Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኢትዮጵያና አሜሪካ የሕግ ማስከበር እና የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ስምምነት ተፈራረሙ

$
0
0
የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሀት ካሚልና የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክል ሬይኖር ዛሬ መንግሥቶቻቸውን ወክለው የሕግ ማስከበር እና የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱም ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና ለፌደራል ፖሊስ እንዲሁም ለፍትህና ሕግ ማስከበር አካላት ድጋፍ በመስጠት የሕግ ማስፈጸም እና የፍትሕ ዘርፉን ለማሻሻል ያለመ ነው ሲል የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል ። FBC

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የብሔራዊ ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ማጠናቀቂያ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0
የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል በአፈና አይገታም ! የህዝባችን ሁለንተናዊ ትግል አምጦ የወለደው አብን የአማራ ህዝብ መሰረታዊ የኅልዉና፣ የፍትኅና የእኩልነት ጥያቄዎችን በመለየትና አማራዉን በማደራጀት የተጋረጠበትን የኅልውና አደጋ በመቀልበስ ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በእኩልነትና በፍትኃዊነት የሚኖርባትን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ በሰላማዊ መንገድ እየተንቅሳቀሰ ያለ ድርጅት ነዉ፡፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ብሔራዊ ምክር ቤት ከነሃሴ 11-12/2011 ዓ.ም […]

ብራንድ የሚሰርቁ በሞት ቢቀጡስ? –በስንታየሁ ግርማ

$
0
0
በሙስና እና በመግደል መካከል ያለዉ ልዩነት ኢምንት ስለመሆኑ የሚናገሩ የኢኮኖሚ ምሁራን ቁጥራቸው ቀላል አይደለም የተደራጀ ሙስናና የሠብአዊ መብቶች ጥሰት እ.አ.አ. በ2ዐ15 በኢትዮጵያ የደረሰውን ቀውስ አስከትሏል /ክሪያ 2ዐ19/ ክሪያ አክላም ሙስና በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ገፅታ ተላብሶ የተንሠራፋ እንደሆነ ትገልፃለች፡፡ ኪራይ ሠብሣቢነት እና የመንግሥት ሥልጣን መፈናጠጥ ዋና መገለጫዎቹ እንደሆኑ ክሪያ በፅሁፏ አስቀምጣለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም […]

ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታውን ለማድረግ ዳሬ ሰላም ገብቷል

$
0
0
ቡድኑ ዳሬ ሰላም ሲደርስ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ እና ሌሎች አካላት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ በመሆን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው ፋሲል ከነማ የመጀመሪያውን የማጣሪያ ጨዋታ በባህርዳር አለማቀፍ ስታዲየም አዛምን 1ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡ ነሃሴ 18 የመልሱ ጨዋታ ዳሬ ሰላም ላይ ከአዛም ጋር የሚያደርገው ፋሲል ከነማ ለጨዋታው በአዲስ አበባና ባህርዳር ልምምድ ሲያደርግ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለአሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

$
0
0
እንኳን ለአሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በሀገራችን ሴቶችን ወደ አደባባይ እንዲወጡ አስተዋጽዖ ሲያደርጉ ከኖሩት በዓሎቻችን መካከል አንዱ አሸንዳ/ ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል በዓል ነው። በዚህ ምድር አረንጓዴ በለበሰችበት በክረምቱ ወቅት በነሐሴ ወር አጋማሽ በትግራይና በአማራ ክልሎች በሚከበረው በዚህ በዓል ወጣት ሴቶች ልዩ የሆነ የሀገር ልብሳቸውን ለብሰውና ከወገባቸው ላይ እርጥብ ሰሌን በአንቀልባ መልክ አሥረው እያዜሙ ይወጣሉ። አደባባዮቻችን በአብዛኛው በወንዶች ብቻ […]

”በአንድ ስም ሁለት የፓለቲካ ፓርቲዎችን መመዝገብ አንችልም ”የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ

$
0
0
አማራ ሚዲያ ማዕከል /አሚማ / ነሐሴ 15 ቀን 2011 ዓም አዲስ አበባ ሸዋ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ እና በአባ ነጋ ጃራ የሚመራው ኦነግ ቀደም ሲል ተዋህደው አንድ እንደሚሆኑ ያስታወቁ ቢሆንም በቅርቡ ግን ሁለቱም በኦነግ ስም ከምርጫ ቦርድ እውቅና ለማግኘት የምዝገባ ሂደት መጀመራቸው ተሰምቷል። ጉዳዩን በማስመልከት የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ […]

ኢትዮጵያኒዝም (Utopia ምድረ ገነት) የእኛ ፍትሀዊ መንግሥት –በገ/ክርስቶስ ዓባይ        

$
0
0
በገ/ክርስቶስ ዓባይ ነሐሴ 15 ቀን 2011ዓ/ም ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ማርክሲዝም ሌኒኒዝምም፤ ሊበራሊዝም ሆነ ኒዖሊበራሊዝም የአስተዳደር ፖሊሲ አይደለም። ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ኢትዮጵያኒዝም ወይም ዩቶጵያ በመባል የሚታወቀው አሁን ምዕራባዊያን እንደሚሉት ተምኔታዊ (እውን የማይሆን) ሳይሆን ጥንት ተግባራዊ የነበረ፤ አሁንም ቢሆን ቁርጠኝነት ያለው መሪ ካለ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል፤ ፍትሀዊ የአስተዳደር ዘይቤ ነው፤ (ሊበራሊዝምና የኒዖ ሊበራሊዝምን አስተሳሰብ በተመለከተ ወደፊት በዝርዝር እንመለስበታለን)። ምክንያቱም […]

ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተመረጡ 13 የርብርብ መስኮች በትኩረት ይሰራል –ትምህርት ሚኒስቴር

$
0
0
 በትምህርትና ስልጠናው ፍኖተ ካርታ ከተቀመጡት 37 የመፍትሄ አቅጣጫዎች መካከል ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተመረጡት 13 የርብርብ መስኮች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ መንግስት በመልካም እሴት፣ ስነ ምግባርና በብቃት የታነጸ ዜጋን ለማፍራት እንደሚሰራ ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈም የትምህርት ስርዓቱ የሃገሪቱን አንድነት የሚያስቀጥል፣ ከማህበረሰቡና ከተማሪው ጋር […]

በኢትዮጵያ ከለውጥ ሃይሉ በበለጠ የለውጥ አደናቃፊ እየሆነ ያለው የልሂቃን ያልተገባ መቆራቆስ ነው! –አበጋዝ ወንድሙ

$
0
0
ዶክተር መረራ ጉዲና ብዙ ጊዜ  የአማራ ፣ የኦሮሞና የትግራይ ልሂቃን የሚጋጩ ህልሞቻቸውን  ተወያይተው ካላስታረቁ መዘዙ ሃገር ሊበትን ይችላል የሚል ፍራቻ እንዳለው ይገልጻል። መረራ ለምን እነዚህን ሶስት የብሄረሰብ ልሂቆች ብቻ እንደመረጠ ሙሉ በሙሉ ባልረዳም ፣ የነዚህ ሶስት ብሄረሰቦችን  እንወክላለን የሚሉ ልሂቆች የርስ- በርስ  መቆራቆስ ግን፣ ሃገር ሊበትን ወይንም ሊያጠፋ ወደሚችል ጎዳና ሊውስድ እንደሚችል ያለፈው ዓመት በሀገራችን […]

ስለ ቋንቋ ጉዳይ ልብ ሊባሉ የሚገቡ አራት ነጥቦች

$
0
0
አዲስ ኤክስኘረስ ሚዲያ ነሐሴ 16 ቀን 2011 ዓም ፩) ኦሮምኛ የፌደራል የሥራ ቋንቋ ከመሆኑ በፊት አማርኛ “ኦሮሚያ” የሚባለው ክልል ሁለተኛ የሥራ ቋንቋ መሆን ይኖርበታል። ፪) አማርኛ የፌዴራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ የሆነው በአማራ ህዝብ ሰልፍና ፉከራ ሳይሆን በሁሉም ህዝቦች ሎጂካዊ ቅቡልነት ነው። በመሆኑም ኦሮምኛ የፌዴራሉ መንግሥት ተጨማሪ ቋንቋ ለመሆን ቢያንስ ኢትዮጵያዊያን በደንብ ሊያነቡት በሚችሉት የኢትዮጵያ ፊደል […]

የጋምቤላ ባለስልጣናት በጦር መሳሪያ ንግድ ተጠምደዋል (በታምሩ ገዳ-ሕብር ሬዲዮ)

$
0
0
ጋምቤላ ክልላዊ መስተዳደር ውስጥ አንዳንድ ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣናት ሳይቀር ያካተተ የህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ንግድ እና የሙስና ተግባራት በስፋት እየተካሔደ መሆኑን አንድ የጎረቤት ደ/ሱዳን ባለሰጣን ተናገሩ። የደ/ሱዳን የዜና ምንጭ የሆነው(SSNA)ዛሬ አርብ አንድ ማንነታቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ከፍተኛ የአገሪቱ ባለ ስልጣንን በመጥቀስ እንደዘገበው “በጋምቤላ ውስጥ የሚገኙ እንዳንድ ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣናት የደቡብ ሱዳን ጉዳይ አስፈጻሚዎች በመሆን ቋሚ ደሞዝ ተከፋዬች […]

መተማ የተያዙት ጭነቶች ሕጋዊ ናቸው ተባለ

$
0
0
የመተማ ዮሃንስ አካባቢ የመከላከያ አዣዥ ሳያውቅ ጥይት ጭነው ወደ ሱዳን ሊሻገሩ የነበሩና “የሠራዊቱ ንብረት ናቸው” የተባሉ አምስት የጭነት ተሽከርካሪዎች በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የተመረቱና በሕጋዊ ሰነድ የተሸጡ መሆናቸውን የኮርፖሬሽኑ ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል አሕመድ ሐምዛ ገለፁ። ዋሽንግተን ዲሲ — የምዕራብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ሰላምና ደህነንት ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በበኩላቸው፤ ጭነቶቹን ከፀጥታ […]

የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ የመገንጠል ስነልቦናዊ ፍላጎት ፈፅሞ የለውም –ልኡል  ገብረመድህን

$
0
0
ልኡል  ገብረመድህን (ከአሜሪካ ) 8.20.2019 ሕ.ወ.ሓ.ት የትግራይ ህዝብ ልዕልና ሆነ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ የሚያሳስብ የፖለቲካ ድርጅት አይደለም ። የፖለቲካ አመራሩም ቢሆን በዝምድና ጋብቻና የተሳስረ ነው ። የፖለቲካ ስልጣን ሆነ የኢኮኖሚ ስርአቱ የሚመራው በአንድ የቤተሰበ አምድ እና ታማኝ ታዛዦች አማካይነት ሲሆን ሌላው ገና  የአለም የፖለቲካ ፍልስፍና  በአግባቡ ያልተረዳ ጥቅም ፈላጊና ህዝብ ጨቃኝ የፖለቲካ ካድሬ የሰፈረበት አምባገነን ድርጅት […]

ለኢትዮጵያ መንግስትና ፓርላማ ፣ ግልጽ ደብዳቤ ( በደብሩ ነጋሽ)

$
0
0
ተማሪዎችን አማርኛን ከመማር ማገድ፣ ክትባትን ከመንሳት፣ ያነሰ ወንጀል አደለም የኢትዮጵያ የትምርት ሚኒስቴር ፣ ለ28 አመታት በኢትዮጵያውያን፣ በተለይ በኦሮሞው ወጣት ላይ ሆን ተብሎ የተፈጸመ በደል ለመቀልበስ፣ አማርኛን እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ እንዲማሩ በመርሃ-ግብሩ ፣ ቀርጾ ማውጣቱ፣ ይበል የሚያሰኝ ነው። ካንድ ትውልድ ለበለጠ ግዜ፣ የኢትዮጵያውያንን ስብዐዊ  መብት በመንፈግ፣ በሚሊዎኖች የሚቆጠሩን ዜጎች፣ በተለይ ኦሮሞውን፣ ሆን ተብሎ አማርኛ እንድይማሩ […]

የሰሞኑ ቋንቋን ተከትሎ የተከፈተው ዘመቻ –ህብር ራዲኦ

$
0
0
የሰሞኑ ቋንቋን ተከትሎ የተከፈተው ዘመቻ የራሱን የኦሮሞን ቋንቋ ተናጋሪውን ጭምር ተቃውሞ እየገጠመው ነው።የተቃውሞው ጠሪዎች የፖለቲካ ንግድ ያደረጉት መጫወቻ በሀሰት በአፍ መፍቻ እንዳንማር ሊደረግ ነው በሚል ፈጠራ ወጣቱን ለማሳሳት ዘመቻ ከፍተው አልሰራም።አዲሱ ፖሊሲ በአፍ መፍቻ አትሟሩ አላለም።በፌደራሉ የሥራ ቋንቋ እንደ አንድ ትምህርት መሰጠቱ አትራፊ እንጂ አክሳሪ አለመሆኑን በአደባባይ መናገር የጀመሩ አሉ። ተከታዩን ጽሑፍ ሲያነቡ ብዙ ቁምነገር […]

ቱስክ በለስ ተቀናት እንትን ነኝ ማለቷ እማይቀር ነው! –በላይነህ አባተ

$
0
0
በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) የነሐሴ ሰማይ እንደ አሮጌ ሰፌድ ተነድሎ ዝናብ እንደ ፏፏቴ እየወረደ ጎርፍ በሚጥለቀለቅበት ሌሊት የሽንት ፊኛ  “ቀ…ቀቀቀ…” ብሎ እንደሚተረተር መርጠጣም ሱሪ ተወጥሮ ሊፈነዳ ደረሰ፡፡ የተወጠረው ፊኛም ጪነቱን ለማራገፍ  አንጎልን እንደ አሳብ- የለሽ ወደል ጧ ብሎ ተተኛበት እንቅልፉ ቀሰቀሰው፡፡ ተእንቅልፉ የተወገሰው አንጎል በስጨት ብሎ “አንተ  ከረጢት!  በዚህ የደረቀ ሌሊት ለምን እንደ ላሊበላ ቀሰቀስከኝ?” ብሎ […]

ዘረኝነት ትልቁ ዕብደት – (ከሰሞኑ አንኳር አሣዛኝ ክስተቶች ጥቂቶቹ) –ምሕረት ዘገዬ

$
0
0
ምሕረት ዘገዬ (mz23602@gmail.com) ብዙ የዕብደት ዓይነቶች አሉ፡፡ ከያዙ የማይለቁ፣ ከሰው ወደ ሰው ወይም ከእንስሳ ወደ እንስሳ የሚተላለፉ፣ ልብስ እያስወለቁ መለመላን የሚያስኬዱ፣ ጥሩ ልብሶችን እያስለበሱ አእምሮን ግን የሚያስቱ፣… የዕብደት ዓይነቶች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ ከሁሉም ዕብደቶች በክፉነቱና ሳይገድል እንደማይለቅ በህክምና ታሪክ የተዘገበው ግን የውሻ ዕብደት ነው፡፡ የውሻን ዕብደት መቶ ፐርሰንት ዕብደት ይሉታል የተማሩቱ፡፡ በዘመናችን ግን ያን የውሻ ዕብደት […]

ጥንታዊ የኦሮሞ ነገዶችና የገዳ ስርዓት፣ (ከ ደረጀ ተፈራ)

$
0
0
እንደሚታወቀው በጥንት ጊዜ የነበሩ በርካታ  ፀሃፍትና የታሪክ ተመራማሪዎች ኢትዮጵያን ከአባይ (ግዮን) ወንዝ፣ ከቀይ ባህር እና ከህንድ  ውቅያኖስ ጋር በማዛመድ የምትገኝበትን ቦታና  የህዝቧን አሰፋፈር በተመለከተ ፅፈዋል። ለምሳሌ ከክርስቶስ ልደት በፊት 8ኛው ክ/ዘ እና በ4ኛው ክ/ዘ ይኖሩ የነበሩ ሆሜር  እና ሄሮዱተስ የተባሉ የግሪክ ፀሃፍት በየዘመናቸው ፅፈው ባስቀመጡት ማስታወሻ ኢትዮጵያ ከግብፅ በስተ ደቡብ የምትገኝና የግዛት ክልሏም በአንድ በኩል ቀይ ባህር፣ በሌላ በኩል ደግሞ የህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ እንደሚደርስ ገልፀዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በ12ኛው ክ/ዘ ጥንታዊ የኦሮሞ አርብቶ አደር ነገዶች (Primitive Oromo pastoral tribes) አሁን ደቡብ ሶማሌና ሰሜን ኬንያ ተብሎ […]

ምርጫ ወይስ ተቋም ግንባታ . . . . . . የቱ ይቀድማል? –ኤፍሬም ማዴቦ

$
0
0
የጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ መንግስት አገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ጋብዞ የአገራችንን ችግሮች አብረን እንፍታ የሚል ጥያቄ ካቀረበ በኋላ በነበሩት 16 ወራት ኢትዮጵያ ዉስጥ በአዳራሾች፥ በማህበራዊ ሜዲያ፥ በቴሌቭዥንና እንዲሁም በፖለቲካ ፓርቲዎችና በምርጫ ቦርድ መካከል በተደረጉ ዉይይቶች ዉስጥ ጉልህ ቦታ ከነበራቸዉ የዉይይት አርዕስቶች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ የ2012ቱ ምርጫ ይራዘም ወይስ አይራዘም የሚለዉ ጥያቄ ነበር። […]

የጃዋርን ሀሳብ ስቀሉት! –የቦረናው ሙክታር አደም ለኦሮሞ ጽንፈኞች ይናገራል

$
0
0
(ሙክታሮቪች ኦስማኖቭ) የኦሮሞ ወጣቶች ሆይ ጃዋርን ስቀሉት። አዎ! እሱን ትታችሁ፣ ሀሳብና የገነባውን ተክለስብዕና ስቀሉት። ሀሳቡን ስቀሉት! ይህን ለምን እንደምል በጥሞና አድምጡኝ። ***** የጃዋር መንገድ የጤነኛ ፖለቲካ መንገድ አይደለም። የፖለቲካን መካረር ጉዳይ በቋንቋ ጭንብል ማቅረብ ስህተት ነው። የፖለቲካ ጉዳይ በፖለቲካ መንገድ፣ ሰጥቶ በመቀበል፣ በመደማመጥ እና የጥቅም ግጭትን ወግ ባለው፣ ስርአት በተበጀተለት፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ “እነሱ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live