቅ እንፈልጋለን» የሚለው ቡድን በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እየተመራ ነው፤ እያንዳንዱ እርምጃ፣ ተመጣጣኝ እና ተቃራኒ ድኅረ-ምላሽ አለው። ኢትዮጵያውያን የለውጥ ዕድሎቻቸው ለምን እንደማይፀኑ ሲጠየቁ፥ የሚያገኙት ተደጋጋሚ መልስ “አድኀሪያን” አደናቀፉት […]

በዳላስ ቴክሳስ የመስቀል በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

0
0
በዳላስ ቴክሳስ የመስቀል በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ  

በሞጆ ለዳመራ ስርአቱን ለማድመቅ የሰቀሉትን ባንዲራ በፓሊሶች ተባባሪነት ሰብስበው ይዘው እንዲሄዱ ተደርጓል

0
0
በሞጆ ለዳመራ ስርአቱን ለማድመቅ የሰቀሉትን ባንዲራ በፓሊሶች ተባባሪነት ሰብስበው ይዘው እንዲሄዱ ተደርጓል ፡በኦነግ የሚመራው መንግስት ስርአት ማስያዝ ካልቻለ ህዝብ ስርዓት ሊያሲዛቸው ይገባል ሞገስ መኮነን

“ታማሚ ህሊና  ምንጊዜም ተንኳለኛ ና ጠብ አጫሪ ነው።”–መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

0
0
 የማንም ሰው ህሊና በትዕቢት ና በማን አህሎኝነት ከተወጠረ  ፍርሃ እግዛብሔርን ከውስጡ አምጦ ካወጣ ፣ ታሟል።ህመሙ ለማንም ለምንም ደንታ ቢሥ ያደርገዋል። እራቁቱን አልሄደም እንጂ እብድ ነው።         ለኃይማኖት ደንታ የለውም።ለአማኞቹ ደንታ የለውም። ።ለእምነት ደንታ የለውም።ለቤተ ክርስትያን ደንታ የለውም።ለመስጊድ ደንታ የለውም።        ይህ ሰው  ከላይኛው እስከታችኛው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ካለ ደግሞ  የሚያደርሰው […]

በቢሾፍቱ የደመራ መታጎል ሪፖርታዥ –ዮሃንስ መኮነን

0
0
ትናንት (ዓርብ) ኦርቶዶክሳውያን ካህናት እና ምእመናን ከደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ተነስተው፤ ወደ ደመራ ለመሄድ መንገድ ላይ ሳሉ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የለበሱት ልብስ ላይ “ልሙጥ ባንዲራ አለበት” ያሉ “ቄሮ ነን” የሚሉ ወጣቶች፤ ዝማሬ የሚያሰሙትን ኦርቶዶክሳውያን “አታልፉም” ብለው ከ2 ሰአት በላይ ከመንገድ ላይ ያስቆሟቸዋል:: ካህናት እና ምእመናኑም “ከክርስቶስ ፍቅር የሚለይም ማነው?” በሚለው ዝማሬ ታጅበው አጋቾቹን […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live