Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የተናገረው ስህተት ብቻ አይደለም። ወንጀልም ነው! –ጌታቸው ሽፈራው

$
0
0
“ቤታቸው ሊበረበር እንደሚችል ሲያውቁ መንግስትን ለማሳጣት ብለው እንደዚ አይነት ነገር ሁሉ ሊያዘጋጁ ይችላል ተብሎ ነው መታመን ያለበት። ደብተሩን እንደዚህ አይነት የፌክ ነገር ሁሉ አድርገው ሊያስቀምጡ ሁሉ ይችላሉ ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል።” ሲሳይ አጌና የምናከብራቸው ሰዎች ሁሉ ገዥዎችን እንከላከላለን እያሉ ትዝብት ውስጥ እየገቡ ነው። ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እነ ዐቢይ የሚያጠፉትን ለመከላከል ሲጥር ትዝብት ውስጥ እየገባ ነው። ጋዜጠኛ […]

አቶ መላኩ አላምረው ለዶክተር አቢይ አህመድ የሰጠው አጸፋዊ ምላሽ

$
0
0
ሕገ-መንግሥቱ ሳይሻሻል የተሻለች ኢትዮጵያን አናስቀጥልም፤ በዚሁ እንቀጥል ማለት አሁንም በአማራ ሀገር አልባነት ላይ ሀገር እንገንባ እንደማለት ነው።” —> (፩) “በአንድ ክልል ጠያቂነት ተነስተን ሕገ-መንግሥቱን ልናሻሻል አንችልም” ማለት ይቻላል። ይህንን “አንድ” የተባለን ክልል ያገለለን ብቻ ሳይሆን ከመሠረቱም ያላካተተን ሕገ መንግሥት ይዞ እየመሩ መቀጠል ግን አይቻልም። … (፪) የአማራ ሕዝብ ጉዳይ “የአንድ ክልል” ጉዳይ አይደለም፤ ፈጽሞ ሊሆንም […]

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሞሮኮ እግር ኳስ ፕሬዝዳንትን ከሠሠ

$
0
0
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ሦስተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት ፋውዚ ሌክጃ፤ በፊፋ እውቅና የተሠጠውን በዓምላክ ተሰማ (ዳኛ) ላይ ድብደባ በመፈጸማቸው ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ በሳለፍነው ሳምንት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን በግብፁ ዛማሌክ እና በሞሮኮው ቤርካኔ የእግር ኳስ ክለብ መካከል በተደረገው የፍፃሜ ዋንጫ ላይ በአምላክ ተሰማ የመሐል ዳኛ ሆነው በመሩበት ጨዋታ የግብፁ ዛማሌክ አሸናፊ ሆኖ […]

“በትግራይ ውስጥ የጥላቻ ገበያው ድርቷል”ኤኤፍ ፒ –ህብር ራዲኦ

$
0
0
ሰሞኑን የፓለቲካ ትኩሳቱ ወደ ተጋጋመበት የትግራይ ክልል ያመራው የፈረንሳይ የዜና አገልግሎት (አዣንስ ፍራንስ) ዘጋቢ እሳዛኝ ፣አስገራምእና አሳሳቢ ያላቸው ትዝብቱን አስፍሯል። ፍቅር ሲቀዘቅዝ?:- ለወትሮው አድናቂዎቹን በፍቅር ዘፈኖቹ ያዝናና እና ጮቤ ያስረግጥ የነበረው የሬጌ ሙዚቃ ስታይል አቀንቃኙ አርቲስት ሰለሞን ይኩኑ አምላክ ባልተለመደ ሁኔታ እና ቅጽበት በትግራይ የፓለቲካ ልሂቃኖች የሚቀነቀነው “የጸረ ዶ/ር አብይ አሕመድ አስተዳደር ዘመቻን ለመደገፍ እና […]

ቻይና በባህር ዳር ረዥሙን ድልድይ ልትገነባ ነው

$
0
0
ኢትዮጵያ 49 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተያዘለት ረዥም ድልድይ ልትገነባ መሆኗን ፌስ ቱ ፌስ አፍሪካ በድረገፁ አስነበበ፡፡ ግንባታውም በቻይናው ሲሲሲሲ ኮንስትራክሽን ኩባንያ የሚከናወን ሲሆን ኩባንያው የድልድዩን ግንባታና ዲዛይን በሚመለከት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የስምምነት ፊርማ ማስቀመጣቸውን ዘገባው አስፍሯል፡፡ በባህርዳር አካባቢ በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ድልድይ በ3 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ዕቅድ ተይዞለታል፡፡ በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው […]

የህወሓት ማ/ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው መግለጫ 7 ዉሳኔዎች

$
0
0
1 – በጀግኖች የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ላይ የተፈፀመው ግዲያ ከሀሳብ እስከ ተግባር በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ተሳትፎ የነበራቸው ዉስጣዊ እና ዉጫዊ ሀይሎች በሀገራዊ ገለልተኛ ወገን በፍጥነት እንዲጣራ፡ የፀጥታና ደህንነት ተቋማትና አመራሮች በዚህ ተንኮል የነበራቸው ተሳትፎ ሆነ ሀላፊነታቸው አለመወጣታቸው የተፈፀመው ጥፋት ተጠያቂ እንዲሆኑ፡ ይህ የማጣራት ሂደት በአካሄዱ እና ዉጤቱ በየጊዜው ለኢትዮጵያ ህዝቦች ግልፅ እንዲደረግ የህወሓት ማ/ኮ […]

አምናና ዘንድሮ –ነፃነት ዘለቀ

$
0
0
ነፃነት ዘለቀ (netsanetz28@gmail.com) የ97ን የከሸፈ ምርጫ ተከትሎ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አንድ ድንቅ ነገር ተናግረው ነበር፡፡ እርሱም “ኢቲቪን ማየት ካቆምኩ ጀምሮ ጤንነቴ ተመለሰ” ያሉት ነው – በትክክል ካላስቀመጥኩት ይቅርታ፡፡ እኔም ከርሳቸው ልዋስና ጤንነቴ ስለሚበልጥብኝ ኢቲቪን አላዘወትርም፤ እንዲያውም አላይም ነበር፡፡ ካለፈው ዓመት ለውጥ ወዲህ ግን በመጀመሪያ አካባቢ በደምብ፣ ቆየት እያልኩ አንዳንዴ፣ ከቅርብ ጊዘያት ወዲህ ደግሞ በጭራሽ አላይም፡፡ […]

የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ግምገማ ሂደቱን በተመለከተ የቀረበ አጭር ማብራሪያ

$
0
0
የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 28/2011 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል፡፡ በውይይት መድረኩም አገራዊ እና ክልላዊ፣ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን በዝርዝርና በጥልቀት እየገመገመ ይገኛል፡፡ በክልሉ ህዝቦች የተነሱ የአደረጃጀት እና የመልካም አስተዳደር ጥቄዎችን አስመልክቶ ማዕከላዊ ኮሚቴው ፍፁም በሆነ በሰከነና በኃላፊነት መንፈስ እየተወያየ ይገኛል፡፡ ውይይቱም እጅግ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ በሳል በሆነ መንገድ እየተካሄደ ያለ ሲሆን […]

የአብን ደጋፊዎችና የኛ ጋዜጠኞች ተሞከረ በተባለው መፈንቅለ መንግሥት.. ተረት ተረት እና ነጭ ውሸት ነው

$
0
0
የአብን ደጋፊዎችና የኛ ጋዜጠኞች ተሞከረ በተባለው መፈንቅለ መንግሥት.. ተረት ተረት እና ነጭ ውሸት ነው  

በባህር ዳርና አዲስ አበባ በተከሰቱ ቀውሶችና በሌሎችም አካባቢዎች በሚታዩ ውጥረቶች ተሸንፈን አገራችንን አንድነት በሚፈታትን ቀውስ ውስጥ እንዳንገባ ሰከን ባለ መንፈስ  እናት ኢትዬጵያን በጋራ እንታደግ!!

$
0
0
( ከአበባየሁ አሉላ ) ዋሽንግተን ዲሲ በባሕርዳርና አዲስ አበባ በሰሞኑ የተከሰተው ቀውስ በሁሉም አቅጣጫ የብዙ ወገኖቻችንን ሕይወት የቀጠፈ በመሆኑ በግራም ይሁን በቀኝ የዜጎቻችን ልብ የተሰበረበት ወቅት ነው! በዚህ እንቆቅልሹ ባልተፈታ ቀውስ የአማራው ክልል ወገናችንም ብርቅዬ ልጆቹን ያጣበት ወቅት በመሆኑ ሐዘኑና ምሬቱ እጅግ ከፍተኛ ነው! በመቀጠልም በዚሁ ውጥረት ውስጥ በደቡብ ክልል የሲዳማ የማንነትና ክልል እንሁን እጣብቅኝ […]

ራሱ ነካሽ ራሱ ከሳሽ – ሕወሓትን ያጋለጠው የአዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0
ከአዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ የድርጅታችን አዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰኔ 15/ቀን 2011 ዓ.ም በክልላችን መንግስት ላይ ተሞክሮ ሙሉ በሙሉ በከሸፈው መፈንቅለ-መንግስት እና በከፍተኛ አመራሮቻችን ላይ በተፈፀመው የግፍ ግድያ ምክንያት የማዕከላዊ ኮሚቴያችን ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ ተመስርቶ በወቅታዊ ጉዳይ እና ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎች ግምገማ ለማድረግ ሐምሌ 4 […]

የአብይ አስተዳደር እና ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች፤ ኢትዮጵያን ወዴት?  –ያሬድ ሃይለማሪያም

$
0
0
በደስታ እና በተስፋ የተቀበልነው ለውጥ እየተውገረገረም ቢሆን የአመት ከመንፈቅ እድሜ አስቆጥሯል። ዛሬ ያደስታ እና ተስፋ በብዙዎች ዘንድ እየተሟጠጠ ይመስላል። ደስታችን በበርካታ አስደንጋጭ ክስተቶች ተውጧል። ተስፋችንም በአስተዳደሩ መብረክረክ እጅግ እያቆለቆለ መጥቷል። ከመጀመሪያውም በለውጡ ላይ ደስተኛ ያልነበሩም ሆነ ተስፋ ያላደረጉ ሰዎች የተመኙት ወይም የፈሩት የደረሰ መሆኑን ለማሳየት ንግግራቸውም ሆነ ምልከታቸው ‘እንደተመኘኋት አገኘዋት’ የሚለውን ዘፈን የሚያቀነቀኑ አስመስሏቸዋል። በጎ […]

”ታፍነናል፣ ታከለ ኡማ ይውረዱ!!!”ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ –ህብር ራዲኦ

$
0
0
የአዲስ አበባ ከተማ የባለቤትነት ጉዳይን በቅርበት እየተከታተለ የሚገኘው የባልድራስ ሰብሳቢ፣የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ኢትዬጵያ ወደ ዘመነ ህዋት አገዛዝ እንዳታዘነብል ስጋቱን ገለጸ ፣ለዲያስፖራው ማህበረሰብም ጥሪውን አቀረበ። በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ዛሬ አ/አ ውስጥ ጌዜጣዊ መግለጫ የሰጠው የባላአደራው ም/ቤት ሰብሳቢ እስክንድር ” የህዋት አገዛዝ ከተገረሰሰ ከአንድ አመት በሁዋላ ኢትዬጵያ ዳግም የህሊና እስረኞች ማጎሪያ አገር ሆናለች” […]

ምዕራፍ ሃያ አንድ ኢትዩ-ቴሌኮምና ቻይናዊያን ሾተላይ ሰላዬች! (ክፍል ሁለት)

$
0
0
የቻይና የቴሌኮም ካንፓኒ፤ዜድቲI ZTE Corporationና ሀዊ Huawei Technologies Co. Ltd. የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ንብረት የሆኑት ድርጅቶች ለህወሃት ኢህአዲግ መንግስት የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍን ውስጥ በመሰለልና የሃገሪቱን ምስጢርና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በስለላው መረባቸው በመቆጣጠር ከፍተኛ ጥቃት አድርሰዋል፡፡ ለዚህም ስራቸው ያለ አንዳች ነፃ ውድድርና ጨረታ በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኝ ሥራን ሁሉ እንዲሰሩ ተሰጥቶቸዋል፡፡ የቻይናዊያን ሾተላይ ሰላዬች፤ የቻይና መንግስት የቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽንና […]

ይቅርታ የማስጠየቅ ሱስ (ይሄይስ አእምሮ)

$
0
0
እንደብሂሉ እውነትም አንዳንድ መጥፎ ጠባይ ሳያስቀብር አይለቅም፡፡ ሕወሓትን የያዘው ግፍ የሠራባቸውን ዜጎች ሣይቀር ይቅርታ የማስጠየቅ አባዜ ከመነሻው እስከመጨረሻው ሊለቀው አለመቻሉን ስገነዘብ እጅግ ድንቅ ይለኛል፡፡ ያንን መላው የሀገራችን ሕዝብ የሚያውቅለትን የተጨፈኑ ላሞኛችሁ የይቅርታ ማስባል ጅል ዐመሉን አሁንም የሙጥኝ እንዳለ ነው፡፡ “ሞኝ እንዴት ብሎ ይረታል?” ቢሉ “እምቢ ብሎ” ይባላል፡፡ ወያኔም ከዚህም የባሰ ነው፡፡ ሰሞኑን ባሕር ዳርና አዲስ […]

አዴፓትክክለኛውንመንገድያዘ –ስለሽ ደስታ

$
0
0
ላለፉትሃያሰባትዓመታትየኢዴፓአቋምናአካሄድየተልፈሰፈሰናእራሱንአዋርዶመላውየአማራዉንሕዝብያዋረደ፥ለችግር፥ለመከራ፥ለስቃይ፥ልስደት፥ለእስራትናለሞትየዳረገቡድንእንደነበርየትናንትትዝታችንነው።ሆኖም ግን ላለፉት አሥራ አራት ወራት በነበረው የለውጥ ጭላንጭል ተከትሎ መለስተኛና እራስን ለመሆንእያደረገ የነበረውን የትግል አካሄድ የአማራ በዋናነትም የኢትዮጵን ትንሳኤ ለሚደረገው የትግል እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪና  ጥሩ ጅምር እንደሆነ እያስየዋልን ባለንበት በአሁኑ ወቅት ሰሞኑን በባህር ዳርና በእዲስ አበባ ተከሰተ በተባለው መፈንቅለ መንግሥት ተብየው ድራማን በተመለከተ ህወሃት በአዴፓ ላይ ያወጣዉን ቅጥ ያጣ፥ እርስ በራሱ የሚቃረንና መሰረተቢስ ክስ መላው የኢትዮጵያን […]

በሱዳን የተካሄደው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉ ተነገረ

$
0
0
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 5፣ 201 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት በሀገሪቱ የተካሄደው መፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሽፉን አስታወቀ፡፡ የመፈንቅለ መንግስር መኩራ መካሄዱ የተሰማው የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት እና ተቃዋሚዎች ስልጣንን በመጋራት በሀገሪቱ ሲካሄድ የቆየውን ተቃውሞ ለማርገብ ጥረት እያደረጉ ባሉበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡ ከከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጋር ተያይዞ 16 ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የምክር […]

የሕወሓት እና የአዴፓ የቃላት ጦርነት ፣መዘዙ…–ህብር ራዲኦ

$
0
0
የኢሕአዲግ መስራች ድርጅቶች የሆኑት ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ(ሕወሓት) እና የአማራ ዲሞክራሲ ፓርቲ (አዴፓ) ከከባድ መሳሪያ ፍልሚያ ያልተናነሰ ፣ ሙት እና ቁስለኛ ያል ያልተለቀመበት ፣ያልተቆጠረበት ፣ነገር ግን የተካረረ የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል። ሁለቱ ፓርቲዎች የቆየ ልዪነቶች እንዳሏቸው ቢታወቅም ሰሞነኛው መሻኮት እና ተቃርኗቸው እንዲህ ገኖ እንዲወጣ ዋንኛ ምክንያት የሆነው ባለፈው ሰኔ 15 2011 ዓም በባህርዳር እና በአ/አ […]

በኢትዮጵያ አሁን ለሚታየው ውጥንቅጥ መፍትሄው ፖለቲካዊ ብቻ አይደለም (ድጋፌ ደባልቄ)

$
0
0
ድጋፌ ደባልቄ ጁላይ 12፣ 2019 በኢትዮጵያ አሁን ለሚታየው ውጥንቅጥ መፍትሄው ፖለቲካዊ ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ዲሞክራሲ የለም ሊኖርም አይችልም:: ዲሞክራሲን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ለመገንባት የሚያስችሉ ተሰፋ ሰጪ ሁኔታዎች ግን አሉ፡፡በመሆኑም ለውጡን ተከትሎ የዲሞክራሲ ስርአትን በተቋማዊ መልክ ለመገንባት የሚያስችሉ መሰረቶች እየተጣሉ ነው፡፡ በአንድ አገር የዲሞክራሲ ምህዳር አለ ብሎ ለማለት ቢያንስ ሁለት መመዘኛዎች መሟላት አለባቸው፡፡ አንደኛው […]

ውልክፋ አትደገፍ! –በላይነህ አባተ

$
0
0
ያድነኛል ብለህ ተወዠቦ ተዶፍ፣ ወይራ ሆይ ተመከር ውልክፋ አትደገፍ፡፡   ተወይራ ዋንዛ ሥር ውልክፋን ሲፈጥረው፣ በእምብርክኩ እሚሄድ ልፍስፍስ አርጎ ነው፡፡   በልግን ተመርኩዞ ራስ ቀና ቢያደርግ፣ እውነት አይምሰልህ ቀጥ ብሎ እሚሄድ፣ ውልክፋ አጎንባሽ ነው ወዲያው እሚል እርፉቅ፡፡   እንደ ልጅ አጫዋች ወፌ ቆመች ብትል፣ ውልክፋ ልምሻ ነው ቀጥ ማለት የማይችል፡፡   ወስደው የተከሉት ውልክፋን ተዛፍ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live