Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በአዲስ አበባ በድጋሚ በለገዳዲ የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ መሆኑ ተገለጸ

$
0
0
ለገዳዲ 44 ማዞሪያ አከባቢ ነዋሪዎችን ከቤታቸው በማስወጣት መኖሪያ ቤቶችን እያፈረሱመሆኑን በቦታው የሚገኙ ሰዎች መግለጻቸውን ስዩም ተሾመ ዘግቧል። የፀጥታ ሃይሎች በአከባቢው ተገኝተው መኖሪያ ቤቶቹን በማፍረሱ ሂደት ተባባሪ መሆናቸውን ለማወቅ መቻሉን የገለጸው ይሄ ዘገባ አምና በተመሳሳይ ወቅት ቤት መፍረሱን አስታውሷል። ” ዘወትር ክረምት በመጣ ቁጥር የነዋሪዎችን ቤት የማፍረስ ሰይጣናዊ ድርጊት መቼ እንደሚለቀን አላውቅም። የሚመለከታቸው አካላት ይህን ጉዳይ በአስቸኳይ ሊያስቆሙ […]

አሻጋሪውንም የሚያሻግር ብሔራዊ ሸንጎ ይቋቋም!! –ያሬድ ኃይለማርያም

$
0
0
የአብይ አስተዳደር ቀደም ሲል ቲም ለማ እያልን የምንጠራው እና ለውጡን በአሻጋሪነት እየመራ ያለው ቡድን በጊዜ ክርኑ የዛለ መሆኑን በርካታ ማሳያዎችን እያጣቀስኩ ቀደም ሲል በጻፍኳቸው ዳሰሳዎች ለማሳየት ሞክሬያለሁ። በመጀመሪያ ባሳለፍነው አመት ከመንፈቅ ጊዜ ውስጥ አገሪቱ እጅግ በርካታ እና የከፉ አደጋዎችን ብታስተናግድም የዛኑ ያህል በርካታ መልካም ነገሮች መከናወናቸውን አስምሮ ማለፍ ተገቢ ነው። የለውጥ ማዕበል ከግራ ቀኝ የሚያላጋው […]

“በሀሳቡ የማያሸነፍ በጠመንጃ ይመካል”መ/ ሐዲስ እሸቱ (በታምሩ ገዳ /ህብር ራዲዬ)

$
0
0
በሀሳብ የበላይነት የማያምኑ ሰዎች ሽንፈታቸውን የሚገልጹት በመሣሪያ እና በጉልበት ብቻ እንደሆነ፣ወጣቱ ትውልድም የማንም ፖለቲካ ሀይል መጠቀሚያ ሳይሆን ፣ይልቁንም ለሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አስተሳሰብ ይዞ መጓዝ አለበት ሲሉ አንድ ታዋቂ የሐይማኖት መምህር ገሰጹ። በሐይማኖታዊ አስተምሮታቸው እና በምክሮቻቸው በበርካታ ኢትዬጵያኖች ዘንድ በተለይ ደግሞ በማህበራዊ መገናኛዎች አማካኝነት በስፋት የሚታወቁት በ ኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን(ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን )ውስጥ የሐዲስ ኪዳን […]

በአዲስ አበባ ከተማ  የማንነት ጥያቄ ላይ የኢትዮጵያ ክፍላተሃገር ህብረት ያለው አቋም

$
0
0
ነሓሴ 9 ቀን 2011 ዓም(15-08-2019) አዲስ አበባ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያም አዲስ አበባ ነች! ማንኛውም በመንግሥታዊ ስርዓት የሚመራ አገር ሥርዓተ መንግሥቱን በአንድ አካባቢ በቆረቆረው ከተማ  መዘርጋቱ እንግዳ አይደለም።መንግሥት ወይም  ስርዓት ያለመንበር ወይም ያለከተማ ሊመሰረት አይችልም።የሁሉም አገር ስርዓትና የከተማ አመሰራረት ታሪክ ጊዜና ቦታው ቢለያይም ተመሳሳይ ነው። ኢትዮጵያ መንግሥታዊ ስርዓት መስርታ እንደ አገር ከተዋቀረችበትና በተጓዘችበት ታሪኳ ሁኔታው ባስገደደውና በፈቀደው […]

የሕገ መንግሥት ለውጥ –ለኢትዮጵያዊነት የሚያስፈልግ መሠረታዊ ጉዳይ  –ኪዳኔ ዓለማየሁ

$
0
0
ራዕይ፤ ዓላማና እቅድ፤ ለኢትዮጵያ ተገቢ የሆነ ሕገ መንግሥት ማዘጋጀቱና ተግባራዊ የማድረጉ ራዕይ ውድ ሐገራችን ከጽንፈኛነት፤ ከዘረኛነትና ከጭቆና የተላቀቀ ኢትዮጵያዊነት፤ ሰላም፤ ጸጥታ፤ አንድነት፤ እውነተኛ ዲሞክራሲ፤ ሕብረት፤ መከባበር፤ ፈጣን ልማት፤ ወዘተ. የሰፈነባት ሐገር እንድትሆን ለማረጋገጥ ነው። ይህ ራዕይ ስኬታማ እንዲሆን፤ በአጭር ጊዜ (1 ዓመት) ብቁ በሆኑ ባለሞያዎች የተሟላ ረቂቅ ሕገ መንግሥት እንዲዘጋጅና በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ዓለም አቀፍ […]

የዓለም ባንክና ዓለም አቀፍ የገንዘብ አቅርቦት ተቋም በታዳጊ አገሮች ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ –በገ/ክርስቶስ ዓባይ  

$
0
0
በገ/ክርስቶስ ዓባይ                                                  ነ ሐሴ 5 ቀን 2019 ዓ/ም ስለ ዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ አቅርቦት ተቋም ከአሁን ቀደም “ትንቢት ይፈጸም ዘንድ የግድ ነው፤ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” በሚለው ጽሑፌ በይበልጥ ለማብራራት ቃል በገባሁት መሠረት ‘የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ’ እንዲሉ ይኸው ተከስቻለሁ። እነዚህ ሁለት ተቋማት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ሲሆኑ በይበልጥ ጠንክረው የሚሠሩት የአሜሪካንን ፖሊሲና […]

በሰይጣን ግዛትም ሥላሤዎች አሉ –እንተዋወቃቸው –ወልደ ማርያም ዘገዬ

$
0
0
በፈረንጅኛው Trinity ባማርኛው ሥላሤ አብን (the Father)፣ ወልድንና (the Son) መንፈስ ቅዱስን (the Holy Spirit) ይይዛል፡፡ በምሥጢረ ሥላሤ ትምህርት ሥላሤዎች አንድም ሦስትም ናቸው፡፡ አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ በሚል አገባብ ይታወቃሉ፡፡ ይህ እንግዲህ በሥነ መለኮት ወይም ቴዎሎጂ ሃይማኖታዊ የዕውቀት ዘርፍ የሚተነተን ነው፡፡ እስካሁን ባለው የሥነ መለኮት ትምህርት ፀላዔ-ሠናያት የሆነው ሣጥናኤል እምቅድመ ፍጥረተ አዳም […]

ከመንግሥት ውጭ ያሉ ተዋናዮች (Non state Actors) ሚና  ከወቅቱ የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁ

$
0
0
አንድነት ይበልጣል – ሐዋሳ ነሐሴ 2011 የአንዳንድ ታዋቂ ዜጎችና ተቋማት የበሰለ ወቅታዊ እንቅስቃሴ፣ በገዛ-ራሳቸው የትግልና የመስዋዕትነት ፍሬ ላይ ሳያውቁት ሻጥር ለሚፈጽሙ አንዳንድ “የቀድሞ ታጋዮች” ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው፡፡ አንድ የለውጥ ኃይል፣ ለውጥ ለማምጣት ብዙ መስዋዕትነት ከከፈለ በኋላ የትግሉ ፍሬ መታየት ሲጀምር፣ ለውጡ ወደኋላ እንዳይመለስ፣ መሥመር እንዳይስት፣ ቀሪ ነገሮች እንዲሟሉና ዳር እንዲደርስ ወጥሮ መሥራትና መቀጠል ይገባዋል፡፡ […]

ማንነቱን የማያውቅ የሌላውን ማንነት ሊያውቅ አይችልም፤የወሎ ማንነት ኢትዮጵያዊነት ነው! –ወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር

$
0
0
ከወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር የተሰጠ መግለጫ ነሃሴ 11 ቀን 2011 ዓም(16-08-2019) ወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር ከተመሠረተበት እለት አንስቶ ስለወሎ ክፍለሃገር ታሪክ፣ መልክአምድራዊ አቀማመጥ፣የተፈጥሮ ችሮታ(ሃብት)፣በኤኮኖሚያዊ ዘርፍና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም የሕዝቡን በኢትዮጵያዊነት ላይ ያረፈ ፣ የተለያዩ ጎሳዎችን አቅፎ በተውጣጣ ባህልና እምነት የዳበረ ማንነት ባለቤት መሆኑን ለመተንተን ሞክሯል። ይህንን የአንድነት ምሳሌና ናሙና የሆነ የሚያኮራ ክፍለሃገር ከሃያ […]

ፈርተን ዝም አንልም …ገሃነምባይቀዘቅዝም!   ተፃፉ በመኮንን ሻውል ወልደ ጊዮርጊስ

$
0
0
 ነሐሴ 12 ቀን 2011 _ ዓ/ም እንናገራለን “በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ” ብንባልም፤ ፈርተን  ዝም አንልም ገሃነም ባይቀዘቅዝም ። አፋችንን አንዘጋም  “ገሃነም እሥቲ ይቀዝቅዝ”  ብለን እንቀልጣለን እንጂ እቶኑ ውሥጥ ገብተን መብራታችን አይቀርምና ሻማ ሆነን። ………………………………….. ደሃን አሥጨናቂ ጭቃ ሹም ምሥለኔ በዝቶ በየቀበሌው እየሰለቀጠ የአዞ እንባ የሚያነባ ፣በዝቶ  ፎጋሪው። እያየን ዝም አንልም ገሃነም ባይቀዘቅዝሞ። መለስ መለሰ እያለ ሲጮኽ […]

በአፋር ዳሎል የጠፋቸው እስራኤላዊት ተማሪ ህይወቷ አልፎ ተገኘች

$
0
0
በአፋር ክልል ዳሎል አካባቢ ለጉብኝት ከሄዱ እስራኤላውያን ተማሪዎች መካከል ተነጥላ ጠፍታ የነበረችው እስራኤላዊት ወጣት ዛሬ ጠዋት ሞታ ተገኘች። አያ ናማና የተሰኘችው ወጣት አስክሬን ዛሬ ከሰዓት ወደ አምቡላንስ መወሰዱን አንድ የአፋር ክልል ባለስልጣን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በአፋር ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ዘርፍ የቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ አህመድ አብዱልቃድር እስራኤላዊቷ መጥፋቷ ከታወቀበት ከትላንት ጀምሮ […]

ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ

$
0
0
የኢትዮጵያዊነት ኢንስቲትዩት እና ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ ከሥነ-ዜጋ ትምህርትና ኢትዮጵያዊ ሥነ-ምግባር የታሪክን እውነተኛ ምንጮች እስከመፈተሽ፣ የሃሰት ትረካዎችን እስከማጋለጥና ማስተካከል፣ በኢትዮጵያዊያን መካከል መግባባትና በሃገራዊ ፍቅርና ክብር መተሣሰርን እስከ ማፅናት የሚደርስ ሥራ እንደሚያከናውኑ የድርጅቱና የተቋሙ መሥራቾችና መሪዎች ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል። ዋሺንግተን፣ ዲ.ሲ. —  ኢትዮጵያዊነት – የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ “የሃገሩን ታሪክና የአብሮነት እሴቶች […]

የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ የብድር ዕዳ 1.5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል

$
0
0
ዮሐንስ አንበርብር እስከ መጋቢት 2011 ዓ.ም. ድረስ ያለው የአገሪቱ አጠቃላይ የውጭና የአገር ውስጥ ብድሮች ዕዳ 1.5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮ ቴሌኮም የውጭ ብድር ዕዳ 111.9 ቢሊዮን ብር ነው የሌሎቹ የልማት ድርጅቶች የውጭና የአገር ውስጥ አጠቃላይ የብድር ዕዳ 594 ቢሊዮን ብር ደርሷል ማዕከላዊ መንግሥትና የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልመለሱት ዕዳ 412.5 […]

የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ዑመር ዐል ባሽር ፍ/ቤት ቀረቡ

$
0
0
የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ዑመር ዐል ባሽር የተመሰረተባቸው የሙስና ክስ ሂድት እንዲጀመር ዛሬ በካርቱም ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ዋሺንግተን ዲሲ — ለሰላስ ዓመታት ያህል ሥልጣን ላይ ከቆዩ በኋላ ባለፈው ሚያዝያ ወር ከሥልጣን የተወገዱት ባሽር ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ የውጭ ምንዛሬ ተገኝቶባቸዋል። ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሥጦታዎችን ተቀብለዋል የሚል ክስ ነው የተመሰረተባቸው። አንድ መርማሪ ፖሊስ በፍርድ ቤቱ ቃላቸውን በሰጡት መሰረት ከሳውዲ […]

የአማራ ማህበር በዳላስ የተሳካ ስብሰባ አካሄደ

$
0
0
ትላንት እሁድ August 18, 2019, ዓ ም የተሳካ ስብሰባ አካሄደ፦ በዚህ ስብሰባ ዶክተር ስሜነህ ማዘንጊያ እና ልጅ ተድላ መላኩ ተጋባዥ እንግዳ ሆነው የተገኙ ሲሆን በአማራ ወቅታዊ ሁኔታና በቀጣይ መሰራት ስላለባቸው ጉዳዮች ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። የስብሰባው ዋና ዓላማ አማራ ሕዝብ በተጋረጠበት የህልውና አደጋና ፈታኝ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመወያየትና፥ የመከራ ገፈት ቀማሽ የሆነው ሕዝባችን መብትና […]

ግምታዊ ዋጋው ከ 14 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ወረቅ እና የዉጪ አገር ገንዘብ በቁጥጥር ስር ዋለ

$
0
0
የጉምሩክ ኮሚሽን ግምታዊ ዋጋው 14 ሚሊየን ብር የሚገመት ወርቅ የዉጪ አገር ገንዘብ ህገወጥ በሆነ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙን አስታወቀ፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ከደቂቃዎች በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት ህገወጥ ወርቁ ሲጓጓዝ የነበረው መነሻውን አዲስ አበባ ባደረገ ያሪስ መኪና ሲሆን የሰሌዳ ቁጥሩም ኮድ 2 A 08104 አ.አ ነው፡፡ የወርቁ አጠቃላይ ክብደትም 8.7 […]

የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

$
0
0
የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኙበት እየተከበረ ነው። በበዓሉ ላይ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ተገኝተዋል፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም ቡሄ በየዓመቱ በዛሬዋ ቀን የሚከበር በዓል ነው። በዓሉ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ዓቢይ በዓላት አንዱ ሲሆን አከባበሩም በበርካታ ባህላዊ ቁሶችና የምግብ አይነቶች የሚታጀብ […]

ፌደራሊዝም እነርሱ ሲሉን እኛ ፌደራሊስም ስንል እና የአፓርታይድ ስርአት –መንግስቱ ሙሴ

$
0
0
የዛሬ 69 አመት ህወሓት እና ኦነግ ከመፈጠራቸው 17 አመታት ቀደም ብሎ የደቡብ አፍሪካ የትቂት ነጮች አፓርታይድ መንግስት ለደቡብ አፍሪካ እና ለደቡብ ምእራብ አፍሪካ ሕዝቦች የራሳቸው ፌደራሊዝም ሰጥተው ነበር። የአፓርታይድ ነጮች የመሰረቱት ፌደራላዊነት ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለው አይነት የሚመሳሰል ፌደራላዊነት ነበር። የአፓርታይድ ነጮች 10 Ethno-linguistic (የዘር እና ቋንቋ) ተመሳሳይነት ለአላቸው የደቡብ አፍሪካ ጎሳወች Bantu homeland በሚል […]

ናጫቃማ  –በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

$
0
0
አጭር ልብ ወለድ     የናዝሬት ጫት ቃሚዎች ማህበርን ለመመስረት ከሁሉም ቀበሌዎች ፣ በአቃቃማቸው አግባብ የተመረጡ፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ጫት ቃሚዎች ግር ብለው ወደ “በለጬ”አዳራሽ እየገቡ ነው።    በአብረቅራቂ ወዛም ፊት- በደማቅ፣ፈገግታ -በልዩ አቅል ና ምድራዊ ባልሆነ ስሜት ተሞልተው ።ዐይኖቻቸውን እያጉረጠረጡ – እጆቻቸውን እንደክንፍ እያርገበገቡ –  ሰውነታቸውን እስክስታ እንደሚወርድ እያውረገረጉ- አንዳንዶችም ምድርን ለቀው -በሰማይ ለመብረር […]

የምንጠብቀው ሌላ፥ የሚሆነው ሌላ –ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

$
0
0
ስለ ኢትዮጵያ በፍቅር ተነድፈን የምንጠብቀው አንድም ትንሳሄ (ተስፋ) ወይም መበታተን (ስጋት) ነው።  ግን ሁለቱም እየሆነ አይደለም።  ወደፊትም እነዚህ አይሆኑምና ከመንፈስ መዋዥቅ ለመውጣት ምናልባት ራሳችንን መርምረን የምንጠበቀውን ተስፋም ሆነ ስጋት ከነባራዊ ሁኔታ ጋር አስታርቀን የሚሆን የሚሆነው ላይ ማተኮር ይሻል ይሆን እላለሁ።   እንደ ባለ አዕምሮ ሲታይ በኢትዮጵያ ምድር እንኳን ምርጫ ማድረግ ቀርቶ፥ በሰላም አብሮ መኖር ያልተቻለበት፥ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live