Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ይድረስ ለክቡራትና ክቡራን ወግኖቸ –ዕርቁ ይመር ኢትዮጵያዊነት፡ የዜጎች መብት ማስከበሬ ጉባኤ

$
0
0
በቅድሚያ ጥሪያችንን አክብራችሁ እርዳታችሁን ለሰጣችሁት ኢትዮጵያዊያን ልባዊ መስጋናችንን እያቀረብን ሌሎቻችሁም የምትችሉትን ያህል በዚህ በ Go Fund Me አማካኝነት እርዳታችሁን እንዲታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ ዕድሜየን ሙሉ እንደናንተው በልቤ አቅፌ በዜግነት ኩራት የያዝኩትየኢትዮጵያዊነት ሥነ ልቦና በየአቅጣጫው በሚሰነዘር ጥቃት እንዲጠፋ፤ ወጣቱ ትውልድም ሆን ተብሎ የሚወርሰው የአብሮነት እሴት እንዳይኖረውለማድረግ፤ ባለፉት 30ና 40 ዓመታት የተዘመተብትን አሳፋሪ ዘምቻ ሁላችንም የምናውቀው ነው።አሁን ከሚገኝበት የቁልቁለት መንገድ ለማቅናትም ሆነለወጣቱ ትውልድ ለማውረስ የተጠናከረና የተደራጀ ዘመቻ ማድረግ ጊዜው አሁንና አሁን ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊነት፡ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ የኢትዮጵያዊነት ስነ ልቦናን በትምህርት ዘርፍ፤ በጥናትና ምርምር፤ በባህልና ማህበራዊ ትስስር  ዘርፎችበተዘጋጁ መርሃ ግብሮች አማካኝነት ለማደስና ለማዳበር የኢትዮጵያዊነት ኢንስቲትዩት አቋቁመን እንቅስቃሴ አገር ቤት ውስጥ ጀምረናል። ኢትዮጵያውያንንአሁን አለንበት ድረስ ያዘለቀንን የኢትዮጵያዊነት አብሮነት እሴት ማንሰራራት ሁሉም የበኩሉን […]

ኢትዮጵያ ወዴት? ዘረኝነት: ተረኝነትና ስርዐት አልበኝነት!!! –ሃይለገብረኤል አስረስ

$
0
0
ሃገራችን የምትጏዝበት የፖለቲካ ጎዳና የት እንደሚያደርሰን ከመቼውም ግዜ በላይ እርግጠኛ መሆን ያልቻልንበት ወቅት ቢኖር እሁን ነው:: ተስፉ የተጣለበት የለውጥ ጎዞ መስመሩን ስቶ ጽንፈኞች የነገሱበት ምዕራፍ ውስጥ ከቶናል:: ኢትዮጵያችን ወዴት እየተንደረደረች እንደሆነ የሚታይ ነው:: ከታላቅ ተስፋ ወደ አስፈሪ ስጋት!  ከለውጥ ወደ ነውጥ!  ከአንድነት ወደ መንደርተኝነት :: ዲሞክራሲ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ለውጥን ከመገንባት  ይልቅ ወደ ውድመት ዘረፋና ማህበራዊ […]

ዛሬም ያልተቋጨው የኢትዬጵያኖች ወደ ሞት ጉዞ… (በታምሩ ገዳ)

$
0
0
ብዛት ያላቸው ወጣት ኢትዬጵያኖች ከፊታቸው የተደቀነውን በረሃ፣ባሕር እና የጦርነት ቀጠናን እንዲሁም ሞትን ቸል በማለት እጅግ አደገኛ የህይወት መሰወትነት በመክፈል ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የእንግሊዙ ዘጋርዲያን ጋዜጣ በዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ/ኦገስት 27,2019 እኤአ በምስል በተደገፈው የኢትዬጵያዊያን ወጣቶች የስደት መከራን በተመለከተ ትንታኔው ላይ በኢትዬጵያ ውስጥ የሚታየውን ድህነት እና ስራአጥነትን ለመሸሸ መዳረሻቸውን ሰውዲ አረቢያ ያደረጉ በርካታ ወጣት ኢትዬጵያኖች የጅቡቱ […]

የጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይና የሸዋ ኦሮሞ ከባዱ የፈተና ግዜ። (ከተማ ዋቅጅራ)

$
0
0
ሸዋ ስንል በውስጡ የብዙ ብሔሮች መኖሪያና ዙሪያውም በሌሎች ብሔሮች የተከበበ እንደሆነ ሊሰመርበትና የሸዋ ኦሮሞ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። ሸዋ እንደሸዋ በውጡ ያሉትን ብሔሮች አካቶ እና አቅፎ እራሱን የቻለ ሆኖ እንደ ሸዋ ክልል ተከልሎ ቢንቀሳቀስ በዙሪያው ተከቦ ባሉ ሸዋ ኬኛ…..የኛ ብለው ከሚናጠቁት የጥፋት ሃይሎች ሸዋው እራሱን ከማዳን አልፎ ለኢትዮጵያ መረጋጋት ትልቁን እና ቁልፉን ድርሻ […]

በ ‘ደም የተገኘ’ ደም አፋሳሽ ህገ-መንግሥት –ታሪኩ አባዳማ

$
0
0
ታሪኩ አባዳማ ነሐሴ 2011 የሰው ዘር ዕድገት ታሪክ እንደሚያረጋግጠው የተረጋጋ ማህበራዊ ህይወት እንዲሰፍን ፣ ጉልበተኛው ደካማውን እንዳያጠቃ ፣ ወስላታ የሌላውን ንብረት እንዳይዘርፍ እንዳይመዘብር ፣ መዝጊያ ገልብጥ ከክፉ ዓመሉ እንዲታቀብ እና አጥፊ በጥፋቱ እንዲጠየቅ ፣ ብሎም የሰላም እና ዕድገት ፈር እንዲሰምር በየመስኩ ስርዓት እንዲኖር ህግ እንዲደነገግ እና መንግሥት እንዲቋቋም ግድ ሆኗል። ቅድመ ታሪክ ግኝቶች እንደሚጠቁሙት ማህበራዊ […]

ፍርድ ቤቱ በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የምርመራ መዝገብ የተጠየቀውን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ይግባኝ ውድቅ አደረገ

$
0
0
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 22፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የምርመራ መዝገብ የተጠየቀውን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ይግባኝ ውድቅ አደረገ፡፡ ፍርድ ቤቱ በትናትናው ዕለት የእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የቀዳሚው ምርመራ መዝገብ ለማየት ለዛሬ ቀጠሮ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት ሃምሌ 29 […]

የአክራሪው አይሲስ ፉከራ፣የጠ/ሚ/ር አብይ ቢሮ ዝምታ…(በታምሩ ገዳ)

$
0
0
በጎረቤት ሶማሊያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሰው አክራሪው አልሽባብ ጋር ቁርኝት እንዳለው የሚነገርለት እራሱን የእስላማዊ መንግስት (አይሲስ) ብሎ የሚጠራው አክራሪ ቡድን የጥቃት ኢላማውን ወደ ኢትዬጵያ ለማስፋፋት በቅርቡ በአማርኛ ቋንቋ ካሰረጨው የቅስቀሳ ዘመቻው ለማወቅ መቻሉ ተዘገበ። የአሜሪካ ድምጽ የሶማሌኛ ቋንቋ ክፍል ባለፈው ነሐሴ/ኦገስት 20,2019 እኤአ እንደዘገበው አይሲስ እኩይ ተግባሩን በኢትዬጵያ ውስጥ ለማሳካት ባለፈው ወር ለሶስት ደቂቃዎች የዘለቀ የቅስቀሳ ፕሮፖጋንዳ […]

የአሸንዳ በዓል የፊታችን ነሃሴ 26 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ይከበራል –በደስታ ተካ

$
0
0
ከሀገራችን በርካታ የባህል መገለጫ እሴቶች መካከል ተጠቃሽ የሆነው የአሸንዳ በዓል በሁሉም ኢትዮጵያዊያን መዲና አዲስ አበባ በልዩ ልዩ ዝግጅቶችና በድምቀትና ለማክበር የሚያስችል መርሃ-ግብር መውጣቱም የከተማ አስተዳድሩ ከንቲባ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል። በበዓሉ ላይም የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የከተማው መስተዳድር ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ የትግራይ […]

ኢታርእየኒ ሙስናሃ ለኢትዮጵያ (የኢትዮጵያን ጥፋቷን አታሳየኝ) –ከይኄይስ እውነቱ

$
0
0
የዛሬውን አስደንጋጭ ርእስ የመረጥኩት ኢትዮጵያ አገራችን የምትገኝበት አስከፊ ሁናቴ ወይም ምድር ላይ የሚታየው ጽድቅ መራር ከመሆኑ የተነሳ ባለአእምሮ እንደሆነ ሰውና እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ከማሳሰብም አልፎ ሥጋቴ ጥግ ቢደርስብኝ እኔም በርእሰ መጻሕፍቱ እንደተመዘገቡ ደጋግ ሰዎች ጩኸቴን ለሕይወት ባለቤት ባደባባይ ለማሰማት ነው፡፡ ነገረ ኢትዮጵያን በውስጥ በአፍአ፣ በቀኝ በግራ፣ በፊት በኋላ እያገላበጥኹ አቅሜ በፈቀደው መጠን ስመረምረው ቀንድና ጭራ፣ […]

የለውጡ ጎራ በግልጥ እየጠራ መጣ …የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የጫነብን የዘር ክልል አስተዳደር –አንዱዓለም ተፈራ

$
0
0
የኢትዮጵያ ፖለቲካ – ፲ ፱ ፻ ፹ ፫ እንደገና አሁን ለተዘፈቅንበት የፖለቲካ አረንቋ ምክንያቱ ነው? ወይንስ መፍትሔው? አንዱዓለም ተፈራ፣ ረቡዕ፣ መስከረም ፲ ፮ ቀን፣ ፳ ፻ ፲ ፩ ዓ. ም. (Wednesday, September 28, 2018) ሀገራችን አሁን በአስጊ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች። በዓለም ዙሪያ ተደናቂነትን ያገኘው አሁን የተጀመረው የለውጥ ሂደት፤ ከፍተኛ አደጋ አንዣቦበታል። በፖለቲካ መድረኩ ላይ እየተጫወቱ ያሉት አንዳንድ ድርጅቶች፤ […]

የዓባይ ወንዝ አወራረድና የአዴፓ አሰላለፍ –ድራንዝ ጳውሎስ (ከባህር ዳር)

$
0
0
የከፍታው ቀን ከሽፏል፤ የኩራቱ ቀንም ከወሬ አልዘለለም። መደመር ከአንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሂሳብ ስሌት ውልፍ አላለም፡፡ የለውጥ ኃይል ተብየው ለውጡን ውጤታማ የማድረግ አደራውን ከመወጣት ይልቅ እንደገና ወደ ስልጣን ሽኩቻ ውስጥ ገብቷል፡፡ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ሆነ አዲሱ የክልሉ መንግስት ለክልሉ ሕዝብ ችግሮች መፍትሔ ከማፈላለግ፣ በድርጅት ስም በውስጡ የተሰገሰጉትን የህወአት ተላላኪዎችን ከማጽዳትና ከመንቀል ይልቅ ቀን እየመረጠ የራሱን […]

ህወሃት እባቡ ቆዳውን ገፈፈ እንጂ እስከ መርዙ አልሞተም!!! –መስፍን ቁምላቸው ከስቶኮልም

$
0
0
ህወሃት በሃገራችን ላይ ያደረሰውን ለሶስት አስር ዓመታት መከራ፥ ግፍ፥በደል፥ስቃይ፥ሞት፥መሰደድ መቼም መቼም ቢሆን ታሪክ አይረሳውም “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ ይባል የለ” የህወሃት መርህ የሆነው ብሔርን ከብሄር ከፋፍለህ ግዛው የጎጠኝነትና የዘር ተኮር ፖለቲካ ቀውስ እንዲፈጠርና አሁን ላለንበት ለማንወጣው ማህበራዊ፥ ፖለቲካ፥ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ላይ ዳርጎናል ህወሃት በህዝባችን ላይ ኢ᎗ሰባዊ መብት ጥሰት አድርሷአል ፥ በነፃነት ሃሳብን የመግለጽ፥ የመረጃ ገደብ ጥሰት፥ […]

ኣዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ይፋ ከሆነ ወዲህ የጽንፈኞች ኣጀንዳ ኣማርኛን ኣንማርም የሚል ሆኖኣል –አበበ ቦጋለ

$
0
0
ህወሃት ላለፉት 20 ምናምን ኣመታት በኣገሪቱ ባሰፈነው የትምህርት ፖሊሲ ልጆች በኣፍ መፍቻ ቋንቋቸው የኣንደኛ ደረጃ ትምህርት መማራቸው ቋንቋቸውን በተወሰነ ደረጃ ማሳደጉ ኣይካድም። ልጆች በኣፍ መፍቻ ቋንቋቸው መሠረታዊውን የመጀመሪያ ደረጃ እንዲማሩ የማድረግ ዋናው ኣላማ የሚሰጣቸውን ትምህርት ያለምንም ተጨማሪ ተግዳሮት በቀላሉ ይረዳሉ ከሚል ሙያዊ ምልከታ ኣንጻር ነው። የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ይህ ኣሰራር በኣገራችን እንዲተገበር ከንጉሱ ዘመን (1955 […]

 ህይወት ለማንም አታዳላም፣እናም ዕድል ብሎ ነገር የለም –መኮንን ሻውል ወልደ ጊዮርጊስ

$
0
0
 የሰው የህይወት ጉዞ በተሰጠው መክሊትና ፣በመክሊቱ ተጠቅሞ በሚያገኘው ፋይዳ  የሚወሰን ነው።    ሰዎች እንጂ ይህቺ ዓለም ለማንም አታዳላም።  ህይወት ለማንም አታዳላም።በህይወት ሥንኖር መድሎ ፣ግፍ፣ሐጥያት ወዘተ የተሰኙ ክፋቶች በራሳችን በሰዎች ይፉጠራሉ። ራሳችንንም ይጎዳሉ።ራሳችንንም ይጠቅማሉ።      ለአንዱ ሥጋዊ ና መንፈሳዊ ደሥታን ያጎናፅፋሉ።ሌላውን መቀመቅ ያወርዳሉ።    አንዱ ፣ (ግለሰቡን ባያስገድደውም) አስቅሞ ፣አሥክሮ እንዲሁም መዘሞቻ አልጋ አዘጋጅቶ ገንዘብ […]

የአማርኛ ትምህርት በጀርመኑ ሀምቡርግ ዩንቨርሲቲ (University of Hamburg) መቶ ዓመት አስቆጠረ

$
0
0
በጀርመን ሀገር ከሚገኙ ዝነኛ ዩንቨርስቲዎች አንዱ የሆነዉ የሀምቡርግ ዩንቨርሲቲ የተመሰረተበትን መቶኛ ዓመት በማክበር ላይ ይገኛል። በዩንቨርሲቲዉ የአማርኛ ቋንቋ  ትምህርት ሲሰጥም መቶ ዓመቱን ይዟል።“አማርኛ ቋንቋ በጀርመን ዩንቨርሲቲዎች በ1919 ዓ/ም መሰጠት ይጀምር እንጅ ቀደም ሲልም ቢሆን ኢትዮጵያ ለጀርመኖች ትልቅ የምርምርና ጥናት ሀገር ሆና ነው የቆየችዉ። ኢትዮጵያ የራሳቸዉ ፅህፈት፣ ታሪክ፣ ነፃ የመንግሥት አወቃቀር፣ ጥንታዊ ስልጣኔ ካላቸዉና ነፃነታቸዉን ጠብቀዉ […]

“በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚወጣ ሌላ የህግ ማዕቀፍ ተቀባይነት አይኖረውም” አለ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ደስታ ሌደሞ

$
0
0
(SMN 24/12/2011 ዓ.ም ሀዋሳ) የዞኑ አስተዳደሪ ይህንን ያሉት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው፡፡ በመግለጫቸውም በትላንትናው ዕለት ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝብ ህዝበ ውሳኔ የሚካሄድበት ቀን በማሳወቁ መላውን የሲዳማ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡ ሀዋሳ ከተማና የሲዳማ ህዝብ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ነው ያሉት አቶ ደስታ ሌደሞ በትላንትው ዕለት ምርጫ ቦርድ እንደ ቅድመ ሁኔታ […]

 ሕዝቡ በግልጽ የሚታዬውን የሕግ ጥስትና የፍትህ ጉድለት ሊቃወመው ይገባል! –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት 

$
0
0
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት    ሓሙስ ነሃሴ ፳፫  ቀን ፪ሺህ፲፩ዓ.ም.    ቅጽ ፯ቁጥር ፲፬ በኢትዮጵያ ውስጥ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ያለ ያሚያስመስለው አይን ያወጣው የህግ ጥሰትና የፍትህ መዛባት በአፋጣኝ ካልታረመ ህዝቡበቁርጠኝነት ስርዓት አልባውን አገዛዝ መታገል ይኖርበታል። ሰላም የናፈቀውና ሰላምን የሚመኘው የኢትዮጵያ ህዝብ የአዲሱን የኢህአዴግ ሊቀመንበር የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ለጆሮ የሚጥሙ የሰላም ቃላትና የይቅርታ ተምፅኖ አምኖ በደስታ፣ በተስፋና በድጋፍ እንደተቀበለው ይታወቃል። ነገር ግን በስብሰናል፣ አጥፍተናል፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ምህረት ያድርግልን ብሎ ተለሳልሶ፣ ተረኛው ኢህአዴግ/ኦዴፓ ስልጣን ላይ ተቀመጠ። በዚህ አይነት መንገድ ይቅርታ […]

ማን ቢስምሽ ታሞጠሙጫለሽ? ፖለቲከኞችና እበላ ባይ ተከታዮች ማን መረጣችሁና ነገር የምታምሱ፤ታሪክ የምታረክሱ፤ ሕዝብ የምታናክሱ ሀገር የምታፈርሱ? ኧረ በፈጠራችሁ ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ!

$
0
0
በገ/ክርስቶስ ዓባይ ነሐሴ 24 ቀን 2011 ዓ/ም ፖለቲካ ማለት የሕዝብ አስተዳደር እንደሆነ ምሁራን ይናገራሉ። እንግዲህ ፖለቲከኛ ደግሞ ሕዝብ አስተዳዳሪ ማለት እንደሆነ አድርገን ልንወስደው እንችላለን። ፖለቲከኞች የሚለውን ቃል ስንጠቀም ደግሞ ሕዝብ አስተዳዳሪዎች ማለት እንደሆነ እንገነዘባለን። ነገር ግን እነዚህ ፖለቲከኞች ‘ከየትኛው ዩኒቨርሲቲ ወይም ልዩ የማሠልጠኛ ተቋም ተመርቀው ነው እንዲህ ያለውን የመጠሪያ ማዕረግ ያገኙት?’ ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ […]

ኢትዬጵያኖች አዲሱ አመትን በጸሎት እንዲቀበሉ ተጠየቀ (በታምሩ ገዳ)

$
0
0
ኢትዬጵያኖች መጪው አዲሱ የ ዘመን መለወጫ በዓል ዋዜማን እንደ እየ እምነታቸው ሰለአገራቸው እና ስለሕዝባቸው ከልብ በመነጨ ብሔራዊ የጸሎት ቀን እንዲይደርጉበት ጥሪ ቀረበ። የኢትዬጵያ የሀይማኖትተቋማት ካውንስል( Inter-Religous Council of Ethiopia , IRCE)ተብሎ የሚታወቀው ጉባኤ በሳምንቱ ማብቂያ አርብ እለት የጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫን የጠቀሰው መንግስታዊው የመረጃ ተቋም ፣ኤዜአ እንደገለጸው ከሆነ በአገሪቱ ውስጥ የተከሰተውን ብሔር ተኮር ግጭቴችን እና ያስከተለው […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዓለም አቀፉ የምስራቅ ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ጉባኤ መስራችና ቋሚ አባል በመሆኗ ህልወናዋ የሚገለጠው በአንድ ወጥ ሲኖዶስ መዋቅርና ስር አት ነው

$
0
0
ለማናቸውም የተያያዘውን በጥሞና በትህትና ብታነቡት ትንሽ ፍንጭ ሊስጥ ይችላል። ሌሎችም ሰነዶች አሉ። አሁን የምንሰማው በቋንቋ ላይ ተመስርቶ ሲኖዶሱን አፈንግጦ መውጣት ምርጫም ቢሆን አንጃነትና እምነትን መክዳትም ጭምር ይሆናል የሚል አስተሳሰብ አለኝ። የእውነተኛ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ያለውም ይህን ከቶ አያልመውም። ጉዳዩ ፖለቲካዊና የ፷ አመቱ የጥላቻ ትግል አካል ነው። ” ጊዜ የሰጠው ቅል ፤ ድንጋይ ይሰብራል ” ይባላል። […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live