Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አንድነት እና መኢአድ በመጪው እሁድ በባህርዳር በተጠሩት ሰልፍ የተነሳ ከወዲሁ ወጣቶች እየታፈሱ ነው

$
0
0

abugida “አንድነትና መኢአድ የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ብአዴንን አሳስቦታል “ስራ አጥ” ያላቸውን ወጣቶችን ዛሬ ሲያሳፍስ ውሏል” ሲል ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘገበ። እንደ ጋዜጣው ዘገባ “የባጃጅ አሽከርካሪዎችም ሰልፉን እንዳይቀሰቅሱና እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል”

ፍኖተ ነፃነት ዜናውን ከምንጮቼ አረጋግጫለሁ እንዳለው አንድነት ፓርቲ ከመኢአድ ጋር በመሆን የጠራውና በመጪው ዕሁድ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም ብአዴንን በመቃውሞ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ብአዴንን እንዳሳሰበውና በባህር ዳር ከተማ “ስራ አጥ” ያላቸውን ወጣቶችን ዛሬ ሲያፍስ ውሏል።

የአማራ ክልልን እየመሩ አማራውን በፀያፍ ቃላት የተሳደቡትን አቶ አለምነው መኮንን ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ ከስልጣንም እንዲወርዱ ለመጠየቅ በተጠራው በዚህ የባህርዳሩ ሰልፍ የተነሳ አፈሳው ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ሕዝቡን ለማስፈራራት ነው። እንደፍኖተ ዘገባ አፈሳው በመንገድ ላይ ንግድ የተሰማሩና ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎችንንም የጨመረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ጋዜጣው በተጨማሪም ከዚሁ ጎን ለጎን የብአዴን ካድሬዎች የባህር ዳር ከተማ የባጃጅ አሽከርካሪዎችንም በመሰብሰብ ሰልፉን እንዳይቀሰቅሱና በተቃውሞ ሰልፉ ላይም እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋቸዋል ሲል የዘገበ ሲሆን የባህር ዳር የባጃጅ አሽከርካሪዎች አንድነት ፓርቲ በሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ በባህርዳር ባደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በራሳቸው ተነሳሽነት ቅስቀሳ ሲያሰርጉ እንደነበር ይታወሳል በማለት ዘገባውን አጠናቋል።


Health: ሴቶች በባሎቻቸው ላይ የሚሄዱባቸው 7 ምክንያቶች [Top 7 Reasons Why Women Cheat]

$
0
0

women cheating ‹‹ወንዶች አካላዊ ፍላጎታቸውን ለማስታገስ፤ ሴቶች ደግሞ ለተለያዩ ስሜታዊ ምክንያቶች ይወሰልታሉ›› ሲባል ሰምተው ይሆናል፡፡ ጥቂትም እውነትነት ሳይኖረው አይቀርም፡፡ በቅርቡ ሴቶች በፍቅረኞቻቸው ላይ የሚወሰልቱባቸውን ምክንያቶች ለማወቅ በሚል አንድ ጥናት ተደርጓል፡፡ ‹‹አሳሳሙ ይደብረኛል…›› ከሚለው እስከ ‹‹ለበቀል ነው›› የሚሉ ምላሾች ተገኝተዋል፡፡ ጥናቱ እንስቶችን ለመወስለት ያነሳሳሉ ያላቸውን ሰባት ምክንያቶች እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡

1. ፍቅር ስሜት አልባ ሊሆን
‹‹…ከጆን ጋር ለሶስት ዓመታት አብረን ኖረናል፡፡ በጣም ጥሩ ሰው ነው፡፡ አብሬው መሆን ያስደስተኛል፡፡ ይሁን እና ፍቅራችን ስሜት አልባ ነው፡፡ አብዛኞቹ የምናውቃቸው ሰዎች የተጋቡ ወይንም ለመጋባት የተጫጩ ናቸው፡፡ ጆን ሳይፈልግ ቀርቶ ሳይሆን ጉዳዩን ሲያነሳው ወዲያው ወሬ ስለምቀይርበት ነው፡፡
ወደ አውስትራሊያ በስራ ምክንያት ሁሌም ከሚማርከኝ የስራ ባልደረባዬ ጋር ተጓዝኩ፡፡ በጣም አስደሳች ወቅትም አሳለፍን፡፡ ከጆን ጋር የተለያየሁት እንደተመለስኩ ነበር፡፡ የሰራሁት ተግባር ደረቴን አስነፍቶ የሚያኮራኝ ባይሆንም ከጆን ያጣሁትን ከዚህ ልጅ አግኝቼ ነበር፡፡ ለሶስት ዓመታት በፍቅር ከቆየን በኋላ አሁን ተጋብተን በደስታ በመኖር ላይ ነን›› ስትል ጊሴል የተባለች የ30 ዓመት ወጣት በቀድሞ ፍቅረኛዋ ላይ እንድትሄድ የገፋፋትን ምክንያት ገልፃለች፡፡

2. ፍቅር ካለቀ በኋላ ለመለየት መፈለግን ደፍሮ አለመናገር
‹‹ከቀድሞ ፍቅረኛዬ ከሾን ጋር ከመለያየታችን በፊት በጣም የሚወዳት ውሻው ሞታበት ልቡም በጣም ተሰብሮ ስለነበር ካንተ ጋ ያለኝ የፍቅር ግንኙነት አልቆለታል… መለያየት አለብን›› ብዬ ብነግረው ጭካኔ ይሆንብኛል ብዬ በማሰቤ ስሜቱ እስኪስተካከል ድረስ ለወር ወይንም ከዚያ ለበለጠ ጊዜ ልጠብቀው ወሰንኩ፡፡ ሞራሉ ጥሩ በሆነበት፣ ነገሮች የተስተካከሉ በመሰሉበት እና እኔም ለመንገር በተዘጋጀሁበት ወቅት ደግሞ ከስራው ተባረረ፡፡ በድጋሚ ኑሮው እስኪስተካከል መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ በዚህ መሀል ‹‹ፍቅርስ ከዚህ ጋር… ብዬ የምመኘውን አይነት ሰው አገኘሁና አብሬው መሆን ጀመርኩ፡፡ በጊዜ ሂደት ለሾን የሚሰማኝን ነግሬ ተለየሁት፡፡ ከሱ ጋር እያለሁ ከሌላ ሰው ጋር ፍቅር መጀመሬ ግን አልነገርኩትም ነበር፡፡ ይህን ቢያውቅ ኖሮ የሱን ስሜት ለመጠበቅ ብዬ ያደረኩትን ነገር ሁሉ ከታላቅ ክህደት ይቆጥረው ነበር፡፡ ለሱ ያለኝ ስሜት ተንጠፍጥፎ ባለቀበት ወቅት መንገር እንደነበረብኝ ኋላ ላይ ተሰምቶኛል›› ስቴሲ 30 ዓመት ዕድሜ ያላት የሌክሲንግተን ኗሪ፡፡

sexual-problems3. ርቀት ለፍቅርና ለታማኝነት ጠንቅ ነው
‹‹ከምንኖርበት ስፍራ 320 ኪሎ ሜትር በሚርቅ ኮሌጅ ስኮላርሺፕ አግኝቼ ስሄድ ከፍቅረኛዬ ከክሬግ ጋር ፍቅርን በሩቁ ማስኬድ የምንችል መስሎኝ ነበር፡፡ የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ነገሮችን ባሰብኩበት መንገድ ማስኬድ ችዬ ነበር፡፡ ነገር ግን ቀናት እየገፉ በሄዱ ቁጥር ላብራቶሪ ውስጥ አብሮኝ ከሚማረው ሄንሪ ከተባለ ወጣት ጋር ፍቅር እንደያዘኝ ተረዳሁ፡፡
እንደቀልድ የተጀመረ ልፊያ ቀስበቀስ ወደ አንሶላ መጋፈፍ አደረሰን፡፡ ስልጠናው ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ ግሬክ እቅፍ ተመልሼ ገባሁ፡፡ ነገር ግን ከሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ አዳጋቻ ሆነብኝ፤ ይሁንና እሱንም ስለምወደው ልለየው አልፈለግኩም፡፡
ሄነሪን በተደጋጋሚ ብጎበኘውም ለኔ የሚሆን አይነት ሰው እንዳልሆነ ሳውቅ ከሱ ጋር ያለንን ግንኙነት አቋረጥኩ፡፡ ስለውስልትናዬ ለግሬክ ምንም አለመናገሬ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲያድርብኝ አድርጎኛል፡፡ ይህን ስህተቴንም ባለማወቅ በልጅነት አዕምሮ የተፈፀመ ብዬ ራሴን ለመሸንገል ሞክሬያለሁ፡፡ ኮርሱን ካጠናቀቅኩ ከአራት ዓመታት በኋላ አሁንም ከግሬክ ጋር ነኝ›› ታማራ በፖርትላንድ የምትኖር የ33 ዓመት ሴት ናት፡፡

4. ብቸኝነት እና የማንም አለመሆንን መፍራት
‹‹የሁለት ዓመት ፍቅረኛዬ ዴቭ አልፈልግሽም ብሎ ከተለየኝ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከኤሪክ ጋር መውጣት ጀመርኩ፡፡ በወቅቱ ስሜቴ በጣም ተጎድቶ ስለነበር ኤሪክ ዋነኛው አጽናኜ ነበር፡፡ ከኤሪክ ጋር ለአምስት ወራት እንደቆየሁ ዴቭ ተመልሶ በመምጣት አብሮኝ መሆን እንደሚፈልግ ነገረኝ፡፡ በጣም ናፍቆኝ ስለነበር አብሬው መሆን ጀመርኩ፡፡ ይህን የማደርገው ከኤሪክ ሳልለያይ ነበር፡፡ ይህን ወድጄ ያደረኩት አይደለም፡፡ ምናልባት ዴቭ መልሶ ቢከዳኝ ከኤሪክ ጋር ለመቀጠል እንዲመቸኝ የቀድሞ ጉዳቴ ያስተማረኝ ጥንቃቄ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ነገር ግን አልተሳካልኝም፡፡ ዴቭ አሁንም ከዳኝ ኤሪክ ደግሞ የኔንና የዴቭን ነገር ከጓደኛቹ ሰማ፡፡ ሌላኛውን ትምህርት በሚያም መልኩ ተማርኩ- ከሁለት ወንዶች ጋር ግንኙነት መጀመር ትርፉ ከሁለቱም ሳይሆኑ መቅረት እንደሆነ›› ጄን የ28 ዓመት ወጣት ስትሆን በኦክፓርክ ከተማ ኗሪ ነች፡፡

5. ከመጥፎ ግንኙነት ለመውጣት መሻት
‹‹ኢታን ከሚባልና ሁሌም ከሚተቸኝ ልጅ ጋር ግንኙነት ጀምሬ ነበር፡፡ በየጊዜው ስለክብደቴ፣ ስለ አለባበሴ እና ደባሪ ስለመሆኔ እያነሳ ይተቸኝና ያሸማቅቀኝ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ጓደኞቼ እና ቤተሰቦቼ በጣም ቢጠሉትም፣ እኔን እያበሻቀጠ የፈለገውን ቢለኝም እኔ ግን ከሱ መለየትን አልፈለኩም፡፡ በአንድ የሳምንቱ መጨረሻ ዕለት ፓርቲ ላይ ዊልን ተዋወቅሁት፡፡ ከኢታን ፍፁም የተለየ ደግ፣ ጣፋጭ እና ለጋስ እንዲሁም ፍፁም የተረጋጋና አብረውት ቢውሉ የማይሰለች አይነት ልጅ ነው፡፡ የሳምንቱን የመጨረሻ ቀናት በሙሉ አብረን ካሳለፍን በኋላ ከበሰሉ ወጣቶች ጋ ፍቅር እንዲህ አስደሳች ነው ስል አሰብኩ፡፡ እሁድ ምሽት ለመጀመሪያ ጊዜ ዊልን ሳምኩት፡፡ ብዙም ሳልቆይ ከኢታን ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋረጥኩ፡፡ ከዊል ጋር ለሶስት ዓመታት በፍቅረኝነት ከቆየን በኋላ በጋብቻ ተጠቃለልን፡፡›› አሊሰን የኒውዮርክ ኗሪ ስትሆን የ30 ዓመት ወጣት ነች፡፡

6. ከማንነት ጋር የሚስማማንን ሰው ፍለጋ
‹‹የፍሎሪዳ ተወላጅ በመሆኔ በባህር ዳርቻዎችና በጀልባዎች ላይ መንሸራሸር እወዳለሁ፡፡ የመሀል ሀገር ልጅ የሆነው የቀድሞ ፍቅረኛዬ ክሪስ ደግሞ ይንንን ይጠላ ነበር፡፡ በየጊዜው የት ሄደን መዝናናት እንዳለብን እያነሳን እንጨቃጨቅ ነበር፡፡ ሁልጊዜም እሱ አሸናፊ ነበር፡፡ ለስምንት ወራት ያህል አብረን ከቆየን በኋላ አንድ ዕለት ከጓደኞቼ ጋር ጀልባ ተከራይተን ኪይዌስት ወደተባለ ስፍራ ሄድን፡፡
የጀልባዋ ካፒቴን የባህር ዳርቻዎችን የሚወድ፣ ሳቢና መልከመልካም ወጣት ነበር፡፡ ቀኑን ሙሉ ከሱ ጋር ስጫወት አሳለፍኩ፡፡ ያን ዕለት ምሽትም ለብቻችን ጥሩ ጊዜ አሳለፍን፡፡ ወደ ቤቴ ስመለስ ለክሪስ ስለሆነው ምንም አልነገርኩትም፤ እኔም የጥፋተኝነት ስሜት አልተሰማኝም፡፡ ግማሹ እኔነቴ ክሪስ በጣም ግትር በመሆኑ በሱ ላይ መሄዴ ይገባዋል የሚል ስሜት ነበረው፡፡ ከክሪስ ጋር አብረን መዝለቅ አልቻልንም፡፡ ከተለያየን በኋላ የምይዛቸው ወንድ ጓደኞች የባህር ዳርቻን የማያፈቅሩ ከሆነ እርቃቸዋለሁ›› ሊዝ ቺካጎ የምትኖር የ32 ዓመት ሴት ነች፡፡

7. መቃጠልና መንገብገብ ምን እንደሚመስል ይየው
የቀድሞ ፍቅረኛዬ የለየለት ሴሰኛ ነበር፡፡ እቀይረዋለሁ ብዬ አስቤ የነበረ ቢሆንም ልክ አልነበርኩም፡፡ አብረን እያለን ሌሎች ሴቶችን እንደሚያወጣ ወሬ ብሰማም ስጠይቀው ሁሌ ሽምጥጥ አድርጎ ይክዳል፡፡ አንድ ምሽት አንዲት ልጅ ደወለችልኝና ከፍቅረኛዬ ጋር ሶስት ወር የሞላው ግንኙነት እንዳላቸው፤ ከሌላ ሴት ጋርም ግንኙነት እንዳለው ማወቋን ስትነግረኝ በንዴት ጦፍኩ፡፡ እጅግ በመናደዴም ሽቅርቅር ብዬ ለብሼ ጓደኞቼ ዘንድ ሄድኩ፡፡ ምሽቱንም ከአንድ መልከመልካም ወጣት ጋር አሳለፍኩ፡፡ ለፍቅረኛዬ ያንምሽት ያደረኩትን ነገር እንዲሁም ስለሌሎቹም ሴቶች ማወቄን ስገልጽለት ፊቱ ላይ ያየሁት ነገር ትልቅ እርካታ ሰጠኝ፡፡ ወራዳና የማይረባ መሆኑን ነግሬም አባረርኩት፡፡›› አሻንቴ በኮሌጅ ፓርክ የምትኖር የ25 ዓመት ወጣት ነች፡፡
ከላይ በእውነተኛ ታሪክ ተደግፈው የቀረቡትና ሴቶችን ለውስልትና የሚገፋፉ ድርጊቶች አብዛኞቹ በወንዶቹ ስህተት እና የእውቀት ማነስ የተነሳ የተከሰቱ ናቸው፡፡ ሴቶችን በማንነታቸው ማክበርና ማፍቅር እንዲሁም ማንነታቸውን መቀበል ለዘላቂ ፍቅር ዋነኛው መሰረት ነው፡፡

የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ድርጅት ለረዳት ፓይለቱ ጠበቃ አቆመ

$
0
0

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን ስዊዘርላንድ ላይ ያሳረፈው የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን ጉዳይ አነጋጋሪነቱ እንደቀጠለ ነው። የአውሮፕላን ጠለፋው ጉዳይም ከኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጋር የተያያዘ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው እየተነገረ ይገኛል። ይህን ተከትሎ ረዳት ፓይለቱ የሰራው ሥራ የሚደነቅ ነው በሚል በርካቶች ውዳሴን እያቀረቡለት ሲሆን “ረዳት ፓይለቱ በእጁ እንዳለው የተለያየ ሃገር ቪዛ በማንኛውም ጊዚ ከሃገር መውጣት ይችል ነበር፤ ሆኖም ግን ሊያስተላልፈው የፈለገው መልዕክት ስላለ ነው አውሮፕላኑን የጠለፈው ስለዚህ ይህ ለኢትዮጵያውያን የተከፈለ መስዋእትነት ነው” በሚልም ሰኞ ዕለት ለፈጸመው ድርጊት አድናቆትን እያገኘ እንደሆነ ከሚደረጉ እንስቃሴዎች መረዳት ይቻላል። ዛሬ ቢቢኤን ራድዮ ጣቢያ እንዳደረሰን መረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ የፖለቲካኛ እስረኞች አንድነት ድርጅት ለሃይለመድህን ጠበቃ ማቆማቸውን ይገልጻል። ዝርዝሩን ያድምጡት፦

ethio airlines

መከላኪያ የህዝብ ወይስ የህወሓት?

$
0
0

ከበላይ ገሰሰ
Addera5021@yahoo.com

ህወሓት ደርግን ማሸነፍ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብን ማሸነፍ ማለት ነው ብሎ ስለሚያስብ ተግባሩ ሁሉ የንቀት፣ የማንቋሸሽና የማዋራድ ስራ እየፈፀመ ይገኛል። ሌላውን ትተን ጥቂት የሻዕቢያ ተላላኪ የሆኑትን የህወሓት መሪዎች የግንጠላ አጀንዳቸውን ይዘው በረሃ የሸፈቱበት ቀን ልክ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የትግራይ ህዝብ “ደደቢት ሂዳችሁ ታገሉሉኝ” ብሎ ወክሎ የላካቸው ይመስል “እኛ ታግለን ነፃ ስላወጣንህ እንደፈለግን እናደርጋሃለን” በማለት ዓይን አዉጣ በሆነ መንገድ ሰሞኑን “የካቲት 11 የትግራይ ህዝብ ዳግም ልደት ነው” እየተባለ በመከላኪያ ሰራዊት ታጅቦ በመከበር ላይ ስለሚገኘው የህወሓት አስቂኝ፣ አስገራሚና አሳዛኝ ድራማ የሚከተሉትን ጥቂት ነጥቦችን በአጭሩ እንመልከት።
ethio military
የህወሓት ድራማ ቁጥር 1.

የህወሓት መሪዎች እናስተዳድራለን የሚሉት 90 ሚሊዮን የኢ/ያ ህዝብ ነው እየገዙ ያሉት። ከፍተኛ ባለስልጣናቱን ጨምሮ ካድሬዎቻቸው፣ አባላቶቻቸውና ደጋፊዎቻቸው በቀጥታም ሆነ በስውር እየጋጡ ያሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት ነው። የገጠሩን ትተን በሀሪትዋ ዋና ዋና ከተሞች ቁልፍ ቦታዎችን በመያዝ 90 ከመቶ የትግራይ ባለሀብቶች የቢዝነስ እንቅስቃሴያቸውን የሚያካሂዱትና ባለቤት የሆኑት በሌሎች ክልሎች ነው። በአጠቃላይ የሀገሪትዋ ሀብት በተለያየ መልኩ የተቆጣጠሩት የህወሓት መሪዎች፣ ካድሬዎችና አጃቢዎቻቸው ናቸው። በመሆኑም በመሬት ላይ ያለው ህዝቡ የሚያውቀው ሐቅ ይህ ሆኖ ሳለ እነሱ የሚሉን ግን “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነን” ነው። ልብ በሉ!! ስልጣን ላይ ያሉት እነሱ። ሀገሪቱን የተቆጣጠሩት እነሱ። ሀገሪትዋን እየዘረፉ ያሉት እነሱ። ነገር ግን ነፃ እናወጣለን የሚሉት ህዝብ አንድ ክልል ነው። ታዲያ!! ቆም ብሎ ላሰበውና ላስተዋለው ሰው ይህ መንግስት ከኛ አብራክ የወጣ ኢትዮጵያዊ መንግስት ነው ለማለት ያስችላልን?።

የህወሓት ድራማ ቁጥር 2.

የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን ከነ ባንዴራዋ ከፈጠሩት የታሪክ አስኳል አንዱ መሆኑን ዋቢ የሚያስፈልገው አይደለም። ቢያንስ አንድ ሶስተኛው የትግራይ ህዝብ በመላ ሀገሪቱ ከሌላው ወገኑ ጋር ተሳስሮ፣ ሀብት አፍርቶ፣ ተጋብቶና ተሰባጥሮ በነፃነት ይኖራል። በኢትዮጵያ የትግራይ ተወላጅ የሌለበት መንደር የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ሲኖርም እንደ መጤ ወይም እንደ ስደተኛ አይደለም ራሱም ሆነ ሌላው ሰው የሚያስበው “ሀገሬ!! መብቴ!! ነው” በማለት በልበ ሙሉነትና በመተማመን ይኖራል። በሌላ አነጋገር ህዝቡ ለዘመናት በጋራ የኖሮው በመልካም ጉርብትና ብቻ ሳይሆን በራሱ ፈቃደኝነት በፍቅር፣ በወንድማማችነት፣ በመከባበርና በመተማመን ላይ የተመሰረተ ባንድ እናት ሀገር ጥላ ስር ተቃቅፎ ባህሪያዊ ዝምድናን በመመስረት ነው። ዛሬ 90 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ እሴት አለን የምንለውም ይኸው ነው።
ታዲያ!! ይህ ከሆነ ሐቁ የትግራይ ህዝብ ነፃ የሚወጣው ከማን ነው? ነፃ የሚያወጣውስ ማን ነው? እውነት ለራሱ ነፃ ያልወጣና የሻዕቢያ ሎሌ የሆነውን ዘራፊና ከሃዲ ድርጅት የትግራይ ነፃ አውጪ ነኝ ማለቱ ለታላቁ ህዝብ ውርደትና ሀፍረት አይሆንም ወይ? ለመሆኑ ባድመን ጨምሮ የትግራይን መሬትና ህዝብ የተደፈረው በሀይለ ስላሴ ግዜ ነውን? በሀይለ ስላሴ ስርዓት በትግራይ ምድር ሰው እንደ አራዊት በአደባባይ ተደብድቦስ ያውቃልን? ሀገርን እያፈረሱ ነፃ አውጪ ነኝ ማለቱስ የትግራይ ህዝብ ፍላጎትና ጥቅም መጠበቅ ማለት ነውን? በኢትዮጵያ ደረጃ ትክክለኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትና ፍትሕ ሳይረገጋጥ በትግራይ ብቻ ትክክለኛ ለውጥ ሊረጋገጥ ይችላል ወይ? ህወሓት የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪና መድህን ቢሆን ኖሮ ህዝቡን ከሻዕቢያ ወረራ ያዳነው ማን ነው? እናንተ የትግራይ ነፃ አውጪ ነን ትላላችሁ ነገር ግን ሌሎች ከሰማንያ በላይ ብሄር ብሄረሰቦችስ ማን ነፃ ያውጣቸው?
አዎ!! ይህ ዓይነቱ ድራማና ጥያቄ ላለፉት ሶስት ዓሰርተ ዓመታት እንቆቁልሽ ሆኖ የቆየና ገና በሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ዘንድ በሆድ ውስጥ ታምቆ አንድ ቀን ሊፈነዳ የተቃረበ እሳተ ጎመራ መሆኑን አልጠራጠረም። ከላይ ለተጠቀሱት ጥያቄዎች ህወሓቶች መልስ ይሰጡኛል ብዬም አልጠብቅም። “ከኛ በላይ ወንድ የለም። ተልባ ቢንጫጫ በአንድ መውቀጫ። እኛ እንብላ እነሱ ይጩኹ። እኛ እንግዛ እነሱ ያልቅሱ። ያበጠው ይፈንዳ!! ብለው በንፁኃን ደም የሰከሩ፣ በፍቅረ ንዋይ ዓይናቸው የታወሩ፣ በቂም በቀል አእምሮዋቸው የደነዘዙና በጠባብነት ሻማ የተሸበቡ ካድሬዎችና መሪዎች ዛሬ ዊስኪ እየተራጩና ጮማ እየቆረጡ የልደት በዓላቸውን ቢያከብሩ ብዙም አዲስ ነገር አይደለም።
meles and his milltery
የህወሓት ድራማ ቁጥር 3.

የህወሓት መሪዎች ህዝቡን ለማታለል ከሚሰሩት ድራማ አንዱ በሀገሪትዋ ላይ ሕገ መንግስት፣ መድብለ ፓርቲ ስርዓት፣ ነፃ የመከላኪያ ኃይልና ፍትሕ መኖሩን ለማስረዳት ይሞክራሉ። እነዚህ መሰረታዊ መርሆዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን የአንድ ድርጅት ሞኖፓላዊ ስልጣን ለመጠበቅና ለማገልግል ሲባል ሌላ ቀርቶ ሰሞኑን የህወሓት መሪዎች ልደት ለማከበር እንዴት እንደሚጠቀሙበት ከሚከተሉት ጭብጦች መረዳት ይቻላል።

 ሕገ መንግስት አለ ይሉናል። ነገር ግን በሕገ መንግስቱ የሰፈሩ መብቶች ሌላ ዜጋ እንዳይጠቀምባቸው በተግባር ተገድበዋል። ሕገ መንግስቱ በነፃ መደራጀት ይፈቅዳል በነፃ መንቀሳቀስ ግን በሽብርተኝነት አዋጅ ተገድበዋል። ሕገ መንግስቱ የመናገርና የመፃፍ ነፃነት ይፈቅዳል ነገር ግን በህዝብ ሀብት የሚተዳደሩ የብዙሓን መገናኛ አውታሮች በአንድ ድርጅት በሞኖፓል ተይዟል። የፃፈ ወይም የተናገረ ዜጋ ሁሉ ሰፈሩ ቃሊቲ ወህኒ ቤት ሆኗል። ሕገ መንግስቱ ምርጫ ይፈቅዳል ነገር ግን የምርጫው መወዳደሪያ ሜዳ ተዘግቷል። በአጠቃላይ አንድ ድርጅት ራሱ ሕግ አውጪ፣ ራሱ ሕግ ፈፃሚ፣ ራሱ ገዳይ፣ ራሱ ከሳሽ፣ ራሱ ዳኛ የሆነበት ስርዓት ነው ያለው።

 በሀሪቱ መድብለ ፓርቲ ስርዓት አለ ይሉናል። ነገር ግን አውራ ፓርቲ ወይም ልማታዊ መንግስት በሚል ፓሊሲ ትርጉም ያለው ተቀናቃኝ የፓለቲካ ድርጅት እንዳይበቅል በሩ ተዘግቷል። በሕገ መንግስቱ ላይ አንድ ፓርቲ ከሌሎቹ ፓርቲዎች የበለጠ መብት እንዲኖረው ወይም በአውራ ፓርቲነት የሚፈርጅ አንቀፅ የለም። ነገር ግን ህወሓት ከሌሎቹ የተለየ መብት ያለው የበኩር ልጅ በመሆን የሀገሪትዋን ገንዘባዊ፣ ተቋማዊ፣ ማተሪያላዊና ሰብኣዊ ሀብት በቀጥታም ሆነ በተለያየ መልክ በመጠቀም በዓሉን ሲያከብር እናያለን። ሌላው ሀገር በቀል ኢትዮጵያዊ ድርጅት ያልተሰጠው መብት ለህወሓት ግን ከደደቢት በረሃ በመምጣቱና የመከላኪያ ሰራዊት ከጎኑ ስላሰለፈ ብቻ ሀገርንና ህዝብን እንደፈለገ እንዲንድ፣ እንዲዘርፍ፣ እንዲገድልና እንዲያፍን መብት ተሰጥቶታል።

 መከላኪያ ሰራዊት ከፓለቲካ ነፃ ነው፣ የሕገ መንግስት ዘብ ነው፣ የህዝብ ሰራዊት ነው፣ የልማት ሰራዊት ነው፣ ወዘተ ይሉናል። ነገር ግን በተግባር ሲታይ የአንድ ድርጅት ህወሓት ጠበቃና አጃቢ እንጂ የህዝብ ወገንና መድህን ሲሆን አላየንም። ለምሳሌ ሰሞኑን እንዳየነው ሁሉ የመከላኪያ ሰራዊት ሳምንት በሚል ሽፋኝ እየተካሄደ ያለው ሰልፍና ኤግዚቪሽን ሆን ተብሎ ከህወሓት ልደት ጋር የተያያዘ እንዲሆን ተደርጓል።

“አትረፍ ያለው በሬ ቆዳውን ለከበሮ ይውላል እንዲሉ” የትግራይ ህዝብ ላለፉት አርባ ዓመታት ያሳለፈውን መከራና ስቃይ እንዳይበቃው ዛሬም ከጀርባው አልወረዱም። እንደ ህዝብ መከበር ሲገባው በአንፃሩ ህወሓት ከሕግ በላይ በመሆን አማራጭ መንገዶችን በመዝጋት የአንድ ድርጅት አገልጋይ ሆኖ እንዲኖር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።

ስለዚህ ኢትዮጵያውያን በተለይም የትግራይ ወንድሞችና እህቶች በሙሉ!! ድርጅትና ግለ መሪዎች አላፊ ናቸው።ህዝብና ሀገር ግን ነባሪ መሆናቸውን አምነን ህዝባችንን ከጅብ ምንጋጋ እንዲላቀቅ እጅ ለእጅ ተያይዘን መነሳት አለብን እላለሁ። ዋስትናችን፣ መድህናችንና ጋሻችን አንድ ድርጅት ሳይሆን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑን አማራጭ የሌለው የህልውና ጥያቄ ነው። ስለዚህ አንድ ድርጅት ወይም ግለሰቦች መምረጥ እንችላለን ነገር ግን አንዲት እናት ሀገር ነው ያለችን ሌላ አማራጭ የለንም።

(የሳዑዲ ጉዳይ) የማለዳ ወግ …በጭካኔ እየተገዳደልን ፣ ወዴት እየሔድን ነው ? –ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

$
0
0

(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)

ከሳምንት በፊት እዚህ ጅዳ ሻረ ሄራ በሚባል አካባቢ የሃበሻን ዘር ያሳዘነ የግድያ ድርጊት መፈጸሙን ሰማሁ ። ትውውቅ ባይኖረንም በአይን የማውቀው ወንድም አብዱ ሁሴን ይማም በጭካኔ መገደሉን የሰማሁት ድርጊቱ በተፈጸመ ከሰአታት በኋላ ከአንድ ወዳጀ በኩል በደረሰኝ የስልክ መልዕክት ነበር። በቀጣይ ቀናት ወጣቱ አብዱ የተቀጠፈበትን የጭካኔ ድርጊት የሚያወግዙ በርካታ መልዕክቶች ማስተናገድ ጀመርኩ። በመካከላችን ባሉ ጥቂት የሰው አውሬዎች እየሆነ ያለው እና ስማችን የመክፋቱ ነገር ያሳሰባቸው በርካታ ወገኖች በግድያው ማዘናቸውን በመግለጽ በርካታ መልዕክቶችን ልከውልኛል። በጭካኔ ተፈጸመ የተባለው ድርጊት ዘልቆ ነፍሱን አስጨንቆ ያሳዘነው አንድ ወንድም የላከልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል ….

” ጩኸት ሰሚ ሲያጣ እንዴት ያናዳል … ሀበሻ የድሮወቹ የሉም … ወድ የሆነውን የሰውን ደም በከንቱ የሚጠጡ እርኩስ መንፈስ የተጠናውታቸው ውሾች ናቸው .so ሰሞኑን በ ጅዳ አካባቢ ሸር ሄራ አካባቢ የተደረገውን ግፍ ልንገርክ …በሀበሾች ጭካኔ የተገደለውን ልጅ በአካል አውቀዋለሁ አብዱ ሁሴን ይማም ይባላል … በሳንጃ ገደሉት ! ልብ በል … የሳውድ መንግስት ታዲያ እንዴት አያሳድደን ! እንደነዚህ አይነት እርኩሶች እያሉ እኛ ቤተሰብ እንዴት እንርዳ? ልጅስ እንዴት እናስተምር? ..ነብዩ ሰው እንዴት …የሰውን ነፍስ ያጠፋል? ደግሞም ሳውዲ ውስጥ ? ከተሰራ ለሚገኝ ገንዘብ እጅግ ያሳዝናል ይጎመዝዛል ! ጌታ እውነቱን ይፍረድ ለሀበሻ ጩኸት በቃኝ እኔም ሀበሻ ነኝ!!! ” ይላል !

ሰሞኑን “ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊ ላይ በግፍ የግድያ ወንጀል ተፈጸመ !” የሚለው ወሬ ከጓዳ እስከ አደባባይ ሲናኝ አስከፊውን ሂደት የታዘቡ ወገኖች ኢትዮጵያውያን ብቻ አልነበሩም። ጉዳዩን በቅርብ ከሚያውቁና ከሚከታተሉ የሃገሩ ሰዎችም መልዕክቶችና አስተያየቶች ደርሰውኝ በሃፍረትም ቢሆን ለማስተናገድ ተገድጀም ነበር … የሟችን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተሉ ፣ ኢትዮጵያን የሚወዱና ስለኢትዮጵያ የሚጽፉ ፣ አንድ ከፍ ያለ ሃላፊነት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያና ሃያሲ የሃገሩ ሰው አዝነውብን አግኝቻቸዋለሁ ። በቁም ነገር በቢሯች አስጠርተው ያሉኝ እንዲህ ነበር ” ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ምንድ ነው እንዲህ የመሰለ የዘቀጠ በሃበሾች ያልተለመደ ጉዳይ ተደጋገመሳ ? ሀበሾች ምን ገባባችሁ? ከአመታት በፊት በሪያድ መንፉሃ ፣ ከወራት በፊት በመዲና በአብሃ እና በዙሪያው ያን ሰሞን ደግሞ በኪሎ ተማንያ እና በዙሪያው በሃበሾች መካከል መጨካከን የተሞላበት ድርጊት ታይቷል። ከሁሉም የሚያሳዝነው የግድያ ምክንያቶቹ ጊዜያዊ ጸብን ፣ ጥቅምንና ጥቃቅን የሰው ህይዎትን በጭካኔ ሊያስጠፉ የማይገባቸው ምክንያቶች ናቸው ። ግን ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ወደ የትስ እየተኬደ ነው? ” ሲሉ በጥያቄ ላፋጠጡኝ ሳውዲ ወዳጀ የሚሆን መልስ ግን አልነበረኝም ! ብቻ የሆነው አሳዝኖ ፣ አሳፍሮ አንገቴን አሰበረኝ …

እርግጥ ነው ፣ ባሳለፍናቸው አመታት በሪያድ መንፉአ አካባቢ አልፎ አልፎም በኢትዮጵያውያኑ መካከል በሚፈጠር ግጭት ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ዜጎች በሰላ ጩቤ አሰቃቂ ጥቃት ተፈጽሞባቸው የመቁሰልና የመገደል አደጋ ምክንያት እንደ ነበር የአይን እማኞች አጫውተውኝ ነበር ። በጩቤ ለመወጋጋቱ ዋንኛ ምክንያትም ደግሞ ተራ ከገንዘብና ከሴት ጋር የተያያዙ እዚህ ግቡ የማይባሉ መሆናቸው ማጤንና መገንዘብ ደግሞ በእጅጉ ያሳዝናል …በቀደሙት ጥቂት አመታት በሳውዲና የመን ድንበር ከተሞች ይህ መሰሉ ወንጀል የከፋ እንደ ነበር አውቃለሁ። በተለይም በጀዛን ፣ በአብሃና በከሚስ ምሽት በሚባሉ አካባቢዎች በዙሪያው ባሉ የከተማና የገጠር ከተሞች በከተሙ ኢትዮጵያውያን መካከል ተፈጸሞ የምንሰማው ግድያ ፍጹም ጭካኔ ያልተለየው መሆኑ ይጠቀሳል ! ወደ አብሃና ከሚስ ምሸት ለስራ ባቀናሁባቸው ቀናት በእኛ ዙሪያ እየሆነ ያለውን ለመስማት የከበደ መረጃ በእጀ መድረሱን አስታውሳለሁ። በህገ ወጥ መንገድ ዜጎቻችን ከየመን ሳውዲ በሚያመላልሱ ለገንዘብ በገንዘብ እየሸጡ የሚተዳደሩ ደላሎችና አቀባባዮች በጎሳ ተቧድነውና ብሔርን ለይተው የሚከሰተውን ግጭት ከጩቤ ያለፈ እንደ ነበርም በቦታው ተገኝቸ ታዝቤያለሁ። በተለይም በአብሃ አካባቢ በግጭቱ ስለተቀጠፈው ህይዎት ፣ ፍርድን ይጠባበቁ ስለነበሩ የእኛ ገዳዮችም የፍርድ ሂደት በቅርብ እከታተል ነበር ። ከሁሉም የሚያሳዝነው የሰውን ልጅ ያህል ታላቅ ፍጡር በስለት የሚጠፋበትን ምክንያት መስማት እንደ ነበርም ትዝ ይለኛል። ከሃገር ቤት ያለ የዘር ፣ የግል ጥላቻና ጸብን መሰረት ያደረገው የደም መቃባት ፣ በገንዘብ መካካድ ” ጓደኛየን ነጠቀኝ!” ፣ “የሰማንያ ሚስቴን ደፈረ !”፣ በሚሉትና በመሳሰሉት ክሶች የሚያጠነጥነው ብቀላ በፍትህ ሳይሆን በጭካኔ ለመወጣት የሚፈጸም ያረጀ ያፈጀ ይትበሃል ሳውዲ ተከትሎን መጥቶ ስማችን ማርከሱ ደግሞ ከሁሉም በላይ ያማል!

በያዝነው አመት ከጅዳ በ400 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው በሙስሊማን ቅዱስ ከተማ በመዲናም በዜጎቻች መካከል በተፈጠረ የቨዛ ሽያጭ እና ተጓዳኝ የገንዘብ መካካድ ያስከተለው አምባጓሮ በቅዱሷ ከተማ ቅዱስ የማይባል ግድያ ለመፈጸሙ ምክንያት ነበር ። ይህም የጭካኔ ወንጀል የተፈጸመበት ኢትዮጵያዊ ፣ ወንጀል ፈጻሚው ኢትዮጵያዊው መሆኑ ደግሞ ጉድ አሰኝቶ አሳፍሮን አልፏል። ከወራት በፊትም እዚሁ ጅዳ በተለያዩ አካባቢዎች በኢትዮጵያውያን መካከል የተነሱ አምባጓሮዎች በተመሳሳይ ጭካኔ በተሞላባቸው የግድያ ድርጊቶች የተከበቡ ወንጀሎች ምክንያት ነበሩ ማለት ይቻላል። እናም ጉዳዩ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል ….

ባሳለፍነው ሳምንት በጭካኔ የተገደለው ወንድም ወንጀል ተጠርጣሪ ፣ ተጠያቂ የቅርብ ጓደኛ ወዳጁ እንደነበረና ከቀናት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ሰማን ! አብዱ በማጣታቸው ትልቁ የሃዘን መርግ የወደቀባቸው፣ የሚይዙት የሚጨብጡ ያጡት ፣ ቤታቸው የጨለመባቸው አንዲት ሴት ልጂና የስድስት ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱ ሃዘን የከበደ ነው…ስለአብዱን ቅንነት፣ ሰው አማኝ ፣ ትጉህና ታታሪነቱን የሚመሰክሩት ባልንጀሮቹም ሃዘናቸው መሪር ያደረገው የተፈጸመው የጭካኔ ወንጀል ብቻ ሳይሆን የወንጀሉ ቀዳሚ ተጠርጣሪ የቅርብ ወዳኛ መሆኑ ነበር ። በዚህም ሊያምኑት በከበደ ድርጊት እርር ድብን ብለው አዝነዋል! ዛሬ የማይሰማ የማያየን አብዱ ሁሴን በሰላሳዎቹ የእድሜ ክልል ይገኝ እንደነበር በቅርብ ጓኞቹ ጨምረው አጫውተውኛል ። የወንድም አብዱ ሁሴን ይማም የቀብር ስነ-ስርዓት ትናንት የካቲት 12 / 2006 ረቡዕ ከቀትር በኋላ በጅዳ ከተማ ተፈጽሟል ! አብዱ የሔደው ሁላችንም ወደ ማንቀርበት የላይኛው ቤት ነው ! ነፍሱን ይማረው ! ” አላህ ይርሃሙ !”

ወንጀሉን በትኩሱ ለማቅረብ በፖሊስ ክትትክ መሆኑና ተጠርጣሪ ወንጀለኛው ባለመያዙ የማለዳ ወጌን እንዳዘገየው ቢያስገድደኝም መረጃውን ባሳለፍናቸው ቀናት ከበርካታ ነዋሪዎች አስተያየቶችን ለመሰብሰብ ሞክሬ ነበር ። በዚህ መሰል ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ዙሪያ እየተነጋገረ የሚገኘውን አብዛኛው የጅዳ ነዋሪ ” ህጋዊ ህገ ወጥ ” ነገን ምን ይከተል ይሆን እያለ በጭንቀት በሰቀቀን እየጠበቀ ባለበት ሰአት የዚህ መሰሉ ድርጊት መፈጸም ” እንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ !” ሆኖበት ተመልክቻለሁ! ለእኔም የሆነብኝ እንዲያ ነው …

ድርጊቱ አሳዝኖኝ ለማውገዝ ያነሳሁት ብዕር መቋጫ የሚሆነው ሳውዲው ሃያሲ ወዳጄ ያጫወቱኝን ዘልቆ የሚሰማ ያልመለስኩት ጥያቄ ነው ። ሃያሲው ሃበሾች በዚህ መሰል ድርጊት እንደማንታወቅ ተንትነው ከቅርብ አመታት የሰበሰቧቸው መረጃዎች ቢያሳስቧቸው ቆጣ ብለው በንዴት ሲያጠይቁ “ግን ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ወደ የትስ እየተኬደ ነው? ” ነበር ያሉኝ …እኔም ተጠርተን የማናውቅበት ወንጀል ሲደጋገም አሞኛልና ድርጊቱን አወግዘዋለሁ! ወደ መጨረሻም አሳፍሮ መልስ ያጣሁለትን የሃያሲውን ወዳጀ ጥያቄ ላጠይቅ ግድ አለኝ … ግንስ … በጭካኔ እየተገዳደልን ፣ እየተጠላላን ወዴት እየሔድን ነው ? ምንድን ነው እየሆነ ያለው?
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ

መኢአድ እና አንድነት ለባህርዳሩ ሰልፍ በአደባባይ እየቀሰቀሱ ነው፤ ቀስቃሾች በፖሊስ ታግተዋል

$
0
0


(updated) የፊታችን እሁድ በባህርዳር መኢአድ እና አንድነት በጋራ የፊታችን እሁድ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ሕዝብ ወጥቶ ድምጹን እንዲያሰማ ለመቀስቀስ ዛሬ በባህር ዳር አደባባዮች መኪና እና በትልቅ የድምጽ ማጉያ ሲቀሰቅሱ የዋሉ የድርጅቱ አባላት በፖሊስ ወከባ ሲደርስባቸው፤ ሲታሰሩ መዋላቸውን የድርጅቶቹ ቃል አቀባዮች ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ አመልክተዋል።

abugida“ብአዴን አማራውን የመምራት ብቃት የለውም” በሚል መፍክር እያሰሙ ሲቀሰቅሱ የዋሉ የሁለቱ የተቃዋሚ ድርጅቶች አባላት በፖሊስ ታግተው ቅስቀሳውን እንዳያደርጉ ቢስተጓጎልም፤ በፖስተር፣ በበራሪ ወረቀት፣ በስልክ ቴክስት፣ በፌስቡክ፣ በትዊተርና በኢሜሎች በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳዎችን የባህርዳር ሕዝብ በንቃት እየተከታተለ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ ትግል አማራጫችን ነው፤ አንድም ጥይት ሳይተኮስ ኢሕአዴግን ለማውረድ እንታገላለን የሚሉት አንድነት እና መኢአድ እሁድ በባህርዳር የጠሩት የሰላማዊ ሰልፍ አገዛዙን እጅግ እንዳስነገጠው ከሚወስዳቸው እርምጃዎች መረዳት ይቻላል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

በተጨማሪም፡
ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በባህርዳሩ ሰልፍ ቀስቃሾችና በእሁዱ ሰልፍ ዙሪያ የሚከተለውን ዘግቧል።
የፊታችን እሁድ አንድነትና መኢአድ ለሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ የቅስቀሳ ስራ በመስራት ላይ የነበሩት ወጣቶች በፖሊስ ተወስደው ከክልሉ አስተዳደር የተጻፈ ወረቀት እንደቅድመ ሁኔታ ተቀብለው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል፡፡ወጣቶቹ ግን ቅድመ ሁኔታውን አንቀበልም በማለት በህጋዊ መንገድ በአሁኑ ሰዓት በመከራከር ላይ ይገኛሉ፡፡

ቅድመ ሁኔታው ‹‹ባስገባችሁት የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ ቅስቀሳ የምናደርገው በባህርዳርና አካባቢዋ ለሚገኝ ህዝብ ነው ብላችኋል፡፡በደፈናው ባህር ዳር አላችሁ እንጂ የየትኛው ቀበሌ፣ወረዳና ሰፈር ህዝብን እንደምትቀሰቅሱ አልጠቀሳችሁም ከዚህ ባሻገር የአቅራቢያው ህዝብ የትኛው እንደሆነ አላብራራችሁም ስለዚህ ቀበሌዎቹን፣ወረዳዎቹን፣ሰፈሮቹንና አካባቢውን በመዘርዘር በድጋሚ ደብዳቤ እንድታስገቡ ››የሚል ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንመለሳለን።

ለባህርዳሩ ሰልፍ አንድነት እና መኢአድ በዩቲዩብ የለቀቁት ማስታወቂያም የሚከተለው መልክ አለው።

ከአውሮፕላኑ ጠለፋ በኋላ የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች – (ዜና ትንታኔ)

$
0
0

ethio airlines
ምኒልክ ሳልሳዊ እንዳጠናቀረው

የኢትዮጵያ አየር መንገድን አስተድደራዊ ብልሹነት እና የዘረኝነት አድልዎን ያማከለ የኢትዮጵያን እና የአማራን ጉዳይ ያካተተ አንገብጋቢ አጀንዳዎች ይዞ እንዲሁም በግሉ ከጀርባው አልወርድ ያሉትን የወያነ ቅማሎች ደህንነቱን የሚያበረውን አውሮፕላን በመጥለፍ አሊያም በማገት በሰላም ጀነቭ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን የተመለከቱ ዘገባዎች መውጣታቸውን እንደቀጠሉ ነው።

በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ድጋፍ የተቸውረው ይህንን የጠለፋ /እገታ ጉዳይ በተመለከተ የወያነው መንግስት ለውጥ የሚያደርግበት እና ለፖሊሲዎቹ አፋጣኝ አትኩሮት ሊሰጥ ይገባዋል ከሚሉ የስር አቱ ደጋፊዎች ጀምሮ እስከ የሃገሪቷን የሰብ ኣዊ መብት ጥሰቶች እያነሱ የፖለቲካው ምህዳር ጥበቱን በዘረኝነት ልይ የተመረኮዘን የኢኮኖሚ ብዝበዛውን እና የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ ጎን ያገለለውን ስር ኣት ማስረጃ እያጣቀሱ በመተቸት ጠላፊውን የደገፉ እንዲሁም በተሰቡን ጨምሮ ጀግና እስከማለት የደረሱበት ሁነታ ተከስቷል።

እስካሁን ድረስ ጠላፊውን በተመለከተ ምንም አይነት ዝርዝር ጉዳዮችን ያልተናገረው የስዊዘርላንድ ፖሊስ አይሮፕላኑ በተጠለፈበት ሰኞ የወጡ ዘገባዎች እንደሚይመለክቱት ረዳት አብራሪው የደህንነት ስጋቶች እንዳሉበት እና በሃገሪቱን ያለው ስር ኣት የሚከተላቸው የዘረኝነት አስተዳደር እና የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት እንዲሁም የአየር መንገዱ የአስተዳደር ብልሹነት የፈጠሩት እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው።

የወያነ ስር ኣት የቅርብ ሰዎች የረዳት አብራሪውን ስም እና የበተሰቡን ስም ጥላሸት ከመቀባት ጀምሮ ጉድዩን ወደ ዘረኝነት የወሰዱትም ጠባቦች ሲኖሩ ወደ ወያነ ጠጋ ብለው ለመኖር የፈለጉም ሃይለመድህንን አብጠልጥለዋል ሆኖም አንዳቸውም አልተሳካላቸውም።….

ጉዳዩን በቅርብ እየተከትተለ ያለው የኢሳት ተለቭዥን በተሰቦቹን ወዳጆቹን ጓደኞቹን እና የአየር መንገድ ሰዎቹን በማነጋገር ሰፊ ጊዘውን ሰቷል። ያነጋገራቸው የበተሰቡ አባላት ሃይለመድህንን በመደገፍ የሃገር ጉዳይ የሚያንገበግበው ጀግና ሲሉት ወዳጆች እና ጓደኞቹ የሃይለመድህንን መልካምነት በይፋ መስክረዋል። እንዲሁም የአየር መንገዱ ሰራተኞች የሃይለመድህንን ታታሪነት እና ጸባየ ሸጋነት አረጋግጠዋል።

እንዲሁም ቢቢኤን ራዲኦ ኢትዮጵያውያን በአውሮፓ ጠበቃ እንዳቆሙረት በፕሮግራሙ ላይ ዘግቧል። የጠለፋውን ሁነታ ተከትሎ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ ደህንነት ስራ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገለውና በክትትልና ደህንነት ስጋት ከአመት በፊት ድርጅቱን ለቆ በስዊዘርላንድ ጥገኝነት የጠየቀው ሚካኤል መላኩ ከኢሳት ጋር ባደረገው ሰፊ ቃለምልልስ፣ በድርጅቱ ውስጥ ያለውን ዘረኝነትና የአስተዳደር መበላሸት አጋልጧል።

ወጣቱ ፓይለት የተለያዩ አውሮፕላኖችን አብርሮ ልምድ ካካበተ በሁዋላ 767 የተባለውን አውሮፕላን በረዳት ፓይለትነት ለማብረር መቻሉን የገለጸው ሚካኤል፣ በዚህ ደረጃውም ከፍተኛ የሆነ ክፍያ የሚከፈለው በመሆኑ የገንዘብና የምቾት ችግር እንደማያጋጥመው ገልጿል። አብራሪው የ3 ሺ ሰራተኞችን ዋይታ ይዞ መምጣቱን የሚናገረው ሚካኤል፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎኑ ሊቆምለት ይገባል ብሎአል

የካፒቴን ሃይለመድህን የጠላፋ ምክንያት አወዛጋቢ ሆኖ በቀጠለበት ሁኔታ ፣ ካፒቴኑ ከአጎቱ ከዶ/ር እምሩ ስዩም ሞት ጋር በተያያዘ እየተረበሸ መምጣቱን አቶ አሳምነው መላኩ የተባሉ የካፒቴን ሃይለመድህንን አጎት በመጥቀስ በአሶሺየትድ ፕሬስና በክርስቲያን ሞኒተሪንግ ተዘግቧል። አዲስ አበባ የኑቨርስቲ በድረገጹ ባሰፈረው መረጃም የዶ/ር እምሩ አሟሟት መንስኤ እንግዳ እንደሆነ ጠቅሷል። ኢሳት በበኩሉ ከዘመዶቹ ባገኘው መረጃ መሰረት ዶ/ር እምሩ በሰዎች መገደላቸውን አንዳንድ የቤተሰብ አባሎች እንደሚያምኑና አጎቱን ማን ገደላቸው የሚለው ጥያቄ አለመመለሱን ዘግቧል።

ይሁን እንጅ የዶ/ር ስዩም ባለቤት ነኝ ያሉ ወ/ሮ አንጓች ቢተው ባለቤታቸው የሞቱት ታህሳስ ወር ላይ ጧት ፍላሚንጎ አካባቢ ተሳፍረው ቤተመንግስት አካባቢ ሲደርሱ ከጠዋቱ 2፡30 ላይ መሞታቸውን፣ የሞታቸውም ምክንያት በልብ ህመም ምክንያት መሆኑን በመግለጽ ሰው ገደለው ተብሎ የቀረበው ዘገባ ስህተት መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል። ወ/ሮ አንጓች ካፒቴን ሃይለመድህን በአጎቱ ምክንያት እንደተረበሸ ተደርጎ በሚሰጠውን አስተያየት ዙሪያም ምንም የሚያዉቁት ነገር እንደሌለ፣ ከካፒቴኑ ጋር በአመት በአል ወቅት ካልሆነ ብዙም እንደማይገናኙ ተናግረዋል።

ካፒቴን ሃይለመድህን ከአጎቱ ሞት ጋር በተያያዘ ይረበሽ ነበር በማለት መግለጫ የሰጡትን ሌላውን አጎት አቶ አሳምነውን ለማግኘትና ማብራሪያ ለመጠየቅ የተደረገው ሙከራ አልተሰካም። በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየቱን የጠየቅነው ዘጋቢያችን፣ ዶ/ር ስዩም በልብ ህመም መሞታቸውን ካፒቴን ሃይለመድህን የሚያውቅ ከሆነ፣ የሚጨነቅበት ምክንያት አይኖርም፣ ከአጎቱ ሞት ጋር በተያያዘ የሚሰጠው አስተያየትም ትክክል ላይሆን ይችላል ብሎአል።

ጠላፊው አውሮፕላኑን ወደ ጄኔቭ ከመውሰዱ በፊት ሮም ላይ ማረፉን የገለጸቸውን ዜና በተመለከተ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች አውሮፕላኑ ሮም ላይ እንዳላረፈ በመግለጽ አስተያየታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ኢሳት በድጋሜ ተሳፋሪዋን ባነጋገረበት ወቅት፣ በአቋሟ በመጽናት አውሮፕላኑ ሮም ላይ አርፎ ወደ ሚላን ሲያቀና መጠለፉን፣ የበረራ ትኬቱዋን ለኢሳት በመላክ ትክክለኛ መረጃ መስጠቱዋን በድጋሜ ተናግራለች።

ጉዳዩ እንዴት ሊሆን ይችላል ስንል ጥያቄ ያቀረብንለት ሚካኤል መላኩ አውሮፕላኑ ሮም ላይ አርፎአል በሚል የተላለፈው ዘገባ ትክክለኛ ነው ብሎ እንደሚያምን የአየር መንገዱን አሰራር በመግለጽ አስረድቷል
የመንግስት የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን አውሮፕላኑ ካርቱም ላይ ማረፉን ፣ ቀጥሎ ደግሞ ካርቱም ላይ ማረፍ የነበረበት ቢሆንም ተጠልፎ ማረፍ ሳይችል ቀረ ብለው የገለጹት የአየር መንገዱን አሰራር ሳይዉቁ የተናገሩት አሳፋሪ ንግግር ነው ብለዋል። በአየር መንገድ የበረራ ታሪክ አውሮፕላኑ በቀጥታ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም እንደሚያርፍ በመግለጽ ካርቱም ላይ ማረፍ ነበረበት የሚለውም ትክክል አይደለም ብሎአል።

አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ፓይለቱ አውሮፕላኑን ይዞ ጄኔቫ ላይ በመሽከርከር ለማስፈራራት ሙከራ አድርጎ ነበር በማለት ዘገባዎችን አቅርበዋል። ይሁን እንጅ እንደ ሚካኤል ገለጻ ማንኛውም አውሮፕላን ከማረፉ በፊት ነዳጅ ማቃጠል ስለነበረበት ፓይለቱ ይህን ማድረጉን እንዲሁም ለ10 ደቂቃ ጉዞ ብቻ የሚበቃ ነዳጅ ነበረው ተብሎ በመገናኛ ብዙሃን የቀረበውም ትክክል ያልሆነና በአየር መንገዱ ህግ መሰረት ለ2 ሰአት በረራ የሚያበቃ መጠባበቂያ ነዳጅ እንደሚይዝ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ “የረዳት አብራሪው አኩሪ ገድል የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃ እስኪወጣ ይቀጥላል”አለ

$
0
0

ethio airlines
“የወጣት ሃይለመድህን አበራ አኩሪ ገድል የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነትእውን እስኪሆን ድረስ ይቀጥላል” ሲል የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ንቅናቄው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ ለአለም ህብረተሰብ ያስተጋባው መልዕክት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድምፅን ነውና፤ አላማና ተግባሩም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ምኞትና ፍላጎት መሆኑን በፅኑ ያምናል” ብሏል። በተጫምሪም አኩሪ ተግባር ፈጽሟል ላለው ለረዳት አብራሪው የንቅናቄው የክብር አባል እንዲሆን የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡ ሙሉ መግለጫው ከምስክር ወረቀቱ በታች እንደወረደ እንደሚከተለው ተስተናግዷል።

honoray memebership

“የወያኔ/ኢህአዴግ ጨቋኝ ሥርዓት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ቁጥር ስፍር የሌላቸው አፋኝ ህጎችን በመጫን፤ እንዳሻው ንጹሃን ዜጎችን መጥፎ ስም በመስጠት፤ ባልሰሩት ሃጥያትና በተፈበረከ የሃሰት ወያኔያዊ ውንጀላ በየእስር ቤቱ እንዲማቅቁ እያደረገ መሆኑ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ግልጽ ነው። ይህ አፋኝ ሥርዓት የምንወዳት ሃገራችን ኢትዮጵያንና ህዝቧን የማጥፋት እኩይ አላማ ሰንቆ፤ ምሁራን ዜጎች ለሚወዷት ሃገራቸውና ለሚሳሱለት ህዝባቸው የበኩላቸውን ማበርከት እንዳይችሉ፤ በተለይ ወጣት ምሁራን በሃገራቸው ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ተሳተፊ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ግድያ፣ እንግልት፣ ጭቆና፣ በደልና፣ ወከባ እያደረገ ይገኛል።

EYNM New Logoይህ ፋሽስት ሥርዓት በዘረጋው አፋኝ መዋቅር ህዝብ እርስ በርሱ በጥርጣሬ እንዲኖር፤ ቤተሰብ ከቤተሰብ እንዳይተማመን፤ አንዱ ብሄር በሌላው ብሄር ላይ ጥላቻ እንዲኖረውና፤ አንዱ ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት ጋር በፍቅር፣ በመተሳሰብና፣ በመቻቻል እንዳይኖር፤ ባጠቃላይ በሃገሪቷ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር፤ ብሎም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከምድረገጽ ፈፅሞ ለማጥፋት፤ ያልፈነቀለው ድንጋይ ባይኖርም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ያስተሳሰረው የፍቅርና አብሮ የመኖር አኩሪ ባህሉ ነውና፤ የወያኔ/ኢህአዴግ እልቆ መሳፍርት መሰሪ ተንኮልና ደባ ሳያንበረክከው፤ ሥርዓቱ በወጠነው መንገድ ሳይሆን በፍቅር፣ በመተሳሰብና፣ በመቻቻል አንድነቱን ጠብቆ አሁን ድረስ መዝለቅ ችሏል።

የታፈነ ጭስ መውጫ አያጣም ነውና፤ ታጋሽና ሰላም ወዳድ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ጭቆናውና በደሉ ከልክ በላይ ስለሆነበት፤ እየደረሰበት የሚገኘውን ቅጥ ያጣ ግፍ በተለያዩ አያሌ መንገዶች ሲገልጽ ቆይቷል። በየካቲት 10, 2006 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪ በሆነው ወጣት ሃይለመድህን አበራ የተፈጸመው አኩሪ ተግባር ይህንኑ የስርዓቱን አስከፊ ገጽታና በህዝብ ላይ የሚደርሰዉን ግፍ፣ ወከባ፣ እንግልት፣ እስራት፣ ግድያና፣ ሰቆቃ የሚያረጋግጥ አይነተኛ ክስተት ነው። ወጣት ሃይለመድህን አበራ በሥርዓቱ እየደረሰበት የነበረዉን አስከፊ በደል ለማምለጥ በግሉ በርካታ መንገዶች ነበሩት። የአውሮፕላን አብራሪ በመሆኑ አለም ላይ ካሉ ሃገራት ሁሉ በሚፈልግበት የመሄድና የመኖር እድሉ በእጁ ነበር። በኢኮኖሚም ቢሆን በሃገሪቱ ከፍተኛ ክፍያ ከሚያገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች አንዱ በመሆኑ በግል ኑሮው ተንደላቆ የመኖር ችሎታው እንደነበረው ለማንም አጠራጣሪ አይሆንም።

ነገር ግን ወጣት ሃይለመድህን አበራ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁስል ስላመመው፤ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል የሱም እንደሆነ ቀድሞ ስለተረዳ፤ ህልሙ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት እውን ሆኖ፤ መብቱ ተከብሮለት፤ በሃገሩ የመኖር ተስፋን አንግቦ፤ በፍቅር፣ በሰላምና፣ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ሲኖር ማየት በመሆኑ፤ በዙሪያው የጨበጠው እድል ሳያጓጓውና ወጣትነት ሳያታልለው፤ በማስተዋል ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት እጅግ ከፍተኛ መሥዕዋትነትንና ጀግንነትን በተግባር ፈጽሟል።

የወጣት ሃይለመድህን አበራ ታላቅ ተግባር የወያኔ/ኢህአዴግ ከልክ ያለፈ ግፍንና የኢትዮጵያ ህዝብን የታፈነ ሰቆቃ ለአለም ህዝብ በይፋ ከማጋለጡም ባለፈ፤ በኢትዮጲያችን እጅግ ብዙ እሱን መሰል ጀግና ወጣቶች ያለጥርጥር እንደሚገኙና፤ በኢትዮጵያ ነፃነት፣ ፍትህና፣ እኩልነት በአስተማማኝ ሁኔታ እውን እስኪሆን ድረስ፤ ህዝብ ለነፃነቱ ምንግዜም እንደማይተኛ ያረጋገጠ ብሄራዊ የጀግንነት ተግባር ነው። በመሆኑም ወጣት ሃይለመድህን አበራ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት የፈፀመው አኩሪ ተግባርና የከፈለው ታላቅ መሥዕዋትነት በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ለዘላለም ሲታወስ እንደሚኖር ጥርጥር የለንም። ነገር ግን በዚህ ውድ ኢትዮጵያዊ ጀግና የተከፈለው ታላቅ መሥዕዋትነት በኢትዮጵያ ሰላም፣ ፍትህ፣ እኩልነትና፣ ተስፋ እንዲመጣ በቁርጠኝነት የታቀደ በመሆኑ፤ ውጥኑ ለታለመለት አላማ ግቡን እንዲመታ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ እድሜ፣ ሃይማኖት፣ ብሄር፣ ወይንም ሌላ ማንኛውም ልዩነቱ ሳይገድበው፤ ለጋራ ነፃነቱ በጋራ በመነሳት አንድነቱን ለአለም ማሳየትና የዚህን ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ጀግንነት ማስተጋባት ይኖርበታል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ ወጣት ሃይለመድህን አበራ ለአለም ህብረተሰብ ያስተጋባው መልዕክት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድምፅን ነውና፤ አላማና ተግባሩም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ምኞትና ፍላጎት መሆኑን በፅኑ ያምናል። ስለሆነም ንቅናቄያችን በአለም ዙሪያ የሚገኙ አባላቶቹን ሙሉ በሙሉ በማስተባበር፤ የወጣት ሃይለመድህን አበራን ድምፅ መልሶ በማስተጋባት፤ አንድነቱን ለአለማቀፉ ህብረተሰብና ለአለም መንግስታት፣ እንዲሁም ለሚመለከታቸው አለማቀፋዊ ተቋማት በሙሉ በማስመስከር፤ እውነታዉን ለማሳወቅ የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎችን፣ ዲፕሎማሲያዊ ሂደቶችንና፣ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን በማከናወን፤ ግንባር ቀደም ሚና እንደሚጫወት ከወዲሁ እያስታወቀ፤ ወጣት ሃይለመድህን አበራ ለኢትዮጵያውያን የነፃነት ትግል ላበረከተው ታላቅ አስተዋዕፅዎ ብሄራዊ ጀግና ሲል መሰየሙን ለኢትዮጵያ ህዝብ በታላቅ ኩራት እያበሰረ፤ የብሄራዊ ጀግና የክብር የምስክር ወረቀት በአድናቆት ያበረክታል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ በዚህ ዘረኛ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ከልክ ያለፈ ጭቆና፣ ረገጣና፣ እንግልት ሠለባ ሆኖ በመሰቃየት ላይ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ ተቆርቋሪ ለሆናችሁና በምንወዳት ሃገራችን ሰላም፣ ነፃነት፣ ፍትህ፣ ተስፋ እንዲሰፍንና ለህዝብ የሚበጅ ቀና ለውጥ ለዘለቄታው ይሰፍን ዘንድ ለምትመኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ፤ እንዲሁም ለተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ለሃይማኖት ተቋማትና፣ ለሲቪክ ማህበራት ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነትና የህዝብ አደራ በጫንቃችሁ እንደተሸከማችሁ በመገንዘብ፤ ልዩነታችሁን ወደ ጎን በመተው ለዚህ ወሳኝ ህዝባዊ ጥሪ በአንድነት ምላሽ በመስጠት የሚጠበቅባችሁን ህዝባዊ አደራ እንድትወጡ ዘንድ በጥብቅ እያሳሰበ፤ ሃገራዊ የመተባበር ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ


ከድልድይ ላይ ራሷን በመወርወር ለመግደል ስትሞክር የነበረችው ወጣት ማን ትሆን?

$
0
0

ከዳዊት ሰለሞን

በርብርብ የተረፈችው ወጣት

ትናንት ከሰዓት አካባቢ አራት ኪሎ ለመንገደኞች መሸጋገሪያ ተብሎ በተሰራ ድልድይ ላይ የወጣች በሃያዎቹ መጨረሻ አካባቢ የምትገመት ሴት ራሷን ወደ መኪና መንገዱ ለመወርወር በምትዘጋጅበት ወቅት በአካባቢው የተገኙ ሰዎች ባደረጉት ርብርብ አደጋ ሳይደርስባት ለመትረፍ በቅታለች፡፡
ወጣቷን ለማትረፍ ሁለት የእሳት አደጋ መኪኖች ብዛት ያላቸው ፖሊሶች በስፍራው ተገኝተው የነበሩ ቢሆንም ወጣቷ ‹‹ሙስሊሞችን እወዳለሁ እነርሱን ጥሩልኝ››በማለቷ ሁለት ሙስሊም የሆኑ ሴቶች ቀርበው አነጋግረዋታል፡፡ በዚህ ቅጽበትም ሰዎች ቀርበዋት ይዘዋታል፡፡ ወጣቷን ለዚህ ውሳኔ ያበቃት ምን ይሆን?በቅርቡ ከሳኡዲ የተመለሰች ስደተኛ ትሆን? በስፍራው የነበሩ ሰዎች ይህን መሰል ጥያቄዎች እንድትመልስላቸው ይፈልጉ የነበረ ቢሆንም ፖሊሶች አጣድፈው ወስደዋታል፡፡የት አድርሰዋት ይሆን?

ከድልድይ ላይ ራሷን በመወርወር ለመግደል ስትሞክር የነበረችው ወጣት ማን ትሆን?

Sport: ሁለቱ የቸልሲ ምርጦች፦ ኤዲን ሃዛርድ እና ኔማኒያ ማቲች

$
0
0

eden-hazard-goal-hd-best-pic-chelsea
ኤዲን ሃዛርድ ኳሷን የግሉ አደረጋት፡፡ የቡድን ጓደኞቹም በላይዋ ላይ ፊርማቸውን አኖሩ፡፡ በኒውካስል ዩናይትድ ላይ ላስቆጠረው ሃትሪክ ማስታወሻ ትሆነዋለች፡፡ በመጀመሪያው ግማሽ ስምንት ደቂቃዎች ውስጥ ሁለቱን ጎሎች ካገባ በኋላ የሃትሪክ ምኞቱ እንዲሳካ የፍራንክ ላምፓርድ ተባባሪነት አስፈላጊው ነበር፡፡ እንግሊዛዊው ፍፁም ቅጣት ምቱን አሳልፎ ባይሰጠው ኖሮ ቤልጅየማዊው ኳሷን ለመውሰድ ባልበቃ ነበር፡፡ ላምፓርድን አመስግኖ ወደ መኖሪያ ቤቱ አመራ፡፡

ሃዛርድ በቤቱ አልጋ ላይ ተንጋሎ ከቼልሲ ጋር ፕሪሚየር ሊጉን በሻምፒዮንነት ስለመደምደም ያልማል፡፡ ይህንኑ ምኞቱን ለቼልሲ ኦፊሴላዊ ቴሌቪዥን ተናግሯል፡፡ ‹‹በሊጉ ሠንጠረዥ አናት ላይ ተቀምጠናል፡፡ ወደ አልጋዬ ስሄድ ሻምፒዮንነትን አስባለሁ፡፡ የውድድር ዘመኑ ሲጠናቀቅ ምኞቴ እውን ይሆናል ብዬ ተስፋ አለኝ›› በማለት በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ከፍተኛ ፉክክር የታየበትን የውድድር ዘመን በሰማያዊዎቹ የበላይነት እንዲጠናቀቅ ያለውን ህልም ይገልፃል፡፡

ለቼልሲ ሃዛርድ የጨዋታ ውበትን ያላብሳል፡፡ በሁለት እግሩ የሚጫወት፣ ሚዛኑን የጠበቀና የቡድኑን የማጥቃት እንቅስቃሴ ለመጀመር እይታን የታደለ ወጣት ነው፡፡ በማንችስተር ሲቲን በገዛ ሜዳው ባሸነፉበት ምሽት ሃዛርድ የጨዋታው ኮከብ ነበር፡፡ ለሲቲ ተከላካዮች አልጨበጥ ብሎ ለተደጋጋሚ ስጋት ሲዳርጋቸው አምሽቷል፡፡

በዕለቱ የቼልሲ የማጥቃት ቅመም ሃዛርድ ነበር ካልን የቤልጅየም ተጨዋች ተልዕኮ አመቺ የኋላ ደጀን በመሆን ጀርባውን ሲጠብቅ የነበረው ኔማኒያ ማቲች ነበር፡፡ በጨዋታው የማቲችን ያህል ሰፊ ርቀት የሸፈነ ተጫዋች በሜዳው ላይ አልነበረም፡፡ 12.6 ኪሎ ሜትር ባካለለው ብርታቱ የቼልሲን የመሀል ሜዳ ከሲቲ ጥቃት ሲከላከልና ኳስን ሲቀበል እና ሲሰጥ አምሽቷል፡፡ ሃዛርድ 1.72 ብቻ የሚረዝምና ለመሬት ቅርብ የሆነ ተክለሰውነቱ የባላጋራ ተከላካዮችን ሚዛን እያሳጣ ለማለፍ ያስችለዋል፡፡ ማቲች ደግሞ 1.94 ሜትር የሚለካውን ግዙፍ አካሉ የቼልሲ መሀል ሜዳ ጉልበትና የአየር ላይ ደጀን እንዲያገኝ አድርጎታል፡፡ የማያቋርጥ ታጋይነቱን በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ከ12 ኪሎ ሜትር የላቀ ርቀት በመሸፈን አረጋግጧል፡፡ ቁመቱ እንደ ያያ ቱሬ ፍጥነቱን አልገታውም፡፡ በሜዳው ዙሪያ ፈጣንነቱን አረጋግጧል፡፡ ጠንካራ ሸርተቴዎችን የሚወርድ ተጨዋች ቢሆንም ኳስን በእግሩ ስር ሲቆጣጠርም ምቾት ይሰማዋል፡፡ በተክለሰውነት፣ በአካል ብቃትና በቴክኒክ ተሰጥኦ የታደለውን ተጨዋች ጆዜ ሞውሪንሆ ወደ ቼልሲ ሲያስመጡት የተከፈለበት 21 ሚሊዮን ፓውንድ የጥርጣሬ ጥያቄዎችን አስከትሎባቸው ነበር፡፡ ቆፍጣናው ፖርቹጋላዊ አሁን ስለመሳሳታቸው የሚናገር እንዳይኖር አድርገዋል፡፡ የማቲች አገልግሎት ለተከፈለበት ገንዘብ ትክክለኛ ምላሽ መሆኑን የቼልሲ ደጋፊዎችም መስክረዋል፡፡ ቼልሲ ሁሉን ያሟላ ዘመናዊ አማካይ አግኝቷል፡፡

ሞውሪንሆ በማቲችና ሃዛርድ የወቅቱ ብቃት ፍፁም ደስተኛ ናቸው፡፡ ሃዛርድ ከፕሪሚየር ሊጉ ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ስለመሆኑ እየተነገረ ባለበት ሰዓት ጆዜ ግን ለአድናቆታቸው ንፅፅራቸውን ከእንግሊዝ ይልቅ በዓለም ደረጃ አሳድገውታል፡፡ ‹‹በዚህ ሰዓት ከሁሉም ወጣት ከዋክብት ተጨዋቾች ሁሉ ምርጡ ይመስለኛል፡፡ ከግዙፎቹ ጋር ላነፃፅረው አልፈልግም፡፡ ምክንያቱም ትልልቆቹ ተጨዋቾች የ10 ዓመታት ዋንጫዎችን የማሸነፍ እና ጎሎችን የማስቆጠር ታሪክ አላቸው፡፡ ስለዚህ ትልልቆቹንና ይህንን ልጅ በአንድ ሚዛን መመዘን አይገባም፡፡ እንደ ወጣት ተጫዋች ግን ከእርሱ የተሻለ መኖሩ አይታየኝም፡፡ ኔይማር ድንቅ ተጨዋች ቢሆንም በዘንድሮው የውድድር ዘመን ብቃቱ እየዋዠቀ ይገኛል፡፡ ይጎዳል፣ ይጫወታል፣ ይጎዳል፣ አይጫወትም…›› በማለት ሞውሪንሆ ለሃዛርድ ያላቸውን አድናቆት ገልፀውለታል፡፡

የቀድሞው የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዠርዥ ሊከንስ በበኩላቸው ሃዛርድ ከፕሪሚየር ሊጉም አልፎ በብራዚል የዓለም ዋንጫ ከክሪስቲያኖ ሮናልዶና ሊዮኔል ሜሲ ጥላ ውስጥ በኮከብነት ብቅ እንደሚል ተንብየዋል፡፡ ባለፈው ነሐሴ ሞውሪንሆ ተጫዋቹን ከወጣት ባለተሰጥኦነት ወደ ትልቅ ተጫዋች እንዲያድግ ምክር ለግሰውት ነበርር፡ በመላው 90 ደቂቃው በመከላከል ስራ ላይ እንዲሳተፍና ኳስም በእግሩ ስትገባም እንዳይሰስትበት ጥሪ አስተላልፈውለት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ከማንችስተር ሲቲ እና ከኒውካስል ጋር ሲጫወቱ ለጆዜ ጥሪ ትክክለኛውን ምላሽ ሰጥቷል፡፡
‹‹በሊል ሳለ ሃዛርድ የችሎታውን 70%-80% እየተጫወተ በፈረንሳይ ምርጡ ተጨዋች ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከችሎታው 100% በማበርከት ላይ ነው፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት ልምምዱን በቀላሉ የመመልከት ጥፋተኛነት ይሰነዘርበት ነበር፡፡ አሁን ግን በልምምድ ሰዓት ብዙ ይለፋል፡፡ ጆዜም የአድናቆት ደረጃቸውን ከፍ አድርገውለታል›› በማለት ሊከንስ ስለሀገራቸው ኢንተርናሽናል ተጨዋች መጎልበት ያስረዳሉ፡፡ ሸርተቴዎችንም እንዲወርድ ይጠብቁበታል፡፡
MATIC
በታክቲካዊም መስክ የሃዛርድ ጥቅም ይለያል፡፡ ቼልሲ ከሳሙኤል ኤቶ በስተጀርባ ሶስት የማጥቃት ባህሪይ ያላቸውን አማካዮችን ያሰልፋል፡፡ ሃዛርድ ወደ ጎን እየገባ ለጎል ከመምታቱም በተጨማሪ ከዊልያንና አስካር ጋር በነፃነት ቦታ እየተቀያየረ ይጫወታል፡፡ ከኒውካስል ጋር ኳስ ባገኘ ቁጥር የተጋጣሚ ተለካካዮች ላይ አደጋ ይፈጥር ነበር፡፡ በዚሁ እንቅስቃሴ ወደ ቀኝ ሲወጣ ክሮሶችን ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ይጥላል፡፡ በመሀል ሲገኝ ደግሞ ለፈጠራው የሚያመች ክፍተት ያገኛል፡፡
ማቲች ከጥቂት ዓመታት በፊት በቼልሲ ስለተጫወተ ለፕሪሚየር ሊጉ አዲስ አይደለም፡፡ ሊጉን ፈጥኖ ለመልመዱም ምክንያቱ ይኸው ሊሆን ይችላል፡፡

በኤፍ.ኤ ካፕ ከስቶክ ጋርማቲች እንደ አስፈላጊነቱ ወደ ሁለቱ የመሀል ተከላካዮች እየተመለሰ የፒተር ክራውችን እንቅስቃሴ ተቆጣጥሯል፡፡ በተለይ በአየር ላይ የነበረው ብቃት ረጅሙን አጥቂ ፍሬ ቢስ ለማድረግ አመቺ ነበር፡፡ ማንቸስተር ሲቲን ሲገጥሙ ደግሞ ዴቪድ ሲልቫን ከጨዋታ ውጭ በማድረግ አስደናቂ የመከላከል አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ ከኒውካስል ጋር አማካይ ክፍሉን እንደልቡ ሲዟዟርበትና ሲሶኮን በአካላዊ እንቅስቃሴ ይጋፈጠው እንደነበር ታይቷል፡፡ መካከለኛና ረጃጅም ኳሶችንም በአስፈላጊው ሰዓት እየሰጠ ተመልካቹን አስደምሟል፡፡ በዚህም ምክንያት በቼልሲ አማካይ ግራ ወገን በመጫወት ያለፉትን 10 ዓመታት ያሳለፈው ላምፓርድ ለግራ እግሩ ማቲች የኳስ ስርጭት ቦታ ለመልቀቅ ሲል ወደ ቀኝ አማካይነት ተቀይሯል፡፡ ሰርቢያዊው ኳስ በእግሩ ስር ስትገባ ወደ ፊት በመጠጋት በሚደነቅ ሁኔታ ተንቀሳቅሷል፡፡ ሳይታሰብ በማጥቃት ለሃዛርድ የመጀመሪያ ጎል መነሻ ምክንያት ሆኗል፡፡ ቼልሲ ይህን ብቃት ከጆን ኦቢ ሚኬል አያገኘውም፡፡ ማቲች ግን በሶስት አይነት የአማካይ ክፍል ጨዋታ ይልቃል፡፡ ኳስን በመንጠቅ፣ በሰፊ ቀጠና ውስጥ በመንቀሳቀስ እና በአስፈላጊ ርቀት ኳሶችን በማቀበል ተክኗል፡፡ የቼልሲ የዋንጫ ጉዞም በሃዛርድና ማቲች አስደናቂ ብቃት ተጠናክሯል፡፡

ኢትዮጵያውያን ረዳት ፓይለቱን በመደገፍ በዋሽንግተን ዲሲ የስዊዘርላንድ ኢምባሲ ደጃፍ የፊታችን ሰኞ ሰልፍ ሊወጡ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሰኞ ዕለት ሮም ላይ ማረፍ የነበረበትን አውሮፕላን ስዊዘርላንድ ላይ እንዲያርፍ ያደረገው ኢትዮጵያዊው ረዳት ፓይለት “የታፈነውን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰት ለዓለም ያሳየ ጀግና ነው” የሚሉ ኢትዮጵያውያን የፊታችን ሰኞ ጠዋት ፌብሩዋሪ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ የስዊዘርላንድ ኢምባሲ ደጃፍ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ። የስዊዘርላንድ መንግስት ነገ ወይም ከነገ በስቲያ በረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

በዋሽንግተን ዲሲ የስዊዘርላንድ ኢምባሲ ደጃፍ የተጣራው ይኸው ሰልፍ ረዳት አብራሪው አውሮፕላን ጠላፊ አሸባሪ እንዳልሆነና ድርጊቱን የፈጸመው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ በስርዓቱ ውስጥ የሰፈነውን የአንድ ብሔር የበላይነትን ለዓለም ለማሳየት የተጠቀመበት ዘዴ በመሆኑ የስዊዘርላንድ መንግስት የጥገኝነት ጥያቄውን እንዲቀበለው እንደሚጠይቅ ከሰልፉ አስተባበሪዎች ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

“ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ይህ ወንድማችን ለኛ ነፃነት የታፈነውን ያገራችንን ህዝብ በአለም አደባባይ ያንድ ዘር ብቻ የነገሰው የዘረኛው ወያኔን ስራ ለአለም ያጋለጠ ጀግና ወንድማችን አሸባሪ ሳይሆን የነፃነት ታጋይ ወንድማችን መሆኖን ለመግለጽ ይህን ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል” ያለው የዋሽንግተን ዲሲው ሰልፍ አስተባባሪዎች ጥሪ ፍላየር ለዘ-ሐበሻ ደርሷታል። ሰልፉ የሚደረገው Embassy of Switzerland in the United States of America ሲሆን አድራሻውም ፦ 2900 Cathedral Ave., NW, Washington, D.C. ነው።

ረዳት ፓይለቱን በመደገፍ ተመሳሳይ ሰልፍ በስዊዘርላንድና በሌሎች ሃገራት ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑ የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ የስዊዘርላንድ መንግስት በረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ዙሪያ ነገ ወይም ከነገ በስቲያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል። ይህንን ተከትሎም በርካቶች ጋዜጣዊ መግለጫውን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው።
dc

[የረዳት አብራሪው ጉዳይ] ሕዝብን አፍኖ እና ረግጦ በመግዛት የስልጣን እድሜን ማራዘም አይቻልም

$
0
0

gezahegn abebe(በገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ)

ዘረኛው እና አምባገነኑ የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ወደስልጣን ወንበር በሀይል ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍኖና ረግጦ መግዛትን ተያይዞታል:: በአሁኑ ጊዜ ወያኔ የሚያራምደው በዘረኝነት የተሞላው የተሳሳተ እና የተወላገደ ፖለቲካ ሕዝቡን ከማማርር ባለፈ የኑሮ ውድነቱ፣ ስራ አጥነቱ፣ እና በሀገሪቷ ላይ ክፉኛ ወንጀል መበራከቱ እና በየሁሉም መስሪያ ቤቶች ከቀን ወደ ቀን ሙስና፣ ሌብነትና አይን ያወጣ ዝርፊያ እየጨመረ መምጣቱ የኢትዮጵያ ህዝብ የሰቋቋ እና የመከራን ኑሮ መኖርን ተያይዞታል:: ወያኔ እያራመደው ያለው በዘር የተሞላ ፖለቲካ አንዱን ዘር ከአንዱ ዘር በማበላለጥ እና በመከፋፈል አንዱን ዘር ከፍ ሌላውን ዘር ዝቅ በማድረግ ፣ እያወረደ እና እየናቀ ዜጓች በገዛ ሀገራቸው እና ምድራቸው ላይ በሰላም እና በነጻነት እንዳይኖሩ ይኼው የወያኔ መንግስት ሲፈልግ ነፍጠኛ፣ ጉርጠኛ፣ትምክህተኛ፣ ተገንጣይ፣አሸባሪ ወዘተ….. በማለት ሕዝቦችን በማስፈራራት እና ነጻነትን በማሳጣት በሀይል እና በጉልበት አፍኖ እየረገጠ በመግዛት ላይ ይገኛል::
ethio airlines
በአሁኑ ወቅት ተማሪው ተምሮ ስራ ለማግኘት እና ለመቀጠር ሰራተኛውም በስራው ገበታው ላይ ለመቆየት እና ስራውን በነጻነት ለመስራት በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ጥራት በሌለው የወያኔ የትምህርት ፖሊሲ ከመንግስትም ሆነ ከግል ዩንቨርስቲ እና ኮሌጆች ብዙ ወጣት ተማሪዎች በሀገሪቷ ላይ ትምህርታቸውን ጨርሰው ቢመረቁም በስራ አጥነት እየተንከራተቱ የሚገኙ ዜጓች ቁጥራቸው ከቀን ወደቀን እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ አንድ ሰው የሆነ መስሪያ ቤት ውስጥም ሆነ ድርጅትውስጥ ስራ ለማግኛት እና ለመቀጠር የግድ የወያኔ ኢህአዲግ አባል መሆን የሚጠበቅበት ሲሆን በስራ ገበታም ላይ ያሉ ሰዎች ቢሆንም እንኮነ በሚሰሩበት ቦታ የግድ የወያኔ አባል እስካልሆኑ ድረስ ነጻነት እንደሌላቸው ፣ ስራቸውንም በነጻነት መስራት እንደማይችሉ የተለያዩም ግፍ እና ጭቋናዎች እንደሚደርስባቸው የታወቀ ነው::

በቅርቡ መምህር አማኑኤል መንግስቱ የተባለ የማዝገበ ብርሀን አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ትምህርት ቤት መምህር የአንድነት አባል በመሆኑ በሚያስተምርበት ትምህርት ቤት የወያኔ ካድሬ በሆነ በትምህርት ቤቱ አስተዳደር የተለያዩ ዛቻዎችና ማስጠንቀቂያዎች እየደረሱበት እንደሆነ እና ከስራም ሊባረር እንደሚችል የማስንጠቀቂያ ደብዳቤ ከትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር እንደደረሰው የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ መዘገቡን አስታውሳለው:: ይህን እንደምሳሌ አልኩኝ እንጂ በጣም ብዙ ዜጓች ናቸው በየሚሰሩበት መስሪያ ቤቶች በዘር በተበላሸ በወያኔ ፖለቲካ አመለካከት የኢህአዲግ አባል ባለመሆናቸው የሚጨቁኑት ነጻነታቸውን አተው በሀገራቸው ተሸማቀው በወያኔ ካድሬዎች ታፍነውነው እና ተረግጠው የሚኖሩት ::

የወያኔ ባለስልጣናት ሊያውቁ የሚገባው ነገር ሕዝብን አፍኖ እና ረግጦ በመግዛት የስልጣን እድሜን ማራዘም እንደማይቻል ነው :: ለዚህም በዚህ ሳምንት የተከሰተው እና የአለም መነጋገሪያ እየሆነ ያለው እና የብዙ አለማት ሚዲያን ቀልብ የገዛው የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ የአውሮፕላን ጠለፋ ትምህርት ሊሆናቸው ይገባል :: ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ በእኔ አመለካከት ጀግና ነው ክብርም ይገበዋል :: ምንም እንኮን የሰራው ስራ የሚያስፈራ እና ዋጋ የሚያስከፍልም ቢሆንም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የወያኔ የተበላሸ የፖለቲካ አካሂድ ምን ያክል የከፋ እንደሆነ ፣ የደህንነት ስጋት ፤የአስተዳደር ብልሹነት እና የዘረኝነት መድልዎን ከመቼውም ጊዜ የባሰ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለአለም ሕዝብ ያመላከተበትን ጀብዱ ፈጽሞል:: ስለዚህ ፓይለት ሃይለመድህን አበራ በዘር ለተረገጦ ፣ ለተገፉ እና ለተጨቋኑ ኢትዮጵያኖች ድምጽ ሆኖል ነው የምለው ::

ፓይለት ሃይለመድህን አበራ አስቦ እና አቅዶ የተነሳበት ዋንኛው አላማ ይኼው ይመስለኛል:: የመንግስት ቃል አቀባይ ተብዪው አቶ ሬድዋን ፓይለት ሃይለመድህን ሙሉ ጤነኛ ሰው እንደሆነ ለአምስት አመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪ ሆኖ እንዳገለገለ ፣ የሽንገን ቪዛ እንዳለው ፣ነጻ ትኪት እንደሚያገኝ እና የትም ሀገር ሂዶ ትምህርቱን መቀጠል እንደሚችል ነገር ግን ፓይለት ሃይለመድህን ለእራሳቸውም እንደገረማቸው እና እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል በርግጥ ልክ ነው ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን የትም ሀገር ሂዶ አሳይለም የመጠየቅ እድል (opportunity) ይኖረው ነበር ብዙም ሰዎች በዚህ ጉዳይ ላይ የራሳቸውን ሀሳብ እየሰነዘሩ ሲሆን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ ደህንነት ስራ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገለውና በክትትልና ደህንነት ስጋት ከአመት በፊት ድርጅቱን ለቆ በስዊዘርላንድ ጥገኝነት የጠየቀው አንድ የቀድሞው የድርጅቱ ሰራተኛ አቶ ሚካኤል መላኩ የካፒቴን ሃይለመድህን አበራ የጠለፋ ምክንያት በአየር መንገዱ ውስጥ የሚታየውን የአስተዳደር መበላሸት ለአለም ለማሳየት ሊሆን ይችላል የሚለው ምክንያት አሳማኝ ነው ሲል ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ የተናገረው ነገር ትክክል ነው ብዪ አምናለው::

ፓይለት ሃይለመድህን አበራ በድፍረት የተሞላ ጀብዶ መፈጸሙ የወያኔን ባለ ስልጣናቶች ያስደነገጠ፣ ያሳፈረ እና ያሸማቀቀ ተግባር ሲሆን በወያኔ መንግስት በዘር፣በሀይማኖት ተገፍቶ እና ተጨቆኖ ላለው ምስኪኑ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ደስ የሚያሰኝ ተግባር ነው :: ምክንያቱም ህወሃት መራሹ መንግስት እያራመደ ባለው የዘረኝነት ፖለቲካ በሀገሪቱ ላይ ያላው የደህንነት ስጋት፣ አፈና እና ሰበሃዊ መብት ረገጣ ምን ያህል እየከፈ መምጣቱን ለአለም ሕዝብ ያመለከተበት ተግባር በመሆኑ:: ስለዚህ የወጣት ፓይለት ሃይለመድን ጀግንነት የተሞላበት ተግባር ወኔ እና ብርታት ሆኖን በወያኔ ታፍኖ እና ተረግጦ መገዛትን እንቢ በማለት እና የወያኔን በዘረኝነት የተሞላውን ፖለቲካ በመቃወም በአደባባይ በማውጣት ወያኔን በማስረበሽ እና በማስደንገጥ የስልጣን እድሜውን ማሳጠር የመላው ኢትዮጵያኖችን ነጻነት መወጅ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዲታ መሆን ይጠበቅበታል::

ፍትህና ነጻነት ለሚናፍቅ ኢትዮጵያዊ የማስተላልፈው መልህክት ህወሃቶች ዜጎችን ከሰው በታች አድርገው ለመግዛት እንዲመኙ ያደረጋቸው በእብሪት የተሞላ የፖለቲካ አካሄድ የሚተነፍስበት ዘመን እሩቅ አይሆንምና አሁንም አትፍሩ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
gezapower@gmail.com

በባህርዳር የአንድነትና የመኢአድ ደጋፊዎች ጫማቸውን በማውለቅ ተቃውሟቸውን ገለጹ፤ ለእሁዱ ሰልፍ ቅሰቀሳው ቀጥሏል

$
0
0

Bahrdar UDJ
ብአዴን እና አመራሮቹን በመቃወም እሁድ የካቲት 16 በባህር ዳር ከተማ በአንድነትና በመኢአድ ለተጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ለመቀስቀስ ዛሬ ወደ ባህር ዳር ማቅናታቸውን የአንድነት የዜና ምንጮች ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ ላይ አስታውቀዋል። እንደ አንድነት የዜና ምንጮች ገለጻ እሁድ ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳው በሰፊው የቀጠለ ሲሆን በኢሕአዴግ በኩል የሚፈጸምባቸው ትንኮሳም በዛው ልክ በሰፊው ቀጥሏል ብለዋል።

“በረዳት አንስፔክተር ክንፈ ሀይሌ ጉልላት የሚመራ የፖሊስ ሀይል በተለምዶ ከአባይ ማዶ በሚባለው አካባቢ የመኪና ላይ ቅስቀሳ እናዳይደረግ ማይክራፎን መበስበር ጭምር ሙከራ ማድረጉን” የገለጹት የአንድነት የዜና ምንጮች የከተማዋ ነዋሪዎች ግን የፖሊሶቹንና የትራፊኮቹን ህገወጥ ድርጊት በማስቆም ተባብረዋል ብለዋል። አካባቢው “ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም” በሚለው ዜማ መድመቁን የገለጹት እነዚሁ የዜና ዘጋቢዎች ፖሊሶቹ ከህጉ ይልቅ ለአለቆቻቸው ታማኝነታቸውን እያረጋገጡ መሆናቸው ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል ብለዋል። ህዝቡ የመኢአድ እና የአንድነት ደጋፊ የሆኑት ቀስቃሾቹ ሊነኩ አይገባም በማለት ተቃውሞውን ሲያሰማ ረዳት ኢንስፔክተሩ ተጨማሪ ሀይል እንዲመደብላቸው ትዕዛዝ ቢያስተላልፉም በህዝቡ ጫና የቅስቀሳ ቡድኑ ስራውን ቀጥሏል፤ ይህም የሚያኮራ ተግባር ነው ተብሏል።

ዘገባዎቹ እንደጠቆሙት በባህር ዳር የአንድነትና የመኢአድ አባላት ጫማ በማውለቅ በብአዴን ላይ ተቃውሟቸውን በመግለፅ ቅስቀሳቸውን የቀጠሉ ሲሆን፤ ይሄም በቅርቡ አቶ አለምነው መኮንን የአማራውን ሕዝብ ለመሳደብ የተጠቀሙበትን ቃል ለማስታወስና ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። በዛሬው እለት 14/06/2006 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የአንድነትና የመኢአድ አባላት በሞንታርቦ በመቀስቀስ ላይ ሲሆኑ በራሪ ወረቀት የሚያድሉ አባላት በፍፁም ቁርጠኝነት የብአዴኑ ባለስልጣን የተናገሩትን በመቃወም በባዶ እግራቸው በከተማዋ በመዘዋወር ለህዝቡ ግንዛቤ እየፈጠሩና በራሪ ወረቀቶችን እያደሉ ሲሆን የከተማው ነዋሪ በቁጭት አጋርነቱን እየገለፀ ይገኛል፡፡

በባህርዳር አቶ አለምነው መኮንን አማራውን ከተሳደቡ ወዲህ ብአዴን ከፍተኛ የሆነ ደጋፊ እንዳጣ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

ዘ-ሐበሻ እና የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በሚኒሶታ በሳዑዲ ለተጎዱ ወገኖች ያሰባሰቡት ገንዘብ ለIOM ተሰጠ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሳዑዲ አረቢያ ሕገወጥ ያለቻቸውን ዜጎችን ከሃገሯ እንዲወጡ ማዘዟን ተከትሎ የሳዑዲ ፖሊሶች በፈጸሙት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በመበሳጨትና የተገደሉትንም ለማሰብ በሚኒሶታ ዘ-ሐበሻ እና የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በመተባበር ባዘጋጁት የሻማ ማብራት ምሽት ላይ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮአሜሪካውያን ያዋጡት ገንዘብ ለዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ተሰጠ።

በኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በኩል የተላከውን ይኬንኑ ቼክ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ተወካዮች መረከባቸውን የሚገልጽ ደብዳቤም ልከዋል።

እሁድ ኖቬምበር 17/2014 ብሎሚንግተን በሚገኘው ራዲሰን ሆቴል በተደረገው የሻማ ማብራት ሥነሥርዓት ላይ $3,050.00 ዶላር (60 ሺህ 390 ብር) የተሰበሰበ ሲሆን ይህኑኑ ገንዘብ በኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ገንዘብ ያዥ አቶ አንተነህ ተፈራ በኩል በተጻፈ ቼክ ለ IOM እንዲላክ ተደርጓል።
ፌብሩዋሪ 11 ቀን 2014 ከIOM ፕሬዚዳንት ሉካ ዳል ኦሊጎ በተፃፈ ደብዳቤም ገንዘቡን መረከባቸውን የሚገልጽ ለኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ተልኳል።
ፕሬዚዳንት ሉካ በደብዳቤያቸው ተቋማቸው እስካሁን ድረስ ከሳዑዲ የተመለሱ ከ160 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን እየረዳ እንደሚገኝ አስታውቀው በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ይህን ጥረት ለመደገፍ ያሳየው ትብብር የሚደነቅ ነው ብለዋል።
SKMBT_C25014021217200
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በሚኒሶታ የራሱን ህንጻ ለመግዛት የሚያደርገውን ጥረት በመቀጠል 2ኛውን የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ማርች 29/2014 እንደሚያካሄድ አስታወቀ። በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት የሚኒሶታ ታዋቂ ዲጄዎች እና አርቲስቶች እንደሚሳተፉ አቶ መስፍን ነጊያ ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል።
ከዚህ ቀደም ለመጀመሪያ ጊዜ በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ቃል ከተገባው 50 ሺህ ዶላር ውስጥ ግማሽ ያህሉ ገቢ መደረጉን የገለጹት አቶ መስፍን ቃል የገቡ ሰዎች ክፍያውን በፍጥነት እንዲፈጽሙ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላት ቁጥር በአንድ ዓመት ውስት ከ11 ወደ 300 በላይ ማደጉን የጠቆሙት አቶ መስፍን እየሠራን ያለው ሥራ ብዙዎቹን እያስደሰተ መሆኑን ከምንሰማቸው አስተያየቶች እንረዳለን ብለዋል።
ኮምዪኒቲው እንደተለመወደ ዘንድሮም የአድዋ ድል በዓልን በተከራየው የቢሮው አዳራሽ ውስጥ ማርች 1/2014 እንደሚያከበር አስታውቆ ሁሉም የአድዋ ድል ታሪክ ኮሪዎች በስፍራው እንዲገኙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ማርች 1 በሚከበረው የአድዋ ድል በዓል ላይ ጥናታዊ ፊልሞች፣ የኢትዮጵያ ህፃናት የሙዚቃና የውዝዋዜ ሥራዎች፣ ግብዣ በተደረገላቸው እንግዶች ውይይት እንደሚደረግና ዝግጅቱን ከሰዓት በኋላ ከ2 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ አቶ መስፍን ጨምረው ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።

ባሶንዳ በተባለችዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማ 77 ኢትዮጵያዉያን ተገድለዋል ተባለ

$
0
0

(ቢቢኤን) ከመተማ ቀጥላ በምትገኘዉ ባሶንዳ በምትባለዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማና አካባቢ በኢዮጵያዉን ሽፍቶችና በሱዳን ሽፍቶች መካከል የተነሳዉን ግጭት ተከትሎ አራት ሱዳናዉያን በመሞታቸዉ ሳብያ ለብቀላ የተነሱት ሱዳናዉያን ታጣቂ ሐይላት ኢትዮጵያዉይንን በጅምላ እየገደሉ ነዉ አገር ወገን የድረስልን ሲሉ ወደ ሱዳን በመተማ በኩል የገቡ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እየተጣሩ ነዉ።
metama gonder
አራት ሱዳናዉያን ስለሞቱ በመቶ ኢትዮጵያዊ ነዉ የምንበቀለዉ ያሉት ሱዳናዉያን እስከ አሁን 77 ኢትዮጵያዉይንን መገደላቸዉን በኩራት ይናገራሉ ያሉት ኢትዮጵያዉያን የአብዛኛዎቹ ሟቾች መቃብር የማታወቅ መሆኑንም ይናገራሉ። በየጫካዉ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያን አስክሬናቸዉ ለዱር አራዊት መወርወሩን የሚገልጹት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ሌላ 42 ኢትዮጵያዉያን የተቀበሩበት መቃበር መኖሩንም ይጠቁማሉ፤ ይህ መቃብር ግን ከሞቱት 77 ሰዎች ጋር የሚያገናኘዉ ነገር ይኑር አይኑር የሚያዉቁት ነገር እንደሌለም ያስረዳሉ ።

በህዳር 24/2006 የሱዳኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሊ አህመድ አልቀርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሱዳንና ኢትዮጵያ ያላቸዉን የድንበር ልዩነት አስወግደዉ መስማማታቸዉን ይፋ አድርገዋል። ይህንንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ወደ ሱዳን ለስራ ጉብኝት አቅንተዋል። የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኡመር ሐሰን አልበሽር ሁለቱ አገራት በጥበቃ፣በደህንንነት፣ ህገወጥ የሰዉና የ አደንዛዥ እጽ ዝዉዉርን ለመግታት መስማማታቸዉን ገልጸዋል። በሱዳኗ ባሶንዳ የኢትዮጵያዉያን በጅምላ መገደል ከዚሁ የደህንነት ስጋት ጋር ግንኙነት እንዳለዉ ባይታወቅም ሱዳናን ኢትዮጵያ ግድያዉን ለማስቆም ምንም አይነት ጥረት እንዳላደረጉ ከጥቃቱ የተረፉ ኢትዮጵያዉያን ያስረዳሉ ።

በየካቲት 11/2006 ህወሃት የተመሰረተበትን 39ኛ አመት ለማክበር የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ልዩ የክብር እንግዳ ሆነዉ መቐሌ ድረስ መምጣታቸዉ ታዉቋል። የሁለቱ አገራት መሪዎች ስለ ቀድሞ ስማእታት ቢናገሩም ወደ ሱዳን በኢኮኖሚ ሳቢያ ተሰደዉ ስለሚሞቱት ኢትዮጵያዉያን ምንም ያሉት ነገር አልነበረም። በባሶንዳ ሱዳን ኢትዮጵያዉያን ነጥሎ የማጥቃቱ ዘመቻ እንደቀጠለ ነዉ! ኢትዮጵያዉያን ወገን ይድረስልን ሲሉም ይጣራሉ።

ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 14/2006 (ቢቢኤን )


ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 60 – PDF

$
0
0

zehabesha 60 page page 13 to 24
በሰሜን አሜሪካ ትልቋ የኢትዮጵያ ጋዜጣ ዘ-ሐበሻ እነሆ ቁጥር 60 ለንባብ በቅታለች።
እንደተለመደው በውስጧ የያዘቻቸውን ቁምነገሮች እፍታውን እናጨብጣችሁና ንባቡን ለናንተው እንተወዋለን።

* ዓብይ ትኩረታችን ያደርግነው በአውሮፕላኑ ጠለፋ ዙሪያ ነው። የተለያዩ ጉዳዮች ተዳሰዋል።
- ከአውሮፕላኑ ጠለፋ ባሻገር የፖለቲካ ይዘት አለው
- አውሮፕላኑን የጠለፈው ኃይለመድህን አበራ ተገኝ ማን ነው?
- የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የዜጎች እኩልነት አለመረጋገጥ፣ በሥራ ቦታ ላይ ነጻነት ማጣት፣ የኢኮኖሚ ችግር፣ የነፃነት እጦት አውሮፕላኑን አስጠለፈው
- የረዳት ፓይለቱ ድርጊት የአፈናው ውጤት?
- የኢትዮጵያ ነገርና – የአብራሪው ጉዳይ የሚሉ ወቅታዊ ዘገባዎችን ይዘናል።
* በወሩ ታላቅ ዜና አምዳችን፡ የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ “ኢትዮጵያዊነት-”የለህም ይሉኛል፤ እውን የለህም ወይ?” በሚል የፃፈውን ወቅታዊ ትንታኔ ይዘንላችኋል።
* ከሚኒሶታ የጤና ማዕከል ጋር በመተባበር በምናቀርበው አምዳችን ‘ስለ ክትባቶች እና ስለ እርግዝና ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች” የሚል ትንታኔ ይዘናል፤ ቢያነቡት ይጠቀማሉ።
* አዲሱን የNYPD (የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት) ስማርት ካር ውስጡ ምን እንዳለው ሰምተዋል? – ሊያመልጥዎ አይገባም።
* በሕይወት በአሜሪካ አምዳችን፡ ሥራ ፍለጋ ኢንተርኔት ገብቼ ፌስቡክ ላይ ተሰጥቼ እውላለሁ የሚል ትዝብታዊ ጽሁፍ አካተናል።
* ተወዳጁ ድምፃዊ ብርሃኑ ተዘራ (ያምቡሌ) በሚኒሶታ ሥራዎቹን ማርች 15 ያቀርባል
* ዲያቆን ዳንኤል ክብረት “የመረረው አብዮተኛ (ለ1966ቱ አብዮት 40ኛ ዓመት ማስተዋሻ)” በሚል የፃፈው መጣጥፍም የቁጥር 60 ዕትማችን አካል ነው።
በወንጀል ዜና አምዳችን፦
- 3 ልጅ የወለደችለት ሚስቱን በጥርጣሬ የተነሳሕይወቷን አጠፋ
- በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ የታክሲ ሾፌሩን ተሳፋሪው ገደለው የሚሉ ሁለት ዜናዎችን ይዘናል ትንታኔ አላቸው።
በእንመካከር አምድ 4 ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።
- “ከባለቤቴ ጋር ስምምነት መፍጠር ተሳነኝ፤ እባካችሁ አንድ በሉኝ”
- ከድብርት ለመላቀቅ ወሲብ ማድረግ ቢነገረኝም እርሱም አልረዳኝም
- ጉሮሮዬ ከተዘጋ 10 ዓመት ሆነው
- በዱካክ ተሰቃየሁኝ፤ ምን መፍትሄ አላችሁ? ምላሾቹን ያንብቧቸው፤ ይማሩባቸዋል።
* በጤና አምዳችን 3 ጉዳዮች እንደተለመደው ተካተዋል።
- ፕሮቴስት የወንዶች ብቻ ችግር (ወንዶች ልብ ብላችሁ አንብቡት)
- ትራኮማ እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ
- የነስር ነገር – Epistaxis ፦ ለምን ይነስረናል? የሚሉ 3 ምርጥና አስተማሪ ዘገባዎችን አካተናል ያንብቡን።
* በሴቶች አምድ፡ ማስካራ ትጠቀሚያለች? እንግዲያውስ ይህን አንብቢ ትለናለች ሊሊ ሞገስ፤ ያንብቡላት።
* በሳይኮሎጂ አምዳችን፤ ቅናት ለፍቅር ምኑ ነው? የሚል ቆንጆ ዘገባ አለን።
* በስፖርት አምድ እንዳስለመድነው 3 ጉዳዮች አሉን።
- ፍሌቸር በቀን እስከ 30 ጊዜ መጸዳጃ ቤት ይመላለስ ነበር
- ማርቴሳካር፡ ግዙፉ ጀርመናዊ
- ጋሪ ኩክ የማንቸስተር ሲቲው አዳኝ
በዘ-ሐበሻ ቁጥር 60 ላይ እነዚህ ብቻ አልተካተቱም፤ በርከት ያሉ ዘገባዎች ከማስታወቂያዎች ጋር ታጅበው ቀርበዋል። ያንብቡ።

ጋዜጣውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ቦይንግ 767 –እገታ እና እንድምታው –ክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

ethio airlines

አንድ የኢህአዴግ ካድሬ፣ ቤት ለመከራየት ወደ አንዲት ወይዘሮ መኖርያ ይሄዳል። ስፍራው እንደደረሰ ሌላ ተከራይም ከወይዘሮዋ ቤት ብቅ እንዳለ አስተዋለ። ሌላኛው ተከራይ ሰይጣን ነበር። ሁለቱ ተከራዮች ሰርቪስ ቤቱን ለመያዝ እንደ ጨረታ ብጤ ጀመሩ። ሰይጣኑ 400 ሲጠራ፣ ካድሬው ግን 500 ሊሰጥ ተስማማ። በመጨረሻ፣ ወይዘሮዋ ቤቱን ለሰይጣኑ በትንሽ ዋጋ ማከራየቱን መረጡ። የወይዘሮዋ ውሳኔ እንግዳ ነገር ነበር። ለሰይጣን፣ ለዚያውም በትንሽ ዋጋ ቤታቸውን ለመስጠት የወሰኑበትን ምክንያት ሲጠየቁ፤ “ሰይጣኑ አልወጣ እንኳን ቢል በጸበል ይለቃል። ካድሬው ገብቶ ቤቴን አልለቅም ቢለኝ ምን ላደርግ ነው?” ነበር ያሉት ወይዘሮዋ። ከፍ ባለ ገንዘብ ለኢህአዴጉ ሰርቪስ ቤታቸውን ቢያከራዩት ኖሮ ባጭር ጊዜ ዋናውን ቤታቸውን ለቀው የመውጣት ክፉ እድል ይገጥማቸው ነበር።
ዶ/ር መረራ ጉዲና ባለፈው ሳምንት ዘ ሄግ ላይ ስለ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ሲነግሩን ጣል ያደረጓት ቀልድ ናት። የዚህች ቀልድ የፖለቲካ እንድምታ ቀላል አይደለም። መልእክትዋ ሲጠቃለል የኢትዮጵያን ህዝብ እየለቀቀ መሆኑን ትነግረናለች። እየከፋ የመጣው የኑሮውና የፖለቲካ ሁኔታ የህዝቡን አእምሮ ብቻ አይደለም እየነካው ያለው። ህዝቡ እየተገፋ ሃገርሩን ለቆ እንዲሰደድ እየተገደደም ይገኛል። በተለይ ደግሞ ሃገሪቱ በድህነት ያስተማረቻቸው ምሁሮችዋንና ባለሞያዎችዋን እንደዋዛ እያጣች ከመጣች እነሆ ሁለት አስርተ-ዓመታት ተቆጠሩ።

እለተ ሰኞ የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም.።

የአለም ዜና ርዕስ ሁሉ ትኩረት የጣለው በኢትዮጵያዊው ፓይለት ጉዳይ ላይ ነበር። እንደዚህ አይነት ክስተት ሲፈጸም አዲስ አይደለም። ግን ይኽኛው ልዩ ነው። ይዘቱ ለየት ይበል እንጂ በ 1998 (እ.ኤ.አ.) ዩዋን ቢን በተባለ ቻይናዊ ፓይለት ከተፈጸመው ድርጊት ጋር ይመሳሰላል። የ30 አመቱ ወጣት የበረራ ቁጥር CA905 የሆነውን የቻይና አውሮፕላን በመያዝ የታይላንድን የአየር ጠረፍ ሰብሮ ገባ። የ27 አመት እድሜ ያላት ሚስቱን ይዞ ታይዋን ላይ ያረፈው ፓይለት ለዚያ አደገኛ ውሳኔ የሰጠው ምክንያት የኢኮኖሚ ችግር ነበር። የደረጃ እድገት፣ የደሞዝ ጭማሪ፣ የመሳሰሉ ከራስ ወዳድነት ያላለፉ ጥያቄዎች በማንሳት የፓይለቱ የራሱን ክብር ዝቅ አደረገው።

በ 1995 (እ.ኤ.አ.) ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ በግዳጅ ከአውስትራልያ ወደሃገሩ እንዲመለስ ተደረገ። ኢትዮጵያዊ ግን የኦሎምፒክ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ጀት ግሪክ ላይ ለመጥለፍ በመሞከሩ የአለምን ዜና ርእስ ሆኖ ነበር። ጋዜጠኛው የፕላስቲክ ቢላዋ የበረራ አስተናጋጅዋ አንገት ላይ በመደገን ወደ ሀገሩ እንዳይላክ ጥያቄ አቀረበ። በመጨረሻም ኢትዮጵያዊ ወገን ባደረገው ርብርብ የዚህ ወጣት አላማ ተሳካለት።
የሃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለየት የሚያደርገው ለዚህ ከባድ ውሳኔ የሰጠው ምክንያት ነው። የግል ሳይሆን የሃገር፣ የራስ ሳይሆን የወገን ጉዳይ። ረዳት ፓይለቱን እብድ ያሰኘውም ይኸው ነገር ይመስለኛል። ሃይለመድህን የ40 ሺህ ብር ደሞዝተኛ ነው። በኑሮው ምንም የጎደለበት ነገር የለም። ከመካከለኛው ኢትዮጵያዊ ዜጋ በላይ ይኖራል። የስደት ጥማት እንኳን ቢኖርበት ለመሰደድ በዚህ ሁኔታ አውሮፕላን ማገት እንደማይኖርበት ጠንቅቆ ያውቃል። ለዓለም ህዝብ ማስተላለፍ የሚፈልገው አንድ መልእክት ነበር። “ሜይዴይ… ሜይዴይ… የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ላይ ነው!”

ተልእኮው በሚገባ ተሳክቷል።

Hailemedhin Abera ሰኞ ማለዳ የመስርያቤታችን የውይይት ርእስ የነበረው ጄኔቭ ላይ ሳይታሰብ ያረፈው ቦይንግ 767 ጉዳይ ነበር። የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ታሪካዊ ውሳኔ የስራ ባልደረቦቼን ከሁለት ጫፍ ከፍሎ ለረጅም ውይይት ጋብዟቸውዋል። አንደኛው ወገን ፓይለቱ ያደረገው ጠለፋ ነው ብሎ ሲከራከር፤ ሌላኛው ወገን ደግሞ ድርጊቱ እንደጠለፋ መታየት የለበትም ይላል። የሁለቱን ወገን ክርክር እየሰማሁ ምንም ሳልተነፍስ ለረጅም ግዜ ቆየሁ። አእምሮዬ ግን አንድ ነገር ላይ ተጠምዶ ነበር። ክስተቱ ለፖለቲካ ደንታ የሌላቸውን እነዚህ ነጮች ማነጋገር መቻሉ እጅግ ደንቆኛል። “ወጣቱ ፓይለት ምን ያህል በደል ቢበዛበት ይሆን ለዚህ ካባድ ውሳኔ የበቃው?” የሚለው ጥያቄ በብዙዎች አእምሮ ይመላለስ የነበረ ጉዳይ ነው። አብዛኞቹ ስለ ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታ በደንብ እንዲረዱ ማድረጉም አልቀረም። ጅብ በቀደደው ውሻ ይገባል’ ነውና ሁሉንም ነገር ለማስረዳት አሁን በጣም ቀላል ሆነ።

ሃይለመድህን አበራ ‘እብድ ነው’ የሚሉም አልጠፉም፤ ልክ እንደ አፈቀላጤው ሬድዋን። ለነጮቹ ነገሩ እንግዳ መሆኑ አልቀረም። ፓይለት ሆኖ፣ ጥሩ ኑሮ እየኖረ፣ ቤት- ንብረቱን፤ የሚወዳት ሃገሩንና ቤተሰቡን ትቶ ለእስራት፣ ለስደትና ለእንግልት ራስን ማዘጋጀት እብደት ነው ሊባል ይችላል።

በኢትዮጵያ ተመክሮም የፓይለት ሞያ ያስከብራል። በሃገራችን የፓይለቶች የኑሮ ደረጃ አንደኛውን ረድፍ ይይዛል። ይህንን የመሰለ ህይወት ጥሎ የስደትን ኑሮ መምረጥ የሚያስችል ውሳኔ ላይ መድረስ ደግሞ እብድ ቢያስብል የሚደንቅ አይደለም። የሚገርመው የስርዓቱ ካድሬዎች ይህንን አባባል መደጋገማቸው ነው። ከራሳቸውም አልፈው የፓይለቱ ቤተሰቦችን በማስፈራራት ይህንን እንዲመሰክሩ ሲያደርጉ ይታያል። ወትሮውን በእብዶች መሃል አንድ ጤነኛ ሰው ካለ፣ እሱ እብድ ነው። እነሱ በሰብአዊ መብት ላይ ሲቀልዱ በዚያ የማይተባበራቸው ሁሉ እብድ ነው። ለህሊናው ሳይሆን ለመኖር ሲል ሰበአዊ መብቱ ላይ የማደራደር ሁሉ ሽብርተኛ – አልያም የአእምሮ በሽተኛ ነው።

እብድ ሰው ያንን ግዙፍ አውሮፕላን በስርዓት አብርሮ፤ በስርዓት ካሳረፈ፤ በኢትዮጵያ ፓይለት ለመሆን የቅጥር መስፈርቱ እብድ መሆን ነው። ግና በአውሮፕላኑ የነበሩ 202 ተሳፋሪዎችን ምን እንደተፈጠረ እንኳን ሳያውቁት ጄኔቭ ላይ ማረፋቸው ብቻ እነሱ የሚሉት ይጻረራል። ሃይለመድህን ዋናውን ፓይለት በሃይል አላስገደደውም። ተሳፋሪዎች እንዳይረበሹም ስለድርጊቱ አንዳች ነገር አልተነፈሰም።

ለባለስልጣናቱ ጥያቄ አለኝ። የሃይለመድህን እብድ መሆኑን እያወቁ ለምን ፓይለት አድርገው ቀጠሩት? የእሱ እብድ መሆኑ ለባለስልጣኖቹ እንዴት አሁን ታያቸው?

ያም ታባለ ይህ – የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. በስዊስ ላይ የተፈጠረው ነገር “ከሺ ቃላት… ” እንደሚሉት አይነት ነው። አንዲት ትንሽ ድርጊት የአለምን ህዝብ ከጫፍ እስከጫፍ አነጋገረች። ሃይለመድህን በአንዲት ቅጽበት እና በአንዲት ቃል ብቻ ላለፉት 20 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይፈጸም የነበረውን ግፍ ሁሉ ለአለም አሳወቀ። ይህንን ለማድረግ ግን ራሱን መስዋዕት ማድረግ ነበረበት። ወጣቱ ሊደርስ የሚችልበትን ነገር ሁሉ አስቀድሞ ያውቀዋል። ከሃገር አመራረጥ ጀምሮ የወሰዳቸው እርምጃዎች በሙሉ የተጠኑ እና በጥንቃቄ የተደረጉ መሆናቸውን ሂደቱ ራሱ ይመሰክራል።

ወጣቱ ፓይለት ሃገሩን ይወዳል። የልጅነት ህልሙን እውን ያደረገበትን የፓይለትነት ሙያም ያከብራል። ለኢትዮጵያ አየር መንገድም የተለየ ክብር አለው። ራስ ወዳድ ቢሆን ኖሮ ፓይለት ሁሉ እንደሚኖረው በሃገሩ እየሰራ መኖር ይችላል። እንደ እብደት ያስቆጠረበት የዚህ ውሳኔ ምክንያቱ ግን ለህሊናው ብቻ ተገዥ መሆኑ ነው። ለሱ ቅርብ የሆኑትም ይህንኑ መስክረዋል።

በሃገራችን ሰርቶ የመኖር ዋስትና በአንባገነኖች እጅ ላይ ወድቋል። በነጻነት የመስራት፣ በነጻነት የመናገር፣ በነጻነት ሃሳብን የመግለጽ…ወዘተ ዋስትና ሳይኖር የመኖር ትርጉሙ ምንድነው? ሰው ያለ ነጻነት ምንድነው? ለመኖርማ እንስሳትም እየበሉ ይተኛሉ እየተነሱም ይበላሉ – ከዛ ይተኛሉ። ከእንስሳ የሚለየን ነጻነታችን መሰለኝ። ያለ ነጻነት ህይወት ትርጉም የለውም።

በኢትዮጵያ 80 ሚሊየን ህዝብ ያለነጻነት ይኖራል። ሃይለመድህን በአንዲት ቅጽበት የዚህ ሁሉ ህዝብ ድምጽ ሆነ። የ80 ሚሊየን ህዝብ ድምጽ ሆኖ በራሱ ላይ መፍረድ መቻል ደግሞ እብደት ሳይሆን ጀግንነት ነው። አንድ ሰው እንዴት መኖር እንዳለበት፣ ምን መናገር እንዳለበት…ወዘተ ሲወሰንት ለአንባገነኖች ብቻ ሳይሆን ለራሱ ህሊናም ባርያ ይሆናል። በተለይ የራስ መተማመን እና የሙያው የተካነ ሰው ተገዥ የሚሆነው ለህሊናው ብቻ ነው። እንዲህ አይነቱ ሰው መብቱን ለድርድር አቅርቦ ራሱን በባርነት አያስገዛም። በመብቱ ላይ የሚደራደር ካለ ህሊናውን የሸጠ ሰው ብቻ ነው። ነጻነት የሚገዛ ውይንም የሚሸጥ ነገር አይደለም። ነጻነትን ሊገዛው የሚችለው ህሊናችን ብቻ ነው። ያለ እራሳችን መልካም ፈቃድ ደግሞ ማንም ሃይል ነጻነታችንን ሊደፍር አይቻለውም። ሰዎች በአካል ሊታሰሩ ይችሉ ይሆናል። የሰውን ህሊና ግን ማንም ሃይል ሊያስረው አይችልም። ኔልሰን ማንዴላ ለ27 አመታት ሲታሰር ህሊናው ነጻ ነበር። በአንጻሩ አሳሪዎቹ ነጮች የአካል ሳይሆን የህሊናቸው እስረኞች ነበሩ።

ሃይለመድህን የህዝብ ድምጽ በመሆን ከህሊናው ጋር የገጠመውን ሙግት ያሸነፈ ጀግና ነው። አላማው በውስጡ የቆሰለበትን የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ ለአለም ለማሳወቅ ነበር። ይህ ባይሆን ኖሮ ችግር ውስጥ ያማያስገቡት ሌሎች ብዙ አማራጮች እና እድሎች ነበሩት። “ዘ ክርስቲያን ሳይንስ ሞኒተር” የተባለው ጋዜጣ የሃይለመድህንን ስደት መጠየቅ አስመልክቶ ባሰፈረው ዘገባ የኢህ አዴግ ስርአት ብልሹነትና የሰብአዊ መብት ረገጣው መባባሱን በስፋት ዘግቧል። ሌሎች መገናኛ ብዙሃንም የሃገሪቱን ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው እንዲመረምሩት አድርጓቸዋል።
ዶ/ር መረራ ጉዲና ሲነግሩን የኢሕአዴግ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ሃገሪቱን ወደ ጥርነፋ ፖለቲካ እና ቁምራ ኢኮኖሚ አሸጋግሯታል። ጥርነፋ እና ቁምራ አዲሶቹ ኢህአዲግኛ ቋንቋዎች ናቸው። ጥርነፋ ማለት አንድ ሰው አምስት ሰዎችን እየሰለለ በማገት ከገዥውፓርቲ አሰራር እንዳያፈነግጥ የማሰርያ ዘዴ ነው። ማንነትን የሚፈታተነው ይህ አሰራር አየር መንገድን ጨምሮ በሁሉም መንግስታዊ ተቋማት ተግባራዊ እየሆነ መጥቷል።

ቁምራ ደግሞ ቁርስ፣ ምሳና ራት በአንድ ግዜ ማለት ነው። ነብሳቸውን ይመርና አቶ መለስ በአንድ ወቅት ሲጠየቁ የኢትዮጵያ ህዝብ ሶስቴ በልቶ እንዲኖር ነበር ህልማቸው። እነሆ ዛሬ 70 በመቶው የኢትዮጵያ ህዝብ ሶስቱንም የእለት ምግብ አንድ ግዜ በቁምራ እንዲያጠቃልል አበቁት። 10ሺህ የሚሆን የአዲስ አበባ ነዋሪ የሚተዳደረው ከቦሌ አየር መንገድ እና ከሆቴሎች የሚጣል ቆሼ እየበላ ነው። በአንጻሩ ደግሞ እነ ስብሃት ነጋ ለአንዲት ጠርሙስ ሉዊስ ኮኛክ 260፣ 000 (ሁለት ሞቶ ስልሳ ሺህ ብር) ያወጣሉ። የ100 ሺህ ብር መጋረጃ ያለው፤ የ60 ሚሊየን ብር መኖርያ ቤት ውስት በሚዋኙ እጅግ ጥቂቶች እና ቆሻሻ እየተመገቡ በሚኖሩ ብዙሃን ወገኖች መሃል ያለው ክፍተት ይህ ነው አይባልም። ይህንን የኑሮ ሚዛን መዛባት የሚቃወመውን ስም ያወጡለታል። ኢ-ፍትሃዊ የሆነውን ይህንን የሃብት ድልድል ለመቀበል ህሊናው የማይፈቅደውን ሁሉ “እብድ” የሚል ስም ይሰጡታል።

የ”እብዱ” ፓይለት ጉዳይ በህግ አይን ሲታይ ጠለፋ ሳይሆን እገታ ነው – የስዊዘርላንድ አቃቢ ሕግ እንደገለፀው። እገታ እና ጠለፋ እጅግ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ድርጊቱ ጠለፋ ቢባል ኖሮ ቅጣቱም የከፋ ይሆናል። እገታም ቢሆን በስዊስ ህግ ከ3 እስክ 20 አመት ሊያስቀጣ ይችላል። የዳኝነት ስልጣኑም ያለው አውሮፕላኑ በግዛቷ ያረፈበት የስዊዘርላንድ ፌዴራል መንግስት ላይ ነው። ለግዜው ሃይለመድህን አበራን አግኝቶ ማነጋገር ስለማይቻል ወጣቱን ያቆሰለው ጉዳይ ላይ ከዚህ የበለጠ ማለት አይቻልም። የአቃቤ-ህጉ ምርመራውን እንዳበቃ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። ያን ግዜ የበለጠ መረጃ ይኖራል።

ኢትዮጵያዊ ወገን በሙሉ፣ ራሱን አሳልፎ ለሰጠው ለዚህ ፓይለት ባገኘው መንገድ ሁሉ ድጋፉን መግለጽ ይጠበቅበታል።

“አውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ ተሳፋሪው የተደነቀው በረዳት አብራሪው ችሎታ ነበር”–በተጠለፈው አውሮፕላን ውስጥ የነበረው ኢትዮጵያዊ ይናገራል

$
0
0

ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ስዊዘርላንድ ላይ ተጠልፎ ባረፈው አውሮፕላን ውስጥ ተሳፍሮ የነበረውን ኢትዮጵያዊ ቃለምልልስ አስነብቧል። ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ግንዛቤ እንዲሰጥ በሚል እንደወረደ አቅርበነዋል።

“የተሳፋሪው ፍላጎት የሆነ መሬት ላይ ማረፍ ብቻ ነበር”
co pilot ethiopia
በሃዋሳ ከተማ በተለምዶ ኬሮ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተወልዶ ያደገው ወጣት ምህረቱ ገብሬ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቀድሞው ሀዋሳ ኮምቦኒ የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ነው የተከታተለው። የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና የመሰናዶ ትምህርቱንም በቅዱስ ዳንኤል ኮምቦኒ የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ት/ቤት አጠናቋል። ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2001 ዓ.ም በሲቪል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪውን ካገኘ በኋላም፤ እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመምህርነት አገልግሏል፡፡ በመቀጠልም ነጻ የትምህርት ዕድል በማግኘት፣ ወደ ጣሊያን አምርቶ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱን በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡
በቅርቡ ለእረፍት ወደ አገሩ የመጣውና በሃዋሳ ቆይቶ ወደ ጣሊያን ለመመለስ አውሮፕላን የተሳፈረው ምህረቱ፣ ባለፈው ሰኞ በረዳት አብራሪው ተጠልፎ ጄኔቭ እንዲያርፍ በተደረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 አውሮፕላን ውስጥ ከነበሩት 200 ገደማ ተሳፋሪዎች ውስጥ አንዱ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት በጣሊያን የሚገኘው ምህረቱ፣ የጠለፋውን አጋጣሚ በተመለከተ ጋዜጠኛ አንተነህ ይግዛው በኢ-ሜይል ለላከለት ጥያቄዎች የሰጠውን ምላሽ እንደሚከተለው አጠናቅረን አቅርበነዋል፡፡

የጉዞው አጀማመር ምን ይመስል ነበር?
አርፍዶ ወደ አውሮፕላን ጣቢያ መምጣት የሚያደርሰውን ጣጣ ስለማውቀው፣ አውሮፕላኑ ከሚነሳበት 50 ደቂቃ ያህል ቀድሜ ነበር የተገኘሁት፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ማለት ነው፡፡ ያው ጉዞው ሲጀመር እንደሌላው ጊዜ ሁሉ ስርአቱን የጠበቀና ሰላማዊ ነበር። አውሮፕላኑ ከበራራ ሰዓቱ ሰባት ደቂቃ ያህል ዘግይቶ ነበር የተነሳው።
አውሮፕላኑ ውስጥ አቀማመጥህ እንዴት ነበር? የት አካባቢ ነው የተቀመጥከው?
የመቀመጫዬ ቁጥር 27F ነበር። የተሳፈርንበት ቦይንግ 767 በርዝመቱ ትይዩ 7 የመቀመጫ መደዳዎች አሉት። ሁለት ሁለት መደዳዎች በሁለቱም ጥጎች እና ሶስት መደዳዎች መሃል ላይ። እኔ የተቀመጥኩት ከመሃል ሶስቱ መደዳዎች የመሃለኛዋ ወንበር ላይ ነበር። ከበስተግራዬ ያለችው ወንበር ላይ የተቀመጡት ሪካርዶ የተባሉ የ85 አመት የዕድሜ ባለጸጋ ጣሊያናዊ ነበሩ፡፡ በቀኜ በኩል እንዲሁ በግምት በስድሳዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሌላ ጣሊያናዊ ተቀምጠው ነበር፡፡ ተዋውቀን ነበር፣ አሁን ግን ዘንግቼዋለሁ። ኢትዮጵያን ተዟዙረው እንደጎበኟት እያጫወቱኝ ነው ጉዞውን የጀመርነው፡፡
ጉዞውስ እንዴት ነበር?
እንደማስታውሰው ጉዞው ሲጀመር ሰላማዊ ነበር። ከፓይለቱ ጋርም ግንኙነት (ኮሙኒኬሽን) ነበረን፡፡ እኔ ድካም ስለተሰማኝ ወዲያው አሸለብኩ፡፡ በረራው ከተጀመረ በግምት ከ1 ሰዓት በኋላ የሱዳን አየር ክልል ውስጥ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ. . . መብራት ሲበራ ከእንቅልፌ ነቃሁ፡፡ የምግብ ሰዓት መድረሱ ገብቶኛል። ወደ ፊት አሻግሬ ሳይ ሆስተሶቹ እያስተናገዱ ከእኔ ፊት 4ኛ ይሁን 5ኛ ረድፍ ደርሰዋል። ሁሉም ተዘገጃጅቶ እየተጠባበቀ ነበር። በዚህ መሃል የፕሌኑ ፍጥነት ሲጨምር ይታወቀኛል፡፡ ከፍታዉም ሲጨምር በጆሮዬ ላይ በሚሰማኝ ስሜት አስተዋልኩ። በተሳፋሪዎች ፊት ላይ የመረበሽ ስሜት ሲፈጠር አየሁ። እኛ ኢኮኖሚ ክላስ ስለነበርን ከፊት ምን እየተካሄደ እንደነበር አላየንም። በኋላ ስሰማ ከፊት የነበሩትም የቢዝነስ ክላስ ተሳፋሪዎች ምንም መረጃ አልነበራቸውም፡፡
ከዚያም በድምጽ ማጉያው የሆነ ድምጽ ተሰማ፡፡ የረዳት አብራሪው ድምጽ ነበር።
“ተሳፋሪዎች ከ 12 ደቂቃዎች በኋላ ሚላን እናርፋለን” አለ ረዳት አብራሪው፡፡ ጥቂት ቆይቶም፣ “ስለተፈጠሩ አንዳንድ መጉላላቶች ይቅርታ እንጠይቃለን” ሲል አከለ-በእንግሊዝኛና በአማርኛ ቋንቋ። የረዳት አብራሪውን ንግግር ተከትሎ የተወሰኑ ተሳፋሪዎች ማጉረምረም ጀመሩ፡፡ አንዳንዶችም ጮክ ብለው ሲያወሩ ይሰሙ ነበር፡፡ ከኔ በስተግራ በኩል ሶስት አራት መደዳዎችን አልፎ ከፊቴ ተቀምጦ የነበረ አንድ ወፍራም ሰው፣ በጣሊያንኛ ቆጣ ብሎ እየጮኸ ተናገረ – “መጀመሪያ ሚላን ሳይሆን ሮም ነው ማረፍ ያለብን ፣ ወደ ሮም ውሰዱን!” በማለት። ሌሎችም የሰውየውን ሃሳብ ደገፉ፡፡ ምክንያቱም አብዛኛው ተሳፋሪ ወደ ሮም ነበር የሚጓዘው። ረዳት አብራሪው ሚላን ላይ እንደምናርፍ መናገሩ ብዙዎችን አበሳጭቶ ነበር፡፡
እውነቱን ለመናገር፣ እኔ ግን ሚላን እንደምናርፍ ስሰማ ደስ ብሎኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም እኔ ሚላን ወራጅ ነኝ፡፡ ረዳት አብራሪው የነገረን አስራ ሁለቱ ደቂቃዎች እየተገባደዱ መሆናቸው ሲገባኝ፣ ከአውሮፕላኑ ለመውረድ መዘገጃጀትና ጓዜን መሸካከፍ ሁሉ ጀመርኩ። ሆኖም አስራ ሁለቱ ደቂቃዎች አልፈውም አውሮፕላኑ አላረፈም፡፡ ካሁን አሁን ሚላን አውሮፕላን ማረፊያ ደረስን እያልን ስንጠባበቅ፣ ሌላ አስራ ሁለት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ አሁንም ሌላ አስራ ሁለት ደቂቃዎች—
ተሳፋሪው ሁሉ ግራ በመጋባት ሰዓቱን ደጋግሞ መመልከትና እርስ በርስ በጥርጣሬ መተያየት ጀመረ። ከአስራ ሁለት ደቂቃዎች በኋላ ሚላን ላይ ያርፋል የተባለው አውሮፕላን፣ ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ በአየር ላይ ቆየ፡፡ የሚገርመው ያን ያህል ጊዜ አየር ላይ መቆየቱ ብቻ አይደለም፡፡ አበራረሩ የተለየ ነበር፡፡ አንዴ ፍጥነቱን ጨምሮ ይከንፋል፣ ከዚያ ደግሞ ፍጥነቱን ይቀንስና ተረጋግቶ ይበራል፡፡ እንደገና ይፈጥናል፣ እንደገና ይረጋጋል፡፡ ግራ ገብቶን እያለን፣ ከመቅጽበት አውሮፕላኑ ማረፊያው ላይ ደርሶ ማኮብኮብ ጀመረ፡፡ ያንን ያህል ግዙፍ አውሮፕላን፣ በዚያች ጠባብ ቦታ ላይ ያለችግር ማሳረፍ መቻሉ፣ የረዳት አብራሪውን ብቃት ያሳያል፡፡ ለማንኛውም አውሮፕላኑ በሰላም አረፈና እኛም እፎይ አልን፡፡
Hailemedhin Abera
አውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ የተሳፋሪዎች ስሜት ምን ይመስል ነበር?
የሚገርመው ነገር፣ አውሮፕላኑ እንዳረፈ በተሳፋሪው ፊት ላይ ከታየው ደስታና እፎይታ በተጨማሪ፣ ተሳፋሪው ለረዳት አብራሪው የሰጠው አድናቆት ነበር፡፡ አብዛኛው ተሳፋሪ ስለረዳት አብራሪው ችሎታ ነበር ተደንቆ የሚያወራው፡፡ በከፍተኛ የአድናቆት ስሜት ተውጠው፣ ለረዳት አብራሪው ያላቸውን አድናቆት በጭብጨባና በፉጨት የገለፁም ነበሩ፡፡ እኔም በደመነፍስ ሳጨበጭብ ነበር፡፡ ሚላን ምድር ላይ በሰላም እንዲያሳርፈኝ ለፈጣሪዬ ያደረስኩትን ጸሎት የማውቀው እኔ ነኝ፡፡
ሚላን እንዳረፋችሁ ነበር የምታውቁት ማለት ነው?
የሚገርመው እኮ እሱ ነው!… አውሮፕላኑ መሬት ከነካ በኋላ ሁሉ፣ ተሳፋሪው በሙሉ ጣሊያን ሚላን እንዳረፈ ነበር የሚያውቀው፡፡ ሚላን እንደምናርፍ ነው ረዳት አብራሪው የነገረን፡፡ ትኬት ከፍለን የተሳፈርነውም ወደ ጣሊያን እንጂ ወደ ስዊዘርላንድ ለመሄድ አልነበረም። በዚህ ቅጽበት ጄኔቭ የምትባል ከተማ በምን ተአምር እንሄዳለን ብለን እናስብ?
ጄኔቭ መሆናችሁን ያወቃችሁት እንዴት ነው?
አውሮፕላኑ በሰላም ካረፈ በኋላ ተሳፋሪው ከጭንቀቱ ተገላግሎ መረጋጋት ጀመረ፡፡ አንዳንዶች ሞባይል ስልኮቻቸውን አውጥተው መነካካት ያዙ። በሞባይላቸው የኢንተርኔት መስመር በመጠቀም ጎግል ማፕ የተሰኘውን የአገራትና የከተሞች ካርታ የሚያሳይ ድረገጽ፣ ጂ ፒ ኤስ ከሚባለው አቅጣጫ ጠቋሚ ቴክኖሎጂ ጋር አያይዘው ሲመለከቱ፣ ፊታቸው ላይ ድንገተኛ መደናገር ሲፈጠር አየሁ፡፡ አንዱ ተሳፋሪ ሞባይሉ ላይ ያየውን መረጃ በመጠራጠር፣ የሌላኛውን ሞባይል ማየት ጀመረ፡፡ “የት ነው ያለነው?” ለሚለው ጥያቄ እርግጠኛ የሆነ መልስ የሚሰጥ ጠፋ፡፡ ግማሹ “ ኦስትሪያ ነን!” ሲል፣ ገሚሱ “የለም ፈረንሳይ ነን!” ብሎ ይመልሳል፡፡ አንዳንዱ “ጀርመን ውስጥ ነው የምንገኘው!” ይላል፡፡ ሌላው “ስዊዘርላንድ ጄኔቭ ነው ያረፍነው!” እያለ ይናገራል፡፡ ጭንቀትና ውጥረት የፈጠረው መደናገር ሊሆን እንደሚችል ያሰብኩት በኋላ ነው፡፡
ጄኔቭ ማረፋችሁንና አውሮፕላኑ መጠለፉን ያወቃችሁት እንዴት ነበር?
እያንዳንዱ ተሳፋሪ አውሮፕላኑ ያረፈበትን አገርና ከተማ በተመለከተ የየራሱን መላምት እየሰነዘረ ግራ ተጋብቶ ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ በዚህ መሃል ነው፣ ድንገት የአውሮፕላኑን ዋና አብራሪ ድምጽ የሰማነው። በረራው ከተጀመረ አንስቶ የዋና አብራሪውን ድምጽ ስንሰማ ለመጀመሪያ ጊዜያችን ነበር፡፡ ዋና አብራሪው በጣሊያንኛ ቋንቋ ነበር የሚያወሩት፡፡ በጣሊያን ቆይታዬ የቀሰምኳት ቋንቋ ብዙም የምታወላዳ አልነበረችምና፣ ደቂቃዎችን ከፈጀው የአብራሪው ንግግር የተወሰነችዋን ተረድቼ፣ ቀሪውን ከጎኔ ከተቀመጡት ጣሊያናውያን ጠይቄ ለመረዳት ሞከርኩ፡፡
አብራሪው ወደመጸዳጃ ቤት ሲወጡ ረዳት አብራሪው በር እንደዘጋባቸው፤ አውሮፕላኑን ለሰዓታት ሲያበር የቆየው ረዳት አብራሪው እንደነበር፤ አውሮፕላኑ ያረፈው ጄኔቭ መሆኑን፤ በተፈጠረው ነገር ማዘናቸውን መግለጻቸውን እንዲሁም እያንዳንዱ ተሳፋሪ የስዊዘርላንድ ፖሊሶች ለሚያደርጉት ምርመራ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ነገሩኝ፡፡ ተሳፋሪው ስለ ጠለፋው ያወቀው በዚህ ጊዜ ነው፡፡
ተጠልፋችሁ ያላሰባችሁት ቦታ እንዳረፋችሁ ስታውቁ ምን ተሰማችሁ?
ethio airlines
እውነቱን ለመናገር በወቅቱ የሁሉም ተሳፋሪ ጸሎትና ምኞት በረራው በሰላም መጠናቀቁና አውሮፕላኑ አደጋ ሳያጋጥመው ማረፉ ብቻ ነበር፡፡ የተሳፋሪው ፍላጎት የትም ይሁን የት፣ ብቻ የሆነ መሬት ላይ ማረፍና ከጭንቀት መገላገል ነበር፡፡ አስበው እስኪ… ከአብራሪውም ሆነ ከሆስተሶቹ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት በሌለበት አደናጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ለሰዓታት የበረርነው፡፡ ከዚያ ደግሞ… ሮም የማረፍ ዕቅዱ ተሰርዞ፣ ከ12 ደቂቃዎች በኋላ ሚላን እንደምናርፍ ድንገት ተነገረን፡፡ ይሁን ብለን ተቀብለን፣ አስራ ሁለቱን ደቂቃ በጉጉት ስንጠባበቅ ደግሞ፣ ለተጨማሪ አንድ ሰዓት ተኩል ያህል ጊዜ በረራው ቀጠለ፡፡ በዚያ ላይ በረራው ጤነኛ አልነበረም፡፡ አንዴ የሚፈጥን፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የሚረጋጋ ምቾት የማይሰጥ በረራ ነበር፡፡
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያለ ተሳፋሪ፣ የትም ቢሆን ማረፍን እንጂ፣ማረፊያ ቦታውን አይመርጥም፡፡ እኔም ሆንኩ ሌሎች ተሳፋሪዎች ጉዳዩን ያወቅነው፣ ጠለፋው ከተጠናቀቀና አውሮፕላኑ ጄኔቭ ውስጥ በሰላም ካረፈ በኋላ ዋና አብራሪው ሲነግሩን በመሆኑ እምብዛም አልተደናገጥንም፡፡
ከአውሮፕላኑ ስትወርዱ የነበረው ሁኔታ ምን ይመስላል?
አውሮፕላኑ ጄኔቭ ካረፈ በኋላ በግምት ለአንድ ሰአት ያህል በሩ ሳይከፈት ቆሞ ቆየ፡፡ ዋና አብራሪው ሁሉንም ነገር በግልጽ ከነገሩን በኋላ፣ ከእግር ጣታቸው እስከ ራስ ጸጉራቸው የብረት ጭንብል የለበሱ ሰዎች፣ በሩን በርግደው በፍጥነት ወደ ውስጥ ገቡ። አገባባቸውና መላ ሁኔታቸው አክሽን ፊልም የሚሰሩ ነበር የሚመስሉት፡፡ ሁኔታው እጅግ ያስጨንቅ ነበር፡፡ በመካከል አንደኛው ፖሊስ በእጁ በያዛት አነስተኛ የድምጽ ማጉያ ፈረንሳይኛ በሚመስል እንግሊዝኛ መናገር ጀመረ።
“ዚስ ኢዝ ኤ ፖሊስ ኦፔሬሾን። ዶንት ሙቭ!… ፑት ዩር ሃንድስ ኦን ዩር ሄድ!… ዶንት ሜክ ሙቪ ባይ ሞባይል (በሞባይል አትቅረጹ ማለቱ ነው)” ሲል ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ ሁሉም እጆቹን አናቱ ላይ ጭኖ ድምጹንም አጥፍቶ አቀረቀረ፡፡ ተሳፋሪው በፖሊሶቹ መሪነት አንድ በአንድ ከአውሮፕላኑ እየወረደ፣ ሁለት ሁለት ጊዜ ተበርብሮ ተፈተሸ፡፡
ፍተሻው እንደተጠናቀቀም በትላልቅ ሽንጣም አውቶብሶች እየጫኑ ወደ ተርሚናሉ ወሰዱን፡፡ ተርሚናሉ ላይ ስንደርስ የሚገርም አቀባበል ተደረገልን፡፡ የምንበላው ቁርስና ሻይ ቡና እንዲሁም ለብርዱ ብርድልብስ ተዘጋጅቶ ጠበቀን፡፡ የህክምና ባለሙያዎችና የስነልቦና ባለሙያዎች እርዳታ ሊሰጡን እየተጠባበቁ ነበር፡፡ አስገራሚ አቀባበል ነው የተደረገልን።
ኢትዮጵያውያንስ አላገኛችሁም?
ተርሚናሉ ዉስጥ ገብተን ትንሽ እንደቆየን አንድ ኢትዮጵያዊ ወደ እኛ ሲመጣ ተመለከትን፡፡ ለጊዜው ስሙ ትዝ አይለኝም። ከኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደመጣ ነገረንና ስለሁኔታው ጠየቀን። “አይዟችሁ!… ደርሰንላችኋል!…” የሚል መንፈስ ያለው ማበረታቻ ሰጠን፡፡ ከዚያም የግል ሞባይሉን ከኪሱ አውጥቶ አገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቻችን ጋ ደውለን ደህንነታችንን እንድናረጋግጥ ራሱ እየደወለ ያገናኘን ጀመር፡፡
በዚህ ጊዜ ነው፣ በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የመጡት፡፡ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበርን ኢትዮጵያውያንን አነጋግረው አረጋጉን፡፡ በስተመጨረሻም ከተርሚናሉ እንዲወጡ ስለታዘዙ የማስታወሻ ፎቶግራፍ አብረውን ተነሱና ጉዳያችንን በቅርብ እንደሚከታተሉ ነግረውን አበረታቱንና ሄዱ፡፡ ሌሎች ሁለት የኤምባሲው ባልደረቦችም፣የሚፈቀድላቸው ቦታዎች ላይ ሁሉ እየተገኙ ድጋፍ በማድረግ እስከመጨረሻው አብረዉን ነበሩ።
በእለቱ ስለተከሰተው ሁኔታ ምን ትላለህ?
እናቴ እንደነገረችኝ፣ በህፃንነቴ የወራት ዕድሜ ላይ እያለሁ፣ የሆነ ቀን ከታላቅ ወንድሜ መላኩ ገብሬ ጋር ከጎማ ላስቲክ የተሰራ አልጋ ላይ ተኝቼ ነበር። ቡና ስታፈላ ምንጊዜም ዕጣን ማጨስ እማትዘነጋው እናታችን፣ ያጨሰችዉን እጣን እኛ የተኛንበት አልጋ አጠገብ አስቀምጣው ኖሮ፣ እሷ ጎረቤት ደርሳ ስትመለስ ቤቱ በጭስ ተሸፍኖ ጨልሞ ጠበቃት። ጩኸቷን ለቀቀችው። ጩኸት ሰምቶ የመጣ ጎረቤት ነው አሉ ፈልጎ አግኝቶኝ በመስኮት ወደ ውጭ የወረወረኝ። ምህረቱ የተባልኩትም በዚያ ምክንያት ነው። እንዳጋጣሚ እሳቱ ቀድሞ የተያያዘው ወንድሜ በተኛበት በኩል ስለነበር እሱን ማትረፍ አልተቻለም።
የፈጣሪ ምህረት ዛሬም አልተለየኝም፡፡ በአውሮፕላኑ ላይ ሊደርስ ከሚችለው አሰቃቂ አደጋ አትርፎኛል። እንደትላንትናው ሁሉ ነገዬም በፈጣሪ እጅ እንደሆነች አምናለሁ። እርሱ ይሁን ያለው ሁሉ መልካም ነው። ቸርነቱ አይለየኝና ፍቃዱ ሆኖ ለነገ ካበቃኝ ለልጆቼ የምነግረው ተጨማሪ ታሪክ አግኝቻለሁ።
ደህና ነኝ እንኳን ብላት የማታምነኝ እናቴ ብርሃነማርያም ኪአን፣ እጮኛዬ ዮዲት ቦርሳሞን፣ ወንድሞቼን፣ ብቸኛዋን እህቴን፣ አክስቶቼን ከነቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቼን፣ስለደህንነቴ የሚጨነቁልኝን ሁሉ ደህና መሆኔን ንገርልኝ። ከሁሉ አስቀድሞ ስለሆነውም ስለሚሆነዉም ክብር ሁሉ የእርሱ ነውና ፈጣሪ የሚገባዉን ክብር እና ምስጋና ይውሰድ።

የኢትዮጵያን ገጽታ አደባባይ ያወጣው አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን አበራ

$
0
0

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

ልማታዊ ግስጋሴ እስከ ግድበ ህዳሴ በደረሰበት ታሪካዊ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በፈጣን የእድገት መስፈርት ውስጥ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም
ከቻይና ቀጥሎ ሁለተኛ ነች እየተባለ በመሪዎቿ በሚነገርላት ጊዜ። አሸባሪዎችን ከመነሻቸው ለማምከን በአይነቱ ልዩ የሆነ የአንድ
ለአምስት አደረጃጀት የሰዎችን ድርጊት ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብን ጭምር የሚመረምር ምትሃታዊ ሃይል ተደራጅቶ ባለበት ሁኔታ
የዴርቶጋዳን ልብወለድ መሰል ነገር መታየቱ ብዙዎችን አስደምሟል። ለመሆኑ የዛሬ ልጆች ጀግና አይደሉም የሚል ማን ነው?
በውጭ ሃገር የዜና ማሰራጫዎች ወሬው እንደተሰማ አስተያየት ለመክተብ ጣታቸው እንደ ክላሺኒኮቭ ፊደል የሚያንጣጣ ሁሉ ፓይለቱ
ጥገኝነት ለማግኘት ብሎ እንዲህ ማድረጉ አሳፋሪ ነው፣ አላዋቂ አፍሪካዊ መሆን አለበት፣ ይቀጣ! ይቀጣ! የሚሉ ሃረጎች በርክተው
ነበር። እነዚህ በአብዛኛው አፍሪካ ማለት አንድ ሃገር የሚመስላቸው የእውቀት ብርሃን የጨለመባቸው ናቸውና ምንም ማድረግ
አይቻልም።
Hailemedhin Abera
ሁለተኛው ሰሞኑን ነገረ ስራው አያምርም ነበር የሚልና አእምሮው ለየት ያለ ነገር የሚያሳየው ‘ሺዞፍሬንያ’ እሚሉት ነገር
እየጀማመረው ነበር የሚለው ነው። እህት ሁሉም ይስማልኝ በማለት በመረጃ መረቦች በተነች የሚባለውን ያነበበ ሰው ለበረራ ብቁ
ነው የሚለውን ፈቃድ ሰጪም ወፈፍ ያደረገው መሆን አለበት ቢል አላጋነነም። ይሄ እብድ እየመሰለ ሲሰልል የኖረ ወያኔ ወፈፌነትን
በጣም ስለተለማመደው አማኑኤል ሆስፒታልን የደህንነት ማሰልጠኛ ኮሌጅ አድርጎ ቢመለከት አይፈረድበትም ብለን መሳቅም
መብታችን ነው። ቁም ነገሩ ግን የበረራውን ደህንነት ለማስጠበቅ የአብራሪዎችንምጤናና ደህንነት መከታተል ስለሚገባው ያንንም
ማድረግ ባለመቻሉ ወደ ትልቅ ስህተት ራሱን እየጨመረ ነው። በዚህ ሁኔታ ምን ያህል ወፈፌ ፓይለቶች ይኖሩ ይሆን ብሎ
መጠየቅም ያስፈልጋል። ከሆነም ምን አይነት አስተዳደር ቢኖር ነው ጨርቅ ጥሎ የሚያሳብደው፣ ሃገር ጥሎ የሚያስኮበልለው ብሎ
መጠየቅም ተገቢ ነው። የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ እንደሚባለው በአንድ-ለአምስት ተጋግዞ መዋሸት ይቻል ይሆናል ከዚያ መረብ ውጪ
ላለነው ግን አስቂኝ ትዕይንት ነው።
እኔ አውሮፕላኑን ጠለፈ የሚለው አገላለጽ እጅግም አልተመቸኝም። ረዳት አብራሪው ድምጼ ይሰማልኝ በማለት ማቆም የማይገባው
ስፍራ ላይ አውሮፕላኑን አቆመ ለዚያውም ያለ ፍርሃትና ሽብር መደናገጥና መርበትበት ተሳፋሪውም ኮሽታ ሳይሰማ። አቅጣጫ
በቀየረው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ ሰራተኞች ለተሳፋሪዎቻቸው ቡና ሻይ እያቀረቡ ምቾታቸውን እየጠበቁ ዋናው አብራሪ
ጋዜጣቸውን እያነበቡ ምቾታቸው ሳይጓደል አረፉ። ተሳፋሪዎች የሆነውን ሁሉ ሳያዩ ረዳቱ አብራሪ በገመድ ወርደው ለፖሊሶች
እጃቸውን ሰጡ። እንግዲህ የአእምሮ በሽተኛ እንደዚህ ከሆነ ተጋግዘን ብንታመምስ ምን ነበረበት?
ረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ስለመኖሩ መጠራጠር አውቆ መጨፈን ይሆናል። በአንድም
ይሁን በሌላ መልኩ የሀገሪቱ አስተዳደርን ገጽታ የሚያበላሽ ድርጊት ተከናውኗል። ስለምን የሃገሪቱን ገጽታ የሚያጎድፍ እንደሚባል
አይገባኝም። የሀገሪቱን ገጽታ የሚያጠለሹት ጎጠኞችና አምባገነኖች ናቸው። የነርሱ አስተዳደር መበስበሱን፣ ሁሉንም ዘርፍ ማለትም
ብዙሃኑን የሀገሪቱ ሕዝብ ማሳዘኑን በዚህም ምክንያት ምሬት መኖሩን ነው ይህ ወንድማችን አደባባይ ያወጣው። አዎ የአስተዳደሩን
ብልሹነትና እንዳይድን ሆኖ መታመም ነው አደባባይ ያወጣው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ገጽታ ሳይሆን ዓለም የተመለከተው የአስተዳደሩን
መጥፎነት ነው።
ቤተሰቦቹ ተገድደው የሚያወጧቸው መግለጫዎች ይበልጥ የሚያጋልጡት ይህ ማፍያ ቡድን እስከምን ድረስ ሊሄድ እንደሚችልና
በቤተሰብ ችግርና ሃዘን ውስጥ እንኳን በመግባት ሊፈጽም የሚችለውን አረመኔያዊ ድርጊት ነው። ቤን የሚሉት ለማጅ ጋዜጠኛ ወሎ
ሄዶ ባላቸውን አለቆቹ ገድለው እርሱ ደግሞ በሙስሊም አክራሪዎች እንደተገደሉ ለማስመሰል ሃዘንተኛዋን ባለቤት ሌላ ፖለቲካ
ሲያሰራ እንደነበረው ያለ ዜናን ማስታወስ ተገቢ ነው። ያለንበት ዘመን የራሽያ አብዮት የፈነዳበት ጊዜ አይደለም በአይነቱ በተለይም
በመረጃ ቅብብሎሹ ረገድ እጅግ በጣም የተለየ ዘመን ነው። የዚያን ጊዜ ታክቲክ በመጠቀም አሁን የሚታየውን አመጽ ማፈን
አይቻልም። ይልቁኑ እብዶቹ መንግስት ነኝ ባዮችና ወፈፌዎቹ ጋዜጠኛና ካድሬዎች ከአሳፋሪ ተግባር ቢታቀቡ ነው የሚሻላቸው።
ረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ቃል ሳይተነፍስ ማለት የሚፈልገውን የተናገረ ይመስለኛል። የምቾት ህይወትን ትቶ ሙያውን
ተሰናብቶ መሄዱ ጀግንነት ነው። የብዙዎችን ሰቆቃና ቁጣ ያለውን የአስተዳደር በደልና ዘረኛነት ማጋለጡ ጀግንነት ነው። ራሱን ከዚህ
ጨቋኝ ስርዓት ነጻ ማውጣት ለርሱ ቀላል እጅግ በጣም ቀላል ነገር ሆኖ ሳለ በሙያው በክህሎቱ የአለምን ትኩረት የሚስብን ነገር
የአንድ ሰው ሕይወት ሳያጠፋ ማስተላለፍ መቻሉ ጀግንነት ነው። ይልቁንም ደግሞ የታወከ አእምሮ ኖሮ(አዋኪውና አስቀዋሹ ምክንያት
ምን እንደሆነ ይታወቃልና) በዚህ አይነት የተረጋጋ መንፈስ እንዲህ ያለ መልዕክት ማስተላለፍ መቻሉ ይበልጥ አስደናቂ ያደርገዋል።
ምናልባትም በሽታ መሆኑ ቀርቶ ልዩ ስም የሚሰጠው የመንፈስ ጥንካሬ ተብሎ የሚታወስ ይሆናል። ለወንድማችን ሃይለመድህን አበራ
መልካም ጤንነትና ፍትህን እመኛለሁ። ቤተሰቡና ወዳጆቹ ተመሳሳይ የመንፈስ ጥንካሬ ያድርባቸው ዘንድም አሳስባለሁ።
biyadegelgne@hotmail.com

የረዳት አብራሪ ኃይለመድህን ተግባር

$
0
0

ናትናኤል ካብትይመር (ኦስሎ ኖርዌይ)
Natnael Kabtimer
ስለ ረዳት አብራሪ ኃይለመድህን ብዙ ተብሏል ብዙ ተፅፏል ቢሆንም የጀግንነት ተግባሩ ስላኮራኝ እኔም የበኩሌን ልበል። ጥቂቶች በተለይም የወያኔ ህወሃት አባላትና አቀንቃኞች እንዴት ጀግና ይባላል ሲሉ እያስተዋልኩ ነው ፡ ነገር ግን እኔም ሆንኩ በርካታ ሰዎች ረዳት አብራሪውን ጀግና ያልንበት ዋነኛ ምክንያት “በጭቆና ስርዓት ውስጥ ላሉና ብሶታቸውን ማሰማት ላልቻሉ ድምፅ የሆነና ብሶታቸው እንዲሰማ ብሎ ራሱን መስዋዕት ያረገ ሁሉ ጀግና ስለሆነ ነው” እንላለን።
በአየር መንገድም ሆነ በተለያዩ ከፍተኛ አገልግሎት ሰጪ የመንግስት ተቋማት በሚያገለግሉ ከወያኔ ዘር ወይም አባል ባልሆኑ የተለያዩ ባለሞያዎች ላይ ገሃድ የወጣ የመብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሆነ እናውቃለን። በማናለብኝነትና በዕብሪት ላይ የተመሰረተ የመንግስት ጣልቃ ገብነት በርካታ ለሃገር እድገት ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጡ ባለሞያዎችን በአግባቡ አላሰራና አላፈናፍን ማለቱን ማንም ኢትዮጲያዊ ያውቃል።
የኢትዮጲያ አየር መንገድም በተለያዩ ግዜያት የመንግስት ጣልቃ ገብነት እያማረረው እንደኖረ የቀድሞ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ግርማ ዋቄ በተለያዩ ግዜያት ለመጠቆም ሲሞክሩ አስተውያለው። የኢትዮጲያ አየር መንገድ እንደ አለማቀፍ ድርጅትነቱ ከሌሎች ሃገራት አምሳያ ድርጅቶች አንፃር ሲታይ የበለጠ የሰራትኞች ስራ መልቀቅ (Employee turnover) በእጅጉ የሚያጠቃው እንደሆነ በርካታ ኢትዮጲያዊያን ያውቃሉ። በርካታ ወጣትና አንጋፋ ባለሞያዎች በአየር መንገድ በተለያዩ ሞያዎች በአብራሪነት ፣ በበረራ አስተናጋጅነት ፣ በቴክኒሺያንነት ፣ በአስተዳደር ፣ በማርኬቲንግ እና በደንበኞች አገልግሎት ስራ የተሰማሩ ድርጅቱ ለስልጠናና መሰል ክህሎት ማጎልበቻ ከፍተኛ ወጪ ያወጣባቸው ሰራተኞች ባለው የህወሃት ሰዎች አጉል ጣልቃ ገብነት በፈጠረው መጠነ ሰፊ አስተዳደራዊ በደል ተማረው ስራቸውንና የሚወድዋትን ሃገራቸውን ጥለው ወደተለያዩ የሌላ ሃገራት አየር መንገዶች ሄደው እንደሚሰሩ የሰነበተ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በወያኔ አስተዳደራዊ መድሎና ብልሹነት በርካታ ለሃገር ጠቃሚ የህክምና ባለሞያዎች ፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን እንዲሁም በርካታ የተለያዩ ክህሎቶች ባለቤት የሆኑ ባለሞያዎችን ሃገራችን ስታጣ መቆየቷ ሁላችንም ስናየው የኖርነው ሃቅ ነው። የእድገት ፣ የስልጠናና የደሞዝ ጭማሪን የመሳሰሉ የሰራተኞች የኑሮ ደረጃና ክህሎት ማሳደጊያ ለተወሰነ ዘርና ሰዎች ብቻ የማረግ ሌሎችን የበይ ተመልካች በማድረግ መግፋት መረን ወጥቶ በኢትዮጲያ አየር መንገድ ከፍተሻ ሰራተኛ እስከ ዋና ስራ አስፈፃሚ ድረስ የወያኔ ህወሃት አባላትና አቀንቃኞች መቆጣጠራቸውን በሌሎች መንግስታዊ ተቋማትም እንዲሁ መሆኑን ማንም ኢትዮጲያዊ ያውቃል።
ረዳት አብራሪ ኃይለመድን በአጠቃላይ የወያኔ ህወሃት አካሄድ አጉል የሆነና ሃገርን የሚጎዳ መሆኑ እንዲሁም በተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት የተንሰራፋው አስተዳደራዊ መድሎ በሃገር አቀፍ ደረጃ ስር ሰዶ ሃገራችንን ባለሞያ አልባ እያረጋት እንደሆነ የተረዳ መሆኑና ለዚህም የጀግንነት ተግባር እንደፈፀመ እንዲሁም ለሌሎች በሃገራቸው ተምረው በሞያቸው ሃገራቸውን ለማሳደግ ፣ ህዝባቸውንም ለመጥቀምና ለማገልገል አላሰራ ላላቸው ጨቋኝ አገዛዝ ድምፅ መሆኑን ሁላችንም ገብቶን ጀግና ብለነዋል።
አሁንም ሁልግዜም አምባገነናዊነትን አጥብቀን እንቃወማለን !!
natnaelkab@gmail.com

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live